ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

16
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 4 ቁጥር 2-ታህሳስ 2008 ዓ.ም Ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ለኮርፖሬሽኑ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ አደርጋለሁ አለ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ስኳር ኮርፖሬሽን በበጀት አመቱ የያዛቸውን እቅዶች እና የስኳር ልማት ዘርፍ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ በሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሐምቢሳ የተመራው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ልዑክ በቅርቡ የከሰም፣ የመተሐራና የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የምርምር እና ሥልጠና ዘርፍ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን በሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ከታህሳስ 8-9/2008ዓ.ም ድረስ በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄደ፡፡ ይህንን አስመልክቶ በተዘጋጀው የሁለት ቀናት የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ ላይ የኮርፖሬሽኑ የመልካም አስተዳደር ሁኔታ መነሻ ሃሳብ በካይዘንና ለውጥ አመራር በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ውይይት ተካሄደ » ወደ ገጽ2 ዞሯል በውስጥ ገጾች » ወደ ገጽ 3 ዞሯል -> የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ እያደረገ ነው >>ገጽ 4 -> የምሥራቅ ኮኮብ >> ገጽ 9 -> የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ >> ገጽ 14 የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች 10ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ • የአለም የፀረ-ኤድስ እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀናትም ተከብረዋል የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች “የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተሳትፎ ለላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን!” በሚል መሪ ቃል 10ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በዋናው መ/ቤት ህዳር 25 ቀን 2008ዓ.ም አከበሩ፡፡ በዕለቱ የአለም የፀረ-ኤድስ እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀናት አንድ ላይ ተከብረዋል፡፡ በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ባደረጉት ንግግር የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና » ወደ ገጽ 3 ዞሯል

Upload: ethiopian-sugar-corporation

Post on 16-Feb-2017

636 views

Category:

Government & Nonprofit


11 download

TRANSCRIPT

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!

ቅፅ 4 ቁጥር 2-ታህሳስ 2008 ዓ.ምEthiopiansugar.com || facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ለኮርፖሬሽኑ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ አደርጋለሁ አለ

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ስኳር ኮርፖሬሽን በበጀት አመቱ የያዛቸውን እቅዶች እና የስኳር ልማት ዘርፍ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊውን

ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

በሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሐምቢሳ የተመራው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ልዑክ በቅርቡ የከሰም፣ የመተሐራና የወንጂ ሸዋ

ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የምርምር እና ሥልጠና ዘርፍ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን በሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ከታህሳስ 8-9/2008ዓ.ም ድረስ በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄደ፡፡

ይህንን አስመልክቶ በተዘጋጀው የሁለት ቀናት የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ ላይ የኮርፖሬሽኑ የመልካም አስተዳደር ሁኔታ መነሻ ሃሳብ በካይዘንና ለውጥ አመራር

በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ውይይት ተካሄደ

» ወደ ገጽ2 ዞሯል

በውስጥ ገጾች

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

-> የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ እያደረገ ነው >>ገጽ 4 -> የምሥራቅ ኮኮብ >> ገጽ 9-> የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ >> ገጽ 14

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች 10ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ• የአለም የፀረ-ኤድስ እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀናትም ተከብረዋል

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች “የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተሳትፎ ለላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን!” በሚል መሪ ቃል 10ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን

በተለያዩ ዝግጅቶች በዋናው መ/ቤት ህዳር 25 ቀን 2008ዓ.ም አከበሩ፡፡ በዕለቱ የአለም የፀረ-ኤድስ እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀናት አንድ ላይ ተከብረዋል፡፡

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ባደረጉት ንግግር የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና » ወደ ገጽ 3 ዞሯል

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 2

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ...

ከጉብኝቱ በኋላ የልዑካን ቡድኑ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሐምቢሳ እንደገለፁት ለኮርፖሬሽኑ የበጀት አመቱ እቅድና ለስኳር ልማት ዘርፍ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት መስሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡

የስኳር ልማት ዘርፍ ሰፊና ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ደሚቱ ከዚህ አንጻር ፕሮጀክቶቹ በአገር ደረጃ ከፍተኛ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም ያላቸው በመሆናቸው ለስኬታቸው አስፈላጊው ድጋፍና ትኩረት ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በኮርፖሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠርና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በተጠናከረ

መልኩ ለማከናወን እንደሚሰራም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ የሚሰሩ የባለድርሻ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ በየወሩ እንደሚዘጋጅ ያስታወቁት ወይዘሮ ደሚቱ ይህም ሥራዎችን ለማፋጠንና ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ እቅዶቹን በማሳካት የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከቀድሞው በተሻለ መልኩ ጥረት ማድረግ እንዳለበት አሳስበው ማነቆዎችን በውስጥ አቅም የመፍታት ጅማሬው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ

እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራባቸው ይገባል ያሏቸውን ነጥቦች አቅርበዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ከቀረቡት ነጥቦች ውስጥ የአመራርና የፈጻሚው አቅም በተሻለ መልኩ እንዲገነባ፣ የአቅርቦት ሥርዓቱ ቀልጣፋ እንዲሆን እና በኮንትራት አስተዳደር ረገድ የሚስተዋለው ክፍተት እንዲሞላ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በሚኒስትሯ የተመራው የልዑካን ቡድን በስኳር ፋብሪካዎች በነበረው ቆይታ የፋብሪካዎቹ አመታዊ እቅድ፣ በካይዘን ያስመዘገቧቸው ውጤቶችና የተገኙ ልምዶችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎለታል፡፡

» ከገጽ 1 የዞረ

በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ... » ከገጽ 1 የዞረ

ዘርፍ ቀርቧል፡፡ በዚህም የንቅናቄው ዓላማ፣ በማቀጣጠያ መድረኩ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ዝርዝር የአፈጻጸም አቅጣጫ እና በስኳር ልማት ዘርፍ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በችግሮቹ መንስኤዎች እና በሚፈቱበት አግባብ ዙሪያም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተወያይተዋል፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳወቅ አብቴ እንዳስታወቁት፤ ከዚህ ቀደም በቋሚነት የመልካም አስተዳደር መድረኮች ባለመዘጋጀታቸው እና በተቆራረጠ መልኩም ቢሆን በተካሄዱ መድረኮች ላይ ለተነሱ ችግሮች መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ኮርፖሬሽኑ ለበርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተዳርጎ

ቆይቷል፡፡ ችግሮቹም የተከሰቱት አመራሩ እና ሠራተኛው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት እንደሆነ አክለው አስረድተዋል፡፡

በእያንዳንዱ የኮርፖሬሽኑ አሠራር ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዳልነበር የጠቆሙት አቶ እንዳወቅ፤ የችግሩ መንስኤም ከአሠራር እና ከአመለካከት ጋር የተገናኘ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶችና ቅሬታዎች የኮርፖሬሽኑን ነባራዊ ሁኔታ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው ያሉት አቶ እንዳወቅ፤ በቀጣይ በቀረቡት አስተያየቶችና ቅሬታዎች መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት፣ የድርጊት መርሃ ግብር

» ወደ ገጽ3 ዞሯል

በሚኒስትሯ ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ የተመራው ልሁክ የከሰም ስኳር ፋብሪካን ሲጎበኝ ውይይት ሲካሄድ

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 3

በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ... » ከገጽ 2 የዞረ

በማዘጋጀት እና ለሥራው ፈጻሚ በመመደብ ችግሮቹን ለመፍታት ርብርብ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የውይይት መድረኮች በቋሚነት የሚዘጋጁ ሲሆን፤ በተለይም የህግ፣ የኦዲት እና የስነ ምግባር የሥራ ዘርፎች ችግሮቹ በሚፈቱበት አግባብ ላይ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እና በአሰራር እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ያሳሰቡት አቶ እንዳወቅ ከሠራተኛው ጋር በመሆን ችግሮቹን መፍታት እንደሚቻልም አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ሠራተኞች በሰጡት

አስተያየት በኮርፖሬሽኑ አሠራር ላይ ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ዲሞክራሲያዊነት እና አሳታፊነት በእጅጉ ይጎድሉባቸው የነበሩ መገለጫዎችን አንስተዋል፡፡

የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የተዘጋጀው ቀደም ሲል በተለያዩ የሃሳብ መስጫ እና በአካል የቅሬታ አቀራረብ ዘዴዎች ከውስጥና ከውጭ ሲነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውይይት እንዲደረግባቸው በኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በመወሰኑ ነው፡፡

በተመሳሳይ በስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ ለማዘጋጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት ታቅዷል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች 10ኛውን ... » ከገጽ 1 የዞረ

ሕዝቦች የሉዓላዊነት መገለጫ እና የህዳሴ መሰረት መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉንም ሕዝቦች በእኩልነት ያሳተፈ እና እኩል የህግ መብትና ፍትሀዊ የሀብት ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው ያስቻለ የቃል ኪዳን ሠነድ ነው ብለዋል፡፡

ይህ በመሆኑም ሕዝቦች በሀገራቸው ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ የኢኮኖሚ ልማት ግንባታና ሌሎች ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት መቻላቸውን ነው ያስታወቁት ።

ሕገ-መንግሥቱ ባለፉት አመታት የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በማጠናከር ረገድ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ የሚያስችሉ መደላድሎችን መፍጠሩን የተናገሩት አምባሳደሩ፣ ከዚህ አኳያ መንግሥት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ በማሳደግ የሕዝቦችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወጠናቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ልማት ዘርፍ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በስኳር ልማት ዘርፍ ባለፉት አመታት በተካሄዱ መጠነ ሰፊ ተግባራት በመሰረተ ልማትና በማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተደራሽ ያልነበሩ በርካታ

የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች የልማቶቹ ተቋዳሽ እንዲሆኑ መደረጉን ያስታወቁት አምባሳደሩ፣ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የተያዘውን ግብም ለማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በእነዚህም ሥራዎች በልማቱ አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ የልማቱ ተጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የስኳር ምርትን በተመለከተም አገራዊ የስኳር ፍጆታን በአስተማማኝ ሁኔታ ከማረጋገጥ ባለፈ ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የማስገኘት ሰፊ እድል እንዳለ አሁን በዘርፉ የተደረሰበት ደረጃ ያመለክታል ብለዋል፡፡

የፀረ ኤድስ ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክትም በሽታውን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ቃል የሚገባበት ጊዜ ነው ካሉ በኋላ በዋናው መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የተቋቋሙት የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ግብረ ሃይሎች በኤች አይ ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን ለመርዳት እያደረጉ ያሉትን ሁለገብ እንቅስቃሴ በስፋት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል በሴቶች ላይ በሥራ ቦታ፣ በመኖሪያ አካባቢዎች እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ የፆታ ጥቃቶች እንዳይደርሱ መከላከል የሁሉም ዜጋ ግዴታ መሆኑን በዚሁ ወቅት አስገንዝበዋል፡፡

» ወደ ገጽ4 ዞሯል

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 4

የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ እያደረገ ነው

* ሌሎችም ስኳር ፋብሪካዎች ተመሳሳይ ስራዎችን በማከናወን ላይ ናቸው

በበዓሉ ወቅት “የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግሥት እና አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ ግንባታ” በሚል ርዕስ በዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ በአቶ አብርሃም ደምሴ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የአለም የፀረ-ኤድስ ቀን እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀንን አስመልክቶም በጤና እና በሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬቶች መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ በፌደራሊዝም ሥርዓትና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረበ የጥያቄና መልስ ውድድር

አሸናፊዎች ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡ በዕለቱ በየኔታ ኪነጥበባትና ፕሮሞሽን የቀረቡ የሙዚቃ፣ የግጥም እና የጭውውት ዝግጅቶች ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተዋል፡፡

በተመሳሳይ 10ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንዲሁም የአለም የጸረ-ኤድስ እና ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀናት በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች 10ኛውን ... » ከገጽ 3 የዞረ

የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በኤልኒኖ ምክንያት በድርቅ ለተጎዱ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ለእንስሳት መኖ የሚውል ሳር እና የማሽላ ተረፈ ምርት በማቅረብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የትግራይ ክልል የሰፈራ መርሐ ግብር አስተባባሪ አቶ ፀጋይ ፍትዊ እንደተናገሩት በክረምት ወራት በክልሉ በተከሰተው የዝናብ አለመኖርና መቆራረጥ ምክንያት በድርቅ ለተጎዱ የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ማእከላይ እና ምስራቅ አካባቢዎች ፕሮጀክቱ በየቀኑ ከ400 በላይ የቀን ሰራተኞችን ቀጥሮ

ለእንስሳት መኖ የሚውል 320 ሄክታር የማሽላ ተረፈ ምርት እና 450 ሄክታር ሳር አሳጭዶ በራሱ ማጓጓዣ በየአካባቢዎቹ ማድረሱን አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሰረት እያንዳንዳቸው 15 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ 10ሺ የሳር እስር እና 1ሺ 200 ኩንታል የማሽላ ተረፈ ምርት ተሰብስቦ መከፋፈሉን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የህዝብ አደረጃጀት፣ ካሳና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሃይለ ገብረመድህን በበኩላቸው

ፕሮጀክቱ በዝናብ እጥረት ምክንያት በትግራይ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ የወንጂ ሸዋ፣ የመተሃራ፣ የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎች በድርቅ ለተጎዱ በአቅራቢያቸው ለሚገኙ አካባቢዎች ለእንስሳት መኖ የሚውል ሞላሰስ፣ የአገዳ ገለባና ውሃ ለችግሩ ተጎጂዎች በማቅረብ ላይ ይገኛሉ::

የሕገ መንግሥት ጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዋ ሽልማታቸውን ሲቀበሉ

ውይይት ሲካሄድ

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 5

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በአካባቢው ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንግድ ቤት ሰርቶ ሰጠ

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከፋብሪካው ፊት ለፊት ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች አነስተኛ የንግድ ቤት ሰርቶ በመስጠት ወደ ሥራ እንዲገቡ አደረገ፡፡

ቤቱ ተሰርቶ ከተሰጣቸውና በማህበር ተደራጅተው ምግብ በማዘጋጀት ስራ ላይ ከተሰማሩት ተጠቃሚዎች መካከል ወይዘሮ ልኬ በፍቃዱ እንደተናገሩት፣ ፋብሪካው

አነስተኛ የንግድ ቤት ሰርቶ ሰጥቷቸው ስራ በመጀመራቸው ተደስተዋል፡፡ በሚያገኙት ገቢም ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መርዳት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ያመለከቱት ወ/ሮ ልኬ ወደፊትም ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ እድል በመፍጠር የሀገር ተስፋ እንደሚሆን

አስታውቀዋል፡፡

ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወ/ሪት ዘመድ አደመ በበኩላቸው ፋብሪካው የንግድ ቤት ሰርቶ ሳይሰጣቸው በፊት ለሥራ በማያመች የኪራይ ቤት ውስጥ ሲሰሩ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ግን እፎይታን ማግኘታቸውን እና የስራ ተነሳሽነታቸውም እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፋብሪካው ሥርዓተ ፆታ ቡድን ሴቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ነውየፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ሥርአተ ፆታ ቡድን ሴቶችን በተለያዩ ዘርፎች በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረጉን ገለጸ፡፡

የፋብሪካው የሥርዓተ ፆታ ቡድን ኦፊሰር ወይዘሪት ተሊሌ ዱጋሳ እንደገለጹት የሥርዓተ ፆታ ቡድኑ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ባደረገው ጥረት ከፋብሪካው

ሠራተኞች ውስጥ አጠቃላይ የሴቶች ተሳትፎ 31% የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ወደፊት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በፋብሪካው አካበቢ የሚገኙ ሴቶችን የማደራጀት እና የአቅም ግንባታ ሥልጠና የመስጠቱ ስራ መቀጠሉን የተናገሩት ኦፊሰሯ 32 ሴቶች እና 8 ወንዶች በወፍጮ ሥራ እንዲሁም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው የቀድሞ ሠራተኞች ደግሞ በሌሎች የሥራ መስኮች ለመሰማራት ተደራጅተዋል፡፡ ከዚህም ውጭ ሁለት ሴቶች የሎደር ኦፕሬተርነት ሙያ ሥልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመሰማራት እየተጠባበቁ ነው፡፡

የሥርአተ ፆታ ቡድኑ የቤት እመቤቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቆ የጤና ኤክስቴንሽን እና የቤት ውስጥ

ካይዘንን በመተግበርም ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያጠናክር ገልጿል፡፡

ቡድኑ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጽሕፈት ቤት እና ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ 281 ሕጻናት ተማሪዎች ለ2008ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደብተር እና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ማወቅ ተችሏል፡፡

ህብረተሰቡ ስለ ሴቶች ያለው አመለካከት ምን ያህል እንደተቀየረ የተጠየቁት ወ/ሪት ተሊሌ ለውጦች መኖራቸውን ገልጸው “ሴቶችን ለማበረታታት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ በኮርፖሬሽን ደረጃ ቢኖር የሴቶች ተሳትፎ ይበልጥ ይሆናል” ብለዋል፡፡

ወ/ሪት ተሊሌ ዱጋሳ

የፀረ ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀንን በማስመልከት የእግር ጉዞ ተደረገከስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት እና አዲስ አበባ ከሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች አገናኝ (ላይዘን) ቢሮዎች የተውጣጡ ሠራተኞች የፀረ ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀንን በማስመልከት ህዳር 27 ቀን 2008ዓ.ም. ካዛንቺስ ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በመነሳት ወደ ሃምሊን ፊሲቱላ - ኢትዮጵያ ሆስፒታል የእግር ጉዞ አደረጉ፡፡

ተጓዦቹ “በወንዶች ቁልፍ አጋርነት የፆታ ጥቃትን በጋራ እንከላከል!”

የሚል መሪ ቃል በማንገብ ነበር ጉዞውን ያካሄዱት፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በፊስቱላና በፆታ ጥቃት ዙሪያ የባለሙያ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ የጉዞው ተሳታፊዎችም በሴቶች ላይ ስለሚፈፀሙ ጥቃቶች ሰፊ ግንዛቤን ለማግኘት ችለዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ሦስት ኩንታል ስኳር በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን በድጋፍ መልክ ተሰጥቷል፡፡

የባለሙያ ገለፃ - በሃምሊን ፊስቱላ- ኢትዮጵያ ሆስፒታል

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 6

የኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ እየተከናወነ ነው

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ እንደተናገሩት ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ወደ ምርት ሲገባ በ25ሺ ሄክታር መሬት ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ የሚያስፈልገው ሲሆን ይህንን ለማሟላትም ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ እስካሁን በ12ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ መተከሉን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸው በተያዘው በጀት አመት በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነውን መሬት 17ሺ ሄክታር ለማድረስ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የፋብሪካ ቁጥር ሁለት የመሬት በታች የሲቪል ግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ስትራክቸሮችን ማቆም መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ለፋብሪካ ቁጥር ሁለት የሚያስፈልገው የሸንኮራ አገዳ ልማት ከፋብሪካ ተከላው ጎን

ለጎን በስፋት እየተካሄደ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ካሳ ለፋብሪካ ቁጥር ሦስት የሚያስፈልጉ ሰፋፊ የመስኖ አውታር ዝርጋታ ስራም በመፋጠን ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ቁጥር አንድ የእርሻ ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ አሰፋ በበኩላቸው ከተለያዩ ነባር ፋብሪካዎች ምርጥ የሸንኮራ አገዳ ዘሮችን በማምጣት የተከላ ስራው እየተከናወነ መሆኑን ተናግረው፣ ለፋብሪካ ቁጥር አንድ በአገዳ ቆረጣ ላይ የሚሳተፍ በቂ የሰው ኃይል፣ ጋሪዎች፣ ትራክተሮች እና ኦፕሬተሮች መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የሲቪልና መስኖ ምህንድስና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ በሀይሉ ጌታቸው በበኩላቸው በኦሞ ወንዝ ላይ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የተገነባው ጊዜያዊ ግድብ የ58 ኪሎ ሜትር የዋና ቦይ፣ የአፈር ቁፋሮና የስትራክቸር ግንባታ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ ከ13ሺ 273 ሄክታር በላይ የሆነ መሬት በመስኖ ለማልማት ዝግጁ

መሆኑን ጠቁመው፣ ፋብሪካው ምርት ሲጀምር አገዳውን በፍጥነት ለማመላለስ እና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎ እና የኛንጋቶም፤ በቤንች ማጂ ዞን ማጂ እና ሜኢኒትሻሻ እንዲሁም በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳዎች ውስጥ የሚካሄድ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የኦሞ ወንዝን በመጠቀም በ175ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብአትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያላቸው ሦስት ፋብሪካዎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው በቀን 24ሺ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያላቸው ሁለት ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡ ከእነዚህ አምስት ፋብሪካዎች ውስጥ የፋብሪካ ቁጥር አንድ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 7

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢውን ማህበረሰብ በስራ እድል ተጠቃሚ እያደረገ ነው

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በልማቱ አካባቢ የሚገኘውን ማህበረሰብ በስራ እድል ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ ለረጅም ጊዜያት በተለያዩ የስራ መደቦች በጊዜያዊነት ሲያገለግሉ የቆዩ 152 የአካባቢውን ማህበረሰብ አባላትና ልጆቻቸውን በቅርቡ በቋሚነት ቀጥሯል፡፡ ከተቀጠሩት ውስጥ ከ28 በመቶ በላይ የሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ በአካባቢያቸው ተግባራዊ መደረግ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ መልኮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀው፣ አሁን ደግሞ ቋሚ የሥራ ዕድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሠራተኞቹ በፕሮጀክቱ ረዘም ላለ ጊዜ በጊዜያዊነት ሲያገለግሉ እንደነበር ጠቁመው ቋሚ መደረጋቸው የተረጋጋ ኑሮ ለመምራት እንደሚረዳቸውና ሌሎች ጊዜያዊ ሠራተኞች በተስፋና የእኔነት ስሜት ስራቸውን በትጋት እንዲያከናውኑ እንደሚያነሳሳቸው ገልጸዋል፡፡

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሰው ኃብት አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ በለጠ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በአካባቢው ተግባራዊ መደረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአካባቢውን ማህበረሰብና ልጆቻቸውን በተለያዩ የስራ እድሎች ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በጊዜያዊ የስራ መደቦች ተቀጥረው በመስራት ላይ የሚገኙትን የአካባቢው ማህበረሰብ አባላትና ልጆቻቸውን በቋሚ የስራ መደቦች ላይ እንዲሰሩ መደረጉ ፕሮጀክቱን ከማህበረሰቡ ጋር ይበልጥ እንደሚያስተሳስርና የባለቤትነት ስሜትን እንደሚፈጥርም አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአካባቢዎቹ መተግበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ እስካሁንም ከ18ሺ 5ዐዐ በላይ ለሆኑ ዜጐች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ እድሎችን ፈጥሯል፡፡

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በሚገኙት በአዊ እና መተከል ዞኖች በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ አማካኝነት 75ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብአትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያላቸው ሦስት ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡ በዚህ መሰረት የበለስ 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በክረምት የጥገና ወቅት ውጤታማ የማሻሻያ ሥራዎች ተከናወኑ

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በክረምት የጥገና ወቅት ከዲዛይን ችግር ጋር በተያያዘ በሸንኮራ አገዳ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ይከሰት የነበረውን የመገልበጥ አደጋ ለመቀነስ እና ለማስቀረት የሚያስችሉ ውጤታማ የማሻሻያ /ሞዲፊኬሽን/ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ፡፡

የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን መረጃ እንደሚያስረዳው በማሻሻያ ስራው “17 HBT” በመባል የሚታወቁ የአገዳ ተሸካሚ ጋሪዎች የጐን ስፋትን ከአራት ሜትር ወደ 3.6 ሜትር በማሳነስ በጎኑ ስፋት ምክንያት በሸንኮራ አገዳ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ይከሰት የነበረውን የመገልበጥ አደጋ ለመከላከል ተችሏል፡፡

በፋብሪካው የመስክ መሣሪያዎች ጥገና » ወደ ገጽ 8 ዞሯል

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 8

አገልግሎት የተሰሩት እነዚህ የማሻሻያ ሥራዎች ፋብሪካው በ2ዐዐ8 የምርት ዘመን ለማምረት ያቀደውን የ1.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ምርት ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክቱ ተጠቁሟል፡፡

በመስክ መሣሪያዎች ጥገና አገልግሎት ሠራተኞችና ኃላፊዎች ያላሰለሰ ጥረት የፋብሪካው የምርት ሂደት እንዳይስተጓጎል የሚያስችሉ የማሻሻያ ስራዎች ከመከናወናቸው በተጨማሪ 739ሺ 667 ብር የሚገመት ወጪ ማዳን መቻሉን ከፋብሪካው የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚሁ የክረምት የጥገና ወቅት በመስክ መሣሪያዎች ጥገና አገልግሎት የተለያዩ

የመለዋወጫ እቃዎችን ጨምሮ በ”ቤል ትራክተር ዳምፐር” ላይ የማሻሻያ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በሁሉም የቤል ትራክተሮች ላይ የተሰራው የማሻሻያ ስራ በኦኘሬተሮቹ ላይ ይከሰት የነበረውን ከፍተኛ የጤና መታወክ ከመከላከል ባለፈ የማሽኑንም የአገልግሎት ዘመን እንደሚያራዝም ተጠቁሟል፡፡ በተያያዘ ዜና ሸንኮራ አገዳ በተፈለገው መጠንና ፍጥነት ለፋብሪካው ለማድረስ አዲስ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በዚህም ከአዋሽ መልካሣ እስከ ወለንጪቲ በተዘረጋው መስመር አቅጣጫ 25 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ በመገንባት ላይ ነው፡፡

በፋብሪካው ባለሙያዎችና ማሽኖች እየተገነባ የሚገኘው ይህ መንገድ ሲጠናቀቅ በወለንጪቲ፣ ቦፋና ወለንሱ አካባቢ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ እየለማ የሚገኘው የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት ያለምንም የትራፊክ መጨናነቅና የአገዳ ብክነት ወደ ፋብሪካው ለማጓጓዝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ በተጨማሪም መንገዱ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የሚኖረው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሚሆን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በክረምት የጥገና ..

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የንብረትና የደህንነት ጥበቃ ሠራተኞችን አስመረቀ

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በሁለት ዙር በንብረትና ደህንነት ጥበቃ ያሰለጠናቸውን 577 የጥበቃ ሠራተኞች በአገምሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቀ፡፡

መስከረም 22 ቀን 2008 ዓ.ም በተከናወነው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ መኮንን የጥበቃ ሠራተኞቹ የተሰጣችውን ስልጠና በስኬት በማጠናቀቃቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ተመራቂ የጥበቃ ሠራተኞች በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ተጠቅመው ለፋብሪካው እቅድ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የቀረበለትን የስልጠና ድጋፍ ጥያቄ ተቀብሎ ፋብሪካው ድረስ በመምጣት አስፈላጊውን ስልጠና መስጠቱን

የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ለተደረገላቸው የስራ ትብብርም በፋብሪካው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ተሬሳ ካሳ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ከወንጀል ነፃ የሆነ አካባቢን መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን አለበት ብለዋል፡፡ አክለውም በስልጠናው ኮሌጁ 12 የፖሊሳዊ ሳይንስ መምህራንን እና 16 የመስክ ወታደራዊ ሳይንስ አሰልጣኞችን በመመደብ ለ577 የድርጅቱ ንብረትና ደህንነት ጥበቃ ሠራተኞች በጥበቃ ሠራተኛ ሥነ ምግባር፣ በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በመንግስታዊ ተቋማት

ደህንነት አጠባበቅ፣ በወንጀል መከላከልና ፍተሻ፣ በመሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም እና ተያያዥ ወታደራዊ ክህሎቶች ስልጠና መስጠቱን አብራርተዋል፡፡

ሰልጣኝ ተመራቂዎችም ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር በቆራጥነት፣ በትጋት፣ በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር የተጣለባቸውን ታላቅ ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ ብርሃኑ ጥላሁን ባሰሙት የመዝጊያ ንግግር የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለዞኑም ሆነ ለሀገሪቱ ኩራት የሆነ ብሔራዊ ሀብት በመሆኑ ለፋብሪካው ደህንነት ዞኑ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡

» ከገጽ 7 የዞረ

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 9

የምሥራቅ ኮኮብ » ሲሳይ ደርቤ - ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

የኢትዮጵያ ህዳሴ መሐንዲስ የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሀገራችንን ወደላቀ ስልጣኔ ምዕራፍ ለማሸጋገር የነበራቸውን ምጡቅ ራዕይ ለማሳካት ከሩቅ ምስራቅዋ ጃፓን የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና ቀልባቸውን ሳበው፡፡

ይኸው የጃፓናውያን «ሁለተኛ ዕምነት» የተባለለት ካይዘን ጃፓንን በአጭር ዓመታት የዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ማማ ላይ አድርሷታል፡፡ አቶ መለስ ፍልስፍናው በሀገራችን ኢንዱስትሪዎች እንዲተገበር በሰጡት ቁርጠኛ አመራር በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ - በሀገረ ኢትዮጵያ ብርሃን እየፈነጠቀ ይገኛል ፡፡

አቶ መለስ ካይዘንን አስመልክተው እንዲህ ብለው ነበር፡፡ «የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን ወስደን በመተግበር የግልና የመንግሥት የልማት ድርጅቶቻችንን የምርትና የአገልግሎት ጥራታቸውን ያለማቋረጥ በማሻሻል ምርታችንን የማሳደግ ተስፋችንን እውን እናደርጋለን፡፡»

በዚህ መነሻነት በአሁኑ ወቅት ካይዘን በሀገራችን ፍሬያማ እንዲሆን መንግስት ሰፊ ርብርብ እያደረገ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያ የካይዘን የልህቀት ማዕከል እንድትሆን የሩቅ ምሥራቅዋ ጃፓን የአፍሪካዋን የምሥራቅ ኮከብ ተመራጭ አድርጋታለች፡፡

በዋናነትም ካይዘን በመተግበር ላይ ከሚገኝባቸው ተቋማት መካከል የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግንባር ቀደም ነው፡፡

ታሪካዊ ትስስርየምስራቅ አፍሪካዋ ኢትዮጵያ እና የሩቅ ምሥራቅዋ ጃፓን ከብረት የጠነከረ ታሪካዊ ትሥሥር ያላቸው ሀገሮች ናቸው ፡፡

ሩቅ ምሥራቅ ሳለሁ ጃፓኗን ወድጄ ትዝ ትለኛለች በፍቅሯ ነድጄ ……… ተብሎ ጥበባዊ፣ አይረሴ እና ዘመን ተሸጋሪ ዜማ ተዜሟል ፡፡

ይህም ብቻ አይደለም ጃፓን ባዘጋጀችው ሁለተኛው የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር በማራቶን ሩጫ ጥቁር አፍሪካዊ ባለድል ሆኖ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በከፍታ እንዲውለበለብ ያደረገው ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ለታሪካዊ ትስስሩ በር ከፋች ነው፡፡ ያኔ በዓለም አደባባይ የምስራቅ አፍሪካዋ ኮከብ ሀገር - ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ኩራትነቷ ዳግም አንፀባረቀ ፡፡

ሮም በባዶ እግሩ ቶኪዮ በጫማ አሸንፎ ገባ አበበ ቢቂላ …………የተሰኘው ታሪካዊ ዜማም አይረሴ ነው፡፡በቅርቡ ኒውዮርክ በተካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጃፓን አቻቸው ሽንዞ አቤ ጋር ባደረጉት ውይይት የካይዘን ንቅናቄን በኢትዮጵያ ለማሳደግ ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳለ መግለፃቸው ይህንኑ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በበኩላቸው የጃፓን ውጭ

ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ቢሮውን አዲስ አበባ ለመክፈት መወሰኑን አብስረዋል ፡፡

የሁለቱ ሀገሮች ታሪካዊ ትሥሥራቸው በካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና ይበልጥ እየደመቀ መጥቷል፡፡ በርካታ የሀገራችን ተቋማት ለተወዳዳሪነት የሚያንደረድራቸው አቅም በካይዘን ስራ አመራር አማካኝነት ተፈጥሯል፡፡ በዚህም በጥቂት አመታት ውስጥ ሀገራችን የመጀመሪያ ደረጃ ካይዘን ባለቤትነቷን አረጋግጣለች ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሔደው የካይዘን ውድድር ከገቢ ምርቶች ዘርፍ በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ እንዲሁም ከመላው ሀገር አቀፍ ተወዳዳሪዎች ደግሞ በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ አንደኛ ደረጃን በማግኘት የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶችን በሙሉ ያገኘው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ እናም ኢትዮጵያና ጃፓን ታሪካዊ ትስስራቸው በካይዘን ይበልጥ እንዲያበራ ለማድረግ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አመራር፣ ሰራተኛ፣ የሰራተኛ ቤተሰብ፣ የፈንታሌ ወረዳና የመተሀራ ከተማ መስተዳድር እና በፋብሪካው ዙሪያ የሚገኘው አርብቶ አደር ሚና የላቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም አዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ላይ ሀገር ዓቀፍ ሁነት አካሂዶ ነበር፡፡ በዝግጅቱ በካይዘን ትግበራ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ፊት መሪ ለሆኑ ተቋማት፣ የካይዘን ልማት ቡድኖችና ግለሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ወርሃ መስከረም የካይዘን ጥበብ በመላው ሀገራችን እንዲተገበር ንቅናቄ የሚፈጠርበት ወር መባሉም ይፋ የተደረገው በዚሁ ወቅት ነበር፡፡

ምልሰት ወርሃ መስከረም 2008 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ደረጃ ካይዘን ትግበራና በማስቀጠል ደረጃ ተቋማትን ሲያወዳድር ቆየ፡፡ የውድድሩ ሂደት ዜና ለመላው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ማህበረሰብ ሲበሰር ታላቅ ጉጉትን አሳደረ፡፡ ቀናት እንደነፍሰጡር ተቆጠሩ፤ የድሉን ብስራት ዜና ለመስማት ሁሉም ጉጉት አደረበት ፡፡

በእርግጥም ያጓጓል፡፡ በ2006 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ካይዘን ትግበራ ውድድርን ያለተቀናቃኝ በብቃት ባሸነፈው ተቋም - በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2007 ዓ.ም በማስቀጠል ደረጃ ቁርጠኝነትና ፅናትን የጠየቀ ሰፊ ርብርብ ተደርጓል፡፡ በ1012 የካይዘን የልማት ቡድን የተደራጀው የልማት ሰራዊት ካይዘንን በማስቀጠል ረገድ ወገብን የሚያጎብጥ ግን ደግሞ በከፍተኛ የአመራር ጥበብ እንዲሁም ህብራዊ የሆነ የሰራተኛው ልማታዊ ጀግንነት ከፍተኛ ውጤቶችን አስመዝግቧል ፡፡

በዋናነትም ለ2007 ዓ.ም የምርት ዘመን የፋብሪካውን የጥገና ሂደት በተቋሙ ታሪክ በራስ አቅምና በ10 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በብቃት ማከናወን ተችሏል፡፡ እንዲሁም ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል

» ወደ ገጽ10 ዞሯል

ቆይታ

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 10

ቆይታ በላይ ስኳር እና ከ8.5 ሚሊዮን ሊትር በላይ

ኢታኖል ተመርቷል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ዓመት 423 ሚሊዮን 735 ሺህ ብር ማዳን ያስቻሉ የፈጠራና የማሻያ እንዲሁም የወጭ ማዳን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ 10 ነጥብ 3 ሺህ ሄክታር የሚሸፍነው የሸንኮራ አገዳ ማሳ ምርታማነቱ እንዲሻሻል የመሬት ዝግጅት፣ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች ላይ ሰፊ ተግባራት በመከናወናቸው የቀጣይ ዓመታት የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት አስተማማኝ እንዲሆን አስችሏል፡፡

በአጠቃላይ የአንድ ኩንታል ስኳር ማምረቻ ወጪ ከብር 620 ወደ ብር 540 ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ የ2007 ዓ.ም የስኳር ምርታማነት የካይዘን ስራ አመራር ትግበራው ከመቀጣጠሉ አስቀድሞ ከነበረው 2005 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በ312ሺ 532 ኩንታል ስኳር ወይም በ28.1% ብልጫ አሳይቷል፡፡

ፋብሪካው በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማመን

በሚያስቸግር ሁኔታ ቅጽበታዊ ለውጥ ያስመዘገበው በተዓምር አይደለም፡፡ ይልቁንም የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና የወለደው አወንታዊ የለውጥ አስተሳሰብና የአሸናፊነት አመለካከት በፋብሪካው ዙሪያ እንደቋያ እሣት በመቀጣጠሉ ነው፡፡ በመሆኑም የለውጥ አስተሳሰቡ ከሥራ ቦታ ባሻገር ጠቅላይ ሰፈርን ጨምሮ በሰባት የሰራተኞች መኖሪያ ካምፖች ልምላሜን አግኝቷል፡፡ በጤና ኤክስቴንሽንና በኮሙኒቲ ፖሊሲንግ አንድ ለአምስት አደረጃጀት አማካኝነት አካባቢዎች ለኑሮ ምቹና የኢንዱስትሪ ሠላም የሰፈነባቸው እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም ካይዘን በፋብሪካው መኖሪያ ቤቶችም ጭምር ባህል እየሆነ ሊመጣ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ካይዘናዊ አስተሳሰብን በተላበሰ ንቅናቄ አማካኝነት ከአካባቢው መስተዳድር አካላትና ከአርብቶ አደር ጋር የተፈጠረው

ልማታዊ ትስስር በስራ ዕድል ፈጠራ እና የልማት ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው፡፡

በዋናነትም በ2007 ዓ.ም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ድረስ በአካባቢው በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት ለፋብሪካው አዋሳኝ የሆኑና በቅርብ ርቀት የሚገኙ የፈንታሌ ወረዳ 18 ገጠር ቀበሌዎችን እንዲሁም ከምእራብ ሐረርጌና በቅርብ ርቀት ያሉ የአፋር አርብቶ አደሮችን ለመታደግ በፋብሪካው የተደረገው ድጋፍ የአመራሩን ህዝባዊና ሀገራዊ ተልዕኮ ብቃት ያስመሰከረ ነበር ፡፡

በዚህም ለችግሩ የተጋለጡ ወገኖች የእንስሳት ሃብቶቻቸው ላይ ሊደርስ ይችል የነበረውን መጠነ-ሰፊ ጉዳት ለመታደግ በተደራጀ ሁኔታ በመደበኛነት የሸንኮራ አገዳ ገለባ እና ውሃ በማቅረብ የእንስሳት ሃብቱን ከእልቂት ማትረፍ ያስቻለ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የምሥራቅ ኮኮብ ... » ከገጽ 9 የዞረ

የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና በመላው የፋብሪካው አካባቢ በብቃት እንዲተገበር የሚያስችሉ ሌሎች አደረጃጀቶችም ተተግብረዋል፡፡ የኪነጥበባት ማእከል በማቋቀቋም እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት የተፈጠሩ የመልካም ግንኙነትና የንቅናቄ ስራዎች ለካይዘን ትግበራው መሳለጥ ሚናቸው የላቀ ነበር ፡፡ በዚሁ መሰረት የካይዘንን ጥበብ ያከበረው መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ጥበቡ አስከበረው፤ ከውድቀት ወደ ቀልብ ሳቢነትም አሸጋገረው፡፡ እናም ከተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪ እና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች

አንስቶ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ድርጅቶች የመጡ በድምሩ ከ6ሺ በላይ ጎብኝዎች የፋብሪካውን ተጨባጭ የለውጥ ፍሬዎች ቃኝተው ተሞክሮ ቀስመዋል ፡፡

በዋናነትም ከከሰም፣ ከተንዳሆና ከኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በተለያዩ ጊዜያት ወደ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የተላከ የሰው ሃይልን የማብቃት ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ ስልጠናዎቹም በፋብሪካና በእርሻ ዘርፎች ልዩ ልዩ ሙያዎች ላይ ያተኮሩ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በአጠቃላይ ከ600 ለሚበልጡ የስኳር ልማት ዘርፍ ባለሙያዎች ተሞክሮ የማስፋት ስራ

ተሰርቷል፡፡

እንዲሁም በካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና አማካኝነት የተፈጠረው ልማታዊ የለውጥ ማዕበል በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ብቻ አልተገደበም፡፡ ይልቁንም ለስኳር ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎችም ብርሃን ፈንጣቂ ሆኗል፡፡ በካይዘን ነጥረው የወጡ የፋብሪካው አመራሮችና ባለሙያዎች ወደ ከሰም፣ተንዳሆ፣ወልቃይት፣ኦሞ ኩራዝ፣አርጆ ዲዴሳና ጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በመዝመት ንቅናቄን ፈጥረዋል፡፡

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ላይ በካይዘን ጥበብ

» ከፈንታሌ ወረዳ የአርብቶ አደሮች ተወካዮች ጋር በተዘጋጀ የጋራ መድረክ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች ሲመርቁ

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

አማካኝነት የተፈጠረው አወንታዊ አመለካከት፣ የይቻላል አስተሳሰብ፣ የተወዳዳሪነትና የአሸናፊነት መንፈስ ካይዘንን በማስቀጠል ለተከናወነው ርብርብ የአሸናፊዎች አሸናፊነትን የማስቀጠል ብርቱ ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው፡፡

በአጠቃላይ የፋብሪካው አመራር እና ሠራተኛ ያላሰለሰ ትጋት እና ቁርጠኝነት መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት አዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ላይ በተዘጋጀው የአገር አቀፍ የካይዘን ውድድር ላይ ካይዘንን

በማስቀጠል በተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የአንደኝነት የክብር መዳሊያዎችን በዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ዘነበ ይማም እና የታርጌት ልማት ቡድን ተወካይ ወጣት ያስችለዋል ብርሃኑ አማካኝነት አጠለቀ፤ ዋንጫዎችንም በክብር ወደ ላይ ከፍ አደረገ፡፡

ወደፊትም የአሸናፊዎች አሸናፊነቱን ለማስቀጠል እንደከዚህ ቀደም ጊዜያት በትጋት እንደሚሰራ ይታመናል፤ አረንጓዴው በረሀ - የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ፡፡

የምሥራቅ ኮኮብ ... » ከገጽ 9 የዞረ

ቆይታ

የፕሮጀክቱ ትሩፋት » መልአኩ ካሕሱ-ከወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

የኢፌዲሪ መንግሥት ሊተገብራቸው ካቀዳቸው አዳዲስ ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አንዱ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ በቀን 24ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለመገንባት ስራዎች ተጀምረዋል፡፡ በልማቱ ሳቢያም የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል፣ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተጠቃሚ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ በተለይም ፕሮጀክቱ በፈጠረው ቋሚ፣ ጊዜያዊ እና ኮንትራት የስራ እድል እስካሁን ድረስ 50ሺ የሚጠጉ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ለስኳር ፋብሪካው ግብአት የሚውል የሸንኮራ አገዳ ለማልማት በዛሬማ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የሜይ ዴይ ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፕሮጀክቱ በ3ሺ 870 ሄክታር መሬት ላይ ሰሊጥ፣ ማሽላና ጥጥ እያለማ ይገኛል፡፡ በዚህ የተጓዳኝ ሰብሎች ልማት ላይ ብቻ በተፈጠረው የስራ እድል በ2007ዓ.ም

መጨረሻ 4ሺ200 የሚጠጉ የቀን ሠራተኞች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

ከእነዚህ እድለኞች አንዱ ወጣት ደመላሽ ጥጋቡ ይባላል፡፡ የተወለደው ኮሰበር ዞን፣ ቻግኒ ወረዳ ግቤ ስላሴ ሲሆን፣ በጓደኛው አማካኝነት ነበር መጋቢት 2007 ዓ.ም ወደ ፕሮጀክቱ የመጣው፡፡ በጉልበት ሠራተኛነት መቀጠሩን የሚናገረው ይህ ወጣት በፕሮጀክቱ በጥጥ ተከላና ለቀማ እንዲሁም ሰሊጥ በመዝራት፣ በማረምና በማጨድ ስራዎች እየተሳተፈ መሆኑን አጫውቶናል፡፡ ስለ ፕሮጀክቱ ሲገልጽም “ፕሮጀክቱን ከእናት እና አባቴ ለይቼ አላየውም” ይላል፤ እንደውም ቤተሰቤም ጭምር ነው በማለት፡፡

በሚሰራበት ወቅት ድካምና መሰልቸትን እንደማያውቅ የሚናገረው ደመላሽ ከፕሮጀክቱ የምግብ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት ማግኘቱ ስራው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርግ እንዳስቻለው ያስረዳል፡፡

ያገኘውን ጥቅም ሲያስረዳም በተመደበበት የስራ መስክ ጠንክሮ በመስራቱ በስምንት ወራት ብቻ 18ሺ ብር ለመቆጠብ ችሏል፡፡

ከዚህ የበለጠ ደስታ ምን አለ? በማለት የሚጠይቀው ደመላሽ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ቤተሰቦቹና ጓደኞቹን ወደ ፕሮጀክቱ አምጥቶ ሰርተው እንዲለወጡ ለማድረግ አስቧል፡፡ ከዚህ ባሻገር ከቤተሰቦቹ ጋር ጠንክሮ በመስራት በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ወፍጮ ቤት

» ወደ ገጽ 12 ዞሯል

» ከግራ ወደ ቀኝ ወጣት ያስችለዋል ብርሃኑና የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም ካይዘንን በማስቀጠል በተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ የአንደኝነት ሽልማትን ሲቀበሉ

» ወጣት ደመላሽ ጥጋቡ

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 12

ለመክፈት ያለውን እቅድም ጠቁሞናል፡፡

ፕሮጀክቱ ለደመላሽና መሰሎቹ የተለያዩ የስራ መስኮችን አመቻችቶና እጁን ዘርግቶ በመቀበሉ ለዛሬ የደመላሽና ሌሎች ወጣቶች ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት ችሏል፡፡

ሌላዋ በፕሮጀክቱ በተፈጠረ የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆነችው ከትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ላዕላይ ማይጨው ወረዳ የመጣችው ወጣት መድህን ፀጋይ ናት፡፡ መድህን የ12ኛ ክፍል ትምህርቷን ብታጠናቅቅም ከፍተኛ ተቋም የሚያስገባ ውጤት አላመጣችም፡፡ ቁጭ ብላ የቤተሰቧን እጅ መጠበቅ ያልፈለገችው ወጣቷ ለወረዳው ስራ ፈላጊ ወጣቶች በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የተለያዩ የሥራ እድሎች እንዳሉ የሚገልጸውን ማስታወቂያ እንዳየች ለመመዝገብ አላመነታችም፡፡

መድህን ከቀየዋና ከቤተሰቦቿ ተለይታ ስለማታውቅ በርካቶች “ይቅርብሽ” ቢሏትም በጀ አላለቻቸውም፡፡ ይልቁንም ወደ ፕሮጀክቱ በመሄድ ሕይወትን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ቆረጠች፡፡ መድህን ልክ እንደ እርሷ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ወደ ፕሮጀክቱ ከመጡ ሌሎች ወጣቶች ጋር በመሆን ከጥጥ ለቀማ እስከ አገዳ ቆረጣና ሰሊጥ አጨዳ ባሉ ስራዎች ላይ ተሳትፋለች፡፡

ለስራ ጊዜና ቦታ እንደማትመርጥና ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ቁጭ ብላ እንደማትጠብቅ የምትገልጸው ወጣቷ ሁል ጊዜም ለስራ በተሰማራችበት ማሳ ውስጥ ስራው እስኪገባደድ ድረስ ደፋ ቀና እያለች እንደምትውል አጫውታናለች፡፡ ከዚህ

ትጋቷም የተነሳ በቀን 200 ብር ያገኘችበት ጊዜ እንደነበር ታስታውሳለች፡፡

“ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን የማውቀው በወሬ ነበር፡፡ እዚህ መጥቼ ሳየው ጠንክሬ ከሰራሁ ቶሎ መለወጥ እንደምችል የተረዳሁት ወዲያው ነው፡፡ የፕሮጀክቱ የሥራ ኃላፊዎች እኛ በማይረባ ነገር እንዳንታለልና እንዳንወድቅ፣ ጠንካራ የሥራ መንፈስ እና ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖረን ረድተውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሴቶች እድሉ ከተሰጣቸው ከወንድ እኩል መስራት እንደሚችሉም ተምሬበታለሁ፡፡

“ትምህርቴን ጨርሼ ምንም ገቢ አልነበረኝም፡፡ በፕሮጀክቱ ጠንክሬ በመስራቴ በስድስት ወር 7ሺ 800 ብር መቆጠብ ችያለሁ፡፡ አሁን እዚህ ስመጣ በጥርጣሬ ያዩኝና አትሄጅም ያሉኝን ቤተሰቤን በመደገፍ ላይ እገኛለሁ፡፡ ጓደኞቼም እኔን አይተው እዚህ መጥተው ለመስራት ፍላጎት እያሳዩ ናቸው፡፡” በማለት በሥራዋ ያገኘችውን እርካታ ትገልጻለች፡፡ ቀጣይ እቅዷም በፕሮጀክቱ የተወሰነ ጊዜ ሰርታ ምግብ ቤት መክፈት እንደሆነ ትናገራለች፡፡

ወጣት ዳምጤ መላኩም በፕሮጀክቱ በጥጥ ተከላና ለቀማ እንዲሁም ሰሊጥ በመዝራት፣ በማረምና በማጨድ ስራዎች ጉልህ እንቅስቃሴ እያደረጉ ከሚገኙ ታታሪ የቀን ሰራተኞች አንዱ ነው፡፡ የመጣው ከደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ ነው፡፡ ወደ ፕሮጀክቱ ለመምጣቱ ምክንያት የሆነው ስለ ፕሮጀክቱ በመገናኛ ብዙኃን የተመለከተው ዝግጅት መሆኑን ይናገራል፡፡ በፕሮጀክቱ ሰፊ የስራ እድል መኖሩን የተገነዘበው ይህ ወጣት በ2007ዓ.ም በፕሮጀክቱ ለተወሰነ ጊዜ

ከሰራ በኋላ ወደ ትውልድ ቦታው ተመልሶ ወንድሙን ይዞ በመምጣት አሁን አብረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ያሳለፈውን የሕይወት ውጣ ውረድ ሲገልጽም “ለሥራ ፍለጋ እስከ ሱዳን ዓብደልራፊዕ ድረስ ሄጃለሁ፡፡ አገር አቋርጬ ብሄድም ሁሉም ነገር እንደፈለግሁትና እንዳሰብኩት አልሆነልኝም፡፡ እዚህ ግን እንደዛ አይደለም፡፡ ፕሮጀክቱን የምመለከተው እንደ ቤቴ ነው፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ በመስራት ላይ ነው ያለሁት፡፡ ዓላማዬ ሰርቶ መለወጥ በመሆኑ ሌተ ተቀን ሳልል በርትቼ በመስራቴ በቀን እስከ 200 ብር አገኛለሁ፡፡ በቀን ከ110 ብር በታች ሰርቼ አላውቅም፡፡ ከማገኘው ገንዘብ ላይም ቤተሰቦቼን እየረዳሁ በሦስት ወር 6ሺ ብር መቆጠብ ችያለሁ፡፡ ለማስበው የንግድ ስራ በቂ መንቀሳቀሻ እስካገኝ ድረስም በርትቼ እሰራለሁ” ይላል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ጠንክረው በመስራታቸው እና ራሳቸውን በመለወጣቸው ለአብነት ቀረቡ እንጂ በፕሮጀክቱ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሰሊጥ፣ ማሽላና ጥጥ ልማት ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

የፕሮጀክቱ የመስኖ፣ አገዳ ተከላና እንክብካቤ ሥራ አስከያጅ አቶ እምባየ ግርማይ እንደሚገልጹት የቀን ሠራተኞቹ ጠንክረው በመስራታቸው ራሳቸውን ከመጥቀም አልፈው ለፕሮጀክቱም ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

“ጠንክሮ የሰራ የልፋቱን አያጣም” የሚሉት ሥራ አስኪያጁ ወጣቶቹ ጥሩ ገቢ ከማግኘት አልፈው ቀጣይ ተስፋቸውንም እያለመለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በቀጣይም የጥጥ ለቀማ፣ የአገዳ ተከላና መሰል ስራዎች ስለሚኖሩት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም አሁን የስራ እድል አግኝተው ውጤታማ እንደሆኑት ወጣቶች ሁሉ ሌሎችም ወደ ፕሮጀክቱ በመምጣት ለራሳቸውና ለሀገራቸው የሚጠቅም ስራ ሊሰሩ ይገባል እንላለን!

የፕሮጀክቱ ትሩፋት... » ከገጽ 11 የዞረ

ቆይተ

» ወጣት መድህን ፀጋይ

Page 13: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 13

የአዲስ ራዕይ ሠልጣኞች የት ደረሱ?

ቆይተ

በሀገራችን በተለያየ ምክንያት ሰዎች ለጎዳና ሕይወት አሊያም ለሥራ አጥነት ይዳረጋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ለተለያዩ ሱሶች ከመጋለጣቸውም በላይ አብዛኛውን ጊዜ ሠርቶ የራስን እና የማህበረሰቡን ሕይወት በአወንታዊ መልኩ ከመቀየር ይልቅ በአሉታዊ መልኩ የሰላም መደፍረስ ምንጭ ሲሆኑም ይስተዋላል፡፡

የጎዳና ተዳዳሪነት ችግር የዚህ አካባቢ ወይም የዛኛው አካባቢ የሚባል ሳይሆን ዓለም አቀፍ መልክ ያለው ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ችግሩ በሀገራችንም በስፋት ይታያል፡፡

መንግሥት ችግሩን በዘላቂነት ለማስወገድ የተለያዩ መርሐ ግብሮችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን፣ የችግሩ ተጎጂ የሆኑ ወገኖችም ሠርተው እንዲጠቀሙና ሀገርንም እንዲያለሙ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከመርሐ ግብሮቹ አንዱ የችግሩ ተጎጂዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ወደ ሥራ ማሰማራት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በሥልጠና ታግዘው የአመለካከት እና የአኗኗር ለውጥ ካመጡ እና በሥራ ተሰማርተው ሕይወታቸውን እየለወጡ ካሉ ወጣቶች ውስጥ በአፋር ክልል በሚገኘው በአዲስ ራዕይ ማሠልጠኛ ሠልጥነው ወደ ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ከነዚህ ወጣቶች 280ዎቹ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት አማካይነት በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተመድበው ካለፉት ስምንት ወራት ጀምሮ በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀብታም ተጋበር ከወጣቶቹ መካከል አንዷ ናት፡፡ ሀብታም ትውልዷ ጎንደር ቢሆንም የኖረችው ባሕርዳር ነው፡፡ ስለጎዳና ሕይወት ስትጠየቅም “ምንም እንኳ ጎዳና ወጥቼ ባልኖርም በዘመድ ቤት ከዛ ባላነሰ አስከፊ ኑሮ ኖሬአለሁ፤ ወላጆቼ ይህን አያውቁም” ትላለች፡፡

ከዚህ በኋላ ነው ከምትኖርበት ክልል ተመልምላ በአዲስ ራዕይ ማሰልጠኛ አማካይነት

በተመቻቸ የስልጠና መድረክ በመሳተፍ በማሽኒስትነት ሙያ ሰልጥና አምቦ አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት የተግባር ልምምድ ያደረገችው፡፡ በመቀጠልም በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተመድባ መስራት ጀመረች፡፡ ከፕሮጀክቱ በምታገኘው 5ሺ ብር የወር ደመወዝም ከራሷ አልፋ ታናናሽ ወንድሞቿን እና ቤተሰቧን ትረዳለች፡፡ የወደፊት ዕቅዷን አስመልክታ ስትናገርም “ ሲ.ኦ.ሲ ተፈትኜ ትምህርቴን በዲግሪ ፕሮግራም ለመቀጠል እፈልጋሁ” ብላለች፡፡

ሌላው ያነጋገርነው ወጣት አያልነህ ሙሉሰው ግን በጎዳና አስከፊ ሕይወት አሳልፏል፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ ቢወለድም ለጎዳና ሕይወት የተዳረገው ግን በአዲስ አበባ ነው፡፡ የተለያዩ ሱሶችም ሰለባ ነበር፡፡ በዚህም በጣም ይጸጸታል፡፡ ምክንያቱን ሲያብራራም ወደ ጎዳና የወጣሁት መውጣት የለብኝም ብዬ ራሴን ስላላሳመንኩና መስራት ስችል ባለመስራቴ ነበር ይላል፡፡

ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው በአዲስ ራዕይ የከባድ ማሽን ሜካኒክነት ሥልጠና የወሰደው፡፡ “ወጣቶች ስለሆኑ ሠርተው መለወጥ ይችላሉ በሚል እምነት መንግሥት አሰባስቦን በማሰልጠን አሰማራን” የሚለው አያልነህ “አሁን መጥፎ ባህርዬን አስተካክዬ ከሰው ጋር ተግባብቼ እና ከሱስ ጸድቼ ጥሩ ሥራ እየሰራሁ ነው” ካለ በኋላ ነባር መካኒኮች ልምድ እያካፈሉት መሆኑን፣ እሱም በሚያገኘው ገቢ ቤተሰብ እየረዳ እንደሆነ እና ሙያውንም ይበልጥ ለማሻሻል እንዳቀደ አጫውቶናል፡፡

እዚያው ጣና በለስ በትራክተር ኦፕሬተርነት እየሠራ የሚገኘውን ተስፋሁን ሰንደቁንም አነጋግረነው ነበር፡፡ ከቤተሰቡ ከተለየ 12 ዓመት እንደሞላው የሚናገረው ይህ ወጣት በችግር ሳቢያ በትምህርቱ ብዙም እንዳልገፋና ለአራት ዓመታትም የጎዳና ላይ ህይወትን እንዳሳለፈ ገልጾልናል፡፡ የአዲስ ራዕይን ሥልጠና ከተከታተለ በኋላ ከሚያዝያ 2007 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ተሰማርቶ በወር ከ4ሺ ብር በላይ ያገኛል፡፡ ትዳር መስርቶ ኑሮን በጋራ በማጣጣም ላይ የሚገኘው ተስፋሁን ትምህርቱን በርቀት በመቀጠል ደረጃውን ለማሻሻል እያሰበ ነው፡፡

ከሥልጠና በፊት የመስተንግዶ ሠራተኛ እንደነበረች ከምትናገረውና የአንድ ሴት ልጅ እናት ከሆነችው ነጻነት ወንድሙ ጋርም ቆይታ አድርገን ነበር፡፡ እሷ በተሳተፈችበት ጊዜ በአዲስ ራዕይ ሥልጠና 4ሺ ያህል ሠልጣኞች እንደነበሩ

ትገልጻለች፡፡ በዚያም በአውቶሜካኒክነት ሙያ ለስድስት ወራት ከሠለጠነች በኋላ በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተቀጥራ በ4ሺ ብር የወር ደመወዝ እየሠራች ነው፡፡ ለወደፊት ሕይወቷን ይበልጥ ለማሻሻል በማሰብም ትምህርቷን በርቀት ለመቀጠል አስባለች፡፡

ሌላው ያነጋገርነው ወጣት በጓደኛ ተጽእኖ ቃሚ እና አጫሽ እንደነበር ያጫወተን ሀብታሙ ሃሰን ነው፡፡ ከነበረው ሕይወት ጋር ሲነጻጸር የአሁን ኑሮውን “ለኔ የኢትዮጵያ ዲቪ ነው” ይላል፡፡ እሱም በትራክተር ኦፕሬተርነት ሰልጥኖ በስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በመቀጠር በወር 6ሺ ብር እየተከፈለው እየሰራ ነው፡፡ ያሳለፈውን ሕይወት በማስታወስም ጓደኞቹ ከዛ አስከፊ ሕይወት እንዲወጡ ስልክ እየደወለ መምከር የጀመረው ገና ሥልጠናውን ጨርሶ ሥራ ላይ ሳይሰማራ ነው፡፡ ለወደፊት ሥራውን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠልም በግብርና ሙያ ለመሰማራት አልሟል፡፡

በዚህ መልኩ በርካታ ወጣቶች በስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በሥራ ላይ በመሰማራት እራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ ቤተሰባቸውንና ሀገራቸውን እየጠቀሙ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች በዚህ መልኩ በመሰማራታቸው በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመጣ ለውጥ ካለ የተጠየቁት በፕሮጀክቱ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አድገህ መኩርያ “ከአካባቢው ማኅበረሰብ ከተመለመሉት ጋር በመስራቱ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እየሆነ ነው፡፡ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር 69ሺ ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉት እንደ አንድ ፕሮጀክትም የሰው ኃይል እጥረታችንን በመጠኑ ቀርፎልናል፡፡” ብለዋል፡፡

እናም የአዲስ ራዕይ ሠልጣኞች የት ደረሱ? ለሚለው ጥያቄያችን ምላሹ ከእነርሱ መካከል የተወሰኑት በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዚህ መልኩ ኑሯቸውን እያሻሻሉ ነው፤ ሌሎችም በመሰል ፕሮጀክቶች ራስንና ቤተሰብን ከመርዳት አልፎ በአገሪቷ ልማት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው የሚል ይሆናል፡፡

» ወጣት ሃብታም ተጋበር

» ወጣት ተስፋሁን ሰንደቁ

Page 14: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 2 | ታህሳስ 2008 ዓ.ም | 14

የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ የቦታው አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥ እና የአፈር ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት ፈንድ፤ የስውዲን፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግስታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ ስራ ጥር 1981ዓ.ም ተጀመረ፡፡

ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ የሚገኘውን ቦታ ጨምሮ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ጠቅላላ ይዞታ (ኮማንድ ኤሪያ) 67ሺ 98 ሄክታር ነው፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ በማለፍ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫነት ከዋለ በኋላ ሸለቆውን ከሁለት ከፍሎ ወደ ሰሜን በመጓዝ ከአባይ ወንዝ ጋር በሚቀላቀለው የፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ ክፍል በዌስት ባንክ ያለውን

6ሺ 476.72 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማልማት እና የፋብሪካ ተከላ በማከናወን ነበር የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የተገነባው፡፡

የአካባቢው ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ1350 ሜትር እስከ 1600 ሜትር ይደርሳል፡፡ በሸለቆው ውስጥ ያለው ከፍተኛው የሙቀት መጠን 31 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን፣ ዝቅተኛው 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም በአማካይ 1300 ሚሊ ሊትር ይሆናል፡፡ ይህም የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ አካባቢን «ለምለም በረሃ» በሚል ልዩ ስም እንዲታወቅ አድርጎታል፡፡

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡

ፋብሪካው ኢታኖልን በማምረት ከቤንዚን ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት እንዲውል ከሚሰጠው አገልግሎት

በተጨማሪ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎችም በግብዓትነት በማገልገል ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ ድርሻ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

የነባሩ ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት የጀመረው የካቲት ወር 1990ዓ.ም ቢሆንም መደበኛ የማምረት ስራውን የጀመረው ግን በ1991 ዓ.ም ነበር፡፡ በዚሁ ዓመት ፋብሪካው 500 ሺህ ኩንታል ስኳር አምርቷል፡፡ ደረጃ በደረጃም ዓመታዊ የማምረት አቅሙን በማሳደግ 850 ሺህ ኩንታል ስኳርና 8 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ማምረት ችሏል፡፡ በቀጣይም የአጭር ጊዜ የምርታማነት መሳደጊያና ማነቆዎችን ማስወገጃ ፕሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ በማድረጉ የፋብሪካው የማምረት አቅም እያደገ መጥቶ በ2002ዓ.ም 1ሚሊዮን 105ሺ 596 ኩንታል ስኳር አምርቷል፡፡ ይህም ፋብሪካው ሲተከል የነበረውን የማምረት አቅም በ30% አሳድጎታል፡፡

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካእናስተ

ዋውቃችሁ

Page 15: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 15

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካየፋብሪካው አጠቃላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክት

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክት የተጀመረው በ1998ዓ.ም ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በአገዳ ልማት በኩል በዌስት ባንክ 8ሺ 300 ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት እና የኢስት ባንክ እና ነሼ አካባቢዎችን በማከል ወደ 21ሺ ሄክታር መሬት ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 7 ሺህ ሄክታር በኢስት ባንክ እንዲሁም 4ሺ 670 ሄክታር በነሼ አካባቢ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የፋብሪካውን አገዳ የመፍጨት አቅም በማሳደግ አመታዊ የስኳር ምርቱን ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል እንዲሁም ኤታኖል የማምረት አቅሙን ወደ 20 ሚሊዮን ሊትር ከፍ ለማድረግ ታቅዶ የማስፋፊያ ስራው ተካሄደ፡፡

በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 6ሺ 600 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 1ሚሊዮን 600ሺ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ስኳር የማምረት አቅም ያለው አንድ ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካ ተገንብቷል፡፡ ይህ ደግሞ ነባሩ ፋብሪካ ካለው አቅም ጋር ተዳምሮ አጠቃላይ በሁለቱም ፋብሪካዎች የሚመረተውን አመታዊ የስኳር መጠን 2ሚሊዮን 700ሺ ኩንታል ያደርሰዋል፡፡

ለመኖሪያ መንደሮችና ለፋብሪካው አገልግሎት የሚውል የኃይል አቅርቦትን

በተመለከተም ፋብሪካው በመሰረታዊነት የራሱን የኃይል ምንጭ ቀደም ሲልም በመጀመሪያው ምዕራፍ ከተተከለ ሁለት ባለ 3.5 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ያሟላ ነበር፡፡ በማስፋፊያ የተገነባው ሁለት ባለ 12 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ሲጨመርም በድምሩ 31 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለፋብሪካው እና ለመስኖ ፓምፖች እንዲሁም ለሠራተኛ መኖሪያ መንደሮች እና ለልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት 21 ሜጋ ዋት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ ቀሪው 10 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ ቋት ይገባል፡፡

አዲሱ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት የስኳር ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ በአብዛኛው ያቀፈና በቴክኖሎጂ ልቀት ከነባሩ ስኳር ፋብሪካ የተለየ ሲሆን፣ የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ ተጠናቆ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ የማምረት ሂደት ውስጥ ገብቷል፡፡ በእርሻ ማስፋፊያ ስራም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008ዓ.ም ድረስ ከ19ሺ 400 ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ ለመሸፈን ተችሏል፡፡

ፋብሪካው ለሰራተኞቹና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ከሚሰጡ አንድ ጤና ጣቢያና ስድስት ክሊኒኮች በተጨማሪ 75 አልጋዎች ያሉት ሆስፒታል አለው፡፡ እንዲሁም ከአፀደ ህጻናት ጀምሮ እስከ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ መለስተኛ

ኳስ ሜዳ፣ የመዋኛ ገንዳን ያካተተ ጂምናዝዬምና ሌሎች በርካታ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም በፋብሪካው ይገኛሉ፡፡

በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ተተግብሮ ከፍተኛ ውጤት እያስገኘ ያለው የካይዘን አመራር ፍልስፍና በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካም በልማት ቡድኖችና የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም ምርታማነትን የሚያሳድጉና ወጪን ሊቀንሱ የሚችሉ ሃሳቦችና አሰራሮች እንዲፈልቁ፣ በሠራተኛው ዘንድ የሥራ ተነሳሽነት እንዲኖር፣ ምቹና ጽዱ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር፣ የዳበረ የቡድን አሠራር እንዲቀጥል፣ የሥራ ግንኙነት እንዲጠናከር እና ለፈጠራ ሥራ ተነሳሽነት እንዲያድግ በማድረግ ለፋብሪካው ምርታማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ 13ሺ ለሚጠጉ ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት ሠራተኞች የስራ እድል የፈጠረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ መቀጠል የሚያስችለውን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ተግብሮ እና መመዘኛዎቹን አሟልቶ በመገኘቱ ISO (አይ ኤስ ኦ) 9001-2000 የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ችሏል፡፡

Page 16: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A

Ethiopiansugar.com

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ የሚመራው የልሁካን ቡድን ስኳር ፋብሪካዎችን ሲጎበኝና ውይይት ሲያካሄድ