ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች - aurora, colorado...አለብኝ? የድጎማ...

2
የአውሮራ የኢኮኖሚ እርዳታ ብድርና ድጎማ መርሃ ግብር የአውሮራ የኢኮኖሚ እርዳታ ብድርና ድጎማ መርሃ ግብር ምንድነው? የአውሮራ ከተማና የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ከ CEDS Finance (CEDS ሒሳብ) ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ውጤት የሆነውን በወቅቱ ያለውን የኢኮኖሚ ጫና ለማስታገስና በማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች ለማቆየት በአውሮራ ውስጥ ለሚገኙ አነስተኛ ንግዶች የሚውል የ$1 ሚሊዮን ድጎማና ብድር መርሃ ግብር ሊጀምሩ ነው። የመርሃ ግብሩ ግብ ምንድነው? ሥራ ማቆየት አንደኛ ግቡ ነው። የአውሮራ አነስተኛ ንግዶች ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ከስቴትና ከፌዴራል ተቋሞች ለማግኘት በሚጠብቁበት ጊዜ፥ ይህ የአካባቢው መርሃ ግብር አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ለማስገኘት ይረዳል። ምን ዓይነት እርዳታ ማግኘት ይቻላል? አመልካቾች መጠኑ እስከ $5000 የሆነ የድጎማ ማመልከቻ ወይም ከ$5000 እስከ $50000 ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር ለመጠየቅ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። ማነው ማመልከት የሚችለው? ይህ መርሃ ግበር የተዘጋጀው ለሬስቶራንት፥ ችርቻሮ፥ አገልግሎትና መዝናኛ አነስተኛ ንግዶችና ከኪነ ጥበብ ጋር ለተያያዙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ብቻ ነው። መስፈርቱን የሚያሟሉ ንግዶች በአውሮራ ውስጥ ቢያንስ ላለፉት 12 ወራት በአካል ሲሠሩ የነበሩ፥ ከ50 ሠራተኛ በታች ያላቸው፥ ከሕጋዊ ተቋማት ጋር ጥሩ አቋም ያላቸው፥ ዝቅተኛውን የገንዘብ መስፈርት የሚያሟሉና በዚህ እርዳታ አማካኝነት ቢያንስ አንድ ሥራ (ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ የገቢ መስፈርቶች የሚያሟላ) የሚያቆዩ መሆን አለባቸው። መቼ ማመልከት እችላለሁ? የማመልከቻ ሂደቱ ረቡዕ ኤፕሪል 8 AuroraGov.org/AER ላይ ክፍት ይሆናል። ንግዶች ድጎማም ብድርም ማግኘት ይችላሉ? አይችሉም። ንግዶች ማመልከቻው ላይ ድጎማ ወይም ብድር ብለው ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል። የማመልከቻ ሂደቱ እንዴት ነው የሚሠራው? የተቀላጠፈው የማመልከቻ ሂደት ፈጣንና ቀላል ነው። ንግዶች ከኤፕሪል 22 በፊት የቅድመ-ብቃት ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው። የማመልከቻው ሊንክ AuroraGov.org/AER ላይ ይገኛል። መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያ ይደርሳቸውና ገንዘብ ነክ ሰነዶችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ደህንነቱ የተጠበቀ ኢሜል ይሰጣቸዋል። ዝቅተኞቹን መስፈርቶች ካሟላሁ ገንዝቡን በቀጥታ ለማግኘት ብቃት አለኝ ማለት ነው? አይደለም። የገንዝብ መጠኑ ውስን ስለሆነና ይህ መርሃ ግብር ብዙ ተወዳዳሪዎች ስለሚኖሩት ተጨማሪ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ይገባሉ። ገንዘቡን ለመመደብ ይረዳን ዘንድ ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ይዘው የሚቆዩ ሰዎችን ቁጥር፥ የገንዘብ አስፈላጊነት አስቸኳይነትን፥ ንግዱ የሚያቀርበው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ገቢያቸው ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ የሆኑ ኗሪዎች የሚያስፈልጓቸው ወይም ለመጠቀም አቅማቸው የሚፈቅዷቸው መሆናቸውን፥ ንግዱ የሚገኝበት ሥፍራ የከተማ እድሳት አካባቢ መሆኑን፥ የንግዱ ባለቤት የአናሳ ቡድን አባል፥ ሴቶች እና/ወይም ስደተኛ መሆኑንና የሚጠፋው የገቢ መጠን መቶኛን በተጨማሪ ከግምት ውስጥ እናስገባለን። AuroraGov.org/AER ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

Upload: others

Post on 29-Jul-2020

10 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች - Aurora, Colorado...አለብኝ? የድጎማ መርሃ ግብር አመልካቾች የአውሮራ ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው

የአውሮራ የኢኮኖሚ እርዳታ ብድርና ድጎማ መርሃ ግብር

የአውሮራ የኢኮኖሚ እርዳታ ብድርና ድጎማ መርሃ ግብር ምንድነው? የአውሮራ ከተማና የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ከ CEDS Finance (CEDS ሒሳብ) ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ውጤት የሆነውን በወቅቱ ያለውን የኢኮኖሚ ጫና ለማስታገስና በማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች ለማቆየት በአውሮራ ውስጥ ለሚገኙ አነስተኛ ንግዶች የሚውል የ$1 ሚሊዮን ድጎማና ብድር መርሃ ግብር ሊጀምሩ ነው።

የመርሃ ግብሩ ግብ ምንድነው?

ሥራ ማቆየት አንደኛ ግቡ ነው። የአውሮራ አነስተኛ ንግዶች ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ከስቴትና ከፌዴራል ተቋሞች ለማግኘት በሚጠብቁበት ጊዜ፥ ይህ የአካባቢው መርሃ ግብር አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ለማስገኘት ይረዳል።

ምን ዓይነት እርዳታ ማግኘት ይቻላል? አመልካቾች መጠኑ እስከ $5000 የሆነ የድጎማ ማመልከቻ ወይም ከ$5000 እስከ $50000 ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር ለመጠየቅ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።

ማነው ማመልከት የሚችለው? ይህ መርሃ ግበር የተዘጋጀው ለሬስቶራንት፥ ችርቻሮ፥ አገልግሎትና መዝናኛ አነስተኛ ንግዶችና ከኪነ ጥበብ ጋር ለተያያዙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ብቻ ነው። መስፈርቱን የሚያሟሉ ንግዶች በአውሮራ ውስጥ ቢያንስ ላለፉት 12 ወራት በአካል ሲሠሩ የነበሩ፥ ከ50 ሠራተኛ በታች ያላቸው፥ ከሕጋዊ ተቋማት ጋር ጥሩ አቋም ያላቸው፥ ዝቅተኛውን የገንዘብ መስፈርት የሚያሟሉና በዚህ እርዳታ አማካኝነት ቢያንስ አንድ ሥራ (ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ የገቢ መስፈርቶች የሚያሟላ) የሚያቆዩ መሆን አለባቸው።

መቼ ማመልከት እችላለሁ? የማመልከቻ ሂደቱ ረቡዕ ኤፕሪል 8 በ AuroraGov.org/AER ላይ ክፍት ይሆናል።

ንግዶች ድጎማም ብድርም ማግኘት ይችላሉ?

አይችሉም። ንግዶች ማመልከቻው ላይ ድጎማ ወይም ብድር ብለው ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል።

የማመልከቻ ሂደቱ እንዴት ነው የሚሠራው?

የተቀላጠፈው የማመልከቻ ሂደት ፈጣንና ቀላል ነው። ንግዶች ከኤፕሪል 22 በፊት የቅድመ-ብቃት ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው። የማመልከቻው ሊንክ AuroraGov.org/AER ላይ ይገኛል። መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያ ይደርሳቸውና ገንዘብ ነክ ሰነዶችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ደህንነቱ የተጠበቀ ኢሜል ይሰጣቸዋል።

ዝቅተኞቹን መስፈርቶች ካሟላሁ ገንዝቡን በቀጥታ ለማግኘት ብቃት አለኝ ማለት ነው?

አይደለም። የገንዝብ መጠኑ ውስን ስለሆነና ይህ መርሃ ግብር ብዙ ተወዳዳሪዎች ስለሚኖሩት ተጨማሪ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ይገባሉ። ገንዘቡን ለመመደብ ይረዳን ዘንድ ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ይዘው የሚቆዩ ሰዎችን ቁጥር፥ የገንዘብ አስፈላጊነት አስቸኳይነትን፥ ንግዱ የሚያቀርበው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ገቢያቸው ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ የሆኑ ኗሪዎች የሚያስፈልጓቸው ወይም ለመጠቀም አቅማቸው የሚፈቅዷቸው መሆናቸውን፥ ንግዱ የሚገኝበት ሥፍራ የከተማ እድሳት አካባቢ መሆኑን፥ የንግዱ ባለቤት የአናሳ ቡድን አባል፥ ሴቶች እና/ወይም ስደተኛ መሆኑንና የሚጠፋው የገቢ መጠን መቶኛን በተጨማሪ ከግምት ውስጥ እናስገባለን።

AuroraGov.org/AER

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

Page 2: ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች - Aurora, Colorado...አለብኝ? የድጎማ መርሃ ግብር አመልካቾች የአውሮራ ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው

የአውሮራ የኢኮኖሚ እርዳታ ብድርና ድጎማ መርሃ ግብር

AuroraGov.org/AER

ዝቅተኛ መስፈርቶቹን ካሟላሁ ምን ዓይነት ተጨማሪ ሰነዶች ማቅረብ አለብኝ?

የድጎማ መርሃ ግብር አመልካቾች የአውሮራ ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፥ እንዲሁም በተጠየቁበት ጊዜ የግል ገንዘብ መግለጫና የ2019 ዓ.ም. የገቢ ግብር ማስረጃ ወይም የዓመት መጨረሻ የገቢ መግለጫ፥ የደሞዝና ወጪና ገቢ ሒሳብ መመዝገቢያ ማቅረብ መቻል አለባቸው። መስፈርት የሚያሟሉ የብድር አመልካቾች ያለፉትን ሶስት እስከ ስድስት ወራት የንግድ ባንክ ሒሳብ መግለጫዎችና የዚህን ወር ጊዜያዊ ሒሳብ መግለጫ እንዲሁም ያለፉትን ሶስት እስከ ስድስት ወራት የግል ባንክ ሒሳብ መግለጫዎች፥ የገቢ መግለጫ (ያለፉት 12 ወራትን) እና የወጪና ገቢ ሒሳብ መመዝገቢያ (ያለፈው የበጀት ዓመት መጨረሻ)፥ እንዲሁም ከዓመት መጀመሪያ እስካሁን ድረስ ያለ የገቢ መግለጫና የደሞዝ ወጪዎችን በሙሉ የሚያሳይ የወጪና ገቢ ሒሳብ መመዝገቢያ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።

መርሃ ግብሩ ያተኮረው በአውሮራ ውስጥ ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ማቆየት ላይ ነው። ሆኖም ገንዘቡ ለሌሎች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ላይ ለምሳሌ የንግድ ቦታዎን ጥልቅ ጽዳት፥ የዕቃ ወጪ መጨመር፥ ደሞዝ፥ የኪራይ ወጪዎችና ሌሎች የሥራ ካፒታል ጉዳዮች ላይ መዋል ይችላል። ገንዘቡን ዕዳ ለመክፈል መጠቀም አይቻልም።

የብድሩ ወለድ ምን ያህል ነው?

የብድሩ ወለድ 2% ሲሆን የመጀመሪያው የብድር ጊዜ ከአምስት ዓመት ያላለፈ ይሆናል (ወይም ማሻሻያ እና/ወይም ማራዘሚያ ከተደረገ እስከ ሰባት ዓመት ይቆያል)።

አይደለም። ሁለተኛ የገንዘብ ድጋፍ ዙር ሜይ 6 ይጀመራል። በመጀመሪያው ዙር የገንዘብ ድጋፍ ያላገኙ መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች ለሁለተኛው ዙር በቀጥታ ከግምት ውስጥ ይገባሉ። በሁለተኛው የገንዘብ ድጋፍ ዙር ወቅት አዲስ አመልካቾችም ማመልከት ይችላሉ።

ጥያቄ ካለኝስ? በ [email protected]. ኢሜል ያድርጉልን።

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

የድጎማውን ወይም የብድሩን ገንዘብ በምን መልኩ መጠቀም እችላለሁ?

የገንዝብ ድጋፍ የሚገኘው አሁን ብቻ ነው?