ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

12
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 4 ቁጥር 1-መስከረም 2008 ዓ.ም www.etsugar.gov.et || facebook.com/etsugar ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን (2003- 2007) ከስኳር ልማቱ ጋር በተያያዘ ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የኮርፖሬሽኑ የእቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ አስታወቀ፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶለሳ ገደፋ እንዳስታወቁት በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትግበራ አመታት ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር በተደረጉ ርብርቦች በእቅዱ ከተያዘው ግብ በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በእቅድ ዘመኑ አምስት አመታት ለ200 ሺህ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ይዞ ሲሰራ መቆየቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው፣ በአፈጻጸም ከ350 ሺህ በላይ የሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ የስኳር ምርትን ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ አቀደ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2012ዓ.ም) የኩራዝ 1፣2፣3፣እና5፤ የበለስ 1፣2፣3 እና የወልቃይት አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ ስራ በማስጀመር አሁን ያለውን 3.7 ሚሊዮን ኩንታል ዓመታዊ የስኳር ምርት ከ10 እጥፍ በላይ አሳድጎ ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ አቅዷል፡፡ ለዚህም ስኬት እስካሁን የለማውን 96 ሺህ ሄክታር መሬት ጨምሮ 325 ሺህ 324 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ይለማል፡፡ በዕቅድ አመቱ መጨረሻ ከሚመረተው ስኳር ውስጥም 12 ሚሊዮን 220 ሺህ ኩንታል የተጣራ እና 17 ሚሊዮን 740 ሺህ ኩንታል ጥሬ ስኳር ወደ ውጭ በመላክ 1.3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማስገኘት ታቅዷል፡፡ በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ የኤሌክትሪክ ኃይልን በብዛት ለብሔራዊ የኃይል ቋት ለመላክ የሚያደርገውን ጥረት በማጠናከር በ2012 መጨረሻ ከስኳር ተረፈ ምርት (ባጋስ) ይመነጫል ተብሎ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ የስኳር ምርትን ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ ታቀደ ምርቱን ወደ ውጭ በመላክም 1.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታስቧል » ወደ ገጽ3 ዞሯል በውስጥ ገጾች » ወደ ገጽ 3 ዞሯል ምልከታ››ገጽ 10 ጣፋጭ አዲስ ዓመት ይሁንልዎ! የኦሮሚያ ዲያስፖራ የልዑካን ቡድን የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ጎበኘ››ገጽ 5 በስኳር ልማት አካባቢዎች በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተገነቡ *አርሶ/አርብቶ አደሮች ሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነዋል በመጀመሪያው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በስኳር ልማት አካባቢዎች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት አውታሮች መገንባታቸውን የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አስታወቀ፡፡ » ወደ ገጽ 4 ዞሯል አዲሱ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ››ገጽ 11 የእቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶለሳ ገደፋ

Upload: ethiopian-sugar-corporation

Post on 16-Feb-2017

928 views

Category:

Government & Nonprofit


13 download

TRANSCRIPT

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!

ቅፅ 4 ቁጥር 1-መስከረም 2008 ዓ.ምwww.etsugar.gov.et || facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል

ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን (2003-2007) ከስኳር ልማቱ ጋር በተያያዘ ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የኮርፖሬሽኑ የእቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ አስታወቀ፡፡

የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶለሳ ገደፋ እንዳስታወቁት በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትግበራ አመታት ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር

በተደረጉ ርብርቦች በእቅዱ ከተያዘው ግብ በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በእቅድ ዘመኑ አምስት አመታት ለ200 ሺህ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ይዞ ሲሰራ መቆየቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው፣ በአፈጻጸም ከ350 ሺህ በላይ የሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ የስኳር ምርትን ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ አቀደ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2012ዓ.ም) የኩራዝ 1፣2፣3፣እና5፤ የበለስ 1፣2፣3 እና የወልቃይት አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ ስራ

በማስጀመር አሁን ያለውን 3.7 ሚሊዮን ኩንታል ዓመታዊ የስኳር ምርት ከ10 እጥፍ በላይ አሳድጎ ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ አቅዷል፡፡ ለዚህም ስኬት እስካሁን የለማውን 96 ሺህ ሄክታር መሬት ጨምሮ 325 ሺህ 324 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ይለማል፡፡

በዕቅድ አመቱ መጨረሻ ከሚመረተው ስኳር

ውስጥም 12 ሚሊዮን 220 ሺህ ኩንታል የተጣራ እና 17 ሚሊዮን 740 ሺህ ኩንታል ጥሬ ስኳር ወደ ውጭ በመላክ 1.3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማስገኘት ታቅዷል፡፡

በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ የኤሌክትሪክ ኃይልን በብዛት ለብሔራዊ የኃይል ቋት ለመላክ የሚያደርገውን ጥረት በማጠናከር በ2012 መጨረሻ ከስኳር ተረፈ ምርት (ባጋስ) ይመነጫል ተብሎ

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ የስኳር ምርትን ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ ታቀደ

• ምርቱን ወደ ውጭ በመላክም 1.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታስቧል

» ወደ ገጽ3 ዞሯል

በውስጥ

ገጾች

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

ምልከታ››ገጽ 10 ጣፋጭ አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!

የኦሮሚያ ዲያስፖራ የልዑካን ቡድን የአርጆ

ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ጎበኘ››ገጽ 5

በስኳር ልማት አካባቢዎች በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተገነቡ

*አርሶ/አርብቶ አደሮች ሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ እንዲሆኑ የሚያስችሉ

ሥራዎች ተከናውነዋል

በመጀመሪያው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በስኳር ልማት አካባቢዎች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫና የመሰረተ ልማት አውታሮች መገንባታቸውን የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አስታወቀ፡፡

» ወደ ገጽ 4 ዞሯል

አዲሱ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ››ገጽ 11

የእቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶለሳ ገደፋ

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 1 | መስከረም 2008 ዓ.ም | 2

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክትትልቅ ራዕይ አንግበን የማያቋርጥ እድገት ለማስመዝገብ ያላሰለሰ ርብርብ ማድረግ ከጀመርን ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ አመታት በተደረጉ ጥረቶች ባለ ሁለት አኃዝ የኢኮኖሚ እድገት ለተከታታይ ጊዜያት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

በሀገራችን ማምጣት የምንፈልገው ሁለንተናዊ ለውጥ በትልቁ ማቀድና ሌት ተቀን መስራትን የሚጠይቅ ነው፡፡ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የያዝናቸው ትላልቅ የልማት ስራዎች የዚሁ ፍላጎታችን አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ሁሉም እንደሚገነዘበው ባለፉት አምስት አመታት በበርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች የተወጠኑትን ትላልቅ ግቦች ለማሳካት በተደረገው ርብርብ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

እንደሚታወቀው በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የእድገትናትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከተያዙት ትላልቅ እቅዶች ውስጥ የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ አንዱ ነው፡፡ በስኳር ልማት ዘርፍ ባለፉት አምስት አመታት በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች በሀገሪቱ በ1946ዓ.ም የተጀመረውን የስኳር ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እና ለማስፋፋት የተቻለበት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በቀጣይ ልማቱን አጠናክሮ በመቀጠል ኢትዮጵያ በ2016ዓ.ም በዓለም ላይ ከሚገኙ 10 ከፍተኛ የስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ማድረግ እንደሚቻል መገመት ከባድ አይደለም፡፡

በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከ2003ዓ.ም በፊት ተጀምሮ የነበረውን የወንጂ ሸዋ እና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ የፋብሪካዎቹን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል፡፡ በእቅድ ዘመኑ ማጠናቀቂያ ዓመት መንግሥት ከፓኪስታን ባለሃብት በግዢ ያዘዋወረውን የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ አጠናቆ ማስመረቅ እንዲሁም የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎችን የግንባታ ስራ አጠናቆ የሙከራ ምርት ማስጀመር ችሏል፡፡

በሸንኮራ አገዳ ልማትም በ65ሺህ 363 ሄክታር መሬት ላይ አገዳ የተተከለ ሲሆን፣ ይህም በዕቅዱ መነሻ ዓመት ከነበረው 30,397 ሄክታር ጋር ሲነፃፀር የ215 በመቶ ዕድገት መመዝገቡን ያመለክታል፡፡ በስራ ዕድል ፈጠራም ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡ በዚህም የስኳር ልማቱ በሚካሄድባቸው ቆላማ የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተያዘውን እቅድ በማሳካት ረገድ ረጅም ርቀት መጓዝ ተችሏል፡፡ ከእርሻ ስራ ጋራ እምብዛም የማይተዋወቁ የኦሞ ኩራዝ አካባቢ ማህበረሰቦችን ወደ ከፊል አርሶ አደርነት ማሸጋገር የተጀመረበት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ህብረተሰቡ የልዩ ልዩ መሠረተ ልማቶችና የማሕበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡ በሌላ በኩል የግልና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችን በልማቱ ዙሪያ በስፋት በማሳተፍ ከፍተኛ ሀገራዊ የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ሽግግር የማረጋገጥ ሥራም የተጠናቀቀው የዕቅድ ዘመን ሌላው ስኬት ነበር፡፡

የመጀመሪያውን አምስት ዓመት የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ዕቅድ ግቦችን ለማሳካት በብዙ ረገድ ረጅም ርቀት የተኬደ ቢሆንም ልማቱ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት አውታሮች ባልተዘረጉባቸው ቆላማ

የሀገሪቱ አካባቢዎች የተጀመረ ከመሆኑ አንጻር እንዲሁም ዘርፉ ከሚጠይቀው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እና ከማስፈጸም አቅም ውስንነት አኳያ የተፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አልተቻለም፡፡ ይሁንና በነዚህ ጊዜያት በቀጣይ የዘርፉን ልማት ማፋጠንና ግቦቹን ማሳካት የሚያስችሉ ወሳኝ መደላድሎችን መጣል ተችሏል፡፡

እነዚህን የተፈጠሩ መደላድሎች በመጠቀም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ (2012) የስምንት አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታን አጠናቆ ስራ በማስጀመር አሁን ያለውን 3 ሚሊዮን 650 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ዓመታዊ የስኳር ምርት ከ10 እጥፍ በላይ በማሳደግ ወደ 42 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ ታቅዷል፡፡ ከሚመረተው ስኳር ውስጥም 12 ሚሊዮን 220 ሺህ ኩንታል የተጣራ እና 17 ሚሊዮን 740 ሺህ ኩንታል ጥሬ ስኳር ወደ ውጭ በመላክ 1.3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማስገኘትም በዕቅዱ ተካቷል፡፡ ለዚህም ስኬት እስካሁን በሸንኮራ አገዳ የለማውን 96ሺህ ሄክታር መሬት ወደ 325ሺህ 324 ሄክታር ለማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

በሌላ በኩል በ2012 መጨረሻ ከስኳር ተረፈ ምርት (ባጋስ) ይመነጫል ተብሎ ከሚጠበቀው 709.5 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 448 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ለማስገባት ዕቅድ ተይዟል፡፡

ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

| 3

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የእድገትና ...የሥራ ዕድል ፈጠራው በኮርፖሬሽኑ ተቀጥረው የሚሠሩትን ጨምሮ በየፕሮጀክቱ በኮንትራክተሮች ተቀጥረው የሚሰሩ ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተደራጅተው ከስኳር ልማቱ ጋር ተያይዞ የግል ሥራ የተፈጠረላቸውን ሁሉ የሚያጠቃልል መሆኑንም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ያስረዱት፡፡

የሥራ ዕድል በፕሮጀክቶች አካባቢ በስፋት መፈጠሩን ተከትሎ በአንዳንድ ፕሮጀክቶች አካባቢ አነስተኛ ከተሞች እየተፈጠሩ መሆናቸውንም አቶ ቶለሳ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በነባር የስኳር ፋብሪካዎች ተግባራዊ ባደረጋቸው የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የአገሪቱን የስኳር ምርት በ2002 ዓ.ም ከነበረበት በ38 በመቶ ማሳደግ መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ በ2002 ዓ.ም 291 ሺህ ቶን የነበረው የአገሪቱ ዓመታዊ የስኳር ምርት ወደ 365 ሺህ ቶን ማደጉን በመጥቀስ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ተረፈ ምርቶች የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ለብሔራዊ የኃይል ቋት ለማቅረብ በእቅዱ አመታት

የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አቶ ቶለሳ ተናግረው በአሁኑ ወቅት ከወንጂ ሸዋና ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች 30 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለብሔራዊ የኃይል ቋት በመላክ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የሸንኮራ አገዳ ልማትን በተመለከተም በዕቅድ ዘመኑ ለስኳር ፋብሪካዎች ግብአት የሚሆን የሸንኮራ አገዳ በ65 ሺህ 363 ሄክታር መሬት ላይ መተከሉን ገልጸው፣ በአሁኑ ጊዜ በጠቅላላ 96ሺህ ሄክታር በአገዳ መሸፈኑን እና አፈጻጸሙም በዕቅዱ መነሻ ዓመት ከነበረው 30ሺህ 397 ሄክታር ጋር ሲነፃፀር የ215 በመቶ ዕድገት እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በተጠናቀቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ከ2003 ዓም በፊት ተጀምሮ የነበረውን የወንጂ ሸዋ እና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም በ2007ዓ.ም የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ማስመረቅ እና የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎችን የግንባታ ስራ አጠናቆ የሙከራ ምርት ማስጀመር ተችሏል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ...ከሚጠበቀው 709.5 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 448 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ለማስገባት ዕቅድ ይዟል፡፡

ከስኳር ምርቱ ጎን ለጎንም የስኳር ተረፈ ምርትን በግብአትነት የሚጠቀም የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን በማቋቋምና 2.4 ሚሊዮን ቶን የእንስሳት መኖ አምርቶ አርሶ/አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡፡

በስራ እድል ፈጠራ ረገድም በዕቅድ ዘመኑ በፕሮጀክቶች እና በፋብሪካዎች፣ በኮርፖሬሽኑ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትና በኮንትራክተሮች በቋሚነት፣ በጊዜያዊነትና በኮንትራት ከ1.15 ሚሊዮን በላይ የሥራ እድል እንደሚፈጠር ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ በነባሮቹና ሥራ በሚጀምሩ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች ያለውን የቋሚ ሠራተኞች ቁጥር አሁን ከሚገኝበት 13,267 ወደ 65,254 ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል፡፡

ሴቶች በልማቱ ዙሪያ የሚጫወቱትን ሚና ከማጎልበት አንጻርም በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ተሳትፎ 40 በመቶ ለማድረስና የሴት ሠራተኞችን ብዛት ወደ 45 በመቶ ለማሳደግ እቅድ ተይዟል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ሥራዎች ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ አንዱ በመሆኑ በመስኩ የደን፣ አፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራትን በስፋት ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ 15 ሚሊዮን ችግኞችን በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለመትከል እና የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው ፋብሪካዎችን ብዛት ለማሳደግ ሰፋፊ ስራዎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስራ እድል ፈጠራ ረገድም በዕቅድ ዘመኑ በስኳር ፕሮጀክቶች እና በፋብሪካዎች፣ በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትና በኮንትራክተሮች አማካኝነት በቋሚነት፣ በጊዜያዊነትና በኮንትራት ከ1.15 ሚሊዮን በላይ የሥራ እድል ለመፍጠር ታቅዷል፡፡

ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎንም በዕቅድ ዘመኑ ዘመናዊ የእንስሳት መኖ አዘጋጅቶ በማቅረብ ሀገራችን ካላት ሰፊ የእንስሳት ሃብት ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ ለማገዝ እቅድ ተይዞ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለተጓዳኝ ምርቶች ትኩረት በመስጠት የከብት ማድለቢያ፣ የወተት ላሞች እና የንብ እርባታ ጣቢያዎችን ማቋቋም እና የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በስፋት ማካሄድ ሌሎች የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ትኩረቶች እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የያዝነው ዕቅድ ለትልቅ ስኬት የምንበቃበት የመሆኑን ያህል ካለፉት አመታት ይልቅ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግን የሚጠይቀን ነው፡፡ ስለሆነም በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የነበሩን ጥንካሬዎችን አጠናክረን በማስቀጠል፤ አጋጥመውን ከነበሩ እጥረቶች ደግሞ ተገቢውን ትምህርት በመውሰድ አፈጻጸማችንን በእጅጉ ማሻሻል ይጠበቅብናል፡፡

ውስን በሆነው የሀገሪቱ ሃብት የምንሰራ እንደመሆኑ መጠን ቁጠባን የበለጠ በማጠናከር ከምናወጣው ከእያንዳንዱ ሃብት በብዙ እጥፍ ለማትረፍ አስበን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ ባለፉት አመታት በዘርፉ የያዝናቸውን ትላልቅ ግቦች ማሳካት የሚችል ትልቅ ሀገራዊ አቅም እንደፈጠርን አምናለሁ፡፡ ይህን እምቅ የልማት አቅማችንን አውጥተን የምናስበውን ውጤት ለማምጣት እንደ አንድ የልማት ሠራዊት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን እያቀረብኩ፣ አዲሱ አመት የሰላም፣ የደስታና የስኬት ጊዜ እንዲሆንልን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

መልካም ዘመን!

» ከገጽ 1 የዞረ

» ከገጽ 1 የዞረ

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 1 | መስከረም 2008 ዓ.ም | 4

በስኳር ልማት አካባቢዎች በርካታ...

ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ

ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ • ከፈንታሌ ወረዳ የተውጣጡ ወጣቶችን ለማሰልጠን የ317 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በአካባቢው የሚገኘውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ፡፡ ከፈንታሌ ወረዳ የተውጣጡ 50 ወጣቶች በአዳማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለተከታተሉት የሙያ ስልጠና 317 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን እና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ በአዳማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለ45 ቀናት በልሰና፣ በግንበኝነትና በአናፂነት ሙያዎች የተሰጣቸውን የሙያ ስልጠና ላጠናቀቁ 50 የፈንታሌ ወረዳ ወጣቶች በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ነሐሴ 2/2007ዓ.ም በተዘጋጀው የምስክር ወረቀትና የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ስርዓት ላይ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም ባደረጉት ንግግር ፋብሪካው ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ ወደፊትም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአጎራባች ገጠር ቀበሌዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት በመቻሉ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውንም ዋና ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

ለሰልጣኞቹ የተደረገው ድጋፍ ፋብሪካው ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሚያደርጋቸው የበርካታ ድጋፎች አንዱ መገለጫ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዘነበ፣ በቀጣይም ወጣቶቹ በሰለጠኑባቸው ሙያዎች ከፋብሪካው ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር የስራ ዕድል እንደሚመቻችላቸው ገልፀዋል፡፡ ወጣቶቹ በቀጣይ ለሚካሄዱ ተመሳሳይ ድጋፎች አርዓያ

በመሆን ለጥራትና ለተወዳዳሪነት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ነው አቶ ዘነበ ያስገነዘቡት፡፡

ሰልጣኞቹ በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት የስራ ዕድል ፈጣሪ መሆን ለሚያስችላቸው ስልጠና ድጋፍ ስለተደረገላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም በሚፈጠርላቸው የስራ ዕድል ተጠቅመው ራሳቸውን ብሎም አካባቢያቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን ለሰልጣኞች ውሎ አበል፣ ለአዳማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የስልጠና ክፍያ እና ለሰልጣኞች የማደሪያ ቤት ኪራይ በጠቅላላው 317 ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡

እንደ ዘርፉ ገለፃ ኮርፖሬሽኑ ከ2003ዓ.ም እስከ 2007ዓ.ም ባሉት ዓመታት በስኳር ፋብሪካዎችና በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና የጠጠር መንገዶችን ሲገነባ፤ የወፍጮ አገልግሎት እና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትም እንዲመቻች አድርጓል፡፡

በአዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችና በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮችን ለማደራጀት ባደረገው ጥረትም፤ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣ በተንዳሆ እና በከሰም ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ የሚገኙ አርብቶ

አደሮች ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አገዳ አብቃይና አቅራቢ የህብረት ሥራ ማህበራት ልምድ እንዲያገኙ እና በማህበር እንዲደራጁ በማድረግ እንዲሁም በመስኖ የለማ መሬት በማከፋፈል ወደ ሥራ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን ዘርፉ ገልጿል፡፡

በወንጂ ሸዋና ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በልማቱ የበለጠ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ስራዎችም ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

በሌላ በኩል ስኳር ኮርፖሬሽን ባለፉት አምስት ዓመታት በስኳር ልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ወደ 2ሺህ የሚጠጉ የአርብቶ አደሩና የአርሶ አደሩ ልጆችን በ4.2 ሚሊዮን ብር ወጪ በትራክተር እና ማሽን ኦፕሬተርነት፣ በአናጺነት፣ በግምበኛነት፣ በቀለም ቀቢነት፣ በለሳኝነት እና በመሳሰሉት ሙያዎች

በማሰልጠን ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረግ መቻሉን ነው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ መረጃ የሚጠቁመው፡፡ በተመሳሳይ በ500ሺህ ብር ወጪ ከ1ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አመራሮች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱ ታውቋል፡፡

በተጠናቀቀው ዕቅድ ዘመን ኮርፖሬሽኑ በአዳዲስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና በነባር ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ ከሚገኙ ከ101ሺ 600 በላይ አርሶ/አርብቶ አደሮች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የመስተዳድር አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተለያዩ ጊዜያት ውይይቶች በማድረግ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ መግባባት መፈጠሩን ዘርፉ አስታውቋል፡፡

» ከገጽ 1 የዞረ

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

| 5

የኦሮሚያ ዲያስፖራ የልዑካን ቡድን የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ጎበኘ* የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካም ተጎብኝቷል

የኦሮሚያ ዲያስፖራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ጎበኘ፡፡

የልዑካን ቡድኑ 100 ያህል የጉብኝት ተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ላይ አምባሳደሮች፣ በውጭ አገር የሚኖሩ የኦሮሚያ ተወላጆች (ዲያስፖራ) እና የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር አባላት ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ማሞ፣ ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት

ባለፈ ምርቱን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ አቅዳ እየሰራች ያለች አገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡

በዋናነትም የተጣራ ነጭ ስኳር በማምረት ላይ የሚገኘው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ለውጭ ገበያ የሚውል ስኳር ለማምረት ያለውን አቅም ካስረዱ በኋላ ይህም ለዲያስፖራው ኩራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ ዲያስፖራው በያለበት አገር የገጽታ ግንባታ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት የገለጹት ኃላፊው፣ በአገሪቱ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በግልም ሆነ በጋራ ኢንቨስት ማድረግ

እንደሚችሉና ለዚህም አገሪቷ እጇን ዘርግታ እንደምትቀበላቸው አመልክተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያት በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸው፣ የአገሪቷን ገጽታ በበጎ ጎኑ ለመገንባት አምባሳደር ሆነው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በሌላ አቅጣጫ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት የተሰማራው የኦሮሚያ የዲያስፖራ ልዑካን ቡድን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ጎብኝቷል፡፡

በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተካሄደየወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞችና በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች “የአካባቢ ልማት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በፕሮጀክቱ ዙሪያ በሚገኘው መለስ ፓርክ ሐምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም ችግኝ ተክለዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ከ600 በላይ የሆኑ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ በፕሮጀክቱ የተለያዩ ግንባታዎችን በማከናወን ላይ የሚገኙ ተቋማት ሠራተኞች እና በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስከያጅ አቶ አመናይ መስፍን በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር አገራችን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በማድረግ ላይ የምትገኘውን ጥረት ከመደገፍ ባለፈ አካባቢውን ከደን መራቆት እና ከአፈር መሸርሸር ለመጠበቅ በማሰብ መርሐ ግብሩ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

“የወልቃይት ስካር ልማት ፕሮጀክት የሚገኝበት አካባቢ ቆላማ በመሆኑ የደን ልማታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻልን መሄድ ግድ ይለናል” ያሉት አቶ አመናይ ለዚህም የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ተሳታፊ ከነበሩ ሠራተኞች ውስጥ አንዱ የሆኑት አቶ ጎይተኦም ነጋሽ በየዓመቱ በፕሮጀክቱ በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

“በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን በሙቀትና በአየር ንብረት መዛባት በምትታመስበት ጊዜ ሀገራችን በደን አጠባበቅ አርአያ በመሆን ላይ ትገኛለች፡፡ እኔም የዚህ ታሪክ አካል በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ይህ ለልጆቼ የማወርሳቸው ሃብት ነው” ብለዋል፡፡

የችግኝ ተከላው ሌላዋ ተሳታፊ ወይዘሪት ነጨይ ብርሃነ በበኩሏ የፕሮጀክቱ አካባቢ ሞቀታማ በመሆኑ የተተከሉት ችግኞች ስነ ምህዳሩ እንዲስተካከል ጉልህ ድርሻ እንደሚያበረክቱ ተናግራለች፡፡

የትግራይ ክልል የደን ልማት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሂወት ደስታ በበኩላቸው ችግኝ ተከላው አካባቢው አረንጓዴ እንዲሆን፣ የአየር ሁኔታው እንዲስተካከል እና የመሬቱ ምርታማነት እንዲጨምር አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ 16ሺህ 850 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ በ2008 በጀት አመት 89ሺህ 925 ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያስረዳል፡፡

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 1 | መስከረም 2008 ዓ.ም | 6

በስኳር ልማት ዘርፍ በ2007 ዓ.ም ከተካሄዱ

አበይት ክንውኖች ውስጥ በከፊል

በተንዳሆ

በወልቃይት

በአርጆ ዲዴሳ

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

| 7

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ምረቃ

በፊንጫአ

በኩራዝ የቢ ኤስ +ሲ ሰነድ ርክክብ

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 1 | መስከረም 2008 ዓ.ም | 8

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማህበራት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት ለተደራጁ ማህበራት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በፕሮጀክቱ የሕዝብ አደረጃጀት ካሳና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ የካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ቡድን እንደገለጸው በሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት በማህበር የተደራጁ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ለማህበራት አመራሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በፕሮጀክቱ ኩኩሉሚሪ ኢሊጎቢያ፣ ቤሊሎንግ እና ጉራ የተባሉ ሦስት ነባር መንደሮች ነዋሪ አርብቶ አደሮች የተመሠረቱ ማህበሮች አመራር ለሆኑ 49 አርብቶ አደሮች

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ቡድን መሪው አቶ ጌቱ ደበበ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው የአገዳ አብቃዮች ህብረት ሥራ አመራር አደረጃጀት ሂደትና የአመራር ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ መሰጠቱን ነው ቡድን መሪው ያከሉት፡፡

የፕሮጀክቱ የህዝብ አደረጃጀት ካሳና መልሶ ማቋቋም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስረስ አዳሮ በበኩላቸው በተያዘው የበጀት አመት በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች በአራት መንደሮች የሚሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት በማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

የጃዊ ወረዳ የፈንድቃና አካባቢዋ ነዋሪዎች የአገዳ ተከላ ዘመቻ አካሄዱ

የጃዊ ወረዳ የፈንድቃ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች እና ባለሀብቶች በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአገዳ ተከላ ዘመቻ በማካሄድ ለፕሮጀክቱ ያላቸውን አጋርነት ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ7ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት የአገዳ ተከላ ዘመቻ ሁለት ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በመትከል በቀጣይም ለፕሮጀክቱ ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በአገዳ ተከላ ዘመቻው ወቅት ከ65 በላይ የጉልበት ሠራተኞችን ቀጥረው አገዳ ያስተከሉት ሳጅን ተሰራ ቄሴ በሰጡት አስተያየት የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአካባቢያቸው ተግባራዊ ተደርጎ በርካታ ጠቀሜታዎችን ማግኘታው በአገዳ ተከላው እንዲሳተፉ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

ሳጅን ተሰራ ቄሴ በ2006ዓ.ም በፕሮጀክቱ በተካሄደ ተመሳሳይ የአገዳ ተከላ ዘመቻ 25 የጉልበት ሠራተኞችን ቀጥረው በተከላው መሳተፋቸውን አስታውሰው፣ “ፕሮጀክቱ በአካባቢያችን ተግባራዊ በመደረጉ በሆቴል ንግድ ከፍተኛ ገቢ እያገኘን ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ምክንያት የአስፋልት መንገድ አካባቢያችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በርካታ

የአካባቢያችን ወጣቶችም የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡” በማለት ፕሮጀክቱ ያስገኘውን ጠቀሜታ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ 10 የቀን ሠራኞችን በመቅጠር በአገዳ ተከላ ዘመቻው ላይ የተሳተፉት አቶ በሽር ነጋ በበኩላቸው የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአካባቢያቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን በማስገኘቱ ለፕሮጀክቱ አጋርነታቸውን በተግባር እንዲያረጋግጡ እንዳነሳሳቸው ጠቁመዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በ2ዐዐ7 በጀት ዓመት በጣና በለስ ስካር ልማት ፕሮጀክት 2ሺህ 7ዐ7 ሄክታር ሸንኮራ አገዳ ተተክሏል፡፡ በፕሮጀክቱ በአገዳ የተሸፈነ መሬት ስፋት 12ሺህ 716 ሄክታር መድረሱም ታውቋል፡፡

የፕሮጀክቱ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮንን አደም እንደገለጹት በ2ዐዐ7 በጀት ዓመት በአጭር ጊዜ የተከላ ስራ ሰፊ ማሳ መሸፈን ተችሏል፡፡ ለዚህም ውጤት መመዝገብ ከቀን ሠራተኛው እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ የነበረው የላቀ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበርም መናገራቸውን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

የአካባቢው ህብረተሰብ በአገዳ ተከላ ዘመቻ ላይ

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

| 9

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ችግኝ ተከሉ

የሴት ሠራተኞችን ተሳትፎና እኩል ተጠቃሚነት ማሳደግን መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ሐምሌ 22 ቀን 2007ዓ.ም በኮተቤ የደን ክልል በመገኘት ዓመታዊ የችግኝ ተከላ መርሐግብር አከናወኑ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ሠራተኞች በየካ ክፍለ ከተማ የኮተቤ ደን ክልል ተገኝተው ችግኝ ተከላውን ባከናወኑበት ወቅት የተገኙት የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ተወካይ እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የተከሏቸው ችግኞች በሙሉ ጸድቀዋል፡፡ በዚህም ተግባር ኮርፖሬሽኑ አረንጓዴ ልማቱን እየመሩ ካሉ መ/ቤቶች ተርታ በግንባር ቀደምነት መሰለፉን ገልፀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዘመድኩን ተክሌ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር “አረንጓዴ ቦታዎችን ለመጪው ትውልድ እናስረክብ!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከሦስት በመቶ በታች የነበረውን የሀገሪቱን የደን ሽፋን ተስፋ ሰጪ እድገት እያሳየ እንዲሄድ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርገን ከመሆኑም ባሻገር ሀገሪቱ ከካርቦን ንግድ በጎላ ደረጃ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ የስኳር ኢንዱስትሪ ከአረንጓዴ ልማት ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት

ያወሱት አቶ ዘመድኩን የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ችግኞቹ እንዲጸድቁ ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ አክለዋል፡፡

ዝግጅቱን ያስተባበሩት የኮርፖሬሽኑ የማኅበራዊ ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰናይት በላይ በበኩላቸው ችግኝ መትከል ብቻ በቂ ስላልሆነ የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ ማኅበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ለቀጣዩ ትውልድ ቅርስ እናስተላልፍ ብለዋል፡፡

በተከላው የተሳተፉ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በአንድ ችግኝ 37 ብር የወጣበትን የዝግባ እንዲሁም የወይራ ችግኞች ተክለዋል፡፡

በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በዱብቲና አሳይታ መንደሮች በተለያዩ የስራ ክፍሎች ተሰማርተው የሚገኙ ሴት ሠራተኞችን ተሳትፎና እኩል ተጠቃሚነት ማሳደግን መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከሐምሌ 10 እስከ 15/2007ዓ.ም ድረስ ተሰጠ፡፡

በሥልጠናው ወቅት የሴቶችን ተሳትፎና ውሳኔ

ሰጪነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች ለውጥ እየታየ መሆኑን በፋብሪካው የሥርዓተ ፆታ ባለሞያ ወ/ሪት ሙሉ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በፋብሪካው ከ600 በላይ ሴት ሠራተኞች መኖራቸውን የጠቆሙት ባለሙያዋ፣ በሁሉም የሥራ ዘርፎች ቁጥራቸው እያደገ መምጣቱ ሴቶች በተደራጀ ሁኔታ

መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩ እና ለልማቱ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ይረዳል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በፋብሪካው የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የበለጠ ለማሳደግ እንዲችል ከእህት ፋብሪካዎች ያገኙትን ልምድ ስራ ላይ እንደሚያውሉ ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ወላጆቻቸውን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ያጡ ህፃናትን እየደገፉ ነው

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በጃዊ ወረዳ የሚገኙ 10 ወላጆቻቸውን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ያጡ ሕጻናትን በመደገፍ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

የፕሮጀክቱ ሁሉም ሠራተኞች ከደመወዛቸው ላይ በየወሩ 10 ብር በማዋጣት 10 በጃዊ ወረዳ የሚገኙና ወላጆቻቸውን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ያጡ ሕጻናትን በመደገፍ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በፕሮጀክቱ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል ምክትል ሰብሣቢ አቶ አለሙ አብርሃ አስታውቀዋል፡፡

ለ10 ሕጻናት ለእያንዳንዳቸው በወር 600 ብር ድጋፍ በማድረግ ሕጻናቱ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ምክትል ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በአመት አንድ ጊዜ ሙሉ ልብስ እንደሚሰጣቸው እና የመማሪያ ቁሳቁስም እንደሚሟላላቸው ምክትል ሰብሳቢው መግለጻቸውን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል፡፡

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 1 | መስከረም 2008 ዓ.ም | 10

ምልከታበሲሳይ ደርቤ - ከመተሐራ

ቆይታ

አዳማ ከተማ … ገልማ አባገዳ አዳራሽ:: ጊዜው ሐምሌ 18 ቀን 2007ዓ.ም፡፡ አዳራሹ መርፌ መጣያ የለውም:: ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ በሚያስመርቃቸው ተማሪዎች፣ በቤተሰቦቻቸውና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች ተሞልቷል፡፡ መድረኩ ላይ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ምሁራንና የክብር እንግዶች ከነክብር ካባቸው በግርማ ሞገስ ሥፍራቸውን ይዘዋል፡፡ በመድረኩ ከሚስተዋሉት ሽልማቶች መካከል ባለወርቃማ ቅብ ዋንጫ በኩራት ተኮፍሷል፡፡ ከዋንጫው ግርጌ ላይ ‹‹በሀገር አቀፍ ደረጃ በካይዘን ትግበራ ግንባር ቀደም ለሆነው መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የተበረከተ ሽልማት›› የሚል ፅሑፍ ይነበባል፡፡

በአዳራሹ ውስጥ በታደሙት ምሁራን መካከል በኩራት በተኮፈሰው ዋንጫ ውስጥ “አረንጓዴው በረሃ” … መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ገዝፎ ይታያል፡፡ የፋብሪካው መዓዛ ጠረኑ ከሩቅ ይጣራል፡፡ የቁርጠኛና የታታሪ ሠራተኞች ትጋት፣ የማይዋዥቅ የአመራር ብቃት፣ ቁርጠኛ ልማታዊ ንቅናቄ፣ የአሸናፊዎች አሸናፊነት አመለካከት በዋንጫው ውስጥ ብርሃናማ ነፀብራቃቸውን ፈንጥቀዋል፡፡ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ከታደሙት ተማሪዎች መካከል የአንበሳውን ድርሻ የያዙት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መሆናቸው ደግሞ የአዳራሹን ዓውድ እንደ ነጩ ስኳር አጣፍጦታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዕለቱ 280 ያህል የፋብሪካው ሠራተኞች በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፕሎማ ይመረቁ ነበርና፡፡

ከዋንጫው በተጨማሪ ሌሎች ድሎችም

ተበሰሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በየትምህርት መስኮቹ በዲግሪ መርሃ ግብር ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለማዕረግ ተመራቂዎች የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መሆናቸው ደግሞ ተጨማሪ ኩራት ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አራቱ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀው ሜዳሊያ በማጥለቅ መድረኩን ይበልጥ እንደ ኮከብ አደመቁት፡፡ ይህም ‹‹ የአሸናፊዎች አሸናፊ እንሆናለን ›› የሚለው የፋብሪካው መርህ በሠራተኛው ዘንድ ሰርፆ የተወዳዳሪነት ብቃትን የሚያስመዘግቡ ሠራተኞች መፍለቂያ መሆኑን ያመለክታል፡፡

በ2007ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል በማለት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሽልማት ካበረከተላቸው ተቋማት መካከል የላቀውን ድርሻ የያዘው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በመሆኑ የአንደኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚነቱ ሲበሰር አዳራሹ በጭብጨባና በእልልታ ተናጋ፡፡ በዕለቱ የታደሙት

የማኔጅመንት ቡድን አባላትም ፈጥነው መድረኩ ላይ ተገኙ፤ የክብር ዋንጫውን በጋራ ከፍ ለማድረግ፡፡ ታዲያ ያን ጊዜ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በመድረኩ ላይ ገዝፎ እና ክብርና ሞገስን ተላብሶ ታየ፡፡

የሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈይሣ አራርሣ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት ተመራቂ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለሠጠው አዎንታዊ ድጋፍ እንዲሁም በካይዘን የአሠራር ፍልስፍና አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት ተሸላሚ በመሆኑ ዋንጫው እንደተበረከተለት ገልፀዋል፡፡

በዚህ መልክ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ዕውቅና ሰጥቶ ‹‹ክብር ይገባችኋል›› በማለት ያበረከተው የዋንጫ ሽልማት ከሽልማት ባለፈ ለፋብሪካው ቀጣይ ልማታዊ ተልዕኮ ስኬት የቤት ሥራን የሰጠ ጭምር ነው፡፡

የማዕረግ ተመራቂዎች

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

| 11

ስኳር ፋብሪካአዲሱ ወንጂ ሸዋ

በአገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ ስኳር ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች በእርጅና ምክንያት ስራቸውን እስካቆሙበት ጊዜ ድረስ ማለትም ወንጂ እስከ 2004 እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ የነበራቸው የማምረት አቅም በአማካይ በአመት 75,000 ቶን ስኳር ነበር፡፡

ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡ ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማስፋፊያ ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ ዘርፍ ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራው 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ተጠናቋል፡፡

አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የተቋቋመው የተዘጉበት ፋብሪካዎች የነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ፋብሪካው አሁን ባለበት ደረጃ በቀን 6250 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት ከ174 ሺህ ቶን በላይ ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ወደፊት የማምረት አቅሙን በማሳደግ በቀን ወደ 12 ሺህ 500 ቶን አገዳ እየፈጨ ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን እስከ 222 ሺህ 700 ቶን እንደሚያሳድግ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ ምርት በዓመት እስከ 12 ሺህ 800 ሜትር ኩብ የሚደርስ ኤታኖል ለማምረት የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ ለመገንባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ረገድም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 31.15 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 10 ሜጋ ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪውን 21.15 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተወሰነ ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ማስገባት ጀምሯል፡፡

በፋብሪካው የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠቃላይ 16,000 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው በግብዓትነት እየተጠቀመ ከሚገኘው 12 ሺህ 800 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ 7 ሺህ ሄክታሩ በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ 34 የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበራት የለማ ነው፡፡ ማኅበራቱ ያቀፏቸው 5 ሺህ 651 ወንዶችና 1 ሺህ 982 ሴቶች በጠቅላላው 7 ሺህ 633 አባላት የሸንኮራ አገዳ እያለሙ ለፋብሪካው በማቅረብ በሚያገኙት ገንዘብ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ናቸው፡፡

አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በ2007 በጀት ዓመት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1.1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ማምረት ችሏል፡፡

እናስተዋውቃችሁ

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት:+251-(0)11-552-7475 : +251-(0)11-552-7050 : 20034 Code 1000 A.A

www.etsugar.gov.et || facebook.com/etsugar

ጣፋጭ አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!