special issue # 48 june 2015 - midrocspecial issue # 48 june 2015 a bi-monthly publication of the...

12
1 Addis Ababa, Ethiopia Special Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO ወደ ገጽ 2 ዞሯል ዶ/ር አረጋ ይርዳው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ዓመታዊ የስፖርት በዓል በደማቅ ሥነሥርዓት ተጠናቀቀ ለ12ኛ ጊዜ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አዘጋጅነት ከጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች እና 10 በሆኑ ተጋባዥ የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እንዲሁም አንድ የመንግስት ተቋም መካከል ሲካሄድ የቆየው የወዳጅነት የስፖርት ውድድር ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በመቻሬ ሜዳ ተጠናቀቀ፡፡ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቪ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በዕለቱ በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለፁት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር ሠራተኛውም ሆነ የሠራተኛውን ቤተሰብ የበለጠ የሚያቀራርብ፣ ሠራተኛው ትርፍ ጊዜውን አእምሮውንና አካላዊ ብቃቱን የሚያዳብርበት፣ ለኩባንያው ያለውን ወገናዊነት የሚያሳይበት፣ ከሌሎች ኩባንያ ሠራተኞች ጋር ለመቀራረብና ለመተዋወቅ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ በየዓመቱ የምናካሂደው የስፖርት ውድድር ውጤታማ ነው ብለዋል። በመቀጠልም ሠራተኛው ውስጣዊ ብቃቱን የሚያሳይበት አጋጣሚም ስለሚሆን ለተሻለ ዕድልና ውጤት ራሱን የሚያበቃበት እንደሆነ ገልፀው በየዓመቱ ይህ የስፖርት ባህላችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞች የኩባንያዎቻቸውን ዓርማ በመያዝ በክብር እንግዶች ፊት በሠልፍ በማለፍ ላይ Special Issue # 48

Upload: others

Post on 22-Feb-2020

3 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

1Addis Ababa, Ethiopia

Special Issue # 48 June 2015

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

ዶ/ር አረጋ ይርዳው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ዓመታዊ የስፖርት በዓል በደማቅ ሥነሥርዓት ተጠናቀቀ

ለ12ኛ ጊዜ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አዘጋጅነት ከጥር 12

ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች

እና 10 በሆኑ ተጋባዥ የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እንዲሁም

አንድ የመንግስት ተቋም መካከል ሲካሄድ የቆየው የወዳጅነት የስፖርት

ውድድር ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በመቻሬ ሜዳ

ተጠናቀቀ፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቪ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው

በዕለቱ በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለፁት በየዓመቱ

የሚካሄደው ይህ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር ሠራተኛውም ሆነ

የሠራተኛውን ቤተሰብ የበለጠ የሚያቀራርብ፣ ሠራተኛው ትርፍ ጊዜውን

አእምሮውንና አካላዊ ብቃቱን የሚያዳብርበት፣ ለኩባንያው ያለውን

ወገናዊነት የሚያሳይበት፣ ከሌሎች ኩባንያ ሠራተኞች ጋር ለመቀራረብና

ለመተዋወቅ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ በየዓመቱ የምናካሂደው የስፖርት

ውድድር ውጤታማ ነው ብለዋል። በመቀጠልም ሠራተኛው ውስጣዊ

ብቃቱን የሚያሳይበት አጋጣሚም ስለሚሆን ለተሻለ ዕድልና ውጤት ራሱን

የሚያበቃበት እንደሆነ ገልፀው በየዓመቱ ይህ የስፖርት ባህላችን ተጠናክሮ

እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞች የኩባንያዎቻቸውን ዓርማ በመያዝ በክብር እንግዶች ፊት በሠልፍ በማለፍ ላይ

SpecialIssue # 48

Page 2: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

2

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የዘንድሮ የስፖርት ውድድር የተካሄደው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ

ግሩፕ ኩባንያዎች ውስጥ የሚገኙትን 21 ኩባንያዎች እንደ ሥራ

አካባቢያቸው ኩባንያዎች በራስ ውስጥ ከሚኖር ቁርኝት በበለጠ በተሸለ

ግንኙነት ከሌሎች ጋር የሚኖረውን መቀራረብ እንዲያዳብሩ ታስቦ

የተደረገ የቡድን አመሠራረት እንዲሆን ግንዛቤ ተወስዶ በአራት ምድብ

ተመድበዋል። እነሱም

ምድብ 1 - ቴክ ሣር ቤት

በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ እና በአካባቢው ያሉትን ኩባንያዎች

በማቀፍ የተዋቀረ ሲሆን እነሱም

1. ሚድሮክ ሲኢኦ ማኔጅመንት እና አመራር አገልግሎት ኃ.የተ.የግል

ማኀበር (MIDROC CEO)

2. ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማኀበር (MIDROC

GOLD)፣

3. ትረስት የሰው ኃይልና የጥበቃ አገልግሎት ኃ.የተ.የግል ማኀበር

(TRUST)፣

4. ሁዳ ሪል እስቴት ኃ.የተ.የግል ማኀበር (HUDA)፣

5. ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (TNA)፣

6. አዳጐ ሚድሮክ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (ADAGO)፣

7. አዲስ ሆም ዲፖ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (aHD)

8. ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የጉብኝት አገልግሎት ኃ.የተ.የግል

ማኀበር (RAINBOW)

9. ሚድሮክ ጂኢኦ ኤክስፕሎሬሽን ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግል ማኀበር

(MIDROC GEO) ተካተዋል፡፡

ምድብ 2 - ቴክ መገናኛ

በመገናኛ አካባቢ የሚገኙትን የቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎች የሚያካትት

ሲሆን፣

1. ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (ELFORA)

2. ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ኃ.የተ.የግል ማኀበር (Queen’s)

3. ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (DAT) እና

4. ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ (UNITY) በዚህ ምድብ ተመድበዋል

ምድብ 3 - ቴክ ሰሚት

በሰሚት አካባቢ የሚገኙትን ኩባንያዎች የሚያቅፍ ሲሆን፣

1. ሰሚት ፓርትነርስ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (SUMMIT)

2. ሰሚት ኢንጂኔርድ ፕላስቲክ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (SEPCo)

3. አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (aGP) እና

4. ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (WANZA)

ያካትታል፡፡

ምድብ 4 - ቴክ አቃቂ

በአቃቂ አካባቢ የሚገኙትን የቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎች በመያዝ

1. ኮምቦልቻ የብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማኀበር

(KOSPI)

2. ዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማኀበር (MBI)

3. ብሉናይል የፒፒና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ.የተ.የግል

ማኀበር (Blue Nile) እና

4. ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃ.የተ.የግል ማኀበር

(UAM) ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ከእነዚህ አራት ምድቦች በተጨማሪ ተጋባዥ አሥራ አንድ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እና አንድ የመንግሥት ተቋም

ተካፍለዋል እነሱም፡ -

1. ዳሽን ባንክ አ.ማ

2. ኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኀበር

3. አዲስ ኢንተርናሽናል ካተሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር

4. ናሽናል ሞተርስ ኮርፖሬሽን አክስዮን ማኀበር

5. ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማኀበር

6. ሜፖ ኮንስትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር

7. ፖልሪስ እና ልጆቹ ሊሚትድ

8. የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዲስትሪ አክስዮን ማኀበር - ንፋስ ስልክ

ፋብሪካ

9. ሆራይዘን አዲስ ጎማ አክስዮን ማህበር

10. ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማኀበር

11. ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቅርንጫፍ (መንግሥታዊ

ተቋም)

ባለፉት 6 ወራት ከፍተኛ ፉክክር የነበረበት ውድድር በማድረግ በዚሁ ቀን

ለዋንጫ የደረሱት ሞሐ ለስላሣ መጠጥ ኢንዱስትሪ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ

እና ቴክ ሣር ቤት ቡድኖች ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች

መደበኛ የጨዋታ ጊዜያቸውን 0 ለ 0 በመለያየታቸው ተጨማሪ አምስት

አምስት ሪጎሬ በተሰጣቸው መሠረት የሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ 5-4

በሆነ ውጤት ቴክ ሣር ቤትን በማሸነፉ የ2007 ዓ.ም. የእግር ኳስ ጨዋታ

ውድድር አሸናፊ በመሆን ዋንጫ አንስቷል፡፡

በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ውድድሮች ሲካሄዱ የቆየ ሲሆን በዕለቱ

የተካሄዱት የሩጫ፣ የገመድ ጉተታና የመሳሰሉት ስፖርቶች በነበረው

ፉክክር ተመልካቹ በከፍተኛ ሁኔታ ደስታውን ገልጿል፡፡

በበዓሉ መዝጊያ ወቅት

• የሴትና የወንድ ሠራተኞች 3.5 ኪሎ ሜትር የረዥም የጎዳና ላይ

ሩጫ

• በወንዶችና በሴቶች የገመድ ጉተታ፣

• የወንዶች 100 ሜትር፣ የ200 ሜትር እና የ400 ሜትር፣

• 50X2 የሴቶች ሪሌ፣

• የሴቶች የዕንቁላል በማንኪያ ውድድር፣

• ዕድሜያቸው ከ8-10 የሚሆኑ የሠራተኞች ወንድ እና ሴት ልጆች

ውድድሮች፣ እና

• ከቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ውስጥ የማርኬቲንግ ክፍል የሥራ

ኃላፊዎች ተሣታፊ የሆኑት የገንቦ ሰበራ ውድድሮች የተካሄዱ

ሲሆን፣ አሸናፊዎች የተዘጋጀላቸውን ሜዳልያ ሠርተፍኬትና

የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዓመቱ ፕሮግራም ላይ በእግር ኳስ ውድድር 210፣ መረብ ኳስ 96፣

ገመድ ጉተታ 50 በቤት ውስጥ ውድድር 16፣ በሜዳ ቴንስ 16፣ በሩጫ

48፣ በ50x 2 ዱላ ቅብብል16፣ በዕንቁላል ሰበራ 8፣ በታላቁ ሩጫ 120

በጠቅላላ 610 ስፓርተኞች በሁለቱም ፆታ የተሳተፉ ሲሆን በዳኝነት 30

የሚሆኑ ባለሙያዎች ተካፍለዋል፡፡ በተጨማሪም ጉልህ ድርሻ ላበረከቱ፣

ምድባቸውን ላስተባበሩና ለኮሚቴ አባላት ሠርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡

Page 3: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

3

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የእግር ኳስ ውድድር አሸናፊ የሆነው የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ የእግር ኳስ ቡድን የዋንጫ ሽልማት ከዶ/ር አረጋ ይርዳው

ሲቀበል

አጠቃላይ የስፖርት ውድድሮች አሸናፊ የሆነው የቴክ አቃቂ ቡድን በሊቀመንበራችን ሥም የተሰየመውን ዋንጫ ከዶ/ር አረጋ ይርዳው እጅ ሲቀበል

በዚህ መሠረት 1ኛ ለወጣው ለሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ ንፋስ ስልክ

ቅርንጫፍ የእግር ኳስ ቡድን ዋጫ እና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት

ሺህ)፣ 2ኛ ለወጣው ቴክ ሣር ቤት ቡድን ብር 15,000.00 (አሥራ አምስት

ሺህ)፣ 3ኛ ለወጣው የእግር ኳስ ቡድን ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ)፣

በዓመቱ ውድድር የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ለሆነው ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ

ቡድን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ)፣ እንዲሁም ፀባዩን ማሻሻል አለበት

ለተባለው ሜፖ ኮንስትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስ የእግር ኳስ

ቡድን ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ)፣ በአጠቃላይ ለልዩ ልዩ ውደድሮች

አሸናፊ ለሆኑት የግል እና የቡድን ተወዳዳሪዎች ብር 150,000.00 (አንድ

መቶ ሃምሣ ሺ) ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ በተጨማሪ በሜድሮክ ኢትዮጵያ

ቴክኖሎጂ ግሩፕ ታላቅ ሩጫ ለተሳተፉ ሯጮች በቂ ልምድ ሳይኖራቸው

3.5 ኪ.ሜ ሮጠው በብቃት በመወጣታቸው በሩጫው ውድድር ላይ ተሳታፊ

ለነበሩት በሙሉ የብር 60,000 (ስልሣ ሺህ) ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር በግራ በኩል አቶ ጌታቸው ቢርቦ የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኩባንያ ሲኢኦ እና በቀኝ በኩል አቶ አስፋው ዓለሙ የዳሽን ባንክ ፕሬዚዳንት ፕሮግራሙን በመከታተል ላይ

በዚህ ልዩና ደማቅ በሆነው የስፖርት በዓል መዝጊያ ፕሮግራም ላይ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች፣ ተጋባዥ የሆኑት

የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ

የማኔጅመንት አባላት፣ ሠራተኞች፣ ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ከእህትና ተባባሪ ኩባንያዎች አቶ ጌታቸው ቢርቦ

የሞሐ ለስላሳ መጠጥና ኢንዱስትሪ ኩባንያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣

አቶ አስፋው ዓለሙ የዳሽን ባንክ ፕሬዚዳንትና አቶ ጣሂር መሐመድ

ፖልሪስ እና ልጆቹ ሊሚትድ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተገኙ ሲሆን ይህ

ዓመታዊ የስፖርት በዓል በዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ

ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር የመዝጊያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ተጠቃሏል፡፡

Page 4: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

4

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የውድድሩና የሥነ-ሥርዓቱ ገፅታ በከፊል

መቻሬ ሜዳ ቅጥር ግቢ ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጅ ግሩፕ ኩባንያ አመራር አባላት

የፕሮግራም ትውውቅ

ሠልፈኞች በታዳሚዎች ፊት በማለፍ ላይ

ተጋባዥ ተቋማት በሥነ-ሥርዓት ላይ

ስፖርተኞች በሠልፍ በማለፍ ላይ

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለታዳሚው ንግግር ሲያደርጉ

Page 5: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

5

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የሚ.ኢ.ቴ.ግሩፕ የ3.5 ኪ.ሜ ታላቁ ሩጫ አጀማመር ታላቁ ሩጫ ውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት ነበር

አቶ ጌታቸው ሐጎስ ለአቶ ሠለሞን ደጀኔ (የትረስት ዋና ሥራ አስኪያጅ) የኩባንያቸውን የተሣትፎ ምስክር ወረቀት ሲሰጡ

አቶ አለማየሁ ታከለ የሚድሮክ ወርቅ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

እንግዶች ውድድሩን በአፅንኦት በመከታተል ላይ

አቶ ይድነቃቸው መኮንን የኤም.ቢ.አይ ዋ/ሥ/አስኪያጅ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

አቶ ሚካኤል ምትኩ የአዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ኩባንያ ዋ/ሥ/አስኪያጅ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

አቶ ዳንኤል ተፈራ የአዳጐ ሚድሮክ ዋ/ሥ/አስኪያጅ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

Page 6: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

6

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የዳሽን ባንክ ፕሬዚዳንት ከአቶ ከተማ አሰፋ /ፒኦኦ/ የኩባንያቸውን የተሣትፎ ምሥክር ወረቀት ሲቀበሉ

የአንድ መቶ ሜትር ፈጣን ሩጫ ውድድር ሲደረግ

ለውድድሩ የተዘጋጁ ሜዳልያና ዋንጫዎች

ዶ/ር አረጋ ይርዳው የበዓሉን መዝጊያ ምክንያት በማድረግ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ

በመቻሬ ሜዳ ታዳሚው ስፖርቱን ሲከታተል

ህፃናት በተዘጋጀላቸው ቦታ ሲጫወቱ የቴክ ሣር ቤት የሴቶች ገመድ ጉተታ ቡድን /እልህ አስጨራሽ/

የሞሐ ለስላሣ መጠጥ ኢንዱስትሪ /ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ/ ስፖርተኞች ከዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር የተነሱት ፎቶግራፍ

Page 7: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

7

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የቴክ አቃቂ የሴቶች ገመድ ጉተታ ቡድን /አይበገሬነት/ የቴክ አቃቂ የወንዶች የገመድ ጉተታ ቡድን

ከተመልካቹ በከፊል

የማርኬቲንግ የሥራ ኃላፊዎች የገንቦ ሰበራ ውድድር ሲካሄድ

ከአቶ አስፋው ዓለሙ የዳሽን ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትዕግሥት ገብሩ የኮሚቴ አባልነት ተሣትፎ ወረቀት ሲቀበሉ

አቶ ኃይለየሱስ የኮሚቴ አባልነት የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

የክብር እንግዶች ውድድሩን ሲከታተሉ

Page 8: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

8

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

ወ/ሮ ዳርምየለሽ በየነ ቴክ ሣር ቤት ሜዳልያ ሲቀበሉ ህፃናቱ የውድድሩ ተሸላሚ ነበሩ

ህፃናቱ ማበረታቻ ሲበረከትላቸው

ቴክ አቃቂ ቡድን - አለሙ መላሻ ታላቁ ሩጫ ቴክ መገናኛ ቡድን ንግስቲ በታላቁ ሩጫ አሸናፊ

ቴክ ሣሚት ቡድን እመቤት ካብትይመር የበርካታ ሜዳሊያ ባለቤት ቴክ ሣር ቤት አቶ ለገሠ ተ/ማርያም በሜዳ ቴኒስ ጨዋታ ተሣትፎ ምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

ቴክ አቃቂ ቡድን ሃና ታፈሰ 50x2 ሩጫ አሸናፊ

Page 9: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

9

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

የ2007 ዓ.ም የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 12ኛ ዓመት የስፖርት ውድድር ፕሮግራም ውጤት

I. እግር ኳስ

የዓመቱ የእግር ኳስ ተወዳዳሪ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ኩባንያዎችና አንድ የመንግስት ተቋም

ምድብ “ሀ” ምድብ “ለ” ምድብ “ሐ” ምድብ “መ”

አዲስ ካተሪንግ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ኒያላ ኢንሹራንስ ዳሽን ባንክ

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ፖልሪዬስ እና ልጆቹ ሜፖ ኮንስትራክቲንግ ኢትዮ ሌዘር

ኢትዮ ቴሌ ኮም ናሽናል ሞተርስ ሞሐ ለስላሳ ቴክ ሰሚት

ቴክ ሣር ቤት ቴክ አቃቂ ቴክ መገናኛ

ለጥሎ ማለፍ የደረሱ ለፍፃሜ የደረሱ ለደረጃ ጨዋታ የደረሱ ለዋንጫ ጨዋታ የደረሱ

ሆራይዘን አዲስ ጎማ (ምድብ ሀ) ዳሽን ባንክ (ምድብ መ) ቴክ ሣር ቤት ከቴክ መገናኛ ቴክ ሣር ቤት ከሞሐ ለስላስ

ቴክ ሣር ቤት (ምድብ ሀ) ሞሐ ለስላሳ (ምድብ ሐ) ዳሽን ባንክ ከሞሐ ለስላሳ

ቴክ አቃቂ (ምድብ ለ) ቴክ መገናኛ (ምድብ ሐ)

ፖልሪየስ (ምድብ ለ) ቴክ ሣር ቤት (ምድብ ሀ)

ቴክ መገናኛ (ምድብ ሐ)

ሞሐ ለስላሳ (ምድብ ሐ)

ኢትዮ ሌዘር (ምድብ መ)

ዳሽን ባንክ (ምድብ መ)

በአጠቃላይ፤ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የ2007 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድር የዋንጫ አሸናፊ የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ

አክስዮን ማህበር ሲሆን፣ የ2007 ዓ.ም የጥሩ ስፖርታዊ ሥነ-ምግባር እና የጠባይ የዋንጫና ብር ተሸላሚ ኢትዮ ሌዘር ኩባንያ ሆነዋል።

በዓመቱ የእግር ኳስ ውድድር የስፖርታዊ ሥነ ምግባር በማጓደል (የፀባይ ጉድለት በማሳየት) የሜፖ ኮንስትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስ

ኃ.የተ.የግ.ማህበር ተሸላሚ ሆኖ የዓመቱ የስፖርት ውድድር ተጠናቋል።

የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ኢትዮ ሌዘር ኩባንያ /ELICO/ ቴክ ሣር ቤት የእግር ኳስ ውድድር ሁለተኛ በመውጣቱ የቡድኑን ሜዳልያ አምበል - አጂክማን አላሚን ሲቀበል

በዳኝነት አገልግሎት ሲያበረክቱ ከነበሩት ዳኞች መካከል አቶ ዳዊት አሰፋ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ

ዶ/ር አረጋ ይርዳው የመዝጊያ ንግግር ሲያደርጉ

Page 10: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

10

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

I I. መረብ ኳስ

1. የወንዶች መረብ ኳስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ

ቴክ መገናኛ 6 6 - 1ኛ

ቴክ አቃቂ 6 4 2 2ኛ

ቴክ ሰሚት 6 2 4 3ኛ

ቴክ ሣር ቤት 6 0 6 4ኛ

2. የሴቶች መረብ ኳስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ

ቴክ አቃቂ 6 6 - 1ኛ

ቴክ ሣር ቤት 6 4 2 2ኛ

ቴክ ሰሚት 6 2 4 3ኛ

ቴክ መገናኛ 6 0 6 4ኛ

I I I. ገመድ ጉተታ

1. የወንዶች ገመድ ጉተታ ውጤት

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ

ቴክ አቃቂ 4 4 - 1ኛ

ቴክ ሰሚት 4 3 1 2ኛ

ቴክ መገናኛ 3 2 2 3ኛ

ቴክ ሣር ቤት 3 0 4 4ኛ

2. የሴቶች ገመድ ጉተታ ውጤት

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ

ቴክ አቃቂ 4 4 - 1ኛ

ቴክ ሣር ቤት 4 3 1 2ኛ

ቴክ መገናኛ 3 2 2 3ኛ

ቴክ ሰሚት 3 1 2 4ኛ

IV. የሜዳ ቴኒስ

1. የወንዶች ሜዳ ቴኒስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ ሰሚት 6 6 - 1ኛ አቶ ታዮ ተስፋዬ /ዋንዛ/

ቴክ አቃቂ 6 3 3 2ኛ አቶ ዘውዱ ዑመር /ብሉ ናይል/

ቴክ ሣር ቤት 6 2 4 3ኛ አቶ ለገሠ ተ/ማርያም

ቴክ መገናኛ 6 0 0 4ኛ አቶ ወንደሰን ኢሳያስ /ኤልፎራ/

2. የሴቶች ሜዳ ቴኒስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ አቃቂ 6 6 - 1ኛ ወ/ሮ እመቤት ካብቴመር /ብሉ ናይል/

ቴክ ሣር ቤት 6 4 2 2ኛ ወ/ሪት ስመኝ መስፍን /ሲ.ኢ.ኦ/

ቴክ ሰሚት 6 3 3 3ኛ ወ/ሪት ሣምራዊት ፈይሣ /ሰሚት ፓርትነርስ/

ቴክ መገናኛ - - - 4ኛ ለውድድሩ የተካፈለ የለም

V. ጠረጴዛ ቴኒስ1. የወንዶች ጠረጴዛ ቴኒስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ አቃቂ 6 5 1 1ኛ አቶ ግርማ ቸርነት /ኤም.ቢ.አይ/

ቴክ ሣር ቤት 6 4 2 2ኛ አቶ ተስፋዬ እንዳለ /ሚድሮክ ወርቅ/

ቴክ ሰሚት 6 2 4 3ኛ አቶ አለማየሁ በላይ /ሰሚት ፓርትነርስ/

ቴክ መገናኛ 6 1 5 4ኛ አቶ ወንድወሰን ኢሳያስ /ኤልፎራ/

Page 11: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

11

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

2. የሴቶች ጠረጴዛ ቴኒስ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ ሣር ቤት 6 5 1 1ኛ ወ/ሮ ሃና አየለ /ሲ.ኢ.ኦ/

ቴክ ሰሚት 6 4 2 2ኛ ወ/ሪት ሣምራዊ ፈይሣ /ሰሚት ፖርትነርስ/

ቴክ አቃቂ 6 3 3 3ኛ ወ/ሮ እመቤት ካብቴመር /ብሉ ናይል/

ቴክ መገናኛ 6 - 6 4ኛ ወ/ሪት አበባ ክንዴ /ኤልፎራ/

VI. ዳርት

1. የወንዶች ዳርት የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ ሰሚት 6 5 1 1ኛ አቶ ዮሴፍ በቀለ /ስሴፕኮ/

ቴክ አቃቂ 6 4 2 2ኛ አቶ መስፍን አበበ /ዩ.ኤ.ኤም/

ቴክ ሣር ቤት 6 2 4 3ኛ አቶ እስከአጥናፍ መዝገቤ /ሲ.ኢ.ኦ/

ቴክ መገናኛ 6 1 5 4ኛ አቶ አዲሱ ደንቦባ /ኤልፎራ/

VII. ቼዝ

1. የወንዶች ቼዝ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ አቃቂ 6 5 1 1ኛ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ /ብሉ ናይል/

ቴክ ሰሚት 6 4 2 2ኛ አቶ የሺጌታ ከበደ /ስኤፕኮ/

ቴክ ሣር ቤት 6 2 4 3ኛ አቶ ያሬድ ታዬ /ሲ.ኢ.ኦ/

ቴክ መገናኛ 6 - 6 4ኛ ተወዳዳሪ ተጫዋች አላቀረቡም

2. የሴቶች ቼዝ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ ሣር ቤት 6 5 1 1ኛ ወ/ሪት ሠላማዊት አሠፋ /ሁዳ/

ቴክ አቃቂ 6 4 2 2ኛ ወ/ሮ ገነት ድንቁ /ብሉ ናይል/

ቴክ ሰሚት - - - 3ኛ በውድድሩ አልተካፈሉም

ቴክ መገናኛ - - - 4ኛ በውድድሩ አልተካፈሉም

VIII. ዳማ

1. የወንዶች ዳማ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ አቃቂ 6 5 1 1ኛ አቶ ወንዲፍራው አድማሱ /ትረስት/

ቴክ ሰሚት 6 4 2 2ኛ አቶ እሸቱ በቀለ /ዩ.ኤ.ኤም/

ቴክ ሣር ቤት 6 3 3 3ኛ አቶ ጌታሁን አደራ /ሰሚት ፓርትነርስ/

ቴክ መገናኛ 6 1 5 4ኛ አቶ አዲሱ ደቦባ /ኤልፎራ/

2. የሴቶች ዳማ የተወዳደሩ

ተወዳዳሪ የጨዋታ ብዛት አሸነፈ ተሸነፈ ደረጃ የተጫዋች ሠራተኛ ስም

ቴክ አቃቂ 6 6 - 1ኛ ወ/ሮ ገነት ድንቁ /ብሉ ናይል/

ቴክ ሰሚት 6 3 3 2ኛ ወ/ሮ ነፃነት በላይ /ሰሚት ፓርትነርስ/

ቴክ ሣር ቤት 6 2 4 3ኛ ወ/ሪት መሠንበት ፍቃዱ /ቲ.ኤን.ኤ/

ቴክ መገናኛ 6 - 6 4ኛ ተወዳዳሪ ባለማቅረብ

Page 12: Special Issue # 48 June 2015 - MIDROCSpecial Issue # 48 June 2015 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office O f the chei f executvi e Officer This Newsletter provides customers, employees,

12

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 48 June 2015

Addis Ababa, Ethiopia

ዶ/ር አረጋ ይርዳውDr. Arega Yirdaw

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያChief Executive Officer, MIDROC Ethiopia

u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: MIDROC Ethiopia Technology GroupOffice of the Chief Executive Officer, Fax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

ስፖርት ከሰው ልጆች ሥልጣኔና ዕድገት ጋር ተያይዞ የመጣና አገራት

በአሁኑ ጊዜ ለሠላም እና ለመልካም የወዳጅነት ግንኙነት ማጠናከሪያ

እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ በእኛም አገር በርካታ የስፖርት ዓይነቶች

ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው እስከ ብሔራዊና ፕሪሚየር ሊግ በሚካሄዱ

ውድድሮች ወጣቶች ደማቅ የስፖርት ግጥሚያዎችን ያደርጋሉ፡፡

በነዚህም የስፖርት ውድድሮች የስፖርቱ አድናቂዎች የሚፈልጉትን

የስፖርት ውድድሮች በመከታተል እንዲደሰቱ እና የእረፍት ጊዜያቸውን

በመዝናናት እንዲያሳልፉ ረድቷቸዋል፡፡

ይህ ሁኔታ የአቅሙና የይዘቱ ጉዳይ ይለያይ እንጂ በመንግሥታዊም

ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አዘጋጅነት የተለያዩ የስፖርት

ውድድሮች በተቋሞች መካሄዱ የህብረተሰቡን የስፖርት ፍላጎት

ከማነሣሣቱም በላይ ወጣቶች/ሠራተኞች አካላዊና አእምሮአዊ

ብቃታቸውን እንዲያዳብሩ እድል ይሰጣል፡፡

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክሎጂ ግሩፕ የተደራጀው ዓመታዊ የስፖርት

ውድድርም የዚሁ አካል ሲሆን በግሩፑ ሥር ያሉት ሀያ አንድ

ኩባንያዎች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ሊወዳደሩ የሚችሉበት፣ እርስ

በእርስ የሚተዋወቁበትና የሚግባቡበት፣ የአካል ብቃት ማዳበሪያ፣

የቤተሰብነት ማጠናከሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ በመሆኑ ሁሉም

ሠራተኞች ይህንን አቅጣጫ በመከተል ተግባራዊ እያደረጉት ይገኛሉ፡፡

ዓመቱን በሙሉ የውድድሩ ተካፋይ የሆኑ የኩባንያዎቻችን ሠራተኞች

እና ቤተሰቦች በእረፍት ቀናቸው (እሁድ) የስፖርት ውድድሮች

በሚካሄድበት በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኮርፖሬት

ሴንተር በሆነው መቻሬ ሜዳ በመገኘት በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች

በመሣተፍ እና ታዳሚ በመሆን ከፍተኛ ድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡

በ2007 ዓ.ም የተደረገው የስፖርት ውድድርም ቀደም ሲል የነበረውን

አደረጃጀት በመለወጥ እያንዳንዱ ኩባንያ የሚያደርገውን ውድድር

ከሌሎች አቻ ኩባንያዎች ጋር እንደሥራ አካባቢያቸው ተደራጅተው

እንዲቀርቡ በማድረግ ነበር፡፡ ይህን በምሣሌ ስንገልፀው በምድብ አንድ

ቴክ አቃቂ (ኮስፒ፣ ኤም.ቢ.አይ፣ ብሉ ናይ እና ዩ.ኤ.ኤም)፣ በምድብ

ሁለት ቴክ ሣር ቤት በመቻሬ ሜዳ ግቢ የሚገኙት (ሚድሮክ ሲኢኦ፣

ሚድሮክ ወርቅ፣ ቲ ኤን ኤ፣ ሁዳ ሪል እስቴት፣ ትረስት፣ ሬይንቦ፣

ሆም ዲፖ፣ ሚድሮክ አዳጎ) ሲሆኑ በምድብ ሦስት ቴክ መገናኛ

(ኤልፎራ፣ ኩዊንስ፣ ዩኒቲና ዴይ ላይት) ታቅፈዋል በምድብ አራት

ቴክ ሰሚት (አዲስ ጋዝ፣ ዋንዛ፣ ሴፕኮ፣ ሰሚት ፓርትነርስ) በመመደብ

እጅግ ደማቅ ውድድር የተካሄደ ሲሆን በእግር ኳስ ዘርፍ ከቴክኖሎጂ

ግሩፑ ውጭ የሚገኙት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕና ተባባሪ የሆኑት

10 ኩባንያዎችና አንድ የመንግሥት ተቋም (የኢትዮ ቴሌ ኮም ደቡብ

ምዕራፍ ቅርንጫፍ) ተሣትፈዋል። ሁሉም ተሳታፊዎች በዲሲፕሊን

ውድድራቸውን በማድረግ ላሳዩት ወደር የሌለው ስኬት ሊመሰገኑ

ይገባል፡፡ በአራት ቡድን የተከፈሉት 21 ኩባንያዎች ከቴክኖሎጂ ግሩፑ

ውጭ ተሣታፊ የነበሩት 11 ድርጅቶችን በመጨመር በድምራቸው 32

ድርጅቶች እሁድ እሁድ በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች እንዲሣተፉ

ሲደረግ 610 የሚሆኑ ሠራተኞች በተናጠልና በቡድን በልዩ ልዩ

የስፖርት ውድድሮች ላይ ተሣትፈዋል።

ይህም ሠራተኞች ትርፍ ጊዜያቸውን በመዝናኛ ሥፍራ ሲያሣልፉ

እንደከረሙ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስፖርት ለወዳጅነት እና ለጤንነት

ጠቃሚ ነው ካልን በመቻሬ ሜዳ የተካሄዱት የስፖርት ውድድሮች ምን

ያህል ውጤታማ እንደሆነ ሁሉም የሚገነዘበው ይመስለናል፡፡

በመቻሬ ሜዳ የሚደረጉት የስፖርት ውድድሮች ዓላማው የእርስ በእርስ

ግንኙነትን ለማጠናከር፣ የሠራተኛውን ሞራልና ጥንካሬ ለመጠበቅ፣

ሠራተኞች ለኩባንያቸው ያላቸውን ፍቅርና ቅርበት ለማዳበር በመሆኑ

ዋንጫ ወይም ልዩ ልዩ ሽልማት ለመሰብሰብ በሚል የሚመጣ

ፉክክር የለም፡፡ እንደ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አስተሳሰብ ሁሉም አሸናፊ

ናቸው ምክንያቱም ዓላማው ዋንጫና ሽልማት ለማግኘት ሳይሆን

በተሣትፎአቸው ሁሉም የሚደነቁና የሚመሰገኑ በመሆናቸው ነው፡፡

እነዚህ ውድድሮች በሥርዓትና በህግ ስለሚካሄዱ የሥነ-ምግባር

ግድፈት አይታይም። ይህም የዓላማችንን ታላቅነት የሚያጎላና

በራሳችን ስርዓት፣ ደንብ፣ አስተዳደር፣ ዳኝነት፣ ሽልማቶች በማዘጋጀት

ስለምንመራው አጓጊና ሣቢ ነው፡፡ የስፖርት በዓሉ መዝጊያን በተመለከተ

ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች ማጠናቀቂያ የተደረጉ ሲሆን የሚድሮክ

ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የጎዳና ላይ ሩጫ የ3.5 ኪ.ሜ በሴትም

ሆነ በወንድ የተደረገው ውድድር ምን ያህል ጠንካራ ሠራተኞች

በኩባንያዎቻችን ውስጥ መኖራቸውን ለማየት ችለናል፡፡ የሠራተኛው

ቤተሰብ ህፃናት በተዘጋጀላቸው ቦታ ሲጫወቱና ሲዝናኑ በሴትም ሆነ

በወንድ የተደረጉት ልዩ ልዩ ውድድሮች በሙሉ እጅግ አዝናኝና አጓጊ

በመሆን ተጠናቋል። በአጠቃላይ በኩባንያችን ውስጥ እንደ ባህል ይዘነው

የመጣነው የስፖርት ውድድር በሠራተኞቻችን ፍላጎት ላይ ተመስርቶ

በናፍቆት የሚጠበቅ በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥልበታለን፡፡

በመጨረሻም በስፖርት ዝግጅቱ በተወዳዳሪነት፣ በደጋፊነት፣ በአዘጋጅነት

ለተሣተፋችሁት በሙሉ ምሥጋናዬን እያቀረብኩ እያንዳንዱ ሠራተኛ

የእረፍት ጊዜውን ከሥራ አጋሮቹ ጋር በመገናኘት እና በመቀራረብ

በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች ተሣታፊ በመሆን በቀጣዩ ዓመት

በምናደርገው የስፖርት ውድድሮች ንቁ ተሣታፊ እንደምትሆኑ እምነቴ

ነው፡፡