ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

13
በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A ዜና መፅሔት ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር ቅፅ 2. ቁጥር 3 - መጋቢት 2006 www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar ጣፋጭ ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ በስኳር፣ በስኳር ተረፈ ምርቶችና ሌሎች ተያያዥ የልማት መስኮች ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ መጋቢት 7/2006 ዓ.ም በሱዳን ካርቱም የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ስኳር ኮርፖሬሽንን በመወከል የፈረሙት በሚኒስትር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ሲሆኑ የሱዳኑን ኬናና ስኳር ኩባንያን በመወከል ደግሞ የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሞሐመድ ኤልማርዲ ኤልቲጋኒ ናቸው፡፡ የቦዲ ማህበረሰብ የልዑካን ቡድን በወንጂ ስኳር ፋብሪካ የስራ ጉብኝት አደረገ ከኩራዝ ስኳር ልማት ኘሮጀክት አካባቢ የተውጣጣ 44 አባላትን የያዘ የቦዲ ማህበረሰብ የልዑካን ቡድን የወንጂ ስኳር ፋብሪካን እና ለፋብሪካው ሸንኮራ አገዳ የሚያቀርቡ የአገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበርን እንቅስቃሴ ለሁለት ቀናት ጎበኘ፡፡ የካቲት 29 እና 30 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በፋብሪካው የስራ ጉብኝት ያደረገው ቡድን 36 የቦዲ ማህበረሰብ ተወላጅ የሆኑ አርብቶ አደሮች፣ አራት ባለሙያዎች፣ ሁለት የስራ መሪዎች እና ሁለት የወረዳ አስተዳዳሪዎችን ያካተተ ነው፡፡ በተመሳሳይ የቡድኑ አባላት የኩሪፍቱ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበርን፣ የዋቄ ሚያ ቀበሌ » ገጽ.2 በውስጥ ገፆች በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዞን ሦስት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአሚባራ እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በሸንኮራ አገዳ አብቃይነት፣ የመሸጥና የመግዛት ስምምነት ውል ተፈራርሟል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ የተመራ የኮርፖሬሽኑ አመራር ቡድን መጋቢት 12/ 2006 ዓ.ም በፕሮጀክቱ የፋብሪካ ግንባታ፣ የአገዳ ተከላና የቤቶች ግንባታን ተዘዋውሮ ከመጎብኘቱ በተጨማሪ በፕሮጀክቱ ዙሪያ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከልማቱ ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ » ገጽ.6 » ገጽ.15 የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ ነው ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የተቀጠሩ የአፋር ክልል ተወላጆች በፋብሪካ ኦፕሬሽን የተግባር ስልጠና እየወሰዱ ነው ››ገጽ 7 ስኳር ኮርፖሬሽን እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በትብብር ለመስራት ተስማሙ ››ገጽ 20 • ፕሮጀክቱ ከአሚባራ እርሻ ልማት ኃ.የተ.የግ. ማህበር ጋር የአውትግሮወር ስምምነት ተፈራርሟል ግንባታው በመፋጠን ላይ ሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ኩባንያ በተለያዩ መስኮች ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል የልሁካን ቡድኑ አባላት ከወንጂ የቀሰሙትን ልምድ በአካባቢያቸው ለመድገም ቃል ገብተዋል

Upload: meresaf

Post on 09-Jul-2015

547 views

Category:

Government & Nonprofit


22 download

DESCRIPTION

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006

TRANSCRIPT

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር

ቅፅ 2. ቁጥር 3 - መጋቢት 2006

www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar

ጣፋጭስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ በስኳር፣ በስኳር ተረፈ ምርቶችና ሌሎች ተያያዥ የልማት መስኮች ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

መጋቢት 7/2006 ዓ.ም በሱዳን ካርቱም የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ስኳር ኮርፖሬሽንን በመወከል የፈረሙት በሚኒስትር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ሲሆኑ የሱዳኑን ኬናና ስኳር ኩባንያን በመወከል ደግሞ የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሞሐመድ ኤልማርዲ ኤልቲጋኒ ናቸው፡፡

የቦዲ ማህበረሰብ የልዑካን ቡድን በወንጂ ስኳር ፋብሪካ የስራ ጉብኝት አደረገከኩራዝ ስኳር ልማት ኘሮጀክት አካባቢ የተውጣጣ 44 አባላትን የያዘ የቦዲ ማህበረሰብ የልዑካን ቡድን የወንጂ ስኳር ፋብሪካን እና ለፋብሪካው ሸንኮራ አገዳ የሚያቀርቡ የአገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበርን እንቅስቃሴ ለሁለት ቀናት ጎበኘ፡፡

የካቲት 29 እና 30 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በፋብሪካው የስራ ጉብኝት

ያደረገው ቡድን 36 የቦዲ ማህበረሰብ ተወላጅ የሆኑ አርብቶ አደሮች፣ አራት ባለሙያዎች፣ ሁለት የስራ መሪዎች እና ሁለት የወረዳ አስተዳዳሪዎችን ያካተተ ነው፡፡

በተመሳሳይ የቡድኑ አባላት የኩሪፍቱ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበርን፣ የዋቄ ሚያ ቀበሌ » ገጽ.2

በውስጥ ገፆች

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዞን ሦስት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአሚባራ እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በሸንኮራ አገዳ አብቃይነት፣ የመሸጥና የመግዛት ስምምነት ውል ተፈራርሟል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ የተመራ የኮርፖሬሽኑ አመራር ቡድን መጋቢት 12/ 2006 ዓ.ም በፕሮጀክቱ የፋብሪካ ግንባታ፣ የአገዳ ተከላና የቤቶች ግንባታን ተዘዋውሮ ከመጎብኘቱ በተጨማሪ በፕሮጀክቱ ዙሪያ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከልማቱ ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

» ገጽ.6

» ገጽ.15

የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ ነው

ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የተቀጠሩ የአፋር ክልል ተወላጆች በፋብሪካ ኦፕሬሽን የተግባር ስልጠና እየወሰዱ ነው ››ገጽ 7

ስኳር ኮርፖሬሽን እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በትብብር ለመስራት ተስማሙ ››ገጽ 20

• ፕሮጀክቱ ከአሚባራ እርሻ ልማት ኃ.የተ.የግ. ማህበር ጋር የአውትግሮወር ስምምነት ተፈራርሟል

ግንባታው በመፋጠን ላይ ሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ

ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ኩባንያ በተለያዩ መስኮች ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል

የልሁካን ቡድኑ አባላት ከወንጂ የቀሰሙትን ልምድ በአካባቢያቸው ለመድገም ቃል ገብተዋል

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

ገበሬ ማህበር የሸንኮራ አገዳ ማሳን እና አዲሱን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የወንጂ አካባቢ አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ እና የኩሪፍቱ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሊቀመንበር ስለማህበሮቻቸው አመሠራረት እና ማህበራቱ ስለአፈሩአቸው ሀብቶች ለጎብኚዎቹ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም የማህበሩ ጽ/ቤት፣ የሚገለገልባቸው ትራክተሮች እና የእርሻ ማሽነሪዎች የተጐበኙ ሲሆን በመስክም የማህበሩ የሸንኮራ አገዳ ማሳዎች እና የገበሬው ተጓዳኝ የሽንኩርት፣ የቲማቲም እና የበቆሎ ማሳዎች ተጐብኝተዋል፡፡ በወቅቱም አርብቶ አደሮቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በማህበሩ አባላት፣ ባለሙያዎች እና አመራሮች ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን በማህበሩ የእድገት ደረጃ አርብቶ አደሮቹ መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በዋቄ ሚያ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ማሳ ቁጥር 1ዐ ላይም የቡድኑ አባላት የሸንኮራ አገዳ ከቦሎቄ ጋር በስብጥር እንዴት ማምረት እንደሚቻል እና የማህበሩ አባላት በቡድን በመሆን በማሳቸው ላይ የተለያዩ የአረም፣ የቦይ ቁፋሮ እና የውሀ ማጠጣት ስራዎችን ሲሰሩ መመልከት ችለዋል፡፡

አርብቶ አደሮቹ በፋብሪካው አካባቢ በሸንኮራ ተረፈ ምርት ገለባ እና ሞላሰስን እንደ መኖ በመጠቀም በሠራተኛው በግል የሚከናወኑ የስጋ እና የወተት ከብቶች ርቢን በፋብሪካው 3ኛ መኖሪያ መንደር ጐብኝተዋል፡፡

በአዲሱ ፋብሪካም በተደረገ ጉብኝት በማሳ ላይ ያዩት የሸንኮራ አገዳ እንዴት ተመዝኖ ወደ ፋብሪካ አንደሚገባ የተመለከቱ ሲሆን በፋብሪካ ውስጥ የሚካሄደውን የምርት ሂደት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በፋብሪካው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጐላቸው የጉብኝታቸው ማጠቃለያ ሆኗል፡፡

የልኡካን ቡድኑ አባላት በጉብኝቱ ባዩት ልማት እጅግ መገረማቸውንና ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የጉብኝት ዕድሉን ላላገኙ የአካባቢው ማሕበረሰብ አባላት ስለልማቱ በማስረዳት በተፋጠነ ሁኔታ ልማቱ በአካባቢያቸው ተተግብሮ ለማየት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አትክልቲ ተስፋይ የቦዲ ማህበረሰብ አባላቱን ለጉብኝታቸው አመስግነው ወደፊት የፋብሪካው ባለሙያዎች ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ድረስ በመሄድም ልምድና እና እውቀታቸውን ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን እንዳረጋገጡላቸው የፋብሪካው የህዝብ ግንኙነት ዘገባ ያመለክታል፡፡

የቦዲ ማህበረሰብ የልዑካን ቡድን በወንጂ ... በመጠናቀቅ ላይ ያለው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዘንድሮ 75 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት እንደሚችል ተገለጸ

ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በዚህ አመት ተመርቆ በበጀት ዓመቱ የታቀደለትን 75 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት እንደሚችል በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ አስታወቁ፡፡

በዋና ዳይሬክተሩ የተመራው የኮርፖሬሽኑ አመራር ቡድን ከጥር 20-23/2006 ዓ.ም የተንዳሆ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል፡፡ ቡድኑ በአራት ቀን ቆይታው የሸንኮራ አገዳ እርሻ ስራውንና የፋብሪካ ተከላ ማጠናቀቂያ ስራዎችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የአስተዳደር አካላትና ከፋብሪካው ተቋራጭ ኩባንያ አመራሮች ጋር በፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

አቶ ሽፈራው ከውይይቱና ከጉብኝቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደገለፁት ለፋብሪካው የሚቀርበው የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራ በእቅዱ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ፋብሪካው በቅርቡ ስራ ሲጀምር ዘንድሮ እንዲፈጭ የታቀደው 75 ሺህ ቶን ሸንኮራ መፍጨት እንደሚቻልም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የፋብሪካው ተቋራጭ ኩባንያ በአንዳንድ አካባቢዎች ከእቅዱ ወደኋላ እንደቀረ መገምገም ችለናል ያሉት አቶ ሽፈራው ይህንን አስተካክሎ ስራውን እንዲያፋጥን ባደረግነው ውይይት ተስማምተናል ነው ያሉት፡፡ በአሁኑ ወቅትም አፈጻጸሙ በየሁለት ሳምንቱ እየተገመገመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ እስማኤል አሊሴሮን ጨምሮ ከከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ጋር በተደረገ ምክክርም የአካባቢው ሕብረተሰብ ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ

በሚሆንበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ነው ዋና ዳይሬክተሩ ለጋዜጠኞቹ የገለጹት፡፡

በአቶ ሽፈራው የተመራው ቡድን ከየካቲት 18-22/2006 ዓ.ም በተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተጨማሪ የስራ ጉብኝት አድርጎ የፕሮጀክቱን የስራ እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡

በዚሁ ወቅት በተለይም ከሸንኮራ አገዳ ማሳ ወደ ስኳር ፋብሪካው የሚያደርስ አቋራጭ መንገድ ግንባታ ሂደት የጎበኘ ሲሆን በፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት ላይም ከክልሉ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የሸንኮራ አገዳ ተክል ልማት ዳይሬክተር አቶ በላቸው መሐሪ በበኩላቸው በተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዚህ አመት 16 ሺህ ሄክታር መሬት ሸንኮራ አገዳ ለማልማት ታቅዶ በቀን 50 ሄክታር እየተተከለ ይገኛል ብለዋል፡፡ የእርሻ ስራው እስካሁን ለ5ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረም ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 50 ሺህ ሔክታር መሬት የሚሸፍን የሸንኮራ አገዳ ልማት እንደሚካሄድበት የገለጹት ዳይሬክተሩ በመጀመሪያው ዙር 25 ሺህ ሔክታር መሬት በመልማት ላይ ነው ብለዋል፡፡

በአፋር ክልል የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ፋብሪካ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ሲሆን፣ ሁለቱም የፋብሪካው ምዕራፎች ተጠናቀው በሙሉ አቅማቸው ስኳር ማምረት ሲጀምሩ እያንዳንዳቸው በቀን 13 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በአመት ከ6ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር በጋራ ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

32

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ምክንያት ወደ ሌላ አካባቢ ለሚሰፍሩ ዜጎች የማሕበራዊ ተቋማት ግንባታዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል

የ22 አመቱ ወጣት ጌታቸው ትሮሬ ኡሳሞ የአስረኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በአገሩ ሰርቶ ለመለወጥ ከመጣር ይልቅ ከሰው አገር "የሚያፍሰውን" ገንዘብ በመናፈቅ ወደ ሱዳን ካርቱም ተሰዶ አንድ አመት ከስድስት ወር በዚያ ቆይቷል፡፡ በባእድ አገር ያሳለፋቸው ጊዜያት የትውልድ ቀዬውን ጥሎ ሲሰደድ እንዳሰበው ሆኖ አላገኘውም፡፡

በሱዳን በነበረው የ18 ወራት ቆይታው የተሻለ ነገር ፍለጋ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሯል፡፡ ከርሃብና ጥማቱ በተጨማሪ በርካታ የሕይወት መሠናክሎችን ለመጋፈጥና ለማለፍም ተገዷል፡፡

የሄደበት የስደት አገር እንዳልተመቸውና ያሰበውን እንዳላገኘ የሚያውቁትና ካለአባት ያሳደጉት እናቱና ቤተሰቦቹ በትውልድ ቀዬው ሕይወቱን ሊቀይርለት የሚችል የስኳር ልማት ፕሮጀክት መጀመሩን የሚያበስር

መልእክት ይልኩበታል፡፡ ወትሮውንም የስደት ኑሮ ያልተመቸው ወጣት ጌታቸው ጊዜ ሳያባክን ወደ እናት አገሩ ተመልሶ ወደ ትውልድ ቀዬው ያቀናል፡፡

አስረኛ ክፍል ያጠናቀቀበትን የትምህርት ማስረጃዎቹን ይዞ ወደ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ያመራል፡፡ጽሕፈት ቤቱም ፕሮጀክቱ ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎን የአካባቢውን ሕብረተሰብ እንዲሁም በፕሮጀክቱ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ዜጎችንና ልጆቻቸውን መጥቀም ዓላማው መሆኑን በመግለጽ ወጣት ጌታቸው ጫንጮ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የማሠልጠኛ ማዕከል በትራክተር ኦፕሬተርነት እንዲሰለጥንና የፕሮጀክቱ ቋሚ ሠራተኛ እንዲሆን እድል ይሰጠዋል፡፡ አጋጣሚውም ራሱን ከመቻል አልፎ አቅመ ደካማ የሆኑ እናቱን እንዲረዳ አስችሎታል፡፡

ይህ ከአስር ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው የጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ በ576 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች የሚገነቡበት ፕሮጀክት ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የሚገነቡት እነዚህ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ በአመት እያንዳንዳቸው 242 000 ቶን ስኳር እንደሚያመርቱ የሚጠበቁ ሲሆን፣ ለዚህም በግብአትነት በ75 ሺ ሔክታር መሬት ላይ በበለስ ወንዝ አማካይነት የሚለማውን የሸንኮራ አገዳ ይጠቀማሉ፡፡

በፕሮጀክቱ የፋብሪካ ተከላ ፣ የአገዳ ተከላ ፣ የመኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን በፕሮጀክቱ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን

ወደ ሌላ አካባቢ ለማስፈር የሚያስችሉ የመሠረተ ልማትና የማሕበራዊ ተቋማት ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡እነዚህ ግንባታዎች ከሚካሄዱባቸው ቦታዎች መካከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መተከል ዞን ፓዊ ወረዳ በተለምዶ" አባ ወሬኛ " በመባል የሚጠራው ስፍራ ይገኝበታል፡፡

ይህ 1276 የቤተሰብ መሪዎች እንደሚሰፍሩበት የሚጠበቀው አካባቢ ልማቱ የኛ ነው በማለት ከቀያቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለሚመጡ አርሶ አደሮች ከመምጣታቸው በፊት ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት ፣ ለእነርሱና ለእንሰሶቻቸው የሕክምና መስጫ ተቋማት ፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃና የወፍጮ አገልግሎት መስጫ ግንባታዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በበለስ ስኳር ልማት ምክንያት በተጠቀሰው አካባቢ ለሚሰፍሩ ዜጎች ቀድሞ ከነበሩባቸው አካባቢዎች ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ ወይም የተሻሉ ማሕበራዊ ተቋማትንና የመሠረተ ልማት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማሰብ ኮርፖሬሽኑ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዜጎቹ ከመሠረተ ልማቱ በተጨማሪ በፕሮጀክቱ የስራ እድል እንዲያገኙ እንደተደረገና ይህም የአካባቢው ነዋሪዎች ልማቱ መጣብን ሳይሆን መጣልን እንዲሉ እንዳስቻላቸው ነው የገለጹት፡፡ በልማቱ አካባቢም የሚገኘው ሕብረተሰብ ከጅምሩ በተጨባጭ ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆኑን እንዲያረጋግጥ እየተደረገ የሚገኘውንም ጥረት አመልክተዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች ከማሕበራዊ ተቋማትና ከመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተጨማሪ የእርሻ መሬትም ተዘጋጅቶላቸው በመከፋፈል ላይ ይገኛል ብለዋል አቶ ዳመነ፡፡

የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አስራቴ አለኸኝ በበኩላቸው ለፕሮጀክቱ በተከለለው 75 ሺ ሔክታር መሬት ላይ የሚገኙ የፓዊ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲሄዱ የሚደረገው የመኖሪያና የእርሻ መሬት ተዘጋጅቶላቸውና ተገቢው ካሳ ተከፍሏቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በ2005 ዓ.ም በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳ በተመሠረቱ ሁለት የሰፈራ ጣቢያዎች እንዲሰፍሩ ለተደረጉ 1909 የቤተሰብ መሪዎች ኮርፖሬሽኑ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉንና ከ59 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ የማሕበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዳንጉርና በፓዊ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ሁለት መንደሮች ለሚሰፍሩ 1525 ዜጎች ኮርፖሬሽኑ ላፈሩት ሐብትና ንብረት ከ72.3 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉንና ለተለያዩ የመሠረተ ልማትና የማሕበራዊ ቷቋማት ግንባታዎች ከ 66 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው የሚካሄደው ልማት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ልማት ነው በሚል አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ለሚሰፍሩ ወገኖች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ ቀድሞ ከነበሩባቸው ስፍራዎች በተሻለ መልኩ እንዲገነቡ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

የጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ወጣት ጌታቸውን ለመሳሰሉ የአካባቢው ተወላጆች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ ልማቱ የእኔ ነው በሚል በፈቃደኝነት ቦታቸውን ለልማቱ ለሚለቁ ወገኖች ደረጃቸውን የጠበቁ የማሕበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮችን መገንባቱ ልማቱ ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ያሳያል፡፡

በመገንባት ላይ ከሚገኙት የማህበራዊ ተቋማት መካከል የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት

  ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን         ጣፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

5

ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

4

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ስኳር...

ኮርፖሬሽኑና ኩባንያው የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ተቋማቱ የትብብር ስትራቴጂያዊ አጋርነት በመፍጠር በስኳርና በስኳር ተረፈ ምርቶች እንዲሁም ተያያዥ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ያስችላቸዋል፡፡

ተቋማቱ መረጃዎችን በመለዋወጥና አቅማቸውን በማስተባበር የንግድ እድሎችን ፈጥረው በተገቢው መልኩ ተጠቃሚ ለመሆንም ተስማምተዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ በሸንኮራ አገዳ እርሻና በስኳር ቴክኖሎጂ ፣ ምርምርና ጥናትን ፣ ማማከርን ፣ የቴክኒክ ድጋፍን ፣ የዕውቀት ሽግግርን እንዲሁም የአቅም ግባታን በመሳሰሉት መስኮች ተባብሮ መስራትን ያጠቃልላል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽንና የሱዳኑ ኬናና ኩባንያ በስኳርና ተያያዥ ምርቶች ዙሪያ ገበያ ማፈላለግን በተመለከተ በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ የተመራውና የኮርፖሬሽኑን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ያካተተው የልዑካን ቡድን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነትና በኬናና ስኳር ኩባንያ ጋባዥነት ለአንድ ሳምንት በኩባንያው ባደረገው የስራ ጉብኝት ጠቃሚ ልምዶችን አግኝቶ ተመልሷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኩባንያው ባደረገው ጉብኝት በፋብሪካ ግንባታ ረገድ ከዲዛይን፣ ቴክኖሎጂ መረጣ፣ የግንባታ ኮንትራት ውል ከማስተዳደር ጀምሮ ግንባታው ሲጠናቀቅ

የሚፈለገውን ጥራት ጠብቆ መጠናቀቁን የሚያረጋግጥና በምርት ሂደትም የምህንድስና ቴክኒካዊ ምክር የሚሰጥ ለኮርፖሬሽኑ ተጠሪ የሆነ የምህንድስና አቅም በመገንባት ላይ ጠቃሚ ልምድ ቀስሞ ተመልሷል፡፡

ከእንስሳት ምርታማነት አኳያም የስኳር ተረፈ ምርትን ተጠቅሞ የእንስሳት መኖ በማምረት ገቢን ማሳደግ የሚያስችል ተሞክሮ ከኩባንው ተገኝቷል፡፡

ኬናና ስኳር ኩባንያ የተለያዩ ኩባንያዎችን በስሩ ያቀፈ ሲሆን በእርሻ ፣ በምህንድስና ፣ በስኳርና በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የካበተ ልምድ ያለው የሱዳን ኩባንያ ነው፡፡

በአፋር ክልል ለሚገኘውና በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር ለሚጠበቀው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከተቀጠሩ 418 የክልሉ ተወላጆች መካከል 122ቱ ከአንድ ወር በላይ በፋብሪካ ኦፕሬሽን የተግባር ስልጠና ወሰዱ፡፡ ቀሪዎቹም በቀጣይ ዙሮች ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የምርምርና ስልጠና ዘርፍ የስልጠናና ስርጸት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በፊንጫአና በወንጂ ስኳር ፋብሪካዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው ይህ የተግባር ስልጠና የአፋር ክልል ተወላጆች በፋብሪካው የተለያዩ ማሽነሪዎች ላይ እንዲሰሩ ክህሎት የማስታጠቅ ዓላማ ያለው ነው፡፡

የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሰው ሀብት ልማትና ስራ አመራር ም/ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጉርጃ በላይ የካቲት 2006 ዓ.ም በፊንጫአና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ተገኝተው የስልጠናውን ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ሰልጣኞቹ ከአፋር ክልል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተመረቁ ሲሆን በተቀጠሩበት የስራ መደብ ላይ አግባብነት ያለው የተግባር ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢውን ህብረተሰብ የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአሁኑ ጊዜ የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ3000 በላይ የአካባቢውን ህብረተሰብ በቋሚ፣ በኮንትራትና ጊዜያዊ ሰራተኝነት ይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በስኳር ልማት ፕሮጀክቱ አካባቢ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ህብረተሰቡን በማደራጀት ከልማቱ ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ የስራ እድሎች ተጠቃሚ እንዲሆን ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ም/ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የምርምርና ስልጠና ዘርፍ የስልጠናና ስርጸት ዳይሬክተር አቶ ዋቅሹም ዱጋሳ በ 2005/6 በጀት ዓመት ለ1495 አዳዲስ ቅጥሮች እና ነባር ባለሙያዎች በሽንኮራ አገዳ አመራረትና በስኳር ቴክኖሎጂ የቅድመ-ስራ እና የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ የ418ቱ የአፋር ክልል ተወላጆች ስልጠናም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፊንጫአና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች የተግባር ስልጠናውን በተለያዩ ማሽነሪዎች ላይ ሲወስዱ ያነጋገርናቸው ሰልጣኞችም በስልጠናው በአጠቃላይ የስኳር አመራረት ሂደት ላይ ጥሩ ግንዛቤና በሚሰሩባቸው ማሽነሪዎች ላይ ደግሞ አስፈላጊውን ክህሎት እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡

ያገኙትንም ክህሎት ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ስራ ሲጀምር ለመተግበር በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሆነ ነው ሰልጣኞቹ የተናገሩት፡፡

ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የተቀጠሩ የአፋር ክልል ተወላጆች በፋብሪካ ኦፕሬሽን የተግባር ስልጠና እየወሰዱ ነው

ሰልጣኞቹ በስልጠና በቂ ክህሎት እንዳገኙ ተናግረዋል

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የአስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአገምሳ ፊንጫአ የሰፈራ ጣቢያ በመንደር ለማሰባሰብ የስኳር ኮርፖሬሽን በመደበው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች በፋብሪካው ወሰን ክልል ውስጥ ኩይሳ ተብሎ በሚጠራ መንደርና በሌሎች አካባቢዎች የተሟላ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት ተቋማት ሳያገኙ የቆዩ ናቸው፡፡

ይህን የህብረተሰቡን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ብሎም የፋብሪካውን ወሰን ክልል ነፃ ለማድረግ የስኳር ኮርፖሬሽንና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከፋብሪካው ወሰን ክልል ውጪ አዲስ ቦታ በመምረጥና መሰረተ ልማት በማሟላት ህብረተሰቡን ወደ አንድ ቦታ በመሰብሰብ ቋሚ ንብረት አፍርቶ የሚኖርበት ምቹ የመኖርያ መንደር ለመመስረት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ አገምሳ ፊንጫአ ተብሎ በተሰየመው አዲሱ መንደር ላይ የተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ እና የመሰረተ ልማት ተቋማትን በፍጥነት በማስገንባት ላይ ይገኛል::

ከግንባታዎቹ መካከል የጤና ጣቢያ፣ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ የመብራት ዝርጋታ፣ የመጠጥ ውሃ፣ የቀበሌና የፖሊስ ፅ/ቤቶች ይገኙባቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተቋማቱ ግንባታ 50 በመቶ ያህል የደረሰ ሲሆን፣ በ2006 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የህዝብ ግንኙነት የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ለአገምሳ ፊንጫአ አዲስ መንደር ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ

የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ

በመፋጠን ላይ ነው

ኮርፖሬሽኑ ዕቅዱን ለማሣካት አቅሙን እያሣደገ መጥቷል

ስኳር ኮርፖሬሽን ከጥር 8 እስከ 12/2006 በዋናው መ/ቤት ባካሄደው የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተቀመጠውን ግብ 7ዐ በመቶ ለማሣካት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

በሚ/ር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አፈፃፀምና የወደፊት አቅጣጫ ላይ ጥር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የስድስት ወር ግምገማው በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ማሣካት እንደምንችል ያሣያል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ስኳርን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በዚህም በዓመት ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

አቶ ሽፈራው በየፋብሪካዎቹ መጋዘኖች ውስጥም በቂ የስኳር ምርት እንደሚገኝ ነው ያረጋገጡት፡፡

ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሂደት ያጋጠሙትን የተለያዩ ተግዳሮቶች እየፈታ አቅሙን እያሣደገ እንደመጣም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ አሁን ባሉት ሦስት ነባር የስኳር ፋብሪካዎችና እስከ 2007 ዓ.ም መጨረሻ በየደረጃው ወደ ማምረት የሚገቡትን ሰባት አዳዲስ ፋብሪካዎች በመጠቀም በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ በዓመት 1.58 ሚሊዮን ቶን ስኳር ለማምረት ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አቶ ሽፈራው አመልክተዋል፡፡

በአፈፃፀም ግምገማው ላይ የታዩ ውስንነቶች ተለይተው ለቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በሚ/ር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን         ጣፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

6 7

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለምርታማነት የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞችን ሸለመ

የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን ትግበራ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የፋብሪካው ምርታማነት እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰራተኞች ጥር 29/2006 ዓ. ም. ሽልማት ሰጠ፡፡

የካይዘን ፍልስፍና በፋብሪካው በመተግበሩ በሰራተኛው ዘንድ በተፈጠረው ከፍተኛ የአመለካከት ለውጥ የፋብሪካው የስኳር ምርት 70 በመቶ መጨመሩ በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ የፋብሪካው በቀን ስኳር የማምረት አቅሙም በ35 በመቶ መጨመሩ ነው በወቅቱ የተመለከተው፡፡

ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ ብክነቶችም በካይዘን ትግበራ ምክንያት መቀነሳቸውንና በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ የተለያዩ ቁሳቁስም በፋብሪካ ደረጃ በሰራተኞች መሰራት በመቻላቸው ከፍተኛ ወጪ ማስቀረት እንደተቻለ የፋብሪካው ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ባስጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ገለጻ አስረድተዋል፡፡

የካይዘን ትግበራው በእርሻም ሆነ በፋብሪካ ስራዎቸ ላይ የተሻለ የጊዜ አጠቃቀምና ጥራትን ማስገኘት እንደቻለም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የካይዘን ፍልስፍናን በስራ ቦታ ከመተግበር አልፈው በግለሰብ ደረጃ በመኖሪያ ቤታቸው የተገበሩና ውጤታማ የሆኑ የፋብሪካው ሠራተኞችም ተሞክሮአቸውን አስጎብኝተዋል፡፡

በእለቱ በ633 የልማት ቡድን ተደራጅተው በለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ከሚገኙት ሰራተኞች፣ አመቻቾችና አመራሮች ውስጥ

42 የልማት ቡድኖች፣ 65 አባላትና 17 አመቻቾች ተሸልመዋል፡፡ በፈጠራና በማሻሻያ ስራ ደግሞ 20 ሰዎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ተሸላሚዎቹም በእለቱ ከነበሩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እጅ የዋንጫ፣ ከ500 እስከ 6 ሺህ ብር ዋጋ ያለው የህዳሴ ግድብ ቦንድ፣ ከወርቅ የተሰራ የአንገት ሀብልና ሠርተፊኬት ተቀብለዋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ኮርፖሬሽኑ በ2007 ዓ.ም ከ1.5 ሚሊዮን ቶን በላይ ስኳር ለማምረት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመጥቀስ ለዚህ እቅድ ስኬት ሁሉም መረባረብ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ በተለይም መተሐራን ጨምሮ ያሉት ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የራሳቸውን እቅድ ከመፈጸም ጎን ለጎን የካበተ ልምዳቸውን ተጠቅመው ለሌሎች አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚ/ር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና የሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪሰ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር፣ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶና የቀድሞ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ አባል አቶ አባይ ጸሐዬን ጨምሮ የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2006 በጀት አመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የወንጂ ሸዋ አካባቢ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የኅብረት ሥራ ዩኒየን የሚያመርተውን አንድ ኩንታል ሸንኮራ አገዳ በ50 ብር እንዲሸጥ

ከስምምነት ላይ ተደረሰየወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና የአካባቢው ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የኅብረት ሥራ ዩኒየን ለዘጠነኛ ጊዜ ባደረጉት ሸንኮራ አገዳ የማምረት፣ የመሸጥና የመግዛት ስምምነት ውል መሰረት ዩኒየኑ አንድ ኩንታል ሸንኮራ አገዳ በ50 ብር ለፋብሪካው እንዲሸጥ ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ አምራቾቹ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን በሄክታር ምርታማነትን ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡

በአዳማ ሪፍት ቫሊ ሆቴል የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የስምምነት ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ባደረጉት ንግግር ፋብሪካውና ዩኒየኑ የደረሱበት ስምምነት ወደፊት ተቀራርቦ ለመስራት በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም የዩኒየኑ አመራሮችና የመስተዳድር አካላት የወንጂ አካባቢ ገበሬዎች ከሸንኮራ አገዳ ምርት ጎን ለጎን የፋብሪካውን ተረፈ ምርቶች በመጠቀም በሌሎች ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

የመንግሥትም ሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን

የመጨረሻ ግብ ሕዝቡን ከልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ የሸንኮራ አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ስምምነቱ ከሚያስገኘው ጥቅም የበለጠ ማግኘት የሚቻልባቸውን አማራጮች ማየት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

በዩኒየኑና በፋብሪካው መካከል የተደረሰው ስምምነት ኮርፖሬሽኑ እየገነባቸው ለሚገኙ ሌሎች የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ማሳያ መሆኑንም ነው አቶ ሽፈራው የጠቀሱት፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ተስፋይ በበኩላቸው የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከሌሎቹ ፋብሪካዎች በተለየ በአብዛኛው ለምርቱ በግብአትነት የሚጠቀመውን የሸንኮራ አገዳ የሚያገኘው ከአብቃይ ገበሬዎች በመሆኑ ስምምነቱ ለፋብሪካው ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው በራሱ ከሚያለማው 6 ሺ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ በተጨማሪ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ በ 4 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚያለማውን የሸንኮራ አገዳ ምርት በግብአትነት በመጠቀም ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ አክለውም

በቀጣይ የሸንኮራ አገዳ ልማቱን ወደ 16 ሺ ሄክታር ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸው ከዚህ ውስጥ አስር ሺ ሄክታሩ ወይም 75 ከመቶ የሚጠጋው መሬት የሚለማው በዩኒየኑ አባላት እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽንም ሆነ ፋብሪካው ገበሬው ከስምምነቱ በዋናነት መጠቀም አለበት የሚል ጠንካራ እምነት እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አታክልቲ በቀጣይም በፋብሪካው አካባቢ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የማሕበራዊ ተቋማትን ለመገንባት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የወንጂ አካባቢ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የኅብረት ሥራ ዩኒየን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወንድምአገኘሁ በበኩላቸው ዩኒየናቸው በስኳር ልማት ውስጥ ጉልህ ሚና መጫወት በሚያስችለው ቁመና ላይ መሆኑን ገልጸው ከፋብሪካው ጋር የደረሱበት ስምምነት የጋራ ተጠቃሚነትንና የአገሪቱን ልማት ማስቀጠልን መሠረት አድርጎ የተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

» ገጽ.11

ሽልማት በተሰጠበት ወቅት

ስምምነቱ የወንጂ አካባቢ አርሶ አደሮችን የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን         ጣፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

8 9

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና በምርምርና ስልጠና ዘርፍ

መካከል የቴክኖሎጂ ሽግግር ተካሄደየወንጂ ሸዋ አካባቢ ሸንኮራ

አገዳ አብቃይ ----

ስምምነቱ የአባሎቻቸውን ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ በመሆኑ ደስታቸው ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ታደሰ በቀጣይም የአመለካከት ችግሮችን በመቅረፍ፣ የአመራረት ክህሎትን በማዳበርና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነትን ለማሳደግ ዩኒየናቸው እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

የወንጂ አካባቢ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የኅብረት ስራ ዩኒየን አባል የሆኑት ወይዘሮ መሠረት ቶሎሳና አቶ ተስፋዬ ካሳ አዲሱ የስምምነት ውል ከዚህ ቀደም ከነበረው ስምምነት በተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የአዋሽ መልካሳ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መሠረት ቶሎሳ በስምምነቱ መደሰታቸውን ገልጸው "እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ እኛም ሆንን ዩኒየኑ ብዙ ጥረት አድርገናል፡፡ ከዚህ በኋላ በርትተን በመስራት ጥሩ ውጤት ላይ እንደርሳለን ብዬ አስባለሁ" ብለዋል፡፡

ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ የሸንኮራ አገዳ አብቅለው ለወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በማቅረብ ላይ የሚገኙትና የወንጂ ኩሪፍቱ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ የኅብረት ሥራ ማህበር አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ካሳ በበኩላቸው ዩኒየናቸው ከፋብሪካው ጋር የተፈራረመው አዲስ ስምምነት በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ሕይወት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ነው የገለጹት፡፡

"ከዚህ ስምምነት በፊት በነበሩት ስምንት ድርድሮች ገበሬው የሚያገኘው ጥቅም እየተሻሻለ ቢመጣም የዘጠነኛው ዙር ግን ለኛ ከሁሉም የተሻለ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩ የተደረገ ስምምነት ነው" የሚሉት አቶ ተስፋዬ ስምምነቱ ገበሬውን ይበልጥ ለስራ እንደሚያነሳሳውና ምርታማነቱን ለማሳደግ እንደሚረዳው አስረድተዋል፡፡

ለሦስት ዓመታት በሚቆየው ስምምነት ዩኒየኑ የሚያመርተው የአንድ ኩንታል የሸንኮራ አገዳ ዋጋ ወደ 50 ብር ከፍ እንዲል የተደረገው ከ35 ብር ነው፡፡

የወንጂ አካባቢ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የኅብረት ስራ ዩኒየን 16 ሺህ አባላት ባላቸው 5 ሺህ አባል ማኅበራት አማካይነት በ1993 ዓ.ም የተመሠረተ ዩኒየን ነው፡፡

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በስኳር ኮርፖሬሽን የምርምርና ስልጠና ዘርፍ መካከል የምርምር ሂደታቸውን ያጠናቀቁ የአራት ቴክኖሎጂዎች ሽግግር ተካሄደ፡፡

በሸንኮራ አገዳ ምርምር ዳይሬክቶሬት የተሠሩት አራት ቴክኖሎጂዎች ምርታማነትን እንደሚያሳድጉና የማምረቻ ዋጋ እንደሚቀንሱ በምርምር ሂደት መረጋገጡ የካቲት 29/2006 ዓ.ም በወንጂ የቴክኖሎጂ ውጤቶቹ ሽግግር በተደረገበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የምርምር ሂደታቸውን የጨረሱትና ለስርፀት የተላለፉት አራቱ ቴክኖሎጂዎች አዲስ የሸንኮራ አገዳ ዝርያ፣ ፊልተር ኬክና ማዳበሪያ በቅንጅት መጠቀም በሸንኮራ አገዳ ምርት ላይ ያለው ተጽዕኖ፣ የትራክተርና ተቀጽላው (accessary) ምጣኔ ሐብታዊና ቴክኒካዊ ውህደት እንዲሁም ሄለራትና ኢትዮዝኖን የተባሉ ፀረ ተባይ መድሐኒቶች አገዳ ቆርቁርን ለመቆጣጠር ባላቸው ብቃት ላይ የተደረጉ ጥናቶች ናቸው፡፡

በኮርፖሬሽኑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ተጠባባቂ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ መኳንንት የቴክኖሎጂ ሽግግር

መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የምርምር ውጤቶቹ ስራ ላይ ውለው የዘርፉን ውጤታማነት ያግዛሉ ብለዋል፡፡

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ላይ ምርምር ተደርጎባቸው ወደ ተግባር የተሸጋገሩት አራቱ ቴክኖሎጂዎች የፋብሪካውን ምርታማነት የበለጠ እንደሚያሳድጉ የታመነባቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን የተጠናቀቁ ምርምሮች ሳይተገበሩ መቀመጥ እንደሌለባቸው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በቀጣይም ዘርፉ በምርምር የሚያገኛቸውን ቴክኖሎጂዎች ከኦፕሬሽን ዘርፍ ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተመልክቷል፡፡

ቴክኖሎጂዎቹን ተረክቦ ተግባራዊ የሚያደርገው የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የእርሻ ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው ቴክኖሎጂዎቹ የፋብሪካውን ምርትና ምርታማነት ለማሳድግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው ገልጸው ኮርፖሬሽኑ በዘርፉ ያቀዳቸውን ሥራዎች ለማሳካት ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂዎቹ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ አካባቢን ከብክለት በመጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድም ጠቀሜታ እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡

አዲሶቹ ግኝቶች የፋብሪካውን የማምረቻ ዋጋ ለመቀነስ እንደሚያስችሉም አቶ ግደይ ጠቁመው ፋብሪካቸው በቀጣይ ምርምሮችን በማስረጽና ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ከምርምርና ስልጠና ዘርፍ ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

በሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ብቃት ላይ ለረዥም ጊዜ በተደረገ ግምገማ በምርታማነቱ፣ በሽታን በመቋቋም አቅሙና በስኳር ይዘቱ የተሻለ ሆኖ የተገኘው N52-219 የተባለ የአገዳ ዝርያ ከሁሉም ልቆ በመገኘቱ ወደ ምርት ለማስገባት ተወስኗል፡፡ ዝርያው B52-298 በመባል ከሚታወቀው ነባር ዝርያ ጋር ሲነጻጸር በተከላ ማሳ 21 ሺ 780 ብር፣ በቆረጣ ማሳ ደግሞ 3 ሺ 780 ብር ለፋብሪካው ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝ የምርምር ውጤቱ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በስኳር ምርት ሂደት የሚመረተውንና ፊልተር ኬክ ተብሎ የሚጠራውን ተረፈ ምርት በምን ያህል መጠን ከማዳበሪያ ጋር በቅንጅት መጠቀም እንደሚቻል ለማወቅ በተደረገው ጥናት በሄክታር 30 ቶን ፊልተር ኬክ ከማዳበሪያ ጋር በመጠቀም የሸንኮራ አገዳ ምርታማነትን 40 በመቶ ማሳደግና እስከ 35 ሺ 200 ብር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት እንደሚቻልም በምርምሩ መረጋገጡ ታውቋል፡፡

በትራክተርና ተቀጽላ ምጣኔ ሐብታዊና ቴክኒካዊ ውህደትን አስመልክቶ በተደረገው ምርምር ፋብሪካው በሚሰራቸው የመሬት ዝግጅት ስራዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት ትራክተሮችና ተቀጽላዎቻቸው ተመጣጥኝ እንዳልሆኑና በዚህም ምክንያት ፋብሪካው በአመት ሁለት ሚሊዮን ብር እንደሚያጣ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የእርሻ መሣሪያዎች ግዥ ሲከናወን ትራክተሮችና ተቀጽላዎቻቸውን ተመጣጣኝ በማድረግ ሁለት ሚሊዮን ብር ማዳን ከመቻሉም በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን ትራክተሮች ከተቀጽላዎቻቸው ጋር ተመጣጣኝ የሚሆኑበትን መንገድ መቀየስ እንደሚያስፈልግ ጥናቱ አመላክቷል፡፡

አገዳ ቆርቁር በሸንኮራ አገዳ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል አሁን በጥቅም ላይ የሚገኘውን ኢትዮዝኖንና ሄለራት የተሰኙት ጸረ ተባይ መድኃኒቶች ያላቸውን ብቃት ለመገምገም በተደረገው ምርምር ሄለራት የተሻለ ሆኖ ከመገኘቱም በላይ የጸረ ተባይ ወጪን በ60 በመቶ ወይም በሄክታር 226 ብር ማዳን እንደሚያስችል በጥናቱ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

በምርምር የተደገፈ ስራ ምርታማነትን ያጎለብታል

    ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

1 1

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

1 0

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአርብቶ አደሩ በርካታ ጠቀሜታዎችን እያስገኘ ነው

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የኦሞ ወንዝን በሚጋሩት ደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች በ 175 ሺ ሄክታር መሬት ላይ አምስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመትከል በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የእርሻ ትራክተር ኦፕሬተሩ ሉሶሩ ኩታ ደግሞ የዚህ ፕሮጀክት ባልደረባ ነው፡፡

ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነው የ29 አመቱ ሉሶሩ ስኳር ኮርፖሬሽን የስኳር ልማት ስራዎች በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማሰብ በጫንጮ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ማሠልጠኛ ማዕከል ለሦስት ወራት አሰልጥኖ በየፕሮጀክቶቹ የስራ እድል እንዲያገኙ ካደረጋቸው ባለሙያዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

ወጣቱ በእርሻ ትራክተር ኦፕሬተርነት ስልጠና ከማግኘቱና በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት መስራት ከመጀመሩ በፊት የነበረውን ሕይወት ሲያስታውስ "በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስራ ከመጀመሬ በፊት አርብቶ አደር ነበርኩ፡፡ አብዛኛውን ጊዜዬን አሳልፍ የነበረውም ለከብቶቼ ውሃና ግጦሽ በመፈለግ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ነበር " ይላል፡፡

በፕሮጀክቱ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሆኖ በመስራትና የተረጋጋ ሕይወት በመምራት ላይ እንደሚገኝ የሚገልጸው ወጣቱ ሉሶሩ በአቅራቢያው በሚገኝ ከተማ እንዲማር ወንድሜን እየረዳሁ ነው በማለት ያክላል፡፡ በብሔረሰቡ ባህል መሰረት የሐብት መጠን ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደውን ከብት እርባታም "አልዘነጋሁትም " ይላል፡፡

"በማገኘው ደመወዝ ከራሴ አልፎ ቤተሰቤን እረዳለሁ፡፡ በሬም እገዛለሁ ፡፡ ወንድሜ በአቅራቢያ በሚገኝ ከተማ እንዲማር በመርዳት ላይ እገኛለሁ፡፡ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሕይወቴ ተቀይሯል " በማለት ከፕሮጀክቱ ያገኘውን ጠቀሜታ ይዘረዝራል፡፡

እንደ ሉሶሩ ሁሉ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከፈጠረው የስራ እድል ተጠቃሚ ከሆኑት የአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች መካከል ጸሐይነሽ የልጦና ትጠቀሳለች ፡፡

በአሁኑ ወቅት 28 አመት ወጣት የሆነችው ጸሀይነሽ በአካባቢው ማሕበረሰብ ልማድ መሠረት በ12 አመቷ በእድሜ እጅጉን ለሚበልጧት አዛውንት በ38 ከብትና በአንድ ክላሽንኮቭ መሣሪያ " ሚስት " እንድትሆን መሠጠቷን መቃወሟን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቡና ጫናና አካላዊ ቅጣት አስተናግዳለች፡፡ የጥንካሬ ተምሳሌት የሆነችው ጸሀይነሽ በአሁኑ ሰዓት ፈቅዳ በትዳር ከተጣመረችው ባለቤቷ አንድ ልጅ ወልዳለች፡፡

በፕሮጀክቱ በእንግዳ ተቀባይነት በመስራት ላይ የምትገኘው ጸሐይነሽ ባሏ እንዲሆኑ በወላጆቿ ከተመረጡላት አዛውንት በ" ጥሎሽ " ተቀብለው ያልመለሷቸውን ከብቶች ዋጋ በየወሩ በመክፈል ላይም ትገኛለች፡፡

ወጣቷ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከእርሷ አልፎ ለአካባቢው ማሕበረሰብ ያስገኘውን ጠቀሜታ ስትገልጽ " የከብት ጭራ ተከትለን እንኖር የነበርን ሰዎች ዛሬ እርሻ አርሰን ፣ ንጽህ የመጠጥ ውሃ እሩቅ ሳንጓዝ አግኝተን ፣ ወፍጮ በመኖሪያ አካባቢያችን ተተክሎልን እየተጠቀምን ነው " ትላለች፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ረገድ ለማሳያነት ቀረቡ እንጂ የኦሞ ኩራዝ ልማት ፕሮጀክት 10 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኩራዝ ቁጥር 1 የስኳር ፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ ባለበት በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በርካታ ጠቀሜታዎችን አስገኝቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ቀድሞ በተበታተነ ሁኔታ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ይኖሩ የነበሩ አርብቶ አደሮች በመንደር እንዲሰባሰቡና የማሕበራዊና የመሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡

"ፕሮጀክቱ መጀመሪያዉኑ ሲቀረጽ የአካባቢውን አርብቶ አደር ሕይወት ሙሉ ለሙሉ መቀየርና ተጠቃሚ ማድረግ ቀዳሚ ዓላማው ነበር " የሚሉት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ኑረዲን አሳሮ "ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት አዘጋጅቶና ለእርሻ ምቹ አድርጎ በመንደር ለተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች

መስጠቱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመኖሪያ መንደሮቻቸው የወፍጮ፣ የትምህርት ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃና የጤና ተቋማትን የመሳሰሉ ማሕበራዊ ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ያክላሉ፡፡ከአካባቢው አርብቶ አደር ጋር በተደረሰው ሙሉ ስምምነት መሠረት እስካሁን በሦስት መንደሮች ለተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች ከተገነቡት ከእነዚህ የማሕበራዊ ተቋማት መካከል ለትምህርት ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውም ነው አቶ ኑረዲን የሚናገሩት፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዱ " በዚህ አካባቢ ከሰባተኛ ክፍል በላይ የተማረ የአርብቶ አደር ልጅ ማግኘት በጣም ፈታኝ ነው፡፡ በመሆኑም አርብቶ አደሩ ልጁን እንዲያስተምርና ልጆቹም በአካባቢያቸው ከሚካሄደው ልማት ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለትምህርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል " ይላሉ፡፡

አርብቶ አደሩ ልጆቹን እንዲያስተምር በተደረገው ጥረትም በርካታ ሕጻናት የትምህርት እድል አግኝተዋል፡፡በተለይም አርብቶ አደሩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመተው ሴት ልጆቹን ጭምር ለማስተማር ፈቃደኛ መሆኑ የትምህርትን ጥቅም እየተረዳ መምጣቱን አመላካች ከመሆን ባለፈ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከጅምሩ አንስቶ የአካባቢውን ማሕበረሰብ በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ ይዞት የተነሳውን ዓላማ እያሳካ መሆኑን ያሳያል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ የአካባቢው አርብቶ አደር ከአገሪቱ ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑን ተከትሎ ለዚህ ችግር መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ፕሮጀክቱ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን ይናገራሉ፡፡

" የአካባቢው አርብቶ አደር ተበታትኖና ለከብቶቹ ግጦሽና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ነበር ኑሮውን የሚገፋው፡፡ ይህንን የአኗኗር ሁኔታ ለመቀየር በአርብቶ አደሮቹ ሙሉ ስምምነት በመንደር እንዲሰባሰቡ ተደርጓል፡፡ በመንደር ለተሰባሰቡት ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችና ማሕበራዊ ተቋማት ፕሮጀክቱ ገንብቶላቸዋል፡፡ለአርብቶ አደሮቹ ብቻ ሳይሆን ለክብቶቹም አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ተሟልተዋል፡፡ የአርብቶ አደሮቹ ሕይወት መሠረታዊ በሚባል መልኩ እስኪለወጥ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል " በማለት ይናገራሉ፡፡

የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሉካ ውብነህም የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአካባቢው አርብቶ አደር ኑሮ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡ " በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች የስኳር ፕሮጀክቱ አዘጋጅቶ ከሰጣቸው በመስኖ የሚለማ መሬት በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ በአርብቶ አደር አካባቢዎች በአንድ ትምህርት ቤት 20 ተማሪዎችን ማግኘት በጣም ከባድ የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን እስከ 207 ተማሪዎችን ማስተማር ተችሏል፡፡ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ከወንዶች ጋር ተመጣጣኝ መሆኑም አበረታች ነው፡፡ ይህ በአርብቶ አደር አካባቢ የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ይህም የመንደር ማሰባሰብ ስራው ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ የሚያሳይ ነው " በማለት ይዘረዝራሉ፡፡

ለአካባቢው አርብቶ አደር ማሕበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን በመስጠት ላይ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከጅምሩ የሰራቸው ስራዎች የተነሳለትን ዋና ዓላማ በማሳካት ላይ እንደሚገኝ አመላካች ነው፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች በ“ቾይስ ቅድሚያ ለሴቶች” የሩጫ

ውድድር ላይ ተሳተፉ

ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት፣ ከነባር ስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችና ከግብይት ዘርፍ የተውጣጡ 156 ሴት ሠራተኞች ለ11ኛ ጊዜ በተካሄደው በ“ቾይስ ቅድሚያ ለሴቶች” የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተሳተፉ፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ሠራተኞቹ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ለ11ኛ ጊዜ መነሻና መድረሻውን መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ አድርጎ በተካሄደው ውድድር ላይም እንደከዚህ ቀደሙ ጥሩ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ተወዳዳሪዎቹ "ሴቶችን ለማብቃት የሴቶች ሚና ምን መሆን አለበት?" በሚል ርዕስ በባማ ሬስቶራንት ውይይት አድርገዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የካቲት 29 ቀን 2006 ዓ.ም በዓለም ለ103ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ38ኛ ጊዜ "የፆታ እኩልነት የልማት እቅዶቻችንና የህዳሴያችን መሠረት ነው" በሚል መሪ ቃል የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች በድምቀት ታስቦ ውሏል፡፡

በፕሮጀክቱ ድጋፍ አርብቶ አደሮቹ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት በመሸጋገር ላይ ይገኛሉ

    ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

1 3

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

1 2

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

ኮርፖሬሽኑ መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ

ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል

ስኳር ኮርፖሬሽን መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ በሚኒስትር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ገለጹ፡፡

በካይዘንና የለውጥ ስራ አመራር ዘርፍ በለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት የካቲት 24/2006 ዓ.ም በተዘጋጀው የመልካም አስተዳደር የውይይት መድረክ በኮርፖሬሽኑ የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት በመንግሥት ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው መልካም አስተዳደርን የማረጋገጥ ስራ በኮርፖሬሽኑም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ስኳር ለማምረት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ወሳኝ እንደሆነም አቶ ሽፈራው ገልጸዋል፡፡

በካይዘንና የለውጥ ስራ አመራር ዘርፍ የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ታፈሰ አሰፋ የመልካም አስተዳደር ጽንሰ ሃሳብን እና በኮርፖሬሽኑ ያለውን የመልካም አስተዳደር ሁኔታ የዳሰሰ መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ዓላማ በኮርፖሬሽኑ የተጠናከረ የልማት ሰራዊት በመፍጠር የማስፈጸም አቅም መገንባት እንደሆነም አቶ ታፈሰ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከሰራተኞች ለቀረቡ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ከዋና የውይይት መድረክ በመቀጠል በስራ ዘርፎች ደረጃም ሰራተኛው በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በስፋት ተወያይቷል፡፡

በሌላ ዜና የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች በቀሪዎቹ የ2006 በጀት ዓመት ወራት ውስጥ ርብርብ በሚያስፈልጋቸው የኮርፖሬሽኑ እቅድ ላይ የካቲት 25/2006 ዓ.ም ተወያይተዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ እቅድ መሰረት በቀሩት ወራት ውስጥ በፕሮጀክቶች የአገዳ ተከላ ስራው በከፍተኛ ፍጥነትና ቅንጅት መከናወን እንደሚገባው የኮርፖሬሽኑ እቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶለሳ ገደፋ አሳስበዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት ስራ እንደሚጀምሩ ለሚጠበቁና ግንባታቸው እየተፋጠነ ለሚገኙ ፋብሪካዎች ከወዲሁ የአገዳ ተከላ ስራው አብሮ መሄድ እንደሚገባው ነው አቶ ቶለሳ የገለጹት፡፡ ለዚህም ሲባል ሁሉም ዘርፎች ከፕሮጀክቶች ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎችና ድጋፎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለእቅዱ መሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡ በአጽንኦት አስገንዝበዋል፡፡

በማጠቃለያም የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ አገዳ የመትከል ስራን እንደ ቁልፍ ስራ በመውሰድ ሁሉም ዘርፍ የሚያከናውነውን ስራ ከዚህ ጋር አስተሳስሮ ለስኬቱ እንዲረባረብ አሳስበዋል፡፡

ውይይቱ በተደረገበት ወቅት

የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ...

ዋና ዳይሬክተሩ ፋብሪካውን በመገንባት ላይ ከሚገኘው ኮምፕላንት የተሰኘ የቻይና ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የፋብሪካ ግንባታው የእስካሁን እንቅስቃሴ አጥጋቢና በተያዘለት እቅድ መሠረት በመጓዝ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የግንባታው በተያዘለት እቅድ መሠረት መጠናቀቅ ለኮርፖሬሽኑና ለኩባንያው የጋራ ተጠቃሚነት መልካም መሆኑንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

በግንባታው ሂደት የሚያጋጥሙ ማናቸውንም ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚፈቱ ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተው በቀጣይ በየወሩ በመገናኘት በሚኖሩ ለውጦችና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካባ መርጋ እንደገለጹት በኮምፕላንት ኩባንያ አማካይነት በመከናወን ላይ የሚገኘው የፋብሪካ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

ለፋብሪካው ግንባታ ከሚያስፈልጉ ግብአቶች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው የፕሮጀክቱ ሳይት ላይ መድረሱንና ቀሪው 20 በመቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሎ አገር ውስጥ እንደሚገባም አቶ ካባ አስታውቀዋል፡፡

የፋብሪካው ግንባታ በህዳር ወር 2007 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ከኩባንያው ጋር ውል የተገባ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ የእስካሁኑ ስራ ግንባታው በእቅዱ መሠረት እየሄደ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል፡፡

መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ግንባታን በተመለከተም ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት በሁለት መንደሮች የ184 የመኖሪያ ቤቶችና መኖሪያ ያልሆኑ የ22 ብሎኮች ግንባታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አቶ ካባ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ መንደሮች በመከናወን ላይ የሚገኘው የመኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ግንባታ አፈጻጸም 72.5 በመቶ መድረሱንና በፋብሪካ ሳይት የሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በመጋቢት ወር እንደሚጀመርም ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሲጂኦሲ በተባለ የቻይና ኩባንያ አማካይነት በማስገንባት ላይ የሚገኘውና ከአዋሽ አርባ እስከ ፋብሪካው የሚያደርሰው የ25.2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታም በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ አቶ ካባ ጠቁመው ግንባታው እስከሚቀጥለው ታህሳስ ወር ድረስ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡

ከስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን 13ሺ የሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት ክፍተት እንዳይኖር ፋብሪካው ከአሚባራ እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የሸንኮራ አገዳ አብቃይነት፣ የመሸጥና የመግዛት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት ፋብሪካውን በመወከል ስራ አስኪያጁ አቶ ካባ መርጋ ሲሆኑ የእርሻ ልማት ማህበሩን በመወከል ደግሞ የልማቱ ባለቤትና ስራ አስፈጻሚ ሼህ የሱፍ ዑመር ናቸው፡፡

በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት መጋቢት 18/2006 ዓ.ም በተከናወነው የፊርማ ሥነ ስርአት ላይ የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ካባ ባደረጉት ንግግር የአሚባራ እርሻ ልማት ማህበር 6ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ አልምቶ ለፋብሪካው ለማቅረብ መስማማቱን ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ የፊርማ ሥነ ስርዓቱ እስከተደረገበት ቀን ድረስ 600 ሄክታር መሬት ላይ አገዳ መትከሉን አስታውቀው የተከላ ስራውን እስከ ግንቦት 30/2006 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠናቅቅ ተናግረዋል፡፡

የአሚባራ እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ስራ አስፈጻሚ ሼህ የሱፍ በበኩላቸው የእርሻ ልማታቸው ከፋብሪካው በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ከኮርፖሬሽኑ ጋር በገቡት ውል መሠረት የሸንኮራ አገዳ አምርተው ለፋብሪካው እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡

በሌላ ዜና በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች በሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት ተሠማርተው ከልማቱ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተርና የስራ ኃላፊዎች ከአፋር ክልል፣ ዞንና ወረዳ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ለአመራሮቹ በሸንኮራ አገዳ አምራችነትና አቅራቢነት ጠቀሜታዎች ዙሪያ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተሞክሮ ምን እንደሚመስል ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን አመራሮቹም በቀጣይ አርብቶ አደሮቹን በጉዳዩ ዙሪያ ለማወያየት ተስማምተዋል፡፡

አቶ ካባ መርጋ

ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

1 51 4

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የምርምር ጣቢያ ባለፉት ስድስት ወራት የስኳር ምርታማነትን ማሻሻል የሚያስችሉ የምርምር ሥራዎችን በማከናወን ረገድ ከስኳር ፋብሪካው ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወዮ ሮባ ጣቢያውን በጐበኙበት ወቅት እንደተገለጸው የምርምር ጣቢያው የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን ከተለያዩ አገሮች በማስመጣትና ከአካባቢው የአየር ጸባይ ጋር በማላመድ ወደ ማስፋፊያና ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

የምርምር ጣቢያው ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ሀጎስ በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ ከፈረንሳይ፣ ከኩባ፣ ከሱዳንና ከህንድ ወደ 12ዐ የሚጠጉ አዳዲስ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን በማስመጣትና በወረር ኳራንቲን ከበሽታ ነፃ መሆናቸውን በማረጋገጥ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የእርሻ ማሳዎች የማላመድ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ሓዱሽ ገለጻ የመተሐራ ምርምር ጣቢያ ወደ አገር ውስጥ የገቡ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን በማባዛት በስኳር ኮርፖሬሽን ስር ለሚገኙ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና የስኳር ፋብሪካዎች የዘር ምንጭ ሆኖ እየሠራ ነው፡፡

ከ12ዐዎቹ የአገዳ ዝርያዎች መካከል ከ5ዐ በላይ የሚሆኑት በማሳ ላይ ተተክለው የስምንት ወር ዕድሜ ላይ መድረሳቸውና ከዚህ ቀደም ለምርት ከሚደርሱበት 2ዐ ወራት ዕድሜ በግማሽ መቀነስ መቻሉ ተመልክቷል፡፡

በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በፕሮጀክቱ አካባቢዎች እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በፕሮጀክቱ አካባቢ የዲዴሳ ሸለቆን የከበቡ ተራራማ ቦታዎች ሰፊ የደን ሽፋን ያላቸው ሲሆን ደኑ በአካባቢው የሚለማውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ ከጎርፍ አደጋ የመከላከል ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ በኩል በደኑ ውስጥ በየዓመቱ የሚከሰት የሰደድ እሳት የደን ሃብቱ ላይ ጉዳት የሚያደርስና ለፕሮጀክቱ ንብረቶችም ስጋት መሆኑ በመታመኑ የእሳት አደጋውን

ለመከላከልና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ለመስራት ኮሚቴ ተቋቁሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

በዚህ መሰረት የሸንኮራ ልማቱን አስቀድሞ ከእሳት አደጋ ለመከላከል እንዲቻል በማሳዎች ዙሪያ የእሳት መከላከያ ስራዎች እንዲሁም በፋብሪካ፣ በመጋዘኖችና፣ በሰራተኞች መኖሪያ አካባቢዎች ደግሞ የደረቁ ቁጥቋጦዎችንና ሳሮችን የማስወገድ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር በመጪው የክረምት ወራት የዛፍ ችግኞችን መትከል እንዲቻል የተለያዩ

ዝርያዎች ያላቸውን ችግኞች የማፍላት ስራም እየተሰራ ነው፡፡

በተጨማሪም ለአካባቢው የአየር ሁኔታ ጤናማነት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለውንና ለተለያዩ የዱር እንስሳት መኖሪያ የሆነውን የአካባቢውን ደን ለመጠበቅና ለመንከባከብ በፕሮጀክቱ አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማዳበሪያ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ ከአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ያለክፍያ ተጨማሪ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ ሰጪ የስራ ዘርፍ ሰራተኞች ከመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ውጪ በቀን ከ30 ደቂቃ እስከ 1፡00 ሰዓት ተጨማሪ አገልግሎት ያለክፍያ መስጠት ጀመሩ፡፡

ሰራተኞቹ አገልግሎቱን ለመስጠት የወሰኑት ከጥር 23 እስከ የካቲት 15/2006ዓ.ም በፋብሪካው የመልካም አስተዳደርና የአሰራር ክፍተቶች ላይ በየደረጃው የለውጥ ንቅናቄ መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

በፋብሪካው የካይዘን ፍልስፍናን ወደ ላቀ ደረጃ የማድረስ ዓላማን ይዞ የተነሳው የለውጥ ንቅናቄ መድረኩ በየዘርፉ ያሉ የድርጅቱን ሰራተኞች፣ የመስተዳድር

አካላት፣ የአካባቢውን ማህበራዊ ተቋማት፣ ት/ቤቶች፣ የፀጥታ ኃይሎችንና ቤተ-እምነቶችንም ጭምር ያሳተፈ ነበር፡፡

ከውይይት መድረኩ ቀደም ብሎ የአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማናጅመንት ሰራተኞች በተለይም የንብረት ጥበቃ ሰራተኞች አስቀድሞ በተጀመረው የካይዘን ትግበራ በመነሳሳት ያለክፍያ ባደረጉት በቀን የአንድ ሰዓት ተጨማሪ አገልግሎት 20.38 ሄክታር ማሳ ከእርሻ ዘርፍ ተረክበው አገዳ በመትከል፣ አርመውና ማዳበሪያ ሰጥተው በማሳደግ አገዳው ሲደርስ ቆርጠው ለፋብሪካው ለማቅረብ ቃል ገብተው ነበር፡፡እነዚህ ሰራተኞች በአሁኑ ወቅትም ቃላቸውን በመተግበር በተረከቡት ማሳ

ላይ አገዳ ተክለው በሚገባ በማጠናቀቅ ሞዴል መሆን መቻላቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ሌሎች የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችም በዚህ ውጤት በመነሳሳት በተለያዩ መስኮች በቀን ከ30 ደቂቃ እስከ 1፡00 ሰዓት ተጨማሪ አገልግሎት ያለክፍያ ለመስጠት ወስነው ተግባራዊ እቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡

የንቅናቄ የውይይት መድረኩ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ምክክርና የስድስት ወራት የአፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥርዓተ ፆታ ኃላፊዎችና ተጠሪዎች ከየካቲት 13 -15/2006ዓ.ም በሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ላይ ምክክርና የአፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የተካሄደው ምክክርና ግምገማ ያተኮረው ከአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንፃር በስኳር ልማት ዘርፍ የሴቶችና ወጣቶች እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ላይ ነው፡፡ በወቅቱ በዘርፉ ልማት የሴቶች ተሳትፎ በቁጥር እጅግ አነስተኛ ከመሆኑ አንፃር የሴቶችን ሚና ለማጎልበት የተከናወኑ ተግባራት በስፋት ተዳሰዋል፡፡

መድረኩ የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ የተደረገበትና መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት መሠረት የተጣለበት ከመሆኑም ባሻገር በቀጣይነት የአገሪቱን የሥርዓተ ፆታ ዕቅድ በስኳር ልማት ዘርፍ ለማሳካት ምን አይነት ተግባራት መከናወን እንዳለባቸው ምክክር የተካሄደበት ነበር፡፡

የሥርዓተ ፆታ ጉዳይ ከሌሎች ዘርፍ ዘለል ሥራዎች /cross cutting issues/ ጋር መቀናጀቱ ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ የሚያስችል እንደመሆኑ በሥርዓተ ፆታና ተዛማጅ ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አቶ ግርማ ጉማታ የኮርፖሬሽኑ የማኅበራዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያ፣ ኤች.አይ.ቪ. ኤድስን በተመለከተ ወ/ሮ ካሠች ሺበሺ የኮርፖሬሽኑ ኤድስን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች አስተባባሪ፣ እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃና ሥርዓተ ፆታ ጥብቅ ተዛምዶ ላይ አቶ ብርሃኑ ራቦ የኮርፖሬሽኑ የአካባቢ ጥበቃ ቡድን መሪ በምክክር መድረኩ በመገኘት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

በተመሳሳይ በኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በኩል ሊደረግላቸው የሚገቡ ድጋፎችን በተመለከተ ከዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ተወካይ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ አስተያየት የሰጡት የኮርፖሬት ሥርዓተ ፆታ ዳይሬክተር ወ/ሮ እንጉዳይ አሰፋ የአብዛኛዎቹ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥርዓተ ፆታ ጽ/ቤቶች በተያዘው በጀት ዓመት የተከፈቱ ከመሆናቸው አንፃር ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በዘርፉ የተመዘገቡት ውጤቶች አበረታች መሆናቸውንና በጎ ጅምሮችም መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተዘጋጀው መድረክ አቅም እንደፈጠረላቸው በመግለጽ ይህን መሰል መርሃ ግብር በየወቅቱ መካሄድ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

የመተሐራ ምርምር ጣቢያ ከስኳር ፋብሪካው ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው

• ከተለያዩ አገራት ያስመጣቸውን የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ወደ ምርት እንዲገቡ በማድረግ ላይ ይገኛል

» ገጽ.19

የፋብሪካው ሰራተኞች ያለክፍያ የሸንኮራ አገዳ ሲተክሉ

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን         ጣፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

1 6 1 7

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

የመተሐራ ምርምር ጣቢያ ...

በምርምር እና ስልጠና ዘርፍ በሸንኮራ አገዳ አመራረትና ዝርያ ዴቨሎፕመንት ምርምር ዳይሬክቶሬቶች የ51 ሙከራዎች ትግበራ እና ክትትል መደረጉ ተገለጸ፡፡

ዘርፉ በተያዘው የበጀት አመት ዝርያዎችን በማላመድ፣ በማሻሻል እና በማፍለቅ ላይ ያተኮሩ 59 ሙከራዎችን ለመተግበር አቅዶ 51 ሙከራዎችን ማከናወን መቻሉ ነው የተጠቆመው፡፡

ከሙከራዎቹ ትግበራና ክትትል ጎን ለጎን የአዳዲስ ንድፈ ሃሳቦች እና ሙከራዎች ዝግጅት ስራ መቀጠሉንና የዚሁ ዝግጅት አንድ አካል የሆነው የአዳዲስ ንድፈ ሃሳቦች እና ሙከራዎች ክለሳ/Annual Research Review/ ተካሂዷል፡፡

በአዳዲስ ንድፈ ሃሳቦች እና ሙከራዎች ክለሳ ላይ በተካሄደ የውይይት መድረክ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር

ተቋማት የተጋበዙ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን፣ በሸንኮራ አገዳ አመራረት፣ በዝርያ ዴቨሎፕንት እና በስኳር ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬቶች 20 የምርምር ሙከራዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተሰጡ ሙያዊ አስተያየቶች ተካተው የዘርፉ ቀጣይ የምርምር አውታሮች ሆነው እንዲጸድቁ ተወስኗል፡፡

በወቅቱ እንደተገለጸው የምርምር ሙከራዎቹ ረዘም ላለ ጊዜ በጥንቃቄ የተለዩ፣ የምርታማነት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉና ከሦስት እስከ ዘጠኝ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ተተግብረው ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመርና ወጪ ለመቀነስ የሚያስችሉ እንደሚሆኑ መገለጹን የዘርፉ የሕዝብ ግንኙነት ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ የአገሪቷ ክልሎች በተሰባሰቡ ከ4ዐዐ ዓይነት በላይ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ላይ ጥናት እየተካሄደ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል በሽታን የመቋቋም አቅም ያላቸውንና የበለጠ ውጤት የሚያመጡትን በአጭር ጊዜ በመለየት ወደ ተግባር እንደሚገባ ነው በጉብኝቱ ወቅት የተብራራው፡፡

በሌላ በኩል የምርምር ጣቢያው እያካሄደ ያለው የፊልተር ኬክ ማዳበሪያ ጥናት እየተጠናቀቀ ሲሆን፣ ተግባር ላይ ሲውል የፋብሪካውን የማዳበሪያ ግዥ ወጪ ከ25 – 3ዐ% እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወዮ ሮባ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ የምርምር ዘርፍ እንዲያድግ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልፀዋል፡፡

በአለም ገበያ ተፎካካሪ ለመሆን የምርምር ሥራን ማጠናከር እንደሚገባ ያመለከቱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ምርምር ጣቢያው እያከናወነ ያለው ተግባር እጅግ የሚያበረታታና መተሐራ ስኳር ፋብሪካም የምርት ጥራትን በማሻሻል የተጀመረውን ለውጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስበት እንዲሆን ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አመራር የምርምር ጣቢያው ደጋፊ በመሆኑ ለውጦች መታየታቸውን ያወሱት ኃላፊው ይህም ለሌሎች ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች አብነት ሊሆን የሚችል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በምርምር እና ስልጠና ዘርፍ የ51 ሙከራዎች ትግበራና ክትትል ተደረገ

በተንዳሆ በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በቆሎና የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ

በተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ በመንደር የተሳበሰቡ 1 ሺ 500 የሚጠጉ የቤተሰብ መሪ አርብቶ አደሮች 3 ሺ 700 ሄክታር መሬት ላይ በቆሎና የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

በዱብቲ ወረዳ ኡንዳ ቡሪ በተባለው አካባቢ አርብቶ አደሮች በተዘጋጀላቸው የእርሻ ማሳ በቆሎ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲምና ቃሪያ በማምረት ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነትና ማህበረሰብ ጉዳይ አገልግሎት ኃላፊ ሀጂ አብዱ ሀሰን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አርብቶ አደሩ በመንደር ተሰባስቦ የተሻለ ሕይወት እንዲመራ ለማድረግ በዱብቲ ወረዳ 10 መንደሮችን ለመገንባት አቅዶ የዘጠኙ ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ከነዚህም መካከል በአስቦዳ፣ ቦይና ኡንዳ ቡሪ የተሰባሰቡ የቤተሰብ መሪዎች የተረጋጋ ሕይወት

መምራት መጀመራቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በመንደሮቹ ለሚሰባሰቡ አርብቶ አደሮች ለእርሻ ስራ የሚውል ከ10 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ሀጂ አብዱ ከዚህም ውስጥ የ3 ሺ 700 ሄክታሩ ዝግጅት ተጠናቆ ለአርብቶ አደሮቹ መከፋፈሉንና አርብቶ አደሮቹም የተለያዩ ሰብሎችን በመዝራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አርብቶ አደሮቹ በተሰባሰቡባቸው መንደሮች የትምህርት፣ የጤና እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆንና በልማቱም ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዲያጎለብት ከማኅበረሰቡ ጋር በቅርበት እየተሰራ

እንደሚገኝ ሀጂ አብዱ ጠቅሰው አርብቶ አደሮች እንዲሰባሰቡባቸው የተገነቡ መንደሮች በውስጥ ቁሳቁስ እንዲሟሉና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ጋሱሪ በተባለ ሳይት ለእርሻ በተሰጣቸው ማሳ ላይ የተለያዩ ሰብሎችን ያለሙት አርብቶ አደር አሊ አደም "በስኳር ልማቱ አማካኝነት በተፈጠረልኝ ምቹ ሁኔታ ከብት ከማርባት ጎን ለጎን የእርሻ ስራ በመስራት እየተጠቀምኩ ነው" ብለዋል፡፡

አርብቶ አደሩ አክለውም "በአሁኑ ሰዓት ቲማቲምና ቃሪያ ስለደረሰ ምርት በመሰብሰብ ላይ እገኛለሁ፡፡ በቆሎም እየደረሰ ነው፡፡ ለከብቶቼም ሳር እዚሁ አገኛለሁ" ማለታቸውን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ አመልክቷል፡፡

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በቀን ከ70 ሄክታር መሬት በላይ ሸንኮራ አገዳ እንዲተከል አቅጣጫ ተቀመጠ

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በቀን ከ70 ሔክታር መሬት በላይ በሸንኮራ አገዳ ተክል ለመሸፈን የሚያስችል ስራ ለመስራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተስማሙ፡፡

ስምምነቱ የተደረሰው ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልልና በፌዴራል ደረጃ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ከጥር 25-27 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በተደረገ ውይይት ነው፡፡

ውይይቱ የተመራው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ሽፈራው ጃርሶ ሲሆን የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ባለድርሻ አካላቱ በአፈጻጸማቸው እስካሁን የደረሱበትን ደረጃና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች አንስተው በዝርዝርና በጥልቀት መክረውባቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሁለት ቡድን ተከፍለው በመንደር ማሰባሰብ ሂደት፣ በመሠረተ ልማት አቅርቦት፣ በመስኖ ግንባታ፣ በእርሻ ስራ፣ በመንገድና በቤቶች ግንባታ ያሉትን አፈጻጸሞች በስፋት ከገመገሙ በኋላ በቀጣይ ማን ምን መስራት እንዳለበትና መቼ መስራት እንዳለበት የድርጊት መርሐ ግብር አውጥተዋል፡፡

በድርጊት መርሃ ግብሩ መሠረትም በኩራዝ ቁጥር አንድ በ2006 ዓ.ም እስካሁን የለማውን 3ሺህ ሄክታር ጨምሮ 16 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት ከስምምነት ተደርሷል፡፡ ይህንንም ለማሳካት በአሁኑ ወቅት በቀን ከ70 ሔክታር በላይ ሸንኮራ አገዳ መትከል እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ተሰጥቶት ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር አርብቶ አደሩን በአገዳ አብቃይ ሕብረት ስራ ማሕበራት በማደራጀት እያንዳንዱ የቤተሰብ መሪ ለልማት ከሚሰጠው አንድ ሔክታር መሬት ላይ 0.25 ሄክታር ለሰብል ልማት እንዲያውለውና ቀሪውን ሸንኮራ አገዳ አምርቶ ለፋብሪካ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ለዚህም ሲባል በየደረጃው ያሉ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት አርብቶ አደሩን በማወያየትና ጥቅሙን በማስገንዘብ ፈቃደኛነታቸውን የማረጋገጥ ስራ እንዲሰሩ ተወስኗል፡፡

ለፕሮጀክት ስራዎች መቀላጠፍ በስኳር ኮርፖሬሽን እያንዳንዱን ፕሮጀክት የሚከታተልና የሚደግፍ ዴስክ እንደሚቋቋምም በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

የድርጊት መርሐ ግብሩን አፈጻጸም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ እየገመገሙ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ እያስቀመጡ ለመሄድ በውይይቱ ወቅት ተስማምተዋል፡፡

ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በተደረገው በዚህ የውይይትና የምክክር መድረክ ላይ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መስተዳድር፣ የፌዴራል ውሃ ስራዎችና ዲዛይን ድርጅት፣ የፌዴራል ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን፣ የፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን፣ የደቡብ ውሃ ስራዎች ዲዛይን ኢንተርፕራይዝ፣ የደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ የደቡብ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የደቡብ ክልል ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ ተሳትፈዋል፡፡

አርብቶ አደር አሊ አደም በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል

  ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን         ጣፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

1 9

ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

1 8

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

ስኳር ኮርፖሬሽን እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

ስኳር ኮርፖሬሽን እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኮርፖሬሽኑን የሰው ሀብት በማልማት ረገድ በትብብር ለመስራት ተስማሙ፡፡

በስኳር ልማት ዘርፍ የተሰማራውን እና ወደፊትም የሚሰማራውን የሰው ሀብት ለማልማት የሚያስችላቸውን የትብብር መርሐ ግብር የመግባቢያ ሰነድም ኮርፖሬሽኑ እና ኤጀንሲው ፈርመዋል፡፡

የሰው ሀብት ልማት የትብብር መርሐ ግብር የመግባቢያ ሰነዱን ኮርፖሬሽኑን በመወከል በሚንስትር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ እንዲሁም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲን በመወከል የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድወሰን ክፍሉ ፈርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና የስኳር ልማት ዘርፉ የሰው ሀብት ወጥ በሆነ እና በተቀመጠው መስፈርት መሠረት ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ በስምምነቱ ወቅት ተመልክቷል፡፡

ስኳር ፋብሪካዎችና ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሚፈልጉትን በተለያዩ ደረጃ በዘመናዊ መንገድ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማሟላት የፌደራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲና በየክልሉ የሚገኙ የማሰልጠኛ ተቋማት ለስኳር ልማት ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችንና ቴክኖሎጂን በማቅረብ የአገሪቷን ስኳር ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት መጨመር የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑም ተገልጿል፡፡

የሰው ሀብት ልማት የትብብር መርሐ ግብሩ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለስኳር ኢንዱስትሪው በበቂ ሁኔታ በማፍራት የዘርፉን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ወሳኝ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በትብብር መርሐ ግብሩ መሠረት ስኳር ኮርፖሬሽን እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ለስልጠና መርሐ ግብሩ አስፈላጊ የሆኑ መምህራንን እና የዘርፉ ኢንዱስትሪ አሰልጣኞችን ለማፍራት፣ በዘርፉ የሚያስፈልገውን የሥርዓተ ትምህርትና ሌሎች አጋዥ መሣሪያዎችን ለማዘጋጀት እንዲሁም ለትብብር ስልጠናው አግባብነት ያላቸውን የማሰልጠኛ ተቋማትና የኢንዱስትሪውን አቅም ለመገንባት በጋራ ይሠራሉ፡፡

በተጨማሪም በስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን በትብብር ሥልጠና ለማፍራት፣ የትብብር ሥልጠናውን ሂደት በጋራ ለመደገፍና ክትትል ለማድረግ እንዲሁም የሙያ ብቃት ምዘና ለማከናወን በጋራ እንደሚሠሩ ተመልክቷል፡፡

በመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነ ስርአቱ ወቅት በሚኒስትር

በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚሰራው የጊዜያዊ ግድብ ግንባታ

እየተፋጠነ ነው

በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዛሬማ ወንዝ ላይ በሱር ኮንስትራክሽን በመገንባት ላይ የሚገኘው ጊዜያዊ የውኃ አቅጣጫ መቀልበሻ ግድብ ( ኮፈር ዳም ) ግንባታ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ የተመራ የኮርፖሬሽኑ አመራር ቡድን የካቲት 12 / 2006 ዓም የግድቡ ግንባታ የሚከናወንበትን ስፍራ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አመናይ መስፍን በወቅቱ እንደገለጹት 80 ሜትር ቁመት ያለው የኮፈር ዳም ስራ 33 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ቀሪውን ስራ ክረምት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

ኮፈር ዳሙ በወንዙ ላይ ለሚገነባውና 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ለሚኖረው ለዋናው የሜይዴይ ግድብ ሥራ ጥሩ መደላድል እንደሚፈጥርም ነው አቶ አመናይ የተናገሩት፡፡

የሜይዴይ ግድብ ከሚይዘው ውሃ ውስጥ ፕሮጀክቱ ከ40 ሺህ እስከ 50 ሺህ ሄክታር በሚደርስ መሬት ላይ ለሚያለማው የሸንኮራ አገዳ የሚጠቀመው 890 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ብቻ መሆኑንም ነው ስራ አስኪያጁ ያመለከቱት፡፡

በግድቡ አማካይነት የሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ከአገዳ ልማቱ ባሻገር ለአካባቢው ስነ ምህዳር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትና የቱሪስት መስህብ በመሆንም ተጨማሪ ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል አቶ አመናይ ገልጸዋል፡፡

ከኮፈር ዳሙ ግንባታ ጎን ለጎን 75 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የዋና የውሃ መሄጃ ቦይ (ሜይን ካናል) የመጀመሪያው 10 ኪሎ ሜትር ስራ 65 በመቶ መጠናቀቁንም ዋና ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡ ቀሪ ስራው በተያዘው የበጀት አመት እንደሚጠናቀቅና በ2007 የበጀት አመት ተጨማሪ የ10 ኪሎ ሜትር ስራ እንደሚጀመር አክለው ተናግረዋል፡፡

የዋናው የሜይዴይ ግድብ ስራ እስከሚጠናቀቅ በቃሌማ ወንዝ ላይ ግድብ ተሰርቶ 12 ሚሊዮን ኩብ ውሃ መያዙን ያስታወቁት አቶ አመናይ በዚህም 3 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ መትከል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ከተከዜ ውሃ በመሳብ 7 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ የማልማት ስራም በሂደት ላይ እንደሚገኝስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

12 ሺ ቶን አገዳ በቀን የመፍጨት አቅም የሚኖረው የመጀመሪያ ምዕራፍ ፋብሪካ ግንባታ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው ግንባታው ከሰኔ 2006 እስከ መስከረም 2007 ባሉት ጊዜያት በቻይና ኩባንያ ይጀመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ባደረጉት ንግግር የትብብር የሰው ሀብት ስልጠና መርሐ ግብሩ ከስኳር ምርት ባለፈ ከዘርፉ ልማት ጋር ተያያዥ ለሆኑ መስኮች አስፈላጊውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት የሚቻልበትን ሁኔታ መዳሰስና ማካተት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ልምድ የተወሰደባቸው የጎረቤት አገሮችና ሌሎችም የስኳር ኢንዱስትሪዎች የራሳቸው ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሏቸው የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ የትብብር ስልጠናው የአገሪቱን የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት የጎላ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወንድወሰን ክፍሉ በበኩላቸው በስኳር ልማት ዘርፍ የትብብር ስልጠና ለመስጠት የሙያ ደረጃ ምደባና ስልጠናዎች የሚሰጡባቸው ሙያዎች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

እነዚህ የተለዩት ስልጠና የሚሰጥባቸው የሙያ ዓይነቶች ከእርሻ ጀምሮ እስከ ምርት ድረስ ያለው ሥራ የሚፈልጋቸውን ክህሎቶች እና የዕውቀት መስኮች የሚያካትቱ መሆኑንም አቶ ወንድወሰን አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሁለቱ ተቋማት በትብብር ባከናወኗቸው ተግባራት መሰረት በ " ሲ " ወይም በደረጃ 1 እና 2 የሚያሰለጥኑ 70 ባለሙያዎች በስኳር ፕሮጀክቶች ተግባር ተኮር ሥልጠና ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡በደረጃ 3 እና 4 አሠልጣኞችን ለማፍራት የተለያዩ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ እንደሚገኙም አብራርተዋል፡፡

ስምምነቱ ለስኳር ኢንደስትሪው የሰለጠነ ሰው ኃይል እንደሚያስገኝ ታምኖበታል

የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አመናይ መስፍን

በመገንባት ላይ የሚገኘው ኮፈር ዳም

    ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

2 1

  ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት       ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

2 0

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

እናስተዋውቃችሁ

ስኳር ልማት ፕሮጀክትኦሞ ኩራዝ

ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የኦሞ ወንዝን በሚጋሩት በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ እና በኛንጋቶም ወረዳዎች ፣ በቤንች ማጂ ዞን በሱርማና በሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች እንዲሁም በካፋ ዞን በዴቻ ወረዳ በተመረጡ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው፡፡

በፕሮጀክቱ አምስት የስኳር ፋብሪካዎች የሚገነቡ ሲሆን ሙሉ አገዳ የመፍጨት አቅማቸው ላይ ሲደርሱም ከአምስቱ ሦስቱ እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት እና በአመት 278 ሺ ቶን ስኳር እንዲሁም 26 ሺ 162 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል የሚያመርቱ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ ሁለቱ ፋብሪካዎችም በሙሉ አቅም መፍጨት ሲጀምሩ እያንዳንዳቸው በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ በመፍጨት እያንዳንዳቸው በአመት 556 ሺ ቶን ስኳር እንዲሁም 52 ሺ 324 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የሚገነቡት ስኳር ፋብሪካዎች ከላይ በተጠቀሱት

ወረዳዎች ውስጥ በሚገኝ 175 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብአትነት የሚጠቀሙ ሲሆን ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚሆነው ውሃ ደግሞ በኦሞ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ከሚገኘውና 318 ሜትር ስፋት እና 22 ነጥብ 4 ሜትር ከፍታ ከሚኖረው የውሃ መቀልበሻ ዊር የሚገኝ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የሚገነቡት አምስት የስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ በአጠቃላይ በአመት እስከ 1 ሚሊዮን 946 ሺ ቶን ስኳር እና 183 ሺ 134 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ያመርታሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፋብሪካዎቹ 415 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመርቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 275 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቋት ያበረክታሉ፡፡

በፕሮጀክቱ በመገንባት ላይ የሚገኘው ቁጥር አንድ ፋብሪካ በግብአትነት የሚጠቀመውን አገዳ በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ የተለያዩ የመሬት ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ የሚገኙ ሲሆን እስከ የካቲት ወር 2006 መጨረሻ ድረስ በ4546 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ተተክሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የስራ መስኮች በፕሮጀክቱ በቋሚና ኮንትራት ተቀጥረው እንዲሁም በማሕበር ተደራጅተው ለሚሠሩ አስር ሺ ለሚጠጉ የአካባቢው ተወላጆችና የአገሪቱ ዜጎች የስራ እድል ከፍቷል፡፡ ወደ ፊትም በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈም የአካባቢውን አርብቶ አደር ሕብረተሠብ ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ተበታትነው ይኖሩ የነበሩ አርብቶ አደሮች በመንደር ተሰባስበው የተለያዩ የመሠረተ ልማትና የማሕበራዊ ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በሦስት መንደሮች ለተሰባሰቡ አምስት መቶ ለሚጠጉ አርብቶ አደር የቤተሰብ ኃላፊዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የወፍጮ፣ የሰውና የከብቶች የሕክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች፣ የአርብቶ አደሮች ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንዲሁም የትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙባቸውን ተቋማት አስገንብቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

ከማሕበራዊ ተቋማቱ ግንባታ ባሻገር አርብቶ አደሮቹ በሂደት ወደከፊል አርሶ አደርነት እንዲሸጋገሩ ለማስቻል ከ535 ሄክታር በላይ በመስኖ የሚለማ መሬት አዘጋጅቶና ከእርሻ ስራ እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ስልጠና ሰጥቶ ለአርብቶ አደሮቹ አከፋፍሏል፡፡ እስካሁንም በ405 ሄክታር መሬት ላይ አርብቶ አደሮቹ በቆሎና ሌሎች ሰብሎችን አምርተው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

ከእርሻ መሬት ዝግጅት በተጨማሪ እያንዳንዱ የቤተሰብ መሪ በሚሰባሰብበት መንደር ከቤቱ አጠገብ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን የሚያለማበት መሬት ባለቤት እንዲሆን አስችሏል ፕሮጀክቱ፡፡

በፕሮጀክቱ ከሚገነቡት አምስት ፋብሪካዎች መካከል 12ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው የፋብሪካ ቁጥር አንድ ግንባታ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካይነት በመከናወን ላይ ነው፡፡

ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን       ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ጣ ፋጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት     ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን    

2 32 2

Page 13: ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected]

www.etsugar.gov.et || facebook.com/etsugar

የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት፣ የተሞክሮ ልውውጥ እና የመግባቢያ ሰነድ

የፊርማ ስነ-ስርዓት በሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ

የጎንዮሽ ልማት