ልሳነ ህዝብ -...

13
የሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቹ ለእሳት ሲዳርግ ሌላው ጥግ ይዞ በማየትና እንደ ኦባማ ያለ ብልጥ ደግሞ ሰራዊቱን ላለመላክ የተለያዩ ተስፋዎች በመስጠት የወያኔ መሪዎችን ያማልላል። የቻይና ጉዳይ ሲነሳ ለአሜሪካ መንግስትና ለካፒታሊስቶቹ ከባድ ራስ ምታት ከሆነ ሰንብቷል። ቻይና ከመሪያቸው ማኦ ዜዱንግ የፅንሰ ሃሳብ ክለሳ አንስቶ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮትን ከተጨባጭ ማህበራዊ መረጃና ከፖለቲካዊ ገቢራዊነት አንፃር የማያዛልቅ ነው በማለት ያው አብዮታዊውን በአዲሱ ዲሞክራሲያዊ አብዮት ቀይረው ይሰራል ባሉት መንገድ ተጉዘው መላው ዓለም በተለያዩ ጊዚያዊ ግጭቶች ተጠምዶ የጥፋትና የእልቂት ተግባር ሲያከናውን በራቸውን ለምእራባውያን ዝግ በማድረግ ማንም ባልጠበቀው መንገድ የኢኮኖሚ ልዕለ ሃያልነታቸውን አረጋገጡ። በኢኮኖሚያቸው መበልፀግና በሰው ሃይል ሃበታቸው በመጠቀም ዓለምን በሙሉ የኢንቨስትመንት መድረካቸው ለማድረግ ባወጡት ረቂቅ ስልት ምክንያት እንደነ አሜሪካ ያሉት ልዕለ ሃያል ሃገሮች የወደፊት መስፋፊያችንና የኢኮኖሚ አጋራችን ያሉዋቸውን አገሮች ቀድማ በመያዝ መጪው የአሜሪካ ተሰሚነትና ተቀባይነት ልታቀጭጭ የምትችልበት አድማስ ላይ ደርሳለች። አብዛኛዎቹ ምእራባውያን የሰጡትን ብድር ሳይቀር በራሳቸው ባለሙያና በራሳቸው ኩባንያዎች እንዲሰሩ በማድረግ ታዳጊ አገሮች በቂ ጥቅም ሳያገኙ የሚቀሩበት ሁኔታ ከማብዛቱም ሌላ የእውቀት ሽግግር እንዳይኖር እንቅፋት ነበር። ይህንን በሰፊ ጥናት ላይ የተመሰረተ ስልት ቻይና እንደ አንድ ዓለም አቀፍ ግብ በመውሰድ አገሮች በራሳቸው ሙያተኛ የሚያሰሩበትና የስራ አጥ ቁጥር የሚቀንሱበት ኢኮኖሚ ከመፍጠሯም ባሻገር የእውቀት ሽግግር እንዲኖር የሚረዳ አሰራር በመዘርጋቷ በርካታ የአፍሪካ ሃገሮች እጃቸውን ዘርግተው ሊቀበሏት መቻላቸው ለምእራባውያን ከባድ አደጋና ራስ ምታት ነው። የፕረዚደንት ኦባማ ሁለተኛው አጀንዳም ይሄ ነው። ወደዱም ጠሉም ባሁኑ ጊዜ አፍሪካን ያላካተተ ያደጉት አገሮች አካሄድ ትርጉም አልባ መሆኑን በደንብ ገብቷቸዋል። ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ ተለማማጮቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ሰው ይታዘበናል እንኳን ለማለት ልቦና አጡ ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ ሰሞኑን የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው አፍሪካን የጎበኘ በስልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ ፕረዚደንት በመሆን ሪከርድ ሰብረዋል። እንዲህ ሊሆን የቻለው የዓለም የፖለቲካ ጨዋታ በመቀየሩ ምክንያት ዋይት ሃውስ ውስጥ ቁጭ ብሎ የአፍሪካን ቀልብ መሳብ እንደማይቻል ስላመኑ እንጂ እሳቸው ከሌሎች መሪዎች በበለጠ በአፍሪካ ላይ ትኩረት አድርገዋል ማለት አይደለም። ባሁኑ ጊዜ በምስራቅ አፍሪከ ያለው የአሸባሪዎች መስፋፋት ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት አስጊ በመሆኑና እንደ ወያኔ ያለ የህዝብ ልጆችን ወደ ጦር ሜዳ ለመማገድ የማይጨነቅ መንግስት ባገራችን ስላለ የአሜሪካ ወታደሮች ሄደው ማከናወን ያለባቸውን ተግባር በኢትዮጵያውያን እንዲተካ ለማድረግና ለሚፈሰው የኛ ልጆች ደም ካሳ ይሆን ዘንድ ጥቂት ምፅዋት እንደሚቸሩን ለመናገር ነበር የሄዱት። ፕረዚደንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት በሚያማምሩ ቃላት የታጀቡ ንግግሮችን አድርገዋል። ስለ ኢትዮጵያውያን አርበኝነትና አደገኛ ተዋጊነትም መሰከሩ። ይህ በግርድፉ ሲታይ እውነትና መልካም ቢሆንም ውስጣዊ መልእክቱ ግን እናንተ አፍሪካ ቀንድ ላይ ያለውን አደጋ ተጋፈጡ የኛ ወታደሮች እዚሁ መጥተው መዋጋትና መሰዋት የለባቸውም እንደውም እናንተ በጣም ጎበዝ ተዋጊ ናችሁ የሚል መልእክት በማስተላለፍ የራሳቸውን ሰራዊት ህይወት ለመታደግና የኢትዮጵያ ሰራዊት አደራ ተቀባይ አድርገው በሚፈሰው የድሃ ልጆች ደም ለመደራደር ነበር። እሳቸው የህዝባችንን ጀግንነትና አርበኝነት እንደ አዲስ ሲመፃደቁበት እያየን ከመሳቅ ሌላ ምን ማድረግ እንችላለን? የኢትዮጵያውያን ተዋጊነትና አልበገር ባይነትማ ከዘመነ መሳፍንት አንስቶ እስከ ዘመነ ወያኔ ድረስ በመላው ዓለም የታወቀና የተመሰከረለት ነው። የወያኔ ታጋዮች ጀግንነትና አርበኝነት የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አርበኝነት ውጤት ነበር። መሪዎቹ የታገለለትን ዓላማ ጠልፈው ስርአት አልበኝነትና ሙስና የተንሰራፋበት አምባገነን ስርዓት ፈጠሩ እንጂ የወያኔ ታጋዮች ጀግንነትና አርበኝነትን መካድ ኢትዮጵያዊ ክብርን ከመፃረር ያነሰ ተግባር አይደለም። ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ፣ ከምእራብ ይምጣ ከምስራቅ ኢትዮጵያዊ ሁሉም ጀግናና በምክንያታዊነት ከተነሳ ህይወቱን ለመሰዋት ላፍታ እንኳ የማይጠራጠር አንበሳ መሆኑን ጠላትም ሆነ ወዳጅ ያውቀዋል። ፕረዚደንት ኦባማ ይህንን መድገማቸው መልካም ነገር ከመሆን አልፎ ያን ያክል የሚያስገርምና አታሞ እሚያስደልቅ ተአምር አይደለም። ፕረዚደንቱ ለምን አሁን ወደ አፍሪካ ፊታቸውን ማዞር ፈለጉ? አፍሪካ ከድሮም ያውቋታል በተማሪነታቸው ጊዜም ሄደው ዘመዶቻቸውን ከኬንያ ጠይቀዋል፤ ታዲያ ምን ተገኝቶ ነው አሁን እንደ አዲስ ነገር በስልጣን ማብቂያ ዘመናቸው አፍሪካን በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የፈለጉት? እንደ ዝግጅት ከፍላችን ትንተና ሁለት አንኳር ነገሮችን መጥቀስ እንፈልጋለን። አንደኛው ባከባቢው ያለው የአሸባሪዎች እንቅስቃሴና በዋነኛነት የኢትዮጵያን ወሳኝ ሚና ያማከለ ፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ አገራችንን በሰፊው ወደ አውደ ወጊያው እንድትገባላቸው ለመማፀንና መሪዎቻችንን ለማሳመን ነው። ሁለተኛውና ለአሜሪካ ካፒታሊዝም እንደ አንድ ካንሰር የሚታየው የቻይና በአፍሪካ መስፋፋት ነው። አሸባሪዎችን በመዋጋት ዙሪያ ሰሞኑን እንኳ በአራት ኪሎ ዊስኪ ሲፈስና ጮማ ሲቆረጥ ስንት የኢተትዮጵያ ልጆች ሞቃድሾና ሌሎች የሶማሊያ ክልሎች ውስጥ እንደተሰዉ ማሰብ ተገቢ ነው። አሸባሪነት በምንም መለኪያ ሊመታና ሊጠፋ የሚገባው የአስተሳሰብና የእምነት ንቅዘት ውጤት መሆኑን በአፅንኦት እናምናለን። በአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪነት መስፋፋት ለህዝባችንና ለጎረቤቶቻችን አደገኛ ሁኔታ ስለሆነ ሁሉም አፍሪካውያን በህብረት ሊዋጉትና ሊመክቱት ብለውም ሊደመስሱት ባለፈው እትማችን ወ/ሮ መንበረን ስለ ኢኮኖሚው ነበር የጠየቅናቸው ቀሪዎቹ ጥያቄዎች በዚሁ እትም መልስ ሰጥተውባቸዋል። ል/ህ፡- ወ/ሮ መንበረ መንግስት አሁን እየተደላደለ የመጣበት ሁኔታ ይታያል ይህ መንግስት መቼ ይወድቃል ብለው ይገምታሉ? ወ/ሮ መንበረ፡- የኛ ግብ መንግስት መገርሰስ አይደለም። ከመንግስት መውደቅ ጋር የተገናኘ ስራም አናከናውንም። እኛ ህዝቡ በሰለማዊ መንገድ እምቢ በማለት ዲሞክራሲና ፍትህ የሚያገኝበት መንገድ ማመቻቸት ነው። ያለው መንግስት ዲሞክራሲና ፍትህ ተቀብሎና አዳብሮ ከቀጠለም እሰየው። ችግሩ የአሰራር እንጂ ሰውን የመተካት ጉዳይም አይደለም። አንዳንድ ሰዎች የፖለቲካ ትግል ስልጣን መቆናጠጫ አድርገው ያስቡታል፤ እንደኔ አስተሳሰብ የህዝብ ጥቅም ማስቀደም ከቻለ ማንም ሰው ስልጣን ላይ መውጣት የሚችለው በmerit መሆን አለበት። ል/ህ፡- ለምሳሌ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የወያኔ መሪዎች ከስህተታችን ተምረናልና የጎደሉንን አርመን ወደፊት ዲሞክራሲና ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ የሰሞኑ የኦባማ ድራማ ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል የምርጫ ታዛቢ ሊሆኑ የነበሩት ለስደት ተዳረጉ። ከወ/ሮ መንበረ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ—ክፍል ፪ ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ ልሳነ ህዝብ ድምፅ ለተነፈጉት የቆመ ልሳን ነሐሴ 2/2015 ቅፅ 1 ቁጥር 12 በዚህ ዕትም 1. የሰሞኑ የኦባማ ድራማ 2. የወ/ሮ መንበረ ቃለ ምልልስ ክፍል ፪ 3. የደ/ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ምዝበራ 4. ንጉስ ዓምደፅዮን /ታሪክ/ 5. ኦባማ ክፉኛ ተተቹ 6. ዕርቅና ሰላም 7. ግጥሞች 8. የፕሮፌሰር ዓለማየሁ ፅሁፍ 9. አንዳርጋቸው ፅጌ 10. ዜናዎች እንዲሁም ሌሎች ዘገባዎች የሳምንቱ ምርጥ ግጥሞች ስጋና ነፍስ ምግብ ካፈር በቅሎ ከድስት ተቀቅሎ ያመ ያም ተቀላቅሎ በጥርስ ተፈጭቶ ባንጀት ተላምቶ ገላ ባሻው መንገድ ጉበት ሳምባ ሰርቶ ወደ ደም ስር ገብቶ ያንጎል ሴል ተክቶ አጥንትን ገንብቶ ካፈርና ካፈር የተሰራ ገላ ተፈጥሮው ነውና ደቼ አፈር ቢበላ ምኑ ያስገርማል መመለስ ወዳፈር በመጥፎነት እንጂ በነፍስ ሞት ማፈር ነበስያ ሳትቆሽሽ ስጋ ብትጠፋ ዘላለም ትከብራለች ህያው ታሪክ ፅፋ አባ ዘወንጌል ዘአንገረብ ገብረክርስቶስ ደስታ “አለ በውስጣችን … እውነት ፍፁም ሆና የምታበራበት ደግሞም ማወቅ ማለት ከውጭ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ ከውስጥ ያለውን እንዲበራ ማድረግ” ሹመት። (ውስጠቀ፡ ግጥም፡) ካላጨበጨቡ፡ ወይ፡ ካልቸበቸቡ፡ ወይም፡ ካልሰረቱ፡ ወይ፡ ካላሰረቱ፡ ወይ፡ ካላሳበቱ፡ ማ፡ ለማ፡ ያቀምሳል፡ ከዚያ፡ ከሱረቱ? ባሻ አሸብር በአሜሪካ (የፖለቲካ እስረኛ ግጥሞች) | ከመንግስቱ ለማ | ታተመ 1967 ገጽ 5 የመልካም አስተዳደር፣ የዲሞክራሲና የፍትህ እጦት ውጤቱ ስደት ነው

Upload: others

Post on 29-Oct-2019

67 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

የሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

የሚቆጠሩ ዜጎቹ ለእሳት ሲዳርግ ሌላው ጥግ

ይዞ በማየትና እንደ ኦባማ ያለ ብልጥ ደግሞ

ሰራዊቱን ላለመላክ የተለያዩ ተስፋዎች

በመስጠት የወያኔ መሪዎችን ያማልላል።

የቻይና ጉዳይ ሲነሳ ለአሜሪካ መንግስትና

ለካፒታሊስቶቹ ከባድ ራስ ምታት ከሆነ

ሰንብቷል። ቻይና ከመሪያቸው ማኦ ዜዱንግ

የፅንሰ ሃሳብ ክለሳ አንስቶ ብሄራዊ

ዲሞክራሲያዊ አብዮትን ከተጨባጭ ማህበራዊ

መረጃና ከፖለቲካዊ ገቢራዊነት አንፃር

የማያዛልቅ ነው በማለት ያው አብዮታዊውን

በአዲሱ ዲሞክራሲያዊ አብዮት ቀይረው

ይሰራል ባሉት መንገድ ተጉዘው መላው ዓለም

በተለያዩ ጊዚያዊ ግጭቶች ተጠምዶ የጥፋትና

የእልቂት ተግባር ሲያከናውን በራቸውን

ለምእራባውያን ዝግ በማድረግ ማንም

ባልጠበቀው መንገድ የኢኮኖሚ ልዕለ

ሃያልነታቸውን አረጋገጡ። በኢኮኖሚያቸው

መበልፀግና በሰው ሃይል ሃበታቸው በመጠቀም

ዓለምን በሙሉ የኢንቨስትመንት መድረካቸው

ለማድረግ ባወጡት ረቂቅ ስልት ምክንያት

እንደነ አሜሪካ ያሉት ልዕለ ሃያል ሃገሮች

የወደፊት መስፋፊያችንና የኢኮኖሚ አጋራችን

ያሉዋቸውን አገሮች ቀድማ በመያዝ መጪው

የአሜሪካ ተሰሚነትና ተቀባይነት ልታቀጭጭ

የምትችልበት አድማስ ላይ ደርሳለች።

አብዛኛዎቹ ምእራባውያን የሰጡትን ብድር

ሳይቀር በራሳቸው ባለሙያና በራሳቸው

ኩባንያዎች እንዲሰሩ በማድረግ ታዳጊ አገሮች

በቂ ጥቅም ሳያገኙ የሚቀሩበት ሁኔታ

ከማብዛቱም ሌላ የእውቀት ሽግግር እንዳይኖር

እንቅፋት ነበር። ይህንን በሰፊ ጥናት ላይ

የተመሰረተ ስልት ቻይና እንደ አንድ ዓለም

አቀፍ ግብ በመውሰድ አገሮች በራሳቸው

ሙያተኛ የሚያሰሩበትና የስራ አጥ ቁጥር

የሚቀንሱበት ኢኮኖሚ ከመፍጠሯም ባሻገር

የእውቀት ሽግግር እንዲኖር የሚረዳ አሰራር

በመዘርጋቷ በርካታ የአፍሪካ ሃገሮች እጃቸውን

ዘርግተው ሊቀበሏት መቻላቸው ለምእራባውያን

ከባድ አደጋና ራስ ምታት ነው። የፕረዚደንት

ኦባማ ሁለተኛው አጀንዳም ይሄ ነው። ወደዱም

ጠሉም ባሁኑ ጊዜ አፍሪካን ያላካተተ ያደጉት

አገሮች አካሄድ ትርጉም አልባ መሆኑን በደንብ

ገብቷቸዋል።

ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ

ተለማማጮቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ሰው ይታዘበናል እንኳን

ለማለት ልቦና አጡ ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ

ሰሞኑን የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ

የመጀመሪያው አፍሪካን የጎበኘ በስልጣን ላይ

ያለ የአሜሪካ ፕረዚደንት በመሆን ሪከርድ

ሰብረዋል።

እንዲህ ሊሆን የቻለው የዓለም የፖለቲካ

ጨዋታ በመቀየሩ ምክንያት ዋይት ሃውስ

ውስጥ ቁጭ ብሎ የአፍሪካን ቀልብ መሳብ

እንደማይቻል ስላመኑ እንጂ እሳቸው ከሌሎች

መሪዎች በበለጠ በአፍሪካ ላይ ትኩረት

አድርገዋል ማለት አይደለም።

ባሁኑ ጊዜ በምስራቅ አፍሪከ ያለው

የአሸባሪዎች መስፋፋት ለአሜሪካ ብሄራዊ

ደህንነት አስጊ በመሆኑና እንደ ወያኔ ያለ

የህዝብ ልጆችን ወደ ጦር ሜዳ ለመማገድ

የማይጨነቅ መንግስት ባገራችን ስላለ

የአሜሪካ ወታደሮች ሄደው ማከናወን

ያለባቸውን ተግባር በኢትዮጵያውያን

እንዲተካ ለማድረግና ለሚፈሰው የኛ ልጆች

ደም ካሳ ይሆን ዘንድ ጥቂት ምፅዋት

እንደሚቸሩን ለመናገር ነበር የሄዱት።

ፕረዚደንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ሁልጊዜ

የሚጠቀሙበት በሚያማምሩ ቃላት የታጀቡ

ንግግሮችን አድርገዋል። ስለ ኢትዮጵያውያን

አርበኝነትና አደገኛ ተዋጊነትም መሰከሩ። ይህ

በግርድፉ ሲታይ እውነትና መልካም ቢሆንም

ውስጣዊ መልእክቱ ግን እናንተ አፍሪካ ቀንድ

ላይ ያለውን አደጋ ተጋፈጡ የኛ ወታደሮች

እዚሁ መጥተው መዋጋትና መሰዋት

የለባቸውም እንደውም እናንተ በጣም ጎበዝ

ተዋጊ ናችሁ የሚል መልእክት በማስተላለፍ

የራሳቸውን ሰራዊት ህይወት ለመታደግና

የኢትዮጵያ ሰራዊት አደራ ተቀባይ አድርገው

በሚፈሰው የድሃ ልጆች ደም ለመደራደር

ነበር።

እሳቸው የህዝባችንን ጀግንነትና አርበኝነት

እንደ አዲስ ሲመፃደቁበት እያየን ከመሳቅ ሌላ

ምን ማድረግ እንችላለን? የኢትዮጵያውያን

ተዋጊነትና አልበገር ባይነትማ ከዘመነ

መሳፍንት አንስቶ እስከ ዘመነ ወያኔ ድረስ

በመላው ዓለም የታወቀና የተመሰከረለት

ነው። የወያኔ ታጋዮች ጀግንነትና አርበኝነት

የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አርበኝነት ውጤት

ነበር። መሪዎቹ የታገለለትን ዓላማ ጠልፈው

ስርአት አልበኝነትና ሙስና የተንሰራፋበት

አምባገነን ስርዓት ፈጠሩ እንጂ የወያኔ

ታጋዮች ጀግንነትና አርበኝነትን መካድ

ኢትዮጵያዊ ክብርን ከመፃረር ያነሰ ተግባር

አይደለም። ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ፣

ከምእራብ ይምጣ ከምስራቅ ኢትዮጵያዊ

ሁሉም ጀግናና በምክንያታዊነት ከተነሳ

ህይወቱን ለመሰዋት ላፍታ እንኳ

የማይጠራጠር አንበሳ መሆኑን ጠላትም ሆነ

ወዳጅ ያውቀዋል። ፕረዚደንት ኦባማ ይህንን

መድገማቸው መልካም ነገር ከመሆን አልፎ

ያን ያክል የሚያስገርምና አታሞ እሚያስደልቅ

ተአምር አይደለም።

ፕረዚደንቱ ለምን አሁን ወደ አፍሪካ

ፊታቸውን ማዞር ፈለጉ? አፍሪካ ከድሮም

ያውቋታል በተማሪነታቸው ጊዜም ሄደው

ዘመዶቻቸውን ከኬንያ ጠይቀዋል፤ ታዲያ

ምን ተገኝቶ ነው አሁን እንደ አዲስ ነገር

በስልጣን ማብቂያ ዘመናቸው አፍሪካን

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት

የፈለጉት?

እንደ ዝግጅት ከፍላችን ትንተና ሁለት አንኳር

ነገሮችን መጥቀስ እንፈልጋለን። አንደኛው

ባከባቢው ያለው የአሸባሪዎች እንቅስቃሴና

በዋነኛነት የኢትዮጵያን ወሳኝ ሚና ያማከለ

ፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ አገራችንን በሰፊው ወደ

አውደ ወጊያው እንድትገባላቸው ለመማፀንና

መሪዎቻችንን ለማሳመን ነው። ሁለተኛውና

ለአሜሪካ ካፒታሊዝም እንደ አንድ ካንሰር

የሚታየው የቻይና በአፍሪካ መስፋፋት ነው።

አሸባሪዎችን በመዋጋት ዙሪያ ሰሞኑን እንኳ

በአራት ኪሎ ዊስኪ ሲፈስና ጮማ ሲቆረጥ

ስንት የኢተትዮጵያ ልጆች ሞቃድሾና ሌሎች

የሶማሊያ ክልሎች ውስጥ እንደተሰዉ ማሰብ

ተገቢ ነው። አሸባሪነት በምንም መለኪያ

ሊመታና ሊጠፋ የሚገባው የአስተሳሰብና

የእምነት ንቅዘት ውጤት መሆኑን በአፅንኦት

እናምናለን። በአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪነት

መስፋፋት ለህዝባችንና ለጎረቤቶቻችን አደገኛ

ሁኔታ ስለሆነ ሁሉም አፍሪካውያን በህብረት

ሊዋጉትና ሊመክቱት ብለውም ሊደመስሱት

ባለፈው እትማችን ወ/ሮ መንበረን ስለ

ኢኮኖሚው ነበር የጠየቅናቸው ቀሪዎቹ

ጥያቄዎች በዚሁ እትም መልስ

ሰጥተውባቸዋል።

ል/ህ፡- ወ/ሮ መንበረ መንግስት አሁን

እየተደላደለ የመጣበት ሁኔታ ይታያል ይህ

መንግስት መቼ ይወድቃል ብለው

ይገምታሉ?

ወ/ሮ መንበረ፡- የኛ ግብ መንግስት መገርሰስ

አይደለም። ከመንግስት መውደቅ ጋር

የተገናኘ ስራም አናከናውንም። እኛ ህዝቡ

በሰለማዊ መንገድ እምቢ በማለት

ዲሞክራሲና ፍትህ የሚያገኝበት መንገድ

ማመቻቸት ነው። ያለው መንግስት

ዲሞክራሲና ፍትህ ተቀብሎና አዳብሮ

ከቀጠለም እሰየው። ችግሩ የአሰራር እንጂ

ሰውን የመተካት ጉዳይም አይደለም።

አንዳንድ ሰዎች የፖለቲካ ትግል ስልጣን

መቆናጠጫ አድርገው ያስቡታል፤ እንደኔ

አስተሳሰብ የህዝብ ጥቅም ማስቀደም ከቻለ

ማንም ሰው ስልጣን ላይ መውጣት

የሚችለው በmerit መሆን አለበት።

ል/ህ፡- ለምሳሌ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት

የወያኔ መሪዎች ከስህተታችን ተምረናልና

የጎደሉንን አርመን ወደፊት ዲሞክራሲና

ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ

የሰሞኑ የኦባማ ድራማ

ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል የምርጫ ታዛቢ ሊሆኑ የነበሩት ለስደት ተዳረጉ። ከወ/ሮ መንበረ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ—ክፍል ፪

ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ

ልሳነ ህዝብ ድምፅ ለተነፈጉት የቆመ ልሳን

ነ ሐ ሴ 2 / 2 0 1 5 ቅ ፅ 1 ቁ ጥ ር 1 2

በዚህ ዕትም

1. የሰሞኑ የኦባማ ድራማ 2. የወ/ሮ መንበረ ቃለ ምልልስ ክፍል ፪ 3. የደ/ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ምዝበራ 4. ንጉስ ዓምደፅዮን /ታሪክ/ 5. ኦባማ ክፉኛ ተተቹ 6. ዕርቅና ሰላም 7. ግጥሞች 8. የፕሮፌሰር ዓለማየሁ ፅሁፍ 9. አንዳርጋቸው ፅጌ 10. ዜናዎች

እንዲሁም ሌሎች ዘገባዎች

የሳምንቱ ምርጥ ግጥሞች

ስጋና ነፍስ ምግብ ካፈር በቅሎ ከድስት ተቀቅሎ ያመ ያም ተቀላቅሎ በጥርስ ተፈጭቶ ባንጀት ተላምቶ ገላ ባሻው መንገድ ጉበት ሳምባ ሰርቶ ወደ ደም ስር ገብቶ ያንጎል ሴል ተክቶ አጥንትን ገንብቶ ካፈርና ካፈር የተሰራ ገላ ተፈጥሮው ነውና ደቼ አፈር ቢበላ ምኑ ያስገርማል መመለስ ወዳፈር በመጥፎነት እንጂ በነፍስ ሞት ማፈር ነበስያ ሳትቆሽሽ ስጋ ብትጠፋ ዘላለም ትከብራለች ህያው ታሪክ ፅፋ አባ ዘወንጌል ዘአንገረብ

ገብረክርስቶስ ደስታ “አለ በውስጣችን …

እውነት ፍፁም ሆና የምታበራበት ደግሞም ማወቅ ማለት

ከውጭ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ ከውስጥ ያለውን እንዲበራ ማድረግ”

ሹመት። (ውስጠቀ፡ ግጥም፡)

ካላጨበጨቡ፡ ወይ፡ ካልቸበቸቡ፡ ወይም፡ ካልሰረቱ፡ ወይ፡ ካላሰረቱ፡ ወይ፡ ካላሳበቱ፡

ማ፡ ለማ፡ ያቀምሳል፡ ከዚያ፡ ከሱረቱ?

ባሻ አሸብር በአሜሪካ (የፖለቲካ እስረኛ ግጥሞች) | ከመንግስቱ ለማ | ታተመ 1967

ገጽ 5

የመልካም አስተዳደር፣ የዲሞክራሲና የፍትህ

እጦት ውጤቱ ስደት ነው

Page 2: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

“To catch the reader's attention, place an

interesting sentence or quote from the story

here.”

ከወ/ሮ መንበረ ... ከገፅ ፩ የዞረ

ፍትህ እናሰፍናለን ቢሉ ተቀባይነት ያገኛሉ?

ወ/ሮ መንበረ፡ ይህ የአመለካከት ጉዳይ ነው።

ዋና ግብ ፍትህና ዲሞክራሲ ማስፈን ከሆነ

እንኳንስ የራሳች ዘርና ዜጎች የሆኑ ሰዎች

ሌላም ይዞ ቢመጣ በመልካም ጎኑ ከማየት

በስተቀር ሌላ አማራጭ ያለን አይመስለኝም።

እነዚህ ሰዎችኮ እጅግ በጣም የካበተ

ወታደራዊና ፖለቲካዊ ልምድ ያላቸው

ናቸው። እነዚህ ጎደሎአችንን አርመን ለሌሎች

ኢትዮጵያውያንም በሚፈልጉት አስተሳሰብ

ወደ ህዝብ ዘልቀው ማስተማርና ሰላማዊ

የፖለቲካ ውድድር እንዲካሄድ እውነተኛ

ፍላጎት አለን ቢሉ ላገራችንም ሆነ ለህዝባችን

እጅግ በጣም መልካም ነው።

የፍትህና የዲሞክራሲ መታጣት ከተወገደ

ሃገራችን ወደ መልካም አስተዳደርና ወደ

ብልፅግና የማትጓዝበት ምክንያት

አይታየኝም።

ል/ህ፡ የብሄር ብሄረሰብ መብት የሚለው

የወያኔ አስተሳሰብ እንዴት ያዩታል?

ወ/ሮ መንበረ፡ አስተሳሰቡን መተቸት

አልፈልግም። ባጠቃላይ ግን ባገራችን በርካታ

ብሄርና ብሄረሰቦች አሉ፡ እነሱ ባህላቸውንና

ማንነታቸውን አክብረው በሰላምና

በመከባበር መኖር የሚችሉበት ስርዓት

መፍጠር በራሱ መልካም እንጂ ጎጂ

አይደለም። ይህ አስተሳሰብ በሰለጠኑት

ሃገሮችም ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ነው።

ብሄር ብሄረሰብ የሚለው ሃረግ ህዝብና

ህዝብ ለማራራቅና ለማለያየት

እስካልተጠቀምንበት ድረስ የሰዎች ማንነት

መቀበልና ማክበር ተገቢና መልካም ነገር

ነው።

ል/ህ፡ የብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ

ከመወሰን አንስቶ እስከ መገንጠል

የሚደነግገው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት

አንቀፅ 39ን እንዴት ያዩታል?

ወ/ሮ መንበረ፡ በመጀመሪያ የብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ መወሰን መብት ለድርድር የማይቀርብ መብት ነው። በግልባጩ ስትመለከተው አማራጭ የሌለው ስለሆነ። የብሄር ብሄረሰቦች መብት እራሳቸው ካልወሰኑ ማን ይወስንላቸው የሚለው ከባድ ጥያቄ መልስ የለውም። እንደ ግለሰብ እንኳ የራሴን መብት እራሴ ካልወሰንኩ ማን ነው የሚወስንልኝ? ከዚህ አንፃር ስታየው ጥያቄው በምንም ስህተት ለድርድር አይቀርብም ማለት ነው። አንቀፅ 39 በህገ መንግስቱ ባይኖር መልካም ነው። መኖሩ ደግሞ የሚፈጥረው ያን ያህል የተጋነነ ነገር ሊኖር አይችልም። ሰዎች ወይም ብሄረሰቦች የመገንጠል ጥያቄ ካላቸው አንቀፁ ቢኖርም ባይኖርም ጥያቄውን ማንሳታቸው አይቀርም። ሃሳቡ ወደ ህግነት ስለተቀየረ አንዳንድ ብሄረሰቦች እንዲገነጠሉ ምክንያት ይሆናል የሚል የአንዳንድ ሰዎች አስተሳሰብ ትክክለኛ አይደለም። እንደውም አንድን ህዝብ እኔን በገባኝ መልኩ ሊገባው አይችልም ብሎ ማሰብ በራሱ ለራስ ከሚሰጥ የተሳሳተ ግምት የሚመነጭና የሌሎችን አስተሳሰብ አሳንሶ የሚያይ አደገኛ አመለካከት ነው። ብሄር ብሄረሰቦች የአንድነት ጥቅም በመረዳት አብረው እንዲኖሩ ይጥራሉ እንጂ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄዳሉ ብሎ ማመን ለኔ አይመቸኝም። በዓለማችን የተገነጠሉ ሃገሮች ብዙዉን ጊዜ በማይወጡት ሁከትና ውድቀት ላይ እንዳሉ እያየና እየሰማ በ21ኛ ክፍለ ዘመን እገነጠላለሁ የሚል ህዝብ ይኖራል ብዬ አላምንም፡ በተለይ ባገራችን ተጨባጭ ሁኔታ። ል/ህ፡- በስተመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልእክት አለ? ወ/ሮ መንበረ፡- ማስተላለፍ የምፈልገው ነገር

አንድና አንድ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችንን ወደ መልካም መንገድ የሚያወጣ ዘዴና መላ መቀየስና በሰላማዊ መንገድ ባለው መንግስት ላይ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣና ተቃዋሚዎችም በሰላማዊ መንገድ ገብተው ህዝባቸውን የሚያስተምሩበትና ያገራችንን ሃብት እኩል ተጠቃሚ የሆነ ህዝብ የሚፈጥሩበትን ስርዓት ለማነፅ መስራት አለብን። እንደዚያ እሰካደረግን ድረስ ደግሞ ለውጥ መታየቱ የማይቀር ነው። እዚህ ውጭ አገር አንዳንድ ሰዎች በፖለቲካ ተቃውሞ ስም ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥላላት ስራ ሲሰሩ በየድረ ገፁ ታያለህ። እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ላገራችን አደገኛና ወደከፋ ሁኔታ የሚገፋት መርዝ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ምናልባትም እንደዚህ የሚያደርጉ ሰዎች ያገራችን ታሪካዊ ጠላቶች በኛ ስም እያሉት ሊሆኑ ይችላሉ። እንደዚያ ከሆነም ነቅተን መጠበቅ ይገባናል። ሃገራችን በሰላም ውላ ካደረችልን ችግሮቿን መፍታት እንችላለን። እንደዚያ ማድረግ በእውነት ላገሩ ከሚያስብ ዜጋ ህሊና ይመነጫል። በስተማጠቃለያ ደግሞ መፅሄታችሁ ያን ያህል ክብር ሰጥቶ ቃለ መጠይቅ ስለጠየቀኝ በጣም አመሰግናለሁ። ል/ህ፡- በአንባቢዎችና በዝግጅት ክፍላችን ስም ከለልብ አመሰግንዎታለን። በሌላ ቃለ ምልልስ እስከምንገናኝ ድረስም ቸር እንሰንብት። የኦባማ ... ከገፅ 1 የዞረ ቻይና በበርካታ የአፍሪካ ሃገሮች የልማትና የኢንቨስትመንት ውሎችን በማከናወን በነዳጅ ፍለጋ፣ በመዓድን ስራ፣ መንገድ ግንባታ፣ ኦርሻና ኢንዳስትሪያላይዜሽን ዘርፍ በስፋት ተሰማርታለች። የቻይና የግንባታና የጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት ከጠራት አንፃር ሲታይ በርካታ ቅሬታዎች የሚነሱ ቢሆን ሌሎች ጥቅሞቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት በርካታ ሃገሮች ከአሜሪካና ካደጉት ሌሎች ምዕራባውያን የበለጠ ከቻይና ጋር የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲኖራቸው ይመርጣሉ። ይህ የቻይና ተስፋፊነት ለአሜሪካ የወደፊት ግንኙነት በጣም አስጊና እንቅፋት እንደሆነ ይነገራል። ይህ ተጨባጭ ዓለም አቀፋዊ እውነታ ነው የአሜራካ ፕረዚደንት አፍሪካን አንዲጎበኝ ያስገደደው፡ ስለዚህ ጉብኝቱ ለአሜሪካ እንጂ ለአፍሪካ ጥቅም በማሰብ የተከናወነ አይደለም። በጉብኝቱ ሂደት በጣም የሚያሳፍረው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ህፃናዊ ባህሪይ ነው። ፕረዚደንቱን ለማየት ከሚያሳዩት ፕሮቶኮል የጎደለው ግፊያ ጀምሮ የሚያሳዩት ገደብ ያለፈና ያለቦታው የሆነ ግልፈጣ ያሳፍራል። ከአውሮፕላን ወርዶ ደነሱ የሚጣውን ፕረዚደንት ለማየት እርስ በርስ እየተጋፉ ወደፊት መውጣት “ሁሊም በየቤቱ ትልቅ ነው” የሚለው የመይሳው ካሳን ንግግር ያቀጨጨ ነበር ቢባል የተጋነነ አይሆን። እዚሁ ሰሜን አሜሪካ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት ታዋቂ አርቲስት ሲመጣ እሱን ለማየት እንደሚሆኑት ሁሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም አእረርስ በርሳቸው እየተጋፉ የኦባማ ከአውሮፕላን መውረድ ሲመለከቱ ማየት ክብረ ነክ ነው። ዘጠና ሚሊዮን ህዝብን ወክለው በህዝባችን ስም እዚያ መቆማቸውን በጭራሽ መርሳት የለባቸውም። ባለስጣኖቻችን ስለ ፕሮቶኮል እውቀተቱ ቢኖራቸው እንዲህ ባልሆኑ ነበር። ፕረዚደንት ኦባማ የጃፓኑን መሪ በሁለት እጆቻቸው ጎንበስ በብለው ሰላምታ በመስጠታቸው የአመሪካ ቤሄራዊ ክብር የመሚነካ ነው በማለት ህዝቡና መገናኛ ብዙሃን እንዴት እንደወሳቸው ማስታወስ ተገቢ ነው። የኢተትዮጵያ ህዘብ በስፋት ተንቀሳቅሶ ያከናወናቸው የጤናና የእርሻ ዕድገቶችም

በሙሉ የአሜሪካ ውጤት አስመስለው ፕረዚደንቱ ሲገልፁት እሱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ትክክል እንዳልሆነ በማስረዳት ፈንታ አሜሪካ ባትረዳን አንድ ኩንታል እህል ማምረት የማንችል ወባም መቆጣጠር የየማንችል አስመስሎ መናገር በጣም አሳፋሪና የህዝባችንን ዕይታ በዓለም ዘንዳ ለማኝ ያስመሰለ ድርጊት ነው። አሜሪካ ለወባ መቆጣጠሪያ የተወሰነ ድጋፍ አደረገች እንጂ ስራው የተሰራው ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ አእርዳታ አይደለም። ፕረዚደንቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኝ የግለሰብ የምግብ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ሳይቀር አመሪካ የተከለቺው አስመስሎ ለመላው ዓለም ማሳየት በጣም አሳፋሪና ከሁሉም በላይ ደግሞ ከእውነታ የራቀ ነው። ወደፊት በዚሁ ዙሪያ አርማቶ ማከናወን ተገቢ ነው በማለት ሃተታችንን አእንዘጋለን።

የምርጫ ታዛቢው በካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀ

ቃለ መጠይቅ ለማከናወን ፈቃደኛ አይደለም

ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ

ባለፈው ቅፅ 1 ቁጥር 11 እትማችን ላይ

ባወጣነው ሃተታ ወያኔ ኢህአዴግ በርካታ

ሰዎች ፓርቲያቸውን በመወከል ያለፈው አገር

አቀፍ ምርጫ ታዛቢና ዕጩ ተመራጭ

በመሆናቸው ለእስር ለስቃይና ለመጥፋት

የተዳረጉ ሰዎች ስም ዝርዝር አውጥተን

እንደነበር ይያወሳል።

በወቅቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደነበረ

ያላወቅነውና መታሰሩ ብቻ የተዘገበው በአዲስ

አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ

የምርጫ ታዛቢ እንዲሆን በመመረጡ

ምክንያት ታስሮና ተሰቃይቶ በዋስ የተለቀቀው

መንግስቱ ቢፍቱ ከነቤተሰቡ በካናዳ የፖለቲካ

ጥገኝነት መጠየቁ ታወቀ።

ካናዳ ከሚገኙ ምንጮቻችን ኢንፎርሜሽኑ

የደረሰው ዘገጋቢያችን ቶሮንቶ ካናዳ ደውሎ

አቶ መንግስቱን በስልክ ሊያነጋግረው

ቢሞክርም አቶ መንግስቱ ቃለ ምልልስ

ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም።

ዝግጅት ክፍላችን ሰዎች ለምን ቃለ መጠይቅ

ለማድረግ ፈቃደኛ እንደማይሆኑ በቂ ግንዛቤ

ያለው ስለሆነ ዜናውን በዚሁ ሁኔታ ለህዝብ

ይፋ እንዲሆን ወሰነ።

ክቡራን አንባቢዎቻቸን በቀጣይ ተደጋጋሚ

ሙከራ በማድረግ አቶ መንግስቱ ቃለ ምልልስ

ከሰጠን ቃለ ምልልሱን ይዘን የምንቀርብ

መሆናችንን በትህትና እንገልፃለን።

ኢህኣዴጎች ባገኙት ኣጋጣሚ ሁሉ ስለመለስ

ያወራሉ። ወደው እንዳይመስላቹ። ሌላ

የሚግባቡበት ነጥብ ስለሌላቸው ነው።

የመበታተን ኣደጋ ሲደቀንባቸው ስለ ‘መለስ

ራእይ’ (ምን ዓይነት ራእይ መሆኑ ባያውቁቱም)

ይተርካሉ።

ኣሁን ኣሁን ተቃውሞ ሲያይልባቸው የ ‘መለስ

ታሪክ’ ደጋግሞ ከማውራት የበለጠ ኣማራጭ

ኣላገኙም። ለዚህ ሲባል ታድያ በቅርቡ (ከሁለት

ቀናት በፊት) ‘የመለስን ታሪክ የሚያጎድፉ ሰዎች

በመከላከል የመለስን ታሪክ መገንባት’

በሚቻልበት ጉዳይ ኣጥንቶ የሚያከናውን ኮሚቴ

(ወይ ግብረ ሃይል) በኢህኣዴግ ደረጃ

ተቋቁሟል።

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 2

የህዝብ ቁጣ

የስደት አስከፊ ገፅታ

ይህ ሰቆቃ መቼ ያብቃ?

የህሊና እስረኛው አብርሃም ደስታ

Page 3: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

የግጥም መዓድ በድን ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ፊት ለፊትህ ሰው ጠኔ ይዞት በቁንጣን እያገሳህ ልብህ ቢደነድን፣ ለተራበው አዝነህ ባትመግበው አንተ የኖርክ ቢመስልህም ነህ በድን። አንተ ቪላ ውስጥ ተንሰራፍተህ ወገንህ መንገድ ላይ ወድቆ ልብህ ቢደነድን፣ በሰብዓዊ ርህራሄ አዝንህለት ባታስጠጋው፣ አንተ ያለህ ቢመስልህም፣ የለህም ነህ በድን። ህልቆመሳፍርቱ አለአግባብ ሲታሰር፣ ሲገደል፣ ጉዳዬ አይደለም፣ ብለህ ልብህ ቢደንድን፣ እስራት፣ ግድያውን ያለፍርሃት ባትቃወም፣ ያልሞትክ ቢመስልህም፣ ሞተህ ሆነሃል በድን። አቅመኛ ደካማውን ሲዘርፈው እኔ ምንግዴ ብለህ ልብህን ብታደነድን፣ አንት በሕይወት ያለህ ቢመስልህም፣ ከድንጋይ የባስክ ሆነሃል በድን። አበሳና ሮሮ በዝተው ጠፈር ነክተው አይመለከተኝም ብለህ ልብህን ብታደነድን፣ አንተ የቆምክ ቢምስልህም፣ ወኔህን ተሰልበህ ሆነሃል በድን። ፍትህና ርት ሲጎሉና ጭቆና ሲገን፣ ምን ቸገረኝ ብለህ ልብህ ቢደነድን፣ አንተ ነፍስ ያለህ ቢመስልህም፣ ነፍስ የለህም ሆነሃል በድን። ወገኖችህ ሲዋረዱ፣ ሲደፈሩ፣ ሬሳቸው ባደባባይ ሲጎተት፣ አያገባኝም ብለህ ልብህ ቢደነድን፣ አንተ እስትንፋስ አለኝ ብትልም፣ ደርቀሃል አንደ እንጨት፣ ሆነሃል በድን። አገርህ በእብሪተኞች እየተገዘገዘች፣ እየጎረፋት የደም አበላ ልብህ ቢደነድን፣ አንተ እንቀሳቀሳለሁ ብትልም፣ የቁም-ሙት ነህ ሆነሃል በድን።

ህዝብህ ብሶቱን እንዳይገልጽ አፉን ተለጉሞ፣ ጉዳዩ ነው፣ ብለህ ልብህ ቢደነድን፣ እመነኝ ፍጹም የለህም በሕይወት፣ እሬሳህ ነው የሚላወስ፣ ሆነሃል በድን። የትውልድህ ስፍራ እስር ቤት ሆና፣ ያገርህ ልጆች እስር ቤት ሲማቅቁ ልብህ ቢደነድን፣ መቃብር ውስጥ ነው ያለኽው፣ አጽምህ ረግፎ ሆነሃል በድን።

ቅርስህ፣ ኃይማኖትህና ታሪክህ እየወደመ ቅርስህን፣ ኃይማኖትህን፣ ታሪክህን ባታድን፣ የምድርህ ደብዛ ሲጠፋ ልብህን ብታደነድን፣ አልሞትኩም ብለህ አትዋሽ፣ ተዘርረህ ሆነሃል በድን። ካብራኩ የወጣኸው ሰውህ ድረስልኝ እያለ፣ የቁምስቅሉን ሲያይ ልብህ ቢደነድን፣ ካንተ ይልቅ ሽል ሆኖ የቀረው ይሻላል፣ መንፈስ፣ አካልህ ደንዞ ነህ በድን። ሰቆቃ፣ ዋይታ፣ እሪታ ምስኪኖቹ ላይ ተንሰራፍቶ፣ እምባና ደማቸውን ተራምደህ ልብህን ብታደነድን፣ እኔ እስካልተነካሁ ምን ዶሎኝ ብትል፣ ባትቆጣ፣ ባታምጽ፣ ለወገንህ ባትሆን መድን፣ አሁንስ በዛ! አሻፈረኝ! ባትል፣ ካንተ ይብስ የሞተ፣ የለም ካንት ይብስ በድን። ሌላው ቢቀር ሽንጥህን ገትረህ፣ ለውነትና ለፍትህ ሳትቆም፣ ልብህን ብታደነድን፣ ከራስ በላይ ንፋስ ብትል፣ ፍጹም ባይሰጥህ ግድን፣ ከመሬት በታች ድሮ በስብሰሃል፣ ህያው የሆንክ ቢመስልህም ነህ የበድን በድን። ደሞም እወቀው፣ በደልንና ግፍን ለማድረግ በቀጥታ ባትሳተፍም፣ በጅ አዙር በደልን እንደምትደግፍ፣ ዝም ብለህ ግድ ሳይልህ በማየትህ ብቻ፣ ግብረአበር እንደሆንክ ከግፈኞችና ግፍ።

ዳንኤል ነጋሽ በካናዳ

የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀ ከምስረታው ጀምሮ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ አባል

የነበረውና ከጣልያን ወደ ኢትዮጵያ እንደሄደ በመንግስት

ታስሮና ተሰቃይቶ በዋስ ከተፈታ በሁዋላ ካናዳ የገባው

ዳንኤል ነጋሽ በካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ማመልከቻ

ማቅረቡን ምንጮቻችን ከካናዳ ዘግበዋል።

ወጣቱ ምሁር ዳንኤል በቅንጅት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን

መንግስት ሲቃወም ከቆየ በሁዋላ አንድነት ለዲሞክራሲና

ለፍትህ ፓርቲም ከምስረታው ጀምሮ በአባልነት መቀላቀሉ

ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

ለትምህርት በሄደበት በሮም ኢጣሊያ በነበረበት ወቅት

ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ ያደርግ እንደነበርና በሰላማዊ

ሰልፎች ላይም የመሪነት ሚና ይጫወት እንደነበር ለማወቅ

ተችሏል።

ዳንኤል በአያቱ መሞት ምክንያት ከሮም ወደ አዲስ አበባ

ለቀብር እንደሄደ ብዙም ሳይቆይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር

ውሎ በማዕከላዊ እስር ቤት ከተሰቃየ በሁዋላ በዋስና

በተለያዩ ውሎች መፈታቱን ለማወቅ ችለናል።

እንደገና እታሰራለሁ በማለት ሲፈራና ሲጨነቅ የቆየው

ዳንኤል በቤተሰብ እርዳታ በሰላም ካገር ለመውጣት

መቻሉና በካናዳ የፖለቲካ ጥገኘነት ማመልከቻ

ማቅረቡን ከታማኝ ምንጮቸቻችን ለመረዳት ችለናል።

ዳንኤልን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው

ሊሰሳካልን አልቻለም። የዳንኤል ነጋሽን ስልክ

የምታውቁ የመፅሄታችን ታዳሚዎች

[email protected] በሚል አድራሻችን ልትፅፉልን እንደምትችሉ እየያሳሰብን ለትብብራችሁም

በቅድሚያ እናመሰግናለን።

ወደፊት ዳንኤል ነጋሽን ካገኘነው ቃለምልልስ

እንዲሰጠን በመጠየቅ ይዘንላችሁ እንደምንቀርብ ቃል

እንገባለን።

አቶ በረከት ስምዖን በጠና

መታመማቸው ይወራል

ተቃዋሚም ሆነ ደጋፊ በሚሏቸው ሰዎች ላይ

ያላቸውን ስልጣን በመተማመን የስድብ ናዳ

በማውረድና በማንቋሸሽ የታወቁት አቶ በረከት

ስምዖን በጠና መታመማቸውና ለህክምና ወደ

ውጪ ሃገር መሄዳቸው በስፋት ይወራል።

አቶ በረከት ከልጅነታቸው ጀምሮ የኢህአፓ ታጋይ

በመሆን እስከ ብአዴን ድረስ እየታገሉ የኖሩና ያሉ

በጦር ሜዳ ጀግንነታቸው በጣም የታወቁ ታጋይ

ናቸው።

ዝግጅት ክፍላችን አመለካከት እንጂ ሰዎችን

መጥላት አይቀበልም። አቶ በረከት እግዚአብሄር

እንዲምራቸውም እንመኛለን።

ቅዳሜ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ከብዙኃን ምእመናን የተሰበሰበ በብዙ ሚልዮን ብር የሚገመት የቤተ ክርስቲያን ሀብት እና ንብረት አላግባብ ተመዝብሮበታል የተባለው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሒሳብ፣ በገለልተኛ እና ሕጋዊ አካል በይፋ እንዲመረመር ተጠየቀ፡፡ ሓላፊነትን አላግባብ በመጠቀም እና የሒሳብ አያያዝ እና የንብረት አጠባበቅ ድንጋጌዎችን በመጣስ በደብሩ አስተዳደር ተፈጽሟል በተባለው ምዝበራ እና ብክነት÷ ጥናት እና ጥራት ለጎደላቸው ሥራዎች ከፍተኛ ወጪዎች ይታዘዛሉ፤ ከተመደበው እና ከተወሰነው ውጭ በሕገ ወጥ ትእዛዝ የደብሩን ካፒታል የሚንዱ የተለያዩ ክፍያዎች ይፈጸማሉ፤ ለተከራይ በሚያደሉ እና የደብሩን ጥቅም በሚጎዱ የሕንፃ ኪራይ ውሎች ግለሰቦች መቶ ሺሕዎችንና ሚልዮን ብሮችን ያካብታሉ፤ በዐውደ ምሕረት በምንጣፍ አና በስእለት የተሰበሰበ ገንዘብ በአግባቡ ሳይቆጠር እና በሞዴል ገቢ ሳይኾን እየተወሰደ የገባበት አልታወቀም፡፡ ከኹለት ዓመታት በላይ የደብሩ ሒሳብ ሹም ኾነው ሲሠሩ የቆዩት ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ሥዩም÷

by Monitor Ethiopian News on August 1, 2015 in Amharic News 0 st-urael-church በኹለት ዓመት ውስጥ ለደብሩ ከብር 18 ሚልዮን በላይ ተቀማጭ አስመዝግቤአለኹ የተነሣሁት ሕገ ወጥ ክፍያዎችን በመቃወሜ እና ምዝበራዎችን ለመሸፋፈን ሲባል ነው ሕገ ወጥ አሠራር ቢረጋገጥም ውሳኔ አያገኝም፤ በአጥፊዎችም ላይ ርምጃ አይወሰድም የሰነዶቹ ደኅንነት ታይቶ ቢሮዬ ይታሸግልኝ፤ መንግሥት ኦዲተሮችን መድቦ ያጣራልኝ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለሚፈጸሙ አደገኛ አሠራሮች ቀርቤ በቃል እንዳስረዳ ይመቻችልኝ የሀገር ሀብት በባለሥልጣናት በሚያስፈራሩት ዋ/ሥ/አስኪያጁ ሲዘረፍ ማየቱ አደጋ ያስከትላል የየማነ ቢሮ የንግድ ማስታወቂያ አልተለጠፈበትም እንጂ የሰው ዘር መሸጫ መደብር ኾኗል ለፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ የኮቴ ይከፈላል፤ እስከ ግማሽ ሚልዮን እንዲሰጣቸው በቃል ያዛሉ ፓትርያርኩ ሙስና ይጥፋ ቢሉም ከሚዲያ አላለፈም፤ በሥራ እንጂ በሚዲያ አይጠፋም /ሒሳብ ሹሟ ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ሥዩም/

(ምንጭ፡- ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ ፫ ቁጥር ፻፲፬፤

ከብር 6 ሚልዮን በላይ የተመዘበረበት የደ/ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሒሳብ እንዲመረመር ተጠየቀ፤ ‹‹የበጀት

ዓመቱን ሒሳብ ዘግቼ ለመመርመር ሰባት ቀን ሲቀረኝ ተዘዋውሬአለኹ››/ሒሳብ ሹሟ/

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 3

የሒሳብ ሠራተኛ የተመረመረ ሰነድ ማስረከብ እንዳለበት ሒሳብ ሹሟ ጠቅሰው፣ ከመጋቢት/2005 ዓ.ም. ጀምሮ እስከተዘዋወሩበት ሰኔ 22/2007 ዓ.ም. ድረስ በደብሩ በቆዩባቸው 27 ወራት ከብር 54 ሚልዮን በላይ ገቢ እና ወጪ የሠሩባቸው፤ ከብር 18 ሚልዮን በላይ ተቀማጭ ያስመዘገቡባቸው የሒሳብ ሰነዶች እና መዛግብት በይፋ እንዲመረመሩ በአድራሻ÷ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በሀገረ ስብከቱ ለፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እና ለዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በጻፉትና በግልባጭ ደግሞ ለሰብአዊ መብቶች ተቋማት እና ለመንግሥት የደኅንነት አካላት ባደረሱት ሰፊ ጽሑፍ ጠይቀዋል፡፡

ቀጣዩ በገፅ 9 ይመልከቱ

Page 4: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፤ በአፍሪካ ህብረት ያደረጉት ንግግር የሽንገላ ነው” ሲልም ትዝብቱን ገልጿል፡፡

“ባለፈው እሁድ አመሻሽ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ

ሲገቡ ስመለከት ከደስታዬ ብዛት አልቅሻለሁ” ያለው ሌላው አስተያየት ሰጪ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪ የሆነው ቢንያም በበኩሉ፤ ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ያለውን ለውጥ መመልከታቸውና ሰላም መሆኑን ማየታቸው ትልቅ ነገር ነው ባይ ነው፡፡ “ፕሬዚዳንቱ እንዴት ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮጵያን

ይጎበኛሉ? በሚለው ሃሳብ አልስማማም” ያለው ቢኒያም፤

“ማንም በስልጣን ላይ ቢኖር የታላቅ ሃገር መሪ መጥቶ ሲጎበኝ አገሪቱ ተሰሚነቷና ተቀባይነቷ እያደገ መምጣቱን ጠቋሚ ነው፤ ነገ ይሄ መንግስት ወርዶ በሌላ ቢተካም ሃገራዊ ጥቅምን አስቀድሞ ማየት ተገቢ ነው” ብሏል፡፡ ከጥቂት ዓመታተ በፊት ፕሬዚዳንት ኦባማ፤ ሆስኒ ሙባረክ የሚመሩትን ሃገር ለመጎብኘት ግብፅ መሄዳቸውን ያስታወሰው አስተያየት ሰጪው፤ በወቅቱ በኢትዮጵያ እንዳደረጉት ለ30 ዓመት በስልጣን ላይ ከቆዩት ሙባረክ ጋር ተወያይተው፣ ግብፅን አድንቀውና አንቆለጳጵሰው ተመልሰዋል፤ በጥቂት ወራት ውስጥ ግን የተፈጠረው ሌላ ታሪክ ነው፡፡” ይላል፡፡ በፕሬዚዳንት ኦባማ የተጎበኙት ሙባረክ፤ በህዝባዊ አመፅ ከስልጣናቸው ሲወርዱ አመፁን ከደገፉትና በአመፅ ስልጣን ላይ ለወጣው መንግሥት እውቅና ከሰጡት ቀዳሚ ሃገራት አንዷ አሜሪካ ነበረች በማለት አሁኑ ጉብኝት ዋስትና እንደማይሆን ገልጿል፡፡ “የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ በአሜሪካ

የሚተማመን መንግሥት አይመስለኝም” ያለው አስተያየት ሰጪው፤ ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ ህብረትም ሆነ በብሄራዊ ቤተ መንግሥት ያደረጓቸው ንግግሮችና የሰጧቸው መግለጫዎች ብዙም የአቋም ለውጥ የሚያስከትሉበት አይመስለኝም”

ብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ህብረት ባደረጉት ንግግር ላይ የተገኙት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤

“የፕሬዚዳንቱን ንግግር ልብ ብሎ ያዳመጠ ሰው ጠንከር ያለ

መልዕክት መያዙን ይረዳል” ይላሉ - በተለይ በዲሞክራሲ ሂደት ላይ የአፍሪካ መሪዎች መከተል የሚገባቸውን መናገራቸውን በመግለፅ፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሬዚዳንቱን ንግግር ሰምቶ ተግባራዊ ያደርጋል የሚል ግምት የለኝም፤ ዶ/ር

ጫኔ፡፡ ኦባማ፤ “በኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ

መንግሥት ነው ያለው” ማለታቸው ከዲፕሎማሲ ቋንቋነት የዘለለ ትርጉም አይኖረውም ያሉት የኢዴፓ መሪ፤ ኦባማ ሃገሪቱን ለመጎብኘት ሲመጡ የግድ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት መቀበል ስላለባቸው እንጂ ሙሉ እውቅና ከመስጠት ጋር አይያያዝም ባይ ናቸው፡፡ “በየትኛውም መንገድ አምባገነን መሪ በስልጣን ላይ ሊቀጥል

ይችላል” የሚሉት የፓርቲው መሪ፤ ኃያላኑ መንግስታት ማተኮር የሚፈልጉት የዲሞክራቲክ ተቋማት በሚጠናከሩበት ሁኔታ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡ ልማት ያለ ዲሞክራሲ ብዙ አያስኬድም ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ የአረብ ሃገራት በልማት የመጠቁ ሃብታሞች ቢሆኑም በዲሞክራሲ ያለመጠናከራቸው በፈጠረባቸው ጣጣ እንደገና እየፈረሱና እየወደቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በኢትዮጵያም መልካም አስተዳደርና የህዝብ ይሁንታ ያለው መንግስት በስልጣን ላይ እስካልተቀመጠ ድረስ እድገቱ ቀጣይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡ የኦባማ ንግግሮች ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም አላቸው ብዬ አላስብም ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ካለው አደረጃጀትና አወቃቀር አንፃር እንዲህ በቶሎ ይቀየራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡ ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን በበጎ ጎኑ እንደሚመለከቱት የተናገሩት ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው በበኩላቸው፤ ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ በነበራቸው ቆይታ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ለውጦች መኖራቸውን መገንዘባቸው መልካም እንደሆነ ጠቁመው በሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ ጉዳይ ላይ ግን የነበራቸው ግንዛቤ የተዛባ ይመስለኛል ብለዋል፡፡ በንግግራቸው ላይ የመለሳለስና ከእውነታው የመሸሽ ነገር ማስተዋላቸውን በመግለፅ፡፡

Written by Alemayehu Anbesse From Addis Admas

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ ሁኔታ ትኩረት ነፍገውታል ብለዋል፡፡ ኦባማ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት “በዲሞክራሲያዊ

መንገድ የተመረጠ ነው” ማለታቸውን ተቃዋሚዎች

ተቃውመውታል፡፡ መንግሥት በበኩሉ፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ እውነታውን ነው የገለፁት ብሏል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት አስመልክቶ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሚሰነዝሯቸው ትችቶች ውሃ የማይቋጥሩ ናቸው ሲልም መንግሥት ነቅፏል፡፡ በማህበራዊ ድረገፆች ላይ የግል ፖለቲካዊ ዕይታዎቹን በማቅረብ የሚታወቀው የፖለቲካል ሣይንስ ተመራቂው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በሰጠው አስተያየት፤ ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያስተላለፉት መልዕክት ከጠበቀው በተቃራኒ እንደሆነበት ይናገራል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ስለ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት አያያዝ አሉታዊ ሪፖርቶችን እያወጡ ባሉበት ሁኔታ፣ ፕሬዚዳንቱ እዚህ ድረስ መጥተው “በአገሪቱ ያለው መንግሥት በዲሞክራሲያዊ መንገድ

የተመረጠ ነው” በማለት እውቅና መስጠታቸው ፈፅሞ

ያልጠበቅሁት ነው” ብሏል፡፡ በፕሬስ ነፃነት ጉዳይና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ላይ ፕሬዚዳንቱ ይፈጥራሉ ብዬ የጠበኩትን ያህል ተፅዕኖ አለመፍጠራቸውን ተገንዝቤአለሁ ብሏል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ ህብረት ያደረጉት ንግግር ይበልጥ ቴክኒካል የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ነው ያለው ጋዜጠኛው፤ “ያ ግን በአጠቃላይ አፍሪካን እንጂ ኢትዮጵያን የሚመለከት ባለመሆኑ የሀገሪቱን የመንግስት እንቅስቃሴ ለሚከታተል ኢትዮጵያዊ ትርጉም አልባ ይሆንበታል” ብሏል፡፡ እንደ አጠቃላይ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ከተወሰደ ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ ህብረት ያደረጉት ንግግር ከሊበራል መሪ የሚጠበቅ ነው የሚለው አስተያየት ሰጪው፤ ፕሬዚዳንቱ እንዲህ ያለ ንግግር ሊያደርጉ የቻሉትም አሜሪካውያን ካላቸው ግብረ-መልስን እንደትልቅ ግብአት የመጠቀም የሠለጠነ አካሄድ በመነሳት፣ በቤተመንግስት በተሰጠው መግለጫ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደተከፋ ተገንዝበው ያደረጉት የተሠላ ንግግር ይመስለኛል ብሏል፡፡ “ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያላቸውን ትክክለኛ አቋም ያንፀባረቁት በቤተመንግስት

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚያውቁትን ያህል ትችት ይሰነዝራሉ ብሎ መጠበቅ ያስቸግራል ያሉት አቶ ልደቱ፤ የጉብኝታቸው አላማ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ በመሆኑ በአዎንታዊ ነገሮች ላይ ለማተኮር መርጠዋል፡፡ መጀመሪያም በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ በትክክል የሚያሳይ ንግግር ያደርጋሉ ብዬ አልጠበቅሁም፤ የሆነውም እንደጠበቅሁት ነው ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ህብረት ባቀረቡት ንግግር፣ የአፍሪካ መሪዎችን ስልጣንን የሙጥኝ ማለት በተመለከተ በቀልድ አዋዝተው ያስተላለፉት መልዕክት የተሻለ ነበር ያሉት አቶ ልደቱ፤ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ ሁኔታ ግን ያወቁ አልመሰለኝም፡፡ የሚያውቁትም ከሆነ ጠንከር ባለ ቋንቋ ለመግለፅ ድፍረት አጥተዋልሰ ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ያለው መንግስት “በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው” ማለታቸው ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው በአፍሪካ ህብረት ባደረጉት ንግግር ግን መሰረታዊ ችግሮችን በማንሳት መናገር የሚገባቸውን ያህል ተናግረዋል ብለዋል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስተሳስራቸው ዋነኛ ጉዳይ ሽብርተኝነትን የመዋጋት አጀንዳ ነው ያሉት ምሁሩ፤ በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ዙሪያ ብዙም ተፅዕኖ ለማድረግ አለማሰባቸውም መነሻው ይሄው ነው ብለዋል፡፡ ሌላው አንጋፋ ፖለቲከኛና የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ለኢህአዴግ መንግስት ውዳሴና ቡራኬ ከመስጠት ባሻገር ብዙም ፋይዳ አልነበረውም ባይ ናቸው። “በጉብኝቱ ኢህአዴግ ድል ተቀዳጅቷል” ያሉት

ሊቀመንበሩ፤ ኦባማ የኢትዮጵያ መንግሥት “በዲሞክራሲያዊ

መንገድ የተመረጠ ነው” ማለታቸውን የጠቀሱት ፕ/ር በየነ፤ ኢህአዴግ ከዚህ በላይ የሚፈልገው ነገር ሊኖር አይችልም ሲሉ ጉብኝቱ ለመንግሥት ትልቅ ድል ማስገኘቱን ገልፀዋል፡፡ ለእኛና ለህዝቡ ግን ምንም ፋይዳ አልነበረውም ይላሉ ፕ/ር በየነ፡፡

የኢህአዴግ ጽ/ቤት የህዝብና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋው ግን ከአብዛኛው አስተያየት ሰጪዎች የተለየ አቋም ነው ያላቸው። ኦባማ የኢትዮጵያ መንግሥትን “በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው” ማለታቸው ትክክለኛ አቋም መሆኑን ጠቁመው፤ ይሄ ደግሞ የእሳቸው ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ መንግሥትም አቋም ነው ብለዋል፡፡ “ተቃዋሚዎች አሁንም ምርጫውን በተመለከተ ራሳቸውን ዞር

ብለው ማየት አለባቸው፤ ህዝቡ ኢህአዴግን ለምን መረጠ? እኛ

ለምን ተሸነፍን? ችግራችን ምንድን ነው? የሚለውን በዝርዝር ማየት ይገባቸው ነበር፤ ነገር ግን ይሄን ለማድረግ አሁንም ፍላጎቱ የላቸውም” ያሉት አቶ ደስታ፤ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግም አልፈው የአሜሪካ መንግስትን በመወንጀል ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ “ይሄ አካሄዳቸው ግን ትክክል አይደለም፤ ከእውነታው ያፈነገጠ

ነው፤ የህዝቡን ውሳኔም ማክበር አለባቸው” ሲሉም አቶ ደስታ

ተናግረዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሰላም፣ በልማትና በዲሞክራሲ ዘርፎች የተቀዳጀነው ስኬት ውጤት ነው ያሉት አቶ ደስታ፤ ኦባማ አገሪቱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት ያላት መሆኑን መመስከራቸው የአገሪቱን ገፅታ በበጎ መልኩ እንደሚገነባ ገልፀዋል፡፡

ልሳነ ህዝብ

ኦባማ በተቃዋሚዎች ክፉኛ ተተቹ መንግሥት ትችቱን አጣጥሎታል

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 4

በአፋኙና ጨቋኙ የወያኔ መንግስት ምክንያት የተሸበቡ የኢትዮጵውያን ልሳኖች

እንደተዘጉ አይቀሩም። ስለነሱ የሚናገርላቸው፣ አቤት የሚልላቸውና

የሚያስተጋባላቸው ልሳን አለ። ይህንንም ልሳን የህዝብ እንጂ የማንንም እንዳልሆነ

ላማሳየት ልሳነ ህዝብ በድረ ገፁ በየወሩ የማያወጣው ጋዜጣ ነው።

ልሳነ ህዝብ በፖለቲካ ፓርቲነትም ሆነ በማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ መድረክ ላይ

የማይሳተፍ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም ብቻ የቆመ የዲሞክራሲና የፍትህ መድረክ ነው።

ማንም ሰው አመለካከቱን በነፃነት መግለፅ የተፈጥሮ ልግሱ ነው በማለት የተነሳ

መድረክ ነው።

Page 5: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

እንዲቃጠሉ ምእመናኑም ለአፄ አምደጽዮን እንዳይገዙ አውግዙ ብለው የኤጲስ ቆጶስነት ማእረግ እየሰጡ ላኩዋቸው። አላማቸውም አፄ አምድጽዮን የአጻፉትን መጻሕፍት እንዳይቀበሉ ለማውገዝ ነበር። በዚህን ጊዜ የጳጳሱን ፍቅድ ለመሙላት ብለው አባ አኖሪዎስና አባ ፊልጶስ የደብረ ሊባኖስን መነኮሳት አስከትለው ንጉሠ ነገሥቱ አፄ አምደጽዮን ከሚኖሩበት ዳጉ ሂደው በድፍረት ስር ማሽና ቅጠል በጣሽ አስማት ደጋሚ ደብተራ ሰብስበህ እግዚአብሔር የማይወደውን መጽሐፍት አጽፈህ በየገዳማቱ ልከሃልና በቶሎ ሳይራባ እንዲቃጠል አድርግ አሉት።አፄ አምደጽዮንም እኔ የፃፍኩት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የአደረገላቸውን ተአምርና ቃልኪዳን እንዲሁ በዘመናቸው የሆነውን ሁሉ ለትውልድ ታሪካቸው እንዲተላለፍ እንዳይረሳ አጽፌአለሁ እንጂ እናንተ እነደምትሉትና እንደምታስወሩት አይደለም አላቸው። አባ አኖሬዎስም ታሪክ ብትፈልግ ከግብጽ ለኛ ብለው የመጡትን ጳጳስ ቃል በሰማህና የሚሉህን ባደረክ ነበር፡ ግን አሁን በራስህ ፍላጎት ያደረከውን ስህተት አምነህ መጽሐፍቱን አሰብስብህ ባታቃጥለው አውግዤሃለሁ አገርም አይገዛልህ ብለው ተናገሩት። ንጉሥ አምደጽዮንም አባ አኖሪዎስን በገበያ ላይ በጅራፍ እንዲገረፉ አዘዘ። በዚህን ጊዜ የቤተ ክህነቱ ወገን በአባ አኖሬዎስ መገረፍ አጉረመረመ፡ ስሙንም ለማጥፋትና ለማቆሸሽ የአባቱን እቁባት እህቱንም አገባ ከሃዲም ነው ብለው መነኮሳቱ እየፃፉ በየገዳማቱ ላኩ አስወሩበትም፡ ነገር ግን ውግዘቱም ሆነ ሐሰተኛው ወሬ አምደጽዮንን ከክብራቸው ከመንግሥታቸው ሊያወርዳቸው ቀርቶ እንዲያውም በጦርነትም ይሁን በመንፈሳዊ ሥራቸው የእግዚአብሔር መንፈስ አልተለያቸውም፡ ከቀን ወደቀን መንግሥታቸው እየጸና እስከ ውቅያኖስ ባሕር ድረስ ባሉ ጎሣዎች ተከበሩ ታወቁ። በአፄ አምደጽዮን መንግሥት ላይ የሚያምጽና መንግሥታቸውን የሚገለብጥ ሌላ ሰው እንዲነግሥ ቤተ ክህነቱ ተማከረ፡ በጻጻሱ በአባ ያእቆብ አሳሳቢነት በሚፈለጉበት የቱርክና የግብጽ የየመን ሱልጣኖችና ሸሆች በኢትዮጵያው በክርስቲያኑ መንግሥት ላይ እንዲያምጹና እንዲወጉት ለባላባቶች የጦር መሣርያና የጦር አሰልጣኞች ለወላስማዎች ላኩላቸው። የተላኩትም ከባላባቶች ጋር መጥተው ተቀላቀሉ።በዚህን ጊዜ በንጉሥ አምደጽዮን በኩል ያለውን ኃይል የሚገልጽ ሰላይ እየላኩ ለይፋቱ ባላባት ለሃቅ አድዲን እንዲያምጽና እንዲዋጋ በአረብኛ ጽፈው ላኩለት። እርሱም ከአዳሉ ባላባት ጋር ተማክሮ ለአምደጽዮን እንደማይገብር አስታወቀ። እንደዚህም ሆነ፡ ሃቅ አድዲን በወላስማ ላይ የበላይ እንደሆነ ኢትዮጵያንም ጠቅልዬ የክርስቲያን መንግሥት አጥፍቼ የእስላም መንግሥት በምትኩ አስቀምጣለሁ ብሎ ክርስቲያኖችን መግደል ዓብያተ ክርስቲያናትን ማፍረስ ጀመረ። እንዲሁም ንጉሥ ነገሥቱ እንደሚያደርጉት በኢትዮጵያ አገሮች የሚሾሙትን ሱልጣኖችና ኢማሞች ከሊፋዎችንም እየሾመ ይዘጋጅ ጀመር። አፄ አምደጽዮንም ይህንን ወሬ በሰሙ ጊዜ በ 1300 ዓ.ም ከተጉለት ወደ ይፋት ሄደው በወንድሙ በደራደርና በሐቅ አድዲን እየተመራ የሚመጣውን ሠራዊት ድል አድርገው ደራደርን በፈረሱ ላይ እንዳለ በጦር ወግተው ገደሉት። የእስላሞች ጦር መሪ ባላባት ሐቅ አድዲን ወደ ግዞት ወደ ጎጃም ተላከ። በእርሱ ፈንታ የወላስማን ማዕረግ ለወንድሙ ልጅ ለሰበን ሰጥተው የአመጸውን ሽረው ያላደመውን ሹመው በሰላም ወደ ዳጎ ተጉለት ተመለሱ። አፄ አምደጽዮን በነገሡ በአሥራ ስምንተኛው ዘመነ መንግሥታቸው በወላስማ ስብረዲን የሚባል እስላም ተነሳና ለአምደጽዮን የሚገዛውንና የሚገብረውን ሁሉ አጥፍቶ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥሎ በምትኩ ጃሚዎችንና መስጊዶችን ማሰራት ክርስቲያኖችን መግደል ጀመረ። አፄ አምደጽዮንም ሊቀ አፍራስ ዘየማን ሊቀ አፍራስ ዘጸጋም ሊቃውንተ ሃራ ዘፄዋ የሆኑትን ሁሉ ጥሪ አድርገው ከሾሙና ከሸለሙ በኋላ ሰብረዲን (ሰበር-አደዲን)ወደሚኖርበት ወደ አዳልና ወደ ሞራ አገር ላኳቸው። ከተላኩትም የቀኝ ፈረሰኞች የግራ ፈረሰኞች የጨዋ ሠራዊት አለቆች ከሰበር አደዲን ሠራዊት ጋር ገጥመው ድል አድርገው ብዙ ህዝብ ከማረኩና የታሰሩትን ከአስፈቱ በኋላ በመንደሩ ብዙ ወርቅና የዳሉል ሉል ድንጋይ ከአረብ አገር የተላከለት የጦር መስሪያ ሰይፍና ጦር ከሰብር አደዲን ቤት አግኝተው ወሰዱ። ሰብር አደዲን ግን አስቀድሞ ስለሸሸ ሊያገኙት አልቻሉም። በአፄ አምደጽዮን ላይ ጠላት ሁነው የተነሱት የቤተክህነቱ ባለስልጣናት በየገዳማቱና በየአድባራቱ ህዝቡ አንገዛም እንዲልና እንዲያምፅ ሰብከውት ስለነበር በሰሜን በፀለምት በጠገዴ በወገራ በደንቢያ የተሾሙ ሁሉ አመፁባቸው። በዚህን ጊዜ አፄ አምደጽዮን ቸንከር ሰቀልት ጎንደር ሃደር አይደር ከረን ኮረም ዳሞት የሚባሉትን የፈረሰኛንና የእግረኛን ወታደሮች በጦር በአጋዙ በጸጋ ክርስቶስ አንተሁን እየተመሩ የአመጻውን አገር ቀጥተው የጠፋውንም አገር እንዲያለሙ ወደ በጌምድር ላኳቸው። እነዚህም የአምደጽዮን ሠራዊት በሄዱበት አገርና በሰፈሩበት አምባ በስማቸው ስሙ ያው ሆነ፤ ይሄውም በቸንከር ሠራዊት ስም ቸንከር በሰቀልት በጎንደር ሠራዊት ስም ሠፈሩ ጎንደር ተባለ፤ ይሄም ሠራዊት እራሱ ለፍቶ ጥሮ በጉልበቱ ስለሚያድር በጎንህ እደር ሲሉ ጎንደር ተባለ። እንደዚሁ በሳምሮና በሰቆጣ በአዘቦ በሣምሬ ገጽሃን የሚባል ተነሳና ንጉሥ ነኝ ብሎ በአፄ አምደጽዮን መንግሥት ላይ አመጸ። በመልአከ ባህርና በሊቀ ሐመር የሚመራውን ሠራዊት ስሙም የዋግድልናይ የዳህና በለው የሰርቄት ስብስብ ክበብ ማዕከል ተዋዛት ተብሎ የሚጠራውን ሠራዊት ላኩት። እርሱም ከቡግና እስከ ዙላ የአለውን አገር አቅንቶ አፄ አምደጽዮን ለአነገሱት ንጉሥና ለሾሙት ለትግሬ ሹም ለዋግሹም ለደህናሹም እንዲገዛና እንዲያስገብር የአመፀውንም እንዲያጠፋ ላኩት፤ እርሱም እንደተባለው አደረገ። እንደዚሁ በመልአከ ባህር የሚታዘዝ የኩናማ የብሌን የትግሬ ሠራዊት ከሐማሴን ተነስቶ ጠላትን እያሳደደ የአመነውንም እያስገበረ ገብረመንፈስ ቅዱስና ተክለሃይማኖት በክርስትና ሃይማኖት ወደ አሳመኑት አገር ተላከ። ከዚያም ከሰባት ተከፍሎ ሰባት ቤት ጉራጌ ተብሎ አገር እያለማ ከባላባቱ ጋር በጋብቻ ተቀላቅሎ ኖረ። ”ጉራ” ማለት ግራ ሲሆን “ጌ” ደግሞ ሃገር ማለት ነው። ጉራጌ የግራው ሠራዊት አገር ማለት ነው። ይህ ሠራዊት ጥንት ወደመጣበት አገር በሰይፈ አርእድ ጊዜ

ከታሪክ ማህደር ንጉሥ ዓምደጽዮን by ልጅ ሞንሟናው ንጉሥ አምደጽዮን (በመሪራስ አማን በላይ ) የአፄ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅ የአፄ ውድም አርእድ ልጅ አምደጽዮን ስመ መንግሥታቸውን ሣልሣዊ ገብረመስቀል (ንጉሥ ላሊበላ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው በአንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት (1298) ዓ.ም. ነገሡ። የቀደማዊው ምኒልክን (ምንይልክ) ዘርና የነገሥታቱን ታሪክ ለማጥፋት ሮማውያንና አረቦች በሚልኳቸው መልእክተኞቻቸውና ጳጳሳቶች ከአዳም እስከ ምኒልክ የተጻፈው መጽሐፈ ሱባኤ መጽሐፈ አበው ከምኒሊክ እስከ አልአሜዳ ዘመን የተጻፉት መጽሐፍት ተለቅመው ጠፍተው በምትካቸው በአረብኛ ቃል የተጻፉ ተተክተው ሳለ እንዲሁ አይሁዳዊ የሆነቸው የአረቦች ጠላት ዮዲት ተነስታ የአረብኛን መጻሕፍቶችና አዋቂዎችን ስታቃጥል እንዲሁ አብሮ የነበረው በግእዝ የተጻፈው መጻሕፍ ሁሉ የሚበልጠው ተቃጥሎ ነበር። ስለዚህ አፄ አምደጽዮን በነገሡበት በአንደኛው ዘመነ መንግሥታቸው የነገሥታትን ታሪክና የመንፈሣዊን መጻሕፍት የሚጽፉትንና መተርጎም የሚችሉትን ሊቃውንት በመሪራስ ተድላዓለም በኩል ጥሪ አደረጉ። ሊቃውንቶችም በአፄ አምደጽዮን ጥሪ መሰረት መጻሕፍቶቻቸውን ይዘው ወደ ተጉለት ተሰበሰቡ። እነዚህም የታሪክና የጽሕፍት ባለቤት የሆኑት ሊቃውንት የመጡበት አገር፦

ቤተማል

ቢተግራማል

ቢተግአ

ቤተዋልሻ (ዋሸራ)

ቤተሃማራ (አማራሳይንት)

ቤተእንዳ (አንዳ ቤት)

ቤተ አባይ (አፈርዋናት)

ቤተ አሹር (ወገራ-ራስዳሽ)

ቤተጉድረት

ቤተ እንዳት

ቤተሳህል (ጣና ሐይቅ)

ቤተ ሃጌ (ሐረርጌ ድዋሮ)

ቤተወንጂ (አሩሲ)

ቤተቂዳር ዛይላ ቤተ መቅደስ (ሙቃድሾ) ናቸው። ከእነዚህ አገሮች የመጡ ሊቃውንቶች ጸሐፊዎች በዳጎ ሲቀመጡ ቀለም የሚቀምሙና ከፈረስና ከበቅ ብራና ፍቀው የሚያወጡ በሞረት በግራርጌ በአፈርዋናት በአንዳቤት ቀለብና የሚፈልጉት የብራና መፋቂያ መስሪያ ቀርቦላቸው ሥራቸውን ጀመሩ። የጸሐፊዎች አለቃና መጽሐፍት ተረካቢ መሪራስ ዘጉባኤ ሲሆን አስተናጋጁና ቀለብ ሰፋሪ መሪራስ ተድላ ዓለም ሙሉ ስልጣን ተሰጣቸው። ለየራሳቸው ሦስት መቶ ተላላኪዎች ነበሯቸው። በዳጎ ለጽሕፈት የተዘጋጁ አምስት መቶ ሊቃውንቶች ነበሩ። 1 ኛ – በዚህን ጊዜ መጽሐፈ ሱባኤ በዳንግዣ ከደንገቦች ስለተገኝ አሥራ ሁለት መጽሐፍቶች ብቻ ተጻፈ እርሱም ከአዳም እስከ ቀዳማዊ ምኒልክ የመልከጼዴቅን ዘሮች የሆኑትን የካህናት ታሪክና ስለ ስነፍጥረትየሚገልጽ ነው። 2 ኛ – መጽሐፈ አክሱማይ ሲራክ፡ ከመጽሐፈ ሱባኤ ጋር የተያያዘ ሲሆን እርሱም ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ዮዲት የነገሡትን የኢትዮጵያን ነገሥታት ታሪክ የያዘና የተጻፈውም በኑብያ ውስጥ በአክሱማይ ሲራክ ተጽፎ በላሊበላ ወደ ኢትዮጵያ ገባ። 3 ኛ – መጽሐፈ ፍጥረት፡ በመላእክትና በሰው ልጆች በእንስሳትም የሚሰለጥኑትን ባህርያትና ጠባያት የሚገልጽ፡ 4 ኛ – መጽሐፈ ኢያስጼድ ሲራክ የጻፈው የድንጋዮች አይነትና በድንጋይ ውስጥ ስለሚገኘው የጥበብ ኃይል፡ 5 ኛ – ፍካሬ ክዋክብትና አውደ ነገሥት ስለ ሰው ፀባይና ስለክዋክብት የሚመራ፡ 6 ኛ – መጽሐፈ ጥበብ በድንጋይና በእንጨት ቤትም ሆነ ቤተመንግሥት ለመስራት 7 ኛ – መጽሐፈ ቀኖና ዘሱባኤ ስለ ሥጋ ስለ ነፍስ ስለመንፈስ አንድነትና ሦስትነት ስለአለው ልዩነት፡ 8 ኛ – መጽሐፍ መናፍስት በሰው ልጆች ላይ የሚሰለጥኑትንና የሚታዘዙትን ለይቶ የሚያስረዳ፡ 9 ኛ – ክብረነገሥትና ብእለነገሥት የተባሉትንና በአንዳንድ ሊቃውንቶች የተደረሱትን የቅኔና የአገባብን ሙያ የሚገልጹ ነበሩ። ሌሎችም መጻሕፍት ቅዱሳን መጻሕፍተ ነቢያት ወሐዋርያት ወመዝሙረ ዳዊት ወመጽሐፍተ ሰሎሞን የተባሉ ሁሉ ለየገዳማቱና ለየአድባራቱ በግእዝ ተጽፈው ተልከዋል። ለጻፉትም የማእረግ ስምና ልዩ ልዩ ሽልማት ሰጥተው ወደየሃገሮቻቸው ከመሕፍቶቻቸው ጋር በሰላም አሰናብተዋቸዋል። በዚህን ጊዜ ከግብፅ የመጡት ጳጳስ አባ ያዕቆብ፡ በአፄ አምደጽዮን መልካም ተግባር እንዲሁም የኖረውንና የተደበቀውን መጻሕፍት ሁሉ አሰባስቦ በመጻፉ ተናደዱና በየገዳማቱ በየአድባራቱ ለሚኖሩ መነኮሳትና መምህራን ጥሪ አድርገው እኛን ሳያማክር ሳይጥይቅ ወደየገዳማቱ መጻሕፍቶችን ልኮአልና

ተመልሶ ሰልፍ ያሳየበትን አገር ጉራእ ተብሏል። “ሶዶ” ማለት ጠላቱን ሰዶ እራሱ የግራው ሠራዊት ሠፈረበት ማለት ነው። አፄ አምደጽዮን የሃድያን ነጋሽ፡ የጎጃምን ነጋሽ፡ የቋራን ነገሽ፡ የትግሬን ነጋሽና የእናሪያን ነጋሽ የተባሉትን አምስት ነገሥታት ጥሪ አደረጉ። አሥራ ሁለት እራሶች ማለት መልከኃይል ሲባል የነበረው ራስ የሚባል የስልጣን ስም ተሰጥቶ ነበርና እነዚህ ሁሉ ከያሉበት አምባቸው እንዲመጡ ትዕዛዝ በየአገሩ በየአምባው ተላከ። ሁሉም በአንድ ላይ በደብረ ደጎ ተጉለት ተሰበሰበ። አፄ አምደጽዮን ወደ አዳል አገር ከመዝመታቸው በፊት አስራ ሁለት በሮች በአሉበት በአምባ ጽዮን በተድባበ ማርያም በእየሱስ ክርስቶስ እጅ ለቅዱስ ማርሔር የተሰጠው ሰይፍ አለት የሚሰነጥቅ ድንጋይም የሚከፍልስለነበርና በክብርም ይኖር ስለነበር የእግዚአብሔር መልአክ በራእይ ስላሳያቸው ልከው አስመጡት። ይህም ሰይፍ ከመምህር ያሬክ በትር ጋር ሲኖር የነካው ሰው ሁሉ ከደዌው ይፈወሳል፡ ወደ ጦርነትም የሚሄድ በሰይፍ ታሽቶ ሲሄድ የጠላት ሰይፍና ጎራዴ ጦርም አይነካውም። ከሁሉም ስለሚጠበቅ ካህናቱን ልከው አስመጡት፡ ከዚያም በክብር ከታቦቱ ጋር በሚሄዱበት በድንኳን እንዲቀመጥ ተደረገ። አፄ አምደጽዮን ለነገሥታቱና ለራሶች በወርቅና በብር በነሃስ የተጌጡትን ቀስትና ጦር ሰይፍና ጎራዴ ጋሻና የብረት ልብሶች ከሸለሙና ሰራዊቶቻቸውንም ከአስደሰቱ በኋላ የከዳውን አገርና እያደባ ክርስቲያኑን እየገደለ ንብረቱን እየዘረፈ ወደሚሸሽበት የአዳል አገር ለጦርነት ጉዞ አደረጉ። የአፄ አምደጽዮንና የነገሥታቱ ሠራዊት መምጣታቸውን የሰሙ የአዳል የሞራ የጢቆ የበከላይ የወገር የገለባ አለቆችና ሰዎች ከመቶ ሺህ በላይ ሆነው ሌሊት መጥተው ከበቧቸው። አፄ አምደጽዮን የጦር መሣሪያቸውን ልብስ ለብሰው ሰይፋቸውን ይዘው ከድንኳናቸው ወጡና በረቅ ከሚባለው ፈረሳቸው ሁነው ገጠሟቸው። ከፊታቸው የሚቆምና የሚመከት ጀግና ጠፋ ከአንድ ሺህ በላይ ሰውም ገደሉ። እነዚህ የእስላም ሰራዊት አምደ ጽዮንን የሜወጋ ቀስትና ጦር ወይም ሰይፍ እንደማይነካቸው እንደማያርፍባቸው አይተው ተሸንፈው ሸሹ። እንደዚሁ በሌላ ቀን እያዘናጉ ቢመጡም በአፄ አምደጽዮን ከመውደቅና ከመገደል በቀር በአምደጽዮን በኩል አንድ ሰው እንኳ ገድሎ ሰለባ ማድረግ አልቻሉም። አፄ አምደጽዮንም በ 1316 ዓ.ም ስኔ 25 ቀን ለጦር አለቆችና ለነገሥታቱ እንዲህ ብለው ተናገሩ። ጎጃም ቋራም ደንቢያም ወገራም ዳሞትም ሓድያም ባፎም ድሆኖም ዋግም ሌሎችም ሁላችሁ ስሙኝ፡ እነሆ ሁልጌ ሊወጉን መጥተው ተወግተው ብዙዎችን ስንገድል ትንሽቶችም ትልቆችንም አለቆቻቸውንም ማርከናል ይህንን ሁል ድል ያገኘነው በእኛ ኃይል ሳይሆን በእግዚአብሔር ኃይል በልጁም በእየሱስ ክርስቶስ እርዳታ ነው፡ አሁንም እግዚአብሔር ስለእኛ ይዋጋልና እነዚህን ከሐዲዎች አትፍሩ በእግዚአብሔር ጽኑ እንጂ አትጠራጠሩ፡ በሰይፍ ቢመጡባችሁ ሰይፍ አላችሁ፡ በቀስትና በጦር ቢመጡባችሁ እንደዚሁ አላችሁ። እግዚአብሔርም ከእኛ ሠራዊት ቁጥር በላይ ምርኮን ሰጣችሁ፡ ሊወጉን ከመጡት የሚበልጡት ሞቱ እንጂ አልተመለሱም ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ልጅ እየሱስ ክርስቶስን የካዱና በእርሱ ያመኑትን ምእመናን ለመግደልና ለማጥፋት በትምክህት መጥተዋልና ተዋርደው ወደቁ። እነዚህ አረመኔዎች የሚሉትን ቃል አልሰማችሁምን? ክርስቲያኖች በጦርነት ቢገድሉን በሰማይ መልካቸው ያማረ ቆንጆዎች ሴት ልጆችን መላእክት ይዘው ይቆዩናል፡ ማርና ወተት ወዳለበት ጀነት ያስገቡናል፡ እኛ ደግሞ ክርስቲያኖችን ብንገድልና ብናጠፋ እስከ ሰባት ዘር የሆኑ ልጆቻችን ሁሉ ሳይቀሩ እናጸድቃለን ብለው ነው የመጡና በከንቱ የሚጠፉ ከንቱ ቢሶች ፍጥረቶች ናቸው። እናንተስ አብና ወልድን መንፈስ ቅዱስም በአንድ የተጠመቃችሁ በደሙ የተቀደሳችሁ ሳላችሁ ለምን ከሃዲዎችን ትፈራላችሁ? አሁንም እውነተኛይቱን ሃይማኖቱን ለማጽናት ለህጋችሁም ተገዢ ለመሆን ክብርን ለመቀዳጀትና አገራችሁን ኢትዮጵያን ለመጠበቅ በርቱ ሰይፋችሁን ታጠቁ ልባችሁንም አጽኑ ነፍሳችሁንም አታስደንግጡ፡ ይህም ጦርነትና ግድያ አገርን ለመጠበቅ በህጋችን በሃይማኖታችን አይደልም፡ ምክንያቱም እምነታችን በህጋችንን ለመጽናት ለመጠበቅ ነው። የህግን ሥራ ፈጽሞ ማድረግና ሕግን አለመተላለፍ ፍጹምና ብቁነት ነው፡ ነገር ግን የሕግን ሥራ አለመፈጸም ክርስቶስን መቃወም ነው፡ እርሱ ሕግን ፈጽሞአልና። የሕግ መሠረቱ መንግሥታችን ነው የመንግሥታችንም ክብር ሕግ ነው። እንግዲህ በሕግ እምነታችንን እናቆማለን፡ በእምነታችንም ህግአችን እናጸናለን እንጂ አንሽርም። ዳዊት በእግዚአብሔር ታምኜአለሁ የሰው ልጅ ምን ያደርግልኛል ብዬ አልፈራም እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ ጠላቶቼን እመለከታለሁ እንዳለው እናንተ በእግዚአብሔር ታምናችሁ ጽኑ ደግሞም አህዛብ ሁሉ ከበቡኝ በእግዚአብሔር አሸነፍኳቸው ብሏል። አሁንም ልባችሁ ወደነበረበት ወደጦር አድርጉት እንጂ ወደኋላ ለመሸሽ አታስቡ፡ ፍርሃትን ከልባችሁ አስወግዱ እኔ ግን አምላኬ በእግዚአብሔር አብ ልጅ በእየሱስ ክርስቶስ ኃይል እነዚህን ከሃዲዎች ሳላጠፋ ክረምት ሆነ በጋ ወደ ከተማዬ ላልመለስ በእግዚአብሔር ስም ምያለሁ ልቤንም በክርስቶስ አጽንቼአለሁ አሉ። በዚህን ጊዜ ሠራዊቱ በአንድ ላይ አዎን ጌታችን የንጉሦች ንጉሥ ሆይ እንዳዘዝከን እናደርጋለን ነገር ግን ሁሉም እንዲቃናልንና ልባችን እንዲጸና በፈጣሪአችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም ባርከን፡ የእግዚአብሔር መንፈስና ኃይል ከአንተ ጋር እንደሆነ አውቀን አምነናል አሏቸው።አፄ አምደጽዮንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የእግዚአብሔር ኃይል ከእናንተ ጋር ይሁን፡ ሥልጣኑም በውስጣቸው ይደር፡ ሰይፋችሁም ወደጠላት ልብ ይግባ፡ ጦርና ፍላፃም ወደልባቸው ሥር ይቀርቅር፡

ቀጣዩን በገፅ 6 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 5

Page 6: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

አፄ አምደጽዮን በድል አድራጊነት ታቦቱ ወደ አለበት ገብተው ለእግዚአብሔር ምስጋና ተንበርክከው አቀረቡ። ከመሸም በኋላ በሌላ አገር የዋለው ሠራዊት መጣና ትልቅ ደስታ ሆነ፡ ሲነጋም የሞተው በድን እየሸተተ ሰለአስቸገረ አፄ አምደጽዮን ለጨዋ ሠራዊታቸው እንዲህ አሉ፡ እንግዲህ ሳትፈሩ ንገሩኝ ወደፊት እንሂድ ወይስ እንቅር? አንድ ሰው ብቻ በፈቀደው መደረግ የለበትም ማናቸውም ነገር ያለምክር የተደረገ እንደሆነ በፍራቻ የተጀመረ እንደሆነ ይፈርሳል ፍፃሜው አያምርም አሏቸው። በዚህን ጊዜ ሕዝበ እግዚአብሔር የሚባል ካህን እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር በትናንትናው ቀን ከጠላት እጅ አድኖሃል የያዝከውም ሰይፍ የሰውን ገላ እንደሳር ሲያጭድ ሲቆራርጥ የጠላትንም ሰይፍና ጦር ሲሰባብር አይተናል ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ሰይፍ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም አልቀን ሙተን ነበር፡ አሁንም ጌታዬ ሆይ ስማኝ ትናንትና ያየነው ሕዝብ ከሞተው ያልሞተውና የሸሸው አይን አይዘልቀውምና አሁን ብንመለስና ወደ ሃገራችን ብንሄድ ይሻላል አላቸው። አፄ አምደጽዮንም ሰማህ ወዳጄ ሆይ ስማኝ ፈርተህ ሌላውን እንዲፈራና እንዲጠራጠር ታደርጋለሁ እግዚአብሔር እንደሆነ ትናንት ተረድቼዋለሁ ዛሬ ግን አልረዳም የሚል አይምሰልህ በፍጹም ልባቸሁ እግዚአብሔርን እመኑ፡ በርትታችሁም ታገሉ አትጠራጠሩም በየጊዜው አባቶቻችንን ለረዳቸው እኛንም ለጠበቀ ለረዳን ለእግዚአብሔር ተገዙ፡ ስሙንም በክብር አንሱ ዘምሩለት፡ ቅኔውንም ተቀኙለት፡ እግዚአብሔር በእኔ ክንድ ላይ ሆኖ በብዛታቸው ተመክተውና ተባብረው የመጡትን ጠላቶቻችንን ከእሬሳ ላይ እሬሳ እንደክምር እስከሚሆኑ ድረስ ገደልኳቸው ሰይፉም ጨርቅን እንደሚቀድ እንጂ የሰውን ገላ እንደሚቆርጥ አይመስለኝም ነበር፡ ይህም የእግዚአብሔር ኃይል እንጂ የእኔ ክንድ አይደለም። አሁንም እኛ የመጣነው አረመኔን ለማጥፋት በምትካቸው ሰላማዊውን ሰው ለማስቀመጥ እስከሆነ ድረስ በየሃገሩ ሹም ሽር አድርገን ብዙ ሃገር እናቀናለን አሉ። ሠራዊቱም እንስማማለን ትናንትናም በእግዚአብሔር ኃይል ያዳንከን አንተ ዛሬም ሆነ ነገ የምታድነን አንተ፡ በአንተ ልብ በአንተ አሳብ በአንተ ትእዛዝ እንሄዳለን፡ ከአንተ ማንም አይለየን አሏቸው። ከዚያም ተነስተው ዜባ ወደምትባል አገር ደርሰው ሹም ሽር አደረጉ፡ ከዜባም ተነስተው ተአረርክ ሰፈራቸውን አደረጉ፡ በዚያም ያመጸውን አጥፍተው ያመነውን አስገብረው ወደ ዶቤ ሄዱ፡ ከዶቤም ዘሶይ ከዘሶይ ተለግ ሄደው የተቃጠለውን ቤተክርስቲያን አሰርተው በምርኮ ሰልመው የነበሩትን ሁሉ ወደ ክርስትና እምነት መልሰው ሹም ሽር አድርገው አኳ የሚባለውን ወንዝ ተሻግረው መርመጎብ ከሚባለው አገር ደረሱ። በዚያም ጦርነት አድርገው በጠላት በኩል አምስት ሺህ ሰራዊት ገደሉ። አፄ አምደጽዮን ነሐሴ 11 ቀን በላስጌ አገር መስጊዱን አፍርሰው የዮሐንስን ቤተክርስቲያን ተከሉ፡ ከዚያም ዝርአት የሚባል ወንዝ ተሻግረው እራቴ ከሚባል አገር ሰፈራቸው አደረጉ።በዚህን ጊዜ ጆሮአቸውንና ብልታቸውን የተቆረጡና የተሰለቡ ሰዎች ወደ አምደጽዮን ቀርበው ውሃ ልንቀዳ ስንሄድ ድንገት ደርሰው ቆርጠውን ይሄዳሉ በጣም ፈጣኖች ናቸው አሏቸው። ንጉሠ ነገሥቱም ቁስላቸውን አይተው በጣም አዘኑና ለሠራዊታቸው እኔ መለከት እያስነፋሁ ነጋሪት እያስመታሁ ነገ ጠዋት እሄዳለሁ እናንተ ደግሞ ግራና ቀኝ አሸዋውን ለብሳችሁ ተደበቁ ወደ ሰፈር ሲመጡ ግደሉአቸው አሉ። ሠራዊቱ እንደተባሉ አደረጉ። ብዙ የኢሳ ነገዶችን ገደሉ። ከሞቱትም በአግልግላቸው ውስጥ የሰለቡትን ብልትና ጆሮ አገኙ፡ ለአፄ አምደጽዮን አሳዩ። አፄ አምደጽዮን የጠፋውን አገር እያለሙ ሹም እየሾሙ ብልቃዜር ከሚባል አገር ደረሱ፡ በዚያም የእስላሞችን ሼህ አብደላን አስመጥተው ያሰለምካቸውን ክርስቲያኖች አምጣ ብለው አዘዙት፡ እርሱም እንደተባለው አመጣቸው፡ እነርሱንም ወደ ክርስትና እምነት መልሰው የቀጡትን ቀጥተው የእስላሞችን መሪ ሽረው ለወንድሙ ለነስረዲን ስልጣኑን ሰጡበት። በዚያም የመስቀልን በአል አክብረው የዋሉበትን አገር አመራአምባ – አምባ አማራ አሉት በኋላም ዘመነ ስሙን ካራአማራ የአሉት አገር ነው። እርሱም የአማራ ሰራዊት እንዲቀመጥበት ተደረገ። አፄ አምደጽዮን ለኢትዮጵያ የባሕር በር ወደሆነው ወደ ዛይላ ሄደው የኢትዮጵያን ውቅያኖስ ባሕርን የግዛቷን ዳርቻ አይተው በባሕር ዳር የሚኖሩት ጎሣዎች ከክርስትና እምነት ወደ እስልምና እምነት ተዛውረው ሃይማኖታቸውን ቀይረው ነበርና ሁሉንም ሰብስበው ከመከሩና ከአስተማሯቸው በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። በዛይላም የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን አስተከሉላቸው። አፄ አምደጽዮን ከዛይላን የአብርሃ አጽብሃ ተክል የሆነች መቅደስ ማርያም የምትባለውን እስላሞች አፍርሰው መስጊድ ሰርተውባት ነበርና እርሳቸውም እንዲሁ መስጊዱን አፍርሰው የማርያምን ቤተክርስቲያን አሰሩ፡ ስሟንም መቅደስ ተሰየመች። ከዚያም በጎጃም ነጋሽ የሚመራውን የበረንታንና የሸበልን ሰራዊት እንዲሰፍርበትና አገሩን እንዲጠብቅ ሙሉ ዋስትና ሰጡት። በዚህን ጊዜ ዋቢ-ኃላፊ መሆኑን ለመግለጽ የሸበሌዎች ዋቤነት ለማለት ወንዙን ዋቢሸበሌ ብለው ሰየሙት፡ እስከዛሬ ድረስ ስሙ ያው ሆነ። አፄ አምደጽዮን ከዚያም ወደ ደዋሮ ተመልሰው ከሐረራ በሄዱበት ሠራዊት ስም ደዋሮን /ሐረርጌ/ የተዋጊዎች አገር ለማለት ሐረርጌ አሉት፡ ስሙም ያው ሆነ፡ ቤተሃጌ ሁሉ እንዲሁ ሐረርጌ ተብሏል። እንደዚህም ሆነ በደዋሮ በአሁኑ ስሙ ሐረርጌ በተባለው አገር በዘመነ ኦሪት ጀምሮ የእግዚአብሔር ስም የሚጠራበትና የሚመሰገንበት ይባላል፡ ይህም ስም የተሰጠው አዳም ሳይባል አድማኤል ኪሩብ በሚባልበት ጊዜ ከኤዶም ወደዚሁ ተራራ ወርዶ ለአራዊትና ለእንስሳት ስማቸውን የሰየማቸው ንጉሣቸው መሆኑን የነበረበት ስፍራ ነው። ስለዚህ በትንቢተ ሕዝቅኤል እንዲህ ሲል ስለአዳም ይናገራል፦ “በእግዚአብሔር ገነት በኤደን ነበርህ የከበረ እንቁስ ሁሉ ስርጽዮን ቶጻዝዮን/እንቁዮጵያ ግዮን/አልማዝ ቢረሌ መረግጽ ኢያስጲያ ስንፔር በሉር/ድሉል የሚያብረቀርቅ እንቁ ወርቅ ልብስህ ነበር የከበሮህና የእንቢልታህ ስራ በአንተ ዘንድ ነበር በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ

.......ከገፅ 5 የዞረ

ንጉስ ዓምደፅዮን ጎራዴአችሁም የጠላትን አንገት ይምታ፡ ለሃገራችሁ ለእምነታችሁ የጸናችሁትን ሰራዊቱን ሁሉ እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ በጋሻው ከልሎ ከጠላት አይንና እጅ ይሰውራችሁ፡ አሸናፊነቱን ይስጣችሁ፡ ድል ለእናንተ ይሁን አሉ። ሁሉም ሠራዊት እንደቃልህ ከመንፈስህ ጋር ይሁንልን አሜን አሉ። ያም ስፍራ ድል ለናንተ ተባለ። እንዲህም ሆነ ከግንቦት ወር እስከ ሃምሌ ድረስ ጦርነት ሌትም ሆነ ቀን አላቋረጠም ይኽውም አፄ አምደጽዮን እንደሌሎቹ ነገሥታት ሠራዊት ብቻ ልከው አላዋጉም። እራሳቸው በእግዚአብሔር ኃይል ተዋግተው ድል አድርገዋል። ይህም አገር ምስራቁና ምዕራቡ አይታወቅም ውሃውም የፋራ ምንጭ ከጉድጓድ የሚገኝ ነው፡ ሰዎቹም ፈጣን ጨካኞች ናቸው። በዚህን ጊዜ እንደነቢይ የሚያከብሩት በጠጉሩ ወገቡን የሚታጠቅ ከባሕር ማዶ የመጣ ስሙ ቃዚ ሳልህ የተባለ ሰው የአዳልን የበከላን የሃገራን የፈደሴን የግዳድን የነጉበን የዙባባን የሃርላን የሆባትን የተርሳን የአይሞን የአልብሮን የዚልአን የእሴትን የደዋሮን ሸሆችና ከሊፋዎች ለጀሃድ ጦርነት ጥሪ አድርጎ ሁሉንም ሰበሰበ። የመጡት ከሁለት ሺህ መስጊዶች ለጦርነት በይማሞችና በሼሆች የተሰበሰቡ አምስት መቶ ሺህ ከባህር ማዶ የመጡት አንድ ሺህ ነበሩ። በአፄ አምደጽዮን በኩል ስልሳ ሺህ አራት መቶ ሰራዊት ነበር። እነዚህም የቀኝና የግራ የኋላ ደጀንና የፊት ጦር ሰራዊት ፈረሰኛ እግረኛ ብረት የለበሱ ቀስተኛና ጦረኛ ባለ ሰይፍ ባለ ጎራዴ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ አምደጽዮን እምነትን የጣሉባቸው የሚተማመኑአቸው ነበሩና ለጦርነት ንጉሠ ነገሥቱ ከአሉበት ርቀው ሄዱ። አፄ አምደጽዮን በወባ በሽታ ታመው በአልጋ ተኝተው ለሰባት ቀን እህል አልበሉም ውሃም አልጠጡም ነበር። በዚህን ጊዜ ምድርን አንበጣ እነደሚሸፍናት ጉምም መሬትን እንደሚያለብስ ሁሉ የእስላሞች ጦር ሰራዊት እየተርመሰመሰ እንደጉዳንዳ እንደ አንበጣ ሆኖ መጣ። ከአፄ አምደጽዮን ጋር የነበሩት ሠራዊት በሊቀ ንኡሳን የማኑ የሚመሩት ትንሾች ነበሩና ደንግጠው ፈሩ። በዚህን ጊዜ አፄ አምደጽዮን ከመኝታቸው ተነስተው የቀኝና የግራ ጋሻ ጃግሬአችው የጦር ልብሳቸውን እንዲያለብሷቸው አዘዙ ወገባቸው እየተንቀጠቀጠ መቆም አቃታቸውና ወደቁ፡ አይሆንሎትም ቢሏቸውም እኔ እንደፈሪ ወይም እነደሴት ከአልጋ እንደተኛሁ አልሞትም እንደተጋዳይ አርበኛ አሟሟቴን አውቃለሁ አሉና /ከተድባበ ጽዮን/ ከተድባበ ማርያም የመጣውን የማርሄርን ሰይፍ እንዲሰጧቸውና የካህናቱን አዝዙ። ካህናቱም እንደተባሉት ሰይፉን አምጥተው ሰጡአቸው። ንግስት ዣን መንገሣ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይና ታለቅስ ጀመር። አፄ አምደጽዮንም ወደ ሰማይ እንጋጠው በእጃቸው ሰይፍና ጋሻቸውን ይዘው መሐሪውና ሐያሉ እግዚአብሔር ሆይ ሕዝብህን በኃጢአቱ ብዛት አታጥፋው ለጠላቱም አሳልፈህ አትስጠው በምህርተህ ማረው እንደቸርነትህም ብዛት ኃይልህን ስጠው፡ እኔን ግን ደስ የሚልህን አድርግብኝ ሞቴ ስለህዝብህና ስለ አገልጋዮችህ ይሁንብኝ አሉ። ይህንንም ቃል የተናገሩ አገልጋዮችህ ይሁንብኝ አሉ። ይህንንም ቃል የተናገሩ ”መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል” ብሎ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው ሁሉ እንዲሁ አፄ አምደጽዮን ለሕዝባቸው እንጂ ለራሳቸው አልጸለዩም። በዚህን ጊዜ ጠላቶቻቸው በአራቱ ማእዘን ሆነው ሰይፋቸውን እያብለጨለጩ ቀስታቸውንም ደግነው ነፋስ እንዳናወጠው ባህር ማእበልና በዝናብ ጊዜ እንደሚጮህ ነጎድጓድ ቃላቸውን እየሰሙ መጡባቸው። አፄ አምደጽዮን በአጠገባቸው ያሉትን ሠራዊት በእግዚአብሔር ታመኑ አይዞአችሁ እነዚህን የእስላም ሰራዊት ከብዛታቸው አይታችሁ አትፍሩ የእግዚአብሔር ኃይል ካልተጨመረበት በስተቀር ብዙ ሠራዊት በብዛቱ ማሸነፍ ትንሽም ሠራዊት በማነሱ ሊሸነፍ አይችልም አሏቸው። ነገር ግን የአፄ አምደጽዮን ሠራዊት ፈርተው ወደ ኋላ ሸሹ። አፄው ግን ለሚሸሹት እንዲህ አሉ እንደገና ትንሽ ቆማችሁ እንዴት እንደምጋደልና እንደምሞት ተመልከቱ ወይም እግዚአብሔርን በእጄ ላይ ሆኖ የሚሠራውን አስተውላችሁ እዩ አሉ። እነርሱ ግን ሽሽታቸውን ቀጠሉ ወዴት ትሸሻላችሁ የትም ልትሄዱ ልትደብቁ አትችሉም ነገር ግን በእግዚአብሔር ታምናችሁ ታግላችሁም ሙቱ በውርደት ከመሞት እንደጀግኖች አሙዋሙዋት በክብር ሙቱ ብለው በጥቁር አረብ አስፈሬ ከሚባለውፈረሣቸው ላይ ወጡ፡ ከዚያም የንጉሥ ሣፍስገድን ልጅ ዘነአስፈሬን ንጉሥ ተክሉን ንጉሥ ወናግረአድን ወደ እስላሞች ጦር መካከል እንዲገቡ አዘዙ። አፄ አምደጽዮን የጠላት ሠራዊት ወደበዛበት በኩል ገብተው ፍላጻውና ጦሩ እንደበረዶ እየወረደባቸው ከመሃል ገብተው የበረሃ ሰው ጥሻውን እንደሚጥስ በቱጊ እንደሚመነጥር አርእድ በሚባለው ሰይፍ ቆራረጡአቸው። አፄ አምደጽዮን በሄዱበት መሬት የጠላት በድን ሸፍኖት ከበድኑ ላይ በድን ወድቆበት ይታይ ነበር፡ አፄ አምደጽዮን አንድ ግዜ ከፈረስ ላይ ሆነው አንድ ግዜ ከመሬት ሆነው የጠላትን አንገት ሲቀጩትና ሲቆርጡት ፈረሱም ሲከተላቸው ይታይ ነበር። በዚህን ጊዜ የእስላም ሰራዊት ሽሽት ሲጀምር የጠላትን ወታደሮች ሠራዊት ምርኮና ሰለባ ሴቶቹ ይውሰዱ እናንተ ግን ሸሽታችሁ የነበራችሁ ያልሞቱትን የሸሹትን አባራችሁ ግደሉ አሏቸው። እንደተባሉትም ተከታትለው ብዙ የጠላት ሠራዊት ገደሉ። ይህን የመሰለ ጦርነት በአለፉት ነገሥታት አልተደረገም። ጦርነቱም ከስድስት ሰዓት እስከ ፀሐይ ግባት ነበረ። ሲዋጉ የዋሉበት እጃቸው በደም ከሰይፉና ከጋሻቸው ጋር ተጣብቆ በግድ ነው ያላቀቁት። በአፄ አምደጽዮን እጅ የእግዚአብሔር ኃይል ይገለጥ ዘንድ የፄዋ ጦር ሠራዊት በሌለበት በእግዚአብሔር ኃይል ጠላቶቻቸውን በትንሽ ሠራዊት ከሃምሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ ተገደሉ። በአፄው በኩል ፈርሰው ሲሸሹ ሁለት መቶ ሃምሳ ሲሞቱ አንድ ሺህ ሁለት መቶ በአለቆቻቸው የሚመሩ ሰባት መቶ ንጉሠ ነገሥቱን የሚጠብቁ ነበሩ።

በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሻ-ህ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላልሰህ ከተፈጠርክ ቀን ጀምሮ በደል እስከሚገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ በንግድህ ብዛት /ከሣጥናኤል ጋር በመነጋገሩ/ ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ ስለዚህ እንደርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ በውበትህ ምክንያት ልብህ ኮርቶአል ከክብርህ የተነሳ ጥበብህን አረከስህ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገስታት ፊት /በልጅ ልጆቹ/ ሰጠሁህ በበደልህ ብዛት /እፀ በለስን በመብላት/ በንግድህም ኃጢአት/የሰይጣን ቃል በመስማቱ/ መቅደስህን /ሰውነቱን/ አረከስክ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርሷም በልታሃላች በሚያይህም ሁሉ በምድር ላይ አመድ አድርጌአለሁ” [ሕዝቅኤል 28:13-20] ስለዚህ ይህ ተራራ አዳም በተባለው በኩሩብ ደብረ ኪሩብ ተብሏል። ይህ ደብረ ኪሩብ የሚገኘው በቤተ ኃጌ ደዋሮ ሲሆን ነገዶቹም ሞራራ ሸሆ ኢሳ ሱላጤ ሌሎቹም ይኖሩበታል። በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግሥት ከፈንታሌው ነገድ የቢንያስ ልጅ ማታን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደተራራው ወጥቶ ቤተ እግዚአብሔርን አሰርቶ ከጨረሰ በኋላ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን የሆነውን ጽላት በታቦተ ሕጉ ውስጥ አስቀምጦ ስሙንም በራእይ እንዳየው ደብረ ኪሩብ አለው። በዚሁ የእግዚአብሔርን ስም የሚያመሰግኑ ካህናትን አስቀመጠበት፡ በኋላ ዘመንም በክርስቶስ ደቀ መዝሙር በበርተሎሚዎስ ተጠምቀው ኑሪዎች ክርስቲያን ሆነው ነበር፡ በኋላ ግን የእስላም እምነት ተከታዮች ወጥተው ከተራራው ክርስቲያኖችን ገደሉአቸውና ጠፍ ሆነ። ነገር ግን ፩ኛ፤ በአፄ ይኩኖ አምካክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ አባ ተክለጽዮን የሚባሉ መናኝ ባሕታዊ የሚኖሩበትንና የፈራረሰውን ቤተ መቅደስ እንደገና አንጸው ብዙ ባሕታዊዎች በስውር ከኢሣ ተደብቀውይኖሩበት ነበር። ፪ኛ፤ ከደብረ ኪሩብ ወደ ቤተ ሐጌ በኩል ማለት ወደ ደቡብ ከደብረ ኪሩብ ተነስቶ ወደ ደብረ ወገግ የሚያርፍ ብርሃን ስለሚታይና እረቂቅን መላእክት ስለሚወርዱበት ወገሣ ወገግታ ስለታየበት ደብረ ወገግ ተብሏል። እርሱም የዛሬው አሰቦት ነው። ይህ ተራራ በዘመነ ኦሪትም ለእግዚአብሔር መስዋእት የሚዘጋጅበት ሥፍራ አለው፡ ብዙ መናንያን ባሕታዊያኖች ይኖሩበት ነበር፡ በኋላ ግን እንደ ደብረ ኪሩብ አረመኔዎች ስለአቃጠሉትና ስለአወደሙት ጠፍ ሆኖ ሲኖር የአቡነ ተክለሃይማኖት ደቀ መዝሙር የነበሩ አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተባሉ የቡልጋ ሰው ወደተራራው ወጥተው የፈራረሰውን ቤተ መቅደስ እንደገና አድሰው ሰሩ። ገዳሙን እንዳቋቋሙ ብዙ መናንያን መጥተው ይኖሩበት ነበርና በዚህን ጊዜ አፄ አምደ ጽዮን ወደ ተራራው ወጥተው መነኮሳቱን አጽናንተው ቤተከርስቲያኖችን በሰፊው አሰርተው የውኃ ጉድጓድም አስቆፍረው ሄደዋል። አፄ አምደጽዮን ለነዚህ ገዳሞች ጠላት የሆኑትን አረመኔዎችና አለቃቸውንም ኃይደራን ገድለው በምትኩ ሌሎችን ረሺድንና ፈቂህን ሾመው ሸልመው የሳርካንን ሹም ዮሴፍን አስረውና ይዘው ኤረር ሂዱ፡ በዚያም በምርኮ በተገኘው ወርቅ ለአድአጽዮን ቤተክርስቲያን ማደሻ ሰጡ። አድአጽዮንም መንበረ ወርቅ ተሰራላት፡ ጉልላቱም እንዲሁ በወርቅ ተሰራ። አፄ አምደጽዮን እግዚአብሔር አምላካቸውን የሚያመሰግኑ ስሙንም የሚቀድሱ ካህናትን እየሾሙ ሸለሙ ነገር ግን በጳጳሱ በአባ ያዕቆብ ስብከት የተወናበዱ ካህናት አሁንም ስም ማጥፋታቸውንና ማደማቸውን ስለሰሙ ብዙ ካህናት ተገርፈዋል ታስረዋልም። ለዚህም ሁሉ የሚያሳድሙትን ጳጳስ አባ ያዕቆብን ወደ ግብጽ መልሰው ላኳቸው። አፄ አምደጽዮን ካህናቱንና ሊቃውንቱን ጥሪ አድርገው እንግዲህ ለተዋህዶ ኃይማኖታችን መሪና አባት የሚሆን እናንተው ከናንተው መካከል ብጹዕ እና ቅዱስ የሆነውን ምረጡና ሹሙ፡ አይሆንም ካላችሁ ለዘመነ መንግሥቱ ከግብጽ ጳጳስ ማስመጣት ቀርቶ ከዚህ እንኳን መንፈሣዊ ሕይወቱና የአስተዳደጉ ታሪክ እምነቱም ሳይመረመር ዳባ በመልበሱ ቆብ በመድፋቱ የኃይማኖት አባት መሆን አይችልም ብለው ተናገሩ። በዚህን ጊዜ አፄ አምደጽዮን ሞግዚት ሆና ያሳደገቻቸውና አባታቸው አፄ ውድም አርእድ ፈቅደው ያጋቧቸውን ዳዲን ሲነግሡ ዣን ሞገስ ብለው ሰይመው ነበር፡ በኋላ ዣን ሞገስ መካን በመሆኗ አፄ አምደጽዮን ያለልኝ እንዳይቀሩ ብላ ሌላ ሚስት እንዲያገቡ ስላስገደደቻቸው ወደ ዙላ ሂደው ሳለ ከብሌን ነገድ ድርሂት የምትባል አገቡ፡ ስሟንም ዣን ሳባ ተብላ ተሰይማለች። ዣን ሳባ የተባለችው ድርሂት በአምደ ጽዮን ፈቃድ የትግሬ ንግሥት ከመበሏ ሌላ በኃማሴን ውስጥ ይባሩአ (ደብሩዋ) የተባለውን ከተማ ቆረቆረች ደባሩአ ወይም ይባሩዋ ከሚባለው ከተማ የሚቀመጥ በሥራዋ መላከ ኃይል በልአከ ባሕር መባሉ ቀርቶ ባሕር ነጋሽ ትግሬ ነጋሽ የቤተ ክህነቱ ደግሞ አቃቤ በአት እንዲባል አድርጋለች። እንዲሁ በግራ ባልቲሃት በንግሥቲቱ ትእዛዝና በአምደ ጽዮን ፈቅድ ከሰባት ነገዶች የተውጣጣው ሰራዊት በምድረ ከብድ ከሐማሴን ወጥቶ ስለሰፈረና ባለእርስት ስለሆነ ሰባት ቤት ጉራጌ ተብሏል። ይኽውም የግራይቱ ወይም የግራው ሰራዊት አገር ማለት ነው። አፄ አምደጽዮን በዘመነ መንግሥታቸው ኢትዮጵያን ከባሕር ጠረፍ እስከ ባሕር ጠረፍ እስከ ግብጽ ድረስ ባሉ ነገሥታት ላይ ገዝተዋል። የጠፋውንም አገር አልምተዋል። በዘመናቸው ግዛታቸውን የደፈረ አልነበረም፥ በሰላሳ ዘመነ መንግሥታቸው በተወለዱ በአምሳ ሰባት ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ታመው አረፉ። ከአፄ አምደጽዮን ቀጥሎ ልጃቸው ንዋየ ክርስቶስ ስመ መንግሥቱ አባቱ አምደጽዮን አክብሮ ይዞት በነበረው ሰይፈ አርእድ ተብሎ በአንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ስምንት /1328/ ዓ.ም. ነገሠ። ሠይፈአረእድ የተባለበት ምክንያት ይህ ሰይፍ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለማርሄር በግብፅ ምድር ሳለ “ኃይል ሆይ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ” ብሎ የሰጠው በተድባበ ማርያም ይኖር ነበርና የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እንዲታጠቁት ለአምደጽዮን በራእይ ነገራቸው፤ አፄ አምደጽዮንም ባህር ተሻግሮ የመጣን የእስላምን እምነት ተከታይ ሰራዊት ድል አድርገው አጥፍተውበታል።

ቀጣዩን በገፅ 7 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 6

Page 7: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

በእስክንድርያ ስር ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ውል እንዲዋዋሉና አፄ ዳዊትን ደህና አድርጎ በመስበኩና በማሳመኑ ግብራቸውንም ገጸ በረከታቸውንም እንዲያቀርቡ አድርጓል። የኢትዮጵያ ምእመናን በዘመነ ኦሪት ከቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ በሌዋውያን ካህናት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበሉትን አምልኮተ እግዚአብሔር ሥርአትንና ትእዛዛቶችን በሚፈጽሙበት ጊዜ ለማስተው የተለያዩ ጽሁፎችና ስብከቶች አዘጋጅቶ ነበር ሳይሆን ቀረ። በሳልስ ሠላማ አስፈላጊ እንዳልሆነ ከተሰበኩት መካከል ጥቂቶች ለአብርሃም የታዘዘውን ግዝራት በሙሴ ሕግ የተጻፈውን የመብል ስርአት የእግዚአብሔር ቃላት የተጻፈባቸውን ጽላቶችና ታቦተ ሕጉት በቅዱስተ ቅድሳት መቅደስ ውስጥ ማስቀመጥ በአዲስ ኪዳን ስለተሻረ አያስፈልጉም እያለ አስተምሮአል ጽፎአል፤ ነገር ግን በእየሱስ ክርስቶስ በባለቤቱ ቃል “እኔ ሕግና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” ባለው መሠረት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት የብሉይ ኪዳንና የአዲስን ኪዳን በተዋህዶ አዋህደው አጽንተው ኑረዋል።

ፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌ በአንዱ ድህረ- ገፅ “ዕርቅና ሰላም የሕህወት ቅመም” ብለው ጥፈው ነበር፡፡ ነገሩ እውነትነት ነበረው ሲተገበር ግና በጣም ከባድ መሆኑን እንዴት እረሱት፡፡ መልሱ ከእሳችውና ከአቻቸው ዘንድ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ የዛሬ 50 ዓመት ፕሮፈሶር ጌታቸው ሀይሌ የአማርኛ አስተማሬ ነበሩ እንደዚሁም ፕሮፈሰር ክላውድ ሳምነር የሎጂክ አስተማሪያችን ነበሩ፡፡ ፕሮፈሰር ሳምነር ካናዳዊ ዜግነትን ትተው ኤትዮጵያዊ በመሆን እጅግ ጠቃሚ ጥናት አካሂደው በቅርቡ አርፈዋል፡፡ካለማወቅ ወደ ማወቅ ተሸጋግረው የኢትዮጵያ ፈላስፋ ሆነዋል፡፡ ይሀንን ያደረጉት በዘርዓ ያዕቆብ፤ ፈላስፋው ኤትዬጵያዊ የጥናትና የምርምር ዘመቻ በማድረጋቸው ነበር፡፡ በአንጸሩ ደግሞ ፤ ዘረ-ኢትዮጵያውያን ምሁራን የንጉሱ ዘርዓ ያቆብ የሥልሣን ማዕርግ ብቻ በማቀንቀን ሕዝብን በማይጠቅም የንትርክ ስራ መሰማራታቸው ያውቁት ይሆን ካላወቁትም ያሳዝናል፡፡ ዕውቀትን መሻት ይሻላል ወይንስ መንበር/ወንበር? ? ፕሮፈሶር ሐይሌ እንደሚያውቁት በዛን ዘመን አዲስ አበባ ኮለጅ በተከፈተ ማግስት ማለቴ ነው፤ ፖለቲካና ታሪክ ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩ የዕውቀት ዘርፎች አልነበሩም፡፡ ፖለቲካ፤ታሪክና ስነ ጽሑፍ በጋርዮሽ ተጣምረው ትምህርታዊ ባልነበረው አካሄድ እንደተጋዙ ፕሮፈሰር ሐይሌ ያውቁታልና ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደ ወታደራዊና ፋሽስታዊ አገዛዝ (ደርግ)ለጥቆም ወደ ዝርያዊና ወገናዊ (ወያናዊ) አገዛዝ የተሸጋገረችው ከዚሁ ኮለጅ በተገኘው የተበረዘና ያልተበረዘ ጽንሰ-ሀሳብና ንድፈ-ሀሳብ ከዚሁ ከአዲስ አበባ በምሁራንና በጽንሓተ ምሁራን መካከል ግጭትና ክርክር የተመረኮዘ ነበር፡፡ የፖለቲካና የታሪክ ጥናትና ምርምር ሥፍራና ነጻነት ስለአልነበራቸው አማራጭ ሆኖ ለተማሪዎች የቀረበው የአማርኛና የጆግራፊ ክፍለ ትምህረት ነበር፡፡ በእኔ እምነት ጆግራፊና የቓንቃ ትምህርቶች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ በመሆናቸው መንግሥት ተጽእኖ በማድረግ መምሪያዎቹ እንዳያድጉ ተደርገዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡የአገራችንን መልከአ ምድር ሳናውቅ፣ የፖለቲካ ዕውቀታችንና ታሪካችን ሳናውቅ ሁላችን ተደናብረን አደናብረናል፡፡ ለዚሁ በምስክርነት ሊቀርቡ የሚችሉ ምሁራኖችና መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ • ፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌ • ፐሮፈሰር መስፍን ወልደ ማርያም • ፕሮፈሰር በረከት ሀብተ ሥላሴ እና • ታጋይ ስብሐት ነጋ የነዚህ ታላቆቻችን ግለ-ታሪክ፤ ፖለቲካዊ ስራዎቻቸው እና ዕውቀታቸው አሁንም በሕይወት ስለአሉ ማወቅና መረዳት አለብን፡፡በእኔ ግምት እነዚህ አዛውንቶች በቂ ትምህርትና ልምድ (Education and Experience) እያላቸው ለማን ለምንና እንዴት እንደሚያካፍሉት የቸገራቸው ይመስለኛል፡፡ በውስጣቸውም ሰላም ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የውጭውን እናውቀዋለን ግና የውስጣቸውን አናውቀምና ቢነግሩን ለሁላችንም ትምህርት ይሆነን ነበር፡፡ እነሱም ሰላም አግኝተው ለእኛም ዕርቁን ቢያወርሱን መንግሥተ ሰማያት በገቡልን፡፡ ይክን ሳያደርጉ ቢሞቱ ግን የኤትዬጵያ (ኤርትራንም ጨምሮ) ሕዝብ አይዞርበትም ትላላችሁ?? የአማርኛ ቃንቃ መገናኛ መሆኑ ቀርቶ ፍልስፈና/ዕውቀት ሲሆን (በጌታቸው)፤ የኤትዮጵያ መልከዐ ምድር (physical geography) ፖለቲካል ጆግራፊ ሲሆን (በመስፍን)፤ ኤርትራዊ ሥነ-መንግሥት እና ኢትዮጵያዊ አቃቤ ሕግነት ሲቀናጁ (በበረከት)፤ አብዮታችንና ዝርያእችን በጋራ ሲወሀሀዱ(በስብሐት)፤ አይዞርብን ትላላችሁ? የናንተን እንጃ፤ በበኩሌ ግና ዞረብኛል፡፡ ወጣቱ ትውልድ ቦታ ልቀቁ ብሎ ሲጠይቅ ከላይ

ዕርቅና ሰላም ? የፕሮፈሰሮችና የወያኔው መሪ ጉዳይ

.......ከገፅ 6 የዞረ

ንጉስ ዓምደፅዮን ሰይፉ የአረፈበት አለቱን ይሰነጥቀዋል፤ ድንጋይም ይሁን እንጨት ይበታተናል፤ የሰውን ገላ እንደጨርቅ ይቀደዋል፤ ስለዚህ አረቦች ይህ ሰይፍ ከአላህ የመጣ እንጂ በሰው እጅ የተሠራ አይደለም ይላሉ። ተሹመው በመጡት ጳጳስ ለማሰረቅ ተሞክሮ ሳይሆን ቀረ፤ እንዲሁ አፄ ልብነድንግል ለመታጠቅና ከግራኝ ጋር ለመዋጋት ፈልገው ሲሄዱ እግዚአብሔር ስለአልፈቀደ ከተድባበ ማርያም ወደሌላ ዋሻ ውስጥ በድብቅ እንዲቀመጥ ተደረገ። ስለዚህ ይህ ሰይፍ ከተድባበ ማርያም ወደሌላ ከመሄዱ በፊት ለንዋየ ክርስቶስ ስለአስታጠቁት ስመ መንግሥቱ ሰይፈ አርእድ ተባለ።አፄ ሰይፈአርእድ በአምስተኛው ዘመነ መንግሥቱ ወደ እናቱ አገር ሂዶ ገዳሞችን ጎብኝቷል፤ እንዲሁ ከአባ መድኃኒነ እግዚእ ከሚባሉት ባህታዊ ቡራኬ ከተቀበለ በኋላ እግዚአብሔር የሚወደውን ለማድረግ እፈልጋለሁና ይምከሩኝ አላቸው። አባ መድኃኒነ እግዚእም በግብፅ የሚኖሩትን ክርስቲያኖችና ጳጳሳት እስላሞች እያሰቃዩአቸው ነውና ሂደህ የታሠሩትን በሰላም ወይም በጦርነት አስፈታቸው ብለው መርቀው ወደ ግብፅ ላኩት። አፄ ሰይፈአርእድም ሰራዊቱን ክተት ብሎ ወደ ጉርአ ከሚባለው ላይ ሰልፉን አሳይቶ ወደ ኑብያ ሄደ። በዚህን ጊዜ የኑባው ንጉሥ ስናር የደንካን የዳንቡልንን የገሰናን ጎሣዎች እስከ አለቆቻቸው ሠላሳ ሺህ ቀስተኝ ሠራዊት ይዞ ቆየው። አፄ ሰይፈአርእድም ለግብጹ ሱልጣን የአሰርካቸውን ክርስቲያኖች ክርስቲያኖች ካልፈታህ የአፈረስከውን ቤተ ክርስቲያን መልሰህ ካልሰራህ አንተንና ሠራዊትህን ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፡ ባህር ማዶ የአለው ጌታህ ሊያድንህ አይችልም የሚል ደብዳቤ ተላከለት። የግብጹም ሱልጣን የተላከለትን መልስ ሳይሰጥ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ወደ አማርና መጣ፤ ከዚያም በአስዋን ከጠዋት እስከማታ ከተዋጉ በኋላ የግብፅ ሰራዊት ድል ሆነና ሸሸ፤ በዚህን ጊዜ ከአምስት ሺህ በላይ የእስላም እምነት ተከታይ ሰራዊት አለቀ፤ በኑብያና በኢትዮጵያ በኩል ሁለት ሺህ ሞተ። አፄ ሰይፈአርእድም ካይሮን ለመውረርና የታሰሩትን ለማስፈታት ሲዘጋጅ የግብጽ ከሊፋዎችና ሼሆች አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው ለአፄ ሰይፈአርእድ የታሰሩትን ክርስቲያኖችና ጳጳሳቱን እንደሚፈቱና ወደፊት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር የፍቅርና የሰላም ውል በሊቀ ጳጳሱ በአባ ጴጥሮስ በኩል እንደሚይደርጉ ታስረው የነበሩትን ምክትል ሊቀ ጳጳሱን አባ ማርቆስንና ሌሎችንም መንኮሣት ላኩበት። አፄ ሰይፈአርእድም ከጳጳሱ ቡራኬ ከተቀበለና ከግብጽ ሱልጣኖች ጋር ውል ከተዋዋለ በኋላ ኢትዮጵያ ጳጳስ አልነበራትምና አባ ሰላማ የሚባል መነኩሴ ተሰጥቶ ከምክትል ሊቃነ ጳጳስ ማርቆስ በሰላምና በፍቅር ተሰነባበተ። ከዚያም ያመጸውን አገር ወግቶ ድል አድርጎ ሹም እየሾመ ለአመነውም አለቃ እየሸለመ በእናሪያ ከፋ አድርጎ በሰላም ተጉለት ገባ። አፄ ሰይፈአርእድ የተባለው ነዋየ ክርስቶስ በ፪፰ ዘመነ መንግሥቱ በኢትዮጵያ አገር የተቅማጥ በሽታ ገብቶ ብዙ ሕዝብ ከጨረሰ በኋላ መጨረሻ እራሱ ታሞ ሞተ። አፄ ውድም ፍሬ (ንዋየ ማርያም ) ከንዋየ ክርስቶስ (አፄ ሰይፈአርእድ) ቀጥሎ በፈንታው ልጁ ነዋየ ማርያም ስመ መንግሥቱ ውድም ፍሬ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ /በ 1356/ ዓ.ም. ነገሠ። በአፄ ውድም ፍሬ ዘመነ መንግሥት በመላ ኢትዮጵያ እርሃብና በሽታ ሆኖ ስለነበር ከአንዱ አገር ወደ ሌላው አገር የሚዘዋወር ሰው አልነበረም። በዚህን ጊዜ የወላስማን መንበር ይዤ የክርስቲያኑን መንግሥት አጥፍቼ በሸሪያ ሕግ የእስላም መንግሥት አቋቁማለሁ ብሎ ሃቅ አድዲን አህመድ ለጦርነት ተነሳ፤ መጀመሪያ የይፋቱን ገዢ አጎቱን አቦበከር አሊን ገደለ፤ ከዚያም ተዘጋጅቶ መምጣቱን የሰማ አፄ ውድም ፍሬ የተባለው ንዋየ ማርያም ተዋግቶ ገደለው፡ ሃቅ አድዲም ከሞተ በኋላ ለዘጠኝ ዓመት ያህል አገሩ ሰላም ሆነ። እንደዚህም ሆነ፡ እንደ ግብፃውያን ዳግማዊ ሰላማ እንደ ኢትዮጵያውያን ሳልሳዊ ሰላማ ማለት ከሣቴ ብርሃን የተባሉትን ሰላማን ግብፃውያን ከእስክንድርያ መንበረ ማርቆስ በጊዜው ከነበሩት ከአትናትዮስ የጵጵስና ስልጣን እንዳልተሰጣቸው ስለሚያምኑና ስለፃፉ ነው፤ ነገር ግን ከሣቴ ብርሃን ሰላማ በኋላ ማቴዎስ የሚባለውን በአፄ ዋዜብ ዘመነ መንግሥት ሊቀ ጳጳሱ ቄርሎስ በከሣቴ ብርሃን ሰላማ ስም አዲሱ ሰላማ ብሎ ሹሞ ልኮት ነበር፤ እርሱንም ኢትዮጵያውያን ነዑስ ሰላማ ብለውታል፤ የኢትዮጵያን የቀደምት መጽሐፍትን ያስጠፋና በምትኩ የአረብኛን መጽሐፍት ያበዛና ያስተማረ ነበረ። ይህ ግብጻውያን ዳግማዊ ሰላማ ያሉት ጳጳስ በንዑስ ሰላማ የተጀመረውን የመጽሐፍት ትርጉም፡ ማለት በእስክንድራውያን መጽሐፍት ከአረብኛ ብቻ እንደተቀዱ የሚያስተምርና በአፄ አምደጽዮን ዘመነ መንግሥት የተጻፉትን መጽሐፍት መነኮሳትና ቀሳውስቱ እንዲያነቧቸው ያደረገ ነው።ስለዚህ ስሙን ካልእ ሰላማ ወይም ዳግማዊ ሰላማ ተብሎ ተሰይሟል። እርሱም ለአርባ ዓመት ያህል የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መርቷል፤ ነገር ግን በአባ ሰላማ ሰላማ ዘመን የኢትዮጵያ ነገሥታት የአገር ድንበር መጠበቅ ቀርቶ ለራሳቸው እንኳን ስማቸውን የሚያስጠራ ከተማ አልቆረቆሩም። ከእነርሱም መካከል ስማቸው የታወቀው አፄ ዘረያእቆብ ደብረ ብርሃንን ቢቆረቁሩም በደራሲነታቸውና የደረሷቸው መጽሐፍት እስከዛሬ ድረስ በየአድባራቱ ስለሚገኙ ነው እንጂ አባ ሰላማ የእስላም እምነትን የሚከተሉትን ወገኖች ሲረዳና ሲመክር የነበረ በኋላም ጥላቻውና ጠቡ እያየለ ሄዶ ግራኝ መሐመድን ያስነሳ ነው። እነዚህን በመሰሉ ጳጳሳት ከይኩኖ አምላክ እስከ አፄ ልብነ ድንግል የነበሩ ነገሥታት ለአገራቸው እንደ አክሱማይ የአክሱምን ሐውልት እንደ ቅዱስ ላሊበላ ከአንድ ወጥ ድንጋይ አለት የጠረቡ አብያተ ክርስቲያናት ሳይሰሩ አልፈዋል። አፄ ዳዊት ( ንጉሥ ይበቃል ) አፄ ውድም ፍሬ የተባለው ነዋየ ማርያም በነገሠ በአስረኛው ዘመነ መንግሥቱ በተቅማጥ በሽታ ታሞ ስለሞተ ወንድሙ ዳዊት የተባለው ይበቃል ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በ 1366 ዓ.ም. ነገሠ። በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ሣልስ ሠላማ ወይም ካልዕ ሠላማ የተባለው ጳጳስ በዘመነ ጵጵስናው ኢትዮጵያ ለግብጽ ሙሉ በሙሉ የኃይማኖት ጥገኛና

የተጠቀሱትን ግለሰቦችና አስተምሮአቸውም ጭምር ይመስለኛል፡፡እነሱም ቢረዱዋቸው መልካም በሆነ ነበር፡፡ ወጣቱም እንደእነሱ አስቦ ማለት በስፍራ (ሰፔስ) ሳይሆን በአስተሳሰብ (በጊዜ ልዩነት) ማለቴ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፐሮፈሰር ጌታቸውንና ፕሮፈሰር በረከት በአንድ ዐይን መታየት አለባቸው፤ ፕሮፈሰር መስፍንና አቶ ስብሃት አብረው መጣመር አለባቸው፡፡ ይከም ሲባል ሰዎቹ እንዲዋደዱና እንዲፋቀሩ አይደለም፡፡ ሰላም ቢፈጥሩ መልካም ነበር ከፈጠሩ ዕርቅና ሰላም የሕወት ቅመም እንዳሉት ፕሮፈሰር ጌታቸው ይሆናል እሰየው ነው፡፡ እኔ ግና መጀመሪያ ዕርቅ ይቀድማል ሲባል ስለ አማርኛ እንደ ቃንቃ በጌታቸውና በበረከት አመለካካት መጣጣም አለባቸው፤ እንደዚሁም መስፍንና ስብሀት በፊዚካል ጆገራፊ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካል ጆግራፊያ መታረቅ አለባቸው አለበለዚያ ሁሉም መርዛቸውን መርጨት ይቅርባቸው ነው የምለው፡፡ ዕርቅና ሰላም በጣምራ ለማካሄድ የነዚህ አራት ግለሰቦች ሰላም መፍጠር ወሳኝነት አለው፡፡ ይህ ካልሆነ ግና ዕርቅና ሰላም ለየግላቸው በየተራ እንደ አመጣጣቸው እንዲታረቁ ይሆናል፡፡ አድራጊውም እገዚ-አ-ብሔር ይወቀው፡፡ ለአያሌ ዓመታት “ሳይንሳዊ” ባልሆነ መንገድ ጥናት ሳካሂድ ነጻነትና ሐርነት፤ንቃትና ድርጅት፤ትግልና ምርት ዕርቅና ሰላም፤ አንድነትና ዴሞክራሲያ ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቅደም ተከተላቸውም መላ ቅጡ የጠፋ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ምክንያቱም አብዮትና ጦርነት በጥምር በሕብረሰባችን ይጋዙ ስለነበሩ ነው፡፡ ለማነኛውም በአሁኑ ሰዓት ጦርነቱ ቆሞ አብዮቱ ግና እየተካሄደ ስለሆነ ዕርቅና ሰላም አብረው መሄድ ያለባቸው ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡ ለምን አብረው ይጋዛሉ ተብሎ ሲጠየቅ እስከ አሁን በጣምራ ያካሄድናቸው ብቻ ሳንሆን አንዱ ከአንዱ መለየት ስለማንችል ነው፡፡ ለማስረዳት ያህል በሕብረ-ሰባችን አባባል ጠጅን በብርሌ ነገርን በምሳሌ እየተባለ ለዘመናት ተጠቅመንበታል፤ አሁን ግና ብርሌም የለ ምሳሌም የለ፡፡ጠጅና ነገር ግና በሽ-በሽ ነው ይባላል፡፡ ብርሌዎች ወጣቱ ትውልድ ሲሆኑ ምሳሌዎቹ ደግሞ ጌመበስ (ጌታቸው-መስፍን-በረከትና ስብሃት) ከላይ እንደጠቀስኩት በትምህርትና በልምድ የተካኑ ናቸው፡፡ አራቱ በግላቸው ሰላም ቢያወርዱ ሺዎቹ ዕርቅ በፈጠሩ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ያለፈውን የትግል ጉዞአችን ካላገናዘበ፤ ሽማግሌው ትውልድ በበኩሉ የልጆቹን ፍላጎት ካላወቀ፤ የተፈለገው ዕርቅና ሰላም ቀርቶ የግሪክና የኢራን ዕጣ ፈንታ በእኛ ላይም የማይደርስበት ምክንያት አይታየኝምና ነው፡፡ Source http://www.abugidainfo.com/ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ መግለጫ Ethiopian Border Affairs Committee P. O. Box 9536 Columbus, Ohio 43209 USA E-mail: [email protected]

"ውሸት ቢደጋገም እውነት አይሆንም"

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ/ም (July 5, 2015 ) የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግንባር (ወያኔ) መራሹና በሰሜን ሱዳን መንግሥት መካከል በምስጢር የሚደረገውን የድንበር ውል እየተከታተለ ሲያጋልጥ የነበረና ዛሬም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ደባውን ይፋ እያደረገ ይገኛል። በድንበሩ ዙሪያ የሚደረጉ የድብቅ ውይይቶችንና የሚደረስባቸውን ስምምነቶች በሁለቱ አገሮች ሕዝቦች መካከል በሰላም አብሮ በጉርብትና መኖርን የሚያሳጣና ክልሉን የጦርነት ቀጠና ሊያደርገው እንደሚችል ባለፉት በርካታ ዓመታት በጽሑፍና በመገናኛ ብዙኀን ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ አስገንዝበናል። ይኽን የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት የተጻረረ ድርድርና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት የተሰጠውን የድንበር መሬት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በተጨማሪ በአገር ቤትና በውጪ የሚገኙ የማኅበረሰብና የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ታዋቂ ግለሰቦችና ምሑራን እንደመሰከሩት፤ ሱዳንን የሚያዋስነው ረጅሙ የኢትዮጵያ ድንበር በጀግኖች ወገኖቻችን የሕይወትና የደም ዋጋ የተከፈለበት፣ በአካባቢው የሚገኘው ሕዝብና በተከታታይ መንግሥታት ተከብሮና ተጠብቆ ለትውልድ ያወረሱት የብሔራዊና የግዛት አንድነታችን መገለጫ፤ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የማንነታችን ነፀብራቅ ነው። ዜጎች ለሕይወታቸው የሚመኩበት ለልማትና ለአገር ደህንነት ቁልፍ የሆነ፣ ማእድን፣ ለም መሬት፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ የዱር እንስሳት፣ ደንና በርካታ የተፈጥሮ ሀብት የሚገኝበት ነው። በመሆኑም ይህን የማንነታችን መግለጫ የሆነው ድንበር መሬታችን ለድርድር ሊቀርብ እንደማይገባና ሊቀርብም እንደማይችል አስገንዝበናል፤ ዛሬም በጥብቅ ለማሳወቅ እንወዳለን። ቀጣዩን በገፅ 8 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 7

Page 8: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታትና እኛ የምንለው ግዌንና የወከለው የእንግሊዝ መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት ሳይፈቅድ፤ ሳይፈርምና ተወካዮች ሳይልክ ግዌን ይኼን ለማድረግ በፍጹም መብት የለውም፤ አይችልም። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ግዛታዊ አንድነት አንፃር ሲታይ ደግሞ በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው ነው። ሶስት፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን የወያኔ አገዛዝንና የአማራውን ክልል በመወከል 1,600 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን መሬት “ለሱዳን ሰጥቷል” የሚለውን ትችትና አቤቱታ አስተባብሏል። እኛ የምንጠይቀው ከላይ በአንድና በሁለት ያቀረብነው የኢትዮጵያ ተከታታይ መንግሥታት መመሪያ የሆነው መርህ ተጥሷል ወይንስ ተከብሯል የሚል መሠረታዊ የፖሊሲ ጥያቄ ነው። “የኢትዮጵያ መንግሥት አንድም ኢንች መሬት አልሰጠም”፤ የአማራው ክልል ኃላፊዎች የድንበር ድርድር ለማድረግ መብት የላቸውም" ብሏል። አራት፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የተናገረው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሰጠው መግለጫ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለው “እኛ የተከተልነው ከእኛ በፊት የነበሩ መንግሥታት የተቀበሉትን ውል ከሥራ ላይ ማዋል ብቻ ነው” የሚል ነው። ሁለቱም ባለሥልጣናት የሚናገሩት ከእውነቱ የራቀ የመንግሥት ክህደት ብቻ ሳይሆን ተከታታይ መንግሥታት ያልተቀበሉትንና ከሥራ ላይ ያላዋሉትን የግዌንን ጎጂ የድንበር ችከላ ለሱዳን መንግሥት ጠበቃ በመሆን ስኬታማ ለማድረግ የሚደረግ ጥረትና የክህደቶች ሁሉ ክህደት መሆኑ ነው። ከላይ በቁጥር አንድ ላይ እንዳቀረብነው ግዌን የቸከለውን ድንበር ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት እንዳልተቀበሉት በሕይወት የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በምሥክርነት ቀርበው በኢሳት አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለታሪክ ሠፊ መግለጫ ሰጥተውበታል። እኛም ደጋግመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምንና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን የምንጠይቀው ያለፉት መንግሥታት ከሱዳን መንግሥት ጋር የፈረሙት የተለየ ውልና የችከላ ድርድር ካለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአስቸኳይ ማስረጃውን እንዲያቀርቡ ነው። ነገር ግን የአገርን ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ሤራ በህዝብ፣ በታሪክና በሕግ የሚያስጠይቅ እንደሚሆን አንጠራጠርም። አምስት፦ በተከታታይ በማስረጃ እንዳቀረብነውና ወደፊትም እንደምናቀርበው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ብሄራዊ አንድነትና ደኅንነት፣ የረጅም ጊዜ እድገትና ጥቅም፣ የሕዝቦቿን ሕይወትና የኑሮ መሻሻል፣ የአገሪቱን ሰላም አደጋ በሚጥል ሁኔታ ከሱዳን ሕዝብ ጋር ያላትን ታሪካዊና ተሳስቦና ተከባብሮ የመኖር ግንኙነት... ወዘተ ለወዳጁ ለሱዳን መንግሥት መካካሻ ለማድረግ ምንም ሥልጣንና መብት የለውም። ይህን ክህደት የኢትዮጵያ ህዝብ ሊታገለውና ሊያጋልጠው እንደተነሣ እምነታችን ነው። ስድስት፦ ሌላው የወያኔ ባለሥልጣናትና ሥርዓታቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እየደጋገሙ የሚናገሩት ውሸት በቅርቡ አቶ ደመቀም ይፋ ያደረገው ጉዳይ ነው። ይኼውም፤ እ. አ. አ. በ1996 በኢትዮጵያ ከፍተኛ አለመረጋጋት የተከሰተበትን ሁኔታ በመጠቀም ሱዳን ወይንም የሱዳን ዜጎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የወሰዱትን ለም መሬት የኢትዮጵያ መሆኑ እያወቁ ገጽ 3 ወያኔ ከሱዳን ነጥቆ ወስዶት የነበረውን ነው የመልስነው ያለውን ነው። ይህ የተገላቢጦሽ አባባል የወያኔ መሪዎች የሱዳን መንግሥት የዋለላቸውን ውለታ ለመክፈል የሚደረግ ሤራ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እንዳስነብበው “However, the Ethiopian government says it only gave back lands occupied in 1996 which belongs to Sudanese farmers adding no single individual from both sides was displaced at the borders as a result.” (የኢትዮጵያ መንግሥት የሚለው ግን፤ እ.አ.አ. በ1996 የያዝኩትን የሱዳን ገበሬዎች ይዞታዎች የነበሩትን መሬቶች ነው መልሸ የሰጠሁት፤ እንዲሁም በዚሁ ሳቢያ በሁለቱ ወገኖች በኩል በድንበሩ ላይ ያለ አንድም ግለሰብ የተፈናቀለ የለም።) በወቅቱ የወያኔ መከላከያ ሚኒስትር የነበረውና በጉዳዩ ላይ የቅርብ እውቀት ያለው አቶ ስየ አብርሃ “ኢትዮጵያ ከሱዳን መሬት አልወሰደችም። እንዲያውም ሱዳን የወቅቱን አለመረጋጋት በመጠቀም የኢትዮጵያን መሬት ወስዳ ስለነበር ያንን መሬት ነው ያስመለስነው" በማለት በወቅቱ የወያኔ ባለሥልጣናት የተናገሩትን ውድቅ በማድረግ የጻፈው ጽሑፍ በተለያዩ ድረ-ገጾች ቀርቧል። በመጨረሻም፦ የኢትዮጵያና የዓለም ሕዝብ እንዲያውቀው የምንፈልገው ጉዳይ የወያኔ አገዛዝ ጫካ ውስጥ በሚታገልበት ወቅት የመሣሪያ፣ የገንዘብ፣ የስለላ ተባባሪ፣ አጋርና አመቻች፣ መግቢያና መውጫ ሆኖ በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ ያገለገው አገርና መንግሥት ሱዳን ነው። ወያኔ 39ኛውን በዓል በየካቲት 11, 2006 ዓ/ም በመቀሌ ሲያከብር በበዓሉ የተገኘው የሱዳኑ ጄኔራል አል ፋታህ የተናገረው ዋቢ ነው። “እኔም፣ ሌሎችም አብረን ተባብረን ወያኔን ለድል አብቅተነዋል። እኔም ወያኔ ነበርኩ፤ አሁንም ነኝ…….መለስና አል ባሽር የሚተማመኑ ወንድማማቾች በአል በሺር ቤተ መንግሥት እየተገናኙ

...ከገፅ 7 የቀጠለ

ውሸት ቢደጋገም.....

የሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ (Sudan Tribune) በJune 21, 2015 (ስኔ 14 ቀን 2007 ዓ/ም ) እንደዘገበውና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) በሥርጭቱ እንደገለፀው ዛሬ የወያኔ አገዛዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሁኖ የሚያገለግለው የቀድሞው የአማራ ክልል የበላይ ባለሥልጣንና ከሱዳን መንግሥት ጋር የድንበር ውሉን ተደራድሮ የፈረመው አቶ ደመቀ መኰንን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደ መንግሥታዊ ስብሰባ ላይ ከተገኙ ተሳታፊዎች ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን ለም መሬት አሳልፎ ለሱዳን መንግሥት አልሰጠም” ብሏል። ይህን አባባል፤ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ አንዲሉ ቀደም ሲል የተፈራረመውን ውልና ያደረገውን የአገር ክህደት ረስቶ ዛሬ ለምን እንደሚክድና እንደሚያስተባብል ሊገባን አልቻለም። በድጋሚ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው፣ በተለይም አዲሱ ትውልድ እንዲገነዘበውና ወደፊትም በዚህ ጉዳይ ላይ ለሚነሱ ክርክሮች እንደ ማስረጃ እንዲቀርብ የምንፈልጋቸውን ዋና ዋና ማስረጃዎችን እንደሚከተለው እናቀርባለን። ይኸውም፥ አንድ፦ እ.አ.አ በ1902 በአንድ በኩል የአፄ ምኒልክ መንግሥት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ግብፅንና ሱዳንን በበላይነት ይመራ ከነበረው ከቅኝ ገዥው የእንግሊዝ መንግሥት ጋር የተዋዋሉት ውል ግልጽ መሆኑን በተደጋጋሚ በጥናት በተደገፈ ማስረጃ አቅርበናል። ይህንን ውል መሠረት በማድረግ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊና ለአፍሪቃ አንድነት ማኅበር ዋና ኃላፊ ወያኔ ከዚህ ውል ውጭ የሚያደርገውን ማንኛውንም ስምምነት እንደማንቀበል አቋማችን አስመዝግበናል። አሁንም በተደጋጋሚ ልናሰምርበት የምንፈልገው ዓበይት ጉዳይ፤ ወያኔ የፖለቲካ ሥልጣን ከመያዙ በፊት የነበሩት የአፄ ምኒልክ፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴና የደርግ መንግሥታት የሚሉት ተመሳሳይ መሆኑን ነው። ይኼውም የውሉ አንቀጽ አንድ አስኳል የሆኑ የድንበሩ አመልካቾችን ያሳያል። የውሉ አንቀጽ ሁለት ድንበሩን ለመቸከል ሁለቱ መንግሥታት ተወካዮቻቸውን ሰይመው የተወከሉት ሰዎች በተገኙበት ብቻ የድንበሩ አቸካከል ድርድርና ተግባራዊነት ይፈፀማል፤ ለሕዝብም ይፋ ይሆናል የሚል ነው። ይህም የሚደረገው አፄ ምኒልክ በፈረሙትና በቀይ ምልክት ባደረጉበት ካርታ መሠረት ብቻ ነው። ተከታታይ መንግሥታት ይህን ውል እንደተቀበሉና የኢትዮጵያን ድንበር መብት እንዳስከበሩ ካሉት በርካታ መረጃዎች በተጨማሪ በሕይወት የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስለ ጉዳዩ ኢሳት ባቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሳያውቀውና ሳይስማማበት በሌላ መንግሥት ወይንም ተወካይ የተደረገ ውል ተቀባይነት እንደሌለውም አስምረውበታል። ሁለት፦ የአፄ ምኒልክ መንግሥት ሳያውቀውና ሳይስማማበት፤ የእንግሊዝ መንግሥት በራሱ ውሳኔ ሻለቃ ቻርለስ ግዌን የተባለ መኃንዲስ ሠይሞ በፈለገውና በመሰለው መንገድ የሱዳንና የኢትዮጵያን ድንበር አድሏዊ በሆነና ኢትዮጵያን በጎዳ መንገድ የቸከለው የድንበር ምልክት በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ተቀባይነት አግኝቶ አያውቅም። ስለሆነም፤ የወያኔ አገዛዝ ራሱ በፈጠረውና ትርጉም በሰጠው ወይንም ወዳጁና ባለውለታው የሆነውን የሱዳን መንግሥት ለመጥቀም የኢትዮጵያን መብት የሚጻረረ ድርድርና አዲስ የድንበር ምልክት ችከላ ተቀባይነት የለውም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን “የኢትዮጵያ መንግሥት የቀድሞውን ውል አፀደቀ እንጅ መሬት አልሰጠም” ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ የማድረግ ኃላፊነት አለበት እንላለን። “ውሉን አስፈጸመ” ሲል ምን ማለቱ ነው? ተከታታይ መንግሥታት የተመሩበትን አፀደቀና አስከበረ ወይንስ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ውል ተፈራርሞ ሥራ ላይ አዋለ? ይህን መመለስ ያለበት የወያኔ አገዛዝ ነው። የኢትዮጵያን ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ያደረጋቸው ጥናቶችና ሌሎች እውቅና ያላቸው የታሪክና የሕግ ባለሞያዎች ያረጋገጡት የወያኔ አገዛዝ መቀበልና ማክበር ያለበት። ግዌን ኃላፊነት በጎደለው የኢትዮጵያ መንግሥትና ተወካዮች በሌሉበት፤ የውሉን አንቀፅ ሁለት በተፃረረና ባፈረሰ ሁኔታ እ.አ.አ በ1903 የቸከለው የድንበር መለያ ችካል ተቀባይነት እንደሌለው ነው። በተጨማሪም ግዌን ችካሉን ሲቸክል የግል ውሣኔ አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ሃያና ስድሳ ኪሎ ሜትር ገብቶ ብዙ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን እንዲሰጥ አድርጓል። ይህ እንግሊዞችንና ሱዳንን ወክሎ ያደረገው ግፍ የውሉን አንቀጽ አንድና አንቀጽ ሁለት ሙሉ በሙሉ ይጻረራል። በራሱ ግንዛቤ ያደረገው አቸካከል በግሉ በራሱ ውሣኔ እንደሆነ ተቀብሏል (Gwen noted that he acted “ultra-virus,” meaning, he went beyond his power. ይህም

ማለት- ግዌን እራሱ እንደዘገበው ከተሰጠው ሥልጣን በላይ መሄዱን አምኗል።) ከወያኔ አገዛዝ በስተቀር

የተመካከሩ፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በጋራ የተዋጉ፤ ማስረጃ የተለዋወጡ፤ የወያኔን ተልእኮ የተጋሩ ነበሩ… ወያኔ ድል እንደተጎናፀፈ መሪዎችን በሱዳን ልዩ አውሮፕላን ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ አጅበው ከሄዱት መካከል ነበርኩበት…” ወዘተ ሲል በአል በሺር መንግሥትና በወያኔ መካከል ያለውን የጠነከረ ግንኙነት አስምሮበታል። ስለሆነም፤ የህወሓት መሥራቾችና መሪዎች የሱዳን ባለውለታ መሆናቸው ምንም አያከራክርም። እኛ የምንከራከረው፤ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ውለታ ከፋይ መሆን የለባቸውም ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የህወሓት አገዛዝ “አንድም ኢንች መሬት ለሱዳን አልሰጠም፤ የሚያስፈፅመው ተከታታይ መንግሥታት የተዋዋሉትን ብቻ ነው። ለሱዳን የሰጠነው መሬት ኢትዮጵያ የወሰደችውን ነው” የሚለው ሁሉ የውሸት ክምር ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የለውም። "ውሸት ቢደጋገም እውነት አይወጣውም"። የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ማንኛውም በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖረውን አገር ወዳድ ሁሉ የሚጠይቀውና የሚያሳስበው ወያኔ የሚያካሂደውን ኢትዮጵያን የሚጎዳ ሕገ ወጥ የድንበር ውል አፈጻጸም መቃወም ታሪካዊ ግዴታው መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የአገሪቱን ዳር ድንበር፤ ግዛታዊ አንድነትና ሉዓላዊነት የማስከበር ኃላፊነት አለበት። የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለማንም የውጭ አገር የማስተላለፍ መብት እንደሌለውና ነገ ጠዋት ደግሞ በኢትዮጵያ ሕዝብና በታሪክ ተጠያቂ የሚያደርገው መሆኑን በድጋሚ አስረግጠን እናሳውቃለን። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በቆራጥ ልጆቿ ይከበራል! ድል ለጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ! ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር! ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com July 5, 2015

የአዉሮጳ ኅብረትን ያወዛገበዉ የስደተኞች ጉዳይ

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ወደአዉሮጳ ግዛት የገቡ ስደተኞችን ለአባል ሃገራት በሚያከፋፍሉበት መሠረታዊ መመሪያ ላይ መስማማት እንደቻሉ እየተነገረ ነዉ። ሆኖም ግን መሪዎቹ 40 ሺ የሚሆኑትን ጥገኝነት ጠያቂዎች በምን መልኩ ለየሃገራቱ እንደሚያከፋፍሉ ዝርዝሩን አልገለፁም። የአዉሮጳ ኅብረትን ያወዛገበዉ የስደተኞች ጉዳይ አፍሪቃና መካከለኛዉ ምሥራቅ ሃገራት ዉስጥ የሚካሄደዉ ግጭትና ጭቆና በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖችን ከለላ ፍለጋ ወይም ለተሻለ ሕይወት ወደአዉሮጳ እንዲጎርፉ እየገፋፋ መሆኑ እየታየ ነዉ። በርካቶችም ወደአዉሮጳ እንገባለን ብለዉ መንገድ ላይ ሕይወታቸዉን አጥተዋል። ጣሊያን ለአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ጠንከር ያለ አቤቱታና ማሳሰቢያ ማቅረብ ከጀመረች ሰነባብታለች። በትናንታዉ ዕለትም የኅብረቱ መሪዎች ለስደተኞች ጥገኝነት ስለመስጠት ለመነጋገር ማምሻዉን ሲሰባሰቡም የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማቲዮ ሬንዚ እንደአዉሮጳ ኅብረትነታችን ወይ ትብብራችሁን አሳዩን አለያም ጊዜያችንን አታባክኑ በማለት የመጨረሻ ቃል እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። ከአባል ሀገር ጎን የማይቆም የአዉሮጳ ትብብርም በአፍንጫችን ይዉጣ ዓይነት ነዉ ሬኒዚ ለ27ቱ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ያስተላለፉት መልክዕት። ጣሊያንና ወደአዉሮጳ የሜዲትራኒያን ባህርን በጀልባ እያቋረጡ ለሚገቡ በርካታ ስደተኞች መሸጋገሪያ መሆኗ ከአቅሟ በላይ በስደተኞች እንድትጥለቀለቅ ስላደረጋት ሌሎች የኅብረቱ ሃገራት ሸክሟን እንዲጋሩ ማሳሰብ ከጀመረች ሰነባብታለች። ግሪክም በተመሳሳይ ካለባት የፋይናንስ ቀዉስ ባልተናነሰ የስደተኞች መበራከት አስጨንቋታል። ለአብዛኞቹ ስደተኞች ደግሞ ጣሊያንም ሆነች ግሪክ መሸጋገሪያቸዉ እንጂ መድረሻ ግባቸዉ አይደሉም። ድንበር አልፎ ወደሌሎቹ የአዉሮጳ ሃገራት ለመዝለቅ ግን ጥገኝነት ለመጠየቅ በመጀመሪያ የገቡበት ሀገር የሚለዉ የኅብረቱ ስምምነት ስለሚያግዳቸዉ የሁለቱ ሃገራት ዕዳ መሆናቸዉ አልቀረም። EU-Staaten Streit um Flüchtlingsfrage

ቀጣዩን በገፅ 9 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 8

Page 9: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ከገፅ 3 የዞረ

ከብር 6 ሚልዮን ወ/ሮ መና እንደሚሉት፣ ሰነዶቹ እና መዛግብቱ ያልተመረመሩ ብቻ አይደሉም፡፡ የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ በመጣስ ተፈጽሟል የሚሉት የአስተዳደርና የፋይናንስ አሠራር ችግር እንዲጣራ ለፓትርያርኩ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ያለአግባብ የባከነውና የተመዘበረው የብዙኃን ምእመናን ገንዘብ በሀ/ስብከቱ በሚመደቡ ሠራተኞች ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ በቋሚ ሲኖዶስ መመሪያ የተሰጠበት ከፍተኛ ክሥ ያለባቸው ሰነዶች እና መዛግብትም ናቸው፡፡ ይህንንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ከመሾማቸውም በፊት እንደሚያውቁት ያወሱት ሒሳብ ሹሟ፣ ሳይመረመሩ ከብር 54 ሚልዮን በላይ ገቢና ወጪ የሠራኹባቸውን ሰነዶች እና መዛግብት እንደ ቀላል ወረቀት አስረክበው ይውጡ ማለት ‹‹ከአንድ ተቋም ሓላፊ የሚጠበቅ አይመስለኝም፤ አጥፊዎቹ ወገኖቼ ናቸውና ተደብስብሶ እንዲቀርላቸው በማሰብ ነው፤›› ይላሉ፡፡ በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት የሒሳብ ብክነቱን ለማጣራት፣ የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ዋና ክፍል ሓላፊ ባሉበት ልኡክ በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ምርመራ ቢካሔድም ውጤቱ የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ሒሳብ ሹሟ ይገልጻሉ፡፡ ሓላፊው እንኳንስ በደብዳቤ ለምርመራ ተልከው ገንዘብ ጠፋ፤ ንብረት ባከነ ሲባል አጣርተው ለውሳኔ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው ያስገነዘቡት ሒሳብ

ሹሟ፣ ‹‹ቁጥጥር ሳይኾን ቁጥርጥር ነው የያዙት›› ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡ ውሳኔን በውሳኔ በመሻር ከደብሩ የሕንፃ ገቢ ላይ ከብር ስድስት ሚልዮን በላይ ወደ ግለሰቦች ኪስ መግባቱ፤ በውል ላይ ውል በመዋዋል ከአንድ የሕንፃ ኪራይ ብቻ ብር 487,869.32 መመዝበሩ ለቋሚ ሲኖዶሱ ካቀረቧቸው አቤቱታዎች እንደሚገኙበት ሒሳብ ሹሟ ይዘረዝራሉ፡፡ ይህንንም የሕንፃ አጣሪ በሚል ተሠይሞ በደብሩ ጽ/ቤት ለተገኘ ሌላ ኮሚቴ ከመዝገብ ቤት ፋይል እያስቀረቡ በጋራ በማየት መተማመን ላይ ቢደርሱም ‹‹እስከ አኹን ውጤቱ

የት እንደደረሰ አይታወቅም›› ይላሉ፡፡ ሒሳብ ሹሟ በስፋት ከዘረዘሯቸውና በየጊዜው በሚካሔዱ ማጣራቶች ቢረጋገጡም ውጤት ላይ አልተደረሰባቸውም ካሏቸው ሕገ ወጥ አሠራሮች መካከል፡- የቀድሞው አስተዳዳሪ ባልተሾሙበት ዘመን ወደ ኋላ እየተመላለሱ አግባብነት የሌለው ወጭ አድርገዋል፤ በአንድ ወር ከአበልና ከነዳጅ ውጭ እስከ ብር 8,000 በሠንጠረዥ እየፈረሙ ወስደዋል፤ ለአንድ የሰበካ ጉባኤ አባል በወር እስከ ብር 30,000 ወጪ ተደርጓል፤ የበዓል መዋያ ድጎማ ተከፍሏል፤ በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ ከቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ ውጭ ቅጥረኛ ተደርገዋል፡፡ ጥራት ለሌለው የሕንፃ ጠርዝ መሠረት ሥራ፣ ጄኔሬተር ለማዘዋወር፣ ለመኪና እድሳት፣ ለካህናት ጊዜያዊ ቤት ሥራ ጥናት የጎደላቸው ወጭዎች ተደርገዋል፤ በሰኔ 2006 ለኹለት የሰበካ ጉባኤ አባላት ብር 250,000 በአስቸኳይ ወጭ ኾኖ ያለደረሰኝ በሞዴል 6 እንዲከፈል ሕገ ወጥ ትእዛዝ በማዘዝ፤ በነሐሴ 2006 ለደመወዝ ከተወሰነው በላይ በልዩነት ከብር 236,000 በላይ ወጭ በማድረግ የደብሩ ካፒታል ተንዷል፤ የደብሩ ጠበቃ በፍርድ ቤት የተከሰሱ ተከራዮች ውዝፍ ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ለማድረግ ሲዳረስ ክሡን በይቅርታ በማንሣት በምትኩ የደብሩ ገቢ ለግል ጥቅም ውሏል፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡ ወ/ሮ መና እንደሚገልጹት፣ የተጣሩት ሕገ ወጥ አሠራሮች ውሳኔ ሳያገኙ በመቅረታቸው እና ርምጃ ባለመወሰዱ ‹‹ያለፉት አጥፊዎች ምን ተደረጉ?›› በማለት በወቅቱ የደብሩ እና የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪ የተለቀቀ ሱቅ በጨረታ ማከራየት ሲገባቸው ሽያጭ አካሒደዋል፤ ቤተሰቦቻቸውን አስቀጥረዋል፡፡ በሚያዝያ 22 እና ግንቦት 22 የቅዱስ ዑራኤል ክብረ በዓል በዐውደ ምሕረት አስተዳዳሪው በተቀመጡበት ምንጣፍ እና በስእለት ከምእመናን የተሰበሰበ ገንዘብ ሳይቆጠርና በደረሰኝ(በሞዴል 30) ገቢ ሳይደረግ በሻንጣዎች ተሞልቶ ተወስዷል፤ የት እንደገባም አይታወቅም፡፡ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራው በባንክ የመቁጠሪያ ማሽን እንዲከናወን የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በየስብስባው መመሪያ እንደሚሰጡ የጠቀሱት ሒሳብ ሹሟ፣ በዐውደ ምሕረት በምንጣፍ እና በጥላ ስለተሰበሰበው ገንዘብ ቢጠየቅም ሀገረ ስብከቱ እንኳ እንዲያጣራ አለመፈለጉን ይገልጻሉ፡፡ ሒሳብ ሹሟ ለምን በማለት ይጠይቁና ምላሹን ራሳቸው ሲሰጡ ‹‹ፈቃጁ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በመኾናቸውና

አያገባችኹም ስላሉ›› ብለዋል፡፡ እንደ ወ/ሮ መና፣ በማጣራት የተረጋገጡ ጥፋቶች ተገቢው ርምጃ የማይወሰድባቸው፣ የደብሩ የአስተዳደር ሓላፊዎች ለበላይ አካል ያለትእዛዝ በሚያቀርቧቸው ማባበያዎች ስለሚሸፋፈኑ ነው፡፡ የደብሩ ሒሳብ ክፍል ሳያውቀው፣ ገንዘብ ከባንክ ሳይወጣ በዋና ተቆጣጣሪው አማካይነት

ከገፅ 8 የዞረ የአውሮፓ ኅብረትን ... በዚህ ምክንያትም ነዉ ያን ሕግ ወደጎን ብለዉ 40,000 የሚሆኑትን ጥገኝነት ጠያቂዎች በመላዉ የኅብረቱ አባል ሃገራት የማከፋፈሉ ሃሳብ የቀረበዉ። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የአባል ሃገራቱ ሃሳብ በመለያየቱም ከዉሳኔ ለመድረስ ጊዜ መፍጀቱ እየታየ ነዉ። የኅብረቱ የዜና ምንጮች እንደጠቆሙትም በጉዳዩ ላይ የሚከራከሩት የአዉሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ዶናልድ ቱስክና የአዉሮጳ ኮሚሽን ኃላፊ ዣን ክላዉድ ዩንከር ስብሰባ ላይ መግባባት ተስኗቸዋል። ዩንከር ግን የተባለዉን በማስተባበል፤ የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ኮሚሽኑ ባቀረበዉ ሃሳብ መሠረት ጥገኝነት ጠያቂዎቹን ለማከፋፈል መስማማታቸዉን ጠቁመዋል። እንዲያም ሆኖ ስደተኞቹን የማስፈሩ ርምጃ ግን በፈቃደንነት ይሁን አይሁን ተግባራዊ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱንም አመልክተዋል። በአንፃሩ ሀገራቸዉ ፖላንድ ስደተኞችን በኮታ ለየሃገራቱ ማካፈል የሚለዉን ሃሳብ የምትቃወመዉ ዶናልድ ቱስክ በበኩላቸዉ ምንም እንኳን በሀሳቡ መስማማት የተቻለ ቢሆንም የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት የሌለዉ ሕገወጥ ስደተኞች ግን አዉሮጳ ዉስጥ የመቆየት እድል እንደሌላቸዉ ነዉ ግልፅ ያደረጉት። «ከሁሉ አስቀድሞ ሕገወጥ ስደተኝነትን መግታት ይኖርብናል፤ ይህ ደግሞ ቅድሚያ ልንሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ። ዛሬ የአዉሮጳ ምክር ቤት ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል ብዬ እጠብቃለሁ፤ ይኸዉም ጥገኝነት ለመጠየቅ ሕጋዊ ተቀባይነት የሌላቸዉ በሙሉ አዉሮጳ ዉስጥ ለመቆየት የሚያበቃ ምንም ማስተማመኛ አይኖራቸዉም። እናም ይህን መዕክት ግልፅ በማድረግ ብቻ ነዉ ከጣሊያንና ግሪክ ሰዎችን ወደሌሎች ሃገራት ማሻገር የምንችለዉ።» የአዉሮጳ ኮሚሽን ባቀረበዉ ሃሳብ መሠረትም ግሪክና ጣሊያን የሚገኙ 40,000 ሶርያዉያንና ኤርትራዉያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በቀጣይ ሁለት ዓመታት ዉስጥ ወደየአባል ሃገራቱ ይከፋፈላሉ። ከዚህም ሌላ ከአዉሮጳ ዉጭ በመጠለያ ዉስጥ የሚገኙ 20ሺ ሶርያዉያን ስደተኞችም በዚሁ መሠረት በአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት እንዲሰፍሩ ለማድረግ ታስቧል። እያንዳንዱ አባል ሀገርም ስንት ተገን ጠያቂ ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ እስከሐምሌ ወር መገባደጃ ድረስ ማሳወቅ ይኖርበታል። ስደተኞቹን በኮታ ማከፋፈል የሚለዉ ሀሳብ በብዙዎቹ ተቀባይነት ማጣቱን የጠቆሙት ቱስክ በፈቃደኝነት ሲባል ግን አባል ነኝ እያሉ አለመተባበር ተቀባይነት አይኖረዉም ነዉ ያሉት። EU Gipfel zu Griechenland in Brüssel - Don-ald Tusk ዶናልድ ቱስክ «በፈቃደኝነት የሚከናወን ነዉ መባሉ ምንም ላለማድረግ ምክንያት ሊሆን አይችልም። በፈቃደኝነት የሚለዉን አሠራር የሚፈልጉት ወገኖች ለምን እንደሆነ ይገባኛል። ነገር ግን ተዓማኒ የሚሆኑት ቢያንስ እስከሐምሌ ማለቂያ ተጨባጭና የሚታይ ቃል ሲገቡ ብቻ ነዉ። ምክንያቱም መስዋዕትነት ያልታከለበት መተባበር የታይታ ብቻ ነዉ የሚሆነዉ። ስለዚህ አሁን ትብብርን አስመልክቶ ባዶ ዉሳኔዎች ብቻ አይደለም የምንፈልገዉ፤ ተግባርና ቁጥሮችን እንፈልጋለን።» ብሪታንያ፣ ሃንጋሪ፣ እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት የስደተኛ ቁጥር ይጨምርብናል በማለት ይህን ሃሳብ ተቃዉመዋል። በያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ብቻ ከአንድ መቶ ሺህ የሚበልጡ ስደተኞች የሜዲትራኒያን ባህርን ተሻግረዉ አዉሮጳ ገብተዋል። አብዛኞቹም ጣሊያን፤ ግሪክና ማልታ ነዉ የሚገኙት። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አሁን የኅብረቱ ሃገራት በጋራ ለስደት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን በመወጋት ረገድ ከአንድ ዉሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል። «አሁን መደረግ የሚኖርበት ዘላቂ መፍትሄ ለችግሩ መፈለግ ነዉ፤ ለዚህም በአባል ሃገራት መካከል የበለጠ መተባበር ያስፈልጋል። ይህም ለስደት ምክንያት የሆነዉን መንስኤ ለመዋጋት መወሰን ማለት ነዉ። ኮሚሽኑ ያቀረበዉ ሃሳብ በትክክለኛዉ አቅጣጫ የሄደ ነዉ ለዚህም ነዉ ጀርመን በክርክሩ ላይ እጅግ ገንቢ በሆነ መልኩ የተሳተፈችዉ።» የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ተገን ጠያቂዎቹን ወደሁሉም አባል ሃገራት ማከፋፈል በሚለዉ ቢስማሙም ዝርዝር አፈፃጸሙን የየሃገራቱ የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች እስከመጪዉ ሐምሌ ወር ማለቂያ ደረስ አጥንተዉ ያሳዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሸዋዬ ለገሠ ኂሩት መለሰ

ከዕለት ገንዘብ ተቀባዮች በብድር በተወሰደ ብር 430,000 ለፓትርያርኩ ቢሮ በስጦታ የተበረከተው ሶፋ፣ ሒሳብ ሹሟ በጽሑፉ ካሰፈሯቸው ኹለት ማባበያዎች የመጀመሪያው ሲኾን የቅዱስ ዑራኤል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በማይመለከተው እና ባልታዘዘበት በቀድሞው አለቃ የሥራ ዘመን የተፈጸመ ነው፡፡ ‹‹ለአባቶች ራት ግብዣ›› በሚል በሰበካ ጉባኤው የተወሰነውን ብር ስድሳ ሺሕ ወጪ ከማወራረድ ጋር በተያያዘ ከወቅቱ የደብሩ አለቃ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ወ/ሮ መና በጽሑፋቸው አስፍረዋል፡፡ እንደ እርሳቸው፣ መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓትርያርኩ ቢሮ ለተደረገው የመስተንግዶ ወጭ የሚያስፈልገው ብር 38,611.66 ሲኾን አስተዳዳሪው፣ ‹‹ለምግብ ማስገቢያ የኮቴ የከፈልኩትን አብረሽ አወራርጂ፤ ገንዘቡ ተወስኖና ተፈቅዶ ከባንክ ወጪ ኾኗል›› በማለት እንዳዘዟቸው ጠቅሰዋል፡፡

ሒሳብ ሹሟ አክለውም ‹‹ደረሰኝ የሌለው የኮቴ ወጪ አላወራርድም ብዬ ስላልተግባባን ሕጋዊው ሰነድ ሳይወራረድ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ለዘጠኝ ወራት ከቆየ በኋላ ተወራርዷል፤›› ካሉ በኋላ ‹‹የኮቴ ክፍያውም በቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊ ንቡረ

እድ ኤልያስ ኣብርሃ ተፈጻሚ ይኾናል›› ብለዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ በዚኽ መልክ ያለደረሰኝ ወይም ያለሞዴል 6 እየተመዘበረች እንደምትገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ መና፣ ‹‹ሕገ ወጥ ኾኖ አላወራርድም ያልኩት የፓትርያርኩን መመሪያ ወደ ተግባር የለወጥኩ መስሎኝ የነበረ ቢኾንም በእንደራሴ ነን ባዮች የሚፈጸምብኝን ደባ አላሰብኩትም ነበር፤›› በማለት በደብሩ የፋይናንስ አሠራር ላይ ያቀረቧቸው አቤቱታዎች በዝውውር ሽፋን ተድበስብሰው እንዳይቀሩ ተማፅነዋል – ‹‹ምርመራው በቤተ ክህነቱ ሳይኾን መንግሥት በሚመድባቸው ኦዲተሮች ከመሠረቱ ከመጋቢት 2005 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ እንዲደረግልኝ እፈልጋለኹ፤ ቢሮዬም ተሰብሮ ሰነድ እንዳይወጣ ሕጋዊ የመንግሥት አካል ባለበት እስከ አኹን ያለው ደኅንነት ታይቶ እስኪመረመር ድረስ እንዲታሸግልኝ፤ ለማሳያነት ካቀረብኋቸው ጉዳዮች ባሻገርም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለሚፈጸሙ አደገኛ አሠራሮች በአካል ቀርቤ በቃል ለማስረዳት እንድችል ይደረግልኝ ዘንድ እጠይቃለኹ፡፡›› በወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ‹‹እንደራሴ ነን ባዮች›› የተባሉት፣ በቤተ ክህነቱንም ኾነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር ፓትርያርኩን በወሳኝነት ያማክራሉ የተባሉ ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን (መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ፣ መልአከ ብርሃናት ዘካርያስ ሓዲስ እና መልአከ ገነት ተስፋ ፍሥሓ) እንደኾነ በጽሑፋቸው ተመልክቷል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሹመታቸው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ቢኾንም ‹‹በምስጢር ለመላው ኢትዮጵያ

ነው›› እንዳሏቸው ወ/ሮ መና ጠቁመው፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ እና እንደራሴ ነን ባዮቹ በሚሏቸው ብቻ እንዲሠሩ ለፓትርያርኩ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጥብቅ መመሪያ እንደተሰጣቸው በሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ‹‹በዘመናዊ የሙስና አደረጃጀት›› እየተመራ እንዳለ ገልጸው፣ ከዝውውር አሠራር ጋር በተያያዘ በአንድ አካባቢ ተወላጅ ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ባለው የአስተዳደር እና የሰብአዊ መብት ጥሰት የዋና ሥራ አስኪያጁ ቢሮ ‹‹የሰው ዘር መሸጫ መደብር ኾኗል›› ይላሉ፡፡ የፓትርያርኩ የፀረ – ሙስና ዐዋጅ ከሚዲያ ፍጆታነት እንዳላለፈ ተችተው፣ ሙስና በሥራ እንጂ በሚዲያ እንደማይጠፋ የሚገልጹት ሒሳብ ሹሟ፣ ችግሩ አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው ወደፊት ቤተ ክርስቲያኒቷን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላት አሳስበዋል፡፡ ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ተዛውረው በተመደቡበት የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሒሳብ ሹም የነበሩት ሠራተኛ፣ በሰነድ ማጭበርበር በተፈጸመ ከፍተኛ የእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሠው በሰኔ ወር መጨረሻ የተላለፈባቸውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የእስር ቅጣት በመፈጸም ላይ እንዳሉ ተገልጧል፡፡

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 9

Page 10: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 10

የኢትዮጵያ መንግስት

የአንዳርጋቸዉ ጽጌ አያያዝ

የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት አደጋ

ላይ እንዳይጥል እንግሊዝ

አሳሰበች

የተቃውሞ መሪውና ዜጋውም የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘበት ሁኔታ “ጨርሶ ተቀባይነት የሌለውና በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለውን ግንኙነትም የሚጎዳና አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲል የእንግሊዝ መንግሥት ኢትዮጵያን ትናንት አሳስቧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የእንግሊዝን መንግሥት ስሞታ ያስተባብላል፡፡ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞንድ ትናንት በሰጡት መግለጫ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር መወያየታቸውንና “ብርቱ” ያሉትን መልዕክት ያስተላለፉላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የእንግሊዙ የዜና አውታር ሮይተርስ እንደዘገበው ሚስተር ሃሞንድ ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ “እንግሊዛዊው ዜጋ አንዳርጋቸው ፅጌ ከታሠሩ አንድ ዓመት ቢያልፍም የመታሠራቸውን ጉዳይ በሕግ ፊት ለመሟገት እንኳ ሳይቻል ብቻቸውን ተነጥለው እንዲቆዩ ተደርጓል” ብለዋል፡፡ የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክለውም የአቶ አንዳርጋቸው ደኅንነት በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑንና የእንግሊዝ ቆንስላ አቶ አንዳርጋቸውን በየወቅቱ ማግኘት እንዲችል ለማድረግ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃል ቢገባም በተደጋጋሚ የቀረቡት ጥያቄዎች ግን ያለመልስ መምከናቸው ያሳዘናቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ባለፈው ነኀሴ ሎንዶን የሚገኙትን የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈፃሚ መልዕክተኛ ጠርቶ አቶ አንዳርጋቸው ላይ ቀደም ሲል ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ተፈፃሚ እንደማይደረግ ማረጋገጫ እንዲሰጠው ጠይቆ እንደነበር፡፡ ጉዳዩ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል ያለውን ግንኙት ወደአደጋ እየወሰደው እንደሆነ ማስጠንቀቃቸውን ሮይተርስ አክሎ ዘግቧል፡፡ “ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያቀረብንላትን ጥያቄ ሳትቀበል መቅረቷ ተቀባይነት የለውም፡፡ የጉዳዩ አለመንቀሳቀስ እንግሊዝ በብዙ የምታከብረውን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለት ወገናዊ ግንኙነት ይጎዳዋል፡፡” ብለዋል ፊሊፕ ሃሞንድ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው የተያዙት በጥሩ ሁኔታ ነው ስትል ኢትዮጵያ የለንደንን ስሞታ ዛሬ አስተባብላለች፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለሮይተርስ ሲናገሩ ባለሥልጣኖቻቸው ከእንግሊዝ ጋር ሲተባበሩ መቆየታቸውንና አቶ አንዳርጋቸው የሚገኙበትንም ሁኔታ እንደሚያውቁ ገልፀዋል፡፡ “አንዳንዶች ሊስሉ የሚሞክሯቸው አሳዛኝ ታሪኮች መሠረተ ቢስ ናቸው” - ብለዋል አቶ ጌታቸው፡፡ አክለውም ይህ ሁኔታ በግንኙነቶቻችን መንገድ ላይ እንዲቆም ጨርሶ አንፈቅድም ብለዋል፡፡ “ይሁን እንጂ - አሉ አቶ ጌታቸው - እንግሊዛዊያኑ ወዳጀቻችን የሚጠይቁን አንድን የተፈረደበት ሽብርተኛ ያለቅድመሁኔታ እንድንለቅቅ ከሆነ ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡ ይህንን ይረዳሉ ብለን እናምናለን፡፡” የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞን ለማፈን ጋዜጠኞችን፣ የመብቶች ተሟጋቾችን እና ብሎገሮችን እንደሚያስር እየገለፁ በየወቅቱ ቢከስሱም መንግሥቱ ግን በየወቅቱ ሲያስተባብል ይሰማል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለምንድን ነው የእራሱን ጥላ

አይቶ የሚደነብረው? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ በ2015 ለምንድን ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርኃት፣ የአጠቃላይ በፍርሀት የመርበድበድ እና እጅግ በጣም በጭንቀት ውስጥ የመግባት አምላኮች የእራሳቸውን ጥላ የሚፈሩት? እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች የቅርጫ ምርጫ ለማካሄድ በዕቅድ ተይዟል፡፡ የቅርጫ ምርጫው ምንም እንኳ በሸፍጥ የታጀበ እና የተጀቦነ ቢሆንም፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 23/2010 እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ አገዛዝ የፓርላሜንታዊ መቀመጫውን በ99.6 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ይኸ የምርጫ ውጤት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እ.ኤ.አ በ2002 ሳዳም ሁሴን ካስመዘገበው 100 በመቶ በትንሽ በማነስ የሁለተኛነት ደረጃን እንዲጎናጸፍ አድርጎታል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ቢያንስ በ99.6 በመቶ ድል ይቀዳጅ ይሆን? ጠቃጠቆ ያለባቸው ጅቦች በእርግጠኝነት ጠቃጠቆው አለባቸውን? ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ተውጦ በላብ ተዘፍቆ እንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች ነግረውኛል፡፡ እስከ ቅርጫ ምርጫው ድረስ በፍርሀት ርዷልን? ምርጫ! የምን ምርጫ? የዘረፋ ወሮበላ ምርጫ!? ሽንፈትን መፍራት ምክንያታዊ ነው፣ ሆኖም ግን በ99.6 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት ማሸነፍን መፍራት ፍጹም የሆነ እብደት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ የተወሸቀ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ነግረውኛል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ እነዚህ ሰዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት እና ጽኑ ደጋፊዎች እና ተከታዮች ናቸው፡፡ ስለዚህም እውነት ነው ብለው ያምናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በእርግጠኝነት አባላት ለመሆን እና አለመሆናቸው የማረጋግጥበት ምንም ዓይነት ማስረጃ የለኝም፡፡ አንዳንዶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታዛዥ ሎሌዎች እና የቡድን አባላት ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ነጻ በሆነ መልኩ ለንግድ ስራ ሲባል ከአዲስ አበባ በመሄድ እና እንደገና በመመለስ በፍርሀት ተይዘው ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በአሁኑ ጊዜ በፍርሀት ወጥመመድ ተሸብበው እንደሚገኙ አረጋግጠውልኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእኔ መጥፎ ምክር ለመስጠት በማሰብ ከመስመራቸው ውጭ ለመንቀሳቀስ ይችላሉን? ለምንድን ነው እነዚህ ሰዎች በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጎራ ውስጥ ስላለው ፍርሀት እና ጥላቻ ሚስጥራዊነት ዝርዝር እና ጥልቅ በሆነ መልኩ የሚነግሩኝ? ምናልባትም የተሳሳተ መረጃ እየሰጡኝ ይሆናል በማለት ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ሆኖም ግን የእነርሱን የቅጥፈት መረጃ ለመጠቀም የተሰላቸሁ መሆኔን ያውቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ለምንድን ነው ሚስጥራቸውን እያመጡ ለእኔ የሚዘከዝኩት? እውነት ለመናገር እኔ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለኝም፣ እንዲሁም ለማወቅ ደንታ የለኝም፡፡ ሆኖም ግን አንድን ነገር ለማወቅ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ በሕጉ ዓለም ሁልጊዜ እንደምንለው ሁሉ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መረጃ ለመስጠት ምቾት ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ሁሉንም ነገር ይፋ እንደማወጣው ያውቃሉ፡፡ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ለሚገኙት ጉልበተኞች ሁሉ እውነትን እናገራለሁ የሚል ሰው እውነትን በመደበቅ ሌላ ነገር የሚናገርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እነርሱ ደንታ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ምንም ዓይነት ስም መስጠት አያስፈልግም፣ እባካችሁ እውነታውን ብቻ መናገር ነው፡፡ የሚመላለሰው ሀሳብ ጭንቅላቴን በጠበጠው፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት የተጠናወታቸው ሊመስል ይችላልን? አንዳንድ ጊዜ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ ያሉት እና ኃይለኛ ጉልበታሞች ፍጹም የሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውሰጥ ጸጥ ብለው ከሚኖሩት እና አሰልቺ በሆነ መልኩ እያቃሰቱ እንዲሁም እየተወራጩ በችግር ከሚኖሩት ኃይል እና ተስፋ የለሽ ሰዎች የበለጠ መብረቃዊ ነው፡፡ ማቋረጫ የሌለው የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዳለ እየነገሩኝ ነው – ማለትም የደስታ ስሜት መራቅ፣ አሳሳቢ ጭንቀት፣ የሰላም ማጣት እና ትርምስ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ብቻ ሳይሆን በተራው አባላት ላይም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡ እኔ ይህ ሁኔታ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማጎሪያው እስር ቤት እና በህሊና አስሮ እንደፈለገው እየፈነጨ ባለበት ሁኔታ በእራሱ ላይ እንደዚህ ያለ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚታይበት ለምንድን ነው?

በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ያሉት እነርሱ ብቻ አይደሉም፡፡ ሌሎችም አሉ፣ ማለትም ጽንፈኞቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት፣ ተቃሚዎች እና ትችት አቅራቢዎች ጭምር ይካተታሉ፡፡ እንዲህ የሚል አንድ ዓይነት ነገር ነው የነገሩኝ፡፡ “በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ማዕበል ውስጥ ተውጦ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ እየተካሄደ ያለው ምንድን ነው ? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ እና መጠነ ሰፊ የሆነ የማታለል ስራ እየሰራ ነው ያለን? እኔ ይኸ ነገር የሚገርመኝ ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባትም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ የሚለውን የሰን ትዙን ስልታዊ ጨዋታ እየተጫወተ ሊሆን ይችላል፣ “ጠንካራ በሆንክበት ጊዜ ደካማ መስለህ ለመታዬት ሞክር፣ ሆኖም ግን ደካማ በሆንክ ጊዜ ግን ጠንካራ መስለህ ለመታዬት ሞክር፡፡“ ከፍተኛ የሆነ ኃይል ባለህ ጊዜ ለጠላቶችህ የፈራህ በመምሰል ለማሳየት ሞክር፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ነገር ሲታይ ሁከት የመፍጠር ነገር ይመስላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ደጋፊዎች እና ጠላቶች በተደጋጋሚ የሚናገሩትን አንድ ዓይነት ነገር ማዳመጥ የወያኔ አመራሮች እና ተራው አባላት በእራሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ የመጣ ለመሆኑ የጸሐይ ግርዶሽን የመመልከት ያህል ነው፡፡ሁልጊዜ ሊፈጸም የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ ጉዳይ አልፎ አልፎ ሊሆን የሚችል ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የፈሩ መሆናቸውን ነግረውኛል፡፡ እኔ የማቀርበው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፣ “እነዚህ ፍጡሮች ምንድን ነው የሚፈሩት?“ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቀላል የሆነ መልስ የለውም፡፡ ሰውን ምቾት እንዳይሰማው ማድረግ፣ ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእብሪት በመወጠር በባለእንጨቱ ዙፋን (ባለወርቁን ዙፋን ቀደም ሲል ሸጠውታል) ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ኃይለኛው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከ5 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት፡፡ አሁን በህይወት የሌለው እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ የነበረው መለስ ዜናዊ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር ይህንን የተናገረው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ቁጥር እጥፍ ወይም ደግሞ ሶስት ጊዜ እንዲያድግ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ገንዘብ ፍቅርን አይገዛም ሆኖም ግን ያለምንም ጥርጥር ድምጽ ሰጭን እና የፓርቲ አባላትን ሊገዛ ይችላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምጣኔ ሀብቱን የደም ስር አንቆ ይዟል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቢሮክራሲውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፖሊስ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሉን በበላይነት ተቆጣጥሯል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቆሸሸው እጁ የሚበላባት ሜሪካ አለችው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በማደግ ላያ ያለ የዴሞክራሲ ባለቤት ናት በማለት የሚያውጅላት የዩኤስ አሜሪካ 4ኛ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣን አግኝቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ክብር የለም! እነዚህን በጣም የተማሩ እና ሰፊ ልምድ ያካበቱትን ታላላቅ የዲፕሎማሲ ሰዎች ድድብናን በተላበሰ መልኩ በአደባባይ በህዝብ ፊት እንዲናገሩ በማድረግ እንዴት አድርገው እንደ ዕቃ እንደሚጫወቱባቸው አውቃለሁ፡፡ በዩኤስ መንግስት አራተኛ የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማት ባለስልጣን የሆኑት ኢቨሊን ሸርማን ኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ እየጎለበተ ያለ ዴሞክራሲ አላት በማለት ተናግረው ነበር፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ተቃዋሚዎቻቸውን እና ተራውን ዜጋ ለማስፈራራት፣ በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ በእስር ቤት ለማጎር እና ለመግደል የወታደር እና የፖሊስ ጡንቻውን ይጠቀማል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት በዘረፈው አንጡራ የህዝብ ሀብት ሌሎችን ለመሳብ ይጠቀምበታል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ነው፡፡ ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ነውን የሚለው አልገባኝም፡፡ በፍርሀት ላይ ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው? የአዕምሮ ሰላም የላቸውም ማለት ነውን? የፍጻሜው ቀን ደርሷል በማለት ሌሊት እንቅልፋቸውን አጥተው ያድራሉ ለማለት ነውን? በጠራራው ጸሐይ በእንቅልፍ ውስጥ ሆነው በቅዠት የእንቅልፍ ላይ የእግር ጉዞ እያደረጉ ነው ለማለት ታሰቦ ነውን? ሁሉንም የሚያንጸባርቁትን ህንጻዎቻቸውን እንደሚያጡ እያቃዣቸው ያለውን ቅዠት ለእኔ ነግረውኛል፡፡ ጊዜው ሲደርስ እና ጽዋው ሲሞላ ወዴት እንደሚገቡ እና የት ሄደው እንደሚያመልጡ በቀን ቅዠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝባዊ ማዕበል ሊነሳብን ነው በማለት በቀን ቅዠት ውስጥ ሆነው በመዋለል ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንገድ ላይ ነውጦች ወደ ህዝባዊ አመጽ፣ አብዮት፣ ጸረ መንግስት አልገዛም ባይነት እና ወደ ሁለገብ አመጽ ይሸጋገራል በማለት የቀን ላይ ቅዥትን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡ ወታደሩ ትዕዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል በማለት የመጨረሻውን የትዕዛዝ እርምጃ ላይወስድ ይችላል በማለት በቅዠት ዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከቡርኪና ፋሶ ከናይጀር እና ከቡሩንዲ ተግባራዊ

ትምህርት ቀስመዋል የሚል ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ... ገፅ 11

Page 11: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 11

የወያኔ ወሮበላ ከገፅ 10 የዞረ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ ብልሆች ናቸው፡፡ ለበርካታ ዓመታት ያህል በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን በማጎሪያ እስር ቤቶቻቸው አስረው ለበርካታ ጊዜ ለመቆየት በማሰብ በቅዠት ላብ ተጠምቀው ባነው ይነሳሉ፡፡ እኔ ይህንን ነገር አላምንም፡፡ ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ውስጥ የፍርሀት ግዛት መስርቶ ይገኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ እና አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ ይኖር ነበር፡፡ የእርሱ የቅንጦት መኪና በከተማ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እርሱ የሚሄድባቸው መንገዶች ለበርካታ ጊዚያት ዝግ ይደረጉ ነበር፡፡ የእርሱ ደቀመዝሙሮች በነጻ በህዝብ ፊት በአደባባይ መውጣት እና ፊታቸውን ማሳየት ፍርሀታቸው ይገድባቸዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መፈራትን ይወዳሉ፡፡ ፍርሀትን መንዛት እና ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨትን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በፍርሀት የተቀነበበች ሀገርን ፈጥረዋል፡፡ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ የሚኖር አገዛዝን መስርተዋል፡፡ በፍርሀት ባህል ውስጥ በመኖር ላይ ናቸው፡፡ ፍርሀትን ያስባሉ፣ ፍርሀትን ይተነፍሳሉ፣ ፍርሀትን ያልማሉ፣ ፍርሀትን ያራምዳሉ፣ በፍርሀት ይኖራሉ፡፡ የፍርሀት ጌቶች እንዴት ነው ፍርሀትን የሚፈሩት? ሆኖም ግን ወያኔዎቹ በአሁኑ ጊዜ እራሳቸውን በፍርሀት ታስረው አገኙት፡፡ የፍርሀት አራማጆች በአሁኑ ጊዜ እራሳቸው ቦቅቧቃ ፈሪዎች ሆነው ተገኙ፡፡ እኔ የምፈራው ፍርሀትን እራሱን ነው የሚለውን አባባል አልተገነዘቡትምን? ስለሆነም ይፈራሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት አፈታሪክ እኔን በጣም ይገርመኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፎቦስ እና ዲሞስ የተባሉት የግሪክ የፍርሀት የሰቆቃ፣ የሽብር እና ሁሉም የሰይጣናዊ ድርጊት ተምሳሌቶች እራሳቸው በፍርሀት፣በሽብር፣ በስቃይ እና በግፍ ተጠርንፈው ይገኛሉ፡፡ የፍርሀት ጌታ በዲሞን ፍርሀት እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል? ታላቅ ክብር ያላቸው እና የተቀደሱ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “መፈራትን የሚወዱ ሰዎች መወደድን ይፈራሉ፣ እናም ከማንም በላይ እራሳቸው የበለጠ ይፈራሉ፣ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ብቻ የሚፈሯቸው ቢሆንም እነርሱ ግን እያንዳንዱን ሰው ይፈራሉ፡፡“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእነርሱ ላይ እያንዣበበ ያለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጣ በመፍራታቸው ምክንያት ይፈራሉን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የመፍራት ትረካ ሰምቻለሁ፡፡ ከተለመደው ውጭ ትኩረት በመስጠት ለማዳመጥ ሞክሪያለሁ፡፡ ይኸ ሁኔታ እንዲህ የሚለውን የቆዬ አባባል አስታወሰኝ፣ “የሚያውቁ ሰዎች አይናገሩም፣ የሚናገሩ ሰዎች ግን አያውቁም፡፡“ ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የፍርሀት ታሪክ የሚታወቅ ቀላል ጥያቄ እና የሚታወቅ እና የማይታወቅ መሆኑን ለእራሴ ግልጽ አደረግሁ፡፡ ይህም ማለት የሚታወቅ እና የማይታወቅ ፍርሀት ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ጉዳይ ከዚያም የበለጠ ውስብስብ ነገር ነው፡፡ የዶናልድ ሩምስፌልድስ (የቀድሞው የዩኤስ መከላከያ ጸሀፊ ከነበሩት) እንቆቅሎሾች መካከል በመዋስ እስከ አሁን ድረስ እየተነገሩኝ ያሉት ነገሮች ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ፍርሀት በሚመለከት ቀጣይነት ያለው፣ ቀስ በቀስ እያለ የአውዳሚነት ባህሪን የተላበሰ፣ እና የወያኔውን የፖለቲካ ሰውነት እንክት አድርጎ የሚበላ መርዛማ ካንሰር መሆኑን ግንዛቤ ወስጃለሁ፡፡ ሩምስ ፌልድ እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰጥተው ነበር፣ “የምናውቃቸው ነገሮች አሉ (የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች)፡፡ እንደዚሁም ሁሉገ ነገሮች አሉ የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ይህም ማለት የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ሆኖም ግን የማናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ የማናውቃቸው ነገሮች ልናውቃቸው አንችልም፡፡“ ሩምስ ፌልድ የረሱት እና የተውት እንዲህ የሚል ሌላም ነገር አለ፣ “የሚታወቁ የማይታወቁዎች (የሚታወቁትን ታዋቂ ነገሮች እንደማይታወቁ አድርጎ የመካድ ሁኔታ)፡፡“ ስለሆነም ከዚህ አንጻር እንዲህ ማለት ይቻላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር፣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቃቸው እና የሚፈራቸው ነገሮች አሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል በሌላ በምንም ነገር ሳይሆን በኃይል እና በጡንቻው ብቻ በመተማመን ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በህገወጥ መንገድ እየገዛ እንዳለ የሚታወቅ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም እንደዚሁ የተለመደውን ጡንቻውን በመጠቀም የህዝብን ድምጽ በጠራራ ጸሐይ ዘርፎ እና ነጥቆ በመግዛት ላይ እንደሚገኝ ከምንም በላይ አሳምሮ የሚያውቀው

ባለፉት 24 ዓመታት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ውስጥ የአሸዋ ቤተመንግስት በመገንባት ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ አንድ ትንሽ መነሻ ነገር ቢኖር እና የህዝብ የተቃውሞ ማዕበል ቢነሳ በአጭር ጊዜ ወስጥ ተጠራርገው ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ እንደሚጣሉ ያውቃሉ፡፡ እነዚህ ዓይን አውጣ ፈጣጣዎች ህዝቡ በቀን አንደ ጊዜ እንኳ ለመብላት ተስኖት በስቃይ ላይ እያለ መሆኑን እየተገነዘቡ ለማደናገር ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግበናል ይላሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በአሁኑ ወቅት እየጎለበተ ያለ ዴሞክራሲ እየገነቡ እንዳሉ በመጮህ እና በመስበክ ሌሎችንም ቆሻሻ የሆኑ ነገሮችን በመፈጸም እነርሱ ምንም የማይነቀነቁ ኃይሎች እና ስርዓታቸውም እንደማዕበል እየተናጠ ባለበት ሁኔታ የተረጋጋ አስመስሎ ለማቅረብ ግብር በሚከፈልበት የህዝብ መገናኛ ብዙሀን ሌት ቀን እንደበቀቀን ሲደግሙት እና ሲደጋግሙት ይደመጣሉ፡፡ እራሳቸውን በባህር ዳርቻ ላይ እንዳለ እና ሊፈርስ እንደማይችል የአሸዋ ግንብ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዳሉት የታወቁ የወንጀለኛ ድርጅቶች ሳይሆን ከዚያም በበለጠ እና በባሰ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ የተዳራጀ ወንጀለኛ የማፊያ ድርጅት መሆኑን የሚያውቁት ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድርጅት መሰረቱን የጣለው በሙስና ቢዝነስ ላይ ነው፡፡ ወያኔው የሌብነት እና የማጭበርበር ባህልን በማዳበር፣ ማታለልን፣ ሸፍጥ መስራትን በጉቦ ቅሌት ውስጥ ተዘፍቆ መገኘትን እና ህገወጥ በሆነ መልክ ገንዘብ ማግበስበስን እንደዋና ስልት አድርገው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Endowment Fund for

the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) እያለ እራሱን ከሚጠራው የግል የማፊያ ቡድን ስብስብ የግል ንብረት ውጭ አይደለም በአፍሪካ በዓለም ላይም ቢሆን የእራሱ የንግድ ግንኙነት፣ ካፒታል፣ መንግስታዊ ጥበቃ የሚደረግለት፣ ከግብር ነጻ የሆነ፣ ገንዘብን ከህግ አግባብ ውጭ ወደ ውጭ ማስወጣት የሚችል እና በህግ ተጠያቂ ከመሆን ነጻ የሆነ የግል ድርጅት ከማረት በስተቀር ሌላ ሊኖር ይችላልን? እንደዚህ ያለ የበከተ ድርጅት አይደለም መኖር ሊታሰብ የሚችል አይመስለኝም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደ ወንጀለኛ ድርጅት ከማጭበርበር፣ ከመዝረፍ እና ሌሎቸችንም ህገወጥ የሆኑ ነገሮችን ከመስራቱም በተጨማሪ የሰብአዊ መብቶችን በመርገጥ፣ የገንዘብ ማጭበርበር፣ የፖለቲካ እና የጦር እንዲሁም መንግስታዊ ወንጀሎችን በመፈጸም ስራ ላይ ተጠምዶ በመዳከር ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ማፊያ ድርጅታዊ አወቃቀር እና የግንኙነት ሰንሰለቱ በዓለም ላይ እጅግ በጣም በመጥፎነታቸው ከሚታወቁት ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሙስና የበከተ፣ በመንደርተኝነት የተሰባሰቡ ጅቦች ከርስ ማጋባሻ የተቋቋመ ወንጀለኛ ድርጅት ነው፡፡ ይህ ወንጀለኛ ድርጅት በርካታ በሆኑ ግላዊ እና የጎሳ እንቅስቃሴ ተግባራት ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ይህ ድርጅት ውስጣዊ የቤተሰባዊ ውድድር እና ሊሻሻል እና ሊለወጥ በማይችል ግትር የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ ተቀፍድዶ ይገኛል፡፡ የማፊያ ጌቶች ለስልጣን፣ ለተጽዕኖ ፈጣሪነት እና የበላይነትን በመቀዳጀት አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እንደሚያደርገው ጥረት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብም ይህንኑ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ስንቶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ የአመራር አባላት ናቸው ሻርክ እንደሚባለው ዓሳ እርስ በእርስ በመበላላት ላይ ያሉት? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚመራበት ምንም ዓይነት ርዕዮት ዓለም ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የፖለትካ እምነት እንደሌለው የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ እንደ ማፊያ ሁሉ በሙስና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማግኘት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እየዘረፈ እንዲኖር እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነቱን እንደያዝኩ እንድኖር ያስችለኛል ብሎ ያስባል፡፡ ሁሉም ነገር ዝቅተኛውን የጨረታ ዋጋ ላቀረበ የወያኔ አባል ይሸጣል፣ ወይም ደግሞ በነጻ ይሰጣል (ምንም ዓይነት የልውውጥ ግብይት ይደረጋል የሚል ሀሳብ አልሰነዘርኩም)፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ካራቱሪ ግሎባል ለተባለው ዓለም አቀፍ ኩባንያ በዓመት እጅግ በጣም ጥቂት በሆነ የገንዘብ ኪራይ ብቻ ለም የሆነውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር የሀገሪቱን መሬት አስረክቦ ነበር፡፡ ካራቱሪ በአሁኑ ጊዜ ባዶ ሆዱን ሀገር ጥሎ ወጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ በጋምቤላ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአሁኑ ጊዜ የካራቱሪን ባዶ ኮረጆ ተሸክመው ይገኛሉ፡፡ ሌሎች መንታፊ ሌቦች ግን ከካራቱሪ ጋር በተደረገው ስምምነት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ባለቤት ሆነዋል! የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ብቸኛው በስልጣን ላይ

የመቆያ ዘዴ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ ማነሳሳት፣ የኃይማኖት

ጽንፈኝነት እንዲፈጠር እና በኃይማኖቶች መካከል መተማመን

እንዳይኖር አበርትቶ ማስራት እና የጥላቻ እና የበቀል መንፈስ

ስር እንዲሰድ ሽንጡን ገትሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ

የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡

ቀጣዩን በገፅ 12 ይመልከቱ

የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን በማንኛውም ጊዜ በህዝብ ቁጣ ከተቆናጠጠበት የስልጣን ወንበር ላይ በኃይል እንደሚወገድ ይገነዘባል፡፡ ይህ ፍርሀት ነባራዊ እውነታነት አለው፡፡የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከስልጣን ወንበሩ ላይ የማይወገድ ቢሆን ነበር የሚያስገርመው ነገር፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ህዝብ ዓይን፣ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዕውቅና እንደሌለው የሚያውቀው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መንበረ ስልጣኑን የተቆናጠጠው በኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ እና ሙሉ ፈቃድ ሳይሆን በጠብመንጃ እጃ በጡንቻ ኃይል እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል፡፡ እስከ አሁን ድረስ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምን ያህል የተጭበረበሩ እና ዝርፊያ የተካሄደባቸው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫዎች እንዳካሄደ የሚታወቅ ቢሆንም ማንም በሰከነ አዕምሮ ለሚያስብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተካሄዱት የቅርጫ ምርጫዎች ሁሉ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያላቸው እንዳልነበሩ የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ህጋዊ ዕውቅና ያለው መንግስት የህዝቡን ፍላጎት ይወክላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግን የሚወክለው የወያኔውን እና የእርሱን ተላላኪዎች እና ጋሻጃግሪዎች ፍላጎት እና ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ለሚካሄደው የቅርጫ ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋናው ዓላማው ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው ምርጫ በማካሄድ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ሳይሆን በገንዘብ እየደገፉ እና እየረዱ የኢትዮጵያን ህዝብ መከራ እና ስቃይ በሚያራዝሙት አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች ዘንድ ህጋዊ መስሎ ለመቅረብ ነው፡፡ ገንዘብ በእራሱ ይናገራል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ዴሞክራሲ በመጎልበት ላይ ያለ ነው ካለች ማነው አይደለም ኢትዮጵያ ጭካኔነት በተንሰራፋበት አምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ በመዳከር ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ሊል የሚችለው? እኮ ንገሩኛ! በእርግጥ ሄለን ኤፕስተን እንዲህ ብለው ነበር፣ “የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ህጋዊነት ዩኤስ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዩኤስ ኤይድ እውቅና የሚሰጡ ቢሆንም ምንም ነገር ማለት አይደለም…“ የቅርጫ ምርጫው እንዲካሄድ የሚፈለገው ዩኤስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመችው ላለው ዕኩይ ድርጊት የሞራል ኪሳራን ለማካካስ በሚል አጉል ፈሊጥ ልዕልናን ለመቀዳጀት የምታደርገው አሳፋሪ ሁኔታ ነው፡፡ የቅርጫ ምርጫው በየጊዜው መቶ በመቶ እየተዘረፈ እና እየተሰረቀ በሚገባ እየተገነዘበች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቷ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን ያህል ንቀት እና ትዕቢት እንዳላቸው በግልጽ የሚያመላክት ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ በማለት ይሳለቃሉ፣ “ኢትዮጵያ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እያራመደች በመሆኑ በቀጣይነት የሚደረገው ምርጫ ነጻ፣ ፍተሀዊ፣ በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው፣ በህዝብ ዘንድ ግልጽ እና ሁሉን አቀፋ አሳታፊ እንደሚሆን እንጠብቃለን፡፡ ምርጫ በየጊዜው እንዲደረግም የምንጠብቀው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ከምንጊዜውም በላይ እየተሻሻለ የመጣበት ሁኔታ ነው የሚስተዋለው፡፡“ በማለት ነበር የዩኤስ አሜሪካ ረዳት ጸሐፊ የሆኑት ኢቨንሊ ሸርማን በህዝብ ፊት በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ምን ያህል ሸፍጠኝነትን የተላበሰ አባባል ነው! ደህና፣ እንግዲህ በግንቦት ይካሄዳል እየተባለ ስለሚደሰኮርለት ይቅርጫ ምርጫ ወደፊት የምናየው ስለሆነ የሚያስቸኩል ነገር የለም፡፡ ከህዝብ ይሁንታ ውጭ በኃይል በስልጣን ማማ ላይ ተንጠልጥሎ ለሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህሎች ባይተዋር መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ውስብስብ ታሪክ ማህበረሰብ እና ባህል እንደማያወቁት ያውቃሉ፡፡ ይህ ካልሆነማ ታዲያ ለምንድን ነው ኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ብቻ ታሪክ ያላት ሀገር ናት እያሉ ህዝብን ሲያደናግሩ የከረሙት? ታዲያ ይህ ባይሆን ኖሮማ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተቀባው መሪ የነበረው እና በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በአያት ቅድመ አያቶቻችን የደም መስዋዕትነት ተከብራ የኖረችውን የነጻነት ቀንዲል አርማ የሆነችውን ባንዲራችንን በአደባባይ ጨርቅ ናት ለማለት ደፈረ? ምናልባትም ይህ እኩይ አባባሉ ከጨካኙ እና ከአምባገነኑ የቤኒቶ ሙሶሎኒ አስተሳሰብ ጋር ቤተሰብነትን በመመስረት እንዲህ ከሚለው አባባል ጋር መሳ ለመሳ ሊሆን ይችላል፣ ”ለእኛ ብሄራዊ ባንዲራ ማለት በከብቶች የእበት ቁልል ላይ የተተከለ ቡትቶ ነው፡“ በአጠቃላይ በህዝቡ ዘንድ በጣም እንደተጠሉ እና ተቀባይነት እንደሌላቸው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቁት የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ እያንዳንዱን ሰው በመከፋፈል እና በመለያየት እንዲሁም አንድ ለአምስት በሚለው ጥርነፋቸው አማካይነት እያንዳንዷን ነገር የተቆጣጠሩ ይመስላቸዋል፡፡ ጎሰኝነትን የፖለቲካ መሳሪያ አድርገው የመጠቀም ስልትን ነድፈው ላለፉት 24 ዓመታት ህዝቡን በማናቆርና እና በማጫረስ ስኬታማ ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ጥላቻን እና በእነርሱ ላይ መጥፎ አመለካከትን በማጨድ ላይ ይገኛሉ፡፡

Page 12: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 12

የወያኔ ወሮበላ ከገፅ 11 የዞረ ዘለቄታዊነት ባለው ሁኔታ በስልጣን ላይ ለመኖር እንዲችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እኔ ከሌለሁ ሀገሪቱ ትበታተናለች እናም ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ እና ትርምስ ይፈጠራል በማለት ያስፈራራሉ፡፡ እነርሱ ባመጡት የጎሳ የመበላላት ፖለቲካ ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ እነርሱ እንደሚሉት ወደ ጦርነት ሊገባ እንደማይችል ወያኔዎቹ እራሳቸው ያውቁታል፡፡ እንደ ፍራንከንስተይን ልቦለዳዊ ታሪክ እብዱ ሳይንቲስት በሰው ልጆች ላይ ያደረገው ምርምር መጨረሻው እጅግ በጣም ግዙፍ እና አስቀያሚ የሆነ ፍጡርን ማግኘት ነበር፡፡ በአዲስ መልክ ወደዚች ዓለም በምርምር እንዲመጣ ያደረገውን ሰይጣናዊ ሰው ምንንነት ሳይገነዘብ የእርሱን ፍጡር በማጥፋት ረገድ ሙሉ እድሜውን ጨርሶ ቀርቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የእራሳቸው የግል የሆነች ኢትዮጵያን የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ በሚጠራ መርዛማ በሆነ የጎሳ ፖለቲካ ቤተሙከራ ውስጥ በእራሳቸው ምዕናብ ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልሎችን (መንቀሳቀስ የሚከለክሉ በረቶችን) ወይም ደግሞ ታዋቂ የሆነውን የአፓርታይድን አይነት ባንቱስታንስ ወይም የጎሳ መንደሮች ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ከ25 ዓመታት በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የእራሱን ፍርንከንሰትይንን አግኝቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ያጠፋዋል ወይም ደግሞ እራሱ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እንደሚያጠፋ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውጭ የጎሳ ፌዴራሊዝም እንደማይኖር እና ከጎሳ ፌዴራሊዝም ውጭም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊኖር እንደማይችል የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እንደ ዶ/ር ቪክተር ፍራንከንስተይን ሁሉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጭንቅላት እና ልብ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የመለስ ሁሉም ታዛዥ ሎሌዎች እና ታዛዦች ምሁራዊ ክህሎት በአንድ ላይ ተጨምቆ የመለስን አራት አስረኛ እንኳ እንደማይሆን እንዲሁም የእነርሱ ዶ/ር ፍራንከንሰተይን ቢሞትም እርሱ የፈጠራቸው አጭበርባሪዎቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደቀመዝሙሮች በአሁኑ ወቀት በፍርኃት፣ በሰቀቀን፣ በጭንቀት እና በሽብር የቅዠት ዓለም ውስጥ በመኖር ላይ እንደሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚፈጥረው የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ የሚጠራው የፍራንከንሰተይን ስርዓት እራሱ አኝኮ እንደሚተፋው የታወቀ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት ሀገር ለመምራት የሚያስችል አቅም እና ችሎታ እንደሌላቸው የሚታወቅ ታዋቂ ጉዳይ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ተቃውሞ አቀጣጥለዋል በሚል ጅል አስተሳሰብ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን ከዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አባረዋል፡፡ ምንም የማያውቁ ደናቁርት ካድሬዎችን፣ የፓርቲ ተማኝ ሎሌዎችን እና ጋሻጃግሬዎቻቸውን በመተካት ልምድ ያላቸውን የሀገር ባለውለታ የሆኑትን ምርጥ የኢትዮጵያ የቢሮክራሲ አራማጆችን እና ወታደራዊ ኃይሉን በማስወገድ እንዲጸዳ አድርገዋል፡፡ ሰፊ ልምድ ያካበቱ እና ችሎታ ያላቸው አስተዳዳሪዎች እንዲወገዱ ተደረጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ አመራሮች በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሆነው በድረ ገጽ በመጠቀም ዲፕሎማዎችን እና ዲግሪዎችን ከሚቀፈቅፈው ወፍጮ በገንዘብ እየገዙ እራሳቸውን ምሁር በማስመሰል ደንቆሮነታቸውን በሀሰት የወረቀት ምስክር ወረቀት ጭንብል ለመደበቅ ሞክረዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ተራ አባላት በትምህርት እና በሙያ ክህልት ድርቀት እየተሰቃዩ መሆናቸው የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ አብዛኛውን ጊዚያቸውን በጫካ ውስጥ ያሳለፉ ናቸው፡፡ የተመረቁትም የጭካኔ፣ የማሰቃየት፣ የግድያ እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን መፈጸም የሚባሉ ዋና ዋና የትምህርት ኮርሶችን አጠናቅቀው ነው ከጫካ ዩኒቨርስቲ የተመረቁት፡፡ ሆኖም ግን የህግ የበላይነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ወዘተ የተባሉ የትምህርት ኮርሶች በጫካው ዩኒቨርስቲ በፍጹም አይታወቁም ነበር፡፡ ማንም የሚያስብ እና ጭንቅላት ያለው ሰው ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲ ስልጠና እና ትምህርት የሌለውን ወይም ደግሞ በሙያው ዘርፍ ምንም ዓይነት ልምድ እና ተሞክሮ የሌለውን የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነን ግለሰብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሀገሪቱ ዋና የዲፕሎማት ሰው አድርጎ የሚሾም ማን ነው? ሌላ ምንም ሳይሆን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ነው፡፡ የአካባቢ ንጽህና መሀንዲስ የሆነን ግለሰብ የአንድ ታላቅ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሚሾም ማን ነው (ሹመቱ ለስም ብቻ ለይስሙላ መሆኑ እንዳለ ሆኖ)

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እጅግ በጣም ደካማ የሆነ ስብዕና ያለው ድርጅት ነው! የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የወሮበላ ስብስብ የዘራፊ ጥርቅም መሆኑ የሚታወቅ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ (“አምባገነናዊ ዘራፊነት፡ የአፍሪካ ከፍተኛው የአምባገነንነት ደረጃ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትችት ልብ ይሏል፡፡) እነዚህ አምባገነኖች በእራሳቸው ልክ የተሰፋ ልብስ ለብሰው ምንም ዓይነት ዝርፊያ እና ሙስና የማያካሂዱ ለመምሰል ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን ዘራፊ ሌቦችን ከጫካው ማውጣት ይቻላል፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከዘራፊዎች ማውጣት አይቻልም፡፡ ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዘራፊ ጌቶች ያለምንም ተጠያቂነት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ከግንቦቱ የሸፍጥ የቅርጫ ምርጫ በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደተለመደው ሲሰራው የነበረውን የቢዝነስ ስራ እንደዚያው ሊቀጥልበት እንደሚችል የታወቀ ታዋቂ ነገር ነው፡፡ የአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በእርዳታ መልክ እንዲፈስ ያደርጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዩኤስ ኤይድ የተባለውን ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት እንዲመሩት በኦባማ የተጠቆሙት እና እ.ኤ.አ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ደጋፊ የሆኑት ጋይሌ ስሚዝ ጸድቆላቸው ድርጅቱን የሚመሩት ከሆነ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዶላር ባህር ውስጥ የሚዋኝ ይሆናል፡፡ ስለመልካም ዕድል ሰበር ዜና! ከይስሙላው የቅርጫ ምርጫው በኋላ የገንዘብ ዕርዳታዎች ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ ከቻይና፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከሌሎችም እንደ ወንዝ ውኃ ይፈስሳል፡፡ በእርግጥ ህይወት ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጥሩ ይሆናል፡፡ ይኸ ነገር በእርግጥ በእውን የሚሆን ነውን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት መንስኤዎች፡ የሚታወቁ የማይታወቁዎች፣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቃቸው ጥቂት የማይታወቁ ነገሮች አሉ፡፡ ስለሆነም በፍርሀት ይርበደበዳል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጓደኞች እንዳሏቸው ያውቃሉ፡፡ ሆኖም ግን የቁርጥ ቀን ሲመጣ ከእነዚህ ጓደኞች መካከል ስንቶቹ በጽናት ሊቆሙ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የላቸውም፡፡ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አዲሱ ለገሰ ባለፈው ዓመት ስለመልካም ጓደኞች 1፡09 የፈጀ ጊዜ ለቡድኑ እንዲህ የሚል ንግግር አድርጎ ነበር፡ ከእራሳችን ሁኔታ ጋር አዛምደን ስንመለከተው ነገሮች ሁሉ ከእጃችን የወጡ ይመስላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር አይደለም፡፡ ይህንን ጉዳይ የመምሀራን ማህበር ምን ሲያደርግ እንደነበር በማስረጃነት መመልከት ይቻላል፡፡ 2/3ኛ የሚሆነው የመምህራን ብዛት የእኛ ፓርቲ አባላት ሲሆኑ ከመስመር በመውጣት እኛን እየተቃወሙ ናቸው፣ እንግዲህ ይኸ ነው የታሪኩ መጨረሻ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ችግር እየፈጠረ ያለው አረና ትግራይ ብቻ ነው ብየ አላስብም፡፡ ግንቦት 7ትም እንደዚሁ አለ፡፡ የባህርዳር ሁኔታም አለ ብየ አስባለሁ፡፡ በራሪ ወረቀቶች በመበተን ላይ ነው ያሉት፡፡ ይህ ነገር እውነት አይደለምን? ይህንን አልተቀበላችሁምን? ባህርዳር ላይ ተደርጓል፡፡ ምንጩ ከየት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን በራሪ ወረቀቶችን ሲያሰራጩ ነበር እናም በህዝቡ ሲታዩ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ሁኔታ ሲታይ እስከ ህዋስ ደረጃ ድረስ የወረዳ አካሄድ ድረስ እንደሄዱ አስባለሁ፡፡ እራሱን ያደራጀ ኃይል ያለ ይመስላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወዳጆች እንዳሉት ያውቃል ሆኖም ግን ከወዳጆቹ መካከል የትኞቹ እውነተኛ ወዳጆች እንደሆኑ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ወሳኙ ቀን ሲመጣ አባላቱ/ወዳጆቹ መካከል የትኞቹ ዋና ጠላቶች እንደሆኑ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ስለሆነም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንደተወሸቀ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ስርጭቶች የአየር ሞገዱን እንደተቆጣጠሩት እና በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭ የመረጃ ምንጭ እየሆኑ እንደመጡ ያውቃል፡፡ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስሌት እና ግምት መሰረት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በእርግጠኝነት የኢሳትን ፕሮግራሞች የሚመለከቱ እና የሚያዳምጡ መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳት ፕሮግራሞች በህዝቡ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ምን ዓይነት ሽግግራዊ እና መዋቅራዊ እንደምታ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢሳትን ስርጭት ለማፈን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወጭ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በበርካታ አጋጣሚዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የተቆጣጠሯቸው የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን መገናኛ ዘዴዎች በአብዛኛው ህዝብ እንደማይታዩ እና እንደማይደመጡ ለህዝብ አምነዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የማይታወቀው የማይታወቅ ነገር፣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቃቸው የሚችላቸው የማይታወቁ ነገሮች እንዳሉ ያውቃል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሁሉም ክልሎች የለኮሱት የጎሳ እሳት በመጨረሻው ምን እንደምታ ሊያስከትል እንደሚችል የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልሎች በአመጽ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ የፖለቲካ አመጾች አስቤስቶስ በመሆን ከሚቀጣጠለው እሳት ሊድኑ እና ሊያገለግሉ እንደሚችሉ እና አገዛዙን ለዘላለም ሊያቆዩለት እንደሚችሉ አድርጎ ያስባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልል እየተባለ የሚጠራው የትም ሊያስሄድ እንደማይችል እና ተግባራዊነቱ አጠራጣሪ መሆን በውል ተገንዝቧል፡፡ ሆኖም ግን የክልሎች አስቤስቶሱ የበለጠ እየጋለ ሲሄድ እና ጋሱ ወደፊት እና ወደ ኋላ እያለ ሲቀልጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ከፍተኛ ግፊት ይፈጠር እና የህዝቡ ከፍተኛ ቁጣ እና ጥላቻ አውዳሚ የሆነ እሳት በመጫር ሊያስከትል የሚችለውን እንደምታ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ሁኔታ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቀላሉ ሊፈነዳ በሚችል በሰዓት በተሞላ ቦምብ ላይ የተቀመጠ መሆኑን የሚያውቀው አይመስልም፡፡ የማቀጣጠያው ፊውዝ ከክልሎች ጋር የሚገናኝ መሆኑን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፊውዙን በማቋረጥ እሳቱ ተቀጣጥሎ ፍንዳታ እንደሚያመጣ ብልሀቱን የሚያውቀው አይመስልም ምክንያቱም በእብሪት እና በድንቁርና በመሞላት በጭፍን እየጋለቡ ያሉ ፍጡርች ናቸው፡፡ ተቀጣጣዩ ፊውዝ መቀጣጠሉን ቀስ በቀስ እያያዘ ይገኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊ ያለመረጋጋት በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመትን ሊያስከትልበት እንሚችል ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በየመን፣ በሶማሊያ፣ በኤርትራ እና በደቡብ አፍሪካ የተቀሰቀሱት አመጾች ወደ ኢትዮጵያም ሊዛመቱ እንደሚችሉ እና ያልተጠበቀ ቀውስ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያዉቁት ነገር የላቸውም፡፡ ያ አውዳሚ ክስተት መቸ ሊፈጸም እንደሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችል የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔው ጣቶቹን እያወዛወዘ እና እራሱን እያከከ ዝም ብሎ የሚመጣውን ነገር በመመልከት ላይ ይገኛል፡፡ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እሳት እያደገ ሄዶ ወደ 7ኛ የብሄራዊ እሳት ሊሸጋገር የሚችል ማስጠንቀቂያ መሆኑን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችል የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዓይኑን በጨው ታጥቦ በኃይማኖት ላይ ያለምንም ይሉኝታ እጁን በማስገባት ለክርስትና እና ለእስልምና ኃይማኖት እምነቶች የኃይማኖት መሪዎችን እራሱ መርጦ በመሾም እንካችሁ ብሏል፡፡ በኃይማኖት ቡድኖች እና በእምነት ተቋሞች መካከል የኃይማኖት ጽንፈኝነት ጦርነትን ለማምጣት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በእምነቶች መካክል ጭረውት የነበረው ግጭት በምን ምክንያት ስኬታማ ሊሆን እንዳልቻለ ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኃይማኖት ጽነፈኞች በኩል እየጫሩት ያለው እሳት በመጨረሻ እራሳቸውን ሊያወድም እንደሚችል ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የጫካ እሳት ምንም ዓይነት ልዩነት አያደርግም፣ በመንገዱ ላይ ያገኘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ይለበልባል፣ ያወድማል፡፡ ወጣቱ ወደፊት ምን ለማድረግ እንደሚችል ምንስ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወጣቱን በጥቅማ ጥቅም እና በሌሎች ዕድሎች በመደለል የወጣቱን ልብ እናአዕምሮ ለመቆጣጠር እንደማይችል የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በጥቅማ ጥቅም በመደለል ወጣቱን ታማኝ እና ለድርጅቱ ምን ያህል ፍቅር እንዳለው በአባልነት የተለያዩ መደለያዎችን በመስጠት ጥቂት የሆኑ ወጣቶችን ሊያገኙ ለመቻላቸው እንኳ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ገንዘብ ፍቅርን ወይም ደግሞ ታማኝነትን ሊገዛ እንደማይችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚያውቀው ነገር አይደለም፡፡ ወጣቱ ከምንም በላይ ነጻነቱን ይፈልጋል፡፡ አብዛኛውን ሙያዊ ህይወቴን ያሳለፍኩት በዓለም ላይ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ነው፡፡ ከሁሉም ነገሮች በላይ ወጣቶች በሁለት ነገሮች ላይ የበለጠ ፍላጎት ያሳያሉ፡ እነርሱም እኩልነት እና ነጻነት ናቸው፡፡ የእኔ አመለካከት “የዓለም ወጣቶች ድምጽ በድህረ 2015” በሚል ርዕስ በበርካታ ሀገሮች ከተጠናው ጥናት ጋር ተደጋጋፊ ሆኖ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የዜግነት ደረጃቸው፣ የህይወት ዕድሎቻቸው እና ዕጣፈንታዎቻቸው በአባልነት እና በታማኝነት ላይ በተመሰረተ መብትን፣ እኩልነትን እና ነጻነትን በገፈፈ በአንድ ቡድን ወይም ድርጅት እንዲወሰን በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ወጣቶች ግላዊ ነጻነትን መቀዳጀት እና የሀገራቸውን ዕድል መወሰን እንደሚፈልጉ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ወጣቶች የህግ የበላይነት የሰፈነበት እና የግለሰብ መብቶች ሙለ በሙሉ የሚጠበቁበት እኩልነት የሰፈነበት

ስርዓት ተመስርቶ ማየት ይፈልጋሉ፡፡ .... ወደ ገፅ 13

Page 13: ልሳነ ህዝብ - welkait.comwelkait.com/wp-content/uploads/2015/08/ልሳነ-ህዝብ-ቅፅ-1-ቁጥር-12.pdfየሚገባ ተግባር ነው:: ይህም አንደኛው በሺዎች

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 1 ቁጥር 12 ገፅ 13

የወያኔ ወሮበላ ከገፅ 12 የዞረ የተቃዋሚ ኃይሎች በአንድነት ህብረት ፈጥረው በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘውን አካል በአንድ ወቅት አስፈንጥረው እንደሚጥሉት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው ያልቻለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ ጋዳፊ እየታደነ እና እንደ አይጥ ከፉካ ውስጥ ተወሽቆ በተቃዋሚዎች ተይዞ በተገደለበት ወቅት እንዲህ የሚል የመማጸኛ ንግግር ተናግሮ ነበር፣ “ህዝቦች እኔን ይወዱኛል!“ በታሪር አደባባይ ላይ እርሱን ከስልጣን ለማውረድ ህዝባዊ አመጽ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በነበረበት ጊዜ ለሙባረክ ማንም የተጻፈ ማስታዋሻ ወይም ደግሞ የኢሜይል መልዕክት አልላከም ነበር፡፡ ጊዜው በመጣበት ጊዜ መጣ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ላይም ጊዜው ሲመጣ ይመጣበታል፡፡ ሆኖም ግን ጊዜው መች እንደሚመጣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቀው የማይችለው የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ መቸ እንደሚወድቁ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውስ ምን ሊሆን እንደሚችል ቀኑ መቸ እንደሆነ ለመተንበይ በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን በማሳለፍ ላይ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ መች እንደሚመጣ እና እነርሱን ወደ ታሪክ አተላ ሊጥላቸው እንደመሚችል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቁት የማይችሉት የማይታወቅ ነገር ነው፡፡ ዴሞክራሲ የህግ የበላይነትን ጋሻ እና የተጣያቂነትን ጦር በመያዝ መቸ እንደሚመጣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊያውቁት የማይችሉት ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርሀት ምክንያት፡ የማይታወቀው የሚታወቅ ነገር (የሚታወቅን ታዋቂ ነገር መካድ)፣ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እያወቀ ሆን ብሎ ለመቀበል ፈቃደኛ የማይሆንባቸው እና እያወቀ ዕውቅና የማይሰጥባቸው እውነታዎች አሉ፡፡ ስለሆነም ይፈራል! የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እስከ አሁን ድርስ ለሰሯቸው ወንጀሎች አሁን ወይም ቆይቶ በህግ አደባባይ ቀርበው እንደሚጠየቁ እያወቁ ያላወቁ መስለው ለመቅረብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ “ፍትህ እንደ ባቡር ነው፣ ሁልጊዜ ይዘገያል” የሚለውን እውነታ የማያውቁት ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይዘገያል የሚለውን ቃል በፍጹም እንደሚል ቃል አድርገው ይገነዘቡታል፡፡ በእነርሱ የድንቁርና እብሪት ተነግሮ ለማያልቀው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለፈጸሟቸው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ የማያውቁ መስለው ለመቅረብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁ 193 ሰላማዊ ዜጎችን በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ ገድለው እና ሌሎች 800 የሚሆኑትን ደግሞ የመግደል ሙከራ አድርገው በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆኑ በእርግጠኝነት አምልጠው የሚሄዱ ይመስላቸዋል፡፡ ጊዜው ሲደርስ ለህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ ማለት ጸሐይ በጠዋት ትወጣለች የማለት ያህል እውነታነት ያለው ነገር ነው፣ ምክንያቱም የዩኒቨርስ ግማሽ ጥምዝ ክብነት ረዥም ነው፣ ሆኖም ግን ሁልጊዜ ወደፍትህ ያጋድላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ ህዝብ ላይ ተካሂዶ ከነበረው እልቂት ጋር በተያያዘ መልኩ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተመስርቶበት ከነበረው ክስ እንዲለቀቅ ለማድረግ ያለ የሌለ ጥረታቸውን አድርገዋል፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ አምባገነኖች ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በመቅረብ ጉዳያቸው በፍትህ አደባባይ እንዲመረመር ስልጣን የሚሰጠውን የሮም ስምምነት በመጣስ የአፍሪካ የድርጅቱ አባል ሀገሮች በጅምላ ለቀው እንዲወጡ በማስተባበር ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል እድርገዋል፡፡ ኡሁሩ በሰራው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል ወደ ዘብጥያ ሲወርድ በቀጣይነት ደግሞ እነርሱ እንደሚገቡ ያላወቁት ሆኖም ግን የሚያውቁት ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፍትህ እንደባቡር ትዘገያለች፡፡ በማረፊያ ጣቢያዋ እስከምትድርስ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደሚባለው በእርግጠኝነት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ነውን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ውስጥ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ በአጠቃላይ ወታደሩን፣ የምጣኔ ሀብቱን፣ ቢሮክራሲውን በብቸኝነት ጨምድዶ ይዞ እና ከ5 ሚሊዮን በላይ አባላት አለኝ የሚል ኃይል በፍርሀት ውስጥ ነው የሚለው ክርክር አመክንዮ የለውም፡፡ ከዚህ በተጻረረ መልኩ ግን ፍርሀት እራሱ ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወታደራዊ ኃይሉን፣ ቢሮክራሲውን፣ የምጣኔ ሀብቱን፣ ወዘተ በብቸኝነት ጠቅልሎ ይዞት እንዲቀጥል ያደረገው፡፡ ፍርሀታቸውን ለማሸነፍ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስልጣንን ያዙ፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ይገኛሉ፡፡ ፍርሀት እራሱ እነርሱን ድል አድርጓቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ፍርሀት ግላዊ እንጅ ድርጅታዊ አይደለም፡፡

በመጨረሻም የህዝቡ ቁጣ እነዚህን አምባገነኖች እንዳለ በመክበብ ውጧቸዋል፡፡ ዓሊን በቱኒሲያ ለማስወገድ ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው የወሰዱት፡፡ ሙባረክን ከዙፋኑ አውርዶ ለመጣል ጥቂት ሳምንታትን ወስዷል፡፡ ጋዳፊን ለማስወገድ ደግሞ ጥቂት ወራትን ጠይቋል፡፡ በሶሪያ አላሳድን ለማስወገድ 5 ዓመታትን የወሰደ ሲሆን አሁንም ቢሆን ከስልጣኑ አንኮታኩቶ ጥሎ ወደ ታሪክ ቆሻሻነት ለመቀየር ኃይለኛነቱን እንደቀጠለበት ይገኛል፡፡ እነዚህ አምባገነኖች ለበርካታ አስርት ዓመታት ያህል የጭራቃዊነትን ረዥም ጥላቸውን በህዝብ ላይ ጥለው ቆይተዋል፡፡ በመጨረሻም የእራሳቸው ጭራቃዊ ጥላ ከስልጣናቸው ላይ እንዲያጠላባቸው ተደርገዋል፡፡ ታሪክ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ዋና ፍርሀት ያወግዛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የገነባው የፍርሀት ግንብ ጡቦች ቀስ በቀስ እያሉ እየፈረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ እየፈረሱ የሚወድቁት ጡቦች ወያኔው እራሱን እንዲደብቅበት ከለላ ሆነዋል፡፡ ሆኖም ግን የህዝቡን የቁጣ የሱናሜ ማዕበል ሊያስቀር የሚችል ምንም ዓይነት ግድግዳ የለም፡፡ ፍትህን የደፈጠጠ ማንም ደፋር የሆነ ወንጀለኛ ሰው ቢሆንም እንኳ ዞር በማለት እራሱን ይመረምራል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ምን እንደሰራ ስለሚያውቅ ነው፡፡ በጭራቃዊው ምዕናብ ላይ የሚታይ ይሆናል፡፡ ፖሊስ ከእርሱ በኋላ ሲመጣ ይታያልን? ሰዎች ሲተነፍሱ የሚመለከት የአዕምሮ በሽተኛ ሆኗል፡፡ ስለእርሱ ጉዳይ ያወራሉን? የፖሊስ መኪና የፎቶግራፍ ካሜራ ይዞ ይመለከታል፡፡ እርሱን ለማግኘት እየመጡ ነውን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወንበዴዎች ሁለጊዜ ትከሻዎቻቸውን ነው የሚመለከቱ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን በከበበው ፍርሀት ላይ የመጨረሻው ክሴ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች መጠጫ ምን ሊሆን እንደሚችል ጥቂቶች ሊተነብዩት የሚችሉት ጉዳይ ነው፡፡ እነርሱ ገንዘብ አይደለም የሚፈልጉት፡፡ ይኸ እጅግ በጣም ብዙ አላቸው፡፡ ሁሉንም ነገር ለማድረግ ሁሉም ስልጣኑ አላቸው፡፡ ሙገሳን አይፈልጉም፡፡ ሆኖም ግን አንድ በጣም የሚፈልጉት ግን የማያገኙት ነገር ቢኖር ከህዝቡ ጋር አብሮ መሄድ እና የህዝቡን ከበሬታ ከማግኘቱ ላይ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና የእነርሱ ታዛዥ ሎሌዎች በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው እየኖሩ ስለመሆናቸው እውነታውን በእርግጠኝነት አላውቅም፡፡ ነግር ግን በእርግጠኝነት የማውቀው ጉዳይ ቢኖር ህዝቡ ከቀን ወደ ቀን ድፍረቱን እየጨመረ መጥቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱ በፈጠረው ችግር ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ፍርሀት ውስጥ እየሰመጠ እንደሚገኝ እውነታውን አውቃለሁ፡፡ ህዝቡ እየተነሳሳ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደግሞ ወደ መቀመቅ እየወረደ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁለት አማራጮች አሉት፡፡ እንዲህ የሚለውን የኔልሰን ማንዴላን መንገድ መከተል ይችላሉ፡፡ “ጀግና ማለት የማይፈራ ማለት አይደለም ሆኖም ግን ጀግና ማለት ፍርሀትን የሚያሸንፍ ነው፡፡“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ያለበትን ፍርሀት በነባራዊ ካሉት እና ሊመጡ ከሚችሉት ጠላቶች ጋር ሰላም በመፍጠር ድል ማድረግ ይችላል፡፡ ሌላው አማራጭ ደግሞ ፍርሀትን እራሱን በመፍራት ከፍርሀት ግድግዳ ጀርባ በመሆን የአሸዋ ቤተመንግስት መገንባት ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ፍራንክሊን ሩዝቬልት እንዲህ በማለት ተናግረው ነበር፣ “እኛ መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ስምየለሹን፣ በአመክንዮ የማያምነውን፣ የሚያስልጉ ጥረቶችን በሽብር የሚያመክነውን ፍርሀትን እራሱን ነው፡፡“ እንግዲህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫ ይኸ ነው! የዘረፋው የግንቦት 24/2015 የቅርጫ ምርጫው እንዴት ነው? ምርጫን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለአፍሪካ ህዝቦች ሁሉ ያስተምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ መርህ አልባው የሱዳኑ ኦማር አልባሽር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አካሂዶት በነበረው ምርጫ 94.04 በመቶ በሆነ የድምጽ ውጤት ያሸነፈ መሆኑን አውጆ ነበር፡፡ ይኸ ምንም ነገር ሳይሆን ባዶ ነገር ነው! የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከአምስት ዓመታት በፊት የቅርጫ ምርጫ በማካሄድ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ሲያውጅ አሁን በህይወት የሌለው መለስ እንዲህ የሚል ንግግር ነበር ያሰማው፡ ለእኛ ድምጻቸውን ያልሰጡን ዜጎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ለእኛ ድምጻቸውን ያልሰጡን ዜጎችን ፍላጎት በጽኑ በማክበር የነበሩብንን ደካማ ጎኖች እና ድክመቶች በማስተካከል የእነርሱን ድምጽ በቀጣዩ ምርጫ ለማግኘት ስንል ሌት እና ቀን የምንሰራ መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ስለሆነም ትክክለኛው ጉዳይ እና በግንቦት 2015 ስለሚካሄደው የቅርጫ ምርጫ እ.ኤ.አ በ21010 ድምጻቸውን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ያልሰጡትን ሰዎች ልብ ማሸነፍ እና የአንድ ፐርሰንት 4/10ኛ የሆነችዋን ቁርጥራጭ ቁጥር በማሟላት በ2015 መቶ በመቶ ማሸነፍ ነው፡፡ አልባሽር ተበልጠሀል ልብህን ብላ! መቶ በመቶ በማምጣት አስከንድተንሀል! እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ በማለት እንዲህ የሚል ንግግር ያደርጉልናል፣ “ባለፈው ጊዜ ምርጫውን መቶ በመቶ ባለማሸነፋችን በጣም አዝነናል፡፡ ጭራዎቻችንን በእግሮቻችን መካከል ወትፈናል፡፡ አሁን ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል!“ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሙሉ የቅርጫ ምርጨውን መቶ በመቶ በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አስደማሚ በሆነ መልኩ በዝረራ ለሚያሸንፈው የቅርጫ ምርጫ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለማስተላለፍ የመጀመሪያው እኔ እንደምሆን ለእያንዳንዱ ሰው ግልጽ ለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ “መንግስት ህዝብን መፍራት ሲጀምር ነጻነት አለ ማለት ነው፡፡ ህዝብ መንግስትን መፍራት ሲጀምር ደግሞ አምባገነንነት ተንሰራፍቷል ማለት ነው፡፡ “ ቶማስ ጃፈርሰን ህዝብን ፍሩ! እውነትን ፍሩ! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም

ሰላም እንሰንብት ሃሳባችሁን በ [email protected] ላኩልን እናስተናግዳቸዋለን።

እያንዳንዳቸው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር እና አባላት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ናቸው፡፡ ነግር ግን የሁሉም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በመቀላቀል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የግል ኃላፊነቱ የተወሰነ የፍርሀት ማህበር ድርጅትን ፈጥረዋል፡፡ ፍርሀት እራስን ለመጠበቅ ከሚደግ ተፈጥሯዊ ክስተት ይመነጫል፡፡ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ በቶማስ ሆብስ ጽሁፎች ላይ በጣም እመሰጥ ነበር፡፡ ይህ ሲባል እነ ሎኬን፣ ማቻቬሊን፣ አኩይናስን፣ ዲስካርተስን፣ ማርክስን፣ ሩሴልን እና ሌሎችን ጥቂቶች ጸሐፊዎችን በማግለል አይደለም፡፡ በእርግጥ ስለአምባገነንነት ጽሁፍ ያበረከተው እና ክብር የማይሰጠው እንዲሁም ሁሉንም ባህል ለማጥፋት ጥረት የሚያደርገው ቶም ባይኔም አለ፡፡ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ በተለይም በሆብስ “የሉዓላዊነት ፍጹምነት” ሀሳቦች ላይ እና ፍርሀት ፍጹምነትን በምን ዓይነት አመክንዮ እንደሚመለከት በሚለው ላይ የተለየ ትኩረት አለኝ፡፡ ሆብስ አምባገነንነት እያልን በምንጠራው ላይ ጠቃሚ የሆኑ እይታዎችን አካትቷል፡፡ ንጉሳዊ አገዛዙ በተገዥዎች ላይ ፍጹም የሆነ ስልጣንን የሚያሳይ የንጉሳዊ መንግስት ቅርጽን በመፍጠር ረገድ በጣም ፍላጎት ነበራቸው፡፡ የሆቤሲያን ፍጹማዊ ንጉሳዊ አገዛዝ በአሁኑ ጊዜ ካለው ዘመናዊ ፍጹማዊ አምባገነንነት ጋር እኩል ይሆናል፡፡ ሆብስ ፍርሀት በተፈጥሯዊ ባህሪ ላይ ይሰራጫል በማለት ሞግተዋል፡፡ (ምዕናብ የሰው ልጆች የሲቪል ማህበረሰቡን ከመፍጠራቸው በፊት እራሳቸው እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡) በተፈጥሮ ባህሪ የሰው ልጆች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በፍርሀት እና በኃይለኛ የሞት አደጋ ውስጥ ገብተው ይናጣሉ፡፡ እናም የሰው ልጅ ህይወት ብቸኛ፣ ደኃ፣ ደስታ የራቀው፣ ጨካኝ እና ባለጌ ይሆናል፡፡ ሆብስ ሲቪል ማህበረሰቡ በጋራ ፍላጎት ላይ በመመስረት እና ለእያንዳንዱ በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ሁሉም እያንዳንዳቸው ባላቸው ፍርሀት እንደነበር ሞግተዋል፡፡ ፍርሀታቸውን ከማውጣት ከሚጠብቃቸው ውጭ እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው ጋር ተጻራሪ በመሆን ጦርነት እየተባለ በሚጠራው መጥፎ ድርጊት ውስጥ እራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያን ሲቨል ማህበረሰብ ወደ ሆቤስቲያን የተፈጥሮ ባህሪ ወስዶታል ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣንን ሲቆናጠጥ በጫካ ውስጥ ሲሰሩት የነበረውን ባህል ይዘው በመምጣት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ላይ መተግበር ጀመሩ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ በጫካው ህግ ይገዙ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጫካውን ህግ በህግ የበላይነት ለመተካት ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ስለሆነም አሁንም ቢሆን በጫካ ውስጥ ሲያደርጉት አንደነበረው ሁሉ ሰላማዊውን ህዝብ ያስፈራራሉ፣ ያሸማቅቃሉ፣ ያስራሉ፣ ስቃይ ያደርሳሉ እንዲሁም በተቃዋሚዎቻቸው ላይ ግድያን ይፈጽማሉ፡፡ ከዚህም በላይ በሲቪሎች ላይ የሽብር ድርጊትን ይፈጽማሉ እንዲሁም በሀሰት ተቃዋሚዎቻቸውን ይወነጅላሉ፡፡ በእርግጥ ለእነርሱ በሚስማማ መልኩ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ለሩብ ዓመታት ያህል የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በጣም ውስብስብ የሆነውን የኢትዮጵያን ሲቪል ማህበረሰብ ወደ ሆቤሲያን የተፈጥሮ ባህሪ መልሰውታል፡፡ በሆቤስቲያን የተፈጥሮ ህግ መሰረት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፍጹማዊ አምባገነኖች ተፈጥረዋል፣ ይከሰታል ብለው በሚፈሩት የህዝብ አመጽ፣ ሽፍትነት፣ ህዝባዊ ነውጥ እና አብየት ምክንያት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ አስቀድሞ ሊወሰን በማይችል የሚታወቅ ታዋቂ፣ በሚታወቅ የማይታወቅ እና በማይታወቅ የማይታወቅ የተፈጥሮ ባህሪ ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋናው ፍርሀቱ ለውጥ ነው፣ ለውጥ መጣ ማለት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት 24 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ያከማቸውን ስልጣኑን እና ክብሩን አጣ ማለት ነው፡፡ ለውጥን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥ ማለት ደህና፣ ማን ያውቃል? ለውጥ የማይቀር ተፈጥሯዊ ህግ ነው፡፡ በዩኒቨርስ ላይ በቋሚነት በሂደት ላይ የሚገኘው ለውጥ እራሱ ነው፡፡ ለውጥ የሚታወቅ ታዋቂ፣ የሚታወቅ የማይታወቅ፣ የማይታወቅ ታዋቂ ወይም ደግሞ የማይታወቅ ታዋቂ ያልሆነ ቢሆንም ባይሆንም መምጣቱ የማይቀር የተፈጥሮ ህግ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች አናሳ የሆነ አመላካከት እና እይታ ያላቸው በመሆናቸው ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ነገር ብቻ አይደለም የሚፈሩት ሆኖም ግን የወደፊቱን ጭምር ነው፡፡ ድንቁርና ፍርሀትን ይፈለፍላል፡፡ ፍርሀት ማቆሚያ የሌው ደህንነትን ይጠይቃል፡፡ አንድ ዋና የሆነ የሚታወቅ ታዋቂ፣ ታዋቂ የማይታወቅ እና መወሰን ከማይቻለው ፍርሀት ጋር እንዴት ነው ስምምነት ማድረግ የሚቻለው? ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መሰረት የሌለውን ፍርሀት መፍራቱን እንዲያቆም በመወገዝ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ለእዚህ የእራሳቸውን ቅርጽ ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ናቸው፡፡ ግንቦት 7፣ አንድነት ፓርቲ፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና አረና ፓርቲ…አሸባሪነት ነው፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በተለይም አክራሪው እና ጽንፈኛው ዲያስፖራ ነው በዚህ ዓይነት መልክ እየተፈረጀ ያለው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በስልጣን ላይ እስከሌለ ድረስ በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ስርዓተ አልበኝነት ሊፈጠር እንደሚችል በተደጋጋሚ ሲለፍፍ ቆይቷል፡፡ እነርሱ በስልጣን ላይ እስካልኖሩ ድረስ የእርስ በእርስ ጦርነት እና እልቂት እንደሚመጣ ህዘቡን በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይኸ ድድብና የተቀላቀለበት ንግግር ቀበሮ በጎችን እረኛ ሆኖ ከመስክ ሲጠብቃቸው ውሎ ማታ ወደ ጉረኗነቸው በማምጣት እንደሚያስገባቸው ዓይነት የመጠበቅ ሁኔታ ነው፡፡ በአረቦች የጸደይ አብዮት ህዝብ ፍርሀቱን አስወግዷል እናም አምባገነኖችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጀንበር ላይ ይፈጸማል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ይህን ሁኔታ በአስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ የአረብ አምባገነኖች ለበርካታ አስርት ዓመትት በብረት ጡንቻቸው ቀጥቅጠው ገዝተዋል፡፡