awramba times issue 176

22
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ በውስጥ ገፆች መሪዎቻችንና ግራ አጋቢ ክልከላዎቻቸው የተበከሉ ምግቦች የሚያስከትሏቸው በሽታዎች በወቅቱ አስፈላጊው ሕክምና ተደርጎ በቁጥጥር ስር ይውላሉ። ለነፍስ ጠንቅ የሆኑ የመንግስታት ትዕዛዞች በቁጥጥር ስር የሚውሉት በስሪንጅ አይደለም። በተበከለ ትዕዛዝ የቆሰለ ህዝብ የሚፈወሰው፣ ንፅህናው በተጠበቀ አዲስ መንግስት እና አዲስ ትዕዛዝ ብቻ ነው የውስጥ ዜናዎች በ ገፅ 8 በ ገፅ 3 በ ገፅ 19 በ ገፅ 19 የአትላንታው ፌስቲቫል፣ ከዚያም ሰለሞን ተካልኝ ክንፉ አሰፋ (ከቶሮንቶ) ክንፉ፡- “ወደ ኳስ ሜዳው ለምን ብቅ አላልክም?” ሰለሞን፡- “አገር ወዳድ ዘፋኞችን አይወዱም። በዚያ ላይ እኔን በአምስት መቶ ሲያሰሩኝ፣ ለነ አስቴር አወቀ ግን በሺህዎች ይከፍሏቸዋል።... እኔ የፈለግኩትን የመሆን መብት የለኝም እንዴ?” ክንፉ፡- “አምነህበት ከገባህ ወያኔ የመሆን መብትህ እንደተጠበቀ ነው። ሥራህን በተመለከተ ግን ስለሚያልፍ ሥርዓት እና ግለሰብ ከመዝፈን ይልቅ ስለ ሀገር ለምን አትዘፍንም?” ሰለሞን፡- “ጥሩ ሥራ የሰራን መሪ ባወድስ ምን አለበት? የእስክንድር ነጋን ፅሁፎች እያነበባችሁ ወደ ስህተት እንዳትገቡ…” ሲል ቀጠለ። 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09 2003 ዋጋ 7፡00 ብር ‹‹አንድን ሀገር ደሀ የሚያደርገው የሕዝቡ አመለካከት ነው›› ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን በጎ አመለካከት የሌላቸው ሰዎች ሁሌ የሚታያቸው ጨለማና ችግር ነው፡፡ እነሱ ከዚህ መከራና ችግር ለመውጣት ነው የሚሮጡት። ሪከርድ ለመስበር የሚሮጡት ደግሞ በበጎ አመለካከት መልካም ውጤት ላይ የላቀ ብቃትን ለመደረብ ነው። በ ገፅ 11 በ ገፅ 16 በ ገፅ 9 ዴሞክራታይዜሽን እና ልማታዊ መንግሥት ገዥ ኤሊቶች ብርቱ ሥጋት በሚያጋጥማቸው ወቅት አፋኝ ፖሊሲን አግባብነት እንዳለው ትክክለኛ ምላሽ ይቆጥሩታል። አልያም፣ የረዥም ጊዜ ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ ማሻሻዎችን እንደ ምርጥ አማራጭ ይወስዳሉ። ታሪክ እንደሚመሰክረው፣ ከሁለቱ መንገዶች መካከል ለውት ማሻሻያ የመውሰድ አማራጭ ይበልጥ ላቅ ባለ መልኩ የገዥውን ኤሊቶች ጠቅሟል። በመሳይ ከበደ (ፕ/ር) ገነት ዘውዴ ማልቀስ ይችላሉ እንዴ?” ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን ያነበቡ ድህነትን ተረት የምናደርገው በፕሮፖጋንዳ ነውን? እንደማመጥ! ሚዲያውን እናዳምጥ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚሰነዝሯቸው ገንቢ ሀሳቦች ቦታ እንስጥ ‹‹መርዶ ነጋሪነት ነው›› ከሚል ተራ ጨዋታ እንውጣ፡፡ ‹‹የኒዎ ሊበራሎች ዳንኪራ ነው›› ማለቱን ትተን አለምአቀፍ ሚዲያዎችና ለጋሽ ድርጅቶች በሚሰነዝሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እንምከር፡፡ በኤልያስ ገብሩ ባለፈው ረቡዕ አዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢያ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ሁለት ቦምቦች ሳይፈነዱ መገኘታቸውን የአውራምባ ታይምስ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በዕለቱ ፓርላማው አጠገብ ለግንባታ ተብለው በፈረሱ ቦታዎች ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተቀብረው ነበር የተባሉት ሁለት ቦምቦች በአካባቢው በቁፋሮ ሥራ ላይ ተሰማርተው በነበሩ ሰዎች አማካኝነት ሊታወቁ ችለዋል። ወዲያውም ፓርላማውን ሲጠብቁ ለነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይህ ጥቆማ ደርሷቸው አካባቢውን በመከለል የማጣራት ሥራ የተካሄደ ሲሆን፣ በወቅቱ በስፍራው በመገኘት ቦምቦቹን ከተቀበሩበት ቦታ ያገኙት የአካባቢው ወጣቶች ለተጨማሪ ምርመራ በቅርብ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንና ተቀብረው የተገኙት ቦምቦችም በፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ክፍል መክነው ሊነሱ መቻላቸውን ምንጮች አስረድተዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ በአረዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ በፓርላማ አቅራቢያ ቦምቦች ተቀብረው ተገኙ በአስኮ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፡- አንድ ጄሪካን ውሃ በ10 ብር እየተሸጠ ነው በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ አስግቷል - ድርቅና ርሀብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ለዶክተሮች አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት ተዘጋጀ - በሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ቀዳሚ መስፈርት ሆኗል በ ገፅ 14 ፓርላማው እና ክራሞቱ

Upload: balemlayl

Post on 09-Mar-2015

191 views

Category:

Documents


6 download

TRANSCRIPT

Page 1: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በውስጥ ገፆች

መሪዎቻችንና ግራ

አጋቢ ክልከላዎቻቸውየተበከሉ ምግቦች የሚያስከትሏቸው በሽታዎች በወቅቱ

አስፈላጊው ሕክምና ተደርጎ በቁጥጥር ስር ይውላሉ።

ለነፍስ ጠንቅ የሆኑ የመንግስታት ትዕዛዞች በቁጥጥር

ስር የሚውሉት በስሪንጅ አይደለም። በተበከለ ትዕዛዝ

የቆሰለ ህዝብ የሚፈወሰው፣ ንፅህናው በተጠበቀ አዲስ

መንግስት እና አዲስ ትዕዛዝ ብቻ ነው

የውስጥ ዜናዎች

በ ገፅ 8

በ ገፅ 3

በ ገፅ 19

በ ገፅ 19

የአትላንታው ፌስቲቫል፣ ከዚያም ሰለሞን ተካልኝክንፉ አሰፋ (ከቶሮንቶ)

ክንፉ፡- “ወደ ኳስ ሜዳው ለምን ብቅ አላልክም?” ሰለሞን፡- “አገር ወዳድ ዘፋኞችን አይወዱም። በዚያ ላይ እኔን በአምስት መቶ ሲያሰሩኝ፣ ለነ አስቴር አወቀ ግን በሺህዎች ይከፍሏቸዋል።... እኔ የፈለግኩትን የመሆን መብት የለኝም እንዴ?” “

ክንፉ፡- “አምነህበት ከገባህ ወያኔ የመሆን መብትህ እንደተጠበቀ ነው። ሥራህን በተመለከተ ግን ስለሚያልፍ ሥርዓት እና ግለሰብ ከመዝፈን ይልቅ ስለ ሀገር ለምን አትዘፍንም?” ሰለሞን፡- “ጥሩ ሥራ የሰራን መሪ ባወድስ ምን አለበት? የእስክንድር ነጋን ፅሁፎች እያነበባችሁ ወደ ስህተት እንዳትገቡ…” ሲል ቀጠለ።

4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

‹‹አንድን ሀገር ደሀ የሚያደርገው የሕዝቡ አመለካከት ነው››

ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን

በጎ አመለካከት የሌላቸው ሰዎች ሁሌ

የሚታያቸው ጨለማና ችግር ነው፡፡ እነሱ

ከዚህ መከራና ችግር ለመውጣት ነው

የሚሮጡት። ሪከርድ

ለመስበር የሚሮጡት

ደግሞ በበጎ

አ መ ለ ካ ከ ት

ባ መ ጡ ት

መልካም ውጤት

ላይ የላቀ ብቃትን

ለ መ ደ ረ ብ

ነው።

በ ገፅ 11

በ ገፅ 16

በ ገፅ 9

?ዴሞክራታይዜሽን

እና ልማታዊ መንግሥት

ገዥ ኤሊቶች ብርቱ ሥጋት በሚያጋጥማቸው ወቅት አፋኝ

ፖሊሲን አግባብነት እንዳለው ትክክለኛ ምላሽ ይቆጥሩታል።

አልያም፣ የረዥም ጊዜ ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ

ማሻሻዎችን እንደ ምርጥ አማራጭ ይወስዳሉ። ታሪክ

እንደሚመሰክረው፣ ከሁለቱ መንገዶች መካከል ለውት

ማሻሻያ የመውሰድ አማራጭ ይበልጥ ላቅ ባለ መልኩ

የገዥውን ኤሊቶች ጠቅሟል።በመሳይ ከበደ

(ፕ/ር)

“ገነት ዘውዴ ማልቀስ ይችላሉ እንዴ?”ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን ያነበቡ

ድህነትን ተረት የምናደርገው በፕሮፖጋንዳ ነውን?እንደማመጥ! ሚዲያውን እናዳምጥ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚሰነዝሯቸው ገንቢ ሀሳቦች ቦታ እንስጥ ‹‹መርዶ ነጋሪነት ነው›› ከሚል ተራ ጨዋታ እንውጣ፡፡

‹‹የኒዎ ሊበራሎች ዳንኪራ ነው›› ማለቱን ትተን አለምአቀፍ ሚዲያዎችና ለጋሽ ድርጅቶች በሚሰነዝሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እንምከር፡፡

በኤልያስ ገብሩ

ባለፈው ረቡዕ አዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢያ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ሁለት ቦምቦች ሳይፈነዱ መገኘታቸውን የአውራምባ ታይምስ የቅርብ ምንጮች ገለፁ።

በዕለቱ ፓርላማው አጠገብ ለግንባታ ተብለው በፈረሱ ቦታዎች ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተቀብረው ነበር የተባሉት ሁለት ቦምቦች በአካባቢው በቁፋሮ ሥራ ላይ ተሰማርተው በነበሩ ሰዎች አማካኝነት ሊታወቁ ችለዋል።

ወዲያውም ፓርላማውን ሲጠብቁ ለነበሩ

የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይህ ጥቆማ ደርሷቸው አካባቢውን በመከለል የማጣራት ሥራ የተካሄደ ሲሆን፣ በወቅቱ በስፍራው በመገኘት ቦምቦቹን ከተቀበሩበት ቦታ ያገኙት የአካባቢው ወጣቶች ለተጨማሪ ምርመራ በቅርብ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንና ተቀብረው የተገኙት ቦምቦችም በፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ክፍል መክነው ሊነሱ መቻላቸውን ምንጮች አስረድተዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ በአረዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ

በፓርላማ አቅራቢያ ቦምቦች ተቀብረው ተገኙበአስኮ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፡-

አንድ ጄሪካን ውሃ በ10 ብር እየተሸጠ ነው

በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ አስግቷል

- ድርቅና ርሀብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ለዶክተሮች አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት ተዘጋጀ- በሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ቀዳሚ መስፈርት ሆኗል

በ ገፅ 14

ፓርላማው እና ክራሞቱ

Page 2: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ድህነትን ተረት የምናደርገው በፕሮፖጋንዳ ነውን?

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

Ÿõ}— ]þ`}a‹ ›?MÁe Ñw\

c<^õ›?M Ó`T

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹cKV” VÑe

ታዲዎስ ጌታሁን SpÅe õeNደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

የማስታወቂያ ክፍሉ ስልክ0911629281

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 0923 02 88 91 ®911 62 92 82 0911 15 62 48 þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

ከዛሬ 36 ዓመት በፊት ኢ ት ዮ ጵ ያ ው ስ ጥ ሰ ላ ም ፣ ነ ጻ ነ ት ና ዴሞክራሲ የ ለ ም ፤

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት አልተረጋገጠም፤ ረሀብና የፍትህ እጦት አለ፤ የሚል አላማ ያነገቡ የነጻነት ታጋዮች ለእነዚህ መሰረታዊ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥ በብሄርም ይሁን በህብረብሄራዊ ማዕቀፍ ተደራጅተው በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበሩ ገዢዎችን ለመፋለም የወሰኑበት ዘመን ነበር፡፡ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዱ ዛሬ የመንግስትን ስልጣን ተቆናጥጦ የሚገኘው ኢህአዴግ ይገኝበታል፡፡ በጣት በሚቆጠሩ የሕወሓት ታጋዮች ትግራይን ነጻ ለማውጣት የተጀመረው ትግል፤ ኋላ ላይ ኢህአዴግ በሚል አገር አቀፍ አደረጃጀት ከደርግ ስልጣን የተረከበው ይህ ስርዓት፤ ከ36 ዓመታት በፊት ወደ ጫካ እንዲገባ ምክንያት የሆኑ የቀድሞ ገዢዎችን መለያ ባህሪያት እየተላበሰ ነው

የሚሉ አያሌ ክሶች እየቀረቡበት ይገኛል፡፡ ኢህአዴግ የጀርባ አጥንቴ ብሎ የሚመካባቸው ገበሬዎች ከእርሻቸው እየተፈናቀሉ ለም መሬቶቻቸው ለውጭ ኢንቨስተሮች እየተሰጡባቸው ነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች በፓርቲ አባልነት እንዲጠመቁ እየተገደዱ ነው፡፡ የፕሬስ ነጻነት በአደገኛ ሁኔታ የኋሊዮሽ እየተራመደ መንግስትን የሚተቹ ጋዜጠኞች መኖሪያ ስደት እየሆነ ነው፡፡ የኑሮ ውድነት በአደገኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ ዜጎች በረሀብ አለንጋ እየተገረፉ ነው፡፡ ከ26 ዓመታት በፊት የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ርዕሰ ጉዳይ የነበረው ረሀብ ዛሬም የእነዚሁ ሚዲያዎች የዜና ርዕስ ነው፡፡ ‹‹አለምአቀፍ እርዳታ ለጋሾች የእርዳታ እጃቸውን እንዳይዘረጉ አድርገዋል›› ብሎ የቀድሞ መንግስታትን የሚወነጅለው ኢህአዴግ አሁንም በቁጥሮች የድብብቆሽ ጨዋታ ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር እየተወዛገበ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ሚዲያዎች ስለ ጥጋብ እየሰበኩን ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያን

ጥንታዊ ስልጣኔ ለመመለስም መንግስት እየተጋ መሆኑን ያለ አንዳች መሸማቀቅ እየነገሩን ይገኛሉ፡፡ ሀቅን በፕሮፖጋንዳ መጋረድ እንደማይቻል ካለፉት መንግስታት ትምህርት መቅሰም እንዴት ያቅተናል?

‹‹ችግሩ የኛ ሳይሆን የተፈጥሮ ጉዳይ ነው›› በማለት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አለመዝነቡ በየጊዜው በምክንያትነት የምናቀርበው እስከመቼ ነው? ለመሆኑ የዛሬይቱ አለም ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ሚሊዮኖች የሚላስ የሚቀመስ የሚያጡባት፤ ህጻናት ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተመተው የሚወድቁባት ናትን? ተፈጥሮስ ከአለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ የምትባልን አገር ብቻ መርጦ የሚቀጣበት ምክንያት ምንድነው? ዛሬ እኮ ትናንት አይደለም፡፡ ዛሬ ያለው ተጨባጭ አለም ከ30 ዓመት በፊት እንደነበረው አይደለም፡፡ የዛሬው ተጨባጭ ዓለም በአመትና በወራት የሚለካ ሳይሆን በደቂቃዎችና በሰኮንዶች ተመንዝሮ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት ነው፡፡ ምን እየሆንን ነው? ምን እያልን

ነው? ምን እያደረግን ነው? ዜጎች ነን ችግሩ በግልጽ ከተወያየንበትና በመኖሩ ላይ ከተማመንን መፍትሄው እኮ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡ እንደማመጥ! ሚዲያውን እናዳምጥ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚሰነዝሯቸው ገንቢ ሀሳቦች ቦታ እንስጥ ‹‹መርዶ ነጋሪነት ነው›› ከሚል ተራ ጨዋታ እንውጣ፡፡ ‹‹የኒዎ ሊበራሎች ዳንኪራ ነው›› ማለቱን ትተን አለምአቀፍ ሚዲያዎችና ለጋሽ ድርጅቶች የሚሰነዝሯቸው አስተያየቶችና ስጋቶችን መሰረት አድርገን የአለም መሳቂያና መሳለቂያ ባደረጉን ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እንምከር፡፡ ባሉት ነባራዊ እውነቶች ላይ መፍትሄ እንስጥ? አፍራሽ አጀንዳ ያላቸው የውጭ ኃይሎች አሉ ብለን የምናምን ከሆነም የምናሸንፋቸው በመካከላችን አንድነት፣ መከባበርና መመካከርን ስናሰፍን ነው፡፡ አሻፈረኝ ባይነትን፤ የማንፈልገውን ላለመስማት ሳይሆን ለአገራችን ጥቅም ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹ይቅርታ አሁንስ መንግስቱን መሰልከኝ አልኩት። ቤቱ በድንጋጤ ተናወፀ። በተለይ ከጎጌ ተቀምጣ የነበረችው ገነት ዘውዴ ‹እንዴት ከመንግስቱ ጋር ታወዳድረዋለህ› በማለት ስቅስቅ ብላ አለቀሰች››

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳየቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት

በ1993 ዓ.ም ኢህአዴግን ስለተሰናበቱበት ክስተት አስመልክቶ በቅርቡ ለንባብ በበቃው መፅሀፋቸው

ላይ ካሰፈሩት የተወሰደ።

….አፄ ኃ/ሥላሴ ፌዴሬሽን ማፍረሳቸውም ሌላ የመገንጠል ምክንያት ነው። ደርግም ኤርትራ

መሬትዋ እንጂ ህዝቧን አንፈልግም ያለውስ ምን ሊባል ነው የአንድነት ጥሪ ነው

አቶ ስብሃት ነጋ የቀድሞ የሕወሓት ሊቀመንበር

በኤርትራ ጉዳይ ላይ ይህ መንግስት ብቻ ተጠያቂ መሆን እንደሌለበት ለማስረዳት በፍትሕ ጋዜጣ ላይ

ካሰፈሩት ማስታወሻ የተወሰደ

ማን ምን አ ለ

‹‹ከቢንላደን በላይ ማን ነው አሸባሪ? በየትኛው ሀገር ነው የቢንላደንን መልዕክት ማስተላለፍ ወንጀል

የሆነበት? ቢንላደንን መደገፍና ስለ ቢንላደን መዘገብ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያው ፀረ-ሽብር ሕግ

በዚህ ልዩነት ላይ በሩን የዘጋ ነው፡፡››

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

የኢትዮጵያ ጸረ ሽብርተኝነት ህግ በጋዜጠኞች ላይ ያመጣውን ጫና አስመልክቶ ለአዲስ ወሬ ጋዜጣ

ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ

Page 3: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ድህነትን ተረት የምናደርገው በፕሮፖጋንዳ ነውን?

ዴሞክራታይዜሽን እና ልማታዊ መንግሥት

3

ለልማታዊ መንግሥት ዕድገት የተሰሩ አስገንዛቢ ጥናቶች እንደሚስማሙት፣ የሥልጣን ሥጋት ስለምን አምባገነናዊ ኤሊቶች የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያጠናክሩ ማሻሻያዎችን ይወስዳሉ ለሚለው ምክንያት መሆኑን ነው። ማሻሻያዎቹ አንዳች ላልታሰበ ድንገተኛ የዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የታለሙ ሳይሆኑ፣ በመሰረታዊነት ሥልጣንን ለማስጠበቅ በሚል የሚወሰዱ ናቸው። ሥጋቱ ውስጣዊ ወይም ውጫዊ ወይም ከሁለቱን ሊሆን ይችላል። ዋናው ቁም ነገር ያለው የገዥው ኤሊት ማሻሻያዎችን አለመውሰድ የእኔ ናቸው የሚላቸውን ነገሮች በጠቅላላ የሚያጣቸው መሆኑ በማያሻማ መልኩ የተጤነ ዕውነታ መሆኑ ነው።

የቅኝ አገዛዝ ሥጋትን ለማስወገድ በሚል ምክንያት፣ በአንድ ወቅት የለውጥ አቅጣጫን የተከተሉ ሥር-ነቀል ማሻሻያዎችን ወስዳ የነበረቸውን ጃፓንን እዚህ ጋር እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል። እንደ ታይዋን፣ ሆንግ ኮንግ፣ ሲንጋፓር እና ደቡብ ኮርያ ያሉ

ሀገራት ደግሞ የኮሚኒዝምን አደጋ ለማምከን እንደ ጃፓን አይነት ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አድርገው ነበር። የላቲን አሜሪካን ሀገራትን ስንመለከት፣ መሰል የለውጥ ማሻሻያዎቻቸውን የተገበሩት በኩባ አብዮት መነቃቃትን ያገኙ በማርክሲስት ቡድኖች ለተመሩ ውስጣዊ አመጾች ምላሽ ይሆን ዘንድ በማቀድ ነበር።

ገዥ ኤሊቶች ብርቱ ሥጋት በሚያጋጥማቸው ወቅት አፋኝ ፖሊሲን አግባብነት እንዳለው ትክክለኛ ምላሽ ይቆጥሩታል። አልያም፣ የረዥም ጊዜ ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ ማሻሻዎችን እንደ ምርጥ አማራጭ ይወስዳሉ። ታሪክ እንደሚመሰክረው፣ ከሁለቱ መንገዶች መካከል ለውት ማሻሻያ የመውሰድ አማራጭ ይበልጥ ላቅ ባለ መልኩ የገዥውን ኤሊቶች ጠቅሟል።

በ ተ ጨ ማ ሪ ፣ አመክንዮዓዊው የማሻሻያዎች ፖሊሲ በአምባገነናዊ አገዛዞች ምክንያት የተከሰቱ ፖለቲካዊ አጣቢቂኞችን እንደ መቅረፊያ መንገድ ተደርገው ይታያሉ። ዘልማዳዊ ኤሊቶች

በመሳይ ከበደ(ፕ/ር)

በዴሞክራታይዜሽን ሂደት ትግበራ በሚሰማሩበት ወቅት፣ ፍላጎታቸው እና አመለካከታቸው ከዘልማዳዊው የሥልጣን ህዝባዊ ተቀባይነት ጋር ተጣጥሞሽ በሌለው በምዕራቡ ትምህርት አማካኝነት የዘመነኛ ኤሊት አካሄድን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ይህም አለመግባባት በቀላሉ ለፖለቲካ ሥልጣን ቁጥጥር ወደሚደረግ ፉክክር ይለወጣል። ከዚያም አምባገነናዊነት እየተጠናከሩ ያሉ ኤሊቶችን የበታች ቦታን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንደማፈኛ ጉልበት ጥቅም ላይ ይውላል። እንዲያም ሆኖ የገዥው ኤሊቱ እይታ የአፈና ፖሊሲ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትንም ሆነ ሰላምና ፖለቲካዊ መረጋጋትን የማያመጣ፣ የማያሰፍን ነው የሚልም ሊሆን ይችላል። ማብቂያውና ውጤቱ በግልፅ የማይታወቅ ፖለቲካዊ አለመግባባት የመከሰቱ ዕድል መኖር በአምባገነናዊው ኤሊትና ተስፈኞች በሆኑ ኤሊቶች መካከል መቀራረብን የሚፈጥር ነው። በሌላ አገላለፅ፣ ሁለቱም ወገኖች ፖለቲካዊ መፍትሄ አለመኖሩን

በ ገፅ 14

የሰብአዊ መብቶች ጉባዔHUMAN RIGHTS COUNCIL

ሰመጉ የቆመው ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ ልዕልናና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ነውHRCO Stands for democracy, the rule of law and the respect of human right

የጨረታ ማስታወቂያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በተለያዩ ቅ/ጽ/ቤቶቹ ሲገለገልባቸው የቆውን የቢሮ እቃዎች ማለትም ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ ሼልፎችንና የፋይል ማስቀመጫዎችን እንዲሁም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ የሆኑትን ኮምፒዩተሮች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣

ፕሪንተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከዚህ በታች በተገለጸው መስፈርት መሰረት መወዳደር ይችላል።

ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) ለእያንዳንዱ የጨረታ 1. ሰነድ በመክፈል የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ስታድየም ሳህለ ሥላሴ ህንፃ 8ኛ፣ ቢሮ ቁጥር 19 ከሚገኘው ቢሮአችን በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች እቃዎቹን ኮተቤ በሚኘው ቅጥር ግቢ ይህ ማስታወቂያ 2. ከወጣበት ጊዜ አስከ ሐምሌ 16 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ማየት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 3. 17 ቀን 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ዕቃዎቹ በሚገኙበት ቦታ ይካሄዳል / ይከፈታል። ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት 4. ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከተታይ ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ክፍያ ከፍለው ዕቃዎቹን ማንሳት አለባቸው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም 5. ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ስታዲየም ላሊበላ ሬስቶራንት ጎን ሳህለ ሥላሴ ህንፃ 8ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር19

ስልክ + (251-11) 551 4489 /0912164050ፋስክ + (251-11) 551 7704

ስ ገዥ ኤሊቶች ብርቱ ሥጋት በሚያጋጥማቸው ወቅት

አፋኝ ፖሊሲን አግባብነት እንዳለው ትክክለኛ ምላሽ ይቆጥሩታል።

አልያም፣ የረዥም ጊዜ ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ ማሻሻዎችን

እንደ ምርጥ አማራጭ ይወስዳሉ። ታሪክ እንደሚመሰክረው፣

ከሁለቱ መንገዶች መካከል ለውት ማሻሻያ የመውሰድ አማራጭ

ይበልጥ ላቅ ባለ መልኩ የገዥውን ኤሊቶች ጠቅሟል።

Page 4: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003ፊ ቸ ር4

‹‹ድህነት ተረት እንደሚሆን፣ ረሀብ በሚሊኒየሙ ማግስት ከኢትዮጵያ ምድር ተጠራርጎ እንደሚጠፋ እጅግ አማላይ በሆኑ ቃላት አበክሮ በመስበክ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከቀናት በፊት ‹‹እንደገና›› በሚል ርዕስ የኢትዮጵያን የ3000 ዘመን ታሪክ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም አቅርቦ ነበር። ፊልሙ ከአክሱም ዘመን

መንግስት አንስቶ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ስልጣኔ የነበረበትን ደረጃ በማሳየት ባለፈው ሚሌኒየም አጋጠሙ ያላቸውን የረሀብ እልቂቶች (በተለይ በኃይለ ስላሴና በደርግ ዘመን የተከሰቱትን) በማንሳት መንግስታቱ ነባራዊውን ሁኔታ በመደበቅ፣ የረሀብተኞቹን ቁጥር በማሳነስና አለማቀፉ ማህበረሰብ ለረሀብተኞቹ የእርዳታ እጁን እንዳይዘረጋ አድርገዋል በማለት የንጉሱንና የደርግን ስርዓት አጥብቆ ወንጅሏል። ዘጋቢ ፊልሙ ይህንን በዝርዝር ካቀረበ

በኋላ መሰል አሰቃቂ ረሀቦች በዚህች ምድር ዳግም አይከሰቱም በሚል ምፀት፤ ልማታዊው የኢህአዴግ መንግስት ምስጋና ይግባውና የአገሪቱን የጥንት ገናና ስልጣኔ ዳግም እንደሚያንሰራራ የዘጋቢ ፊልሙ ፕሮዲውሰሮች ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ‹‹ቃል›› ገቡ።ከላይ የጠቀስነው ዘጋቢ ፊልም ለእይታ

ከመብቃቱ ከሰዓታት በፊት ግን የአልጀዚራው ማይክ ሀና ‹‹inside story›› በተሰኘ የቴሌቭዥን ጣቢያው ተወዳጅ ፕሮግራም ላይ እጅግ በሚያሳቅቁ ምስሎች የተደገፈ የረሀብ ዘገባ ለእይታ አበቃ። ‹‹Africa’s drought፡ is weather or war to blame?›› በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ፕሮግራም፤ በ60 ዓመታት ታሪክ ውስጥ የአለማችን እጅግ አስከፊ የተባለለትን የአፍሪካ ቀንድ ዘግናኝ ረሀብ የቀረበበት ሲሆን በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በጅቡቲና በሶማሊያ በአጠቃላይ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለአስከፊ ረሀብ መጋለጡን ዘገባው አሳይቷል። ጋዜጠኛ ማይክ ሀና በፕሮግራሙ ላይ

ሦስት እንግዶችን በመጋበዝ ለዚህ ማነው ተጠያቂው የሚል አይነት ይዘት ያለው ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት; የዘርፉ የፖሊሲ

ጥናት ተመራማሪዎች ደፊን ዌይሻይ እና ዓሊ ካሀን ሳቱቹ እንዲሁም የኬር ኢንተርናሽናል የፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ኦላን ቶሚልሰን ናቸው። በውይይቱ መሀል ለእንዲህ አይነቱ ረሀብ መንሰራፋት የአየር ጸባይ ብቻ ሳይሆን መንግስታት የሚከተሉት የተንጋደደ ፖሊሲም አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

‹‹እንደገና›› ያልነው ረሀቡን ወይስ ስልጣኔውን

ከላይ በመግቢያችን ላይ የጠቀስነው እና የቀድሞ መንግስታት ህዝባቸውን አስርበዋል፣ የአሁኑ መንግስት ግን የኢትዮጵያን የጥናት ስልጣኔ ለመመለስ እየተጋ ስለመሆኑ የሚሰብከው ዘጋቢ ፊልም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቀረብ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ምትኩ ካሳ ከአምባሳደር ዶልናልድ ቡዝ እና የአለም ምግብ ድርጅት ተወካይ ከሆኑት ፕ/ር ገቢሳ እጄታ ጋር

ባለፈው ሰኞ በሂልተን ሆቴል ከጋዜጠኞች ጋር ተፋጠዋል። ምኒስትር ዴኤታው የሰጡት መግለጫ ግን በመግቢያችን ላይ የገለጽነውን የኢቲቪ ዶክሜንቴሪ በሚፃረር መልኩ ከአራት ሚሊዩን ተኩል በላይ ኢትዮጵያዊያን ለረሀብ መጋለጣቸውን ይፋ የሆነበት ነው። ይህንን የመንግስት ጥሪ የሰሙ ተንታኞች ‹‹እንደገና›› በሚል ርዕሰ ለእይታ የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ዳግም ረሀብ መከሰቱን ለማመላከት የቀረበ ወይስ የኢትዮጵያን ስልጣኔ ለመመለስ ያለመ? ሲሉ በጉዳዩ ላይ መገረማቸውን ይገልጻሉ፡፡መንግስት ከአመት እስከ አመት ዜጎቹን

በህይወት ለማቆየት የእርዳታ ለጋሾችን እጅ የግድ መመልከት እንዳለበት የሚገልፁ ተንታኞች ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተባባሰ በሄደበት ሁኔታና በከተሞች ሳይቀር በረሀብና ችጋር በህልፈት የሚዳረጉ ዜጎች በበረከቱባት ኢትዮጵያ፤ ሁኔታዎችን ሊያሻሽል የሚችል ፖሊሲ ተቀርጾ ስራ ላይ ከማዋል ይልቅ በቀድሞ መንግስታት ላይ ብቻ ጣትን የመቀሰር አባዜ እስከመቼ? ሲሉ በቁጭት ይጠይቃሉ።

የረሀብተኞችን ቁጥር አሳንሶ የመግለጽ አባዜ

በአፄ ኃይለስላሴ መንግስት ላይ ተቃውሞው በርትቶ መንበረ ስልጣናቸውን ለመነቅነቅ ምክንያት ከሆኑ አበይት ነጥቦች መካከል ግንባር ቀደሙ የ1966ቱ የወሎ ረሀብ

እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ። በ1977 ዓ.ም በአገራችን የተከሰተው ረሀብም በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማሪያምን ገጽታ ያበላሸ ክስተት ከመሆኑ ባሻገር ያኔ በሽምቅ ውጊያ ላይ የነበረው የአሁኑ መንግስት ከክስተቱ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ፖለቲካዊ ትርፍ ሸምቶበታል። አለምአቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን የዘረጋው መንግስታቱ ባሰራጩት መረጃ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን እነ ጆናታን ዲምቢልቢና መሀመድ አሚን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች በሰሯቸው አጋላጭ ዘገባዎች አማካኝነት ነው፡፡ ይሁንና ግን ‹‹ረሀብተኞቹን ደብቀዋል፤

ትክክለኛውን የተረጂዎች አሀዝ አሳንሰው ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳውቀዋል›› የሚሉ ትችቶችን በቀድሞዎቹ መንግስታት ላይ በመሰንዘር የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ‹‹እጅግ በተባባሰ ሁኔታ የቀድሞ መንግስታትን ስህተት እየደገመ ነው›› የሚሉ ትችቶች ከአለምአቀፍ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች ጠንከር ባለ ሁኔታ እየተሰነዘሩበት ነው፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት የአለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል በማለት ነባራዊው ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚገልጸው በላይ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡መንግስት በድርቅ የተጎዱ ዜጎቹን ቁጥር

እስከመቼ?

?

የአውሮፓ አገራት ቀደም ብሎም በኢንዱስትሪው፣

በንግዱና በመጓጓዣው ዘርፍ በደንብ የተደራጁ

ነበሩ። የሚያስፈልገው ኢኮኖሚያቸው እንዲያንሰራራ

ማድረግ ብቻ ነው። በሌላ በኩል ግን ድሃ አገራት

በውጭ እርዳታ አማካኝነት መንገዶች፣ ትምህርት

ቤቶችንና ክሊኒኮችን ቢገነቡም አገራቱ የተፈጥሮ

ሀብት፣ አስተማማኝና ፍትሀዊ የንግድ ሥርዓት ብሎም

ምቹ የሆነ የንግድ መስመር ስለሌላቸው ሕዝቦቻቸው

እስከአሁን ድረስ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ።

በዳዊት ከበደ

Page 5: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

ማስታወቂያ

በ ገፅ 15

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ከዓለም ሲኒማ ተመልካቾች የተሰበሰበ

በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው 1. ግሩም ኤርሚያስ የተዋጣለት 2. አማላይ ነው በተለይ ለእንደእኔ ትውልደ 3. ኢትዮጵያዊ ይመቻል በጥራት ስለሰራችሁት 4. አመሰግናለሁ ፊልም ማለት እንደዚህ ነው 5. ሁለት የተለያዩ ስቶሪዎች በፍቅር 6. አይቻለሁ ግሩም እኔን በጣም ነው ያማለለኝ 7. አስተዋውቁኝ እኔና ጓደኞቼ የእውነት ማለናል፡፡ 8.

ምስጋና ለዓለም ሲኒማ

ከባለሙያዎች የተሰጠ አርቲስት መርዓዊ ስጦት - ዘመኑን የዋጀ ፊልም አርቲስት ሠይፉ አርአያ - የወጣቶችን ልብ የሚማርክ ዘመናዊ ፊልም አርቲስት ጌትነት እንየው - በጣም የሚጣፍጥ ቀለል ያለ ታሪክ አርቲስት ቢኒያም ወርቁ - በሁሉም መስክ የተዋጣለት ፊልም ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ - በባለሙያዎች የተሰራ ምርጥ ፊልም የሜዳሊያ ደራሲ አማኑኤል መሀሪ - ምርጥ ፕሮዳክሽን ሊያዩት የሚገባ

የአማላዩ ፊልም እውነታዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተቀረፀ - በCanon 5D እና 7D የተቀረፀ- በከፍተኛ በጀት የተዘጋጀ፣ 7 ወራትን የፈጀ - በየጊዜው መረጃዎችን በጋዜጣዊ መግለጫ ያበሰረ - ለቀለም እርማት ሥራ ወደ ለንደን የተጓዘ - ከተመረቀ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በ21 እይታ የታየ- ተመልካቾችንና ባለሙያዎችን ያስማማ ምርጥ ፊልም - አማላዩ-

በእምቢልታ ሲኒማ፣ በኤድና ሞል፣ በአለም ሲኒማ፣

በዩፍታሄ ሲኒማ፣ በፓናሮሚክ ሳምንቱን ሁሉ ይገኛል

‹‹አማላዩ›› ከካም ግሎባል ፒክቸርስ አማላዩ ሮማንቲክ ኮሜዲ

ስለ ‹‹አማላዩ›› ፊልም ተመልካቾች ምን ይላሉ

አሳንሶ ይገልፃል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው የሚናገሩት የዩኤስአይዲ የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄሰን ፍሬዘር በደቡብ ክልል ብቻ ከ750 ሺህ ህዝብ በላይ ለአደጋ መጋለጡን የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች በእጃችን ላይ እያሉ መንግስት ግን ይፋ ያደረገው 252 ሺህ ብቻ መሆኑንና ይህ አሀዝ ደግሞ የግማሽ ሚሊዮን ያህል ለውጥ እንዳለው ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

ድህነትን በእርዳታ እስከመቼመኖሪያቸውን በሰሜን አሜሪካ - ኒው

ዮርክ ከተማ ያደረጉት የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተድላ አስፋው በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ረሀብ “Starvation in Ethiopia can be made history” በሚል ርዕስ ባለፈው ሳምንት ለንባብ ባበቁት መጣጥፋቸው ‹‹የኢትዮጵያ የደን ሀብት በአሳዛኝ ሁኔታ እየተመነጠረ

አለም ሲኒማ ሰኞ ምሽት በ2፡30 ማክሰኞ 8፡00ረቡዕ 12፡30አርብ 10፡00

ዮፍታሔ እሁድ 12 ሰዓት እሮብ 10 እና 12 ሰዓት

ነው፤ በርሃማነትን የምንቋቋመው ከአገሪቱ የህዝብ ቁጥር 85 በመቶ ያህል ድርሻ ያላቸውን ገበሬዎች ማስተባበር ስንችል ብቻ ነው›› በማለት አሁን በአገሪቱ እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒና ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ለውጭ ባለሀብቶች በማከራየት በርሀማነትን የማባባስ እርምጃ ነው ይላሉ፡፡ድሃ አገራትን ከድህነት እንዲወጡ

ከመርዳት ይልቅ የበለፀጉ አገራትን ጦርነት ካስከተለው ጉዳት እንዲያገግሙ መርዳት የበለጠ ቀላል ሆኖ ተገኝቷል የሚሉት የዘርፉ ተመራማሪዎች፡፡ የአውሮፓ አገራት ቀደም ብሎም በኢንዱስትሪው፣ በንግዱና በመጓጓዣው ዘርፍ በደንብ የተደራጁ ነበሩ። የሚያስፈልገው ኢኮኖሚያቸው እንዲያንሰራራ ማድረግ ብቻ ነው። በሌላ በኩል ግን ድሃ አገራት በውጭ እርዳታ አማካኝነት መንገዶች፣ ትምህርት ቤቶችንና ክሊኒኮችን ቢገነቡም አገራቱ የተፈጥሮ ሀብት፣ አስተማማኝና ፍትሀዊ የንግድ ሥርዓት ብሎም ምቹ የሆነ የንግድ መስመር ስለሌላቸው ሕዝቦቻቸው እስከአሁን ድረስ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ። MAKE POVERTY HISTORY የተሰኘውና

ከአለማችን ድህነት እንዲጠፋ የመስራት አላማን አንግቦ ዋና ጽህፈት ቤቱን በለንደን ያደረገው የሲቪክ ተቋም፤ የበለጸጉ አገራት ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት በአለምአቀፍ ደረጃ እንዲዘረጋ ፍቃደኛ እስካልሆኑ ድረስ ድህነትን ለማጥፋት የሚደረገው ርብርብ ፍሬ አልባ ነው ይላል፡፡

እምቢልታ ሲኒማ ማክሰኞ ማታ 2 ሰዓትሀሙስ 12 ሰዓት ቅዳሜ 8 ሰዓት እሁድ 10 ሰዓት

ኤድናሞል ሰኞ 12 ሰዓት

አጎና ቅዳሜ 8 ሰዓት እሮብ 8 ሰዓት

?ድህነት የሚወልዳቸው ችግሮች መልሰው

ለድህነት መንስኤ ስለሚሆኑና ችግሮቹም በጣም የተወሳሰቡ እንደመሆናቸው ከዚህ እሽክርክሪት መውጣት ቀላል አይደለም። እነዚህ ተንታኞች የሚያቀርቡት ምሳሌ በሽታ የድህነት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ በአንጻሩ ደግሞ ድህነትም ለበሽታ መንስኤ መሆኑን በመግለጽ በምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናት አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገታቸው ስለሚቀጭጭ ሲያድጉ የራሳቸውን ልጆች ከመንከባከብ አንስቶ እንደ ዜጋ ማበርከት የሚገባቸውን ድርሻ መወጣት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። በተጨማሪም የበለፀጉ አገራት የተረፋቸውን ምግብ በዕርዳታ ስም ወደ ድሃ አገራት ወስደው ሲያራግፉ የአገሬው ገበሬና የችርቻሮ ነጋዴ ኪሳራ ላይ ይወድቃሉ፤ ይህም ድህነትን ያባብሳል። ለድሃ አገራት ገንዘብ መለገስም ቢሆን ሌላ

አሸክርክሪት ሊፈጥር ይችላል፤ የሚሉት እነዚህ ምሁራንና የዘርፉ ተመራማሪዎች ይኸውም በእርዳታ የተገኘ ገንዘብ ለስርቆት የተጋለጠ በመሆኑ ሙስናን ይፈጥራል፣ ሙስና ደግሞ የአንድን አገር ሁለንተናዊ ህልውና ለአደጋ ያጋልጣል ከእነዚህ አደጋዎች ውስጥ አንዱ ደግሞ ድህነት መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ። የውጭ እርዳታ የተለመደውን ዒላማ የማይመታበት ዋነኛ ምክንያት የድህነት መንስኤ የሆነውን ነገር ስለማያጠፋ ነው።

የድህነት መንስኤለአስከፊ ድህነት መንስኤው አገራት፣

መንግስታትና ግለሰቦች የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ለማራመድ መሯሯጣቸው ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የበለፀጉ አገራት መሪዎች የሚመረጡት በዴሞክራያዊ መንገድ በመሆኑና መሪዎቹም የመረጣቸውን ሕዝብ ፍላጎት የማሟላት ግዴታ ስላለባቸው ድህነትን ለማስወገድ ቅድሚያ ሰጥተው እይንቀሳቀሱም። ከዚያ ይልቅ በአገራቸው ያሉ ገበሬዎች ለኪሳራ እንዳይዳረጉ ለመከላከል ሲሉ በድሃ አገራት ያሉ ገበሬዎች ምርታቸውን በበለፀጉ አገራት እንዳይሸጡ ይከለክላሉ። ከዚህም በላይ በበለፀጉት አገራት የሚገኙ ገበሬዎች ምርታቸውን በድሃ አገራት ውስጥ ካሉት ገበሬዎች ባነሰ ዋጋ በማቅረብ ተወዳዳሪ ሆነው መቀጠል እንደሚችሉ መንግስት ከፍተኛ ድጎማ ያደርግላቸዋል። በግልፅ ለማየት እንደሚችለው ለድህነት

መንስኤው ሕዝቦችና መንግስታት የየራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የመሯሯጥ ዝንባሌ ያላቸው መሆኑ ነው፤ በሌላ አባባል ችግሩን የሚፈጥሩ ሰዎች ራሳቸው ናቸው።

የማርሻል እቅድን እንደሞዴል

ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የአውሮፓ ሀገራት ክፉኛ ከመጎዳታቸውም በላይ አብዛኞቹ ዜጎቻቸው በረሃብ እንጋለጣለን የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ሶሻሊዝም በአውሮፓ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱ አሳስቦት ነበር። በመሆኑም የአሜሪካ መንግስት የእሱን መርሆዎቹ በሚቀበሉ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የኢንዱስትሪውንና የግብርናውን መስክ መልሶ ለማቋቋም ለአራት ዓመታት ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሰጠ የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ። የማርሻል እቅድ በመባል የሚታወቀው

ይህ አውሮፓን መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም ስኬታማ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ። ዩናይትድ ስቴትስ በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ በምዕራብ አውሮፓ የምታሳድረው ተፅዕኖ እየጨመረ በመምጣቱ በእነዚህ አገራት ውስጥ የተከሰተው ለሕይወት አስጊ የሆነ ድህነት ቀስ በቀስ እየተወገደ መጣ። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የማርሻል

እቅድ ስኬታማ መሆኑን ሲመለከት በመላው ዓለም የሚገኙ ድሃ አገራት በእርሻ፣ በጤና፣ በትምህርትና በትራንስፖርት ዘርፍ ዕድገት እንዲያደርጉ እርዳታ መስጠት ጀመረ። ዩናይትድ ስቴትስ ራሷ በግልፅ እንደምትናገረው ይህን እርዳታ የምትሰጠው የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ ብላ ነው። ሌሎች አገራትም እርዳታ በመስጠት በብዙ አገራት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ይሞክራሉ። ከስልሳ ዓመታት በኋላ የተደረገው ግምገማ እንደሚያሳየው ለማርሻል እቅድ ከወጣው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ መዋዕለ ንዋይ ቢፈስም የሚፈለገው ውጤት አልተገኘም። እውነት ነው፣ ቀደም ሲል ድሃ የነበሩ በተለይም በምሥራቅ እስያ የሚገኙ አንዳንድ አገራት በጣም ሀብታም መሆን ችለዋል። በሌሎች

አገራት ግን የውጭ እርዳታ፣ የሕፃናት ሞት በጣም እንዲቀንስና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆች ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ያስቻለ ቢሆንም አብዛኞቹ አሁንም ቢሆን የሚገኙት በአስከፊ ድህነት ውስጥ ነው። በተድላ አስፋው እምነት የአገሪቱን የጀርባ

አጥንት የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን ችላ ብለንና በስሜታዊነት ታውረን እጅግ የናጠጡ የውጭ ኢንቨስተሮችን ፍላጎት ብቻ በማሟላት እስከተጠመድን ድረስ በየአመቱ ምጽዋት ከመጠየቅ አንገላገልም ሲሉ ስጋታቸውን ያጋራሉ፡፡

/ኤሊያስ ገብሩ ለዚህ ፊቸር አስተዋጽኦ አበርክቷል/

ለአስከፊ ድህነት መንስኤው አገራት፣ መንግስታትና

ግለሰቦች የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ለማራመድ

መሯሯጣቸው ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የበለፀጉ አገራት

መሪዎች የሚመረጡት በዴሞክራያዊ መንገድ

በመሆኑና መሪዎቹም የመረጣቸውን ሕዝብ ፍላጎት

የማሟላት ግዴታ ስላለባቸው ድህነትን ለማስወገድ

ቅድሚያ ሰጥተው እይንቀሳቀሱም

Page 6: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 20036 የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

ኢሳያስ ሜንዲቪች በርሊን የተወለደው ሪጋ፣ ላትቪያ ውስጥ ነው። ጣውላ ነጋዴ ባለፀጋ የነበረው አባቱ ጀርመኖች በ1915 ሪጋን ሲወርሩ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ራሺያ ተሰደደ። በኋላም ይህ ቤተሰብ በ1920 ወደ ኢንግላንድ በመሄድ በለንደን በቋሚነት መኖር ይጀምራል። ያም ሆኖ ግን ቤተሰቡ ወጣቱን በርሊን ወደግል ትምህርት ቤት ለመስደድ የሚያስችል በቂ ሀብት አትርፏል። በ1928 ኮርፖስ ክሪስቲ ኮሌጅ የገባ ሲሆን በ1931 በመጀመሪያ የሮማን እና የግሪክን ታሪክ እና ፍልስፍና አጥንቷል፤ እንዲሁም ፍልስፍና፣ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚክስ በ1932 ተምሯል።

በኒው ኮሌጅ ጥያቄ ቀርቦለት ሌኽቸረር የሆነው በርሊን፣ በ1957 በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ፅንሰ-ሀሳብ (በሄንሪ ቺችል የተሰየመውን) የቺችል ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በማግኘት የጂ.ዲ.ኤች ኮል (የመጀመሪያው የቺችል ፕሮፌሰር) ቀጥሎ ሁለተኛው መሆን ችሏል፤ በ1966 የአዲሱ የድህረ-ምረቃ ተቋም፣ የዎልፍሰን ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ሆኗል፤ በ1971 ጡረታ እስከሚመጣ ድረስም ይህንን ቦታ እንደያዘ ቆይቷል። አብዛኛዎቹ የበርሊን ፅሁፎች፣ በእርሱ ጊዜ እንደነበረው ማይክል ኦክሾት፣ በውስን ርዕሰ-ጉዳይ ላይ የሚያውጠነጥኑ ምጥን ጥናቶች (essay) ነበሩ፤ ከ1978 እስከ 2000 ባሉት ዓመታት ውስጥም በዛ ባሉ ጥራዞች ተሰብስበዋል። በርሊን የክብር ማዕረግ በተሰጠው ጊዜ ወዳጁ ማውሪስ ቦውራ ስለእሱ እንዲህ ብሎ ነበር፡-

‹‹ምንም እንኳን እንደ ሶቅራጠስ ማሳተም ላይ እምብዛም ቢሆንም በከፍተኛ መጠን የሚያስብ እና የሚናገር ሰው ሲሆን በዘመናችን እጅግ ግዙፍ ተፅዕኖ ማሳደር የቻለ ነበር።››

በፖለቲካ እሳቤ ተማሪዎች ዘንድ በይበልጥ የሚታወቅለት ሥራው በቺችል ፕሮፌሰርነቱ መጀመሪያ ሰሞን የሰጠው “Two Concepts of Liberty” የተሰኘ ሌክቸሩ ነው። (ስለ ሁለቱ የነፃነት እሳቤዎች፣ ማለትም “ፖዘቲቭ” እና “ኔጌቲቭ” ነፃነት ስለሚባሉት የተነተነበት ነበር።) ይህ ታዋቂ ሥራው ብዙ ጊዜ የሚጠቀስ ሲሆን በ1969 ‹‹Frour Essays on Liberty” በተሰኘ መፅሐፉ ውስጥም ተጠቃሎ ታትሟል።

የበርሊን የመጀመሪያ ፍላገት ፍልስፍና ላይ ነበር፤ በተለይም በሳይንስ ፍልስፍና ላይ። ልክ እንደ ሰር ካርል ፓፐር ሁሉ እርሱም “ሎጂካል ፖዘቲቪዝም” ላይ ትችት የሚያቀርብ ነበር። (ሎጂካል ፖዘቲቪዝም፡- የዲበ አካል (Metaphysics) ፍልስፍናን በመቃወም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መረጋገጥ በሚችሉ ወይም በአመክኒያ ወይም ሂሳባው በሆነ ስሌት ማረጋገጫ ሊሰጣቸው በሚችሉ ነገሮች ላይ የሚያተኩር የፍልስፍና ዘርፍ ነው።) ለብዙ ዓይነት ድርሰ-ፍልስፍና ገለፃዎች እውነትነትና ትርጓሜ ማረጋገጫ (verification) ብቻውን በቂ መስፈርት እንዳልሆነ በርሊን ያምናል። ከጦርነቱ በኋላ የራሺያዊው ለውጥ ናፋቂ የአሌክሳንደር ሄርዘን ተፅዕኖ ያደረበት በርሊን ፍላጎት እና ትኩረቱን ከፍልስፍና ወደ የእሳቤዎች ታሪክ ሊለውጥ ችሏል። (ቀድሞውኑ በ1939 የካርል ማርክስ ህይወትን አስመልክቶ

ጣልቃ-ገብነት ሲቀንስ ነፃነት ይጨምራልሰር ኢሳያስ በርሊን /1909-97/

“Karl Marx: His Life and Environment” በማለት መፅሐፍ አሳትሟል)።

በተለይም ማኪያቬሊን፣ ቪኮን እና ሄርደርን በማጥናት አሀዳዊ የሆነና በግልፅ የሚጠቀስ የሰብዓዊ ጥሩነት ምልከታ የለም፣ ሊኖርም አይችልም የሚል የልብወለዳዊነት (Romanticism)፣ የፀረ-አብርሆት (anti-Enlightenment) ምልከታን ለመያዝ በቅቷል። ከእርሱ ጋር ብዙውን ጊዜ ተያይዞ የሚነሳው እምነት ይህ ነው። እንደ በርሊን አቋም፣ እየኖርን ያለነው ቁጥራቸው በግልፅ የማይታወቅ እሴቶች በሚገኙባት ዓለም ነው። እሴቶች ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ መመዘኛ የማይለኩና እርስ በርሳቸውም የማይጣጣሙ መሆናቸውን እንደ እውነታ መቀበል አለብን።

‹‹እኔ እንደማምነው፣ የሰው ልጅ ግቦች ብዙ ከሆኑና በመርህ ደረጃ የእርስ በርስ መጣጣሙ በሁሉም ዘንድ ካልሆነ፣ ግጭት እና ስቃይ የመከሰታቸው እድል ከግላዊም ሆነ ከማህበራዊ ሰብዓዊ ህይወት ውስጥ መቼም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ሊወገድ አይችልም። ፍፁም ከሆኑ ጥያቄዎች መካከል አንዱን የመምረጥ አስፈጊነት ሊወገድ የማይችል የሰብዓዊ ሁኔታ ባህሪይ ነው።›› - (Two Concepts of Liberty)

ይህ በግለሰብ ደረጃ፣ በባህል ደረጃ ወይም በሀገር ደረጃ እውነትነት አለው። የትኛውም የጥሩ ህይወት ዓይነት ከሌላው የተሻለ መሆኑን ማሳየት የሚችል አንዳችም የምክንያት ወይም የአመክኒዮ መስፈርት (ማረጋገጫ) የለም፤ ህይወት ምክንያት ሊገልፀው የሚችል አንድ ነጠላ ግብ የለውም። እንደሞራላዊ ፍጡራን የምናደርጋቸው ምርጫዎች ብዙውን ገዜ ከባድ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አስጨናቂዎች ናቸው። ይህም ምናልባት ነፃነት እና እኩልነት፣ ፍትህ እና ምህረት፣ እንዲሁም የመሳሰሉት ሁለቱ በአንድነት ሊኖሩ ስለማይችሉ ይሆናል። ሞራላዊ እምነቶቻችን በዋናነት ግለሰባዊና ኢ-ምክንያታዊ ናቸው። እንዲህ በመሆናቸው ሳቢያም ምንም ያህል በውስጣችን ስር የሰደዱ እምነቶች ቢሆኑም እንኳን እነዚህን እምነቶች በሌሎች ላይ በግዴታ ብንጭን መቼም ተቀባይነት ሊኖረን አይችልም። የትኛውም አስተምህሮ ወይም ርዕዮት ለሰው ዘር ችግሮች ሁሉን አቅፍ የሆነ መፍትሔ ያቀርባል የሚል እምነት ተቃርኗዊ ወይም የተሳሳተ ሲሆን፣ እንዲህ ባሉ መፍትሔዎች ስም ብዙ ጊዜ በሚፈፀሙት ነገሮች ሳቢያ ጉዳት አምጪ እምነት ነው።

የእነዚህ ትዝብቶች ተግባራዊ ድምዳሜ በርሊን ‹‹Two concepts of Liberty›› ላይ የሚያቀነቅነው የብዝሃነት ዓይነት ነው፡፡ በዚህ ፅሁፉ ነው ታዋቂውን የ‹ፖዘቲቭ› እና ‹ኔጌቲቭ› ነፃነትን ንፅፅሮሽ ያቀረበው (በርግጥ ፖዘቲቭ (Positive) እና ኔጌቲቭ (Negative) ነፃነት የተሰኙት ቃላት በቀዳሚነት የተቀመሩት በቲ.ኤች ግሪን እንጂ በበርሊን አልነበረም)። ፖዘቲቭ ነፃነት ግለ-ብቁነትን (Self-mastery) ወይም ግሉ-ምሉዕነትን (Self-realisation) ማሳካት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ ግለ-ምሉዕነት ማለታችን የግለሰቦች ከፍተኛው የብቃታችን ጥግ ነው ብለው የሚረዱትን በፈቃዳቸው ሆነው መገኘት ማለታችን ከሆነ

ግለ-ምሉዕነት በራሱ ተመራጩ መልካም ነገር ነው።

ይሁንና ግን ችግሩ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታሪክ በግላጭ የሚያስቀመጠው ነው፡- ይኸውም ‹‹ግለ-ምሉዕነት›› አንድ እውነተኛ ግብ እንዳለና ያም ‹እውነተኛ› ነፃነት የሚመጣው የሀገሪቱ ሕዝባዊ ጥረት፣ እንዲያውም የአጠቃላዩ የሰው ፍጥረት ጥረት ስኬታማነቱ ላይ የተጋ በሆነ ጊዜ ነው ብለው በሚያምኑ ወገኖች በተቀመረ አገላለፅና ብዙውን ገዜ በኃይል በተጫነ መልኩ ሊተረጎም የመቻሉ ሁኔታ ነው። እንዲህ ዓይነት ግብ አለ የሚለው እምነት መጠነ-ሰፊ ስቃይን ሲያፈራ እንደቆየ በርሊን ያስባል። በተጠቃሽም ‹ላዕላይ› ወይ

መንፈሳዊ ማንነት እና ‹ዝቅተኛ› ወይ አካላዊ (ተጨባጭ) ማንነት አለን የሚለውን (ከእንግሊዛዊው ሀሳባዊ ፈላስፋ በርናርድ ቦሳንኪዩት ጋር የሚገናኘውን) እሳቤ የሚያጣጥል ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘም የአንድ ሰውን ተጨባጭ ማንነት በማስገደድ (በማስጨነቅ) ብቻ ላዕላይ ማንነት ነፃ ሊወጣ ይችላል የሚለውን ጥቆማም አይቀበልም።

በ ር ሊ ን እንደሚያስበው፣ ትክክለኛ ነፃነት በዋናነት የሞራላዊ ምርጫን ግላዊ እና ኢ-ምክንያታዊ ባህሪይን ከግምት ሊያስገባ ይገባል። ‹ኔጌቲቭ› ነፃነት ሊሆን ይገባል፡- ይኼውም የሌሎች ክልከላ ወይም ጣልቃ ገብነት ሳይኖር

የራስን ምርጫዎች የማድረግ እና የመከተል ነፃነት። ‹‹ከዚህ አንፃር ነፃ መሆን ስል ሌሎች ጣልቃ የማይገቡበት ማለቴ ነው። ጣልቃ የማይገባብኝ ጉዳይ እየሰፋ በመጣ ቁጥር ነፃነቴም እንደዚሁ እየሰፋ ይመጣል።››

እርሱ በ1997 ከሞተ በኋላ ከተፃፉለት መወድሶች አንፃር ሰር ኢሳያስ በርሊን (ሰር - Sir - የሚለውን ክብር ያገኘው በ1957 ነው) በሚያውቁት ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እና አክብሮትን ያተረፈ እንደነበር ግልፅ ነው። ለራሱ እምብዛም ትኩረት የማይሰጠው በርሊን፣ እራሱን ለሰብዓዊ እሳቤዎች ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከ አድርጎ አይመለከት ነበር። የእርሱ እሳቤ፣ ልክ እንደ ካርል ፓፐር እሳቤ፣ በይበልጥ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ጦርነቶችን በቀጥታ የታዘበ ሰው እሳቤ ነው። ይሁንና ግን ሥራው አንፃራዊ በሆነ መልኩ አነስተኛ ተቀባይነት ኖሮት ቆይቷል፤ ይህም በከፊል በትኩረቱ ስፋት ምክንያት፣ በከፊል ደግሞ አብዛኛው ሥራው በመፅሐፍ መልኩ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ በአጫጭር ትንታኔ (essay) መልኩ በመሆኑ ምክንያት፣ እንዲሁም በከፊል ከማንኛውም ዓይነት እራሱን የቻለ አስተምህሮ ጋር እራሱን ላለማዛመድ በነበረው ቁርጠኝነት ምክንያት ነው። የበርሊን ኤዲተር እና ከሞተ በኋላ የሙት መወድሱን የፃፈው ሄንሪ ሀርዲ፣ በርሊንን የገለፀበት ሁኔታ የጠራና ፍትሃዊ ነው፡-

‹‹[ፖዚቲቭ እና ኔጌቲቭ ነፃነትን አስመልክቶ] የእርሱ ምልከታ እስካሁን ድረስ ለነፃነት እሳቤ እጅግ አስፈላጊ ማጣቀሻ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ በተከታይ ጥልቅ ውይይቶች ዘንድም የተሰራጨ ነው፤ ይሁንና ግን ምናልባትም በከፊል እሳቤዎቹ የማንነቱን ጥንካሬ የማያሳዩ በመሆናቸውና ሆን ተብሎም ውስንነት በሌለው የአወቃቀር ባህሪያቸው ምክንያት፣ እንዲሁም ለችግሮች ማንኛውንም ዓይነት መፍትሔ ማቅረብ ባለመፍቀዱ ምክንያት ተከታዮችን አላፈራም ወይም እራሱን የቻለ እሳቤያዊ ፈርጅ አልገነባም።›› - (ኖቬምበር 7 ቀን 1991 በታተመው “Independent” ጋዜጣ ላይ እንደሰፈረው።)

ሞራላዊ እምነቶቻችን በዋናነት

ግለሰባዊና ኢ-ምክንያታዊ ናቸው።

እንዲህ በመሆናቸው ሳቢያም ምንም

ያህል በውስጣችን ስር የሰደዱ እምነቶች

ቢሆኑም እንኳን እነዚህን እምነቶች

በሌሎች ላይ በግዴታ ብንጭን መቼም

ተቀባይነት ሊኖረን አይችልም።

እድሜሽ፣ፍቅርሽ፣

ደስታሽ ይብዛልን!

ወላጆችሽ ሰለሞን

እና ፍሬህይወት

የእኛ አርሴማእንኳን ደህና መጣሽልን

Page 7: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

አንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው›› ሲል ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

እነሆ እኔ ሰሞነኛ አገልጋዮ የሳምንቱን ምን ተባለዎች ሰብስቤ ጎንበስ ቀና እያልኩኝ እገኛለሁ።

እናም ይኸው ከጥቂት ዓመታት በፊት የተተኮሰ ጥይት ሽል ለማለት ጎንበስ ቀና የሚባልባት ሱዳን እንኳን እንደ አሜባ ለሁለት በመከፈል ሰላሟን ማዝለቅ ተያይዛዋለች። እንኳን ደስ ያላችሁ ማለቱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም። እኔ አገልጋይዎ ይህንን ለማለት የቻልኩት ጉዳዩን በብዙ መንገድ ተመልክቼው ነው። እንዲያውም ልዘርዝርልዎት፡-

አ ን ደ ኛ ው ና የመጀመሪያው መለያየቱ የሁለቱም ሱዳኖች ስምምነት ያደረበት ከሆነ ዘንዳ መስማማትን የለመደ አፍሪካዊ ሕዝብ በቅርባችን ተገኝቷልና እንኳን ደስ ያለን ያሰኛል። በሌላ በኩል ደግሞ እሳተ ጎመራ ከኋላው እንደሚከተለው የዱር አራዊት ቀን በቀን ያለማቋረጥ ወደ ጁባ እየተሳደደ የሚገኘው ሕዝባችን እዚያው ባለበት ጁባ ከተማ ሆኖ፣ አንዳችም ሳይንቀሳቀስ ተኝቶ ሲነሳ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ተጉዞ እራሱን አግኝቶታል፤ ምስኪኑን ስደተኛ ሕዝችንን በዚህ ተዓምረኛ ድርጊቱ እንኳን ደስ ያለህ ልንለው ይገባል።

ዋ ና ው ን ና የመጨረሻውን ልንገራችሁ። እንግዲህ ሰሜን እና ደቡብ ሱዳን በሰላም ቢለያዩም የዚያች የነዳጅ ባለጠጋዋ ግዛት፣ የአብዬ ነገር ገና አልተቋጨም። እናልዎ ተልዕኮው የዩ.ኤን. ቢሆንም ይቺን ግዛት ይቆጣጠር ዘንድ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንደሚሄድ ሲነገር ሰንብቷል። ታዲያ ለዚህ ከፍተኛ የሱዳን የነዳጅ ሀብት ከሰሜን ሱዳንም ሆነ ከደቡቡ እኛው ቀረብን አይሉኝም? ታዲያ ይኼ እንኳን ደስ አለን አያሰኝም? ያወጣነው ነዳጅ ባይኖረንም፣ የነዳጁ ዋጋ በወር በወር እየጨመረ መድረሻ ቢያሳጣንም የሰው ነዳጅ እንደራሳችን አድርገን ልንጠብቅ ነውና እንኳን ደስ አለን።

ለማንኛው ጌታዬ እንዴት ሰንብተውልኛል፤ እኔማ ባካኝ አገልጋዮ ይኸው ከወዲያ ወዲህ እያልኩ አለሁ። እንዲያው የዚህን ሀገር ፖለቲካ ነገር የጠየቁኝ እንደሆን ‹‹ፖለቲካው ተጧጡፏል›› እሎታለሁ። ከአንድ ፓርቲ ወደሌላ ፓርቲ የሚደረገው ፍልሰት እንደቀጠለ ከመሆኑ በተጨማሪ በ2002 የኢህአዴግ ‹‹ታላቅ ባለውለታ›› እየተባሉ ሲነገርላቸው የነበሩ ትልቅ ሰው፣ ለዚያውም በ97 አደባባዮችን ያንቀጠቀጠውን አንድ ግዙፍ የፓርቲዎች ጥምረት ስያሜ ለብሰው የነበሩ፣ ኧረ እንዲያውም የ2002 ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሥነ-ምግባር ተሽቀዳድመው የፈረሙ ትልቅ ሰው ሀገር ጥለው ኮበለሉ መባሉ ተሰምቷል። የእኚህን ሰው ጉዳይ የሰማ አንድ ወዳጄ ‹‹ፓርቲያቸውን ጥለው ኮበለሉ በሉ እንጂ፣ ሀገር ጥለው ከኮበለሉማ ዘመን አለፈ›› ሲል ወርፏቸዋል።

እናልዎ እኚህ ሰው መኮብለላቸውን ከአንድ ጋዜጣ አንብቤልዎት ያኔ በምርጫው ሰሞን ያደረጉት የምርጫ ክርክር ነበር ትዝ ያለኝ። ወይ የኔ ነገር ማን እንደሆኑም እስካሁን አልነገርኩዎትም አይደል? ሰውዬውማ አቶ አየለ ጫሚሶ ናቸው። (ታዲያ ማን ሊሆኑ ይችላሉ? ካሉኝ የተቀሩት የፓርቲው አባላት ይቀየሙናልና አለማለቱ ይሻላል)። እናም ያኔ በምርጫ

ክርክሩ ጊዜ ‹‹እውነተኛው ቅንጅት እኛ ነን፤ ኢህአዴግ የሚፈራው እኛን ነው፤…›› የመሳሰሉት አባባሎቻቸውን ሳስታውስ በወቅቱ ያደመጧቸው ወዳጆቼ ‹‹ታዲያ ኢህአዴግ ማንን ይፍራ? ኢንጂነሩም እጅ ሰጥተዋል፤ ብርቱካንም ታስራለች፤ የሸፈቱትም ሸፍተዋል፤…›› ማለታቸውንም ደርቤ አስታውሳለሁ።

አቶ አየለ ጫሚሶ ከሀገር ወጡ የተባለው ብቻቸውን አይደለም። ለፓርቲያቸው የመጣውን የጀርመን ሀገር ሥልጠና የፓርቲው አባል ላልሆኑ አምስት ሰዎች አሳልፈው በመስጠታቸውንና በምትኩም ከያንዳንዳቸው 135 ሺህ ብር ተዋውለው ቅድመ ክፍያውን 50X5 = 250 ሺህ ብርንም አብረው ለስደት ዳርገዋል ተብሏል። ይህንን የአቶ አየለ ጫሚሶን ክህደት የዘገበውን ዜና ያናበበኝ አንድ ወዳጄ ግን ዜናውን ሊያምነው አልተቻለውም። ‹‹ኢህአዴግ ዝም ብሎ አይለቃቸውም፤ ቢያንስ በ250 ሺህ ብሩ የአባይ ቦንድ አስገዝቷቸዋል›› በማለት ሲከራከረኝ ቆይቷል።

በነገራችን ላይ ፍልሰቱ ወደ ውጭ ሀገር ብቻ አይደለም ብዬዎት አልነበር? ከኢንጂነሩ መኢአድ ወደ አንድነት የሚደረግ የሀገር ውስጥ ፍልሰት መኖሩንም ሰምተናል። በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን ክፍል ሕዝባችን ለከብቱ የሚያስግጠው ሳር አጥቶ፣ ለራሱ የሚጎነጨው ውሃ ጠፍቶ ስደት ገብቷል። እዚህ በከተማችን ደግሞ ከፓርቲ ፓርቲ የሚሰደዱ ተበራክተዋል። እንዴት ነው ነገሩ? ስደት እጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ ማለት ነው? እነሆ ፈጣሪ የተራቡ ወገኖቻችንን ይታደግልን፣ ከስደትም ይመልሳቸው፤ የፓርቲ ስደተኞቹን ግን አሁን በሚታየን እውነታ ‹ከጋን ጋን ቢገለብጡት› ነውና እንደፈቀዳቸው ብለን እንተወዋለን።

እስኪ ደግሞ ወደ አኗኗሪዎቼ ልውሰድዎ። ዛሬ ርዕስ ያደረኩት የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ነገር በዚያች ለአምስት በምንኖርባት ቤታችን ውስጥ የተነሳ ነው። የሰሞኑ ብርድ አንገብግቦኝ ወደ ቤታችን ሳመራ የሴቶች ሊግ አባል የሆነችው የቤታችን ባልደረባ እሳት አያይዛ እንደምትጠብቀኝ እርግጠኛ ነበርኩኝ። (እንዴት እርግጠኛ ሆንክ እንዳይሉኝ፤ እነሱ ‹‹በእሳት ተፈትነን እዚህ ደረስን›› እንጂ ‹‹እሳት አያያዦች ነን›› አላሉም።) ብቻ እርግጠኝነቴ ከልምድ የመነጨ እንደሆነ ይታወቅልኝ። እናልዎ ልክ ስደርስ የሴቶች ሊግ ባልደረባችን ምድጃ ከስሯ አስቀምጣለች፤ ሊሞቃት ሲገባ ግን ጭራሹኑ ከኔ ብሳ ያንቀጠቅጣታል። የባልደረባችን መንቀጥቀጥ የንዴት እንደሆነ ስለገባኝ ምን ሆና ነው ብዬ ሌሎቹን ጠየኳቸው። ከነሱ ቀድማ፣ ‹‹እያንዳንድሽ የሰውዬው ቀረብ ቀረብ ማለት ሊያስደስትሽ አይገባም፤ 17 ዓመት ሙሉ ጫንቃችሁ ላይ ተቀምጦ እንኳን ምንም አላመጣላችሁም›› አለች። ዜናውን ረፋድ ላይ ሰምቼ ስለበር ሴቲቱ ስለማን እንደምታወራ ገብቶኛል። ደቡብ ሱዳኖች ገና ሀገር ከመሆናቸው ለጓድ መንግስቱ መኖሪያ ቤት እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ይኼን ጊዜ የደርግ ሥርዓት ናፋቂው የኑሮ በልረባችን፣ ‹‹ምነው? ስጋት ገባችሁ እንዴ?›› ሲል አንጓጠጠባት። በመሀል ከኢህአዴግ አፈንግጦ የወጣው አኗኗሪያችን ደግሞ ‹‹ይኼን ጊዜ ዝምባቡዌ እርቋችሁ ወደ ደቡብ

ሱዳን እንዲመጣ የምታሴሩት እናንተው ትሆናላችሁ፤ መቼም ለአዲሲቱ ሀገር ከናንተ የቀረበ የለም›› በማለት ሸነቆጣት። በዚህን ሰዓት ያየውን የሚነበብ ነገር ሁሉ የመመንተፍ ባህሪይ ያለው የ‹‹ያ ትውልድ›› አፍቃሪው የቤታችን አባል ይዤው የገባሁትን መፅሐፍ ተቀብሎኝ እያገላበጠ ነበር። ከዚያም ድንገት የገነፈለ ሳቅ እየሳቀ፣ ‹‹እንዴ? ገነት ዘውዴ ማልቀስ ይችላሉ እንዴ?›› አይል መሰልዎት።

ይዤው የገባሁት መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ የበቃው ‹‹ዳንዲ የነጋሶ መንገድ›› የተሰኘው ሲሆን በዳንኤል ተፈራ ጀ. የተፃፈ ነው። በአጠቃላይ ፀሐፊው ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ያደረገው ዘርፈ ብዙ ቃለ-ምልልስ ሲሆን ከወ/ሮ ገነት ማልቀስ ጋር የተያያዘው ሀሳብም በመፅሐፉ ውስጥ የተጠቀሰ ነው። (በነገራችን ላይ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ገነት ዘውዴ፣ አስራት ጣሴ እና እኔ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጣም የምንግባባ ጓደኛሞች ነበርን” ማለታቸው በመፅሐፉ ውስጥ በግርጌ ማስታወሻነት ሰፍሯል።)

መቼም ጌታዬ እኔ ሰሞነኛ አልጋይዎ በአንድ ወቀት ዶ/ር ነጋሶ ጠ/ሚኒስትር መለስን ‹‹አሁንስ መንግስቱን መሰልከኝ›› ማታቸውን ለእርሶ አልነግሮትም፤ ደጋግመው ሰምተውታልና። ዛሬ የምነግሮት ለእኔም አዲስ የሆነብኝን ነገር ነው - የወ/ሮ ገነት ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ። እናም የ‹‹ያ ትውልድ›› አፍቃሪው አኗኗሪያችን እስኪፈርስ የሳቀው ነጋሶ በመፅሐፉ ውስጥ ያሉትን ይህኛውን ክፍል አንብቦ ነበር፡-

‹‹መለስም ‘ጃኬታቸውን አስወልቀን ራቁታቸውን አባረርናቸው’ እያለ ሲፎክር ያ የመንግስቱ ፉከራ ትውስ ብሎኝ እጄን አነሳሁና ‹‹አስተያየት›› አልኩኝ። ‘ይቅርታ አነጋገርህ መንግስቱ ኃ/ማርያምን አስታወሰኝ። መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ’ አልኩት። ቤቱ በድንጋጤ ተናወፀ። በተለይ ከጎኔ ተቀምጣ የነበረችው ገነት ዘውዴ ‘እንዴት ከመንግስቱ ጋር ታወዳድረዋለህ?’ ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።››

ታዲያ ይህን ጊዜ ‹‹ገነት ዘውዴ ማልቀስ ይችላሉ እንዴ?›› በማለት የማላገጥ ሳቅ የሳቀው ጓደኛችን ከሴት ሊግ አባሊቱ ባልደረባችን የሚያናውጥ ግልምጫና ቁጣ ወረደበት። ‹‹ይኼ ምን ያስቃል፤ የተከበሩ አምባሳደር ማልቀስ አይችሉም እያልክ ነው?›› - የሴቲ ልግ አባሊቱ ጥያቄ ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጠው ግን የደርግ ሥርዓት ናፋቂና አፍቃሪው አኗኗሪያችን ነበር። እንዲህም አላት፣ ‹‹እኛ የምናቀው ተማሪዎችን እንዴት እንደሚያስለቅሱ እንጂ እርሳቸው ሲያለቅሱ አይተንም ሰምተንም አናውቅም።››

ሰ ሞ ነ ኛ

“ገነት ዘውዴ ማልቀስ ይችላሉ እንዴ?”ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን ያነበቡ

ነገ በ8 በ10 በ12 በመላው ኢትዮጵያ ይመረቃል

(በነገራችን ላይ የእኔ ጨዋነት ሆኖ ነው እንጂ ከሴት ሊግ አባሏ የቤታችን ባልደረባ በስተቀር ሁሉም ስለ ወ/ሮ ገነት ሲናገሩ በአንቱታ ሳይሆን በአንቺታ ነበር።) እናም ክርክሩ ጦፈልዎ። ሴቲቱ ስሯ የነበረውን ምድጃ እንደማሽቀንጠር አድርጋዋለች፤ ‹‹ድሮስ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ከአምባገነኑ ሰው-በላ ልታወዳድሯቸው ትፈልጋላችሁ እንዴ?›› ስትል እያጉረጠረጠች ጠየቀቻቸው። እኔ በመሀል ቤት ብርዱን አልቻልኩትምና የተሽቀነጠረውን ምድጃ ስቤ ስሬ ከትቼዋለሁ።

የደርግ ሥርዓት ናፋቂው ጓደኛችን ‹‹አንድ ያልገባኝ ነገር አለ?›› ሲል እጁን አወጣ። ሴቲቱ እድል ባትሰጠውም ጥያቄውን ቀጠለ፤ ‹‹ወ/ሮ ገነት እንደዚያ ያለቀሱት ጋሽ ነጋሶ ጠ/ሚኒስትሩን ከጓድ መንግስቱ አሳንሰዋቸው በቁጭት ነው፣ ወይንስ አስበልጠዋቸው በደስታ ነው?››

ይህን ጊዜ ከሴቲቱ መላ አካላት የገነፈለውን ንዴት በቦንድ

ግዢ የተገነባ ግድብ እንጂ ማንም ሊያቆመው የሚችል አልነበረም። ሆኖም ገላግሌያችን፣ አከራያችን ወ/ሮ ጦቢያ በእኛና በእርሳቸው ቤት መሀል ባለው በኮምፖርሳቶ የተሸፈነ በር ላይ የተሰቀሉትን ሳፋና ድስቶች በማማሰያ አንጓጓቸው። የሴቲቱንም ንዴት ያለቦንድ ገደቡት። እኛ ደግሞ አትንጫጩብኝ ብለው ሊቆጡን መስሎን ደንብረናል፤ እሳቸው ግን ሀሳብ ሊጨምሩ ኖሯል። ‹‹እስኪ ከጀገናችሁ መስፈርት እያወጣችሁ አወዳድሯቸው፤ የሀገር ፍቅር፣ የሕዝብ ክብር፣ የመሳሰሉትን እያነሳችሁ < ወይም > ወይም = እያላችሁ ነጥብ ስጧቸው›› በማለት ከባድ ፈተና ሰጡን።

እናም ጌታዬ እኛ ወደፈተና አታግባን የምንል የጥንት ባልንጀሮች ነንና የወ/ሮ ጦቢያን ፈተና ትተን የ‹‹ያ ትውልድ›› አፍቃሪ አኗኗሪያችን ያመጣውን በቆሎ እሸት በሴት ሊግ አባሊቱ ፍም ጠብሰን እየቆረጠምን አደርን። እርሶም አዳሮት ሰላም ይሁንልኝ።

ሰላምዎት ይብዛልኝ!

‹ይኼ ምን ያስቃል፤ የተከበሩ አምባሳደር ማልቀስ አይችሉም እያልክ ነው?›› - የሴቲ

ልግ አባሊቱ ጥያቄ ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጠው ግን የደርግ ሥርዓት ናፋቂና

አፍቃሪው አኗኗሪያችን ነበር። እንዲህም አላት፣ ‹‹እኛ የምናቀው ተማሪዎችን እንዴት

እንደሚያስለቅሱ እንጂ እርሳቸው ሲያለቅሱ አይተንም ሰምተንም አናውቅም።››

Page 8: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 20038

አትሳቅስ በሉኝ፣ግድ የለም ከልክሉኝ።

የፊቴን ፀዳል፣አጠልሹት በከሰል።የግንባሬን ቆዳ፣ስፉት በመደዳ።

ጨጓራ አስመስሉት ግድ የለም፣አትጫወት በሉኝ ዘፈኔን ንጠቁኝ

ግድየለም።ብቻ አታልቅስ አትበሉኝ፣

አትጩህ አትበሉኝ።(ደበበ ሰይፉ)

መነሻ አንድ አፄ ቴዎድሮስ በዚያ

ዘመን ያሉ ነገስታት ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ እርሳቸው ቤተክርስቲያን ማሰራት ፈለጉ።

“ለአንድ ቤተክርስቲያን አምስት ልዑክ በቂ ነው፤ ከዚያ በላይ አቴና ወጊ ወገቡን ሰባቂ ሁሉ አርሶ ይብላ” ብለው ያወጁት ንጉስ ቴዎድሮስ በአንድ በኩል መጠኑ ብዙም ከፍ ያላለ በሌላ በኩል ደግሞ በውበቱ ይህ ቀረው የማይባል ቤተክርስቲያን ለማሰራት ነበር የፈለጉት።

ታዲያ ይህንን የመሰለውን ሥራ ለመስራት ማሰብና ማማከር አስፈላጊ በመሆኑ ሊቃውንቱን ሰብስበው ሐሳባቸወን አካፈሏቸው። ከሊቃውንቱ ጋር ከመከሩበት ነገር ሁሉ አፄ ቴዎድሮስን የማረከው ሐሳብ እንዲህ የሚለው ነው፡- ‹‹ለዚህም ቤተክርስቲያን ሥራ አንድ መቶ ሃምሳ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ። ሃምሳ ሰሪ፣ ሃምሳ ደንጓሪ ሃምሳ አነዋሪ። ሃምሳው ሰሪ ለቤተክርስቲያኑ የሚሆነውን እንጨቱን፣ ድንጋዩን፣ ጭቃውን፣ አቴናውን፣ አጎበሩን፣ ሳንቃውን፣ መስኮቱን፣ ሳር ክዳኑን እያዘጋጁ ያቀርባሉ። ሃምሳው ደንጓሪ የቀረበላቸውን እየተቀበሉ በመልክ በመልኩ እያስቀመጡ ውበቱንና

… በዚህ ሰዓት የአክሱም ሐውልት በድጋሚ ተሰርቆ በአጠገቡ ቢያልፍ እንኳን ጮሆ አሊያም ተደባድቦ ዝርፊያውን የሚያጋልጥ አይመስልም። እጅግ ደንዝዟል፤ ፈዟል። ብቻውን ቀርቶ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች መሐል ቢቀመጥ እንኳን ፍፁም የማይለቅ የመፍዘዝ ባህርይ አካብቷል።

ይህ ፀባዩ ከጊዜ በኋላ ‘ተፈፀመብኝ’ የሚለውን ደባ ተከትሎ የመጣ ነው። ድንገቴ ከተጠናወተው ፀባይ አስቀድሞ የነበረውን የመኖር አቋም የሚያውቁ የቅርብ ወዳጆቹ፣ የጓደኛቸው ሕይወት መመሰቃቀል አሳስቧቸዋል። ወደ መጀመሪያ ሕይወቱ ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ውጤት ከማምጣት ይልቅ እንደ 1953ቱ የታህሳስ ግርግር ከሽፏል።

ግለሰቡ ሰሞኑን የሚያሳየው አንድ እንግዳ አኳኋን፣ በደል የፈፀሙበትን ሰዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ ያህል አስፈርቷቸዋል። ‘ሳይቀድመን እንቅደመው’ የሚል አቋም ይዘው ቢንቀሳቀሱም፣ ወታደራዊ በሚመስለው ኮስታራ አቋሙ እንደ ንጉሰ ነገስቱ ገልብጧቸው ለምሳ ሲያስቡት ቁርስ አደረጋቸው።

ሆኖም የወሰደባቸውን እርምጃ ከተበላሸው ሕይወቱ ጋር ሲመዝነው እርምጃው ቀልሎ ስለታየው፣ ሌላ አፀፋዊ ምለሽ ለመስጠት ሰይፍ ይዞ ተነሳ። ወደ አሳዳጆቹ ከማምራቱ በፊት ከዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላዕክት ወደ አንዱ ‘የምሄድበትን አሳካልኝ’ ሲል ልመናውን አቀረበ።

“ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ የሚለውን አልሰማህምን?” የሚል ምላሽ ከመልዓኩ ወደ ግለሰቡ ተላከ።

ኮሜንተሪ

“ታዲያ አንተ ለምን ሰይፍ ይዘህ ትዞራለህ?” በማለት መሰረታዊ ጥያቄ ለማቅረብ ባለመድፈሩ፣ የመልዓኩን ትችት ተቀብሎ ዝም አለ።

… ከፊት ከኋላ፣ ከግራ ከቀኝ የሚመጡ ብዙ ዓይነት ትዕዛዞች አሉ። የሰው ልጆች መንግስት አቋቁመው መምራትና መመራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ብዙ አይነት ትዕዛዞችን አፍርተዋል፣ አርቅቀዋል። እያንዳንዱ ትዕዛዝ አፅናኝ አሊያም አስደንጋጭ የሚሆነው ተዕዛዙን ካረቀቀው መንግስት ባህርይ የተነሳ ነው።

የአንድ ሀገር ህዝቦች የመንግስታቸውን ፀባይ በሚገባ ከሚመረምሩበት ዋነኛው እና ሁነኛው ሥልት አንዱ መንግስታቸው ያወጣባቸው ትዕዛዝ ነው። መንግስታት በፊርማቸው የሚያፀድቁት ትዕዛዝ፣ ድብቁን የውስጥ ባህርያቸውን ማለትም ክፋት ደግነታቸውን ፍንትው አድርጎ በማሳየት፣ ወደር የለሽ ውለታ ይውላል - ለህዝባቸው።

በአንድ ቅል ውስጥ የተንቆረቆረ ወተት ሊኖረው የሚችለው ቅርፅና ፀባይ የራሱን የቅሉን እንጂ የባልዲ ወይም የኮዳ አይደለም። በተጣመመና በጨረጨሰ ትዕዛዝ ውስጥ የአንድን መንግስት ቅርፅና ፀባይ ማግኘት ይቻላል። የቅሉ አፈጣጠርና አሰራር ለወተቱ ‘መርጋት’ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። የአንድ ሀገር ህዝብ ስደት ሳይመኝ በሀገሩ ‘ረግቶ’ እንዲቀመጥ በማድረግ በኩል የአንድ መንግስት ትዕዛዝ ሁለንተናዊ ተፈጥሮው የገዘፈ አስተዋጽኦ አለው። የቅሉ ውስጣዊ የንፅህና መጠን በወተቱ ላይ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። ማንም ሰው ዕጅ እጅ በሚያስብል ቅል ውስጥ ወተት

ማስቀመጥ እንደማይፈልግ ሁሉ፣ የትኛውም ህዝብ ልበ-ንፁህ ያልሆነ መንግስት ባረቀቀው ቆሻሻ ትዕዛዝ መተዳዳር አይፈልግም። ለጤና ብቻ ሳይሆን ለነፍስ ጭምር ጠንቅ ነውና።

የተበከሉ ምግቦች የሚያስከትሏቸው በሽታዎች በወቅቱ አስፈላጊው ሕክምና ተደርጎ በቁጥጥር ስር ይውላሉ። ለነፍስ ጠንቅ የሆኑ የመንግስታት ትዕዛዞች በቁጥጥር ስር የሚውሉት በስሪንጅ አይደለም። በተበከለ ትዕዛዝ የቆሰለ ህዝብ የሚፈወሰው፣ ንፅህናው በተጠበቀ አዲስ መንግስት እና አዲስ ትዕዛዝ ብቻ ነው።

ይህም ሲባል፣ ህዝቦች መዳኒት የሚሆናቸውን አዲስ መንግስት ‘በወቅቱ’ አቋቁመው ግሉኮስን የሚተካ ትዕዛዝ ካላገኙ ለሕይወት መመርቀዝ ይዳረጋሉ። በዛ ላይ ተቃውሞን ማፈን፣ ካንሰርን እንደማፈን ይቆጠራል።

ሕዝብ የማይወዳቸውን ሰዎች በግልፅ መቃወሙ አግባብ ነው። አለበለዚያ ተቃውሞ ታምቆ ኖሮ ድንገት በራሱ ሰዓት የሚፈነዳ ከሆነ፣ በማዕበሉ የሚናወፁት የማይወደዱት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ የሚወደዱት ጭምር ናቸው።

ረሀብን ችሎ ወይም አምቆ የሚተኛ ሰው ሊኖር ይችላል። ሲነጋ ግን የሳጥን ነጋዴዎች ገበያ በአንድ ሰው መጠን ይጨምራል። ተቃውሞን ካፈንከው ተበላልተህ ታልቃለህ። የሚጨርስህ ደግሞ የማትወዳቸው ሰዎች የሚያወጡት እና የሚያገቡት ትዕዛዝ ነው።

በሌላም በኩል ተቃውሞን ባፈንከው ቁጥር የማትወዳቸው ሰዎች /መንግስታት የተወደዱ እየመሰላቸው ቦታውን ሳይለቁ ዘመናት ይከንፋሉ። የዘመናት መክነፍ ደግሞ

እድሜህን እየገመሰውና ሞትህን እያቀረበው ይመጣል። በተበከለ ትዕዛዝ ተበልተህ ላለመሞት ያለህ አማራጭ ደግሞ ወቅታዊ ተቃውሞህን በወቅታዊ ሰዓት ማፈንዳት ነው - ሕመም ጊዜ አይሰጥህምና በአዲስ ትዕዘዝ መታከም አለብህ።

በተለያዩ ዘመናት የተነሱ መንግስታት በገዛ ብዕራቸው ያፀደቁት የገዛ ትዕዛዛቸው ጦስ የሚያመጣባቸውና መንበራቸውን የሚንጥባቸው ያለ ምክንያት አይደለም። ለአስር፣ ለሃያ፣ ለሰላሳ እና ለአርባ ዓመታት አቅደው የሚያረቅቁት ትዕዛዝ፣ ወደፊት ምን አይነት ጉዳት እንደሚያደርስ ከወዲሁ ስለሚነቃባቸው ነው - በህዝባቸው።

ይህን መሰሉን ስውር ፀባያቸውን የራሳቸው (የመንግስት) ሚዲያዎች በቀጥታ ለህዝቡ ላያስተላልፉት አሊያም ላያጋልጡት ይችላሉ። ትዕዛዞቻቸው ግን ድብቅ አጀንዳቸውን ለህዝብ ያስተላልፉታል። በትዕዛዞቻቸው አማካይነት ይጋለጣሉ።

አንድ መንግስት በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ማዕቀብ የሚጥለው፣ ህዝብ በአደባባይ ወጥቶ እንዳይቃወመው ስለሚፈራ ነው። በሰልፍ ላይ የጣለው የዕገዳ ትዕዛዝ፣ ያ መንግስት ‘ፈሪ’ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ራሱ ባወጣው ትዕዛዝ የራሱን ማንነት አጋለጠ።

… ብዙውን ጊዜ ደግሞ መንግስታት ህዝባቸው አሊያም ተቃዋሚዎቻቸው እንዲያደርጉት የማይፈልጉትን (ትዕዛዝ የሚያወጡበትን) ነገር፣ መልሰው ራሳቸው ሲያደርጉት ይስተዋላል።

በኢትዮጵያ የነገሱ አብዛኛዎቹ ነገስታት ‘ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረብን ነን’ ብለው

የሚያምኑ ነበሩ። የፈጣሪያቸውን ትዕዛዝ ህዝቡ እንዳይሽረው ያስጠነቅቁ ነበር። ነገር ግን ህዝቡን ‘አደብ ግዛ’ እያሉ፣ እነሱ በጎን አደብ ያጡ ነበር። መግደል ሐጢያት ነው ብለው ያምናሉ። እነሱ ግን ጭፍጭፍ አድርገው ሲገድሉ ኖረዋል።

“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ለሚለው ለፈጣሪያችን ሕግ እንገዛለን ይላሉ። ነገር ግን ራሳቸውን ከአማልክት አስበልጠው፣ ሕዝቡ ጉልበቱ እስኪላጥ ድረስ እንዲሰግድላቸው አድርገዋል። ሌላው ቀርቶ የሰረገላዎቻቸው ጎማ የሄደበትን መሬት አስልሰውታል። ደርግ ደግሞ መዝረፍና አስገድዶ መድፈር ወንጀል መሆኑን ደንግጎ ነበር። ግን በአደባባይ ሲዘርፍና በየቀበሌው ሴት ሲደፍር ከርሞ ነበር።

ኢ ህ አ ዴ ግ እንደመንግስት ሳይሆን እንደ ፓርቲ፣ የህዝብ/የመንግስት ሚዲያዎችን ለግል ጥቅሙ ማዋል የለበትም። እሱም /ኢህአዴግም ለግል ጥቅሜ ወይም ለቅስቀሳ ማዋል የለብኝም ብሎ ትዕዘዝ አውጥቷል። ነገር ግን ቲቪውንም ሆነ ሬዲዮኑን ለፓርቲው ገፅታ ግንባታ ሲጠቀምበት ይታያል።

ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ያሉት የኢትዮጵያ መንግስታት አካሄድ ከአንድ ክስተት ጋር ይመሳሰላል። ሰይፍ ይዞ የወጣውን ግለሰብና ሰይፍ ይዞ የገሰፀውን መልዓክ ይመስላሉ። መልዓኩ ሰይፍ ማንሳት “ክልክል” መሆኑን ለግለሰቡ የነገረው እሱ ራሱ ሰይፍ ይዞ ነው። መግደል ‘ክልክል’ መሆኑን ለህዝቡ የነገሩት እነሱ ራሳቸው እየገደሉ ነበር። ሌሎቹም እንደዛው።

ጥንካሬውን እያሰማሙ ያለሐሳብ ይገነባሉ። ሃምሳው አነዋሪ ደግሞ ዙሪያውን ከብበው የጎደለውን፣ የተበላሸውን፣ የተጣመመውን፣ ያፈነገጠውን እየነቀሱ እያወጡ እዚያው ላይ እንዲስተካከል ያደርጋሉ።”

ዳንኤል ክብረት (የሁለት ሐውልቶች

ወግ)መነሻ ሁለት

ሽብርተኝነት የዓለምን ሕዝብ ዕለታዊ እንቅስቃሴ እያወከ ያለ አደጋ መሆኑ አያጠያይቅም። ሽብርተኝነት ሊወገዝ ይገባል። በሽብር የሚሳተፍም ሆነ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ሊጠየቁ ይገባል። የእኛ ሀገር ሽብርተኝነት ግን ትንሽ ሰምና ወርቅ የሆነ ይመስላል።

“ውብሸት ቦምብ ታጥቆ የቴሌኮሙኒኬሽን መሥሪያ ቤትን ሊያፈነዳ ሲል ተደርሶበት ተይዞ ከሆነ ጓደኛዬና ባልደረባዬ ስለሆነ ከተጠያቂነት መዳን አለበት አልልም። በአስር አንድ ዓመት የጓደኝነት ዘመናችን ግን እጁ ላይ እስክርቢቶና አጀንዳ እንደማይጠፋ አውቃለሁ። በእርግጥ የውብሸት ብዕር የሚተፋቸው ቃላት የሕግ የበላይነትን ለሚጥሱ፣ ሰብዓዊ መብትን ለማያከብሩ በ‹ብተና ፖለቲካ› ለተካኑ ከቦንብ በላይ ሆነው ይሆን?”

ዳዊት ከበደ አውራምባ ታይምስ፣

ሰኔ 25/2003ማሳረጊያ መነሻ

የባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አውራምባ ታይምስ እትም ላይ የጋዜጣው አምደኛ የሆኑት አቶ ሰሎሞን ሞገስ ‹‹መፃፍ አቁሜያለሁ› ብለው ከጋዜጣ አምደኝነት ራሳቸውን ማግለላቸውን አየሁ።

በ ፅ ሁ ፋ ቸ ው ምክንያት በኢሜይል እና በስልክ

ስለደረሰባቸው ማስፈራሪያ ብዙ ብለዋል። በዚህም ምክንያት ከሚወዱት እና ከሚተዳደሩበት የህትመት ጋዜጠኝነት ስራ መለየታቸውን መረር ባሉና ውስጥ ድረስ ዘልቀው በሚቆረቁሩ ቃላት ገልፀዋል።

ዛሬ መነሻዎቼ በዙ መሰለኝ። መብዛትም ብቻ ሳይሆን የተለያዩም ይመስላሉ። ይሁንና መምሰላቸውን ትተን መለያየታቸውን ረስተን ለማለት ወደፈለግሁት ነገር ልለፍ።

በ አ ፈ - ታ ሪ ክ እንደምንሰማው ጥንታዊያን ወይም ቀደምቶቹ የሀገራችን መሪዎች ነገስታት ከእያንዳንዱ ስራዎቻቸው ዙሪያ አነዋሪዎችን ያቆሙ ነበር። አነዋሪዎች አሁን ብዙዎቻችን የሚሰማንን አይነት ከንቱ ስራ አይደለም የሚሰሩት። አሁን በዘመናዊ አባባል እንደምንለው የሰላ ትችትን እንጅ።

እነዚህ አነዋሪዎች በመንግስት የግንባታ ስራዎች ዙሪያ አይጠፉም። ይህን እውነት ለማሳየት ነው የመጀመሪያውን መነሻዬን ያስቀመጥኩት። እነዚህ አነዋሪዎች ደግሞ የወቅቱ ሊቃውንት ናቸው። ሊቃውንትነታቸው ከምድራዊም፣ ከሰማያዊም ትምህርት፣ ከእድሜም፣ ከማንበብም፣ ከመስራትም፣ ከመኖርም የተማሩት ነው። እነዚህ የወቅቱ ሐያሲያን እንደ ዐይን ብሌን ይጠበቁ ነበር። ለየቤተመንግስቱ ባለሟል ነበሩ። ከባለወንበሮች ዙሪያ እንዲጠፉ፣ እንዲሰደዱ፣ የክፋት ውሳኔ አይወሰንባቸውም ነበር።

ይህ ሁሉ የሚሆነው ባለወንበሩም አነዋሪውም ለሀገራቸው እንደሚሰሩ ለህዝባቸው እንደሚያገለግሉ ስለሚታወቅ ነው። አነዋሪው የመንግስት አካላትን እየተመለከተ ስራቸውን

እየገመገመ አስተዳደራቸውን እያስተዋለ ሲልለት በቅኔ ያለዚያም በእረኛ ተረት ወይም ዘፈን አስመስሎ በሚሰነዝረው ሒስ የመንግስቱን ወይም የንጉሱን ደካማ ጎን ማጋለጡ ፊት ለፊት ለሽልማት ባያበቃው እንኳ ሐሳቡ ይደመጥለታል። አነዋሪነቱ ተመስክሮለት በዐይን ባይገልጡት በልባቸው በያዙለት ፍቅር ያስተዳድሩታል። እንዲያም ሲል አበጀህ ይባላል።

ይህ አነዋሪ ያየውን ግፍ በተናገረ፣ ያስተዋለውን ጉድለት በመሰከረ የተጣመመውን አቅኑ፣ የጎደለውን አሟሉ፣ የዘመመውን ደግፉ፣ የተበላሸውን አድሱ ብሎ በመከረ የሚወግረው የለም፤ የሚሰቅለው አልነበም፤ የሚያሳድደው አልነበረም። ቀደም ያሉት ነገስታት “በዚህ ዙሪያ እገሌ ምን አለ?” እያሉ ይጠይቁ ነበር። ከአነዋሪዎቻቸው ሐሳብ ይሰበስቡ ነበር። ጦርነት እንኳ ይዘዋቸው ይዘምቱ ነበር።

የዚህ ሁሉ ምክንያት ከፍ ሲል ያልሁት ነው። ሁሉም ለሀገሩ እንደሚሰራ ያምናሉ። ንጉሱ ንጉስ ነኝና አልመከረም፣ አልነወረም አይልም። ይልቁንም በተሐ ጠጁን በገንቦ አስቀርቦ፣ “እስቲ አጫውቱኝ፤ ምን ቅኔ ተዘረፈ? እረኛ ምን ዘፈነ?” እያለ የአነዋሪዎችን ሐሳብ ይሰበስባል።

አነዋሪዎች የሰጡትን ሐሳብ ሰብስቦ ለማስተካከል ይመክራል እንጅ እነዚህ አነዋሪዎች ዙፋኔን ሊቀሙኝ እያሴሩ ነው ብሎ የህልም ስጋት አይሰጋም።

አነዋሪዎችም ያሉትን ሁሉ የሚሉት ለሀገራቸው፣ ለንጉሳቸው እና ለህዝባቸው ካላቸው ታማኝነትና አገልጋይነት በመነሳት በመሆኑ ዛሬ እሰቀላለሁ፣ ዛሬ ጾሜን አድራለሁ - ወይም ማስፈራሪያ ይደርስብኛል፣ የእስር ማዘዣ ይወጣብኛል ብለው

አይፈሩም። ምክንያቱም ስህተትን ማሳየት እንጅ ወንበር የመገልበጥ ዓላማ እንደሌላቸው እንኳን እነሱ አገር ያውቅላቸዋልና።

እ ን ዳ ለ መ ታ ደ ል ሆኖ የዘመናዊ መንግስት ዕሳቤ ማቆጥቆጥ ከጀመረበት ዘመን በተለይም ይህ መጥፎ ልማድ ያኛውን ደጉን ሀገራዊ ልማድ መደርመስ የጀመረው ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግስት ጀምሮ ይመስለኛል። ይመስለኛል የምለው በዘመናዊ ትምህርት ከተጠቀሱት እውነታዎች ብቻ ስለተነሳሁ ነው።

ከተጠቀስሁት ዘመን ጀምሮ ፖለቲካ ሽፍጥ እየሆነ መጣ። ሐሳብን መግለፅ እያስደነገጠ መጣ። የመንግስት ሰዎች አነዋሪዎችን ማሳደድ ጀመሩ። እወደድ ባዮች የአነዋሪዎችን አንገት ቆልምመው እየገደሉ አንዴ የከሰል ጢስ አፈናቸው፣ አንዴ ተባራሪ ጥይት መታቸው፣ አንዴ አረቄ ገደላቸው እያሉ ማስወራት ጀመሩ።

የሆነው ሆኖ በተለይ የህትመት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ሲመጣ የንጉስ እወደድ ባዮች ፀሀፊዎችን ማደሳደድ የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ሆነ። መንግስታችን በሚሰራው ስራ ማንም ኢትዮጵያዊ እንዳይመለከተው በግድም በውድም ማዘዝ ጀመሩ።

አዎ! ስለኢትዮጵያ መጨነቅ ያለበት መንግስታችን እንደመሆኑ ስለመንግስታችን የማውራት መብት ያለው አጥንት ሰባሪ ያልሆነ የነገስታት ዘር ብቻ ነው እያሉ በየሞሰቡ ማውራት ጀመሩ። እንደሚፈክሩትም አደረጉ። ፊደል የቆጠረ የገበሬ ልጅ ኢትዮጵያዊነቱ ተረስቶ ‘የገበሬ ልጅ’ነቱ መቀጣጫ ሆኖ ተደሰበ፣ ተንጓጠጠ። ስለሥርዓቱ

በታዲዎስ ጌታሁን

መሪዎቻችንና ግራ አጋቢ ክልከላዎቻቸውየተበከሉ ምግቦች የሚያስከትሏቸው በሽታዎች በወቅቱ አስፈላጊው ሕክምና ተደርጎ በቁጥጥር ስር ይውላሉ። ለነፍስ ጠንቅ የሆኑ የመንግስታት ትዕዛዞች በቁጥጥር ስር የሚውሉት በስሪንጅ

አይደለም። በተበከለ ትዕዛዝ የቆሰለ ህዝብ የሚፈወሰው፣ ንፅህናው በተጠበቀ አዲስ መንግስት እና አዲስ ትዕዛዝ ብቻ ነው

የአነዋሪ ጥላቻ እስከመቼ?በደሳለኝ ስዩም

በ ገፅ 23

የተበከሉ ምግቦች

የሚያስከትሏቸው በሽታዎች

በወቅቱ አስፈላጊው ሕክምና

ተደርጎ በቁጥጥር ስር ይውላሉ።

ለነፍስ ጠንቅ የሆኑ የመንግስታት

ትዕዛዞች በቁጥጥር ስር

የሚውሉት በስሪንጅ አይደለም።

በተበከለ ትዕዛዝ የቆሰለ

ህዝብ የሚፈወሰው፣ ንፅህናው

በተጠበቀ አዲስ መንግስት እና

አዲስ ትዕዛዝ ብቻ ነው።

እነዚህ አነዋሪዎች በመንግስት የግንባታ ስራዎች

ዙሪያ አይጠፉም። ይህን እውነት ለማሳየት ነው የመጀመሪያውን

መነሻዬን ያስቀመጥኩት። እነዚህ አነዋሪዎች ደግሞ የወቅቱ

ሊቃውንት ናቸው።

Page 9: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

የአትላንታው ፌስቲቫል፣

ከዚያም ሰለሞን ተካልኝ

9ኮሜንተሪ

ጁላይ 1፣ ዓርብ ምሽት አትላንታ ጆርጂያ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስኩ እንደቀድሞው ብዙ አበሻ ሲርመሰመስ አላየሁም። የአበሻው ትርምስ በ2005 አትላንታ ላይ ተመሳሳይ ፌስቲቫል በተዘጋጀ ጊዜ ከነበረው እጅግ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር። ይልቁንም ዝግጅቱ አልቆ አትላንታን ስንሰነባበት አውሮፕላን ማረፍያው በአበሻ ተጨናንቆ አሜሪካ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ነበር የሚመስለው።

ከአውሮፕላን ማረፍያው እንደደረስኩ፣ አበሻ ወገኔን ሳፈላልግ መውጫው በር አካባቢ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሰው ላይ ዓይኔ አረፈ። በቆዳ የተሰራ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው እግራቸውን በዘመናዊ የጫማ መጥረግያ ላይ አሳርፈዋል። ጫማ ጠራጊ (ሊስትሮ) ናቸው። አለባበሳቸውም ሆነ መልካቸው ጫማ አስጠራጊ እንጂ ጠራጊ እንኳን አይመስሉም። የኳሱንና የአትላንታውን ሁኔታ ለመጠየቅ ስለጓጓሁ ወደ እኚህ መልከ መልካም አዛውንት አመራሁ። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፣ ወደጥያቄዬ ገባሁ፡፡

“ዘንድሮ እንዴት ነው፣ አበሻው በብዛት እየገባ ነው?”

“ለሶከሩ (ለእግር ኳሱ) ማለትህ ነው?”

“አዎ፣ ለእግር ኳሱ፡፡”“ዘንድሮ ብዙ ሰው

አላየሁም። ለነገሩ ሰዉ ከሮብ ጀምሮ ነው የሚገባው። ግን ምን እግር ኳስ አለ ብለህ ነው። ኢትዮጵያና ሶማሌዎች እሱን ትተው ሆኪ ቢጫወቱ ያዋጣቸው ነበር።” ሲሉ ቀልድ ጣል አደረጉ።

የሊስትሮው አባባል ቶሎ አልገባኝም። ረጅም ዱላ ይዞ ውልወላ (ጽዳት) የሚሰራ “ሆኪ ተጫዋች” እንደሚባል የተገነዘብኩት ከቀን በኋላ ነበር።

ቅኔው የገባኝ ደግሞ ዘግይቶ ነው። በአንድ በኩል አበሻ ወገኔ ከሀገሩ ሲወጣ ሥራ ማክበሩን እና በውጭ ሀገር የሥራ ዲሲፕሊን መማሩን ያስተውሏል። ኢትዮጵያዊ በባዕድ ሀገር ሥራ አክባሪ በመሆኑ ምክንያት ተከብሮ እና ራሱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ አድርጎታል። ችግሩ ያለው በማህበራዊ ህይወት፣ በጋራ እና በተደራጀ መልኩ በሚከናወኑ ሥራዎች አካባቢ ብቻ ነው።… አዛውንቱ ሊስትሮ ሊሉኝ የፈለጉትም ይህንኑ ነበር። አበሻ በግል እንጂ በጋራ (በቡድን) የተዋጣለት ሕዝብ አይደለም። በዚህ ረገድ ፈጽሞ አልታደልንም።

ወዳጅ ከወዳጅ፣ ዘመድ ከዘመድ፣ ሊገናኝ፤ ለቤተሰብ ስብስብ እና ቅልቅል፤ ጓደኛ የሌለው ለአዲስ የጾታ ጓደኛ ፍለጋ፤ ነጋዴው ለንግድ ሥራ፤ የጥበብ ሰው ሥራውን ሊያስተዋውቅ፣ ስፖርተኛው ለዋንጫ፤ ጋዜጠኛው ክንውኑን እና ትዝብቱን ሊዘግብ፤ ወጣቱ ሊዝናና... በየዓመቱ ሰሜን አሜሪካ ስቴቶች ይዘዋወራል። የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል የሰሜን አሜሪካ ፌስቲቫል ለበርካታ አዘውታሪዎች እንደ ሱስ ሆኗል።

ዘንድሮ የአትላንታን ሙቀት ከወትሮው ለየት ያለ ሆኖ አግኝተነዋል። የአየሩ ሙቀት ከፍ ከማለቱ የተነሳም ከማቃጠል አልፎ እንፋሎቱ (ሁሚዲቲ) ለመተንፈስም አስቸጋሪ ነበር። የአየሩ ግለት እንዳለ ሆኖ፣ በስፖርት ፌዴሬሽኑ ዙርያ ተጋግሎ የነበረው ሙቀትም እንደነበረ ቀጥሎ ነው የሰነበተው። በፌዴሬሽኑ ሥራ አመራር እና በቦርድ አባላቱ መካከል የተፈጠረው ውጥረት አጀማመሩ ላይ የረገበ ይምሰል እንጂ እንዲያውም

ብሶበታል። ቀርበን እንደሰማነው ቦርዱ በሙሉ ድምጽ አስተላልፎት የነበረው ውሳኔ የሥራ አመራር ኮሚቴውን ለሶስት ከፍሎታል።

ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው፣ ይህ የቦርድ ውሳኔ ተግባራዊ ባይሆን ኖሮ ጆርጂያ ዶም ሳምንቱን ኦና ሆኖ ይሰነብት፣ 28 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን ሲያሰባስብ የቆየው ብቸኛ ተቋምም ዛሬ ፈርሶ እናየው ነበር።

ከቡድኖቹ አንዱ በሼኩ ሰዎች ጥላ አመራር (ሻዶው) የሚመራው አንጃ ሲሆን፣ ሌላኛው የቦርዱ ውሳኔ ይከበር የሚለው የሥራ አስፈፃሚ ክፍል ነው። በሶስተኛ ደረጃ ያለው ደግሞ በመሃል የአስታራቂነት ሚና ሲጫወት የነበረው አካል እንደሆነ አስተውለናል። የሕዝብ ግንኙነቱ ፋሲል አበበ ማስታረቁ ላይ ከፍተኛውን ሚና ሲጫወት ቆይቶ የኋላ ኋላ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንበት ሜዳውን ዳግም ላይመለስበት ተሰናብቶት ሲወጣ ተመለከትን። ከዱላ የተረፈው የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አብይ ኑርልኝም ተበሳጭቶ በወሳኙ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ሳይገኝ መቅረቱ ችግሩ ምን ያህል እንደከረረ ያሳየናል።

በፕሬዝዳንቱ በመኮንን ደምሴ እና በምክትሉ አብይ ኑርልኝ መካከል የተፈጠረው የማይታረቅ የሚመስል ቅራኔ የዚሁ የቡድን ስሜት ውጤት እንደሆነ ነው የቦርድ አባላቱ የሚናገሩት። ኢትዮጵያዊያኑ ባረፉበት ሆቴል ተፈጥሮ የነበረው የሁለቱ አመራር አባላት ብጥብጥ እና ጸብ ስፖርታዊ ስነ-ምግባርን ፈጽሞ የሚጻረር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ጨዋነትም እንዳልሆነ ይገነዘቡታል። አንዳንዶች ሲቀልዱ በመሃላቸው የገባው በቻርተር

አውሮፕላን ተጭኖ ከአዲስ አበባ የመጣ ሰይጣን ነው ይሉ ነበር። የጸቡ መንስኤ ምንም ይሁን ምን አመራር አባላቱ በእንግዶቻቸው ፊት ለጸብ ሲሯሯጡ፣ 28 ክለቦችን ወክለው ከ20 ሺህ ሕዝብ በላይ በማስተናገድ ላይ ያሉ ስለመሆናቸው ያስተዋሉ አይመሰሉም። በዚህም የተነሳ አጠቃላይ የዝግጅቱ ሁኔታ በትርምስ ተጀምሮ በትርምስ እንዲያልቅ ግድ ሆነ። አንዳቸውም ጨዋታዎች ሆነ ዝግጅቶች በተያዘላቸው ፕሮግራም አልተካሄዱም።

በተለይ የዓርቡ የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት በመርሃ ግብሩ ከተያዘለት ከአምስት ሰዓት በኋላ በመጀመሩ ምክንያት ዘግጅቱ በእጅጉ ተዘበራረርቆ፣ እንግዶችን አማርሮ አልፏል። በዚህ ረገድ የሼኩ ሰዎች ተሳክቶላቸው ሊሆን ይችላል፤ የበዓሉን ድምቀትና ለክብር እንግዳዋ የተደረገውን ሞቅ ያለ አቀባበል ግን ፈጽሞ ሊያስቆሙት አልቻሉም።

ከበርካታ ውጣ ውረድ፣ ከብዙ ግርግርና አታካራ በኋላ የአትላንታው ዝግጅት መቀጠል ያጠራጠራቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ይህ ነው የሚባል አልነበረም። የሼኩ ሰዎች የሰጡትን 240,000 ዶላር እንዲመለስ መጠየቃቸው ተደምሮበት በየጎራው ይደረግ የነበረው የማዕቀብ ዘመቻ ጥርጣሬውን ጎላ አድርጎትም ነበር።

ሁሉም አልፎ ቀኑ ደረሰ። እሁድ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክብር እንግዳዋ ዳኛ ብርቱካን መገኘት ባትችልም፣ ዝግጅቱ ከሞላ ጎደል ሞቅ ብሎ ነበር ያለፈው። በተለይ የኮንግረስማን ጆን ሊዊስ በመክፈቻው ላይ መገኘት በዓሉን የበለጠ አድምቆታል። ከሰኞ እስከ

የአነዋሪ ጥላቻ እስከመቼ?

ሐሙስ የነበረውን ዝግጅት ግን ከሕዝብ ቁጥር አንጻር ከወተሮው የቀዘቀዘ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ሲሰጡ ሰንብተዋል። በፌዴሬሽኑ አመራር አካባቢ በተፈጠረው ውዝግብ ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል። አንዳንዶች በነበረው ግርግር ተበሳጭተው ቀርተዋል፣ አልያም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሄሪቴጅ ዝግጅት አቅንተዋል።

በአንድ በኩል በኤልያስ ክፍሌ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሼኩ ሰዎች ይጧጧፍ የነበረው የ ‘ቦይኮት’ (ማዕቀብ) ዘመቻው በሰው ላይ የፈጠረው የሥነ-ልቦና ቀውስ ይህ ነው ባይባልም ግምት ውስጥ የሚገባ ጉዳይ ነው። በተለይ በግል አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ተጭነው ለዚሁ ዘመቻ አትላንታ የገቡት የሼኩ ሰዎች ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሁሉ በቫን በመሆን ሕዝቡ ወደ ጆርጅያ ዶም (ሜዳ) እንዳይገባ ሲቀሰቅሱ አስተውለናል። እነዚሁ ሰዎች የፌዴሬሽኑን የምሽት ዝግጅትም ለማሰናከል በተመሳሳይ ቀን በቅዳሜ ምሽት ያደረጉት ተደራቢ ዝግጅት በፌዴሬሽኑ ላይ ያስከተለው ጉዳት ቀላል አይደለም።

በአቶ አብነት መሪነት፡ በነተስፋዬ ቅቤ አጃቢነት በግል (ቻርተር) አውሮፕላን ዲሲ አርፈው እና መክረው አትላንታ ከገቡት ውስጥ አንድ ሁለቱ ሜዳ ብቅ ብለው ሹክ ያሉትን ሰማን። አቶ አብነት ፈርቶም ይሁን አኩርፎ፣ በፌዴሬሽኑ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በጆርጂያ ዶም ሳይታይ ወደመጣበት ተመልሷል። ከቶውንም ስታዲየም ገብቶ ዝግጅቶችን ማየት ካልፈለገ አትላንታ ድረስ መጥቶ ዝግጅቱ ሲያልቅ ለምን ተመለሰ? በእርግጥ ዝግጅቱን ለማወክ እና ለመበጥበጥ?... ይኽ የብዙዎች ጥያቄ ነበር።

በገንዘብ ኃይል ሰዎችን በመደለል የ ‘ቦይኮት’ እና የብጥበጣ ዘመቻ ለመምራት መጡ የተባሉትም እንደጠበቁት አልተሳካላቸውም። በተለይ ዓርብ ዕለት፣ ጁላይ 8 የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር የዳኛ ብርቱካንን ንግግር ለመስማት የመጣው ሕዝብ ብዛት

ክንፉ አሰፋ (ከቶሮንቶ)

በየቀኑ፣ ከቤቴ በጠዋት ወጥቼ ሲመሽ ወደዚሁ መኖሪያዬ እስከምገባ ድረስ ብዙ ነገሮችን እታዘባለሁ። አስደሳች፣ አሳዛኝ፣ አንዳንዴ የሚያበሳጩ ሁኔታዎች ይገጥሙኛል። ከእያንዳንዱ ነገር መማር፣ በእያንዳንዱ ነገር መማርር ይጠቅማል። እናም የታዘብኩትን እናንተም ታጤኑት ዘንድ እያካፈልኳችሁ፣ የእኔን ሃሳብ እንደመነሻ አድርገን በጋራ ለምን አንማማርም? እነሆ!

ሚያዚያ 9 ቀን 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ስዓት አካባቢ፣ ከምኖርበት ኮንዶሚኒየም (4ኛ ፎቅ ካለው) ቤት ጀርባ ባለች ትንሽዬ በረንዳ፣ አግዳሚ መቀመቻ ላይ ቁጭ ብዬ ፊት ለፊት ያለውን ሌላ የኮንዶሚኒየም ሕንፃ እና ወረድ ብሎ የሚኘውን የብሔረ ፅጌ ጫካ ስቃኝ ቆየሁ። ፀጥ ብዬ ራሴን ለማዳመጥ፣ ሥራዬን ለመገምገም ሞከርኩ። የጀመርኳቸው የሚፃፉ ነገሮች ስላለ እነሱንና መደበኛ ሥራዬንም በተመለከተ ካቀድሁት ምን ያህሉን ፈፀምሁ? በዚህስ አካሄዴ ወዳሰብሁት እደርሳለሁ? . . . ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። ወደአሁኑ ሥራዬ ለመግባት እንደ ጥሩ መሸጋገሪያነት የሚያገለግለኝ ዘዴ ነው - ለደቂቃዎች በፀጥታ ስለራሴና ስለስራ ማሰብ።

ነጣ ያለ ፕላስቲክ ነጠላ ጫማ አድርጌያለሁ። በቀኝ እግሬ ግርግዳውን፣ በግራ እግሬ መሬቱን ረግጬ በጀርባዬ አግዳሚውን ተደግፌ ፊት ለፊት ካለው የኮንዶሚኒየም ሕንፃ ጋር ተፋጠጥሁ።

የማየው የተፈጥሮ ነገር ሁሉ ሲስበኝ ሰው ሰራሽ ከሆኑት ግን አንዳንዶቹ ሊያበሳጩኝ ሞከሩ። የተፈጥሮው ሰማይ ዓይን እስከሚችለው ሲያዩት ወሰን የሌለው የማሰብና የደስታ ነፃንት ያላብሳል። ዛፎቹም ሲያዩአቸው በግል ጥረት ሊፈጥር የሚችል ልዩ

ሰላም በልብ ውስጥ ያፈስሳሉ።በዚህ ሁሉ መሀል

ቆስጣ ሰፈር ከሚባለው መንደር አንድ ኃይለኛ ድምፅ ረበሸኝ። የሃይማኖት ዘፈን /መዝሙር/ ነው። እየደጋገመ ተመሳሳይ ነገር ይላል - ዘማሪው። ይህ ሰው ለምን ሰውን ሰላም ያሳጣል ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። ዘፈኑን የከፈቱት ሰዎች እነሱ ስለፈለጉት ብቻ ያን ዘፈን ከሚገባው በላይ ለቅቀው በአካባቢው ያሉ የብዙ ሰዎችን ፀጥታና ነፃነት ማሳጣታቸው አላዋቂ ወይም ኋላ ቀር ያሰኛቸው ይሆን የሚል ሃሳብ መጣብኝ።

በእውነቱ አንድ ሰው የሌሎችን በፀጥታ የመሆን መብት ሊጋፋ ይገባዋልን? የአንድ ቤት ዘፈን (ሃይማኖታዊውም ሆነ ሌላ) ከቤቱና ዘፈኑን ፈልገው ከከፈቱት ከቤቱ ባለቤቶች አልፎ ሌላ ሰው መረበሽ አለበት የሚል የሞራልና ማህበራዊ ሕግ ወይም ደንብ ሊኖር የሚችል አይመስለኝም። ምናልባት አንድ ሰው ሁል ጊዜ እንደእሱ አዋቂ እንደሌለ፣ እንደእሱ ሙዚቃ ቆንጆ ሊኖር እንደማይችል፣ የእሱን እምነት የሚስተካከል እምነት እንደሌለ ሊያስብና ሊገምት ይችላል። የዚህ ሰው አስተሳሰብ ካለንበት ዓለም ሀቅ ጋር የማይጣጣም፣ እና በየትኛው ፕላኔት ላይ እንደሚሰራ የማይታወቅ ቢሆንም፣ ማሰቡን ማንም ሊከለክለው አይችልም።

በዓለም ላይ ከ6 ቢሊዮን በላይ ሰዎች አለን። እያንዳንዳችንም አይናችን፣ እጃችን፣ ፊታችን፣ አፍንጫችን የተለያየ ነው። እንደው እጅግ አልፎ አልፎ ከስንት አንድ ካልሆነ በስተቀር፣ አንድ አይነት የሆኑ 2 ሰዎችን ማግኘት አይቻልም። ይህንን ካመንን፣ ሰዎች በባህርያቸው እና በአሰተሳሰባቸው የተለያዩ መሆናቸውን መገመት ይሳነናል ብዬ አላስብም።

በእኔ ግምት፣ አንድ የሰለጠነ ሰው ወይም ሕዝብ፣ የእሱ እምነት ለራሱ ብቻ እንደሆነ፣ እሱ የሚወደውን የሚያከብረውን እምነቱንና አስተሳሰቡን የማይቀበሉ የራሳቸውን የተለየ እምነት የሚያራምዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚያውቅ ይመስለኛል። ይህንን ስለሚገነዘብም የእሱ እምነት ለእሱ መልካም እንደሆነ ሁሉ፣ የሌሎችም እምነት ለራሳቸው መልካም ሊሆን ይችላል ብሎ ያስባል። እናም በራሳቸው በሚወዱት እምነት የመደሰት ነፃነት የራሳቸው በመሆኑ፣ በእሱ እምነት በግድ ሊረብሻቸው አይፈልግም። የሰለጠነ ሰው ሌሎች ሰዎች በማንኛውም ሰዓትና ወቅት ፀጥታን ይፈልጋሉ የሚል ግንዛቤ ስላለው በዘፈኑ፣ በመዝሙሩ ከእሱ አልፎ ማንንም መረበሽ፣ የማንንም ፀጥታ መንካት አይወድም። እኔ ዘመናዊና የነቃ ሰው የምለው ከሚለይባቸው ነጥቦች አንዱ ይሄ ነው። ዛሬ በምንም ነገር የሰዎችን ነፃነት መንካት የለብንም።

የእኛ የግላችን የራሳችን የእምነት፣ የአስተሳሰብ ጉዳይ፤ ዘፈን፣ መዝሙር፣ ለቅሶ ወዘተ ሌሎችን አልፎ ከረበሸ፣ ሰላም ከነሳ፣ ሌሎችም እንደእኛ መሆናቸውን አልተቀበልንም ማለት ነው። እኛ በእነሱ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ስናስብ እነሱ ከራሳቸው ፈቃድ ውጭ በማንም ሰው ተፅዕኖ እንዳይደረግባቸው እንዲጠበቁ የሚያስችል የተፈጥሮ መብት እንዳላቸው ማመን አለብን።

በሌሎች ላይ ተፅዕኖ ከማድረግ የሚበልጠውና ቀድሞ የሚመጣው መብት በማንም ተፅዕ እንዳይደረግብን የሚያስችለን መብት ነው። አንድ ሰው ባለሥንልጣን ወይም ፖሊስ ስለሆነ አንድ የሰረቀን ወይም ያጠፋን ሰው የማስፈራራት ወይም የመደብደብ

መብት አለኝ ብሎ ሊያስብ ይችል ይሆናል። በእኛ ሀገር የምናየው ነገር ነው። ነገር ግን እሱ በሌሎች ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ወይም ሰዎች በፃፉት ውሳኔ፣ ደንብ ወይም ሕግ ከተሰጠው ሥልጣን ቀድሞ የሚመጣው (ሌባ ወይም ጥፋተኛ የተባለው) ሰው ባልተፃፈ የተፈጥሮ ሕግ ያገኘው በማንም ያለመነካት ወይም ያለመደብደብ መብት ነው። ፖሊሱ ወይም ባለስልጣኑ ባለስልጣንነቱን ያገኘው በተፈጥሮ አይደለም። የተወሰኑ ሰዎች ናቸው በሹመት የሰጡት።

እንደውም የእሱን ሥልጣን ብዙ ሰው ላያፀድቀው ይችላል። የተወሰኑ ወይም አያሌ ሰዎች የሥልጣኑን ተገቢነት ላይስማሙበት ወይም ላይቀበሉት ይችላሉ። ሥልጣኑም ዘላለማዊ ሳይሆን ጊዜያዊ ነው። ሌባ የተባለው ሊደበደብ የታሰበው ሰው፣ ሰው በመሆኑ ብቻ ያገኘው እና በሌላ ሰው ያልተሰጠ ያለመነካት መብት አለው። የእሱን ሰው መሆን ደግሞ ሁሉም ሰው ይስማማበታል። ሰው መሆኑ /ሰውነቱ/ መቼም የሚለወጥ አይደለም። ከሞት በኋላ ስለሚኖረው ‘መብት’ ባናውቅም፣ በሕይወት እስካለ ድረስ ሰውነቱ አይሻርም።

ሁላችንም ባንሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስለሰው ልጅ መብቶች ያለንን የግንዛቤ እጥረት (ድንቁርና) በግልፅ የሚያሳዩ ብዙ ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል። ቀኑን ሙሉ መንገድ ላይ ተጎልተው ቀጠን ያለች ቆንጆ ስታልፍ ‹‹አንቺ ቋንጣ››፣ ወፈር ያለች ልጅ ስትመጣ ደግሞ ‹‹አንች ሮቶ፣ ኩንታል›› የሚል ስድብ በመወርወር በሴቶች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የሚውሉ፣ በሰሩት የማይፀፀቱ፣ ይባስ ብሎም በመሳደባቸው የሚኩራሩ ደንቆሮዎች በየሰፈራችን ሞልተዋል። መንገድ ላይ

በአከለው የሻነው

መቼ ይሆን የምንሰለጥነው?በድንገት ያገኘውን አንድ ሕፃን ልጅ ያለፈቃዱ እንዲላካቸው የሚያስገድዱ፣ እምቢ ካላቸው በስድብ አጥረግርገው በመጨረሻ የሚደባደቡ ጎረምሶች በሀገራችን መኖራቸው፣ ስለሰው መብትና ነፃነት ምንነት አንዳች ግንዛቤውና እውቀቱ የሌላቸው ኋላ ቀር ኢትየጵያዊያን መኖራቸውን ያረጋግጥልናል። ታክሲ ውስጥ ካንድ ሌላ ሰው ጋር መሀል ወንበር ላይ ቁጭ እንዳለ የእርስዎን ፈቃድ ሳይጠይቅ በጉልበት እየገፋ ‹‹ጠጋ በል፣ ጠጋ በይ›› የሚለው ተሳፋሪ ስለሰው ነፃነት ያውቃል ሊሉኝ ይችላሉ? የሚገርመው ሰውዬው የሚሰራው አስገርሞዎ፣ ያለእኔ ፈቃድ እኔን ገፍቶ መቀመጡ ጥፋት መሆኑን ይወቅና ሌላ ጊዜ ይህን ጥፋት እንዳይደግም ላስተምረው ብለው አልጠጋም ቢሉት ሊመታዎ ይቃጣዋል። እኔ ይህ ዓይነት ገጠመኝ ስንት ቀን እንደደረሰብኝ ልቆጥርልዎ አልችልም።

ወደ ሥራ አካባቢ ትዝብታችንን ብንቀጥል ብዙ እናያለን። መንገድ ላይ አንድ ትራፊክ ፖሊስና አንድ አሽከርካሪ ሲከራከሩ ወይም ሲወያዩ አይተው ያውቃሉ? ምን ታዝበዋል? እኔ የታዘብኩትን ላካፍልዎ። ሁል ጊዜ የማየው ትራፊክ ፖሊሱ አሽከርካሪን ለመሳደብ የተፈጠረ ይመስል ሲሳደብ ወይም በንቀት ሲቆጣ፣ አሽከርካሪው ደግሞ ሲለማመጥ ወይም አንገቱን ደፍቶ ስድቡን እንደ ምርቃት ሲያዳምጥ ነው። ታዲያ ይህን የሚያደርግ የትራፊክ ፖሊስ ስለሰው ልጅ መብትና ነፃነት ሀሁ ያልቆጠረ መሃይም ነው ብል እውነት ይላሉ ወይስ ውሸት?

የእኛ ነገር አረ ስንቱ ይዘረዘራል! ሁለት ሰዎች ሲከራከሩ

በ ገፅ 23

በ ገፅ 23

መንገድ ላይ አንድ ትራፊክ ፖሊስና አንድ አሽከርካሪ ሲከራከሩ ወይም ሲወያዩ አይተው ያውቃሉ?

ምን ታዝበዋል? እኔ የታዘብኩትን ላካፍልዎ። ሁል ጊዜ የማየው ትራፊክ ፖሊሱ

አሽከርካሪን ለመሳደብ የተፈጠረ ይመስል ሲሳደብ ወይም

በንቀት ሲቆጣ፣ አሽከርካሪው ደግሞ ሲለማመጥ ወይም

አንገቱን ደፍቶ ስድቡን እንደ ምርቃት ሲያዳምጥ ነው።

አቶ አብነት ፈርቶም ይሁን አኩርፎ፣

በፌዴሬሽኑ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በጆርጂያ ዶም ሳይታይ ወደመጣበት

ተመልሷል። ከቶውንም ስታዲየም ገብቶ ዝግጅቶችን

ማየት ካልፈለገ አትላንታ ድረስ መጥቶ ዝግጅቱ

ሲያልቅ ለምን ተመለሰ? በእርግጥ ዝግጅቱን ለማወክ

እና ለመበጥበጥ?... ይኽ የብዙዎች ጥያቄ ነበር።

Page 10: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 200310

p Ç T@ S ´ “ —

“በዓለም ላይ ስቃይ እና መከራ ስለምን በረከተ? እግዚአብሔርስ የሆነ ነገር የማያደርገው ለምንድነው?” በማለት ጠቢቡን ጠየቀው፡፡ እነሆ የጠቢቡ ምላሽ የሚከተለው ነበር፡፡ “በአንድ ትምህርት ቤት የተከሰተውን ላጫውትህ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከሌሎች ትምህርት ቤቶች ብዙም የሚለይ አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ ሲበዛ መጫወት፣ መዘመር እና መጯጯኽ የሚወዱ ነበሩ፡፡ ጉጉነት ተፈጥሯቸው ላይ ተከትቧል፡፡ በእረፍት ክፍለ ጊዜ

ተንኮል መሰራራትን ልምዳቸው አድርገውታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ጉዳት የለሽ ተረቦችን እና ቀልዶችን ነበር የሚያዘወትሩት፡፡ ሆኖም ቀስ በቀስ ይህ ተንኮል ይበልጥ እየከረረና የሚያስቆጣ፣ ጥል የሚያስነሳ ዓይነት እየሆነ መጣ፡፡ “በትምህርት ቤቱ ውስጥ መጠነ ሰፊ ነፃነትን የሚያጣጥሙ ቢሆንም፣ ይህ ነፃነት ዋጋ የማያስከፍላቸው አልሆነም፡፡ ያልጠነከሩ ትናንሽ እግሮች በድንጋያማ መሬት ላይ በጣም በፍጥነት የሮጡ እንደሆን መጋጋጥና መድማታቸው አይቀርምና፡፡ አየህ፣ አንዳንድ ጊዜ እነዚያ ተረቦችና አልባሌ ቀልዶች የሚያስከትሉት የመልስ ምት ይኖራል፡፡ በልበ-ቀና የሚሰነዘሩ ተረቦች እንኳን ወደ ግጭት የሚመሩበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ጩኸታማ ድምፆች ጉሮሮን ያቆስላሉ፤ ለሳል ይዳርጋሉ፡፡ እናም እነዚያ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን የሚወዱትም አንዳንድ ጊዜ የመቁሰል፣ የመድማት፣ እንዲሁም አጥንት የመሰበር ጭምር ጉዳት ይደርስባቸው ይሆናል፡፡ “ይህ ሆኖ ሳለ፣ አንድ ቀን በትምህርት ቤቱ አዲስ ዳይሬክተር ተቀየረ፡፡ ይህ አዲሱ ዳይሬክተር በጣም ቁጡ እና ጥብቅ ነበር፡፡ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ማንኛውንም ዓይነት ባህሪይ የመታገስ ፈቃዱ አልነበረውም፡፡ ስለዚህም የተለያዩ ገደቦችን፣ እቀባዎችን እና ሕጎችን ተፈፃሚ አደረገ፡፡ ተማሪዎቹ ከዚህ በኋላ እንዳይሯሯጡ፣ እንዳይጮሁ፣ እንዳይቃለዱ፣ አለመስማማት ውስጥ እንዳይገቡ፣ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን እንዳይጫወቱ፣ አሊያም ድፍረት የሚጠይቁ እንቅስቃሴዎችን እንዳያደርጉ ክልከላ ወረደባቸው፡፡ ሰው የመሆን አላባ የሆኑ ነገሮችን እንዳይሰሩ ታገዱ፡፡ “እነዚህ ሕግጋት ተፈፃሚ መሆን እንደጀመሩ ትምህርት ቤቱ ወዲያውኑ ተለወጠ፡፡ የሕክምና መስጫ ክፍሉ ዳቦ ሆኗል፡፡ በአንድ ጊዜ አስፈሪ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር እርካታው መጠን አልነበረውም … ተማሪዎች መታመም እስኪጀምሩ ድረስ፡፡ መጀመሪያ አንድ፣ ከዚያ ብዙ ተማሪ ታመመ፡፡ በቅድሚያ ቀላል፣ በኋላ ከባድ ህመም ተበራከተ፡፡ ምክንያቱ ግልፅ ነበር፡፡ ዳይሬክተሩ ነፃነታቸውን ሲነጥቅ፣ የራሳቸውንም አንድ አካል፣ የማንነታቸውን ክፍል ነጥቋቸው ነበር፡፡ “በዓለም ላይ ስቃይ እና መከራ ስለምን በረከተ? ምክንያቱም ስለመረጥነው፡፡ ሁል ጊዜ ሰውን በፈረጅን፣ በተቸን፣ በዋሸን፣ በሰረቅን፣ ባታለልን፣ በአማን፣ በወቀስን፣ በጠላን ቁጥር የመረጥነውን እያደረግን ነው – ከፍርሃታችን የመነጨ አንድን ድርጊት መፈፀምን እንመርጣለም፡፡ እግዚአብሔር ስቃይ እና መከራን ስለምን አያስቆምም? ምክንያቱም እግዚአብሔር ይህንን ለማድረግ የእኛን ነፃ ፈቃድ (ነፃ ምርጫ) መገደብ፣ የእኛነታችንን ክፍል ማስወገድ ይኖርበታል፡፡ በምትኩ እኛው እራሳችን የፍቅርን ተግባራት ብቻ በመምረጥ ስቃይ እና መከራን እንድንቀንስና በመጨረሻም በቁጥጥራችን ስር እንድናደርገው እግዚአብሔር በጥሞና ይጠብቀናል፡፡” ስቃይ እና መከራ የምርጫ ተረፈ-ምርቶች ወይም ያልታቀዱ የምርጫ ውጤቶች ናቸው፡፡ ምርጫዎች ተቀፅላ ውጤቶችን ይፈጥራሉ፡፡ ምርጫን መገደብ፣ ነፃነትን መገደብ ነው፡፡

ጥቃቅን ታሪኮችእነዚህ ተተርጉመው የሚቀርቡት መንፈስ አነቃቂ ጥቃቅን ታሪኮች

ዳንኤል ብራኮ የተባለው ደራሲ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት

“Microstories” በሚል ርዕስ በመፅሐፍ ያሳተማቸው ናቸው ምናልባት እንደእኛ ላሉ ሀገራት ጭቃ ብርቃችን አይደለም። በልጅነታችን እስኪበቃን አድገንበታል፤ እድሜያችን ሲገፋ ደግሞ ክረምት በመጣ ቁጥር

መንገድ አሳጥቶን እንማረርበት ይዘናል። ፈረንጆቹ ግን እንዲህ ቀን ሰይመውለታል።

በዓለም ዙሪያ ባይንሰራፋም በተለያዩ ሀገራት ዓመት ዓመት እየጠበቀ ሲከበር ይኸው ዘንድሮ ለ24ኛ ጊዜ ነው። ስያሜው ‹‹የጭቃ ቀን›› ወይም ‹‹Mud Day›› በመባል ይታወቃል። በተለይ ፈረንጆቹ ጋር ጭቃ ተፈልጉ አይገኝምና አፈር በውሃ ተቦክቶ በላዩ ላይ በመጨመላለቅ ያከብሩታል። በዓመት አንዴ ያለተቆጪና ከልካይ ጭቃ ላይ መንከባለል፣ በተለይ ለሕፃናቱ ወደር የሌለው ደስታ ነው።

ቀደም ሲል (ጁን 29) በኔፓል፣ በአውስትራሊያና በሌሎች ሀገራትም ሕፃናት ከየትምህርት ቤቱ ተሰባስበው በጭቃ ላይ በሮጥና ኳስ በመጫወት የጭቃ ቀንን አክብረው ነበር።

ከቀናት በፊት፣ በጁላይ 12 ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በዌስት ላንድ፣ ሚቺጋን ታላቅ የጭቃ ፌስቲቫል ተካሂዷል። በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሕፃናት 75 ሺህ ሊትር ውሃ እና ከ180 ኩንታል በላይ አፈር በአንድ ላይ በተቀላቀሉበት የጭቃ ቡኮ ሲንከባለሉ ውለዋል። የተለየዩ ጨዋታዎችንም በመጫወት ቀኑን አሳለፈዋል። እንዲሁም ከሕፃናቱ መካከል ንጉስ ጭቃ እና ንግስት ጭቃ ተመርጠው ንግስናን ተችረዋል።

የጭቃ ቀን መከበር ምክንያቱ በተለያዩ ሀገራት የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ቢችልም ለተፈጥሮ፣ ለልምላሜ፣ ለህይወት ክብር መስጠት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ለሕፃናቱ ከፍተኛ መዝናኛ መሆኑም ሳይዘነጋ ነው።

በሰሜን ምስራቅ ብራዚል በምትገኘው ሞሶሮ ከተማ የ11 ዓመቱ ልጅ የማግኔትነት ተፈጥሮ እንዳለው ተዘግቧል።

ፓውሎ ዴቪድ አሞሪም ይባላል። ሹካ፣ ማንኪያ፣ መቀስ፣ ቢላ፣ ፂም መላጫ፣ ጥፍር መቁረጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ስልክ፣ ድስት እና መሰል የማድ ቤት እቃዎች ሳይቀር ሰውነቱ ላይ በማግኔት እንደተሳቡ ሆነው ይጣበቃሉ።

የትምህርት ቤት ጓደኞቹ ‹‹ማግኔቱ ልጅ›› የሚል ቅፅል ስም ያወጡለት ፓውሎ ‹‹በትምህርት ቤት ሁሉም እቃዎችን በሰውነቴ እንዳጣብቅላቸው ይጠይቁኛል›› ይላል።

የጭቃ ቀን ሲከበር

በኦስትሪያ፣ የብራውና የከተማ ምክር ቤት በቀርቡ ተሰብስቦ ከ78 ዓመታት በፊት ለናዚው አምባገነን፣ ለአዶልፍ ሂትለር ተሰጥቶት የነበው የክብር ዜግነት እንዲሰረዝ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

በርግጥ ሂትለር የተወለደው ከብራውና አጠገብ በምትገኝ ሪንሸፈን በምትባል በጣም ትንሽ መንደር ውስጥ ነበር። በ1933 የክብር ዜግነቱንም ያገኘው ከዚችው ትንሽዬ መንደር ነበር። ሆኖም ከጥቂር ዓመታት በኋላ ራንሾፈን የብራውና አካል በመሆኗ የሂትለር የትውልድ ቦታ በብራውና እየተጠራ ይገኛል።

ይህንን እውነታ የያዙ የታሪክ ተመራማሪዎች እንዲህ ዓይነቱ ክብር ዜግነት ከራንሾፈን ወደ ብራውና ሊሸጋገር ይችላል ወይስ አይችለም የሚለውን ሀሳብ መወያያ

ይህ ነገሮችን የመሳብ ተፈጥሮው በጤናው ላይ ምንም ዓይነት ገዳት የማያስከትልበት መሆኑን ማረጋገጣቸውን የሚናገሩት ዶክተሩ ሮዛዳ ሶብሪሆ በ30 ዓመታት ሙያቸው እዲህ ያለ ነገር ገጥሟቸው እንደማያውቅ ይገልፃሉ።

“ማግኔቱ ልጅ” በብራዚል

ከወራት በፊት ቦግዳን የተባለ ሰርቢያዊ ቁሶችን በሰውነቱ ላይ የማጣበቅ ተመሳሳይ ችሎታ እንዳለው ሜይልኦንላይን ዘግቦ የነበረ ቢሆንም የ11 ዓመቱ ፓውሎ ተፈጥሮ ግን የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።

ማድረጋቸው አልቀረም። ይሁንና ግን የብራና የከተማ ምክር ቤት ‹‹መሸጋገር ይቻልም፣ አይቻልም ለማንኛውም›› በሚል የሂትለርን ስም ከክብር ዘግነት መዝገቡ ፍቋል።

የአዶልፍ ሂትለር ሞት ከተሰማ እነሆ 66 ዓመታት ነጉደዋል።

አዶልፍ ሂትለር ዜግነቱ ተሰረዘ

የብራና የከተማ ምክር ቤት ‹‹መሸጋገር

ይቻልም፣ አይቻልም ለማንኛውም›› በሚል

የሂትለርን ስም ከክብር ዘግነት መዝገቡ ፍቋል

Page 11: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —

ጎጂውን ባህል ከጠቃሚው እየለየን ለራሳችንም ሆነ ለምናሳድጋቸው ልጆች ካላስተማርንና ችግሩን ካልፈታን ሁል ጊዜ በባህል እያሳበብን የትም አንደርስም፡፡ እነዚህ የሴት ልጅ ችግሮች ናቸው ማጠንጠኛዎቼ።

የሚገርምሽ ባህሉን እግዚአብሔር ሳይሆን እኛ ነን የፈጠርነው። ሴት ልጅ ሀብት እንዳትወርስ ማድረግ፣ ገላዋን መተልተል፣ መድፈር፣ ያለ እድሜዋ መዳርና መሰል ጥቃቶች በባህል እየተሳበቡ ነው የሚደርሱባት። ይህ ጎጂ ባህል መለወጥ አለበት፣ ሴት ከወንድ እኩል ሰብዓዊ መብት አላትና። ዋናው ነገር በማንም ሳናሳብብ ተፅዕኖን አልቀበልም ማለት አለብን። ለውጥ ከራስ ይጀምራል። እኔ ተፅዕኖ አልቀበልም ካልኩ አልቀበልም። አንቺም የእኔን ተከትለሽ አልቀበልም ማለት ትጀምሪያለሽ። እኔ በግሌ በምንም ዓይነት መልኩ ለተፅዕኖ ተገዢ መሆን አልፈልግም። ባለቤቴም እምቢ ቢል ፈትቼው እቀመጣለሁ። ያለባል መኖር ሐጢያትም አይደለም፣ ሀኪምም አላዘዘልኝም [ኮስተር በማለት]።

እራስሽን ከተፅዕኖ ለማውጣት ስትይ የደረሱብሽ አስቸጋሪ ፈተናዎች አሉ?እኔ ብዙ ተፅዕኖዎችን ለማለፍ በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጫለሁ። ሥራ እስከመልቀቅ ደርሻለሁ። መብቴን ለማስከበር ትልቅ የኮንትራት ውሎችንም አፍርሼ አውቃለሁ። በሴትነቴ ላይ የተቃጡ ትንኮሳዎችንና መሰል ጥቃቶችን ለመከላከል ብዙ ትግልና መስዋዕትነት ከፍያለሁ።

በመድረክ ላይ መናገር ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመንሽም ይጎላል፤ ምስጢሩ ምንድነው?ይኼ በራስ የመተማመን ጉዳይ የእናቴ ተፅዕኖ ይመስለኛል። እኔ አምስት ዓመት ሳይሞላኝ ነው አባቴ የሞተው። እናታችን እኛን ሥታሳድግ ብዙ ፈተናዎችን አልፋለች። ሆኖም መብቷን ለማስከበር ወደ ኋላ የምትል ሴት አልነበችም። በእኛ አገር ሴት ልጅ እንዴት ተደርጎ እርሻ ታርሳለች ይባላል፤ ግን በሬ ጠምዳ እርሻ ታርስ ነበር። ሊነኳት የሚፈልጉትንም በመቃወም መብቷን ታስከብር ነበር። ታዲያ እኛን ሥታሳድገን በባህሉ ተፅዕኖ እያደረገችብን ነበር። እሷ ደፋርና ጠንካራ ሆና ሳለ እኛን ‹አትግቡ፣ አትውጡ፣ ሴት ልጅ ይህን አታደርግም› በማለት ትቆጣጠረን ነበር። እኔ ግን የማይሆን ነገር ሲደረግ ከልጅነቴ ጀምሮ እቃወማለሁ፡፡ እገረፋለሁ፤ ተገረፍኩ ብዬ ያንን ያልሆነ ነገር መቃወሜ አይቀርም። ግርፋቱም ይቀጥላል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው በራስ የመተማመኔ ሁኔታ አየዳበረ፣ አሁን አሁን በተለያዩ መድረኮች ላይ በማነሳቸው

ሀሳቦች ሰዎች ገንቢ አስተያየትና አድናቆት ሲቸሩኝ በራስ መተማመኔ እየዳበረ መጣ ማለት ነው። አሁንም የትኛውም ቦታ ላይ፣ የትኛውም ሰው ባለበት የማምንበትን እናገራለሁ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ከማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር እኩል ነኝ የሚል ጠንካራ እምነትም አለኝ።

በቃልሽ ሳይቀር ስለ ‹Unity› ወይም ‹አንድነት› በእንግሊዝኛ የምትገጥሚው ግጥም አለ፤ እንዴት ልትገጥሚው ቻልሽ?እኔ አብሮ በመስራት አምናለሁ። ልዩነታችን ለአንድነታችን ጠቀሜታ አለው ብዬም አምናለሁ። ብዙ ሰዎች ስለ አንድነት ሲያወሩ ልዩነቱን ማስወገድ ይፈልጋሉ። እኔ ደግሞ ስለ አንድነት ሳወራ ልዩነትን ማጉላት እፈልጋሁ። እስኪ ንገሪኝ፣ ልዩነት ከሌለ ምኑን ነው አንድ የምታደርጊው? አንድ ዓይነትማ ሁሌም አንድ ዓይነት ነው በቃ! እንደውም በቅርቡ በሰላም ስብሰባ ላይ ያቀረብኩትን ግጥም ብዙ ሰው ወዶታል። ይገርምሻል፣ አንድ ሰው ዜማ ደርሼ እና አቀናብሬ እሰራዋለሁ ብሎኝ ልሰጠው ነው። ግጥሙ ‹‹የሰዎች መልክ ሁሉ አንድ ዓይነት ቢሆን አያስጠላም?›› የሚል ይዘት አለው። እኛ’ኮ የተለያየ መልክ ስላለን ነው የምናምረው ያለበለዚያ ሁሉም ነገር አሰልቺ ይሆን ነበር። የሃይማኖት፣ የጾታ፣ የቀለም ልዩነት ይጥፋ ሳይሆን እንዳለ ሆኖ በብዝሃነቱ ውበት ሆኖ ይቀጥል ነው የምለው።

እንዴት ገጠምሽው ላልሽኝ በአንድ ወቅት በአሜሪካን አገር ከተለያየ የዓለም ከፍል የመጣን ሴቶች ‹ግሎባል ውመን ሊደርሺፕ› በሚል ሥልጠና እንወስድ ነበር፡፡ ያኔ እስኪ ሁላችሁም እንደተሰጥዖዋችሁ አንዳንድ ሥራ አቅርቡ ተባልን። ግማሹ ሙዚቃ፣ ሌላው እጅ ሥራ፣ ከፊሉ ስፖርት ሲያቀርብ፤ እኔ ‹‹Women of the World Unite›› በሚል ርዕስ ፅፌ አቀረብኩኝ። መነሻዬ ደግሞ በሥልጠናው ላይ ከተለያየ ዓለም የመጡ ሴቶች ተሳታፊ መሆናቸው ነው። እንዲያውም አንዲት እንግሊዛዊት ሴት ተደስታ የአንገቷን ጌጥ ሸልማኛለች። ከአፍሪካ እንዲህ ዓይነት ግጥም እንዳልጠበቀች በመግለፅ። የሚገርምሽ የተለያየ መድረክ ላይ እንዳቀርበው ሰዎች ግፊት ስለሚያደርጉብኝ አቀርበዋለሁ። ይህ ግጥም ‹‹ጊዜ›› በተሰኘው መፅሐፌም ውስጥ ተካቷል።

ከ‹‹ጊዜ›› ውጭ ሌሎች መጽሐፍት ፅፈሻል?አዎ ፅፌያለሁ። ጊዜ የተሰኘው መፅሐፍ

አ ፍታ1በምን በምን ጉዳዮች ዙሪያ ተሳትፎ ታደርጊያሽ?በብዙ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ለምሳሌ በአከባቢ ጉዳዮች፣ በሥነ-ፅሁፍ፣ በሰላም ነክ ጉዳዮች፣ በቢዝነስ እና በአገር ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ አለኝ። ተሳትፎዬ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችንም ያካትታል። በአጠቃላይ የማልሳተፍበት ጉዳይ ያንሳል ብዬ ነው የማስበው።

ማስተርስሽን ኢንቫይሮመንት ላይ እንደመስራትሽና ጉዳዩም ዓለማቀፋዊና አንገብጋቢ ጉዳይ እንደመሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድርድር የተካሄደባቸው አገሮች ላይ ለምሳሌ ጃፓን (ኪዮቶ)፣ ዴንማርክ (ኮፐንሀገን)፣ ሜክሲኮ (ካንኩን) ድርድሮች ላይ የመካፈል እድል ገጥሞሻል?በእርግጥ በጠቀሻቸው አገሮች ላይ ሄጄ አልተሳተፍኩም፡፡ ሆኖም እንቅስቃሴዎቹን እከታተላለሁ። በመሪዎች ደረጃም ሆነ በአካባቢ ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ባለሞያዎች የሚከናወኑ ተግባራትን አውቃለሁ። ምክንያቱም ጊዜው የመረጃ ሥለሆነ ሁሉን ነገር ታያለሽ ትሰሚያለሽ እዚያ ቦታ ላይ ያለሽ ያህልም ይሰማሻል። ከዚህ በተጨማሪ በእያንዳንዱ የኢንቫይሮመንት ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ አለኝ። ሴቶችን በተመለከተ በተለያዩ መድረኮች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችን በማንሳት ትታወቂያሽ ዋናው ማጠንጠኛሽ ምንድነው?እርግጥ ነው በሴቶች ላይ የማነሳቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። መነሻዬ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጎዱ በመሆናቸው ነው። እንደሚታወቀው በዓለም ላይ የሴቶች ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ነው። ያም ሆኖ ከዓለም ሀብት አንድ በመቶውን ብቻ ነው የሚያስተዳድሩት። ነገር ግን እጅግ አሰልቺውንና አድካሚውን፣ እንዲሁም አብዛኛውን ሥራ የሚሰሩት ሴቶች ናቸው። በተለያዩ መ/ቤቶችም ብትሄጂ ዝቅተኛውን አድካሚ ሥራ ሴቶች ይሰራሉ። ወጣ ብትይ ጉሊትና የመሳሰሉት ቀጥተኛ ያልሆኑ ንግዶች ላይ ያሉት ሴቶች ናቸው። ከዚህም አልፎ የሴቶችን ጉዳይ በተመለተ ብዙ ይዘፈናል፣ ማርች 8 ይባላል ግን ምንም ለውጥ የለም። ለውጥም ቢኖር በጣም አነስተኛና ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት ጋር የማይመጣጠን ነው።

ለዚህ ምክንያቱን ስትጠይቂ ባህሉ ነው፣ ኮሚቴው ነው፣ … መሰል ምክንያቶች ይደረደራሉ። ባህሉም ቢሆን አየር ላይ አይደለም ያለው። ባህሉን የምንተገብረው እኔ፣ አንቺ፣ እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እህት ቤተሰብ ህብረተሰብና መንግስት ነን። ታዲያ በ ገፅ 18

‹‹አንድን ሀገር ደሀ የሚያደርገው የሕዝቡ አመለካከት ነው››

ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን

በቴክሳስ 7 ኪሎ ግራም ልጅ ተወለደአዲስ የተወለደ ሕፃን አማካይ ክብደት 3.4 ኪ.ግ አካባቢ እንደሆነ

ይነገራል። ቴክሳስ ውስጥ የተወለደው ሕፃን ግን 7.26 ኪ.ግ መዝኖ ወላጆቹንም፣ ሰሚንም አስደንግጧል።

የሕፃኑ ቁመት 61 ሴንቲ ሜትር ገደማ ሲሆን እናቱም ‹‹ገዝተን ያዘጋጀንለት ብዙዎቹ ልብሶች በጣም ትናንሽ ናቸው›› በማለት ያልጠበቀችው እንደተከሰተ መግለፅዋ ተዘግቧል።

እንደዚህ ትልቅ ሆነው የሚወለዱ አራስ ልጆች በሕክምና ቋንቋ ‹‹ማክሮሶሚያ›› በመባል ይጠቀሳሉ። እናም እንዲህ ትልቅ ሆኖ ለመወለድ ጤና ነክ ችግሮች መንስዔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሙያዎቹ ይጠቁማሉ።

ከአራት ኪ.ግ ተኩል በላይ የሆኑ አራስ ልጆች ከአማካዩ ክብደት በጣም የተለቁ ተደርገው እንደሚወሰዱ ‹‹babycentre.com›› የተባለው ድረ-ገፅ ያብራራል። እንዲህ ዓይነት ክብደት ያላቸው ሕፃናት ለመወለዳቸው በእርግዝና ወቅት በደም ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን መኖር ሊሆን እንደሚችል የጠቆመው ድረ-ገፁ በእርግዝና ጊዜ የነበረ አመጋገብና የሰውነት መጨመር ተጠቃሽ መንስዔዎች እንደሚሆኑ አስታውቋል።

የሕፃኑ ጾታም ተደራቢ መንስኤ ሊሆን ይችላል ተብሏል፤ ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ ክብደት የሚመዝኑት አራስ ሕፃናት ወንዶች ናቸው።

በሄደችበት ስለ ሴት ልጅ መብት ተናግራ አትጠግብም። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢንቫይሮንመንትና በዴቨሎፕመንት የማስተርስ ዲግሪዋን ሰርታለች፤ እዚያው ዩኒቨርስቲ ‹‹ኢንተርፕረነርሺፕ›› ታስተምራለች፤

ፒኤችዲዋን ለመስራት ፕሮፓዛል እያዘገጀች ትገኛለች። ገጣሚ ናት፤ ፀሐፊ ናት። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች መፅሐፎችን አሳትማለች፤ ለመታተም የተዘጋጁ ደግሞ አስር የሚሆኑ አሏት። ‹‹ባለቤቴ እምቢ ቢል ፈትቼው እቀመጣለሁ፤ ያለባል መኖር ሐጢያትም አይደለም፣ ሐኪምም አላዘዘልኝም›› ከምትለው

ከወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን ጋር ናፍቆት ዮሴፍ አንዳፍታ አውግታለች።

‹‹የኔ ጀግኖች›› በሚል ርዕስ የስዕል አውደ ርዕይ ይከፈታልበቀጣዩ አርብ ‹‹የኔ ጀግኖች›› በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ

ሙዚየም ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ የስዕል አውደ ርዕይ እንደሚከፈት አዘጋጁ ሰዓሊና መምህር ሀይሉ ክፍሌ ለአውራምባ ታይምስ ገልጿል። ይህ የስዕል አውደ ርዕይ 31 ምስሎችንና ሌሎች ከወረቀት ተልጠው የተሰሩ አስር ምስሎችንም እንደሚያካትት የገለፀው የአውደርዕዩ አዘጋጅ ወረቀትን በመላጥ ምስሎችን መስራት አዲስ የአሰራር መንገድ እንደሆነ አስረድቷል። አውደ ርዕዩ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያልም ተብሏል።

ሰዓሊና መምህር ሀይሉ ክፍሌ አውደ ርዕዩን ‹‹የኔ ጀግኖች›› ያለበትን ምክንያት ‹‹የህይወቴ ጀግኖች ከሆኑት እናትና አባቴ በተጨማሪ በህይወት ጉዞዬ ላይ ጥርጊያ መንገዴን ላሳመሩልኝ እና በጥሩ ጎናቸው አርአያ ለሆኑኝ ሁሉ መታሰቢያ ይሆንልኝ ዘንድ ነው›› ብሏል።

‹‹መፈንቅለ ሴቶች›› እና ‹‹ወደመጣሁበት››ፊልም ይመረቃሉበዘላለም ይታገሱና በተመስገን አለማየሁ የተደረሰውና በሚካኤል

ል/ሰገድ ፕሮዲዩሰርነትና ዳይሬክተርነት የተዘጋጀው ‹‹መፈንቅለ ሴቶች›› ፊልም ነገ ከቀኑ በሰባት ሰዓት በአለም ሲኒማ ይመረቃል። በመብረቅ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ይሄው ፊልም የ1፡35 ሰዓት ርዝመት ያለው ሲሆን ሰባት መቶ ሺህ ብር እንደወጣበትና ሰርቶ ለማጠናቀቅ የስድስት ወር ጊዜ መፍጀቱን አዘጋጆቹ ለአውራምባ ታይምስ አስታውቀዋል። በፊልሙ ላይ ደራሲ ስብሀት ገብረእግዚአብሄርን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂና አንጋፋ ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

እንዲሁም በጌታቸው አያልቄ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው የስንታየሁ ሲሳይ ‹‹ወደመጣሁበት›› የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ከነገ በስቲያ ሐምሌ 11 ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር በአዲስ አበባ ባሉ ሲኒማ ቤቶች ፤ ሐምሌ 17 በመላው ኢትዮጵያ ይመረቃል። ከዚህ በፊት በሙዚቃ ስራዎቻቸው የሚታወቁት አቢ ላቀው እና ሳሚ በየነ በመሪ ተዋናይነት የተጣመሩበት ሲሆን አልማዝ ሐይሌ ፅዮን ግርማ ሜሮን ቴዎድሮስ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

አዳም ረታ ዛሬ ከአድናቂዎቹ ጋር ይገናኛልግራጫ ቃጭሎች፣ አለንጋና ምስር፣ እቴሜቴ ሎሚሽታ፣

ከሰማይ የወረደ ፍርፍር እና ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ በሚሉ ልብ-ወለድ መፅሀፎቹና በኢትዮጵያ ሥነ-ፅሁፍ ታሪክ በረጅምና የአጭር ልብ-ወለድ አፃፃፍ ስልቱ የሚታወቀው ደራሲ አዳም ረታ ዛሬ ረፋድ ላይ በሀገር ፍቀር ቴአትር አዳራሽ ከአድናቂዎቹ ጋር ይገናኛል። ደራሲው ከረጅም የባህር ማዶ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ መመለሱን ምክንያት በማድረግ ይህን መድረክ ማዘጋጀቱን የማህሌት አሳታሚ ድርጅት ሀላፊዎች የገለፁ ሲሆን በዚሁ የኪነ-ጥበብ መድረክ ላይ በደራሲው ሥራዎች ዙሪያ ጥናት ያካሄዱ የዩኒቨርስቲ ምሁራንና ሌሎች የስነ-ፅሁፍ ተንታኞች ተገኝተው ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡም አዘጋጆቹ ለአውራምባ ታይምስ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። እንደ አዘጋጆቹ ገለፃ በፕሮግራሙ ላይ የደራሲው ትረካዎች ተቀንጭበው የሚቀርቡ ሲሆን ግጥሞችም ይነበባሉ። ደራሲው በእለቱ በስራዎቹ ዙሪያ ከአድናቂዎቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል።

Page 12: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

የቢስ አትክልትና ፍራፍሬ አክሲዮኖች

በፍጥነት በመሸጥ ላይ ናቸው።

እርሶም ፈጥነው የዚህ ግዙፍና ትርፋማ

አክሲዮን ባለቤት ይሁኑ!!!

12

ኔቸርየእንጉዳይ ምርት

በቤትዎ ውስጥ እንጉዳይ በማምረት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?ከ 100 ብር ጀምሮ ወጭ በማድረግ አምራች መሆን እንደሚችሉስ ያውቃሉ?ማምረት በጀመሩ በ መጀመሪያው ወር ብቻ ወጭዎን መመለስ እንደሚችሉስ ያውቃሉ?

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችየእንጉዳይ

አመራረት ሙሉ የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና እንሰጣለን

እንጉዳይ ማምረት ለሚፈልጉ የ እንጉዳይ ዘር እና ሙሉ የማምረቻ መሳርያዎችን እናቀርባለን

ያመረቱትን የእንጉዳይ ምርት እንገዛለንአድራሻችን: ከ ለም ሆቴል ወደ ሾላ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሴፍቲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የሚገኝበት ህንፃ ስር ማክሲ ገበያ ውስጥስልክ:

0920641808

0912610300

ባቀረበችው ጥያቄም መሰረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ሪፐብሊክ ደቡብ ሱዳንን የድርጅቱ 193ኛዋ አባል ሀገር መሆኗን በይፋ ያወጀው ከሁለት ቀናት በፊት ነበር። ውሳኔውም ራሷን የቻለች ሉዓላዊ ሀገር ለመመስረት ለአስርት ዓመታት የተካሄደውንና የሚሊየኖችን ሕይወት የቀጠፈውን የትጥቅ ትግል ለአንዴና ለመጨረሻ የቋጨ ተብሎለታል።

ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች የሞቱበት በሰሜንና ደቡብ ሱዳን መካከል የተካሄውን የ20 ዓመታት ጦርነት በቋጨውና በ2005 በተደረገው የሰላም ሥምምነት አማካኝነት ነበር የደቡብ ሱዳን የነፃነት ህዝብ-ውሳኔ የተካሄደው።

ከሱዳን ለመገንጠል በታህሳስ ወር ውስጥ ደቡብ ሱዳንያዊያን ድምፃቸውን ከሰጡ እና ‘መገንጠል’ የሚለው ውሳኔያቸው በካርቱም መንግሥት ተቀባይነት ካገኙ በኋላ ነበር ባለፈው ቅዳሜ በዋና ከተማዋ ጁባ ነፃነቷን ይፋ ላደረገችው ደቡብ ሱዳን ጉባዔው ካለምንም ተቃውሞ የአባልነት ይሁንታውን የሰጠው።

ከደቡብ ሱዳን በፊት ተ.መ.ድ ለመጨረሻ ጊዜ በአባል ሀገርነት የተቀበላት ከሰርቢያ የተገነጠለችውን ሞንቴኔግሮን ነው - በ2006። የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባዔ ከስድስቱ የድርጅቱ ዋና ዋና አካላት መካከል አንዱ ነው። በሁሉም አባል ሀገራት የሚወከለው ይህ ጉባኤ ሲሰየም ሁሉም ሀገራት እኩል አንድ አንድ ድምፅ አላቸው።

በሃይማኖት፣ ብሄር፣ ርዕዮተ-ዓለም፣ የተፈጥሮ ኃብት - በተለይ በነዳጅ ዘይት - ወዘተ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለዓመታት የተካሄደው ጦርነት ደቡብ ሱዳንን እጅግ እጅግ አቆርቁዟታል። በዚህም ምክንያት መንግስቷ በኢኮኖሚ ተኮር ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ከእርስ በእርስ ጦርነቱ በኋላ ያለው ሁኔታ የሀገሪቱን ጥንሬና ስኬታማ የፖሊሲዎች ትግበራን

ለማጤን እንደሚረዳ ታዛቢዎች ይናገራሉ። እንደሚባለው የተቀናጀ ዕቅድና የበጀት መሰናዶ ማድረግ የደቡብ ሱዳን መንግስት ትርጉም ያለው ስኬት ያስመዘገበበት አንዱ እንቅስቃሴው ነው። ይህም ስኬት የተመዘገበው በሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር ውጤታማ ቢሮክራሲ ነው።

ቢሆንም የአንድ መንግስታዊ አካል እንቅስቃሴ ብቻውን ሀገርን አያለማምና የሀገሪቱ መንግስት በሌሎች ኢኮኖሚን በሚያሳድጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ አስገድዶታል። እናም ፈጣን መንግስታዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ትገኛለች - አዲሷ ሀገር። ባለፈው ማክሰኞ የሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር እንደገለፁት የሀገራቸውን

ብሔራዊ የነዳጅ ዘይት ካምፓኒና የነዳጅ ዘይት ገበያውን ለማጠናከር መንግስታቸው ከአንድ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዘይት ድርጅት ጋር ተጣምሯል።

‹‹ናየል ፔትሮ›› ተብሎ የተሰየመው ይህ አዲስ ካምፓኒ 51 በመቶ የሚሆነው ድርሻ በባለቤትነት የሚያዘው በናየልፔት (የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ዘይት ካምፓኒ) ሲሆን፣ የተቀረው በግሌንኮር ኢንተርናሽናል እንደሚያዝ ተነግሯል።

ከሐምሌ 9/2011 አንስቶ የደቡብ ሱዳን ንብረት መሆናቸው የታወቁ በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ ያሉ የነዳጅ ዘይት ማውጫዎች በቀን 375 ሺህ ገደማ ድፍድፍ ዘይት ያመነጩ ነበር። ዋነኞቹ አውጮዎች የቻይና ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን፣

የማሌዢያው ፔትሮሊየም ብሔራዊ ካምፓኒ እና የሕንዱ የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ኮርፖሬሽን ናቸው።

ለዓመታት ከደቡብ ሱዳን ይወጣ የነበረው የነዳጅ ዘይት ትርፍ (ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል) በሱዳን የካርቱም መንግስት ነበር የሚዛቀው። በ2005 የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከተቋጨ በኋላ ከደቡብ ሱዳን ክልል ከሚወጣ ነዳጅ የሚገኝ ትርፍ ለሁለቱም ሱዳኖች በአንፃራዊ እኩሌታ እንዲከፋፈል ሆኗል።

እስከዛሬ ሳምንት ድረስ በአፍሪካ በቆዳ ስፋት አንደኛ የነበረችው ሱዳን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጣችው በ1956 ውስጥ ነበር። አሁን ደግሞ ደቡብ ሱዳን ራሷን ችላ ሀገር ሆናለች። ሀገሪቱም ነፃነቷን ከማወጇ ከሁለት ቀናት አስቀድሞ ጊዜያዊ ሕገመንግስት አፅድቃለች። የ2005ቱን የሽግግር ሕገመንግስት የሻረው ይህ ሕገመንግስት ፕሬዝዳንታዊ የመንግሥታት ሥርዓት አቋቁሟል። ፕሬዝዳንቱም የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር፣ ርዕሰ መስተዳደር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መሆኑን ይደነግጋል።

የ ኤ ስ . ፒ . ኤ ል . ኤም መስራች ጆን ጋራንግ በሐምሌ 30/2005 እስካረፉበት ጊዜ ድረስ የደቡብ ሱዳን ራስ-ገዝ መንግሥት የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። የእርሳቸውንም ሞት ተከትሎ ምክትላቸው የነበሩት ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት በነሐሴ 11/2005 ላይ ነበር።

በሀገሪቱ ሕግ የማውጣት ሥልጣን የተሰጠው ለመንግስት እና ለደቡብ ሱዳን ሕግ አውጪ ምክር ቤት ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የሀገሪቱ ላዕላይ የሚያደርግ የፍትህ ሥርዓትንም አቋቁሟል - ሕገመንግስቱ።

በአስር ክፍለ አገራት የተከፋፈለችው ደቡብ ሱዳን፣ ሶስት የሱዳን ታሪካዊ ክልሎችን ባማከለ መልኩ ነው ክፍፍሏ የተቀመረው። እነርሱም ባህር ኤል ጋዛል፣ ኢኳቶሪያ እና ግሬት አፐር ናየል ናቸው። [ባህር ኤል ጋዛል፡- ሰሜን ባህር ኤል ጋዛል፣ ምዕራባዊ ባህር ኤል ጋዛል፣ ሌክስ እና ዋራፕ፤ ኢኳቶሪያ፡- ምዕራባዊ ኢኳቶሪያ፣ ማዕከላዊ ኢኳቶሪያ እና ምስራቅያዊ ኢኳቶሪያ (የሀገሪቱ ዋና ከተማ መገኛ)፤ ‹‹ግሬተር አፐር ናየል፡- ጆንግሌይ፣ ዩኒቲ፣ እና አፐር ናይል። በተጨማሪ እነዚህ አስር ክፍለ ሀገራት በ86 ንኡስ ግዛቶች የተከፋፈሉ ናቸው።

አዲሷ አፍሪካዊት ‘ሙሽራ’ - ደቡብ ሱዳን

Page 13: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

እ ን ግ ዳ

14

ዓ ለም አቀፍ

ተገንዝበው በሚያስሟሟቸው ነጥቦች ላይ ለመነጋገር ይወስናሉ። ውሳኔውም በገዥው ኤሊት በኩል ያለው አፈና መቅረትን፣ እና በሌላኛው ጥግ ባሉት ዘንድ የሚደረገውን የሥርዓቱን የማስወገድ ጥሪ ማክተም ውጤት አለው ማለት ነው። ይህም በሥርዓቱ ላይ ለሚደረጉ ማሻሻያዎች በአግባቢ ጭብጦች ላይ ለመስማማት ሁለቱም ያላቸውን ዝግጁነት የሚያሳይ ነው።

እያልኩ ያለሁት የኢትዮጵያ ሁኔታ በተጨባጭ ፖለቲካዊ መፍትሄ ዕጦትን የሚያሳይ ነው የሚል ነው፤ የድህረ ምርጫ 97 የሥርዓቱ በተግባር የታየ የአፈና አዝማሚያ ተቃዋሚ ኃይሎችና መሪዎች፣ ከትጥቅ ትግል (ከዚህ አይነት ትግል ጋር ያሉ አጠራጣሪነቶች እንዳሉ ሆነው)፣ እና ስኬታማነቱ በአቶ መለስ የዴሞክራሲያዊ መብቶች መጠበቅ ላይ ከተወሰነው ከሰላማዊ ትግል አንዱን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል። ሶስተኛው ሊሆን የሚችለው የአረቡን ዓለም እያንቀጠቀጠ እንዳለው አይነት ያለ ሕዝባዊ ተቃውሞ ነው። ምንም እንኳን መቼና እንዴት ይከሰታል የሚለውን ማንም ሰው የማያውቀው ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝባዊ ተቃውሞ ይከሰታል አይከሰትም የሚለው ዝቅተኛ ግምት ሊሰጠው አይገባም። አንድ ነገር ግን የተረጋገጠ ነው፤ የሆነ ነገር ካልተደረገ በስተቀር መከሰቱ አይቀርም።

ዴሞክራታይዜሽንየዚህ ጽሑፍ ዓላማ

ስለዴሞክራሲና ስለኤሊቶች ድርሻ ስንወያይ ልናጤናቸው የሚገቡን የተወሰኑ ነጥቦች ላይ አፅንኦት መስጠት ነው። ባነሳሁት ሃሳብ ላይ ጠንካራ መከራከሪያ ካቀረቡ ሰዎች መካከል አብይ ተ/ማርያም መገንታ እና እስክንድር ነጋ ያነሱት ነጥብ ተጠቃሽ ነው። ካለሕዝብ ንቁ ተሳትፎ ኤሊት-መር ፖለቲካዊ ለውጥ ዴሞክራሲያዊ ውጤቶች አይኖረውም የሚል ነው ያነሱት ነጥብ። ከእነርሱ ጋር ሙሉ በሙሉ የምስማማ ቢሆንም፣ ዴሞክራሲ እንዴት ይተገበራል የሚለው ጉዳይ ዴሞክራሲ እንዴት እውን ይሆናል ከሚለው ጭብጥ ጋር የተለያየ ነው የሚል ምልከታ ነው ያለኝ። ዴሞክራሲ፣ ጥቅምን ለማስጠበቅ አልያም ለማራማድ አመፅን እንደአማራጭ የማይወስድ የሰለጠን ባህርይን የሚጠይቅ ነው። አመፅ አንዴ ከምስሉ ውጭ ከሆነ፣ በቁሳዊና በሥልጣን ላይ ያሉ አለመግባባቶችን ለመፍታት ድርድርና ስምምነት ከማድረግ በስተቀር ሌላ ምንም የሚቀር ነገር የለም።

ዋናው ጉዳይ፣ ኤሊቶች ሌላኛውን ወግን በበላይነት ከመግዛት እና ከማግለል ይልቅ ድርድርና ስምምነትን እንዲሹ የሚያስገድዳቸው ምንድ ነው የሚለው ነው። የዴሞክራሲያዊ ለውጦች ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ለሥልጣንና ለጥቅሞች በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ትግሎች የአጣቢቂኝ ደረጃ ሲደርሱ ወይም የጋራ ሥጋት ሲጋረጥባቸው፣ ለምሳሌ በውጪ ኃይል የሚደረግ ወረራ ወይም የእርስ በእርስ ግጭትና ጦርነት፣ ተፎካካሪ ኤሊቶች በሚያስሟሟቸው ነጥቦች ላይ የመደራደር አዝማሚያ ይኖራቸዋል። ለምሳሌ፣ ኤሊቶች የድርድር መፍትሄ እንዲቀይሱ ከሚያነሷሷቸው ምክንያቶች አንዱ፣ አብዛኛውን ጊዜ ከተለመደው ያፈነገጡና ፅንፈኛ ኤሊቶች (አክራሪ ምሁራን፣

አክራሪ ሃይማኖተኞች፣ ተገንጣይ መሪዎች ወዘተ) የፖለቲካ ሥልጣን እንዲይዙ መንገዱን ለያመቻቹ የሚችሉ አብዮቶች ሚያሳድሩባቸው ፍራቻ ነው። ስለዚህም፣ ተራማጅ ሃሳቦች ወይም እምነቶች ካላቸው ወሳኝነት አንፃር፣ ዴሞክራሲያዊ አዝማሚማን ማመንጨት ከእውነታው ጋር የሚጣጣም ነው፤ ርዕዮተ-ዓለማዊ ዕምነቶች በተጨባጭ ለመሳካት፣ ለዴሞክራሲያዊ ለውጦች ባሉ ፍላጎቶች መደገፍ አለባቸው። በሌላ አገላለፅ፣ ለዴሞክራሲ መተግበር አስፈለላጊ የሆኑ ሁኔታዎች የሚመጡት ባላንጣ ኤሊቶች አለመግባባቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ ቁርጠኛ ሲሆኑ ነው፤ ያም ውሳኔ በራሱ የረዥም ጊዜ ፍላጎቶቻቸውን ለማስጠበቅ በይበልጥ የተሻለ መንገድ የመንደፍ ቀመር ውጤት ነው።

እርግጥ ነው ለዴሞክራሲ የተሰጠው የተለመደው ትርጉም የህዝብ አገዛዝ የሚለው እንደሆነ አውቃለሁ። ቢሆንም፣ ያ ማለት ህዝቡ በተጨባጭ ይገዛል ማለት አይደለም። ከዚህ ይለቅ፣ ህዝቡ የሚመራው ማን እንደሆነ ለመወሰን ሥልጣን ያለው መሆኑንና የሚመራውም ለህዝቡ ተጠያቂ መሆኑን የሚያመላክት ነው። መንግስታዊ ሥልጣን መያዝ የፖለቲከ ኤሊቶች ጉዳይ እንጂ የተራው ህዝብ ጉዳይ አይደለም። ከዚህም በላይ፣ ዴሞክራሲ የአለመግባባቶች አለመኖርን ሳይሆን የሚያመላክተው፣ እንደውም በይበልጥ የአለመግባባቶቹን መኖር ነው፤ በትክክልም በካርል ማርክስ እንደተገነዘበው ነው፡- ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠ ዕለታ፣ የመንግሥታዊ ሥልጣንና የፖለቲካ ፍፃሜ ይሆናል።

ኤ ሊ ቶ ች አለመግባባቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ በሚወሰኑት ውሳኔና በህዝባዊ ሥልጣን መካከል ተፈጥሮዓዊ ቁርኝት መኖሩ ሊታወቅ ይገባል። የኤሊቱ ኃይል መጠቀም ማቆም ወዲያው አለመግባባቶችን ገለልተኛ ሆኖ የሚያስታርቅ አካል አስፈላጊነትን የማያጠራጥር ያደርጋል። ይህም በይበልጥ የህዝብን ድምፅ ለማግኘት በሚደረግ ነፃና ፍትሃዊ ፉክክር አማካኝነት ተግባራዊ ይሆናል። እንደ መደራጀትና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት እና የግለሰብ መሰረታዊ መብቶች ያሉ መሰረታዊ መብቶችን ካላከበረ በስተቀር፣ የሚደረገው ፉክክር መቼም ነፃና ፍትሃዊ ሊሆን እንደማይችል ሳታለም የተፈታ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ህዝቡ አስፈላጊው ሥልጣን ካልተሰጠው በስተቀር በእርሱ አማካኝነት የሚደረግ ምንም የግጭቶች አፈታት ሂደት አይኖርም።

የራሳቸውን ፍላጎት ከህዝቡ መሻቶች ጋር አስተሳስረው ማስቀመጥ የተካኑ የኤሊት ቡድኖች በምርጫ አማካኝነት ሥልጣን የመያዝ ዕድላቸው የላቀ ነው። ያም ሆኖ ግን፣ በኤሊቶች እና በህዝቡ መካከል የሚኖረው አይቀሬ የጥቅሞች አለመጣጣም ተፎካካሪው ኤሊት ቡድን በተራው ሥልጣን የመያዝ እድል እንዲኖረው የሚያስችል ዕድል የሚያቀርብ ነው።

አስቀድሜ የፃፍኩት ፅሁፌ ዋና መልዕክት በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መፍትሄ አለመኖር ላይ ያሰመረ ነበር። የ2002 ምርጫ፣ አቶ መለስና ተከታዮቻቸው ለመንግሥት ሥልጣን ከሚደረግ አንድ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ካለው እሳቤ እጅግ ርቀው መሄዳቸውንና በማናቸውም መንገዶች ሥልጣን ላይ ለመቆየት እንደቆረጡ

በማያሻማ መልኩ ያሳየ ነበር። ይህ የኋሊት ጉዞ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ቡድኖችን ከንቱ የሚያደርጋቸውና በነፃ ምርጫ አማካኝነት የሚመጣን የለውጥ ተስፋ እንዲያከተም የሚያደርግ ነው። እናም፣ የፖለቲካ መፍትሄ አለመኖሩ ተጨባጭ ነው፤ አቶ መለስ በልማታዊ መንግሥት መከራከሪያቸው እንዳሰፈሩት በፈጣን ኢኮኖሚ አማካኝነት ተቃዋሚዎችን ማግለል አይቻላቸውም፤ እንዲሁም ተቃዋሚዎች በምርጫ ድል አማካኝነት አቶ መለስን ከሥልጣናቸው ማውረድ አይቻላቸውም።

እርግጥ ነው አሁን ሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ ለማስወገድ የትጥቅ ትግልን እንደ ብቸኛ መንገድ መከተል ምንም መውጫ ቀዳዳ አይኖርም። እኔን የሚያሳስበኝ የትጥቅ ትግል የመሳካቱ ጉዳይ ሳይሆን የዴሞክራታይዜሽን ችግርን የማይቀርፍ መሆኑ ነው። የዴሞክራታይዜሽን ችግርን ከመቅረፍ እጅግ በራቀ መልኩ የፖለቲካ ሥልጣን በትጥቅ ትግል መያዝ ልክ በህወሀትና ሻዕቢያ ታሪክ እንደታው፣ በሌሎች ላይ ገደብ የለሽ ቁጥጥር የማድረግ አዝማሚያን የሚፈጥር ነው። እናም፣ እውነተኛ ዴሞክራታይዜሽን ከተፈለገ ከድርድርና ህብረት ማምለጥ አይቻልም።

በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል መፍትሄ ማጣቱ አንድ ውጤት ብቻ ነው ሊያስከትል የሚችለው፤ ህዝባዊ አመፅ ወይም አብዮት። ያ መቼ እንደሚከሰት ካለመታወቁ በተጨማሪ፣ በብሄር ውጥረቶች ፅንፍ በያዘ ማህበረሰብ ውስጥ ግን መከሰቱ አያጠራጥርም። ከዚህ ፖለቲካዊ መፍትሄ መታጣትና በሀገሪቱና ለሥልጣን በሚፎካከሩ ኤሊቶች ላይ ከሚኖረው አስከፊ አደጋ አንፃር፣ የሁሉንም የረዥም ጊዜ ጥቅሞች መመልከት ጊዜውን የጠበቀና አስፈላጊ ነው።

ለእኔ አጠያያቂ ሆኖ የማገኘው እውነተኛ የዴሞክራሲ ኃይሎች ህዝባዊ አመፅ ለመምራት ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት ዝግጁ ናቸው የሚለው ግምት ነው። ከዚህ የባሰ የዋህነት የለም፤ ስለዴሞክራሲና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሰዎች በማውራታቸው ያወሩትን ለመተግበር ፍቃደኛ ናቸው ማለት አይደለም።

ብዙ ጊዜ ኤሊቶች ዴሞክራሲያዊ መፈክሮችን ህዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ይጠቀማሉ፤ ምንም እንኳን እውነተኛ እቅዳቸው የራሳቸውን አይነኬ የሆነ መንግሥት መመስረት ቢሆንም። በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም በፖለቲካው ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላት ይህን ዕውነታ አስረግተው ያውቁታል። ሁሉን የማጣት አደጋ የተጋረጠባቸው፣ ገና ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት ካላቸው በበለጠ ጠርጣራ ቢሆኑ አይደንቅም። ከዚህም በላይ ዴሞክራሲ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥር ሊይዝ አይችልም። ጥበቃ የሚደረግላቸው የተቋማት ግንባታ፣ የባህል ለውጥ፣ ህዝባዊ የሥልጣን ባለቤትነት፣ እንዲሁም በኤሊቶች መካከል መተማመንን ይሻል። ባደጉት ዴሞክራሲያዊ ሀገራት ውስጥ እንደታየው፣ ዴሞክራሲ ተደጋጋሚ ጋሬጣዎች ቢጋረጡበትም እመርታ በሚያሳዩ እርምጃዎች አማካኝነት ነው የተሳካውና የፀናው።

ዴሞክራታይዜሽን... በአስኮ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፡-

አንድ ጄሪካን ውሃ በ10 ብር እየተሸጠ ነው

በኤልያስ ገብሩ

ከአስኮ እስከ ፊናንስ፣ ዊንጌት ቀለበት መንገድ ድልድይ ድረስ እየተሰራ በሚገኘው መንገድ ምክንያት የውሃ ፓምፕ ፈንድቶ 123 ፎቆች በሚገኙበት አስኮ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የመጠጥ ውሃ በመቋረጡ፣ ካለፉት 10 ቀናት ወዲህ 20 ሊትር በሚይዝ ጄሪካን ውሃ በ10 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ለአውራምባ ታይምስ ገለፁ።

በመንገዱ ግንባታ ምክንያት ቀደም ሲል እየተቆራረጠ የሚመጣ የውሃ አቅርቦት መኖሩን የሚናገሩት የኮንዶሚኒየም ቤት ነዋሪዎች፣ በተለይ ከ10 ቀናት ወዲህ ምንም ዓይነት የውሃ አቅርቦት ባለማግኘታቸው የተነሳ ማዘጋጃ ቤት በቀን አንድ ቦቴ መኪና ውሃ በማቅረብ እያከፋፈለ ይገኛል።

ሆኖም ግን እዚያው ውሃ ቀድተው ከላይ ለተጠቀሰው የውሃ ሊትር በ10 ብር ለነዋሪው ሕብረተሰብ እየሸጡ የሚገኙ ሰዎች በመኖራቸው ምክንያት ነዋሪዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። እንዲሁም የተከሰተው የውሃ ችግር በአስቸኳይ እንዲስተካከልላቸው ነዋሪዎቹ የሚመለከተውን አካል በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ አስግቷል

- ድርቅና ርሀብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

በሱራፍኤል ግርማ

ከ4.5 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በድርቅና ረሐብ እየተሰቃዩ በሚገኙባት ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ ደግሞ ሌላ ስጋት እንደጋረጠ ተገለፀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዜና ወኪል የሆነው ኢሪን፣ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲን ጠቅሶ በድረ-ገፁ እንዳስነበበው፣ ከሰኔ - መስከረም በሚዘልቀው የክረምቱ ወራት ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን ሊጥል ይችላል። በዚህም የተነሳ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚገኙት የጣና ዙሪያ፣ ኦሞ እና አዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ አንዣቦባቸዋል።

ለኢሪን አስተያየተቸውን የሰጡት በሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር አቶ ድሪባ ቆሪቻ፣ ‹‹ረባዳማና የወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች እንደ ሁልጊዜው ጎርፍ ሊያጠቃቸው ይችላል። ክረምቱ እየገፋ ሲሄድና ከባድ ዝናብ መጣል ሲጀምር ደግሞ በማንኛውም አካባቢ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያጋጥም ይችላል›› ብለዋል።

ምንም እንኳን በተጠቀሱት አካባቢዎች ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋ ስጋት ቢኖርም፣ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ በአስከፊ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ሐምሌ 4 ቀን 2003 ዓ.ም የሰብዓዊ ዕርዳታ ጥሪ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ያቀረበ ሲሆን፣ በመንግስት ስሌት መሠረት ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን ነው። የ398 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዕርዳታም ጥያቄ ቀርቧል።

ነገር ግን በኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቃል-አቀባይ የሆኑት ጁዲት ሹለር የእርዳታ እጥረት መኖሩን ለኢሪን ገልፀዋል። ከሚፈለገው የዕርዳታ መጠን ውስጥ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ያህል (112 ማሊዮን ዶላር ግምት ያለው) እጥረት እንዳለ የተናገሩት ሹለር፣ ‹‹በእጥረቱ የተነሳም የምናከፋፍለውን የሬሽን መጠን ለመቀነስ ተገደናል›› ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በረሐብና በጦርነት የተነሳ ከሶማሊያ ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ችግሩን አባብሶታል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ሁኔታ ‹‹በምድር ላይ የተደቀነ አስከፊ የምግብ ዕጥረት›› ሲል የገለፀው ሲሆን፣ ‹‹ክርስቲያን ኤይድ›› የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ደግሞ በበኩሉ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገቢውን ዕርዳታ ካልለገሰ ታይቶ የማይታወቅ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያጋጥም አስገንዝቧል።

ለዶክተሮች አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት ተዘጋጀ

- በሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ቀዳሚ መስፈር ሆኗል

በናፍቆት ዮሴፍየፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ የሚውልና በሣይንስ ትምህርት

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ባለሙያዎች ለዶክተርነት የሚሰለጥኑበት አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት መቅረፁን ይፋ አድርጓል፡፡ ለዚህም ሲባል ከ10 ዩኒቨርስቲዎችና ከሶስት ሆስፒታሎች የተውጣጡ 75 ያህል አስተማሪዎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በአዳማ ከተማ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

ሥልጠናው ለሦስት ሣምንት እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ጌታቸው አክለውም ከዚህ ቀደም ዶክተሮች ተምረው ሲወጡ በህክምና ላይ ብቻ ይሰማሩ

እንደነበር ገልፀው አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ግን እነዚህ ዶክተሮች በአመራር ቦታ ላይም እንዲሰሩ የሚያስችል ሥልጠናን ያካትታል ብለዋል፡፡

በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ሰልጣኞች እንደ ኢንተርኔት ያሉ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑና በህብረተሰብ ችግሮች ላይ ምርምር በመስራት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የሚያደርግ እንደሆነም ተብራርቷል፡፡

‹‹ይህን ሥርዓተ-ትምህርት ከቀድሞው ለየት የሚያደርገው በርካታ ነገሮች አሉት›› ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ኦፊሰሩ፣ ከእነዚህም ውስጥ ቀድሞ ለዶክተርነት ሰባት ዓመት እንደሚማሩና አምስት ዓመት በንድፈ-ሀሳብ፣ ሁለት ዓመት የተግባር ሥልጠና የሚወስዱ መሆኑን አስታውሰው፣ በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ግን አራት ዓመት ተኩል ብቻ እንደሚማሩና የተግባርም ሆነ የንድፈ-ሀሳብ ትምህርቱ ተምረው እስኪወጡ እኩል ጐን ለጐን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በድሮው ሥርዓተ-ትምህርት የህክምና ትምህርት ተማሪዎች የሚመለመሉት ከ12ኛ ክፍል እንደነበር የገለፁት አቶ ጌታቸው፣ በአሁኑ ሰዓት በሳይንስ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መሆኑ ለህክምናው ዘርፍ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ከማድረጉም በላይ በሐኪሞች ላይ የሚነሳውን የሥነ-ምግባር ችግሮችም እንደሚቀርፍ አስታውቀዋል።

ዜ ና ዎ ች

Page 14: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15

Page 15: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 200316

ምክር ቤቱ

የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም›› የሚል መልስ በመስጠታቸው የም/ቤቱ አዳራሽ በሳቅ ቢሞላም፣ ከም/ቤቱ ውጪ ያሉት ተቃዋሚዎች ግን ‹‹የሚገባን ቋንቋ ምንድን ነው? ምን ለማለትስ ተፈልጎ ነው?›› የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸው ነበር።

ሌላኛው የዶ/ር አሸብር ግራ አጋቢ አስተያየት የተደመጠው ም/ቤቱ አንደኛ ዓመት የመጨረሻ ስብሰባውን ባካሄደ ጊዜ ነው። ስብሰባው የመዝጊያ እንደመሆኑ መጠን የም/ቤቱ የ203 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በአፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ቀርቧል፡፡ በግራ አጋቢነት የተመዘገበው የዶ/ር አሸብር አሰተያየትም አጠቃላይ ም/ቤቱንና አፈ-ጉባዔውን አስመልክቶ የተናገሩት ነው።

‹‹ፓርላማውን እንደ ቤተሰብ አድርገው ስላስተዳደሩት አመሰግናለሁ›› በማለት አፈ-ጉባዔውን በማሞካሸት የጀመሩት ዶ/ር አሸብር፣ ‹‹እርስዎን የመደቡትን ጠ/ሚኒስትር መለስ አመሰግናለሁ፤ ገዢውንም ፓርቲ በጣም አመሰግናለሁ›› ብለዋል።

ሆኖም ይህ የምስጋና ድርድር ዶ/ሩን ለትዝብት የዳረገ ነበር፡፡ በስፍራው የነበሩ ታዛቢዎች ‹‹እንዴ የሕዝብ እንደራሴው አፈ-ጉባዔ የሚሰየመው ከም/ቤት አባላት መካከል ተመርጦ እንጂ በጠ/ሚኒስትሩ ሿሚነት አለመሆኑን አያውቁም እንዴ?›› እንዲሉ ከመገደዳቸው በተጨማሪ፣ የሀሳብ ፍጭት ሊካሄድበት ይገባ የነበረው ፓርላማ ‹‹እንደ ቤተሰብ›› የመመራቱ ጥቅም ግልፅ አልሆነላቸውም።

ከዚህ ባሻገር ከሁለቱ ‹‹ብቸኛዎች›› አንዱ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ከወከሉት ግንባር ጋር ለአፍታም ቢሆን መወዛገባቸው ከ4ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጋር ተያይዘው ከተከሰቱ ጉዳዮች አንዱ ነው።

በአስገራሚነት የተመዘገበውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ አስተያየታቸውን አውራምባ ታይምስን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲሰጡ የነበሩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ አመራሮች ለአቶ ግርማ ዕውቅና አለመስጠታቸውን ሲገልፁ ነበር።

አመራሮቹ በወቅቱ ለዚህ አስተያየታቸው በምክንያትነት አቅርበውት የነበረው አቶ ግርማ አማካሪ እንኳን ሳይኖራቸው በም/ቤቱ መገኘታቸው ‹‹የኢህአዴግን ቴአትር ከማጀብ›› ውጪ ምንም ፋይዳ አለመኖሩን ነው።

ሆኖም ቀስ በቀስ ፓርላማው ሥራውን በጀመረ ሰሞን ሲደመጥ የነበረው ይህ እሰጥ አገባ ወደ ዝምታ ተቀይሮ ብቸኛው ተቃዋሚ በአንድ ዓመት ቆይታቸው ሲሰነዝሩ የነበሩትን ትችቶችና አስተያየቶች በፓርቲያቸው ስም ‹‹እኛ›› እያሉ ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡

አስፈፃሚ አካላትን የማይሞግተው ፓርላማ

የም/ቤቱ ዋና ዋና ሥልጣንና ተግባራት ሕግ ማውጣትና መንግስታዊ አካላትን መከታተል፣ መቆጣጠርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርምጃ መውሰድ ናቸው። ነገር ግን የተጠቀሱትን ተግባራት ም/ቤቱ በትክክል መወጣቱ በጥያቄ ምልክት ውስጥ ያለ ነው፡፡

በርካታ አስፈፃሚ አካላት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ለም/ቤቱ አቅርበው የነበረ ቢሆንም የመድረክ ወኪል ከሆኑት ውጪ ሌሎች አባላት አስፈጻሚ አካላትን ሳይሞግቱ ነበር ዓመቱ የተጠናቀቀው።

የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ሥራ በዋንኛነት የቁጥጥር ስራ ማከናወን እንደመሆኑ መጠን ተቃዋሚዎች በሌሉበት የተከናወነው የቁጥጥር ሥራ በቂ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ ኢህአዴግ የሾማቸውን ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የም/ቤት አባላት ‹‹ኮስተር›› ብለው ሲቆጣጠሩ አለመስተዋሉ ነው።

የሕግ ማውጣት ሂደቱም ቢሆን ከትችት አላመለጠም። እንኳንስና “አንድ ተቀዋሚ ብቻ” ኖሮ ቁጥራቸው በርካታ ተቃዋሚዎች እያሉ በኢህአዴግ አባላት የተዋቀሩት አስፈፃሚ አካላት የሚያመጧቸው ረቂቅ አዋጆች በኢህአዴግ ድምፅ ብልጫ ይፀድቁ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ኹነት የዓመት ዕድሜን ባስቆጠረው ፓርላማም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህም ‹‹የኢህአዴግ ፓርላማ

አይሆንም›› በሚል ይቀርብ የነበረውን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ሌላው በፓርላማው ውስጥ በተደጋጋሚ ከተስተዋሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በርካታ ቁጥር ያላቸው አባላት (አንዳንዴ ከሁለት መቶ በላይ) በቀሪነት መመዝገባቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የአፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ለአንድ ሰሞን ‹‹ጥፍት›› ብሎ መክረም መነጋገሪያ አጀንዳ እስከመሆን መድረሱም አይረሳም።

ለም/ቤቱ የቀረቡአወዛጋቢ አዋጆች

ፓርላማው ከአስፈጻሚው አካል እንዲያጸድቃቸው የቀረቡለትን ረቂቅ አዋጆች “እንደወረዱ” በድምጽ ብልጫ ሲያጸድቃቸው ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳን በማጽደቂያ ቀናት የኢህአዴግ አባላትና አጋሮች በተቃውሞ እጆቻቸውን ባያወጡም፣ ሁለት ረቂቆች ላይ ውይይት ሲካሄድ ቅዋሜአቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል፡፡

ባካተታቸው አንቀጾች የተነሳ በመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው ህዳር 2 ቀን 2003 ዓ.ም የቀረበው የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ነው፡፡ ረቂቁ በአንቀጽ 10/2/ሀ/ለ፣ ‹‹ከማህበራዊ ፍ/ቤቶች ወይም ተመሳሳይ ደረጃ ካላቸው ሌሎች ፍ/ቤቶች የተነሱ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አቤቱታዎችንና ግምታቸው እስከ 25ሺህ ብር የሚደርሱ የገንዘብና የንብረት ክርክሮችን ከዓለም

አቀፍ ስምምነቶች፣ ከሕገመንግስቱ እና ከፌዴራል ሕጎች ጋር የሚገናኙ ካልሆኑ በስተቀር የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር አያየውም›› ይላል፡፡

የፓርላማ አባላቱ ይህንን መረር አድርገው ነበር የተቃወሙት፡፡ ‹‹የታች ፍ/ቤቶች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ቢፈጽሙ ወዴት ሊኬድ ነው?›› ሲሉ የጠየቁ ሲሆን፣ በሕገመንግስቱ መሰረት የመጨረሻው የዳኝነት እርከን የሆነው ሰበር ችሎት ሆኖ ሳለ፣ ረቂቁ የኢኮኖሚ አቅምን መሰረት በማድረግ ያስቀመጠው ድንጋጌ ተገቢ አለመሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ይህን መሰል ነቀፌታ ያስተናገደው ረቂቅም ሳይጸድቅ ለቀጣዩ ዓመት ቀጠሮ ተይዞለታል።

ሌላው ከም/ቤቱ አባላት ተቃውሞ ገጥሞት የነበረው ረቂቅ የግል ድርጅቶች ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ነው። በረቂቁ አንቀጽ 26 መሰረት፣ አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ ከ10 ዓመት ያላነሰና 20 ዓመት ያልሞላ አገልግሎት ፈጽሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ፣ ወይም ከ20 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈጽሞ በራሱ ፈቃድ ከለቀቀ የአሰሪውን ድርሻ ሳይጨምር ለጡረታ ያዋጣው ገንዘብ ይመለስታል።

ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈጽሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ ደግሞ ምንም ዓይነት ክፍያ አያገኝም። የም/ቤት አባላቱም ይህንን ነበር እንዲሻሻል የጠየቁት፤ ምንም እንኳን ረቂቁ አዋጅ ሆኖ ያለማሻሻያ ሲጸድቅ ለመቃወም ባይደፍሩም።

ሶስተኛው አዋጅ ሳይሆን ውሳኔ ነው - አምስት ድርጅቶችን በአሸባሪነት ለመሰየም የቀረበው ውሳኔ። ምንም እንኳን ይህ ውሳኔ በም/ቤቱ የገጠመው ተቃውሞ አንድ ብቻ ቢሆንም፣ ከም/ቤቱ ውጪ ባለው ተጽዕኖ የተነሳ አወዘጋቢነቱ ጎልቶ ተስተውሏል።

በሌላ በኩል ም/ቤቱ አንዳንድ መልካም ነገሮች ተስተውለውበታል፡፡ ከእነዚህም በም/ቤቱ ውስጥ ያሉት ብቸኛ ተቃዋሚ ሀሳባቸውን በሚያሰሙ ወቅት በ3ኛው ም/ቤት ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ገና ንግግር ሲጀምሩ ‹‹ይሄን ያህል ደቂቃ ቀርቶታል›› በሚል ይሰነዘርባቸው የነበረው ዓይነት ዕቀባ መቅረቱ ተጠቃሽ ነው።

የሆነው ሆኖ፣ ም/ቤቱ የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን አጠናቅቆ እረፍት ላይ ነው። ‹‹ሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑንም በዘንድሮው መልኩ ይቋጨ ይሆን?›› የሚለው ግን የበርካቶች ጥያቄ ነው።

በሱራፍኤል ግርማ

4ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 35 መደበኛ ስብሰባዎችን በማካሄድና ከቀረቡለት 31 ረቂቅ ሕግጋት ውስጥ የ2004 ዓ.ም በጀት አዋጅን ጨምሮ 29 ረቂቅ አዋጆችን በማፅደቅ የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን አጠናቋል፡፡ ከአዋጆች በተጨማሪ አምስት ድርጅቶችን በሽብርተኛነት ለመሰየም በመንግስት /አስፈፃሚው አካል/ የቀረበውን ውሳኔ ጨምሮ 14 ውሳኔዎችን በማፅደቅ ነበር የመጀመሪያ ዓመት ቆይታውን ያጠናቀቀው።

ምስረታውበወርሃ ግንቦት 2002 ዓ.ም ላይ

የተካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ኢህአዴግ ለ‹‹መቶ በመቶ›› በቀረበ ውጤት እንዳሸነፈ በምርጫ ቦርድ መታወጁን ተከትሎ ትኩረት ስቦ የቆየው ‹‹በምርጫው ውጤት መሠረት የሚቋቋመው ፓርላማ ገፅታ ምን ይሆናል?›› የሚለው ነበር።

በወቅቱ (ከአንድ ዓመት በፊት) አንዳንድ ተቃዋሚዎች የምርጫውን ውጤት ውድቅ በማድረግ ‹‹የኢፌዴሪ 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደ ስሙ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሳይሆን የኢህአዴግ ጉባዔ ነው የሚሆነው›› በማለት ሲገልፁ የነበረ ሲሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ም/ቤቱ በምንም ዓይነት ተዐምር የአንድ ፓርቲ የምክክር መድረክ ሊሆን እንደማይችል ሲሞግቱ ቆይተዋል።

መድረስ አይቀርምና የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የመጨረሻ ሳምንት ተፈጥሮአዊ የጊዜ ዑደቱን ጠብቆ ተከሰተ። በሕገመንግስቱ አንቀጽ 58 ንዑስ-አንቀጽ 2 መሰረት በመስከረም ወር የመጨረሻዋ ሰኞ ፓርላማው ሥራውን ጀመረ፡፡

አዲሶቹ የፓርላማ አባላት ቃለ መሐላቸውን ከፈፀሙ በኋላ የተካሄደው የመጀመሪያው ክንውን አፈ-ጉባዔ መምረጥ ነበርና አቶ አባዱላ ገመዳ የም/ቤቱ አፈ-ጉባዔ ሆነው ተሰየሙ፡፡ ይህን ምርጫ ተከትሎ በተካሄደው የምክትል አፈ-ጉባዔ ምርጫ ደግሞ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ‹‹በለመዱት ቤት›› እንዲቆዩ ሆነ።

ሁለቱ ‹‹ብቸኛዎች››ኢህአዴግ ከተቆጣጠራቸው 545 የም/

ቤት መቀመጫዎች የተረፉትን ሁለት ወንበሮች የወሰዱት አንድነት /መድረክን ወክለው በአዲስ አበባ ወረዳ 6 የተወዳደሩት አቶ ግርማ ሰይፉ እና በከፋ ዞን ጊምቦ የምርጫ ጣቢያ በግል የተወዳደሩት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ናቸው።

ምንም እንኳን የተፎካከሯቸውን የኢህአዴግ ዕጩዎች በማሸነፍ ወደ ፓርላማ የመግባት ዕድል የገጠማቸው ሁለቱ ግለሰቦች ናቸው። ቢሆንም ዶ/ር አሸብር በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት በይፋ እንደተናገሩት፣ የኢህአዴግን ፖሊሲዎች በፅኑ (አንዳንዴም ከኢህአዴግ አባላት በላይ) ሲደግፉና ከኢህአዴግ አባላት የተለየ ሀሳብ ሲያመነጩ ባለመስተዋላቸው “በም/ቤቱ ውስጥ ያለው የተቀዋሚ ቁጥር አንድ ብቻ ሆኗል” የሚሉ ሰዎች አልታጡም።

ዶ/ር አሸብር በም/ቤቱ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ስፖርት ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሚያነሷቸው ጭብጥ ያላቸው ጥቄዎች ውጪ፣ በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰነዝሯቸው አንዳንድ አስተያየቶች ጥያቄ ማጫራቸው አልቀረም።

ለአብነት ያህል የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ በፀደቀ ቀን ተቃዋሚዎችን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት ተጠቃሽ ነው። ዕለቱ ዕቅዱ የሚፀድቅበት ነበርና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከም/ቤቱ ተገኝተው ነበር። በወቅቱም በዕቅዱ ዙሪያ እና በሚመጡት ዓመታት መንግስታቸው ስለሚከተለው አቅጣጫ ማብራሪያ ሰጠተዋል።

ከጠ/ሚኒስትር መለስ ማብራሪያ ቀጥሎ የም/ቤቱ አባላት አስተያየት እንዲሰጡ መድረኩ ክፍት መሆኑን ተከትሎ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ስለዕቅዱ ሀሳብ ያቀረቡት ዶ/ር አሸብር፣ ‹‹በኢትዮጵያ የተመዘገበው የ11 በመቶ ዕድገት ያልገባቸው ወገኖችን ጠ/ሚኒስትራችን ለመጨረሻ ጊዜ በሚገባቸው ቋንቋ ለምን አያስረዷቸውም?›› ነበር ያሉት።

ምንም እንኳን ዶ/ሩ ይህን በማለታቸውና አቶ መለስ ደግሞ በበኩላቸው ‹‹አውቆ

እና ክራሞቱፓርላማው

ምንም እንኳን የተፎካከሯቸውን የኢህአዴግ ዕጩዎች

በማሸነፍ ወደ ፓርላማ የመግባት ዕድል የገጠማቸው

ሁለቱ ግለሰቦች ናቸው። ቢሆንም ዶ/ር አሸብር በምረጡኝ

ቅስቀሳቸው ወቅት በይፋ እንደተናገሩት፣ የኢህአዴግን

ፖሊሲዎች በፅኑ (አንዳንዴም ከኢህአዴግ አባላት በላይ)

ሲደግፉና ከኢህአዴግ አባላት የተለየ ሀሳብ ሲያመነጩ

ባለመስተዋላቸው “በም/ቤቱ ውስጥ ያለው የተቀዋሚ ቁጥር

አንድ ብቻ ሆኗል” የሚሉ ሰዎች አልታጡም።

Page 16: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ጫት ‹‹አምላኪው›› ጎልማሳጫት ካልቃምኩ በግ ነኝ •የእናቴ ልጅ ቢጠይቀኝ ጫት አልሰጥም •

17

1895 ዓ.ም. የተቆረቆረችው ድሬዳዋ የፍቅር መዲና መሆኗ ሲነገርላት፤ ሲቀነቀንላት ኖሯል። ሙቀቷ ይፋጃል። የግዴታ ልብስ እስኪመስል ድረስ በርካታ ሴቶችም ሺቲ (በሱማሊኛ፡- ስስ ጨርቅ ማለት ነው) በመልበስ ሙቀቱን ለማቅለል

ይጥራሉ። ወንዶችም ቀላል ልብስ መጠቀም ያዘወትራሉ፡፡ ነጠላ ጫማ (ሸበጥ) መጫማት የሁለቱም ፆታዎች የግዴታ ምርጫ ነው፡፡

በሰኔ አጋማሽ ላይ በቦታው ስገኝ ‹‹በዚህ አይነት ግንቦትን እንዴት አለፋችሁ?›› ብዬ ባልጠይቅ ነበር የሚገርመው! ‹‹ሰኔማ ለእኛ ብርዳማ ጊዜያችን ነው ማለት ይቻላል። በግንቦት መጥተህ ቢሆን ኖሮ ምን ልትል ነው?›› በማለት ነበር የአንድ ምግብ ቤት አስተናጋጅ እኔን ያንገበገበኝ የቀኑ አጋማሽ ሙቀት ለእነሱ ‹‹መለስተኛ›› መሆኑን የነገረችኝ። ይህቺ ወጣት የ‹‹ከሰዓት›› በኋላ ተረኛ ከሆነች በመስተንግዶ ስራዋ ላይ ሆና ጫት መጉረስ የዘወትር ልማዷ ነው። ‹‹ሙቀትን ይቀንስልኛል›› የሚል እምነት አላት። ይህን ድርጊት ወደ ድሬ ሲያቀኑም ሆነ ሲመለሱ ‹‹አረፍ›› በሚሉባት አሰበ ተፈሪ እንደ ድሬዳዋ ሁሉ ደንበኛን በሚያስተናግዱ የተለያዩ ቦታዎች ሊመለከቱ ይችላሉ።

በድሬ በመንገድ ላይ የተመለከትኳቸው በተለምዶ ‹‹እብድ›› ብለን የምንለያቸው በርካታ ሰዎች ይታያሉ። ጉዳዩን ከሚመለከተው አካል ጠይቄ ማረጋገጫ ባላገኝም መንስዔው የጫት መቃም ‹‹ትሩፋት›› መሆኑን ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

አበራ ነጋሽ ግን ጫት መቃም በማብዛቱ ሳቢያ በላይ ነገ የእኔም እጣ ፈንታ ‹‹ማበድ›› ይሆናል የሚል ስጋት የለበትም። ከእንቅልፉ ሲነቃ ጫት፣ ውሎውን ጫት፣ ሊተኛ ሲቃረብ ድረስም ጫት ከአጠገቡ የማይጠፋ ‹‹ወዳጁ›› ነው። ከአረንጓዴው ቅጠል ያተረፈው ነገር ባይኖርም የጫት ‹‹አምላኪ›› ነው፡፡

የለበሳቸው አዳፋ ቢጫ ሸሚዝ እና ጥቁር ሱሪ መቀየሪያ የላቸውም፡፡ ከሰውነቱ የሚወልቁት ገላውን ሲታጠብ እና የአገልግሎት ዘመናቸው አብቅቷል ብሎ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሲያስወግዳቸው ነው፡፡ [ሰውነቱ ግን ፅዱ ነው]። የወየቡ ጥርሶቹ የሱስ ድር ቤት እንደሰራበት ይጠቁማል። የጎዳና ህይወትን ይገፋል። አስተሳሰቡ ግን ብሩህ ነው። የራሱ የሆነ አቋም አለው። ወቅታዊ መረጃ እየተለዋወጡ ሊያዋራዎት የሚችል አይነት ሰው ነው።

ይህን የ40 ዓመት ጎልማሳ (አበራ ነጋሽ) ያገኘሁት ድሬዳዋ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል አቅራቢያ ነው። ‹‹በአፍንጫው ነው የሚያወራው?›› እስክትሉ ድረስ ሲያወራ ይነፋነፋል። ‹‹የየት አገር ልጅ ነህ?›› የሚል ጥያቄ ጠላቱ ነው። ‹‹ኢትዮጵያ የሁላችንም አገር ነች። ‘የየት አገር ልጅ? አገርህ የት ነው?’ የሚል ጥያቄ አዕምሮዬን ይነካኛል። ከሌላ አፍሪካ አገር፣ ከአውሮፓ ወይም ከአሜሪካ አልመጣሁም። ኢትዮጵያዊነቴ እየታወቀ ‘ከየት ነው የመጣኸው?’ ስባል እናደዳለሁ። ወንጀል እስካልሰራሁ ድረስ በአገሬ ላይ ተሽከርክሬ በፈለግኩበት ቦታ የመኖር መብት አለኝ። ‹‹ከየት ነህ?›› ልባል አይገባም›› ሲል በቁጭት ይናገራል። ብዙዎች በትውልድ ከተማቸው ወደ ጎዳና አይወጡምና አስቀድሜ መደበኛ ባልሆነ ጨዋታችን ወቅት ‹‹የድሬ ልጅ ነህ?›› ስለው በንዴት አይኑን ከድኖ ሁለት እጆቹን ፊቱ ላይ እስኪያኖር ድረስ በንዴት ‹‹ጨሶ›› ነበር።

አበራ ‹‹ጭሱ›› በ1963 ዓ.ም. የተወለደው ሾኔ ውስጥ ቢሆንም ብዙ ዕድሜውን የኖረው ሀረር ነው። በ13 ዓመቱ ከሸኖ ወጥቶ የማያውቃት ሀረር ደረሰ። ለ26 ዓመት በዚያ ‹‹ወጣ ገባ›› እያለ ከጫቱ ጋር ከቆየ በኋላ ከባልንጀሮቹ ጋር በመጣላቱ ወደ ድሬዳዋ ከተሻገረ ዘጠኝ ወር አልፎታል። ሀረር መንገድ፣ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል አጠገብ ካለው ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት ያለው የአጥር ጥግ ቀን መቃሚያው፣ ምሽት ለጥቂት ሰዓታት ደግሞ መኝታው ነው።

በሀረር እና በድሬዳዋ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የኖረው በጎዳና ነው። ከቤቱ ስለወጣበት ምክንያት ሲገልፅ ‹‹ልጅነት እና ጥጋብ›› መሆኑን ያስረዳል። ‹‹ቤት ገብቼ ክትፎ ብላ ቢሉኝ አይዋጥልኝም። የጎዳና ቦሎቄ ግን ከክትፎ በለጠብኝ። አዕምሮዬ ማገናዘብ ሲጀምር ራሴን ጎዳና ላይ አገኘሁት።›› በማለት ባላወቀው መንገድ የመንገድ ላይ ህይወትን እንደሚመራ ይጠቁማል።

‹‹ጫት፣ ጫት፣ ጫት››ከድሬዳዋ ወደ ናዝሬት እና አዲስ አበባ

የሚጓዙ መንደገኞችን ከመኪና ማገናኘት የአበራ የገንዘብ ማግኛ መንገድ ነው፡፡ [ትራፊኮች እና መንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞች ሌሊት አይኖሩም ተብሎ ስለሚታሰብ ተሳፋሪ የጫኑ ሾፌሮች ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ መኪናቸውን አቁመው በሌሊት ለመክነፍ ሲሰናዱ ተመልክቻለሁ፤ ለዚያውም ረዥም ጉዞ ለማድረግ ያልተፈቀደላቸው ሚኒባስዎች፡፡]

ድሬዳዋን ለቀው በራሪ ከመሰሉት በአጠገቡ ሲያልፉ፤ አያልፎትም። ‹‹እ…ተጓዥ ናችሁ ምርጥ ‹‹አባዱላ›› አለኝ›› በማለት ከተቀመጠበት ሳይነሳ ይደልላል። ቆም ብለው ከሰሙት ከኃላ ኪሱ አውጥቶ ባለመኪኖቹ የሚጠቀሙበት ስልክ ቁጥር የሰፈረበት፤ ውሀ ነክቶት ፅሁፉ እየጠፋ ያለ (ያረጀ) ቢዝነስ ካርድ ይሰጥዎታል። ‹‹የተጓዦችን ስልክ ቁጥር እቀበልና ካሉበት ሄደን እናነሳቸዋለን። ሚኒባስዎች ወጥተው ካለቁ በኋላ ደግሞ ቅጥቅጥ አይሱዚዎች ስላሉ እነሱን የሚፈልጉትንም እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ አገናኛለሁ። ከዚያ በማገኘው ገንዘብ ‘እተዳደራለሁ’ ካጣሁ አማልነት (ወዛደርነት) ሰርቼ አድራለሁ›› ይላል።

ጎልማሳው ብዙ ገንዘብ ለማግኘት የሚጓጓ ሰው አይደለም። የሚሰራው ለቀን ጫት መቃሚያው የሚበቃውን ያህል እስከሚያገኝ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ያንን ካገኘ በቃ ለእሱ ህይወት ሙሉ ነች። ቤት ውስጥ እና ደጅ የማደር ልዩነት መኖሩን ቢያውቅም ከምንም በላይ ዋናው ነገር ጤና መሆኑን ስለሚያምን ከማደሪያው ይልቅ ለጤናው እና መቃሚያ እንዳይቸግረው ይፀልያል።

‹‹ስማ የእናቴ ልጅ ከእኔ በላይ ልታውቅም/ላታውቅም ትችላለህ። ከሃብት ይልቅ ሙሉ ጤንነት እንዲሰጠኝ እለምናለሁ። እዚህ ላይ [ቀን መቃሚያው ማታ መተኛው የሆነችውን ካርቶን እየጠቆመኝ] ተኝቼ ባድር ምንም አልሆንም።›› የሚለው ግድ የለሹ አበራ ብርድ፣ ዝናብ እና ሙቀት ቢፈራረቅበትም በጤናው ላይ የከፋ ጉዳት እንዳላመጣበት ቢገልጽም ከወራት በፊት አይኑን ታምሞ ድሬዳዋ በአንድ በጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝት ታክሞ አገግሟል። ወደ ድርጅቱ ለህክምና ሲገባ አሳስቦት የነበረው ከጫት መጠፋፋቱ ቢሆንም ወጣ እያለ ጫቱን መለቃቀሙን አልተወም ነበር፡፡

ቢያገኝም፣ ቢያጣም አምላኩን አያማርርም። በወየቡ ጥርሶቹ ጫቱን እያመዠገ ‹‹ሁሌም ‹ረሀ› ነኝ›› ይላል፤ ከ1979 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 24 ዓመታት ጫት ‹‹ሲበላ›› ኖሯል። ሲጋራም የጀመረው በዚሁ ወቅት ሲሆን በቀድሞ ጊዜ በቀን ሦስት ፓኬት ኒያላ ሲጋራ ያጨስ እንደነበር እና በአሁን ወቅት ግን ከሁለት ብር (5 ኒያላ ሲጋራ) በላይ አያጨስም። ሲጋራን ለመተው ይፈልጋል። ጫት ግን መተው አያስብም። አይኑን እያጉረጠረጠ ወደ ሚቅመው የጫት ቅጠል እየጠቆመ ‹‹ይሄን… ይሄን መቼም አልተወውም›› ይላል፤ ‹‹ለአገሬ እሞታለሁ!›› እንደሚል አርበኛ እየፎከረ።

ገንዘብ ካለው 24 ሰዓት ጫት ሲያመነዥግ እንደሚያድር ይናገራል። እንቅልፍ ጠላቱ ነው። ‹‹ሀረር እያለሁ የምተኛው የዶሮ እንቅልፍ ነበር። እዚህ ከመጣሁ ግን መጋደም ጀምሬያለሁ። ማታ አራት ሰዓት አካባቢ እተኛለሁ፡፡ መንገደኛ ከሌለኝ እስከ ጠዋት ድረስ እተኛለሁ። ሀረር እያለሁ ግን በሳምንት ሁለት ቀን ብተኛ ነበር›› ሲል ተገርማችሁ ‹‹እንዴት በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ?›› ብትሉት ‹‹እሱንም ስራ ከሌለ ነው›› ሲል ይበልጥ ያስገርማችኋል።

መቃሚያ ገንዘብ ቢያጣ ገራባ ለቃቅሞ ይቅማል እንጂ ቅጠል አፉ ሳያሳድር አያድርም። ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይም በየቀኑ ሳይፎርሽ ቅሟል። ሀረር እና ድሬዳዋ ደግሞ ጫትና ቃሚ በብዛት ስላሉ ‹‹ባጣ ባጣ ገራባ አላጣም›› በማለት ያመሰግናል።

‹‹ጫት ካልቃምኩ በግ ማለት ነኝ፤ ሰውነቴ አይሰራም።›› የሚለው አበራ አይኑን ለመግለጥ ያገኘውን ቁርስ ቀማምሶ ኢጄበና (የአይን መግለጫ) የጫት ቅጠል አፉ ማድረግ አለበት። ፊሽካው ከተነፋ በኃላማ አለማቆም በትንሹ ለ12 ሰዓታት ያህል የጫት ቅጠል ሲጎሰጉስ ይውላል። ሳይቅም ስለመኖር ለአፍታ ማሰብ አይፈልግም። ይህን ጥያቄ ስሰነዝርለት ጫት መቃም የሚከለክል አቃጅ ፀደቀ ያልኩት ያህል ‹‹ክው!›› ብሎ ‹‹ሳልቅም ልኖር? አቦ ተወና አትጠይቀኝ›› ብሎ አራስ ነብር ሆነ፤ ደበርኩት፣ ፊቱን አዞረብኝ። ‹‹በቃ! ጥፋ›› ነው ነገሩ። እንደ ምንም ላግባባው ሞከርኩ። አንገቱን መለስ አደረገና ‹‹ልኬን›› ነገረኝ፡፡ ‹‹ጫት ካልነካሁ ምንም ነገር አይመቸኝም። አንተም ሰው

አትመስለኝም።›› በማለት በጫት እንዳልመጣበት አስጠነቀቀኝ።

‹‹ጫት ቃሚ አይጨካከንም፤ ተረዳድቶ ሱሱን ያስታግሳል›› የሚባለው ያልተፃፈ ‹‹እውነታ›› አበራ ጋር ፉርሽ ነው። ገዝቶም ሆነ ለቃቅሞ ያመጣውን ጫት ለማንም አያካፍልም። ቸግሮት ቸሮት የሚያቅ ሰው ጫት ቢቸግረውና አበራ ሞልቶ ቢተርፈው ትንሽ ሊሰጠው ፍፁም ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ‹‹የእናቴ ልጅ እንኳን ቢሆን አልሰጠውም›› በማለት ለጫት ያለው የስስት እና ፍቅር ከፍታን ያሳያል።

ጫት ‹‹አምላኪው›› እዚህ ምድር ላይ ቁጥር አንድ የሚወደው እና መቼም ሊተወው የማይችለው ነገር ጫት መሆኑን ሲገልፅ የጠፋችበትን እናቱን እንዳገኘ ህፃን በደስታ ተሞልቶ ነው፡፡ ሰስቶ ቅሞ፣ ስለ ጫት ተርኮ የሚኖረው ከርታታው አበራ ነጋሽ ብዙዎች የጎዳናው ላይ ናላቸው ዞሮ ከጠዋት እስከ ማታ እንዲሽከረከሩ ምክንያት ሆኗቸዋል የሚባለው ጫት የእሱን መጨረሻ ምን እንደሚያደርገው ባያውቅም የሚኖረው ለዚሁ ቅጠል ነው፤ ‹‹የምኖረው ለመቃም ነው›› ይላል።

ድሬዳዋ ፀረኝነት የሌለባት ከተማ በመሆኗ እንደተስማማችው ይገልፃል። እግር መስቀያ ባይኖረውም ‹‹እግሬን ሰቅዬ ረሀ ሆኜ እየቃምኩ እኖራለሁ›› ሲል ከፍቅር ከተማዋ ጋር እንደተዋደ ያስረዳል። እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ወደ ትውልድ መንደሩ በቅርቡ ከ26 ዓመት በኋላ ደረሶ ወደ ድሬዳዋ ተመልሷል። አርባ ለማውጣትም ገንዘብ ሰብስቦ ሊሄድ እየተዘጋጀ ነበር። አባቱ ጎዳና ተዳዳሪ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ግን ምን ያድርጉት? ሾኔ ገብቶ ስለመኖር አያስብም። ‹‹ሞቴ ድሬ ላይ ነው›› ባይ ነው፤ ከጫቱ ጋር።

ወደ ፍቅር ከተማዋ ድሬዳዋ ተጉዞ የተመለሰው አቤል

ዓለማየሁ ውሎ፣ አዳሩ በመንገድ ላይ ከሆነ፣ ጫት ለመቃም

ከሚኖር ወጣት ጋር አውርቶ ተከታዩን ፅሁፍ አሰናድቷል።

‹‹የየት አገር ልጅ ነህ?›› የሚል ጥያቄ ጠላቱ ነው። ‹‹ኢትዮጵያ

የሁላችንም አገር ነች። ‘የየት አገር ልጅ? አገርህ የት ነው?’ የሚል ጥያቄ

አዕምሮዬን ይነካኛል። ከሌላ አፍሪካ አገር፣ ከአውሮፓ ወይም ከአሜሪካ

አልመጣሁም። ኢትዮጵያዊነቴ እየታወቀ ‘ከየት ነው የመጣኸው?’ ስባል

እናደዳለሁ። ወንጀል እስካልሰራሁ ድረስ በአገሬ ላይ ተሽከርክሬ በፈለግኩበት ቦታ የመኖር መብት አለኝ። ‹‹ከየት ነህ?››

ልባል አይገባም››

‹‹የም

ኖረው ለ

መቃም ነው›› ባ

ዩ አበ

ራ ነጋሽ

ል ዩ ቅኝት

Page 17: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 200318

ሴት

“ለከፋ”

ይጎዳል። በመንገድ ላይ ስንሄድ የሚሰጡን አስተያቶች (ጥሩም ሆኑ መጥፎ)

አንዳንዶች እንደሚያስቡት ልክ እንደ አስተያየት አልቀበለውም። ለከፋ በራሱ ‹‹መላከፍ፣ ልክፍት›› ነው ብዬ ነው የማምነው። ስላላስደሰተው ወይም ስላስደሰተው ሁኔታዬ የሚሰጠኝ አስተያየት ከሆነ መጥቶ ሊነግረኝ ይገባል። ነገር ግን በተራራቀ ሁኔታ የሚሰነዘር አማርኛ ስሜት ጎጂ ከመሆን የዘለለ አይደለም። እንዲህ ስል ደግሞ ወጣቱ ባለው ሃሳብ ሳልስማማ አላለፍኩም። አዎ! አንዳንዴ የሴቶች አለባበስ ከማማር ባነሰ መልኩ የሚረብሽበት ሁኔታም አለ። ተመልካችን መረበሽ ብቻ ሳይሆን የለባሹን ማንነት የሚያወርድበትም መንገድ።

መልከፍ የወንዶች፣ መለከፍ ደግሞ የሴቶች ብቻ ለምን ሆነ? ይህን ጥያቄ ያቀረብኩለት ወዳጄ ‹‹ወንድ ከሴት ይለያል። እሱ የማይገባ፣ የሚያምር ወይም የሚያስቀይም አለባበስ ለብሶ ቢሄድ የሴቷን እይታ ሊስብ አይችልም። ቢስብ እንኳ በሴቷ የሚሰነዘርበት ትችት ወይም አድናቆት የለም። ነገር ግን ወንዶች ባዩት ነገር (በውጫዊ ነገር) ይሳባሉ። ያን የመግለጫቸው ብቸኛው መንገድ ደግሞ ‹ለከፋ› ነው›› ሲል ሊያግባባኝ ሞክሯል። በተወሰነ መልኩ ተስማምቼበታለሁ። ሴቶች ወንዶች የፈለጉትን ሆነው ቢሄዱ ልብ የማይሉት፣ ነገር ግን ወንዶች ጥቃቅን ነገር ብትሆን እንኳ የማያልፉ አይነት ፍጥረት ናቸው።

ወደ ሴቶች ስንመጣ፤ አሁን ወቅቱ ክረምት ነው። ስንቶቻችን ክረምትን ያማከለ ልብስ እንጠቀማለን? ነው ጥያቄው።

ወቅቱን ያገናዘበ አለባበስ በመከተልና ባለመከተል በኩል ሴቶች ብቻ ናቸው የሚስተዋሉት ብል ማጋነን አይሆንም። ወንዶች ክረምቱን ያላማከለ ልብስ ቢለብሱም ባይለብሱም እንደ ሴቷ የመስተዋል እድላቸው የጎላ አይደለም።

አንዳንዴ ሰዎች (ሴቶች) የአየሩን ሁኔታ ያላማከለ አለባበስ ስንጠቀም በመጀመሪያ የእኛን ምቾት ቀጥሎ ደግሞ የሌላኛውንም ምቾት በሚጎዳ መልኩ ይሆናል። እርር ባለ ፀሐይ ወፍራም ሹራብ ማድረጋችን፣ በሚያንዘፈዝፍ ብርድ ስስ ነገር መልበሳችን ከጎናችን ያለው ሰው ምቾት እንዳይሰማው ያደርጋል።

ከወንዶች በተለየ ሁኔታ የሴት ልጅ ሰውነት እንክብካቤን ይፈልጋልና ወቅቱን ያገናዘበ ነገር መጠቀም አይከፋም፤ ይመከራልም። ከዛም ባለፈ ደግሞ ለተመልካች በሚስብ መልኩ ቢሆን። ያኔ ሰዎች ለእኛ ያላቸው ግምት ‘እንዳይዛባ’ እናደርጋለን ማለት ነው።

እንግዲህ ከላይ እንዳልኩት ቢሆን እንኳ ለከፋ ሊቀር አይችልም ብለን እንድንደመድም የሚያደርጉ ሁኔታዎች አሉ። ነገር ግን ቢያንስ፣ ቢያንስ ቅስምን ከሚሰብሩና ማንነትን ከሚያጠለሹ ለከፋዎች እንድናለን ብዬ አስባለሁ።

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀ ነው። ከሴት ደራሲያን ጋር በጋራ ያዘጋጀነው ‹‹እጣ›› የተባለ መፅሐፍ ውስጥ ‹‹የባህል ጦስ›› እና ‹‹ደመትን በጥሬ›› የሰኙት የኔ ሥራዎች ናቸው። ከነዚህ ውጪ ‹‹ስንክ ፍሬ›› የተሰኘ የቅኔ መፅሐፍ አለኝ፡፡ በኦሮምኛ ያዘጋጀሁት ‹‹ሲምቢሮ›› የተሰኘ ቅኔና ግጥም አለኝ፡፡ ከዚህ በተረፈ በለተያየ የግል ችግር ምክንያት ያላሳተምኳቸው ግን ደግሞ እስካሁን መታተም የነበረባቸው፣ በተለያየ ዘርፍ ላይ ያዘጋጀኋቸው 10 ያህል መፅሐፍት አሉኝ። በቅርቡ ለህትመት ይበቃሉ።

ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ እንዴት መሆን አለባቸው ትያለሽ?በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ትዳሮች ችግር ይገጥማቸዋል። ታዲያ በችግሩ የበለጠ ተጎጂዎቹ ሴቶች ናቸው። በተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ሴቶች ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናቸው ሰብዓዊ መብት ያስፈልጋቸዋል ብሎ ያለማሰብ ችግር አንዱ ነው። ወደተማሩት እንኳን ስንመጣ፣ ሴትና ወንድ እኩል አይደሉም ብለው የሚናገሩ የተማሩት ሰዎች አሉ። እኛ ወንድና ሴት እኩል ሰብዓዊ መብት አላቸው ስንል ብዙ ሰው ጉዳዩን የባልና የሚስት ያደርገዋል። በሌላው ላይ ያለውን መብትና ግዴታ አውቆ መኖር እንዲቻል ሁለቱንም የአስተሳሰብ ለውጥ ባለቤት ማድረግ ያሻል። እንደኔ እንደኔ፣ ለዚህ ትልቁ መፍትሔ የነቃን ሴቶች አንድን ሴት ቀርበን በማስተማር እሷ ተለውጣ ሌሎችን እንድትለውጥ ማድረግ ነው እላለሁ። ሴቶች ሥልጣን ሲሰጣቸው ለብዙዎች አይመቹም ይባላል። ለምሳሌ ትዕዛዛቸው በጣም ከባድ እንደሆነና በውሃ ቀጠነ እንደሚናገሩ ይገለፃል። በዚህ ትስማሚያለሽ?ይኼ ሊሆን ይችላል። እኔ በአንድ ወቅት የገጠመኝን ልንገርሽ። እኔ እዚያ መሥሪያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ሆኜ ስመደብ ሥራ ልትለቅ ተዘጋጅታለች፤ መልቀቂያም አስገብታለች። ለምን እንደምትለቅ ስጠይቃት አንድ የኮምፒዩተር ት/ቤት ተከፍቷል እዚያ ልማር ነው አለችኝ፡፡ በኋላ እኔን ለሚቀርበኝ ሰው ግን፣ ‹‹ሴት አለቃ ስለመጣች ሴቶች አለቃ ሲሆኑ ችግር ይፈጥራሉ ስለሚባል ፈራሁ ለዚህ ነው የምለቀው›› ብላ ነገረችው። እሱም ‹‹በይ ተሳስተሻል አርፈሽ ሥራሽን ስሪ፤ እንዲያውም ከእርሷ ጋር ከሰራሽ በጥሩ ሁኔታ ትለወጫለሽ›› ሲላት ሥራዋንም ቀጠለች። ተግባባንም፡፡ መምከር ያለብኝን እየመከርኩ ተግባባን። ሌላውም የዚህች ዓይነት ሴት አመለካከት ሊኖረው ይችላል። ይህቺ ዓለም የወንድ አለም ናት። ሴቶች ወደ ሥልጣን ሲመጡ የወንድ መብት ይነጠቃል ማለት አይደለም። ወንዶች እንዲህ ይጨቁናሉ ሴትን ይበድላሉ የሚል አመለካከት ያላት ሴት ወደ ሥልጣን ስትመጣ ወንድን ለመበደል አይደለም። ለምሳሌ አንድ መንግስት ‹‹ደርግ መጥፎ ሥራ ሰርቷል፣ መጥፎ ሥርዓት አራማጅ ነበር›› ሲል እርሱ ከደርግ በጣም የተሻለ

ሥራ መስራት አለበት። ያለበለዚያ ሲነቃቀፉ መኖር ነው እንጂ ለውጥ አይመጣም።

ሴቶች በትንሽ በትልቁ ይጨቃጨቃሉ የተባለው፣ ሴቶች ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ አነስተኛ ሥራዎችን ሲሰሩ የቆዩና ትንንሽ ስህተቶችን ሁሉ በማንሳት ሁሉም ነገር ፍፁም ይሁን ሊሉ ይችላሉ። ይኼ ደካማ ጎናቸው ሊሆን ይችላል። ግን በሂደት ይታረማል። ወንዶችም ከስህተታቸው እየተማሩ ነው የኖሩት። ወንድ የአደባባይ ሥራ ሲሰራ በመኖሩ ጥቃቅኖቹ ላይ ትኩረት እያደርግም። እንዲያውም ‹‹ለመሳሳት እንዘጋጅ›› የሚል ግጥም አለኝ። ሰው ሲሳሳት ነው የበለጠ የሚማረው፤ ‹ኤክስፔሪያንስ› የሚባለውም እኮ ‹ኤክስ› ከሆንሽው ነገር እየተማርሽ መሄድ ማለት ነው።

አንድ አባባል አለ። ‹‹በሁሉም ነገር ውስጥ ቅደም ተከተል አለ፤ ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ፍሰትና አካሄድ አለው፤ ከዩኒቨርስ ፍሰት በተፃራሪው ለመንቀሳቀስ ከተነሳን ግን ዙሪያችንን በቀውስና በረብሻ እንሞላዋለን›› ይባላል። ትስማሚያለሽ?አልስማማም! [ቆፍጠን ብላ] ለምን ብትይ፣ ለምሳሌ ተፈጥሮ ራሷ የፈጠራቻቸውን ነገሮች ስንታገልና ከተፈጥሮ ውጭ እንሁን ስንል እንቅፋቱም ችግሩም ሊገጥመን ይችላል። ወደ እውነቱም ስንመጣ፣ እኔ ሴት ነኝ ለምን ወንዱን አላስረገዝኩም ወይም ወንድ ለምን አያረግዝም የሚለው ነገር አይደለም ያጣላን። ሁሌም ሴት አርግዛ እንደምትወልድ፣ ወንድ እንደሚያስረግዝ ስለምናውቅ ይኼ አያጣላንም፡፡ አጣልቶንም አያውቅም። የሚያጣላን እኛ ሰዎች የፈጠርነው የሥራ ድርሻ ነው። ሴት ቤት ውስጥ ምግብ ታብስል፣ ልጅ ብቻዋን ታሳድግ፣ ወንድ አደባባይ ይዋል የሚሉት ነገሮች ናቸው የሚያጋጩን። ይኼን የሥራ ድርሻ እኛ ፈጠርነው እንጂ ከፈጣሪ የተሰጠ አይደለም። ተፈጥሮ እንዳለ ሆኖ በዚያ ውስጥ ሰው የፈጠራቸው አግባብነት የሌላቸው የሥራ ከፍፍሎች አግባብነት ይኑራቸው ነው ያልነው። የሥራ ክፍፍሎሽ ብቻ ሳይሆን አግባብነት ያለው የሀብት ክፍፍሎሽ ማግኘት አለባቸው፤ ለጉልበታቸው ተመጣጣኝ ክፍያ ማግኘት አለባቸው ነው ያልነው። እንጂማ የተፈጥሮን ዑደት እናዛባ አላልንም።

አንዳንዶች መከራን ታግለው ለማሸነፍ ሲሮጡ ሌሎች ግን ሪከርድ ለመስበር ይሮጣሉ የሚባውን ነገር እንዴት አየሽው?ይኼ እንግዲህ የአመለካከት ጉዳይ ነው። ይህቺን ዓለም የሚለውጣት አመለካከት (attitude) ነው። አንድን አገር ደሀ የሚያደርገው የሕዝቡ አመለካከት እንጂ የወርቅ፣ የጥሬ እቃ እጥረትም የሚባለው ቁሳዊ ነገር አይደለም። እነጃፓን ምንም አልነበራቸውም። አሜሪካን ያሳደጓት መልካም አመለካከት ያላቸው ኢንተርፕርነሮች ናቸው፡፡ በጎ አመለካከት የሌላቸው ሰዎች ሁሌ የሚታያቸው ጨለማና ችግር ነው፡፡ እነሱ ከዚህ መከራና ችግር ለመውጣት ነው የሚሮጡት።

ሪከርድ ለመስበር የሚሮጡት ደግሞ በበጎ አመለካከት ባመጡት መልካም ውጤት ላይ የላቀ ብቃትን ለመደረብ ነው። ይህን የሚገልፅ ይመስለኛል አባባሉ።

በዛሬና በትላንትና ትውልድ መካከል ያሉትን ሴቶች እንዴት ትገልጫቸዋለሽ?የአሁኑ ወጣቶች በጣም ፈጣንና የራሳቸውን ጥቅም ማየት የሚችሉ ናቸው፤ ከሌላው ጋር ሲነጻጸሩ። ያንን በማድረጋቸው የሚፈልጉትን አግኝተዋል ወይስ አላገኙም፣ ያ ሌላ ጥያቄ ነው። እንደድሮዎቹ ሴቶች የዋህ አይደሉም። ብልጠት አብዝተው የሚጎዱም አሉ፡፡ ለዚህ እንግዲህ የዘመኑ ሁኔታና የኢንፎርሜሽን ጉዳይ እያደገ በመምጣቱ የአሁኑን ትውልድ ቀልጣፋ አድርጎታል። ለዚህ ደግሞ መገናኛ ብዙሃን ትልቅ ሚና አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ የድሮዎቹ በባህል ተጨቁነው አንገት ደፍተው የኖሩ ናቸው፡፡

‹‹ሴት ልጅን ማወቅ ወይም መረዳት አይቻልም፤ ከዚህ ይልቅ ዝም ብሎ ማፍቀር ነው የሚሻል›› ይባላል።አዎ ይላሉ። ግን ሴቶችንም ብትጠይቂ ወንድ ልጅ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ እሱን አውቆ መጨረስ አይቻልም ይላሉ። ነገር ግን ሴትን፣ ወንድን ሳይሆን በአጠቃላይ የሰውን ልጅ አውቆ መጨረስ አይቻልም ብሎ ማጠቃለል ነው የሚቀለው፡፡ ጥሩም መጥፎም ወንዶችም ሴቶችም አሉና።

አንድ ጊዜ ስትናገሪ መኪና ውስጥ ሆነሽ አንድ አሸከርካሪ አስቸግሮች መኪና አቁመሽ ለድብድብ መጋበዝሽን ተናግረሻል ተደባዳቢ ነሽ?አሁን የሰላም አምባሳደር ስለሆንኩ አልደባደብም፤ ነገር ግን ያኔ ተደባድቤያለሁ [በጣም እየሳቀች]። ገጠመኙ እንዴት መሰለሽ፣ ኡራኤል አካባቢ ነው። እኔ ወደ መ/ቤት ስሄድ በኔ መንገድ መጣ። ታክሲ ሹፌር ነው፤ ወደ መገናኛ ሌላውን ታክሲ ቀድሞ ለመጫን ነው የመጣው፡፡ ‹‹ባክሽ ወደዛ… እነዚህ ሴቶች ማንንም ወንድ መኪና ያስገዙና ሰው ላይ ይዝናናሉ›› አለኝ። ልብ በይ ጥፋቱ የሱ ነው። ቦግ አለብኝ። እንዳይንቀሳቀስ መኪናውን አስጠግቼ ካቆምኩ በኋላ ወረድኩና ኮሌታውን ጨምድጄ በቦክስ አስነክቼ አስነክቼ ለቀቅኩታ፡፡ [የአንድ እጇን ቡጢ ሌላው አጇ ላይ እየመታች።] ትመታኛለች ብሎ በፍፁም አልጠበቀም። ‹‹አየህ እኔ እናቴ በደንብ አስተምራኝ፣ ለፍቼና ደክሜ ነው መኪና የገዛሁት። ማንም ወንድ አይደለም የገዛልኝ›› አልኩት። በኋላ ግን ንዴቴ ሲበርድ ይህን በማድረጌ በጣም ተፀፅቻለሁ፡፡

አሁን አንድ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄ ልጠይቅሽ ነው። የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ማን ይባላሉ?ኦኦ አቶ ማን ነበሩ ባክሽ ኧረ አውቃቸዋለሁ። አቶ ሶፍያን አህመድ አይደሉ?

በትክክል ተመልሷል በጣም አመሰግናለሁ።

‹‹አንድን ሀገር ደሀ የሚያደርገው...

በሱራፍኤል ግርማ

በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሕይወት ታሪክና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የሚያተኩር መፅሐፍ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ።

መፅሐፉ የተዘጋጀው የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ በሆነው ዳንኤል ተፈራ ሲሆን፣ ‹‹ዳንዲ የነጋሶ መንገድ›› የሚል ርዕስ ነው። ‹‹ዳንዲ›› ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ቀጭንና ጠመዝማዛ መንገድ መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን የገለጸው ዳንኤል፣ የመፅሐፉ ዋና ዓላማ ዶ/ር ነጋሶ ያለፉበትን የፖለቲካ መንገድ እያስቃኘ አጠቃላዩን የኢትዮጵያ ፖለቲካ መዳሰስ መሆኑን ተናግሯል።

መፅሐፉን ለመፃፍ ያነሳሳው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለመመርመርና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማመላከት መሆኑን የገለፀው ዳንኤል ተፈራ፣

በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዙሪያ መፅሐፍ ታተመ

‹‹ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ያሳያል›› ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ነጋሶ ትልቅ ታሪክና ልምድ ያላቸው እንደመሆኑ መጠን ታሪካቸውን በራሳቸው ነጋሪነት መዝግቦ ማስቀመጥ ዋናው የመፅሐፉ ዓላማ መሆኑን የመፅሐፉ አዘጋጅ ተናግሯል።

መፅሐፉን ለማዘጋጀት አንድ ዓመት ከሶስት ወር የፈጀበት ዳንኤል፣ በመፅሐፉ ዝግጅት ወቅት

ረቂቁን ያዩት ዶ/ር ነጋሶ ጥሩ የእርማት ሀሳቦችን እንደሰጡት ገልጾ ከታተመ በኋላ ደግሞ በደስታ ‹‹መቼስ ምን እላለሁ?›› ማለታቸውን ተናግሯል።

በ20 ሺህ ኮፒዎች የታተመውና ከሐሙስ ከሰዓት ጀምሮ ገበያ ላይ የዋለው ‹‹ዳንዲ - የነጋሶ መንገድ›› በዶ/ር ነጋሶና በጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መካከል ስለ ነበረው ግጭት፣ ስለህወሓት መሰንጠቅ እና ስለሌሎች በርካታ ጉዳዮች ያትታል።

በ20 ሺህ ኮፒዎች የታተመውና ከሐሙስ ከሰዓት ጀምሮ ገበያ ላይ የዋለው ‹‹ዳንዲ - የነጋሶ

መንገድ›› በዶ/ር ነጋሶና በጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መካከል ስለ ነበረው ግጭት፣ ስለህወሓት መሰንጠቅ

እና ስለሌሎች በርካታ ጉዳዮች ያትታል።

አለባበስ ቋንቋ ነው - ይናገራል። የእኛ አለባበስ በሌላኛው ሰው እይታ ማንነታችንን ‹እንዲገምት› (የዛ ሰው ግምት የተሳሳተም ይሁን ትክክለኛ) እድል ይከፍታል ብዬም አስባለሁ።

ቅዳሜ ረፋድ ላይ ‹‹ሴቶችን›› መሰረት ያደረገ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ፕሮግራም እያየሁ ነበር። ጉዳዩ ‹ለከፋ›ን በተመለከተ ነው። የፈለጉትን የመልበስ መብት እንዳላቸው እየታወቀ እነሱን በሚረብሽ ሁኔታ በወንዶች መለከፋቸው ቅር ያሰኛቸው እንስቶች ‹‹ለምን?›› ብለው የጠየቁበት መድረክ ነበር። ይሄ ጥያቄ በዛ ቦታ ያሉት ወንዶች ተቀባይነት እንዳይኖረው ተከራክረዋል።

አንድ ፈገግ ያስባለኝን አባባል አንድ ወጣት ተናገረ። ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ አለ፡- ‹‹በመለከፏ መብቴ ተገፈፈ ስላለች ብቻ እይታ በሚረብሽ መልኩ ወይም በሚያስጠላ መልኩ ለብሳ የምታልፍን ሴት ከመናገር አልምርም ... ያ ለከፋ አይደለም። እሷ ጥሩ ነገር የማየት መብቴን ተጋፍታለችና ልናገራት ግድ ይላል።›› ንግግሩ አስደመመኝ። ‹‹መልካም ነገር ለብሳ ቢሆንና ባደንቃት … ያንን ለከፋ ትለው ይሆን?›› አይነት ድምፀት ያለውን ጥያቄም አቅርቧል።

ወጣቱ እንዳለው ለከፋን በአግባቡ ስንጠቀምበት የዛን ሰው ድክመትና ጥንካሬ መግለጫ መንገድ ነው። ቆንጆ የሆነን የማድነቂያ፣ መጥፎ የሆነን ደግሞ የማስተማሪያ መንገድ ነው ለከፋ - እንደወጣቱ አገላለጽ። ነገር ግን ለከፋ ከጾታዊ ትንኮሳ በምን ይለያል?

አንዴንዴ መልካም ለከፋ ሞቅ ያደርገናል። ውስጣዊ ማንነትን በሚረብሽና በሚነካ መልኩ የሚደረግ ለከፋስ? ያበሽቀናል።

ተላካፊዎቹ ‹ለምን እንላከፋለን?› ብለው ራሳቸውን ቢጠይቁ እንኳ ምክንያት አልባ መሆናቸው ግልጽ ነው። ለእኔ ስለለበስነው ነገር አስተያየት ከመስጠት ባለፈ ለከፋ ለእነሱ ሱስ ነው። አንዲት ሴት አስጠላባትም አማረባትም፣ ምንም ሆነ ምን - ከለከፋ አታመልጥም። ያ ደግሞ ስሜትን

መልከፍ የወንዶች፣ መለከፍ ደግሞ የሴቶች ብቻ ለምን ሆነ? ይህን ጥያቄ ያቀረብኩለት ወዳጄ ‹‹ወንድ ከሴት ይለያል። እሱ የማይገባ፣ የሚያምር ወይም የሚያስቀይም አለባበስ ለብሶ ቢሄድ የሴቷን እይታ ሊስብ አይችልም።

ቢስብ እንኳ በሴቷ የሚሰነዘርበት ትችት ወይም አድናቆት የለም።

Page 18: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዜ ና ዎ ች 19

በሱራፍኤል ግርማ

በግብርና ዘርፍ ባበረከቱት ጉልህ የምርምር ውጤት የተነሳ የዓለም ሎሬት የሆኑት ፕ ሮ ፌ ሰ ር ገቢሳ እጄታ፣ የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ን ግብርና ለማሳደግ

ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች እዚሁ መሥራት እንዳለባቸው ገለፁ። ፕሮፌሰር ገቢሳ ይህን ያሉት ባገባደድነው ሳምንት በአሜሪካ

ኃላፊ የሆኑት ዋና ሳጅን መንግስቱ ለማን አነጋግረናቸው ነበር። ጉዳዩ እውነት መሆኑን የገለፁልን ዋና ሳጅን፣ ተቀብረው የተገኙት ቦምቦች የፕላስቲክ ስሪት መሆናቸውን እና ቦምቦቹም ወደ ፌዴራል ፖሊስ የፈንጂ አምካኝ ልዩ ጥበቃ ኃይል ክፍል መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

ለልማት ተብለው በሚፈርሱ አካባቢዎች እንደዚህ ዓይነት ተግባሮች አልፎ አልፎ እንደሚከሰቱ የጠቀሱት ዋና ሳጅን

መንግስቱ፣ በቀጣይ ሕብረተሰቡ ተመሳሳይ ክስተት ሲያጋጥመው አደጋ ሳይከሰት በፊት ወዲያው ለፖሊስ የጥቆማ መረጃ መስጠት እንዳለበትና ቦምቦችን መነካካት እንደማይገባ አሳስበዋል።

ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተይዘው የመጡትና በቁፋሮ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ሁለት ግለሰቦች በዕለቱ መለቀቃቸውን ከፖሊስ መምሪያው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

በኤልያስ ገብሩ

ኢንተርፌይዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢንሽዬቲቭ (አይ.ፒ.አይ) እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የሰላምና የምክክር የጋራ ጉባዔ በመተባበር ‹‹ሃይማኖቶች ለሰላም ያላቸው ሚና›› በሚል ርዕስ ያዘጋጁት የአንድ ቀን አውደ ጥናት ከትላንት በስትያ በግዮን ሆቴል ተካሄደ።

በዕለቱም ለተለያዩ ቤተ-ዕምነቶች የሃይማኖት አስተማሪዎች በሰላምና በግጭት አፈታት ዙሪያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ተደግፎ በቀረበው አውደ ጥናት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ የግጭቶች አፈታትና የሰላም ጥናት መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ታረቀኝ አዴቦ (ዶ/ር) ‹‹ሃይማኖትና ሰላም› በሚል ርዕስ ለውይይት የሚሆን መነሻ ሀሳቦችን አቅርበዋል። አያይዘውም፣ የተለያዩ ቤተ-ዕምነቶች ተወካዮችም በሰላም ዙሪያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ያስረዱ

ሲሆን፣ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዓለም ከምትታወቅባቸው መልካም እሴቶች አንዱ በሃይማኖቶች መካከል ያለው ተከባብሮ የመኖር ባህል በተለያዩ እምነቶች ምዕመናን ዘንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተለያዩ የሃይማኖት አስተማሪዎች ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

እንዲሁም የሃይማኖት አስተማሪዎች ዘወትር በትምህርት ፕሮግራማቸው ላይ ስለሌላው ሃይማኖት የጥላቻና የማንቋሸሽ ትምህርትን ከመስጠት መቆጠብና ሌላውን ማክበር የሃይማኖትም ሆነ የዜግነት ኃላፊነት መሆኑን ሊረዱ እንደሚገባ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አስረድተዋል።

‹‹በኢትዮጵያ በተለያዩ እምነቶች ጥሩ የሆነ የመከባበርና የመቻቻል ባህል ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ተከስተው የታዩ የአብሮነትንና የሰላምን መንፈስ የሚፈታተኑ አዝማሚያዎች

ሲታዩ ቶሎ ለመፍታት የሚያስችል የሰላም ብቃት ትምህርትን መገንባት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው›› ሲሉ የገለፁት ደግሞ የኢንተርፌይዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢንሽዬቲቭ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አምባሳደር ሙሴ ኃይሉ ናቸው።

ለዚህም ዝግጁነትን ማጠናከርና ጥልቅ የውይይት መድረክ መፍጠር የሁሉም ቤተ-ዕምነቶች ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባና በተለያዩ ሃይማኖታዊ መፅሐፍት ላይ ሰፍሮ የሚገኘውና ለሰላም መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለውን ‹‹በአንተ ላይ ሊደረግብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ፤ ላንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላው አድርግ›› የሚለውን የወርቃማውን ሕግ አስተምህሮ የሃይማኖት አስተማሪዎችና የተለያዩ ቤተ-ዕምነቶች ዋጋና ልዩ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

‹‹ሃይማኖቶች ለሰላም ያላቸው ሚና›› በሚል አውደ ጥናት ተካሄደ

‹‹የመንግስት ጋዜጠኞች ፍርሃት

አለባቸው››ተሳታፊዎች

‹‹የመንግስት ሚዲያ ባለሙያዎች የሕግ

አስፈፃሚውን ችግሮች አትዘግቡ የሚባሉበት

የተፃፉም ሆነ ያልተፃፉ መመሪያዎች የሉም››አቶ ሽመልስ ከማል

/የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ሚኒስትር ዴኤታ/

በኤልያስ ገብሩ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተገቢው መንገድ ለሕዝብ ተደራሽ፣ አሳታፊና ግልፅ ለማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት

ጋር ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክክር መድረክ ተካሄደ።

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የመክፈቻ ንግግር በተጀመረው የምክክር ፕሮግራም ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል፣ የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ባለሙያዎች፣ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና ጥቂት የመንግስትና የግል ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።

በመጀመሪያም ‹‹የፓርላማ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችና የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት›› የሚለውን ፅሁፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ አልቃድር ኢብራሂም ያቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ሽመልስም የሁለቱን ቀን ፕሮግራም በአወያይነት መድረኩን መርተውታል።

በፅሁፉ ላይ የፓርላማ ዴሞክራሲ እሴቶች እና የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ የፓርላማ ዴሞክራሲያዊነት መመዘኛዎች፣ የፓርላማ የሥራ እንቅስቃሴዎች፣ ግልፅነት፣ ለጋዜጠኞች ምቹ ሁኔታን መፍጠር፣ ተጠያቂነት፣ የፓርላማ ውጤታማነት፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከፓርላሜንታዊ እሴቶች አንፃር ሲመዘን … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። በፓርላማው ላይ የሚቀርቡ ሂሶችን ይፋ በማድረግ ደረጃ በተለይ የመንግስት ጋዜጠኞች ድፍረት እንደሌላቸው፣ አስፈፃሚው አካል ድክመቶቹ እንዲተላለፉበት እንዳማይፈልግና ‹‹እንደው ይህቺ ሳትዘገብ ብትቀር›› የሚሉ አስፈፃሚዎች መኖራቸውን፣ በክልል የሚደረጉ የፓርላማ ውይይቶች በቂ የሚዲያ ሽፋን እየተሰጣቸው እንደማይገኝ፣ የቋሚ

ኮሚቴ ስብሰባዎች ሲደረጉ በሚዲያው ‹‹አበረታች ሥራ ተሰርቷል›› ከማለት ውጪ በውይይቶች ላይ ተነስተው ስለነበሩ ጉድለቶች እንደማይገለፁ በመጀመሪያ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

እንዲሁም የኮሚቴ ሥራዎች እኩል ሽፋን እንደማይሰጣቸው፣ ብዙ ጊዜ ወቅታዊ ያልሆኑና ተደጋጋሚ የፓርላማ ዘገባዎች እንደሚቀርቡ፣ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮች ዋና ኮሚቴ በጭራሽ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ እንደማያውቅ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ዘወትር እሁድ ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚቀርበው የፓርላማ ፕሮግራም በሚስብ አቀራረብ ስለማይቀርብ ሕብረተሰቡ በአትኩሮት እንደማይመለከተው፣ ለአስፈፃሚ አካላት የተለየ የሚዲያ ሽፋን እንደሚሰጣቸው፣ አስፈፃሚ አካላት የሚሰሩትና ሕዝብ የሚያነሳው ጥያቄ ችግር እንዳለበትም ከመድረኩ የቀረቡ

ሀሳቦች ናቸው።ለተነሱት ጥያቄዎችም

አቶ አልቃድር፣ ‹‹ስህተቶች ሲከሰቱ የሚስተካከሉባቸው ሁኔታዎች አሉ›› ብለዋል። ‹‹የተነሱት ሀሳቦች ገንቢ ናቸው›› ያሉት አቶ ሽመልስ፣ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተከናወኑ ጉዳዮችን ለሕብረተሰቡ ተገቢውን ወቅታዊ መረጃ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ተደራሽ ለማድረግ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቀጣይ በሚከፍታቸው የቴሌቭዥን ስርጭት ቻናሎች በኩል በቂ ሽፋን መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።

‹‹በመንግስት ሚዲያ ባለሙያዎች በኩል የፓርላማ ዘገባዎችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተላለፍ ፍርሃትና በራስ ያለመተማመን ችግሮች አሉ?›› ተብለው ለተነሱት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሚኒስትር ዴኤታው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል። ‹‹የመንግስት ሚዲያ የሕግ

አስፈፃሚውን ችግሮች አትዘግቡ የሚባሉበት የተፃፉም ሆነ ያልተፃፉ መመሪያዎች የሉም። የመንግስት የዘወትር ለቅሶ ተዓማኒ ሚዲያ እንዴት ይኑረን? በመንግስትና በሕዝብ መካከል ያለውን የመተማመን ክፍተት እንዴት ይሞላ? የሚል ነው። ሚዛናዊ ዘገባዎችን መዘገብ ዋናው መፍትሔ ሲሆን ሚዲያውን በሂደት ላይ እንዳለ ተቋም ማየት ያስፈልጋል።››

በአጠቃላይ በሁለቱ ቀናት የምክክር መድረክ ላይ የፓርላማ ዲሞክራሲያዊ እሴቶች፣ በሀገራዊ መግባባት ዙሪያ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሚና፣ የም/ቤቱን መረጃ ለሕዝብ በማሰራጨት ሂደት የክልልና የፌዴራል ሚዲያዎች፣ የኮሙኒኬሽን መ/ቤቶች ሚና እና የፓርላማና ሚዲያ ትብብር አስፈላጊነት እና የሌሎች አገራት ተሞክሮ የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮችን የያዙ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ፓርላማውን እና መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከት ውይይት ተካሄደ

ተራድዖ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ) የተዘጋጀውና በርካታ የግብርና ተመራማሪዎች በተሳተፉበት የምክክር መድረክ ላይ ነው።

የምክክር መድረኩ በተካሄደ ጊዜ ከጋዜጠኞች ‹‹ኢትዮጵያ ያለባትን የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍ መፍትሔው ምንድን ነው?›› የሚል ጥያቄ ለፕሮፌሰር ገቢሳ ቀርቦ ነበር። እሳቸውም፣ ኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ካለባቸው ችግር ለመውጣት በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ ምርምር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

‹‹የእኛ ውይይትም

የሚያተኩረው የምርምር ውጤቶች ለገበሬው የሚቀርቡበትን መንገድ ማመቻቸት ነው›› ያሉት ፕሮፌሰር ገቢሳ፣ አገሪቱ ከችግር መላቀቅ የምትችለው የራሷንና የድርጅቶቿን አቅም ስታጠናከር ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በውጪ ሀገራት ስለሚገኙ የግብርና ተመራማሪዎችም ፕሮፌሰር ገቢሳ አስተያየት ሰጥተዋል። ‹‹ሁላችንም በውጪ የምንገኝ ተመራማሪዎች አገር ቤት ገብተን በሙያችን አስተዋፅኦ ለማበርከት እንፈልጋን›› ያሉ ሲሆን፣ ባለሙያዎች ልምዳቸውን

ይዘው እንዲመጡ አመቺ ሁኔታዎች መመቻቸት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

ሌላው ከጋዜጦች ጥያቄ የቀረበላቸው የዝግጅቱ ተሳታፊ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ስለሺ ጌታሁን ናቸው። ‹‹በርካታ ጥናቶች ተሰርተዋል ግን ተግባራዊ ሲሆኑ አይታይም። ይኼን ለማስተካከል ምን እየተሰራ ነው?›› በሚል ነበር ለአቶ ስለሺ ጥያቄ የቀረበው።

ሚኒስትር ዲኤታው ጥያቄውን ‹‹የምርምር ውጤቶች ወደ አርሶአደሮች ሳይደርሱ የሚቀሩበት

ዕድል ቀንሷል›› ሲሉ የመለሱ ሲሆን፣ በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት አማካኝነት መልካም ጅምሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩን የመሩት ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ ድርቅን የሚቋቋም የማሽላ ዝርያ በምርምር በማግኘታቸው የዓለም የምግብ ሎሬትነት ማዕረግ ያገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ተሹመው ዓለም አቀፉን የግብርና ልማት ቦርድ እያገለገሉ ይገኛል።

‹‹እያንዳንዱ ተመራማሪ እዚህ መሥራት አለበት››ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ

በፓርላማ አቅራቢያ ቦምቦች ...

Page 19: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003ጤ ና20

በ1948 የሰብዓዊ መብቶች ሁሉ-አቀፍ መግለጫ የሰው ልጆች ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡርነታቸው ክቡር መሆናቸውን፣ እንዲሁም እኩል እና ሊጣሱ የማይችሉ መብቶች ያሏቸው መሆኑን አውቆ መቀበሉ ለዓለም የነፃነት፣ የፍትሕና የሠላም መሠረት ሆኖ መደንገጉን፣ ‹‹ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች›› በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በእኛው 1999 ዓ.ም ያሰራጨው የአማርኛ ጥራዝ ያሳያል።

ሰብዓዊ መብቶችን ችላ ማለትና መናቅ የሰው ልጅን ህሊና ያስጨነቁ አረመኔያዊ ተግባሮችን በማስከተሉ እና የሰዎችም ከፍተኛ ፍላጎት ‹‹የሰው ልጀች ሁሉ የንግግርና የእምነት ነፃነት የሚጎናፀፉበት፤ ከፍርሃትና ከችግር ነፃ የሚወጡበት ዓለም መፍጠር ነው›› ተብሎ ታውጇል። እንዲሁም፣ ክፉ አገዛዝንና ጭቆናን ለማስወገድ ሰዎች አመፅን የመጨረሻ አማራጭ አድርገው ለመውሰድ እንዳይገደዱ ሰብዓዊ መብቶች በሕግ እንዲከበሩ ማድረግና በሕዝቦችና አገሮች መካከል የወዳጅነት ግንኙነት እንዲስፋፋ ማበረታታት አስፈላጊነቱ ተሰምሮበታል።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት ሕዝቦች በመሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች፣ በሰው ልጅ ክብርና ልዕልና፣ ወንዶችና ሴቶች እኩል መብቶች ያሏቸው ለመሆኑ ፅኑ እምነታቸውን በድጋሚ ስላረጋገጡና የማሕበራዊ ኑሮንና የተሻለ የኑሮ ደረጃን ሰፋ ባለ የነፃነት ሁኔታ ለማራመድ ተወስኗል። … እስኪ ጤናን ከሰብዓዊ መብቶች አኳያ እንመልከት።

ትኩረት ተነፍጎት

የነበረ ጉዳይበኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ

የማሕበረሰብ ጤና መማሪያ መፅሐፍ ጤናና ሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ እንዲህ ሲል ይገልፃል፡- ‹‹ከተመሰረተ ከ60 ዓመታት በላይ ያሳለፈው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጤናና ሰብዓዊ መብቶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ዓለም አቀፍ ኃላፊነት ትኩረት እየቸረው ይገኛል። ይሁንና በሁለቱ ጉዳዮች መካከል ስለነበረው ግንኙነት ለጥቂት አስርተ ዓመታት ያህል የዕውቅና ንፍገት ችግር ነበረበት። በሁለቱ ዓለሞች መካከል በመሠረታዊ ሁኔታ ተቃርኖዎች ስላላቸው ትይዩና የየራሳቸው የተለያዩ መንገዶች ነበራቸው። ነገር ግን፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የተደረጉ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሁኔታዎች በአሁን ወቅት በጤናና በሰብዓዊ መብቶች መካከል አንድነትን ለመፍጠር እገዛ አድርገዋል።››

በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ ቫይረስ ወረርሽኝ፣ ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ በሴቶች ላይ የሚደርሱ የጤና ጉዳዮች፣ እንዲሁም በባልካንና በአፍሪካ በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ በሚገኙ ሀገራት ውስጥ ከሕግ እና ሥርዓት ውጪ በግላጭ ይደረጉ የነበሩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በጤናና ሰብዓዊ መብቶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ተፈጥሯዊ የጠበቀ ግንኙነት ትልቅ ትኩረት

እንዲሰጠው በር ከፈቱ። እነዚህ እያንዳንዱ ጉዳዮች የተለየ፣ ነገር ግን የተያያዙ የጤናና የሰብዓዊ መብቶች ትስስር ምሳሌ ሊሆኑም ቻሉ።

የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታሁለቱም ዘርፎች

ተነጣጥለው ሊታዩ እንደማይገባ ግንዛቤ ስለተፈጠረ በእነዚህና በተመሳሳይ ጉዳዮች አማካኝነት አርቆ የማሰብ ጥልቅ ስሜት በጥቂቱ ዳብሮ የጤናና ሰብዓዊ መብቶች የቋንቋ አጠቃቀም ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግልፅና ቀለል ያሉ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት በፅንሰ ሐሳብ፣ በትንታኔያዊ፣ በፖሊሲ ደረጃ እና በፕሮግራም የተቃኙ ሥራዎችን እንደ ድልድይነት በመውሰድ እነዚህ በሁለት በተቃርኖ አቅጣጫ ይገኙ የነበሩ ወሳኝ ዘርፎችን በአንድነት ወደፊት እንዲጓዙ እያደረጋቸው ይገኛል። በቅርብ ዓመታት ውስጥም የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የጤናና የልማት ጉዳዮች የትንታኔ ማዕከል በመሆን ዕድገት እያሳየ እንደሆነ ተደርጎ ቢገለፅም፣ በጉዳዩ ላይ ተቋማት ያላቸው ደረጃና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት በጭራሽ ከፍተኛ ሆኖ አያውቅም። ይኼም በተባበሩት መንግስታት ሥርዓት፣ በመንግስታት ሥራ እና መንግስታዊ ባለሆኑ ድርጅቶች (ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ደረጃ) ውስጥ የሚታይ ተጨባጭ ዕውነታ መሆኑን የሚገልፁ ወገኖች አሉ።

የ ኤ ች . አ ይ . ቪ / ኤ .አይ.ዲ.ኤስ ወረርሽኝ በጤናና ሰብዓዊ መብቶች መካከል መዋቅራዊ ግንኙነቶችን ለመፍጠር አቀጣጣይ ጉዳይ በመሆኑ ላይ የላቀ ትኩረት እንዳልተሰጠው ይገለፃል። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ቀለል ባለ መልኩ የማሕበረሰብ ጤና

ሥትራቴጂዎችን የደገፈው በ1980 ነበር። ይህንንም ተከትሎ ከበሽታው ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ፍቅርና ወገንተኝነት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የዓለም የጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ እየሰጠ ያለውን ትኩረት አስመልክቶ በ1987 ባደረገው ውይይት ላይ አስምሮበታል።

ቀጥሎም ላለፉት አስርተ ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ አማካኝነት ተከታታይ የሆኑ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በጤናና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ተደርገው በዘርፎቹ መካከል ሊኖር የሚገባው ትስስር ወሳኝ ጠቀሜታን እንደሚሰጥ አፅንዖት ተችሮት ነበር። በ1990 ተደርጎ ከነበረው ዓለም አቀፍ የሕፃናት ጉባኤ ጀምሮ በ2001 በዘረኝነት ዙሪያ በተደረገው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ጤናና ሰብዓዊ መብቶችን በጥምረት የመመልከት ትኩረት ተሰጥቷል።

ኃላፊነትና ተጠያቂነትን

አለመዘንጋትበ1994 በሥነ-ህዝብና

ዕድገት ዙሪያና በ1995 የሴቶች ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ኮንፈረንስ በተደረገበት ወቅት በተጠቀሱት ርዕሰ ጉዳዩች ላይ ወሳኝ ውይይቶች ተደርጎባቸው ነበር። በእነዚህ ኮንፈረንሶች ላይ ፖሊስ አውጪዎች፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ የክልላዊ፣ ሀገራዊ፣ መንግስታዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኤጀንሲዎች ተወካዮች ተገኝተዋል። ድርድር የተደረገባቸው የሰነድ ውጤቶችም ለመጀመሪያ ጊዜ በጤናና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ጠንካራ ትስስር መፈጠሩን በማሳየት ዓለም አቀፍ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ላይ ተደርሶ መንግስታት ጤናና ሰብዓዊ

መብቶችን በአንድነት የሚጠብቁት የሕግ አስገዳጅነት እንዲኖር የትኩረት አቅጣጫን ቀየሱ።

ይኼ የመግባቢያ ሰነድም መንግስታት፣ ሌሎች በፖሊሲና በፕሮግራም በመንደፍ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ አካላት ጤናን ከሰብዓዊ መብቶች ጋር ግልፅና ቀለል ባለ መልኩ አቆራኝተው እንዲመለከቱ የብርሃን ጭላንጭል መክፈቱን መረጃዎች ያስረዳሉ። እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ብለው መንግስታትን የሚያግዙ የሥራ ዕቅዶችን በሚነድፉበት ጊዜ የአንድ ሀገር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ያለውን ኃላፊነት፣ የሰብዓዊ መብቶች ቋንቋዎች በሆኑት የኃላፊነትና የተጠያቂነት መሠረት ላይ ሆኖ ሚናውን መወጣት ይጠበቅበታል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ባሉት ሁሉም የልማት ኤጀንሲዎችና ፕሮግራሞች ውስጥ ሁለቱን ዘርፎች በተሻለ መልኩ ለመርዳት ለሚያስችሉ መልካም ትግበራዎች እየተሰጠ ያለው የትኩረትና ሀብት መጠኖች እየጨመሩ ይገኛሉ።

የፕሮግራም መሻሻሎችበ1997 የቀድሞ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የነበሩት ኮፊ አናን በድርጅቱ ፕሮግራሞች ላይ መሻሻሎች እንዲኖሩ አድርገው ነበር። በመንግስታት ድርጅቱ ሥር በዋነኝነት የሚሰሩ አራት የሥራ ዘርፎች መኖራቸውም ይገለፃል። እነዚህም ሰላምና ደህንነት፣ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ጉዳዮች፣ የልማት ትብብርና የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዩች ናቸው። በእነዚህ ላይ ኃላፊነት ወስደው የሚሰሩ እያንዳንዱ ኤጀንሲዎች የጤናን ጉዳይ የማካተት ኃላፊነት እንዳለባቸው የተሻሻሉት ፕሮግራሞች ያስረዳሉ። በአሁን ወቅት በተለያዩ ደረጃ ያሉ የጤና ፖሊሲ ጉዳዮች በጥምረት ለጤናና ሰብዓዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል። የመንግስታት ድርጅቱ የቴክኒክ

ቡድንም በተወሰኑ ሥራዎቹ ላይ ቢያንስ የሰብዓዊ መ ብ ቶ ች ጉ ዳ ዮ ች ን እንዲስገባ ወይም እ ን ዲ ተ ገ ብ ር ኃ ላ ፊ ነ ት ተጥሎበታል። ይኼን መሰል ጉዳይ ግን ከ ዓ መ ታ ት በፊት የሚታሰብ አልነበረም።

ዩኒሴፍ በ2000 በሕፃናት መ ብ ቶ ች ስምምነት ላይ ያሉ የፖሊሲና የ ፕ ሮ ግ ራ ም መ ዋ ቅ ሮ ች እ ን ዲ ሻ ሻ ሉ

አድርጓል። በተ.መ.ድ ስር በኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው (UNAIDS) ተቋም በፖሊሲ እና ፕሮግራሙ ዙሪያ ባሉ ጉዳዮች ላይ ሰብዓዊ መብቶችን ማካተት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ማሻሻያ ማድረጉ መረጃዎች ያስረዳሉ። በ1999 ደግሞ በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅትና በሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራምም በ2000 ላይ ባቀረበው የልማት ሪፖርቱ ላይ ለሰብዓዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጠው ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በ1999 የዓለም የጤና ድርጅት በጤናና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የመጀመሪያውን ሥትራቴጂ ለመንደፍ ተዘጋጅቶ እንደነበረ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የማሕበረሰብ ጤና መማሪያ መፅሐፍ ይጠቅሳል።

ተከታዩን ጽሑፍ በቀጣዩ ሳምንት እንመለስበታለን።

/በተለይ ከተገለፁት በስተቀር ሁሉም አቆጣጠሮች

እ.አ. ናቸ/ው

በኤልያስ ገብሩ[email protected]

ሰብዓዊ መብቶች ሲመቱ

ጤና ያለቅሳል!

በአሁን ወቅት በተለያዩ

ደረጃ ያሉ የጤና ፖሊሲ ጉዳዮች

በጥምረት ለጤናና ሰብዓዊ

መብቶች ትኩረት እንዲሰጡ

እየተደረገ ይገኛል። የመንግስታት

ድርጅቱ የቴክኒክ ቡድንም

በተወሰኑ ሥራዎቹ ላይ ቢያንስ

የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮችን

እንዲስገባ ወይም እንዲተገብር

ኃላፊነት ተጥሎበታል። ይኼን

መሰል ጉዳይ ግን ከዓመታት በፊት

የሚታሰብ አልነበረም።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራምም በ2000 ላይ ባቀረበው የልማት ሪፖርቱ

ላይ ለሰብዓዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጠው ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በ1999 የዓለም የጤና

ድርጅት በጤናና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የመጀመሪያውን ሥትራቴጂ ለመንደፍ ተዘጋጅቶ

እንደነበረ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የማሕበረሰብ ጤና መማሪያ መፅሐፍ ይጠቅሳል

Page 20: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21ሳይንስና ቴክኖሎጂ

በአብዱ መሐመድ

ኤሌ ክ ት ሮ ኒ ክ ስ መሳሪያዎች ውስጥ የምንመለከታቸው የኤሌክትሮኒክስ ም ን ጣ ፎ ች

የተዘጋጁት “ካፓሲተር”፣ “ሬዚስተር” እና “ኮንዳክተር” ከተባሉ መሰረታዊ ቁሶች ነው። እነዚህም ለምንጣፎቹ አስፈላጊውን ኃይል የሚመግቡ ትራንስፎርመሮች ናቸው።

ሰዎች፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተቃጥለዋል ብለው የሚነገሩን ‘አይሲ’ዎችም (Integrated Circuit) ከላይ ከተጠቀሱት የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች የተዘጋጁ ናቸው።

በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በኮምፒዩተር፣ በኤምፒ-3 እና አይፖድ በመሳሰሉ የሙዚቃ ማጫወቻዎች ውስጥ ከፍተኛውን መረጃ የሚያቀነባብሩ ማይክሮቺፕስ የተባሉ የኤሌክትሮኒክስ ምንጣፎች ውስጥ መረጃን በተፈለገ ቦታ የሚያደርሱ፤ የመረጃ ቋቶችን እየከፈቱና እየዘጉ ዘብ ሆነው የሚመሩትና (Electronics Gets) በተፈለገው አቅጣጫ የሚጓጓዙት ‘ትራንዚስተር’ በተባሉ ማብሪያ ማጥፊያዎች አማካኝነት ነው።

‘ፔንቲየም 4’ የተባለው በዘመናዊ ኮምፒዩተሮች ውስጥ የሚገኝ ሲም ካርድ ወይም የጣታችንን አንድ አንጓ የሚያህል ማይክሮቺፕስ በአይን የማይታዩ ሰባት ሚሊየን ትራንዚስተሮችን በውስጡ ይዟል።

“ሲልከን ቫሊ” በተባለው የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ለማመን በሚከብድ ፍጥነት በሳይንስ ልብ-ወለዶች ሲተነብዩ የቆዩ ትናንሽ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችና መሳሪያዎች ለመስራት የተቻለው “ማይክሮቴክኖሎጂ” በተባለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው።

የጃፓን ሳይንቲስቶች እ.አ.አ በ1991 “ካርቦን ፋይበር” የተባለ ከፀጉር ሃያ አምስት እጅ የሚቀጥን፣ ከብረት በ100 ዕጥፍ የሚጠነክር ሞሎኪዩል ማግኘታቸው ነው “ናኖ ቴክኖሎጂ” የተባለው የጥናት ዘርፍ ሕያው የሆነው፤ ሰውነት ውስጥ ገብተውም የጤና መረጃ የሚያቀብሉ ኤሌክትሮኒክስ እንክብሎች፣ የማይታዩ ሰላይና አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች መፈብረክ የተቻለው።

የናሳ ተመራማሪዎች ከሃያ ዓመት በፊት ያቀዱትን ህልም እውን ባደረገው በናኖ ቴክኖሎጂ ለውጤት ከበቁ መሳሪያዎች መካከል በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ተመራማሪዎች የተሰራው ቴክኖሎጂ የሚጠቀስ ነው። የፀጉር ያህል ውፍረት ነው ያለው፤ በደቂቃም አምስት መቶ ጊዜ ይሽከረከራል - ሳይንቲስቶቹ ያዘጋጁት፣ በአጉሊ መነፅር በሚታዩ የብርሀን ክሮች ተያይዞ የተዘጋጀውና ለስለላ የሚሰማራው የነፍሳት ያህል መጠን ያለው ሮቦት።

በባልቲሞር ሜሪላንድ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሰውነትን የሙቀት መጠን እየለካ መረጃ የሚያስተላልፍ የሙቀት መለኪያ ዕንክብልና በደም ውስጥ እንደ ሰርጓጅ መርከብ እየዋኘ ህዋሳትን የሚያክም መሳሪያ አዘጋጅተው ተግባራዊ ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።

በጃፓን ቶኪዩ ዩኒቨርስቲ የደም ዑደት አማካኝነት በሰውነት ክፍሎች ውስጥ ገብተው በበሽታው

የተመረዙ ህዋሳትን መመርመር የሚችሉ ሮቦቶች የህክምና ሥራን እያቀላጠፉ ይገኛሉ።

የናሳ ሳይንቲስቶች ባዘጋጁት ንድፍ አይ.ቢ.ኤም፣ ጀነራል ሞተርስ፣ ፎርድ፣ ሐውሌት ፓካርድ፣ ዱፓርድ፣ ዱፓንት፣ በርክሌይ፣ ስታንፎርድ እና የአሜሪካ ባሕር ኃይል ቤተ-ሙከራ በምስጢር እየገነቧቸው የሚገኙት ማይክሮ-ሮቦቶች፣ የጠላት ጀነራሎችን አእምሮ መስለብ እስከሚችል ብቃት ተላብሰው የሚቀርቡ መሆናቸው ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

ይህንኑ በተመለከተ የአሜሪካ ናሽናል ሳይንስ ፋውንዴሽን በሰጠው ጥቆማ አንድ የስኳር ቅንጣት የሚያህሉ ሮቦቶች እንደ ወታደር ወይም እንደሰላይ በጦር አውድማ የመረጃ አውታሮችን በማደናገር፣ መረጃን በመጥለፍና በማስቀየስ የጠላት ሠራዊት የራሱን ጦር እንዲያደባይ የማድረግ ብቃት የተላበሱ ናቸው።

እየተፈበረኩ የሚገኙት ማይክሮ-ሮቦቶች በኮምፒዩተር መስመሮች ውስጥ ትዕዛዝ እየጠበቁ ያለምንም ዕንቅስቃሴ መቆየት መቻላቸው ሌላው የብቃታቸው መለኪያ ነው። እነዚህ ያደፈጡ ሰላይ ሮቦቶች ከራዳር በሚያገናኛቸው የሬዲዮ ሞገድ እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ሲታዘዙ የጠላትን ጦር ማሸበር ይጀምራሉ።

ሮቦቶቹ የኤሌክትሮኒክስ ምንጣፍ መስለው የጠላት የኮምፒዩተርና የመገናኛ አውታር ውስጥ ስለሚለጠፉ ከውስጥ ፈልጎ ለማግኘት የማይሞከር ነው።

የነፍሳት ያህል መጠን ያላቸው አየር ወለድ ሮቦቶች፣ ከቀይ በደበዘዘ የቀለም ምልክት የጠላት ሰራዊት የሰፈረበትን ቦታ በመጠቆም ከታቀደ መርሃ ግብር ቀድመው ተግባራቸውን

ያከናውናሉ። በአሸባሪዎች የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል፣ በአሸባሪዎች የታገቱ ሰዎችን ለማስለቀቅ፣ አሸባሪዎችን ለመደምሰስና በቁጥጥር ሥር ለማዋል፣ አሸባሪዎችና ታጋቾች ባሉበት ህንፃ ሰርገው እየገቡ መረጃ ያቀብላሉ።

“SEAL” የተባለው የአሜሪካ ልዩ የባህር ኃይል ኮማንዶ ቢን-ላድንን ለመግደል ከመንቀሳቀሱ በፊት በፓኪስታን በኦታባድ ለስምንት ወራት የቢንላደንን ዕንቅስቃሴ በምስጢር ሲከታተል የነበረው በእነዚህ ሮቦቶች ረዳትነትና ምሽት ላይ ወደቅጥር ግቢው እየበተነ ለሳተላይት የምስል መረጃ በሚያቀብል ማይክሮቺፕስና በሰላይ ሮቦቶች ነበር።

ከእነዚህ ሰላይ ሮቦቶች አንዱ በጊነስ ቡክ የዓለማችን ትንሹ ሰላይ በማለት ዕውቅና የሰጠው ‹‹ብላክ ዊዶው›› የተባለው ሮቦት ነው።

በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘው ኤይሮቫይሮመንት ሞኖሮቪያ የተዘጋጀው የትንሹ ሰላይ አውሮፕላን የክንፍ ርዝመት ስድስት ኢንች ወይም 15.24 ሳንቲ ሜትር ነው። ክብደቱ 80 ግራም ሲሆን ሁለት ግራም በሚመዝን ባለቀለም ካሜራ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ከአእዋፍና ከሌሊት ወፍ ተመሳስሎ በሰዓት 425 ኪሎ ሜትር ወይም በሰከንድ 7.08 ኪሎ ሜትር የመክነፍ ብቃት የተላበሰ ነው።

ሰላይ ሮቦቶች መረጃን ከመጥለፍ በተጨማሪ የተዋጊ አውሮፕላኖችና ሂሊኮፕተሮችን የማጥቀት እንቅስቃሴ ያፋጥናሉ። የግንኙነት መስመር ሲቋረጥ ፊት ቀድመው አውሮፕላኖችና ሂሊኮፕተሮችን ይመራሉ። የተበላሹ የመገናኛ አውታሮችን በፍጥነት ይጠግናሉ። መፍትሄ ሲገኝ የብርሀን ብልጭታ በማሳየት ሊደርስ ከነበረ አደጋ ማምለጡን ለአብራሪው ይጠቁማሉ።

ለህክምናው ዘርፍ የተዘጋጁ ማይክሮ-ሮቦቶች በመጠናቸው ትናንሽ የሆኑ ኮምፒዩተሮችን፣ መጋዞችን፣ መቀሶችን ይዘው የቀዶ ጥገና ረቂቅ ጥበብ በርቀት እየተቆጣጠሩ ለማከናወን በሚያስችል ተግባር እየተንቀሳቀሱ ነው።

በእንግሊዝ ብሔራዊ የፊዚክስ ላብራቶሪ የኳንተም ዲቴክሽን ተመራማሪ በዶክተር ዴቪድ ኮክስ የተዘጋጀው የዓለማችን ትንሹ የሰው ሮቦት (‹‹The World’s Smallest Snow Man››) የጊነስን ክብር የተቀዳጀው ከፀጉር አንድ አምስተኛ መጠን ያለው ተክለሰውነት ተላብሶ የማይክሮ ሮቦቶች ግንባታ ላይ ከተሰማራ በኋላ ነው።

ከጥቃቅን የፕላቲኒየም ብናኞች የተሰራውና ከአይን ጨረሮች በተሰሩ አይኖቹ ፊቱ ላይ ሰማያዊ ብርሀን የሚያፈነጥቅ ፈገግታ እየታየ በናኖ ቴክኖሎጂ የተሰማራው ‹‹ስኖው ማን››

ሰላዮቹ

ሮቦቶችአዳኝና አዳኝበኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሌንስ በሚደርሰው መረጃ እየተመራ ከአንድ ሚሊ ሜትር አንድ መቶኛ ቅንጣት የማይበልጡ ማሽኖችን ያዘጋጃል።

ከእነዚህ ማሽኖች ውስጥ ‹‹ስፒንትሮኒክስ›› የተባሉ የእያንዳንዷን የፓርቲክል ቅንጣት እየፈተሹ የአየር ፀባይ መረጃ የሚያቀብል መሳሪያ፣ የሴል አወቃቀር የሚያጠና የዲኤንኤ መሳሪያዎች የአተም ቅንጣቶችን ማግቴቲክ ባህሪ የሚፈትሹ ሮቦቶችን በዋቢነት ያስቀመጠው ብቃቱን አረጋግጦ እውቅናውን የሰጠው ጊነስ ቡክ ‹‹ወርልድ ሪከርድስ አካዳሚ›› በተባለው ድረ-ገፁ ባሰራጨው ዜና ነው።

አሜሪካ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ጦሯን ባዘመተችበት በአፍጋኒስታን ጦርነት ለግዳጅ ባሰማራቻቸው ሰው አልባ ጀቶች ለ‹‹ድሮንስ፣ ፕሪዳታር ሪፐር›› የጠላትን ዕንቅስቃሴ የሚጠቁሙት በአፍጋኒስታን ምድር እንደ አሸዋ የተዘሩት ማይክሮ-ሮቦቶች ናቸው።

ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ እና ቻይና ህዋን ለመቆጣጠርና ተቀናቃኞቻቸውን ለመገዳደር የሚያዘጋጇቸውን ሳተላይቶችና የረዣዠም ተወንጫፊ መሳሪያዎች ግንባታንና ሙከራ የሚያጋልጡት እነዚህ የነፍሳት ያህል መጠን ያላቸው አየር ወለድ ሮቦቶች ለተሰላዮቹ ሀገራት የተሰወሩ አይደሉም።

በዓለማችን ላይ ሁሉም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደወታደራዊ መሳሪያነት የተቀየሩት የሰውን ችግር ለመቅረፍና መረጃን ለማቀላጠፍና ወጪን ለመቀነስ እንደታሰበ በሚገልፅ ፕሮፓጋንዳና በጀት እየተደገፈ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።

የዓለም መንግስታት በኮንክሪት ዋሻዎች ውስጥ ያከማቹዋቸው ለህዝብ ትራንስፖርት ቢውሉ ሰማይን እንደ ታክሲ የሚያጥለቀልቁ የጦር ጀቶች ለገበያ የቀረቡት የአየር ትራንስፖርት መጓጓዣዎችን ግኝት ገልብጠውና በስማቸው የፀደቀ በጀት አወራርደው ነው።

አውዳሚ ሚሳየሎች በየሀገሩ የአጠና ቁልል የሰሩት በሳተላይት ጥቁር መጋረጃ እየተሸፈኑ፣ እንደ ህንድና ፓኪስታን የኑክለር ጦር መሳሪያ የታጠቁት፣ የኑክለር ኃይል ማመንጫ እንገነባለን የሚል አቋም እያራመዱ ለመሆኑ ከታሪክ በላይ ምስክር የለም።

ፔንታጎን ለህዋ ምርምር ጥናት ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋሉ፣ ሳተላይቶች ሲበላሹ ይጠግናሉ፣ ለጥገና የሚመላለሱ የህዋ ተመራማሪዎችን ድካምና ወጪ ይቀንሳሉ ያላቸውን ማይክሮ-ሮቦቶች ወደ ጦር መሳሪያና የስለላ ማሽን የቀየረው የተለመደውን ማዘናጊያ እያናፈሰ ለመሆኑ ነጋሪም መስካሪም አያስፈልግም።

ከፋም ለማም ማይክሮ-ሮቦቶች የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎችን አሸባሪ እያሉ የሚያግቱ እና ወደወህኒ የሚከቱ አምባገነን መንግስታት ጓዳ እየዘለቁ መረጃ በመጥለፍ ቅጥፈትን የማጋለጥ ብቃት ተላብሰዋል የሚለው ዘገባ እሰየው የሚያሰኝ ነው።

ከጥቃቅን የፕላቲኒየም ብናኞች የተሰራውና

ከአይን ጨረሮች በተሰሩ አይኖቹ ፊቱ ላይ ሰማያዊ

ብርሀን የሚያፈነጥቅ ፈገግታ እየታየ በናኖ

ቴክኖሎጂ የተሰማራው ‹‹ስኖው ማን››

በኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሌንስ በሚደርሰው መረጃ እየተመራ ከአንድ ሚሊ

ሜትር አንድ መቶኛ ቅንጣት የማይበልጡ ማሽኖችን ያዘጋጃል።

Page 21: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003ስ ፖ ር ት22

የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የኃላ መስመር ደጀን ነበር። የክለቡን ቤተሰብዎች አግኝታችሁ ብትጠይቋቸው ይህ ተጨዋች በታማኝነት እንዳገለገላቸው ሳይሳስቱ ይነግሯችኋል። ከቡድኑ

ከተለየ ስምንት ዓመት ቢደፍነውም ዛሬም ድረስ የአንጋፋው ቡድን ደጋፊዎች ቢጫ እና ቀዩ መለያ ጀርባ 16 ቁጥር ሲመለከቱ ትውስ የሚላቸው እሱ ነው። ይህ ተጨዋች የቅ/ጊዮርጊስ ዋና ቡድን ከ1985-1995 ዓ.ም. መጨረሻ አቋሙ ሳይዋዥቅ ያገለገለው ዘሪሁን ሽንገታ (ሚሪንዳ) ነው።

በ1984 ዓ.ም. ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ይከታተልበት የነበረውን ተፈሪ መኮንንን ወክሎ ሲጫወት የተመለከቱት ችሎታውን ለቅ/ጊዮርጊስ ወጣት (ቢ) ቡድን አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ይነግሩታል። ስዩምም ሲጫወት ተመልክቶት የቡድኑ አባል አደረገው። በቀጣዩ ዓመት የዋናው ቡድን አሰልጣኝ የነበረው መንግስቱ ወርቁ ወደ ዋናው ቡድን አሳደገው። ቶሎ የመሰለፍ እድል ቢያገኝም ይጫወት የነበረው የቦታ ለውጥ አድርጎ ነበር።

ለትምህርት ቤት እና ለቅ/ጊዮርጊስ ቢ ቡድን የሚሰለፈው በአጥቂ ስፍራ ነበር፡፡ በዋናው ቡድን ግን አገሩን እና ክለቡን በጠቀመበት፣ በርካታ አድናቂ በሰበሰበበት በተከላካይ ቦታ መሰለፍ ጀመረ። በርግጥ ይህ ዞን ለእርሱ አዲስ አልነበረም። በወጣት (ቢ) ቡድን ሳለ ከመሩ እና ውጤት ለማስጠበቅ ሲያስብ እንዲሁም ተከላካዩ ከሳሳ አሰልጣኙ ወደ ኃላ እየመለሰው ያጫውተው ነበር።

ከመንግስቱ ወርቁ በኋላ የዋናው ቡድን ኃላፊነትን የተረከበው አስራት ኃይሌ በዘሪሁን የተጨዋችነት ዘመን አብላጫውን ዓመት ያሰለጠነው አሰልጣኝ ነው። በዲስፕሊን ላይ ጠንካራ አቋም ያለው አስራት (ጎራዴው) የሚሰጣቸውን መመሪያዎች ስለሚተገብር አሰልጣኙም በእሱ ላይ እምነት ስላለው ‹‹የአስራት ልጆች›› ከሚባሉት ተጨዋቾች አንዱ ነበር፤ ፋሲል ተካልኝ እኛ አሸናፊ ሲሳይ ሌሎቹ ‹‹የአስራት ልጆች›› ናቸው። ‹‹እኛ የአስራት ልጆች የተባልንበት የተለየ ምክንያት ኖሮ ሳይሆን የምንታዘዘውን በአግባቡ አክብረን ስለምንሰራ፤ እሱም ከእኛ ጋር እሰጣ አገባ ውስጥ ገብቶ ስለማያውቅ ነው›› ይላል ዘሪሁን ምክንያቱን ሲያስረዳ።

አስተያየት ሰጪዎች 1980ዎቹ መጨረሻ ይካሄድ የነበረውን የአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ሻምፒዮና ‹‹በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ የነበረው የመጨረሻው የፉክክር ዘመን›› ይሉታል። ቅ/ጊዮርጊስ፣ መብራት ኃይል፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ባንክ፣ መድን ድርጅት ጠንካራ የሊጉ ተፋላሚ ቡድኖች ነበሩ። አየር መንገድ፣ እርሻ ሰብል፣ ኦሜድላና ኪራይ ቤቶችም በቀላሉ እጅ የማይሰጡ የውድድሩ ድምቀቶች ነበሩ፡፡ ዘሪሁንም ያ ትውልድ የነበረው የጨዋታ ፍላጎት እና መንፈስ ከፍተኛ እንደነበር ይገልፃል። ‹‹የአሁን ተጨዋቾች ‘ፍላጎት የላቸውም’ ማለት ባይሆንም የዚያ ወቅት የተጨዋቾች፣ የውድድሩና የደጋፊውም ስሜት ግን ከፍተኛ ነበር፡፡››

ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር በድል የደመቀው ዘሪሁን ሸንገታ ዋንጫ ያልሳመው በ1989 እና 1993 ዓ.ም. ብቻ ነው። ‹‹የቅ/ጊዮርጊስ ቡድን የማሸነፍ ስሜት ተመሳሳይ ስለሆነ ሁለሌ የሚጫወተው ዋንጫ ለማንሳት ነው›› ይላል ቡድኑ አገራዊ ዋንጫዎችን ስለሰበሰበበት ምስጠር ሲገልፅ።

በ1995 ዓ.ም. ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በገጠመበት የመጨረሻ ሊግ ጨዋታ ኬኒያዊው ኤሪክ ሙራንዳ ባስቆጠራት ወሳኝ ጎል ‹‹ሻምፒዮን›› ቢሆንም ይህ ድል ዛሬም ድረስ

በአነታራኪነቱ ይታወሳል። በዚህ ዓመት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዘሪሁንን ወደዚህ ክለብ የቀላቀለው ስዩም ከበደ ሲሆን ዘሪሁንም እንደቀድሞው የመሰለፉ ሁኔታ አነስተኛ ነበር።

ጫማውን ሰቀለ። ክለቡ 50 ሺህ ብር ሸልሞ አመስግኖ ሸኘው። ከዚያ በኋላ ከእናት ክለቡ ጋር የነበረው ግንኙነት በደጋፊነት በስታዲየም ታድሞ ጨዋታ ከመከታተል የዘለለ አልነበረም። ከሰባት ዓመት በኃላ በዘንድሮ መስከረም ወር ዳግመኛ የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ አባል ሆነ፤ የአዳጊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት በመረከብ።

‹‹በተጨዋችነት ዘመን ኃላፊነት የሚወስድልህ ሰው (አሰልጣኝ) አለ። አሰልጣኝ ስትሆን ግን ሙሉ ኃላፊነቱን የምትወስደው አንተ በመሆንህ ከባድ ነው›› በማለት አዲሱ ሙያው ትልቅ ትጋት እንደሚጠይቅ ዘሪሁን ያወሳል። ባለፈው እሁድ በፍፃሜ ጨዋታ የቅ/ጊዮርጊስ አዳጊ ቡድን ከመብራት ኃይል አቻው ጋር በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2-2 በመለያየቱ በተሰጠው የመለያ ምት 5-3 በማሸነፉ ዘሪሁን በመጀመሪያ ዓመት የአሰልጣኝነት ህይወቱ ጣፋጭ

ድልን አጣጥሟል። ክለቡ ያስቀመጠበት ዋና

ኀላፊነት ዋንጫ መሰብሰብ ሳይሆን በሂደት ለዋናው ቡድን የሚጠቅሙ ተጨዋቾችን መመገብ ነው። ዘሪሁን ‹‹ወንድሜ›› ሲል ለሚገልፀውና ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫ ባነሳው ፋሲል ተካልኝ ለሚሰለጥነው ወጣት ቡድኑ ተጨዋች ያቀርባል። ተጨዋቾች በቀጥታም ወደ ዋናው ቡድን የሚሄዱበት መንገድ ክፍት ነው። የዋናው ቡድን አለቃ ጣሊያናዊው ጁሴፔ ዶሴና የዘሪሁን ቡድን አጥቂዎች አጥላባቸው ጨንቆ እና አምደ ጽዮን ጥላሁን ላይ አይናቸው አርፏል። በቅድመ የውድድር ዘመንም ለዝግጅት ይዘዋቸው ይጓዛሉ። ይህ ሂደት መሰረቱን ጠብቆ እንዲጓዝ አዳዲስ ተሰጥኦን ማደን ስላለበት የቤት ስራው ቀላል የማይባል መሆኑ አያጠያይቅም። ለዚህም ዝግጁ

መሆኑን ያወሳል። ፋሲል ተካልኝ ከዘሪሁን

ጋር በመጣመር በቀዩ እና ቢጫው መለያ ያደርጉት እንደነበረው የተናበበ የመስመር ላይ እንቅስቃሴ ሁሉ በአሁን ሰዓት ለቅ/ጊዮርጊስ አዳዲስ ልሂቃንን የመፍጠር ኃላፊነት ተደቅኖባቸዋል። የቅ/ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ፋሲል አዳጊዎችን ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ጓደኛው ዘሪሁን ተገቢ ሰው መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ‹‹ዘሪሁን በእግር ኳስ ጨዋታ ህይወቱ ለቅ/ጊዮርጊስ እና ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን ከሰራው እና ካካበተው ልምድ አንፃር ታዳጊዎችን ለመፍጠር ትክክለኛው አሰልጣኝ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ከጅምሩም ይህንኑ አሳይቷል፡፡ ወደፊት ደግሞ የበለጠ መስራት ይችላል፡፡›› በማለት መልካም ዓመታት ከፊቱ እንዳሉት ጠቁሟል፡፡

በ2003 ዓ.ም. መጀመሪያ በአዳጊ ቡደኑ ከነበሩት ውስጥ ወደ ወጣት ቡድኑ አድገው፣ ወደ ሌላ

ክለብ ሄደውና ተቀንሰው የቀሩት አስር ብቻ የነበሩ ሲሆን ፋሲል እና ዘሪሁን በጋራ በመሆን ከ1400 በላይ አዳጊዎች መሀከል በመመልመል 14 ተጨዋቾችን መርጠው የሲ ቡድኑን ስኳድ አሟልተዋል።

ዓመታዊ ውድድሩ ጠንካራ ፉክክር የተካሄደበት እንደበር ለአውራምባ ታይምስ የገለፀው ዘሪሁን ሸንገታ በሃያ ቡድኖች መሀከል በሦስት ምድብ ተከፍሎ በተካሄደው ውድድር 7 ቡድኖች ከነበሩበት ከምድባቸው አንድም ጨዋታ ሳይሸነፉ በ36 ነጥብ ምድባቸውን በአንደኝነት በመጨረስ ወደ ሩብ ፍፃሜ የገቡ ሲሆን የሌሎቹ ምድቦች መሪዎች ግን የነበራቸው እኩል 21 ነጥብ ነበር።

‹‹አሸናፊ እንድንሆን ተጨዋቾቼ ብርቱ ጥረት አድርገዋል›› በማለት በ15 ጨዋታ ላይ የመዘናቸውን ልጆቹን ያመሰግናል። ወደ ፊትም ለቅ/ጊዮርጊስም ሆነ ለአገር የሚጠቅሙ ተጨዋቾች እንዳሉት በልበ ሙሉነት ይናገራል። ‹‹ምን ህል ይሆናሉ?›› ብላችሁ ቁጥራቸውን ብትጠይቁት ‹‹በቃ!›› እስክትሉት ድረስ ከስምንት በላይ ተጨዋቾችን ይጠራላችኋል።

በቀጣይ ጊዜያት ካለው ካፍ እውቅና ከነፈገው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ሰርተፍኬት ከፍ ያሉ ስልጠናዎችን ወስዶ በተጨዋችነት በደመቀበት ክለብ በአሰልጣኘነትም ማገዝ ይሻል። ‹‹ለመለያው ሟች ነበር፡፡ ስነ ስርዓት ያለው እና ሙያውን አክባሪ ነው፡፡ ይህንን ወደ ተጨዋቾቹ ማስተላለፍ ይቻላል›› ይላል ፋሲል፡፡

2003 ዓ.ም. የዘሪሁን ዓመት!በዓመቱ የቅ/ጊዮርጊስ ዋናው

ቡድን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስረኛ፣ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ውድድር የመጀመሪያ ዋንጫውን ያነሳል ተብሎ ተጠብቆ ባዶ እጁን ቢቀርም፤ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ከአንደኛው ዙር ማለፍ ቢሳነውም በወጣት እና አዳጊ ቡድኑ ግን አላፈረም፡፡

2003 ዓ.ም. በብዙ መልኩ ለዘሪሁን የስኬት ዓመት ነው። እሱም ይህንን ሲገልጽ በደስታ ተሞልቶ ነው። ‹‹ኪዳነ ምህረት ከሰጠችኝ ሶስና ኃይሌ ጋር ትዳር የመሰረትኩበት፣ ወደምወደው ክለቤ ቅ/ጊዮርጊስ ተመልሼ በአሰልጣኝነት ስራ የጀመርኩበት፣ እግዚአብሔር ረድቶኝ በመጀመሪያ ዓመቴ ዋንጫ ያነሳሁበት፣ ኮከብ አሰልጣኝ ተብዬ የተመረጥኩበት በመሆኑ ይህ ዓመት የእኔ ነው ማለት እችላለሁ። የረዱኝን ሁሉ አመሰግናለሁ›› ሲል ደስታውን ለአውራምባ ታይምስ ገልጿል፤ ሚሪንዳ ደጋግሞ ከመጠጣቱ የተነሳ የለስላሳ መጠጡን መጠሪያ ቅፅል ስሙ ያደረገው ዘሪሁን ሸንገታ።

በአቤል ዓለማየሁ

በ2004 ዓ.ም. የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚቀላቀሉ ሁለት ቡድኖች ነገ ይለያሉ። ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከአየር ኃይል የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት አግኝቷል።

በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው ተቀራራቢ የሆኑ ክልሎች በአንድነት ውድድር ያካሄዱበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ላይ የመጨረሻዎቹ አስር ቡድኖች፣ በሁለት ምድብ ተከፍለው ለሁለት ሳምንት ያህል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከትላንት በስቲያ የተጠናቀቀ ሲሆን ከምድብ ‹‹ሀ›› አየር

ኃይል እና አርባ ምንጭ ከነማ፣ ከምድብ ‹‹ለ›› መተሐራ ስኳር እና ኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንደ ቅደም ተከተላቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው በማለፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ገብተዋል። በዚህ መሰረት ነገ በ8፡00 የምድብ ‹‹ሀ›› አንደኛ አየር ኃይል ከምድብ ‹‹ለ›› ሁለተኛ ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ቡድኖቹ ካላቸው ታሪክ እና ተቀራራቢ አቋም ሳቢያ ይጠበቃል። በ10፡00 አርባ ምንጭ ከነማ ከመተሐራ ስኳር ይጫወታሉ። የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች በቀጣዩ ዓመት ፕሪምየር ሊጉን መቀላቀል የሚያስችላቸውን ትኬት ይቆርጣሉ።

መድን ካሸነፈ ልደታው ኒያላ በፕሪምየር ሊግ በመውረዱ ሊያንስ የነበረውን የአዲስ አበባ ክለቦች ቁጥር ይሞላል። ድሉ የአየር ኃይል እና መተኃራ ስኳር ከሆነ በመውረዳቸው ሳቢያ ተወካዮቹን ሰበታ ከነማ እና ፊንጫ ስኳርን ያጣው ኦሮሚያ ተስፋ ዳግም ያብባል። አርባ ምንጭ ከነማ አሸናፊነቱን ካወጀ ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ የደቡብ ተወካዮች ቁጥር ወደ ሦስት ከፍ ከማለቱም በላይ በ1995 ዓ.ም. መጨረሻ ከአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ክለብ መፍረስ በኋላ የደበዘዘው የከተማው እግር ኳስ ይነቃቃል።

ፕሪምየር ሊጉን የሚቀላቀሉ ቡድኖች ነገ ይለያሉ

የቅ/ጊዮርጊስን መለያ ብቻ ለብሶ ጫማውን የሰቀለው ዘሪሁን ሸንገታ በተጨዋችነት ዘመኑ ያገኘውን ስኬት በአሰልጣኝነቱም ለመድገም የሚያስችለውን የመጀመሪያ ድል ከቅ/ጊዮርጊስ አዳጊ ቡድን ጋር አግኝቷል፡፡ ተከታዩ ፅሁፍ የቀድሞውን ተከላካይ የተጨዋችነት ዘመን እያስታወሰ ስለ አሰልጣኝነት ጅማሮው እና ለምን “ይህ ዓመት የእኔ ነው” እንዳለ ይነግረናል፡፡

ዘሪሁን ሸንገታ [ቅ/ጊዮርጊስ] ፡-

‹‹ይህ ዓመት የእኔ ነው!››

አጭር መልሶች

በተጨዋችነት ዘመንህ ከተመለከትካቸው

ተከላካይ ተጨዋቾች ማንን ታደንቃለህ?

አንዋር ሲራጅ እና ሳሙዔል ደምሴን (ኩሻሻ፡

፡)

ምርጡ አሰልጣኝህ?

ብዙ ዓመት ያሳለጠነኝ አስራት ኃይሌ እና

መንግስቱ ወርቁ።

የህይወትህ ምርጡ ጊዜ?

ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ዋንጫ ያነሳሁባቸው

ዓመታት።

የምታስቀድመው አሸናፊነት?

በ1987 ዓ.ም. ባንክ ሦስት እድል ይዞ

ገብቶ 3-1 በማሸነፍ ዋንጫ ማግኘታችን

የማይረሳ ትልቅ ድል ነው።

የህይወትህ መጥፎ ዓመታት?

ተወው እሱ ይቅር።

የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ‹‹ዘሪሁን ሸንገታ

የወያላ ጌታ›› እያሉ ያወድሱሀል። ወያላው

ግን ማነው?

ወያላው ይሄ ነው የምልህ ነገር የለም።

ደጋፊዎች ጥሩ ነገር ስታደርግ የሚያሞካሹበት

የራሳቸው ዘዬ አላቸው። የእኔም እንዲሁ ነው

ማለት ነው።

በአሰልጣኝነት ያገኘኸውን የመጀመሪያ

ዋንጫ መታሰቢያነቱን ለማን አደረግከው?

ኤሊያስ በስር የቡድኔ የአማካይ አጥቂ

ተጨዋች ነው። ከተጨዋቾች ጋር ምሳ

ለመብላት ሲሻሙ በለስለሰ ተሰ……አይኑ

ጥቀሩን ስለተጎዳ የመጨረሻዎቸን ጨዋታዎች

አልተጫወተም። እኔም ሆንኩ ሁሉም የቡድኑ

ተጨዋቾች መታሰቢያነቱን ለእሱ አድርገናል።

‹‹በተጨዋችነት ዘመን ኃላፊነት የሚወስድልህ ሰው (አሰልጣኝ) አለ። አሰልጣኝ ስትሆን ግን ሙሉ ኃላፊነቱን

የምትወስደው አንተ በመሆንህ ከባድ ነው›› በማለት አዲሱ ሙያው ትልቅ ትጋት እንደሚጠይቅ ዘሪሁን ያወሳል።

Page 22: Awramba Times Issue 176

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 176 ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃየሚያወርድ

ምቾት እናጥራት ያለው

ከበቂ መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ የተመሳሰሉትን

ይለዩ

ስ ፖ ር ት

እና ተፈጥሮ የነበረው የሕዝቡ የአንድነት መንፈስ ሊረብሹ የተላኩትንም ያስደነገጠ ክስተት ሆኖ ነበረ ያለፈው።

በዕለቱ ታቅዶ የነበረው ግርግር የአደባባይ ምስጢር ነበርና፣ ክስተቱ ቢፈጠር ኖሮ አጸፋውን ለመመለስ የተዘጋጁም እንደነበሩ ስለታወቀ የሚዲያው ሰዎች ካሜራቸውን ደግነው ሲጠባበቁ፣ የግቢው ሴኩሪቲ አባላት እና የአትላንታ ፖሊሶችም ባይነ ቁራኛ ይከታተሏቸው እንደነበር ተመለከትን።

ዳኛ ብርቱካን ንግግር በምታደርግበት ጊዜ እነ አያያም ከመድረኩ ጎን ነርቨስ ሆነው ሲቁነጠነጡ የካሜራ ዓይን ውስጥ ገብተዋል። ፕሮግራሙ በጣም ዘግይቶ እንዲጀመር መደረጉ፣ የድምፅ ማጉያው እንዳይሰማ የተደረገው ተንኮል… ወዘተ የሼኩን ሰዎች ሊያስደስታቸው ይችል ይሆናል እንጂ ሕዝቡ መልዕክቱን እንዳያዳምጥ አላደረገውም።

የክብር እንግዳዋ ንግግር የፈጠረው ሙድ እነ እያያን ለምን እረፍት እንደነሳቸው የሚደንቅ ነው። ምናልባት እነዚህ ወገኖች ንግግሩን ሰሙ እንጂ አላዳመጡት ይሆናል። ንግግሩን ቢያደምጡት ኖሮ ስለ ይቅር ማለት፣ ስለ መዋደድ እና ስለ አንድነት ዳኛ ብርቱካን በመናገርዋ ይልቁንም በተደሰቱ ነበር።

የአትላንታው አድማስ ሬዲዮ ላይ ቴዲ እና ሰይፉ ፋንታሁን፣ ውስጥ አዋቂዎችን በማጣቀስ የሼኩ ገንዘብ ተከፋፍሎ ሊመለስ መሆኑን፣ ሁለቱ ወገኖችም በዚህ መስማማታቸውን ሲናገሩ ተደምጠዋል። እነ አብነት በገንዘቡ ተቋሙን በቁጥጥር ስር ማድረግ ስለተሳናቸው በእርዳታ መልክ የሰጡትን 240,000 ዶላር ለማስመለስ፣ ከዚያ በላይ ወጭ ማድረግ ነበረባቸው። ያም ሆነ ይህ ብሩ ሲሄድ ችግሩንም ይዞት ይሄዳል የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉምና ለነዚህ ውገኖች ይህ በበጎ የታየ ጥሩ ዜና ነው።

አትላንታ በዚህ ዓይነት

ሊጠናቀቅ ቻለ። የወደፊቱን ግን ማወቅ በጣም ከባድ ነው። ፌዴሬሽኑ ብዙ ትናንሽ ችግሮች - እና ትልቅ የአመራር ችግር - ላይ ነው የሚገኘው። ከትናንሽ ችግሮቹ ይልቅ ትልቁን ችግር መፍታቱ የሚቀል ይመስላል። አመራሩ በቅርቡ በአዲስ ኮሚቴ ይተካል። አዲሱ አመራር ካለፈው ስህተት ይማርና የብዙሃኑን ፍላጎት ይጠብቃል የሚል እምነት አለ። ይህ ካልሆነም ብዙ አያሰጋም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን የሚያሰባሰብ ሌላ አማራጭም ብቅ ብሏል። … የኢትዮጵያ ውርስ እና ቅርስ! በጥቅሉ ስናየው የአትላንታው ዝግጅት ልዩ ነበር። የሕዝብ ድምጽ የገንዝብን ኃይል ያሸነፈበት፤ መርህ ሕገ-ወጥነትን የረታበት፤ የብዙሃኑ ውሳኔ የጸናበት… ።

በመጨረሻም ሰለሞን ተካልኝ…

ዕለተ ዓርብ፣ ከላውረንስቪል ካውንቲ ወደ አትላንታ ስንጓዝ በክላርክስተን ማቋረጥ ነበረብን። እዚያ ካሉት የኢትዮጵያ ሱቆች መካከል ‘ሶል ሙዚቃ ቤት’ አንዱ ነው። የሰለሞን ተካልኝ ሙዚቃ ቤት እንደሆነ ወዳጄ ዳዊት ነገረኝ እና ሰለሞንን ለማግኘት ወደዚያው አመራሁ።

ከውጭ በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ። በግራ በኩል የሚታዩ ትናንሽ ክፍሎችን አልፌ ወደ ሙዚቃው ቤት አመራሁ። ግራና ቀኝ ባማትር ምንም ሰው ስላላየሁ ወደመጣሁበት ተመለሰኩ። ከሱቁ ለመውጣት እበር ላይ ስደርስ ሰለሞን ከውስጥ ሆኖ ‘ክንፉ’ ሲል ጠራኝ።

“ከውስጥ በካሜራ አይቼህ ነው የመጣሁት። ና ግባ” ብሎ ወደ ሱቁ ጋበዘኝ።

ሰለሞን ብሶቱን መናገር የጀመረው ገና ቁጭ በል ከማለቱ አስቀድሞ ነበር።

“እንደናንተ የጥላቻ ዘመቻ ቢሆን እንዲህ ቆሜ ባልሄድኩ ነበር። እንደምታየኝ ግን ከአርቲስቶቹ ሁሉ በላይ ሆኜ ነው የምኖረው።

ከዚህ ሱቅ ጎን የምታያቸው ሁሉ እኔ ያከራየኋቸው ንብረቶቼ ናቸው።… ”

ሰለሞን ፋታ አልሰጠኝም መናገሩን ቀጠለ…“ያኔ ከአስመራ እንደተመለስኩ የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆቹ ጉዳዩን እንዳስረዳቸው የሳምንት ጊዜ እንኳን አልሰጡኝም ነበር። ተረባርበው ዘመቱብኝ… ይህ ዘመቻ በኔ ላይ ብቻ አላበቃም… የዚህ ሰለባ የሆኑ በርካታ ሰዎች እየተገፉ ወደ ወያኔ እየገቡ ይገኛሉ…”

“ወደ ኳስ ሜዳው ለምን ብቅ አላልክም?” ስል ንግግሩን አቋረጥኩት። ቀጥታ መልስ አልሰጠኝም።

“ፌዴሬሸኑን የምታውቀው ነው። አንተ ራስህ የነበርክበት አንድ ዝግጅት ላይ ስለ ኢትዮጵያ እንዳልዘፍን ከለከሉኝ። አገር ወዳድ ዘፋኞችን አይወዱም። በዚያ ላይ እኔን በአምስት መቶ ሲያሰሩኝ፣ ለነ አስቴር አወቀ ግን በሺህዎች ይከፍሏቸዋል።... እኔ የፈለግኩትን የመሆን መብት የለኝም እንዴ?” መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ።

“አምነህበት ከገባህ ወያኔ የመሆን መብትህ እንደተጠበቀ ነው። ሥራህን በተመለከተ ግን ስለሚያልፍ ሥርዓት እና ግለሰብ ከመዝፈን ይልቅ ስለ ሀገር ለምን አትዘፍንም?”

“ጥሩ ሥራ የሰራን መሪ ባወድስ ምን አለበት? የእስክንድር ነጋን ፅሁፎች እያነበባችሁ ወደ ስህተት እንዳትገቡ…” ሲል ቀጠለ።

ሰለሞን ስለ አቶ መለስ ሥራ ሳይሆን ስለ ቅንድባቸው እና ውበታቸው መዝፈኑን ለአፍታ የዘነጋው መሰለኝ። እናም ይቅርታ ብዬ አቋረጥኩት። በርግጥ ሰው ውጭ አቁሚያለሁ። አመጣጤም ቀጠሮ ይዤ ለረጅም ሰዓት ለመነጋገር ነበረ። “ደውልልኝ እና በሰፊው እንነጋገራለን” ብሎ ቢዝነስ ካርዱን ሰጥቶኝ ተለያየን።/ክንፉ አሰፋ፣ የኢትዮፎረም ድረ-

ገጽ ኤዲተር ነው/

አነውራለሁ ያለ ደራሲ መጀመሪያ በመላ በዘዴ ማባበልም ማስፈራራትም መጎንተልም ይደረግበት ነበር። አቤ ጉበኛን የመሰለው እምቢ ባይ አነዋሪ በመጣ ጊዜ የመንግስት ሰዎችም ሰይፋቸውን እስኪያብለጨልጭ መሳል ጀመሩ።

ደራሲዎችና ጋዜጠኞች የወቅቱን መንግስት አወዳሾች፤ ፈገግ ሲባል ሳቂዎች፤ አንድ ሲነገር አርባ ለፍላፊዎች፤ ነቅነቅ ሲባል ቋሚዎች፤ አንድ ግንብ ተሰራ ሲባል ስለመቶ ግንብ

መሰራት የሐሰት ሰባኪዎች፤ ንጉስ አንድ ብር ለአንድ ተማሪ መስጠታቸው ሲነገር ስለንጉሱ አምላዊኪነት ቸርነት ወዘተ ለሰው የማይገባ መለኮታዊ ቅድስና ያላቸው የሚያስመስል ውዳሴ መፃፍ ብቻ መተዳደሪያቸው እንዲሆን ተፈለገ። ውስጥ ለውስጥ በእጅ አዙርም ቢሆን ይህንን ጉዳይ ለሁሉም ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ይደርስ ነበር።

በእርግጥ የንጉሱ ጊዜ አልተሳካለትም አይባልም። ከእውነተኛ ጋዜጠኞች በላይ

ሐሰተኞች፣ ከሐቀኛ ደራሲዎች ይልቅ ጓልተኛ ባንዳዎች ተከብረው ኖሩ፤ ተቀማጥለው አደጉ። (ስለ የመንግስት አጨብጫቢ ጋዜጠኞችና ደራሲዎች በሌላ ጽሑፍ እመጣለሁ።) ዛሬ ግን የተነሳሁት ስለሐቀኛ ብዕረኛ ታጋዮች ለማንሳት ነው። ንጉሱ ለደርግ፣ ደርግ ለኢህአዴግ ያስረከባቸውን የብዕረኛ ጥላቻዎች ሁለተኛ ክፍል ሳምንት እመጣበታለሁ።

ቸሩ ያሰንብተን!

የአትላንታው ፌስቲቫል...

ወይም ሲወያዩ ያለፈቃዳቸው ጥልቅ ብለው ባንደኛው ላይ የሚፈርዱ፣ አንድ ሰው ስለለበሰው ልብስ፣ ስለ አካሄዱ አስተየየት የሚሰጡ፣ አልፎ አለፎም ስድብ የሚወረውሩ ሰዎች ምን እየሰሩ እንደሆነ ለምን ዞር ብለው አይታዘቡም? አንድ ሰው አንድን ልብስ ለምን እንደመረጠ ወይም ለምን እንደለበሰው ከሌላ ሰው የበለጠ ራሱ አያውቅምን? እኛ እናውቃለን ብለን በእሱ ጉዳይ አስተያት ለመስጠት ስንከጅል እሱ ለራሱ ሊያውቅ እንደሚችል እንዴት መገመት ይሳነናል? እስቲ ልብ ብለን እናስበው።

የራሳችን ጭንቅላት የሚቀርበው ለእኛ እንጅ ለሌሎች አይደለም። እናም የእኛ ጭንቅላት ስለራሳችን እንጅ ስለሰዎች ፈትፋችና አዋቂ ሊሆን አይገባውም። አንድ ሰው መንገድ ላይ ቢደንስ፤ መሳደብ ወይም መምታት የለብንም። ፍቃደኛ ሆኖ ያካፍለን ከፈለገ በሥርዓት የደነሰበትን ምክንያት መጠየቅና ማወቅ እንችላለን እንጂ ከመሬት ተነስተን ወይም ከራሳችን ችግር ወይም ልምድ ተነስተን፣ “አብዶ ነው፣ የኑሮ ውድነት አንገሽግሾት ነው” ብንል ምናልባት ስለራሳችን እየተናገርን ሊሆን ይችላል። አንድን ነገር የሚያደርግበትን ምክንያት የሚያውቀው ራሱ አድራጊው ነው።

ከአንድ ከአራት ዓመት በፊት በራሴ ላይ የደረሰ አንድ የሚገርም ነገር ላካፍላችሁ። ሳሪስ አቦ አካካቢ ከእርሻ ሰብል በስተምሥራቅ፣ ከቀለበት መንገዱ ወረድ ብሎ አንድ ቤት ተከራቼ ነበር። ከቤቱ አጠገብ አንድ ቤተ-ሃይማኖት ነበር - ዛሬም አለ። አመሻሽ አካባቢ ከቤተ-ዕምነቱ ‘ድንገት’ የሚለቀቅ፣ ‘እብድ’ በሚያህል የድምፅ ማጉያ ድጋፍ ለምዕመናን የሚደረግ ጥሪ አለ። ያ ድምጽ ሲለቀቅ ድንጋጤ ከተቀመጥኩበት አንስቶ ካነጠረኝ በኋላ መልሶ

መሬት ላይ ይጥለኝ ነበር። ሌሊት ሊነጋጋ አካባቢም ወደድሁም ጠላሁ ከእንቅልፌ ይቀሰቅሰኝ ነበር። በአካባቢ ለረዥም ጊዜ የኖሩ ጓደኞች ነበሩኝ። እዚያ ሰፈር መኖር እንደማልችል በምሬት ስነግራቸው ነገሩን ቀለል አድርገው፣ “ትለምደዋለህ” አሉኝ። እውነትም እየቆየሁ ለመድኩት። አልፎ አልፎ ካለሆነ በስተቀር ልብ አልለውም ነበር። የሚገርመው ግን በዚህ ዓይነት መላ ስላጣን ብቻ ሳንወድ በግድ የለመድናቸውና የተሸከምናቸው አበሳዎቻችንና መከራዎቻችን ስንት ይሆኑ ብዬ ስጠይቅ መልስ ማጣቴ ነው። ቆጥሬ ልጨርሳቸው አልቻልኩም።

አንድ ሰው የራሱ የሆነ እምነትና አስተሳሰብ ይኖረዋል። አንድ ሰው በክርስቶስ፣ በመሐመድ፣ በአለቃ አያሌም፣ በአባ ጉተማ፣ በእማሆይ ንግስቲ፣ በቃልቻ ሁሴን ወይም በደንጋይ፣ በወንዝ፣ በጨረቃ፣ በራሱ፣ በሚስቱ ወዘተ የማመን፣ ከፈለገም በምንም በማንም ያለማመን ነፃገት እንዳለው ማወቅ ተገቢ ይመስለኛል። የሰለጠነ ሕዝብ ይህን ሀቅ ስለሚገነዘብ በማነኛውም መንገድ ቢሆን የሰዎችን እምነትና ሰላም፣ ፀጥታ፣ ደስታ መንካት እንደሌበት ያምናል። እነሱም እንዲሁ እንደሚያደርጉ ይረዳል።

ይሄ እምነትና ግንዛቤ ለገባቸው ኢትዮጵያዊያን “ሰልጥነዋል!” የሚል መፈክር በየአደባባዩ ልንለጥፍላቸው እንችላለን። በጣም እርግጠኛ ሆነን ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሥልጡን ሕዝብ ለመባል ከሚያበቁ መመዘኛዎች አንዱን አሟልተዋል ብለን በኩራት እናወራለን። እኔ የምመኘው የዚያን ቀን መምጣት ነው። ዕድሜ ይስጥህ ብላችሁ ብትመርቁኝና ምርቃታችሁ ደርሶ ዕድሜዬ ረዝሞ ያንን ቀን ባይ ደስታዬ ይገለኝ ይሆናል።

ሰላም እንሁን!

መቼ ይሆን የምንሰለጥነው...

የአነዋሪ ጥላቻ . . .ከ207 በላይ የዓለም አቀፉ አ ት ሌ ቲ ክ ስ ፌዴሬሽኖች ማ ህ በ ር የ ተ ው ጣ ጡ

2,472 አትሌቶች በሚካፈሉበት የዳኤጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለሁለት ዓመት ያህል ከውድድር የራቀው ቀነኒሳ በቀለ እንደሚካፈል ታወቀ። ውድድሩ ከነሐሴ 21-29 2003 ዓ.ም ይካሄዳል።

የ ደ ቡ ብ ኮሪያ ደቡብ ምስራቅ ከተማ በሆነችው ዳኤጉ

በሚካሄደው በዚህ ሻምፒዮና ላይ 200 ሺህ ኮሪያዊያን እና 30 ሺህ የውጪ አገር ዜጎች ከተማዋን ውድድር ለመመልከት እንደሚጎበኙት የተገለፀ ሲሆን ቀኑ ሲቃረብ ምናልባትም ቁጥሩ ያሻቅባል ተብሏል።

ለዚህም ሲባል አዘጋጆቹ የተመረጡ 410 ትልልቅ ሞቴሎች እና እንግዶችን የሚስተናገድ አቅም ያላቸው ቤቶች መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በ ሻ ም ፒ ዮ ና ው ላይ ከጉዳት መልስ ልምምድ የጀመረው ኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ በቤጂንግ ኦሎምፒክ የድርብ ድል ባለቤት በሆነበት በ5 ሺህ እና

በ10 ሺህ አሊያም በ10 ሺህ ብቻ ሊሳተፍ እንደሚችል ዘገባዎች ጠቁመዋል። ይህንን ለማረጋገጥ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ደውለን እሱን ባናገኘውም ስልኩን ያነሱት ሰው ‹‹ወሬው ትክክለኛ ነው›› ብለዋል።

ከቀነኒሳ በተጨማሪ ሌላው ከጉዳት የተመለሰው ዩሴን ቦልት፣ አሰፋ ፓውልና 27 የዓለም ሪከርዶችን የሰበረችው የሌና ኢዜንባዬቫ ውድድሩን ያደምቁታል ይላል ዘገባውን ያኘንበት ከchosun.com ነው። በዚህ ውድድር የደቡብ ኮሪያ ባላንጣ ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ አምስት አገሮች አይሳተፉም።

ቀነኒሳ በዓለም ሻምፒዮና ላይ ይሮጣልለዚህም ሲባል አዘጋጆቹ የተመረጡ

410 ትልልቅ ሞቴሎች እና እንግዶችን የሚስተናገድ አቅም ያላቸው ቤቶች

መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል