ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. · 2019-12-16 · 4 ብርሃን ባንክ አ.ማ....

19
ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.

Upload: others

Post on 07-Mar-2020

34 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

ዓመታዊ ሪፖርት2011 ዓ.ም.

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 3

ማውጫየዳይሬክተሮች ቦርድ መልዕክት 4

የፕሬዝዳንቱ መልዕክት 6

አጭር አፈጻጸም ማሳያዎች 8

ዋና ዋና የአፈፃፀም ማሳያዎች 9

ራዕይበልህቀት አንጸባራቂና አስተማማኝ ባንክ መሆን

ተልዕኮብቁና ተነሳሽነት ያለው ሠራተኛን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሟላ የባንክ አገልግሎትን በመልካም ሥነ-ምግባር በመስጠት ለባለድርሻ አካላት የላቀ እሴት መፍጠር

እሴቶችጥራት ያለው አገልግሎት በብቃት መስጠት በትብብርና በጋራ መሥራት ደንበኞችን በአክብሮት ማገልገል የህብረተሰብ አመኔታ ፈጠራን፤ልህቀትን፤ዕድገትን መከተል ፍትሃዊነት የላቀ ሙያዊ ብቃትና በቡድን መስራት ምስጢር ጠባቂነት ሐቀኝነትና ታማኝነት

w w w . b e r h a n b a n k s c . c o m

ዓለም አቀፍ

በቀልጣፍ እና አስተማማኝ

ዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎታችን

ተጠቃሚ ይሁኑ!

ገንዘብአስተላላፊዎች

Tel +251 11 663 0127 / +251 11 618 5732

+251 11 662 9568

Fax +251 11 662 3431 Swift BERHETAA

E-mail [email protected] www.berhanbanksc.com

P.O.Box 387 Code 1110, Addis Ababa, Ethiopia

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.4

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር መልዕክት

የተወደዳችሁ ባለአክሲዮኖች !

እ.ኤ.አ. 2018/19 የበጀት ዓመት አጠቃላይ የባንኩን ታላቅ

አጀንዳ ከማስቀደምና ከማስፈጸም አንጻር እጅግ በጣም

ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡ በተለይም ባንኩ የተመሰረተበትን

10ኛ ዓመት በሚያከብርበት ወቅት 10ኛውን ዓመታዊ የሥራ

እንቅስቃሴ ዘገባ ሳቀርብ እጅግ ደስታ ይሰማኛል፡፡

በቅድሚያ ባንኩ በእነዚህ ከፍተኛ ዋጋ በምንሰጣቸው ዓመታት

ውስጥ ስላስመዘገባቸው ተከታታይ ስኬቶች እንኳን ደስ

አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡ እነዚህ አሥር ዓመታት ባንኩ

መነሻ አድርጎ የያዘው ልዩ ራዕይ ተጠብቆ የቆየበት፣ ውጤታማ

የአሰራር ስልቶች ተወጥነው ተግባራዊ የሆኑበት፣ የአብሮነት

ዓመታት፣ የዕድገትና የመሻሻል ዓመታት፣ በመጨረሻም ህልም

አካል ገዝቶ በተጨባጭ የታየባቸው ዓመታት ናቸው፡፡

ሌላው ይህንን 10ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረበአል ልዩ

የሚያደርገው ባንካችን እንደ ተጨማሪ ምዕራፍ በይበልጥ

ራዕዩን በሚያጎላውና የእሴቶቹን ጠንካራ ገጽታ የሚያሳየውን

አዲስ መለያ ምልክትና አርማ ይፋ ማድረጉ ነው፡፡

ይህ ወጥነት ያለው ዕድገት የተመዘገበው ባንኩ በተከተለው

የተቀናጀ የዕድገት ስልትና የባንኩ ማህበረሰብ ከዳር እስከ

ዳር ለባንኩ ራዕይ ስኬታማነት በሙሉ በመሰጠት መስራቱ

እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የባንኩ ጠንካራ ክንዋኔ ጎልብቶ

የምናገኘው ደንበኞችን በሚገባ ለማስተናገድ ባለው ጽኑዕ

ዓላማና በተጨማሪም ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ አስተዋጽዖ

ሊሆን የሚችል ቁርጠኝነትን በማሳየቱ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. የ2018/19 በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ

የራሱን ዕድሎችና ተግዳሮቶች ይዞ መጥቶ ነበር፡፡ በዚህ

ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ

በበርካታ ተግዳሮቶች ተከብቦ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ አገሪቱ

አሁን ከገባችበት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ለውጥ ምክንያት፣

በትንሹ የጀመረው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተግዳሮት፣ በቀላሉ

የማይፈታና ስር የሰደደ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከዓለም አቀፍ

የፖለቲካ ለውጦች ጋር ተደምሮ በንግድ ትስስሮች ላይ አሉታዊ

ተጽዕኖ አምጥቷል፡፡

ሆኖም ባንካችን በነዚህ ተጨባጭ ሁኔታዎች ሁሉ በማለፍ

ዛሬም እንደገና ጠንካራነቱንና ጽናቱን ሊያስመሰክር የሚችል

ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ይህም ውጤት በፋይናንስ ዙርያ

ብቻ ሳይሆን የባንኩ ባለድርሻ አካላት በባንኩ ላይ ያላቸውን

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 5

መተማመን እንዲጨምር በማድረግና አዳዲስ የንግድ እድሎችን

በመፍጠር ረገድም ውጤታማ አድርጎታል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በባንኮች መካከል ለታየው የተጧጧፈ

የንግድ ውድድር የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና የደንበኞች

አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በወቅቱ የነበረውን የንግድ አቋም

በመለወጥ ረገድ እንደ አንድ ወሳኝ መሣሪያ አገልግሏል፡፡

ባንካችንም ዘመኑ የሚጠይቀውን የዲጂታል ፋይናንሺያል

ቴክኖሎጂን በመገንባትና ጥራቱን የጠበቀ የሰው ኃይል አብቅቶ

በመመደብ ደንበኞች በተቀላጠፈ መንገድ አገልግሎታቸውን

እንዲያገኙ ለማድረግ በተጨማሪም አስተማማኝነቱን

በማጠናከር ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ፣ ተገቢውን ሥራ

ሰርቷል፡፡

በዚህም መሠረት ደንበኞቻችን ያለ ችግር ሊጠቀሙባቸው

የሚችሉባቸው አዳዲስ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አገልግሎቶች

ሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ ከዚሁ ጎን እነዚህን አገልግሎቶች

ተደራሽነታቸውን ለማስፋትና አቅማቸውን በመጨመር

አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የተሟላ

አዲስ የዳታ ማዕከል ግንባታ በስኬት ተጠናቆ ባንኩ ያሉትን

መረጃዎች በሙሉ ወደ አዲሱ የመረጃ ማዕከል የማሸጋገር

ሥራ ተከናውኗል። እንደዚሁም ቀድሞ ከነበረው የላቀ አቅም

ተጨምሮ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት

ተችሏል፡፡

በተጨማሪም የደንበኞችን አገልግሎት ጥራትና ዘመናዊ

ቴክኖሎጂን መጠቀም ሃብትን ከማሰባሰብ አንፃር ያላቸውን

ሚና በማየትና በንግዱ ዙሪያ የሚገኙትን ከባቢ ዕድሎች

ለመጠቀም እንዲያስችለው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ታማኝነት ከባንኩ ጋር አብረው የሚሰሩ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ

ባለ ድርሻ አካላት በባንኩ ላይ ያላቸው ዕምነት የተገነባበት፣

የባንኩ ዋና መለያ ነው፡፡ የባንካችን የውጭ ምንዛሬ ፍሰት

ምንም እንኳን ውስንነት ቢኖረውም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ

ባንክ ለባንኮች የውጭ ምንዛሬ ድጋፍ ሲያደርግ ባንካችንም

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ድጋፍ ካገኙ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ

መመረጡ ለዚህ እውነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ይህም የውጭ

ምንዛሬን በማስተዳደር ረገድ ባንካችን የብሔራዊ ባንክን

መመሪያዎችና ደንቦችን በማክበር በታማኝነት ማስፈጸሙንና

ለህግ ተገዥ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ባንካችን እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት ዓመት ከግብር በፊት

ብር 580.1 ሚሊዮን ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ በዚህም መሠረት

ለባለአክሲዮኖች የሚደርሰው አንድ ብር 1000 ዋጋ ያለው

አክሲዮን የትርፍ ክፍፍል ብር 246.5 ደርሷል፡፡ የባንኩ ትርፍ

ከአምናው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ41.2 በመቶ ዕድገት

አሳይቷል፡፡ ይህም ዕድገት በኢንዱስትሪው ውስጥ ካለው ከፍተኛ

ውድድር አንጻር ሲታይ የሚበረታታ ነው። በተጨማሪም

ባንካችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው ቀነ ገደብ

በፊት የተከፈለ ካፒታል መጠኑን ወደ ብር 2 ቢሊዮን በማሳደግ

ትልቅ ስኬት መጎናፀፉን ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

በበጀት ዓመቱ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድና ከፍተኛ የሥራ

አመራር እንደዚሁም መላው ሠራተኞች ደንበኞችን በጥራትና

በቅልጥፍና በማገልገል መልካም ውጤት ለማስመዝገብ

ከፍተኛ መሰጠትና ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ ይህም ውጤት

ሊያስመሰግንና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት የሚያስደፍር

መሆኑን በደስታ መግለጽ እወዳለሁ፡፡

በተለይም ባለፉት አሥር አመታት ባሳለፍናቸው ውጣ

ውረዶች ከእኛ ሳይለዩ ለዚህ ስኬትና ከፍታ ለመድረስ ላገዙንና

ጥሪታቸውን በማዋል አመኔታቸውን የሰጡንን የባንኩን ባለ

አክሲዮኖች ፣ እንዲሁም ተቆጣጣሪ አካል የሆነውን የኢትዮጵያ

ብሔራዊ ባንክን፣ በተጨማሪም ክቡራን ደንበኞቻችንን በባንኩ

የዲሬክተሮች ቦርድ ሥም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡.

በመጨረሻም ለብርሃን ባንክ ከፍተኛ አመራርና ለመላው

ሠራተኞች የባንኩን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በተባበረ መንፈስ

ላሳዩት እጅግ ቅንነት የተሞላ ትጋትና መሰጠት ከፍተኛ ምሥጋና

አደርሳለሁ፡፡

አመሰግናለሁ !

ጉማቸው ኩሴ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.6

የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች !

እ.ኤ.አ. በሰኔ 30 ቀን 2019 የተዘጋውን የባንኩን ዓመታዊ

አፈጻጸም ሳቀርብ እጅግ ደስታ ይሰማኛል፡፡ ይህ ወቅት የባንካችንን

የ10 ዓመት ጉዞና ስኬቱን በመዘከር የምሥረታ በዓሉን

የምናከብርበትና በተጓዳኝም የወደፊቱን ዕድገት ለመተለም

በሚያስችለን ደረጃ አቅማችንን እንደገና የምናድስበት ወቅት

በመሆኑ የማስተላልፈው መልዕክት ልዩ ስሜት ይሰጠኛል፡፡

እ.ኤ.አ. የ2018/19 በጀት ዓመት በባንካችን ውስጥ የራሱን

ክንዋኔ እና የፋይናንስ አፈጻጸም አሻራ ትቶ አልፏአል፡፡ የክንዋኔ

አፈጻጸሙን ስንመለከት ባንኩ አሁን በደረሰበት የዕድገት ደረጃ

በሚገባ ተወዳዳሪነቱን ያስመሰከረበትና ትክክለኛና ጠንካራ

ገጽታውን ያሳየበት መሆኑን ለማየት ይቻላል፡፡ የተገኘው ውጤት

በእርግጥም የውድ ባለአክሲዮኖች፣ የታማኝ ደንበኞቻችን፣

በሙሉ መሰጠት ያገለገሉ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ

ከፍተኛ ሥራ አመራርና የመላው ሠራተኛ የልፋትና የትጋት

ውጤት እንደሆነ መግለጽ እወዳለሁ፡፡

ምንም እንኳን በበጀት ዓመቱ በሃገር እንዲሁም በዓለም አቀፍ

ደረጃ የገበያ አለመረጋጋት ተግዳሮቾች የታዩበት ቢሆንም

ባንካችን መልካም የሆነ አፈጻጸም ያስመዘገበበት ዓመት ሆኗል፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2018/19 የበጀት ዓመት ውስጥ ባንካችን ብር 4.1

ቢሊዮን የተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰብ ወይም በ 38 በመቶ

እድገት በማስመዝገብ አጠቃላይ የባንኩን የተቀማጭ ገንዘብ

መጠን ብር 14.9 ቢሊየን አድርሶታል፡፡ የባንኩን አጠቃላይ

የተቀማጭ ገንዘብ እድገት በቋሚነት ለማስቀጠል ውጤታማ

የሆነ የአሰባሰብ ስልት እና አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በሌላ

በኩል ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 161.7 ሚሊዮን

የአሜሪካን ዶላር የሰበሰበ ሲሆን ካለፈው ዓመት 108.5

ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነጻጸር 49 በመቶ እድገት

ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ባንኩ ተደራሽነቱን ለማሳደግና ለማስፋት ባለው ዕቅድ መሠረት

እ.ኤ.አ. በ 2018/19 የበጀት ዓመት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ

ክፍሎች 18 ቅርንጫፎችን በመክፈት አዳዲስ ዘመናዊ የዲጂታል

ባንኪንግ አገልግሎቶችን በመጀመር እንደዚሁም የደንበኞች

አገልግሎትን በማጠናከር ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት በመስጠት

ላይ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2019 የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ ባንካችን

የፕሬዝዳንቱ መልዕክት

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 7

ለደንበኞች የሰጠው የብድር መጠን ብር 10.2 ቢሊዮን

ደርሷል፡፡ ይህም አሃዝ ባለፈው በጀት ዓመት ብር 7.2 ቢሊዮን

ሆኖ ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር የብር 3.02 ቢሊዮን ዕድገት

አሳይቷል፡፡ ይህ የብድር መጠን እድገት የሚያመላክተው

ባንካችን በአገራችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን

ፋይናንስ ለማድረግ የሚያስችል አቅም እንዳለው ነው፡፡ በባንኩ

የተሰጠው ብድርና የተበላሹ ብድሮች ምጥጥን ሲሰላም

ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ ገደብ በታች 3.55

በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም የባንኩን የብድር ጥራት

አስተዳደር ሥርዓት ጥንካሬን ማሳያ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት የባንኩ

አጠቃላይ ሃብት ብር 19.2 ቢሊዮን ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን

ካለፈው ዓመት አፈጻጸም በብር 5.1 ቢሊዮን ወይም 36.3

በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የባንካችን እ.ኤ.አ. የ2018/19 በጀት ዓመት ትርፍ ከግብር በፊት

ካለፈው የበጀት ዓመት ትርፍ በ41.2 በመቶ ዕድገት አሳይቶ

ከግብር በፊት ብር 580.1 ሚሊዮን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዚህም

መሠረት የባለአክሲዮኖች የትርፍ ክፍፍል ድርሻ ብር አንድ ሺህ

ዋጋ ላለው አንድ አክሲዮን ብር 246.5 ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ

በበጀት ዓመቱ ውስጥ ባንካችን ጤናማና የተረጋጋ የገንዘብ

ፍሰት የነበረው ሲሆን ፣ ይህም ለተመዘገበው ውጤት ከፍተኛ

አስትዋጽኦ አድርጓል።

ከቴክኖሎጂ አንጻር በተለይም በድጅታል ቴክኖሎጂ ዓለማችን

ምን ያህል በፍጥነት እያደገች እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እነዚህ

ቴክኖሎጂዎች የባንክንም አገልግሎት አሰጣጥ ወሳኝ በሆነ

መንገድ በስፋት ለመለወጥ ተጽዕኖ እያደረጉ እንደሆነ ግልጽ

ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት

የባንኩን የተለያዩ አገልግሎቶች ዲጂታል በማድረግና በማዘመን

ደንበኞቻችን ምቹ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ

ተደርጓል፡፡

ባንካችን በአሁኑ ወቅት 657 ሺህ ለሚሆኑ ክቡራን ደንበኞቹ

አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ውስጥ

108,771 የሚሆኑት የብርሃን ባንክ ኤ.ቲ.ኤም ካርድ ያላቸው

ሲሆን 108,680 የሚሆኑት ደግሞ የሞባይል ባንኪንግ

አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከሞባይል ባንኪንግ

አገልግሎት በተጨማሪም የኢንተርኔት ባንኪንግ መዘርጋት እና

የማስተር ካርድ የመመንዘር አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የቪዛ

ካርድን የመመንዘር አገልግሎት ለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎች

እየተመቻቹ መሆኑንና በሚቀጥለው የበጀት ዓመት አገልገሎቱ

እንደሚጀምር ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

የደንበኞችን የአገልግሎት ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ ደንበኞች

በአገልግሎታችን ላይ ቅሬታ ቢያድርባቸው በቀጥታ ቅሬታቸውን

ለመግለጽ የሚችሉበትን ነጻ የስልክ መስመር ማዘጋጀት በበጀት

ዓመቱ ልዩ ትኩረት ከተሰጠባቸው ተግባራት መካከል አንዱ

ነበር፡፡

በበጀት ዓመቱ የሂሳብ መዝገብ አያያዛችንም ከ IAS 39

ወደ ዓለም አቀፍ የሂሳብ መዝገብ ዘገባ ማቅረቢያ ደረጃ

(International Financial Reporting Standard – IFRS 9)

የማሸጋገር ሂደት በስኬት ተጠናቋል፡፡ ይህም ሂደት የተከናወነው

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አማካይነት በጋራ በተቀጠረው

[KPMG] ከተባለው አማካሪ ድርጅት ጋር በመቀናጀት ነው።

ዓለም አቀፍ የሂሳብ መዝገብ ዘገባ ማቅረቢያ ዘዴ (IFRS 9)

ትግበራ የባንኩን የፋይናንስ አቀራረብ ተዓማኒነት በዓለም አቀፍ

የንግድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሳድጋል ተብሎ ይታመናል፡፡

ባንካችን 10ኛውን የምሥረታ በዓል እያከበረ ይገኛል፡፡ በነዚህ

አሥር አመታት ውስጥ ታላቅ መሰጠትና ትጋት ካለው ከመላው

የባንኩ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ከጅምሩ የተቋቋመበትን

ተልዕኮ አስጠብቆ በስኬት እየተጓዘ ይገኛል፡፡ ካለፈው ወደ አዲሱ

ምዕራፍ ለመሸጋገርና የወደፊቱን በአዲስ አቅምና ጉልበት

ለመጀመር ዋና ዋና እሴቶቻችንን በሚገልጽ መልኩ ባንካችን

አሁን በአዲስ መለያ ምልክትና አርማ ብቅ ብሏል፡፡

በመጨረሻም የባንኩን ራዕይና ተልዕኮውን እንዲሁም የማዕዘን

ድንጋይ የሆኑትን እሴቶቹን በመጠበቅ ለታየው አመርቂ

ውጤት በትጋትና በንቃት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደረጉትን

የባንካችንን የዲሬክተሮች ቦርድ ፣ ከፍተኛ የሥራ አመራሩንና

መላው ሠራተኛውን ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

አመሠግናለሁ !

አብርሃም አላሮ

ፕሬዝዳንት

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.8

ተቀማጭ ገንዘብ (በሚሊዮን ብር)

ሰኔ, 2

017 ሰኔ

, 201

8

ሰኔ, 2

019

7,670

10,862

14,964

ሰኔ, 2

017 ሰኔ

, 201

8

ሰኔ, 2

019

10,535

14,068

19,173

ሰኔ, 2

017

ሰኔ, 2

018 ሰኔ

, 201

9

429 411

580

ሰኔ, 2

017 ሰኔ

, 201

8

ሰኔ, 2

019

5,406

7,191

10,216

ሰኔ, 2

017 ሰኔ

, 201

8 ሰኔ, 2

019

1,396

1,7092,000

ሰኔ, 2

017 ሰኔ

, 201

8

ሰኔ, 2

019367,379

523, 705

657, 026

አጭር አፈጻጸም ማሳያዎች

የብድርና ቅድሚያ ክፍያዎች (በሚሊዮን ብር)

የተከፈለ ካፒታል (በሚሊዮን ብር)

የደንበኞች ቁጥር

ሃብት (በሚሊዮን ብር)

የተጣራ ትርፍ ከግብር በፊት (በሚሊዮን ብር)

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 9

1. የ2018/19 በጀት ዓመት ዐበይት ክንዋኔዎች

እ.ኤ.አ. በ2018/19 የዓለም ኢኮኖሚ በብዙ መልኩ የተቀያየጠና

እጅግ ተለዋዋጭ መልክ ነበረው፡፡የንግድ ውጥረት፣ የታሪፎች

ማሻቀብ፣ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች የሸቀጥ አቅርቦት

ላይ ተጽዕኖ መፈጠር እና በሸቀጥ አቅርቦትና ዋጋ ላይ

አስደንጋጭ የሆነ መለዋወጥ መገለጫዎቹ ሆኖ አልፎአል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ የሚወጡት የተለያዩ ፖሊሲዎች የኢኮኖሚውን

ሁኔታ እርግጠኝነት ጥያቄ ውስጥ በመክተት እና የንግድ ሥራዎች

ላይ ተጽዕኖውን በማሳደር ኢንቨስትመንቶች በሚጠበቁት

ልክ እንዳያድጉ ከማድረጉም በላይ የየአገሩ የነፍስ ወከፍ ገቢ

ዕድገትም እንዲያዘግም ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ የዓለም ኢኮኖሚ

ዕድገት ዝግመት ጎልቶ የታየው እ.ኤ.አ. በ2018 ዓ.ም. ሁለተኛው

አጋማሽና በ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ነበር፡፡ ይህ

የኢኮኖሚ ዝግመት የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት አገሮች ላይ እና

በኢኮኖሚያቸው ባላደጉት አገሮች ላይም ተንፀባርቋል፡፡

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ዕድገት ጠንካራ

ነው፡፡ ይህም በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪው

ዘርፍ እየታየ ባለው ዕድገት ሳቢያ የመጣ ሲሆን በየዓመቱ

የሚመዘገበው አማካይ የዋጋ ግሽበት ግን አሁንም ከፍተኛ

ነው፡፡ በተጨማሪም ካለፈው ዓመት ጀምሮ እንደ ቡና፣ ሰሊጥና

ሌሎችን የቅባት እህሎችን እንደዚሁም ቆዳና የቆዳ ውጤቶችን

በመላክ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ እየወረደ መምጣት ጋር

ተያይዞ ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦች ገቢ ቀንሷል፡፡

በተለይ ባለፈው ዓመት የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቀድሞ

ከነበሩት ዓመታት ጋር በተለያዩ መሠረታዊ ማነጻጸሪያዎች

ሲተያይ እጅግ የተዳከመበት ዓመት እንደነበር አይዘነጋም::

ለዚህም በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ከውጭ የሚገቡት

የግንባታ ዕቃዎች ዋጋቸው ከማሻቃባቸው ጋር ተያይዞ የግንባታ

ሥራዎች በጣም መዳከማቸው እና የአገሪቱ የዓለም አቀፍ ብድር

መጨመር እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህም የአገሪቱን

ወጪ እንዲንር በማድረግ ከሚኖራት ገቢ ጋር ካለመመጣጠኑ

የተነሳ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ መዳከም አስተዋጽዖ እንዳደረገም

ይጠቀሳል፡፡

በአዎንታዊ ገጽታው ደግሞ የዓለምን የኢኮኖሚ አቅጣጫ

ባገናዘበ መልኩ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ካለበት አጣብቂኝ ውስጥ

ለማውጣትና የዕድገት አቅጣጫ ለመተለም እንደ አዕማድ

የሚታዩትን ትላልቅ የንግድ ተቋማትን ከመንግሥት ወደ ግል

ለማዞር የተጀመረው ሂደት የሚያበረታታና ተስፋ የሚጣልበት

ነው፡፡

ብርሃን ባንክ በሚገባ ሊገለጽ በሚችል መልኩ በተቀናጀ ስልትና

ከውጭ ወደ ውስጥ የሚቀርበውን ጥያቄ ምላሽ በመስጠትና

ተከታታይ መሻሻሎችን በማሳየት ዕድገቱን ጠብቆ ለማስቀጠል

ችሏል፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2018/19 በጀት ዓመት የተለያዩ የዲጂታል ባንኪንግ

አገልግሎቶችን አዘጋጅቶ በተለያዩ የአገልግሎት መተግበሪያዎች

በማጠናከርና በኮምፒውተር ሥርአቱ ውስጥ በማስረጽ

የባንካችን የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን ከመቼውም ይልቅ

እንዲጠናከር ተደርጓል። በተጨማሪም ባንኩ የሂሳብ አያያዙን ከ

IAS 39 ወደ ዓለም አቀፍ የሂሳብ መዝገብ ዘገባ አቀራረብ ደረጃ

9 (International Financial Reporting Standard – IFRS 9)

በቀላሉ ያለምንም ችግር የማሸጋገር ሥራ ሰርቷል:: ይህ ሽግግር

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አማካይነት በጋራ በተቀጠረው

[KPMG] በሚባለው አማካሪ ድርጅት ድጋፍ ተከናውኗል፡፡

በሌላ በኩል የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትን ለማሳደግ የሎቶሪ

ዕጣ ፕሮጄክት ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማ ለመሆን ተችሏል፡፡

ይኸውም ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን ገንዘብ በባንካችን

በኩል ሲቀበሉ የሎቶሪ ዕጣ እንዲወስዱ በማድረግ ብዙ

ደንበኞቻችን ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ለማግኘት ተችሏል፡፡

ሆኖም አሁንም በገሃድ የሚታየው የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታና

የኢኮኖሚ መዋዠቅ ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ትልቅ ተግዳሮት

እንደሆነ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

2. የበጀት ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም

2.1 የተቀማጭ ገንዘብ እንቅስቃሴ

እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት ዓመት ብርሃን ባንክ በአጠቃላይ ብር

4.1 ቢሊዮን ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ በአለፈው

በጀት ዓመት ብር 10.9 ቢሊዮን ሆኖ ከተመዘገበው አጠቃላይ

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ወደ ብር 14.9 ቢሊዮን አሳድጎታል::

በዚህ አመት ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ የአንበሳውን

ድርሻ የሚይዘው የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፣ ተንቀሳቃሽ

ሒሳብ ደግሞ ተከታዩን ድርሻ ይዟል፡፡ ሃብት ማሰባሰብን፣

ማሳደግንና ማጠናከርን ግብ በማድረግ ባንኩ የተለያዩ አዳዲስ

ዋና ዋና የአፈፃፀም ማሳያዎች

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.10

የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አገልግሎቶችን ይዞ ወደ ገበያው የገባ

ሲሆን በተጨማሪም በመላው አገሪቱ በተለይም የሃብት ምንጭ

በሆኑ በተጠኑ አካባቢዎች የቅርንጫፍ ስርጭቶችን በማሳደግ

በጥንካሬ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የተቀማጭ ሂሳብ

ደንበኞች ቁጥር 657,026 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

2.2 ብድርና ቅድሚያ ክፍያዎች

እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት ዓመት የብርሃን ባንክ ጠቅላላ የብድር

ክምችት ብር 10.2 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን በአለፈው በጀት

ዓመት ከተመዘገበው ብር 7.2 ቢሊዮን ጋር ሲነጻጸር የብር 3.02

ቢሊዮን ዕድገት አሳይቷል፡፡ የባንኩ የብድር ክምችት በኢኮኖሚ

ዘርፍ አመዳደብ ስንቃኘው በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ትርጉም

ያለው ዕድገት የተመዘገበ ቢሆንም የአገር ውስጥ ንግድ፣

የህንጻና የግንባታ ዘርፎች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ከዚህ ጎን

ለጎን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ የተበላሹ ብድሮች ምጥጥን

3.55 በመቶ ሆኗል፡፡

2.3 የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት እንቅስቃሴ

ባንካችን እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት ዓመት 161.7 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያሰባሰበ ሲሆን ይህ ውጤት በአለፈው በጀት ዓመት 108.5 ሚሊዮን ሆኖ ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር የ49 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮች ያላቸውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅርፍ ባወጣው የድጋፍ መርሃ ግብር መሠረት ባንካችን በመጨረሻው ሩብ ዓመት መገባደጃ ላይ የተደረገለት የውጭ ምንዛሬ ድጋፍ የነበረበትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍና በተወሰነ መልኩ የገበያውን ፍላጎት ለማሟላት አስተዋጽኦ አድርጓል።

በሌላ በኩል የባንኩን የውጭ ምንዛሬ አቅም ለማሳደግ ከባንካችን ጋር ሊሰሩ የሚችሉ የውጭ አገር ባንኮችን በማፈላለግና ከማነጋገር ባለፈ የባንኩ የአገልግሎት ጥራት በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ እንደዚሁም ለውጭ ምንዛሬ እንደ ምንጭነት ያገለግላሉ የሚባሉትን ተቀዳሚ ደንበኞችን በመድረስና ግንኙነት በመፍጠር ሠፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሎቶሪ ፕሮጀክት በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ክምችታችንን ለማሳደግ ያላሰለሰ ጥረት ተደርጓል፡፡

3. የፋይናንስ አፈጻጸም

3.1 ሃብት

እ.ኤ.አ. በሰኔ 30 ቀን 2019 የተዘጋው የበጀት ዓመቱ ሒሳብ እንደሚያሳየው የባንካችን አጠቃላይ ሃብት፣ በአለፈው በጀት ዓመት ከተመዘገበው ብር 14.1 ቢሊዮን ወደ ብር 19.2 ቢሊዮን ከፍ ብሎ የ36.3 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የባንኩ የብድር ክምችት ኣድገትና በብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዢ ላይ የተደረገ የመዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የዚህ ዕድገት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው።

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ

14,964

10,862

5,359

ተንቀሳቃሽ ቁጠባ የጊዜ ገደብ

8,299

5,772

1,3071,122

የተቀማጭ ሂሳብ ክፍፍል በሚሊዮን ብር

3,967

* የግል ብድሮችን ያካትታል**የቅድመ ጭነት፣ የተንቀሳቃሽ አና የቃ ግዢ ብድሮችን ያካትታል

1,326

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

399

766

285260

923

1,802

2,188

1,507

19

ትራንስፖርት ሌሎች የሰራተኞች ብድር

ማምርቻ የገቢ ንግድ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት

የወጪ ንግድ

የግንባታ ሥራ ግብርና ምርትየሀገር ውስጥ ንግድና አገልግሎት

የብድርና የቅድሚያ ክፍያዎች ስርጭት በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በሚሊዮን ብር

-

579 480468

1,492

1,082 926

464

2,393

48

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 11

3.2 ካፒታል

እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2019 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባንኩ

የተከፈለ ካፒታል ቀድሞ ከነበረበት ብር 1.7 ቢሊዮን ወደ ብር

2 ቢሊዮን አድጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለግል ባንኮች

ያስቀመጠውን የካፒታል መጠን ከተወሰነው የግዜ ገደብ

(እ.ኤ.አ. 2019/20 በጀት ዓመት) በፊት በማሟላት ባንኩ

በዚህ ረገድ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም የባንኩ

አጠቃላይ ካፒታል እ.ኤ.አ. በ 2018/19 በጀት ዓመት መጨረሻ

ላይ ብር 2.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን በአለፈው በጀት ዓመት

ከተመዘገበው ብር 2.2 ቢሊዮን 27.0 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ከዚሁ ጎን የባንኩ የባለአክሲዮኖች ቁጥር 14,906 ሆኗል፡፡

3.3 ገቢ

እ.ኤ.አ 2018/19 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የባንኩ ገቢ ከአለፈው በጀት ዓመት 42.6 በመቶ ዕድገት አሳይቶ ብር 2.2 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ከተገኘው ገቢ ውስጥ ከወለድ የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 38.0 በመቶ ዕድገት ያሳየ ሲሆን ከክፍያና ኮሚሽን የገቢ ምንጮች የተገኘው ገቢ ደግሞ የ54.2 በመቶ ዕድገት ታይቶበታል፡፡ ከአጠቃላይ ገቢው ውስጥ ከወለድ የተገኘው 69.6 በመቶ ድርሻ ሲይዝ 30.4 በመቶ

የሚሆነው ደግሞ ወለድ ካልሆኑ የገቢ ምንጮች የተገኘ ነው::

3.4 ወጪ

በበጀት ዓመቱ ውስጥ የባንኩ አጠቃላይ ወጪ ብር 1.6 ቢሊዮን

ደርሷል፡፡ ይህም ከአለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ43.1

በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ለወለድ የተከፈለው ወጪ ከአለፈው

በጀት ዓመት ጋር ሲወዳደር የ45 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ከወለድ

ውጭ የተከፈለ ወጪ ደግሞ በ41.9 በመቶ አድጓል፡፡ የወጪውን

የአንበሳ ድርሻ ምጣኔ የሚይዘው ከወለድ ውጭ የተከፈለው

ወጪ ሲሆን ይህም በመቶኛ ሲሰላ 62.8 በመቶ ይሆናል፡፡ ቀሪው

37.2 በመቶ ለወለድ የተከፈለ ወጪ ነው፡፡

3.5 ትርፍ

እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት ዓመት ባንኩ ከግብር በፊት ብር 580.1 ሚሊየን ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ ይህ የትርፍ መጠን ከአለፈው በጀት ዓመት ትርፍ ጋር ሲነጻጸር የብር 169.1 ሚሊዮን ወይንም የ41.2 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ይህ አበረታች ውጤት የተመዘገበው ሁሉም የባንኩ ባለድርሻ አካላት ያገኙትን ዕድል ሁሉ በመጠቀም እና ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ባደረጉት ከፍተኛ ርብርቦሽ ነው።

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

አጠቃላይ ካፒታል

2,000

የተክፈል ካፒታል

የካፒታል ስርጭት በሚሊዮን ብር

2,202

2,796

1,709

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

አጠቃላይ ገቢ

2,206

1,536

ከወለድ ገቢ ሌሎች ገቢዎች

671

የገቢ ስርጭት በሚሊዮን ብር

1,548

1,113

435

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

አጠቃላይ ወጪ

1,626

605

ከወለድ ወጪ ሌሎች ወጪዎች

719

የወጪ ስርጭት በሚሊዮን ብር

1,137

417

1,021

ሰኔ 2019

ሰኔ 2018

አጠቃላይ ገቢ

2,206

1,137

አጠቃላይ ወጪ ትርፍ ከግብር በፊት

410.9

የ 2018/19 የበጀት ዓመት ትርፍ በሚሊዮን ብር

1,5481,626

580.1

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.12

4. የሰው ኃይል

እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2018/19 በተዘጋው በጀት ዓመት የብርሃን

ባንክ የሠራተኞች ቁጥር 3,853 ደርሷል፡፡ ይህ ቁጥር ከአለፈው

በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ616 ወይም በ19 በመቶ ዕድገት

አሳይቷል፡፡ ከጠቅላላ ሠራተኞች ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት

ወንዶች ሲሆኑ የተቀሩት 35 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች

ናቸው፡፡

በበጀት ዓመቱ ባንኩ የደንበኞች አገልግሎትን ጥራት ለማሳደግ፣

አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ እና ተነሳሽነት ያለው

ብቁ የሰው ሃይል ለመፍጠር እንዲረዳው ለ 3,033 ሰራተኞች

የተለያዩ ስልጠናዎች ሰጥቷል። በበጀት ዓመቱ ውስጥ ሥልጠና

ከወሰዱት ውስጥ 162 የሚሆኑት ለመጀመሪያ ድግሪና ከዚያ

በታች በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሥራ ሰዓት ውጭ

እንዲማሩ ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው፡፡

5. የቅርንጫፍ ሥርጭት

ደንበኞች የባንኩን አገልግሎት ከሚኖሩበትና ከሚሰሩበት

አካባቢ ብዙም ሳይርቁ በአቅራቢያቸው እንዲያገኙና ሃብት

የማሰባሰብ አቅሙን ለማሳደግ እንዲያስችል ባንኩ የቅርንጫፍ

ሥርጭቱን በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጪ በማስፋፋት ላይ

ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት እ.ኤ.አ. በሰኔ 2019 መጨረሻ ላይ

የባንኩ ቅርንጫፎች ቁጥር 200 ደርሷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 18

አዳዲስ ቅርንጫፎች በበጀት ዓመቱ ውስጥ የተከፈቱ ሲሆን 7ቱ

ከአዲስ አበባ ውጪ ቀሪዎቹ 11 ቅርንጫፎች ደግሞ በአዲስ

አበባ የተከፈቱ ናቸው፡፡

6. ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀም ባንኩ አገልግሎቱን በጥራትና

በቅልጥፍና እንዲሰጥ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥርለትና

ከሌሎች በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር ብቁ ተወዳዳሪ

እንደሚያደርገው ይታመናል፡፡ የደንበኞችን የማያቋርጥ ጥያቄ

ከመመለስ አንጻር ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ ማዕከል ግንባታ

አጠናቅቆ ለአገልግሎት በማብቃት ለሌሎች ቀጣይ ፕሮጀክቶች

መሰረት ጥሏል። የዳታ ማዕከል ግንባታውን ተከትሎ የባንኩን

የኮር ባንኪንግ ስርአት የበለጠ የማሳደግና የማዘመን ስራ

ተሰርቷል። በዚህም ባንኩ ቀድሞ ከሚሰጣቸው የኤሌክትሮኒክስ

ባንኪንግ አገልግሎቶች በተጨማሪ ሌሎች ድጅታል ባንኪንግ

አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችለውን አቅም እንዲፈጥር እና

የቅርንጫፍ አድማሱን በማስፋት የባንኩ የደንበኞች መሠረት

በስፋትና በአይነት እንዲጨምር እና እገዛ እንደሚያደርግ እሙን

ነው፡፡ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ባንኩ ላለፉት ዓመታት

የያዛቸውን መረጃዎች ወደ አዲሱ የመረጃ ማዕከል የአገልግሎት

አሰጣጡ ሥራ ከቶም ሳይረበሽ በቀላሉ የማሸጋገር ሥራ በስኬት

ተከናውኗል፡፡

7. የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎቶች

የድጅታል የፋይናንስ አገልግሎቶች አንድም ደንበኞች በሁሉም

ቦታና ግዜ የባንክን አገልግሎት እንዲያገኙ ፣ ሁለትም ባንኮች

አገልግሎታቸውን ዘርፈ ብዙ በሆነ መልኩ ለደንበኞቻቸው

እንዲያቀርቡና ሃብትን ማሰባሰብ እንዲችሉ የሚረዱ ጠንካራ

መንገዶች ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለሆነም ባንካችን

እነዚህን የድጅታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በመጠቀምና

የአገልግሎት አድማሱን አስፍቶ ደንበኞችን በሚገባ በማገልገል

ከዚያም የሚገኘውን ትሩፋት ለማግኘት በመወሰን በበጀት

ዓመቱ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ በዚህም

መሠረት የሞባይል ቶፕ አፕ እና አፕሊኬሽን ቤዝድ ሞባይል

ባንኪንግ አገልግሎቶች ለደንበኞች ክፍት እንዲሆኑ ተደርጓል::

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ

ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉና ፣ የማስተር ካርድ የምንዛሬ

አገልግሎትም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ሌላ ባንኩ ቪዛ ካርድን

የሚጠቀሙ ማናቸውም ደንበኞች ከባንካችን መመንዘር

የሚችሉበትን ሥርአት ለማመቻቸት በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን

በቅርቡም ይህ አገልግሎት ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የኤጀንሲ ባንኪንግ እና የትምህርት ቤት ክፍያ ስርዓት ውስጥ

ለመግባት የሚያስችሉ ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ። በሌላ

በኩል የድጅታል ባንኪንግ አገልግሎት በደንበኞች ዘንድ ያለውን

ጠቀሜታ በማስመልከት ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ለመስራት

የተገኙትን ዕድሎች ሁሉ በመጠቀም የተለያዩ ሥልጠናዎች

ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ተሰጥቷል፡፡

8. የባንኩ 10ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረበዓል

ብርሃን ባንክ ያለፉትን አሥር ፍሬያማ አመታት በማለፍ

አሁን 10ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ በነዚህ አሥር

የአገልግሎት ዓመታት አብሮ ያለፈ ደንበኛ የባንኩን ግልጽ

አሰራር፣ የደንበኞች አመኔታንና ታማኝነትን ማስረጹን በሚገባ

ይመሰክራል፡፡ በእርግጥም ብርሃን ባንክ ከቶም ሳያመቻምች

በሚከተለውና በሚተገብረው ታማኝነትን የተላበሰ አሰራር

ለሌሎች ምሣሌ መሆን እንደሚችል የሚያጠያይቅ አይሆንም::

ብርሃን ባንክ አሥረኛ ዓመት ክብረ በዓሉን የሚያከብረው

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 13

ከጅማሬው አንስቶ አነሳሱን የሚያውቁና በውጣ ውረዱ ሁሉ

አብረውት ጸንተው በመቆም ለፍሬና ለውጤት እንዲበቃ

የበኩላቸውን እንደ አቅማቸው ካበረከቱት ከመስራቾች፣

ከዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከከፍተኛ ሥራ መሪዎች፣ ከመላው

ሠራተኞችና ከተለያዩ የባለአድርሻ አካላት ጋር ነው፡፡

ይህ የባንኩ 10ኛ ዓመት ክብረ በአል ያለፉትን ስኬታማ አመታት

በማሰብ ብቻ ሳይሆን የሚቀጥሉትን አሥር አመታት ደግሞ

እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ ወስዶ የበለጠ ፍሬያማ የሚሆንበትን

ትልም በመተለም ይከበራል፡፡ በመሆኑም ባንኩ በአሁኑ ወቅት

ከክብረበአሉ ጎን ለጎን በአዲስ መለያ ምልክትና አርማ በመገለጥ

ይህንን እንደ አንድ ሌላ አዲስ ምዕራፍ በመውሰድ ላይ ይገኛል::

የባንኩን አዲስ መለያ አርማና ምልክት በማዘጋጀቱ ሂደት ውስጥ

በመስኩ የዳበረ ሙያና ልምድ ካለው ዲዛይነር ጋር በመነጋገር

፤ አዲሱ አርማና መለያ ምልክት የባንኩን የሥራ ፍልስፍና፣

የታማኝነትና የሃቀኝነት እሴቱን በዝርዝር በማጥናት ምልክቱም

ያንን እንዲያሳይ በመቅረጽ ለመተግበር ተችሏል፡፡

በዚህ መሠረት አዲሱ አርማና መለያ ምልክት ባንኩ አሥረኛ

ዓመቱን በይፋ በሚያከብርበት ዕለት የሚመለከታቸው

ባለድርሻ አካላት ሁሉ በተገኙበት በይፋ ሥራ ላይ እንዲውል

ተደርጓል፡፡ በቀጣይም ባንኩ በአዲሱ መለያ አርማና ምልክት

የሚታወቅ ይሆናል፡፡

9. የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ

ባንኩ ተመስርቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ግዜ

አንስቶ የራሱ የሆነ ዋና መሥሪያ ቤት እንደሚያስፈልገው

ስለሚታመንበት ዋና መሥሪያ ቤት ሊገነባበት የሚችልበትን

ቦታ በማፈላለግና ዕድሎችን ሁሉ በመሞከር እስካሁን

ቆይቷል:: በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይህ ጉዳይ የባንኩ

ቀዳሚ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ሆኖም በተለያዩ

ምክንያቶች የተነሳ እስካሁን ሳይሳካ ቆይቷል፡፡ በበጀት ዓመቱ

ባንኩ ይህንን ዕቅድ ለማሳካት እና ወደ ፍጻሜ ለማድረስ

በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ስለዚህ ይህ

ሂደት በዚህ በያዝነው በአዲሱ በጀት ዓመት ማለትም እ.ኤ.አ.

በ2019/20 ላይ ወደ ፍጻሜ እንደሚደርስና ለግንባታ የሚሆን

ቦታ እንደምናገኝ ተስፋ ይደረጋል፡፡ ይህ ስኬት ባንኩ በዘመናት

መካከል ዕሴቱንና ተልዕኮዉን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፉን

ተስፋ እንደሚያለመልመው ይታመናል፡፡

10. ማህበራዊ ኃላፊነት

ባንኩ ገና ከምሥረታው ጀምሮ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ

እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ዘንድሮም እ.ኤ.አ. በ2018/19 በጀት

ዓመት ‹‹ሸገርን በማስዋብ ፕሮጄክት›› ከተማዋን አቋርጠው

የሚያልፉ ወንዞችን በማጽዳትና ለመዝናኛነት በማብቃት

አዲስ አበባን ለማስዋብ መንግስት በሚያደርገው እንቅስቃሴ

ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎና ድጋፍ በማድረግ ሃላፊነቱን

ተወጥቷል፡፡ በተጨማሪም በየጊዜው በሚደርሰው መፈናቀል

ምክንያት ከተለያዩ የክልል አስተዳደር ቢሮዎች በሚቀርበው

የእርዳታና የድጋፍ ጥያቄዎች መሠረት ግንባር ቀደም በመሆን

የበኩሉን ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ባንኩ ተመሳሳይ

ድጋፎችንና ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ ፕሮጄክቶች ላይ ተሳታፊ

በመሆን ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

11. የወደፊት ዕቅዶች

ብርሃን ባንክ በሚቀጥሉት ዓመታት ሊፈጽማቸው ያሰባቸውን

ዋና ዋና ዕቅዶችን እንደሚከተለው ያስቀምጣል፡፡

• ሃብትን የማሰባሰብ ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ ማስቀጠል

• የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በተጠናከረ

ሁኔታ ማሳደግ

• የሃብት ጥራት አመራርን ማጠናከር

• የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በከፍተኛ ደረጃ

ማሻሻልና ማሳደግ

• የተቀናጀ ድርጅታዊ ባህልን ማዳበር እና ጠንካራ የሥራ

ኃይል መፍጠር ናቸው።

ለብርሃን ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች የቀረበ ገለልተኛ የኦዲተሮች ሪፖርት

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 15

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

ለብርሀን ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኞች የቀረበ ገለልተኛ የኦዲተሮች ሪፖርት

አስተያየት እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 2019 ለተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት በብርሀን ባንክ አክስዮን ማህበር የተዘጋጁ የሂሳብ መግለጫዎች ማለትም የሀብትና እዳ መግለጫ፣ የትርፍና ኪሳራ መግለጫ፣ የባለአክሲዮኖች ካፒታል ለውጥ መግለጫ፣ የገንዘብ ፍሠት መግለጫ እና የሂሳብ አሰራር መርች ማጠቃለያ እና ማብራሪያዎችን መርምረናል፡፡

በእኛ አስተያየት የሂሳብ መግለጫዎቹ አጠቃላይ ተቀባይነት ባላቸው የሂሳብ አያያዝ መርች መሰረት እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2019 የነበረውን የባንኩን የሂሳብ አቋምና በዚያው እለት በተጠናቀቀው የሂሳብ ዘመን የተገኘውን አጠቃላይ ውጤት፤ የባለአክሲዮኖች ካፒታል ለውጥ መግለጫ፣ አና በዓመቱ የነበረውን የጥሬ ገንዘብ ፍሠት ከዓለምአቀፍ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመዘኛዎች ቦርድ (አይ/ኤ/ኤስ/ቢ) በተገኘው በዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት መመዘኛዎች (አይ/ኤፍ/አር/ኤስ) መሠረት በትክክልና በተገቢው ሁኔታ ያሳያሉ፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን በሚመለከት በ1952 በወጣው የንግድ ህግ አንቀፅ 375 መሰረት በእኛ በኩል የምንሰጠው የልዩነት አስተያየት የሌለን መኑን እየገለፅን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበውን የሂሣብ መግለጫ ሪፖርት እንዲያፀድቅ እንጠይቃለን፡፡

የአስተያየታችን መሠረት የኦዲት ስራችንን ያከናወንነው በዓለምአቀፍ የኦዲት መመዘኛዎች (አይ/ኤስ/ኤ) መሠረት ሲን በእነዚህ መመዘኛዎች ወስጥ የእኛ ኃላፊነት የኦዲተሮች ኃላፊነት በተሰኘው ሥር ይበልጥ ተብራርቷል። በተጨማሪም የኦዲት ስራችንን ስናከናውን የዓለምአቀፍ የስነምግባር መመዘኛዎች ቦርድ፥ የፕሮፊሸናል አካውንታቶች የስነምግባር ደንብ (አይ/ኢ/ኤስ/ቢ/ኤ ኮድ) እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የሂሳብ መግለጫዎችን ኦዲት ስለማድረግ አና ተያያዥ የኑ የስነምግባር መመዘኛዎችን፡ መሠረት አድርገን ከኩባንያው ገለልተኛነታችንን በመጠበቅ ስነምግባራዊ ኃላፊነቶቻችንን አሟልተናል። በኛ እምነት የሰበሰብናቸው የኦዲት ማስረጃዎች አስተያየታቻችንን ለመስጠት በሚስቸል ሁኔታ በቂ እና ተገቢ ናቸው።

ቁልፍ የኦዲት ጉዳዮች ቁልፍ የኦዲት ጉዳዮች የሚባሉት ለእኛ ሙያዊ ውሳኔ እንዲሁም ለሂሳብ መግለጫዎች ኦዲት እጅግ ዋጋ ያላቸው ጉዳዮች ሲኑእነዚህ ቁልፍ የኦዲት ጉዳዮች በአጠቃላይ ኦዲታቸን ውስጥ የተዳሰሱ እና አስተያየታችን በእነዚህ ላይ የተመሠረተ ቢኑምስለእነነዚህ ጉዳዮች የተለየ አስተያየት አላቀረብንም።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ውስጥ አዲስ የሚተገበሩ የዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት መመዘኛዎች አይ/ኤፍ/አር/ኤስ 9 ጨምሮ ተግብረዋል፡፡ ይህም የቀድሞ ዓመት ተነጻጸሪ ቁጥሮች እንዲሁም የመክፈቻ ቀሪ ሚዛን ላይ ተጽእኖ አለው። አዳዲሶቹ የፋይናንስ ሪፖርት መመዘኛዎች የሚፈጥሩትን ተጽእኖ በተገቢዉ መለየት እና የሒሳብ መዝገብ ዉስጥ በትክክል መካተታቸዉን መፈተሽ የዓመቱ የኦዲት ቁልፍ ጉዳዬች ኖ ተወስደዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የአዳዲስ ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት መመዘኛዎች ተጽእኖን ለማጣራት እና የቁልፍ እሳቤዎችን ትክክለኛነት ለመመዘን የባንኩን የትግበራ ሂደት ሰነዶች ተቀብለን በጥልቀት መርምረናል።

በሒሳብ መግለጫወዎቹ አዘገጃጀት የሥራ አመራሮች ኃላፊነት የባንኩ የሥራ አመራሮች ከዓለምአቀፍ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመዘኛዎች ቦርድ በተሰጠው የዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት መመዘኛዎች መሠረት የሒሳብ መግለጫዎችን የማዘጋጀት እና በትክክል የማቅረብ ሃላፊነት ያለባቸው ሲን ፥ ይህም በሥራ አመራሩ በሚዘረጋ የውስጥ ቁጥጥር የሂሳብ መግለጫዎቹ ከመጭበርበርም ነ ከስህተት የጠሩ መናቸውን ማረጋገጥን ይጨምራል፡፡

የሒሳብ መግለጫዎችን ዝግጀት በተመለከተ፥ ሥራ አመራሮች የኩባንያውን ቀጣይነት በመገምገም፣ የኩባንያው የሂሳብ መዛግብትም ይህንኑ ቀጣይነት በሚያሳይ መንገድ መዘጋጀታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.16

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

የሒሳብ መግለጫዎች ኦዲትን በሚመለከት የኦዲተር ኃላፊነት የእኛ ኃላፊነት የኩባንያውን የሒሳብ መግለጫ በአጠቃላይ በማጭበርበርም ነ በስህተት ከሚመጣ ከይዘት መዛባት የጸዳ ስለመኑ አሳማኝ ማረጋገጫ ማግኘት፤ እንዲሁም የእኛን አስተያየት ጨምሮ የኦዲተር ሪፖርት መስጠት ነው። በአይ/ኤስ/ኤዎች መሠረት የተሠራ ኦዲት ከፍተኛ የነ ማረጋገጫ ቢሰጥም መዛባቶችን ሁሌ ያገኛል ማለት አይደለም። መዛባቶች የሚከሰቱት በማጭበርበር ወይም በስህተት ሊን ይችላል።

የኦዲት ምርመራው በአይ/ኤ/ኤስ መሠረት ሲከናወን፥ በኦዲት ተግባሩ ውስጥ ሁሉ ሙያዊ ውሳኔዎችን እየተጠቀምን ሙያዊ ጥርጣሬዎችንም ተጠቅመናል። ደግሞም፡

• ከመጭበርበርም ነ ከስህተት የመጣ የገንዘብ ነክ መግለጫዎች መሠረታዊ መዛባት ስለመኖሩ አደጋዎችን ለይተንበመዳሰስ፣ ለእነዚህ አደጋዎች ምላሽ የሚን አካሔድ ቀርጸን ኦዲት ያደረግን ሲን፥ ለአስተያየታችን መሠረት የሚንተገቢ የነ መግለጫ የሚያስገኝ በቂ የነ የኦዲት ማስረጃ ነበረን። ማጭበርበር ሲፈጸም መመሳጠር፣ ማታለያ መጠቀም፣ን ብሎ ማጉደል፣ የተሳሳተ አመዘጋገብ ወይም የውስጥ ቁጥጥርን መጣስ ሊኖርበት የሚችል በመኑ፥ አደጋው ከስህተትይልቅ በማጭበርበር የሚከሰት የይዘት መዛባት ሳይታይ ሊታለፍ መቻሉ ነው።

• በሁኔታዎቹ ተገቢ የኑ ኦዲት አካሔዶችን ለመቅረጽ ሲባል ከኦዲቱ ጋር ተዛማጅ የኑ የውስጥ ቁጥጥር ግንዛቤ ያገኘንቢንም፥ ይህ ግን የኩባንያውን የውስጥ ቁጥጥር ውጤታማነት በሚመለከት አስተያየት ለማንጸባረቅ አይደለም።

• ጥቅም ላይ የዋሉን የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ፖሊሲዎች ተገቢነት እንዲሁም የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ግምቶች አሳማኝነትእና ተዛማጅ የኑ በሥራ አመራሮች የተሰጡ መግለጫዎችን መመዘን፤

• የንግድ ሥራውን ሒደት የሒሳብ መዝገብ አያያዝ አካል አድርጎ ሥራ አመራሩ መጠቀሙ ተገቢ ስለመኑ ፥ በቀረቡልንየኦዲት ማስረጃዎች ላይ፥ ከክስተቶቹ ወይም ሁኔታዎቹ ጋር ተያያዥ የነ መሠረታዊ የማይጠበቅ ነገር ኖሮ ቡድኑበቀጣይነት የንግድ ሥራውን እያከናወነ እንዳይቀጥል የማይታበል ጥርጣሬ ሊፈጥሩ የሚችሉ ስለመናቸው ድምዳሜላይ ለመድረስ ነው። መሠረታዊ የነ ያልተጠበቀ ነገር እንዳለ ከደመደምን፥ ለሚመለከተው የሒሳብ መግለጫ ይዘቶችበእኛ የኦዲተር ሪፖርት ውስጥ ትኩረት እዲደረግበት ማድረግ ወይም፥ ምናልባት ይህን መግለጫ መስጠት ብቻ የማይበቃቢን፥ አስተያየታችንን ማስተካከል ይጠበቅብናል። ወደፊት የሚያጋጥሙ ሁኔታዎች ወይም ክስተቶች ታሳቢ ሰይደረጉየእኛ ድምዳሜዎች መሠረታቸውን የሚያደርጉት የኦዲት ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ዕለት ድረስ በተገኙት የኦዲትማስረጃዎች ላይ ነው።

• የሒሳብ መግለጫዎቹን አቀራረብ፣ አወቃቀር እና ይዘት መገምገም፤ እና እነዚህ መግለጫዎች መሠረታዊ ግብይቶችን እናክስተቶችን የሚያሳዩ እና ትክክለኛ መግለጫዎች መናቸውን መመዘን፤

ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ፥ ኦዲቱን እና ጠቃሚ የኦዲት ግኝቶችን የታቀደ አድማስ እንዲሁም የጊዜ ሰሌዳ፣ ማናቸውንም በኦዲት ሥራችን ወቅት ያገኘናቸውን የጎሉ የውስጥ ቁጥጥር ጉድለቶችን ጨምሮ በሚመለከት የአመራር ኃላፊነት ላለባቸው እናሳውቃለን።

ደግሞም፥ ተዛማጅ የኑ ስለገለልተኝነት የተቀመጡ የስነምግባር ቅድመሁኔታዎችን በማጠናቀር ስናቀርብ፥ ሁሉንም በእኛ ገለልተኝት ላይ አሳማኝ የነ ሀሳቦችን የሚያስከትሉ ግንኙነቶችን እና ሌሎች ጉዳዮችን እንዲሁም አስፈላጊ ኖ ሲገኙ መከላከያወቻችንንም የማስተዳደር ኃላፊነት ላለባቸው አካላት እናሳውቃለን፤

የማስተዳደር ኃላፊነት ላለባቸው አካላት ከምናሳውቀው በተጨማሪ፥ እነዚህ ጉዳዮች የሒሳብ መግለጫዎቹ ኦዲት ውስጥ እጅግ ላቅ ያሉ የነባራዊው ወቅት ጉዳዮችን በመወሰን የኦዲቱ ጉዳይ ቁልፍ እናደርጋለን። እነዚህንም የኦዲት ሪፖርት ጉዳይ አድርገን ስንገልጽ፥ በሕጉ ወይም በመመሪያዎች እነዚህን ጉዳዮች ይፋ ማድረግ የሚከለከል እስካልነ ድረስ፥ በጣም አልፎ አልፎ በሚከሰቱ አጋጣሚዎች፥ እነዚህ ሪፖርቶች እንዲታወቁ መደረጋቸው ማሳወቁ ለህዝቡ ከሚያስገኘው ጥቅም የሚበልጥ የነ ከባድ የነ ጉዳት ያለው ከነ ሪፖርቶቹ መታወቅ የለባቸውም ብለን እንወስናለን።

ይህን ኦዲት በበላይነት የመራ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋ ታደሰ ነው።

ቲ. ኤ. ዋይ የተፈቀደላቸው የሒሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች

አዲስ አበባ ህዳር 10, 2012 ዓ.ም.

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 17

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

ብርሀን ባንክ አ.ማ የትርፍ ወይም ኪሳራ እና ሌሎች የተጣመሩ ገቢዎች መግለጫ እ.ኤ.አ በሰኔ 30 2019 ለተጠናቀቀው ዓመት

ማስታወሻ በሰኔ 30፣ 2019 ብር“000

በሰኔ 30፣ 2018 ብር“000

የወለድ ገቢ 8 1,535,806 1,112,786

የወለድ ወጪ 9 (605,036) (417,346)

የተጣራ የወለድ ገቢ 930,770 695,440

የክፍያ እና የኮሚሽን ገቢ 10 550,814 349,413

የክፍያ እና የኮሚሽን ወጪ 10 (7,565) (6,105)

የተጣራ የክፍያ እና የኮሚሽን ገቢ 543,249 343,308

ከሌሎች የአገልግሎት ክፍያ የተገኙ ገቢዎች 11 119,660 85,558

ጠቅላላ የተጣራ የእንቅስቃሴ (አገልግሎት) ገቢ 1,593,679 1,124,306

ለደንበኞች የተሰጡ አጠራጣሪ ብድሮች መጠባበቂያ ክፍያ 12 (61,334) (25,179)

ለሌሎች መጠባበቂያ ክፍያ 12 (5,493) (14,703)

የተጣራ የእንቅስቃሴ(አገልግሎት) ገቢ 1,526,852 1,084,424

የሠራተኞች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ክፍያዎች 13 (622,858) (438,751)

የንብረት እና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅንስናሽ 22 (32,610) (28,907)

የማይዳሰሱ ሐብቶች የእርጅና ቅንስናሽ 21 (1,390) (484)

ሌሎች የእንቅስቃሴ (አገልግሎት) ወጪዎች 14 (289,941) (205,348)

ጠቅላላ ወጪዎች (946,799) (673,490)

ትርፍ ከግብር በፊት 580,053 410,934

የገቢ ግብር በኃላ 15 (122,128) (83,088)

ትርፍ ከግብር በኋላ 457,924 327,846

ሌሎች የተጣመሩ ወጪዎች (Other Comprehensive Income) ከግብር በፊት ለሰራተኞች የአገልግሎት ጥቅም መጠባበቅያ ዳግም ልኬት (Defined benefit obligations)

26 (24,571) (16,726)

በአክሲዮን ኢንቨስትመንት ላይ የጥቅም ዕቅዶች የተገኙ ገቢዎች (ወጭዎች) ድጋሚ ልኬት (ከ. ግብር ውጭ) Gain/ Loss on revaluation of Equity investments

26 7,421 -

የዓመቱ ድምር የተጣመረ ገቢ፣ ከግብር በኋላ (Total comprehensive income for the year, net of tax)

440,775 311,120

የባለአክስዮኖች ድርሻ 457,924 327,846

የአንድ ባለ ብር 1000 አክስዮን የትርፍ ድርሻ (EPS) % 27 24.65 20.36

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.18

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

ብርሀን ባንክ አ.ማ የሀብትና ዕዳ መግለጫ እ.ኤ.አ በሰኔ 30 2019 ለተጠናቀቀው ዓመት

ማስታወሻ በሰኔ 30፣ 2019 ብር“000

በሰኔ 30፣ 2018 ብር“000”

ሐብቶች በባንክና በእጅ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ 16a 3,057,666 2,676,716 በሌሎች ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ አና ብድር 16b 71,050 44,104 የደንበኞች ብድር እና ቅድመ ክፍያ (የተጣራ) 17 10,033,356 7,067,044 የአክስዮን ኢንቨስትመንት 18 33,344 18,948 የብሔሪዊ ባንክ ቢል ኢንቨስትመንት 18 4,256,177 3,029,999 ሌሎች ሐብቶች 19 548,542 443,426 ኢንቬንቶሪዎች -(አላቂ እቃዎች) 19b 15,480 12,568 ለሽያጭ የተዘጋጀ የማይንቀሳቀስ ሐብት 19c 9,996 7,166 ኢንቨስትመንት ንብረት - ህንጻ 20 3,045 2,758 የማይዳሰሱ ሐብቶች 21 12,326 1,111 ቋሚ ንብረት እና መሣሪያ (የተጣራ) 22 365,819 215,914 የተገደበ ፈንድ (ለእንቅስቃሴ የተገደበ የገንዘብ ሚዛን) 18a 754,000 542,000 ወደፊት የሚሰበሰብ የትርፍ ግብር (Deffered tax Asset) 15c 11,754 6,224 ጠቅላላ ሐብት 19,172,555 14,067,978

ዕዳዎች ከሌሎች ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ አና ብድር 23a 16,854 27,323 የደንበኞች ተቀማጭ ሂሳብ 23b 14,964,280 10,861,680 የዚህ አመት ተከፋይ የገቢ ግብር 15b 140,070 68,219 ለሌተር ኦፍ ክሬዲት መከፈት ማርጅን 23b 569,464 314,518 ብድሮች 23b - - ለሎች ዕዳዎች 23c 527,475 492,088 ለወደፊት እዳ መጠባበቅያ (provision) 23d 89,095 58,624 ለስራተኞች የአልግሎት ጥቅም መጠባበቅያ (Defined benefit obligations) 23c 69,354 43,848 ወደ ፊት የሚከፈል የትርፍ ግብር (Deffered tax liability) 15c - - ጠቅላላ ዕዳ(ግዴታ) 16,376,592 11,866,300 የተጣራ ሐብት የተከፈለ አክሲዮን ካፒታል 24 2,000,000 1,709,050 ያልተከፈፈለ ትርፍ 25 397,591 208,132 ሕጋዊ መጠባበቂያ 26 422,871 308,309 ሌሎች መጠባበቂያዎች 27 (24,499) (23,894) ጠቅላላ የተጣራ ሐብት 2,795,963 2,201,678 ጠቅላላ የተጣራ ሐብት እና ዕዳ 19,172,555 14,067,978

የሂሳብ መግለጫዎቹ ጸድቀው በዳይሬክተሮች ቦርድ አማካይነት ህዳር 9, 2012 ዓ.ም. ተፈቅደው ፊርማ የተደረገባቸው፡

________________________ ________________________________ አቶ ጉማቸው ኩሴ አቶ አብረሀም አላሮ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ፕሬዝዳንት

አቶ አብርሃም አላሮ

ፕሬዝዳንት

አቶ ጉማቸው ኩሴ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም. 19

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

ብርሀን ባንክ አ.ማ

የባለአክሲዮኖች

ካፒታል

ለውጥ

መግለጫ፣

እ.

ኤ. አ

. በሰኔ

30፣

201

9 ለተጠናቀቀው

ዓመት

ማስታወሻ

የተከፈለ

የአክሲዮን

ካፒታል

ብር”

000

ያልተከፋፋለ

ትርፍ

ብር

“000

ሌላ መጠባበቂያ

ብር“

000

ሕጋዊ

መጠባበቂያ

ብር“

000

ድምር

ብር”

000

እ. ኤ

. አ በሐምሌ

1፣ 2

017

1,396

,123

214,

376

(1,70

6)

227,

469

1,836

,262

የዘመኑ ትርፍ

22

32

7,84

6 -

- 32

7,84

6 ሌላ የተጣመረ ገቢ

ለስራታኞች

የአገልግሎት

ጥቅም

መጠባበቅያ

ዳግም

ልኬት

የተገኘ

ገቢ

(ወጭ

) (R

e-m

easu

rem

ent g

ains

(lo

ss)

on d

efin

ed b

enef

it pl

ans

(net

of t

ax)

24

(22,

188)

-

(22,

188)

በአክሲዮን ኢንቨስትመንት

መጥባበቂያ

(m

ove

m e

nt in

FV

of e

quity

in

stru

men

ts )

ጠቅላላ የተጣመረ የዘመኑ ገቢ

32

7,84

6 32

7,84

6 የባለ አክስዮቹ

ሂሳብ

ተጨማሪ አክሲዮን

21

312,

927

- -

- 31

2,92

7 የተከፈለ/ለክፍያ የተዘጋጀ

ድርሻ

22

(2

61,4

64)

- -

(261

,464

) የግብር ማስተካከያ

22

8,29

5 ወደሕጋዊ

መጠባበቂያ

የተላለፈ

23

(80,

921)

80,9

21

ጠቅላላ

312,

927

(6,2

44)

(22,

188)

80

,921

36

5,41

6 እ.

ኤ. አ

በሰኔ

30፣

201

8 1,7

09,0

50

208,

133

(23,

894)

30

8,39

0 2,

201,6

78

የ አይ

ኣፍ

አር ኤስ የመነሻ

ባላንስ ማስትካከያ

54,14

8 54

,148

የተስተካከለ የመክፈቻ

ባላንስ ሐምሌ

1 20

18

25

1,709

,050

26

2,28

0 (2

3,89

4)

308,

390

2,25

5,82

5

የዘመኑ ትርፍ

25

45

7,92

4 45

7,92

4 ሌላ የተጣመረ ገቢ

ለስራታኞች

የአገልግሎት

ጥቅም

መጠባበቅያ

ዳግም

ልኬት

የተገኘ

ገቢ

(ወጭ

) (R

e-m

easu

rem

ent g

ains

(lo

ss)

on d

efin

ed b

enef

it pl

ans

(net

of t

ax)

27

(11,2

07)

(11,2

07)

በአክሲዮን ኢንቨስትመንት

መጠባበቂያ

(m

ovem

ent

in

FV

of e

quity

in

stru

men

ts )

27

10

,602

10

,602

ጠቅላላ የተጣመረ የዘመኑ ገቢ

45

7,92

4 (6

05)

457,

319

የባለ አክስዮኖቸ

ሂሳብ

ተጨማሪ አክሲዮን

24

290,

950

290,

950

የተከፈለ/ለክፍያ የተዘጋጀ

ድርሻ

25

(2

08,13

3)

(208

,133)

ወደሕጋዊ

መጠባበቂያ

የተላለፈ

26

(114,

481)

114,4

81

እ. ኤ

. አ በሰኔ

30፣

201

9 2,

000,

000

397,

591

(24,

499)

42

2,87

1 2,

795,

963

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ ሪፖርት 2011 ዓ.ም.20

ብርሃን ባንክ አ.ማ.ለተጠናቀቀው ዓመት በተዘጋጁት የባንኩ የሂሳብ መግልጫዎቸ ላይ የቀረበ የውጪ ኦዲተሮች አመለካከት

ብርሀን ባንክ አ.ማ የገንዘብ ፍሰት መግለጫ እ. ኤ. አ. በሰኔ 30፣ 2019 ለተጠናቀቀው ዓመት

ማስታወሻ በሰኔ 30፣ 2019 ብር“000

በሰኔ 30፣ 2018 ብር“000

ከሥራ እንቅስቃሴዎች የታየ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ትርፍ ከግብር በፊት 580,053 410,934 ማስተካከያ፡ ለተበላሸ ብድሮችን መጠባበቂያ ወጪ 12 61,334 25,179 ለተበላሸ ሌሎች ሀብቶች መጠባበቂያ ወጪ 14 5,493 14,192 የማይዳሰሱ ሐብቶች ተቀናሸ 21 1,390 484 ቋሚ ንብረት እና መሣሪያዎች ተቀናሽ 22 32,974 28,972 ለሽያጭ የተዘጋጀ የማይንቀሳቀስ ሐብት ተቀናሽ 19C (30) 320 ኢንቨስትመንት ንብረት - ህንጻ ዳግም ልኬት 20 (287) (196) ለኢንቬንቶሪ ተቀናሽ 32 (261) ከቋሚ ንብረት እና መሣሪያዎች ሽያጭ የተገኘ (137) (374)

ከሥራ እንቅስቃሴዎች የታየ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ከስራ ማስኬጃ ለውጥ በፊት 680,822 479,250

በብድርና ቅድመ ክፍዎች የአመቱ (ጭማሪ)/ቅናሽ 17a (3,024,329) (1,785,507) ለሽያጭ የተዘጋጀ የማይንቀሳቀስ ሐብት ተቀናሽ (ጭማሪ)/ቅናሽ 19c (2,800) 4,111 የሌሎች ሀብቶች (ጭማሪ)/ቅናሽ 19 (48,899) (167,317) የተገደበ ፈንድ (ጭማሪ)/ቅናሽ 16c (212,000) (166,000) የደንበኞች ተቀማጭ ጭማሪ/(ቅናሽ) 23b 4,102,600 3,191,572 ለሌተር ኦፍ ክሬዲት መከፈት ማርጅን ጭማሪ/(ቅናሽ) 23b 254,946 (53,893) ሌሎች ሀብቶች ጭማሪ/(ቅናሽ) 23c 34,949 109,874 ለኢንቨንተሪ ጭማሪ/(ቅናሽ) 19b (2,944) (3,745) በሌሎች ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ አና ብድር ጭማሪ/(ቅናሽ) 16b (26,946) 59,546 ለወደፊት እዳ መጠባበቅያ ጭማሪ/(ቅናሽ) (provision) 22d 30,471 10,770 ክሌሎች ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ አና ብድር (ጭማሪ)/ቅናሽ 23a (10,471) (2,144) ለስራተኞች የአልግሎት ጥቅም መጠባበቅያ (D efined benefit obligations) ጭማሪ/(ቅናሽ 23c 14,299 6,282 ከሥራ እንቅስቃሴዎች የተገኘ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ የሚሰበሰብ ግብር - - ለትርፍ ግብር የተከፈለ 15b (68,219) (122,793) ከሥራ እንቅስቃሴዎች የተገኘ የተጣራ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት 1,721,479 1,560,006

ከመዋዕለንዋይ ፍሰት እንቅስቃሴዎች የተገኘ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት የቋም ንብረቶች ግዢ 22 (183,755) (64,025) የማይዳሰሱ ንብራቶች ግዢ 21 (12,605) - የብሔሪዊ ባንክ ቢል ኢንቨስትመንት (ጭማሪ)ቅናሽ 18 (1,226,391) (824,334) ለኢንቨስትመንት ነክ ንብራቶች ግዢ 18 (1,530) (727) ከቋሚ ንብረት እና መሣሪያዎች ሽያጭ የተገኘ 1,013 1,053 ከመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እንቅስቃሴዎች የተገኘ የተጣራ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት (1,423,268) (888,033)

ከገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎች የተገኘ የገንዘብ ፍሰት የተሸጡ መደበኛ አክሲዮኖች 24 290,950 312,928 የተከፈፈሉ ድርሻዎች 25 (208,132) (261,464)

ከገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎች የተገኘ የተጣራ የገንዘብ ፍሰት 82,818 (23,536) በጥሬ ገንዘብ እና የጥሬ ገንዘብ እኩያዎች የታየ 381,029 648,436 በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የነበረ ጥሬ ገንዘብ እና የጥሬ ገንዘብ እኩያ 2,676,716 2,028,280 በዓመቱ ማብቂያ ላይ የታየ የጥሬ ገንዘብ ሚዛን 3,057,745 2,676,716