2008 ዓም10+last.pdf · 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞ ግንባር...
TRANSCRIPT
የኢትዮዽያ ሕዝብ በኑሮ ውድነት እና በፍትህ እጦት ምክንያት በእርሀብ፣ በእስራት እና በስደት ላይ ይገኛል
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ምክር ቤት በጀርመን ተመሰርተ
አዲሱ አመት 2008 ዓ.ም. ለኢትዮዽያውያን የነጻነት እና የሰላም ጊዜ እንዲሆን እንመኛለን
2008 ዓ .ም.
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞ ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባውን በፍራንክፈርት ከተማ
በ11/07/2015 በተሳካ ሁኔታ አካሄደ
(The regular meeting of EPPFG held successfully on 11/07/2015 in
Frankfurt)
ጎሕ መጽሔት
1 Goh magazine, July 2015, 2
ዋና ስራ አስኪያጅ ልዑል ቀስቅስ
ዋና አዘጋጆች ደሳለኝ አበባው አለሜ ቡቃያ
ም/አዘጋጅ ጌታቸው ሐይለማርያም አያኖ
ኤዲተር አለማየሁ ጥበቡ
ኮምፒውተር ፁሁፍ ፎዚያ ጫጮ
ግራፊክስ ሙሴ ቢሆነኝ በትረ
ካርቶኒስት & መፅሐት ስርጭት ሞሐመድ ባልቻ አብዱልሀኪም
ፎቶግራፍ ይህደጎ ሚካኤል ምኮንን
ፅሁፍ አስተባባሪ ምነወር አብድልዋሂድ ክማል
መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
General Manager Leul Keskis
Editors in Chief Desalegne Abebew
Alemie Bukaya
Assistant Editor in chief Getachew Hailemariam Ayano
Editor Alemayhu Tibebu
Computer Writing Foziya Chacho
Graphics Musie Bihonegn Betre
Cartoonist & Distributer Mohammed Balcha, Abdulhakim
Photographer Yihedego Michael Mekonnen
Organizer Minewer Abdulwahid Kemal
Getachew Hailemariam Ayano
Cartoonist & Distributer Mohammed Balcha, Abdulhakim
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
2 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ማውጫ
የመጣጥፎች ይዘት ገጽ ነጻነታችን በእጃችን ነው፣ ህወሃት ካልተገረሰሰ እርሐቡም፣ እስሩም ይቀጥላል! ......................................................................... 3
ተነስ ወገኔ .................................................................................................................................................... 4
አንድ መሪ ኣላት ተብሎ የምትከበር አገር ............................................................................................................... 4
በተጭበረበረ የፖለቲካ ሽፋን የህግ የበላይነት ተቀብሯል ............................................................................................ 4
የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው .................................................................... 5
ሃገራችንን ሃገር እናድርግ .................................................................................................................................. 5
የ 2007 ምርጫ ቢቀርስ................................................................................................................................... 6
የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻ ........................................................................................................................... 6
ማስመሰል ይብቃን ......................................................................................................................................... 7
በወያኔ ድንክየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ዕስከመቸ? ....................................................................................................... 7
የወያኔ ጥላቻ ፍሬ ........................................................................................................................................... 8
ያለፈውን ስርዓት መናፈቅ ................................................................................................................................. 8
የሕወሓት ማፊያ ቡድን ከምድረገጽ መጥፋት አለበት ................................................................................................ 9
መሪ አልባ አገር .............................................................................................................................................. 9
ኑሮ ተወደደ ................................................................................................................................................ 10
መሪ የሌለው ህዝብ ....................................................................................................................................... 11
የነጻነት ተስፋ .............................................................................................................................................. 11
Ethiopia is Stuck .................................................................................................................................... 12
The youth of Ethiopia ............................................................................................................................ 13
Ethnic politics is an existential threat to all Ethiopians ......................................................................... 14
What shall we do? ................................................................................................................................. 15
Weyane (TPLF) und die Verfassung ..................................................................................................... 16
አርበኛ የሚያሰኝህ ........................................................................................................................................ 19
ድምጽ የሌለው ጥይት.................................................................................................................................... 19
ዱላ ቅብብል (ለአሁኑ ገዢዎቻችን) ................................................................................................................... 19
ፍትህን ፍለጋ .............................................................................................................................................. 19
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
3 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ርዕሰ አንቀፅ ኢትዮዽያ በዲሞክራሲ እና በምግብ እጥረት በአንደኝነት ላይ ትገኛለች
ሕወሃት ሁለት መገለጫዎች አሉት። የመጀመሪያው የጦር ሃይሉን በመተማመን፣ በጉልበት ስልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ
ዘላለም እገዛለሁ ብሎ ማሰቡ ነው። የመሳሪያ ባለቤት በመሆኑ፣ የተቃወመኝን እያሰርኩ፣ ጠላቴን እየገደልኩ፣ እንዲሁም
ከተቃውሞ የማይታቀበውን እያስፈራራሁ ለረጅም ጊዜ እኖራለሁ ብሎ ያምናል። እዉነትም ህወሃት በከፊል ትክክል
ነበር፣ በጉልበት እያስፈራራ፣ እያሰረ፣ እየገደለ ለ25 አመታት ያለምንም ችግር ዘልቋል። ከራሱ ከህወሃት የተፈጠሩ የጦር
መኮንኖችን ብቻ ስልጣን ላይ አስቀምጦ፣ በሙስና እንዲዘፈቁ በማበረታታትና፣ የሚያማልል ስጦታ በመስጠት፣
እንዲሁም እነዚሁን የጦር መኮንኖች የወንጀል ተባባሪና መሪ በማድረግ የ”አብረን እንዝለቅ” ጨዋታ ተክኖበታል።
ሁለተኛው የህወሃት መገለጫ ደግሞ ከመንግስት ባለስልጣናት ያውም ከሚኒስትሮች የማይጠበቁ ዘረኝነት፣
ስግብግብነት፣ ውሸትና፣ የሞራል ዝቅጠት ነው። አብዛኞቹ ባለስልጣናት በዘረኝነት ዛር የሰከሩ ወፈፌዎች ናቸው።
የራሳቸውን ብሄር “ወርቅ” በማለት የሚያሞካሹ፣ ሌላውን ብሄረሰብ ግን “ትምክህተኛ፣ አክራሪ፣ ብሄርተኛ” የሚል
ታፔላ በመለጠፍ በጅምላ የሚሳደቡ ናቸው። እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመታት በኋላም
ቢሆን ከችግር፣ ረሃብና፣ እርዛት ኣልተላቀቀም። የህወሃት ባለስልጣናት ግን ገንዘብ ተርፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠር
ዶላር ወደ ውጭ አገር እያሸሹ እንደሆነ አለም የሚያውቀው ሃቅ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይኸው ከ 24 አመት
የስልጣን ጊዜ በኋላም ከ24 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ይፈልጋሉ። የህወሃት አሽከሮችና ጭፍሮቻቸው
በምግብ ራሳችንን ችለናል የሚል ልፈፋ ሲያሰሙ ከርመው ነበር። የታል ታዲያ? እርግጥ ነው የህወሃት ባለስልጣናት
ኪስ በ11 ሚሊዮን % አድጓል። የህዝቡ ኑሮ ግን 1% እንኳን ከፍ አላላም። እርግጥ ነው በህወሃት መንደር እና
ሎሌዎቻቸው ቤት ምግብ ተትረፍርፏል፣ በሱማሌ፣ በአፋርና፣ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች፣ የገበሬዎች የቤት እንስሳትና
የቀንድ ከብቶች ተረፍርፈዋል።
እንግዲህ ህወሃቶች ለስልጣናቸው ሊያሰጋቸው የሚችል ሰው ባይሆንም እንኳን ለሆድ የማይደለል ተቃዋሚ ወይም
ጋዜጠኛ ባጋጠማቸው ቁጥር በመጀመሪያ ማስፈራራትና ማሰር፣ ካልሆነም መግደል ለአስርተ-አመታት የተካኑበት አሳዛኝ
ድራማ ነው። እናም በኢትዮጵያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በውሸት ፖለቲካዊ ክስ ተፈርዶባቸው የሚማቅቁ
ኢትዮጵያውያንን ማዕካላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ እና ስማቸው የማይታወቁት የጨለማ እስርቤቶች
ይቁጠሯቸው! እንግዲህ ምርጫ በመጣ ቁጥር ተቃዋሚዎችን እያደኑ ማሰር ምርጫው ካለፈ በኋላ እንደገና መልሶ
መፍታት የተነቃበት የህወሃት ታክቲክ ከሆነ ሰነባብቷል። ስለዚህ መቀየር ያለበት የህወሃት ሶፍትዌር ነው። አርጅቷል።
በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የዘረኝነት፣ የአምባገነንነት፣ የማን አለብኝ ባይነት፣ አድሏዊና የቂመኝነት አስተሳሰብ ይዞ
አገርን የሚያክል ግዙፍ ነገር መምራት አይቻልም። ስለሆነም በአዲስ አሰተሳሰብ መቀየር አለበት። ከአርባ አመት ከፊት
በነበረ ሶፍትዌር አሁንም አገር እየመሩ ያሉ ቡድኖች መፍረስ አለባቸው። ያ የሚሆነ ደግሞ የህወሃት ዘረኞችን ከስልጣን
በማባረር ነው። ትግል መደረግ ያለበት ከሻቢያ ወይም ከግንቦት ሰባት ጋር አይደለም ፣ ከወያኔ ጋር ነው። ወያኔ
ከተለወጠ ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ የሚገደል፣ በውሸት ክስ የሚታሰር አይኖርም። ከሁሉም በላይ ውሸት የሚፈበርክ
ተቋም አይኖርም።
ነጻነታችን በእጃችን ነው፣ ህወሃት ካልተገረሰሰ እርሐቡም፣ እስሩም ይቀጥላል!
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
4 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ተነስ ወገኔ Merry Adnen Abdo Frankfurt, Germany
ኣትነሳም ወይ ኣትነሳም ወይ ይሄ
ባንዲራ ያንተ ኣይደለም ወይ?
ከነኩት የማይተው ቆራጥ ህዝብ
ኣንዴ ከተነሳ የሚያስቆመው
የለምና የወያኔ መንግስት እራሱ
በመላው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ዱላ
ይዞ ህዝብን ሲደበድብ ዋለ። ቆይ
ግን ህዝብ ለዳቦና ለዘይት ብቻ
ነው እንዴ ሰልፍ የተፈቀደለት
ኢትዮጵያ ውስጥ?ያሳፍራል።
በጣም ያሳፍራል። ኢቲቪ የሟች
ቤተሰብን ሳያሳየን እናጣራለን ባለ
ቅጽበት ኣልጀዚራ የሟች
ቤተሰቦችን በቴሌቪዥን መስኮት
ብቅ ኣደረገ። ከዚያ ቀጠል
ኣደረገና የወያኔ ኣጎብጓቢ ሰልፍ
በሰላም ተጠናቀቀ ሲል ያ
የለመደው የኢትቪ ጠላት ሰልፍ
ኣንዴት እንደተጠናቀቀ ግልጽ
በሆነ መረጃ ኣሳየን። ከራሱ ታሪክ
ተሞክሮ መማር ያልቻለው
የኢሃዴግ ስር ኣት በተደጋጋሚ
የሚፈጽማቸው የመብት ጥሰቶች
እና ተቃዉሞን በሃይል ለመፍታት
ስለሚወስደው እርምጃም
ችግርን፣ ቁጣን፣ ተቃዉሞን
ከማባባስ በስተቀር መፍትሄ
ካለመሆኑም በላይ በሰላማዊ
መንገድ የስልጣን ሽግግር
እንዲካሄድ እና የኣመጽና የጦርነት
ኣዙሪት እንዲከስም ጭቆናን
ተቋቁመን የምናደርገው ትግል
ለማኮላሸት መሞከሩ የከፋ ኣደጋ
ኣንዳለው ለማስገንዘብ
እወዳለሁኝ። የህዝብን ጥያቄ
ያለፍርሃት በማንሳት እና
ተቃውሞ በማሰማታችን እየደረሰ
ያለዉን ኣፈናና ድብደባ ችለን
በምናደርገው ትግል ውስጥ ድልን
እንጎናጸፋለን። ኣትነሳም ወይ
ኣትነሳም ወይ ይሄ ባንዲራ ያንተ
ኣይደለም ወይ? ድል ለኢትዮጵያ!
አንድ መሪ ኣላት ተብሎ የምትከበር
አገር Zeweter Woldetsadik Frankfurt, Germany
ዜጎቿ ላይ እንዲህ ኣይነት በደልና
ጭካኔ ሲደርስባቸው እየሰማና
እያየ ዝም የሚል መንግስት ኣለ
ቢባል ግፍ ይሆናል። የወያኔ
መንግስት ምን እየሰራ ነው
ያለው? በስደት ያሉት ዜጎች
ኣይደሉም ። ለኢትዮጵያ
ኢንቨስት ለማድረግ የሚገባዉን
ዲያስፖራ በማለት በደስታ
ይቀበለዋል። ኣገሩ ውጭ
በሚደርስበት ችግር ግን ከጎኑ
የለም። እንዴት መንግስት ያላት
ሃገር ዜጎቿ ላይ እንዲህ ኣይነት
ችግር ሲደርስበት ዝም ይላል።
ከዚህ ቀደም ከኣረብ ኣገር ያ ሁሉ
በደል በዝምታ ኣሁን ደግሞ
በደቡብ ኣፍሪካ የደረሰው ጭካኔና
በደል ኣጅግ በጣም የሚዘገንን
ነው። መጠለያ ያጣ ትውልድ
ባገሩ ለመኖር ለመስራት ያልቻለ
ትውልድ ለነገሩ ወያኔ እራሱ ባገሩ
የሚፈጽመው በደል በሰው ሃገር
ቢደገም ምን ቸገረው? ዝምታው
ይብቃ። እኛ በስደት ያለን
ተጋግዘን ያገራችንን ሰላም፣
ፍቅር፣ ኣንድነት እንመልስ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
በተጭበረበረ የፖለቲካ ሽፋን የህግ የበላይነት ተቀብሯል
Mulugeta Mulat Germany
በተግባር ፍትህን እና መልካም
አስተዳደርን እውን ለማድረግ
በቁርጠኝነት የተነሳ ማንም
የለም::ስርኣቱም በጥቅመኞች
የሚመራ ህዝቡም ላላወጣው ህግ
በዝምታ ተቃውሞውን እየገለጸ
ነው; ፍትህን እና መልካም
አስተዳደርን የሚጥስና
የሚያደናቅፍ የስርኣቱ
ባለሥልጣን፣ ዜጋም ሆነ ግለሰብ፣
በማስረጃ ሲታይና ሲረጋገጥ
ዕርምጃ ለመውሰድ ሕግ ፊት
ለማቅረብ ምንም አይነት የተሰራ
ስራ ካለመኖሩም በላይ በባሰ
መልኩ በይፋ ህጎች ሲደፈጠጡ
እያየን ነው:: ባለሥልጣንም ሆነ
ባለ ሀብት፣ ታዋቂም ይሁን ተራ
ዜጋ፣ ከፈለገው ብሔር ብሔረሰብ
ይምጣ፣ የፈለገውን ሃይማኖት
የሚከተል ይሁን፣ የጾታና የዕድሜ
ልዩነት ሳይኖር ተቃዋሚም ይሁን
ደጋፊ ሁሉም ሕግ ፊት፣ ፍትሕ
ፊት፣ መልካም አስተዳደር ፊት
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
5 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
እኩል መሆኑን አምነን በተግባር
ለማዋል ቁርጠኝነት በፍጹም
የለም::ፍትህ መልካም አስተዳደር
የአገልግሎት አቅርቦት እና ሰላም
ለማግኘት በጃችን ያለውን ነጻነት
ለመቀዳጀት ከትግሉ
ያልተቀላቀላችሁ እንድትቀላቀሉ
ያስፈልጋል።
የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች
ናቸው Wassihun Tegegn
Germany
ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል
ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ
የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት
መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም
ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን
አጭበረብራለሁ እንደማለት
ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት
ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው
በጠበንጃ ሃይል በሚኖሩባት
በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና
የመልካም አስተዳደር ጥያቄ
አሁንም እጅግ መልስ
የሚያሻቸው ጉዳዮች
ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው
እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው
ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ
እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ
የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ
የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት
መሆኑ እሙን ነው::ህዝቦች ህግ
እየጸደ ህግ እየተሽሞነሞነ እና
እየተብለጨለጨ ቢቀመጥ ምንም
የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለ
መታወቅ ያለበት ሲሆ አንድ
ህዝብ ባላረቀቀ ባልተወያየበት እና
ባላጸደቀው ህግ እየተገዛ ፍትህን
እና መልካም አስተዳደርን እንዴት
ማስፈን ይቻላል??? መተማመን
እና የዜግነት ኩራቱን በሚሰብሩ
ባለስልጣናት እየተሰበረበት ያለ
ህዝብ ፍትህን እና አስተዳደራዊ
እንዲሁም አገልግሎቶችን
በተግባል ለማየት እና ለመጨበጥ
አልቻለም:: ለተበደለና ፍትሕ
ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር
አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና
መልካም አስተዳደር እንዲኖር
በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን
ብናወራ ዋጋ የለውም::
ሃገራችንን ሃገር እናድርግ
Bikisegn Haileleul Germany
የኢትዮጵያዊያን ጥቁር ሳምንት
ኣስደንጋጭ ክስተቶች በተከታታይ
የሰማንባቸው ሳምንታት ሚያዚያ
2007 ኣ\ም። በሊቢያ ከሰው
ያልተፈጠረ በሚመስሉ ነፍስ በላ
ኣረመኔዎች ኣይሲስ የተባለ ኣሸባሪ
ቡድን የኢትዮጵያዊያን
ወንድሞቻችንን ኣንገት
ቆርጠዋል። በጥይት ደብድበዋል።
በደቡብ ኣፍሪካ እስከ
ህይወታቸው የተቃጠሉ በድብደባ
ጉዳት የደረሰባቸው እና
ንብረታቸዉን የተዘረፉ እህት
ወንድሞቻችን፣ በየመን በጦርነት
ቀጠና በስደት ላይ ዘረፋ ብዙ
እንግልት ኣየደረሰባቸው የሚገኙ
እና ኣንዲሁ በሊቢያ በኣሸባሪ
ቡድኖች እጅ ውስጥ ያለበቂ እህል
እና ዉሃ ታፍነው እና ተደብቀው
የነበሩ ኢትዮጵያዊያን
በሃገር ቤት ይኸን ክስተት
መቋቋም ኣቅቷቸው ከኣምሮ በላይ
ቢሆንባቸው መንግስት ለዜጎች
የሚሰጠው ክብር ኣዚህ ግባ
የሚባል ኣልሆን ሲላቸው ብሎም
እኔ መንግስታችሁ ነኝ ብሎ ራሱን
ከሚጠራ ኣካል የማይጠበቅ
ሲሆን ዜጋው በራሱ ተነሳሽነት
ስሜቱን ለመግለጽ ኣደባባይ
ሲወጣ የተለመደው እስር፣
ድብደባና ኣፈና ተስፋፍቶ
ቀጥሏል። ይሄ ክስተት
ኢትዮጵያዊ የሆነን ሁሉ ያለምንም
ልዩነት የሚያስደነግጥ፣
የሚያሳዝን የሚያስቆጭ እና ጥያቄ
የሚያስነሳ ነው። ነገር ግን
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና
የሃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉትን
ባለስልጣናት ስሜት ሊሰጣቸው
ኣልቻለም። ሌላው ኣነዚህ ሃገር
እናስተዳድራለን የሚሉ ሃገር
ኣጥፊ ቡድኖች በትእቢት
በማናለብኝነት እና በንቀት
ሰባዊነት የሚጎድለዉን ተራ
ምላሾቻቸው ለዜጎቻቸው
ሰጥተዋል። ይሄ ምላሻቸው
ኣንደወትሮው ዜጋው ዝም ብሎ
የሚያዳምጠው ኣልነበረም።
የህብረተሰቡን ስሜት የጎዳ እና
በራሱ ተነሳሽነት ወደ ኣደባባይ
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
6 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
በመውጣት ቁጣውን፣
ተቃውሞውን ገልጿል።የወያኔ
ባለስልጣናት ኣሁን ከዚህ ድርጊት
ባለመማር እጃቸውን ወደ ሰማያዊ
ፓርቲ ቀስረዋል። ይኸን ኣመጽ
የሚያደራጁት የጥፋት ሃይሎች
ናቸው ይላሉ። በኔ ኣመለካከት
ኣዎ ህብረተሰቡ ወደ ኣደባባይ
ለብሶት የወጣው በጥፋት ሃይሎች
ምልሽ እና ድርጊት ምክንያት
ነው። የጥፋት ሃይሉም እራሱ
ኣገር ኣስተዳድራለሁ የሚለው
የወያኔ ቡድን ነው። ወያኔወች
ለሃገር፣ ለዜጋ፣ የማይጨነቁ
የራሳቸው ኪስ በመሙላት ስራ
ላይ የተጠመዱ ናቸው። ኪሳቸው
ሞልቶ ከህብረተሰቡ ተከሻ ላይ
ለመውረድ እንደሚያስቡ ግልጽ
ኣይደለም። በነገራችን ላይ የነዚህ
የኢትዮጵያዊያን ስደት በዋናነት
በማን በምን ምክንያት ነው?
የኢትዮጵያዊያን በየደረስንበት
በይ\ኣለንበት ቦታ መገደል፣
መቃጠል፣መንገላታት፣መደብደብ
፣መዘረፍ እና መዋረድ
ለምን?እስከመቼ ነው
የሚቀጥለው ? ችኤ ነው
የሚቆመው?በኔ በግሌ
ኣመለካከት ይሄ የሚሆነው
ሃገራችንን ሃገር ስናደርግ፣ ለወገኑ
ለሃገሩ የሚጨነቅ በትእቢት፣
በማናለብኝነት፣ በንቀት ያልተሞሉ
ሃገር ኣስተዳዳሪወች መፈጠር
ሲችሉ ብቻ ነው። ሃገራችን ሃገር
እንድናደርግ ኣስከመቼ በሰው
ሃገር በስደት እንኖራለን? ወንድም
ኣህቶቼ ጊዜው ኣሁን
ነውልዩነታችንን ወደ ጎን
በማድረግ ኣንድ በመሆን
ሃገራችንን ሃገር እናድርግ።
ለኢትዮጵያ ሃገራችን እና
ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ኣምላክ
በቃችሁ ይበለን። ሰላም።
የ 2007 ምርጫ ቢቀርስ
Emebet Teshome Eschenburg, Germany
በኢትዮዽያ ምርጫ ባይኖርስ
በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ
የሀገር ሀብት ና የሰው ሃይል
የባከነበት ምርጫ
ለኢትዮዽያውያን ሞት፣ ስቃይ፣
ስደት የሚመጣ ከሆነ ቢቀርስ?
ከምርጫው ጋር በተያያዘ
በኦሮሚያ ክልል ና በ አማራ ክልል
የምርጫ ታዛቢዮች በመንግስት
ታጣቂውች እየተገደሉ ነው።
የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትም
ዕንዲሁ ዕየታሰሩ ና ዕየተገደሉ
ነው።በየቦታው ታዛቢወች
በሚደርስባቸው ድብደባ ና ወከባ
ቀየ መንደራቸውን ትተው
ዕየተሰደዱ ነው። ዕናም ምርጫው
ቢቀርስ? አወ ዕወነት ነው የህግ
የበላይነት ዕስጊረጋግጥ ና
ዕውነተኛ ዲሞክራሲ በአገራችን
ዕስኪሰፍን ድረስ ምርጫ
በኢትዮዽያ አሁን ባለው ስርአት
በጭራሽ አያስፈልግም። ለምን?
የንጹሀን ደም ለምን በከንቱ
ይፈሳል?
የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻ Mengesha Gebru
Marburg, Germany
ኢትዮጵያ የሶስት ሽ አመት ዘመን
ሀገርነት ተክዶ በብሄር ብሄረሰቦች
ዕስር ቤትነት የተተካበት፣ አማራ
የተሰኘ አንድ ትልቅ ኢትዮዽያዊ
ማህበረሰብ በወራሪነት፣
በጨፍጫፊነት፣ በቅኝ ገዥነት
ተወንጅሎ የጎሳ ብሄረሰቦች
የጥላቻ ማራገፊያ ና የተደራራቢ
ቅጣት ሰለባ የተደረገበት
የኢትዮጵያ አባቶች አኩሪ ታሪክ ና
ገድል በፊውዳል ጉልተኛ ስርአት
የጭቆናና የብዝበዛ ተራኪነት
የተለወጠበት የነጻነት ወዳድነት፣
ጠንካራ በራስ መተማመን ና
ብሄራዊ ስሜት ተመልሶ ሊታደስ
በማችልበት መልኩ ከስሩ ተንቅሎ
ዕንዲጠፋ የተደረገበት የሀገራችን
ምሰሶ የሆነው ባህል፣ ወግ ና
ዕምነታችን ባስነዋሪነት፣
ባአድሃሪነት ና ኋላቀርነት
ተፈርጀው ዕንዲዋረዱ፣ ዕንዲጠፉ
የተዘመተበት። ባጠቃላይ
ኢትዮጵያ ና ኢትዮጵያዊነት
አውዳሚ ብሄርብ ሄረሰብ
ከፋፋይ ህዝቦችን ለስደት፣
ለድህነት የዳረገ መንግስት
ስለዚህም ይህ ትውልድ ለራሱ
ክብር ና ለሀገሩ ክብር ሲል ይህን
አምባገነን መንግስት ተባብሮ
ነቅሎ መጣል ነው።
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
7 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ማስመሰል ይብቃን Molalsh Getnet
Oberusel Germany
ዕኛ ኢትዮዽያውያን ለ24 አመት
በስደት ና በጭቆና ኑረናል። ሰው
በሀገሩ ሰርቶ መኖር ዕየቻለ አገሩን
ትቶ በየብስ በባህሩ ብሎም
ለእስር ና ለሞት ሲሰቃይ
የሚኖረው በጣም ብዙ
ኢትዮዽያዊ ነው። ኢትዮዽያ
ያላት ዲሞክራሲያዊ መንግስት
ነው የሚባለው ከ አፍ ወደ አንገት
የሚያልፍ ነገር ነው። አንድ ሰው
በዲሞክራሲ የሚኖረው ሲባል
ህሳቡን በነጻነት ሲያንጸባርቅ ፣
ሃይማኖት፣ ባህል፣ ደንበር፣ ጎጥ
ሳይወስነው ሲኖር ብቻ ነው።
የወያኔ መንግስት በዘመድ
አዝማድ ተንተርሶ የሚሰራ
ድርጅት ነው። በኢትዮዽያ 2007
ምርጫ የተካሄደው ምርጫ
ሳይሆን ዕርግጫ ነው።
የወገኖቻችን ሞት አብዝቶ
አሳዝኖናል ና በ አደባባይ ማልቀስ
አለብን ብሎ የወጣ ሰላማዊ ህዝብ
ላይ ዱላ የሚሰነዝር አስለቃሽ ጋዝ
የሚረጭ ፖሊስ በተሰማራባት
አገር መኖር ሲሰለቸው ሲሰደድ
ማን ይጠይቀው? ከንግዲህ በኋላ
ግን ማስመሰል ይብቃን። ዕኛ
ኢትዮዽያዊ ለኢ ዲሞክራሲያዊ
የሚመራውን ወያኔን ዕጅ ለዕጅ
ተያይዘን ቀደምቷን
ኢትዮዽያችንን መመለስ አለብን።
በወያኔ ድንክየ የፖለቲካ አስተሳሰብ
ዕስከመቸ? Tilahun Tadese
Borken, German y
ድንክየ አስተሰኣሰብ ግላቸው
የሚመራው ህዋት ኢህ አዴግ
በኢትዮዽያ ህዝብ ላይ ከቀን ወደ
ቀን የሚያደርሰው ግፍ ና መከራ
ልጓም ሊበጅላት ይገባል።
ከሰሞኑ በኢትዮዽያውያን ላይ
በተለያዩ ሀገራት የሚደርስብንን
ስቃይ ና በደል ስናስብ የበደሉ
ዋነኛ መንስኤ የብልሹ አስተዳደር
ውጤት መሆኑ ጸሀይ የሞቀው
ሀቅ ነው። ምክንያቱም ዜጎች በገዛ
ሀገራቸው ላይ ያለምንም አድልወ
በነጻነት የመስራት ና ሀብት
የማፍራት ምኞታቸው በዘመነ
ኢሀዲግ የማይታሰብ ሆኗል።
ይህንንም ብዙወች አደባባይ
ወጥተው ተቃውመዋል። በዚህም
ምክንያት የኢትዮዽያውያ ህዝብ
በዚሁ በተጠላ ስርአት ታስሯል፣
ተገርፏል፣ ተሰዷል፣ ተበድሏል፣
ንብረቱ ተዘርፏል፣ ተፈናቅሏል።
በሌላም በኩል በ በአዋቀሩት
የአፈና ስር አት አማካኝነት
ስራቸውን የሚቃወሙት ሁሉ
ጥቃት ዕየፈጸሙበት ያሉ
መሆኑን ከዚህም የተነሳ ብዙ
ህዝብ ለስደት ዕየተዳረገ መሆኑ
ዕጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
አሁንም በየመን፣ በሳኡዲአረቢያ፣
በደቡብ አፍሪካ ዕንዲሁም
በሊብያ የወገኖቻችን አንገት
ዕንደበግ ዕየተቀላ ወደ ወንዝ
ዕንዲጣል ያደረገው የወያኔ
አስነዋሪ ና አምበገነናዊ የ አገዛዝ
ስልት ነው። ስር አቱም ለዜጎች
ደንታ ዕንደሌለው
የሚያስታውቀው ISIS
በተባለው ሰው በላ የ አረመኔወች
ቡድን የታረዱ ኢትዮዽያዊ
ወገኖቻችን ዕንዲሁም ደግሞ
አንገታቸው ላይ ጎማ ዕየተደረገ
አደባባይ ላይ የተቃጠሉ
ወንድሞቻቸውን ምስል በመያዝ
ድርጊቱን ለመቃወም በወጡ
ንጹሀን ዜጎች ላይ መንግስት
ከጽንፈኛው ቡድን ባልተናነሰ
የከፋ ዕርምጃ ወስዶባቸዋል።
አሁን ያለው የወያኔ ስር አት
ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር ና መከራ
ዕየዳረገው ከመምጣቱም በላይ
ህዝቡ በዚህ አስከፊ ስር አት ላይ
ጥላቻውን በከፍተኛ ሁኔታ ዕያሳየ
ይገኛል።ለዚህም ያለመተባበራችን
ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክቷል። በኛ
ሀገር ሁኔታ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ
የራሳቸውን ና የዘመዶቻቸውን
ሆድ በመንግስት ላይ በሚገኙ
ድንክየ አስተሳሰብ ባላቸው
የፖለቲካ መሪወች ሰበብ በህዝብ
ላይ በዲሞክራሲ ስም
ተቀልዷል፣ተነግዷል፣ ይባስ
ብሎም በሀገሪቱ ላይ ና በህዝብ ላ
ተቅልዶበታል። ስለሆነም የወያኔ
ሹማምንቶች የበላይ ይሚሆኑበት
ዘመን አብቅቶ ኢትዮዽያዊ
አንድነት ዕንዲያብብ ና የህዝብ
የመከራ ዘመን ዕንዲያጥር
የተበታተነውን ና የላላውን ትግል
ይህንን አፋኝ ስራት ለምጣል
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
8 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
በሚስችል መልኩ የተደራጀ
ሀይል በበቂ ሁኔታ አዘጋጅተን
ደካማ የሆነውን የህዝቡን
ዕንቅስቃሴ በማንቃት በሁሉም
የፖለቲካ ድርጅቶች ሆነ መሪወች
በ አንድነት በመቆም ዕስከዛሬ
ድረስ ለውጥ ያላመጣውን
የተናጥል ዕንቅስቃሴ አስወግደን
ህውሀት መራሹ ወያኔን በተባበረ
ክንዳችን ለመጣል ቆርጠን ዕነነሳ።
ድል ለኢትዮዽያ ህዝብ። በግፍ
የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን
ነብስ ይማር።
የወያኔ ጥላቻ ፍሬ Zafu Amare
Hattersheim, Germany
ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ሀብትና
ብልጽግና አመጣ ብለው
የሚያምኑ ሰወች ብዙ ናቸው።
ወያኔ የስልጣን ወንበሩ ላይ
በመውጣቱ ትግሬወች ሁሉ
አልፎላቸዋል። ይታመናል በተለይ
በ አውሮፓ ና በ አሜሪካ የሚኖሩ
ኢትዮዽያውያን በዚህ ላይ
የጠነከረ ዕምነት አላቸው። በዚህ
ጉዳይ ላይ ከኢትዮዽያ ውጭ
ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ
ይደረጋል። በኢትዮዽያ ውስጥ
ግን የተፈራ ርዕስ ነው። ውስጥ
ውስጡን ዕንጅ አደባባይ
ለማውጣት ጊዜው የደረሰ
ይመስለኛል። አረጋዊ ብርሄ፣
ገብረ መድህን አርአያ፣ አሰግድ
ገብረ ስላሴ፣ አብርሀ ደስታ
ዕየደጋገሙ ቢያነሱትም ሌሎች
በቁም ነገር የተቀበሉት
አይምስሉም። ህዝቡ ግን በራሱ
መንገድ ዕየተናገረ ና ምስክርነት
ዕየሰጠ ነው። በመቀሌ
የተሰራውን የመኳንንት መንደር
ህዝቡ ´´አፓርታይድ´´ ብሎ
ሲሰይመው በ አዲስ አባ ባ
የተሰራውን መንደር ´´መቀሌ´´
ብሎ ሲሰይመው ዕየመሰከረ
ነው።
ያለፈውን ስርዓት መናፈቅ
ዮሐንስ ደሳለኝ Frankfurt, Germany
አንዳንዴ የአገራችንን የፖለቲካ፣የማህበራዊና
የኢኮኖሚ አዘዋወር ሳስበው ግርም ይለኛል በተለይ በአሁኑ ግዜ ብዙ ሰዎች ያለፉትን
ስርዓቶችን መመኘት ጀምረዋ። ይህ ለእኔ እንደ አንድ ኢትዬጵያዊ ጤናማ አመለካከት አይመስለኝም፣ ለወያኔ ግን እመራዋለሁ በሚለው ህዝብ ዉስጥ እያስቀመጠ ያለውን ስነ ልቦና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ያለፉት ሁለቱም ስርዓቶች የራሳቸው የሆነ ጥፋትም ልማትም አስተናግደዋል ፣ ከትክክለኛ ግንዛቤና ስሜታዊ ባልሆነ ምልከታ ስናየው ግን ሁለቱም ሥርዓቶች ይሄን ያህል የሚናፈቁ አልነበሩም ግን ሆነ ፣አዎ አንድ ህዝብ ትክክለኛ መስመር አቅጣጫና የማንነቱን ታሪክ
የሚያወሳውና የሚያሳየው ሲያጣ
አማራጭ ባይሆንም ላይመለሱ የሄዱትን መናፈቅ ግድ
ይለዋል። አሁን ነዉ እንግዲህ ጎልያዶቹ መሪዎቻችን ራሳቸዉን ማየት ያለባቸው፥ ይህ ወቅት
ነገሮችን አመላካችና ወያኔም በምን ምክኒያት ነው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሙሉ የህዝብ ይሁንታ ማግኘት ያልቻልኩት ብሎ መጠየቅ ያለበት። ለእኔ እስገሚገባኝ ድረስ የአሁኖቹ መሪዎቻችን ህዝብ ያልተቀበላቸው ምክኒያቶች ዘርፈ ብዙ ቢሆኑም ዋናዉ ግን የወያኔዎቹ ኢትዬጵያ ለምትባለው
አገር ደንታ ቢስነት ነዉ ፣ ኤርትራን ከማስገንጠል የጀመረዉ ሀሳብ ዛሬ በየቦታዉ ተዳርሶ ያች አንድነቷን ለረዥም ግዜ ጠብቃ የቆየች አገር ተመልሳ አፄ ቴዎድሮስ ከመንገሳቸው በፊት
ወደነበረዉ ዘመነ መሳፍንታዊ አገዛዝ ወስጥ የተዘፈቀችዉ፡ የአማራው ገዠ ነኝ የሚለው የሚያስተዳድረውን አማራን ይሳደባል የኦሮሚያ አስተዳደር የኦሮሞ ወጣቶች ፍትሃዊ የሆነ የመሬት ክፍፍል ይኑር ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር
ይስፈን ብለው በጠየቁ
የአስተዳደሩ መልስ የጥይት አረር ሆነ ፧ የትግራይ ልጆች በስማቸው ሲነገድ የበይ ተመልካች ሆነው ከሌላው ወንድሞቻቸው ለማጣላት ሴራ ሲጠነሰስባቸው አቅም አጥተው ተቀምጠዋል።ታዲያ ይህ ሕዝብ ተገነባ የተባለው መንገድ፡ ተዘረጋ የተባለው የባቡር መስመር ፡በህንጻ ሜካፕ የተዥጎረጎረችው አሮጊቷ አዲስ አበባ ልቡ ውስጥእንዴት ይግቡና ይዋጥለት። ተወደደም ተጠላም እኛ ኢትዬጵያዊያን ስናድግ በተረት ፡ በታሪክ ትምህርት
አሊያም በተለያየ ጊዜና ሰዓት የአገራችንን ታላቅነት ፡የአፍሪካ
ህዝብ ነፃነት ተምሳሌትነትና አንድነቷን ጠብቃ የቆየች መሆኗ ተነግሮናል አምነንም በውስጣችን
አትመነዋል እንጅ እንደ አሁኑ ገዥዎቻችን የተለየ የምድጃ ዳር ወግ ወይም ተረት አልሰማንም ፣
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
9 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ለነገሩ እነሱም ከእኛ የተለየ አልሰሙም ነበር የምዕራባዊያን
ብርና ብልጭልጭ ስጦታ በለጠና ተተራምሰው ዙሪያዋን የተቀደደች አገር አበጁልን እንጅ።
ይህ አልበቃ ብሏቸው ዛሬ በእነሱ ግዜ የተፈጠሩት ብላቴናዎች መጻፍ ሲጀምሩና ደባቸውን ሲያጋልጡ ጎልያዶቹ ወያኔዎች ባዶነታቸው በገሃድ ወጣና እንደ አንድ ዜጋ እንጻፍ እንናገር ፡ ዜጎች ቢያንስ የመናገር የማሰብ ነፃነታቸው ይከበር ባሉ ለመስማትም ለመናገርም የሚቀፍ ስቃይና እንግልት እያደረሱባቸው የሚገኙትና በአገሪቷም ላይ የማይረሳ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ እንዲያልፍ የተፈለገው ። ስለዚህ ውድ መሪዎቻችን እስቲ ረጋ በሉ አትዋከቡ የጦር መሳሪያ እንደሆነ ደርግም ይዞት ነበረ አልጠቀመውም እናንተው ራሳችሁ ነጥቃችሁ አብሮ የታገለውን ወገናችሁን ወጋችሁት ። ግን ግን ስታስቡት ይህ የጦር መሳሪያ አገዛዝ ነገ እንደሚያከትምለት ታሪክ አያስተምራችሁም ፤ እርግጠኛ ነኝ ናፖሊዮን ቦናፖርትን ፡አዶልፍ ሂትለርን ፧ የቅርብ ግዜ ሳዳም ሁሴንን፡ ወንድም ጋዳፊን ታውቃላችሁ ብየ እገምታለሁ ፡ወይም ደግሞ ወዳጃችን የአክራሪዎችን ሴራ ድባቅ የመታ ያሉትን ሁስኒ ሙባረክን ስትሬቸር ላይ ሆኖ ፍርዱን ሲከታተል አድናቂዎቹ ምዕራባዊያን ከነመፈጠሩም እንደረሱት። የአሜሪካፕሬዚዳንት እናንተን ለመጐብኘት መምጣት (መቼም ህዝቡን ለመጐብኘት እንዳልመጡ እርግጠኛ ነኝ።) ዴሞክራት መሆናችንን አሳይቷል ብላችሁ ከሆነ አትሸወዱ ግዜው ሲደርስና የአንድነት የዴሞክራሲና የነፃነት ታጋዮች ሲመጡ ከምንም አያስጥሏችሁም ፣ የመንጌ አትመጣም ወይ ፣መንግስት
የሌለው እዚህ ብቻ ነው ፣የውስጥ አንበሳ የውጭ ሬሳና የመሳሰሉትን የህዝብ ብሶቶች ቆም ብላችሁ እያደመጣችሁና ድንጋይ ክመራውን ትታችሁ ቅድሚያ ለሰው ልጅ ደህንነት ስሩ አገር ን መውደድን ተማሩ ፡ በተለይ ደግሞ የያገባኛልና የተጠያቂነት ልምድ አዳብሩ ። የ 1 ለ 5 ፍልስፍና እንደሆነ በአሁኑ ዘመን አይሰራም ሰሜን ኮሪያ ዓይነት አገር መመስረት ፈልጋች ከሆነ ያ ግዜ አልፏል እንደ ኬምልሱንግ ሁሌ ይዘመርለታል ብላችሁ የጠበቃችሁት ሟቹ መሪያችሁን ነበረኝ ካለው ራዕዮ ጋር ህዝቡ ቀብሮት ከስድብና ከዘለፋ እፉይ ብሏል ፡ይባስ ብሎ « አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ » ዜማን ተቀኘ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ህዝቡ ጭንቀቱን ፧ብሶቱን ፧አማራጭ ማጣቱን በግልጽ ነገራችሁ ። የመንጌ አትመጣምን ዜማ በንቀት አትመልከቱት ልብ ያለው ልብ ይበል ውድቀት የሚጀምረው እመራዋለሁ የሚሉትን ህዝብ ሲንቁና ሲጠየፉ ነው ።
የሕወሓት ማፊያ ቡድን ከምድረገጽ መጥፋት
አለበት Mulugeta Teka
Dreieich, Germany
የሕወሓት ማፊያ ቡድን ወራዳ
ነው:: ኢትዮጵያ የምትባል አገር
እንዳትኖር የሚመኝ ይህ አሸባሪ
ድርጅት ለማንም አይበጅም::
ብናወራለት ተተካኩ ተባሉ
ተፋቀሩ ብንልለት ምንም
አይበጅም::የሚበጀን ነገር ቢኖር
ትግሉን በአራቱም አቅጣኛ
በማጠናከር ሕዝቦችን
በማስተባበር በመቀስቀስ እና
በማደራጀት ይህንን ከይሲ
የማፊያ ቡድን ማስወገድ ብቻ
ነው:: እስኪ ራሳችን እንጠይቅ?
ስንቶቻችን ነን ለራሳችን አላማ
እና ግብ ጠላቶች የሆንን?በወሬ
ናዳ እያሽካለልን ትግሉን
የጎተትን?እርስ በራሳችን በተራ
የመንደር ወሬ ተቧድነን
የምንወነጃጀል? ከትግል ይልቅ
በሃሜት እና በፍረጃ ላይ
በፕሮፓጋንዳ ላይ የተተከልን
ስንቶቻችን ነን? ከዚህ አይነቱ
ጋሬጣ ራሳችንን አላቀን ሕዝብን
አስተባብረን የሕወሓትን ጉጅሌ
አገዛዝ በተገኘው መንገድ ሁሉ
በጋራ እና በአንድነት ሆነን
መደምሰስ አለብን ::
አይደለንም::ደግሜ እናገራለሁ
ጠላቶቻችንን የምናንበረክክበት
እና በሚገባቸው ቋንቋ
የምናናግርበት ጊዜ ላይ ነን::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
መሪ አልባ አገር Sara Mesfin
Viernheim, Germany
ኢትዮጵያ ዛሬ የምትተዳደረዉ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይስ
በአረመኔዉ የመለስ ዜናዊ ሙት
መንፈስ? ብዙዎች የሚስማሙበት
ግን ራሱን የትግሬ ነፃ አዉጪ ነኝ
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
10 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ብሎ በሚጠራዉ የዘረኞችና
የነፍሰገዳዮች ገዢ ቡድን መሆኑን
ነው።በእርግጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ
ራሱን እያስተዳደረ እንዳልሆነ
እናዉቃለን። ማንም በዚህ መልኩ
ራሱን እያታለለ
አይገኝም።የኢትዮጵያ ሕዝብ
ራሱን ማስተዳደር ጀምሯል
የሚባለዉ ሃቀኛ ተወካዮችን
መርጦ በእንደራሴና በአደራ
መልክ በአመራሩ መንበር ላይ
ሲያስቀምጥ ብቻ ነዉ። እስከአሁን
ደግሞ ይህ ስላልሆነ በሥልጣን
ላይ ያለዉ የትግሬ ነፃ አዉጪ
ቡድን በዉስጥና በዉጭ ፀረ
ኢትዮጵያ ሃይሎች እየተረዳ
በጉልበት የገባና በጠመንጃ የሚገዛ
ኃይል ነዉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ
የሚጨነቀዉ በኢትዮጵያ
የመንግሥት ምስረታ ላይ ነዉ።
የሌሎቹ ጭንቀት ግን
ስለተፅእኖአቸዉ ያስቀመጡት
አሻንጉሊት አገዛዝ መመሪያቸዉን
ከማክበሩ ላይ ነዉ። ይህ
መሠረታዊ አላማና የእምነት
ልዩነት በመካከላችን አለ። ሌላዉ
የሚገርመዉ በሥልጣን ወንበር
ላይ የሚገኘዉ ኃይል ሕልሙና
አላማዉ ስልጣን እንጂ የሕዝብ
ሰላም ስላልሆነ ዛሬም
እንደትናንቱ ከተቃዋሚ ኃይሎች
ጋር አይን ለአይን ለመተያየት
አለመቻሉ ነዉ። በሌላ አገር
ቢሆን ዲሞክራሲ በዚህ የፓለቲካ
ይዘትና ሥርአት ዉስጥ በስም
እንኳ ባልተጠቀሰ ነበር።
ዲሞክራሲ እርስ በርስ መፈራራት
ባልሆነ ነበር። ኢትዮጵያዉያን
ተገናኝተዉ ተወያይተዉና በሃሳብ
ተፋጭተዉ ከአንድ ስምምነት ላይ
ለመድረስ አለመቻል በበለጠ
ሁኔታ ጠላትን ከመጥቀሙ ባሻገር
ታላላቅ መንግሥታቱ በአገሪቱ
ሉአላዊነት ዉስጥ እንዲፈተፍቱ
ማድረጉ ግልፅ ሆኗል። ሥልጣን
የያዙትም ሆነ ተቃዋሚ ሃይሎች
በነፃ ኢትዮጵያዊነት ኩራትና
መንፈስ “በኢትዮጵያ ጉዳይ
የሚያገባን እኛ ብቻ ነን የሌሎችን
አቋም አዉቀናል ስለዚህ የዉጭ
ኃይሎች እጃቸዉን ይሰብስቡ”
ከሚባልበት ደረጃ መድረሳቸዉን
በተረዱ ነበር። የዓላማና የአቋም
ልዩነት መኖሩ የዉጭ ዳኛና
ተቆጭ እንድንሾም አስገድዶናል።
የኢትዮጵያን የዘወትር ተጋድሎ
ጌታ ለመለዋወጥ አልነበረም።
“ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዉያን”
መፈክር በተግባር መተርጎም
ነበረበት። ለኢትዮጵያ ነፃነትና
ሕልዉና የታገሉና የዉደቁ
ልጆችዋ ለአንድ አፍታ ቀና ብለዉ
አገሪቱ ልምድም እዉቀትም
የኢትዮጵያዊነት እምነትም
የሌላቸዉ ጎጠኞች የተንሰራፉባት
መሆኑን ከተረዱ አፅማቸዉ
መቃብራቸዉ ዉስጥ ምንኛ
በተንቀጠቀጠ ነበር ያሰኛል?!
ኑሮ ተወደደ Habetamu Gabermaram
Germany
በእናት ኣገራችን ኢትዮጵያ
ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ የኑሮ
መወደድ ነው። ኣምባገነኑ
የኢትዮጵያ መሪ የኢሃዴግ
መንግስት ስልጣን ላይ ከሰፈረ
ጀምሮ የኑሮ ውድነት ኣየናረ
እንጅ እየቀነሰ ኣይታይም። የዚህ
ችግር ምንጭ የጠንካራው ኣርሶ
ኣደር ገበሬ መሬት በግፍ መነጠቅ
ነው። ከዚያም ገበሬው ያለ ስራ
መቀመጥ ወይም ከቤት ንብረቱ
ከቀየው ያለ ፍላጎቱ በመፈናቀል
ሳይወድ በግድ ወደ ከተማ
በመፍለስ ወደ ምጽዋእት(ልመና)
ስራ ላይ ይሰማራል። <<ለምን
ሰርተህ ኣትበላም ጉልበት
ኣለህ>>በማንልበት ጊዜ መሬቱን
የኢሃዴግ መንግስት ነጥቆኝ ምን
ሰርቼ ልበላ ነው የሚለን
ይታያችሁ። ጉልበት ጤና እያለው
የሃገራችን ህዝብ በልመና
ሲተዳደር በጣም ያሳዝናል ኣርሶ
ኣደሩ ገበሬው ነበር እኮ
የከተማውን ሰው ሆዱ ሞላ ዛሬ
ለሃዱ ሲል እነዚያን ሞፈር ቀንበር
የጨበጠበት እጁን ለልመና
ዘረጋቸው። የከተማን ኑሮ ያላየ
ሁሉም ልስራ በማለት ወደ ከተማ
ይገባል። የስራ እጦት ልመና ላይ
ይጥላል። ወገኔ እስከመቼ ይሆን
የገዥው መንግስት ግፍና ጭካኔ
የሚቀጥለው ። ኑሮ ተወደደ
ከማለት ይልቅ ኑሮ የተወደደበትን
ምክንያት በጋራ በኣንድነት
ታግለን እናጥፋና ገበሬውም
በታየው ኣርሶ የሚተዳደር
ለከተማውም የሚተርፍ እንዲሆን
በኣንድነት እንታገል።
እግዚኣብሄር ሃገራችንን ይባርክ።
ኣሜን።
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
11 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
መሪ የሌለው ህዝብ Rute meleak
Rüsselsheim, Germany
የኢትዮጵያ ህዝብ የተፈጥሮ
እድሉ ሆኖ በህዝብ የተመረጠ
የህዝብ መብት የማያከብሩ
መሪዎች ማግኘት ኣልቻለም።
የተለያዩ መሪዎች እየተፈራረቁ
ሃገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል።
እስካሁን ድረስ ያለው የመንግስት
ስልጣን በጦርነት እና በመሳሪያ
ያሸንፋሉ። ሃይል የሃገሪቱን
የመሪነቱን ስልጣን እየያዘ
ቀጥሏል። ገዥው ወያኔ በመሳሪያ
ሃይል ወደ ስልጣን ከመጣ ሃያ
ኣራት ኣመታት ያስቆጠረ ሲሆን
እነዚህ ጊዜያት ለኢትዮጵያ ህዝብ
የመከራና የሰቆቃ ኣመታት ነበሩ።
ወያኔ በሚከተለው የብሄር
ፖለቲካ ምክንያት ለብዙ ኣመታት
በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ ሲኖር
የነበረውን ህዝብ በጎሳና በብሄር
እንዲከፋፈልና ኣንዱ ብሄር
ከሌላው ብሄር ጋር በጥላቻ
እንዲተያይ እያደረጉት ይገኛል።
ከምርጫ 1997 በሁዋላ
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ወደ
መቃብር የወረደ ሲሆን መንግስት
በተቃዋሚ ፖለቲካ በደረሰበት
ሽንፈት የተለያዩ የዴሞክራሲ
ስራቱን የሚያቀጭጩ ኣፋኝ ህጎች
በማውጣትና ጠንካራ የፖለቲካ
ፓርቲዎች በማዳከምና በማፍረስ
የሃገሪቱን የዴሞክራሲ ስር ኣት
የቁልቁለት እንዲጓዝ ኣድርጓል።
የወያኔ መንግስት በኣሁኑ ወቅት
ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣
ጋዜጠኞችን፣ጦማሪያን፣
የተቃዋሚ ኣባላትንና የሞስሊም
መፍትሄ ኣፈላላጊ ኮሚቴዎችን
ስለ ሃገራቸው ጉዳይ ያገባናል
ስላሉና ፍትህ ስለጠየቁ በገዥው
ፓርቲ የሃሰት ክስ ተከሰው በእስር
እየማቀቁ ይገኛሉ። ኣንዳንዶችም
በገዥው ፓርቲ በሚደርስባቸው
ጫና እስራትና ማስፈራሪያ
ሃገሪቱን ጥለው ለመሰደድ
በቅተዋል።
በዘንድሮ ምርጫ ከምርጫው
በፊት ኣስቀድሞ ገዥው እንዳሸነፈ
የምርጫው ዉጤት የታወቀ
ሲሆን ገዥው ፓርቲ የይስሙላ
ምርጫ በማካሄድና የህዝብን
ድምጽ በመስረቅ መቶ ፐርሰንት
ኣሸነፍኩኝ በማለት የኣለም
ህዝብን በማስገረም ላይ ይገኛል።
በምርጫው ውጤት ኣምባገነን
መሆናቸውንና ለተቃዋሚ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳብ ቦታ
የሌላቸው መሆኑን
ኣረጋግጠዋል። ገዥው መንግስት
ምርጫ የሚያካሂደው ሌሎች
መንግስታትን ዲሞክራሲያዊ
መንግስት ሆኖ ለመታየት ኣንጅ
ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ኣስቦ
ኣይደለም።
በሃገራቸው መብታቸው የተገፋ
ህዝቦች መብታቸዉን ለማስከበር
እና ነጻነታችውን ለማስመለስና
ሃገሪቱን ካለችበት ውድቀት
ለመታደግ ሃገር ውስጥም ሆነ
በውጭ የሚካሄደው ትግል እስከ
ነጻነት ድረስ ተጠናክሮ
እንዲቀጥል እጠይቃለሁ። ድል
ለኢትዮጵያ ህዝብ።
የነጻነት ተስፋ Soliyana kindie
Frankfurt, Germany
የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን
በትግሉ እንዲቀዳጅ በህብረት
ለመታገል ሁላችንም የኢትዮጵያ
ልጆች በያለንበት እንደራጅ።
ይህንንም ለማለት ያስቻለኝ
ዋናው ጉዳይ ዘረኛውና ኣፋኙ
ህወሃት መራሹ በኢትዮጵያ ህዝብ
ላይ በርካታ ዘግናኝ ወንጀልና ደባ
እየፈጸመ ይገኛል።
ዘረኛው የወያኔ መንግስት
ህዝቦችን ከቀያቸው ከቤት
ንብረታቸው እያፈናቀለ በኦሮሞ
ህዝቦችና በኣማራው ብሄረሰብ
ንብረት እየወረሰ ልግል ባለሃብት
እያደለ ልጆቻቸው ጥሩ
የትምህርት እድል ኣግኝተው
የወደፊት እጣ ፈንታቸውን
በመልካሙ እንዲያዩ ራእያቸው
ድቅድቅ ጨለማ ተላብሷል።
እናት ኣገር ኢትዮጵያ ፍትህ፣
እኩልነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ
የሚጠይቁትን ጦማሪያን
ጋዜጠኞች ዘብጥያ በማጎር
የሃይማኖት እኩልነትን
በሚጠይቁት ሞስሊም
ወንድሞቻችን ላይም ይህ ነው
የማይባል ግፍና በደል እያደረሰ
የከፋ መከራ ገፈቱንም እየወሰደ
ይገኛል። እምቢ ኣሻፈረኝ
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
12 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
የተወለድኩበት ሃገር ነጻነት፣
ኣኩልነት፣ ፍትህ ኣልባ በመሆኑ
ተምሬ ሃገሬንና ወገኔን ቤተሰቤን
ለመርዳት የማልችልበት ደረጃ
ስለደረሰ ወጣቱ ወደ ሰው ሃገር
ስደትን መርጦ በሊቢያ በረሃ
ኣንገቱ በኣክራሪ ሞስሊም
ጽንፈኞች እየተቀላ
በሜዲትራኒያን ባህር ኣየሰጠመ
ሴቶች እህቶቻችን በየኣረብ ኣገሩ
እራሳቸውን ከፎቅ በመጣል
ወይም ህይወታቸውን በራሳቸው
በማጥፋት እንደ ኣማራጭ
ኣድርገው ይዘውታል። ይህ ሁሉ
ይህን ሁሉ ሰቆቃና ግፍ ያመጣው
የወያኔ የግፍ ኣገዛዝ ነው። እናት
ኣገር ኢትዮጵያ የፋሽሽት
ኣምባገነናዊ ወንጀል ሳቢያ
ክብሯን ነጻነቷን ሰብ ኣዊ
መብቷን ኣጥታ መብት፣ ክብር፣
ነጻነት ኣጥተው በወያኔ ፍርፋሪ
ሆዳቸዉ ባበጠው ካድሪዎች
እየተረገጡና እየተገረፉ የሰቆቃ
ህይወታቸውን በቃሊቲ ወህኒ
ቤት እየኖሩ ይገኛሉ።
ባጭሩ ከላይ እንደዘረዘርኩት
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው
ግፍና በደል ሳያበቃ የወያኔ
መራሹ መንግስት በ 2007 ኣ\ም
የመንግስት ምርጫ
በዴሞክራሲያዊ ምርጫ መቶ
በመቶ ኣሸንፊያለሁ በማለት
ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሆኖ
ቀርቦልናል። ቁርጠኛ የህዝብ ልጅ
የሆነውንም ግንቦት ሰባት ዋና
ጸሃፊ ኣንዳርጋቸው ጽጌ
በሽብርተኝነት ፈርጆ እያለ የወያኔ
መንግስት የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ቴዎድሮስ ኣድሃኖም
እስረናውን ኣንዳርጋቸው ጽጌን
በጥሩ ሁኔታ እንደተያዘና ፍጹም
የሆነ ዴሞክራሲ የሰፈነባት
ኢትዮጵያ ኣድገው
ኣቅርበውልናል።ቆንጆ የውሸት
ድራማ ሰሚ ቢያገኝ። ውድ
ወገኖቼ በኢትዮጵያ
ዴሞክራሲያዊ የሆነ በህዝብ
የተመረጠ መንግስት ለመመስረት
የዘር፣ የሃይማኖት ልዩነት
ሳይኖረን በጋራ የተባበረ
ድምጻችንን ለኣለም ኣቀፍ
ህብረተሰብ በማሳወቅ ለኣንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ የህወሃትን
ኣፓርታይድ ለማስወገድ
በቁርጠኝነት እንታገል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን፣
ክብሩን ለመጎናጸፍ ከወጣት
ኣርበኞች ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን ጋር ወደ ጦር
ኣውድማ ሜዳ በመቀላቀል
ኢትዮጵያዊ ግዴታችንን በትጥቅ
ትግል እንተርጉም። ድል ለሰፊው
ህዝብ።
ኢትዮጵያን እግዚኣብሄር ይጠብቅ።
Ethiopia is Stuck Samuel Petros
Alsbach, Germany
In 180 degree turn around
from ist previous
laudatory positions, the
economist concluded a
highly critical article as
follows- <<endless red
tape and restrictions on
finance deter
investors…only further
reforms can sustain the
goals of economic growth
and political
stability…(but) Ethiopia
is stuck.>>
Reform versus deadlock:
That is the heart of the
economic problem. First
in the dock is the EPRDF.
It has turned the entire
state and its components
in to a satellite. Front and
state have merged. Civil
servants who are are not
party members are few
and far between. As a
result the agenda of the
front and its hierarchy
takes precedence over that
of the state, party
obedience hinders the free
exercise of professional
competence. The
complaints about this
issue are constant. Yet the
smarter public
management required by
a more advanced
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
13 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
economy demands that
administrative managers
should have freedom in
their analyses and
proposals. In the private
sector, the obligation to
meeting the government.
The youth of
Ethiopia
Mulatua Ayehu Fanta Aschaffenburg,
Germany
A great deal has been said
about the youth of
Ethiopia being the
countr,s next generation
of leaders in the Ethiopian
political scene, however,
the youth are mainly
sought not as leaders but
rather as side kickers to
the establishment.
One of the most tasks of
families, the society and
the government is to
educate and empower the
youth but do these entities
genuinely dialogue and
have a common
understanding on this
mission? Are they
committed to transform
the youth from meek
followers to leaders? Not
by a long shot! They do
not go much beyond
engaging in empty
rhetoric. Being committed
to enable the youth
requires ensuring that
they participate directly in
the political economic and
social affairs of their
country. if one were to
ask what meaningful steps
have been taken to
enhance the youth,s
capacity and bring them
to leadership positions,
the sad answer is
practically nothing. This
obviously does not bode
well for the country.
The youth in Ethiopia are
surrounded by a raft of
problems. The number of
establishments where they
do both mild and hard
drugs, imbibe alcohol and
resort other vices close to
dwellings schools and the
work place is mush
rooming by the day. a
sizable proportion of
young graduates who
have joined the work
force barely make it day
to day owing to the
inadequate salary they
draw. Uneven greater
number is unemployed
and a burden to their
families. Unless a
comprehensive policy is
formulated to extricate the
youth from such multi-
faceted challenges and
prepare them to take over
the leadership of their
country, the ensuring
consequences will very
much be dire.
Are political parties
making tangible efforts to
enable the youth beyond
recruiting them to swell
their membership and use
them as slogan material?
Have they ever made a
conscious decision to
abandon the common
practice of employing the
use to do legwork and
elevate them to positions
of responsibility? Do they
adequately steep youth in
their ideology and coach
them on leadership or do
they imbue them with the
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
14 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
politics of intolerance as
they inclined to? Do they
embrance or shun
youngsters who are
critical thinkers self-
starters and display
leadership quality? All
political parties Ethiopia
including the ruling
Ethiopian peoples
revolutionary democratic
front (EPRDF) are guilty
of not giving the due
attention the youth
deserve.
Ethnic politics is
an existential
threat to all
Ethiopians
Desalegne Abebew & Yalemwork Meswaet Schöneck, Germany
It is not an accident that
after almost 25 years of
hate mongering you now
have a generation of
Ethiopians who are as
alien to each other as they
are to foreigners. Without
a forward looking
national forgiveness and
reconciliation strategy and
a shared history built on
interaction and common
experience, ethnic groups
are wider apart today than
before, and as a result, the
very fabric of the nation is
withering away. You
can’t cultivate suspicion
and hate at the primary
and secondary school
levels and suddenly
expect harmony to swell
at the university level.
Moreover, you can’t
aspire to achieve peace,
stability, and sustainable
economic progress in
such a poisonous
environment. No amount
of “renaissance” or
“growth and
transformation plan”
would get you there. Any
progress made in such a
divisive environment can
only be fleeting. First you
need to shrink the
yawning and ever-
expanding gap among
ethnic groups. In fact, if
not corrected quickly, the
divide and discord will
eventually lead to assured
conflict and
disintegration. Ethiopians
need to heed Obama’s
July 26th message to
Kenyans – “that a politics
that is solely based on
tribe and ethnicity is a
politics that’s doomed to
tear a country apart. It is
a failure – a failure of
imagination.”
How is it possible to hold
an election in a diverse
and huge country such as
Ethiopia and come out
winning 100 percent?
This defies elementary
logic, decency, and self-
respect. You can’t have it
both ways. You either
declare no elections and
rule by fiat or conduct
elections and accept the
verdict of the people (no
contradiction in both
instances).
One needs to also
remember that the TPLF
and its lackeys, after
nearly 25 years of
unaccountable leadership,
have amassed
considerable wealth and
influence that they want
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
15 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
to protect. But in an
environment of ethnic
disharmony, ethnic
favoritism
(discrimination), growing
income inequality and
poverty, and lack of
freedom and liberty,
sustaining the status quo
is increasingly becoming
difficult. Such is the state
of the TPLF today that
something has to change;
otherwise the cancer of
ethnic politics could have
a Frankenstein ending,
consuming its very
creator, the TPLF.
Ethiopia is where it is
now after sustained
propaganda, misguided
decisions and actions
made by those in power
for nearly the past 25
years. It will take time,
effort and resources to
reverse the damage
already inflicted.
It is this generation’s
historic calling to devise a
more promising and
brighter future based on
love and respect for each
other and individual
freedom and liberty for
all.
The Future is indeed in
our collective hands!
God Bless Ethiopia and
Ethiopians!
What shall we do?
Hailu Kassa (Niedernhausen,
Germany)
Democracy is first
originated from God that
no one else has the right
to give and to take. It is
just naturally gifted from
God. But human beings
limited this right from
exercise. That is what we
see every day in many
African Countries
especially east Africa
particularly Ethiopia.The
current government of
Ethiopia has been on
power since May 1991
throwned after civil war
with the former regime
Mengistu Hailemariam
(Derg). The EPRDF first
started this war fooling
the Ethiopian People that
it brings democracy and
freedom but it was
andisironic.Rather this
regime is killing the
Ethiopian people
especially youth mentally,
physically, and spiritually
through the name of
Pseudo-Democracy
running a strategy of
cheating the International
Communities as if there is
democracy and freedom
in the country but the
truth is does not care
locally for its people. That
is what the Europeans and
American do not know.
What shall we do!!!
Every Five year there is
the so called election
organized in Ethiopia but
itisandhasneverbeenfreean
d fair.Againitis a
systemtocheatthe western
nation as if there is
democratically elected
government but the truth
is not never has been. At
first the election board is
supposed to be neutral but
internally it is set up by
EPRDF and its stuff
members. They are all
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
16 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
hidden supporters of the
current government. It is a
fact that no strong
opposition political
parties in the country
because of the different
systematic attack by the
government in different
times many of them left
the country and some
others are in Jail. There is
also limited air time of
electronic media for
opposition political
parties. Much of it used
by the government for its
propaganda. Every civil
servants are forced to
elect EPRDF directly and
indirectly.The Ethiopian
people are desperate on
election because they
always know beforehand
how in the election. The
people do not have trust
on the government but in
timidated to participate in
this foolish election. Over
all there is no and has
never been free and fair
election in Ethiopia.
What shall we do!!!
Medias are all
monopolized by the
government. There are
some private printmedi as
but they are always under
the pressure of this
government. Most of the
private media institutions
are attacked by the
government, the flow of
Journalists out of Ethiopia
is increasing from time to
time. A number of
Journalists and bloggers
are now found in jail. If a
Journalist and Media
organization witness the
truth on the government
poor quality and they are
claimed as Terrorist.
EPRDF always dislike
criticism. So if its own
people do not witness the
truth, whoelsewitness.
What shall we do!!!
Every year in Ethiopia
more than hundred
thousand students
getgraduated in different
Universities and colleges.
Basically the Ethiopian
education policy always
focuses on quantity than
quality. Even if these
number of students get
graduated, there is no job
opportunities in the
country and because of
this most of these
graduates remain addicted
to alcohol and drugs
finally insulted by the
government as loiter.
What else choice the
young and vibrant
generations would have?
What shall we do!!! To
be continued............
Weyane (TPLF)
und die
Verfassung
Rodas Tesfaye Langen(Hessen),
Germany
Mit der Spaltung von
Stämmen gelingt Weyane
(TPLF) die Menschen in
einem Land gegenseitig
zum Kampf zu bringen.
Die Spaltung hatte bei
den bisherigen
äthiopischen Geschichten
nie gegeben.
TPLF gibt den Menschen
neue Identitäten, wo nur
eine Volksgrupp die
Führungsposition
übernommen hat und
über die anderen herrscht.
Die Aufteilung der
Ethenien welches Weyane
erfunden hat, ist auf dem
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
17 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
weg das Land in eine
großen Absturz zu
geraten. Selbst an die
Verfassung das TPLF
nach seinem Geschmack
für sich geschrieben hat
kann sich noch nicht mal
daran halten.
Hier sind einige
Paragraphen der
Verfassung an denen sich
TPLF nicht einhalten
könnte
[11/07 00:53] Netsi:
1)Paragraph 5 über
Sprachen
5.1. Die sämtlichen
Sprachen in Äthiopien
genießen gleichwertige
Anerkennung seitens der
Staates
5.2.Amharisch ist die
Arbeitssprach der
Bundesregierung
5.3. Die föderal
Bundesländer dürfen
deren eigenen
Arbeitssprache mit der
Rechtsordnung.
Schauen wir uns mal
Paragraph 5.1.und 5.3.
genauer an.
5.1. " Die sämtlichen
Sprachen in Äthiopien
genießen gleichwertige
Anerkennung seitens der
Staates"Diese Aussage ist
von der Wahrheit weit
entfernt.Eine Volksgruppe
nutzt sogar die Sprache
dazu aus, um die
restlichen Stämmen
einzuschüchtern. Die
Menschen, die diese
Volksgruppe angehören,
sind die höchsten
Offiziere des Landes und
haben Vorrang in der
Gesellschaft.
[11/07 00:54] Netsi: 5.3.
"Die föderal
Bundesländer dürfen
deren eigenen
Arbeitssprache selbst
bestimmen".
Hierdurch würden die
Bürger blockiert, sich von
Ort zu Ort in ihren
eigenen Mutterland zu
bewegen, weil die
einzelnen Bundesländern
nochmal selbstständig
Arbeitssprache bestimmt
haben obwohl amharisch
die Amtssprache des
ganzen Landes ist. Man
ist z.B nicht in der Lage
ein Hotelzimmer
außerhalb seine Regions
zu buchen oder
medizinische
Versorgungen zu
bekommen weil man sich
mit den Leuten dort nicht
verständigen kann.
Paragraph 10.
Demokratische und
Menschenrechte
10.1. Die würde des
Menschns ist unantastbar
10.2. Bürger,
Menschenrechte und
demokratischerechte
werden eingehalten.
[11/07 00:54] Netsi:
Wenn wir uns die Punkte
10.1 und 10.2
Betrachten, sehen wir
was wicklich Weyane aus
der Verfassung daraus
macht.
Trotz dass man diese
Rechte von Geburt an
hat, werden viele
Menschen gequält und
sogar ermordet.
Äthiopien hat mehrmals
weltliche Verträge
unterschrieben. Unter
diesem befindet sich das
Grundgesetz.
TPLF missachtet diese
weltweite Gesetze und
lässt die Menschen
darunter leiden. Obwohl
Weyane auch mehrmals
Warnungen von anderen
Länder und Amnesty
International bekommen
hat, ignorierte die
diktatorische Partei
TPLF.
Paragraph 11. Trennung
zwischen Religion und
Staat
11.1. Regierung und
Religion sind getrennt
11.2. Es gibt keine
staatlichen Religion
11.3. Die Staat mischt
sich nicht in religiöse
Angelegenheiten ein.
[11/07 00:55] Netsi:
Äthiopien hat eine große
Tradition von
respektvollen Umgang
miteinander
gehabt.Seitdem aber
Weyane die
Führungsposition
übernommen hat, haben
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
18 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
die Menschen das
gegenseitiges Tolerierung
verloren. Die Staat mischt
sich in religiöse
Angelegenheiten ein,
richtet die Leute, die im
Bereich des Religions
arbeiten nach TPLF
Willen alles zu tun.
Wer dagegen etwas
unternimmt wird von der
diktatorischen
Bundesregierung
verhaftet oder ermordet,
denn bei denen spielt die
Freiheit eines Religions
keiner Rolle.
Paragraph 12.
Arbeitsleistung und
Verantwortung der
Bundesregierung
12.1. Die Menschen
wissen was die Staat tut
[11/07 00:55]
Netsi: 12
.2. Eine der durch eine
Wahl gewählte Beamte
wird wieder abgewählt
wenn die Menschen das
Vertrauen verlieren, dass
er seine Verantwortung
nicht übernehmen kann
sagt die Verfassung. Die
Offizier, die von der
diktatorischen Partei
TPLF eingesetzt wurden,
lagern Geld für sich
welches der Menschen
des Landes gehört und
werden auch nicht
angeklagt. Im Gegensatz
werden die restlichen, die
unter diese Beamten nicht
mehr unter leiden wollen
diskriminiert und
verfolgt. Man sieht
hier unter die oben
genannten wenigen
Paragraphen, dass TPLF
der seit 24 Jahre das
ganze Land unter einem
Stamm im Griff hat,eine
Verfassung geschrieben
hat wobei ein paar Sachen
sehr kritisch sind und den
noch nicht in der Lage si
zu befolgen.
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
19 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ስነ ግጥም
አርበኛ የሚያሰኝህ
Tesfaye Gebreyohannes Abraha
Eppertshausen, Germany
ኣርበናኛ የሚያሰኝህ ላንተ ቁም ነገሩ የህዳሴ ግድብ ብሎ መዘመሩ ይህ ነው ቁም ነገሩ ላንተ ጀግንነቱ ህጻናትን ገድሎ እሬሳ ተራምዶ ዉስኪ መራጨቱ ማንነት ማዋረድ ማንነት ማንጓተቱ ቁም ነገሩ ላንተ ሰዉን መዘርጠጡ የማንም ሰው ችግር ከኣባይ ግድብ ኣይደል ወይ ከሃገሩ ያንተ ጓደኞች ከብረው በፎቅ ቤት ሲኖሩ ጮማ እየቆረጡ ከቆንጆ ሲዳሩ ሚሊዮኖች ተርበው በችግር ተጠብሰው ከትርፍራፊ ጉርሻቸዉን ገዝተው እግረኛ መንገድ ላይ ካርቶኑን ኣንጥፈው ባረረ ኣንጀታቸው ሙቀትና ብርዱ ተፈራርቆባቸው ይህንን ማየት ነው ላንተ ቁም ነገሩ ላንተ ጀግንነቱ ይህንን ማየት ነው ላንተ ቁም ነገሩ ላንተ ጀግንነቱ ያንተ ሹማምንቶች ቢሮኣቸዉን ዘግተው በየቢሮው ደጃፍ ባለ ጉዳቱ ይ ትተው ህዝብ እንደሚያጉላሉ ይህ ላንተ ተፍቶህ ነው የቱ ነው ጥፋቱ የቱ ነው ዉሸቱ የቱ ነው ጥፋቱ የቱ ነው ዉሸቱ ካገሬው ሰው ይልቅ ለውጭው ማጎብደዱ ከዉጭ ለመጣው ቱጃር ማጎብደዱ ይሄ ነው ክደቱ ይሄ ነው ዉሸቱ
ድምጽ የሌለው ጥይት
Dawit Kasahun, Germany
ድምጽ የሌለው ጥይት የወያኔ ስር ኣት ድምጽ በሌለው ጥይት ኣፋችን ኣፈኑት ድምጽ በሌለው ጥይት እጃችን ኣሰሩት ኣንድ ለኣምስት ብለው ህዝባችን ከፈሉት ኣማራ ኦሮሞ ጉራጌ እያሉት የበስ ተመልካች ህዝባችን ኣረጉት ከጥንት ከጥዋቱ ኣንድ ናት ኢትዮጵያ እንዲህ ያለማ ወጣት ልቅም ትፍር ኣድርገው መጣል ነው ኣስር ቤት ጋዜጠኛው ኮርቶ በሙያው ለመስራት ያየሁትን እዉነት እጽፋለሁ ብሎ ብእሩን በማንሳት ኣንብበው ይረዱ የኢትዮጵያ ልጆች ይሕንማ እውነት ኣንደዚህ ከኣልክማ እጆችህን ኣስረው ኑሮህ ወደ ኣስር ቤት ተነሱ እንነሳ በኣንድነት ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን የኣረመኔን ስር ኣት መገርሰስ ኣለብን ላዩ ዴሞክራሲ ውስጡ ኣፈና እንግልት እስከመቼ እንኑር በእንዲህ ያለ ስር ኣት እዩልን ስሙልን የኣለም መንግስታት ማራዘሚያ ኣንሁን የወያኔን ስር ኣት
ዱላ ቅብብል (ለአሁኑ
ገዢዎቻችን) Tiraza Tsiga
(Frankfurt, Germany )
ድንቅ ያፍሪካ አትሌቶች የሚሰሩት ስራ መላውን ጥቁር ህዝብ እጅግ ስላኮራ በየደረሱበት በየውድድሩ ታሪክ እየሰሩ ድል እያበሰሩ የናት ምድራቸውን ስም ስላስከበሩ ለታላቅ ስልማት ወደ አፍካ አዳራሽ በክብር ተጠሩ: ከዚያም ጋዜጠኛ ተናግሮ አናጋሪ የወሬ ሱሰኛ ወደ አንዱ አትሌት ቀርቦ አድናቆቱን ገልፆ ድምፁን አለዝቦ
"ፅናት በሚጠይቅ ረዥም ርቀት ታሸንፋላችሁ ሁሌም ያለጭንቀት አምስት ሺ አስር ሺ ውጤቱ ቢያረካም ዱላ ቅብብሉስ ለምን አይሳካም?" በማለት ጠየቀ ታዋቂው አትሌትም በስሱእየሳቀ "ቀን ከሌት በመስራት ውጤታችን አምሮ ጥረታችን ሰምሮ በስካሁን ድላችን ረክቷል ህዝባችን ዌል እንግዲህ ደሞ ዱላ ቅብብሉን ለመሪወቻችን" ብሎ ተናገረ በዚህ ንግግሩም ሪከርድ ሰበረ::
ፍትህን ፍለጋ
Solomon Worku Schwalbach, Germany
ጥላቻን የዘራች ቂምን ያበቀለች፣ የወያኔ መንግስት ህዝብን ያማረረች፣ ተማሪን ያሰረች ጋዜጠኛ አፍና ተኩሳ ገደለች። ሙስሊም ክርስትያኑን ደብድባ ቂሊንጦ ያሰረች፣ የመለስ ዕራዕይ ዕንዲያው ስትታወቅ ስንቱን አማረረች። ዲቃላ ልጅ ዲቃላ ወለደች፣ ምናለ ያን ጊዜ ሽል ሆና በቀረች። ጥላቻን የዘራች አማራን ነው ትግሬ ነው ደቡብ ነው ኦሮሞ ነፍጠኛ ዕያላሁ፣ ዕንዳው በዕንጉርጉሮ ዜማ ዕያዜማች ሁ፣ ህዝቤን ዕንጨት ዕየሰነጠራችሁ፣ ዕናንተ ወያኔ ዕንዳው ምን ተሻላችሁ። ሀይ ባይ ብታጡ ተናግሮ የሚሰማ፣ ፈጣሪ ዕንደሰው ድምጽህን አሰማ። ልዚች ምስኪን ሀገር ፍት ህ ለተጠማች፣ አሳያት ክንድህ ን አለሁልሽ በላት።
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
20 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
ስቃያቸው በዛ ዕረ የወገኔ፣ ስራም የለም አሉ ካልሆኑ ወያኔ። አልኖርም ለሆድ ክብሬ ዕየተቀማ፣ ዕኔም ዘረጋሁኝ ሰጭው ካልተቀማ።
ነጻነት በብላሽ
(ሄኖክ የሺጥላ) የምን ነጻ እንውጣ ገንዘቤን ሰብስቤ ጭኔ እስክወጣ አልፈልግም ጣጣ !
እስካለሁኝ ድረስ መቶ እጅ የኔ ነው ሞቶ ሞቶ ሞቶ አንተ መሪ ልትሆን ፣ አትችልም ከቶ
የዘመናት ብሶት ፣ ጸንሶ ና ወልዶኝ ገና ቁሜ ሳልሄድ ፣ የምን ወግድልኝ ይመስልሃል እውነት ፣ በምርጫ
እምወጣ ይመስልሃል እንደው ፣ ካርታ
የምጠጣ ገንዘቤን ዘርፌ ፣ ቀምቼ ሳልወጣ ?
የኔ ነው ሃገሩ ፣ የኔ ነው ሰፈሩ አቅም ካለህ ቀማ እኔም ቀምቼ ነው ያኔ ብቻ ያኔ ያኔ እለቃለሁ ! እንጂ በስብሰባ በሰላማዊ ሰልፍ አትሞክረው ተወው ይሄን ተራ ዘራፍ ! ነገርኩህ ደግሜ በመቶ እጅ ድል ቀልድ አላውቅም እኔ ትገባለህ ገደል !
ተራራ ደርምሼ ያመጣሁትን ድል አንተ በስክርቢቶ ፣ ጽፈህ ልትቀበል
ቅማል ተሸክሜ ያመጣሁትን ድል አንተ በኮሮጆ ፣ በእጣ ልትጥል ?
ሞኝ ነህ ፣ ከረፈፍ ጅላንፎ ፣ ቂላቂል የማየረባ ጩኸት ያህያ ላይ ደውል !
ይልቅ ነጻነቱ ፣ መከበር ካማረህ ቀማ ብዬሀለው ፣ ውርደት ካሳፈረህ
ነገርኩህ እኮ እኔ ሊማልሞን ውጣ እሾህ በሾህ እንጂ ፣ በሽኮኮ ላይወጣ እንጂ በልምምጥ በእግዚኦታ ፣ ስልጣን እኛ በዚያ ዋጋ መች ገዝተን አስመጣን
እያልክ ያለኸው ፣ እኔን እንደገባኝ በብላሽ ሽጥልኝ ፣ በብላሽ አስወጣኝ አያዋጣም አንተ ቁረጥና ክተት ቁረጥና ግባ ያንተ ድምጽ እሱ ነው ለኔ የሚገባ !
ጎሕ መጽሔት ሐምሌ 2007 ዓ. ም. 2ኛ አመት ቁጥር 10
21 Goh magazine, July 2015, 2nd edition, No. 10
አስደሳች ዜና: በጀርመን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ምክር ቤት ህጋዊ ማህበር እውቅና አግኝቶ ተመሰርተ
Äthiopischer Migrationsrat in Deutschland .e.v (Verein)
ይህ ማህበር የተቋቋመበት ዋናው ዓላማ እና ተግባሩ በተለያዩ ምክንያቶች አገራቸውን ትተው ለተሰደዱ እና የተለያየ ችግር ለሚደርስባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ፈጥኖ መድርስ እና የህግ ከለላ እዲያገኙ ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆም ነው። ስለዚህ ይህ ማህበር ተጠናክሮ ለቆመለት ዓላማ ስኬታማነት ለውጤት እንዲበቃ
ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች ከሆኑት ሁሉ ማንኛውንም ድጋፍ ይፈልጋል። 50
ሎሜ ለ50 ሰው ጌጡ ነው ለአንድ ሰው ግን ሸክም ነው እደተባለው ሁሉ እስካሁን ለቆምንለት ዓላማ ከጎናችን ሁናችሁ ስትታገሉ እና ሥትታግሉ ለነበራችሁ እና እንዲሁም በቅርብ ርቀት ሁናችሁ ስትከታተሉ ለቆያችሁ ውድ ወገኖቻችን በሙሉ ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ ድጋፋችሁን እድትለግሱ በክብሮት እንጠይቃለን። ስለዚህ የተቻለዎትን
ከለገሱ ሰው ለወገን ያለውን ከወረወረ 50 ሎሚ ለ50 ሰው ሆነ ማለት ነው።
ማሳሰብያ: ይህን መልዕክት ተርድታችሁ ለመርዳት የምትፈልጉ ሁሉ የድጋፍ መሥጫው ዘዴ እደሚከተለው ተገልጿል።
Subject: To support Ethiopian Migrations Counsel financially in Germany
Äthiopischer Migrationsrat in Deutschland e.v
Bank Contacts = Bank Sparkasse
Account Number.16094435
Bank sort Code-50852553
IBAN: DE41508525530016094435
Bank Code (BIC):HELADEF1GRG
Bank verbindung: Sparkasse
Konto Nummer.16094435
Bankleitzahl 50852553
IBAN:- DE41508525530016094435
Bank Code (BIC):HELADEF1GRG