awramba times issue 170

22
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ቆይታ -በ ሲ ኤን ኤን ‹‹አካላዊ ነፃነትን ለመጎናፀፍ፣ ከእስርና እንግልት ለመገላገል ስደት አማራጭ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የልጅነት ህልሜ የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያዬን ትቼ በስደት መኖር የመንፈስ ነፃነት አይሰጠኝም። እናም የሚመጣውን በፀጋ እየተቀበሉ እየታሰሩና እየተፈቱ ሙያዊ ኃላፊነትን መወጣት ይበልጥ የመንፈስ ነፃነት ይሰጣል ከእንቅልፍ ጋር ለተያያዙ ችግሮች 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003 ዋጋ 7፡00 ብር ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ጥያቄ፡- ሔዋንንና ያሁን ጊዜ ሴቶችን እንዴት ታነፃፅራቸዋለህ? ሰይጣን፡- ሔዋን የመጀመርያዋ ሴት እንደመሆኗ የየትኛውም ሀገር ፖሊሲ ተፅዕኖ አልነበረባትም። ደግሞ የራሷን ቆራጥ ውሳኔ እንድትወስን ረድቷታል። በአሁን ጊዜ ያሉት ሴቶች ግን ብዙ ዓይነት አስተሳሰቦችን ስለሚሰሙ፣ የትኛውን ተቀብለው ምን መወሰን እንዳለባቸው ትንሽ የሚቸገሩ ይመስለኛል። ይኼ ነው ልዩነታቸው። ‹‹ትንሽ አረፍ በሉ›› የጎጃም አርሶ አደሮች ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት ሃያን አከበርነው። እሱ ባያከብረንም እኛ ግን አከበርነው። እናቶችና አባቶች አንብበው የማይረዱትን፣ እርግማን ይሁን ምርቃት የማያውቁትን መፈክር ተሸክመው ወደ አደባባይ ጎረፉ። መስከረም ሁለትን ሲሰለፉ የኖሩ ወላጆች ዛሬም ለግንቦት ሃያ ተሰለፉ። እድሜ ይስጣቸውና ለመጪውም ሌላ አብዮት ሳይሰለፉ አይቀሩም። በ ገፅ 8 በ ገፅ 9 በ ገፅ 3 በ ገፅ 7 በ ገፅ 19 በ ገፅ 23 ‹‹ለአሰልጣኙም ሆነ ለኢትዮጵያ መልካሙን እመኛለሁ›› የኢፊ ኦኑራ 5 ምላሾች - ከኢንግላንድ ‹‹መንግስት ከአንገት በላይ ሕክምና ያስፈልገዋል›› ዘይት ናፋቂዎች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደሚያሽቆለቁል አይ.ኤም.ኤፍ ገለፀ በ ገፅ 12 “ብዙ ሰው ያላወቀው አብርሃም ያየህ ትንታኔያቸውን ቀጥለዋል። ኢህአዴግን ከሌሎች መንግስታት ጋር ማነጻጸር “ስላቅ ነው” ቢሉም የሚኖሩባትን ዴንማርክ እየሳሉ ዲሞክራሲዋን ያሳዩናል። የህወሓትን ፍጹም የበላይነት፣ ከብቃት ይልቅ የታማኝነትን ተመራጭነት፣ የአቶ መለስን ብቸኛ መሪነት፣ የትግራይን ባንዲራና የመሳሰሉትን እያነሱ የሥርዓቱን ውስጠ-ዲሞክራሲ ይተቻሉ። ወደኋላ ግን በኢትዮጵያ ምድር በጭንቀት የተወጠረ ሥርዓት እንዳለ ይገልፃሉ። ከዚያም ሥርዓቱ እራሱ የደረሰበት በቅርቡ ነው ያሉትን “ብዙ ሰው ያላወቀው” ምስጢር ያካፍሉናል። የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማታዊ መንግሥቱ ጋብቻ በ ገፅ 4 ደርጎች እና አዲስ ሕይወት ጊዜው ታህሳስ 23 ቀን 1998 ዓ.ም ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፣ ዞን 4 ተብሎ በሚታወቀው የእስር ክልል፡፡ በዚህ ጊዜና ቦታ ቀደም ሲል በዚህች ሀገር ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ድርሻ የነበራቸው ሶስት የደርግ ባለሥልጣናት አንድ ላይ ተቀምጠው ይመክራሉ - ፍቅረስላሴ ወግደረስ፣ ተስፋዬ ወ/ስላሴ እና ደበላ ዲንሳ፡፡ እነዚህ ሶስት የቀድሞ የሀገሪቷ ባለሥልጣናት የሚያካሂዱትን ውይይት በ ገፅ 18 በ ገፅ 19 ኮሜዲያን መስከረም በቀለ ከቦሌ ኤርፖርት ተይዞ ታሰረ ‹‹ስለጉዳዩ በቂ መረጃ አለን›› በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ለፉት 20 ዓመታት መኖሪያውን በሰሜን አሜሪካ አድርጎ የቆየውና በተለያዩ የኮሜዲ ስራዎቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን መስከረም ዙዎች የአሁኑንም መንግስት አቋም የመጨረሻው እንደሆነ አይሰማቸውም፡ ፡ በድንገት ደግሞ አዲስ አይነት መመርያ ሊወጣ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አላቸው፡፡ ይህ በገበያ ስርኣቱ ላይ ያለመተማመን መንፈስ ደግሞ የተዛባ አመለካከት በመፍጠር ሁኔታውን ሊያረጋጋው እንዳልቻለ እየተነገረ ይገኛል እንዲያውም አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሁኔታውን የገለጹት ‹‹መርሕ አልባ፣ አቅጣጫ አልባ ሲሉ ነው፡፡›› አቅጣጫ አልባ የዋጋ ትመና በ ገፅ 5 ምስጢር አለ!!”

Upload: esubalew-lakie

Post on 24-Mar-2015

365 views

Category:

Documents


13 download

TRANSCRIPT

Page 1: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ቆይታ -በ ሲ ኤን ኤን

‹‹አካላዊ ነፃነትን ለመጎናፀፍ፣ ከእስርና እንግልት ለመገላገል ስደት አማራጭ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የልጅነት ህልሜ የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያዬን ትቼ በስደት መኖር የመንፈስ ነፃነት አይሰጠኝም። እናም የሚመጣውን በፀጋ እየተቀበሉ እየታሰሩና እየተፈቱ ሙያዊ ኃላፊነትን መወጣት ይበልጥ የመንፈስ ነፃነት ይሰጣል

ከእንቅልፍ ጋር ለተያያዙ ችግሮች

4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

ጥያቄ፡- ሔዋንንና ያሁን ጊዜ ሴቶችን እንዴት ታነፃፅራቸዋለህ?ሰይጣን፡- ሔዋን የመጀመርያዋ ሴት እንደመሆኗ የየትኛውም ሀገር ፖሊሲ ተፅዕኖ አልነበረባትም። ያ ደግሞ የራሷን ቆራጥ ውሳኔ እንድትወስን ረድቷታል። በአሁን ጊዜ ያሉት ሴቶች ግን ብዙ ዓይነት አስተሳሰቦችን ስለሚሰሙ፣ የትኛውን ተቀብለው ምን መወሰን እንዳለባቸው ትንሽ የሚቸገሩ ይመስለኛል። ይኼ ነው ልዩነታቸው።

‹‹ትንሽ አረፍ በሉ››የጎጃም አርሶ አደሮች

ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት ሃያን አከበርነው። እሱ ባያከብረንም እኛ ግን አከበርነው። እናቶችና አባቶች አንብበው የማይረዱትን፣ እርግማን ይሁን ምርቃት የማያውቁትን መፈክር ተሸክመው ወደ አደባባይ ጎረፉ። መስከረም ሁለትን ሲሰለፉ የኖሩ ወላጆች ዛሬም ለግንቦት ሃያ ተሰለፉ። እድሜ ይስጣቸውና ለመጪውም ሌላ አብዮት ሳይሰለፉ አይቀሩም።

በ ገፅ 8

በ ገፅ 9

በ ገፅ 3

በ ገፅ 7 በ ገፅ 19 በ ገፅ 23

‹‹ለአሰልጣኙም ሆነ ለኢትዮጵያ መልካሙን እመኛለሁ››

የኢፊ ኦኑራ 5 ምላሾች - ከኢንግላንድ

‹‹መንግስት ከአንገት በላይ ሕክምና ያስፈልገዋል››

ዘይት ናፋቂዎች

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደሚያሽቆለቁል

አይ.ኤም.ኤፍ ገለፀ

በ ገፅ 12

“ብዙ ሰው ያላወቀው

አብርሃም ያየህትንታኔያቸውን ቀጥለዋል። ኢህአዴግን ከሌሎች መንግስታት ጋር ማነጻጸር “ስላቅ ነው” ቢሉም የሚኖሩባትን ዴንማርክ እየሳሉ ዲሞክራሲዋን ያሳዩናል። የህወሓትን ፍጹም የበላይነት፣ ከብቃት ይልቅ የታማኝነትን ተመራጭነት፣ የአቶ መለስን ብቸኛ መሪነት፣ የትግራይን ባንዲራና የመሳሰሉትን እያነሱ የሥርዓቱን ውስጠ-ዲሞክራሲ ይተቻሉ። ወደኋላ ግን በኢትዮጵያ

ምድር በጭንቀት የተወጠረ ሥርዓት እንዳለ ይገልፃሉ። ከዚያም ሥርዓቱ እራሱ የደረሰበት በቅርቡ ነው ያሉትን “ብዙ ሰው ያላወቀው” ምስጢር ያካፍሉናል።

የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማታዊ መንግሥቱ ጋብቻ በ ገፅ 4

ደርጎች እና አዲስ ሕይወትጊዜው ታህሳስ 23 ቀን 1998 ዓ.ም ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፣ ዞን 4 ተብሎ በሚታወቀው የእስር ክልል፡፡ በዚህ ጊዜና ቦታ ቀደም ሲል በዚህች ሀገር ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ድርሻ የነበራቸው ሶስት የደርግ ባለሥልጣናት አንድ ላይ ተቀምጠው ይመክራሉ - ፍቅረስላሴ ወግደረስ፣ ተስፋዬ ወ/ስላሴ እና ደበላ ዲንሳ፡፡እነዚህ ሶስት የቀድሞ የሀገሪቷ ባለሥልጣናት የሚያካሂዱትን ውይይት

በ ገፅ 18

በ ገፅ 19

ኮሜዲያን መስከረም በቀለ ከቦሌ ኤርፖርት ተይዞ ታሰረ

‹‹ስለጉዳዩ በቂ መረጃ አለን››በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ

ላለፉት 20 ዓመታት መኖሪያውን በሰሜን አሜሪካ አድርጎ የቆየውና በተለያዩ የኮሜዲ ስራዎቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን መስከረም

ብዙዎች የአሁኑንም መንግስት አቋም የመጨረሻው እንደሆነ አይሰማቸውም፡፡ በድንገት ደግሞ አዲስ

አይነት መመርያ ሊወጣ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አላቸው፡፡ ይህ በገበያ ስርኣቱ ላይ ያለመተማመን መንፈስ ደግሞ የተዛባ አመለካከት በመፍጠር ሁኔታውን ሊያረጋጋው እንዳልቻለ እየተነገረ ይገኛል እንዲያውም አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሁኔታውን የገለጹት ‹‹መርሕ አልባ፣ አቅጣጫ አልባ ሲሉ ነው፡፡››

አቅጣጫ አልባ የዋጋ ትመና በ ገፅ 5

ምስጢር አለ!!”

Page 2: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹cKV” VÑe

ታዲዎስ ጌታሁን SpÅe õeNደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ0911629281

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑት ሚር. ሚልስ ሌሴሎ ሲረሰን ‹‹አዲስ ሜትሮ ፖሊታን›› የተሰኘ የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን ህትመት ቲም መፅሔት ቃለ-ምልልስ

እየሰጡ ነው። በቃለ-ምልልሱ ውስጥ ለቀረበላቸው አንድ ጥያቄ፣ ‹‹ይህ ከባድ ጥያቄ ነው።…› ሲሉ ጀመሩ። ጥያቄው፡- ‹‹በኢትዮጵያ ያለውን የዴሞክራሲ ዕድገት እንዴት ይገመግሙታል?›› የሚል ነበር።

ጀርመንን የምታክል ግዙፍ አገር (በፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት) የወከሉ ዲፕሎማት ስለሚመጡባት አገር ሁለንተናዊ ሁኔታ ቢያንስ በቂ የሚባል አይነት መረጃ ሳይይዙ መጡ ቢባል ማንንም የሚያሳምን አይሆንም። አምባሳደሯ ምላሽ የሰጡበት መንገድ የሚያስተላልፈው አንድ ግልፅ መልዕክት አለ፤ እስኪ በአጭሩ እንመልከተው፡-

‹‹ . . . ይህ ከባድ ጥያቄ ነው። እኔም በዚህ ሥራዬ ወደ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የመጣሁ እንደ መሆኔ አስተያየት መስጠት ይከብደኛል። … ›› ካሉ በኋላ የቀረበላቸውን የዴሞክራሲ ጥያቄ በስልት ወደ ጎን በማድረግ የአጀንዳውን አቅጣጫ አስቀየሩ። እናም ‹‹ … በአጠቃላይ አስተያየት ለመስጠት፤ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለመልማት ከፍተኛ ተስፋ ያላት አገር ናት። … ›› ዋናውን ነጥብ አጽንኦት ሲሰጡበትም፣ ‹‹ … ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በመግለፅ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ጠቃሚ ነው። የእኛ አገር ልምድ የሚያመለክተው ይህንን ነው፤ በጀርመን ዴሞክራሲ የጎለበተው በዜጎች ሀሳብን በነፃነት መግለፅ ላይ ተመስርቶ ነው። … ››

የዳበረ ፖለቲካዊ ዕውቀትንና ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅ ባይተዋር ያልሆኑ ዲፕሎማት ስለዴሞክራሲያዊ ዕድገታችን መንግስታዊና (በዚያውም ግላዊ) ግምገማቸውን ተጠይቀው ‹‹ይህ

ከባድ ጥያቄ ነው›› ሲሉ ጉዳዩን አቅልሎ ከመመልከት ይልቅ በመጠኑም ቢሆን ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር እያነፃፀሩ መመርመር ተገቢ ይሆናል። ለምንድነው በኢትዮጵያ ያለውን የዴሞክራሲ ዕድገት መገምገም ‹‹ከባድ›› የሆነው?

ዓላማችን ፈፅሞ የአምባሳደሯን ሙሉ ቃለ-ምልልስ መፈተሽ አይደለም። በተነሳው ጭብጥ ላይ በዲፕሎማሲያዊ ካባ ተሸፋፍኖ ያለፈን ጉዳይ ወደ ውስጣችን ተመልክተን መነጋገርና ለዴሞክራሲያዊ አስተሳሰባችን የሽበባ ትብታብ የሆነብንን ነገር ከላያችን ላይ አውልቀን መጣል ስለምንችልበት መንፈሳዊ ልዕልና የጋራ አቋም መያዝ ነው። እኒህ አምባሳደር ‹‹የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ዕድገት መገምገም ከባድ ነው›› ካሉ በኋላ የሰጡትን ምክር ማስተዋሉም ስለቀረበላቸው ጥያቄ የሚያውቁትን በገደምዳሜ የተናገሩበት ነው እንድንል ያደርገናል። ‹‹ … ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በመግለፅ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ጠቃሚ ነው። … የእኛ አገር ልምድ ይህን ያመለክተል። … ›› ብለዋል። የሚጠቅመው ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በነፃነት እንዲገልፁ ማስቻል ነው ማለት ነው። ታላቅና የተቀደሰ ሀሳብ ነው። ስለዚህም በአስተውሎት ሊተገበር የሚገባው ነው ብለን እናምናለን። ገንቢ ምክሮችን ማዳመጥ ለሚፈልግ ማንኛውም መንግስት በቁም ነገር የተጫነ ምክር ነው።

እኛም የምንለው ይህንኑ ነው። የሚጠቅመው ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በፍፁም ነፃነት እንዲገልፁ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው። ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁ ማስቻል ከምንም አይነት የከበረ ሥጦታ የተሰጣቸው ዜጎችም የጎለበት ፖለቲካ፣ በቁጥር ሳይሆን በልማት የሚገለፅ ኢኮኖሚ፣ በሞራል የበለፀገ ማኅበረሰብ ይገነባሉና!

ማንኛውም አገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለመገንባት የሚከተለው መስመርና ያለፈበት ሁለንተናዊ ሂደት በተጨባጭ ለሚገኝበት ደረጃ አስተዋጽኦ

እንደሚኖረው እንረዳለን። ይህ ማለት ግን እየተከተሉት ያሉትን መስመር መፈተሽና ውጤቱ ዘገምተኝነት የሚታይበት ከሆነ መቀየር አይቻልም ማለት አይደለም። ‹‹እየተከተልኩት ያለው መስመር የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ብቻ ነው›› የሚለው በዘመናዊው ዓለም ተቀባይነት የሌለው፣ ያረጀና ያፈጀ አስተሳሰብ ነው እያልን ነው።

ያለፉበትን ሂደት አሉታዊ ጎኖች ወደሚፈለገው ደረጃ ላለመድረስ በተደጋጋሚ ምክንያት አድርጎ ማቅረቡም የዝቅተኛ ሥነ-ልቦና መገለጫ ከመሆን አልፎ ሌሎችን የሚያሳምን አመክንዮ ሊሆን አይችልም። የሚጠቅመው ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በነፃነት እንዲገልፁ ማስቻል ነው ስንል ለጉዳዩ ከፍተኛ አፅንኦት በመስጠት ነው። እንዲህ እንድንል ከሚያደርጉን በርካታ ጉዳዮች ቢያንስ አንዱን በምሳሌነት ማንሳቱ ተገቢ ይሆናል።

እንደሚታወሰው ልክ የዛሬ ሳምንት ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበትን /የደርግ ሥርዓት የወደቀበት/ ግንቦት 20ን አስታኮ ‹‹ለታላቁ የህዳሴ ግድብ›› ግንባታ የድጋፍ ሰልፍ በመዲናችንና በተለያዩ የአገራችን ክልሎች ተጠርቶ ነበር። ሰልፉ በተጠራባቸው ሁለት ተያያዥ ጉዳዮች /የኢህአዴግ አገሪቱን መቆጣጠር እና የግድብ ግንባታው/ ላይ በእምነትና በእውቀት ድጋፋቸውን ለማሳየት የወጡ ወገኖች አሉ። የዚህ ዓይነቶቹ ወገኖች የተለየ ቅስቀሳ ወይም ተፅዕኖ ሳይደረግባቸው ሀሳባቸውን እንደሚገልፁ ይታወቃል። ማንም ወገን ሀሳቡን በነፃነት እንዲገልፅ ማስቻል ጠቃሚ ነው የሚለው ዕምነታችን በእነዚህ ወገኖች ላይ የሚቀየርበት ምንም ምክንያት የለም። ሙያዊ ግዴታችን ከየትኛውም አቅጣጫ የሚነሱ አስተሳሰባዊ ዕምነቶችን/ ብንቀበላቸውም ባንቀበላቸውም/ እንድናከብር እንደሚያስገድደን ሁልጊዜ እናስታውሳለንና በዚህ ሚዛን መዝነን አስተናግደነዋል።

እንደ አንድ የሚዲያ ተቋም በቦታው ተገኝተን የገመገምናቸውን ሌሎች መገለጫዎች ማንሳቱም በኃላፊነት ስሜት እውነታውን ፈትሸው የእርምት እርምጃ መውሰድ ለሚፈልጉ መንግሥታዊ አካላት የማይታለፍ ጥቆማ ይሆናቸዋል ብለን እናምናለን። ምክንያቱም በድጋፍ ሰልፉ መካከል ተገኝተን ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁልን /ማንነታቸውን ለመደበቅ ቃል በመግባት/ ከጠየቅናቸው፣ በየምንኖርባቸው ወረዳዎች የሆነውን ከተመለከትነው፣ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ካሰባሰብናቸው መረጃዎች በመነሳት ግምገማችንን በአጭሩ ስናስቀምጠው ቀላል የማይባሉ ዜጎች በሰልፉ ላይ የተገኙት ‹‹የግዴታ ውዴታ›› ሆኖባቸው ነው። አዝነናል።

በሰልፉ ላይ በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕምነታቸው በተገኙት ዜጎች ዕምነትና እርምጃ የምንደሰተውንና የምንኮራውን ያህል፣ ያለፈቃዳቸውና ዕምነታቸው በተለያዩ ተፅዕኖዎች በቦታው እንዲገኙ በተደረጉ ዜጎች መራር ስሜት እናዝናለን። ዜጎችን በዚህ መንገድ አደባባይ ማውጣትም የዴሞክራሲ ግንባታውን ያመክነዋል። በዚህ መንገድ ዜጎችን በተፅዕኖ አደባባይ አውጥቶ የሚረካ ወገን ካለም የቆመበት መሰረት ባልጠበቀው ጊዜ እንደሚከዳው ባይዘነጋው መልካም ነው እንላለን።

በእርግጥ የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ነው። ሂደቱ ግን እየተሻሻለ፣ እየጎለበተ እና ዜጎችን በስፋት ተቋዳሽ የሚያደርግ መሆን አለበት። ሂደት ነው፣ ጊዜ ይፈጃል፣ ወዘተ እያልን ሰበብ አስባቦችን የምንደረድር ከሆነ ግን የዕድገት ደረጃውን ለመግለፅ ሚዛን ላይ የወጣ ቀን ለመገምገም እንኳን የከበደ ሆኖ ይገኛል።

በድጋሚ እንናገረዋለን። የሚጠቅመው ዜጎች የመሰላቸውን ሀሳብ በነፃነት እንዲገልፁ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹የአሊ አብደላ ሳላህ (የአገሪቷ) ወታደሮች እናንተ ሙታናችሁን አታነሱም ብለው

በጥይት እና በዱላ አባረውን ራሳቸው ሬሳውን በክፍት መኪና ጭነው ወደ ኩዌት ሆስፒታል

ወስደዋቸዋል››

አቶ አማረ በየመን የሚኖሩ ግለሰብ

በአገሪቷ ለአራት ኢትዮጵያዊያን መሞት ምክንያት ስለሆነው እየደረሰባቸው ስላለው

ወቅታዊ ችግር ባለፈው ሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ፡፡

‹‹አንዳንዴ እንደ ኢኮኖሚስትነታችን ስንናገርም ችግር አለብን። አስረግጦ ሕዝቡ እንዲያውቀው

አናደርግም። በኢኮኖሚክስ ትምህርት ልማትና እድገት የተለያዩ ናቸው ብለን ነው

የምናስተምረው።

ዶክተር ደምስ ጫንያለው የኢኮኖሚክስ መምህር እና ተመራማሪ

በከተማም በገጠርም ችግሩ በግልጽ ይታያል። በአንፃሩ ደግሞ ኢኮኖሚው አድጓል ይባላል። እድገቱ ኃብታሙን የበለጠ ኃብታም ደኃውን

ደግሞ የበለጠ ደኃ ያደርጋል ማለት ነው? ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ

የሰጡት ምላሽ።

ጠቃሚው ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት መግለፃቸው ነው!

ማን ምን አ ለ

‹‹በአሁን ሰዓት በፍጥነት እያደግን የመግዛት

አቅማችንም ደረጃ በደረጃ እየጨመረ

ያለበት ሁኔታ አለ…››

አቶ ሬድዋን ሁሴን የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባል እና የጽ/ቤት ኃላፊ

የግንቦት 20 በዓልን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት አስመልክቶ ተጠይቀው

ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ፡፡

Page 3: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003 3

በውብሸት ታዬ

ታዋቂው ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ.ኤን.ኤን ከአንድ ሳምንት በፊት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ከሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ጋር ለ30 ደቂቃ የዘለቀ ሰፊ ቃለ-ምልልስ አካሂዶ ነበር። ጋዜጠኛ ዳዊት የተስተናገደው በሳምንት አንድ ቀን በሚቀርበው ‹‹አፍሪካን ቮይስ›› (‹‹African Voice››) በተሰኘ ፕሮግራም ላይ ሲሆን፣ በሲ.ኤን.ኤን መረጃ መሰረት በዚሁ ፕርግራም ላይ የሚስተናገዱት አፍሪካ ውስጥ ለየት ያለ ስብዕና ያላቸውና በሥራቸውም ገንቢ አስተዋጽኦ በማበርከት አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች ናቸው።በቃለ-ምልልሱ ወቅት ዳዊት በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ለመግባት ምን እንዳነሳሳው ከሲ.ኤን.ኤንዋ ጋዜጠኛ ዲያኒ ማካርቲ ለቀረበለት ጥያቄ እንዲህ ሲል ነበር ምላሽ የሰጠው፡- ‹‹የሶስት እና የአራት ዓመት ልጅ እያለሁ አባቴ የጀርመንና የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ፕሮግራሞች ያለማቋረጥ ይከታተል ነበር። በወቅቱ በዚች አነስተኛ ማሽን (ሬዲዮ) ውስጥ ሆነው የሚያወሩ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው!? ስል አባቴን በጥያቄ አጣድፈው ነበር። ሆኖም አባቴ በተመስጦ ማዳመጡን ገታ

ጠቃሚው ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት መግለፃቸው ነው!

ያደርግና፣ ‹ጋዜጠኞች ናቸው፤ አንተም በትምህርትህ ጎበዝ ከሆንክና ከበረታህ እንደነሱ መሆን ትችላለህ፤ አሁን አትረብሸኝ ላዳምጥበት› ሲል ይመልስልኝ ነበር። እና እንደነዚህ ሰዎች የመሆን ፍላጎቴ የጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው›› ሲል ምላሽ ሰጥቷል።ጋዜጠኛው ሙያዊ ግዴታውን እየተወጣ ለእስር ስለተዳረገበት የ1997ቱ ምርጫ፣ በወቅቱ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃ አድርጎ ስላቀረበበት ርዕሰ አንቀጽ፣ ስለተመሰረቱበት የወንጀል ክሶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል። ከ350 ያላነሱ ሰዎች በታጎሩበት በአንድ መለስተኛ አዳራሽ ውስጥ ለ21 ወራት መታሰሩን የገለፀው ዳዊት፣ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ሌሎች አብረውት የታሰሩ ጋዜጠኞች ‹‹ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በሙያችን መስራት ያስቸግረናል›› ብለው ከአገር መሰደዳቸውን አስታውሶ በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ እነሱ የወሰኑት ውሳኔ ተገቢ ነው ብሎ እንደሚያምን ካብራራ በኋላ፣ እሱ ግን ነፃነትን በተለየ መልኩ እንደሚያየው ለጋዜጠኛዋ የገለፀላት፣ ‹‹አካላዊ ነፃነትን ለመጎናፀፍ፣ ከእስርና እንግልት ለመገላገል ስደት አማራጭ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የልጅነት ህልሜ የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያዬን ትቼ በስደት መኖር የመንፈስ

ነፃነት አይሰጠኝም። እናም የሚመጣውን በፀጋ እየተቀበሉ እየታሰሩና እየተፈቱ ሙያዊ ኃላፊነትን መወጣት ይበልጥ የመንፈስ ነፃነት ይሰጣል በሚል የግል እምነት እሱን መርጫለሁ›› በማለት ነበር። ጋዜጠኛ ዳዊት ከእስር ቤት በይቅርታ በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ በወቅቱ ወደነበረው የማስታወቂያ ሚኒስቴር በማምራት ፍቃድ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ መጀመርያ በኃላፊዎቹ ውድቅ መደረጉን በቃለ-ምልልሱ ወቅት አስታወሶ ከብዙ ጊዜ መመላለስ በኋላ ግን በይቅርታ የወጣበትን (በርዕሰ-ብሔር

ግርማ ወልደጊዮርጊስ የተፈረመ) ሰርተፍኬት ከሚያቋቁመው ሚዲያ ኤዲቶሪያል ፖሊሲው ጋር እንዲያቀርብ ተነግሮት በአዲስ ስያሜ ‹‹አውራምባ ታይምስ›› ጋዜጣን መመስረቱን ለቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል።በዛሬይቱ ኢትዮጵያ መንግሥትን እየተቹ የጋዜጠኝነት ሙያን በገለልተኝነት መወጣት ፈታኝ መሆኑን የገለፀው ዳዊት፣ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግን የመሳሰሉ ለትርጉም በእጅጉ የተጋለጡ አዋጆች ጋዜጠኞች ጠንከር ያሉ ትችቶችን በመንግሥት ላይ እንዳይሰነዝሩ ጋሬጣ መሆናቸውን፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ

ያለው ገለልተኛ ሚዲያ በስጋት ቀንበር ስር መሆኑን አልሸሸገም።‹‹በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ላይ ያለው ፕሬስን የሚመለከት አንቀጽ ለሰፊ ትርጉም የተጋለጠ ነው›› ሲል የገለጸው ዳዊት፣ መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጃቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖችን የሚመለከት ዘገባ ጨርሶ እንዳይስተናገድ ታሳቢ ያደረገ አንቀጽ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ በግልጽ መደንገጉን ያብራራል። ‹‹ ... ማናቸውም የሽብርተኝነት ድርጊት እንዲፈጽሙ ወይም ለመፈጸም እንዲዘጋጁ ወይም እንዲነሳሱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያበረታታቸው ወይም በማናቸውም ሁኔታ የሚገፋፋቸው እንደሆነ አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት ሆነ ብሎ ወይም በግዴለሽነት ያተመ ወይም ያሳተመ እንደሆነ እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል … ›› የሚለውን አንቀጽ በመጥቀስ እንዲህ ብሏል፡-‹‹ሚዲያው በዚህ አንቀጽ ምክንያት አይደለም ማበረታታት እነዚህን ቡድኖች የመተቸት መብት እንኳን የለውም፤ ምክንያቱም በተዘዋዋሪ

ማበረታታትና ማስተዋወቅ ነው ተብሎ ሊተረጎም ስለሚችል››።‹‹ወታደራዊውን የደርግ ሥርዓት በማስወገድ ወደ ሥልጣን የመጣው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ነፃ ፕሬስን በመጀመርያዎቹ ዓመታት በመፍቀድ በአዎንታዊ መልኩ ቢወደስም፣ ዛሬ ከ20 ዓመታት በኋላ ያንኑ መሰረታዊ መብት በተለያዩ ዘዴዎች በማፈን 20 ዓመታት ወደ ኋላ እየተመለስን ይመስላል፤ አንዴ ነፃነቱን ማጣጣም የጀመረ ሕዝብ ደግሞ ነፃነቱን መልሶ መንጠቅ አስቸጋሪ ነው›› ሲል ጋዜጠኛ ዳዊት ለሲ.ኤን.ኤን ገልጿል።

የኢኮኖሚ ዕድገት ወይስ የዜጎች መሰረታዊ ነፃነት?

ኢህአዴግ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡን ደጋግሞ ይገልፃል። የተባለው ዕድገት ተመዝግቦ ቢሆን እንኳን፣ ‹‹የዜጎች መሰረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብት በመንፈግ የሚገኝ ዕድገት የትም አያደርስም›› ሲል የገለፀው ጋዜጠኛ ዳዊት፣ ‹‹ከአስርና ሃያ የማይበልጡ ባለኃብቶች በርዕሰ ከተማዋ

በየአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ቆይታ

በአፍሪካ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ተብላ የምትሞካሸው ጋና

በርዕሰ ከተማዋ አክራ ይህ ነው የሚባል ህንፃ እንደሌለ

በማነጻጸር የጋና ሕዝብ ግን መሪዎቹን በዴሞክራሲያዊ

ምርጫ የመቀያየር ሙሉ መብት የመጎናፀፉን እውነታ

በቃለ-ምልልሱ አጽንኦት ሰጥቶ ገልጾታል።

በ ገፅ 15

Page 4: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003ፊ ቸ ር4

ፅሑፉጊዜው እ.ኤ.አ ኦገስት 8/2006፤ ወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእንግሊዝ ማንቸስተር ከተማ የአፍሪካ የልማት አማራጮችን በተመለከተ በተካሄደው ኮንፍረንስ፣ ‹‹African Development: Dead Ends and New Beginnings›› የሚል ርዕስ የተሰጠውን ያልተቋጨ መፅሐፍ ለውይይጥ ያቀረቡበት ነበር። በአስራ ዘጠኝ ምዕራፎች የተከፋፈለውን የዚህን መጽሐፍ መውጣት ተከትሎ በርካታ የትችትና የድጋፍ ፅሑፎች (በይበልጥ የትችት) በተለያዩ ድረ-ገፆችና ወረቀቶች ለንባብ በቁ።ጽሑፉ፡- የሚያነሳቸው የመከራከሪያ ሀሳቦችን በደንብ አሳማኝ በሆነ መልኩ አለማሳየቱ፣ ጸሐፊው መራሄ መንግሥት እንደመሆናቸው፣ እንዲሁም የመንግሥት አቋም በጽሑፉ እንደማይንፀባረቅ ቢገለጽም፣ ገዥው ፓርቲው በሥልጣን ዘመኑ በተግባር ለማዋልና ለመኮረጅ የሚያልመው የኢሲያውያንን የልማት ሞዴል በመሆኑና በሀገር ቤት ዘወትር እንደሚደረገው የኒዮሊበራሊዝምን ዕሳቤና ኃልዮቶች የማጣጣልና ውድቅ ለማድረግ ያለመ መሆኑና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በምክንያትነት ተጠቅሰው ትችት ቀርቦበታል።

ልማታዊውከጽሑፍ መቅረብ በኋላ እንደተለመደው የመንግሥት ሚዲያዎችና የመንግሥት ወገንተኛ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያን መንግሥት ልማታዊ በሚል በአደባባይ መሰየማቸውን ተያያዙት። ቀስ ብሎም የኢህአዴግ ልዩ ልዩ የልማት ሥትራቴጂ ሰነዶች፤ እንደ አዲስ ራዕይ፣ ሕዳሴ ጋዜጣና ሌሎች ወቅታዊ የመገምገሚያ፣ ማወያያ፣ ማደራጃና የንቅናቄ የፓርቲ ሰነዶች፣ እንዲሁም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ሁሉ ‹‹ልማታዊ መንግሥታችን›› በሚል የማንቆለጳጰስና የመቀባባት ተግባር በስፋት መስተዋሉ የተለመደ ተግባር ሆኖ ቀጠለ።

ሰማያዊው መጽሐፍበዛው ዓመት፣ በሀገርኛው ጥር 1999 ዓ.ም፣ ኢህአዴግ አዲስ ለመካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች፣ እና አባላቱ ለማድረግ ላሰባቸው ወጣት የመንግሥት ሰራተኞች (ከሥልጠናው መጠናቀቅ በኋላ እንደተለመደው የአባልነት ፎርም በገፀ-በረከትነት ቀርቦላቸዋል) የአራት ዙር ሥልጠና አዘጋጀ። በሥልጠናውም፣ ‹‹ልማት፣ ዴሞክራሲ እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚል ባለ ሰማያዊ ቀለም ሰነድ አዘጋጅቶ ለማጥመቂያነት አቀረበ።በሰነዱ ውስጥም ‹‹የምስራቅ ኢሲያ የልማታዊ

መንግሥታት አማራጭ›› የሚል ክፍል ኢህአዴጋዊ ትንተና ተሰጥቶት በግልፅ ሰፍሯል። የሚያስገርመው ነገር፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሑፍ የተነሱት ሀሳቦችና እንደምርጥ ተሞክሮ (በጣም የታወቀው የኢህአዴግ ቃል) በመውሰድ የቀረቡት ደቡብ ኮሪያና ታይዋን በዚህኛውም ሰነድ ውስጥ በምሳሌነት ተወስደዋል። የሁለቱ ልዩነት ምንድን ነው የመጀመርያው ለውጭ ሀገር ውይይት የቀረበ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተተየበ እና የድርጅቱን አቋም አያንፀባርቅም መባሉ ነው። ይሄኛው ሰነድ ግን በአማርኛ መዘጋጀቱ፣ ለሀገር ቤት ፖለቲካው ለድርጅቱ አባላትና ለመንግሥት ፈፃሚዎች የተሰናዳ እና እንዴት ኢህአዴግ የኢሲያውን ሞዴል በመኮረጅ በተግባር ላይ ማዋል እንደሚችል እራሱን ያመሳሰለበት ነው።እነዚህን ሁነቶች ተከትሎም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ ተቋማትን፣ ተግባራትን/ዘርፎችን በልማታዊ እና ልማታዊ ባልሆነና ልማታዊ በሚል መልኩ የመመደብ ሂደትና ይባስ ብሎም ወንጀለኛ የሚያደርጉ ፍረጃዎች ብቅ አሉ። በዚህም ልማታዊ ወይም ጥገኛ ባለኃብት፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ልማታዊ ኪነ-ጥበብ፣ ልማታዊ ጋዜጠኝነት፣ ልማታዊ ባሕልና አመለካከት ወዘተ የሚሉ ቃላትን መስማት የዕለት ተዕለት ተግባር ሆነ። ለዚህ አስረጂ የሚሆነን በአንድ ወቅት የግሉ ዘርፍና ባለኃብቶች ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የዋጋ ተመንን አስመልክተው ባካሄዱት ውይይት ላይ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ሕንጻ በማከራየቱ ኪራይ ሰብሳቢ ስለመሆኑ ሸንቋጭ በሆነ መልኩ የተጠየቀበትን መንገድ ማስታወስ በቂ ይሆናል።

የልማታዊ መንግሥት ከፍና ዝቅልማታዊ መንግሥት በፖለቲካ ኢኮኖሚ ዕሳቤ ደረጃ ላለፉት 30 ዓመታት በአጥኚዎችና በፖሊሲ አውጭዎች ከፍተኛ

ትኩረት ሲቸረው ቆያቷል። ይሁንና በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ከፍተኛ አለመስማማት ይስተዋልበታል። ከንግርት (Rhetoric) ባለፈ እንደ የጎለመሰ እሳቤ (Ideology) ግልፅ የሆነ ትርጉም፣ መመዘኛ፣ ፅንሰ-ሀሳባዊ ማዕቀፍ እንዲሁም ከተግባር አኳያ እጅግ ግልፅነት የጎደለው፣ ኃልዮታዊነቱ የሳሳ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ‹‹ፍልስፍና›› ነው።

የስያሜው አመጣጥእ.ኤ.አ በ1982 ቻልመር ጆንሰን ‹‹MITI

and The Japanese Miracle›› የሚል ርዕስ በሰጠው እና የጃፓንን ድህረ-ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አስገራሚ የኢኮኖሚ ግስጋሴን ተዓምር (Miracle) ብሎ በሰየመበት መጽሐፉ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ልማታዊ መንግሥት (Developmental State) የሚለውን ሀረግ ተጠቀመ። ጆንሰን፣ ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያሳየችውን የኢኮኖሚ ዕድገት አበይት አብነቶች እና ምስጢሮች ናቸው ያላቸውን ሁነቶች በጥናቱ አስቀምጧል። ጆንሰን እንደሚከራከረው፣ የጃፓን ልማታዊ መንግሥት ሞዴል በዋናነት የዕድገት ሂደቱ በምዕራቡ ዓለም ቁጥጥር ስር ከዋለው የዓለም ሥርዓት የተለየና ጠንክሮ ለመውጣት የቻለ ነው የሚል ምልከታውን ያሰፈረ ሲሆን፣ ልማታዊ መንግሥትን ለማብራራት የዕቅድ ኃልዮታዊነትን ከገበያ ኃልዮታዊነት ሥርዓት ጋር አንድ ላይ መሳ ለመሳ በማድረግ ይመለከተዋል።ጆንሰን የጃፓንን ልማታዊ መንግሥትነት ሶስት መከራከረያ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ይተነትናል። በመጀመርያ ደረጃ፣ ገበያ ለብቻ ተነጥሎ የሚኖር ሳይሆን ይበልጡኑም የመንግሥትና የፖለቲካ ፍጥረት ውጤት ነው ይላል። ሁለተኛው፡- ልማታዊ መንግሥት በዚህ መንገድ የሚመጣና የልማት ቅድመ-ሁኔታዎች ስፍራቸውን ከመያዛቸው በፊት የሚከሰት የሂደት ውጤት መሆኑን ይተነትናል። በሶስተኛ ደረጃ የመንግሥቱ ሕዝቡን በአንድ የልማት አጀንዳ ላይ በካፒታሊስት ሥርዓት ስር ማስተባበሩ ነው ይላል። በሌላ በኩል አሚያ ኩማር ባቺ ልተማታዊ መንግሥትን፣ ‹‹በፖሊሲዎቹ ልማትን ቀዳሚ ትኩረቱና አጀንዳው ያደረገና ውጤታማ መሳሪያዎችን የመቅረፅ ከፍተኛ አቅም ያለው›› ሲል ይገልጸዋል። መሳሪያዎቹም አዳዲስ ወጥ ተቋማትን የመፍጠር፣ መደበኛ ያልሆኑ ከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍልና ኃላፊዎች ጋር እንደድልድይ የሚያገለግሉ የግንኙነት ዘዴዎችን ማበጀትና በንግድና ትርፋማ የምርት ሂደቶች አዳዲስ ዕድሎችን መጠቀምን ይጨምራል። በአፍሪካ የልማት ጉዳዮች ላይ ጥናት በማድረግ የሚታወቀው ታዲካ ማካንዳዋይሪ፣ ‹‹አይዶሎጂያዊ መሰረቶቹ ልማታዊ የሆነና አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ኃብቶቹን በላቀ የትኩረት ደረጃ ለማሰማራት የሚጥር›› ሲል ልማታዊ መንግሥትን ይተረጉማል።ከጆንሰን በተለየ ባቺ የልማታዊ መንግሥት ን አመጣጥ ከጃፓን ጋር መያያዙን በመቃወም ይሞግታል። በዕርሱ እምነት ምንም እንኳን የልማታዊ መንግሥት እሳቤ ከምስራቅ ኢሲያ ከመጀመርያውና ከሁለተኛው ትውልዶች አዳዲስ የኢንዱስትሪ ሀገራት (Newly Industrialized Economies/NICs) ጋር ተያይዞ የሚወሳ ቢሆንም፣ በተግባር ደረጃ እውን መሆን የጀመረው ከረጅም ጊዜ በፊት በ16ኛው ክ/ዘመን ኔዘርላንድ፣ እንግሊዝ ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክ/ዘመን፣ እንዲሁም ጀርመን ከ19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ እስከ መጀመርያዎቹ የሃያኛው ክ/ዘመን ዓመታት ድረስ ልማታዊ መንግሥት እንደነበሩ ይሞግታል።በአፍሪካም ከቅኝ ግዛት በኋላ ልማታዊ መንግሥታት በምኞትም ሆነ በተግባር ተስተውለዋል። መንግሥት መር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ የኢሲያውያን አዲስ ግኝት ሳይሆን፣ ይባስ ብሎ ከመጀመርያዎቹ የ19ኛው ክ/ዘመን ዓመታት በአውሮፓ አንዳንድ ሀገራት ከነበረው የመርካንታይሊስት ሥርዓት (Mercantilist) ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው። ቻንግ ይህንን ሃሳብ በማጠናከር የመንግሥት ጣልቃ ገብነት በኢኮኖሚ በምስራቅ ኢሲያ ሀገራት ብቻ የተለየ ምላሽ ሆኖ በታሪክ በልዩ አጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን፣ በየትኛውም ውጤታማ ኢኮኖሚ፣ እንግሊዝንና አሜሪካንን ጨምሮ፣ በኢንዱስትረ ሂደት መነሻ ወቅት የሚስተዋል ዓለም አቀፋዊና ነባራዊ ገፅታን የተላበሰ መሆኑን ያስረዳል።በታሪክ የልማታዊ መንግሥት ዕሳቤ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምክንያት ከፍ ዝቅ ሲል ተስተውሏል። ልማታዊ መንግሥታት ፣በኢሲያም ሆነ በአፍሪካ በሌሎች አህጉራት ተከስተዋል። ለዚህም የተለያዩ ክስተቶች ይጠቀሳሉ። የመጀመርያው የሁለተኛው የዓለም ጦርነትንና የቅኝ አገዛዝ ዘመን ማብቃትን ተከትሎ ብቅ ያለው ሲሆን፣ በዚህም የ1929ኙ ታላቁ የኢኮኖሚ አዘቅት (The Great Depression) ፍርሃትና ድህረ ጦርነት የፖለቲካ ለውጦች ለኬኔዥያን

ኢኮኖሚ መነሳትን አስከተለ። በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው በብሪቶን ውድስ ተቋማት መሪነትና ወትዋችነት በታዳጊ ሀገራት የተዋወቀው የመዋቅራዊ ማሻሻያ (Structural Adjustment) በዋሽንግተን ስምምነት ላይ ተመስርቶ የተደረገው የኒዮሊበራል የመዋቅራዊ ማሻሻያ በጉልህ ይጠቀሳል።የመንግሥታት ጣልቃገብ የኢኮኖሚ አስተዳደር ውጤታማ ከአለመሆንና የመንግሥታት እጅ መብዛትን ተከትሎ ከተስተዋለው የኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ በዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ፈንድ ጠንሳሽነት ሀገራቱ ብድር ለማግኘት የመዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ የመንግሥትን ሚና እንዲገድቡ በሚል ቅድመ-ሁኔታዎችን የጣሉ ውሎችን ተዋዋሉ። ይሁንና በጣም በጣት ከሚቆጠሩ ሀገራት በስተቀር ማሻሻያው ውጤታማ ከመሆን ይልቅ፣ ይባስ ያልተጠበቀ የኢኮኖሚ ቀውስ አስከተለ። ማካንድዋሬ ይህንን ‹‹የአፍሪካ የመከኑት ዓመታት›› በሚል ይገልፀዋል። ይህም የመንግሥት ሚና የማይተካ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ እንዲደረስ ምክንያት ሆነ። ይሁንና የ1997-98 የኢሲያ የገንዘብ ቀውስ የኢሲያ

የልማታዊ መንግሥት ሞዴል አዋጭነት ተመልሶ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲጋባ አደረገው። የዓለም ባንክም ኋላ ላይ ባወጣቸው ሪፖረቶቹ ቀድሞውንም ቢሆን የያዘውን ‹‹ምንም ተዓምር አልተፈጠረም›› የሚል አቋሙን አጠናከረበት። ይህም የመንግሥታትን ጣልቃገብነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሆነ።የመጨረሻው እ.ኤ.አ. በ2008 የተከሰተው የዓለም የፋይናንስ ቀውስና ብሎም በ2009 ወደ የኢኮኖሚ ቀውስነት የተሸጋገረው ይጠቀሳል። ይህም ብዙዎች የመንግሥትን ጣልቃ-ገብነት የሚደግፉትና ቀድሞውንም የገበያን ኃልዮታዊነት በጥርጣሬ የሚያዩትን ይበልጥ የልብ ልብ ሰጣቸው።

ኢህአዴግ እና ልማታዊ መንግሥቱምንም እንኳን ኢህአዴግ ከሽግግሩ ጀምሮ ልማታዊ መንግሥት ለመሆን በርካታ ያልተሳኩ ጥረቶችን ቢያደርግም፣ ልማታዊ መንግሥት የሚለው እሳቤ በኢትዮጵያ ወደ ፖለቲካውና የኢኮኖሚ ክበቡ ብቅ ያለው በቅርቡ ነው። ይህም የድርጅቱ ምስጢራዊነትና ግልፅ የሆነ ትርጉም አስቀምጦ ፖሊሲዎቹን አለማበጀቱ፤ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር በተገናኘ መዋለሉና ሙከራዎቹ ባለመሳካታቸው ለአደባባይ የፖለቲካ ፍጆታነት ከመዋል እንዲዘገይ ሆኗል።በሽግግሩ ወቅት በኒዮሊበራልና በሶሻሊስታዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሥርዓት መካከል አንዱን ለመምረጥ በመቸገሩ የኋላ ኋላ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ቢገደድም ግንባሩ እንደሚለው፣ ‹‹ … ይህ የመከላከል ሥራ ወጥ ከሆነ የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ የመነጨ ነበር ማለት አይቻልም›› በሚል እራሱ አስተባብሎታል። ግንባሩ ልማታዊ መንግሥት የሚለው እነጆንሰንና ሌሎች የዘረፉ ምሁራን በሚያስቀምጡት መልኩ እንዳይደለ ይስተዋላል። ለዚህም ድርጅቱ ልማታዊነትን የሚያየው ከድርጅቱ መርህና ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር መሆኑ ነው። የተለየ የፖለቲካ አስተሳሰብና አቋም ያላቸውን የፖለቲካ ቡድኖች ልማታዊ አድርጎ አለማየቱ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስጋት አድርጎ ያቀርባል። ለዚህም በ1992 የተከሰተውን ድርጅታዊ መሰንጠቅና የተሃድሶ እንቅስቃሴውን በልማታዊ ኃይሉና ኪራይ ሰብሳቢው በሚላቸው የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች መሀል የተካሄደ መሆኑን በማሰረጃነት ያቀርባል። ይህም ኋላ ላይ የተከሰቱትን ተቃዋሚዎች ፀረ-ልማት የሚል ተቀፅላ መስጠቱ የዚሁ ባሕርያዊ ቅኝት ተደርጎ ይወሰዳል። በወቅቱ የተፈጡሩት ውጫዊና ውስጣዊ ሁኔታዎች የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ የድርጅቱ ለሁለት መሰንጠቅ፣ የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምና የኒዮሊበራሊዝም ጫና መብዛትና በወቅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የልማታዊ መንግሥት ተቀባይነት መሸርሸር ተግባራዊ ላለመሆኑ ይጠቀሳሉ።ኢህአዴግ ከሽግግሩ ጀምሮ ምርጥ ተሞክሮ በሚል የኢሲያውያንን በተለይ የጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ ቻይና እና ማሌዥያን በዋናነት ልምድ ለመውሰድ በመከጀል ይታወቃል። 1994/5 ዓ.ም በመንግሥቱ የሥልጣን ታሪክ ከፍተኛ የፖሊሲና የሥትራቴጂ ሰነዶች ጥራዝ ያቀረበበት ወቅት ነበር። በጊዜውም የኢንዱስትሪ ልማት ሥትራቴጂ፣ የገጠር ልማት ፖሊዎች ሥትራቴጂዎችና ሥልቶች፣ የውጭ

ይግባኝ የሌለው ቅጣት

ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲና ሥትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮችና ሌሎች መጥቀስ ይቻላል። እንዲሁም በኋላ የወጡትን የPASDEP እና የGTP መካከለኛ ጊዜ እቅዶችን አዘጋጅቷል። ይህም እቅዶችን የማዘጋጀት በተለይ በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የታየ የልማታዊ መንግሥታት ዋነኛ ባሕሪ ተደርጎ ይወሰዳል። በሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ የኢሲያውያን ተሞክሮ በግልጽ ሰፍሮ ይስተዋላል።የኢንዱስትሪ ልማት ሥትራቴጂው ካስቀመጣቸው ቁልፍና መሰረታዊ

ሥትራቴጂዎች ውስጥ ‹‹ከፍተኛ የመንግሥት ቁጥጥር›› የሚለው

በጉልህ ሰፍሮ ይገኛል። ይህም የኢሲያውያን

የልማት ሞዴል መሆኑንና የኢትዮጵያ መ ን ግ ሥ ት ም ልማታዊ በመሆኑ ይህንን መከተል እ ን ዳ ስ ፈ ገ ው ያ ት ታ ል ። ብርሃኑ አበጋዝ እ ን ደ ሚ ለ ው ፣ መንግሥቱ ከድህረ ሶሻሊስት ማሻሻያው

ጀምሮ የኢሲያን በተለይም የቻይናን

የልማት ሞዴል ለመኮረጅ እንደሚመኝ ይገልፃል። ይሁንና

ይህ የልማታዊ መንግሥትነት ፍቅር ከ1999 ዓ.ም በኋላ ሊያገረሽ ችሏል። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው የጠ/ሩ ጽሑፍ ነው። ግንባሩ ሁሌም ቢሆን የጠ/ሩን ጽሑፎችና ንግግሮች የመንግሥቱ አይዶሎጂ አድርጎ የማቅረብና መላው አባላቱና ሁሉም አመራሩ (ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ) ይህንን የመቀበልና የማስተጋባት ልማድ ስላለው የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን ወጥ የሆነ ትንተና በመስጠት ከድርጅቱ ነባራዊ መሰረታዊ መርህዎች ጋር እንዴት አድርጎ ተቀናጅቶ ሊሄድ እንደሚችል የማስቀመጥ ችግር ስላለበት ፅንሰ-ሃሳባዊ ጥንካሬው እጅግ የሳሳ ነው። በዛው ዓመት ስለ ልማታዊ መንግሥት ሥልጠና የሰጠ ቢሆንም፣ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ በተለየ መልኩ በልማቱ በኩል ያለውን ትንተና ማስቀመጥ አልቻለም።ግንባሩ ሌላው ልማታዊ መንግሥትን የሚጠቀምበት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከወኑ ተግባራት እንደ ማስተባበያና አስረጂነት ነው። ለዚህም ትችቶቹን ላለመቀበል የኢሲያውያኑ ልማታዊ መንግሥታት የሚያደርጉት መሆኑን በመግለጽ ተቀባይነት ለመግዛት ይሞክራል። ይህም ከፖለቲካ ፍጆታነት ባለፈ ነፍስ ዘርቶ ሀገራዊ ስምምነት ፈጥሮ አልተንፀባረቀም።

ልማታዊ መንግሥታቱ ከወዴት አሉ?በተለምዶ ልማታዊ መንግሥታት የሚባሉት ከኢሲያ ተዓምርራዊ የአካባቢው የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተገናኝቶ የሚወሳ ነው። እነዚህም የመጀመርያው ትውልድ የሚባሉት አዳዲስ በኢንዱስትሪ ያደጉት ሀገራትን - ጃፓንን፣ ደቡብ ኮሪያን፣ ታይዋንንና ሲንጋፖርን የሚይዝ - የተሻለ አቅም ያላቸው ተደርገው የሚታዩ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ የሁለተኛው ትውልድ የሆኑትና ‹‹የኢሲያ ነብሮች›› በመባል የሚታወቁት ማሌዢያ፣ኢንዶኔዥያ፣ ታይላንድ (ሶስቱ ‹‹MIT Economies›› ተብለው ይጠራሉ)፣ ሆንግኮንግ እንዲሁም ፊሊፒንስን ሲጨምር አሁን አሁን ደግሞ ቻይናም ልማታዊ መንግሥት ተብላ በመጠራት ላይ ትገኛለች። መንግሥታቱ በአጠቃላይ ‹‹ከፍተኛ ዕመርታ የሚያሳዩ ኢኮኖሚዎች›› በመባል ይታወቃሉ::ልማታዊ መንግሥታት የተለያዩ ባሕሪያት ያሏቸው ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ እንደኮሪያና ታይዋን ያሉት አምባገነንና ጨቋኝ፣ ደግሞ ግማሽ ዴሞክራሲያዊ የሆኑ እንደጃፓን፣ ሲንጋፖርና ቦትስዋ ያሉ ሀገራት ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ በአውራ ፖርቲ ሥርዓት የሚመሩ (ሲንጋፖር፣ ጃፓን፣ ቦትስዋና) እና በተለዋዋጭ ጥምር መንግሥት የሚመሩትን (ሞሪሽየስ፣ ፊንላንድ) ይመለከታል። በአጠቃላይ ልማታዊ መንግሥታት ተብለው የሚፈረጁት ሀገራት ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን (ከሰሜን ምስራቅ ኢሲያ)፣ኢንዶኔዥያ፣ ታይላንድ፣ ማሌዢያ፣ ሆንግኮንግና ሲንጋፖር (ከደቡብ ምስራቅ ኢሲያ)፣ ቦትስዋና እና ሞሪሽየስ ከአፍሪካ፣ እንዲሁም ከአውሮፓ ፊንላንድን ይጨምራል።

የልማታዊ መንግሥት መመዘኛዎችልማታዊ መንግሥትን ለማብራራት ተንታኞች መሰረታዊ ናቸው የሚሏቸውን ነጥቦች ይዘረዝራሉ። አድሪያን ሌፍትዊች የተለያዩ ነጥቦችን ያስቀምጣል። የመጀመርያው፣

የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማታዊ መንግሥቱ ጋብቻ

በ ገፅ 9

ልማታዊ መንግሥትን ለማብራራት

ተንታኞች መሰረታዊ ናቸው

የሚሏቸውን ነጥቦች ይዘረዝራሉ።

አድሪያን ሌፍትዊች ልማትን

የሚያስቀድም የፖለቲካ ልሂቃን

መኖር ነው ሲል ጆንሰን ደግሞ

ለልሂቃኑ መተባበር ሶስት ነጥቦችን

ያነሳል፡- የጋራ የሆነ ፅኑ ፍላጎት፣

የተፈጥሮ ኃብት እጥረትና ከፍተኛ

የደህንነት ዕጦት። ሌሎች ደግሞ

ይህን ከልማቱ መንገድና ይዘት

ላይ ያላቸው መስማማትን

በምክንያትነት ያስቀምጣሉ።

Page 5: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

ማስታወቂያ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ከዓለም ሲኒማ ተመልካቾች የተሰበሰበ

በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው 1. ግሩም ኤርሚያስ የተዋጣለት 2. አማላይ ነው በተለይ ለእንደእኔ ትውልደ 3. ኢትዮጵያዊ ይመቻል በጥራት ስለሰራችሁት 4. አመሰግናለሁ ፊልም ማለት እንደዚህ ነው 5. ሁለት የተለያዩ ስቶሪዎች በፍቅር 6. አይቻለሁ ግሩም እኔን በጣም ነው ያማለለኝ 7. አስተዋውቁኝ እኔና ጓደኞቼ የእውነት ማለናል፡፡ 8.

ምስጋና ለዓለም ሲኒማ

ከባለሙያዎች የተሰጠ አርቲስት መርዓዊ ስጦት - ዘመኑን የዋጀ ፊልም አርቲስት ሠይፉ አርአያ - የወጣቶችን ልብ የሚማርክ ዘመናዊ ፊልም አርቲስት ጌትነት እንየው - በጣም የሚጣፍጥ ቀለል ያለ ታሪክ አርቲስት ቢኒያም ወርቁ - በሁሉም መስክ የተዋጣለት ፊልም ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ - በባለሙያዎች የተሰራ ምርጥ ፊልም የሜዳሊያ ደራሲ አማኑኤል መሀሪ - ምርጥ ፕሮዳክሽን ሊያዩት የሚገባ

የአማላዩ ፊልም እውነታዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተቀረፀ - በCanon 5D እና 7D የተቀረፀ- በከፍተኛ በጀት የተዘጋጀ፣ 7 ወራትን የፈጀ - በየጊዜው መረጃዎችን በጋዜጣዊ መግለጫ ያበሰረ - ለቀለም እርማት ሥራ ወደ ለንደን የተጓዘ - ከተመረቀ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በ21 እይታ የታየ- ተመልካቾችንና ባለሙያዎችን ያስማማ ምርጥ ፊልም - አማላዩ-

በእምቢልታ ሲኒማ፣ በኤድና ሞል፣ በአለም ሲኒማ፣

በዩፍታሄ ሲኒማ፣ በፓናሮሚክ ሳምንቱን ሁሉ ይገኛል

በቅርብ ቀን በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ይታያል

‹‹አማላዩ›› ከካም ግሎባል ፒክቸርስ

አማላዩ ሮማንቲክ ኮሜዲ

ስለ ‹‹አማላዩ›› ፊልም ተመልካቾች ምን ይላሉ

ፊ ቸ ር

በኤልያስ ገብሩ

ባለፉት 20 ዓመታት በጠ/ሚ/ሩ ጽ/ቤት ውስጥ የተለያየ ውሳኔ የሚፈልጉ ስብሰባዎችና መንግስታዊ መግለጫዎች ሲካሄዱ የነበረ ቢሆንም ታሕሳስ 28 ቀን 2003 ዓ.ም የተጠራው ሰበር የስብሰባ ጥሪ ግን በዓይነቱ ለየት ያለ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ በዚህ ዕለት የአገሪቱን የግብይት ስርዓት ሚመሩ ከ580 በላይ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት በንግድ ሚኒስቴር አማካይነት የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው በጠ/ሚ/ሩ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከተዋል፡፡

የዕለቱን አጀንዳ አስመልክቶ የምጣኔ ኃብት ጠበብቶች በጠሪዎቹም ሆነ በተጠሪዎቹ መካከል የነበረው መንፈስ የመቀራረብና በጋራ መፍትሔ የመፈለግ ሳይሆን ከዚያ ቀደም ‹የሚመራን ገበያው ነው› የተባለለትን አቋም ወደጎን አድርጎ የአድርግ አታድርግ ፍጥጫ የተጀመረበት ይሉታል፡፡ ከጠ/ሚ/ር መለስ በተጨማሪ የኢኮኖሚ አማካሪያቸው አቶ ንዋይ ገ/አብ፣ የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሕመድ ቱሳ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ኃላፊዎች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል፡፡ እናም አቋማቸውን አሳወቁ፡፡ - መሰረታዊ በተባሉ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ የቁርጥ ዋጋ ተመን ይፋ ተደረገ፡፡

ኪሎ ሜትሮች እየተሰሉ የዋጋ ጣራ ተመኑ አገሪቱን ማዳረስ ጀመረ፡፡ መመርያውን ያላከበሩ ነጋዴዎች፣ ትዕዛዙን በአግባቡ ያላስፈጸሙ ባለስልጣናት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገቡ፣ ሕጋዊ የተባሉ እርምጃዎች መወሰድ ጀመሩ፡፡ ምንም እንኳ ንግድ ሚ/ር መመርያውን ተግባራዊ ያደረገው በቂ ጥናት አድርጎ መሆኑን ቢያስታውቅም ከመመርያው በኋ ነበሩት ቀናት በምስቅልቅል ተሞሉ ሆኑ፡፡ ሸቀጦች ጠፉ ወይም ጥራታቸውን ሳይጠብቁ ለሽያጭ ይቀርቡ ጀመር፡፡

ነጋዴዎች ‹በገዛ አገራችን መሳቀቅ አለብን እንዴ? ካላዋጣንስ? በቃ ድርጅታችንን ዘግተን መሄድ ነው› ሲሉ ‹ባያተርፋችሁም ትሸጣላችሁ› የሚል ችግሩን በሳይንሳዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ በጫና ላይ የተመሰረተ ምላሽ ጥናት አድርጌያለሁ ከሚለው ተቋም ይደመጥ ጀመር፡፡ ፖለቲከኞች ‹ወደ ዕዝ የኢኮኖሚ ስርዓት እየተጓዝን ነው!› ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና ስጋቶች ተዘረዘሩ፡፡

ሁኔታውን አስመልክቶ በወቅቱ አስተያታቸውን ለአውራምባ ታይምስ የሰጡት የ‹መድረክ› አመራር አባል አቶ ገብሩ አስራት ‹መንግስት እየተከተለ ያለው መንገዱ ይህ ብቻ ነው የሚል አካሄድ የማያዋጣና የችግሩን ምንጭ ነጋዴው እንደሆነ በማስመሰል ከሕዝብ ጋር የማቆራረጥ ትኩረት የማስቀየር ስልት ነው፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ብዙ የተባለለት መመርያ ግን አምስት ወር እንኳ መድፈን አቅቶት በያዝነው ሳምንት አጋማሽ ላይ በአብዛኛው ለመነሳት ተገዷል፡፡ የንግድ ሚኒስቴር በመጀመሪያ ተመን እንዲወጣላቸው ወስኖ የነበረው ለ17 መሠረታዊ ሸቀጦች ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ የመሠረታዊ ሸቀጦቹ ቁጥር 80 እንዲሆን መደረጉ የሚታወስ ነው።

ውሳኔውም ተግባራዊ መሆን በጀመረበት ወቅት ‹‹አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከኑሮ ወድነት ይገላግላል›› በሚል በአዎንታዊ ጎኑ ቢታይም ከርምጃው በኋላ የዋጋ ንረት፣ ተመን የወጣላቸው ሸቀጦች መጥፋት እንዲሁም የድብቅ ገበያ መበራከት በመከሰቱ መንግስት ያወጣውን የዋጋ ተመን በድጋሚ እንዲያጤን የሚያስገነዝቡ ትችቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። ይሁንና በመንግስት በኩል ይሰጡ የነበሩት ጠንከር ያሉ መግለጫዎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ከተባሉ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ጠ/ሚ/ሩ ውይይት ካደረጉ በኋላ የዋጋ ተመኑ ከአንዳንድ ምርቶች ላይ ሊነሳ እንደሚችል ፍንጭ ታየ።

ጠ/ሚ/ሩ፣ ከነጋዴዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ግን ‹‹እናንተን ማመን አልቻልንም። ዘይቱን ለእናንተ ብንሰጥም ያፍኑታል የሚል ጥርጣሬ አለን። ፍትሐዊ በሆነ ዋጋም ትሸጡታላችሁ የሚል ዕምነት የለንም። እያንዳንዳችሁ የዋጋ ቁጥጥሩ እንዳይሰራ ጥረት አድርጋችኋል፤ መንግስት የያዘውን የዋጋ ቁጥጥር እናስጥለዋለን የሚል አቅም ቢኖራችሁም መንግስት ተስፋ ቆርጦ አይተወውም›› ማለታቸው ተመኑ የሚነሳው ከተወሰኑ የቢራና ለስላሳ ምርቶች ላይ ብቻ እንደሚሆን ግንዛቤ ፈጥሮ ነበር።

የሆነው ሆኖ የንግድ ሚኒስቴር ከዘይት፣ ከስኳርና ከዱቄት ምርቶች

ውጪ ባሉት ሸቀጦች ሁሉ ላይ ያወጣውን ተመን አንስቷል። እርምጃውንም ተከትሎ በሸቀጦች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የቅድመ እና ድሕረ ሽያጭ ክትትል እንደሚደረግ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመግለፅ ላይ ነው። በሚኒስቴሩ ገለፃ መሠረት ቅድመ ሽያጭ ክትትል ማለት የዋጋ ተመን ሲሆን፣ በዘይት፣ በስኳርና በዱቄት ላይ ተግባራዊ ይደረጋል። ድህረ-ሽያጭ ክትትል ደግሞ፣ ነጋዴው በራሱ የሚተምነውን ዋጋ በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት ክትትል ማድረግ ነው።

ነገር ግን መንግስት የዋጋ ተመን ሲያወጣ ‹‹የነፃ ገበያ መርህን ያፋልሳል›› ሲሉ ትችት የሰነዘሩ ወገኖች የተመኑ መቅረትን ተከትሎ አስተያየቶችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ጉዳዩን አስመልክቶ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየት መስጠት የጀመሩት ‹‹ኢህአዴግ በዱብ ዕዳ የተሞላ ነው›› በማለት ነበር። ተመኑ ሲወጣም ሲነሳም በድንገት መሆኑን ያስታወሱት አቶ አንዱዓለም፣ ‹‹ይሄ የሚያሳየው ሁሌ በዘፈቀደ እንደሚሰሩ ነው። ነገሮችን ማገናዘብ የሚጀምሩት ከጥፋት በኋላ ነው›› ብለዋል።

መንግስት በገበያው ውስጥ ጣልቃ መግባቱን እሳቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው እንደማይቃወሙ ነገር ግን ጣልቃ ሲገባ በጥናት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው የሚያስገነዝቡት አቶ አንዱዓለም፣ መንግስት ደስ ባለው ጊዜ ጣልቃ የሚገባ ባልተመቸው ጊዜ ደግሞ የሚወጣ መሆን እንደሌለበት በመግለፅ ‹‹ዱሮውንም በጥናት ላይ ያልተመሰረተ መሆኑ የሚታወቀው እርምጃው የነበረውን ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ በመክተቱ ነው። የዋጋ ተመኑ ሸቀጦችን ከገበያ ሲያጠፋ እና ዋጋቸውን ሲያንር እንጂ የሕዝቡን ጓዳ ሲሞላ አላየንም›› ሲሉ አሰራሩን ነቅፈዋል።

አቶ አንዱዓለም አክለውም በገበያው ላይ የሚስተዋለውን ችግር በዋንኛነት ሊፈታ የሚችለው ኢህአዴግ በተለያዩ የንግድ ድርጅቶቹ አማካኝነት ከተቆጣጠረው ገበያ ሲወጣ መሆኑን በማስገንዘብ ‹‹ኢህአዴግ ባልተገባ አካሄድ ራሱን ቢሊየነር ያደረገ ድርጀት ነው። ብዙ ነጋዴዎችን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ የገበያ ውድድርን ያጠፋው ራሱ ነው›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በትክክል የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲስተካከል ከተፈለገ የፖሲሲ ለውጥ ማድረግና አገር በቀል የሆኑ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማበረታታት ከመንግስት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

መንግስት ዘይትና ስኳርን በብቃት ማቅረብ አለመቻሉን የሚገልፀው ባለሱቅ ወጣት ባሕሩ አብደላ እንደድሮው ነጋዴው ራሱ እያመጣ አትርፎ ቢሸጥ የተሻለ መሆኑን ይጠቅሳል። መንግስት በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ተመን ከማውጣቱ በፊት የተለያዩ ጥራት ያላቸው ሳሙናዎች በገበያ ውስጥ እንደነበሩ የሚያስታውሰው ወጣት ባሕሩ፣ ‹‹በአሁኑ ወቅት ጥራት የሌላቸው የአገር ውስጥ ሳሙና ምርቶች እየተሸጡ ይገኛሉ። … መንግስት የወሰዳቸውና እየወሰዳቸው ያሉት ዕርምጃዎች በፍፁም ለውጥ አያመጡም›› በማለት አስተያየቱን ይሰጣል። በሱቁ ውስጥ ስኳር እንጂ ዘይት አለመኖሩን በመናገር።

ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት ንግድ ሚኒስቴር ከነጋዴው ማሕበረሰብ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ መሳተፋቸውን ለአውራምባ ታይምስ የገለፁት አቶ ወልዴ ሀይሉ ለ20 ዓመታት ያህል ከቤተሰባቸው በተረከቡት ሥጋ ቤትና የመጠጥ ግሮሰሪ ውስጥ በባለቤትነት እየሰሩ ይገኛሉ።

ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በታህሳስ ወር መጨረሻ መንግስት በሥጋ ዋጋ ላይ አውጥቶት በነበረው የዋጋ ተመን ላይ ምን ያህል ጥናት እንዳደረገ መጠየቃቸውን አቶ ወልዴ ይናገራሉ።

‹‹በተወሰነ መልኩ ጥናት አድርገናል። በዋጋ ተመኑ የሚጎዳ ክፍል እንዳለ እያወቅን ዋጋውን ለማረጋጋት ስንል እርምጃውን ወስደናል›› የሚለው የመንግስት ምላሽ ነበር። የዋጋ ተመኑን መነሳት ተከትሎ ከትናንት በስቲያ በፒያሳ አከባቢ አንድ ኪሎ ስጋ ከ65-80 ብር ድረስ እየተሸጠ የነበረ ሲሆን አንድ የስጋ ከብት ከሰባት ሺህ - 15 ሺህ ብር ድረስ እየገዙ ለገበያ እንደሚያቀርቡ ስጋ ሻጮች ይገልፃሉ።

‹‹አንድ ኪሎ ስጋ 52 ብር በነበረበት ጊዜ ለተጠቃሚው አብዛኛውን አጥንት ነበር የምንሸጠው። ንፁህ ጥሬ ስጋንና ለክትፎ የሚሆነውን አንሸጥም ነበር። ጥሩ ስጋ እንድንሸጥላቸው ገንዘብ እንጨምርና በድብቅ እንክፈል

የሚሉን ሰዎች ነበሩ… የመሸጫ ዋጋው ስለማያዋጣን ከስረን ነበር የምንሰራው። በዚህ ምክንያት ብዙዎች ከገበያ ወጥተዋል›› በማለት አቶ ወልዴ ተናግረዋል።

የቁጥጥር ስርዓቱ ገደብ ያለፈ መሆኑን የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች ‹‹መንግስት ከእንደዚህ አይነት (ከሽያጭ) አሰራር መውጣት አለበት፡፡ የሚያቀርበውን በደንብ መቆጣጠር አለበት ግን አልቻለውም፡፡ ለምሳሌ መንግስት ዘይትን እየሸጠ ያለው ከስሮ መሆኑን እየገለጸ ሲሆን በንግድ ስርዓት ሸቀጦችን በዚህ መንገድ ለገበያ ማቅረቡ የኢኮኖሚ ቀውስ የሚፈጥርና የሚጠቀሙትም ጥቂት ግለሰቦች ብቻ እንዲሆኑ የሚያደርግ ስልት ነው።›› ይላሉ፡፡

ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የዋጋ ተመን ማውጣት በገደብ የሚደረግ ሥራ አያስደስትም፤ ለደርግና ለሻዕቢያ አለመጥቀሙን በማስታወስ በደርግ ግዜ ቀበሌ ነው ሰውን የገደለው፣ ለቀበሌ ይኼን መሠል የሽያጭ ስልጣን መስጠት የለበትም። በአሰራሩ ሕዝብ ነው የተጎዳው። የትም አያደርስም›› ሲሉ ይተቻሉ።

በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች እምብዛም በገበያ ላይ እንደማይገኙ፣ ያሉትም ዋጋቸው በጣም መናሩን፣ ከዚህ ጀርባ ሸፍጥ መኖሩንና በመጋዘኖች ተከማችተው እንደሚገኙ በመጥቀስ ‹‹መንግስት እነዚህን ተከታትሎ ገበያ ላይ እንዲወጡ ማድረግ ይኖርበታል›› የሚሉ አስተያችን ከነዋሪዎች አድምጠናል።

ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት በመንግስትና በነጋዴው ሕብረተሰብ ውስጥ ‘ሌቦች‘ መኖራቸውን መናገራቸው ይታወሳል። ‹‹እስከአሁን መንግስት በውስጡ ያሉትን ሌቦች መለየት አልቻለም ማለት ነው?›› በማለት በስላቅ የጠየቁት አቶ አስመላሽ የተባሉ ነጋዴ ‹‹እነዚህን እንኳን መንግስት ሌላውም ያውቃቸዋል። መንግስት ነካ ነካ አድርጎ ሲተዋቸው የተባሉት ሰዎች ባሰባቸው ለዚህም ተገቢ እርምጃ አልተወሰደም›› ይላሉ። የሚታወቁ ‘ሌባ ነጋዴዎች‘ን ለይቶ መምታት እንደሚገባ በማሳሰብ።

በዚህ ረገድ የሙስናን አሳሳቢነት አቶ አስመላሽ በመጠቆም ‹‹የተዘረፉትን ዘርፈው ቃሊቲ የሚገባ አሉ። ለእነዚህ ሙክት ታርዶላቸው በየሳምንቱ ይበላሉ። ሚሊዮናቸውን ይዘው ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ። 10 ሚሊዮን የዘረፈ ጥቂት ዓመታት ታስሮ ይወጣል። ምንም ያልነበራቸው ሰዎች በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሚሊዮነር ሆነው ይታያሉ። ይኼ የሚሆነው የሆነ ደባ ተሰርቶ ነው። መንግስት ይኼንን መፈተሽና መከታተል አለበት›› በማለት ለአውራምባ ታይምስ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

መፍትሔው ምንድነው?በአሁኑ ወቅት በንግዱ ዘርፍ

ያለውን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦች ይደመጣሉ። ንግዱ በውድድር እንጂ በጥቂት ነጋዴዎች እጅ መውደቅ እንደማይገባው፣ ብቸኛ አስመጪ የሚባለው ነገር ቀርቶ ተገቢውን ግብር የሚከፍሉ በርካታ ነጋዴዎች በአስመጪነት ንግድ መሰማራት እንደሚኖርባቸው ተጠቃሽ የመፍትሔ ሃሳቦች ናቸው።

መንግስትም ሌቦችን ይዞ በእነሱ ላይ እርምጃ ካልወሰደ በስተቀር ሌባን ይዞ ሌላ ሌባን መፍጠር የባሰ ችግር እንደሚያስከትል አቶ አስመላሽ ከልምዳቸው በመነሳት ይጠቁማሉ፡፡ በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ፋና የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማሕበር የሽያጭ ክፍል የሆኑት አቶ ግርማ ሞገስ የስኳርና የዘይት ስርጭቱ ምን እንደሚመስል ከአውራምባ ታይምስ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ስኳር በበቂ ሁኔታ በየሱቁ እንደሚገኝ፣ የዘይቱም ስርጭት ጥሩ ቢሆንም ግንቦት 19/2003 ዓ.ም በአከባቢው ለሚገኙ 75 ሱቆች ባላቸው መጠን ለእያንዳንዱ አምስት አምስት ካርቶን ማከፋፈላቸውን እና ከዚያ በኋላም ዘይቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ምርመራ እየተደረገበት መሆኑና በነገው ዕለት (ማብራርያውን የሰጡን ሐሙስ ዕለት ነው) መከፋፈል እንደሚጀምር አቶ ግርማ ተናግረዋል።

ነገር ግን በሱቆች በኩል አንዳንድ ችግሮች መኖራቸውን የጠቆሙት የሽያጭ ኃላፊው ለእያንዳንዱ ሱቅ አምስት አምስት ካርቶን ጥዋት ላይ ተከፋፍሎ ከሰዓት በኋላ አለቀ የሚባል ነገር በመኖሩ ‹‹ሕዝብ ዘይቱን ለበላተኛ ሰጥቷችኋል›› በማለት ቅሬታ እንደሚያቀርብባቸው ይገልፃሉ።

በማስከተልም ‹‹ባለሱቆች ሁሉንም ለተጠቃሚዎች ይሸጣሉ የሚል ግምት የለኝም። እንደሚባለው ሱቆች

ዘይቱን ወደ ሌ ላ ቦታ በስውር ይ ሸ ጣ ሉ ። ያንን የመቆጣጠር ኃላፊነት የእያንዳንዱ ሕዝብ በመሆኑ በዚህ ላይ ጥብቅ ክትትል ያስፈልጋል›› ሲሉ አቶ ግርማ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።

መንግስት የስኳርም ሆነ የዘይት እጥረት አለመኖሩን ይገልፃል። ጠ/ሚ/ር መለስም ዘይትን በከተማው ውስጥ በማጥለቅለቅ ኃይቅ እንደሚፈጥሩ ቢናገሩም ዘይት ተጠቃሚው ዘንድ በተገቢ ሁኔታ እየደረሰ አይደለም። የመንግስት ንግግር ከእውነታው

ጋር አይቃረንም? በማለት በድጋሚ ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው የሸማቾች ማህበር የየራሳቸው ኮታ ስላላቸው በዚያ መሠረት ለባለሱቆች እያከፋፈሉ መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ግርማ ባለሱቆች ለአራትና አምስት ሰው ብቻ ዘይት ከሸጡ በኋላ ‹‹ጨርሰናል›› ስለሚሉ ‹‹የፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣምን ያስከተሉት ባለሱቆች ናቸው። ግለሰብ ነጋዴዎች ለራሳቸው ጥቅም ብለው ሕዝቡን እየጎዱ ነው›› በማለት ይከሳሉ።

በመሆኑም ግለሰቦች ከሸማቾች ማሕበር ዘይት ገዝተው ከወጡ በኋላ ‹‹ለማን ይሰጣሉ? ማን ትክክለኛ ተጠቃሚ ነው?›› የሚለውን በመለየት የቀበሌው ነዋሪ በስውር መጠበቅ እንደሚኖርበት የሚያስገነዝቡት አቶ ሀይሉ ‹‹አንዱ ጎረቤት በአግባቡ ሲጠቀም ሌላኛው ለትንሽ ገንዘብ ትርፍ ብሎ ለነጋዴዎች ይሸጣል። ይኼንን ማጋለጥ ከተቻለ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ይላሉ።

የድህረ ሽያጭ የዋጋ ቁጥጥር በሚደረግባቸው መሠረታዊ ሸቀጦችን እንዴት በአግባቡ መቆጣጠር ይቻላል? በሚል

የንግድ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ አማከለ ጥያቄ አቅርበንላቸው በመ/ቤታቸው በኩል በየቀኑ ክትትል እየተደረገ ሳምንታዊ መረጃ እንደሚሰበሰብ፣ የነጋዴዎች ትርፍም አሳማኝ መሆኑ እንደሚታይ፣ ዋጋ የተጋነነ ሆኖ የሕዝብ ጩኸት እየተደመጠ የቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

ከንግድ መርህ አንፃር ተገቢውን ነገር እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ በበስርጭት እና በአፈፃፀም ሂደቶች ውስጥ ችግሮች የሉም ለማለት እንደማይቻል ለአውራምባ ታይምስ ያስረዳሉ።

የቅድመ ሽያጭ የዋጋ ክትትል በሚደረግባቸው እንደ ስኳርና ዘይት አይነት ምርቶችን ሕብረተሰቡ በተገቢው ሁኔታ እየደረሰው እንደማይገኝ በድጋሚ ለአቶ አማከለ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በስርጭት ላይ ከሚያጋጥሙ ችግሮች ባሻገር ምርቶቹን ደብቀው የሚያከማቹ ነጋዴዎችን ተጠያቂ ማድረግ መንግስት በእነሱ ላይ ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ በሂደት ችግሩ እንደሚፈታ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት በንግዱ ዘርፍ በኩል ያሉንን ችግሮች ለመፍታት መንግስት አልቻለም ተብሎ ለሚቀርብበት ትችትም አቶ አማከለ ‹‹መንግስት አልቻለም ማለት አይቻልም። ከምን ላይ ተነስቶ ነው እንዲህ የሚባለው? የውጤት መለኪያው ምንድን ነው? መንግስት ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ግቦች አንፃር እየሰራ ነው በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ሰድዶ በማሳደድ አይደለም። ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በርካታ ተወዳዳሪ ነጋዴዎችን ማፍራት ስለሚያስፈልግ በዚያ ላይ እየተሰራ ነው›› በማለት ተችቱን ያስተባብላሉ።

ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊም በቅርቡ ከነጋዴዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ወቅት በመንግስት ውስጥም ሌቦች መኖራቸው መጥቀሳቸው የሚታወቅ ሲሆን አቶ አማከለም አሁን የተፈጠረውን አሰራር ሌቦቹን ከደህናው ለይቶ እንደሚያወጣ ተስፋ ያደርጋሉ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ታህሳስ ወር ላይ መንግስት አውጥቶት የነበረውን የዋጋ ተመን ከነፃ ገበያ ጋር የሚሄድ አለመሆኑን በመጥቀስ ‹‹በደርግና በሶሺያሊስት አገሮች ሞክሮ ያልሰራ›› በማለት ያጣጥለዋል።

እ.ኤ.አ በ1991 በራሺያ ሞስኮ ላይ

በ ገፅ 18

መርሕ አልባ፣ አቅጣጫ አልባ የዋጋ ትመና

Page 6: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 20036

(ባለፈው ሳምንት የማክስ ሜበር እሳቤዎችን ስንመለከት ማርክሲስት እሳቤን የሚቃወምበትን መንገድ፣ የቢሮክራሲ እና የምክንያታዊ አደረጃጀት ሁኔታዎችን፣ እንዲሁም በፖለቲካ አደረጃጀት ዙሪያ ሃይማኖቶች የነበራቸውን ሚና ቃኝተናል። ዛሬ ደግሞ ሥልጣን ሦስት ዓይነት ሊሆን እንደሚችል ይነግረናል - ባህላዊ፣ ሕጋዊ-ምክንያታዊ፣ ግርማ-ሞገሳዊ በማለት።)

ማክስ ዌበር “The Profession and Vocation of Politics” በተሰኘ ፅሁፉ በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሰው እራሱን ከአንድ ምክንያት (ዓላማ) ወይም ርዕዮት ዓለም ጋር በማድረግ ሞራላዊ ፍላጐቶቹን ማርካት እንደሚችል ይከራከራል። በፖለቲካ ላይ ጥገኛ የሆኑ፣ ያለምንም ውስን መርሆዎች ሥልጣን በመበዝበዝ ህይወታቸውን የሚመሩ ሰዎች ወደ “ባዶነት እና ምክንያት የለሽነት” ብቻ እንደሚመሩ ያምናል። በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው የማያወላውል (ፍፁም) እስከመሆን፣ ከእውነታ ጋር ድርድር እስከ አለማድረግና ፖሊሲዎች በሌሎች ላይ ያላቸውን ከፍተኛ የጐጂነት ውጤቶች እስከ መውቀስ በደረሰ መጠን እራሱን ለአንድ ዓላማ ፅኑ ሊያደርግ ይችላል። ሆኖም ይህ ፍፁም ሥነ-ምግባር ወይም የፅኑ እምነት ሥነ-ምግባር ኃላፊነት የጐደለው ከመሆኑ ባሻገር ከፍተኛ ጉዳት የማምጣት አቅም ያለው ነበር። ትክክለኛው የፖለቲካ ሙያ ለአንድ ዓላማ፣ ነገር ግን በየኋላፊለት ሥነ-ምግባር ለተሟሸ ዓላማ ትጉ መሆንን፣ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ መልካም ነገርን ለመፍጠር ሲባል ጥፋት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚገባ ተግባራዊ እውቅና መስጠትን ያካትታል። ይህንን ‘የዓለምን የሥነ-ምግባር ኢ-ምክኑያዊነት’ መቀበልን ነው እውነተኛው የርዕዮት ተከታይ ሊቀበለው የማይችለው።

ዌበር ፖለቲካን በጥሩ መንገድ አይምለከተውም፤ በብጥብጥ እና ማቆሚያ በሌለው ትግል የተሞላ እንደሆነ ያስባል። በአገራት መካከልና በአገራት ውስጥ ትግል አይቀሬ ከመሆኑ በተጨማሪ ወደፊት ይመጣል በተባለ የሰላም እና የወንድማማችነት ሀሳባዊ ዓለም ሊቆም የማይችል - መደበኛ ወይም ዘላቂ - ነበር። ዌበር መንግስትን በአንድ ድንበር ውስጥ የሕጋዊ ብጥብጥ የብቸኝነት ቁጥጥር (monopoly) ያለው ተቋም ሲል ይተረጉመዋል፤ በርግጥም የፖለቲከኞች ነገሮችን የማድረግ (የመስራት) አቅም ሙሉ ለሙሉ በአካላዊ ብጥብጥ (የኃይል ጥቃት) ስጋት ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ ያምናል። ፖለቲካ መልካም ግቦችን ለማሳካት በተደጋጋሚ ከሞራል አንፃር አጠያያቂ መንገዶችን መጠቀም ነበረበት። ይህም ፖለቲካ ከሞራል አኳያ ድርድራዊ (Compromised) እና አዛሳኝ ጭምር የሆነ አቅጣጫ እንዲከተል አድርጐት ነበር።

ሆኖም ፖለቲካ ኃይልን ብቻ ሳይሆን ሥልጣንንም ያካተተ ነው፤ እናም የተለያዩ የፖለቲካ ሥልጣን ዓይነቶችን በተመለከተ የዌበር ትንታኔ ለእርሱ የፖለቲካ ሶሺዮሎጂም ሆነ ለኖርማቲቭ የፖለቲካ እምነቶቹ ማዕከላዊ ገፅታ ነው። ሶስት የሥልጣን ወይም ተቀባይነት ያለው ቁጥጥር ዓይነቶች እንዳሉም ያስብ ነበር፤ እነዚህም ባህላዊ፣ ሕጋዊ-ምክንያታዊ እና ግርማ-ሞገሳዊ (charismatic) ናቸው። የመጀመያዎቹ ሁለቱ በከፍተኛ መጠን ይበልጥ የተለመዱ ሲሆኑ ከጥቅል የዘመናዊነት መነሳት ምልከታውና ከምክነያ (Rationalization) ገለፃው ማዕከል ጋር ይጣጣማሉ። ባህላዊ (Traditional) ሥልጣን በባህል

የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

ባህላዊ፣ ሕጋዊ-ምክንያታዊ፣ ግርማ-ሞገሳዊ ሥልጣን ማክስ ዌበር /1864-1920/

ቅዱስነት እሳቤ ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን በቅድመ ዘመናዊ ህብረተሰብ ዘንድ የበላይነት ነበረው። ሕጋዊ-ምክንያታዊ ሥልጣን በሕግ በሚሰጥ ሥልጣን ላይ እና ህብረተሰብ በሕግ አማካኝነት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ይደራጃል በሚለው እሳቤ ላይ መሠረት ያደረገ ነው። ይህም ከቢሮክራሲ ጋር በቅርበት የተዛመደ ሲሆን ለመዘናዊነት ማዕከል የሆነው ከአጠቃላዩ የምክኑያዊነት መነሳት ጋር ይጣመራል። ግርማ ሞገስ ላደረበት መሪ በመሰጠት ላይ መሠረት የሚያደርገው ግርማ-ሞገሳዊ ሥልጣን በይበልጥ አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው፤ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ ሊከሰትና የተቀሩትን ሁለቱን ቆርጦ ሊጥላቸው ይችላል። በአዳዲስ እሴቶች ስም ግርማ-ሞገሳዊ መሪ ባህልን የሚገለብጥ ለውጥ ሊያሰርፅ ይችላል፤ በሌላ በኩል የሕጋዊ-ምክንያታዊ አደረጃጀት ቁልፍ ክፍሎችንም ሊያስቀር ይችላል።

ይህ ነበር የማህበራዊ ዓለም እና የታሪካዊ እድገቱ የዌበር ‹‹ሰይንሳዊ›› ምስል። እንደ የግል ምርጫው ከሳይንሳዊ ህይወቱ በአፅንኦት ለመነጠል ይጥርባቸው ስለበሩት በጥልቅ ስሜት ስለተገለፁት ሞራላዊ እና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነቶቹ ማመላከቻ ያስቀምጣል።

ከእሴት ነፃ ለሆነ ማህበራዊ ሳይንስ የሚተጋው የሳይንቲስትነት ሙያው ለእርሱ በግሉ እጅግ አስፈላጊው ነበር። በተመሳሳይ ሰዓትም ለጀርመን የብሔረተኝነት ዓላማ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ነበረው፤ ምንም እንኳን በየትኛውም የፅንፈኛ ብሔረተኛ ዓይነት ባይመደብም። ሁሉም ጀርመኖች የአንድ አገር አባላት በመሆናቸው አስፈላጊነት ላይ የሚይዘው እምነት የለም፣ እንዲሀም በጀርመኖችም ሆነ በባህላቸው ተፈጥሯዊ የበላይነት አያምንም፤ ነገር ግን እንደ ሌሎች ባህሎች ሁሉ የጀርመንም ባህል ምትክ የለሽ መሆኑንና ይህንንም (ባህሉንም) ለማስጠበቅ (ለመከላከል) መንግስት ማዕከላዊ ኃላፊነት እንዳለበት ያምናል። በተጨማሪም ጀርመን በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጧ እና በታሪኳ ምክንያት በዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ዋነኛ ሚና የመጫወት እድል የገጠማት እንደነበርም ያምናል። ብሔረተኝነት ሃይማኖትን ለመተካት የተሻለ እድል ያለው አማራጭ ነበር፤ ምክንያቱም ይሞትለት ዘንድ የማይቆጭ ዓላማን በማቅረብ ረገድ በትርጉም የለሽ ዓለም ውስጥ ትርጉም ያለው ሞትን ሊያቀርብ ይችላልና።

ዌበር ከሁሉም በላይ የኒቼ ተጠራጣሪነት እና ፀለምተኝነት ተፅዕኖ ያደረበት ሊበራል ነበር፤ በርግጥ ያልተለመደው ዓይነት ሊበራል ነበር። ዌበር ለማንኛውም የእሴቶች ወይም የሥነ-ምግባር ሥርዓት ምንም ዓይነት ምክንያታዊ መሠረት ባለመኖሩ እንደሚያምን ተመልክተናል፤ ነገር ግን የሊበራል እምነት ማዕከላዊ ክፍል ሆኖ በቆየው (ለብዙዎች እስካሁንም ማዕከላዊ ነው) ሀሳብ ላይ ጭምር ጥልቅ ጥርጣሬ ነበረው። ይኸውም ሙሉ ለሙሉ ምክንያታዊ ወደሆነ ዓለም የማደግ (የመሻሻል) እሳቤ ነው። እርግጥ ነው፣ ዌበር የምዕራቡን ሥልጣኔ በማሽቆልቆል ላይ እንደሆነ አድርጎ ወደመመልከት አዘምሟል።

ከመቼውም በላይ ምክንያታዊ የሆነ የዓለም አምሳል (ideal) ከአብርሆት (Enlightenment) ዘመን አንስቶ ማዕከላዊ የሊበራል አምሳል ሆኖ ቆይቶ የነበረ ይሁን እንጂ፣ ዌበር የምክነያን (rationalization) የእድገት ሂደት በሰው ዘር ላይ ከወረደ እርግማ በመጠኑ የተሻለ አድርጎ ነበር የሚመለከተው።

ከምንጊዜውም በላይ ዝርዘር የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀት ሰዎችን ነፃነታቸውን በሚገድበው እና ግለሰባዊነታቸውን በሚያደቅቀው መጠነ-ሰፊ የማህበረ-ኢኮኖሚክ ማሽን ውስጥ ወደሚገኝ አሽከርካሪ ጥርስነት አሳንሷቸዋል። ይህንንም ዌበር ‹‹የብረት አጥር›› እና (ከማህበራዊ ዋስትና አቅራቢ መንግስት እድገት ጋር በተያያዘ) ‹‹አዲሱ ባርነት›› በመሳሰሉ ጥቋቁር ሀረጎች ገልጾታል።

ለዌበር፣ ነፃነት እና ግለሰባዊነት ፍፁም የሆኑ እሴቶች ነበሩ። ኢማኑኤል ካንትን በመከተልም፣ ዌበር ሰብዓዊ ክብር እና ሰብዓዊ ዋጋ ከሰው ልጅ ሞራላዊ እሴቶችን ከመመረጥና እነሱን ተከትሎ ከመኖር ብቃት ጋር የተሳሰሩ እንደሆኑ ያምናል። የኖርማቲቭ ፖለቲካ ፈላስፋ እንደመሆኑም፣ ዌበር ሰብዓዊ ነፃነት እና ግለሰባዊነት በአንድ የጥላቻ ዓለም ውስጥ እንዴት ሊጠበቁ ይችላሉ በሚለው ጥያቄ ተጠምዶ ነበር። በካፒታሊዝም አልነበረም የሚጠበቁት፤ ምክንያቱም (ቢያንስ ይበልጥ አብላጫ ቁጥር ላለው ወገን) ካፒታሊዝም የችግሩ አካል ነበር።

ኒቼያዊ ፀለምተኝነቱ ቢኖርም፣ ዌበር የተወሰኑ ተስፋ ሰጪ አማራጮችንም አስሶ ነበር፤ በተለይ ከጀርመን ፖለቲካ ጋር በተያያዘ። የሚያቀርባቸው ምላሾችም የፓርላማ ዲሞክራሲን በመደገፉ ላይ የሚመረኮዙ ናቸው፤ የፓርላማ ዲሞክራሲን መደገፉ ለተለመዱት የሊበራል ምክንያቶች ሲል ባይሆንም። የፓርላማ

ዲሞክራሲ ማለቱ ሕዝቦች እራሳቸውን በራሳቸው ከመግዛት (ከመግዛት) አንፃር አልነበረም፤ ምክንያቱም በመሠረታዊ መልኩ ሁሌም ቢሆን የሚገዙት ልሂቃን ከመሆናቸው ረገድ ያ ልብ ወለድ ነበር። የፓርላማ ዲሞክራሲ መምጣት በትክክልም በልሂቃን መካከል በሚደረግ ትግል ላይ መሠረት ይጥላል፤ ይህም የሁለት አስፈላጊ ውጤቶችን መፈጠር ያስከትላል፡- የፖለቲካ መደብ እና ግርማ-ሞገሳዊ መሪዎች ሁለቱ ውጤቶች ናቸው።

የቢስማርክ አገዛዝ ጀርመንን ያለጠንካራ የፖለቲካ መደብ እንዳስቀራት ዌበር ያምናል። የፖለቲካ ሥልጣን በንጉሰ ነገስቱ እና በቢሮክራሲ እጅ ላይ የወደቀ ሲሆን ሁለቱም ቢሆኑ ለመግዛት ብቁ አልነበሩም። ውጤቱም መጥፎ የውሳኔ አሰጣጥ ከመሆኑም በለይ በዓለም ጉዳዮች ላይ የጀርመንን ትክከለኛ ቦታ በማስጠበቁ ረገድ ተከታይ ሽንፈቶችን አምጥቷል። በአንፃሩ እንግሊዝ ዌበር እጅጉን የሚያደንቀው ዲሞክራሲያዊ ወይም ከፊል-ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ነበራት። ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ገዥ መደብ ከመያዙ ባሻገር፣ እንደ ግላድስቶን እና ሊዮድ ጆርጅ የመሳሰሉ ግርማ-ሞገሳዊ መሪዎችንም አሳይቷል። የፓርላማ ዲሞክራሲ፣ አገር የሚዋሀድበት ወይም አንድ የሚሆንበት ብቻ ሳይሆን የምክንያታዊ-ሕጋዊ መንግስት እና የግርማ-ሞገሳዊ የፖለቲካ አመራር ተቀባይነት ያለው ጥምረት መፍጠሪያ መንገድ (ዘዴ) ሊሆንም ይችላል፤ ይህም ለዘመናዊ ምክኑያዊ ህብረተሰብ የተዳከመ መጣጣም ፈውስ ሊሆን የሚችል ነው። በዚህም የተነሳ ለግለሰባዊ ነፃነት እና ፈጠራ የመጠበቅ እድሉ ሊፈጠር ይችላል።

ዌበር ቢሮክራሲ እና ግርማ-ሞገሳዊ አመራር የዋልታዎች ያህል ተቃራኒ እንደሆኑ ተመልክቷል። ምናልባት የሁለቱ ውህደት የአደረጃጀት ግዙፉ ተሽከርካሪ ሁሉንም ከመጨፍለቁ በፊት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ይዞ ሊያቆየው ይችላል። ይሁንና ግን የዌበር መፍትሔ ከአሳማኝት ያነሰ

ይመስላል። ግርማ-ሞገሳዊ አመራር በተፈጥሮው የአጭር ጊዜ ክስተት ሲሆን ሊያድግ ወይም ሊየንሰራራ በመቻሉ ላይ የትኛውም ሥርዓት ዋስትና ሊሰጠው አይችልም። ከሁሉም በላይ ግርማ-ሞገሳዊ አመራሩ ወዴት ይመራል ከሚለው ይልቅ የግርማ-ሞገሳዊ አመራር መኖር ለዌበር ይበልጥ ወሳኙ ነገር ይመስላል። ዌበር ናዚዎችንና የቆሙላቸውን ዓላዎች ሀሉ የሚጠላ እንደነበር ጥርጥር የለውም (ሌላው ቢቀር እንኳን የፀረ-ሴሚቲዝም ጠንካራ ተቃዋሚ ነበር)፤ ያም ሆኖ ግን በዘመናዊው ዘመን ለግርማ-ሞገሳዊ አመራር ይበልጥ ትክክለኛ የሆነ ምሳሌ ከአዶልፍ ሂትለር ውጪ ማሰብ ከባድ ነው።

ሆኖም ዌበር እንደመነሻ ያስቀመጠው ችግር እጅግ ሌጣ እና ከእውነታም የራቀ ሳይሆን አይቀርም። እየኖርን ያለነው ሁሉም ነገር አስከመጨረሻው ድረስ ዝርዝር አደረጃጀት ባለው ህብረተሰብ ወስጥ አይደለም፤ ግለሰባዊነት በሚጎለብትበት ህብረተሰብ ውስጥ እንጂ - ዌበር ይመለከተው ዘንድ ባልተቻለው የ ድ ህ ረ - ኢ ን ዱ ስ ት ሪ ያ ሊ ስ ት ‹በአግባቡ ያለተደራጀ ካፒታሊዝም› ውስጥ። አደጋዎቹ በይበልጥ የሚመረኮዙት ለፍጡራዊ ምቾቶች እና ለብዙሃነ መዝናኛዎች ባለን የኮንሲዩመሪስት ገደብ የለሽ ምኞት (ፍቅር)፣ እንዲሁም እነዚህ ሊጭኑት በሚያዘምሙት ባህልን የመከተል ሁኔታ ላይ ነው።

የዌበር ትንበያዎችም ሆነ ጥቆማዎች ላይ የቱንም ያህል ድክመት ሊኖራቸው ቢችልም፣ ዘመናዊው ዓለምን የሚመለከት ትንታኔው በከፍተኛ መጠን ተፅዕኖ አሳዳሪ ሆኖ ቆይቷል። ፍርሃተ-ቢሮክራሲ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ፅንሰ-ሀሳቦች፣ እንዲሁም ትግበራዎች ላይ ጥላውን አሳርፏል። ይህም እንደ ኦክሾት ከመሳሰሉ ወግ-አጥባቂዎች አንስቶ እንደ ሀይክ እስከመሳሰሉት ኒው ራይት ሊበራሎች ድረስ፣ እንዲሁም እንደ ማርከስ እና ዘ-ፍራንክፈርት ስኩል እስከመሳሰሉ አብዩታዊ ማርክሲስቶች ድረስ መታየት ችሏል።

ዌበር ናዚዎችንና የቆሙላቸውን ዓላዎች ሀሉ

የሚጠላ እንደነበር ጥርጥር የለውም (ሌላው ቢቀር እንኳን

የፀረ-ሴሚቲዝም ጠንካራ ተቃዋሚ ነበር)፤ ያም ሆኖ ግን

በዘመናዊው ዘመን ለግርማ-ሞገሳዊ አመራር ይበልጥ ትክክለኛ

የሆነ ምሳሌ ከአዶልፍ ሂትለር ውጪ ማሰብ ከባድ ነው።

ሐዘናችንን ለተጋራችሁን እናመሰግናለንየትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ ዋና ሊቀመንበር የነበሩት ሐጅ ጀማል አብዱ

ግንቦት 7 ቀን 2003 ዓ.ም ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተነሳ የሐዘናቸው ተካፋይ ለሆኑት፤ የብሔረሰቡ አባላት፣ የፓርቲው ደጋፊዎች፣ የሐጅ ጀማል አብዱ ወዳጆች፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ አመራሮችና ለኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ፓርቲው ምስጋናውን ያቀርባል።

ሐጅ ጀማል አብዱ በ1928 ዓ.ም ከአባታቸው ከባላምባራስ አብዱ አግደው እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘምዘም ሼህ አደም በቀድሞ፣ ባሌ ጠቅላይ ግዛት ጎሮ ወረዳ ልዩ ስሙ አስንበሬራ በሚባል ስፍራ ነበር የተወለዱት። በልጅነት ዘመናቸው ፈጣንና ንቁ አዕምሮ የነበራቸው ሐጅ ጅማል አብዱ፣ ከአካባቢያቸው የሃይማኖት አባቶች ታዋቂ በነበሩት ሐጅ ኢብራሒም ትግሪ መሠረታዊ የዲን ትምህርት ተምረዋል። ዘመናዊውን ትምህርትም በአዳማ ከተማ እስከ 2ኛ ደረጃ ድረስ ተከታትለዋል።

በወጣነት ዘመናቸው በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት፣ ሀብሮ ወረዳ በአጥቢያ ዳኝነት ከ1959 እስከ 1964 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል። ከ1964 እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በሸዋ ክ/ሀገር የረርና ከረዮ አውራጃ በሸሪያ ፍርድ ቤት ዳኝነት እና በሐጅና ዑምራ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ለአገራቸው አገልግለዋል።

ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ደግሞ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲን ከምስረታው ጀምሮ በሊቀ መንበርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

በአፄ ኃ/ስላሴ እና በደርግ ዘመነ መንግስታት ለትግሪ ወረጂ ብሔረሰብ መብት ሲታገሉ የቆዩት ሐጅ ጀማል አብዱ ለ20 ዓመታት ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አብሮ በመስራት ለብሔረሰቡ ሕልውናና የማንነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት በትጋት ሲሰሩ መቆየታቸውን ፓርቲው ይገልፃል።

ሆኖም ሲያስጨንቃቸውና ሲያሳስባቸው የነበረው የብሔረሰቡ በፌዴሬሽን ም/ቤት እውቅናና የተጠሪነት ወንበር ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ነበር በተወለዱ በ75 ዓመታቸው ያረፉት።

በመሪያችን ሞት ምክንያት የደረሰብንን ሐዘን ለተጋራችሁን በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም ለትግል ጓዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

የት.ወ.ብ.ዲ.አ.ፓርቲ

Page 7: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

ሰ ሞ ን ኛአንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው››

ሲል ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

በወጋየሁ

እንደ መነሻ“የታህሳስ መንፈስበግንቦት ሲመለስእንዲህ ነው መታመስእንዲህ ነው ማስቀየስ” - የአራዳ ልጆች

መቼም የአራዳ ልጆች ልብ ብሎ ላዳመጣቸው እንደ “እረኞች” ናቸው፡፡ የሆነውን አስተውለው፣ የሚባለውን አመዛዝነው፣ የማህበረሰቡን አመለካከት የሚገልፁበት መላ አያጡም፡፡ እናላችሁ!… በታሪክ የዱሮ ነገስታቶች “እረኛ ምን አለ?” ብለው መረጃ እንደሚያሰባስቡ ሁሉ፣ እኔም “የአራዳ ልጆች ምን አሉ?” ብዬ ጆሮዬን ብሰጣቸው ታህሳስን ከግንቦት ጋር ያለግጥሙ ሲጋጥሙት ሰማሁ፡፡ ሰማሁ፣ ሰማሁና የሰማሁትን ላሰማዎ ወደድሁ፡፡

ይኸውልዎ… የአራዳ ልጆች እንደሚያስታውሱት እየተባባሰ የሄደውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር መንግስት መሰረታዊ ፍጆታ ናቸው ያላቸው ሸቀጦች ላይ ቁርጥ የዋጋ ተመን ማውጣቱን ይፋ ያደረገው በታህሳስ ወር ነው፡፡

ትዝ ይልዎ እንደሆን በታህሳስ ወር በሀገሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው የተባሉ ነጋዴዎች ጠ/ሚኒስትር መለስ በተገኙበት፣ እዚያው እሳቸው ፅ/ቤት ድረስ በክብር ተጠርተው የወጣውን ቁርጥ የዋጋ ተመን በቁርጠኝነት እንዲያከብሩ ተነግሯቸው ነበር፡፡

ታዲያ ያኔ ምን ሆነ?ቁርጥ ተመን ቁርጥ ነው

ብለን ጮማ እያማረጥን ቆረጥን፡፡ ሻኛ ከሽንጥ አገላበጥን፡፡ ምላስ ከሰምበር ዶለትን፤ አስዶለትን፡

፡ ይኼኔ ምን ሆነ? ነጋዴዎች አፈጠጡብን፡፡ ምን ማፍጠጥ ብቻ አጉረጠረጡብን፡፡ እኛ ግን ምን-ተዳችን፣ የቆራጡን መንግስታችንን ቁርጠኝነት አምነን ቁርጡን የተመን ገበታ እየወዘወዝን “ከእንግዲህ አንፈራም፤ ሜኑ በእጃትን ነው” አልን፡፡ ብለንም አስባልን፡፡ አስብለን፣ አስብለን፣ አስብለን ሳናበቃ፣ ሊያውም በመንፈቁ፣ ሊያውም በግንቦት ወር የዋጋ ትመናው ወደ ኋላ ተመልሶ፣ እንደግንቦት ፀሐይ አናታችንን ይበጠብጠን ገባ አሉ፡፡ ያሉት የአራዳ ልጆች ናቸው፡፡ (ለነገሩ ለጨዋታው እንጂ በተለይ በስጋው በኩል ለመቆራረጥ ድርስ የሆኑ ቆራጮችም ገጥመውን፣ እኛም ‹‹ምርጫ እንኳን አሁን በ2002ም ለወጉ ነበር ብለን›› የመረጡልንን እየበላን ነበር አሰነባበታችን፡፡)

ይኼኔ ታዲያ ምን ሆነ?”

አሉ የተባሉት ክቡራን ነጋዴዎች ሽንጣቸውንም ሻንጣቸውንም እያገላበጡ “ሜኑ አለን ያላችሁ፣ እስቲ እንያችሁ” እያሉ ይዘፍኑብን ገቡ፡፡ እናም የአራዳ ልጆች ይህንን ታዝበውና አስተውለው፣ “የታህሳስ መንፈስ፣ በግንቦት ሲመለስ” ሲሉ ተቀኙ፡፡ ምን መቀኘት ብቻ፣ ከዚያም ድንበር

አልፈው “የታህሳሱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ቁርጥ ተመን፣ በግንቦት ተቀለበሰ” ሲሉ ሰማሁ፡፡

ወዳጄ፤ እኔ ሰሞነኛ አገልጋይዎ እንዲህ ዓይነቱ ፌዝ አይዋጥልኝምና “በግንቦት ወር የተነሳውን የዋጋ ተመን የታህስስ ግርግር ከተባለው ግርግር ጋር ልታመሳስሉት ከሆነ ተሳስታችኋል” ብዬ ልገዳደራቸው ብሞክር፣ ቡራዩ አካባቢ ሳሙና ፋብሪካ ውስጥ ተሸሸጎ የተያዘውን 106 ሺህ ሊትር ዘይት እያሳዩኝ ሳቁብኝ፡፡ ምን መሳቅ ብቻ፣ “አብዮታዊ ዲሞክራሲ የፈጠራቸው ባለሀብቶች እንዲህ ናቸው” እያሉ አሳቀቁኝ፡፡

የምር ግን ጎበዝ! ይኼ ነገር እንዴት ነው? በሺህ የሚቆጠሩ ባለ 20 ሊትር ጀሪካኖች አንድ ኳስ ሜዳ በሚያክል ሳሙና ፋብሪካ ነው በተባለ አዳራሽ ውስጥ የተጠቀጠቀው ከባለ ስልጣናቶች ይሁንታ ውጪ ነው?... እንደው እያንዳንዱ ጄሪካን እየተቆጠረ ሲገባና እንደዝቋላ ተራራ ሲከመር ያየም የሰማም የለም? ምነው እንኳን ጠ/ሚኒስትራችን ‹‹መንግስት የሚሰማ ጆሮ፣ የሚያይ ዓይን አለው›› አላሉንም ነበር? ግዴሎትም አንድ ችግርማ አለ! እንዲያውም አንድ ዘይት ናፋቂ ወዳጄ በዚህ ጉዳይ ሲያፋጥጠኝ

ጊዜ፣ ‹‹ጠ/ሚኒስትሩማ አይዋሹም›› በማለት መለስኩለት፡፡ እርሱም ምን አለኝ መሰልዎት፣ ‹‹ልክ ነው፣ እርሳቸውማ አይዋሹም፤ ምን አስጨንቋቸው ይዋሻሉ፤ የሚዋሽስ እውነት የጨነቀው ነው፡፡›› ምን ለማለት እንደፈለገ እያንሰላሰልኩኝ ሳለ ንግግሩን ቀጠለ፡፡ ‹‹ለስንት አባወራ አስቤዛ የሚበቃ ዘይት ከጂቡቲ አዲስ አበባ ተጭኖ እስኪገባም፣ ከገባም በኋላ ቤተሰቦቻቸው የዘይት ያለህ በሚሉ የቀን ሠራተኞች ወርዶ እስኪከመር አንዲት ነገር ያልሰማ፣ ያላየ መንግስት ከአንገት በላይ ህክምና አያስፈልገውም ትላለህ? ወይስ የመንግስት ዓይንና ጆሮ ነጭ ለባሾች ላይ ተተክሎ ቀርቶ ነው?››

እኔም አልኩኝ፣ ‹‹እባክህ ለዚህ ጥያቄ ከእኔ መልስ እንዳትጠብቅ፤ ዝርዝር የለኝም፡፡››

እውነት ግን ነገሩ እኮ አስገራሚ ነው፡፡ ዛሬስ ማንም ሳያየው የገባው ዘይት ነው፤ ሊያውም የምግብ፤ ጥቅም እንጂ ጉዳት የሌለው፡፡ ታዲያ ነገ አንዳች አስፈሪ ነገር ሰተት ብሎ ቢገባ የማን አለ ልንል ነው? ወዳጄ እባክዎትን ‹‹ያን ጊዜ ከአንገት በላይ ህክምናው ያልቃል›› እንዳይሉኝና በሳቅ እንዳያስሞቱኝ፡፡

እንዲያ ከእነሱ

ይሁንታና እውቅና ውጪ ከሆነ ከሆነ እኮ ምኑን አለነው? የለንም! እንዳለን አይቆጠርም፡፡ በዚህ በዚህ ዓይነትማ… ወላ ሳሙና ፋብሪካ ነሽ፣ ወላ ምን ፋብሪካ ተብዬ ሁሉ፣ ስሙ እንጂ ግብሩ ዓይናችን ስር አየር በአየር ንግድ ማካሄድ ነው ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ጫካ ውስጥ ተደብቀው የሕዝብን ደም እየመጠጡ የሚኖሩ ባለሀብቶች ቁጥራቸው ስንት ይሆን?

“በህዝብ ጫካ ውስጥ የተደበቁ” ስል ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ? የዛሬ ሳምንት አካባቢ ጠ/ሚኒስትሩ ከእነዚሁ ነጋዴዎች ጋር ባደረጉት ውይይት “በሕዝብ ጫካ ውስጥ የሚገቡትን የመንግስት (የእኛን) ሌቦች” ብለው የተናገሩት ትዝ አለኝ፡፡ እናልዎ!... እኔ ታማኝ አገልጋይዎ፤ ለዚህ በህቡዕ ገብቶ ለመሸገው ዘይት የእነሱ ሌቦች እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ጥርጣሬ ሽው አለኝ፡፡ እንደው እኮ የኔ ነገር በአራዳ ልጆች ትዝታ ተነስቼ ስተረተር፣ ሌላኛውን የታህሳስ-ግንቦት ግጥምጥሞሽ ረስቼው ቀርቼ ነበር፡፡ እንዴት ያለው ዝንጉ ነው እንደማይሉኝ ተሰፋ አድርጌ፣ እንደወረደ ላውጋዎ፡፡ ይኸውልዎ፡-

ነገሩ የሚያጠነጥነው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ዙሪያ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ነው የሚሰበሰበው፡፡ የአበውን ዶግማና ቀኖና መሰረት በማድረግ በዓመት ሁለት ጊዜ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ በተመክሮና በተዘክሮ የቤተክርቲያኒቱን ጉዳዮች መርምሮ፣ በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ መፍትሄ ያመላክታል፡፡ ውሳኔም ያሳልፋል፡፡ ታዲያልዎ በዚህ ዓመት ወርሃ

ታህሳስ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባካሄደው ስብሰባ ተከሰቱ የተባሉ ችግሮችን በጥሞና ከመረመረ በኋላ፣ በቦሌ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የቆመው የብፁዕ ወ-ቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ኃውልት እንዲፈርስ፣ በፓትርያሪኩና በጳጳሳት መሀከል አለመግባባት እንዲፈጠር አድርገዋል የተባሉት ሴትዮ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ቅፅር ግቢ ድርሽ እንዳይሉ የሚሉና ሌሎች ውሳኔዎችን አሳልፎ ነበር፡፡

ሲኖዶሱ ይህን መሰል ውሳኔዎችን ያሳልፍ እንጂ፣ ፊት ለፊት የሚታየው የፓትርያሪኩ ኃውልት አልፈረሰም፡፡ ፊት ለፊት የማይታየው የሲኖዶሱ ውሳኔ ምን ያህል ተፈፃሚ እንደሆነ የሚታወቅ ነገር አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ ሲኖዶሱ በቤተክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና መሰረት በግንቦት ወር መጀመሪያ የዓመቱን ሁለተኛ ጉባዔ ተቀምጦ ነበር፡፡

ታዲያላችሁ ሕዝበ-ክርስቲያን ሲኖዶሱ በታህሳሱ ጉባዔ ካሳለፈው ውሳኔ የትኛው ተፈፃሚ ሆነ? ያልተፈፀመውስ ለምን አልተፈፀምም? እያለ እየጠየቀ የቅዱሳን ጳጳሳቶችን መንፈሳዊ ምላሽ በሚጠባበቅበት ሰዓት አንዱ ጋዜጠኛ ሴትዮዋን ይዟቸው ብቅ አለላችኋ!... የቷን ሴትዮ አትሉኝም? ሲኖዶሱ በታህሳሱ ጉባዔ ድረሽ እንዳይሉ ብሎ ውሳኔ አሳልፎባቸዋል የተባሉትን ሴትዮ ከነፎቶአቸው ገጭ አድርጎ በመፅሔቱ ቃላቸውን ይዞ ወጣ፡፡

እናልዎ… ሴቲቱ (በነገራችን ላይ “ሴቲቱ” ወደማለት የዞርኩት ሴትየዋ ራሳቸው ለጋዜጠኛው በሰጡት ምላሽ “በእኔ እድሜ ያለች ሴት” ስላሉ እንጂ፣ እኔ ሰሞነኛ አገልጋይዎ የ66 ዓመት ባልቴት ለማሳነስ የምፈልግ ደፋር አይደለሁም)፤ እናልዎ ሴቲቱ ለጋዜጠኛው የሰጠችውን ቃል እያነበብኩ ተደንቅሁ፡፡ እውነቴን ነው የምልዎ!... የመደነቄን መጠን መደነቅ የሚለው ቃል እንኳ በወጉ

‹‹መንግስት የሚሰማ ጆሮ፣ የሚያይ ዓይን አለው›› ጠ/ሚኒስትሩ

‹‹መንግስት ከአንገት በላይ ሕክምና ያስፈልገዋል››

ዘይት ናፋቂዎች

በ ገፅ 15

Page 8: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 20038

አባ ከቤተ መቅደሱ‹‹ልጄ አትጠጣ›› ይሉኛል

ምሽት ስንገናኝሂሳቤን ይከፍሉልኛል

ሰሎሞን ሞገስ (እውነትን ሰቀሏት)

ዛሬ በዚህ ግጥም የተነሳሁት ያለምክንያት አይደለም። እኔ የሃይማኖቱ ተከታይ መሆኔና አለመሆኔ የዚህ አምድ አጀንዳ አይደለም። ይሁንና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ አንዳንደ ነገሮችን ለማንሳት አስቤ ነው።

መነሻ 1በአፍሪካ ደራሲያን ዓለም አቀፍ

ጉባኤ መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከቀረቡት ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች አንዱ ያሬዳዊ ዝማሬ እና ወረብ ነበር። ይህንን ዝግጅት ከታደሙት የምዕራብ አፍሪካ ደራሲያን አንደኛው የደስታ ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት ስሜት እንቅ፣ እንቅ እያደረገው ‹‹ይች ሀገር እናታችን ናት›› የሚል ነገር ነገረኝ። የበለጠ አልጠየቅሁትም። ነፍሱ ከፍ ባለ ትፍስህት ውስጥ እንደነበረች አይቻለሁና። ሰማያዊ የሆነው ያሬዳዊ ዝማሬ ይህንን ያክል እንደሚመስጣቸው እኔ አስበው ነበርና!

መነሻ 2ሰሞኑን ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ

ወደ ጎፋ ገብርኤል አካባቢ ሄጄ ነበር። ቡና ተፈልቶ ከጎረቤቶች ጋር ስንጨዋወት አንዲት ምስኪን እናት መቶ ብር (ለቄሶች?) መክፈል ባለመቻሏ አርባ ቀን የሞላው ወንድ ልጇን ክርስትና ማስነሳት እንዳልቻለች ሰማሁ።

ይህች እናት በቀን ሥራ ነው የምትተዳደረው። አሁን ልጇን ማሳደግ አለባት። ወተት መግዛት፣ ልብስ መግዛት፤ ምናልባትም ሕክምና ክትትል ማድረግ። ብሎም

ጥያቄ፡- ብዙ ሰዎች ጥፋት ካጠፉ በኋላ፣ ‹‹ሰይጣን አሳስቶኝ ነው›› ይላሉ። በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለህ?ሰይጣን፡- ማንኪያ ሲወድቅም፣ ማማሰያ ሲሰበርም ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ማለት ተገቢ አይደለም። ጥያቄ፡- ሚሽንህን (ተልዕኮህን) ለማሳካት እባብን እንደመሳርያነት የተጠቀምከው ለምንድን ነው?ሰይጣን፡- መቼም አንበሳና ዝሆንን ብጠቀም ሔዋን በርግጋ ትጠፋ ነበር። አላማዬም ይከሽፍ ነበር። እባብ ግን ቆዳው ስለሚያብረቀርቅ ይስባል። በዛ ላይ ያኔ እግር ስለነበረው አካሔዱ ያምር ነበር።ጥያቄ፡- ሔዋንንና ያሁን ጊዜ ሴቶችን እንዴት ታነፃፅራቸዋለህ?ሰይጣን፡- ሔዋን የመጀመርያዋ ሴት እንደመሆኗ የየትኛውም ሀገር ፖሊሲ ተፅዕኖ አልነበረባትም። ያ ደግሞ የራሷን ቆራጥ ውሳኔ እንድትወስን ረድቷታል። በአሁን ጊዜ ያሉት ሴቶች ግን ብዙ ዓይነት አስተሳሰቦችን ስለሚሰሙ፣ የትኛውን ተቀብለው ምን መወሰን እንዳለባቸው ትንሽ የሚቸገሩ ይመስለኛል። ይኼ ነው ልዩነታቸው።ጥያቄ፡- ምሳሌ ብትጠቅስልኝ? ሰይጣን፡- ለምሳሌ ከባሏ ጋር የተጣላችን ሴት እንውሰድ። በቀኝ ያለችው ጎረቤቷ መጥታ እንዳትታረቅ ትመክራታለች። በግራ በኩል የሚገኘው ጎረቤቷ ደግሞ እንድትታረቅ ይጎተጉታታል። ይቺ ሴት መሐል አጣብቂኝ ውስጥ ገብታ የራሷን ውሳኔ ለመወሰን ትቸገራለች። የማንን ምክር ተግባራዊ እንደምታደርግ ግራ ይገባታል። በዚህም ምክንያት ቆራጥና የማያዳግም ውሳኔ መወሰን ያቅታታል። ሔዋን ግን በለሱን እንድትበላ ስትጠየቅ አላንገራገረችም። በወቅቱ ደግሞ መካሪ ጎረቤት አሊያም ዘመድ አዝማድ፣ ወይም ደግሞ የተለያዩ ለውሳኔ ሰጪነት የሚያበቁ

ኮሜንተሪ

መፅሐፎች ስላልነበሯት በራሷ ልትወሰን ችላለች።ጥያቄ፡- በእነሔዋን ላይ ሞት ልታመጣባቸው ስታቅድ መጀመርያ የሄድከው ወደሔዋን ነው። ወደአዳም ያልሄድከው ወንድ ስለሆነ ፈርተኸው ነው? ወይስ ቅድሚያ ለሴት ብለህ ነው? ሰይጣን፡- በነገራችን ላይ ቅድሚያ ለሴቶች የሚባለው ነገር የተመሰረተው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ነው። ያኔ የወንድም ሆነ የሴቶች የበላይነት አልነበረም። በቃ ዝም ብሎ መኖር ነበር። ወደ ሔዋን የሄድኩት የተለየ ነገር ኖሮኝ ሳይሆን ቅድሚያ ስላገኘኋት ነው። ጥያቄ፡- አብዮተኛ ነህ? ሰይጣን፡- ተመሳሳይ ነገሮችን አልወድም። ነገሮችን መመርመር ያስደስተኛል። በሰማይ ቤት ያስነሳሁት አብዮት በ1966 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈነዳው አብዮት ተለይቶ መታየት የለበትም። የ66ቱ አብዮት ንጉሡን ለማውረድ ነበር፤ የሰማይ ቤቱም እንደዛው ነው። ጥያቄ፡- ያኔ ካንተ ጋር በሰማይ ላይ የትጥቅ ትግል ካካሄዱ መላዕክት ጋር አሁን ያለህ ግንኙት ምን ይመስላል?ሰይጣን፡- ዛሬ መቅደስ ተገንብቶላቸው በስማቸው ከሚመፀወት መላዕክት ጋር በፍቅር ነበር የምንኖረው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተፈጠረ መከፋፈል በሀሳብ ልንለያይ ችለናል። አሁን ያለንበትን ሁኔታ ማንም ያውቀዋል። እኔ በበኩሌ ከነልዩነቴ መኖር ነው የምፈልገው፤ የእነሱን ባላውቅም።ጥያቄ፡- ኢየሱስ አሁን ወደ ምድር ቢመጣ ልክ እንደይሁዳ በ30 ብርም ባይሆን ከዛ ከፍ ባለ ዋጋ አሊያም በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጠው ሰው ይኖራል ብለህ ታስባለህ?ሰይጣን፡- ምን ነካህ? የዓለም ኢኮኖሚ ባልተቃወሰበት በዚያ ዘመን በ30 ብር የሚሸጥ ከተገኘ፣ ዛሬም በዚህ በችጋራም ዘመን የሚሸጠው ይጠፋል ብዬ

አልደመድምም። በቀን አንዴ በልቶ ማደር ባቃተው ኅብረተሰብ ውስጥ ተረፈ ይሁዳዎች የሉም ለማለት አልደፍርም። የኑሮ ሰቀቀን ያጠራቀሙትን ጥሪት ቀርቶ ሌላም ነገር ያሸጣል። ኢየሱስም በሚሸጠው ሰው የሚያዝን አይመስለኝም፤ ምክንያቱም በረሀብ ከመሞት በመሳሪያ መሞት ይሻላል የሚል ጥቅስ የራሱ የኢየሱስ መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል እኮ። ለነገሩ እሱ ዳግም የሚመጣው ለመሸጥና ነፃ ገበያን በራሱ ላይ ለማስፋፋት ሳይሆን የድርሻውን ነፍሳት ሊወስድና የድርሻዬን ነፍሳት ሊሰጠኝ ነው።ጥያቄ፡- ማለት?ሰይጣን፡- መቼም ኢየሱስ ሁሉንም የሰው ዘር ወደገነት ያስገባል ብዬ አልገምትም። ጥያቄ፡- ሲኦል የሚባል የእሳት

ክምር ለመኖሩ ማረጋገጫው ምንድን ነው?

ሰይጣን፡- በእርግጥ አንዳንዶች የለም ብለው ያምናሉ፤ ሌሎችም አለ ይላሉ። በነገራችን ላይ ሲኦል የሚባል ነገር አለ፤ እሳት ውስጥ ትገባላችሁ ብሎ የተናገረው የሰይጣናት መፅሐፍ አይደለም እኮ። ስልህ እኔ ምንም ልልህ የምችለው ነገር የለም።ጥያቄ፡- ታዲያ ኢየሱሰ የድርሻህን ነፍሳት ሲሰጥ፣ ነፍሳቶቹን የትነው ይዘሃቸው የምትሔደው?ሰይጣን፡- ለወንበዴና ለቀማኛ ማጎሪያ ጭለማ ቦታ ይጠፋል ብለህ ነው?ጥያቄ፡- እኮ ያ ማጎሪያ ቦታ ሲኦል አይደለም?ሰይጣን፡- ልታወጣጣኝ መሆኑ ነው?ጥያቄ፡- አንተ ለመናገር ለምን ፈራህ? ወይስ ሲኦል መኖሩን ካንተ የሚያረጋግጡ ሰዎች ካንተ እንዳይርቁ ሰግተህ ነው?ሰይጣን፡- የቱንም ያህል ለምድ በመልካም ስራ ብትሞላ፣ ለኔ የሚሆን ነፍስ ስለማላጣ ቅንጣት

ታህል አልሰጋም።ጥያቄ፡- ስለ እሳት ያለህ አመለካከት ምንድን ነው?ሰይጣን፡- እሳት በሥርዓት ከተጠቀምክበት በጎ ነገር ነው። አፈንግጠህ በእሳት ልጫወት ካልክም ዋጋህን ታገኛለህ። እንጂ እሳትን በደፈናው ማንቋሸሽ ተገቢ አይደለም። ብዙ ሰዎች ስለኔ ሲያወሩ ከእሳት ጋር ያመሳስሉኛል። በእሳት እንደማቃጥላቸውም አብረው ያወራሉ። ነገር ግን እኔም እንደማንኛውም ሰው እሳትን በአግባቡ እጠቀምበታለሁ። በሕጉ መሰረት አፈንጋጭ ባህርይ ያላቸውን ሰዎች ለመቅጣት እንደ አለንጋ እገለገልበታለሁ።ጥያቄ፡- በምድር ላይ ከምታያቸውና ከምትሰማቸው ነገሮች የሚያስገርምህ የቱ ነው?ሰይጣን፡- ጥሩ ጥያቄ ነው። እህ ... ብዙውን ጊዜ የሃይማኖት ቦታዎችን እጎበኛለሁ። የሁሉንም ሃይማኖት ማለት ነው። ሰባኪ ተብዬዎቹ ናቸው የሚያስገርሙኝ። ሁል ጊዜ ስለኔ ደህና ነገር ሲያወሩ አለመስማቴ ያስገርመኛል። በተደጋጋሚ የሚወራው እኔ መጥፎ ብቻ እንደሆንኩ ተደርጎ ነው። በርግጥ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ጥሩ ቦታ እንደሌለኝ ባምንም፣ ምናልባት የደህናው ዘመን ታሪኬ ለኅብረተሰቡ ቢነገርና ሰው ሚዛናዊ ፍርድ ቢሰጠኝ እላለሁ ሁል ጊዜ።ጥያቄ፡- አስቸጋሪ የሚባል ፀባይ ያለው ነፍስ አጋጥሞህ ያውቃል? ሰይጣን፡- አስቸግራለሁ ቢል ማን ይሰማዋል? ለፖሊስና ለቤተሰብ አልያዝ አልጨበጥ ያለ ሰው (ነፍስ) እኔ ጋር ሲመጣ ቀጥ ለጥ ይላል።ጥያቄ፡- በምድር ላይ ጀግና የምትለው ሰው?ሰይጣን፡- (ፈጠን ብሎ) ሔዋን ነቻ! ሌላ ማን ይሆናል?ጥያቄ፡- በምን መስፈርት?ሰይጣን፡- የሚሉትን የሚሰማ፣ አድርግ የሚሉትን የሚያደርግ

ባጠቃለይ ትዕዛዝ አክባሪ ሰው ጀግና ነው ብዬ አስባለሁ። መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል ትሉ የለም እንዴ? ሔዋንም እኮ መታዘዝ ከመስዋዕት እንደሚበልጥ ስላወቀች ነው ያዘዝኳትን የፈፀመችው። በዚህም ምክንያት የዘላለም ጀግናዬ ብዬ መርጫታለሁ።ጥያቄ፡- ስለሔዋን ጥሩ አመለካከት ያለህ ይመሰላል። አዳምንስ እንዴት ነው የምትገልፀው?ሰይጣን፡- ባክህ ተወው እሱን።ጥያቄ፡- ምነው?ሰይጣን፡- ወግ አጥባቂ ነገር ነው። የሰጡትን አርፎ እንደመብላት ሌላ ዝባዝንኬ ውስጥ ይገባል።ጥያቄ፡- ኢየሱስ ስለዓለም ሲሰቀል አልደነገጥክም?ሰይጣን፡- ምን ያስደነግጠኛል?ጥያቄ፡- በእጅህ ያሉትን ነፍሳት ሊነጥቅህ ስለሆነ?ሰይጣን፡- አንተን ጨምሮ የሰው ልጆች ሞኝ ናችሁ ልበል እንዴ? እሺ ያኔ በእጄ የነበሩትን ነፍሳት ተረከበኝ ልበል። ታዲያ ዛሬ ባዶዬን የቀረሁ ይመስልሃል? ዛሬ ወደኔ የመጣ ምንም ነፍስ የለም? አየህ ሰው ቢሔድ ሰው ይመጣል።ጥያቄ፡- አሁን በእጅህ ከሚገኙት ነፍሳት ዝነኛ ግለሰቦች አሉበት?ሰይጣን፡- መቼም ዝነኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ ይሄዳሉ ተብሎ አይደመደምም።ጥያቄ፡- አብዛኛው ጊዜህን የምታሳልፈው በምንድን ነው?ሰይጣን፡- በማጋጨት።ጥያቄ፡- ምን በማጋጨት?ሰይጣን፡- መቼም የቢራ ጠርሙስ አልልህም። ጥያቄ፡- ዋና መቀመጫህን ያደረግከው የት ነው?ሰይጣን፡- በየትኛው ትርፍ ጊዜዬ ነው የምቅመጠው? መሯሯጥ እንጂ መጎለት አልወድም።ጥያቄ፡- ፖለቲካ ትወዳለህ?ሰይጣን፡- ታዲያ ስራዬ ፖለቲካ አይደል እንዴ? የራሴን አባልና

መደበኛ ወጭዎቿን - ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ - የቀን ሥራ እየሰራች መሸፈን አለባት።

ልጇን ከመንፈስ ቅዱስ ለማስወለድ ግን ድፍን መቶ ብር ተጠየቀች። መክፈል አልቻለችምና በቤተክርስቲያኒቷ ደምብ መሰረት አርባ ቀን የሞላው ልጇን ክርስትና ሳታስነሳ ቀረች። አቤቱ ጌታ ሆይ! የዚህች ምስኪን እናት ሐዘን ምን ያክል ይሆን?

መነሻዎቼን በልቤ ይዤ አብሰለስላቸው ነበር። ጊዜም ወስጃለሁ - በዚህ ጉዳይ መፃፍ ይገባኛል ወይስ አይገባኝም እያልኩ። ልብ በሉ! ይገባኛልና አይገባኝም ስል ሰሚ አገኛለሁ ወይስ አላገኝም ማለቴ እንጂ ባለ ጉዳይ ነኝ ወይስ አይደለሁም ለማለት አይደለም።

ዕምነታዊ የሆነውን ጉዳይ እናቆይና ስለሃይማኖት ከሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ብቻ ሳይሆን ለሙስሊሙ፣ ለፕሮቴስታንቱ፣ ለካቶሊኩ ብሎም ዕምነት አንፈልግም ለሚሉ ፈላስፎችም ቢሆን ጉዳያቸው መሆን ያለበት ይመስለኛል።

ከፍ ሲል እንዳልኩት ስለተዋህዶ ሃይማኖት ስናወራ ስለኢትዮጵያ ዝማሬ ዜማ፣ ፅህፈት፣ ወረብ፣ ነዋየ ቅዱሳት መጽሐፍት፣ ስዕላት ወዘተ ማውራታችን ነው። እነዚህ ኃብቶች ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የኢትዮጵያ መገለጫዎች እንደመሆናቸው ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንደሀገርም ጉዳይ እንደሀገራዊ ኃላፊነት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ያሬዳዊው ዝማሬ ነፍሳቸውን በደስታ ስለፈነቀለ ይመስለኛል ደራሲያኑ ስለቤተክርስቲያኒቷ ብቻ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ ያወሩት። ኢትዮጵያም እናታችን ትሁን የሚሉት የዚህ ኃብት ተቋዳሽ

መሆንን እንደመታደል ስለቆጠሩት ነው። ከዚህም ባሻገር በሥነ-ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ በሳይንስ፣ ሕክምና ጉዳዮች ዙሪያ የቤተክርስቲያኗ ቀደምት ታሪኮች በሙሉ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን መኩሪያ ስለሆኑ ነው።

መጽሐፈ ሄኖክ በዓለም ላይ በብቸኝነት ያለው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ይህም ማለት በአፍሪካ ማለት ነው። በዓለም የራሳቸው ፊደል ካሏቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ኢትዮጵያ ደግሞ አፍሪካዊት ናት። በዚህም ብቻ አይደለም። በስዕል ጥበብ፣ በፊደል፣ በቋንቋ፣ (ግዕዝ የመላዕክት ቃንቋ ነው፤ የሰው ልጅም የመጀመርያ ቋንቋ ነው የሚሉ ብዙ መጽሐፍትን አንብቤአለሁ) በሙዚቃ፣ በኪነ-ሕንፃ ወዘተ ቤተክርስቲያኗ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን እየወከለች በዓለም መድረክ ትቀርባለች።

ይህንንም በማስተዋል ይመስላለ ወይዘሮ ክሪስቲን ሻዮ የተባሉ ግሪካዊ፣ ‹‹The Ethiopian Orthodox Church Tradition›› በተባለ መጽሐፋቸው፣ ‹‹የሁለቱንም ፍፁም አንድነት ለማየት የኢትዮጵያን ታሪክ ማውራት የቤተክርስቲያንን ታሪክ ማውራት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያን ታሪክ ከቤተክርስቲያኗ ታሪክ አለያይቶ መናገር የማይሞከር ነው›› ይሉና ከጥንታዊነት የአክሱም መንግሥት ጀምሮ ያለውን ትስስር ይተነትናሉ።

በዚህ የተነሳ ነው ዛሬ በዚህ አምድ ላይ ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሳት የወደድኩት። እንደሀገር መታሰብ፣ እንደዜጋ መሳተፍ ያለብን ስለሚመስለኝ።

ቋንቋን፣ ማንነትን፣ ባህልን እና

ሥርዓትን በሙሉ ጠብቆ ለማቆየት ዜጎች በሥነ-ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ሁሉም ሃይማኖቶች ግዴታ እንዳለባቸው ይታወቃል። ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደግሞ ከሌሎች በበለጠ ግዴታውን መውሰድ ያለባት ይመስለኛል። ምክንያቱም ቋንቋን ጠብቆ ስለማኖር ከቤተክርስቲያኗ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ ምሁራን በላይ ስለቀደምት ሥነ-ጽሑፎቻችን የሚያውቅ ያለ አይመስለኝ።

ኢትዮጵያዊ ማንነትን ጠብቆ ስለማቆየት፣ ስለሰላምታ አሰጣጥ፣ ስለእንግዳ አቀባበል፣ ስለዘመን አቆጣጠር፣ ስለአመጋገብ፣ ስለአለባበስ ወዘተ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የበለጠውን ግዴታ መውሰድ ያለባቸው ይመስለኛል። ይህንን የምለው በቤተክርስቱያኒቱ ሥርዓት መሰረት የቤተክርስቲያኗ ጠባቂዎች የምዕመናን አባቶች እና ብዙዎቹ ሊቃውንት ባለአደራዎች ዓለምን ጥለው በመውጣት ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ነፍስ ተጠሪ ስለሚሆኑ ነው።

ዓለም በቅታቸው ከዓለም እሰጥ አገባ ሁሉ በምንኩስና የተገለለ ደግሞ ለታላቅና ለታናሽ ሳይል፣ ለሚያምንና ለማያምን ሳይል ኃላፊነት ተረክቦ ለአገር የሚበጅ ነገርን በውሉ መሥራት እንዳለበት ይሰማኛል። በዚህ ነጥብ እንደተስማማን ልገምትና አሁን ለቤተክርስቲያኗ የበላዮች ጥያቄ ማንሻዬ ጊዜ ደረሰ ልበል።

ሀዝሙት ቤቶች፣ መስከሪያ

ቤቶች፣ መጨፈሪያ ቤቶች ወዘተ እጅግ ተንሰራፍተው የሚገኙበት ይህ ዘመን እስኪመጣ ምን እያደረጋችሁ ነበር?

የእነዚህ ቤቶች መስፋፋት ‹‹እየጠበቅነው እዚህ ደርሰናል›› የሚባሉ በጎ ነገሮችን በሙሉ እየሸረሸረ እየሸረሸረ አገራችኝን የአጋንንት ሀገር እንደሚያደርጋት

አታውቁምን? ወይስ ይህንን ትውልድ ከቀሳፊ እኩይ ነገሮች የመታደግን ኃላፊነት ለማን ሰጣችሁት?

ዜጎች ሰላም ውለው ሰላም እንዲገቡ ተምሮ የሚጠቅም ሰርቶ የሚለወጥ፣ ተናግሮ የሚያረካ፣ ፅፎ የሚያስተምር በጠቅላላው ምሉዕ በጎ ስብዕና ያለው መልካም ዜጋ እንዲሆን ቤተክርስቲያኗ ምን እያደረገች ነው? እዚህ ላይ ለምዕመናን ትምህርትና ስብከተ ወንጌል እንደሚደረግ ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም። ከዚህ ጎን ለጎን ግን እንደ ሀገራዊ የሃይማኖት ኃላፊት መንግሥትን በመቀስቀስ፣ በማሳሰብ፣ በማነሳሳት ከላይ የዘረዘርኳቸው መልካም ያልሆኑ ልማዶች እንዲወገዱ ምን አደረጋችሁ ነው ጥያቄዬ።

ቀደምት አባቶቻችን የፈጠሯቸውንና የሰሯቸውን የኪነ-ጥበብ፣ የኪነ-ሕንፃ እና የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች እየጠቀሱ የቤተክርስቲያኗን አስተዋጽኦ ማስጠበቅ የሚቻል አይመስለኝም።

ዛሬ ከቤተክርስቲያን አጠገብ ሸቀጥና ንግድ ተስፋፍቷል። ከቤተክርስቲያን አካባቢ መጠጥና ጫት ቤት መቶ ሜትር ባልሞላ ርቀት ይሸጣል። ነገ እንደ አውሮጳውያን ቤተክርስቲያን ወደ መጠጥና ዳንስ ቤት ላለመቀየሩ ምን ሩጫን ሮጣችሁ?

ዘመኑ እየፈጠነ፣ ቴክኖሎጂው እየዘመነ፤ ማጥበርበሮች፣ ክፋቶች፣ ምቀኝነት፣ ሙስናና እርኩስ ተግባራትም በዚሁ መጠን እየተስፋፉ ነው። ዜጎች ከዚህ ፈተና አምልጠው በፈሪሃ እግዚአብሔር ውስጥ እንዲኖሩ ቤተክርስቲያኒቷ የራሷን አስተዋጽኦ ማድረግ ያለባት ይመስለኛል።

እጅግ የሚገርመው ይበልጥም

በታዲዎስ ጌታሁን

ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

ጥያቄዎች ለአባቶቼደሳለኝ ሥዩም

[email protected]

በ ገፅ 23

በ ገፅ 14

ከአዳም ጀምሮ እስከ አሁን ያሉ ትውልዶችን ብትመረምር፣

በእያንዳንዱ ትውልድ መሐል ብዙ ቀናተኞችን ታገኛለህ። ቀናተኞች

ሚስቴ (ባሌ ለምን ከሌላ ሰው ጋር ታየ) ታየች ብለው ብቻ የሚቀኑ

አይደሉም። ሥልጣንም ያስቀናቸዋል። ቃኤል ለምን በአቤል ተበለጥኩ

ብሎ ቀና፤ ገደለው። ያዕቆብ ራሱ በወንድሙ ብኩርና ላይ ስለሚቀና ነው የኤሳውን ብኩርና (ሥልጣን ወይም የበላይነት) በምስር ወጥ

የገዛው። ባይቀና ኖሮ ወንድሜ ሆይ ርቦሃልና እንካ ብላ ብሎ በቤተሰባዊ

ፍቅር ወጡን በሰጠው ነበር።

‹‹እናንተ ግን ራቅ ወዳሉ ገዳማት ከቤተሰብ ተለይታችሁ የገባችሁት በምንኩስናና በባዕት

የፀናችሁበት ጥቁር በጥቁር ለብሳችሁ ካማረ እንጀራ-ዳቦ፣ ከተመቼ መኝታ

- መሬት የመረጣችሁት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ዓለምን ስላዳነው መድኃኒት ፍቅርና ስለመንግሥተ ሰማያት ብላችሁ ነበር። ወይስ

ከመጀመርያው ምርጫችሁ አሁን የተገለጣችሁበት ፖለቲካ ነው? ሰው

መንፈሳዊ ሳይሆን ለማስመሰል ለማታለል ቢጥር ከፊቱ እሱነቱ

የሚለካበት ጊዜ ይመጣና ማንነቱ ፍንትው ብሎ ይወጣል። አሁን

እናንተ በመንበሩ ላይ በነበራችሁበት ዘመን የነበሩ የሀገሪቱ መሪዎች

በዚህ ምስኪን ሕዝብ ላይ ጅራፍ ሲያወርዱበት በሀዘን አንገቱን

ሲያስደፉ ያለ ከልካይ ሲያስለቅሱት በዝምታ አልፋችኋል።››

Page 9: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

‹‹ትንሽ አረፍ በሉ››የጎጃም አርሶ አደሮች

9ኮሜንተሪ

ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

ይህን ሀተታ የምፅፈው የሀገሬ ሕገ-መንግስት በሰጠኝ ሕጋዊ መብት መሰረት ነው። የለም፣

መብቶቼንማ ሕገ-መንግስቱ ሊሰጠኝ አይችልም። የማሰብ፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ የመደገፍ እና የመቃወም ሰብዓዊ (ዴሞክራሲዊ) መብቶቼን የሰጠኝ እግዚአብሔር ነው። ሕገ-መንግስቱ ግን እነዚህን መብቶች የሚያስከብርልኝ መሳርያ ነው። እስቲ ቆይታችንን በሚከተለው ወግ እንጀምረው፡-

ዋና ዋና የደርግ አባላት በሄሊኮፕተር እየተዘዋወሩ አገር ሲጎበኙ በጉዞ ላይ እንዳሉ ቀልድ ጀመሩና ከመካከላቸው አንዱ፣ ‹‹አሁን እኔ አንድ ባለ ሃምሳ ብር ኖት ብወረውር አንድ ሰው አግኝቶ ይደሰት ነበር›› አለ። ሁለተኛውም፣ ‹‹እኔ ደግሞ ባለ አስር ባደርገው አምስት ሰዎች አግኝተው ይደሰቱ ነበር›› አለ። ሶስተኛው ደግሞ፣ ‹‹እኔም ሃምሳ የባለ አንዳንድ ብር ኖት ብወረውር ሃምሳ ሰዎች አግኝተው ይደሰቱ ነበር›› አለ። አባላቱ ሲቀላለዱ የሰማው አብራሪ፣ ‹‹እኔ ደግሞ እናንተን ብወረውር ሃምሳ ሚሊየን ሕዝብ ይደሰት ነበር›› ብሏቸው እርፍ።

ከላይ የቀረበው ቀልድ በዘመነ ደርግ የተነገረ ሲሆን፣ ገበየሁ አየለ ‹‹ምርጦች እጦራለሁ›› በሚል ርዕስ በ1984 ዓ.ም ካሳተሙት መጽሐፍ ላይ ያገኘሁት ታሪክ ነው። የ17 ዓመታት የደርግ አገዛዝ ምን ያህል አስጨናቂ እንደነበርም ይኸው ቀልድ በአጭሩ ያስረዳናል።

እነሆ ግንቦት ሃያን አከበርነው። እሱ ባያከብረንም እኛ ግን አከበርነው። ድፍን 20 ዓመታት ለገዥዎቻችን ትንሽ ሊሆን ይችላል። ግን ለተገዥዎች ብዙ ነው። ደርግ

17 ዓመት ሙሉ የሥልጣን መንበርን በኃይል ተቆጣጠረው። የኢህአዴግ 20 ዓመታት ደግሞ ከደርግም የሥልጣን ዕድሜ በላይ ሆኗል። ዴሞክራሲ ባለባቸው ሀገራት እነዚህ 20 ዓመታት የአራት ወይም የአምስት መንግሥታት የሥልጣን ዘመናት ናቸው። ታዲያ እንደጎጃም ገበሬ፣ ‹‹ኢህአዴግ ሆይ፣ አረፍ በል›› ብንል ኢህአዴግን ይከፋው ይሆን?

በ1997 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ ነው አሉ። መላው የጎጃም አርሶ አደር ኢህአዴግን ትቶ ቅንጅትን መረጠ። በሆነች ‹‹ተዓምር›› ግን ኢህአዴግ አሸነፈ። ወዲያውም መራጩ ሕዝብ አፋጣኝ ስብሰባ ተጠራ። ካድሬዎቹ በየተራ እየተነሱ አርሶ አደሩን ይቆጡት ጀመር። ‹‹እንዴት ኢህአዴግን አትመርጡም? ኢህአዴግ ይሄን አልሰራም? ኢህአዴግ ያንን አላደረገም? ምርጥ ዘር አላቀረበም፣ ማዳበሪያ አላመጣም? ይህንና ያንን አልሰራም? በሉዋ! ተናገሩ . . . ኢህአዴግ ምን አጎደለ?›› ሲሉ ገበሬውን ይሞግቱ ያዙ። ኋላ አንድ አርሶ አደር እጃቸውን ሰቀሉና የመናገር እድል ሲሰጣቸው፣ ‹‹እኛ መች ይሀዲግ አልሰራም አልነ? ይሀዲግማ ሰርቷል። መስራቱንኮ እናውቃለን። ይሀዲግን ያልመረጥነው ግና ይህን ሁሉ ዓመት ብዙ ስለሰራልነ እስቲ አሁን ደግሞ ይረፍ፤ ይሀዲግ ብዙ ስለሰራልነ ደክሞታልና እስቲ ትንሽ አረፍ ይበል ብለን ነው›› አሏቸው አሉ። እኛም እንደኚህ አርሶ አደር ‹‹ኢህአዴግ ደክሞሀልና እስቲ ትንሽ አረፍ በል ብንል›› ይከፋብን ይሆን?

ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት ሃያን አከበርነው። እሱ ባያከብረንም እኛ ግን አከበርነው። እናቶችና አባቶች አንብበው

የማይረዱትን፣ እርግማን ይሁን ምርቃት የማያውቁትን መፈክር ተሸክመው ወደ አደባባይ ጎረፉ። መስከረም ሁለትን ሲሰለፉ የኖሩ ወላጆች ዛሬም ለግንቦት ሃያ ተሰለፉ። እድሜ ይስጣቸውና ለመጪውም ሌላ አብዮት ሳይሰለፉ አይቀሩም። አንዲት እናት አባይ ሊገደብ መሆኑን አጫወቱኝ። እኔ ይህን አልሰማሁም ነበር። አባይ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሊውል መታሰቡን ሰምቻለሁ። ‹‹አባይ ይገደባል›› እያሉ በየመገናኛ ብዙሃኑ ዜጎችን ማሳሳት ግን ተገቢ አይመስለኝም። አባይን መገደብ ሌላ፣ አባይን ለኤሌክትሪክ አገልግሎት መጠቀም ሌላ። (ስህተታችሁን አታጋቡብን እንጂ። )

በነገራችን ላይ፣ ግንቦት ሃያ ሲከበር ያስታወሰኝ የሀገራችንን የቀናት አከባበር ነው። ኢትዮጵያውያን ቀናትን የማክበር ጠንካራ ባህል አለን። የውሃን ቀን እናከብራለን፤ ነገር ግን ውሃን አናከብርም። የአካባቢ ቀንን እናከብራለን፤ አካባቢያችንን ግን አናከብርም። የአርበኞችን ቀን እናከብራለን፤ ሆኖም አርበኞቹን አናከብርም። የሰርቶ አደሮችን ቀን እንጂ የሰርቶ አደሮችን ተግባር አናከብርም። ቀናቱን እንጂ ከቀናቱ ጀርባ ያለውን ዓላማ መጨበጥ ይቸግረናል። አላማውን ትቶ ዕለቱን ማክበር ልክ አይደለም።

ልክ የዛሬ ሳምንት ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 20ኛ ዓመት ከአባይ ፕሮጀክት ጋር አያይዞ አከበረው። (በአንድ ቀን ሁለት ንግስ እንደሚሆነው) በነገራችን ላይ፣ መንግስት ‹‹ታላቁ የህዳሴ ግድብ›› የሚለውን የአባይ ፕሮጀክት አንዳንድ ሰዎች አዲስ ስያሜ ሰጥተውታል። ቅፅል ስሙ ‹‹ማስረሻ›› ሆኗል። ወደዋናው ጉዳያችን ስንመለስ፤

ኢህአዴግ ከ20 ዓመታቱ አገዛዝ በኋላ ራሱን ቀይሮ ሥልጣኑን ለሌሎች ያጋራል፣ ዴሞክራሲን ያመጣል፤ የኢኮኖሚ እድገትን ያሰፍናል በሚል ለወደፊቱ ተስፋ የሚጥሉበት በርካታ ወገኖች አሉ። ፓርቲው ካለፈው የተሻለ ነገር እንዲያሳይ የሚወተውቱ ድምጾችም ተደጋግመው ይሰማሉ። ከእነዚህ ድምጾች ውስጥ የግል ጋዜጦች ይገኙበታል። በዚህ የግንቦት 20 በዓል ሰሞን የግል ጋዜጦቹ በርዕስ አንቀጾቻቸው ያሰፈሩትም እንዲህ የመሰለውን ተስፋና ጉጉታቸውን ነበር። ከግል ጋዜጦቹ መካከል አንድ ሁለቱ ይህን እያሉ ጠይቀዋል፤ እንዲህ ሲሉ ተማፅነዋል፡- ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹ከ20 ዓመት በኋላ አዲስ ምዕራፍ ይጀመር›› በሚል ርዕሰ አንቀፁ ግንቦት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ባቀረበው ሀተታ፡-‹‹ ... ኢህአዴግ ከላይ በተነሱትና እዚህ ባልተጠቀሱት እንደሥራ አጥነትና ድህነት ያሉ በርካታ ችግሮችን ለመፍታት ታጥቆ መነሳት አለበት። ‹‹ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም›› እንደሚሉት አበው፣ በቅንነትና በአርቆ አሳቢነት ኢትዮጵያን ለመገንባት መነሳት አለበት። ኢህአዴግ ያካበተውን የ20 ዓመት ልምድ በመጠቀም አገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግራት ይገባዋል›› ሲል ተስፋና ምኞቱን ገልጿል። በሌላም በኩል በዕለተ አርብ የሚታተመው ፍትህ ጋዜጣ፣ በግንቦት 20 ዋዜማ ባወጣው ርዕሰ አንቀፁ፡-‹‹ኢህአዴግ በርካታ ዕቅዶችን አቅዶ ምን ያህል ከሸፈ? ምን ያህሉስ ተሳካ? የሚለውን የሚፈትሽበት ወሳኝ የግንቦት 20 በዓል ነው - ይህ በዓል። እናም በመስቀል አደባባይ ከሚደረገው

ጥያቄዎች ለአባቶቼ

የግብዞች ቸበርቻቻ ጀርባ ኢህአዴግ ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት፣ ከሙስና የፀዳ መሆኑን፤ በሀገሪቱ የጠፋውን መግባባት፤ ኢኮኖሚያዊ ክስረት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የፕሬስ አፈናን የመሳሰሉትን ሕገ-ወጥ ድርጊቶቹን የሚፈትሽበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነ በዚህ የግንቦት 20 የድል በዓል ፍትህ ታስገነዝባለች›› ብሏል። አዎ! በርግጥም ሰሚ ካለ፣ አድማጭ ከተገኘ እነዚህ ሀሳቦች ለገዥው ፓርቲ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ወርቃማ ምክሮች ናቸው። ፓርቲው ራሱን እንዲመለከት፣ አካሄዱን እንዲያስተካክል የሚያስችሉ ገንቢ ሀሳቦች ቀርበዋል። ችግሩ ግን ማን ዝቅ ብሎ ይሰማል? እነዚህን ምክሮች ማን ተግባራዊ ያደርጋል? የሚል ነው።

የጋዜጦቹ ርዕሰ አንቀጾች ሀሳብ ኢህአዴግ ከ20 ዓመታት በኋላ ሊለወጥና ሊሻሻል ይችላል የሚሉ ተስፋን ያዘሉ ናቸው። ለእኔ ግን ይህ ተስፋ አይታየኝም። በአጭሩ ኢህአዴግ አይለወጥም። ድርጅቱ ጥንተ-ተፈጥሮውን ሊለቅ አይችልም። ብረት ወደ እንጨት ይቀየራል እንዴ? እንጨትስ ወደ ብረት ይለወጣል? ኢህአዴግ በዚህ በምናውቀው ባህሪና ማንነት እስከመጨረሻው የሚቀጥል እንጂ ሌላ ባህርይና ማንነት ሊላበስ የሚችል ድርጅት አይደለም። ኢህአዴግ የሌለውን ከየት ያምጣ? ያልፈጠረበትን፣ የሌለውን ከየት ይውለድ? ከዚህ በኋላም በመጪዎቹ 20 ዓመታት የሚለወጥ ድርጅት አይመስለኝም።

ደራሲ ከበደ ሚካኤል አዝማሪና የውሃ ሙላት በሚል ድርሰታቸው መንገደኛው አዝማሪው የወንዙ ሙላት እንዲጎልለት መሰንቆ እየተጫወተ ለወንዙ እንደሚዘፍነው ሆነናል። ታዲያ ምን ይሻላል ከተባለ መልሱ አማራጭ ያስፈልገናል ነው። አዎ አማራጭ ያስፈልገናል። እንደ ደርጉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሄሊኮፕተር ላይ ተወርውረው ሕዝብ ይደሰት ባንልም ጎጃሜዎች እንዳሉት፣ ‹‹ኢህአዴግ ደክሞታልና ትንሽ አረፍ ይበልልን›› አማራጭ ያስፈልገናል።

ባለፈው ቅዳሜ

ግንቦት ሃያን አከበርነው።

እሱ ባያከብረንም እኛ ግን

አከበርነው። እናቶችና አባቶች

አንብበው የማይረዱትን፣

እርግማን ይሁን ምርቃት

የማያውቁትን መፈክር

ተሸክመው ወደ አደባባይ

ጎረፉ። መስከረም ሁለትን

ሲሰለፉ የኖሩ ወላጆች

ዛሬም ለግንቦት ሃያ

ተሰለፉ። እድሜ ይስጣቸውና

ለመጪውም ሌላ አብዮት

ሳይሰለፉ አይቀሩም።

በሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)[email protected]

ልማትን የሚያስቀድም የፖለቲካ ልሂቃን መኖር ነው። ጆንሰን ለልሂቃኑ መተባበር ሶስት ነጥቦችን ያነሳል፡- የጋራ የሆነ ፅኑ ፍላጎት፣ የተፈጥሮ ኃብት እጥረትና ከፍተኛ የደህንነት ዕጦት። ሌሎች ደግሞ ይህን ከልማቱ መንገድና ይዘት ላይ ያላቸው መስማማትን በምክንያትነት ያስቀምጣሉ። ይህም ውጤታማ የሆኑ ተቋማትን በመፍጠር በገበያው ላይ አስፈላጊ የሆኑ ጣልቃገብነቶችን ሊያካሄዱ ችለዋል። ሁለተኛው ውጤታማና ነፃነቱ የተጠበቀ ቢሮክራሲን የሚመለከተው ነው። ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት ጋር ሲፃፀር ሀገራቱ የተለየ ብቃትና ነፃነት የተላበሰ ቢሮክራሲ አላቸው። ይህም ኤቫንስ ስር የሰደደ ነፃነት (Embedded Autonomy) የሚለው ነው።እንደ ኤቫንስ ይህ ዘልቆ የገባ ነፃነት ሁለት መልክ ያለው ሲሆን የመጀመርያው መንግሥት በውጪው ላሉ ኃይለኛ የኪራይ ሰባብሳቢ ቡድኖች ጥቅም በመሳርያነት እስካልወደቀ ድረስ ነፃ ይሆናል። በሌላ በኩል ደግሞ ስር ሰድዶ የሚገባው ነፃነት በሕብረተሰቡ ውስጥ ካሉት ጠንካራ ፍልጎቶች ጋር እራሱን በማቀራረብ ለሽግግር ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በመደራደር ለማስገኘት ያለመ እንደ ሆነ ነው ይላል። ሌላው ደካማና በራሱ የማይቆም ሲቪል ሰርቪስ፣ የመንግሥት ነፃነት፣ ደካማ ሲቪል ማኅበረሰብና የኢኮኖሚ ዕድገቱንና አፈፃፀሙን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ተቀባይነት ይጠቀሳሉ።ሀገራቱ ጠንካራና ውጤታማ እንዲሁም እራሱን የነጠለ የኢኮኖሚ ቢሮክራሲያዊ ተቋማትን ለመግንባት ችለዋል። እነዚህም የጃፓን የዓለም አቀፍ ንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር (MITI)፣ የኢኮኖሚ ዕቅድ ቦርድ (EPB) በኮሪያ፣ የኢኮኖሚ ልማት ቦርድ (EDB) በሲንጋፖርና የገንዘብና የዕቅድ ልማት ሚኒስቴር (MFPD) በቦትስዋና ናቸው።በተጨማሪም ከፍተኛ የገንዘብና የካፒታል ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት የኢኮኖሚ ተጋላጭነታቸውንና ውድድርን በማዘግየት በኢኮኖሚው ለመበልፀግ

ችለዋል - ምንም እንኳን ከኪራይ ሰብሳቢነት፣ ክሮኒዝምና ለገንዘብ ፖለቲካ የተጋለጡ ቢሆንም፡በዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ረገድ የሲቪልና የፖለቲካ ነፃነቶች ተገድበዋል።በመጨረሻም እነዚህ መንግሥታት ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ ማግኘታቸው ይጠቀሳል። የሞራል፣ የዲፕሎማሲና የቁሳዊ ድጋፍ ከኃያላን ሀገራት በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የኮሚዩኒዝምን መስፋፋት ለመገደብ ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ ማግኘታቸው ለእድገታቸው ብቸኛው ባይሆንም አንዱ ምክንያት ነው። ምንም እንኳን ‹‹ከዋሽንግተን ስምምነት›› ውጭ የሆኑና ጭራሽ ተቃራኒ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ቢከተሉም በወቅቱ በነበራቸው ጂኦ-ፖለቲካዊ ጠቃሚነት የተነሳ የፖሊሲ ነፃነታቸውን አስጠብቀው ለመተግበር እድል አግኝተዋል።

ኒዮሊበራሊዝም ይውደም!የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ኒዮሊበራሊዝምን በማጥላላትና እንደ አንድ በመንግሥቱ ላይ እንደተቃጣ ብሔራዊ ስጋት አድርጎ ይመለከተዋል። ይህም ሁሉም ሊባል በሚችል መጠን ልማታዊ መንግሥታት በተለይ የመዋቅራዊ ማሻሻያ ያካሄዱና ውጤታማ ያልሆኑ መንግሥታት ባሉባቸው ሀገራት በጉልህ የሚታይ ባሕርያቸው ነው። ግንባሩ የፖሊሲ፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ የሰብዓዊ መብት ይዞታ፣ የኢኮኖሚና ሌሎች ጥያቄዎች ከተቃዋሚውም ሆነ ከገለልተኛ አካላት የሚነሱበትን ትችቶችንና ተቀውሞዎችን ኒዮሊበራሊስቶችና የገበያ አክራሪዎች ብሎ መሰየም አንዱ የሚታወቅበት መለያ ሆኗል።የልማታዊ መንግሥትና የኒዮሊበራል አንዱና ዋነኛው ጉልህ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነሳው በገበያውና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነትን ተንተርሶ የሚስተዋለው ነው። ይሁንና አንዳንድ ተንታኞች የአንድ አገር ኢኮኖሚ ንግድ ክፍት

መሆን የመንግሥትን በኢኮኖሚ አመራር ያለውን ሚና ማነስ እንደማያስከትል ይከራከራሉ። ሊ የተባለ ፖለቲካል ሳይንቲስት ጠንካራ መንግሥት ለውጤታማ ገበያ ክፍት መሆን እንደ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በማውሳት አጥብቆ ይሞግታል። በዚህ ላይ ገበያዎች የፖለቲካና ተቋማዊ ወይም ማኅበራዊ ኦናዎች (vacuums) ውስጥ መሥራት እንደማይችሉና በዚህ ማኅበራዊ ውጤቶችን ለማዳረስ መንግሥት አስፈላጊ ኃላፊነትና ሚና እንዳለው ያስረዳል። ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ክፍት አድረጉ ማለት የኒዮሊበራል ፖሊሲን ተከተሉ ማለትን አያስከትልም። ለዚህም ገበያን የመክፈት ፖሊሲ ከልማታዊ መንግሥትነት አካሄድ ጋር ተቀናጅቶ በተጓዳኝ የሚከወኑ ንቁ የመንግሥት እርምጃዎችን በምሳሌነት ያስቀምጣል። ብሎክ ገበያና መንግሥት በተፈጠሮ በተመሣሣይ የኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ በጥምረት የሚገኙ በመሆናቸው አንዱ ከአንዱ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም ይላል።የኦርቶዶክስ ኒዮሊበራሎች ነፃ ገበያዎች እጅግ ተመራጭ ማኅበራዊ ጥቅሞችን ማስገኛ መንገዶች ናቸው ብለው ያምናሉ። ለዚህም ገበያን መክፈት ዋናው ሲሆን ከዚሁ ጋርም የቁጥጥር መላላት፣ የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግል ማዛወርና የግሉን ተሳትፎ በኢኮኖሚ ውስጥ መጨመር፣ ጥብቅ የገንዘብና የፊስካል ዲስፐሊን እና የመንግሥት የኢኮኖሚ ጣልቃገብነት አለመኖር ይገኙበታል። በኒዮሊበራሊስቶች እምነት እምዛም ቁጥጥር የማያደርግ መንግሥት ሀሳባዊው መንግሥት ሲሆን፣ የግለሰቦችን ኃብት የመጠበቅ፣ የግለሰቦችን፣ የንብረትና በፍቃድኝነትና መግባባት ላይ የተደረሰባቸው የግል ውሎችን በማስፈፀሙ ዙሪያ የተገደበ ሚና ያለው ነው።ኒዮሊበራሊዝም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ተያይዞ የሚነሳና ዋነኛ መሳርያዎቹ ሲሆኑ እነዚህም የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO)፣ የዓለም የገንዘብ ፈንድ (IMF) እና

የዓለም ባንክ (WB) ናቸው። ይህም በተለምዶው የዋሽንግተን ስምምነት (Washington Consensus) በመባል የሚታወቀው ነው። ለኒዮሊበራሎች የመንግሥት እጅ መብዛትና ጣልቃ ገብነት መብዛት ለሙስና እድል ይሰጣል። ይህም ጥገኝነትና ኪራይ ሰብሳቢነት በማስፋፋት የኢኮኖሚ ኃብቶች ስርጭት የሚያዛባ ነው። ለእነርሱ የመንግሥት ክፍተት እጅግ አደገኛና በኃልዮት የማይመራ በመሆኑ የተመጠነ አይደለም። ለእነርሱ የማይታየው እጅ የኢኮኖሚው መሰረት ነው።ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ በወጣ ከጥቂት ወራት በኋላ የመጀመርያውን የኢኮኖሚ ፕሮግራም አወጀ። ፕሮግራሙም የቀድሞውን መንግሥት አካሄድ በማጠናከር በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ድርጅቶችን የመንግሥት ባለቤትነት ማጠናከር፣የኢንዱስትሪ፣ የገንዘብ አገልግሎት ዘርፉን ቁጥጥር ማጠናከር አላማው ያደረገ ነበር።ብርሃኑ አበጋዝ ‹‹Aid and Reform in Africa›› በሚለውና በዓለም ባንክ በተዘጋጀው መፅሐፍ ኢትዮጵያን በተመለከተ እንደሚለው፣ ‹ምንም እንኳን ቆይቶም በዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ግፊት እ.ኤ.አ በ1991 ቢሻሻልም የመንግሥቱ የድህረ-ሶሻሊስት ኢኮኖሚ ፍላጎት በመንግሥት ቁጥጥር ላይ የተመሰረተ የቅይጥ ኢኮኖሚን መመስረት ነበር››። ብርሃኑ የመንግሥቱን ማሻሻያዎች በሁለት ይከፍላቸዋል።የመጀመርያው የፖሊሲ ማዕቀፍ ከ1992-93 የማረጋጋትና የመዋቅራዊ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ለድህነት ቅነሳና የነፃ ገበያ ሥርዓትን ለማስፈን ያሰበ እንደነበር ያስረዳል።ይህም የቀረጥ ቅነሳ፣ ገበያውንና የውጭ ንግድ አስተዳደሩን የመክፈት፣ ውጤታማ የሆኑ የፊስካል ፖሊሲ መከተል፣ በመንግሥት ለተያዙ የቢዝነስ ድርጅቶችን ነፃ ማድረግና የአነስተኛና መካከለኛዎቹን ወደ ግል ማዛወር፣ የፋይናንስ ገበያውን ማሻሻል፣ስድስት የአካባቢ ባንኮችንና

ሰባት የኢንሹራንስ ተቋማትን ለወደ ግል ማዛወር፣ የወለድ ምጣኔን ክፍት ማድረግና ክፍት የሆነ ኢንቨስትመንት በመጀመርያው ውስጥ ይካተታሉ።እ.ኤ.አ በ1996 የሁለተኛውን የመንግሥት የሶስት ዓመት የማሻሻያ ፕሮግራም በIMF የተቀናጀ የመዋቅራዊ ማሻሻያ ስር አካሂዷል። ይህም ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድረግ ያለሙ የመዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ማስተዋወቅ ግቡ ያደረገ ሲሆን ከነዳጅ በስተቀር የሸቀጦች ዋጋ ቁጥጥር ማስቀረት፣ የገቢ አቃዎችን ቀረጥ ከ230 ወደ 40% አውርዷል። ማሻሻያዎቹ የኒዮሊበራሊዝም አራማጅ በሆኑት ተቋማት የተከናወኑና በፊት ከነበረው የዕዝ ኢኮኖሚ (ደርግ ማብቂያው ላይ ቅይጥ ኢኮኖሚን አውጆ ነበር) በእጅጉ የሀገር ውስጥ ገበያውን የከፈተ ነበር ማለት ይቻላል። ይሁንና መንግሥቱ ሁለተኛ ትውልድ ማሻሻያዎችን ለመውሰድ ዳተኝነት ታይቶበታል። ይህም ቋሚና ወጥ የሆነ ፖሊሲ እጥረት እንደሚስተዋልበት ያመላክታል።እነዚህ ማሻሻያዎች የልማታዊ መንግሥትን በሙሉ ለመቀበል ትልቅ እንቅፋት እንደሆኑበት ድርጅቱም ያምናል። ግንባሩ በሰነዱ እንዳስቀመጠው በአንድ በኩል በዓለም የገንዘብ ተቋማት የመንግሥትን ድርሻ ወደ ዜሮ ለማውረድ የሚደረገውን ሙከራ የመከላከል ስራ መስራቱን ነገር ግን ይህ የመከላከል ስራ ወጥ ከሆነ የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ የመነጨ ነበር ማለት አይቻልም ሲል በግልፅ አስፍሮታል፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መመምህር የሆኑት ዶ/ር አለማየው ገዳና ክብሮም ተረፈ፣ ‹‹Galloping Inflation in Ethioipia: A Cautionary Tale for Aspiring ‘Developmental States’ in Africa›› በሚለው ጥናታዊ መጣጥፋቸው መንግሥቱ የኢኮኖሚ እድገቱን የኒዮሊበራል ፖሊሲን ባለመቀበሉና ልማታዊ መንግሥትን ከመምረጡ ጋር እንደሚያያይዘው ይገልፃሉ። ይሁንና የኒዮሊበራል ፖሊሲ ተፅዕኖ በዓለም የገንዘብ ተቋማት መሠረታዊ መርህዎች ባለመለወጣቸው በሚካሄደው የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ፕሮግራምና በሚሌኒየሙ የልማት ግቦች አማካኝነት መቀጠሉን ያስረዳሉ። እንደ እነእርሱ እምነት የኒዮሊበራል ፖሊሲን የሚተኩ ጠንካራ የማክሮ

ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች በሌሉበት ሁኔታ ልማታዊ መንግሥት ነን የሚሉ መንግሥታት የግሉም ሆነ የመንግሥት ወጭ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር በር ይከፍታል። ይህም ለኢኮኖሚ እድገትና ድህነት ቅነሳ ተፃራሪ ለሆኑት የዋጋ ንረትና የምንዛሪ ምጣኔ ተለዋዋጭነት ይዳርጋል።የልማታዊ መንግሥታት ትልቁ ችግርም የመንግሥት ክፍተት መኖሩን አለማገናዘባቸው ነው። ከዚህም ይባስ ብሎ ከመንግሥት ጣልቃገብነትና እጅ መንሰራፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛ የልማታዊ መንግሥታት ችግር ነው። ኢህአዴግም የመንግስቱን አቅም ከግምት ያላስገባና የመንግሥትን ውስንነት ያላጤነ ጣልቃገብነት በጥናት ላይ ባልተደገፈ መንገድ መግባቱ ልማታዊነቱና አዋጭነቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ። ለዚህም አስረጅ የሚሆነው በቅርቡ ገበያን ለማረጋጋት በሚል የተወሰደው ዋጋን የመተመን እርምጃ በጥናት ላይ ያልተመረኮዘና የችግሩን ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም የመንግሥትን አቅም ከግምት አለማስገባቱ ከሁነቱ በኋላ የተፈጠረውን የገበያ ምስቅልቅሎሽ ማየት ይቻላል። በመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተጠና የተባለውን ጥናት እንኳ ከተወሰኑ ቅርበት ካላቸው አካላት በስተቀር ማንም ሰው ማግኘት እንደማይችል በቅርበት ለማወቅ ይቻላል። ይህም መንግስቱ በገበያ ክፍተትን ብቻ መሰረት አድርጎ ጣልቃ እንደማይገባ ማሳያ ነው።ሌፍትዊች እንደሚለው የልማት ሞዴሎች ለኢኮኖሚ እድገት ያላቸው አሰተዋጽኦ አነስተኛ ነው። ዋናው ቁም ነገር የመንግስቱ ባሕሪና የኢኮኖሚ አስተዳደሩ ላይ ያለው ውጤታማነት ነው። ኢኮኖሚስቶች የሚስማሙበት አንድ ነገር አለ። እርሱም የገበያ ክፍተት መኖሩ ላይ። ይሁንና እንዴት መንግሥት ጣልቃ ይግባ የሚለው የልዩነቱ መጀመርያ ነው። መንግሥት ጣልቃ ቢገባም የማይፈታቸው የገበያ ክፍተቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ። ነገር ግን ክፍተቱንና አማራጮቹን አጥንቶ ለአጭር ጊዜ መገባቱ አቅም እስካለውና ይበልጥ እስካላባባሰው (ለመቅረፍ እርግጠኛ እስከሆነ) ድረስ ተመራጭ ነው። መንግሥት ግን አያያዙ ይህን ማድረግ የሚችል አይመስልም።

የአብዮታዊ ዴሞክራሲና...

Page 10: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 200310

p Ç T@ S ´ “ —

(የባለፈውን ሳምንት የአስቴር ትረካ ያቆምነው የሚከተለው ተነግሮን ነበር፡- ‹‹ብዙው ታካሚ አማኑኤል ከገባ በኋላ ለመውጣት ስለማይፈልግ ሠራተኞቹ እንደሚቸገሩ የታወቀ ነው። . . . ለምሳሌ አንዷ ታካሚ እንድትወጣ ሲነገራት እንቢ ስላለች ፖሊስ ተጠራ። አንጠልጥለው በመኪና ይዘዋት ወጡ። የት ይጥሏት ይሆን?››)

ክፍል አምስት(የመጨረሻው ክፍል)

መጀመርያ ሆስፒታል ያመጡዋት ፖሊሶች አሉ።በአንዱ የበዓል ሰሞን እዛው ነበረኩና ይህን ጉድ አየሁ። በጠዋት ወደ በሩ ብቅ ብል ግቢው በሰው ብዛት ተጥለቅልቋል። አሮጊት፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ሕፃን … አስታማሚ …የፊጥኝ ታስሮ የሚንከባለል፣ የሚጮሁ አሮጊት፣ የሚያቀሪሩ … እጅ እግሯ ተጠፍሮ አልበቃ ብሎ በአለንጋ የምትሸነቆጥ … ጉድ ይታያል። እጅና እግሯን ታስራ ልብረር ብላ የምታስቸግረዋንም መድኃኒት ለማዋጥ ራሱ መድኃኑቱ ሟሙቶ ለማጠጣት አሳር ታስቆጥራቸዋለች። ይቺ ኃይለኛ ወጣት እኛ ክፍል ደረሳት። በአለንጋ ሾጥ እያደረገ ልክ የሚያስገባት ባልዋ ነው። መጀመርያ ጠልቼው ነበር። በኋላ ግን እጅግ ወደድኩት፣ አከበርኩት። ጓደኛው እግሯ ታስሮ እጇ ታስሮ ነው ያለችው። እሱን በጠዋት መጥቶ ሽንት ቤት ወስዶ፣ ገላዋን አጥቦ፤ እንደታሰረች ፀሀይ አሙቆ። እሷ ግድ ባይሰጣት እንኳ እሱ ከልቡ ተንከባክቦ ያስታምማታል። ማታ-ማታ በመድኃኒት ሰዓት መጥቶ መዳኒቱን ግቶ አቅፎ ስሞ አስተኝቷት ይሄዳል። ምግብ የሷን ኮታ ለሁለት አብረው ይበላሉ። ብቻ በቀናት ልዩነት ለውጥ አሳየች። እየነቃች-እየተሻላት ሲሄድ የምግብ ፍላጎቷ አየለ። ጓደኛዋ እሷ በልታ እስክትጨርስ ይጠብቃል። ካላስተረፈች ዝም ይላል። እሷን እያጎረሰ ዓይኑ እንጀራው ላይ ሲንከራተት ማየት

አንጀት ይበላል። በዚህ ዕለት እኛ ክፍል የተመደበችው ሌላዋ ወጣት ደግሞ የኃብታም ቤተሰብ ልጅ ነች። በቀን ሶስት ጊዜ ይዘዋት መጡ። የተወጋችው መርፌ አላበርድ ስላላት በቃ ትተኛ ተብሎ ነው። ‹‹የአዳል ሞቴን እቃ እቤቴ አውጡልኝ! አቃጠለኝ! ተቃጠልኩ! ተንገበገብኩ … ›› ትላለች። ባሏ ‹‹እሺ አሁን ሄጄ አወጣለሁ›› ሲል ‹‹አይሆንም! በአንተ መኪና አይደለም፤ በእከሌ መኪና መሆን አለበት … ኡኡ ተቃጠልኩ … ››ብቻ በበዓል ሰሞን በርከት ያሉ በሽተኞችን አማኑኤል ይስተናገዳሉ። በተለይ በቤት ጣጣ የተለከፉ ይበዛሉ።

* * *በአማኑኤል ሆስፒታል የ‹‹ሰብስታንሶች ክፍል›› በመባል የሚታወቅ ክፍል አለ። የሰብስታንሶች ክፍል ፀዳ ያለ ከአራት ሰው በላይ የማያስተናግድ ነው። እኔ በነበርኩበት ሰዓት አስራ አንድ ሰዎች ነበሩ። ሰብስታንሶች የሚባሉት ሄሮይንና ከጫትና ከጋንጃ ያለፉ እፆችን በመጠቀም የሚታመሙ ናቸው። አስራ ዘጠኝ ዓመታተን አሜሪካን

ሀገር ቆይቶ ኃብትና ንብረቱን ጨርሶ አማኑኤል የደረሰው ጓደኛችን የሆስፒታሉን መፃህፍት ሸጦ እንደቃመ በግልጽ ያወራል። የህመምተኞችን ራዲዮ፣ ፔርሙዝ ከአስታማሚዎች ጠቃሚ የመሰለውን እቃ እየሰረቀም ወጥቶ የፈለገውን አድርጎ ይመለሳል። የሚወጣው የሚገባው በበሩ ነው። ለጠፋ ዕቃ እሱ አይጠረጠርም። በርከት ያሉ ዕቃዎች ስላሉት የሚከበር ነው። እሱ ተቀባይ ነው። ሰራቂው አብሮት አንድ ክፍል የተኛው ጓደኛው ነው። ያኛው

ከአዲስ አበባ ጓዳዎች አንዱ:-

አማኑኤል ሆስፒታልአስቴር ጩጬ ትባላለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡ ነፍስ ካወቀች እስከ አሁኑ ደቂቃ ያለውን የግል ሕይወቷን ዳጎስ ባለ መጽሐፍ ለመተረክ ቆርጣ ተነስታለች፡፡ እስከ አሁን ከአስር ደብተር በላይ ጽፋለች፡፡

ከአራቱ ደብተሮች የተቀነጨበው እንዲህ ይነበባል፡፡በስንዱ አበበ

ሌላው በአማኑኤል ሆስፒታል ደስ የሚል ነገር በወር አንድ ቀን

የሚዘጋጀው የቡና ሥነ-ሥርዓት ነው። በትልቁ አዳራሽ ውስጥ

ሴቱ ባንድ ወገን፣ ወንዱ በሌላ ወገን፤ ነርሶችና የሆስፒታሉ

ሰራተኞችም ይቀመጣሉ። በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰገኑ ታካሚዎች

የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል።

ይሰርቃል - ይሄ ወጥቶ ሸጦ ይመጣል። ከዛ የፈለጉትን ይሆናሉ። እኔም አንድ ሁለት ጊዜ በማቀባበል ተሳትፌ - ድርሻዬን አግኝቼ አውቃለሁ።በሳምንት ሁለት ቀን ሰብስታንሶችና በሱስ የተጠቁ ሰዎች ተሰባስበው ውይይት እናደርጋለን። ‹‹ግሩፕ - ቴራፒ›› ይባላል።ይህ ፕሮግራም እጅግ አዝናኝና አስቂኝ ነው። ብዙዎቹ ታካሚዎች ለነርሶችና ለዶክተሮች የደበቁትን ማንነታቸውን የሚያጋልጡበት፣ አንዳንድ ታካሚዎች ከዶክተሮች የላቀ እውቀትና ግንዛቤ እንዳለቸው የሚታይበት፣ በገጠመኞችና በግል ልምዶች ታሪክ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ፣ ብዙ ሰው ደስ ብሎ የሚሳተፍበት ፕሮግራም ነው።ሌላው በአማኑኤል ሆስፒታል ደስ የሚል ነገር በወር አንድ ቀን የሚዘጋጀው የቡና ሥነ-ሥርዓት ነው። በትልቁ አዳራሽ ውስጥ ሴቱ ባንድ ወገን፣ ወንዱ በሌላ ወገን፤ ነርሶችና የሆስፒታሉ ሰራተኞችም ይቀመጣሉ። በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰገኑ ታካሚዎች የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል።ድፎ ዳቦ ይቆረሳል፤ ቆሎ ይቀርባል። ቡና ሲያከትም ሙዚቃ ይከፈታል። የራት ሰዓት እስኪደርስ ሴቱም ወንዱም ጭፈራውን ያስነካዋል። በዚህ ቀን በርከት ያሉ ታማሚዎች ዘነጥ ብለው ይታያሉ። ብዙው በፒጃማ ይህን የቡና ሥርዓት አይታደምም ወይም ንፁህ ፒጃማ ይቀየርላቸዋል።

* * *በአማኑኤል ሆስፒታል የሃያ ሳምንት ቆይታዋን ታሪክ ለመደምደም አንድ ታሪከ እንመርቅላችሁ። እኝህ አሮጊት ዕድሜያቸው ከስልሳ በላይ ይገመታሉ። ፀጥታና ብቸኝነት ፈላጊ ይመስላሉ። ማውራት፣ መወያየት አይወዱም። ማንጎራጎር፣ ማንጎራጎር ብቻ። እሳቸው ገለል ብለው እያንጎራጎሩ በፀጥታ አጠገባቸው ከተቀመጡ ደስ ይላቸዋል። ሆኖም እሳቸው ባሉበት ውር-ውር የሚል ካለ፡- ‹‹እናንተ - ሚኝ - ሚኝ እያለባችሁ እኔን አታድርቁኝ›› ብለው ይበሳጨሉ። ቀጣዩ ግጥም እኝህ ባልቴት ታካሚ ደጋግመው በዜማ የሚያዜሙት ነው። አሮጊቷ ፀሀይ እየሞቁ ያንጎራጉራሉ እንዲህ ...

የነብስራትዬ፣ የነባርዬ እናትአራት ወልዳ ወልዳ ሁለት ብቻ ቀሯት

እንደ አህያ ጡት።***

ከፍ ብለህ ተቀመጥ አንተ ዘበኛዬ

አንተን ተከትዬ አያል ሰው እንዳይ***

እንጀራ መጋገር አታውቅም እናቱየኔ ሊቆዲሞስ ዳዊት ነው ራቱ።

መለስ መለስ አርገው እንደው በቃልህብራና መገልበጥ አይችልም ጣትህአልወራረድም እኔ አልገባም ዕዳየበለጠን አባት የኔን የዳዊቱ ጌታ

***እራሷን ተሰርታ ወለባ ሸጣለችበቅሎዋ ተጭና ጥሬ ትበላለች

አሽኮሌዋን ታጥቃ አገልግል አዝላለችእምዬ ደጅ ይጥኑ ወዴት ትሄዳለች

ደበክ - ደበክ አለችደባካ ካባው

ልታቆራርጠኝ ከመንደርተኛው።***

በናቷ ባለእጅ - ባባቷም ባለእጅየሚለው ከንፈርዋ ለጋ-ለጋ ጠጅአረመኔ ሰው ነህ - ጨካኝ አረመኔ

አንቅልፍ ወሰደህ ወይ ተለይተህ ከኔ?***

ቄሱም ቄስ አይደሉአቡኑም አቡን

የሰው ሚስት አትንኩ፤ እያሉ ብይን***

ተርከክ - ተርከክ አለተርካካ በአንባው

ሊያቆራርጠኝ ነው፤ ከመንደርተኛው።***

አደራ አባዬ የልምጯን ነገርከብት ይነዳበታል፣ የባላገር ነገር።ቅላቷን እንደጀምበር ጥብቅ ዘላቂተኝታ ተወዳጅ ቆማ ተናፋቂእያለቀሰ ነው ደናዋይ ሲላት

እንኳን ውሽማዋ ባሏ አልጠገባት።***

ትላንትና ማታ እኛ ቤት ያደረችሌሊት - በማለዳ እቃ ጠፋኝ አለች።

***ምን ዕቃ - ምን ዕቃ - ምን ዕቃ በያት

አንድ ጥርኝ ሞራ እንደሸረሪትእንኳን ተመልሼ ዞሬም አላያትአራስ ተሸንፈው ንጉስ ወሰዷት

***የገዳም ትርንጎ - የኮከብ ወደር

የዓይኗን ሽፋሽፍት የሚታጨድ ሳርእርሳስ ሀር ይመስላል የራሷ ፀጉርይህ ሁሉ ውበትሽ ተጽፎ መዝገብእልፍኝ ይነበባል እቴጌ አጠገብ

እሽክምክም - እሽክምክምውጭብኝ - ልውጣብሽ

***የአጥቢያ ኮከብ መሳይ - ንጋት ያገዛት

ከሷ ጋ አድሬ - ሲነጋ ልሙትሙትትት ሙትት መትት

/አበቃ/

ሊያ ከበደ የላ’ኦሬል ብራንድ አምባሳደር ሆነች- እነቢዮንሴን ተቀላቅላለችኢትዮጵያዊቷ ሊያ ከበደ የላ’ኦሬል (L’Oréal)

ፓሪስ ኮስሞቲክስ ካምፓኒ ኢዲስ አመባሳደር ሆና መመረጧ ተዘገበ።

ሞዴል፣ ተዋናይትና የሁለት ልጆች እናት ሊያ ከበደ እነ ቢዮንሴ፣ ጄኔፈር ሎፔዝ አና ሌሎች ታዋቂ ቆነጃጅት በአምባሳደርነት የሚያስተዋውቁት ካመፓኒ እርሷንም በውበቷ እና በጥንካሬዋ እንደመረጣት አስታውቋል። ‹‹ጥንካሬዋ እና ትጋትዋ መስጦናል፤ ውበቷም አስደምሞናል›› ብሏል።

ሊያ ከጊዜ ወደጊዜ ዓለማቀፍ ተወዳጅነትንና ተመራጭነትን ያገኘች ሞዴል ከመሆኗ ባሻገር በፊልም እና በተለያዩ መስኮችም ተሰማርታ ትገኛለች። በተለይ የአንዲት ሶማሊያዊ ሞዴል ታሪክን የተጫወተችበት “Desert Flower” የተሰኘው ፊልም ተጠቃሽ ነው።

እ.አ.አ በ2007 በሀገሯ የሚሰሩ ጥበብና የአጅ ሥራ ውጤቶችን ‹‹ለምለም ክሎዚንግ›› በሚል ሰያሜ ማስተዋዋቅ የጀመረችው ሊያ፣ ዓለም አቀፍ እውቀናዋን በመጠቀም ባህላዊ የእጅ ሙያተኞችን ለመደገፍ እንደምትጥር ይታወቃል።

የታዋቂው ላ’ኦሬል ፓርሪስ ካምፓኒ ብራን አመባሳደር መሆኗም ለቀጣይ እንቅስቃሴዎ የስኬት መንገዷን እንደሚያሰፋላት ተዘግቧል።

‹‹ፓኖራሚክ ሲኒማ ቤት›› ተዘጋ

በኤሌያስ ገብሩ

መስቀል አደባባይ በሚገኘው የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ይገኝ የነበረው ፓኖራሚክ ሲኒማ ቤት ‹‹ከሙዚየሙ ዓላማ ጋር አብሮ እየሄደ አይደለም›› በሚል ምክንያት መዘጋቱ ተገለፀ፡፡

‹‹የሰማዕታት ማኅበሩ አባላትና በርካታ የሙዚየሙ ጎብኚዎች ሲኒማ ቤቱ ሙዚየሙ ዓላማና ዕቅድ ጋር አይሄድም የሚል ቅሬታና ተደጋጋሚ ወቀሳ በመነሳቱ ሲኒማ ቤቱ ሊዘጋ ችሏል›› ሲሉ የሲኒማ ቤቱ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ታዬ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

‹‹ቦታው የሀዘን ነው፤ በቀይ ሽብር ወቅት የተገደሉ ሰዎች አፅም በሙዚየሙ የታችኛው ክፍል እያለ፣ ከላይ ያለው ሲኒማ ቤት በሚያስቁ ፊልሞች የደስታና የፌሽታ ቦታ ሆኗል›› የሚል ቅሬታ ቀርቦላቸው እንደነበር ሥራ-አስኪያጁ አስታውሰው፣ ሲኒማ ቤቱም ግንቦት 13/2ዐዐ3 ዓ.ም መዘጋቱን ተናግረዋል፡፡

የሙዚየሙ ሥራ-አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ እመቤት በበኩላቸው በሰጡት አስተያያት፣ ሲጀመር ሲኒማ ቤቱ የደስታና የፌሽታ ቦታ ይሆናል ብለው እንዳላሰቡ ገልፀው፣ ሲኒማ ቤቱ ከዓላማው ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ ምክንያት የሥራ ውላቸውን በአግባቡ እንዲቋረጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹ከሙዚየሙ ጋር የነበረን ውል በሰላማዊ መንገድ ቢቋረጥም፣ በእኛ በኩል ጥሩ ስሜት አልነበረም፡፡ ለሥራው ብዙ ወጪ አውጥተናል›› ያሉት የሲኒማ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ፣ በቅርቡም ሌላ ምትክ ሲኒማ ቤት ለመክፈት ቦታ እያፈላለጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Page 11: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —

“ሀቢቢ” የተሰኘው ዘፈን የአባትሽን ሰም የተካው አይመስልሽም?እውትህን ነው እኮ። ብዙ ሰዎች ዝናሽ ፀጋዬ ከማለት ይልቅ ዝናሽ ሀቢቢ ማለት ይቀላቸዋል። ይህንን ዘፈን በመጀመሪያ በነጠላ ዜማነት ነበር የለቀቅኩት። ሰዎች በጣም ስለወደዱት በ1996 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ባሳተምኩት የመጀመሪያ የካሴት ሥራዬ ውስጥ አካተትኩት።

የካሴቱ መጠሪያ ራሱ ‹‹ሀቢቢ›› ነው አይደል?አዎ!… እና ዘፈኑ በጣም በመወደዱ የተነሳ ብዙ ሰው ከአባቴ ስም ይልቅ ዝናሽ ሀቢቢ ማለት ይቀናዋል።

በዚያው በአንድ ካሴት ተወሰንሽ ማለት ነው? ሌላ ካሴት ለመሥራት አላሰብሽም?ሌላ ካሴት መሥራት ሰርቻለሁ። ሙሉ ሥራውን ጨርሼ ማስተሩን በእጄ ይዣለሁ። አሁን ገበያ እያፈላለግኩ ነው ያለሁት። ያው እንግዲህ እንደምታውቀው ሙዚቃ ቤቶች አካባቢ ያለው ነገር ተስፋ ያስቆርጣል። እና ምን ማድረግ እንደለብኝ እያሰብኩ ነው።

የት ነው የተወለድሽው? ከአዲስ አበባ ብዙም አይርቅም። መናገሻ ነው የተወለድኩት። ምነው?

ሙዚቃ የጀመርሽው እዚህ አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ መሆኑን ሰምቼ ነበር። ልክ ነው?ለነገሩ ሙዚቃ መጫወት የጀመርኩት እዚያው መናገሻ፣ ት/ቤት ውስጥ በክበብ ደረጃ ነው። ወደ አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ ነው መርካቶ አካባቢ ይንቀሳቀስ የነበረው ‹‹መስታወት የኪነ-ጥበብ ማዕከል››ን የተደባለቅሁት።

ይኼ መስታወት ኪነ-ጥበብ ማዕከል የሚባለው እነ ቴዲ አፍሮ ይሰሩበት የነበረ ነው አይደል? አዎ። እነ ቴዲ አፍሮ፣ እነ አብነት፣ እነ ጎሣዬ… በጣም ብዙ ዕውቅ ባለሙያዎች የነበሩበት ነው። እኔንም ጨምሮ ማለት ነው። እና እዚያ ክበብ ስንሰራ ምንም ዓይነት ገቢ አናገኝም ነበር። ስለዚህ በናይት ክለብ ደረጃ በሙሉ ባንድ አትክልት ተራ አካባቢ ‹ሚኪ ባር› እንድንሰራ ሁኔታዎች ተመቻቹልን። እናም መስራት ጀመርን። በነገራችን ላይ አብነት አጎናፍር ያኔ ኪቦርድ ነበር

የሚጫወተው። ነገር ግን በክበብ ደረጃ የኬኔዲን ዘፈን ሲጫወት ድምፁ ይመስጠኝ ስለነበር፣ በድምፃዊነት ካልሰራህ እያልኩ እወተውተው ነበር። እንዲህ፣ እንዲህ እያልኩ በተለያዩ ክበቦችና ናይት ክለቦች ውስጥ እየሰራሁ ነው እዚህ የደረስኩት።

እኔ ሀገር ፍቅር ስትሰሪ ነበር የማውቅሽ። ለምን ሀገር ፍቅርን ለቀቅሽ?ሀገር ፍቅር እየሰራሁ ሳለ ውጪ አገር ሄጄ የመሥራት እድል አገኘሁ። ከዚያ በፊት ውጭ ሀገር ሄዶ መስራት የሚባል ነገር አስቤ አላውቅም ነበር። ሰዎችም ሂደሽ ሥሪ ብለው ሲያበረታቱኝ ለመሄድ ወሰንኩ። ሰርቼ ስመለስ ግን አልቀበልም አሉኝ። ሀገር ፍቅር ያደግኩበት፣ የተማርኩበትና ልምድ ያዳበርኩበት ቤት ስለሆነ ማስታወቂያ ሲወጣ ጠብቄ እንደገና ለመቀጠር ተወዳድሬ ነበር። ግን አሁንም ጥላ ትሄዳለች በሚል ነው መሰል ሊቀበሉኝ ፈቃደኛ አልሆኑም። በወቅቱ ደግሞ ተወዛዋዦችም፣ ድምፃውያኖችም ድንገት ሥራቸውን ለቀው ወደ ውጭ ሀገር ይሄዱ ስለነበር፣ መ/ቤቱን የለቀቀ ሰው አንቀበልም ብለው እንደ ሕግ ነገር

አውጥተው ነበር። ስለዚህ ወደ ሀገር ፍቅር መመለስ አልቻልኩም። እኔም የመቀጠር ሀሳቤን እርግፍ አድርጌ ተውኩት። ከዛ በኋላ ለሶስትና ለአራት ጊዜ ያህል ወደ ዱባይ ሄጄ ተመላልሼ ሰርቻለሁ።

በነገራችን ላይ የመጀመሪያ ካሴትሽ ውጤት አንዴት ነበር? ካሴቴ በውስጡ ጥሩ ጥሩ ሥራዎች ያሉት ነው። ያከፋፈልኩትም ራሴ ነኝ። ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው። ማለት በኦዲዮ ደረጃ ከ40 ሺህ ከቨር በላይ ተሽጧል። ነገር ግን ያከፋፈልኩትን ሁሉ በአንዴ አሰባስቤ ይኼን ያህል ብር አግኝቼበታለሁ፤ ተጠቅሜበታለሁ ማለት አልችልም። ይኼን ያህል ነው ያገኘሁት ማለት ባልችልም፣ አሁንም መብቱ የኔ ነው። በሲዲም እያሳተምኩት ነው። በክሊፕም ብሰራው መብቱ የኔ ነው። በዚህ ላይ በጣም የምወደው ገጣሚ ሞገስ ተካ፣ አቀናባሪው ዳዊት ጥላሁን (አሁን አገር ውስጥ የለም) አማኑኤል ይልማ እና የሌሎችም ጎበዝ ጎበዝ ባለሙያዎች አሻራ ያረፈበት ስለሆነ ያ ሥራ ለእኔ ልዩ ታሪክ ነው። አሳውቆኛልና ለእኔ ታሪካዊ ሥራ ነው። ይህም ራሱን የቻለ ውጤት አይደል?

እስቲ ወደ ሌላ ጉዳይ ወጣ እንበል። ህይወት ለአንቺ ምን ማለት ነው? የምትተረጉሚውስ እንዴት ነው? ለእኔ ህይወት? … (አሰብ አድርጋ) ህይወት ለእኔ ምስቅልቅል ናት። አንዳንዴ ጥሩ፣ አንዳንዴ መጥፎ ነገር ይከሰትባታል። ስለዚህ እንደአመጣጡ ነው የምተረጉማት።

በህይወት ደስተኛ ነሽ ወይስ? በሥራዬ I am so happy በጣም ደስተኛ ነኝ። የምፈልገው ሙያ ውስጥ ነው ያለሁት። እግዚአብሔር የሰጠኝ ሥጦታ ነውና በዓለም ደረጃ እንደኔ ሙያውን የሚወድ ያለ አይመስለኝም። ለሙያዬ በጣም ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬአለሁ። ሙያዬን አከብረዋለሁ። እሱም ያከብረኛል። እና በሙያዬ ደስተኛ ነኝ።

ዝናሽ ሀብታም ነሽ?በሙያ ደረጃ ሀብታም ነኝ። በሥራ ላይ ካለህ እኮ ሀብታም ማለት አንተ ነህ።

በአብዛኛው የሙዚቃ አፍቃሪ ዘንድ

‹‹ሀቢቢ›› በሚለው ዘፈን ነው

የምትታወቀው። በዚህ ዕውቅና የተነሳ

በተደጋጋሚ ከሀገር ውጪ ተጋብዛ

የመስራት ዕድል አግኝታለች። “ህይወት

ምስቅልቅል ያለች ናት” የምትለው ድምፃዊት

ዝናሽ ፀጋዬ፣ ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ጋር

አንዳፍታ ቆይታ አድርጋለች።

ህይወት ለእኔ

ምስቅልቅል ናት።

አንዳንዴ ጥሩ፣

አንዳንዴ መጥፎ ነገር

ይከሰትባታል። ስለዚህ

እንደአመጣጡ ነው

የምተረጉማት

አ ፍታ1‹‹ሙያዬን አከብረዋለሁ፤

እሱም ያከብረኛል›› ድምፃዊት ዝናሽ ፀጋዬ

በ ገፅ 23

‹‹የክረምቱ ጊዜ›› እና ‹‹ሌዲስ ፈርስት X›› ፊልሞች ይመረቃሉ

ማራኪ ፊልም ፕሮዳክሽን በትርሲት አግዝ የተደረሰውን ‹‹የክረምቱ ጊዜ›› የተሰኘ አዲስ የሕፃናት ፊልም ሰርቶ በማጠናቀቅ ነገ በሴባስቶቦል ሲኒማ ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ጀምሮ ሕፃናት፣ ወላጆች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ያስመረቃል። ፕሮዳክሽኑ ‹‹ከዚህ ቀደም በአኒሜሽን እና ፓፔት የሕፃናት ፊልሞች የተሰሩ ቢሆንም በተዋንያን (በሰዎች) የተሰራ ፊልም ባለመኖሩ ፊልማችንን “የመጀመሪያ” ለማለት ደፍረናል›› ብሏል።

በፊልሙ ላይ ሲራክ አግዝ፣ ኢዮስያስ ተካ፣ አልያስ ተስፋዬ፣ ኢየሩሳሌም ተሰማ እና ሌሎችም በትወና የተሳተፉበት ሲሆን የፊልሙ አጠቃላይ በጀት ሁለት መቶ ሺህ ብር መሆኑ ታውቋል።

እንዲሁም የደራሲና ዳይሬክተር በላይ ጌታነህ ‹‹ሌዲስ ፈርስት X›› የተሰኘ አስቂኝ የፍቅር ፊልም በሶፊ እና ጥበብ ኢቲ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ ነገ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በመላው የኢትዮጵያ ክፍሎች በተመሳሳይ ሰዓት ይመረቃል።

በፊልሙ ላይ ረቂቅ ተሾመ፣ ባህሬን ከድር፣ ህብረት በፍቃድ፣ ማህደር ሞገስ እና ሌሎች ከ400 በላይ ወጣትና አንጋፋ ተዋንያኖች እንደተሳተፉበት፣ የ1 ሰዓት ከ42 ደቂቃ ርዝማኔ እንዳለው እና 360 ሺህ ብር እንደወጣበት ፕሮዳክሽኑ አሳውቋል።

የአዳም ረታ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቅቷልበኢትዮጵያ ዘመናዊ የሥነ-ፅሁፍ ታሪክ በአጭር ልብወለድ አፃፃፍ ዓይነተኛ

ለውጥ እንዳመጣ በዘርፉ ባለሙያዎች የተመሰከረት፣ ደራሲ አዳም ረታ ስድስተኛ መፅሐፉን አሳትሞ ከሳምንት በፊት ለአንባቢያን አቅርቧል።

አዳም ረታ፣ በ1981 ዓ.ም “ማህሌት”፣ በ1997 ዓ.ም “ግራጫ ቃጭሎች”፣ በ2001 ዓ.ም “አለንጋና ምስር” እንዲሁም “እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ”፣ በ2002 ዓ.ም “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” የተሰኙ አምስት የልብወለድ ሥራዎችን ለአንባቢያን ማቅረቡ ይታወሳል።

አዳም ረታ አሁን ለህትመት ያበቃው ስድስተኛ መፅሐፉ ሲሆን፣ ርዕሱ “ያደርሳል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ” የተሰኘ ነው። አዳም ለአንባቢያን ያቀረበው ይህ መፅሐፍ የኖቤላ ልብወለድ ስብስቦችን የያዘ ሲሆን፣ በ456 ገፆች የተጠረዘ ነው። መፅሐፉ ገበያ ላይ የዋለው በ45 ብር መሸጫ ዋጋ ነው።

ጥንት ወንድ ጓዳ፣ ሴት አደባባይ ነበሩአሁን ባለንበት ዘመን ሴት ልጅን ‹‹ወደ ማጀትሽ›› ብንላት ላያስገርም

ይችላል። ከሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት ማድ ቤት ውስጥ የታየች፣

ቤትዋን ቤትዋን ያለች ሴት ‹‹ምን እንደወንድ መርመጥመጥ ነው!!›› ልትባል

እንደምትችል ከሰሞኑ ይፋ የሆኑ ጥናቶች እየጠቆሙ ነው። ]በጥንታዊ የሰው ዘር ቅሪት አካላት ላይ ጥናቱን የሚያካሂድ አንድ

ዓለማቀፍ ቡድን በአፍሪካ ዋሻዎች ውስጥ የተገኙ ጥርሶችን መሠረት በማድረግ

ሴቶች ውጪ ውጪ ይሉ እንደነበር፣ ወንዶች ደግሞ ከመኖሪያቸው አካባቢ

አንደማይርቁ ደርሼበታለሁ ብሏል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ በኮሎራዶ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዋ ሳንዲ ኮፕላንድ

የሚመራው ይህ ዓለማቀፍ ቡድን ከ1.7 እስከ 2.7 ሚሊዮን ዓመታት በፊት

በደቡበ አፍሪካ አካባቢ ኖረዋል የተባሉት ሁለት የጥንት ዝርያዎች ጥርሶቻቸውን

በመውሰድ ምርምሩን ይጀምራል። እነዚህ ሁለቱ ዝርያዎች ፓራንትሮፐስ

ሮበስተስ እና አውስትራሎፒቲከስ አፍሪካነስ የተባሉ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያዋ ሉሲ

ጭምር የምትካተትበት ለሰው ዝርያ ቅርብ የሆነው የአውስትራሎፒቴሲነስ ሀረግ

አካልም ናቸው። እናም በጥርሶቻቸው የላይኛው ክፍል (ኢናሜል) የሚገኘውን

የስትሮናቲየም አይሶቶፓች ለመለካት አዲስ የጨረር (ሌዘር) ቴክኒክ

ተጠቅመዋል። ይኼ ሁሉ እንግዲህ እነዚህ ሆሞኒዲሶች ከቦታ ቦታ እንዴት

እንደሚኖሩና ማህበራዊ ቡድኖችን እንዴት እንደሚመሰርቱ ለመረዳት የተደረገ

ነው። ምክንያቱም ይህ በጥርስ ላይ የሚገኘው ንጥረ ነገር የዚያን ጊዜው

የሰው ዝርያ በሕፃንነቱ የተመገበው ምግብ ከወዴት አከባቢ እንሚገኝ ለመጠቆም

የሚያስችል ነው። ታዲያ በኪሎ ሜትር ያህል በሚራራቁት ሁለት ዋሻዎች ውስጥ

በተገኙ ቅሪት አካላት ላይ ያሉት ጥርሶች ምርምር ሲደረግባቸው አብዛኞቹ

የሴቶቹ ጥርሶች ከእሩቅ ቦታ የሚገኙ ምግቦችን በሕፃንነታቸው መመገባቸውን

የሚጠቁሙ ሆኑ። የወንዶቹ ግን እጅግ ከጥቂቶቹ በቀር በአንድ ቦታ ላይ

ተወልደው በዚያው ቦታ ላይ መሞታቸውን ጠቆሙ። ሳንዲ ኮፕላንድ ቡድኗ የደረሰበትን የምርምር ውጤት ስታብራራ፣

እነዚህ ከጥንት የሰው ዘር ዝምድና ያላቸው ፍጥረታት እንደ ጉሬላዎች ጎረምሳ

ወንድ ቡድኑን ጥሎ የሚወጣበት ሳይሆኑ፣ በይበልጥ ከቺምፓንዚዎች ጋር

እንደሚቀራረቡ ትገልፃለች። ልክ እንደ ቺምፓንዚዎች ሴቲቱ የፍቅር አቻዋን

ፍለጋ አሰሳ ትወጣለች። ‹‹በብዙ አጥቢ እንስሳት ዘንድ ሁልጊዜ የሚኖሩበትን

ማህበረሰብ ጥለው የሚወጡት ወንዶች ናቸው›› የምትለው ሳንዲ ኮፕላንድ

በ19 ጥርሶች ላይ የደተረገው ጥናት ከሁለት ዓመታት ሚሊዮን በፊት በነዚህ

ዝርያዎች ዘንድ ተቃራኒው ሊሆን እንደሚችል መደረሱን ገልፃለች። በዚህ ጥናት ላይ ምልከታቸውን የሰጡ ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን

እንዲህ ባለ መጠነኛ የምርምር ናሙና ብቻ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንደማይቻል

ቢጠቁሙም ይህ ዓለማቀፉ የተመራማሪዎች ቡድን ጥናቱን ሲያካሂድ አጅግ

ዘመናዊና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሙ ተዘግቧል።

Page 12: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 200312 እ ን ግ ዳ

ገፅ 16

ካለው ታማኝነት አንጻር ነው። ግለሰቡ ለተመደበበት ሥራ የሚፈለገው እውቀትና ብቃት ከሌለው ከእርሱ ስር አንድ ለቦታው ብቃት ያለው ሰው ይመደብለታል” የሚል ነው። በበኩሌ በመሠረተ ሀሳቡ ላይ ምንም ልዩነት የለኝም። ይህ መርሆ የወያነ ፓርቲ ብቻ የሚከተለው ሳይሆን የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመሰረቱ አገራት ሳይቀር ሲሰራበት የምናየው ያለ እውነታ ነው።

እኔ በተጠጋሁበት አገር በዴንማረክ ባሁኑ ጊዜ

የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር አንዲት ወጣት ሴት ናት። ሴትየዋ ይህንን ሥልጣን የተሰጣት ለፓርቲዋ ባላት ታማኝነት ብቻ እንጂ በጦር ሜዳ በፈጸመችው ጀብዱ ወይም በሚሊተሪ ሳይንስ ብቃቷ አይደለም። ሚኒስትሯ አውቶማቲክ ጠመንጃና መድፍ ቀርቶ በእጇ የሽጉጥ ቃታ መሳቧንም እጠራጠራለሁ። ከሚኒስትሯ ስር ግን፣ አቶ መለስ እንዳለው፣ ዛ

ሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስትን ሥልጣን ጨብጦ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ‹‹ዓለምን ሊያስተምር የሚችል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እየተከተልኩ ነው›› ይላል። ይህንኑ ፌዝ ለጊዜው

ወደጎን አድርገን ሥርዓቱ ራሱ ውስጠ-ዴሞክራሲ አለው ወይ ብለን እንጠይቅ። እናም ዴሞክራሲያዊ ባህርይ የሌለው መሆኑን ከሚያሳዩ አያሌ ማስረጃዎች መካከል በጣም ቀላል የሆኑና ማንም (ስለ ፖለቲካ ምንም ግንዛቤ የሌለው) ወገን ሊረዳቸው የሚችሉ ጥቂት ምሳሌዎችን አንስተን የሥርዓቱን ምንነት በመጠኑ ግልጽ ለማድረግ እንሞክር።

ዛሬ ትግራይ አንድ ራሱን የቻለ የአስተዳደር ክልል ነው። በዚህ ክልል ውስጥ የትግራይ ተወላጆችና ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሌላ ብሔር ተወላጆችም ይኖራሉ። ስለዚህ ጠቅላላው የክልሉ ኗሪ ሕዝብ የህወሓት አባል ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት ያለው ነገር አይደለም። እንዲያውም ክልሉ የህወሓት ተቃዋሚዎች ጭምር የሚኖሩበት ክልል ነው። ከዚህም ሌላ ህወሓትን የማይደግፉም የማይቃወሙም ገለልተኛ የሆኑ ዜጎችም በክልሉ መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው።

ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ጉራማይሌ የሆነ ሕዝብ የሚኖርባት የትግራይ ክልል ባንዲራ ግን ህወሓት ከጫካ ይዞት የመጣው የራሱ የድርጅታዊ አርማ ወይም ባንዲራ ነው። ይህ የሚያሳየው ህወሓት የትግራይ ክልልና ሕዝብን ለዝንተዓለሙ ለመግዛት የቆረጠ ፓርቲ እንጂ አንድ ቀን በሌላ ፓርቲ ተበልጦ ሊተካ የሚችል ፓርቲ መሆኑን አይደለም።

በአንድ ዴሞክራሲያዊ መንግስት አለ እየተባለ በሚለፈፍበት አገር ቀርቶ ምንም ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ፣ በመፈንቅለ መንግስት ጭምር ገዥዎችና መንግስታት ሲለዋወጡ እንኳ የማይለወጡ ነገሮች ካሉ ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝብ መዝሙርና የመከላከያ ኃይሉ ነው። እንደው አለመታደል ሆነና የአሁኖቹ መሪዎች ይዘውልን የመጡት የራሳቸውን ባንዲራ፣ ሠራዊትና መዝሙር ነው። ለዚህ ነው ከእንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት ዴሞክራሲን መጠበቅ የዋህነት ነው የምንለው።

ዛሬ በኢትዮጵያ የሰፈነው የመንግስት አወቃቀር ቋንቋንና ብሔ ር / ብሔ ረ ሰ ብ ን መሠረት ባደረገ ፌዴራላዊ ሥርዓት ነው። ሕዝቦች በነፃነት መ ሪ ዎ ቻ ቸ ው ን የ ሚ መ ር ጡ በ ት ና የሚሽሩበት አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ካለ ይህ በመሠረቱ ችግር የለውም። የኢትዮጵያን ተጨባጭ

ሆኔታ በጥሞና ስንመለከት ኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖባት ያላትን እምቅ ሀብት ተጠቅማ ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ ለማድረስ ከተፈለገ ካሁን ወዲያ ከዚህ አወቃቀር የተሻለ ሥርዓት ማሰብ የሚቻል አይመስለኝም። ይህ ደግሞ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ በሆኑ አገራት (ለምሳሌ ካናዳ፣ ስዊዘርላንድና ቤልጄየም) በአግባቡ እየተሰራበት ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ ከነዚህ አገራት በበለጠና በተለየ ሁኔታ በዚህ ዓይነት ፌዴራላዊ ሥርዓት ለመዋቀር የሚያስገድዷት ብዙ ታሪካዊ ምክንያቶች አሏት።

ስለዚህ ሥርዓቱ በኢትዮጵያ በቀየሰው ፌዴራላዊ አስተዳደር ላይ ልዩነት የለኝም። ችግሩ የኢህአዴግ አመራር የአገሪቱን የዘመናት ችግር ይፈታል ሲል ብዙ የተናገረለትን የአስተዳደር ሥርዓት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ያለመያዙ ብቻ ሳይሆን ለድብቅ ስትራቴጂው እየተጠቀመበት ያለ መሆኑ ነው። ይህንን የምልበት ምክንያት ላስረዳ።

ከብቃት ይልቅ ፖለቲካዊ ታማኝነትንአቶ መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ በአደባባይ በይፋ

ግልጽ ያደረገው፣ “በገዢው ፓርቲ ቋሚ መርሆ መሠረት አንድ ሰው ለአንድ የአመራር ኃላፊነት ሲመደብ የግለሰቡ የትምህርት ደረጃ ወይም የሥራ ልምድና ብቃት መሠረት በማድረግ ሳይሆን ግለሰቡ ለፓርቲውና የፓርቲውን ፖሊሲዎች በማስፈጸም ረገድ

ትንታኔያቸውን ቀጥለዋል። ኢህአዴግን ከሌሎች መንግስታት ጋር ማነጻጸር “ስላቅ ነው” ቢሉም የሚኖሩባትን ዴንማርክ እየሳሉ ዲሞክራሲዋን ያሳዩናል። የህወሓትን ፍጹም የበላይነት፣ ከብቃት ይልቅ የታማኝነትን ተመራጭነት፣ የአቶ መለስን ብቸኛ መሪነት፣ የትግራይን ባንዲራና የመሳሰሉትን እያነሱ የሥርዓቱን ውስጠ-ዲሞክራሲ ይተቻሉ። ወደኋላ ግን በኢትዮጵያ

ምድር በጭንቀት የተወጠረ ሥርዓት እንዳለ ይገልፃሉ። ከዚያም ሥርዓቱ እራሱ የደረሰበት በቅርቡ ነው ያሉትን “ብዙ ሰው ያላወቀው” ምስጢር ያካፍሉናል።

ከአቶ መለስ

አምላኪዎች

እንደሚደመጠው፣ አቶ

መለስ የመሪነቱን ቦታ

የያዘው በኢህአዴግ

ውስጥ የእርሱን

ያክል ብቃት ያለው

ሰው ስለሌለ ነው

ይሉናል። ይህ በራሱ

አሳፋሪ ስድብ ብቻ

ሳይሆን ከትግራይ

ውጭ ያለውን

ሕዝብ እንደመናቅ

የሚያስቆጥር ነው።

“ብዙ ሰው

ምስጢር አለ!!”አብርሃም ያየህ

ያላወቀው

በ ገፅ 16

Page 13: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 200314

ዓ ለም አቀፍ

የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ከቅብጥ (Coptic) ቤተ-ክርስቲያን ጥገኝነት እንድትላቀቅ ለማድረግና አገራዊ ጳጳሳትን ለማፍራት ብዙ አድካሚ ትግል ተካሂዷል። ለዚህም ሃይማኖታዊ ብሔረተኞች ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል።

ለዘመናት የተካሄደው የሃይማኖት ብሔረተኝነት ትግል ካስገኘው ድል ትልቁና ዋነኛው ቤተ-ክርስቲያኒቱ በራሷ ሕግ መመራት መቻልዋና የራሷ የሆነ አመራር እንዲኖራት ማድረጉ ነው። ግንቦት 25 ቀን 1921 ዓ.ም አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ካይሮ ላይ ጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 124 የሚሆኑ ኤጲስ ቆጶሳት ተሹመዋል። ብዛት ያላቸው አህጉረ ስብከት ተቋቁመዋል። የዲቁናና የቅስና ሹመት ለማግኘት አዲስ አበባ ድረስ ይደረግ የነበረው አድካሚ ጉዞ ቀርቶ በየአህጉረ ስብከቱ ሹመት ማግኘት ችለዋል።

ይሁን እንጂ ከብዙ ዘመናት ውጣ ውረድና እልህ አስጨራሸ ትግል በኋላ የተገኘው ‹ራስን በራስ ጳጳሳት› የማስተዳደሩ ሁኔታ በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና እክል የገጠመው ይመስላል ሲሉ አንዳንዶች ትችት ይሰነዝራሉ። ሰሞነኛውንም ሢመተ ጵጵስናን የመናኘት (የሚቀራመት) ጽኑ ፍላጎታቸውንም የእክሉ አንዱ ገጽታ አድርገው የሚወስዱ ብዙዎች ናቸው።

የ1991 ዓ.ም ሕገ ቤተ-ክርስቲያን እንደሚደነግገው፣ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስፈላጊ መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን፣ በሥርዓተ ምንኩስና በድንግልና መንኩሰው ቤተ-ክርስቲያንን ከሚያገለግሉና ለኤጲስ ቆጶስነት ብቁ ከሆኑት ቆሞሳት መካከል በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ዕጩ ሆኖ ሲቀርብ ለኤጲስ ቆጶስነት ዕጩ ሆኖ የሚቀርበው ቆሞስ በመነኮሰበት ገዳም ከሦስት ዓመት ባላነሰ ጊዜ ያገለገለ፣ በትምህርተ-ሃይማኖት በቂ ችሎታ ያለውና ቀኖና ቤተ-ክርስቲያንን ጠንቅቆ ያወቀ፣ በግብረ-ገብነቱ የተመሰገነ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ፅኑዕ የሆነ፤ እንዲሁም በሚመረጥበት ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚሰየም አስመራጭ ካሚቴ ተጠቁሞ የቀረበ መሆን እንደሚገባው በአንቀጽ 18 ከንዑስ ቁጥር 1-4 ሰፍሯል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህን የሕገ-ቤተክርስቲያን ድንጋጌ እና የቀኖና ቤተ-ክርስቲያን በመተላለፍ በሃይማኖትም ሆነ በምግባር ነቀፋ ያለባቸውንና በሕጹጽ ድርጊቶቻቸው ሕዝቡ የሚያውቃቸውን በርከት ያሉ ቆሞሳትን ለመሾም ራሳቸው መልማይ፣ ራሳቸው ዕጩ አቅራቢ ሆነው የስም ዝርዝራቸውን ለቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ በዚሁ ሰሞን በተደረገው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ ቢጠይቁም ተቃውሞ እንደገጠማቸው ተሰምቷል።

ሢመተ ጵጵስናን

የመናኘት መነሻየቤተ ክርስቲያኒቱ አገልገሎትና

የሥራ ክፍሎች ከመስፋፋታቸው፣ ጥቂት የማይባሉ አባቶች በሞተ-ዕረፍት በመለየታቸው፣ አንዳንድ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አህጉረ ስብከትን ደርበው እያስተዳደሩ መሆናቸው ለአሠራር ከሚፈጥረው ጫና፣ ከዕርግና እና ሕመም የተነሣ ዝውውር እና ዕረፍት የሚሹ አባቶች እንዳሉ መነገሩ የኤጲስ ቆጶሳትን ጥያቄ አግባብ ቢያደርገውም የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን እና ተግባር እንዲሁም ‹ከጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ያፈነገጠና ያለወቅቱ የቀረበ› በማለት ቅሬታ የሚያቀርቡ አሉ።

እንዲህ ዓይነቱን ትንተና የሚያቀርቡ ወገኖች የአባ ጳውሎስን ሢመተ ጵጵስናን የማቀራመቱን ጽኑ ፍላጎት /Motive/ በመጠራጠር ቅዱስነታቸው ሢመተ ጵጵስናን በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አጀንዳ ማድረግ የፈለጉት ከላይ የተጠቀሱትን ክፍተቶች ለመሙላት ከማሰብ ሳይሆን

እንዲሟሉላቸው እና እንዲመቻቹላቸው ከሚሿቸው ውስጣዊ ሁኔታዎች ተነስተው ነው ይላሉ። እነዚህንም በሦስት ፈርጆች ከፋፍለው ያስቀምጣሉ።

የተጽዕኖ ሚዛንን / balance of power/ ለማስጠበቅ፡-

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሲኖዶስ ውስጥ ያላቸው የተጽዕኖ ሚዛን /balance of power/ የመሸርሸር ምልክት እየታየበት ነው። በ1991 ዓ.ም ሕገ-ቤተክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ-ሐ እንደተደነገገው፣ በአሥራ ስምንት ዓመት ዘመነ ፕትርክናቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ቀኖና እየጠበቁ አይደለም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያስነቅፉ ተግባራትም እየተፈጸሙ ነው የሚሉ ምሬቶችም እየተነሱባቸው ይገኛሉ።

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤም ሆነ በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎች ላይ ያልተለመዱና ጠንከር ብለው የወጡ ተቃውሞዎች መኖራቸው የተጽዕኖ ሚዛን ለውጥ ስለመፈጠሩ አመላካች ናቸው የሚሉም አሉ። ይህ ደግሞ በቅዱስነታቸው ላይ ሥጋት መፍጠሩ አይቀሬ ነው ሲሉም የቤተ-ክህነቱን ፖለቲካ (church politics) በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ሀሳብ በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ።

ቅዱስነታቸውም፣ የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት አጀንዳ በቋሚ ሲኖዶስ እና በምልአተ ጉባኤ ተግዳሮት እንደገጠመው ቢገለጽም በራሳቸው ለማቅረብ የወሰኑበት ምክንያት “በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተነቅንቋል” ብለው የሚያስቡትን መንበረ ሥልጣን ሊታደጉልኝ ይችላሉ የሚሏቸውንና ብዙ ተቀባይነት የሌላቸው በመሾም ተግዳሮት እየገጠመው ያለውን የተፅዕኗቸውን ሚዛን ለማስጠበቅ እንደሆነ እነዚሁ የቤተ-ክህነቱን ፖለቲካ የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ። ከዚህም በላይ በቅዱስነታቸው ከታሰቡት ተሿሚ ዕጩዎች ጥቂት የማይባሉት በሥነ-ምግባር ብቻ ሳይሆን በሃይማኖትም አለባቸው የሚባለው ነቅ ሲታይ ጉዳዩን የተጽዕኖ ሚዛን ማስጠበቅ ብቻ አያደርገውም። ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ህልውና እና የማንነት ቀጣይነትም ለአደጋ ያጋልጣል። ነገ በቅዱስ ሲኖዶስ መንበር ተቀምጠው ሕግ የሚያወጡት፣ ዐበይት ውሳኔዎች የሚያሳልፉት ሌሎች ኤጲስ ቆጶሳትን እና ካህናትን የሚሾሙት የዛሬዎቹ የአንድ እጅ ‹ኅሩያን› ናቸውና።

ትኩረት ማስቀየሻ ስልት /

diversionary tactic/፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቅዱስነታቸው

“ያልተገራ” ሥልጣንና አመራር ጋራ ተያይዞ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ጥቂት ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያንና የቤተ-ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ ምእመናን በቅዱስነታቸው ላይ የሚያቀርቡት ክስና ተቃውሞ እየጠነከረ መጥቷል።

በቤተ-ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚታዩት ዋነኛ ችግሮች የመልካም አስተዳደር

እጦት፣ ቤተሰባዊ አስተዳደር፣ የተደራጀና ሥር የሰደደ ሙስና፣ የቀኖና ቤተ-ክርስቲያን ጥሰት /የቅዱስነታቸው የምስክርነት ሐውልት፣ በየአጥቢያው የተሰቀሉት ፖስተሮች ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው/፣ እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮ ውጭ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ያሏቸውን የአንድ ወይዘሮ እና የአንዳንድ “የአጉራ ዘለል” ሰባኪያን አሉታዊ ተፅዕኖ በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው።

እነዚህ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ህልውና እየተፈታተኑ የሚገኙት ችግሮች የተፈጠሩት በዋናነት በቅዱስነታቸው ምክንያት በመሆኑ እነዚህ ዋነኛ ጉዳዮች እንዳይነሱና የቤተ-ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግር ያልሆነውን ሢመተ ጵጵስናን በአጀንዳነት በማንሳት ጭቅጭቅ ፈጥሮ ትኩረት የማስቀየስ ስልት ነው ሲሉም ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ግምታቸውን ይሰጣሉ። በየጊዜው የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ገቢራዊ ባለመሆናቸው ሳቢያ የምእምናን ግፊት የበረታበት ቅዱስ ሲኖዶስም ቅዱስነታቸውን ተጠያቂ ማድረግ መጀመሩ እንዲህ ያሉ አወዛጋቢ አጀንዳዎችን እንደ ማስቀየሻ ስልት እንዲፈጥሩ አስገድዷቸዋል።

እርቀ ሰላሙን የማኮላሽት ስልት፡-

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ አባቶች እና እዚህ አገር ቤት ባለው ሲኖዶስ መካከል “የቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሰት” ተፈጽሟል በሚል የከረረ ጠብ መኖሩ የሚታወቅ ነው። የእርቁም ሂደት በተደጋጋሚ ከቅዱስነታቸው በጎ እይታ እንዳልገጠመው ብዙዎች የሚናገሩት የአደባባይ ሐቅ ነው።

ከዚህ አኳያ ቅዱስነታቸው እርቀ ሰላሙን ለማደናቀፍ የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት አለመፈጸምን ቅድመ

ሁኔታ በመተላለፍ እና ከተሳካላቸውም ጳጳሳትን በመሾም በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አባቶችን ከእርቀ ሰላሙ ሂደት ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ በተስፋ የሚጠበቀውን የቤተ-ክርስቲያን አንድነት ጨርሶ እንዲከስም የማድረግ ስልት ነው በማለት በስጋት የሚገልጹ ወገኖች ቁጥርም ቀላል አይደለም።

የሢመተ ጵጵስናው

መግፍኢ ሥረ-ነገርየሢመተ ጵጵስና መግፍኢ ሥረ-ነገር

ከሁለት ወገን ይመነጫል። የመጀመሪያው ከራሳቸው ከቅዱስነታቸው መንታ ሥነ-ልቡና ነው። አንደኛው የኅሩያነ ምስፍና ሥነ-ልቦናዊ ዘይቤ ነው። ራሳቸውን ከቀደሙትም ሆነ አሁን ካሉት አባቶች የተሻሉ እና ምርጥ አድርገው ስለሚመለከቱ፣ አባት የሆኑለትን ሕዝብ እንዲሁም በፕትርክና ለሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ቦታ አይሰጡም። የወሰናቸውን ውሳኔዎች ገቢራዊ አያደርጉም፤ የሥልጣናቸውን ምንጭ የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተሰሚነት በመንሳት በአስተዳደሩ ውስጥ የሥልጣን ሞኖፖሊን አስፍነዋል።

ራሳቸውን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ አባት ወይም መነኩሴ ከማየት ይልቅ እንደ ንጉሥ የማየት የኅሩያን ምስፍና ሥነ-ልቦናዊ (Aristocracy psychological make-up) ጫና ይበዛባቸዋል የሚል ግምት የሚሰጡም አሉ።

ሁለተኛው የሢመተ ጵጵስና መግፍኢ ሥረ-ነገር ዙሪያቸውን ከከበቧቸው ጥቅመኞች ጽኑ ፍላጐት ይመነጫል። ይህ የጥቅም ኃይለ-ግብር ምንም ዓይነት መዋቅራዊ ሥልጣንና ተግባር ሳይኖረው ቤተ-ክህነቱ ውስጥ አዛዥ፣ ናዛዥ ሿሚና ሻሪ ነው። ሊቃውንቱ የዚህን

የሚያሳስበው ከዓለም ወጥተናል መንኩሰናል ያሉት ሳይቀሩ መጠጥ ቤት ውስጥ ሲዘዋወሩ የሚታይበት አስከፊ ዘመን ላይ መሆናችን ነው።

ስለዚህም ጉዳይ ቤተክርስቲያን አንድ ነገር ማድረገ ያለባት ይመስለኛል። የምናወራው ስለግለሰቦች የመዝናናት እና ያለመዝናናት መብት ብቻ አይደለም። ስለአገር ሥነ-ምግባር እና ስለዜጎች ሞራልና ጥቅም ነው። ሲጀመር የሌሊት ዳንስ ቤቶች እና የዝሙት ስፍራዎች በልክ እንዲሆኑ ከመንግሥት ጋር በመሆን አንድ ነገረ ብታደርጉ። የምንኩስና ልብስ ለብሰው በየመጠጥ ቤቱ የሚገቡትን ደግሞ ቢያንስ የምንኩስና ልብሳቸው በቦታው መገኘት ስለሌለበት አስፈላጊውን እርምጃ (የሕግም ቢሆን) ብትወስዱ።

ለየኑሮ ውድነት ሕዝቡን እንዲህ

ሲያንጫጫ ቤተክርስቲያኒቱ ምን እያደረገች ነው?

ዛሬ ከትንሽ እስከ ትልቅ ስለኑሮ ውድነት፣ ስለርሃብ፣ ስለገንዘብ እጦት የማያወራ የለም። ሁሉም በቻለው መልኩ

የትርምስ ኃይለ-ግብር ቡድን መሪ አንድ ሴት ናቸው ካሉ በኋላ ስለእኚህ ሴት ሲያብራሩ፤ ‹እኚህ ወ/ሮ በየትኛውም የቤተ-ክርስቲያኒቱ መዋቅር የታወቀና የተረዳ ሥልጣንና ተግባር ሳይኖራቸው የፈለጉትን ተደራድረው ያሾማሉ፤ ያልፈለጉትን ያሽራሉ፤ የፈለጉትን የውሳኔ ሀሳብ አቅርበው በፓትርያርኩ በኩል ያስወስናሉ፤ ያልፈለጉትን ውሳኔ ያሽራሉ› በማለት ነው።

የዚህ “ኪራይ ሰብሳቢ” ኃይለ-ግብር ተጠቃሚነት ዘላቂ የሚሆነው ቅዱስነታቸው በሕይወተ ሥጋ እስካሉ እና እርሳቸውን ዕረፍተ ዘመን ሲገታቸው ደግሞ የሚያሾሟቸው የጥቅም አጋሮቻቸው የቅዱስ ሲኖዶስን የኃይል ሚዛን መለወጥ ሲችሉ ብቻ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ከዚህ በኋላስ….ቋሚ ሲኖዶስም ሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ

ምልአተ ጉባኤ የቅዱስነታቸውን የሢመተ ጵጵስና ሥረ-ነገር በሕገ ቤተክርስቲያን አግባብ ተረድቶ የሢመተ ጵጵስናውን አጀንዳ ውድቅ አድርጓል። ይህ ደግሞ ለቅዱስነታቸውም ሆነ በዙሪያቸው ሆነው እንሾማለን ብለው የቤተ-ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ከስክሰው እጅ መንሻ ለሰጡት፣ ባሕር አቋርጠው ለመጡት፣ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ደጅ ለጠኑት፣ ድግስ ደግሰው ጳጳሳቱን ለአበሉት እና በጉጉትና በአምሮት ፈረስ ላይ ተቀምጠው የጵጵስናውን አስኬማ ገዝተው ለአስቀመጡት ቆሞሳት መርዶ ነው። የሢመተ ጵጵስናውን መከናወን /መፈጸም/ ለሚቃወሙት ደግሞ ሐሤት ነው። ይህን ጽሑፍ በማዘጋጅበት ወቅት ሲኖዶሱ የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት ጥያቄ ራሱን የቻለ ቅድመ ዝግጅት እንደሚያሻው በመረዳት አጀንዳውን ወደ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ማስተላለፉ መልካም ዜና ሆኖልኛል።

የቅኔው ሊቅ መጋቢ ምስጢር ወልደሩፋኤል፣ “ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ሊቃውንት ጳጳስ አይሹም” ከሚለው የፍትሐ ነገሥቱ የግብፃውያን ‹‹የቀንበር ማጥበቂያ›› ቀኖና ጋራ በማዛመድ የተቀኘውን ቅኔ የጽሑፋችን ማጠቃለያ እናድርገው።

ሰብአግብጽሂ በእንቲአነ እለተነበዩ ቅድመ።

ከመኢይበሉ ዘነበብነ ትንቢትነ ተፈጸመ።

አስኬማክሙ ዕቀቡ ወኢትግድፍዋ ግድመ።

ለአስኬማክሙ ዜና ገድላ እስመ በጊዜነ ኢአደመ።

(‹‹ስለእኛ አስቀድመው ትንቢት የተናገሩ፤

የግብፅ ሰዎች የተናገርነው ትንቢታችን

ተፈጸመ እንዳይሉን፤ አስኬማችሁን ጠብቁ፤ ወደጐንም አትጣሏት፤የአስኬማችሁ የተጋድሎ ዜና

በዘመናችን አላማረምና››)

ብሶቱን ለመንግሥት እያሰማ ይገኛል። መንግሥት ጠብ የሚል ምላሽ አይሰጥም። በየወሩ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር የኑሮ ውድነቱንም በተለያየ ገፅታ እያፈራረቀ ዜጎችን እያስጨነቀ ይገኛል።

ይህንን ችግር መንግሥት ጆሮ እንዲሰጠው ቤተክርስቲያኒቷ ምን እያደረገች ነው? ከዚህ ላይ የቤተክርስቲያን ዋና ተግባር ወደ እግዚአብሔር ወደ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ግና እግዚአብሔር የሚሰራው በሰዎች ምክንያትነት እንደመሆኑ ከመንግሥት ጋር በቅርበት በመሆን ለዜጎች የሚበጀውን ነገር መስራት የሚገባ ነገር ይመስለኛል። ይህ ማለት የፖለቲካ ሥራ ማለት አይደለም። የአባትነታችሁን ለልጆቻችሁ ተጨነቁ ለማለት ነው።

የራበው ዜጋ ከሥነ-ምባር ይወጣል። የቸገረው ሰው ከጤናማነት መስመር ይወጣል። የጠማው ሰው ቅርበቱ ለወንጀል ነው። ኑሮው አልሳካለት ያለ ሰው ሃይማኖቱን፣ ሀገሩን፣ እግዚአብሔርን ወደመሳደብ ያደላል። የታዛዥነትን መንፈስ ያጣል። ከእግዚአብሔር እቅፍ

መራቅን ይወዳል። እናም ይህንን ወቅታዊና ሀገራዊ ችግር ከመንግሥት ጋር በመሆን ዜጎች ያለጭንቀት ሰርተው የሚኖሩበትን ሥርዓት መፍጠር ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ።

ወደመግቢያዬ አካባቢ የሚሰማኝ አለ ወይስ የለም የሚል ስጋት እንዳለብኝ መግለጤ ከዚህ ቀደም ዲያቆን ሕዝቅያስ ማሞ በአንድ መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለው የፃፉትን አንብቤ ስለነበር ነው፡-

‹‹እናንተ ግን ራቅ ወዳሉ ገዳማት ከቤተሰብ

ተለይታችሁ የገባችሁት በምንኩስናና በባዕት

የፀናችሁበት ጥቁር በጥቁር ለብሳችሁ ካማረ እንጀራ-

ዳቦ፣ ከተመቼ መኝታ - መሬት የመረጣችሁት

ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ዓለምን ስላዳነው መድኃኒት

ፍቅርና ስለመንግሥተ ሰማያት ብላችሁ ነበር። ወይስ

ከመጀመርያው ምርጫችሁ አሁን የተገለጣችሁበት

ፖለቲካ ነው? ሰው መንፈሳዊ ሳይሆን ለማስመሰል

ለማታለል ቢጥር ከፊቱ እሱነቱ የሚለካበት ጊዜ

ይመጣና ማንነቱ ፍንትው ብሎ ይወጣል። አሁን

እናንተ በመንበሩ ላይ በነበራችሁበት ዘመን የነበሩ

የሀገሪቱ መሪዎች በዚህ ምስኪን ሕዝብ ላይ ጅራፍ

ሲያወርዱበት በሀዘን አንገቱን ሲያስደፉ ያለ ከልካይ

ሲያስለቅሱት በዝምታ አልፋችኋል።›› ዲ/ን ህዝቅያስ ማሞ (ብኩርናውን

እርሱት፤ ገፅ 128)ሕዝብን የማይሰማ መንግሥት በናንተ

በብፁአን ቢጠየቅ ሊራራ ይችላል።

እናንተም እንደአባትነት ለኢትዮጵያ ዜጎችም አባት ናችሁና ዜጎች በልተው ጠጥተው ተደስተው ረክተው ይኖሩ ዘንድ የማድረጉ ኃለፊነት በላያችሁ ላይ ነው።

ግና ብዙ ጊዜ ትታማላችሁ። እንደምንሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱም ጉባዔያት በየጊዜው በጭቅጭቅ ተጀምረው በንትርክ የሚጠናቀቁት መንግሥትን ለመምከርና ለመገሰፅ የሚያበቃ ቅድስናና ጥበብ ኖሮ ሳይሆን፣ መንግስትን የመሰለ የፖለቲካ አቋም ስላለችሁ ይመስላል።

ለዚህ ፅሁፍ ሁለተኛው መነሻዬ ገና አልተነካም። ሌላም ለቤተክርስቲያን አባቶቼ የማነሳው ጥያቄ አለኝ። ዛሬን እዚህ ላይ ተሰናብቼ ሳምንት ልቀጥል። መድኃኔዓለም ቢፈቅድ ላነሳኋቸው ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ አገኝ ይሆናል።

እንደመውጫ ልጅነት የለገሰንንበመለኮት የቀባንንበእሳቱ ያጠመቀንን

የፍቅር አምላክ በጥበቡበሥልጣን ያለበሰንን

ፈራን አዎን እውነት ፈራንየስሜት እስትንፋስን ነሳን

ፀጋዬ ገ/መድኅን (እሳት ወይ አበባ)ቸሩ ያሰንብተን!

ጥያቄዎች...

ሢመተ ጵጵስናን የማቀራመት ጽኑ መግፍኢሁለተኛው የሢመተ ጵጵስና መግፍኢ ሥረ-

ነገር ዙሪያቸውን ከከበቧቸው ጥቅመኞች

ጽኑ ፍላጐት ይመነጫል። ይህ የጥቅም

ኃይለ-ግብር ምንም ዓይነት መዋቅራዊ

ሥልጣንና ተግባር ሳይኖረው ቤተ-ክህነቱ

ውስጥ አዛዥ፣ ናዛዥ ሿሚና ሻሪ ነው።

በባሮክ ዘሣልሣይ ሺሕ

Page 14: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15

በንፍታሌም

‹‹በዓለም ላይ ካሉ፣ ፍጡራን መሀከልህይወት የምንለው

በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰልየበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል።››

ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው)ባለቅኔው ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው)

በ1950ዎቹ ዓ.ም አጋማሽ ‹‹የበሰለው ያራል›› በሚል ርዕሥ የከተበውን ድንቅ ግጥም ለዚህ መፅሐፍ ዳሰሳ መንደርደሪያ ይሆነኝ ዘንድ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በዛሬው የወፍ በረር ዳሰሳ የምንቃኘው ይህ መፅሐፍ (የጉዞ ማስታወሻ) በውስጡ ያጨቃቸው አንዳንድ ትረካዎች አንባቢን የሚያናድዱ፣ የሚያበሳጩ፣ ጠንከር ባለ አገላለፅ ‹‹የሚያሳርሩ›› ዓይነት በመሆናቸው ነው።

በቅድሚያ የዚህ መፅሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ፣ መፅሐፉ እጁ ገብቶ ካነበበው በኋላ፣ ለወራቶች ያህል ከራሱ ጋር ሙግት እንደገጠመ ለአምዱ ተከታታዮች መግለፅ ይወዳል። ለምን? መልሱን ጥቂት መስመሮች ወረድ ብለው ያገኙታል። ለማንኛውም ዳሰሳችንን እንቀጥል። እነሆ፡-

ከላይ እንደተገለፀው ደራሲው ጣሂር ሻህ ‹‹IN SEARCH OF KING SOLOMON’S MINES›› በሚል ርዕሥ የፃፈውን የጉዞ ማስታወሻ በመፅሐፍነት ለህትመት ያበቃው እ.አ.አ በ2002 ዓ.ም ነው። ከስምንት ዓመት በፊት ማለት ነው። ይህንን መፅሐፍ ነው ብሩክ መኮንን እና እንቆጳጽዮን ሀብታሙ ‹‹የኢትዮጵያ ወርቅ ምስጢር›› በሚል ርዕሥ በጋራ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰው ለህትመት ያበቁት።

ደራሲው ጣሂር ሻህ ለጉዞ የተነሳው ከለንደን መሆኑን ነው የገለፀው። ከዚያም ወደ እስራኤል ሀገር ሄዶ የሰለሞንን ቤተመቅደስ ይጎበኛል። ከ‹አሊ ባባ› የቱሪስት ዕቃዎች መሸጫ ሱቅ ‹‹የተደበቀ ኃብት የተቀመጠበትን ቦታ የሚጠቁም ካርታ›› (ገፅ 1) ይገዛል። ይህ ካርታ ‹‹የንጉስ ሰለሞን የወርቅ ጉድጓዶችን›› ይጠቁማል መባሉ፣ ቦታውን አስሶ የማግኘት ፍላጎቱን ያንረዋል። የተለያዩ ጥንታዊ ኃይማኖታዊ መፅሐፎችን፣ የሀገር አሳሽ መረጃዎችንና ሌሎች ሰነዶችን በማንበብ የሰለሞን ቤተመቅደስ የተሰራበት ወርቅ የተገኘው (የመጣው) ከኢትዮጵያ ነው የሚል መላ ምት ላይ ይደርሳል። እናም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በሰባት አቅጣጫዎች አሰሳ ማድረጉን ነው መፅሐፉ ሙሉ በሙሉ የሚተርከው።

ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያየሁት ወይም የገጠመኝ ብሎ ያሰፈራቸው ተረት መሰል ትረካዎች አንባቢዎችን የሚያሸማቅቀው፣ ከዋና ከተማዋ ተነስቶ ወደ ሰባቱ አቅጣጫዎች ከመጓዙ በፊት በአዲስ አበባ ገጠመኝ ካለው ጉዳይ ጀምሮ ነው። ይህ ትረካ ‹‹ተረት›› ሊባል እንኳ የሚበቃ አይደለም። እናም የሚያነበው ሰው ሁሉ መናደዱ አይቀርም። ንዴቱን አምቆ ንባቡን የሚቀጥል ሰው፣ በደራሲው አንዳንድ ትሪካዎች መገረሙና የኋላ ኋላ ደግሞ እንደቀልድና መዝናኛ ቆጥሮ እስከመጨረሻዋ ገፅ መዝለቁ አይቀርም ብዬ እገምታለሁ። ለማንኛውም የዚህ ዳሰሳ ፅሁፍ አቅራቢ ከጅምሩ የተናደደበትን ታሪክ መሰል ተረት እንደወረደ ሊያቃምሳችሁ ይወዳል። እነሆ፡-

‹‹… ከሁለት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ከደረስኩበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎች ራሴን ከዕብድ ውሾች እንድጠብቅ ያስጠነቅቁኝ ነበረ። ሁሉም የኢትዮጵያ ውሾች ተናካሽ እንደሆኑ በኩራት ይናገራሉ። … ከአንድ ሰዓት በኋላ ራሴን በሌላኛው የአዲስ አበባ ክልል በአንድ የቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ አገኘሁት። የሀኪሙን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች ፊት ለፊት ካለው ግድግዳ ተስቅለዋል። ለዶክተሩ ታፋዬ ላይ ያለውን ቁሰል እያሳየሁ ፊቴን አጨማደድኩ። ዶክተሩ የነከሰኝ ውሻ ዓይን ፈጦ እንደነበር ሲጠይቀኝ የአዎንታ መልስ ሰጠሁ።

ዳ ሰ ሳ

‹በአፉ ዙሪያ ነጭ አረፋ ነበር?›‹አዎ› የቀዶ ጥገና ሃኪሙ ከንፈሩን መጠጠ።

‹ያበደ ውሻ ነው› በማለት በፍራቻ ገለጸ። ‹ሆዴ ላይ ሀያ መርፌ ትወጋኛለህ?›

አልኩት። ‹ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ዕብድ ውሻ

በሽታ መድሀኒት የለም። ወደ ሆቴልህ ሄደህ እረፍት ብታደርግ ይሻላል› አለኝና የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መፃፍ ጀመረ።

‹አረፋ መድፈቅ ብጀምርስ?› ‹ሌሎች ሰዎች አትንከስ› አለ።›› (ከገጽ 23-24 የተወሰደ)ይህቺን ቃል በቃል ከመፅሐፉ

የተወሰደች ክፍል ብቻ ስታነቡ ምን እንደሚሰማችሁ እገምታለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ እብድ ውሻ አለ፤ የእብድ ውሻ መድሀኒት ግን የለም ማለት ምን ማለት ነው? ደራሲው (ፀሐፊው)፣ ዶክተሩ የሙያ ፍቃድ እንዳለው ነግሮናል። ዶክተሩ መድሀኒቱ ባይኖረው እንኳ፣ መድሀኒት ወይም ህክምናው የሚገኝበትን ቦታ ያልጠቆመው ለምንድነው? … ለመሆኑ ይኼ ሁኔታ የገጠመው መቼ ነው? እንደደራሲው አተራረክ ከሆነ በ1990ዎቹ (እ.አ.አ) ነው። በዚህ ዘመንና ጊዜ የእብድ ውሻ በሽታ ህክምና ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለው ወይም የማይኖረው እንዴት ነው? አረፋ ስትደፍቅ ሌሎች ሰዎችን አትንከስ ብሎ መልስ የሚሰጥ፣ ሰርተፍኬት ያለው አላጋጭ ዶክተር በዋና ከተማ አዲስ አበባ አለ ማለትስ ማንን ያሳምናል? ለመሆኑ ይህን ማስታወሻ የፃፈው ሰውና ‹‹ዶክተሩ›› በየትኛው ቋንቋ ይሆን የተነጋገሩት? በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከሆነ ይህንን አይነት የተዛባ መረጃ ሊፅፍ አይበቃም ብዬ እገምታለሁ። ይህም ደግሞ ወደ ሕጋዊው ሀኪምና ህክምና ቦታ አልሄደም ብዬ እጠረጥራለሁ። ወይም ቀድሞውኑ ኢትዮጵያ ለምትባል ሀገር ቀና አመለካከት የለውም ነበር ማለት ነው።

ለዚህ አባባል አብነት የሚሆነን አሳሹ ተጓዥ በአዲስ አበባ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን ከጎበኘ በኋላ (ባታ ቤተክርስቲያንን) የሰለሞን ቤተመቅደስ የተሰራበት ወርቅ የወጣበት ቦታ ነው ብሎ መላ ምት ወደሰነዘረበትና ከሀረር ወጣ ብሎ የሚገኝ ዋሻ ውስጥ አየሁት ብሎ የፃፈውንና የተጠቀመበትን አገላለፅ መጥቀስ ይበቃል። (ገፅ 51) ይህንን አገላለፅ እዚህ ላይ ቃል በቃል መጥቀስ ራስን እንደመዝለፍ ስለሚቆጠር መተውን ነው የመረጥኩት።

የሆነ ሆኖ የጣሂር ሻህን የጉዞ ማስታወሻ እያነበቡ ሲዘልቁ በፀሐፊው የተዛባና የማይመስል አገላለፅ ሳይወዱ በግድ ፈገግ ማለትዎ አይቀርም። ፀሐፊው ወይ ፌዘኛ ነው ወይም ‹‹ዕብድ ነው›› ለማለት ይገደዳሉ።

ሀገር ጎብኚውና አሳሹ የጉዞ ማስታሻ ፀሐፊ የመላምቱን እውንነት ለማረጋጥ ወደ ሻኪሶ የወርቅ ማውጫ ሥፍራ ለመጓዝ በክብረ-መንግስት ከተማ መኪና ያፈላልግ እንደነበር ጠቅሶ፣ አንድ ቶዮታ መኪና ማግኘቱን ይነግረናል። እናም

በሸውራራ ዕይታ ‹‹የኢትዮጵያ ወርቅ ምስጢር››ን ፍለጋስለመኪናዋ ሁኔታ እንዲህ ሲል ይተርካል፡-

‹‹ … የጴጥሮስ መኪና በቅርቡ ግጭት ገጥሟት እንደነበር ከፊት ለፊቷ ጭርምትምት ያሉት ብረቶች ይናገራሉ። ሌላ ሀገር ቢሆን ኖሮ መኪናዋ ወደ ተጨፈለቀ ብረትነት እንድትቀየር ለመወሰን አንድ ደቂቃ አይፈጅም ነበር። የመኪናዋ በሮች ከቀሪው አካል ጋር ተበይደዋል። በዚህ ምክንያት መግባትና መውጣት የሚቻለው በመስኮት ነው። የመኪናው መሪ በብረት ዘንግ መተካቱ በራሱ ሥጋት ይፈጥራል።›› (ገፅ 87)

እርግጥ ነው ኢትዮጰያ ውስጥ አገልግሎት መስጠት የማይገባቸው መኪናዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ አይካድም። ነገር ግን መላ አካላቸው የተበየደና በር የሌላቸው

መኪኖች አገልግሎት ይሰጣሉ ብሎ መቀበል ለማንም ሰው ህሊና ቅቡል ነው ብዬ አላምንም። አንደኛ ነገር፣ በመስኮት ብቻ እየወጣና እየገባ መስራት እችላለሁ ብሎ የሚገምት ሰው ምን አይነት ሰው ነው? ማንስ ነው በመስኮት እየገባና እየወጣ መኪናው ይጠቀመኛል ብሎ የሚያስበው? ሁለተኛው ነገር፣ ባለመኪናው መኪና አለኝ ብሎ ቢያምን እንኳ ማነው በመስኮት ገብቶ ለመውጣት ደፍሮ በሱ መኪና በመገልገልን የሚደፍረው? እንዲህ አይነት ድፍረትና መተማመን የሚመጣውስ እንዴት ነው? ወዘተ ብንል፣ መልስ የማናገኝላቸው ጉዳይ ነው። የማይመስሉና፣ ሊሆኑ የማይችሉ።

ይሁን እንጂ ታሪካዊው የሰለሞን ቤተመቅደስ የተገነባበትን ወርቅ የመጣበትን

ስፍራ ለማሰስ የመጣው ጣሂር ሻህ፣ በመስኮት እየገባና እየወጣ ሻኪሶ ድረስ መጓዙን ይነግረናል። ይኼኔ ‹ግራሞታችን› ይንራል። የሁኔታው አይመስሌነት ሳንወድ በግድ ያስፈግገናል።

ይኼ ብቻ አይደለም። ሌላም ሌላም የማይመስሉ፣ ሊሆኑ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይችሉ በርካታ ገጠመኞችን ይተርክልናል። ለዚህ ዳሰሳችን ግን ከላይ የጠቀስነው ይበቃል ብለን ስለገመትን ወደሌላ ጉዳይ ማለፍን መረጥን።

ይህን መፅሐፍ አግኝቶ የማንበብ ዕድል የገጠመው ሰው በሸውራራ ዕይታ የታጨቀውን እንዲህ አይነቱን አልባሌ ትረካ መተርጎም ለምን ያስፈልጋል? ተርጓሚዎቹ፣ እንዲህ አይነቱን ጭንጋፍ ታሪክ ለመተርጎም ምን አነሳሳቸው? አንባቢያንስ ምን ይጠቀማሉ ብለው ነው? ወዘተ ብሎ መጠየቁ አይቀርም።

የዚህ መፅሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ እነዚህንና እነዚህን መሰል ጥያቄዎች አንስቶ ከራሱ ጋር ሙግት መግጠሙን ከላይ የገለፀው እነዚህን መሰል መጠይቆችን እያብላላ በመክረሙ ነው። መጨረሻም የመፅሐፉ መተርጎም ቢያንስ ሁለት (ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል) ጠቀሜታ ሊኖረው ይችላል ብሎ ነው ያመነው።

አንደኛው፤ የውጭ አገር ሰዎች (በከፊል) ስለዚህች አገር ያላቸው የጠለሸ አመለካከት ምን ያህል እንደሆነ ይረዳል። ስለዚህም እነዚህ የተዛባ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ስለሀገራችን ያላቸውን ብልሹ ግንዛቤ መቅረፍ የሚቻልበትን ሁኔታ የሚያሰላስሉ እና ለተግባራዊነቱ የሚተጉ ኢትዮጵያውያንን ሊያስገኝ ይችላል።

ሁለተኛው፡- እኛ ራሳችን ውስጣችንን ልንመለከት፣ ልንፈትሽ እና ችግራችን ምን እንደሆነ እንድንለይ፣ ለይተንም መፍትሄ እንድንፈልግ ግድ ይለናል። ለምሳሌ

የመፅሐፉ ርዕስ፡- የኢትዮጵያ ወርቅ ምስጢርየመፅሐፉ ደራሲ፡- ጣሂር ሻህየመፅሐፉ ዓይነት፡- የጉዞ ማስታወሻየመፅሐፉ ተርጓሚ፡- ብሩክ መኮንን እና እንቆጳፅዮን ሀብታሙየገፅ ብዛት፡ - 364 ገፅመፅሐፉ የታተመበት ዘመን - የካቲት/2003 ዓ.ም

የመፅሐፉ ዋጋ፡- 40 ብር

የተለያዩ ቦታዎች ሕንፃዎችን ቢገነቡ፣ በቀን ከአንድ ዶላር ያነሰ ገቢ ያለው 80 ሚሊዮን ሕዝብ ምን ተጠቀመ?›› ሲል ይጠይቃል። በአፍሪካ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ተብላ የምትሞካሸው ጋና በርዕሰ ከተማዋ አክራ ይህ ነው የሚባል ህንፃ እንደሌለ በማነጻጸር የጋና ሕዝብ ግን መሪዎቹን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የመቀያየር ሙሉ መብት የመጎናፀፉን እውነታ በቃለ-ምልልሱ አጽንኦት ሰጥቶ ገልጾታል።

የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ቁጣየገዢው ፓርቲ ልሳን እንደሆነ የሚታመነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የሲ.ኤን.ኤን ቃለ-ምልልስ አየር ላይ በዋለ በማግስቱ ‹‹The Paradoxical Criticism of Dawit Kebede against the

Ethiopia Press Freedom›› (‹‹በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ላይ የተሰነዘረ እርስ በርሱ የሚጋጨው የዳዊት ከበደ ትችት››) በሚል ርዕስ በቴሌቭዥን ጣቢያው እና በዳዊት ላይ የዘለፋ ናዳ አውርዷል።ዋልታ እርስ በርሱ ይጋጫል ሲል የጠቀሰው የዳዊት ቃለ-ምልልስ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት ከሌለ እንዴት በየሳምንቱ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ሊያሳትም ቻለ?›› የሚል ነው።ዳዊት በቃለ-ምልልሱ ወቅት የገለፀው ግን ‹‹በየሳምንቱ ጋዜጣ ማሳተም አልቻልንም›› የሚል ሳይሆን፣ ‹‹ከ1997 ዓ.ም በፊት ከነበረው ሚዲያ ነፃነት አኳያ አሁን ያለው ድባብ የፍርሀት ድባብ ነው። ጠንከር ያሉ ዘገባዎችን ለማቅረብ ሁለቴ ማሰብ ግድ ይላል። ጋዜጠኛው ራሱን በራሱ በቅድመ-ምርመራ እንዲታጠር የሚያስገድዱ

አዋጆች አሉ›› የሚል መከራከሪያ ነበር ያቀረበው። እነዚህ መከራከሪያዎች ደግሞ እውነተኛ ለመሆናቸው እየኖርንባቸው ነውና እናውቃቸዋለን። መፍትሄው ፕሬስ ነፃ እንዲሆን መፍቀድ እንጂ ‹‹ነፃነቴ አደጋ ላይ ነው ማለትህ ወንጀል ነው እያሉ ማስፈራራት አሁንም ለአፈናው ተጨማሪ ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው›› ሲል ዳዊት ይገልፃል።የጋዜጠኛ ዳዊት ቃለ-ምልልስ በሲ.ኤን.ኤን መስተናገዱን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ በርካታ ድረ-ገጾችና ብሎጎች ስለቃለ-ምልልሱ ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ዘግበዋል። ከእነዚህም ውስጥ ኢትዮ-ሚዲያ፣ ኢትዮጵያን ሪቪው፣ አባይ ሚዲያ፣ ታዲያስ፣ ኢትዮ ኦብዘርቨር፣ ኢትዮ ሰን ተጠቃሽ ናቸው።

በCNN...

ያህል ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎች (ጎብኚዎችን) የሚያስጎበኙ ሰዎች እነማን ናቸው? ስለአገራቸው ብቁ ዕውቀት አላቸው ወይ? የቋንቋ (በፈረንጅ አፍ የመግባባት፣ ነገሮችን የመግለፅና የማስረዳት) ችሎታቸው ምን ያህል ነው? ጎብኚዎቹ ከትክክለኛ አስጎብኚዎች ጋር ነው የተገናኙት ወይ? ወዘተ ብለን መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል። ከትክክለኛ አስጎብኚዎችና የቋንቋ ችሎታ ካላቸው ጋር ያልተገናኘ ጎብኚ፣ ስለኢትዮጵያ ትክክለኛ መረጃ ይኖረዋል ብሎ መገመት የዋህነት ነው። ጣሂር ሻህ ‹‹IN SEARCH OF KING SOLOMON’S MINES›› በሚል ርዕስ የፃፈውና ብሩክ መኮንን እና እንቆጳፅዮን ‹‹የኢትዮጵያ ወርቅ ምስጢር›› በሚል የተረጎሙት መፅሐፍ፣ ቢያንስ እነዚህን ሁለት ጉዳዮች እንድናስብባቸው ያደርገናል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም የጉዞ ማስታወሻው ፀሐፊ ጣሂር ሻህ፣ ስለሀገሩ በቂ ዕውቀትና ጥሩ የቋንቋ ክህሎት ያለው ሰው ጋር ቢገናኝ ኖሮ፣ እንደዚያ ያሉ የጠለሹ ትረካዎችን ከመከተብ ይቆጠብ ነበር ብዬ አምናለሁና ነው።

ሆኖም የጠለሹና የማይመስሉ ታሪኮችን ከመፃፍ አልፎ ለህትመት አብቅቷል። የተዛባ አመለካከቱን ለዓለም አዳርሷል። በአጭሩ፣ መሆን የማይገባው ሆኗል። ስለዚህ ይህ የሸውራራ ትረካ ትክክለኛ አለመሆኑን ማስረዳትና የጠለሸውን ‹‹ታሪክ›› ማፅዳት የእኛ ጉዳይ ይሆናል። የእኛን ጉዳይ የእኛ ነው ብለን ተገቢውን ተግባር ለመወጣት ደግሞ፣ መጥፎም ቢሆን የመፅሐፉ መተርጎም ‹‹ተገቢ› ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

ለማንኛው የጉዞ ማስታወሻው ፀሐፊ ጣሂር ሻህ በምድረ-ኢትዮጵያ ሰባት አቅጣጫዎች ተጉዞ አየሁ ብሎ የከተበውን ታዩት ዘንድ በመጋበዝ፣ ፍርዱን ለእናንተ ሰጥተን ስንብትን መረጥን።

የሳምንት ሰው ይበለን!

የሚገልፀው አይመስለኝም፡፡ ድን..ቅ!.... ድንቅንቅንቅ አልኩልዎ፡፡

የመፅሔቱ ጋዜጠኛ “ወደ ፓትርያሪኩ ቅፅር እንዳትገቢ መከልከልሽ ይነገራል” ሲል የሲኖዶሱን ውሳኔ አስታውሶ ለሰነዘረላት ጥያቄ፣ ሴቲቱ “በፍፁም ማንም አላለኝም” ስትል መልስ ሰጠች፡፡ ቀጠል አደረገችና ደግሞም “እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ብዙ ሴቶች ይገባሉ፡፡ እኔ ግን የት እና ማን ጋ እንደምገባ ይታወቃል፡፡ ሽፍንፍን የለውም፡፡ እግዚአብሔር መርጦ፣ ከእስር ቤት አውጥቶ፣ ከስደት መልሶ መርጦ ልጄ ነህ ወንበሬም ያንተ ነው ብሎ የመረጣቸው ብፁዕ ወ-ቅዱስ አቡነ ጳውሎሰ ጋ ነው” አለች፡፡ ጥቂት መስመሮችን ወረድ ብላ ደግሞ “እኔን ወደዛ እንዳልገባ የሚከለክሉኝብፁዕ ወ-ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብቻ ናቸው” ብላ እርፍ አለች፡፡

ይኼኔ እኔ “ወንድ ናት” አልኩኝ፡፡ እውነቴን ነው ከደፈሩም፣ ከተዳፈሩም አይቀር እንዲህ እቅጩን ተናግሮ የመሸበት ማደር ነው እንጂ የምን መልመጥመጥ፣ የምን ማድበስበስ ነው እሱ፡፡ “የሴት ወንድ” የሚባለው ወይም መባል ያለባት እንዲህ

አይነቷ ሴት አይደለች እንዴ!? አንዳንዶች ግን በዚህ አባባሌ

ተቃውመውኛል፡፡ ተቃውሞ ያው ተቃውሞ ነውና ወደ ኋላ እመለስበታለሁ፡፡ አሁን ግን ከሴትዮአችን ጋር እንቀጥል፡፡ እናልዎ ሴቲቱ ስለፓትርያሪኩ ሐውልት፣ ስለ ምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ፣ በሲኖዶሱ ውሳኔ ስላለመፍረሱ ወዘተ ተጠየቀች፡፡

“መድኃኒዓለም ምስክሬ ነው፡፡ እመቤቴን እልሀለሁ ምንም አያውቁም፡፡ ሐውልቱን ሲያዩ ደንግጠው አይገባኝም ነው ያሉት፡፡ ይኼ ነገር ለእኔ አይገባም፤ ምን ስላደረግኩ ነው ማን ነኝና ነው ብለው ዝቅ ያደረጉ አባት ናቸው እንጂ ይገባኛል አላሉም” ስትል ፓትርያሪኩ ሐውልት እንዲቆምላቸው እንደማይፈልጉ የምስክርነት ቃሏን ሰጠች፡፡ ታዲያ የሐውልቱ መጨረሻ ምንድነው? ብሎ ጋዜጠኛው ሲጠይቃት፣ ሴቲቱ” ሐውልቱማ አለ፡፡ ይኖራል፡፡… የሚፈርስ ሐውልት የለም” አለችና የእምነቷን ምላሽ ሰጠች፡፡

እና ወዳጆቼ፤ እንዲህ ያለ ደፋር እና እንዲህ ያለ ድፍረት የት ይገኛል!? የትም አይገኝም! ሊገኝም አይችልም፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነቷ ደፋር ሴት “የሴት ወንድ” ብትባል

ያንስባታል እንዴ!? አንዳንድ ተቃዋሚዎች ግን አምርረው መቃወማቸውን ከላይ ጠቀስ አድርጌላችሁ የለ!? ተቃውሟቸው ‹ስለምን ታደንቃታለህ፣ ልትደነቅ የማይገባት ሴት አይደለችምን?› ከሚል የተነሳ ነው፡፡

ጭጭ ብዬ ሰማሁኝ፡፡ ሌላም ሌላም የሴትየዋ ድርጊቶች ያሏቸውን ዘረዘሩልኝ፡፡ ሴትየዋ የምትቻል አለመሆኗን፣ የሚያቆማት እንደጠፋ ነገሩኝ፡፡ በኋላ እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ሌላው ቢቀር በቀጥታ እኔን እንደማይመለከቱ አስረዳኋቸው፡፡ ከዚያም ይህንን ብቻ ነገርኳቸው፣ ‹‹ከያንዳንዱ ስኬት ጀርባ አንድ ጠንካራ ሴት አለች!››

የታህሳስ-ግንቦት ቁርኝት እንዲህ በቀላሉ የሚያልቅ አይደለም፡፡ በመጨረሻዬ አንድ ልጨምርሎ፡፡ ያለፈው ሥርዓት ባለሥልጣናት ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቅ ብለውና የሃይማኖት አባቶች ደግሞ እናስጠይቅ ብለው ‹‹የይሁንታ ቀን›› ሲሉ የሰየሙት ቀን ታህሳስ 16 አልነበር፡፡ ታዲያ ታህሳስ ለግንቦት ነገረውና፣ ይኸው ሰሞኑን ‹ሙቱ› ተብለው የነበሩትን ባለሥልጣናት ‹እድሜ ልክ ኑሩ› ሲል ይኼኛው መንግስታችን መርቋቸዋል፡፡ ምርቃቱ ስለመድረሱ የሚጠራጠር ካለ፣ እርሱ ተመርቆ የማያውቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ‹‹ጠዋት የመረቃቸው መንግስት ማታ ድርጊታቸውን በምልሰት ለሕዝቡ እያስመለከተ ቢኮንናቸው ምርቃቱ ከአንጀት አይደለምና መድረሱን እንጃ!›› ያሉ ወዳጆች ነበሩኝ፡፡

ሰላም ሰንብቱልኝ እንግዲህ!!

‹‹መንግስት ከአንገት በላይ...

Page 15: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 200316

ሥራውን የሚያጣድፉ ሊቃውንት ተመድበውላታል። ፈረንጆቹ፣ “ቸርነት ከቤት ይጀምራል” እንደሚሉት አቶ መለስ ግን ይህንን የራሱ ፓርቲ ቋሚ መርሆ በራሱ ላይ ሲተረጉመው እያየን አይደለም። ይህንን በምን ይገለጻል?

በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ፓርላማ አብዛኛውን ወንበር (ከ240 በላይ) የሚቆጣጠረው የኢህአዴግ ፓርቲ አባል የሆነው “የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ)” ነው። አቶ መለስ የመነጨበት ህወሓት የያዘው ወንበር መጠን ደግሞ 38 ነው። በዚህ ሂሳብ በፓርላማው ወስጥ ኦህዴድ ከህወሓት በስድስት እጅ የሚበልጥ መቀመጫ ይዟል ማለት ነው። ስለዚህ በገዢው ፓርቲ ቋሚ መርሆ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾም ያለበት የኦሮሚያን ክልል እወክላለሁ ከሚለው ከኦህዴድ እንጂ በቆዳ ስፋትና በሕዝብ ብዛት በጣም አናሳ የሆነቺውን ትግራይ እወክላለሁ ከሚለው ከህወሓት መሆን የለበትም። ‹‹ለዓለም የሚተርፍ ዲሞክራሲ አስፍኛለሁ›› በማለት የሚቀልደው ይህ ሥርዓት በለመደበት ቀልድ በኦሮሚያ መሬት አገር ለመምራት ብቃት ያለው ሰው አልተፈጠረም ሊለን ይችላል።

ከአቶ መለስ አምላኪዎች እንደሚደመጠው፣ አቶ መለስ የመሪነቱን ቦታ የያዘው በኢህአዴግ ውስጥ የእርሱን ያክል ብቃት ያለው ሰው ስለሌለ ነው ይሉናል። ይህ በራሱ አሳፋሪ ስድብ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ውጭ ያለውን ሕዝብ እንደመናቅ የሚያስቆጥር ነው። ዓይናቸውን በጨው አጥበው ይህንን ስድብና ንቀት ከሚነግሩን ሰዎች ጋር እንስማማ ብንል እንኳ በኢትዮጵያ “ተወዳዳሪ የሌለው” ሊቀ-ሊቃውንቱ አቶ መለስ በገዢው ፓርቲ ቋሚ መርሆ መሰረት ከሚሰየመው የኦሮሞ/ኦህዴድ ሰው ስር ሆኖ ይሰራል እንጂ ለሩብ ምዕተ-ዓለም በያዘው ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ማለት አልነበረበትም።

ይህ አሳዛኝ አሰራር ግን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ብቻ የሚመለከት አይደለም። በሥርዓቱ አጠቃላይ የሥልጣን ተዋረድ እንደምንመለከተው ቁልፍና ወሳኝ ቦታዎች በአናሳው ፓርቲ በህወሓት ሰዎች የተሞሉ ናቸው። ለይስሙላ በአንዳንድ ቦታዎች የሌሎች ብሔር/ብሔረሰብ ፓርቲ ሰዎች ሲመደቡም እንኳ ከስራቸው ለአቶ መለስና ለህወሓት ታማኝ የሆነ የትግራይ ሰው ይመደብላቸዋል። ለአብነት ያህል በቅርቡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የህወሓቱ አቶ ስዩም ቦታውን ለሌላ ሰው ሲለቅ የሆነውን እንመልከት።

ስዩም መስፍን ሚኒስትር በነበረበት ጊዜ ከእርሱ ቀጥሎ ያለው የኃላፊነት ቦታ በዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ የተያዘ ነበር። ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ በዲፕሎማሲው ሥራ ጥርሱን የነቀለ እና ሰፊ ልምድ ያካበተ ዲፕሎማት እንደመሆኑ መጠን ምንም የዲፕሎማሲ እውቀት የሌለው አቶ ኃይለማርያም ለገዢው ፓርቲ ካለው ተአማኒነት አንጻር የስዩም መስፍንን ቦታ ሲረከብ የዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ እውቀትና ልምድ በእጅጉ እንደሚያስፈልገው አጠያያቂ አይደለም። ይሁን እንጂ የሚኒስትርነቱ ቦታ ከህወሓት እጅ ሲወጣ የምክትሉ ቦታ የገዢው ፓርቲ አባልና የትግራይ ተወላጅ ያልሆነው ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ ይዞት ከነበረው የሥልጣን እርከን ዝቅ ብሎ በአምባሳደርነት ተጋዘ። የዶ/ር ተቀዳን ቦታ የተካው ከዶ/ር ተቀዳ ብቃት ጋር ሲነጻጸር ምንም ሊወዳደር የማይችለው የህወሓት አባልና የአቶ መለስ ታማኝ የሆነው አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ነው። እንዲህ እያሉ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል።

ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅበትግራይ አንድ የሰማዕታት ሐውልት መቆሙ

ይታወቃል። ሰማዕታቱ የተሰዉት በአንድ አገር ልጆች መካከል በተደረገ ጦርነት ስለሆነ የትግራይ ሕዝብ ከጦርነትና ረሃብ ሳያገግም ያንን የመሰለ ሐውልት በጥድፊያ መገንባት ያስፈልግ ነበረ ወይም አልነበረም? ሐውልቱ የተሰራላቸው ሰማዕታት የገደሏቸው ሌሎች ለኢትዮጵያ አንድነት የወደቁት ሰማዕታትስ ሐውልታቸው የት፣ ማን፣ መቼ ይሰራላቸዋል? ወዘተ… እያልን ሰፊ ውይይት መክፈት እንችላለን። ነገር ግን እዚህ ላይ ማንሳት የፈለግሁት እሱን አይደለም። ይህ ሐውልት የቆመው ለሌላ ድብቅ ዓላማ ካልሆነና በእርግጥም ሰማዕታቱን ለመዘከር ከሆነ ንብረትነቱ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሆን ፈጽሞ ባይችልም፣ የጠቅላላው የትግራይ ሕዝብ ንብረት ለመሆኑ ግን የሚያከራክር አይደለም።

እዚህ ላይ ግን አንድ ወሳኝ ነጥብ ልጥቀስ፤ በትግሉ ወቅት በህወሐት ውስጥ ያበረከቱት የትግል አስተዋጽኦ ከነ አቶ መለስ ቢበልጥ እንጂ አያንስም የተባለላቸው፤ የትግራይ ሕዝብ ውድ ልጆች የሆኑ ዜጎቻችን የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሲመሰርቱ የመረጡት አርማ ይህ የመከረኞቹ ሰማዕታት ሐውልት ነበር። ይሁን እንጂ የሰማዕታቱ ሓወልት ‹‹የህወሓት አንጡራ ንብረት (trademark) ስለሆነ ልትጠቀሙበት አትችሉም›› ተብለው ተከለከሉ። በዚህ ሂሳብ ሐውልቱ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሕዝብና የትግራይ አፈር ውሃና ድንጋይ ተጠቃሎ የህወሓት አንጡራ ንብረት ነው እየተባልን ነው። መቼም ጉድ ነው። እኔ እንደውም፣ ‹‹ይህ ሕዝብ ምን ዓይነት እርግማን ቢኖርበት ነው?›› እያልኩ ሁሌም ራሴን እጠይቃለሁ። ስለዚህ፣ ከላይ በግልጽ ያስቀመጥኳቸው የማይታበሉ ሃቆች ድርቅ ብሎ ውሸት ናቸው ብሎ ለመከራከር ካልተፈለገ በቀር፣ ይህ አገዛዝ በባህሪው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማምጣት ይችላል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ካልሆነ ሌላ ትርጉም የለውም።

ኢትዮጵያ ከእነ ዴንማርክ ምን ትማር?

ዴሞክራቲክ አገራት የሚያካሄዱትን የምርጫ ክንዋኔና ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት መጎልበት የሚያመቻቿቸውን መድረኮች ከኢህአዴግ ጋር ለማነጻጸር መሞከር ስላቅ ነው። ሌላው ቀርቶ እዚህ ዴንማርክ ያለው ዴሞክራሲያዊ አሰራር ልዘርዝር ብል የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማስለቀስ በቀር ሌላ ፋይዳ

የለውም። እዚህ ያሉ ሚዲያዎች ሁሉም ነፃ ናቸው። የዴንማርክ ሚዲያ ነጋ ጠባ መንግስት የሰራቸውን መንገዶች፣ ስለቆፈራቸው ኩሬዎችና ቦዮች፣ ወዘተ. በማድነቅ የሕዝብን ጆሮ ሲያደነቁር አይውልም። ምርጫ በመጣ ቁጥር ለፓርቲዎች ደቂቃዎች እየደለደለ የሚያሳትፍ መቀለጃ ሳይሆን የሚያነጋግሩ አገራዊ ጉዳዮች ሲኖሩ ሁሉም ፓርቲዎች አንድ ላይ አቅርቦ የየፓርቲዋቻቸውን አቋምና አመለካከት በእኩልነት የሚያወያይ ነው። ሁሉም ሚዲያዎች በፈለጉት ጊዜና ሰዓት የፈለጉትን የመንግስት ባለስልጣን ቢሮ ሰተት ብለው በመግባት የሚያፋጥጡና ቁም ስቅል የሚያሳዩ ናቸው። ባጠቃላይ አገሩ የሚጠበቀው በፖሊስና በወታደር ሳይሆን በሚዲያ ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል። መንግስትና የመንግስት ባለስልጣኖች ከሁሉም በላይ የሚፈሩትና የሚያከብሩት ተቋም ቢኖር ሚዲያውን ነው።

የምርጫ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ምርጫ አስፈጻሚው አካል በፍጹም ነፃነትና ገለልተኛነት የተመሰረት ነው። በምርጫ ሂደት ገዢው ፓርቲም ሆነ ሌላ ያጭበረብራል ብሎ ማሰብ ህልም ነው። ገዢው ፓርቲም ሆነ ሌላ በምርጫ ጊዜም ሆነ በሌላ ጊዜ አንዲት ሳንቲም እንኳ ብትሆን የሕዝብ ንብረትና ገንዘብ ለፓርቲው ጥቅም ማዋል በወንጀል ከሚያስጠይቀው በተጨማሪ ከጨዋታ ውጪ ያደርገዋል።

የጸጥታ አስከባሪው ክፍል የተመለከትን እንደሆነ፣ እዚህ አገር ፖሊስ የሕዝብ አሽከር ነው ብሎ መደምደም ይቀላል። እዚህ ዴንማርክ በከተማ መንገዶች ጠመንጃ ቀርቶ ሽጉጥ የታጠቀ ፖሊስ ማየት እንኳ የተለመደ አይደለም። የሆነ ችግር ወይም የትራፊክ አደጋ ካጋጠመ ጥቂት የታጠቁ ፖሊሲች ባፋጣኝ ደርሰው በትህትና ሥራቸውን ያከናውናሉ። እዚህ ሕዝቡ ክብሩ፣ መብቱና ጥቅሙ በሚገባ የተጠበቀና የተከበረ ስለሆነ ሁሉም ለአገሩ ዘብ የቆመበት አገር ነው። ለዚህም ነው መንገድ ላይ ዝር የሚል ፖሊስ የማይታየው። በምርጫ ጊዜ በማንኛውም የምርጫ ጣቢያ ፖሊስ የሚባል ነገር አይመደብም።

ኢትዮጵያ ውስጥ እነ ኤፈርትን ጨምሮ ገዢው ፓርቲ በእጅ አዙር የሚያቋቁማቸው ትልልቅ ኩባንያዎች በክፍለ ኢኮኖሚው ምን ያህል የውድድር መዛባት እየፈጠሩ እንደሆነ ግልጽ ነው። እዚህ በምንኖርበት ከፍለ ዓለም ፓርቲዎች ኩባንያ በግልጽ መስርተው መነገድ ይችላሉ ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይገመት ነው።

ሌላው እዚህ ያለው አሰራር የሥራ አስፈጻሚው ክፍል ሥልጣን በሕግ የተገደበ መሆኑ ነው። የሥራ አስፈጻሚው ክፍል በሕግ ተደንግጎ ከተሰጠው ሥራ ውጭ የሆነና ባጠቃላይ የአገሪቱን ሕዝብ የሚመለከት ልዩ ሁኔታ ሲያጋጥም በሁለት መንገዶች ውሳኔ ይሰጥበታል። አንደኛው መንገድ፣ በቀረበው አዲስ ብሔራዊ ጉዳይ (ለምሳሌ ዴንማርክ ገንዘብዋን ወደ ዩሮ ትቀይር አትቀይር የሚል ብሄራዊ ጉዳይ) ላይ ፓርቲዎች የየራሳቸውን አቋም ፍጹም ነፃ በሆነው

ሚዲያና በፓርላማ መድረክ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ ጉዳዩ የፓርላማ አባላት በድምጽ መወሰን አይችሉም። የምክር ቤቱ አባላት ውይይት ካበቃ በኋላ በአዲሱ ብሔራዊ ጉዳይ ላይ ጠቅላላው ህብረተሰብ በሪፈረንደም ድምጽ እንዲሰጥበት ይደረጋል። ሕዝቡ የወሰነውን ፓርላማ ያጸድቀዋል።

ለምሳሌ አዲሱ ብሔራዊ ጉዳይ ቴክኒክ አዘል ከሆነ (ለምሳሌ የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር የመከለል ዓይነት ጉዳይ ቢቀርብ) ሁሉም ፓርቲዎች በታዛቢነት የሚሳተፉበት ነገር ግን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ልዩ ልዩ የቴክኒክ ሙያና እውቀት ያላቸው ከፓርላማው ውጭ ያሉ ሰዎች ያካተተ አንድ ኮሚሽን ይቋቋማል። የዚህ ኮሚሽን የሥራ እንቅስቃሴና በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ውይይት በየጊዜው በግልጽ ሚዲያ ሕዝቡ ይከታተለዋል።

ኮሚሽኑ የሚሰጠው ወሳኔ በፓርላማ ቀርቦ ይወሰናል፤ አስፈላጊ ከሆነ የኮሚሽኑ ወሳኔ ወደ ሕዝብ ቀርቦ በሪፈረንደም ሕዝብ ድምጽ እንዲሰጥበት የሚያስገድድ ሁኔታ ካለም ይህንኑ ይደረጋል። ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ሥራ አስፈጻሚው ክፍል (መንግስት) ብቻውን ውሳኔውን ያስፈጽማል ማለት ግን አይደለም። ወሳኔውን የሚያስፈጽመው የቴክኒክ ኮሚሽኑ ነው። የሥራ አስፈጻሚው ድርሻ የኮሚሽኑ ሥራ በውሳኔው መሰረት እንዲካሄድ ሆኔታዎችን ማመቻቸት ብቻ ነው። ስለዚህ ዲሞክራሲ የሚከተልና ግልጽነት ያለው መንግስት ከሕዝብ ጀርባ ተደብቆ በዝግ ቢሮ ብቻውን የሚያጠናቅቀው ምንም ጉዳይ የለም። በዚህ ሂደት በገለልተኛ ክፍል በተጠናቀቁ ጉዳዮች ላይ (ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ሲደረግ እንዳየነው) መንግስት ጣልቃ ገብቶ ፍጻሜውን ይቀለብሳል ብሎ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም።

የወያኔ ሥርዓት በሚገዛት ኢትዮጵያ ግን ሆኔታው ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው። የሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበር እየተከለለ መሆኑን ማወቅ የቻልነው ሱዳኖች በመከለል ላይ በነበረው ድንበር አካባቢ የሚያርሱ ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ተጎጂዎቹ እሪ ሲሉ ብቻ ነበር። ይህ ከሕዝብ ጀርባ በድብቅ የተካሄደ አስደንጋጭ ጉዳይ ስለሆነ ብዙ አልሄድበትም። ስለዚህ እሱን ወደጎን ትቼ በፓርላማ ቀርቦ በግልጽ በተካሄደ ጉዳይ ላይ አተኩሬ የሆነውን ነገር ላንሳ።

የ1997ቱ አጋጣሚ እንደ

ምሳሌበ1997 ምርጫ ማግስት በተነሳው

አመጽ ምክንያት በአቶ መለስ ትእዛዝ በጸጥታ አስከባሪዎች የተገደሉትን ሰዎች ጉዳይ ለመመርመር ከፍተኛ የሕግና የዳኝነት ሙያ ያላቸውና የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሌላውን ህብረተሰብ ይወክላሉ የሚባሉ ዜጎች የተካተቱበት አንድ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ በምክር ቤቱ ተሰይሞና ተቋቁሞ እንደነበረ ይታወቃል። ይህ ኮሚቴ ሰፊ የማጣራት ሥራ ካከናወነ በኋላ መንግስት አላስፈላጊ ኃይል (excessive force) ተጠቅሟል ሲል ውሳኔ አስተላልፏል።

የኮሚቴው ውሳኔ በማያሻማ መንገድ በቪዲዮ ተቀርጾ በይፋ የተሰራጨ ስለሆነ ምንም የሚያከራክር ነገር የለውም። ኮሚቴው ይህንን ውሳኔ ማድረጉ ሲታወቅ ሥርዓቱ ያደረገው ምንድነው? ወሳኔውን

ያስተላለፈው ኮሚቴ አባላትን ማሳደድ ጀመረ። ስለዚህ የኮሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ዳኛን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ዳኞች የውሳኔውን ቪዲዮ ይዘው አገር ለቀው ለመሰደድ ተገደዱ። ከአገር ለመሸሽ ያልቻሉትን ደግሞ ሥርዓቱ እጃቸውን ጠምዝዞ ውሳኔውን እንዲቀለብሱ በማድረግ “መንግስት አላስፈላጊ ኃይል አልተጠቀም” በሚል ትያትር የተቀለበሰው ውሳኔ ለምክር ቤቱ ቀረበ። እዚህ ባለንበት አገር መንግስት የዚህ ዓይነት ‹‹ተዓምር›› ለመፈጸም ቢሞክር በአንዲት ጨረቃ ከሥራ ይባረራል ብቻ ሳይሆን በፍርድ ተከሶ ወህኒ መውረዱ የሚያጠያይቅ አይሆንም።

የኢህአዴግ

‹‹መልካም አስተዳደር›› ሲሰፈርእዚህ ዴንማርክ በመንግስት የኃላፊነት ቦታዎች

ላይ የሚሰሩ የሲቪል ሰርቪሱ አካላት ሕዝቡን ወይም ባለጉዳዮችን የሚያስተናግዱበት አሰራር የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን እጅግ የሚያስቀናም ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች (ከፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ አስከባሪ ክፍሎች በቀር) ማንንም ባለጉዳይ የሚቀበሉት በአብዛኛው በቀጠሮ ነው። ቀጠሮ ሲወሰድ በአካል ቀርቦ፣ በቴሌፎን ወይም በኢ-ሜይል ሊሆን ይችላል። ቀጠሮ በሚወሰድበት ጊዜ ለምን ጉዳይ እንደሆነ ማስታወሻ ይያዛል። ይህ የሚደረገው ባለጉዳዩ በቀጠሮው መሰረት ከመምጣቱ በፊት አስተናጋጁ ክፍል ተዘጋጅቶ እንዲጠብቀውና ባለጉዳዩም ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ነው። በቀጠሮ ቀንና ሰዓት መገኘት በጣም ወሳኝ ነው።

በቀጠሮ መሰረት ባለጉዳዩ ከቦታው ደርሶ እንግዳ መቀበያ ዴስክ ያለው ሠራተኛ ዘንድ ሄዶ መምጣቱን ያመለክታል። እንግዳ ተቀባዩም በቀኑ የተቀጠሩ ባለጉዳዮችና ተመድበው የሚያነጋግሯቸውን ሰዎች ዝርዝር ቀደም ብሎ ስለሚሰጠው ምልክት አግርጎ ለባለጉዳዮች በተመደበው ምቹ ስፍራ ከቀረበው ሻይ ቡና እየተቋደሰ እንዲጠብቅ ይጋብዘዋል። በተባለችዋ ደቂቃ ባለስልጣኑ ራሱ መጥቶ እጁን ዘርግቶ የባለጉዳዩን እጅ ሞቅ ባለ ሰላምታ ከጨበጠ በኋላ ይዞት ወደ ቢሮው ይሄዳል። አስተናጋጁ ራሱ ከመቀመጡ በፊት እንግዳውን ያስቀምጥና ሻይ ቡና (በብዙ ቦታዎች ኬክ ቢጤም ይቀርባል) ይጋብዝና በከፍተኛ ትህትና ባለጉዳዩን አነጋግሮ ሲጨርስ እንደገና በር ድረስ ሸኝቶ ያሰናብተዋል።

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ለኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የመንግስት ሠራተኞች ከልቤ ለማስተላለፍ የምፈልገው መልእክት አለኝ። ለራሱ ቀርቶ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ድሃ አገሮችን የሚረዳ የዴንማርክ የመንግስት ባለስልጣናትና ሠራተኞች የሚቀመጡባቸው ወንበሮችና ጠረጴዛዎች ብዙዎቻችን በየቤታችን ከምንጠቀምባቸው ተራ ቁሳቁሶች የሚለዩ አይደሉም። በቴሌቪዥን እንደምታዘበው፣ የኛው አገር

የመንግስት ሹማምንቶችም ሆኑ ዝቅ ባለ እርከን ያሉት ባለስልጣናት የሚቀመጡባቸው ወንበሮች ግን ለመኝታ እንጂ ለሥራ የሚመቹ አይመስለኝም። በልመናና በእርዳታ በምትኖር ድሃ አገር በታክስ ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ እንዲህ ያለ የቅንጦት ቁሳቁስ መጠቀም ማለት ህሊና ማጣት ካልሆነ ምን ይባላል? እናም ይህ ዓይነቱ ቅንጦት በውድድር ለሚሰሩ የንግድ ኩባኒያዎች መተው አለበት። ሕዝብን ለማገልገል የተመደቡ ሰዎች ጭንቅላታቸውን ሳይቀር የሚቀብር ለጥርስ ሕክምና ክሊኒኮች ካልሆነ በስተቀር ለቀልጣፋ ሠራተኛ የማይመቹ ወንበሮች ላይ መኮፈስ አክሳሪ ከመሆኑም በላይ አሳፋሪ ነውና በዚህ አጋጣሚ እባካችሁ ድርጊቱ ይቁም እላለሁ።

በነገራችን ላይ እዚህ አገር ማንም የመንግስት ሠራተኛ (ባልስልጣንም ቢሆን) ከሥራ ሰዓት ውጪ የመንግስት መኪና መንዳት ወይም የመንግስት መኪና ቤቱ ማሳደር አይፈቀድም። የኛዎች ጤፍ፣ ቅቤና ጌሾ ሳያጓጉዙ ይቀራሉ?

ስህተትን መልሶ የመድገም አባዜአንድ የእንግሊዝኛ አባባል አለ፤ “The time you

make a mistake is when you repeat that mistake” (ሰው የሚሳሳተው መጀመሪያ ባደረገው ስህተት ሳይሆን በፊት የተሳሳተውን ስህተት መልሶ ሲደግመው ነው እንደማለት)። ሁላችንም የሰው ፍጡራን በመሆናችን በየጊዜው የተለያዩ ስህተቶች ልንፈጽም እንችላለን። በመሠረቱ መሳሳት ስህተት አይደለም። አስፈላጊው ነገር ከዚያ ስህተት ጠቃሚ ትምህርት ቀስሞ ሌላ ስህተት እንዳይፈጸም ማድረግ ነው። የተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን ያብዛኛው ኢትዮጵያዊ ባህርይ ግን በፊት የተሰራውን ስህተት በፊልም ቀርጾ ያንን ስህተት እየደጋገሙ መመልከትና ያንን ስህተት ዝንተ ዓለም መደጋገም ነው።

ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ከሕዝብ የተላለፈላቸው መልእክት “ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚል እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሯል። ይህ መልእክት ለመጀመሪያ ጊዜ የተላለፈው በነ አቶ ጌታቸው ጋረደው ጥረት በጀርመን አገር በፍራንክፈርት ከተማ ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ስብሰባ ላይ ነበር። እንደማስታውሰው በዚህ ብዙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና እኔም በተሳተፍንበት ስብሰባ ላይ ይህንን መፈክር ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው የሽቱትጋርት ነዋሪው ወዳጄ አቶ አእምሮ ጌታነህ ነበር። ስብሰባው የተጠራው የተቃዋሚ ኃይሎች ህብረት የሚፈጥሩበትን ለመመካከር ነበር። ስብሰባው በመልካም ሆኔታ በሚካሄድበትና ወሳኔ ላይ ለመድረስ ሲቃረብ በዚያን ወቅት በቀኛዝማች ነቅአጥበብ ይመራ የነበረው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጀት (መአህድ) የጀርመን ተወካይ ነኝ የሚለው አቶ ፈቃደ ማንደፍሮና እሱን ተከትለው የመጡ የመኢአድ ተወካዮች ስብሰባውን ማወክ ጀመሩ። አስታውሳለሁ፣ አቶ አእሞሮ ጌታነህ እጁን አውጥቶ እድል ሲሰጠው ከመቀመጫው ብድግ ብሎ፣ “እኔ ብዙ የምናገረው የለኝም። ለፖለቲካ ኃይሎች የማስተላልፈው አንድ መልእክት ግን አለኝ፤ ይኸውም ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› የሚል ነው” ብሎ ሲቀመጥ ወደ ስምንት መቶ የሚሆነው ተሳታፊ ብድግ ብሎ በጭብጨባ አዳራሹን አደባለቀው።

ያ የሕዝቡን ስሜት እንደዚያ ያቀለጠው መፈክር ከዚያ በኋላ የሕዝብ መፈክር ሆኖ በየመድረኩ የሚነገር ነው። ያ መፈክር በአንጻራዊ መልኩ መልስ ያገኘው በ1997ቱ ምርጫ ዋዜማ ነበር። ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሕብረት በተለያየ አጋጣሚ በገለጽኩት የመሰሪዎች ሴራና ከዚያም በፊት በምስረታው ወቅት የኔን ድርጅት ጨምሮ ሌሎችንም ያገለለ እንደመሆኑ መጠን መበታተኑ አይቀሬ ነበርና ተመታ። ሕብረቱ እንዴት እንደተመታ ዝርዝሩን ለጊዜው እንለፈውና የቀስተደመና ፓርቲ ከሰማየሰማያት ወርዶ ቢያንስ ኢዴፓ፣ መኢአድንና ኢዴሊን አካቶ ሲቀናጅ ሁላችንም በዚያ ዙርያ ተሰለፍን። አጠር ባለ መልኩ ለመግለጽ ያህል፣ “ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚለው መፈክር ትክክለኛ መፈክርና የአጠቃላዩ ሕዝብ መፈክር እንደሆነ በገሃድ ታየ። ላለመተባበር የተደረገው ስህተት መጥፎ ስህተትና መደገም የሌለበት ስህተት እንደሆነም በግልጽ ታየ።

ውጤቱ ደግሞ ምን እንደሆነ አገር ያየው ስለሆነ በሌለን ጊዜ እዚህ አንስቶ መዘርዘር አያስፈልግም። እመሬቱ ላይ ወለል ብሎ የታየው የሕዝብ ስሜትና ፍላጎት ይህ ሆኖ ሳለ፣ የቅንጅትን ያክል የትብብር ትግል “እኔ ታምሜያለሁና ታክሜ እስክድን የቅንጅት ሞተር ሳይንቀሳቀስ ቆሞ ይጠብቀኝ” በሚል ሰንካላ ምክንያት ማፍረስ ማለት ምን የሚሉት እርግማን ነው? እኔ ይህንን ስህተት አልለውም። በበኩሌ የሕዝብ ንቀት ነው ልለው የምችለው። ይህንን ያለፈ ታሪክ ለታሪክ ትተን እስኪ የቅርቡን ደግሞ እንመከልከት።

የወ/ሪት ብርቱካን ተስፋና የፓርቲዋ አንጃዎች ፖለቲካዊ ስህተት

በቅንጅት መሰባበር የተሰበረውን የሕዝብ ልብ ለመጠገን በወ/ሮ ብርቱኳን መሪነት ብቅ ያለው አንድነት ፓርቲ መመስረቱ በሀገር ቤት ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይገባል ለሚሉ ሰዎች ተስፋ የሚሰጥ እርምጃ ነበር። ሰላማዊ ትግል ማለት ምርጫ በመጣ ቁጥር ከማይቀመሰው ገዢ ፓርቲ ጋር መወዳደር ማለት ብቻ እንዳልሆነ አስምረንበት ማለት ነው። ሆኖም አንድነት ፓርቲ ካለፈው ስህተት ተማረ ወይስ ያለፈውን ስህተት ደገመ? ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው መልስ አስለቃሽ የማያስፈልገው ለቅሶ ነው። የፓርቲው መሪዋ ወ/ት ብርቱኳን ተቃዋሚ ነን ከሚሉ ሴረኞች በተጠነሰሰና ለከት በሌለው ሥርዓት ማንአለብኝነት ወደ ወህኒ ቤት ተወርወራ በምትማቅቅበት ወቅት የአገር ምሰሶ ናቸው የሚባሉ አዛውንቶች መደማመጥ አቅቷቸው እርስ በርስ ሲቦጫጨቁ ማየት እጅግ የሚያሳዝን ነበር። እኔ አንዱን አንጃ ደግፌ ትክክል ነው ሌላው አንጃ ደግሞ ተሳስቷል ማለት ባልፈልግም። ፖለቲካዊ ስህተቱ የሁሉም ነበር። ችግራቸውን በፓርቲው ውስጥ በሰለጠነ ውይይት መፍታት አቅቷቸው ሲወነጃጀሉና ሲደባደቡ ማንን ለማስደሰት ነው። ሌላው ቢቀር ራሷ ወ/ት ብርቱኳን “ቃሌ” በሚል ያስተላለፈችው ልብ የሚነካ መልእክት

ምስጢር ...

ከዚህ ውጭ ግን ብዙ ሰው ያላወቀው ምስጢር አለ። ይህን ምስጢር ሥርዓቱ ራሱም ቢሆን

የደረሰበት በቅርቡ ነው። ሆኖም ሥርዓቱ ምስጢሩን በቅርቡ የደረሰበት ቢሆንም በዚህ

ምክንያት ያለበትን ችግር እንዲሁ በቀላሉ ሰዎችን ከሥራ በማባረርና በተለያዩ ክሶች

በማሰር የሚያቃልለው አይመስለኝም።

በ ገፅ 21

Page 16: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ል ዩ ቅ ኝ ት 17

በውብሸት ታዬ

የመጨረሻ ክፍል

በአብዮተኛው ላይ አብዮት?አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በነገሱ በ10ኛ ዓመታቸው፣

ማለትም በ1443 ዓ.ም፣ ለግብፁ ሱልጣን ጀቅመቅ በፃፉት ደብዳቤ ውስጥ ቀጥሎ ያሉት ትኩረት የሚስቡ ቃላት ይገኛሉ፡፡

‹‹ … የዓባይ ወንዝ ከእኛ አገር ወደ እናንተ አገር እንደሚፈስ ከእርስዎ የተደበቀ አይደለም፡፡ ወደ እናንተ እንዳይደርስ ማድረግ እንችላለን፡፡ ይህን ከማድረግ ያቀበን እግዚአብሔርን መፍራታችን ብቻ ነው፡፡ … ››

ንጉሱ እነዚህን ውስጠ ወይራ ማስፈራሪያዎች ከ600 ዓመታት በፊት አከባቢ ይላኩ እንጂ በተጨባጭ ያንን ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂና አቅም የነበረ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ ስለሆነም ዓባይ እየተንፎለፎለና እየተገማሸረ በዓለም ላይ በርዝመቱ በአንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠውን ርዝመቱን ያካልለዋል፡፡

ዓባይን እየተከተልን፣ እያቋረጥን ለአንድ ሳምንት ያህል በቆየንበት ጊዜ ሁሉ በየፕሮጀክቶቹ የምናገኛቸውን ኃላፊዎች ‹‹ዓባይ ማለት ምን ማለት ነው?›› ማለታችን አልቀረም፡፡ አብዛኞቹ ፈገግ ብለው፣ ‹‹ዓባይ … እንጃ … ብቻ በተለያዩ አገራት የተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አባይ …›› ይሉናል፡፡

‹‹ዓባይ›› ማለት ‹‹አሻፈረኝ አለ›› ማለት ነው፡፡ አመጸ፣ አበየ ማለት ነው፡፡ በኩረ ቃሉ የተገኘውም ከዚሁ ‹‹አበየ› ከሚለው የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ አቻ ትርጉሙ ከላይ የተመለከትናቸውን ይመስላል፡፡ አብዮት የሚለው ቃል መሰረትም ይኸው ‹‹አበየ›› ነው። እና ዓባይ ‹‹እምቢ›› ብሎ በመኖሩ ‹‹እግዚአብሔርን ባንፈራ እንገድበው ነበር›› ባሉት ላይ አብዮተኛ ሆኖባቸው የኖረውን ያህል፣ ተራችንን ‹‹እምቢ›› ብለን ልናቆመው ይሆን እንዴ? ያሰኛል።

38 ያህል የሚዲያ አባላት ባደረጉት በዚህ ጉብኝት አብዛኞቹ ፕሮጀክቶች በመዳሰሳቸው እስኪ ድንበራችንን አቋርጦ ሱዳን ሊገባ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩት በምትገኘው ‹‹ጎባ›› የተሰኘች ወረዳ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ‹‹ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ›› በመቃኘት የሶስት ሳምንታት ቅኝታችንን እንቋጭ፡፡

ውድ አንባቢዬ፡- በአማካይ ተጓዥ አረማመድ ሱዳን ልግባ ቢሉ አራት ሰዓታት ብቻ በሚበቃዎ ርቀት ላይ ግንባታው ስለሚካሄደው ስለዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት መሰረታዊ ነጥቦችን ዳስሰን ስንጨርስ ነገርዬው ለምን ይህን ያህል የሚሊዮኖችን ትኩረት ጨምድዶ እንደያዘ፣ ለምን ከአርባ በላይ ፈርኦናውያን ልዑካንን ወደ መዲናችን በማምጣት ቀደም ሲል የነበረ ትምክህታቸውን በጉያቸው ሸጉጠው ፓትርያርኩን ሳይቀር ‹‹አባታችን፣ ኢትዮጵያ ግብፅን አታስርብም ብለው ቃልዎን ይስጡን›› የሚል ልብ የሚነካ ንግግር እስከማድረግ እንዳበቃቸውና ምስጢሩን በመጠኑ ይገልፅልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ቅኝታችን የሚደመደመው ከ‹‹ጎባ›› ምንጭ በተቀዳ ፈገግ ሊያሰኝዎ የሚችል አንድ ገጠመኝ ይሆናል።

ፕሮጀክቱ …… የሚገኘው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ

ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ልዩ ቦታው ‹‹ጎባ›› በተባለ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት 700 ኪ.ሜ ያህል ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በኃይድሮ አሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከአፍሪካ የመጀመርያውን ደረጃ ይይዛል፡፡ በተደጋጋሚ እንደተገለፀው ሲጠናቀቅ 5250 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ግድብ 145 ሜትር ከፍታ፣ 1780 ካሬ ኪሎ ሜትር ርዝመትና 63 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ የመያዘ አቅም ይኖረዋል፡፡ የጣና ኃይቅን ሁለት እጥፍ ያህል መሆኑ ነው፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሐንዲስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የግድቡን አቅም አስመልክቶ በንፅፅር ያቀረቡበት መንገድ ሁኔታውን የበለጠ ይገልፀዋል፡፡ ‹‹የግልገል ጊቤ 1 ግድብ ውሃ የመያዝ አቅም 900 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ሲሆን፣ ከ66 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ጋር ስታወዳድሩት ከአንድ ስልሳኛ በታች ይሆናል፡

፡ የሕዳሴውን ግድብ የ1780 ካሬ ኪሎ ሜትር ደግሞ ከጊቤ 1 ፕሮጀክቱ 52 ካሬ ኪሎ ሜትር ጋር አነፃፅሩት›› ነበር ያሉት፡፡

ሳይፈቅዱ እየተንቀለቀለ በሚነድ እሳት አጠገብ የቆሙ ያህል በሚለበልብ የአየር ሙቀት ‹‹ጎባ›› ረባዳ ውስጥ ቆመው /በዚህ አጋጣሚ ሥራው እስኪጠናቀቅ በስፍራው ለሚቆዩ ባለሙያዎች ጥልቅ አክብሮታችንን እንገልጻለን/ አብዮተኛው ውኃ ተጠልፎ የሚያርፍበትን የተንጣለለ ዙሪያ ገብ ሲመለከቱ በአንድ እጅግ ከባድ፣ ምናልባትም ጊዜ በሚፈታው ታሪካዊ ምስጢር ምዕራፍ ላይ መሆንዎ ይሰማዎታል፡፡ ‹‹63 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ የሚይዝ ቦታ›› የሚለው ለሙያው ቅርብ ላልሆንን ሰዎች ያን ያህል ግልፅ ላይሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ እስኪ በተጨማሪ ንፅፅር ለመመልከት እንሞክር፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ ከሁኔታው ውስብስብነት አኳያ አሁን በማናነሳው ምክንያት ኢትዮጵያችን በአብዛኛው አዋሽን ማዕከል ያደረገ ግንባታ ስታካሂድ ቆይታለች፡፡ ኢንጂነር ታደሰ ኃ/ስላሴ ከአገራችን ረሃብን ለማጥፋት ብሎም ድህነትን ለመቀነስ ባለመ ጥናታዊ ሥራቸው እንደገለፁት የአዋሽ ወንዝን ከቆቃ እስከ ተንዳሆ ያሉት ሰፋፊ የእርሻ ድርጅቶች የሚጠቀሙበት በዓመት ያለውን የአንድ ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ፍሳሽ ብቻ ነው፡፡ /ይህ አሃዝ አዋሽ መጨረሻ ላይ የሚገኘውን አያካትትም፡፡/

በሕዳሴ ግድብ የሚከማቸው የውሃ መጠን 63 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ነው ብለናል፡፡ 63 ጊዜ የአዋሽን ወንዝ ዓመታዊ ፍሰት ማለት ነው፡፡ ወይም የዝዋይ ኃይቅን ተመልክተውት ከሆነ ከ30 ጊዜ በላይ እጥፍ ማለት ነው፡፡ ይህ የውሃ መጠን በአሁኑ ወቅት ያለው 80 ሚሊዮን የአገሬ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ የእህል ምርት መጠን ከአራት እጥፍ በላይ በመስኖ ለማምረት የሚያስችል /የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዓላማ ከመስኖ ልማት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑ እንዳለ ሆኖ/ ይሆናል ማለት ነው።

በሌላ በኩል ስንመለከተው ከአገራችን በተለያዩ አቅጣጫዎች አሻፈረኝ አያለ ከሚወጣው /አገሩ ምድር ውስጥ የሚቀረው አዋሽ ብቻ ነው/ ግማሽ ያህሉ ይሆናል፡፡ ደግሞም የዓለማችንን ረዥሙን ወንዝ የሚፈጥሩት ተማከሎች አጠቃላይ መጠን 84 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ብቻ መሆኑ ‹‹ጎባ›› ረባዳ ውስጥ የሚሰባሰበውን መጠን ምንነት ያመለክተናል፡፡ የታሰበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ረባዳማ ቦታው ውሃ በማባከን እንቅፋት እንደሚሆን በጥናቱ በመረጋገጡም 4800 ሜትር ርዝመት /አምስት ኪ.ሜ አካባቢ/ እና 45 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ እንደሚገነባ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

ሌላው መስተዋል ያለበት ጉዳይ ደግሞ በየትኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት እንደሚሆነው ሁሉ የግድብ ሥራው ገና በጅምር እና በቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑ ነው፡፡ ይህን ማስታወስ ያስፈለገው ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚኖረውን መልክ የሚያሳየውን ዲዛይን በምስለ መስኮት /በቴሌቪዥን በዜና እወጃዎች ወቅት/ የተመለከቱ አንዳንድ ወገኖች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ያሉ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ በስፍራው ደርሰው ከተመለሱ ‹‹ጋዜጠኞች›› አንዳንዶቹ አስፈላጊነቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ‹‹ከተጀመረ ሁለት ዓመት ያለፈው … እንደተዓምር የሚቆጠር ሥራ ነው ያየነው›› ብለው መግለፃቸው ውዥንብር እንዳይፈጥር በሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ስራ የተጀመረው ጠ/ሚ/ሩ በመጋቢት ወር መጀመርያ 2003 ዓ.ም የመሰረት

የሚል ትንታኔም ይሰጣል/ ለሰባት ሺህ ዓመታት ለዓባይ አማልክት እየገበረ ግብርናውን ሲያከናውን ለኖረው የግብፅ አርሶ አደር በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ሰባት የመከራና የረሃብ ዘመን እንደሚመጣ አስቀድሞ በሕልሙ በመመልከቱ ስንዴ ሲሸምት የነበረውን ዮሴፍን የሚያስታውስ ይሆንበታል፡፡

በዚህም ተባለ በዚያ ከሁሉ የተሻለውና አዋጭ ሆኖ የሚቀረው ተጨባጩን እውነታ ያለመዘንጋትና በድርድር መርሕ የማይፈታ ምንም ነገር እንደሌለ መቀበል ብቻ ይሆናል፡፡ በ11ኛው ሰዓት ላይ ቢሆንም የግብጽ ሕዝብ ልዑካን አዲስ አቀራረብ በዚህ ዕሳቤ የተቃኘ ይመስላል።

ይህ ማለት ግን ከዚህ በኋላ ነገሮች አልጋ በአልጋ ናቸው ማለት አይደለም። በአገራችን በተለያየ ጊዜ ከሚቀሰቀሱ ጦርነቶች ጀርባ የአባይ ጦስ እንዳለ ሲገለጽ ቆይቷል። አባይ ጦርነቶችን ይዞ ሲዞር ኖሯል። ግብጽ ደግሞ ከአባይ ጋር በተያያዘ ለዘመናት ስትከተለው የነበረው አሰላለፍ በግልጽ ይታወቃል። በአንድ ጊዜ የሚቀየርም የተቀየረም ካባ ያለመኖሩን እያስታወሱ መጓዝ ነው። በመግቢያችን ላይ እንመለስበታለን ወዳልናት አጭር ገጠመኝ ስንሄድ …

… ሳይፈልጉ በሚንቀለቀል ዕሳት ዳር የቆሙ በሚመስልዎ የ‹‹ጉባ›› ወረዳ እምብርት ላይ ቆመን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የሚሰጡትን ማብራሪያ በመቅረፀ ምስሎችና ድምጾች በማስቀረት ላይ ነን፡፡ በዚህ ጊዜ የፕሮጀክቱ ዋና ኮንትራክተር የሆነው የጣልያኑ ሳሊኒ ካምፓኒ ተወካይ ኃላፊ መጥተው አስተያየት እንዲሰጡ በኢንጂነር ስመኘው ተጋበዙ፡፡ ይሁንና ወደ ማብራሪያ መስጫው ተጠግተው ከመናገራቸው በፊት ግን እንዲቆሙ ተደረገ፡፡

ሁኔታው ትንሽ ፈገግ የሚያሰኝ ነበር። ምክንያቱም የኢትዮጵያዊው ኃላፊ እርጋታና የበላይነት ስሜት የጣሊያናዊው ድርጅት ተወካይ ከዚህ በተቃራኒ መንፈስ ውስጥ መሆን ሁለቱን ኃላፊዎች በአድዋ ድል ማግስት ያሉ ያስመስላቸው ነበር። ጣሊያናዊው ነገሩ ያልተመቻቸው በሚመስል ሁኔታ ፈታቸውን ወደተንጣለለው ዙሪያ ገብ አዙረው /ጀርባቸውን ሰጥተውን/ ቆሙ፡፡

ኢ/ር ስመኘው ‹‹ሚዲያ ላይ መውጣቱን ብዙም ስለማይፈልጉት ነው›› ሲሉ ገለፁልን፤ ወዲያው ደግሞ ዕድሉን ሰጡዋቸውና ከፊት ለፊታችን ቆመው መናገር ጀመሩ፡፡ ሚዲያ ስላለመፈለጋቸው ምንም ምልክት አላየንባቸውም፡፡- እንዲያውም የወደዱት ይመስሉ ነበር።

‹‹አመሰግናለሁ፡፡ ይህ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ … ለካ ደግሞ እንደገና ስሙን ቀይራችሁታል (በስላቅ አይነት) … የሕዳሴ ግድብ … ጥረት እናደርጋለን፡፡› ተናግረው ‹‹ከጨረሱ›› በኋላ ቦታውን ለሥራ አስኪያጁ ለቀው እዚያው ቆሙ፡፡ ኢንጂነር ስመኘው ከመጀመርያ አንስቶ ይታይባቸው በነበረው ሊሸፈን ያልቻለ የበላይነት አነጋገር ‹‹በቃ የምንፈልገውን ጨርሰናል›› አሏቸው፡፡ ነገሩ ‹‹ከዚህ ጥፋ›› ዓይነት ነበር። ጣሊናዊው ገብቷቸዋል። እናም እንደታዛዥ ልጅ ‹‹እሺ ወደ ሥራዬ እሄዳለሁ›› ብለው ከማብራርያ መስጫው ስፍራ ዞር አሉ፡፡

ግን ወደ ሥራቸው አልሄዱም፡፡ ከዚያ ይልቅ ብዙም ሳይርቁ በ10 ሜትር ርቀት ላይ ለአንድ ጋዜጠኛ መግለጫ ይሰጡ ጀመር፡፡ ኢንጂነር ስመኘው ይህን ሁኔታ በቸልታ አላለፉትም። የሰውየውን መግለጫ መስጠት /በተለየ ሁኔታ የተደረገ ስምምነት እስከሌለ ድረስ ነፃ መብታቸውን/ እንደማይቻል በቁርጠኝነት ገለፁ፡፡ የሳሊኒው ተወካይ ኃላፊ ቅሬታቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ ‹‹ተራምደው›› መኪናቸውን ካስነሱ በኋላ እብስ አሉ፡፡ ጋዜጠኞች እርስ በርሳቸው ተያዩ፡፡ ‹‹ለምን ይሆን?›› የሚል ጥያቄ አጫረ፡፡

ልዩ ማሳሰቢያ ፡-የሕዳሴ ግድብ ወደሚገነባበት ጎባ ወረዳ እስክንደርስ ድረስ

በነበረው በአማካይ መቶ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሬት ላይ የነበረ ደን በዕሳት ወድሞ ተመልክተናል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአገራችን ክልሎች ከፍተኛ መጠን ያለው ደን በተለያየ ጊዜ በዕሳት ሲወድም ቆይቷል። በዚህ ዓይነት የነገይቱ ኢትዮጵያ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት አያዳግትም። ደኖቻችን ይጠበቁ።

ከዓባይ ጋር ለ ሳምንት1ድንጋይ ጥለው መርቀው ከመክፈታቸው በፊት ነው ቢባል እንኳ የመጨሻው ጥናት ተጠናቆ ለመንግሥት ቀረበ ከተባለበት ጊዜ ወዲህ ያለው ጊዜ ሲሰላ በአጠቃላይ የአንድ ዓመት ጊዜ አይሸፍንም፡፡

ወደ ተጨማሪ ዝርዝሮች ከመግባታችን በፊት ግን ፈርኦናውያኑ ለዘመናት የሚታወቁበትን ‹‹ኢትዮጵያ ንክች አድርገሽ በዓባይ ላይ ግድብ ትገነቢና ዋልሽ›› የሚል የማናለብኝ ዛቻ ወደጎን አሽቀንጥረው በመጣል ወደመዲናችን ከመጡ በኋላ ‹‹መለሳለሱን አበዙት›› ያስባለባቸውን ተውኔት እንጂ እውነት የማይመስል ድርጊት ለምን ፈፅሙ? የሚለውን አጠር አጠር አድርገን ለመመልከት እንሞክር፡፡

አሁን የሚያውቋት ግብፅ ቀደምት የዓለም ሥልጣኔ ምንጭ የነበረች፣ ወደ ኋላ ሰባት ሺህ ዘመናት ተንደርድረን ስንገልጣት አንድ ብላ ከጀመረችው የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ግስጋሴዋ ያልተንገራገጨች /በየማሕሉ ፈታኝ ወቅቶችን ማሳለፏ እንዳለ ሆኖ/፣ እንደ አሜሪካን ያሉ አገራት በአህጉሩ ከፍተኛውን ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርጉላት (በነገራችን ላይ አሜሪካን ለግብፅ መንግሥት ያለ አንዳች ገደብ ከፍተኛ መጠን ያላቸውና ዒላማን ለይተው የሚያወድሙ የተለያዩ የጦር ጀቶችን ከመሸጥ አልፋ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት በነፃ የገፍ መሳሪያዎችን ስታስታጥቃት ኖራለች፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሁኔታውን ከስትራቴጂክ ጂኦ-ፖለቲካ በተጨማሪ የ[ቀለም] ነገር እንዳለበትም ይጠረጥራሉ፡፡)

የተፋሰሱ አባል አገር ናት፡፡ የተፋሰሱ አባል አገር የሆነችው የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ በሚሄደው የእኛው ዓባይ ሰበብ ነው፡፡ ሌሎች 1001 አስደማሚ የታላቅነት መገለጫዎቿን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የዚህ ሁሉ መነሻና መድረሻ፣ የታላቅነቱ አልፋና ኦሜጋ ምስጢር ‹‹ከዓባይ ጋር ለ1 ሳምንት›› በሚል እየቃኘነው ያለነው ዓባያችን ነው፡፡

እንዲህም ይሁን እንጂ ግብፅና ሱዳን የሕግ አስገዳጅነት ሊኖረው የማይችል የቅኝ ግዛት ዘመን ውል በማጣቀስ ከተፋሰሱ 86 በመቶ በላዩን የመጠቀም /ለተፋሰሱ ከ85 በመቶ በላይ የምታበረክተውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት አገራት ከ14 በመቶ በታች ይጠቀሙ የሚል/ መብት አለን ሲሉ ይሞግታሉ፡፡

ከላይ የተመለከተው የክፍፍል መርሕ ከግብፅና ሱዳን ውጭ ላሉት የተፋሰሱ አገራት እንደስድብ የሚቆጠር ከመሆኑም በተጨማሪ በተለይ የግብፅ መሪዎች ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ አንዳች ግድብ ብትሰራ ወደ ጦርነት እንደሚያመሩ ሲያስፈራሩ መኖራቸው አንዳንዴም ‹‹ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስለመኖሯ አናውቅም›› እስከማለት መድረሳቸው ከአሁኑ የፈርኦናውያኑ አመጣጥና ሙሉ ለሙሉ ‹‹የተቀየረ›› አቋም ጋር አግራሞትን አጭሯል፡፡ ለዚህ የአቋም ‹‹መቀየር›› ከሚነሱት ተገቢነት ያላቸው ጥርጣሬዎች ባሻገር የዘርፉ ጠበብቶች ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች የተወሰኑት ቀጥሎ ያሉት ናቸው፡፡

* ‹‹ታሪካዊ ስምምነት›› ተብሎ የሚጠቀሰው ውል መከራከሪያውን የሚያነሱት ወገኖች ሕጋዊ መንግስት ባልነበራቸው ወቅት የተፈረመና ከፍትሐዊነት አንፃርም 80 በመቶ ያህሉን ባለድርሻዎች ያላሳተፈ የመጋረጃ ጀርባ ውል መሆኑ፡፡

* ግብፅ የቱንም ያህል የመከላከያ ኃይል ብትገነባም ተጨባጭ ሁኔታው በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የማያስችላት መሆኑ፣ በእርግጥ ወደጦርነት የምትገባ ከሆነም በአፀፋው ለበርካታ ሺህ ዓመታት የገነባችውን የታላቅነት መሰረት ተረት የሚያደርግ ስትራቴጂያዊ የበላይነት በኢትዮጵያ በኩል መኖሩ እንዲሁም የዚህ አይነት ያለመግባባቶችን የሚዳኝ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤትና የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ወንዞች ኮንቬንሽን መኖሩ ዛቻውን ወይም አንዳች ዓይነት የሙከራ እንቅስቃሴውን በአጭሩ እንዲገታ ያስገድደዋል፡፡

* ኢትዮጵያ ለኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ‹‹ጉባ›› ላይ የምትገድበው 63 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ኃይል የሚፈጥረውን ተርባይን አሽከርክሮ የሚያልፍ ነው ቢባልም፣ ግንባታው እንደተጠናቀቀ ሰው ሰራሽ ኃይቁ ወደ ግድቡ ከገባ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመታት የሚቆይ መሆኑ /ይህን ያህል መጠን ያለው ውኃ በአንድ ጊዜ መውሰዱ የተፋሰስ አገራቱን ጥቅም መንካቱ ስለማይቀር ይህን ለማስቀረት ሲባል በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንዲጠራቀም ይደረጋል

Page 17: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 200318

ሴት

ባሳለፍነው ሳምንት በሚዲያ የተዘገበ አንድ ዜና ነበር - ለሁላችንም የቅርብ ጊዜ ትዝታ የሆነው የካሚላት ታሪክ አይነት።የካሚላት በአሲድ መጠበስ ብዙዎቻችንን በንዴት ጠብሶናል። አንዳንዶቻችን (‹‹ታማኝ ባለመሆኗ ነው›› ብለን የደመደምን) ደግሞ የታማኝ ያለመሆን ሰው ምሳሌ መስጫም አድርገናታል፤ ‹‹ዋ! እንደ ካሚላት ... ›› በማለት። ያ ቀልድ አይደለም። ታማኝ ያለመሆን በራሱ ራሱን የቻለ ጥፋት ቢሆንም፣ የእሱ ቅጣት አሲድ ነው ያለው ማነው?

እሷ የተቀበለችውን ዓይነት መከራ ማንም ሊቀበል አይወድም። ከዚያ በኋላም የተሰጠውን ያህል ፍርድ ቢሰጥ እንኳ የእሷን እንባ የሚያብስ አልሆነም። በካሚላት ላይ ይህን ድርጊት የፈፀመው ሰው በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሁላችንም አይጠፋንም። ለዚያም ይሆናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍቅርና በትዳር ግንኙነት ምክንያት አለመግባባት ተከስቶ የመለያየቱ ነገር ያልተዋጠለት ወገን፣ ማን እንደሆነ ይታወቃል፣ ፍፃሜውን አንድና አንድ እያደረገ የሚገኘው - አሲድ።

እንዴት እያሰብን ነው? አንድ ማኅበረሰብ በሥልጣኔ እያደገ እየሄደ ነው ስንል በሁለት መንገድ ይሆን እንዴ? ኋላ ቀር የሆነውን አስተሳሰብ በአዲስ መቀየር፣ እና ኋላ ቀሩን ወደ ዘመናዊነት መቀየር?

ባለፈው ሳምንት ጋዜጦች አንድ ነገር ይዘው ብቅ ብለው ነበር፤ ጉዳዩ ትዕግስት የምትባልን የተመለከተ ነው። ከ25 ቀን በፊት ነው ነገሩ የሆነው፤ ከባለቤቷ ጋር የነበራቸው ቅራኔ የሶስት ዓመት ትዳር በ‹‹አሲድ›› እንዲቋጭ ምክንያት ሆኗል። እኔ ተቋጨ አልኩ እንጂ በወንጀል የሚያስጠይቀውን ተግባር ፈፀመ የተባለው ሰው ‹‹ገና ይቀራል›› እንደሚል ተዘግቧል። ይገርማል! እጅግም ዘግናኝና የለየለት ከሰብዓዊ ባህርይ ያፈነገጠ ነው።

ከላይ እንዳልኩት፣ አንዳንዴ አንደኛው ወገን በዚህ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ልቡ ሲደማ፣ አንዳንድ የዚህ ‹‹ሰይጣናዊ›› ድርጊት አሸብሻቢዎች ደግሞ ‹‹ታማኝ ካልሆነች ይበላት›› ዓይነት ‹‹ፍርደ-ገምድል›› አስተያየታቸውን ይሰነዝሩ ይሆናል። ሴቷ ምንስ ባትታመን የአሲድ ጥቃት ሊፈጸምባት ይገባልን? በጭራሽ! እንደዚህ ዓይነቱን ጭፍን

ጎበዝ … ወደየት

እየሄድን ይሆን?

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

አስተያየት የሚሰጡቱ ለምን አንድ ጊዜ ለአፍታ በተጠቂዋ ቦታ እናታቸውን፣ እህታቸውን አሊያም ራሳቸውን አስቀምጠው መመልከት አቃታቸው?

የሚገርመውና አሳፋሪው፣ እንዲህ ዓይነቱ አሰቃቂ ነገር የሚደርሰው ‹‹የትዳር አጋሬ›› ባሉት ሰው መሆኑ ነው። አሳፋሪነቱ ያ ብቻም አይደለም። ‹‹ሰብዓዊ›› ከምንለው ፍጡር ኃሳቡ መምጣቱ፣ ወደየት እያመራን ነው የሚለው ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳል።

ትዕግስት እንዳለችው፣ ‹‹ባለቤቷ›› ይሄንን ድርጊት ሲፈጽምባት አብሮት ሌላ ሰው እንደነበረም ጭምር ነው። ይሄ እንዲግዲህ የዚህ ድርጊት ተባባሪ የሆነው ሰውም በድርጊቱ አምኖበት ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ሲሆን፣ ይሄ ወንጀል ነገና ከነገወዲያ እንደማይቀጥል በዚሁ እንደሚቆም ምንም ማረጋገጫ የለንም ማለት ነው።

ችግሩን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ በሴቶች ላይ መሆኑ ነው። ያን ስል ወንዶች አሲድን የሚያህል እንኳን ለሰው ይቅርና ለድንጋይ የከበደ ነገር ይቋቋሙታል ማለቴ አይደለም። ነገር ግን፣ ሴቶች ይሄን የከፋ ድርጊት ያውም የትዳር አጋሬ፣ የልጄ አባትና የፍቅር ጓደኛዬ የሚሉት ሰው ላይ የመፈፀም ድፍረታቸው ጭራሹኑ የሌለ ለማለት የሚያስደፍር ስለሆነ እና ጉዳቱ በይበልጥ እነሱ ላይ ያመዘነ በመሆኑ ነው።

ሁለት ሰዎች በትዳር ወይም በፍቅር አብረው ሲሆኑ፣ የአንዱ ሰው የከፋ ድርጊት ሌላኛውን ወገን ከምንጠብቀው በላይ ሊጎዳ ይችላል። አንዳንዴም በትዕግስት ከምናሳልፈው በላይ ይሆናል። ነገር ግን ያንን ቅሬታ በዚህ አይነት መንገድ መመለስ አስደንጋጭ ነገር ነው ባይ ነኝ።

እናስብ! ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በዚህ በአሁኑ ጋብቻና ፍቺ በተበራከተበት ወቅት ስንት እህቶቻችንን ልናጣ ነው? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። ዛሬ እሷ ቤት ዘልቆ የገባው ችግር ነገ የእያንዳንዳችን ቤት አያንኳኳም ብለን ካሰብን ተሳስተናል።

ይህ ሰው በዚህ አልበቃውም፤ እንደሱ አባባል ይሄ ለእሷ ጥፋት የ‹‹ኢምንት›› ያህል ቅጣት ነውና ሌላም ይቀረኛል ባይ ነው። እሷ ነገ ከቤተሰቦቿ አንዱን በተመሳሳይ አደጋ ታጣ ይሆናል። ማን ያውቃል? ግለሰቡ እስካሁን ሰዓት ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አልዋለም። እንደማንኛውም ሰው እየተዘዋወረና በቤተሰቦቿ ላይ ‹‹ዛቻ እያቀረበ ነው››። የዚህች ሴት ቤተሰብ ህልውናም በጥርጣሬና በስጋት ውስጥ ነው። ሕግ ባለበት አገር እንዲህ ያለ ነገር መፈፀሙ ግር የሚያሰኝና አስቸኳይ መፍትሄ አለመወሰዱ፣ ለነገው መጥፎ ድርጊት ተባባሪ ሊሆኑ በሚችሉ እንደማበረታቻ ሊታይ ይችላልና አንድ ይባል።

ሶስቱ ልጆቿ እናታቸው በምን አይነት ሁኔታ እንዳለች አያውቁም። ቤተሰቦቿ እሷን ከማስታመም ባለፈ ሁኔታ፣ ለራሳቸው ጥንቃቄ ማድረግ ከብዷቸዋል። ይህች ሴት ልሳኗ ተዘግቷል። ገጽታዋን በሚቀይር ሁኔታ በአሲድ ተጠብሳ ትላንት የነበረችበት ሁኔታ ላይመለስ ቀርቷል። ነገር ግን፣ ‹‹መንግስት፣ ሕዝብና ሕግ ይፋረደኝ›› ትላለች።

ቢገባን፣ የእሷ ‹‹ይፋረደኝ›› ለእሷ ብቻ አይደለም። የእሷ ነገርማ የፈሰሰው ውሃ ላይታፈስ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬ ለእሷ አቤት ማለታችን፣ ነገ ለእኛ ዋስትና ይሆነናልና ‹‹አቤት›› እንበል።

የሚገርመውና አሳፋሪው፣ እንዲህ ዓይነቱ አሰቃቂ ነገር የሚደርሰው ‹‹የትዳር አጋሬ›› ባሉት ሰው መሆኑ ነው። አሳፋሪነቱ

ያ ብቻም አይደለም። ‹‹ሰብዓዊ›› ከምንለው ፍጡር ኃሳቡ መምጣቱ፣ ወደየት እያመራን ነው የሚለው ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳል።

በቅርብ የመከታተል ዕድል ገጥሞት የነበረ አንድ የቀድሞ የቅንጅት ከፍተኛ አመራር አባል፣ ‹‹ሰዎቹ በውይይታቸው በኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን ከእስር እንለቀቃለን የሚል ተስፋ ጨርሶ የላቸውም›› ሲል ነበር የውይይታቸውን አንደምታ በእስር ቤት ማስታወሻው ላይ የከተበው፡፡ ታህሳስ 23 ቀን 1988 ዓ.ም ከእስር የመፈታት ተስፋ እንደሌላቸው ሲመክሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች፣ በግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም የይቅርታ ዜና መስማታቸው በባለ ግለ-ማስታወሻው ዘንድ አንዳች ግራሞትን ያጫረበት ሆኗል፡፡

የ23ቱ ዜና ለ23ቱ በ17 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተከሰሱትና የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው የነበሩ 23 የደርግ ባለሥልጣናት፣ የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት የተቀየረላቸው መሆኑ በይፋ የተገለፀው ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። ረቡዕ ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም በኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት በተዘጋጀ ልዩ ሥነ-ሥርዓት በደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ወደ ዕድሜ ልክ እሥራት መለወጡን ያሳወቁት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ናቸው። ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ፣ ይቅርታው የተደረገላቸው 23ቱ የደርግ ባለሥልጣናት በጥፋታቸው መፀፀታቸውን በፅሁፍ ጭምር መግለፃቸውን አሳውቀዋል። የሀገራችን ሕዝቦች ያለፈውን የታሪክ ምዕራፍ ዘግተው፣ ለፈጣን ልማት፣ ለመልካም አስተዳዳርና ለዴሞክራሲ ግንባታ በሙሉ አቅምና በአንድ መንፈስ መራመድ እንዲችሉ የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል በሚል ዕምነት የሞት ቅጣት ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲሻሻልላቸው ከተለያዩ ወገኖች ይቀርብ የነበረውን ጥያቄ ተቀብለው ማፅደቃቸውን አብራርተዋል። በዚህም መሠረት ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ፣ ሻምበል ለገሠ አሰፋው፣ ሻለቃ መላኩ ተፈራ እና፣ ኮሎኔል ተስፋዬ ወ/ሥላሴን ጨምሮ 23 የደርግ ባለሥልጣናት የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀየር መወሰኑን፣ ውሳኔውም ከግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የፀና እንደሚሆን አስታውቀዋል። ይህንን የፕሬዝዳንቱን የፍርድ ማሻሽያ ይቅርታ ተከትሎ፣ እስረኞቹ በቅርቡ ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ግምት እየተሰነዘረ መሆኑን ዝግጅት ክፍላችን በጉዳዩ ዙሪያ ያሰባሰበው አስተያየት ያመለክታል።

ደርጎችና የሞት ፍርድኢህአዴግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ እጃቸውን ተይዘው ለእስር የተዳረጉት የደርግ ባለሥልጣናት በተናጠል ተመስርቶባቸው የነበረው ክስ ተሻሽሎ የቀረበውና በከፍተኛ ፍ/ቤት በመደበኛነት መታየት የጀመረው ህዳር 18 ቀን 1988 ነው። በፋይል ቁጥር ል/ዐ/ም/መ/ቁ 401/85 ሌ/ኮ መንግሥቱ ኃይለማርያምን ጨምሮ ክስ የተመሰረተባቸው ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት የተመሰረተባቸው ክስ 211 የወንጀል ዝርዝሮችን የያዘ ነበር፡፡ ይህ ክስ በከፍተኛ ፍ/ቤት ደረጃ ድምዳሜ ያገኘው እጅግ ዘግይቶ ከ12 ዓመታት በኋላ መሆኑም ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በከሳሽ ልዩ ዐቃቤ ሕግና በራሳቸው በተከሳሾቹ የይግባኝ አቤቱታ አቅራቢነት ጉዳዩ በጠቅላይ ፍ/ቤትም ታይቷል። ጠ/ፍ/ቤትም ጉዳዩን አጥንቶ በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም የመጨረሻ ውሳኔ ሰጠ። ጠ/ፍ/ቤት ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ አንደኛ ተከሳሽ ኮሎኔል መንግሥቱ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዳኞች አብላጫ ድምጽ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ የወሰነ ቢሆንም፣ ፍርዱን አሻሽሎ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል። ሌሎች፣ ማለትም ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ፣ ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ፣ ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ፣ ሻምበል ለገሰ አስፋው፣ ሻለቃ አዲስ ተድላ፣ ሌ/ኮሎኔል እንዳለ ተሰማ፣ ሻምበል ገሠሠ ወልደኪዳን፣ ሜጀር ጄኔራል ውብሸት ደሴ፣ ሻለቃ ካሳዬ አራጋው፣ ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ፣ ሻምበል በጋሻው አታላይ፣ መቶ አለቃ ስለሺ መንገሻ፣ ኮሎኔል ናደው ዘካሪያስ፣ ምክትል መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ፣ መቶ አለቃ አራጋው ይመር፣ ሻለቃ ደጀኔ ወንድምአገኘሁ እና መቶ አለቃ ደሳለኝ በላይ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳለፈ። እንዲሁም አምስተኛ ተከሳሽ የነበረው ኮሎኔል ካሳሁን ታፈሰ የይግባኝ ክርክር

ተጠናቅቆ መዝገቡ በመመርመር ላይ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ማረሚያ ቤቱ በማረጋገጡ ከዚህ በላይ በግለሰቡ ላይ የሚወሰን ቅጣት ስለማይኖር መታለፉ ተገልጾ ነበር። 26ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ አክሊሉ በላይነህ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነበት የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዳለ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፀንቷል። ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም፣ ሻለቃ አዲስ ተድላና ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ በሌሉበት የተፈረደባቸው ናቸው። በዚህ ሁኔታ የተቋጨው የደርጎች ክስና ፍርድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተደመደመ መስሎ ነበር። ነገር ግን በያዝነው ዓመት ታህሳስ ወር በይቅርታ ሃሳብ አገርሽቶ ለአደባባይ በቃ።

ይቅርታና ይሁንታበኢትዮጵያ የተለያዩ ዕምነት ኃይማኖት አባቶች በደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተላለፈው ፍርድ በይቅርታ እንዲታይ እንቀስቃሴ ላይ መሆናቸው ይፋ የሆነው በታህሳስ ወር 2000 ዓ.ም ነበር። የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ኃይማኖት መሪዎች ታህሳስ 16 ቀን 2003 ዓ.ም ‹‹የይሁንታ ቀን›› በሚል ታላቅ አገራዊ ጉባኤ ለማካሄድ አቅደው እንደነበር በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።ይህንን ሁኔታ ተከትሎ በወቅቱ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ያነጋገራቸው፣ በእስር ላይ የሚገኙት የደርግ ባለሥልጣናት የሕግ አማካሪና ጉዳይ ተከታታይ አቶ ሞላ ዘገየ፣ እሳቸውም ከፍርደኞቹ ጋር ተከሰው ለ8 ዓመታት ታስረው በነፃ መሰናበታቸውን አስታውሰው፣ በእስር ላይ የሚገኙት የደርግ ባለሥልጣናት ‹‹ይቅርታ የሚያስጠይቁ ድርጊቶች አድርገናል፤ ይቅርታ መጠየቅ አለብን›› የሚል ሀሳብ እንደነበራቸው የሚያውቁት ከዓመታት በፊት መሆኑን አብራርተው ነበር። አክለውም፣ የደርግ ባለሥልጣናት ከ6 ዓመታት በፊት ፊርማቸውን ያሳረፉበት የይቅርታ ማመልከቻ በእሳቸው በኩል ማቅረባቸውን፣ እሳቸውም በፖስታ ቤት ለጠ/ሚ/ሩ ቢሮ መላካቸውን ገልፀው፣ ማመልከቻው ለጠ/ሚ/ሩ ይድረስ አይድረስ እንደማያውቁ አብራርተው ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ የደርግ ባለሥልጣናቱ የይቅርታ ይደረግልን ጥያቄ ከታሳሪዎቹ ከራሳቸው ለኃይማኖት አባቶች የቀረበረው በ2000 ዓ.ም የዘመን መለወጫ እንደሆነም በዛው ሰሞን ነበር የተዘገበው። በወቅቱ ‹‹የይሁንታ ቀን›› በሚል ታስቦ ሲጠበቅ የነበረውን ይቅርታ በተመለከተ በደርግ ሥልጣነ-ዘመን የጉዳት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ማኅበራትም ሀሳባቸውን ሰንዝረውበት ነበር። የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማኅበር አመራሮች የሆኑት አቶ መኮንን ወልዴና አቶ ዮሐንስ ገ/ሕይወት ታህሳስ 9 ቀን 2003 ለወጣው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በይቅርታው ሀሳብ ተቃውሞ እንደሌላቸው ገልፀው፣ ከኃይማኖት አባቶች ጋር በዝርዝር ያልተነጋገሩበት መሆኑን ግን ሳያክሉ አላለፉም ነበር፡፡ ይህ ግን የእነሱ አመለካከት እንጂ አጠቃላይ የማኅበሩን ሀሳብ እንደማይወክልም አክለው አብራርተዋል።

የስቃይ ሰለባዎች ማኅበር የተባለው ሌላው የደርግ ዘመን ተጎጂዎች ማኅበር ደግሞ በወቅቱ ለአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በላከው ደብዳቤ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ወገኖችተ የት እንዳሉ ሳይጠየቅ፣ የወንጀሉ ፈፃሚዎች ክስ ሲመሰረት የካሳ ጉዳይ ጎን ለጎን መሄድ ሲገባው እንዳልተደረገ ጠቅሰው፤ የኃይማኖት አባቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ለቀድሞ የደርግ ሥርዓት ባለሥልጣናት ይቅርታ እንዲደረግ መጠየቃቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀው ነበር። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲያስተናግድ የነበረው የሀገሪቱ የኃማኖት አባቶች ‹‹በይሁንታ ቀን መርህ›› ላይ የተመሰረተው የይቅርታ ይደረግ ጅማሮ፣ ላለፉት አራት ወራት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፍንጭ እንኳ አልታሰጠበትም ነበር። ይሁን እንጂ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ረቡዕ ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ድንገት በሰጡት መግለጫ ይቅርታው ዕውን መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ከይቅርታው በኋላፕ/ት ግርማ የሞት ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት መቀየሩን በይፋ ካሳወቁ በኋላ በይቅርታው ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ፕሬዝዳንቱ ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ በሰጡ ማግስት (ሐሙስ ግንቦት 24/2003) በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒሰቴር ሚኒስትር አቶ ብርሃን ኃይሉ ይቅርታው በሕገመንግስቱ መሰረት የተደረገ መሆኑን አብራርተው፣ በደርግ ዘመን የተጎዱ ቤተሰቦችም የወደፊቱን እያዩ ይቅርታውን እንደሚቀበሉት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። ‹‹ስላለፈው ምዕራፍ ሳይሆን ስለአዲስ ምዕራፍ ነው ማሰብ ያለብን›› ያሉት ሚ/ር ብርሃን ኃይሉ፣ ይቅርታ መደረጉ ከመርህ አንፃር ሕጉን መፈታተን ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበትም በአፅንኦት አስምረውበታል። አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ይቅርታ ሕገመንግስቱን የተከተለ መሆኑን ገልፀው፣ ታሳሪዎቹን ለመልቀቅ ብቸኛው ቀዳዳ ይህ ብቻ አንደሆነ በአፅንኦት አስምረውበታል። ‹‹ይህ ማለት ታሳሪዎቹ በእርግጠኝነት ይለቀቃሉ ማለት ሳይሆን፣ የዕድሜ ልክ ፍርደኞች 20 ዓመት የእስር ጊዜ ካሳለፉ ማረሚያ ቤቱ በአመክሮ ሊለቀቸው የሚያስችለውን በር ይከፍትለታል›› ሲሉ ግምታቸውን ሰንዝረዋል።የደርግ ባለሥልጣናት የሕግ አማካሪና ጉዳይ ተከታታይ የሆኑት አቶ ሞላ ዘገየ ከዚህ በኋላ ምን እንደሚጠብቁ ለቁረበላቸው ጥያቄ ለአውራምባ ታይምስ በሰጡት ምላሽ እንዲህ ይሆናል ብለው መገመት እንደማይችሉ ነው የተናገሩት። ይሁን እንጂ ይቅርታው በራሱ ለሀገሪቱ አዲስ ምዕራፍ ጉዞ ጅማሬ አንድ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ ገልፀውታል። አክለውም፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች እኮ ከተፈረደባቸው ቀን ጀምሮ እስከ ይቅርታው ቀን ድረስ የሚጠብቁት ሞትን ነበር፡፡ ይቅርታው በዕድሜ ልክ የተለወጠ ዕለት ሕይወትን እንደገና በተስፋ እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል። ለሰው ልጅ ደግሞ ዋናው ነገር ተስፋ ነው። ተስፋ ካለ ነገ የራሱን ነገር ይዞ የሚመጣ ይመስለኛል›› ሲሉ በይቅርታው መደሰታቸውን ገልፀዋል።ከፕሬዝዳንቱ የይቅርታ መግለጫ በኋላ የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው አብዛኛቹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ‹‹የጊዜ ጉዳይ እንጂ የደርግ ባለሥልጣናት በቅርቡ ሊፈቱ ይችላሉ›› የሚል ሀሳስ ሰንዝረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ በአብዛኛው ይቅርታ የተደረገላቸው ሰዎች ሊፈቱ እንደሚችሉ ይገምቱ እንጂ፣ ከመንግሥት በኩል ስለሰዎቹ መፈታትም ሆነ አለመፈታት ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ በሰጡ ማግስት (ሐሙስ ግንቦት 24/2003) በጉዳዩ

ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒሰቴር ሚኒስትር አቶ ብርሃን ኃይሉ

ይቅርታው በሕገመንግስቱ መሰረት የተደረገ መሆኑን አብራርተው፣ በደርግ ዘመን የተጎዱ

ቤተሰቦችም የወደፊቱን እያዩ ይቅርታውን እንደሚቀበሉት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

ደርጎች እና...

የነበረው የዳቦ፣ የሥጋና የስኳር ሰልፍ ከእዝ ኢኮኖሚ ወደ ነጻ ገበያ ሲገቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መጥፋቱን የተናገረው ጋዜጠኛ እስክንድር በሰሜን አፍሪካ የነበረው ሁኔታ መንግስት አሳስቦት ወደ ዋጋ ቁጥጥር በመመለሱ ሳቢያ ስኳርና የዘይት ሰልፎች መፈጠራቸውን ይገልፃል። ሰልፉ ኢትዮጵያን በአፍሪካም ሆነ በዓለም ብቸኛዋ እንደሚያደርጋት በማስታወስ።

ሆኖም ግን ይኼ የኢትዮጵያን ገፅታ እንደሚያበላሽ መንግስት በመረዳቱ ከሶስት መሠረታዊ ሸቀጦች በስተቀር የዋጋ ተመን ማንሳቱን በምክንያትነት በመጥቀስ በሦስቱም ሸቀጦች ላይ ያለው የዋጋ ተመን መነሳት እንዳለበት ጋዜጠኛ እስክንድር ሃሳቡን ይሰነዝራል።

‹‹ንግድ ውስጥ የመንግስት እጅ ሲገባ ውጤቱ ቀውስና እጥረትና መዛባት ነው። አሁን የተራመደው ግማሽ እርምጃ ነው። ለዋጋ ግሽበቱ መነሻ የነጋዴዎቹ ስግብግብነት መሆኑን መንግስት ቢገልፅም አይ.ኤም.ኤፍ በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት ለዋጋ ግሽበቱ ተጠያቂው መንግስት ብሎ ነው ብሎ አጣጥሎታል። በሁለቱ መካከል ያለው ክፍተት ሰፊ ነው። እንዲያውም እስክንድር አንድ ማሳሰቢያ አለው፡፡ ‹‹መንግስት እያተመ ገበያ ውስጥ የሚያስገባውን የገንዘብ መጠን መቀነስ አለበት›› የሚል፡፡

ብዙዎች የአሁኑንም መንግስት አቋም የመጨረሻው እንደሆነ አይሰማቸውም፡፡ በድንገት ደግሞ አዲስ አይነት መመርያ ሊወጣ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አላቸው፡፡ ይህ በገበያ ስርኣቱ ላይ ያለመተማመን መንፈስ ደግሞ የተዛባ አመለካከት በመፍጠር ሁኔታውን ሊያረጋጋው እንዳልቻለ እየተነገረ ይገኛል፡፡ እንዲያውም አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሁኔታውን የገለጹት ‹‹መርሕ አልባ፣ አቅጣጫ አልባ ሲሉ ነው፡፡››

ለዚህ ፊቸር ሱራፍኤል ግርማ ገንቢ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

መርሕ አልባ ...

Page 18: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዜ ና ዎ ች 19

መርሕ አልባ ...

በቀለ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አገሩ ሲገባ ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ተይዞ መታሰሩ ተገለፀ።

ቤተሰቦቹን ለመጠየቅና ለአንድ ሳምንት ያህል በአገሩ ለማሳለፍ ከትናንት በስቲያ ከዋሽንግተን ዲሲ አዲስ አበባ የገባው ኮሜዲያን መስከረም ሐሙስ ዕለት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በስፍራው የነበሩ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኦፊሰሮች ለጥያቄ እንደሚፈለግ ከገለፁለት በኋላ ይዘውት መሄዳቸውን ቤተሰቦቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል።

ኮሜዲያን መስከረም የአሜሪካ ዜግነት ያለው በመሆኑ በቁጥጥር ስር መዋሉ ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቹ አዲስ አበባ ለሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ሪፖርት እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የኢምባሲው ቃል አቀባይ ዳያን ብራንት ‹‹ኢምባሲው ስለጉዳዩ በቂ መረጃ አለው›› ካሉ በኋላ ‹‹ነገር ግን የአሜሪካ ዜጎችን በሚያካትት መሰል ጉዳይ㜎 ላ㜎ይ ኢምባሲው አስተያየት አይሰጥም›› ብለዋል።

ጋዜጣችን ወደ ህትመት እስከገባችበት ትናንት ምሽት ድረስም ኮሚዲያኑ እንዳልተለቀቀ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ስለ ጉዳዩ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የቦሌ ኤርፖርት የኢሚግሬሽን ቢሮ ኃላፊዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ጉዳዩ ይመለከታቸው የተባሉ ሃላፊ ሰብሰባ ላይ እንደሆኑ ስለተነገረን ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።

ኮሜዲያን መስከረም...

በሱራፍኤል ግርማ

ትዕግስት መኮንን በተባለች ወጣት ላይ ድብደባና የአሲድ ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ እስካሁን ድረስ አለመያዙን ቤተሰቦቿ አስታወቁ። ጉዳዩን አስመልክቶ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የሰጡት የተጎጂዋ ቤተሰቦች እንዳሉት ከሆነ፣ ጥቃቱ ከተፈፀመ አንድ ወር ቢሞላውም ወንጀሉን ከሚከታተለው የፖሊስ ክፍልም ሆነ ከሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አጥጋቢ ውጤት አላገኙም።

በወጣቷ ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው ዕሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2003 ዓ.ም ሲሆን ወንጀሉን ከግብረ አበሮቹ ጋር ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረው ደግሞ ባለቤቷ አቶ ምናለ አቻም ነው። በዕለቱ ቤተሰቦቿንና የቀድሞ ጎረቤቶቿን ለመጠየቅ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄዳ የነበረችው ትዕግስት ጉዳቱ ሊደርስባት የቻለው ፀበኛዋ የሆነው ባለቤቷ መምጣቱን ልጇ ደውሎ ነግሯት

በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ በግል ባንኮች ላይ በተጣለው የማበደር ገደብ እና በአስቸጋሪ የቢዝነስ ሁኔታ የተነሳ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2011/12 የበጀት ዓመት ውስጥ በ6 በመቶ አካባቢ እንደሚያሽቆለቁል ተገለፀ፡፡

በተያዘው የበጀት ዓመት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ11.4 በመቶ እንደሚያድግ ከገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ግምት በተፃራሪ፣ ኢኮኖሚው የሚያድገው በ7.5 መሆኑን የገለፀው መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን ዋሽንግተን ያደረገው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ነው፡፡

‹‹የማክሮኢኮኖሚው ዋነኛ ጋሬጣ እያሻቀበ ያለ ግሽበት ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ዓለም አቀፍ የምርት ዋጋዎች እየጨመሩ መሆናቸውን በከፊል የሚያሳይ ቢሆንም፣ ዋነኛው መንስዔ ግን የተትረፈረፈ የገንዘብ ዕድገት ነው›› ሲል አይ.ኤም.ኤፍ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በያዝነው ዓመት መጋቢት ወር ውስጥ 25.0 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ ግሽበት፣ በተከታዩ ሚያዝያ ወር ውስጥ ወደ 29.5 በመቶ አሻቅቧል፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመት የገንዘብ አቅርቦት እድገት

በሱራፍኤል ግርማ ከሳምንታት በፊት በኢትዮ-

ኬኒያ ድንበር አካባቢ በሚኖሩ ጎሳዎች መካከል ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ሥፍራውን ተቆጣጥረው የሚገኙት የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ከግዛቷ እንዲለቁ ኬኒያ ጠየቀች። ኬኒያ ጥያቄዋን ያቀረበችው ባሳለፍነው ሐሙስ የሁለቱ አገራት ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስብሰባ ባካሄዱ ጊዜ ሲሆን የማስወጣቱ ሂደትም በድርድር አሊያም በኃይል መሆን እንዳለበት በባለስልጣናቷ በኩል መግለጽዋን የኬኒያው ‹‹ኔሽን›› ዘግቧል።

የኬኒያ የመሬት ሚኒስትር የሆኑት ጄምስ ኦሬንጎ ‹‹በግጭቱ ወቅት

በሱራፍኤል ግርማ

በጅማ ዞን ዴዶ አካባቢ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ያለአግባብ እየወጣና ለብክነት እየተዳረገ መሆኑን የአካባቢው ተመራጭ የሆኑ የምክር ቤት አባላት አስታወቁ። የም/ቤት አባላቱ ስለሁኔታው የገለፁት የማዕድን ሚኒስቴር የ2003 በጀት ዓመት የአስር ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለም/ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነበር፡፡ አባላቱ ‹‹ለናሙና ተብሎ በብዛት ምርቱ እየወጣና እየተሸጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎችና አስተዳዳሪዎች ይገልጻሉ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግሩን ያውቀዋል ወይ? ለመሆኑ ለናሙና የሚወሰደው መጠን ምን ያህል ነው?›› ሲሉ ለሚኒስቴሩ

የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄ አቅርበዋል።የማዕድን ሚኒስቴር የሥራ

ኃላፊዎችም የድንጋይ ከሰል ክምችት ባለበት ቦታ ላይ የምርመራ ሥራ የሚያከናውኑ ባለፈቃድ ኩባንያዎች መሆናቸውንና አንዳንድ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለሙከራ እስከ 10 ቶን ድረስ እንደሚወስዱ በመግለፅ፣ ‹‹ለሽያጭ የዋለ የድንጋይ ከሰል የለም›› ብለዋል።

ሆኖም ጥያቄ አቅራቢው የቋሚ ኮሚቴው አባል ከሚኒስቴር መ/ቤቱ በተሰጠው ምላሽ ባለመስማማት፣ ‹‹ምንም እንኳን ለናሙናና ለሙከራ የተወሰነ መጠን በቂ ቢሆንም ከድሬዳዋ አካባቢ የመጡ ባለ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች 15 ሺህ ቶን ለማውጣት ጠይቀው ለጊዜው አንድ ሺህ ቶን ተፈቅዶላቸው እያመረቱ ነው›› ብለዋል። የሕዝብ ተወካዩ በማከልም

ማዕድኑ ያለአግባብ ከመመረቱ ባሻገር የነዋሪዎች መፈናቀልና የአካባቢ ብክለት እየተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የማዕድን ሚኒስቴር ባቀረበው የ10 ወራት ሪፖርት ላይ በፔትሮሊየም ፍለጋና ልማት ለተሰማራ አንድ ባለሀብት የሥራ ፈቃድ መሰጠቱን፣ ከሀገሪቱ የፔትሮሊየም ዕምቅ ሀብት ውስጥ በኩባንያ የተያዙና ያልተያዙ ብሎኮችን የመለየት፣ የኮንትራት ጉዳዮችንና የፔትሮሊየም ሕጎችን ለኢንቨስተሮች የማስተዋወቅ ሥራ መከናወኑ ሰፍሯል። ከፔትሮሊየም ሥራ 2.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶም 1.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡንም ሪፖርቱ ያመለክታል።

በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 5 ሺህ 815 ኪ.ግ ወርቅ በማስገባት

243.3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማስገኘት መቻሉን የሚገልጸው ሪፖርት፤ 3 ሺህ 706 ኪ.ግ ወርቅ፣ 135 ቶን ታንታለም፣ 123 ሜትር ኩብ ዕምነበረድ እና 240 ቶን ፑሚስ በኩባንያዎች አማካኝነት ወደ ውጪ እንዲላኩ ድጋፍ ተሰጥቶ 142.2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጪ ምንዛሪ መገኘቱን ያሳያል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ‹‹በአስር ወራት ውስጥ አጋጠሙኝ›› ካላቸው ችግሮች መካከል፣ የማዕድንና የፔትሮሊየም ፈቃድ የወሰዱ ባለፈቃዶች በገቡት ውልና ስምምነት መሠረት ሥራቸውን አለማከናወናቸውና ፈቃዶችን ለማስተዳደር የአቅም ማነስ አንዱ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።

22 በመቶ እንደሚሆን አይ.ኤም.ኤፍ አስቀድሞ ግምቱን ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ግን የነበረው ከፍተኛ የገንዘብ አቅርቦት (35 በመቶ) ነበር፡፡

ስጋን፣ ስኳርን፣ ዳቦን እና ቢራን ጨምሮ በ17 የምግብና የመጠጥ አይነቶች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የዋጋ ጣሪያ አውጥቶ ተግባራዊ አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ በመጪዎቹ ቀናትም ሱካር፣ ዘይት፣ ዳቦንና ዱቄትን ሳይጨምር በሌሎች ላይ የተጣለው የዋጋዎች ጣሪያ እንደሚነሳ የንግድ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

ያን የመንግስትን ውሳኔ በማስመልከትም አብዛኛውን የዋጋ ቁጥጥር ለማንሳት የተወሰደውን ውሳኔ በበጎ እንደሚቀበለው አይ.ኤም.ኤፍ ያስታወቀ ሲሆን፣ አያይዞም መንግሥት ያለውን የንግድ ሁኔታ ለማሻሻል እርምጃ እንዲወስድና የግብይት ወጪን እንዲቀንስ አሳስቧል፡፡

‹‹በባንክ ሥርዓቱ ላይ የሚያደርሰውን የመስተጓጎል ውጤት ለመቀነስ›› የግል አበዳሪዎች የመንግስት ቦንድ እንዲገዙ የሚያስገድደውን ትዕዛዝ በመንግሥት ከእንደገና ሊያጤነው እንደሚገባም ተቋሙ አሳስቧል፡፡

‹‹እንዳይረብሻቸው›› በሚል ወደ ልጆቿ በመሄዷ ነው።

የተጎጂዋ ወንድም የሆነው ዮሐንስ ታደሰ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ‹‹ስልኩ እንደተደወለላት ወደ ልጆቿ ለመሄድ ተነሳች፣ ከዛም ባሏ ደውሎ ድብደባ እንደፈፀመባት ነገረኝ። እኔም ኧረ ተዉ ምንድን ነው ሁሌ የሚያጣላችሁ› ስለው ‹ገና አንተንም አጠፋሀለው› አለኝ ከአነጋገሩ በደንብ መጣላታቸው ቢገባኝም አሲድ ይደፋባታል ብዬ ግን አልጠበኩም›› ሲል ያስታውሳል።

አሲዱ የተደፋባት በጭንቅላቷ፣ በጀርባዋ፣ በማጅራቷ፣ በእጅና እግሯ እንዲሁም በከፊል ፊቷ ላይ ሲሆን በተለይም በጭንቅላቷ እና በዓይኗ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል።

ትዕግስት ተኝታ በምትታከምበት የካቲት 12 ሆስፒታል የቃጠሎ ክፍል ውስጥ ባገኘናቸው የህክምና ባለሙያዎች ገለፃ መሠረት ከአሲድ ጥቃቱ በፊት ራሷን እንዳትከላከል ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ

ድብደባ ስለተፈፀመባትና በዚሁ የተነሳ መንቀሳቀስ ባለመቻሏ የጉዳቱ አሰቃቂነት ከዓመታት በፊት የአሲድ ጥቃት ሰለባ ከነበረችው ካሚላት በእጅጉ የከፋ ነው።

በሆስፒታሉ የቃጠሎ ክፍል ውስጥ የሳይኮ-ቴራፒ ባለሙያ የሆነችው ሲስተር ትዕግስት ምህረት፣ ‹‹አዕምሮዋ በጣም ተጎድቷል። ስለልጆቿና ስለወደፊት ሕይወቷ በጣም ትጨነቃለች። ስለ ሰውየውና ስለ ሁኔታውም ስታስብ በጣም ነው የምትረበሸው›› ስትል በአሁኑ ሰዓት ስላለው ሁኔታ ገልፃለች።

ወንድሟ ዮሐንስ ታደሰ ደግሞ በበኩሉ የሶስት ልጆች እናት በሆነችው ትዕግስት መኮንን ላይ ከፍተኛ ድብደባና የአሲድ ጥቃት እንደፈፀመ የሚጠረጠረው አቶ ምናለ አቻም ከነግብረአበሮቹ ለፍትሕ እንዲቀርብና እህቱ የተሻለ ሕክምና የምታገኝበት ሁኔታ ይመቻች ዘንድ ለመንግስትና የኢትዮጵያ ሕዝብ ተማፅኖውን አቅርቧል።

በጅማ ዞን የድንጋይ ከሰል ያለአግባብ እየወጣ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደሚያሽቆለቁል ተገለፀ

የአሲድ ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም

‹‹ጉዳቱ ከካሚላትም ይብሳል››የሕክምና ባለሙያዎች

የአመለካከት ለውጥ

ኤግዚብሽን እና

ባዛር ይካሄዳልየአዲስ አበባ ወጣቶች

ማሕበር፣ ዘልኪ ትምህርታዊ መድረኮችን ማመቻቻ ድርጅትና አዱሊያን የማስታወቂያና ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማሕበር በጋራ ያዘጋጁት የአመለካከት ለውጥ ኤግዚብሽን፣ ባዛርና ፌስቲቫል በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ይካሄዳል።

ኤግዚብሽኑና ፌስቲቫሉ ከሰኔ 29 እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከ300 በላይ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የንግድ ድርድቶች በመሳተፍ ያላቸውን ምርትና አገልግሎት ለሕዝብ እንደሚያስተዋውቁ ባለፈው ሰኞ በፓናሮማ ሆቴል በተደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

በፌስቲቫሉ ላይ አዝናኝና አስተማሪ ቃል-ኪዳን እንደሚደረግ፣ ሥር-ነቀል የአመለካከት ለውጥና አዎንታዊ አስተሳሰቦችን የሚያጎለብቱ የሥራ ፈጠራን የሚያበረታቱ ሥልጠናዎችና የልምድ ልውውጦች እንደሚካሄዱ ጋዜጣዊ መግለጫው ያስረዳል።

በኤልያስ ገብሩ

ለአራተኛ ጊዜ በመርካቶ አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል ሕንፃ ላይ ለተከታታይ አምስት ቀናት የተደረገው የዕደ-ጥበብ አምራቾች ፌስቲቫል በትናንትናው ዕለት ተጠናቀቀ።

ባለፈው ሰኞ በነበረው የፌስቲቫሉ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የአንበሳ ማስታወቂያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ፣ በአዲስ አበባ ኔዘርላንድስ ኤምባሲ የልማት ትብብር ኃላፊ ሚ/ር ፍራንታ ዌጀርስ፣

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማሕበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ አቶ ተሾመ በየነ እና የም/ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድና አመራር አባላት ተገኝተው ነበር።

በዕለቱም የመርካቶ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፍቅርተ ልጅዓለም እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በየተራ ንግግር አድርገዋል። ‹‹ፌስቲቫሉ ልምዶችን የሚለዋወጡበትና ለምርቶቻቸው ገበያ የሚያፈላልጉበት ብቻ ሳይሆን፣ ብቁ የንግድ ተፎካካሪ ለመሆን በምርት ጥራት፣ አቀራረብና ዋጋ ረገድ ዘመናዊ አሰራርን መከተል እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው፡፡›› በማለት ኃላፊዋ ተናግረዋል።

አቶ ተሾመም በበኩላቸው

ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ሴክተር ትኩረት በማድረግ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን አቅም በማጎልበት የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ድህነትን በመቀነስ እና የአገሪቷን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን እየተንቀሳቀሰች መሆኗን በመጥቀስ የዝግጅቱ መካሄድ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ፍቅርተ ፌስቲቫሉ በጥሩ ሁኔታ ተጀምሮ መጠናቀቁን ለአውራምባ ታይምስ አስረድተዋል።

የሽመና፣ የእንጨትና የቀርከሃ ውጤቶች፤ የስጋጃ፣ የሸክላ ሥራና የልብስ ስፌት አምራች የሆኑ 35 ሴቶችና አምስት ወንዶች የፌስትቫሉ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

የተስተዋለውን የንፁሀንን ግድያ ሁለቱም ወገኖች ማስቆም አለመቻላቸው የሰብዓዊ መብት ቁልፍ እሴት ቸል መባሉን ያሳያል›› ማለታቸውንና የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ችግሩን ለመፍታት አንድ ቡድን ተቋቁሞ እየሰራ እንደሆነ መናገራቸውን ‹‹ኔሽን›› በድረ-ገጹ አስነብቧል።

በዘገባው መሰረት የሚኒስትሮቹን ውይይት በጋራ ከመሩት የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ግጭቱ መከሰት እንዳልነበረበት እና ከዚህ በኋላ

ሌሎች ግጭቶች እንዳይከሰቱ አገራቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደምታደርግ ገለፀዋል። አቶ ኃይለማርያም አያይዘውም በድንበር ላይ ያለውን ችግር የሚፈታ ኮሚሽን መቋቋሙን፣ በኮሚሽኑ አማካኝነትም በጋራ የድንበር ላይ ቅኝት እንደሚካሄድ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገለገሉባቸው የልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

የድንበር ግጭቱ የተቀሰቀሰው በግጦሽ መሬት የተነሳ ሲሆን ወደ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች መገደል ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።

የዕደ-ጥበብ አምራቾች ፌስቲቫል ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ከኬኒያ እንዲወጡ ተጠየቀ

Page 19: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003ጤ ና20

በኤልያስ ገብሩ

በኤልያስ ገብሩ

ተፈጥሮ በግለሰቦችና በማሕበረሰብ ጤና ላይ የሚያስከትለው በጎ ተፅዕኖ በአሁን ወቅት የጤና ፕሮሞተሮችን ትኩረት መሳቡን መረጃዎች ይጠቁማሉ። እ.ኤ.አ በ1999 የወጡ የምርምር ውጤቶች እንዳሳዩት ከሆነ ተፈጥሯዊ አካባቢዎች ለግለሰባዊና ማሕበረሰባዊ ጤና ያላቸው ጥቅም የላቀ ነው።ዊልሰን የተባሉ የዘርፉ ተመራማሪም ተፈጥሮ ለጤና ከፍተኛ ጠቀሜታን እንደሚሰጥ፣ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ ከሆነ ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ተጠብቆ በዘላቂነት እንደሚቀጥልና ደህንነቱ እንደሚገነባ ‹‹The Innately Emotional Affiliation of Human Beings to other Living Organisms›› በሚለው የምርምር ጥናት ፅሁፋቸው ላይ አመላክተዋል። ይኼም በጥንታዊ የዕውቀት ዘርፎች (ሳይኮሎጂ እና ባዩሎጂ)፣ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ የምርምር ጥናት ትኩረት በሆኑት የመዝናኛ፣ የመደሰቻና ተፈጥሯቸው በሰዎች ያልተነኩ የዱር ቦታዎች ሕክምና (Wilderness Therapy) ውስጥ ይገኛል። እ.ኤ.አ በ1995 በተደረጉ የምርምር ውጤቶች ማረጋገጫ መሠረት ላለፉት 200 ዓመታት የሰው ልጆች ከገጠር ወደ ከተማ ያደረጉት ፍልሰትና እንቅስቃሴ በተፈጥሮ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን በማስከተል በአካባቢያዊ ሥነ-ምህዳር ላይ መዘበራረቅን ፈጥረዋል። በዚህም በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የሚገኙ በርካታ የሰው ልጆች ቅድመ አያቶቻቸው በተፈጥሯዊ አካባቢያቸው አማካኝነት በጤናቸው ላይ ያገኙ የነበረውን መነቃቃትና የነበራቸውን ልምድ ሳያጣጥሙት ኑሯቸውን በግንብና በፎቅ ቤቶች፣ እንዲሁም እንቅስቃሴያቸውን በመኪና በማድረግ በድምፅና በተለያዩ የአካባቢ ብክለቶች እየተጠቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ። ሰዎች በተፈጥሮ ውስጥ በመኖር ጤናቸውን በማሻሻል ቀጣይነት ያለው ሕይወት እንዳይኖሩ በአሁን ወቅት ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው የተለመደ ግንኙነት እያነሰና እየቀነሰ መምጣቱ ቢገለፅም፣ ይኼንን ችግር ለመቅረፍ ግን ያን ያህል ከፍተኛ ጉልበት ወይም ጥረት እንደማይጠይቅ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሃሳብ ነው።

የሆስፒታል ሕሙማንእ.ኤ.አ በ1984 በእንግሊዝ ሀገር በሆስፒታል ተኝተው ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ በነበሩ ታማሚዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ነበር። በተኙበት ክፍል ውስጥ ሆነው ዛፎችንና እንስሳትን ይመለከቱ የነበሩ ሕሙማን ከሕመማቸው በፍጥነት ማገገማቸው ተረጋግጧል። እነዚህም በሆስፒታል የነበራቸው ቆይታ አጭር እንደነበረ፣ በጣም ዝቅተኛ መጠን ያለው የሕመም ማስታገሻ እንዳስፈለጋቸውና ከቀዶ ጥገና ሕክምና በኋላም በጣም አነስተኛ ችግር እንዳጋጠማቸው ጥናቱ አሳይቷል። ሆኖም በተኙበት ክፍል ውስጥ ሆነው ሌላ ሕንፃን የሚመለከቱና ዕይታቸው ከእፅዋትና እንስሳት ውጪ የሆኑ ሕሙማን ከላይ እንደተገለፁት በሕመማቸው ላይ ያን ያህል የተሻለ ለውጥን በፍጥነት አለማምጣታቸው ተጠቅሷል።

የማረሚያ ቤት

‹‹ጠባቧ›› መስኮትበማረሚያ ቤት ያረፉ የወንጀል ተጠርጣሪዎች (በሕግ ቢከለከልም በተግባር ግን ይታያል - የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ማረሚያ ቤት

ማሳረፍ) እና ፍርደኞች በታሰሩበት ክፍል ውስጥ በምትገኝ ጠባብ መስኮት አማካኝነት የተፈጥሮ እፅዋቶችንና እንስሳትን (ለምሳሌ ወፎችን) የማየት ዕድል የሚያገኙ፣ ተፈጥሯዊ ነገሮችን ለማየት ካልታደሉት በተሻለ ታምመው ወደ ሕክምና ባለሙያዎች የመሄድ አጋጣሚያቸውና ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ። እንዲሁም ዝቅተኛ የሥራ ላይ ውጥረት፣ ከፍተኛ የሥራ እርካታ እና አነስተኛ ሕመም የሚያጋጥማቸው የቢሮ ሠራተኞች ተፈጥሮን በአንክሮ የሚመለከቱ መሆናቸው ይገለፃል። በአውራ ጎዳናና በመኪና መንገድ ግራና ቀኝ ተፈጥሯዊና በሰዎች በተተከሉ ዛፎች፣ እንዲሁም ልምላሜን የተጎናፀፉ አካባቢዎችን እያስተዋሉ የሚያልፉ የመኪና አሽከርካሪዎች የደም ግፊትና ዝውውር፣ የልብ ምት ጥሩ እንደሚሆን እ.ኤ.አ በ1998 የተደረገ ጥናት ያመላክታል።

የሥነ-ልቦና ጤናሰዎች ተፈጥሯዊ እፅዋትንና እንስሳትን በሚመለከቱበት ጊዜ ከአካላዊ ባሻገር መንፈሳዊ (የሥነ-ልቦና) ጤናቸው እንደሚሻሻል ይጠቀሳል። እናም የሰዎች የሥነ-ልቦና ጤና ከተፈጥሮ ጋር ስላለው ዝምድና ጠለቅ ያለ የምርምር ጥናት ተካሂዶ ነበር። ተፈጥሯዊ ነገሮችን መመልከት ቁጣና ንዴትን ይቀንሳል። እንዲሁም ግለሰቦች ወሳኝ በሆኑ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲችሉ፣ እውነተኛ ፍላጎታቸውን በተረጋጋ መልኩና በዘላቂነት እንዲጠብቁና የደስተኝነት ስሜታቸው እንዲጎለብት ያስችላል።

በተፈጥሮ ውስጥ መሆንተፈጥሮን በመመልከት ስለሚገኙ የተወሰኑ የጤና ጠቀሜታዎች

ከላይ ጥቆማ ተሰጥቷል። በተፈጥሮ ውስጥ መሆንም በራሱ በጤና ላይ የሚያከትለው በጎ ተፅዕኖ አለ። በርካታ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከተፈጥሮ ጋር መገናኘት የላቀ ጤናን ይሰጣል። ይኼም ሰዎች አስቀድመው ኖረውባቸው ወደማያውቋቸው ስፍራዎች ወይም ሀገራት በሚገቡበት ጊዜ ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል። ሰዎቹ ከደረሱበት ሀገር ተፈጥሮ ጋር መተዋወቃቸው አቅማቸው እንዲጎለብት፣ ከሀገሪቱ የአየር ንብረት ሁኔታ ጋር የመተሳሰር ስሜት እንዲኖራቸው፣ ለሥራ ያላቸው ተነሳሽነትና ተሳታፊነት ቀና እንዲሆን ያግዛቸዋል። ለተፈጥሯዊ ነገሮች ውስጣዊ ስሜትንና ቀልብን መስጠት የአዕምሮ ድካምን፣ መሰላቸትን፣ ንዴትንና የቁጣ ስሜትን ለመቀነስ ይረዳል። በተጨማሪም፣ ችግር የመፍታት ችሎታን ለማሻሻል የሚጠቅም ሲሆን፣ በከተማ የሚኖሩ ሰዎች ለጥቂት ቀናት በተፈጥራዊ አካባቢዎች ማሳለፍ የሚችሉ ከሆነ

ለሰዎች የሚኖራቸው ትኩረት ይጨምራል።የመኖሪያ ቤት አካባቢን በአበቦችና በተክሎች ማሳመር፣ እንዲሁም የጓሮ አትክልቶችን በመኖሪያ ስፍራዎች መትከል ዓለም አቀፋዊ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። በዓለም ዙርያ በከተሞች አካባቢ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተለያየ የቦታ መጠን የጓሮ ተክሎችን ያለማሉ። እ.ኤ.አ በ1996 ልዊስና ፈርናስ የተባሉ ተመራማሪዎች በመኖሪያ ቤቶች አካባቢና ዙሪያ አበቦችንና የጓሮ አትክልቶችን ማልማት የሰዎችን ጫናና ውጥረት እንደሚቀንስ፣ ፀባያቸውን እንደሚያሻሽል፣ ማሕበራዊ ትስስርን እንደሚፈጥርና ማሕበራዊ አቅምን እንደሚያጎለብት በጥናታቸው አረጋግጠዋል።በቤት ውስጥ የሚገኙ ተፈጥሯዊ ተክሎችም ቢሆኑ ለጤና መልካም ጠቀሜታ አላቸው። እነዚህ የቢሮ ውስጥ የአየር ጥራትን ከማሻሻል ባለፈ የሥራ ምርታማነትን ይጨምራሉ። እንዲሁም

በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራሉ።

እንስሳትእንስሳትም ቢሆኑ ለሰው ልጆች ጤና ከረዥም ዘመናት ጀምሮ እየሰጡ የሚገኙት ጥቅም የጎላ መሆኑ ይጠቀሳል። እንስሳት ለሰዎች የምግብ ምንጭ ሆነው ከማገልገላቸው በተጨማሪ የደም ግፊት መጠንን፣ ጫናና ውጥረትን፣ እና ጥቃቅን የጤና ችግሮችን በመቀነስ ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው።ከቤት እንስሳት ጋር ጥሩ ወዳጅነት ያላቸው ሰዎች የቀዶ ጥገና ሕክምና ካደረጉ በኋላ ቶሎ ለማገገም እንደረዳቸው የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያመላክታሉ - በተለይም በዕድሜ ለገፉ ሕሙማን። ሌላ የምርምር ጥናት ደግሞ ለሳሎን ቤት የሚሆኑ ድንክዬ ውሻዎች ያሏቸው ሰዎች የደም ግፊት፣ የስብና የትሪግላይሴራይድ መጠናቸው ውሾች ከሌላቸው ሰዎች በተሻለ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል። በአሜሪካንና በካናዳ የዱር እንስሳት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከላትንና በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት ማቆያና መንከባከቢያን የሚመለከቱ፣ እንዲሁም ለማዳና የዱር እንስሳትን ለራሳቸው ደስታ ብለው የሚመግቡ ሰዎች ጤናቸው የተሻለ መሆኑን መረጃዎች ይገልፃሉ።

ኤኮ-ሳይኮሎጂኤኮ-ሳይኮሎጂ በአሁን ወቅት አዲስ የትምህርትና የጥናት ዘርፍ ሲሆን ተፈጥሮ እንዴት ጤናማነትን እንደሚያሻሽልና ጠብቆ እንደሚያቆይ ያስረዳል። ኤኮ-ሳይኮሎጂ (በተፈጥሮ የሚመራ ሕክምና - Nature Guided Therapy) ተፈጥሯቸው በሰዎች ያልተነኩ የዱር ቦታዎች

ለጤናችሁ ብላችሁ ከተፈጥሮ ጋር ኑሩ!

በልምላሜ ቦታዎች አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና መዝናናት

ለሰውነትና ለመንፈስ ጤና ያለው ጥቅም የላቀ መሆኑን በዓለም ዙሪያ ጥናት ያደረጉ

ሳይንቲስቶች ማረጋገጫ ይሰጣሉ። በአረንጓዴ ቦታዎች ስፖርት መስራት ዝቅተኛ ወጪና

አካላዊ ውጥረት ሲኖረው የአዕምሮን ኃይል በተሻለ መልኩ ያድሳል። ከድብርት ጀምሮ

የስኳር ህመምንና ያለዕድሜ የሚመጣ ዕርጅናን ለመከላከልም ይጠቅማል።

የመጎብኘት ልምድ (Wilderness Experience) የአትክልትና ፍራፍሬ ሕክምና (Horticultural Therapy) እና በእንስሳት የታገዘ ሕክምና (Animal Assisted Therapy) በዘርፍ ምርምሩ ላይ የሚሰጡት መረጃ እየጨመረ መጥቶ ተፈጥሮ ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።‹‹ብዙ ጥንታዊ የሰው ልጅ ማሕበረሰቦች ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር ያላቸውን ጠንካራ ቁርኝት በሚገባ ይገነዘቡት እንደነበረ ሁሉ፣ በሂደት ለተፈጥሮ ኃብቶች (እፅዋትና እንስሳት) ዝቅተኛ ትኩረትና እንክብከቤ እየተሰጠ እንደሄደም ያውቁታል።›› ሲል እ.ኤ.አ በ2002 የወጣ መረጃ ያስረዳል። … በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስም ያላቸውና በዘርፉ ሰፊ ምርምር ያደረጉት ዴቪድ ሱዚኪና ዴቪድ አተንብራ ተፈጥሮ ለአካላዊ፣ ለአዕምሯዊና መንፈሳዊ ጤና የሚሰጠውን የላቀ ጥቅም በምርምር ውጤታቸው ላይ ገልፀዋል።

አረንጓዴ አካባቢዎችብሔራዊ ፓርኮችና ደኖች ባሉበት አካባቢ በቅርበት መኖርና በተፈጥሯዊ ልምላሜዎች አካባቢ መገኘት ለጤና የላቀ ጠቀሜታን ይሰጣል። በእንግሊዝ ሀገር ጥናት ተደርጎ በለንሴት ሜዲካል ጆርናል ላይ የወጣ የምርምር ፅሁፍ እንደሚያስረዳው፣ የሳንባ ካንሰር ሕመም ኖሮባቸው በአረንጓዴና ለምለም አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውን ካልጎዱ በስተቀር ‹‹ጊዜያቸው ሳይደርስ›› የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው። በግላስጎውና ሴይንት አንድሪው ዩኒቨርስቲ በሁለት ተመራማሪዎች አማካኝነት የተደረገ ጥናት ደግሞ ጤናንና ደህንነትን ለመጠበቅ አረንጓዴ ቦታዎችን ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን እቅድ ለሚያወጡ የእንግሊዝ ባለስልጣናት አስገንዝበዋል።ሁለቱም ሳይንቲስቶች እ.ኤ.አ በ2005 በአጠቃላይ እንግሊዝ ካሉት 41 ሚሊዮን ሰዎች መካከል በጡረተኝነት ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ ጥናት አድርገው (ከ2001-2005) በከባድ ሕመም ሳቢያ ለ366,448 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ከአረንጓዴ ቦታዎች ጋር የነበረው ቁርኝት መሆኑን ያስረዳሉ። [ሟቾች ከተፈጥሮ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በጣም ዝቅተኛ ነበር]። በተጨማሪም በልምላሜ ቦታዎች አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና መዝናናት ለሰውነትና ለመንፈስ ጤና ያለው ጥቅም የላቀ መሆኑን በዓለም ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ሳይንቲስቶች ማረጋገጫ ይሰጣሉ። በአረንጓዴ ቦታዎች ስፖርት መስራት ዝቅተኛ ወጪና አካላዊ ውጥረት ሲኖረው የአዕምሮን ኃይል በተሻለ መልኩ ያድሳል። ከድብርት ጀምሮ የስኳር ህመምንና ያለዕድሜ የሚመጣ ዕርጅናን ለመከላከልም ይጠቅማል።በአሜሪካን ኮኔክቲከት የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አለን ሎጋን ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ዶክተር ኢቫ ስለሀብ ጋር በመሆን ‹‹Your Brain, On Nature›› እና ‹‹The Science of Nature’s Influence on Health, Happiness and your Mojo!›› የሚል መፅሐፍ አዘጋጅተው በዘንድሮ ዓመት ለንባብ አብቅተዋል። ከተፈጥሮ የሚገኘው ቫይታሚን ‹‹ጂ›› ለአዕምሮና ለሰውነት ጥቅሙ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

Page 20: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21

የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታርጋ የለጠፉ ብክለቶችና ብክነቶች

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

በአብዱ መሐመድ

በሰለጠነው ዓለም በተለይ በአሜሪካና በአውሮፓ አዲስ ዓመት ሲቃረብ በገና ሳምንት ቀላል የማይባል ሰው መኝታው ላይ ተኝቶ የሚያብሰለስለው ቴሌቭዥኑንና ሞባይሉን ጥሎ በአዲሱ ዓመት ወደቤቱ የሚያስገባውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ቁሳቁስ ነው። በገና ሳምንት ለወዳጅ ዘመድ ከሚቀርቡ ሥጦታዎች አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ቀጣም ፎዎች፣ አይፎን እና አይፓድ የመሳሰሉት በየቅርብ ጊዜ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው።

ከአሜሪካ ሕዝብ 80 በመቶው በየቀኑ - ልብ በሉ በየቀኑ - 350 ሺህ የሞባይል ቀፎዎችንና 130 ሺህ ኮምፒዩተሮችን ወደ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እንደሚጥል የዘገበው ኢ ዌስት ኖት በሚል ርዕስ በቅርቡ ለንባብ የበቃው ታይም መጽሔት ነው።

ቁልል - የተራራ - ከሚሰሩ ከነዚህ ውዳቂዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ እንደ ሊድና ሜርኩሪ ያሉ መርዛማ ቁሶችን የያዙ ናቸው። እነዚህ ቁሳቁሶች ደግሞ ወደጠቃሚ ምርት መቀየር በጊዜና በጤና ላይ በሚያስከትለው ጉዳት ሲሰላ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዘነ ነው። ለጤና እክል ሊያጋልጡ ይችላሉ የተባሉ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች በኢንዱስትሪ ከበለፀጉ አገራት ወደ ሌሎች አገራት እንዳይልኩ የሚከለክለውንና 21 ዓመት የሞላውን እና በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ የፀደቀውን ‹‹ቤዝል ኮንቬንሽን›› አልፈርም ያለች ብቸኛዋ አገር ኃያሏ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን ናት።

ኤጀንሲው በ2010 ባወጣው ሪፖርቱ፣ በአሜሪካን 43 ካምፓኒዎች ‹‹ካቶድ ሮይ ቲዩብ›› የያዙ ያረጁ ቴሌቭዥኖችን ጨምሮ ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን እንደ ቻይና እና ሕንድ ላሉ አገራት በገፍ እየሸጡ መሆናቸውን ይፋ አድርጎ ነበር። ውዳቂ ቁሶችን በመግዛት እንደገና ወደ ‹‹ጠቃሚ›› ቁስነት ቀይሮ ‹‹ምርቱን›› በማደግ ላይ ላሉ አገራት ለመቸብቸብ ሥራዬ ብለው የተያያዙትና አብዛኛውን ሥራ የሚያከናውኑት የጠለቀ ዕውቀት የሌላቸው ሰዎች ናቸው።

የ ኤ ሌ ክ ት ሮ ኒ ክ ስ ምንጣፎችን (circuit board) በእሳት እያቀለጡ ቀላጭ ሊዶችን በመለየት፣ አሲዶችን እያፈሰሱ ከኤኬትሮኒክስ ቁሶች ውስጥ የወርቅ ቅንጣቢ ለመልቀም የተሰማሩ ቻይናውያን በመርዛማ ጭሶች ስር ለሰደደ የካንሰር በሽታ መዳረጋቸውን የገለፁት በዛው በቻይና ውስጥ የሚገኘው ሻንቲ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ናቸው።

የአካባቢ ጥበቃ ድርጅቱ የሞባይል አምራች ድርጅቶች አነስተኛ ሜርኩሪ፣ አልሙኒየምና መስታወት የያዙ ቀፎዎችን እንዲያመርቱ ያወጣውን መመሪያ እንደአፕል፣ ዴል፣ ሶኒ ያሉ ካምፓኒዎች ከ2004 መተግበር ቢጀምሩም፣ ቻይና በእጅ አዙር ውዳቂዎችን እየገዛች በታዳጊ አገራት ውስጥ

በማምረት ላይ ትገኛለች።በማደግ ላይ ያሉ

አገራት የደረጃ ቁጥጥር መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች አካባቢን እና ጤናን የሚጎዱ ቁሶችን ለይተው እንደሚያውቁ ከግምት ባሻገር በእርግጠኝነት መናገር ቢቻልም፣ የኢንድራ ጋንዲን መርህ ተከትለው የራበው ሰው

ቀድሞ የሚያስበው ስለሚበላው ምግብ

እንጂ ስለሚቀርብበት ገበታ አይደለም

የሚል አቋም እያራመዱ ያሉ ነው የሚመስለው። እቃዎቹን በመጣሉ ሰዉ ጤናው ተጎዳም አልተጎዳም፣ ከባቢ አየር ተበከለም አልተበከለም፣ ሞባይል እንኳን መግዛት አቃተኝ ብሎ እጁን ከሚቀስርብን፤ ሳምንት ተጠቀመበት ወይም አንድ ወር፣ ፍላጎቱ ይሟላና እኛም እግረ-መንገድ እጅግ አነስተኛ በሆነ ወጪ ከፍተኛ የውጪ የምንዛሬ ቀረጥ እንሰብስብ እያሉ ነው።

ቀደም ሲል ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው ፍሎረሰንት አምፖል ከ5 ሚሊ ግራም በላይ ሜርኩሪ በውስጡ በመያዙ አሁን አሁን በኃይል ቆጣቢ አምፖል እየተተካ ከመጣው ከተንጠልጣዩ ኢንካን ዴስንት አምፖል ጋር ሲነፃፀር የያዘው የሜርኩሪ መጠን ከግማሽ ያነሰ ነው። በሌላ በኩል፣ ፍሎረሰንት አምፖል ከተንጠልጣይ አምፖል ዋጋው ከአራት እስከ አምስት እጥፍ ቢበልጥም፣ የሚጠቀመው ኃይል በ3/4ኛ የቀነሰና ለረዥም ዓመት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። (ለማለት የተፈለገው ደረጃውን ጠብቆ የሚመረተውን መሆኑን ልብ ይበሉ።)

ይህንን ከግምት በማስገባት 7 ዋት ኃይል የሚጠቀም ፍሎረሰንት አምፖል የሚሰጠው ብርሃን ከ40 ዋት ኢንካን ዴስንት አምፖል፣ የ26 ዋት ኃይል የሚጠቀመው ደግሞ 100 ዋት ኃይል ከሚልፈው እኩል ነው። ልዩነቱ የተፈጠረው ፍሎረሰንት አምፖል በሙቀት ያባካውን ኃይል በከፍተኛ መጠን የቀነሰ በመሆኑ ነው። በአገልግሎት ዘመን ሲሰላ ተንጠልጣይ አምፖል ከ6 እስከ 12 ወራት ድረስ ሲያገለግል፣ ፍሎረሰንት አምፖል ከ2 እስከ 3 ዓመታት ድረስ አገልግሎት የመስጠት ብቃት የተላበሰ ነው።

አሁን በሰለጠነው ዓለም በስቴዲየሞች፣ በትራፊክ መብራቶች እና በጎዳና መብራቶች አገልግሎት ላይ እየዋለ የመጣው ላይት ኢሚቲንግ ዳዩድ የተባለው አምፖል ደግሞ ከፍሎረሰንት አምፖል በዕጥፍ የቀነሰ (40 በመቶ ያነሰ) ኃይል የሚጠቀምና ከ5 እስከ 10 ዓመት አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

የእኛን ጨምሮ የሌሎች አገራት መንግሥታት እነዚህን ኃይል ቆጣቢ አምፖሎችን በነፃ ለሕዝብ እስከማደል የደረሱት የኃይል አቅራቦት እጥረት አጣብቂኝ ውስጥ ከተዘፈቁት በኋላ ከሕዝቡ ከሚሰበሰቡት የአገልግሎት ክፍያ ይልቅ የኃይል እጥረቱን ለመቀነስ ለጀኔሬተሮች የሚያቃጥሉት ነዳጅ ወጪ እጅግ የገዘፈ መሆኑን ከተረዱ በኋላ ነው።

ኃይልን መቆጠብ መንግሥትን ከአላስፈላጊ ወጪ ከማዳኑ በተጨማሪ፣ ተጠቃሚው

ኅብረተሰብ በኑሮ ውድነት ላይ የሚያሰማውን እሮሮ ለመቀነስም ከፍተኛ ድርሻ እንደሚያበረክት የሚታወቀ አብይ ጉዳይ ቢሆንም፣ ተገቢውን ስፍራ ግን ያገኘ አይደለም።

አሁን ከተማዎችን እያጥለቀለቁ ላሉ ሕንፃዎች ለሚኖራቸው ውበትና ጥንካሬ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው ሁሉ ለኃይል ቁጠባም ተመሳሳይ ቦታ ቢሰጥ እጅግ የተሸለ ነው። መስኮቶቻቸውን የሸፈኑ መስታወቶች በሙቀት ጊዜ ቀዝቃዛ አየር እንዲያስገቡ፣ በቅዝቃዜ ጊዜ ደግሞ ሙቀትን በሚፈጥሩ ድርብ መስታወቶች የተሰሩ፤ ሙቀት በሚያስገባና በሚያስወግድ ኢንሱሌሽን የተለበጡ ቢሆኑ ኖሮ፣ በየዓመቱ 40 በመቶ የኃይል መጠን መቀነስ በተቻለ ነበር። በገሀድ የምናየው ደግሞ መስታወታቸው አይን በሚያጠፋና ለአይን ጠር በሆኑ አንፀባራቂ መስታወቶች የተለጡ መሆናቸውን ነው።

ወደ ሰማይ ለመዝለቅ በሚደረግ እሽቅድምድም ከተማውን እያደመቁ የሚገኙ ሕንፃዎች አብዛኛውን ወጪ የሚያወራርዱት ቁልቁል እየወረዱ የሚቆፍሩትን መሬት ኮንክሪት ለመሙላት በሚያፈሱት የግንባታ ወጪ ነው። በሳይንስ የተረጋገጠው ደግሞ መሰረታቸው 55 በመቶ በኮንክሪት፣ 45 በመቶ በ‹‹ስላግ›› (ከብረት ማቅለጫ በሚወጣ ዝቃጭ - Slag-waste Product from Blast Furnace) ቢሞላ፣ መሰረቱን የበለጠ ጠንካራ ከማድረግ በተጨማሪ 1.2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣውን ወጪ ወደ 3.5 ሚሊየን ዶላር መቀነስ ይቻላል።

ስለብክለትና ስለኃይል

ቁጠባ ሲነሳ መንግሥትና ባለኃብቶች በአቅርቦቱም በምህንድስናውም ቀዳሚውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ለማለት እንጂ ለብክለቱና ለብክነቱ የጎላውን ድርሻ ሚያበረክተው እያንዳንዱ የማኅበረሰቡ ክፍል ነው።

ዓለማችንን ወደእቶን እሳት እየለወጠ ከሚገኘው የተቃጠለ አየር 22.7 በመቶው ወደ ከባቢ አየር የሚዘልቀው

ከየመኖሪያ ቤቱ ምግብ ለማብሰል ከሚቃጠለው ማገዶና ነዳጅ ነው። ኦክሲጂን እየሳበ የተቃጠለ አየር የሚተፋው የሰው ልጅ፣ በአሜሪካን እያንዳንዱ ቤተሰብ ተውቦና ደምቆ ጎዳና ለመሙጣት የአደፈ ልብሱን ለማጠብ በየዓመቱ 1800 ኪሎ ግራም በካይ ልብስ ማጠቢያ ኬሚካሎችን (የሳሙና አረፋዎች) ምድር ላይ እየረጨ ነው። ቆም

እንኳ የፓርቲው መሪዎች ልብ ያለመንካቱ አስገራሚ ነው። እንግዲህ ተቃዋሚዎች ካለፈው ስህተት አልተማሩም ለማለት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይቻላል።

በእኔ እምነት ዛሬ ሥርዓቱን ለመታገል የሚያስፈልገው ለሃያ ዓመት ያህል ያሰለቸን ጉንጭ አልፋ ውይይት፣ እርኩስ ሴራ፣ አግላይ አድማና ሁካታ አይደለም። ዛሬ አንዲት ሁላችንም የምንቆረቆርላት አገር አደገኛ በሆነ ሥርዓት ስር ልዩ በሆነ አደገኛ ሆኔታ ላይ ትገኛለች። (ሁላችንም የምንቆርቆርላት ስል አንዳንዶቹ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ ሆነው በንግድ ተሰማርተው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር በማፈስ ያሉ መሆናቸውን ዘንግቼ አይደለም።) ያም ሆነ ይህ ዛሬ የሚፈለገው የትግል ትብብር ያለፉት ስህተቶች፣ ሴራዎችና አድማዎች መደጋገም ሳይሆን አገሪቱ ያለችበትን ሆኔታ በቅጡ ተንትኖ ያለምንም ተጨማሪ ውይይት የተባበረ ትግል ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ የሮኬት ሳይንቲስቶች ወይም በብር የናጠጡ ፕሮፌሰሮችና፣ ዶክተሮችና መሃንዲሶችን አይጠይቅም።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ መሬት በጭንቀት የተወጠረ ሥርዓት አለ። አገር ያለ ባህር በር በማስቀረቱ፣ አእላፍ የወደቁለትን የድንበር መሬት በማስወሰዱ፣ በኤርትራና በሶማሊያ በኩል በመወጠሩ፣

ጥቂቶች በሚያስገርም ሆኔታ ዓለማቸውን በሚቀጩባት አገር በኑሮ ወድነትና በድህነት አረንቋ በሚማቅቅ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ዓይን በመግባቱ፣ ወዘተ… ምክንያት የተወጠረ ሥርዓት አለ። ይህ የውጥረቱ መጠን ሲሆን ከዚሁ አንጻር መታየት ያለበት ደግሞ ሥርዓቱ ቀድሞ ያስረከበውን ድንበር ለመጠበቅ በሚል ሽፋን አገሪቱ ያፈራችውን ያገር መከላከያ ኃይል በሙሉ በትግራይ መሬት ያሰፈረ መሆኑን ነው። ስለዚህ፣ ከፈለጋችሁ በኔ ስር ትገዛላችሁ ካልተስማማችሁ ደግሞ ትበታተናላችሁ በሚል ሥርዓቱ ይዞት ያለውን አገር የመበተን አጀንዳ በጥበብ ለማስለወጥ ያቀደ፣ የማይለውጥ ከሆነም ለመመከት የሚያስችል ትግል የሚጠይቀው ነገር ቢኖር ፈጣንና አስተማማኝ ትብብር እንጂ ማቆሚያ የሌለው ውይይት ሊሆን አይችልም። ይህ ሲሆን ግን እያየን አይደለምና ተቃዋሚዎች ካለፈው ሆኔታ ተምረዋል የሚል ግምት የለኝም።

ይሁን እንጂ፣ “ያረጀን እንስሳ አዲስ ጨዋታ ማስተማር አይቻልም” እንደሚባለው፣ በስህተት ላይ ስህተት፣ በሴራ ላይ ሴራ፣ በአድማ ላይ አድማ በመድገም ያደጉትና በዚሁ የተካኑት የኔ ትውልድና ከኔ ትውልድ በላይ ያሉ አዛውንቶችን የሚተካ የአዲሱ ትውልድ ትኩስ ኃይል በየቦታው ብቅ-ብቅ እያለ

ስለሆነ ሆኔታው ጨርሶ ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም። በገዢው ፓርቲ ውስጥም ቢሆን በተለያየ ጥበብ የሰረጉ ስለማይጠፉ ተስፋውን የበለጠ ያዳብረዋል የሚል ግምት አለኝ። ትግሉ ግን ከጊዜ ጋር ጭምር ስለሆነ ትንሽ ማሳሰቡ አይቀርም። በፍጥነት ከተሰራበት ግን አሁንም ተስፋ ያለ ይመስለኛል።

የ99.6% የምርጫ ትያትር

ባለፈው ዓመት፣ ማለትም በግንቦት 2002 ዓ.ም የተካሄደው፤ ምርጫ ሳይሆን የምርጫ ትያትር ነው ማለት ይቻላል። አገዛዙ ብቻውን ሮጠ፤ ብቻውን አሸነፈ። በመሰረቱ በ1997 ከነበሩት ሆኔታዎች ውስጥ በ2002 ምርጫ አንዳቸውም አልነበሩም። በርግጥ የ1997 ምርጫ በምርጫ 2002 ላይ ጥላ ማሳረፉ የሚያነጋግር አይደለም። በመጀመሪያ ተቃዋሚዎች በ1997 ምርጫ በነበሩበት ሆኔታ ላይ አልነበሩም። ራሳቸውም ተሰባብረዋል፤ የተበሳጨባቸው ሕዝብም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶ ነበር። ገዢው ፓርቲ ደግሞ አምስቱን ዓመት ያሳለፈው ገንዘብ በማፍሰስ (የአገርን ገንዘብ) ነበርና የሚስማሙትን ሥራ በመስጠትና በመሳሰለው በመደለል ነበር። ሚዲያው ደግሞ አምስት ዓመት ሙሉ የሥርዓቱ መቀስቀሻ መሣሪያ ብቻ ሆኖ ነበር። ስለዚህ አገሪቱን ወደ አንድ ፓርቲ ሥርዓት ለመለወጥ ሆኔታዎቹ ከሥርዓቱ ውስጥም ውጭም

የተመቻቹ ስለነበሩ ውጤቱ ብዙ የሚያስደንቅ አይደለም።

ከዚህ ውጭ ግን ብዙ ሰው ያላወቀው ምስጢር አለ። ይህን ምስጢር ሥርዓቱ ራሱም ቢሆን የደረሰበት በቅርቡ ነው። ሆኖም ሥርዓቱ ምስጢሩን በቅርቡ የደረሰበት ቢሆንም በዚህ ምክንያት ያለበትን ችግር እንዲሁ በቀላሉ ሰዎችን ከሥራ በማባረርና በተለያዩ ክሶች በማሰር የሚያቃልለው አይመስለኝም።

በ1997 እና በ2002 መካከል አገዛዙ አራት ሚሊዮን አባላት መለምያለሁ ባይ ነው። እንግዲህ በ1997 ምርጫ ማግስት የሆነውን ሁሉ ያየ ሕዝብ ምንም እንኳ በተቃዋሚዎቹ ጥፋት ቢበሳጭም የኢህአዴግ ባሪያ ሆኖ ለማገልገል ራሱን አሳልፎ ይሰጣል ብሎ ማሰብ ግን የሚቻል አይደለም። ስለዚህ፣ በወያኔ ፍቅር ተቃጥሎና ልቡ ተሰልቦ ወያነን ለማገልገል ሳይሆን ሁለት ግቦችን ለማሳካት ወደ ወያነ ጎራ በወዶ ገብነት ሰርጎ እንዲገባ ተደርጓል። ይህንን ረቂቅ ሥራ ያጠናቀሩት ደግሞ በጉዳዩ የተካኑና በሚገባ የተደራጁ በገሃድ ከኢትዮጵያ ውጭ፣ በህቡእ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በቂ እንቅስቃሴና የሰው ኃይል ያላቸው የትጥቅ ትግል ኃይሎች ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። እናም ሀሳቤን የማጠቃልለው ሥርዓቱ በ2002 ምርጫ አገኘሁት የሚለው 99% ውጤት ሕዝብ ‹‹በወያኔ ፍቅር በማበዱ›› የተገኘ ሳይሆን በተቃዋሚዎቹ ድክመትና የአንዳንድ ኃይሎች ሰርጎ-ገብ ስልታዊ አስተዋጽኦም ጠቃሚ ግብዓት የነበረው መሆኑን በመጠቆም ነው።

ምስጢር ...

ብሎ በማሰብ ከዚህ የጥፋት አሻራ የተወሰነውን ለመቅረፍ ቢሞክርና ልብሶች ከተጠራቀሙ በኋላ በሞቀ ውሀ በማጠብ በየዓመቱ 480 ኪሎ ግራም ፈሳሽ አረፋዎችን በመቀነስ እግረመንገዱንም ወጪውን መቀነስ ይችላል።

በ ዓ ለ ማ ች ን በትራንስፖርት ዘርፍ ጎዳና ላይ የሚሽከረከሩ አውቶሞቢሎች ለከባቢ ብክለት 14 በመቶ ድርሻ የያዙ ናቸው። ከአሜሪካን ሕዝብ ውስጥ 88 በመቶው ጎዳና የሚወጣው የግል አውቶሞቢል እያሽከረከረ ነው። የተቀረው 12 በመቶ የሚጓዝባቸው በሕዝብ አውቶቡሶች ነው። ባቡሮች በሚያቃጥሉት 5.3 ቢሊየን ሊትር ነዳጅ ወደ ከባቢ አየር በየዓመቱ የሚዘልቀው የተቃጠለ አየር ከ1.4 ቶን የማይበልጥ ነው። በአሜሪካን ኤክስፐርቶች ስሌት፣ 88 በመቶ ከሚጠጋው የአውቶሞቢል ተጓዥ ግማሹ በባቡርና በአውቶቢስ ቢጓጓዝ በየዓመቱ ቢያንስ 539 ሚሊየን ቶን የተቃጠለ አየርና የነዳጅ ፍጆታ መቀነስ ይቻላል።

የ ተ ባ በ ሩ ት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ሚያዝያ 9/2007 ያቀረበውን ሪፖርት በዘገበው ታይም መረጃ ዓለም አቀፍ የሥጋ ኢንዱስትሪ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው የተቃጠለ አየር ከአውቶሞቢሎች የሚበልጥ ከከባቢ አየር ብክለት 18 በመቶ ድርሻ ያለው ነው። ሌላው ከብቶች ሳር እያመነዠጉ በሚጥሉት ዕዳሪ የሚወጣው ሚቴንና ናይትረስ ኦክሳይድ የተባሉ ኬሚካሎች በከባቢ አየር ሙቀት መጨመር ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ከካርቦንዳይኦክሳይድ ሚቴን በ23፣ ከናይትረስ ኦክሳይድ በ296 ዕጥፍ የሚበልጥ ነው።

ወደ ሰማይ ለመዝለቅ በሚደረግ እሽቅድምድም

ከተማውን እያደመቁ የሚገኙ ሕንፃዎች አብዛኛውን ወጪ

የሚያወራርዱት ቁልቁል እየወረዱ የሚቆፍሩትን መሬት ኮንክሪት

ለመሙላት በሚያፈሱት የግንባታ ወጪ ነው። በሳይንስ የተረጋገጠው

ደግሞ መሰረታቸው 55 በመቶ በኮንክሪት፣ 45 በመቶ በ‹‹ስላግ››

(ከብረት ማቅለጫ በሚወጣ ዝቃጭ - Slag-waste Product

from Blast Furnace) ቢሞላ፣ መሰረቱን የበለጠ ጠንካራ

ከማድረግ በተጨማሪ 1.2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣውን ወጪ ወደ

3.5 ሚሊየን ዶላር መቀነስ ይቻላል።

Page 21: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003ስ ፖ ር ት22

ትሁት፣ አመለ ሸጋ፣ ሰው አክባሪ፣ ታዛዥ፣ በሳል ብላችሁ ቃላት ሳትሰስቱ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያምን ብትገልፁት በአንዱም ስህተት እንደፈፀማችሁ ሙግት የሚገጥማችሁ ይኖራል ብላችሁ አትስጉ። ባለፈው ወር ወደ ሩጫው ዓለም የገባበትን ድፍን አስር ሻማ የለኮሰው ይህ አትሌት ድርጊቶቹ ሁሉ በምክንያት የሚከወኑ ናቸው። ስሌታዊ እንቅስቃሴው አፍ አውጥቶ መናገር የሚችል እና አንፀባራቂ ነው።

ከገበሬ ቤተሰብዎች የተገኘው ‹‹ገብሬ›› በልጅነቱ በትውልድ ከተማው ሀውዜን [ልዩ ቦታው ፀንቃኔት ይባላል] በሰማይ ሲከንፍ የሚያየውን አይሮፕላን በአየር ላይ እንዴት መንሳፈፍ እንደቻለ ውስጡ ለማወቅ ይጓጓ ስለ ነበር እሱም አንድ ቀን ‹‹አብራሪ›› መሆን ይመኝ ነበር፤ የሚፈልገውን ሳይሆን መሆን ያለበትን ሆነ እንጂ።

የፀንቃኔቱ ልጅ በጣም ጠንቃቃ ነው። ሰው የሚከፋው ስለሚመስለው ጮክ ብሎ ለመጥራት እንኳን ይፈራል። ሰው ላይ ‹‹መድረስ››ን ይጠየፋል። ይህም ከህፃንነቱ ጀምሮ ያዳበረው ነው። ‹‹በአካባቢያችን የእኛ ቤተሰብ በመጥፎ እንዲነሳ አልፈልግም ነበር። በእረኝነት ወጥቼ የያዝኳቸው ከብቶች ሰው ማሳ ውስጥ ገብተው ቤተሰብ ላይ ወቀሳ እንዳይመጣ በእጅጉ እጠነቀቅ ነበር›› በማለት መልካም ባህሪውን ያስታውሳል።

በልጅነቱ የዘራውን ዛሬም ድረስ ያጭዳል፤ ወደ ትውልድ መንደሩ ተጓዘ ማለት የአካባቢው ነዋሪ ደግ ንጉስ የመጣ ያህል በደስታ ተሞልቶ ይቀበለዋል። ቅን እና መልካም መሆኑን ባገኙት ቁጥር ይነግሩታል። በተለይ እሱነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁት በእድሜ የገፉ (አዛውንቶች) ሲያገኙት ከፍቅራቸው የተነሳ እንባቸው ይቀድማቸዋል። እሱም እነሱን መስሎ የሚበሉትን በልቶ፣ የሚጠጡትን ጠጥቶ፣ እንደ ድሮው ስቆ፣ ተጫውቶ ተገቢ ምላሽ ስለሚሰጣቸው ማንነቱን ባለመርሳቱ ይደሰቱበታል፡፡

የቤተሰብዎቹ ቤት ጣሪያው ቆርቆሮ ለበሰ እንጂ ዛሬም ድረስ ያው ነው። አሁን ታላቅ እህቱ ትኖርበታለች። ገጠር ቀመስ፣ ከከተማ የራቀ በመሆኑ መብራትን ጨምሮ የመሰረተ ልማት አቅርቦት አልጎበኘውም። አባቱ በ1996 ዓ.ም. በሞት ተለይተዋል። እናቱ አዲስ አበባ እሱጋ እና መቀሌ እህቶቹ ቤት እየተመላለሱ ይኖራሉ።

ሳንቲም ማትረፍ የወለደው ሯጭነት

ሯጭ የሆነው በእቅድ አይደለም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ከመኖሪያ ቤቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ከ21-23 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ርቀትን ከጓደኞቹ ጋር በሩጫ ያካልል ነበር። ይህ እውቅና ያልተሰጠው የ‹‹ግማሽ ማራቶን›› ሩጫ በሳምንት ሁለት ቀን ይደረጋል፤ ሰኞ ምግብ ይዞ ከትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ከጓደኞቹ ጋር ለአራት ከተከራዩት መኖሪያው ለመድረስ እንዲሁም አርብ ቤተሰብ ለመጠየቅና የአምስት ቀን ቀለቡን ይዞ ለመመለስ።

ይህ ከዘጠነኛ እስከ 11ኛ ክፍል የተማረበት ኢዳጋሐሙስ ትምህርት ቤት ለመድረስ የሚደረግ መንደርደር የሩጫ ሕይወቴ መነሻ ይሆናል ብሎ ሳይሆን የትራንስፖርት ሳንቲም ለማዳን የሚያደርገው ጥረት ነበር። ሯጭ የመሆን ሀሳብስ መች ነበረውና? በ1993 ዓ.ም. የትምህርት ቤታቸው የአትሌቲክስ ቡድን ውስጥ ሳንቲም ማዳን ያጠነከረው ብርቱ እግር እና ትንፋሽ ተመራጭ አደረገው። ከዚያም በዚሁ ዓመት እድገቱ ተፋጥኖ ክልሉን ወክሎ አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ያየው ኢትዮጵያ ባንኮች ክለብ ጠቀለለው። ከዚያም የሩጫን ሳይንስ ‹‹ሀሁ›› መቁጠር ጀመረ። እስከ ዛሬም ድረስ የባንክ አትሌት ነው። ትምህርትና ሩጫን ጎን ለጎን እያስኬደ በ1994 ዓ.ም. በጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት የመጨረሻው የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ነበር። 2.8 አመጣና ነጥቡ ወደ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም የሚልከው ቢሆንም በ1993 ዓ.ም. ሚያዚያ ወር የጀመረው ሩጫ ከአስተማሪነት በላይ ልቡን ስላሸፈተው በአየር የመብረሩን ሀሳብ ትቶ የመም፣ የአገር አቋራጭና የመንገድ በራሪ ሆነ።

ረዥም ጊዜውን በእርሻ ያሳለፈው ገብረ እግዚአብሔር በአትሌቲክስ የህይወት መስመሩ ቢያብብም ያሰበውን ያህል እንዳልተራመደ ያምናል። ‹‹በስፖርቱ ህይወቴ ተለውጧል። ቤተሰብ አስተዳድርበታለሁ። ከብዙ ሰዎች ተገናኝቻለሁ፣ ውያለሁ። ህዝቡ የሚጠብቀኝን ያህል ለአገሬ የሚገባኝን ያህል አልሰራሁም። በዓለም ዋንጫ እና በኦሎምፒክ ለሜዳሊያዎች መምጣት ምክንያት ከመሆን ባለፈ ሜዳሊያ ማጥለቅ ፈልጋለሁ›› የሚለው

አትሌቱ ውስጡ የ‹‹ገና ነኝ›› ቁጭት ቢፍለቀለቅም በተወዳደረባቸው የአትሌቲክስ መድረኮች የሚያስመዘግበውን ውጤት በፀጋ ይቀበለዋል። ‹‹ለአገሬ እና ለህዝቤ በቂ ላይሆን ይችላል እንጂ እኔ ሁሌም የተወዳደርኩበትን ሩጫ ስጨርስ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ደስተኛ ነኝ›› ይላል።

እ.ኤ.አ. በ2004 በቤልጂየም በተደረገ የዓለም የአገር አቋራጭ ውድደር በሁለት ቀን ልዩነት በአራት እና በ12 ኪሎ ሜትር ተወዳድሮ በሁለቱም ቀነኒሳ በቀለን ተከትሎ በመግባት ሁለተኛ መውጣቱ ገብረ እግዚአብሔር ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን የጠቆመ ነበር። በዚሁ ዓመት በተካሄደው የአቴንስ ኦሎምፒክ የ5,000 ሜትር ቡድን አባል ሆኖ መም ላይ ተገኘ፤ ከቀነኒሳ በቀለ እና ደጀኔ ብርሃኑ ጋር። በኬኒያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ በ0.25 ሰከንድ ተቀድሞ አራተኛ በመውጣት ለጥቂት ሜዳሊያ ማጥለቅ ሳይችል ቀረ። በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ2007 ኦሳካ ላይ በ10,000 ሜትር ስድስተኛ ሆኖ አጠናቋል።

በ2009 በዓለም የአገር አቋራጭ ውድድር አኩሪ ገድል ለራሱ እና ለአገሩ ፅፏል፤ ሪቫኑን በጥሶ የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ። ይህ የ2009-10 የውድድር ዓመት እስኪጠናቀቅ ድረስ አትሌቱ በኦይራስ፣ አታፑርካ፣ ሶሪያና አልኮቤንዳስ በድል የደመቀበት ነው።

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በጉልበት ህመም አቋርጦ በወጣበት የዘንድሮው የኒው ዮርክ ማራቶን ላይ 2፡08.14 በሆነ ሰዓት በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ የሮጠበትን የማራቶን መድረክ በድል ጀመረ። ገብረ ማርያም ኃይሌን በውድደሩ ላይ እንዲቆይ ቢያበረታታውም ‹‹እኔ አልቻልኩም፣ አንተ ቀጥል›› ብሎት ነበር። በሁኔታዎች የተበሳጨው ኃይሌ ስሜታዊ ሆኖ ከውድድር መሰናበቱን መግለፁ መነጋገሪያ መሆን የእሱን ድል ትኩረት ሰርቆት ነበር።

ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ለማራቶን ሪከርድ ባለቤቱ- ኃይሌ ያለውን ክብር እና ፍቅር ሲገልፅ ቃላቶች የሚገድቡት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም በኒው ዩርክ ከሩጫው ፍፃሜ በኋላ ይሄንኑ በተግባር አሳይቷል። ‹‹ኃይሌ መልካም ሰው ነው። ንጉስ ነው። ከእሱ በርካታ ነገሮችን ተምሬያለሁ›› ሲል አወድሶታል።

የአሜሪካንን የሩጫ ግብዣ ጥሪ ‹‹ገብሬ›› የሚያልፍ አይመስልም ከድሉ በኋላም በተከታታይ ተመላልሷል። በመጋቢት ወር በኒው ዮርክ የግማሽ ማራቶን ውድደር አድርጎ በመጨረሻው መስመር ላይ በሁለት ማይክሮ ሰከንድ ተቀድሞ 1፡00.25 በመግባት ለጥቂት በ28 ዓመቱ በትውልድ ሶማሊያዊ፣ በዜግነት እንግሊዛዊ በሆነው ሞ ፋራህ ተቀድሞ ሁለተኛ ወጥቷል። ባለፈው ሚያዚያ ባደረገው የቦስተን ማራቶን ሦስተኛ የወጣ ሲሆን የገባበት 2፡4.53 የግል ምርጥ ሰዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል። ከኃይሌ ገ/ሥላሴ ቀጥሎም በርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን ኢትዮጵያዊ ሯጭ አድርጎታል፤ የትራንስፖርት ሳንቲም ለማዳን የጀመረው ሩጫ፡፡

በገብረ እግዚአብሔር ጥረት ዋንጂሩ ሲታሰብ

ስምንት የዓለም የአገር አቋራጭ ሜዳሊያ ካሰባሰባችሁ የትዳር አጋሩ ወርቅነሽ ኪዳኔ ናትናዔል እና ሙሴ የተባሉ የአምስት እና የሦስት ወር ከዘጠኝ ወር ሁለት ወንድ ልጆች ያፈራው ገብረ እግዚአብሐር በ‹‹ጎሪጥ›› የሚተያዩ አትሌቶችን የማቀራረብ፣ በሩጫ እና በቢዝነስ ዓለም ያላቸውን ተሞክሮ እንዲለዋወጡ የማድረግ፣ ብቁ የአትሌቶች ማኅበር ተመስርቶ የማየት ፅኑ ዓላማ አለው፤ ጥረቶችንም ያደርጋል። ‹‹ትልቅ ትምህርት ቤታችን›› ከሚለው ኃይሌ እና ከሌሎች አትሌቶች ተተኪ አትሌቶች ትምህርት መቅሰም እንደሚችሉ ያምናል። ‹‹ኃይሌ በሁሉ ረገድ ውጤታማ ሰው ነው። በሙያው፣ በሚመራቸው የቢዝነስ ተቋማት፣ በተግባቦት (Communication)፣ ከህዝቡ፣ ከአገር ውስጥና ከውጪ መገናኛ ብዙሐን ጋር ባለው ግንኙነት ስኬታማ ነው። እጃችን ላይ ስላለ ቀላል እናደርገዋለን እንጂ ዓለም ላይ አሻራው የሚፈልግ ሰው ነው፡፡›› የሚለው ገብረ እግዚአብሔር ‹‹አልተጠቀምንበትም›› የሚለውን የኃይሌን ሙሉ ስብዕና ለመካፈል የሚቻለው የውይይት መድረኮች እያዘጋጁ በመማማር መሆኑን ያምናል። ለዚህም ይመስላል ባለፈው ጥር ወር በእሱ ሀሳብ አመንጪነት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ አትሌቶች ልምዳቸውን ያጋሩበት መድረክ በራስ ሆቴል ተዘጋጅቶ ነበር። ‹‹የውይይት መድረኩን ለማዘጋጀት ሀሳቡን የነገርኳቸው ‘ፍፁም ይከብድሃል፤ አይሆንም’ አሉኝ ። ምክንያታቸው ደግሞ አትሌቶች በግልፅነት ተሞክሯቸውን እና ልምዳቸውን ለማካፈል

ግልፅ አይሆኑም የሚል ነበር። እንዳየኸው ግን በጥሩ ሁኔታ ተጠናቀቀ›› በማለት አሉታዊ ሀሳቦች ሳያቆሙት ውይይቱ ማካሄዱን ገልጿል ።

በመድረኩ ላይ በገብረ እግዚብሔር እና በመሰረት አወያይነት ኃይሌ፣ ደራርቱ ቀነኒሳ ልምዳቸውን በግርድፉ አካፍለዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ወክለው የተሳተፉት አቶ ዱቤ ጂሎ የአትሌቶችን ቅሬታ አዳምጠዋል። አንጋፋና ወጣት አሰልጣኞች ሀሳብ ተለዋውጠዋል፤ ተወቃቅሰዋል። ኢትዮጵያዊ ማናጀሮችም በሚነሱባቸው ቅሬታ ዙሪያ መልስ ሰጥተዋል። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት እንደ መጀመሪያ ውይይት የኒው ዩርክ ማራቶን አሸናፊው ሀሳብ ፍሬያማ እንደነበር አመላካች ነው። ከመድረኩም ይህ ምስክርነት ተሰጥቶ ነበር። የመድረኩን የአዳራሽ ኪራይ (27 ሺህ ብር ገደማ) ከኪሱ አውጥቶ ለመክፈል የተሰናዳው እሱ ነበር፤ ፌዴሬሽኑ ‹‹በጭራሽ›› ብሎ ሂሳቡን ‹‹ዘጋው›› እንጂ።

በጎ ተግባራቱ ይቀጥላል… ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በክልል በሚያካሂዳቸው ውድድሮች ላይ እየተገኘ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቢሮ ስራ አስኪያጅ ወ/ት ዳግማዊት አማረ የአትሌቱን ተባባሪነት ‹‹የእኔ ብለህ እንድትተማመንበት የሚያደርግ›› ሲሉ ይገልፁታል። ‹‹ቀና ሰው ነው። በማንኛውም ጊዜ እንደሚያግዝህ እርግጠኛ ትሆንበታለህ። ሰው ወዳድ ነው። የፈለገ ስራ ቢበዛበት ከአፉ ‘እምቢ’ አይወጣውም›› በማለት መልካምነቱን ያስረዳሉ።

ኬኒያዊው የኦሎምፒክ የማራቶን አሸናፊ ሳሙዔል ዋንጂሩ ከሁለት ሳምንት በፊት በመኖሪያ ቤቱ ህንፃ ላይ ወድቆ መሞቱ ሲሰማ የአትሌቲክሱ ዓለም አዝኗል። ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡30 በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬኒያ ኤምባሲ አምባሳደሯ ሞኒካ ጁማ [ዶክተር] እና ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት ለአትሌቱ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

አትሌቶቹ የብሔሪዊ ቡድን ቱታና ጥቁር ሻሽ ለብሰው የተገኙበትን፣ አምሳደሯ ዋንጂሩ በትራክ እና በጎዳና ሩጫ ኬኒያን በጥሩ ሁኔታ ማስተዋወቋን የተናገሩበትን፣ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ዋንጂሩን ያጣው ዓለም መሆኑን በሀዘን የገለፀበትን ይህንን ዝግጅት ሀሳብ ጠንስሶ ያስተባበረው አትሌቶችን ወክሎ በዋንጂሩ መሞት የኢትዮጵያ አትሌቶች ከልብ ማዘናቸውን በመድረኩ የገለፀው ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ነው። በዚሁ ወቅት ‹‹ገብረ እግዚአብሔር ከአትሌትም በላይ ነው›› ሲል የገለፀው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የእለቱን የመታሰቢያ ዝግጅት ጨምሮ የሚያደርጋቸውን በጎ ምግባሮች እውቅና ሰጥቶ ምስጋና ቸሮታል።

‹‹ዋንጂሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኬኒያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም የሚፈልገው ሰው ነበር›› የሚለው ገብረ እግዚአብሔር ህይወቱ ማለፉን የሰማው ልምምድ ላይ ከጓደኞቹ ጋር ነበር።ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት አትሌቶችን ወክለው በቀብሩ ስነ-ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ቢያስቡም የቀብሩ ቀን በመተላለፉ ግን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለኬኒያ መንግስት፣ ህዝብና አትሌቶች ሀዘናቸውን ለመግለፅ የሚያስችል መጠነኛ ዝግጅት በኬኒያ ኤምባሲ ለማሰናዳት እሱ በኤምባሲው ተገኝቶ ለአምባሳደሯ ፀሐፊ በማስታወቅ በበጎ ስለተቀበሉት ባለፈው እሁድ ተከናውኗል።

በዝግጅቱ ላይ የዋንጂሩ ስድስት ፎቶዎች በፍሬም ተሰናድተው ተቀምጠው የነበረ ሲሆን ሁለቱ በዋንጂሩ ጓደኛና የቅርብ ተፎካካሪ ፀጋዬ ከበደ ሌሎቹ ደግሞ በደራርቱ ቱሉ፣ ገዛኸኝ

አበራ፣ ገብረ እግዚአብሔር ገ ብ ረ ማርያምና በአምባሳደር ሞኒካ ጁማ ተከፍቷል። ፎቶዎቹ መጠናቸውን አሳድጎ ለእይታ እንዲበቁ ያደረጋቸው ስብዕናው እየገዘፈ የመጣው ‹‹ገብሬ›› ነው።

ሽማግሌው ገብረ እግዚአብሔር

ሽምግልና ሌላው የገብረ እግዚአብሔር ያልተነገረ መለያ ነው። አትሌቶች ከአትሌቶች፣ ከፌዴሬሽን፣ ማናጀሮች፣ ከክለቦች ቅሬታ ሲገቡ እና ሲኳረፉ አሸማጋይ ሆኖ ይከሰታል። አትሌቶች ያለባቸውን የግል

እና ቤተሰባዊ ችግሮች ሲፈጥሩ ከገብረ እግዚአብሔር ቀድሞ የሚገኝ የለም።

ሟቹ አትሌት ደጀኔ ብርሃኑ በትዳር ውስጥ የነበረውን አለመስማማት ለመፍታት ገብረ እግኢብሔር ብዙ ይጥር ነበር። ይፋ እንዲሆኑ ያልፈለጋቸውን ሽጉጥ እስከ ማማዘዝ የደረሱ ችግሮች ሸምግሏል። በርካታ የውስጥ ለውስጥ ችግሮችን የማያጣው የአትሌቲክስ ሰፈር ችግሮች እንዲፈቱ ጋኑ ስር ጠጠር አኑሯል። የእጅ ስልኩ ቅሬታቸውን በሚያካፍሉት ወዳጆቹ ይጨናነቃል። ‹‹አሁን አሁንማ የልምምድ ሰዓቴን እየተሻማብኝ ነው። ሆኖም ደስተኛ ነኝ›› ይላል አትሌቱ።

ገብረ እግዚአብሔር ለአትሌቶች መልካም የሚያስብ ሰው መሆኑን እና ችግሮች ሲፈጠሩ ለመፍታት ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚገልፀው ባለፈው ሳምንት በኦታዋ የተደረገውን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ያሸነፈው ድሪባ መርጋ ‹‹አመለ ሸጋ በመሆኑ እሱ ሲያሸማግል እምቢ የሚለው ሰው የለም›› ይላል።

‹‹ችግሮች ካሉ ነገርን ማሳደር አልወድም። ሁሉም በአግባቡ ተነጋግረው መፍትሄ ሲያበጁ ማየት ያስደስተኛል። ለህዝብ፣ ለአትሌቱና ለፌደሬሽኑ ይጠቅማል እስካልኩ ድረስ ወደፊትም እገፋበታለሁ›› የሚለው ገብረ እግዚአብሔር ‹‹በጎ ነገር ስከውን ከማንም በላይ እርካታ የማገኘው እኔ ነኝ። የአዕምሮ ነፃነትም ይሰማኛል›› በማለት በስራው ቀዳሚ ተደሳች ራሱ እንደሆነ ይጠቁማል። የሚከውናቸውን በጎ ምግባሮች ‹‹በዚህ ጊዜ አደርገዋለሁ›› ብሎ እቅድ የነደፈላቸው ሳይሆን ወቅት የሚፈጥራቸው ናቸው፡፡

የኃይሌን ዳና መከተል?ገብረ እግዚአብሔር እና ኃይሌ የሚከባበሩና

እርስ በርስ የሚመሰጋገኑ ወዳጆች ናቸው። ቁመተ መለሎው አትሌት እጅግ የሚያከብረውን የኃይሌ ፈለግ እየተከተለ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። እሱ ግን ከኃይሌ ጋር ሊመሳሰል የሚገባው ሰው እንዳልሆነ ይናገራል፡- ‹‹እኔ ከኃይልሻ ጋር መመሳሰል አልችልም። ብመስል እኔ ተጠቃሚ ነኝ›› በማለት። የእሱን ፈለግ እየተከተለ ስለመሆኑ ሰዎች የሚያስቡት ኃይሌ ላይ የሚያዩትን ብሩህ አስተሳሰብ በእሱም ላይ ስለሚመለከቱ ሊሆን እንደሚችል ያስባል። የንግግሩ ብስለትን ከኃይሌ የቀዳ አድርገው የሚነግሩትን ‹‹በእርግጠኝነት ኃይሌን ባልመስለውም አርዓያ የማደርገው ሰው ስለሆነ እንደ እርሱ አንደበተ ርትዑ ለመሆን ስለምጥር ነው›› ሲል ይመልስላቸዋል፤ ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ አምናለሁ የሚለው ገብረ እግዚአብሔር፡፡

አትሌቶች የአገራችንን መገናኛ ብዙሐን ማመን ላይ ብዙ እንደሚቀራቸው ይገልፃል። አትሌቶቹጋ ደርሰው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ማሳወቅ መገናኛ ብዙሐን ድርሻቸው መሆኑን በማወቅ ሊገፉበት እንደሚገባ ይጠቁማል። ‹‹እኔ እና ጓደኞቼ መገናኛ ብዙሐንን መጠቀም አልቻልንበትም። ምን ያህል አቅም እንዳለው ማወቅ ይገባናል›› ሲል አትሌቶችን ይወቅሳል። የሪፖርተር ጋዜጣ የስፖርት አምድ አዘጋጅ ደረጀ ጠገናው አትሌቱ ክልሉን ወክሎ ለውድድር አዲስ አበባ ከረገጠ ጀምሮ ያውቀዋል። ለመጀመሪያ ጊዜም መቅረፀ ድምፅ ሰድሮ ድምፁን የተቀበለው (ቃለ ምልልስ ያደረገው) እሱ ነው። እንደ ደረጀ ገለፃ ከሆነ የአመለ ሸጋው አትሌት ስብዕና ከዕለት ወደ ዕለት እየጎለበተ ከፍ ወዳለ ደረጃ እየሄደ ነው። ‹‹ሳውቀው ጀምሮ ትሁት ነው። በአትሌቶች ላይ የሚታየውን መገናኛ ብዙሐንን እንዴትና መቼ መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። በፈለግከው ሰዓት መረጃ ለመስጠት ተባባሪ ነው። ከሩጫ ውጪ ባለው ህይወቱ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ስታይ የተለየ ስብዕና የተላበሰ ሰው መሆኑን ትረዳለህ›› በማለት ይገልፀዋል።

መልካም አሳቢው ገብረ እግዚአብሔር በቀጣይ በዓለም ዋንጫ ላይ በ10‚000 ሺህ ወይም በማራቶን ኢትዮጵያን ወክሎ ይሮጣል፤ የብሄራዊ ቡድን ምርጫ ገና ቢሆንም ቅሉ። በአትሌቲክሱም በበጎ ስራውም አንፀባራቂ ሆኖ መቀጠልንም ያልማል።

በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ ያሉየስፖርት ስፍራዎች ተጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ግንባታቸው ዘንድሮ ተጀምሮ በቀጣዩ ዓመት ለአገልግሎት የሚበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን፣ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመም ተከላ ስራንና በግንባታ ላይ ያለውን የኮሚሽኑን ህንፃ በትላንትናው እለት አስጎበኘ። ስራዎቹ አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ የተጀመሩት የልማት ስራዎች በአመራር ደረጃ ባሉ አባላት ጉብኝት ተካሂዶባቸው አበረታች ክዋኔ መኖሩ እንደተመሰከረ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ በአገራችን የመጀመሪያ የሆነ ባለ ሁለት ወለል (G+2) ህንፃ ጂምናዚየም መድኃኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የራስ ኃይሉ መናፈሻ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ እየተገነባ ሲሆን በቅርቡ የውሃ ዋና ገንዳ ዲዛይን ስራ ተጠናቆ ተግባራዊ ስራ በቦታው ላይ እንደሚጀመርና ይህም የተዳከመውን የውሃ ስፖርት ሊያበረታታ እንደሚችል ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ አምስት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው በግንባታ ላይ ያለው ባለ 12 ወለል ህንፃ ግንባታም የጉብኝቱ አካል ነበር። ሌላው የተጎበኘው በቅርቡ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተጀመረው የመም (track) ስራም ከሁለት ወር በኋላ ስራው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ መገመቱ ተገልጿል። ስራዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የሆኑት አቶ ከፍያለው አዘዘ እና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጎብኝተዋል።

የጎመራው የገብረ እግዚአብሔር ስብዕና‹‹ገብረ እግዚአብሔር ከአትሌትም በላይ ነው››• ኃይሌ ገ/ሥላሴ [ሻለቃ]

ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም [አትሌት] በአትሌቲክስ እና በግል ህይወቱ አርዓያ ሊያደርገው የሚያስችለውን መልካም ነገሮች ይከውናል። ከአትሌቱ ጋር ቆይታ ያደረገው የአውራምባ ታይምስ የስፖርት ገፅ

አዘጋጅ ተከታዩ ጥንቅር ያልተነገረውን የአትሌቱን መልካም ስብዕና ይዘረዝራል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ህንፃ ላይ ወድቆ ህይወቱ ላለፈው ኬኒያዊው የኦሎምፒክ የማራቶን አሸናፊ ሳሙዔል ዋንጂሩ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬኒያ ኤምባሲ አምባሳደሯ ሞኒካ ጁማ [ዶክተር] እና ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት ለአትሌቱ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል። የፕሮግራሙ ጠንሳሽና አስተባባሪ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ነው።

በአቤል ዓለማየሁ[email protected]

Page 22: Awramba Times Issue 170

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 170 ቅዳሜ ግንቦት 27 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃየሚያወርድ

ምቾት እናጥራት ያለው

ከበቂ መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ የተመሳሰሉትን

ይለዩ

ስለዚህ እየሰራሁ ነውና ሀብታም ነኝ። እንዳልኩህ አዲስ አልበም ሰርቼ ማስተሬን ይዣለሁ። ከዚህ ሌላ ደግሞ የራሴን ናይት ክለብ ለማቋቋም አስቤ የሙዚቃ መሣሪያ ገዛዝቼ አነስተኛ ባንድ መስርቼአለሁ። እና ከራሴ ባንድ ጋር ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ሳንሱሲ ሆቴል ከስማቸው ካሳ ጋር ‹‹ሀቢቢ›› የሚል ናይት ክለብ አቋቁሜ እየሰራሁ ነው። ስለዚህ እየሰራሁ ነውና ሀብታም ነኝ ብዬ አምናለሁ።

መልካም። ትዳር ይዘሻል?አልያዝኩም።

ጓደኛስ አለሽ?የለኝም።

የብቸኝነት ህይወት እንዴት ነው ታዲያ?ለእኔ ጓደኛዬ ሥራዬ ነው። ሌላው ሌላው ነገር ደግሞ ቀስ እያለ ይመጣል።

ወደ ሀገራዊ ጉዳይ ልውሰድሽ እስቲ። በአሁኑ ወቅት የሀገራችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ማን ናቸው?(አሰብ አድርጋ) አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

(ሳቅ በሳቅ) እሳቸውማ የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት ናቸው። በቃ (ሣቅ) አላውቅም። (ለማንኛውም ዝናሽ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።)

ከሀገሪቷ ባለሥልጣናቶች በስም እነማንን ታውቂያለሽ?አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው።

ሌላስ?ስማቸው ጠፋኝ። አንድ ጊዜ

ኮፒ ራይት ስብሰባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ተወክለው መጥተው በእኛ ሙያ ላይ ጥሩ ተስፋ የሰጡን? በናትህ ስማቸው ጠፋኝ።

እሳቸው አቶ ጁነዲን ሳዶ ናቸው?አ…ዎ!!

አሁን ስልጣናቸው ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?በናትህ ይኼን ጥያቄ እለፈኝ።

ማለፍ ብቻ ሳይሆን የአንዳፍታ

ቆይታችን ልናጠናቅቅ ነው። በመጨረሻ የምትይው ካለ ዕድል ልስጥሽ? በናትህ ይኼን የኮፒ ራይት ሙብት ነገር አጥብቃችሁ ያዙልን በልልኝ። ኪነ-ጥበብ እኮ ሁሉም ነገር ማለት ነው። ጥበቃ ያስፈልገዋል። በቂ የሆነ ጥበቃ ስለሌለ ለፍተን፣ ደክመን፣ ሰርተን አጠናቀን፣ ሥራችንን ይዘነው ቁጭ ብለናል። ተጠቃሚ መሆን አልቻልንም። ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የኮፒ ራይትን ጉዳይ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥበት እጠይቃለሁ።

የሚመርጠኝን ለማፍራት እኮ ነው የምሯሯጠው።ጥያቄ፡- አምባገነን ነው፣ ዴሞክራት አይደለም ይባላል።ሰይጣን፡- በምን መልኩ?ጥያቄ፡- ሔዋንን በለሱን እንድትበላ ስትጠይቃት መጀመርያ እምቢ ብላ ነበር። በጭቅጭቅ ነው ያሳመንካት። ይህም ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቷን እንደረገጥከው ነው የሚያሳየው እኮ?ሰይጣን፡- ስለጨቀጨኳት አይደለም የበላችው። የመብላት ፍላጎቷ በጣም ስለጨመረ ነው። እንጂ ያማ ባይሆን የፈጣሪዋን ተዕዛዝ ትታ የኔን ባላከበረች ነበር።ጥያቄ፡- ስለኢትዮጵያ አማኞች ያለህ አመለካከት ምንድነው?ሰይጣን፡- እንደማንኛውም አገር ሰዎች ነው የማያቸው። በርግጥ ከሌላው ዓለም በተለየ ትንሽ ነገር የማክረር አዝማሚያ ይታይባቸዋል።ጥያቄ፡- አክራሪነታቸው መንገድህን (ስራህን) ፈታኝ ያደርገው ይሆን?ሰይጣን፡- ነገሮችን አካብዶ ማየት አልወድም። እነሱ አክራሪ ቢሆኑም እኔም ስልቴን የበለጠ ለማክረር ዝግጁ ነኝ።ጥያቄ፡- ከመላዕክት እንደ አንዱ በነበርክበት ሰዓት የነበረህን ክብር አሁን ስታስበው፣ ምነው አርፌ በተቀመጥኩ ብለህ ታውቃለህ?ሰይጣን፡- ያለፈው ሕይቴም ሆነ አሁን ያለሁበት ሕይወቴ የራሳቸው የሆነ ውበት አላቸው። በዛ ላይ አሁን ያለሁበት ዓለም በራሴ ውሳኔ ያካሄድኩት አብዮት ያመጣብኝ ስለሆነ ብዙም የሚቆጨኝ ነገር የለም።ጥያቄ፡- አሁን ከኢየሱስ ጋር ታረቅ ብትባል ትታረቃለህ?ሰይጣን፡- ምናልባት እኔ ፈልጌ ልታረቅ ብል እንኳን ኢየሱስ የሚስማማ አይመስለኝም። ጥያቄ፡- ለምን?ሰይጣን፡- ከፊሉ የሰው ዘር በሰይጣን ወይም በእኔ ዕጅ እንደሚወድቅ ኢየሱስ አስተምሯል። ከኔ ጋር ዕርቅ ካደረገ ደግሞ በደለኛው የሚባሉትን ነፍሳት ማን ሊረከባቸው ነው? ወይስ ሰይጣን ታርቆ ወደ ቀድሞ ክብሩ ተመልሷልና ሐጢያተኛ ነፍሳትን የሚቀበል አካል ስለሌለ ሁሉም ወደ ገነት ይግባ ይባላል? እንደዛ ቢባል እንኳን ኢየሱስ አስቀድሞ የተናገረው ቃል ሊሻር ነው ማለት ነው። ስለዚህ ቃሉ እንዳይሻር ሲል ብቻ ከኔ ጋር እርቅ እንደማያደርግ እርግጠኛ ነኝ። ጥያቄ፡- በተለያዩ ሀገራት (በተለይ በአፍሪካ) ለተካሄዱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች ተጠያቂ ነኝ ብለህ ታስባለህ?ሰይጣን፡- (ረዥም ሣቅ) በምን ምክንያት?ጥያቄ፡- ለመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ፈር ቀዳጅ በመሆንህ …ሰይጣን፡- ይኸውልህ የኔ ወንድም፤ ከአዳም ጀምሮ እስከ አሁን ያሉ ትውልዶችን ብትመረምር፣ በእያንዳንዱ ትውልድ መሐል ብዙ ቀናተኞችን ታገኛለህ። ቀናተኞች ሚስቴ (ባሌ ለምን ከሌላ ሰው ጋር ታየ) ታየች ብለው ብቻ የሚቀኑ አይደሉም። ሥልጣንም ያስቀናቸዋል። ቃኤል ለምን በአቤል ተበለጥኩ ብሎ ቀና፤ ገደለው። ያዕቆብ ራሱ በወንድሙ ብኩርና ላይ ስለሚቀና ነው የኤሳውን ብኩርና (ሥልጣን ወይም የበላይነት) በምስር ወጥ የገዛው። ባይቀና ኖሮ ወንድሜ ሆይ ርቦሃልና እንካ ብላ ብሎ በቤተሰባዊ ፍቅር ወጡን በሰጠው ነበር።ወደመካከለኛው ዘመን ስትመጣ ደግሞ ቤተ-አይሁድ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በኢየሱስ ሥልጣን ላይ ይቀና ነበር። ይኼን ይኼን ስትመረምር የሰው ልጅ ቀናተኛ መሆኑን ታምናለህ። ስትከፋፍለው ደግሞ ለሥልጣን፣ ለሚስት፣ ለሀገር፣ ለልጅ የሚቀና አለ ብለህ ትደመድመዋለህ።ስለዚህ በተለያዩ ሀገራት መፈንቅለ መንግስታት የሚከሰቱት የሰይጣንን ሙከራ ልምድ በማድረግ ሳይሆን፣ ከሰው ልጅ ቅናት የተነሳ ነው። በርግጥ ለሀገርና ለሥልጣን መቅናት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የሀገርህ መውደቅና አለማደግ አንገብግቦህ ምርጫ በማጣት መፈንቅለ-መንግሥት ብታካሂድ አግባብ ነው ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን እከሌ ወይም ከኔ ጋር የተማረው ልጅ ሥልጣን ይዞ እንዴት እኔ ሳልይዝ እቀራለሁ ብለህ ስለሥልጣን ቀንተህ ግርግር የምትፈጥር ከሆነ አደጋ ነው። ጥያቄ፡- አንድ ሰው የሥልጣን ቅናት የሚያድርበት ከልጅነቱ ጀምሮ ነው ወይስ ሀገሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ ምቹ ስትሆንለት ነው?ሰይጣን፡- የቦኖ ውሃ ለመቅዳት ከተሰበሰቡ ሰዎች መሐል ድንገት የበላይነት የሚሰማውና እኔ በምነግራችሁ መሰረት ቅዱ የሚል የመንደር ውስጥ ጎረምሳ ባለሥልጣን ሊነሳ ይችላል።ምናልባት ይኼን መሰሉን የመንደር ውስጥ የበላይነት ልትንቀው ትችላለህ። ነገር ግን ያ የመንደሪቱ ጎረምሳ ነገ ከነገ ወዲያ በአንድ ሀገር ውስጥ ትልቅ የሚባለውን ሥልጣን ለመያዝ ብጥብጥ ሲያስነሳ ልታገኘው ትችላለህ። ትላንት አንገቱን ደፍቶ በሱ ትዕዛዝ ውሃ የቀዳው የዛች መንደር ነዋሪ ለጎረምሳው የልብ ልብ ሰጥቶታል።መንደርተኛው ጎረምሳውን ‹‹ለምንድነው ባንተ ትዕዛዝ የምንቀዳው?›› ብሎ አፋጦት ቢሆን ኖሮ የሥልጣን ቅናት አድሮበት ብጥብጥ ባላስነሳ ነበር። አንተን የሚያባልግህም ሆነ የሚያስተምርህ አብረኸው የምትኖረው ቤተሰብና ማኅበረሰብ ነው። አንተ ተቀጥተህ ያደግህ ከሆነ ሀገር የፈለገውን ያህል ለሕገ-ወጥ ሥልጣን ምቹ ብትሆን እንኳን፣ ያ ዓይነቱ ሥልጣን አያጓጓህም። ሕገ-ወጥነትን ለማጥፋት ትሯሯጥ ይሆናል እንጂ፣ መቶ ሺህ ሰው ጨፍጭፈህ 10 ሺህ ሰው ለማስተዳዳር የሚያነሳሳ የሥልጣን ቅናት አያድርብህም።ጥያቄ፡- ብዙ ሰዎች የሚፈሩህ ለምን ይመስልሀል?ሰይጣን፡- ከግንዛቤ እጥረት ይመስለኛል። አስተዋይና አመዛዛኝ ሰው ክፉውንም ደጉንም እያስታረቀ መጓዝ አለበት። በበኩሌ ማንም እንዲፈራኝ አልፈልግም። ያለፈው ብርሃናማው ሕይወቴ ያስተማረኝ ብዙ ነገር ስላለ መፈራት አልፈልግም።ጥያቄ፡- ጨርሻለሁ።ሰይጣን፡- ከሰፊው ሕዝብ ጋር ስላገናኘኸኝ አመሰግናለሁ።

(አጽንኦት፡- በዓለም ላይ በግንባር አግኝቼ ጥያቄ ላቀርብላቸው ከምፈልጋቸው ሶስት የታሪክ አካላት አንዱ ሰይጣን ነው። ሆኖም ይህ ቃለ-ምልልስ ምናባዊ መሆኑ ይታወቅ።)

ከሰይጣን ጋር...

‹‹ሙያዬን አከብረዋለሁ ...

ከአዲስ አበባ ከሄዱ በኋላ ምን እየሰሩ ነው?

አዲስ አበባን ከለቀቅኩ በኋላ አሁን በኢንግላንድ እረፍት ላይ ነኝ። ጊዜዬን ለቤተሰቤ ሰጥቻለሁ። እዚህ አሁን የውድድር ዓመቱ ተጠናቋል። በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት እና ወራት ምን አይነት አማራጮችን እንደማገኝ ተረጋግቼ እየተመለከትኩ ነው።

በኢትዮጵያ ቆይታዎ በስራዎ ላይ እንቅፋት የሆነብዎ ሰው አለ?

እግር ኳሱን ለማሳደግ እኩል ተነሳሽነት ያላቸውን ሰዎች በአንድነት [መገናኛ ብዙሐን፣ ፌዴሬሽኑንና አሰልጣኞች] ካለማግኘቴ በስተቀር በስራዬ ላይ እንቅፋት አላጋጠመኝም። በቆይታዬ ለእግር ኳሱ ዕድገት ሁልጊዜ ከልብ በመነጨ ሁኔታ ጠንክሬ መስራቴን ማንም የሚክደው አይደለም።

ኢትዮጵያ አዲስ ቤልጄማዊ አሰልጣኝ ቀጥራለች። አሰልጣኙ

የመጀመሪያ የውጤት ጨዋታቸውን የእርስዎን ቡድን በአቡጃ 4-0 ካሸነፈው ናይጄሪያ ጋር ነገ ያደርጋሉ። ስለ ሰውዬው የሚያውቁት ነገር አለ? በጥቅሉ የሚሰጡት አስተያየትስ አለዎት? አዲስ አሰልጣኝ እንዳገኛችሁ ተመልክቻለሁ። አሰልጣኙን አላውቀውም ነገር ግን ለእሱም ሆነ ለኢትዮጵያ መልካሙን እመኛለሁ። ከባድ ስራ ነው። በመጀመሪያ ጨዋታ ቢሸነፍም

(ባለፈው ሳምንት በወዳጅነት ጨዋታ በሱዳን 2-1 የተሸነፍንበትን ነው) የመጀመሪያው ጨዋታ መሆኑን መርሳት የለብንም። አሰልጣኞች ትዕግስተኛ መሆን

‹‹ለአሰልጣኙም ሆነ ለኢትዮጵያ መልካሙን እመኛለሁ››የኢፊ ኦኑራ 5 ምላሾች - ከኢንግላንድ

በሳምንቱ አጋማሽ አቡጃ ላይ አርጀንቲናን ጠርታ 4-1 ያሸነፈችው ናይጄሪያ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ አራት ግብ አግብታ ነገ የምትገጥማትን ኢትዮጵያ ስታሸንፍ የወቅቱ የቡድኑ አሰልጣኝ የዘር ሀረጋቸው ከዚያው የሚመዘዘው ኢፊ ኦኑራ ነበሩ። አቤል ዓለማየሁ ከአሰልጣኙ ጋር ባደረገው አጭር የኮምፕዩተር

ኤሌክትሮኒካል የደብዳቤ ልውውጥ በድንገተኛ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ለምን እንደተለዩና ስለ ነገው የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ጨዋታ ጠይቋቸዋል። አውራምባ ታይምስ ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን (ዋልያዎቹ) መልካም ውጤት እየተመኘች አምስቱን ምላሾች እንድታነቡ ትጋብዛለች።

በአውሮፓ ረዥም የውድድር ዓመት ስላደረጉ ተዳክመዋል። የሜዳም ተጠቃሚነታችሁ አለ። ከልቤ እንደማስበው እነዚህ ነገሮች ተጠቃሚ እንደሚያደርጓችሁ ነው። አሰልጣኙ ከሱዳን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ በማድረጉ ሰለ ተጨዋቾቹ የበለጠ ማወቅ ችሏል።

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በድንገት የተለያዩበት

ያልተገለፀ ምስጢር አለ ይባላል። አሁን ይፋ ሊያደርጉት ይችላሉ?የእኔ በድንገት ስራውን መተው ምንም ምስጢር የለውም። የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ነበር። ይህ የእግር ኳሱ አንዱ አካል ነው። በአንዳንዶች በተሰጡት ምክንያቶች ተከፍቻለሁ። ሆኖም እዚህ ኢንግላንድ ብዙ ሰዎች ቢቢሲ የእኔን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር መለያት አስመልክቶ ባስተላለፈው አሉታዊ ዘገባ ላይ ተመስርተው መጥፎ ነገር የምናገር እየመሰላቸው ይጠይቁኛል። እኔ ግን እስከ ወደ ፊቱም መጥፎ ነገር አልናገርም። ኢፊ የመለሱት የመጀመሪያዎቹን

አምስት ጥያቄዎች ስለሆነ እንጂ ጥያቄዎቼ እነዚህ ብቻ አልነበሩም። በቀጣይ ጊዜያት

በተለይ እንግሊዝ አገር ሄደውም ስለ ፌዴሬሽኑ ምንም እንዳይናገሩ

አድርጓቸዋል ስለሚባለው ምክንያት ምላሽ ከሰጡን ይዘን

ለመምጣት እንሞክራለን።

ያስፈልጋቸዋል። ተጨዋቾቹን እና ስራውን የሚያግዙ ሰዎችን ለማወቅ ጊዜ ይፈልጋል። ቢያንስ ከናይጄሪያ ጨዋታ በፊት የማሟሟቂያ ጨዋታ አግኝቷል። ይህም በጣም ጠቃሚ ነው። እኔ እዚያ እያለው ሁሌም እጎተጉት የነበረው የልምድ ማካበቻ ጨዋታ ስለማግኘት ነበር።

ነገ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ላይ ምን የሚፈጠር ይመስልዎታል?

በእውነቱ እንደማምነው ከናይጄሪያ ጋር በምታደርጉት ጨዋታ ጥሩ እድል አላችሁ። ብዙዎቹ የእነሱ ተጨዋቾች