news paper no. 54 colour.indd

16
Fñt Fñt www.andinet.org h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54 êUWÝ( 6 BR yx!T×ùà ?ZB yl#›§êE |LÈn# Ælb@T XNÄ!çN XN¬gL! Fñt nÉnT ¥Ks® Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ n/s@ 1 qN 2004 ›.M. 1 qN 2004 ›.M. እንደምትደርስ የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡ አክለውም /ቤቱ የሐምሌ 13 እትም ሙሉ ዘገባዎች እንዲወረሱ መደረጉ አግባብ እንዳልሆነና ይወረሱ ቢባሉ እንኳ ለደህንነት ስጋት ናቸው የተባሉት ዘገባዎች ብቻ መሆን ሲኖርበት፣ የኪነ ጥበብ ዘገባዎች፣ በእውቀቱ ስዩም የለንደን ኦሎምፒክ ምልከታዎችና ሌሎም የገፅ ፅሁፎችና ዘገባዎች መልሰን እንዳንጠቀም መደረጉም ቅር አሰኝቶኛል ሲሉ ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል፡፡ ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ተወካይ ከፍተኛ አመራሮች የተከበሩ /ነጋሶ ጊዳዳ፣የተከበሩአቶ ግርማ ሰይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ትናንት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004.. ከሰዓት በኋላ በድንገት ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደረገ፡፡ እየተንገዳገደ ያለውን የኢህአዴግ መንግሥት እንዴት መተካት ይቻላል? አሁንም እንጮሃለን ! ሕዝቡ ማን እንደሚመራው በግልጽ ማወቅ አለበት ኢህአዴግ የህዝብ አመኔታ ያጣ መንግስት ስለሆነ ሥልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል 6 11 4 ወደ ገፅ 11 ይዞራል.... ወደ ገፅ 13 ይዞራል.... ከወቅታዊው የሙስሊሞች ተቃውሞ ተቃዋሚዎች ምን ይማሩ ? 2 ክቡር / ነጋሶ ጊዳዳ ባለፈው ቅዳሜ ለነምርቃት የበቃው የርዕዮት አለሙ መፅሀፍ ከአዟሪዎች እጅ በፖሊሶች እየተነጠቀ መሆኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተሰማሩ መፅሀፍ አዟሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ በተለይ በላናቻና በቦሌ አካባቢ የመፅሀፍ የሚሸጡ ግለሰቦች እንደተናገሩት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004 .ፖሊሶች የርዕዮትን መፅሀፍ ለይተው በመንጠቅ አባረዋቸዋል፡፡ ሽብርተኝነትተከሳ በሦስት ክሶች ጥፋተኛ ከተባለች በኋላ 14 ዓመት እስራትና 33 ሺህ ብር ቅጣት የተፈረደባት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ በጠየቀቺው ይግባኝ ጥፋተኛ በተባለችበት 1ኛና 3ክስ ጥፋተኛ ልትባል የሚያስችል ማስረጃ ባለመቅረቡ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ይግባኙን የሰማው //ቤት ወሰነ፡፡ የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ከአዟሪዎች ላይ እየተነጠቀ ነው - ጋዜጠኛዋ በስር ፍርድ ቤት የተወሰነባት 14 ዓመት እስር እና 33ሺህ ቅጣት ወደ 5 ዓመት እስራት ዝቅ ተደርጓል - መፅሐፏ ባለፈው ቅዳሜ ተመርቋል ለውይይት የተጠሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ /ቤቱ በሰጠው ውሳኔ በሽብርተኝነት በመሳተፍ እና አመራር በመሰጠት የሚያሰኝ ማስረጃ አለመቅረቡን ጠቅሶ አንድ ሰው አንቀጽ ተጠቅሶ ስለተከሰሰ ብቻ መቀጣት የለበትም በማለት ሁለቱን ክሶች ውድቅ አድርጐታል፡ ሁለተኛው ክስ ከሽብርተኛ ጋር በማንኛውም መንገድ መሥራት በሚለው መሠረት ኢትዮጵያን ሪቪውለተባለ ድህረ ገጽ ዜና ሰርታና ፎቶ ግራፍ አንስታ በመላኳ 5 ዓመት እስራት ተፈርዶባታል፡፡ ከፍርድ ውሳኔው በኋላ አስተያየት የጠየቅናቸው የርዕዮት ዓለሙ ጠበቃ ሞላ ዘገየ በሰጡን አስተያየት ደንበኛዬ በነፃ ትለቀቃለች የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ አሁን ግን ከዚህ በፊት ጥፋተኛ የተባለችባቸው ክሶች ተሽረዋል፡፡ በአንድ የትግራይ ህዝብና የህወሓት ጉዞ! 5 7 የዜጎችን ገቢ ያላገናዘበው 40/60 የቤት መርሃ ግብር በፌደራሉ ከፍተኛ /ቤት ልደታ ምድብ 3ወንጀል ችሎት ውሳኔ ተስጥቶበት በተዘጋው በነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ቁጥር 112546 ተከሳሽዓቃቤ ህግ በሚል ደብዳቤ ለውይይት ተብሎ ፍርድ ቤት የተጠራው የአንድነት 9 ለተከታታይ ሳምንታት ህትመቷ ተቋርጦ የነበረችው ፍትህ ጋዜጣ ከመጪው አርብ ጀምሮ ለአንባብያን እንደምትቀርብ የጋዜጣዋ አዘጋጆች ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገለፁ፡፡ ጋዜጣዋ በፍትህ ሚኒስቴር፤ የፌደራል ዓቃቢ ህግ መታገዷ የሚታወስ ሲሆን ከዛ በኋላ ያሉት የሁለት ሳምንት እትሞች ግን በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ባልታወቀ ምክንያት አላትምም በማለቱ ለአንባቢያን ሳትደርስ ቀርታለች፡፡ የፍትህ ጋዜጣ ቅፅ 5 ቁጥር 167 ሐምሌ 13 ቀን 2004 .እትም የታገደው ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል›› የሚል ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር /ቤትን ጠቅሶ በመዘገቡ እንደሆነ የዓቃቤ ህግ ክስ ያመለክታል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት በወቅቱ የነበረው እትም እንዳይሰራጭና እንዲወረስ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡ የፍ/ቤቱ ውሳኔ ትዕዛዝም ሐምሌ 23 ቀን 2004 .ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ለፌደራል ፍትህ ጋዜጣ የፊታችን ዓርብ ለአንባቢያን ትቀርባለች ፖሊስ፣ ለዓቃቢ ህግና ለተከሳሹ ለፍትህ ጋዜጣ መድረሱ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዱ በኋላ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆች ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ለአንባቢያን እንድትደርስ ዝግጅታቸውን ቢያጠናቁቁም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ‹‹አላትምም›› ብሏል፡፡ ሆኖም ከፍ/ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት የታገደው የሐምሌ 13 ቀን 2004 .እትም ብቻ መሆኑ በመገለፁ የፊታችን አርብ ለአንባቢያን መንግስት ለሀዲያ ዞን ገበሬዎች የማይበቅል ምርጥ ዘር ሸጠ አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ 13 XN¬gL ! / ነጋሶ

Upload: vuliem

Post on 01-Jan-2017

275 views

Category:

Documents


15 download

TRANSCRIPT

Page 1: News Paper No. 54 colour.indd

FñtFñt

www.andinet.org

h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54 êUWÝ( 6 BRyx!T×ùà ?ZB yl#›§êE |LÈn# Ælb@T XNÄ!çN XN¬gL!

Fñt nÉnT ¥Ks® Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@n/s@ 1 qN 2004 ›.M. 1 qN 2004 ›.M.

እንደምትደርስ የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ፍ/ቤቱ የሐምሌ 13 እትም ሙሉ ዘገባዎች እንዲወረሱ መደረጉ አግባብ እንዳልሆነና ይወረሱ ቢባሉ እንኳ ለደህንነት ስጋት ናቸው የተባሉት ዘገባዎች ብቻ መሆን ሲኖርበት፣ የኪነ ጥበብ ዘገባዎች፣ በእውቀቱ ስዩም የለንደን ኦሎምፒክ ምልከታዎችና ሌሎም የገፅ ፅሁፎችና ዘገባዎች መልሰን እንዳንጠቀም መደረጉም ቅር አሰኝቶኛል ሲሉ ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል፡፡

ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ተወካይ ከፍተኛ አመራሮች የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣የተከበሩአቶ ግርማ ሰይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ትናንት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በድንገት ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደረገ፡፡

እየተንገዳገደ ያለውን የኢህአዴግ መንግሥት እንዴት መተካት

ይቻላል?

አሁንም እንጮሃለን ! ሕዝቡ ማን እንደሚመራው በግልጽ ማወቅ አለበት

ኢህአዴግ የህዝብ አመኔታ ያጣ መንግስት ስለሆነ ሥልጣኑን ለህዝብ

ማስረከብ ይጠበቅበታል6

11

4ወደ ገፅ 11 ይዞራል....

ወደ ገፅ 13 ይዞራል....

ከወቅታዊው የሙስሊሞች ተቃውሞ ተቃዋሚዎች ምን ይማሩ?

2

ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

ባለፈው ቅዳሜ ለነምርቃት የበቃው የርዕዮት አለሙ መፅሀፍ ከአዟሪዎች እጅ በፖሊሶች እየተነጠቀ መሆኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተሰማሩ መፅሀፍ አዟሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

በተለይ በላናቻና በቦሌ አካባቢ የመፅሀፍ የሚሸጡ ግለሰቦች እንደተናገሩት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ፖሊሶች የርዕዮትን መፅሀፍ ለይተው በመንጠቅ አባረዋቸዋል፡፡

በ “ሽብርተኝነት” ተከሳ በሦስት ክሶች ጥፋተኛ ከተባለች በኋላ 14 ዓመት እስራትና 33 ሺህ ብር ቅጣት የተፈረደባት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ በጠየቀቺው ይግባኝ ጥፋተኛ በተባለችበት 1ኛና 3ኛ ክስ ጥፋተኛ ልትባል የሚያስችል ማስረጃ ባለመቅረቡ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ይግባኙን የሰማው ጠ/ፍ/ቤት ወሰነ፡፡

የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ከአዟሪዎች ላይ እየተነጠቀ ነው

- ጋዜጠኛዋ በስር ፍርድ ቤት የተወሰነባት የ14 ዓመት እስር እና የ33ሺህ

ቅጣት ወደ 5 ዓመት እስራት ዝቅ ተደርጓል

- መፅሐፏ ባለፈው ቅዳሜ ተመርቋል

ለውይይት የተጠሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ በሽብርተኝነት በመሳተፍ እና አመራር በመሰጠት የሚያሰኝ ማስረጃ አለመቅረቡን ጠቅሶ አንድ ሰው አንቀጽ ተጠቅሶ ስለተከሰሰ ብቻ መቀጣት የለበትም በማለት ሁለቱን ክሶች ውድቅ አድርጐታል፡፡ ሁለተኛው ክስ ከሽብርተኛ ጋር በማንኛውም መንገድ መሥራት በሚለው መሠረት “ኢትዮጵያን ሪቪው” ለተባለ ድህረ ገጽ ዜና ሰርታና ፎቶ ግራፍ አንስታ በመላኳ 5 ዓመት እስራት ተፈርዶባታል፡፡

ከፍርድ ውሳኔው በኋላ አስተያየት የጠየቅናቸው የርዕዮት ዓለሙ ጠበቃ ሞላ ዘገየ በሰጡን አስተያየት “ደንበኛዬ በነፃ ትለቀቃለች የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ አሁን ግን ከዚህ በፊት ጥፋተኛ የተባለችባቸው ክሶች ተሽረዋል፡፡ በአንድ

የትግራይ ህዝብና የህወሓት ጉዞ!5

7

የዜጎችን ገቢ ያላገናዘበው የ40/60 የቤት መርሃ ግብር

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ተስጥቶበት በተዘጋው በነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ቁጥር 112546 “ተከሳሽ” ዓቃቤ ህግ በሚል ደብዳቤ ለውይይት ተብሎ ፍርድ ቤት የተጠራው የአንድነት

9

ለተከታታይ ሳምንታት ህትመቷ ተቋርጦ የነበረችው ፍትህ ጋዜጣ ከመጪው አርብ ጀምሮ ለአንባብያን እንደምትቀርብ የጋዜጣዋ አዘጋጆች ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገለፁ፡፡

ጋዜጣዋ በፍትህ ሚኒስቴር፤ የፌደራል ዓቃቢ ህግ መታገዷ የሚታወስ ሲሆን ከዛ በኋላ ያሉት የሁለት ሳምንት እትሞች ግን በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ባልታወቀ ምክንያት አላትምም በማለቱ ለአንባቢያን ሳትደርስ ቀርታለች፡፡

የፍትህ ጋዜጣ ቅፅ 5 ቁጥር 167 ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም እትም የታገደው ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል›› የሚል ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ም/ቤትን ጠቅሶ በመዘገቡ እንደሆነ የዓቃቤ ህግ ክስ ያመለክታል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በወቅቱ የነበረው እትም እንዳይሰራጭና እንዲወረስ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡ የፍ/ቤቱ ውሳኔ ትዕዛዝም ሐምሌ 23 ቀን 2004 ዓ.ም ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ለፌደራል

ፍትህ ጋዜጣ የፊታችን ዓርብ ለአንባቢያን ትቀርባለችፖሊስ፣ ለዓቃቢ ህግና ለተከሳሹ ለፍትህ ጋዜጣ መድረሱ ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ከእግዱ በኋላ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆች ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ለአንባቢያን እንድትደርስ ዝግጅታቸውን ቢያጠናቁቁም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ‹‹አላትምም›› ብሏል፡፡ ሆኖም ከፍ/ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት የታገደው የሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም እትም ብቻ መሆኑ በመገለፁ የፊታችን አርብ ለአንባቢያን

መንግስት ለሀዲያ ዞን ገበሬዎች የማይበቅል ምርጥ ዘር ሸጠ

አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ

13

XN¬gL!

ቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

Page 2: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

2 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ሰለሞን ስዩም

የመንግስት ሚዲያዎች የሰደቃ ዝግጅቱን ክፉኛ ቢያብጠለጥሉትም በአለም አቀፍ ደረጃ በሁሉን አቀፍ የእስልምና ልሂቅ የሆኑት ዶ/ር ጃይላን ከድር “አላህ በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ምፅዋት አድርገህ ብትሰጥ በልቦናዎቻቸው መካከል አንድ አታደርግም፡፡” ማለቱን በሚያዚያ 2004 ዓ.ም በአንዋር መስጊድ ተዘጋጅቶ በነበረው የአንድነትና የሰደቃ መርሐ ግብር ላይ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ጃይላን ይህ ቁራናዊ መሠረት ያለውን ነገር “አንዳንድ ብዙሃን መገናኛዎችና ባለስልጣናት ሙስሊሙን ህብረተሰብ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮችን በማጥፋት ኢስላማዊ መንግሥት ሥርዓት እንዲመሠረት ይፈልጋሉ” በማለት መናገራቸው አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ እንደ እርሳቸው አገላለጽ አብሮ በሚኖር ህዝብ መካከል ልዩነት የሚያመጡት በዋናነት ባለስልጣናትና ብዙሃን መገናኛዎች ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ወደጐን በመተው የመንግስት ባለስልጣናት የሚከተሉትን ህዝብን የማሸማቀቅ አካሄድ መልስ እንዲሆን የተዘጋጀ ሰነድ “የእምነት ነፃነት ጥሰት መቃወም ከጀመርን እነሆ በነዚህ ጊዜያትም ጥያቄዎቻችንን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እያቀረብን ብንገኝም ሊሳካልን የቻለው ያማረ አካሄድ ማስመዝገባችን እንጂ ያማረ ውጤትን አይደለም፡፡” ሲል የአካሄዱን ሰላማዊነት ገምግሟል፡፡

ሁሉንም አስደምሟል

በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃውሞ መንገድ የተደመሙ ምሁራን በዝተዋል፡፡ አንድ የቀድሞ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ “ከእንግዲህ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴን ለማጥናት የውጭ መፃህፍትን አላገላብጥም፤ የሀገሬ ሙስሊሞች ሁኔታ ከምንም ይበልጣል” ሲል ሀሳቡን በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ አስፍሯል፡፡ ለዚህ አስተያየት መነሻ የሆኑ ሁለት ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፤ የመጀመሪያው ሀገሪቱ የተደራጀ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ የሌላት መሆኑ ሲሆን ሌላው ስማቸው የሽብርተኝነት ጅሃድና ብጥብጥ መገለጫ ወደ መምሰሉ ያደላው ሙስሊሞች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው መንቀሳቀሳቸው ነው፡፡

“እንደማንም መደዴ ሰው እስልምናን ከጦርነት ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው” የሚለው ይሄ ሰው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከዚህ በተቃራኒ በመንቀሳቀሳቸው ሁሉንም አስደምሟል፡፡

የአመጽ እንቅስቃሴዎች ፈተና

የአለም አብዮት አጥኚዎች ባብዛኛው አብዮት ለቁጥጥር ያለመመቸት ያስማማቸዋል፤ የፈረንሳይና የሩሲያ አብዮቶችን በማጥናት ተመሳሳይነታቸውን ያስቀመጠው ያንግ ፕዩፕል “ሁለቱም አብዮቶች ለቁጥጥር አይመቹም ነበር” ይላል፡

ከወቅታዊው የሙስሊሞች ተቃውሞ ተቃዋሚዎች ምን ይማሩ?

፡ አሜሪካዊው የአብዮት ተንታኝ የፈረንሳይ አብዮትን “ከታች ወደ ላይ እና ከላይ ወደታች መጠፋፋት የተቻለበት ነው” ይላል፡፡

በአብዛኛው ሀገሮች አብዮትን ያስጀመሩ መሪዎች እስከ አብዮቱ ፍፃሜ አይጓዙም፤ የታለመለትን ግብ የሚመቱ አብዮቶችም እስከዚህም ናቸው፤ አብዛኛዎቹ አብዮቶች የተደበላለቀ አካሄድ ነበራቸው፡፡

ወቅታዊው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአብዮት በመለስ የተደራጀ በውስጡ በወል የታወቁ መሪዎች ያሉት፣ እና ማንም ተነስቶ “ልሙላው አልሙላው” የሚለው አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ መንግሰት ባህሪን መረዳት

የትኛውም የተቃውሞ ጎራ ላይ ያለ ቡድን የመጀመሪያው ስራ ሊሆን የሚገባው የሚቃወመውን ወገን ባህሪ ማጥናት ነው፡፡ ባለፉት 21 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ይህ ስራ የጎደላቸው ነበሩ፡፡ በዚህ ወቅት የዚህን የቀድሞ ችግር እየቀረፉ የመጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዚህ ያበቃቸው የመጀመሪያ ስራቸውን ያደረጉት ኢህአዴግን በመረዳት ላይ ማድረጋቸው ነው፡፡

ከሀይል በተጨማሪ መንግስት በካድሬዎች አስገዳጅነት የተቀነባበሩ የፀረ ተቃውሞ የተቃውሞ ሰልፎችን በመላ ሀገሪቱ ማደራጀቱን ማየት ተችሏል፡፡ አንዳንድ የመንግስት

Plan B

የወቅቱን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞን የተለየ ደረጃ የሰጠው ተለዋጭ የተቃውሞ ስትራቴጂ ማዘጋጀት መቻላቸው ነው፡፡ የተቃውሞን እንቅስቃሴ የሚመሩ ሰዎች የመጀመሪያ ስትራቴጂ የነበረው ተቃውሞን መታገስ የማይሆንለትን የኢትዮጵያ መንግስትን በምን መልኩ ማለፍ እንዳለባቸው ነበር፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎች ሙስሊሞቹ እንቅስቃሴውን ከሚመሩ ሰዎች እስከ የተቃውሞ አካሄድ ድረስ ሁለተኛና ሦስተኛ አማራጭ ማስቀመጣቸው ነው፡፡ በተለይ የተቃውሞው አመራሮች ከታሰሩ ሌሎች የሚተኳቸው ሰዎች ከወዲሁ መመረጣቸው ጉዳዩን በቀላሉ እንዳላዩት ያሳያል፡፡

ኢህአዴግ በፈለገው ቀን እንደበግ እየጎተተ ወደ ወህኒ የሚወረውራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በዚህ መልኩ ከወዲሁ መተካት ቢችሉ የተሻለ ይሆናል፡፡ አንድነት ፓርቲ አንዱዓለም አራጌን የመሰለ ተፈጥሮአዊ መሪ ሲታሰርበት የተለየ እቅድ ቢኖረው ኖሮ የመጎዳት መጠኑን ይችል እንደነበር አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ኦፌዴንም በበኩሉ እነ በቀለ ገርባን የመሳሰሉ መሪዎችን አሳስሮ መተካት ያለመቻሉ የዚሁ “plan B” እጦት መሆኑ ይነገራል፡፡ ከራድ ማክዶናልድ የትራምፔት ዋና አዘጋጅ ጌራልድ ፋሪ ከአመት በፊት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ተቃውሞ ተንብዮ ነበር፤

ካድሬዎች ከዚህ እንቅስቃሴ ጀርባ የሌሉና ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ለመቃወም እንዲወጣ ቢናገሩም አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው “በከሚሴና በጅማ አሊያም በደሴና በባሌ የተደረጉት `የተቃውሞ` ሰልፎቹ መፈክሮች በይዘት አንድ መሆን ብቻ ሳይሆን የተፃፈበት ፊደል መጠንም ተመሳሳይ ነበሩ” ይላሉ፡፡

ምን እንማር?

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከሙስሊሞቹ “ተቃውሞ የምንወስደው ትልቁ ትምህርት በምንም ሁኔታ ከሰላማዊነት ያለመውጣት መሆኑን ያብራራሉ፡፡ በዶ/ር ነጋሶ እይታ ሰላማዊ ተቃውሞውን ለማደፍረስና ሙስሊሙን ወደ አመፅ ለማምጣት መንግስት ጥረት ማድረጉን” ያብራራሉ፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወደ የኃይል አመጽ ያለመምጣታቸው መንግስት የኃይል እርምጃ ለመውሰድ መንገድ አልሰጠውም፡፡ የሙስሊሞቹ ሌላው አስተማሪ ነገር አንዱ ደፋር መሆን ሲሆን ሌላው “ቀጣይነት ላለው ጊዜ” መቃወም መቻል ነው፤ “አብዛኛው ተቃውሞ በሆነ አጋጣሚ ተነስቶ ወዲያው የሚከስም ነው” የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ቀጣይነት ላለው ጊዜ መቃወም መቻል ነው” ይላሉ፡፡ ለዚህ ያበቃውን ሲያብራሩ ደግሞ ዋናው ነገር ተቃውሞው ስርዓት የተዘረጋለት (system) ነው” ይላሉ፡፡

Page 3: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

3Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ኦ- ኢትዮጵያዬእጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ!

ዳንኤል ተፈራ

መቼም የአፍሪካና የአፍሪካውያን የስቃይ ዘመን የሚያበቃ አይመስልም፡፡ አፍሪካና ልጆቿ ፈጣሪ የተፈጥሮ ሃብቱን ሳይሰስት ቢሰጣቸውም ይሄው ሃብት ባመጣባቸው ጣጣ፤ የተፈጥሮ በረከቶቻቸው ላይ አይኖቻቸውን የጣሉ ነጮች ተቀራምተው ሰብአዊ መብታቸውን ሲጥሱ፤ ሲገርገፉና ሲገሏቸው የነበረበት የጨለማ ዘመን ያለፈው በዚሁ የፍዳ አህጉር አፍሪካ ነው፡፡

የጨለማውና የጭቆናው ዘመን ያበቃ ዘንድ የመጀመርያው የነፃነት ሻማ የተለኮሰው ግን የአፍሪካ ቀንዷባለታሪክ ሃገር ኢትዮጵያ ላይ ነበር፡፡ በተለይ ቄሳራውያን ጥንታዊቷን ኢትዮጵያ በመንካታቸው ቀፎው እንደተነካ ንብ ወደ አድዋ የተመሙት አያቶቻችን ቁጣቸው ፊታቸው ላይ እንደ ደመራ እየተንቀለቀለ ‹‹እንትናቸውን በሳንጃ›› ብለው አባረሯቸው፡፡ የቄሳሮቹ መንግስት በጥቁር ቁጡ ህዝብ መሸነፍም ለሌሎች አፍሪካውያን መነቃቃት ፈጠረና የነፃነት ብርሃንን ለማየት በቁ፡፡

ብላቴን ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንም ነብሳቸውን ይማርና ‹‹ዋ!. . . ያቺ አድዋ›› በሚል የቅኔ መስዋእት የነፃነት ሻማ ለተለኮሰባት ምድር አቀረቡ፡፡ እስቲ እንቆንጥር

‹‹ . . . ዋ!

አድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ

የደም ትቢያ መቀነትዋ

በሞት ከባርነት ስርየት

በደም ለነፃነት ስለት

አበው የተሰውብሽ ለት

አድዋ

የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ

የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ. . . አድዋ. . . አድዋ›› እያሉ ሎሬት ይቀጥላሉ፡፡ አፍሪካውያን የነፃነት ድልን ብዙም ሳያጣጥሙት አምባገነንነት በተጠናወታቸው የራሳቸው ልጆች እጅ ላይ ወደቀ፡፡ አፍሪካም የአምባገነኖች መፈልፈያ ቀፎ፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት መለያ መሆኗን ቀጠለች፡፡

እስቲ አፍሪካ ውስጥ ለህዝባቸው ነፃነትን ያጎናጸፉ መሪዎችን ጥሩልኝ? ብዬ ድንገቴ ጥያቄ ብወረውርላችሁ እርግጠኛ ነኝ የምትጀምሩት ‹‹እእእ! . . .›› በማለት ነው፡፡ ከዚያም ኮርኒስ ላይ እንዳፈጠጣችሁ ‹‹ማንዴላ. . እ. . ›› እያላችሁ መልስ ፍለጋ ታምጣላችሁ፡፡ አፍሪካ ውስጥ አምባገነን መሪዎች ጥሩልኝ ብዬ በመጠየቅ መምህር ብሆንባችሁ ደግሞ ሳትቸገሩ መደርደር እንደምትችሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ በአፍሪካ የዜጎቹ ደም የሌለበት፤ የዜጎቹን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚደፈጥጥ በሽበሽ ነው፡፡

ከዚህ በፊት በነፃነት አውጭነት ስም ዙፋኑን የተቆጣጠሩት እነ ሞቡቱ ሴሴሴኮ፣ ኤዲአሚን ዳዳ፣ መንግስቱ ኃ/ማርያም፣ ጆን ቤዴን ቦካሳ፣ ሳሞራ ሚሸል፤ አምላካችሁና አስተማሪያችሁ እኔ ነኝ የሚሉ የነሩት አሊ ሶሊህ፣ የቱኒዝያው የአሁኑ ከርታታ ቤን አሊ፣ የአልጋ ቁራኛው የግብጹ ሆስኒ ሙባረክ፣ ቱቦ ውስጥ እንደ ሶልሱዋላ ውሻ ተደብቀው የተገኙት ሙአመር ጋዳፊ. . .እና ሌሎችም ህዝባቸውን አስለቅሰው ያለፉ አምባገነኖች እንጂ የአፍሪካ አባቶች አይደሉም፡፡ አፍሪካ አባት

የምትለው መሪ ለማግኘት እምብዛም አልታደለችም፡፡ ለዚህ ነበር የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ እንዲህ ያሉት፡- ‹‹ራሳችንን ለማስተዳደር እድሉ ቢሰጠን በፍጥነት ምድራዊ ገነት እንደምንፈርጥ አስመስለን አወራን፡፡ በተቃራኒው ያሰፈንነው ግን የፍትሕ መጓደልና ፈላጭ ቆራጭነት ነው›› በማለት እቅጩን የተናገሩት፡፡

ዛሬስ? ኦው! ኦው! ኦው! . . በጣም ከባድ ጥያቄ ነው፡፡ እስካሁን ያልተመለሰ እንቆቅልሽ፡፡ ቀደምት የአፍሪካ አምባገነኖች የተተኩት በሌላ ትኩስ አምባገነኖች ነው፡፡ የሩቁን ትተን ኢትጵያችንንና ጎረቤቶቿን እንመልከት፡፡ በጠቅላላ በአምባገነንነት የተቃኘ፣ ሰብአዊ መብትን የሚጥስ አስተዳደር ያሰፈኑ ናቸው፡፡ ጅቡቲ፣ ሶማልያ ከነቁርጥራጯ፣ ኢትዮጵያ፣ ሰሜን ሱዳን እና ኤርትራ ለህዝቦቻቸው ዴሞክራሲን በመንፈግ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ህዝባቸውን አንቀጥቅጠው ለመግዛት የሚቁዋምጡ ቅዠታሞች ናቸው፡፡ የደቡብ ሱዳን ነገርም ገና ባይለይለትም ከጎረቤቶቿ የተለየ እጣፈንታ የሚኖራት አይመስልም፡፡

ለሃያ አንድ ዓመት የቆየው የአቶ መለስ አስተዳደርም የቀደሙ ታሪኮችን ከመድገም ባለፈ ጠብ ያደረገው አዲስ ነገር አለ ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር አይቻልም፡፡ በተለይ በሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበር ዙርያ፤ የፍትሕ ተቋማትን ተስፋ እንድንጥልባቸው ባለማድረግ ዙርያና ነፃ የሆነ የሚያኮራ ፕሬስ ባለመፍጠር ዙርያ የተሳካላቸው አይደሉም፡፡ ወገኛ ነኝ! የምን የሚያኮራ ፕሬስ አመጣሁ? እነዚህ የአንድ ጣት ቁጥሮች የማይሞሉ ጋዜጦችን ለማጥፋት እንቅልፍ አጥቶ አይደል እንዴ የሚያድረው፡፡

‹‹ኢህአዴግ በተፈጥሮው ዴሞክራሲያዊ አይደለም›› የሚለውን ትችት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ አይገደንም፡፡ እንደ ፖለቲካ አዋቂዎች አባባል ከሆነ ደግሞ የልግጥ ዲሞክራሲ(sudo democracy) ሲከተሉ የነበሩት ነፃ አውጪዎች በ1997ዓ.ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ያዩት የህዝብ ፍላጎትና ውጤቱ የልግጥ ዴሞክራሲውንም

እርግፍ አደርገው በመተው ወደ ፍፁም አምባገነንነት(absolute dictator) የሚወስደውን ጎዳና አጥብቀው የያዙ ይሏቸዋል፡፡

እነ አቶ መለስና ተከታዮቻቸው ወደ ፍፁም አምባገነንነት የሚወስደውን ጎዳና ሲይዙ እንደ አንድ ሞኝ ከመሬት ተነስተው ከዚህ በኋላ ምርጫ የለም፣ ተቃዋሚ አያስፈልግም፣ ነፃ ፕሬስ ማየት አንሻም… ብለው አልፎከሩም፡፡ ለምርጫ ተለጣፊ ተቃዋሚዎችን አበጁ፡፡ ለሃቀኛ ተቃዋሚዎችና ለነፃው ፕሬስ ደግሞ የህግ ሽፋን ለመስጠት ለምሳሌ የፀረ-ሽብር ህግ አዘጋጁ፡፡ የፀረ- ሽብርተኝነት ህጉ ተቀናቃኞችና ተቺ ጋዜጦችን ህግ እየጣሱ ለማሳደድ የሚመች ሆነላቸው፡፡ እና ኢህአዴግ ወደ ፍፁም አምባገነንነት እየተለወጠ ያለው ህግ እተጠቀሰ ነው፤ ተቃዋሚ አለ እያስባለና ነፃ ፕሬስ የትረፈረፈ እያስመሰለ ማለት ነው፡፡

ከሦስት ሳምንት በፊት ገዢው ፓርቲ አንድ ሁለት ገበያ ላይ ሃቅን ይዘው ፊትለፊት በመጋፈጥ ከሚገኙ ጋዜጦች መካከል ዋነኛ የሆነችው ፍትሕ ጋዜጣ ላይ የጡንቻ ፍተሻ አካሄደ፡፡ ድርጊቱ የነፃነት ማሳጣቱ ጎርምሶ መንግስት የወጣቶቹን ብእር መንጠቅ እንደጀመረ ነው፡፡ ብእር ነጣቂ መንግስት ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ በፍትህ ጋዜጣና ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው የብእር ነጠቃ ኢትዮጵያን በስጋት ላይ ያለ መንግስት እንደሚያስተዳድራት የሚያመላክት ነው፡፡

ገዥዎች ሆይ! ዴሞክራሲያችንን ነጠቃችሁን ዝም አልን፣ ነፃነታችንን ጠቅልላችሁ ወሰዳችሁ ዝም አልን፣ የሚያስፈልጋችሁ ዳቦ እንጂ ሰብአዊ መብት ምናምን አይመለከታችሁም አላችሁን ዝም አልን፣ ግብር የምንከፍልበት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና አዲስ ዘመን ጋዜጣ የፓርቲ ልሳን እስከሚመስሉ የተቃዋሚዎች መርገሚያ አደረጋችኋቸው አሁንም ዝም አልን፣ ህዝብ ማወቅ የሚገባውን የጠ/ሚኒስትሩን መታመም ደብቃችሁ የጫካ ልምዳችን ነው ስትሉ አፌዛችሁብን ዝም አልን በመጨረሻም የሦስት ብር ብእራችንን በአደባባይ ነጠቃችሁን እንግዲህ ምን ቀረን?

ብእር ነጣቂው መንግስት

አናንያ ሶሪ

ከንግዲህስ ተስፋሽ ማነው? አምላክሽ አይደለንምን?! እስቲ ንገሪኝ ኢትዮጵያዬ፡- ልጆችሽ ያጠባሻቸውን ጡቶችሽን መልሰው አልነከሱምን? ከእጅሽ እንዳልበሉስ ውለታሽን ዘንግተው ፊታቸውን አላዞሩብሽም? ገፃቸውን አላጠቆሩብሽም? ጀርባቸውን አልሰጡሽም? ካንቺው ጉያ የወጡ ልጆች ያንቺኑ ልጆች አልገደሉምን? አብዮት ሲሉ በሰየሙት የመጠፋፋት ቃየላዊ- ስልት እየተገዳደሉ አደባባዮችሽን በደም ጐርፍ አላጠቡትምን? ጐዳናዎችሽንስ በእሬሳ ክምር አልሞሉትም? ልብሽ በሀዘን ተቸንክሮ ወደ ውስጥሽ ስታነቢ ‹አይዞሽ እምዬ!› ብሎ አንገትሽን ቀና ያደረገ አንድ ስንኳ አለ?

ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር፣ የከተማ ትግል፣ የትጥቅ ትግል፤ የራስን ዕድል በራስ መወሰን፣ መገንጠል በሚሉ ፅንሰ ሃሳቦች በጭፍን እየተነዱ በርስ-በርስ ጦርነት የልጅ መካን ያደረጉሽ ያንቺው ልጆች አይደሉምን? ዛሬም በቀሩት ልጆችሽ መሃል የመለያየትን ዘር ዘርተው የመጠፋፋት ቡቃያን ሊሰበስቡ ያሰፈፈሰፉት እኒሁ የማህፀንሽ ፍሬዎች አይሉንምን?

ኦ- ኢትዮጵያዬ! . . . ከንግዲህስ ትምክህትሽ ማነው? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የሚያወጣሽ መተማመኛ ልጅሽስ ከወዴት አለ? ይበጁኛል ያልሻቸው ሲጐዱሽ፣ ያለሙኛል ያልሻቸው ሲያጠፉሽ፣ ያስጌጡኛል ያልሻቸው ሲያኰስሱሽ፣ ይጦሩኛል ያልሻቸው ተመልሰው ካንቺው ሲጦሩ፣ ያበሩኛል ያልሻቸው ሲያጨልሙሽ፣ ሰላም ይሰጡኛል ያልሻቸው ሰላም ሲነሱሽ፣ ነፃ ያወጡኛል ያልሻቸው ወደባርነት ሲከቱሽ እያየሁ በዝምታ ማለፍ አቅቶኝ ይኽው እናገራለሁ -አንድ ቀን

ብቻዬን እስካወራ ድረስ አንቺኑ አናግራለሁ፡፡

ኢትዮጵያዬ፡- አሁንስ ተስፋሽ ማነው? የዛሬ 40 ዓመት ነፍስ “ያሳወቅሻቸው” ልጆችሽ ናቸውን? እነሱማ የዘመናቸው ስህተት አልበቃ ብሏቸው የትውልዳቸውን ተስፋ አምክነው፤ የኛንም ዘመን ተስፋ አንቀው በራሳቸው ምስል ሊቀርፁን የሚተጉ ኋላ ኋላ የሚከተል ጥላ ሆነውብናል፡፡ አንድ ቀን ብርሃን አጥለቅልቆን እስኪሸሹን ድረስ ከእኛ ጋር አሉ! ከነፅንፈኝነታቸው፣ ጥላቻቸው፣ አረመኔነታቸው፣ ተንኰላቸው ታጭቀው ዙሪያችንን ከበው ከጀርባ ሊጋልቡን ይሻሉ፡፡ ብዙዎቻችን ግን ከእባብ እንቁላል እርግብ አንጠብቅም!

“ዘመናዊ” ትምህርት ቀስመናል ያሉትስ፤ ያገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ! ሲል ከተረተው ኢትዮጵያዊ ገበሬ የተሻለ ጥበብ አላቸውን? ምሁራኖችሽ የራስን በመናቅ የሌላን በማድነቅ የታወሩ ፊደላውያን አይደሉምን? ታዲያ እነዚህ ከመጽሐፍ ወደ መጽሐፍ እየዘለሉ ቅንጭብጫቢ ሰበዞችን በመምዘዝ እና ቁንፅል ሀሳቦችን በመጥቀስ ያለ አንዳች ተግባራዊ ምርምር የንድፈ ሀሳብ ጋሻጃግሬ ሆነው የሰበብ ትንታኔያቸውን ከመደርደር ባለፈ ምን ጠብ አረጉልሽ? እንደው ከምርስ ነፍስያሽን ያውቁታልን? የልብሽ ሃሳብና ጭንቀት ይገባቸዋል? ወይስ ያልበላሽን የሚያኩ አላዋቂዎች ሆነውብሻል? ሲተነትኑልሽ እና ሲተነትኑ ብሽ፣ ሲተበትቡልሽ እና ሲተበትቡብሽ የኖሩና ያሉ ‹ልሂቃን› እና ‹አዋቂዎችሽስ› ምነው አንድ ጋት እንኳ ፈቅ አላረጉሽ?

ኢትዮጵያዬ! . . . እማማዬ! . . . . ልጆችሽን በረሃብ እንደቅጠል ከመርገፍ የሚታደጋቸው ማነው? እስከ ዛሬ የእህል ዘር ሲለግሱሽ የኖሩት የዓለም ኃያላን አገራት ምፅዋት ለምን ከረሃብ አላላቀቀሽም? ከአሜሪካ ስንዴስ የእግዚአብሔር መሬት አይበልጥም ኖሯል? ልምላሜን፣ ዝናምን፣ ፀሐይን ለምድርሽ፤ ጉልበትና ጤናን ለህዝብሽ የሰጠው አምላክሽስ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ? የህዝብሽን ጉልበትና ወኔ ያደከመውስ የግፍ

አስተዳደር እና የጥቂቶች አልጠግብ ባይነት አይደለንምን? ከመጨረሻው የዘውድ ስርዓት ጀምሮ ብሄራዊ መለያ ወደ መሆን የተሸጋገረው ረሃብስ የሚያባራው መቼ ነው? ስንቱስ ወገኔ በቀላሉ ሊድንና ሊከላከሉት በሚችል በሽታ እየሞተ ይቀጥላል?

እናት ዓለም! እንደባህር አሸዋ በየዓለማቱ ዳርቻ የተበተኑትን ልጆችሽን የሚሰበስበውስ ማነው? ለስደት ህይወት ብለው በረሃ ሲያቋርጡ እና ባህር ሲሻገሩ እንደወጡ የቀሩትን የልጆችሽን የነፍስ ዋጋስ ከማን ትቀበያለሽ? የወለድሻቸው የአብራክ ክፋይዎችሽ ዘርተው የማይቅሙበት ወልደው የማይስሙበት ይሆን ዘንድ ምድርሽን ከቶ ማን ረገመው?

የኔ ትውልድ ልጆችሽስ በአሁኑ ሰዓት የት ናቸው? ትኩረታቸውስ ምን ላይ ነው? ለዚህ ሁሉ ቀቢፀ ተስፋ፣ ሱሰኝነት፣ ግድ ማጣት፣ የማንነት ቀውስ፣ የምናገባኝ ስሜት የዳረጋቸውን እኩይ-ስርዓት ሴራስ ጠንቅቀው ያውቃሉን? ይህንንስ ለመቀየር ብልሃቱ፣ ወኔው፣ እና ሞራሉ አላቸው?

ኦ . . . ኢትዮጵያዬ! ከንግዲህስ ተስፋሽ ማነው? ልጆችሽ? የዓለም ኃያሏ አገር? የልጅ ልጆችሽ? ወይስ . . . ?

አሁን፡- መልካሙ ወይን ሁሉ አልቆ መናኛው ብቻ ቀርቷል፡፡ አሁን፡- የሰው ልጅ ብልሃትና ዕውቀት ጫፉ ላይ ደርሶ መፍትሄነቱ አብቅቷል፡፡ አሁን፡- ጊዜው የተአምራት ነው! ኢትዮጵያዬ . . . አንቺ ደግሞ የተአምራት አገር ነሽ፡፡ ከሃይማኖት ድርጅቶችና ቲፎዞዎቻቸው ይልቅ መንፈሳዊ እምነቶችና ፈሪሃ -እግዚአብሔር ያላቸው ልበ ብሩሃን በየእምነታቸው ቤት የሚቃትቱልሽ የሚፀልዩልሽ የአምላክ ጥበቃና ቃል-ኪዳን ያልተለየሽ ነሽ፡፡ እግዚአብሔርሽ ደግሞ ዛሬም ከጐንሽ ነው!

እነሆ ተዓምራት ፩፡-

“አንቺ መካን ሴት፤ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ ዘምሪ፤ እልል በይ፤ በደስታ ጩኺ፤

አንቺ አምጠሸ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሄር፡፡

“የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤ የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ ፈፅሞ አትቆጥቢ፤ ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ፡፡ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ትስፋፊያለሽ፤ ዘሮችሽ መንግስታትን ይወርሳሉ፤ በባድማ ከተሞቻቸው ይኖራሉና፡፡

“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኃፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኃፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም፡፡ ባልሽ ፈጣሪሽ ነውና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ታዳጊሽ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል፡፡ እንደተናቀች የልጅነት ሚስት፣ እግዚአብሔር እንደገና ይጠራሻል” ይላል አምላክሽ፡፡

“ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ ነገርግን በታላቅ ርህራሄ መልሼ እሰበስብሻለሁ፡፡ ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለተቆጣሁ፤ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገርግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሄር፡፡

“ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣ እንደኖኅ ዘመን ነው፤ አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቆጣ፣ እንዳልገስጽሽም ምያለሁለለ ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይሳል መሐሪሽ እግዚአብሔር፡፡ . . . .

ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል፡፡ በጽድቅ ትመሰረቻለሽ፤ የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤ የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤ አጠገብሽም አይደርስም፡፡

(ትንቢተ ኢሳያያስ 54)

Page 4: News Paper No. 54 colour.indd

4 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

www.andinet.org

4 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

Uz@ÈCNN “Fñt nÉnT“ Bl¬L “FñT“ ¥lT mNgD ¥lT s!çN knÉnT UR

s!ÈmR ynÉnT mNgD ¥lT nW::www.andinet.orgwww.andinet.org

አምባገነን የሆነው የኢህአዴግ መንግስት ለረጅም አመታት ፓርቲውንና መንግስትን እየመሩ የሚገኙት ጠ/ሚ መለስ በህመም ከስራ ገበታቸው ከተለዩ አንድ ወር አለፋቸው፡፡ የጠ/ሚኒስትሩን መታመም ተከትሎ ከህዝብ ተደብቀው ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚሰሩ ተግባራት ስርዓቱን ፍጹም አምባገነናዊነትና ለህዝብ ያለውን ንቀት አመላካች ሆኗል፡፡ ህዝቡ ሀገሩ በማን፣ በምንና እንዴት እንደምትመራ ማወቅ ሲገባው ሄን ህገ - መንግስታዊ መብቱን ‹‹ሚስጥር መደበቅ የኢህአዴግ የኖረ ባህል ነው ›› በሚሉ ተዋናዮች ተናንቆ፣ ምን ሊከሰት እንደሚችል በውል ወደሚውቀበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

አቶ መለስ ህመም ምንም ይሁን ምንም፣ ይኑሩም አይኑሩም ቅድሚ.. ሊሰጠው የሚገባ ሀገርና ህዝብ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ሀገራችንንና ህዝቧን ድንገት ሊከሰት ከሚችል ነገር የመጠበቅ ሀገራዊ ሀላፊነት እንዳለብንም እንገነዘባለን፡፡

ይሄን ሁሉ ከግምት አስገብተን ህገ - መንግስቱን አክብሮ የጠ/ሚኒስትሩን መምራት አለመቻል በማስረጃ አስደግፎ ለህዝቡ እንዲያውቀው ማድረግ ..ለበት ገዢው ፓርቲ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ ይህን ባለማድረጉ ሀገሪቱ በውዥንብር፣ ባሉባልታና፣ በመላምት ስትናጥ ሰንብታለች፡፡ አሁንም ግልፅ የሆነ ነገር በመጤፋቱ ውዥንብር ውስጥ ናት፡፡ ለዚህ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው አካል አስተዳድራለሁ የሚለው ገዢ ፓርቲ ነው፡፡ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የፓርቲን ጥቅም በማስቀደም ለተሰራው ደባ መንግስት ከተጠያቂነት ሊያመልጥ አይችልም፡፡

ከላይ በጠቀስናቸው ጥቂት ምክንያቶች እንኳ አሁን ሀገሪቷ በማን እየተመራች እንደሆነ አናውቅም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሯል እየተባለፈ የሚወራው ‹‹ የአደባባይ ሚስጥር›› የሆነው የስልጣን ሽኩቻና በቡድን መከፋፈል በጠቅላላ ከህዝብ ፊት ተደብቆ እየተሰራ ያለው ስራ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን ሀገርንና ህዝብን አደጋ ላይ ይጥላል ሚል ስጋት አለን፡፡

ለስጋታችን መነሻ የሆኑንና ኣሳቢ ሀገራዊ ጉዳዮች ከምንላቸው በርካታ ጥያቄዎች ጥቂቱን እናቀማለን፡፡

የጠ/ሚ መለስን ቦታ ሸፍኖ እየሰራ ያለው ማን እንደሆነ በውል ባለመታወቁ ጠ/ሚር ይሰሯቸው የነበሩ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለማቀፋዊ ስራዎች፣ የሚፈረሙ ወረቆች፣ ስምምነቶች፤ ድርድሮችና

ወቅታዊ ስራዎች ወይ አይሰሩም ወይም ማን እንደሚሰራቸው አይታወቅም፤

ጠ/ሚኒስትሩ የሰራዊቱ ጠቅላይ አዛዥ በመሆናቸው፤ ሰራዊቱ ደግሞ ያለ አዛዥ መቆየት ስለሌለበት ማን ሀላፊነቱን ወስዶ እየሰራ እንደሆነ አለመታወቁ፤

ሰራዊቱ ያለ አዛዥ መቀመጡን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የጅኦ ፖለቲክስ አንጻርና ከአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑ ሀገሮች ጁቡቲ፣ ሱማሊያ፣ ደቡብና ሰሜን ሱዳን እና ኤርትራ ያልተረጋጉና የጦር ስጋት ያለባቸው ቀጠናዎች በመሆናቸው ሊከሰት የሚችለው የሉዓላዊነት መደፈር አደጋ ላይ መሆኑ፤

ራሱ ኢህአዴግ ውስጥ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚደረገው ውስጣዊ ግብግቦች ለኢትዮጵያ በጣም አደገኛና ወቅታዊ ፈተናዎች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

ስለዚህም አሁንም ደግመንና ደጋግመን ህዝቡ ማን እንደሚመራው በግልጽ የማወቅ መብት አለው፡፡ ማወቅም አለበት ብለን እንጠይቃለን፡፡

ከዚህ በፊት በግለሰቦች የስልጣን ፍላጎት የሚከሰቱ ግብግቦች የተነሳ ህዝቡና ሀገሪቷ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ሌላ ተጨማሪ አስቀያሚ ታሪክ ያስፈልጋል ብለን አናምንም፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን ሜዳውም ፈረሱም፣ ታሪካዊነቱም ያለው ኢህአዴግ እጅ ነው፡፡ የሚያስፈልገው ጥቂት ቀና መሆን ነው፡፡ በር ዘግቶ ለብቻ ከመደሰት ጥያቄውንና ስልጣኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ታሪክ መስራት ነው፡፡ ይህን ለማድረግ መፍጠን ስፈልጋል ብለን እናምናለን፡፡

አሁን እየተደረገ ያለው ቤት ዘግቶ መደለት በጥብቅ እንደሚያሳስበን ለመናገር እንወዳለን፡፡ ሀገሪቱን ተጨማሪ ዋጋ እንዲያስከፍላት እንሰጋለን፤ ህዝቡ እንዳይሸማቀቅ እንፈራለን፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ቤት ዘግቶ ከመሞከር በመውጣት ለህዝቡ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

ይህንን ሀላፊነት መወጣት ካልቻሉና ህዝቡን በአግባቡ መምራት ካቃታቸው ያላቸው ሌላ ምርጫ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቅ ነው፡፡ ስልጣኑን ለህዝቡ አስረክቦ ምርጫ እንዲካሄድ መፍቀድ፡፡

xNDnT

!äK‰s! lFTH

(xNDnT) ­RtE

UNITY FOR DEMOCRACY & JUSTICE (UDJ

)

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2003 ዓ.ም ተመሰረተ፡

፡ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ

ፓርቲ (አንድነት) ስር የሚታተም በፖለቲካዊ፣

በማህበራዊ፣ወቅታዊ ጉዳዮችና በመዝናኛ ላይ

የሚያተኩር ጋዜጣ ነዉ፡፡

ጋዜጣችን ሚዛናዊና ነፃ ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል መርሁ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ሀሳብና አመለካከት የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት እንዲሆን እንሻለን፡፡ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን አለዉ የሚባለዉ ኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ አቋሙንና ፖሊሲዉን ለማግለፅ ቢፈልግ መድረኩ ክፍት ነዉ፡፡

ዋና አዘጋጅ፡-

ነብዩ ኃይሉ

አድራሻ፡-

ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10

የቤት ቁ. 320

ኢሜይል፡- [email protected]

አዘጋጆች፡- ብዙአየሁ ወንድሙ

ብስራት ወ/ሚካኤል

ሰለሞን ስዩም

አርታኢ፡-

አንዳርጌ መስፍን

አምደኞች፡-ዶ/ር ኃይሉ አርአያ

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

ቀለሙ ሁነኛዉ

በለጠ ጎሹ

አንዷለም አራጌ

ደረጀ መላኩ

ኮምፒዩተር ጽሁፍ፡-

ብርቱካን መንገሻ

ህትመት ክትትል፡-

ወንድወሰን ክንፈ

አከፋፋይ፡-

ነብዩ ሞገስ

አሳታሚዉ፡-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

(አንድነት)

አድራሻ፡-አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁ. አዲስ

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክ/ ከተማ ቀበሌ 07 የቤት ቁ.984

የዝግጅት ክፍሉ ስልክ፡- 01 11249659

09 22 11 17 62

09 23 11 93 74

09 13 05 69 42

ፖ.ሳ. ቁ. 4222

ኢሜይል [email protected]

[email protected]

andinet@ andinet.org

ፋክስ ቁጥር ፡-+251-111226288

አሁንም እንጮሃለን !ሕዝቡ ማን እንደሚመራው በግልጽ ማወቅ አለበት

Page 5: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

5Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

እነ ሚሚ በፖፖ ያቀረቡልን ክትፎ

ዳዊት ሰለሞን

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ወደተማሰለት መቃብር እያመራ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱና የሪፖርተሩ አማረ አረጋዊ ትልቅ አጀንዳ በመያዝ ወደ መድረኩ ቀርበዋል፡፡ ከሳምንት በፊት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ‹‹የሚዲያ ካውንስል›› ለማቋቋም ደፋ ቀና ማለት ከጀመሩ 12 ወራት እንደተቆጠረም ሁለቱ ሰዎች ነግረውናል፡፡

የካውንስሉን ረቂቅ ደንብ ለማዘጋጀት የአንድ መቶ አገራትን ልምድ እንደተመለከቱ የጠቀሱት እነ ሚሚ በኢቴቪ መስኮት በመቅረብ ካውንስሉን መመስረታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሚዲያ ካውንስሉን ‹‹የጋዜጠኞች እምባ ጠባቂ›› በማድረግ ልንወስደው እንችላለን፡፡ በተለያዩ ወገኖች ጫና የሚደርስበት ሚዲያ ወይም ጋዜጠኛ በካውንስሉ አማካኝነት የደረሰበትን ሁኔታ በመግለጽ የታፈነ ድምጽ በማህበሩ አማካኝነት እንዲሰማለት ማድረግ ይችላል፡፡ እነ ሚሚ ይዘውልን የቀረቡት ክትፎ ይህ ነው፡፡ ‹‹ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በህገ መንግስቱ እውቅና ተችሮታል›› በማለት የሚያምን ጋዜጠኛ በሞነጫጨራት ጽሁፍ

የተነሳ ‹‹ሽብርተኛ›› የሚል ታፔላ ተለጥፎለት ወደ ቃሊቲ እየተወረወረ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት ‹‹አብረን እንጩህ›› የሚል ካውንስል ለማዘጋጀት ግምባር ቀደም የሆኑ ሰዎችን ማግኘት ማራኪ ነገር ነው፡፡ በህገ መንግስት በይፋ የተሰቀለውን ቅድመ ምርመራ ከመስቀሉ ለማውረድ የቆረጡ ማተሚያ ቤቶች የጋዜጣ ባለቤቶችን የስንግ በያዙበት በዚህ ፈታኝ ሰዓት ካውንስል ሲዘጋጅ የማይቦርቅ የሚዲያ ባለሞያ የት ይኖራል?

ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም እልፍ ሲልም ከዚህ አለም የመሰናበታቸው ዜና ከተለ ያዩ ወገኖች በማጣራት ለህትመት ልትበቃ የነበረች ጋዜጣ በአጋች ታጋች ድራማ ስትታገት ይህንን ነገር ብቻችሁን በመጮህ ልትቋቋሙት አትችሉም የሚሉ ወገኖች ‹‹ማህበር እናቋቁም›› ሲሉ ለተግባራዊነቱ ሁለት እጁን የማያነሳ ማን ነው

የኢትዮጵያ መንግስት ከ 12 መታት በፊት አሁን እነ ሚሚ ያነሱትን ‹‹የሚዲያ ካውንስል ማቋቋም ይገባኛል በማለት የተወሰነ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የነጻ ሚዲያ አባላቱ ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› የምትለውን ብሂል በማስታወስ ‹‹እናንተው እየገረፋችሁን፣እንዴት እንባ መጥረግ የሚችል ማህበር እናቋቁም ትሉናላችሁ?›› በማለት የካውንስሉን በመንግስት መቋቋም በመቃወማቸው ሂደቱ መሬት መርገጥ ሳይችል ቀርቷል፡፡

እርግጥ ነው የሚዲያ ካውንስል የግድ መኖር ይገባዋል፡፡ ጥያቄው ግን ‹‹በማን ይመስረት?›› የሚለው ነው፡፡ የዚህ ካውንስል መስራች በመሆን ሚሚ ስብሃቱን ከአማረ ጎን መመልከት ግን ‹‹ያልጠረጠረ…›› እንድል ያስገድደናል፡፡ የካውንስሉን ምስረታ እውን ለማድረግ በተጓዙት ጉዞ ብዙ እንቅፋቶች ማለፋቸውን የሚጠቅሱት ወ/ሮ ሚሚ

‹‹ካውንስሉን የማደራጀት ሂደታችንን ሊያግቱ ወይም የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የሞከሩ ወገኖች ነበሩ›› ይላሉ፡፡ የእኔም ስጋት የጀመረው እዚህ ላይ ነው፡፡

መቼም መንግስት በእነ ሚሚ የሚመሰረተው ‹‹ማህበር እንቅፋት ይሆንብኛል›› በማለት ላለመስጋቱ አንድ ሺህ አንድ ምክንያቶችን መዘርዘር ይበቃል፡፡ ሴትየዋ ከቪኦኤ ከተሰናበቱ በኋላ በጀመሯቸው ዛሚ ራዲዮ እስካሁን ድረስ ለመንግስት ስጋት አለመሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡ እንደውም መንግስት ሞዴል ጋዜጠኞችን በየአመቱ የሚሸልምበት መርሃ ግብር ቢኖረው ሚሚን ማስከንዳት የሚችል ‹‹ጋዜጠኛ›› ስለመኖሩ ለመጻፍ ብዕሬ ትፈራለች፡፡

የሚሚን ኡኡታ በሰከነ አእምሮ ለመፈተን የሚሞክሩ ሰዎች አባባላቸው ጅራፍ ራሱ ገርፎ አይነት ይሆንበታል፡፡ ሚሚ በሚመሩት የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ ከዚህ ቀደም ባቀረቧቸው ዝግጅቶች የነጻ ፕሬስ አባላትን ስማቸውን ጭምር እየጠቀሱ ‹‹ለምን አይታሰሩም?›› እስከማለት መድረሳቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ‹‹ነጻ ፕሬስ የሚባል ነገር በአለም ላይ የለም ከሚለው ትንተናቸው አንስቶ በመንግስት ላይ የሰላ ትችቶችን የሰነዘሩ ጋዜጠኞችን ለማስወጋት ሲታትሩ እንዳልቆዩ አሁን ደርሶ ሜዳው እንደተመቻቸ በማሰብ ‹‹የሚዲያ ካውንስልን አቋቋምኩ›› ይሉናል፡፡ እውነቱን ለመናገር በአዲስ ዘመን ገጽ 3 በአይጋ ፎረምና በሚሚ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ? እንዴትስ ስውር አጀንዳ ያለው ግለሰብ ‹‹ነጻ ካውንስል ለመመስረት የሚስችለኝ ሞራል አለኝ›› በማለት ደረቱን ገልጦ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ይላል ?

እነ አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስና ፍትህን የመሳሰሉ የህዝብ ልሳኖች በገዢው ግንባር በፈረጠመ ጡንቻ ከአንባቢዎቻቸው

እንዳይገናኙ ሲደረግና ጋዜጠኞቹ ለእስርና ለስደት ሲዳረጉ ‹‹አበጀህ የእኛ ጀግና!›› በማለት አታሞ ሲጎስም የነበረ ሰው በምን መመዘኛው ‹‹ነጻ ካውንስልን መመስረት ይቻለዋል?

ወይዘሮ ሚሚ ከወዲሁ ካውንስሉን መንግስት ያለ ምንም ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ እንደተቀበለው ይነግሩናል፡፡ ‹‹መንግስት መስራች ጉባኤው ያጸደቀውን ደንብ መሰረት በማድረግ ብቻ እንዲጨመር ወይም እንዲቀነስ ሳያደርግ ተቀብሎ የካውንስሉን ምዝገባ እንደሚያካሂድ ቃል እንደገባ ጨምረው ገልጸዋል ›› ( ሪፖርተር )

በአሁኗ ኢትዮጵያ ማህበር ማቋቋም ቀላል የሚሆነው ለነሚሚ ብቻ ካልሆነ ለሌላው የሚደፈር አይመስልም፡፡ ከዚህ ቀደም የተቋቋሙ ነጻ ማህበራትም እንደ እነ ሚሚ የውስጥ ማልያ ባጠለቁ ግለሰቦች ተመሳሳያቸው እየተፈበረከ የነጻዎቹ ህልውና እንዲደበዝዝ ተደርጓል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች አዲስ ማህበር ማቋቋም ይቅርና የነበረውን እንኳ ይዞ መቀጠል ፈጽሞ የማይቻል ሆኗል፡፡ ሚሚ ግን ከወዲሁ ለአዲሱ ካውንስል ከመንግስት ቡራኬ እንደተቀበሉ ይነግሩናል፡፡

መንግስት ካውንስሉን ለማቋቋም ከመጀመሪያ አንስቶ የነበረው ሃሳብ በጊዜው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አድርጎት ነበር፡፡ አሁን ህልሙን በራሱ መንገድ እንዲያሳካ ታግለውት የነበሩ የሚዲያ አባላት ከመድረኩ ገለል በማለታቸው በእነ ሚሚ በኩል ከመንገድ የወጣ እቅዱን ይዞ መጥቷል፡፡ በርዕሴ ለመግለጽ እንደጠቆምኩት ክትፎ በጣባ እንጂ በፖፖ አይቀርብም፡፡ እንዲህ ቢደረግ ግን የክትፎው ክትፎነት ለማንም አይታይም፡፡ የሚዲያ ካውንስሉን የማቋቋም ሃሳብ ለነጻ ሚዲያ አባላት ወሳኝ ቢሆንም ካውንስሉ ልዩ አላማ ባላቸው ሰዎች በኩል ሲቀርብ ማንም የሚቀርበው አይኖርም፡፡

የትግራይ ህዝብና የህወሓት ጉዞ!

ክብሮም ብርሃነ(ከመቐለ)[email protected]

የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ እና የሀገሩን አንድነትና ህልውና ዘብ ሆኖ ሲጠብቅ የኖረ ሕዝብ ለመሆኑ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ተከባብሮ፣ ተዋዶና ተዋልዶ ለዘመናት የቆየ ህዝብ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በኢህአዴግ አገዛዝ ስር ባሳለፋቸው ሃያ አንድ ዓመታት ውስጥ ግን ቀደምሲል በኢትዮጵያ የነበረውን መልካም ታሪክና ስብእና በነ ስብሓት ነጋና መለስ ዜናዊ አደገኛ ጉዞ ምክንያት በሌሎች ወገኖቹ በጥርጣሬ እንዲታይና ታሪካዊ ክብሩን አጥቶ እንዲናቅ እየተደረገ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ህውሓቶች በጠረጉለት የዘረኝነትና የጥፋት መንገድ ይዞ እንዲጓዝ እነሱ ያለበሱትን የብሄር ካባ እንዲለብስ ያልገለበጡት ድንጋይ የለም፡፡ ራሳቸው “ያልተነገረ እንጂ ያልተደረገ የለም” እንደሚሉት፡፡

ህውሓቶች ህዝቡን “ትግራይ ከአንድ ፓርቲ እሱም ህወሓት በስተቀር ሌላ ፓርቲ መሸከም አይችልም” እያሉ የተለያዩ የዘር

ቅስቀሳዎችን በማድረግ አፍነው ሲገዙት ቆይተዋል፡፡ ሌሎች ብሔረሰቦች ግን ሦስትና አራት ፓርቲዎችን እንዲያቋቋሙ ይፈቅዳሉ፡፡ ይሄም ሰብቅ ነው፡፡ ህውሓቶች የሚጠቀሙበት የዘር ፕሮፓጋንዳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ በእነሱ አስተሳሰብና አካሄድ የትግራይ ህዝብ አንዴ ከአማራዎች አንዴ ደግሞ ከኦሮሞዎች እየተፋጨ እነሱ በመሃል ዲሞክራሲያውያን መሰለው ለመታየት ይጥራሉ፡፡ ባህርዳር ሲሄዱ የአማራ ካባ ለነ አዲሱ ለገሰ፣ አያሌው ጎበዜ፣ ተፈራ ዋልዋ፤ አዳማ ሲሄዱ የኦሮሞ ካባ ለነ አባዱላ ገመዳ፣ ጁነዲን ሳዶ፣ ኩማ ደመቅሳ፤ ደቡብ ሲሄዱ ደግሞ የደቡብ ካባ ለነ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ሽፈራው ሽጉጤ እያለበሱ መቀሌ ሲመጡ ደግሞ መለስ ዜናዊ፣ አዜብ መስፍን፣ ስብሓት ነጋ፣ አባይ ፀሐዬ፣ አርከበ እቁባይ፣ ደብረ ጽዮን ወዘተ ድርብ ካባ ማለት የህወሓትና ኢህአዴግ ካባዎች ለብሰው ዲሞክራሲያውያን በመምሰል የመግዛት ዕድሜያቸውን ሲያራዝሙ ቆይተዋል፡፡ አሁንም በዚሁ መንገድና አሠራር እንደ ቀጠሉበት ነው፡፡

በየአደባባዩ ስለ ብሔር (ብሄረሰቦች) እኩልነት ሲያወሩ የልባቸው እምነት ሳይሆን የኢትዮጵያውያን (ከኢህአዴጎች) በስተቀር የጋራ ፍላጐት መሆኑን ስለሚያውቁ የብሄር ብሄረሰቦችን ካባ እያለበሱ በየክልሉና በየቀበሌው ሲወርዱ ግን ካባቸውን ጥለው ዘረኛ ፖለቲካ ሲያራምዱ እያየናቸው ነው፡፡ የቅጥፈትና የማታለል ቢሆንም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ “የብሔር ብሔረሰቦች ቀን” ተብሎ በያመቱ እየተከበረም ነው፡፡

ለምሳሌ የትግራይ ህዝብ ለብቻው ተነጥሎ እንዲኖርና የህወሓትን ኢ-ፍትሓዊ አስተዳደር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ሆኖ እንዳይታገል ያልዘሩት የጐሳና የዘር ፖለቲካ

የለም፡፡ አሁንም በስውርም ሆነ በግልጽ እየቀሰቀሱ ናቸው፡፡

እውነቱ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ የሚያወሩት እኛ ስለምናውቃትና እየኖርን ያለንባት ትግራይ ከሆነ ህዝቡ የሚፈልገው ልማትና መልካም አስተዳደር የለም፡፡ የትእምት (EFERT) ድርጅቶችን በሚመለከትም ብዙ ጊዜ እንደተነገረው ስማቸው የትግራይ ህዝብ ይባሉ እንጂ ገቢያቸው ግማሹ በነጠ/ሚ መለስ፣ አዜብ መስፍን፣ ስብሓት ነጋ እህታቸው ቅዱሳን ነጋ (የሃለቃ ፀጋይ ሚስት መሆንዋ ነው)፣ ለነ አባይ ፀሐየ፣ ለነስዩም መስፍን ወዘተ የሚከፋፈሉት ነው፡፡ የህውሓት መሪዎች የትእምት (EFERT) ድርጅቶችን ገቢ ልጆቻቸው በቻይና እና በአውሮፓ ተምረው እንደገና በልጆቻቸው እንድንገዛ እያስተማሩበት ነው፡፡ የተቀረውን ገቢ ደግሞ ትግራይ ውስጥ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ ከተቻለ እንዳይፈጠር ካልተቻለ እንደይንቀሳቀስ ማፈኛ፣ የዘር ፖለቲካ እየዘሩ ለሚውሉ በሆዳቸው ለሚያስቡ ካድሬዎች አበልና ደመወዝ ወዘተ እንደ ግል ንብረታቸው አድርገው የተጠቀሙበት እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች እስከ አሁን ለትግራይ ህዝብ ሆስፒታል ይቅርና አንድ ጤና ኬላ፣ ከፍተኛ ት/ቤት ይቅርና አንድ ኤለመንታሪ ት/ቤት፣ በኪሎ ሜትር የሚለካ መንገድ ይቅርና አንድ ሜትር (ከብልስቶን) እንኳን ጭራሽ አልሰሩም፡፡

ሁሌ የሚያሳስበኝ አንድ ነገር አለ፡፡ የህወሓት ካድሬዎች የአማራን ህዝብ “በነፍጠኝነት” ስምና የዘር ፕሮፓጋንዳ በየቀበሌው ሲያወሩ እንደሚውሉ የብአዴን/ኢህአዴግ መሪዎችና አባል ነንባዮች ያውቁ ይሆን? ለነገሩ የግላቸውን ጥቅም አስካልተነካ ድረስ ሰምተው እንዳልሰሙ ተመሳስለው መሄድ ስለሚመርጡ ነው፡፡

እንዲህ ከሆነ ምን ያክል ህሊናቸውን ሽጠው እየኖሩ እንደሆነ ሊረዱ ይገባቸዋል፡፡

ይሄ ባይሆን ኖሮ የአማራ ህዝብ “በነፍጠኝነት” ስም 21 ዓመታት ሙሉ በማያባራ ሁኔታ የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ መሆን አልነበረበትም፡፡ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በየትኛውም ጊዜ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጋር ተባብሮ የሀገሩን ክብርና ዳርድንበር እንዲሁም ታሪክ ሲጠበቅ የኖረ እንጂ ፀረ የትግራይ ህዝብ ሆኖ አያውቅም፡፡ አለ ከተባለ ደግሞ በተጨባጭ ጊዜውንና ቦታውን ለይተው እስከነ ጥፋቱ ለትግራይ ሕዝብ ሊነግሩት በተገባ ነበር፡፡

አሁን አሁን የትግራይ ህዝብ በተለየ መልኩ የህወሓት/ኢህአዴግ ተንኮልና ሴራ ጠንቅቆ በማወቅ በድፍረት ህወሓትን ማጥላላትና መቋቋም ጀምሯል፡፡ ለምሳሌ የመድረክ አባል ፓርቲ የሆነው “ዓረና ትግራይ” በአብዛኛዎቹ የትግራይ ትልልቅ ከተሞችና ወረዳዎች በተደጋጋሚ በመድረክ የሚነሱ በኢህአዴግ እየደረሱ ያሉ የፖለቲካ አፈናዎችና ኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግር ምንጫቸውን የሚያብራሩ በራሪ ወረቀቶች (leaflet) በአባላቱ ለህብረተሰቡ ሲሰጥ ይታያል፡፡ ህዝቡም “አይዟችሁ፤ ጠንክሩ፤ በርቱ፣ መጭው ጊዜ የናንተ ነው ወዘተ” በማለት ድጋፉን እያሳየ ነው፡፡

የህወሓት ካድሬዎች እየተከታተሉ በህብረተሰቡ ላይ ጫና ለመፍጠር ቢሞክሩም እየተሳካላቸው አይደለም፡፡ ከእንግዲህ በኋላ አስፈራርቶ ማፈን እንደማይችሉ የተረዱ ይመስላሉ፡፡ ገና ደግሞ በደምብ ይረዳሉ፡፡ ስልጣን ህዝብ ማገልግያ እንጂ ደሃ ማስፈራሪያ አይደለም!

Page 6: News Paper No. 54 colour.indd

6 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

www.andinet.org

6 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ኢህአዴግ የህዝብ አመኔታያጣ መንግስት ስለሆነ ሥልጣኑንለህዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል

የዛሬው እንግዳችን ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናቸው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ በአሁኑ ጊዜ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ

ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ም/ሊቀመንበርና የፋይናንስ

ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ በወቅታዊ ጉዳዮች ከባልደረባችን

ብዙአየሁ ወንድሙ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ ግን ለብዙ ጊዜ ደብቆናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ መታመማቸውን የሰማነው ከሴኔጋሉ መሪ ነው፡፡ ቀጥለው እጅግ በጣም ዘግይተው አቶ በረከት ተናገሩ ይህም ግልጽነትና ተጠያቂነትን በጣሰ መልኩ ነው፡፡

እንዴት ነው ግልጽነትና ተጠያቂነትን የጣሰ ነው ሲባል?

አቶ መለስ ግለሰብ አይደሉም፡፡ ከአንድ አካባቢ በህዝብ ተመርጠው የመጡ የህዝብ ወኪልና የአገር መሪ ናቸው፡፡ ሲታመሙ ወዲያውኑ በግልጽ ለህዝብ መገለጥ አለበት፡፡ በግልጽ አለመግለጽ ደግሞ ተጠያቂነት አለው፡፡ በሌሎች አገሮች የሚደረገው ይህው ነው፡፡ መሪው ታሞ ሆስፒታል ሲገባ ወዲያውኑ ለህዝብ ይገለፃል፡፡ የህመሙ ዓይነት የሚገኝበት ሆስፒታል የሚያክመው ሐኪም ህዝብ የማወቅ መብት አለው፤ ያለበት የጤንነት ደረጃ በምስል እየተደገፈ ይፋ ይደረጋል፡፡ በየወቅቱ ባለቤቱ በግልጽ እየቀረበች ለህዝብ ታስረዳለች፡፡ ኮሚኒስት አገሮች ድብቅ ናቸው ይባላል፡፡ ይሁን እንጂ ኩባ መሪዋ ሲታመሙ ግልጽ አድርጋለች፤ የፊደል ካስትሮ የጤንነት ሁኔታ የኩባ ህዝብ እግር በእግር እየተከታተሉ ናቸው፡፡ የሕዝብ የማወቅ መብት አለው፡፡ የህዝብ የማወቅ መብት ተጥሷል፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ እንዳይታመን አድርጐታል፡፡ አመኔታ አጥቷል፡፡ አመኔታ ያጣ መንግስት ደግሞ ተጠያቂነት አለበት፡፡ ህዝብ ኢህአዴግን መጠየቅ አለበት፡፡ ታአማኒነትን ያጣ ድርጅት ደግሞ አገር መምራት አይችልም፡፡ አገር ለመምራት መታመን የግድ ነው፡፡

መንግስት በተደጋጋሚ

አሉቧልታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልፃDል፡፡ በየጊዜው ለሚፈጠሩ አሉባልታዎች መልስ መስጠት እንደሌለበት እያስረዳ ነው፡፡ ምን ያድርግ?

የአሉቧልታውን መንገድ የከፈተው ራሱ ኢህአዴግና መንግስት ነው፡፡ የግልጽነት መጥፋት ነው፡፡ የየዕለቱ መልካቸው ሁኔታ ለህዝብ ይፋ ቢሆን የህመማቸው ዓይነትና ያሉበት ቦታና ያሉበት ሁኔታ እግር በእግር ቢገለጽ ምንም ዓይነት አሉቧልታ አይፈጠርም፡፡ ስለዚህ በየዕለቱ ለሚፈጠረው አሉቧልታ ተጠያቂው መንግስት ራሱ ነው፡፡ ሰለዚህ አንቀጽ 12 ተጥሷል፡፡ ኢህአዴግና መንግስት ተጠያቂ ናቸው፡፡ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት እንዴት ነው ህዝቡን አሉቧልታ አወራችሁ ብሎ ማለት የሚችለው? ለምን ህዝብ ይዋሻል? ለምን ህዝብ ይደበቃል? ለምን ያለውን እውነት አይናገሩም፡፡ ህዝብ ስለመሪው ትላንትም ዛሬም ነገም ማወቅ ይፈልጋል? ማ እንደሚመራው ይጠይቃል፡፡ ሲደበቅ የየራሱን ግምት እየወሰደ ሊነጋገር ይችላል፡፡ በዚህ ወቅት አሉቧልታ ተወራ ብሎ መናገር አይችልም፡፡ መፍትሄው ስለጠ/ሚኒስትሩ እውነተኛውን ነገር መነገር አለበት፡፡

በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን የሚመራው ማን እንደሆነ አይታወቅም ይባላል፡፡ ምን አስተያየት አልዎት?

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 75 ፊደል ተራ (ለ) እንዲህ ይላል፡፡ “ጠ/ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፡፡ “ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት ጠ/ሚኒስትሩ ከሌሉ አገሪቱን መምራት ያለበት ም/ጠ/ሚኒስትሩ ናቸው፡፡ ለስንት ጊዜ እንደሆነ ግን ህገ መንግስቱ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡ አገሪቱ ከዚህ በላይ በም/ጠ/ሚኒስትር መመራት የለበትም ብሎ ም/ቤቱ ካመነበት አዲስ ጠ/ሚኒስትር

ሊመርጥ ይችላል፡፡ ም/ቤቱ አዲስ ጠ/ሚኒስትር እስካልመረጠ ድረስ ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ሥራቸው እስኪመለሱ ተክቶ መሥራት ያለበት ም/ጠ/ሚኒስትሩ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አሁንም ኢህአዴግ የህገመንግስቱ አንቀጽ 75 ፊደል ተራ (ለ) ተጥሷል ማለት ነው፡፡ ይህም ያስጠይቃል፡፡ ም/ጠ/ሚኒስትሩም በህገመንግስቱ መሠረት የተሰጣቸው ሥልጣን ኃላፊነት ካልተወጡ መታወቅ አለበት፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ ሥራ ላይ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ሰሞኑን ም/ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱን ለቀው ቻይና ነበሩ፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ አገሪቱን ለቀው መሄዳቸውስ ተገቢ ነው?

ሁለቱም በአንድ ጊዜ አገር ለቀው መሄዳቸው ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ጥሪ ቢደርሳቸውም እሳቸውም ምክትል ስለአላቸው ምክትላቸውን መላክ አለባቸው እንጂ ጥሪ ደርሶኛል ብሎ መሄድ የለባቸውም፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡

በእርስዎ እምነት ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

ኢህአዴግና መንግስት ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፡፡ የሕዝብ አመኔታንም አጥተዋል፡፡ አንድ የህዝብ አመኔታ ያጣ ተመራጭ ወይም የህዝብ አመኔታ ያጣ ድርጅት በማንኛውም ጊዜ ከቦታው ሊያነሳው ይችላል ይላል፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ የህዝብን አመኔታ ስለአጣ ከቦታ ሊነሳ ይገባል፡፡ አግኝቼአለሁ የሚለውን የህዝብ ውክልና አመኔታ ስለአጣ ለህዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡

ሙስሊሞች ከመንግስት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል፡፡ መንግስት “አክራሪዎች” ይላል፡፡ አስተያየት ይኖሮታል?

መንግሥት አንዳንድ ጊዜ ተቃዋሚዎች በህገ መንግስቱ አጥር ዙሪያ አይንቀሳቀሱም እያለ ይገልፃል፡፡ ፓርቲያችሁን ከዚህ አኳያ እንዴት ይመለከቱታል?

ፓርቲያችን ህገ መንግሥቱን መሠረት አድርጐ የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡ የሚንቀሳቀሰው ህገ መንግስቱን አክብረን ነው፡፡ እኛ በእርግጠኝነት ህግን አክብረን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡ የፓርቲያችን ደንብና ፕሮግራምም አደረጃጀታችንም ለህገወጥ ተግባር የተጋለጠበት አንዳችም ክፍተት የለውም፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ አማራጭ ያላቸውን ጠንካራ ህጋዊ ፓርቲዎችን በተለያየ ጊዜ “ተለጣፊ ስም” እየለጠፈ ይፈርጃቸዋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ኢህአዴግ “በምርጫ አሸንፌ አገር እየመራሁ ነው” ይላል፡፡ በተግባር ግን ራሱ ያወጣውን ህገመንግስት እየጣሰ ያሻውን ሲያደርግ ይታያል፡፡ ከዚህ ተግባሩ መቆጠብ አለበት፡፡ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

ኢህአዴግ ህገመንግስቱን ጥሷል የሚያሰኝበት ምን አለ?

የህገ መንግስቱ አንቀጽ 12 ምን ይላል መሰለህ “ ፩ የመንግስት አመራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፡ ፪ ማንኛውም ኃላፊና የህዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ፫ ህዝብ በመረጠው ተወካይ ላይ እምነት ባጣ ጊዜ ከቦታው ለማንሳት ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል፡፡ “ ይላል፡፡ ኢህአዴግ ግን ግልጽነትንና ተጠያቂነት የሚለውን ጥሷል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ የአቶ መለስን ጤንነት በግልጽ

ኢህአዴግ በተለያየ ጊዜ በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ይገባል፡፡ በለመደው መሠረት መንግስት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እየከፋፈላቸው ነው፡፡ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ የሚፈታው በራሱ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ውይይትና ውሳኔ ነው፡፡ አንዱን ቡድን ደግፎ ሌላውን ቡድን በመጥፎ ፈርጆ እርምጃ መውሰድ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ የሰደቃ በዓላቸውን ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ሳሉ ደህንነቶች አወሊያ መስጊድ ገብተው የወሰዱት እርምጃ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ እምነቱን ደፍረዋል፡፡ ችግሩን የፈጠሩ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ጉዳዩ በገለልተኛ አካል መጠራት አለበት፡፡ “ተወካዮቻችሁን በቀበሌ ምረጡ” የሚለው አካሄድ ሌላው ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡ የቀበሌ መስተዳድር የሙስሊሙን መሪዎች ለማስመረጥ የሚችለው በምን አግባብ ነው፡፡ ኢህአዴግ ለምን በማያገባው ቦታ ላይ ሁሉ እጁን ማስገባት ይፈልጋል፡፡ የመንግስት መዋቅር በሃይማኖቱ ውስጥ ምን አገባው? መጅሊሳቸውን በመስጊዳቸው መምረጥ አለባቸው፡፡ በጥቅሉ ኢህአዴግ እጁን ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት መሰብሰብ አለበት፡፡

በቅርቡ ከገጠመዎት ህመም ህክምና ላይ መቆየትዎ ይታወቃል፡፡ አሁን ጤንነትዎ እንዴት ነው?

አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ፡፡ እኔ በአሁኑ ጊዜ እንደሚታወቀው የሙሉ ጊዜ የፓለቲካ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ሥራዬን ከጀመርኩ ሁለተኛ ሳምንቴን ይዤአለሁ፡፡ የታዘዘልኝን መድኃኒት በአግባቡ እየወሰድኩ ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በየ6 ወሩ በሐኪም መታየት ይጠበቅብኛል፡፡ ከዚያ ውጪ ሥራዬን በተገቢው ሁኔታ እየሰራሁ ነው፡፡

Page 7: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

7Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

የሚፈስ ነውና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቅንጅት በኋላም ቢሆን “ወፌ ቆመች” እየተባሉ ነው፡፡ በተለይም በቅንጅት ውስጥ የነበሩ ቁልፍ ሰዎች አሁን ያለውን “አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ” በመመስረት መንቀሳቀስ ሲጀምሩ “በመርህ ይከበር” ጂኒ ታመሱ፡፡ ያም እንደ ሀምሌ ክረምት አለፈና ዛሬ ይህ ፓርቲ በጥሩ መሠረት ላይ ሊቆም ችሏል፡፡ ሕብረ ብሄር ፓርቲም በመሆኑ የተሻለ የህዝብ ድጋፍና ይሁንታ አለው፡፡

የዛሬው ፅሁፌ በብርቱ የሚያንኳኳው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በር ነው፡፡ ከዚህ በፊት እንወዳት በነበረችው ፍትህ ጋዜጣ ላይ አዘጋጁ ተመስገን ደሳለኝ በሰላ ብዕሩ ራሳቸውን እንዲመረምሩ በሚገባ ገልጧቸዋል፡፡ ግን አይበቃም፡፡ ምክንያቱም ለኢህአዴግ እድሜ መራዘም የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አስተዋፅኦም የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለነፃነትና ዲሞክራሲ ትግሉም መቀዛቀዝ ያሳደሩትና እያሳደሩ ያሉት አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት በመላ አገሪቱ (በፌደራል እና በክልል ደረጃ) የተዋቀሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቁጥር እስከ 90 እንደሚደርሱ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ሀቀኛ ወይም ጠንካራ ተቃዋሚ አይደሉም፡፡ “የህዝብ ብሶት የወለዳቸው” እንዳሉ ሁሉ ከኢህአዴግ አብራክ የተከፈሉም ቁጥራቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ እነዚህ በተቃዋሚ ፓርቲ ስም የምርጫ ወቅት ሙሽራውን ኢህአዴግን ለማጀብ የሚታደሙ ናቸው፡፡ ማለዳ ታይተው ማምሻውን የሚከስሙ፣ አድራሻቸው በውል የማይታወቅ ዓላማና ራዕይ የሌላቸው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ናቸው፡፡ ለኢህአዴግ መድብለ ፓርቲ አለ እንዲባል ጥሩ መጋረጃዎች ናቸው፡፡

ከቅንጅት መፈረካከስ በኋላ ሲውተረተሩ የምናያቸው ነባርም ሆኑ አዳዲስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁልቆ መሣፍርት በሌላቸው ችግሮች የተተበተቡ ናቸው፡፡ “ውስጡን ለቄስ” እንዲሉ ከሚጠሩበት ስያሜና ከምርጫ ቦርድ የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በዘለለ ውስጣቸው ሲፈተሽ እያሉ አለመኖራቸውን ያረጋግጣል፡፡

ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ መተዳደሪያ ደንብ፣ ማኒፌስቶ የፓርቲ አባላት፣ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚለው አይታሰብም፡፡ አንዳንዶቹማ ቢሮ እንኳን የላቸውም፡፡

ብልጭ ድርግም በሚለው የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ውስጥ ውር ውር ሲሉ የምናያቸው ተቃዋሚዎች (አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል) የቆሙበት መሠረት በብሄር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እነሱም ኢህአዴግ በሄደበት መንገድ ነው ጉዟቸውን የጀመሩት፡፡ በመሀከላቸው ሰፊ ገደል አለ፡፡ የአንድን ብሄር ነፃነት ለማረጋገጥ በተነሳ ፓርቲና ብሄራዊነትን በሚያቀነቅን ፓርቲ መሀከል ያለውን የዓላማ ልዩነት ተቃርኖ ለማስታረቅ ስርዓቱን ከመታገል በላይ የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ይሄን ልዩነት በውይይትና ተቀራርቦ በመማማር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ቢደረስ እንኳን በውስጣቸው የሚጦዘው የስልጣን ሽኩቻ ብርቱ ጋሬጣ ነው፡፡

በምርጫ 2002 የቅንጅትን መንገድ ተከትሎ ለውድድር ብቅ ያለው መድረክ ሰሞኑን ወደ ግንባር መሸጋገሩን ቢያውጅም “ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ” እንዲሉ ነው፡፡ እንደ ሰንበቴ ጥዋ የመድረክ አባል ፓርቲ መሪዎች የሊቀመንበርነት ቦታውን በየተራ ቢይዙትም እርስ በርስ ከመሻDኮትና ከጋዜጣዊ መግለጫ በዘለለ ሲንቀሳቀሱ አይታይም፡፡ እነዚህ የመድረክ (የግንባር) ስብስብ ፓርቲዎች የራሳቸውን ልዩነት እያጣበቡ ሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለመሳብ አይዳዳቸውም፡፡ ለምሳሌ ከአገሪቱ ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘውን የኦሮሞ ብሄረሰብ እንወክላለን የሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደት ፈጥረው አንድ ጠንካራ ፓርቲ ለመመስረት ለምን ተሳናቸው? አላማቸው የኦሮሞን ህዝብ እምባ ለማበስና ጥቅሙን ለማስከበር ከሆነ ለምን አስር ቦታ መበጣጠስ አማራቸው? በአዲሱ ግንባር ውስጥ የታቀፉትም ሆኑ ብቻቸውን ተገልለው ያሉት ልዩነቶቻቸውን አጥበብውና አቻችለው ለመዋሃድ ለምን አመነቱ? ዛሬ በአቶ መለስ መታመም በኢህአዴግ ሰማይ ላይ ፍርሃትና

ሽኩቻ ባንዣበበት ወቅት በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ለማድረግ መንቀሳቀስ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡

የአቶ መለስ ዜናዊን ለ21 ዓመታት በመሪነት መቆየት አይናቸውን በጨው አጥበው የሚኮንኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ራሳቸው ማየት አቅቷቸዋል፡፡ አቶ መለስ ይህን ያህል ጊዜ በመሪነት ቢቆዩም ይብዛም ይነስ የፓርቲያቸውን ዓላማ እያሳኩ ነው፡፡ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ የተወሰኑትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በወፍበረር እንቃኛቸው

ዶ/ር መረራ ጉዲና (ከኦብኮ እስከ ኦፌኮ)

ፓርቲያቸው “ከርሞ ጥጃ . . .” ወይም ‹አድሮ ቃሪያ› እንዲሉ ነው፡፡ እሳቸው “ኦብኮ” በኢህአዴግ የከፋፍሎ መግዛት የፖለቲካ ጎራዴ ከተሰነጠቀ በኋላ “ኦህኮን” መስርተው ሲመሩ ቆዩ፡፡ ከቅርብ ጊዜያት በፊት ኦህኮ እና ኦፌዴን ተዋሃዱ፡፡ ይሄ ትልቅ አርአያነት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሊመሰገኑ የሚገባቸው ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ከ2002 ምርጫ በኋላ የፓርቲውን መሪነት መልቀቃቸው ዲሞክራት ሰው መሆናቸውን ይመሰክራል፡፡ ነገር ግን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሲመሰረት ዶ/ሩ ሊቀመንበር ሆነው ብቅ ከማለት ይልቅ ለሌላ አዲስ ሰው ቢለቁ የተሻለ በሆነ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ ሙዝዝ ማለታቸው ግን ያሳዝናል፡፡ ያውም የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ሆነው፡፡ ይህ ባህሪያቸው የስልጣን ጥማት እንጂ የጤንነት አይመስለኝም፡፡ እኒህ ሰው በምን የሞራል ብቃታቸው ነው ኢህአዴግን የሚቃወሙት? እሳቸው አድርገው ያላሳዩንን አቶ መለስ እንዲያደርጉት መታገል “ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ” እንዲሉ ነው፡፡ እኒህ ሰው ሀገር የመምራቱን ስልጣን ቢያገኙ ከህዝብ ጫንቃ ላይ በቀላሉ የሚወርዱ አይመስልም፡፡ በኦብኮ ዘመን የነበራቸው ተቀባይነት ዛሬ

የማይጠረቃው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትግልና የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ

እየተንገዳገደ ያለውን የኢህአዴግ መንግሥት እንዴት መተካት ይቻላል?

ቀለሙ ሁነኛው[email protected]

ትግል ፍፁም ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡ትግል የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር ያስከፍላል፡፡ በተለይም ለነፃነትና ለዲሞክራሲ መስፈን የሚደረገው ትንቅንቅ እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ የዛሬዎቹ የህወሓት ኢህአዴግ መሪዎች የመረረ ትግል አድርገው ሥልጣን ቢይዙም ከተዋደቁለት አላማ አንፃር ይሄ ነው የሚባል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አልቻሉም፡፡ ወታደራዊው ደርግ በስልጣኑ ዘመን መጀመሪያ ላይ ያደርግ የነበረውን ኢህአዴጎች ደግሞ በስልጣናቸው ዕድሜ ማብቂያ ላይ እየደገሙት ይገኛሉ፡፡ ወታደራዊውን ደርግ ክፉኛ የተገዳደረው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የወቅቱን ትግል (በተለይም ኢህአፓን የመሳሰሉት) በቀይ ሽብር አሰቃቂ የግድያ ዘመቻ እስከ ወዲያኛው ማሸመድመድ አልተቻለም፡፡

ኢህአዴግ ወደ ስልጣን የመጣው በጠብመንጃ አፈሙዝ በመሆኑ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት አይፈልግም፡፡ በዘመነ ኢህአዴግ የ21 ዓመታት አገዛዝ ጎልቶ ለወጣው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር ስሙ የገነነው ቅንጅት ነው፡፡ በወቅቱ ለተመዘገበው የሕዝብ ድምጽ ተጠቃሹ የቅንጅት ጥንካሬ ሳይሆን የሕዝቡ ገዢውን ፓርቲ ባለመፈለግ በሚያስደንቅ ሁኔታ መንቀሳቀሱ ነው፡፡ በምርጫው የመጨረሻዎቹ ወራት ቅንጅት በሚል ስያሜ የተሰባሰቡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በእርግጠኝነት ያሸነፉ ቢሆንም የኢህአዴግ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ገሀድ የወጣበት ሆኖ አልፏል የቅንጅት መሪዎችም ከእስራታቸው ዘመን በኋላ የእምቧይ ካብ ሆኑ፡፡ ቋንቋቸው ተደበላለቀ፤ ዳግሞ ላይገናኙ ተለያዩ፡፡ ደካማ ጎናቸውን በውል ያጤነው ኢህአዴግ በቆረጣ እየገባ ቆራረጣቸው፡፡ በትግሉ ወቅት በህዝቡ ልብ ውስጥ ሰርፀው የገቡት የፓርቲው መሪዎችም ማንነታቸው ገሀድ ወጣ፡፡ አክ እንትፍ ተባሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ኢህአዴግም የልብ ልብ ተሰምቶት እስከ ዛሬ አውራ ፓርቲ ሆኖ ይገዛል፡፡

ትግል እንደ ወንዝ ጅረት በጋ ተክረምት

ብርሃኔ ዘውዱ

መጀመሪያ፣ “ኢህአዴግ እውን እየተንገዳገደ ነው? አንድ መንግስት በሁለት እግሮቹ መቆም አቅቶት፣ ተንገዳገደ የሚባለውስ ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው?” ብለን እንጠይቅ፡፡

በ1993 የኢህአዴግ ዋና የሥልጣን መሠረት የሆነው ህወሓት ለሁለት ሲሰነጠቅ ኢህአዴግ በእርግጥም ተንገዳግዶ ነበር፡፡ ሆኖም አቶ መለስ “አንጃ” ያሉትን የእነ አቶ ስዬን ቡድን ከሥልጣን በማባረር ኢህአዴግን ከውድቀት አድነውታል፡፡ ከዚያ ወዲህ ደግሞ በ1997 ቅንጅት በምርጫ ሲያሸንፍ ኢህአዴግ በድጋሚ ተንገዳግዶ ነበር፡፡ ከዚያም አግአዚ በሕዝቡ ላይ በአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ ኢህአዴግ እንደገና የህይወት እስትንፋሱን ሊያገኝ ችሏል፡፡

አሁን ደግሞ ኢህአዴግን እያንገዳገዱት ያሉት፣ የአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ፣ የሕዝቡ ጥላቻ ጫፍ መድረሱና የአቶ መለስ ዜናዊ መታመም ናቸው፡፡ የአሜሪካ መንግሥት በኢህአዴግ አመራር ላይ “አሳስቦኛል” እያለ የሚያወጣቸው መግለጫዎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ በተለይ ከእነ አንዱዓለም አራጌ እና ከእነ እስክንድር ነጋ መታሰር በኋላ የአሜሪካ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅቶች የሚያወጧቸው መግለጫዎች እየጠነከሩ መሄዳቸውን ከውጭ የዜና አውታሮች ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል እየተባባሱ የመጡት የኢኮኖሚ ችግሮች (የዋጋ ንረት፣ ስራ አጥነት፣ የመኖሪያ ቤት ችግር ወዘተ) የኢህአዴግን መንግሥት ከመቼውም በበለጠ በህዝብ እንዲጠላ እያደረጉት ይገኛሉ፡፡ የኑሮው ሁኔታ እጅግ ያስመረራቸው መምህራን (የኢህአዴግ አባላት የሆኑትም ጭምር) የሥራ ማቆም አድማ እስከማድረግ የዘለቀ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ኢህአዴግ በሃይማኖቱ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም እጅግ ግዙፍ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያካሄደ ነው፡፡

ሐቀኛ ተቃዋሚዎች “የተቀነባበረ ሰላማዊ ተቃውሞ ያካሄዱብኛል” በማለት ኢህአዴግ እንደ እነ አንዱዓለም አራጌ ያሉትን ትንታግና ወጣት የፖለቲካ መሪዎች እሥር ቤት ቢያጉርም ከስጋት ነፃሊሆን አልቻለም፡፡ እንደ ቀድሞ ጊዜ ጠንካራ ባይሆኑም፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም የኢህአዴግን “ከፍተኛ ትምህርት ለድንጋይ ጠራቢነት” የሚለውን የትምህርት ፖሊሲ በጩኽት ተቃውመዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የአቶ መለስ መታመም ከሁሉም በላይ ኢህአዴግን ከፉኛ አስደንግጦታል፡፡ ኮሚኒስቱን መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ከሥልጣን በማውረድ፣ በዓለም አቀፉ የፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻ አጋር በመሆንና የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ እና በአጠቃላይም በአፍሪካ

አህጉር የሚከተለውን የውጭ ፖሊሲ በመተግበር የምዕራብያውያንን አመኔታና ድጋፍ ያገኙት አቶ መለስ መታመማቸው ለኢህአዴግ ትልቅ አስደንጋጭ ክስተት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አቶ መለስ አንድ ነገር ቢሆኑ ማን ይተካቸዋል?

ከላይ እንደተመለከተው አቶ መለስ የታመሙት ከአሜሪካ መንግሥት ሲቸራቸው የቆየው ድጋፍ እየተሸረሸረ በሄደበት ጊዜ መሆኑ ለኢህአዴግ ትልቅ ሥጋት ፈጥሮአል፤ ምክንያቱም የአሜሪካ መንግሥት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የራሱን ብሔራዊ ጥቅም በማይነካ መንገድ በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ የሚመጣበትን ሁኔታ ሊያመቻች ይችላል፡፡ ማንኛውም ሐቀኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሽብርተኝነትን አጥብቆ ይቃወማል፡፡ እንዲሁም፣ የአሜሪካ መንግሥትን የአፍሪካ ፖሊሲ የሚቃወምበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ በሌላ በኩል ሁሉም ሐቀኛ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ በተጨባጭ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና የዘመናዊነት (democratization and modernization) ሂደት ተጀምሮ እውን እንዲሆን አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡ ታዲያ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እየገነባ ብሔራዊ ጥቅሙን የሚያስጠብቅለት መንግሥት

እንዲቋቋም አይፈልግም ማለት ይቻላል?

በአጠቃላይ፣ የሕዝብ ተቃውሞ እየጨመረ መምጣት፣ ኢህአዴግ ከልዕለ ኃያሉ የአሜሪካ መንግሥት ይቸረው የነበረው ድጋፍ እየተሸረሸረ መምጣትና የአቶ መለስ መታመም ኢህአዴግ እንደገና እየተንገዳገደ ለመሆኑ አሳማኝ ምልክቶች ይመስሉኛል፡፡

የሚንገዳንድ መንግሥት ደግሞ ራሱን ከውድቀት ለማዳን ሲል ጭካኔ የተሞላባቸው እርምጃዎች እንደሚወስድ የታወቀ ነው፡፡ እነ አንዱዓለም አራጌንና እና እስክንድር ነጋን በሐሰት ውንጀላ ዘብጥያ አውርዶ እያስቃያቸው ነው፡፡ የሃይማኖት ነፃነት መብታቸውን የጠየቁ ሙስሊሞችን እየቀጠቀጣቸው ነው፤ እጅና እግራቸውን እየሰበረ ነው፤ እስር ቤት ወርውሮም እያሰቃያቸው ነው፡፡ አስተማሪዎች ለምግብ እንኳን የማይበቃው ደመወዛቸው ይጨመርልን ብለው በጠየቁ፣ ከሥራ እና ከደመወዝ አግዶአቸዋል፡፡ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትንና ተነባቢነትን ያገኘችውን “ፍትሕ” ጋዜጣ አግዶአል፤ ይህን መጣጥፍ በማዘጋጅበት ጊዜም እንደታገደች ነው፡፡

እዚህ ላይ እንቆቅልሹ “ትንሽ ገፋ ቢያደርጉት የሚወድቅን መንግሥት ሕዝቡ እንዴት በጥበብ ሊጥል ይችላል?” የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሐቀኛ ተቃዋሚዎች ለሰላማዊ ሰልፍ ወይም

ወደ ገፅ 15 ይዞራል....

ወደ ገፅ 14 ይዞራል....

Page 8: News Paper No. 54 colour.indd

8 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

www.andinet.org

8 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

yxdÆÆY MS-!éCyxdÆÆY MS-!éC

ለኑዛዜ ሳልበቃ ልሳኔን ይዝጋው!

የአፍሪካ መሪዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ መፈፀም ያለባቸው ቃለ መሃላ በተለመደው የመሃላ ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን ጨብጠው ሣይሆን በሚከተሉት የቃለ መሀላ ዓይነቶች መሆን አለበት፡፡

- ሕዝቤን ለረጅም ጊዜ ከላዩ ላይ ተጎልቸ በሥልጣን ብልግና ባጉላለ እንደ ሙሐመር ጋዳፊ “አይጥ” ባሏቸው አይጥ ጉድጓድ ውስጥ ተወሽቄ ተይዠ በጥይት ግንባሬን ልቦረቀስ!

- ህዝቤን ብንቅና ባንጓጥጥ እንደ ሁሴን ሙባረክ በፈነጨሁባት አገር ተዋርጄ በቃሬዛ ተገፍቼ ፍ/ቤት በመቅረብ 20 ዓመት ያኮናነበኝ!

- ሕዝቤን እያነኩ ብገደል እንደ ኢዲያሚን ዳዳና እንደ ሲያድባሬ ተዋርጄ ካገሬ ተባርሬ ላገሬ አፈር ሳልበቃ በዚያው ያስቀረኝ!

- በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር አቧድኘ ባጨፋጭፍና እንደ አንበሳ ባገሳሁባት አገር እንደ ውሻ ጅራቴን ሸጉጨ ወደ ጎረቤት አገር ያስፈርጥጠኝ!

- እንደ ታምራት ላይኔ አለሁ አለሁ ብዬ ስኳር ስልስ ወደ እስር ቤት ተወርውሬ ከሥር ስለቀቅ ሃይማኖቴን ቀይሬ ካገር ብን ብዬ ልጥፋ!

- “የሰው ምላስ እንኳን ሰው እንጨት ያደርቃልና” ሕዝቤን በጎሳ፣ በነገድ . . . ከፋፍዬ ባዳማ፣ የባሕር በር ባሰጣ፣ የአገሬን የአየር ክልል ባስደፍር፣ ታሪኳን አዋርጀ መቶ አመት ነው ብል፣ ፍትሕን ባጓድል፣ ወጣቱን ባሰድድ፣ በሐሰት እየወነጀልኩ ወደ እስር ቤት ብወረወር ዜጎቼን ንቄ የሌላ አገር ዜጎች ክብር ሰጥቼ ባሰፍር፣ የወርቅ መአድኗን ለአንድ ቱጃር አሳልፌ ብሰጥ፣ በሃይማኖቶች ጣልቃ ገብቸ ብበጠብጥ እንደ አፄ ስሱንዮስ እግዚአብሄር ምላሴን ጎልጉሎ ለንዝ እንኳን ሳልበቃ ልሳኔን ይዝጋው!!

መቻል የመሬት ባለቤት ሆነ

- ማነው መቻል?- መቻል ውሻውነዋ!- የት? - ለገጣፎ- እንደዚያማ ሊሆን አይችልም?- ሆነ! ተደረገ

በፊንፊኔ ዙሪያ ለገጣፎና ለገዳዲ በተባለችው ጨቅላ ከተማ መሬት እንደጉድ እየተቸበቸበ እንደጉድ እየተዘረፈ እንደጉድ እየተበላ ነው፡፡ ታዲያ በይው ከኢህአዴግ ጋር በኢህአዴግ በኩል ጠጋ ያሉ ግለሰቦች ናቸው አሉ፡፡መቻል እንዴት የመሬት ባለቤት እንደሆነ መረጃውን ያደረሱን የለገጣፎ ተቆርቋሪ ኗሪዎች የመሬት ወረራው፣ ሙስናው፣ ዘረፋውና የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ከላይ እስከታች በተደራጁ ካድሬዎች ይፈፀማል ብለዋል፡፡በተለይ በመሬት ወረራው ይላሉ እነዚህ ተቆርቋሪ ኗሪዎች በከንቲባው፣ በመሀንዲሶች፣ በቀበሌ በመሬት ክፍል ሀላፊዎች የተቀናጀና ብርቱ ስራ ቅርምቱ ይካሄዳል፡፡በቅርብ ዘመድ፣ በልጅ፣ የአንድን ስም አባቱን በመቀያየር መሬቱን ሸንሽነው ተከፋፍለውታል የሚሉት ኗሪዎች ዘመድ አዝማድ ያለቀባቸው ባለስልጣናት በውሻቸው ስም ሳይቀር መታወቂያ እየተሰጠ፣ ሰነድ እየተበጀ መሬት ተወስዷል፡፡በዚህም መሠረት “መቻል” የተባለ አንድ ታዋቂ ውሻ በአሳደረው በኩል የመሬት ባለቤት ለመሆን ችሏል፡፡

ብዙአየሁ ወንድሙ

በፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት 14 ዓመት ጽኑ እስራትና 33ሺ ብር ተፈርዶባት በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅጣቱ ወደ አምስት ዓመት ጽኑ እስራት ተቀይሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶ” የሚል መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ አስመርቃለች፡፡ በምረቃው ዕለት ርዕዮት ባትገኝም ወላጆቿ፣ ወንድሞቿ፣ እህቶቿ፣ ጓደኞቿ፣ የሞያ አጋሮቿ፣ አድናቂዎቿና ዘመድ አዝማዶቿ በተገኙበት ባለፈው ቅዳሜ በራስ አምባ ሆቴል በደማቅ ሥነ ሥርዓት የመጽሐፍ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶን” ለመፃፍ ምን አነሳሳት? የመጽሐፉ ይዘትስ ምን ይሆን? ለእስር የበቃችበትን ምክንያት እንዲህ ብላ ነው የገለፀችው፡-

“ገዢው ፓርቲ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ጉዳይን የወረቀት ጌጥ ሲያደርገውና ያለ ፍትሀዊ ውድድር ራሱን በ ‹አውራፓርቲ› ነት ሾሞ ስመለከት አዘንኩ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡ የፕሬስ ነፃነትን እነማን የማይነካውን እንደሚነኩ ማወቂያና እነዚህ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር የራቀ አመለካከት ያላቸውን የዜጎች ማጥቂ ታክቲክ እንዳደረገው ስረዳ ተበሳጨሁ፤ ከዚያም ጻፍኩ፡፡ የህብረተሰቡ እኩሌታ የሆኑ ሴቶች ከሚያዘጋጃቸው

ሰልፎች ማድመቂያነት ባለፈ ዋጋ እንደማይሰጣቸው ሲገባኝ ተቆጨሁ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡ የሥራ ማግኛ መስፈርትን ከትምህርት ደረጃ፣ ከብቃትና ከስራ ልምድ ዝቅ አድርጎ የኢህአዴግ አባልነት መታወቂያ ማድረጉን ስታዘብ ተናደደኩ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡ እንዲህ አይነቱን አምባገነንነት ሀይ ማለት የሚኖርባቸው ሲቪል ማህበራትን ሽባ ሲያደርጋቸውና በሰበብ አስባቡ ምክንያት እየፈለገ ሲኮረኩማቸው ሳይ ‹ለምን?› ብዬ ተብከነከንኩ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡ ግፈኞችን ማውገዝ የሚጠበቅባቸው የሀይማኖት አባቶች ሁኔታ እንዳይሆን እንዳይሆን ሲሆንብኝና የአምላክ አገልጋይነታቸውን ርግፍ አርገው ትተው ለቄሳር መገበራቸውን ሲገባኝ ተገረምኩ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡ በዚህ አይነት ጉዞዬ ‹ከልማታዊነት› ጎዳና በእጅጉ የራቁ ጽሁፎች ማዘጋጀቴን በሰፊው ተያያዝኩት፡፡ ጽሁፎቹም በቼንጅ መጽሄት፣ በአዲስ ፕሬስ፣ በአውራአምባ ታይምስ በመጨረሻም በፍትህ ጋዜጣ ላይ ተስተናገዱ፡፡

ታዲያ ይህ ሁሉ ልፋቴ በማንም ላይ ክፉ ከማሰብ የመነጨ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከሆነለት ራሱን አርሞ ሀገሬን በቅጡ እንዲመራ ካልሆነለት ደግሞ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ በማሳሰብ የሚጠበቅብኝን ሀገራዊና ሙያዊ ግዴታዬን ለመወጣት ስል በፈፀምኩት ውለታ የማይረሳው መንግስታችን ለዚህ መልካም ተግባሬ ‹የሽብርተኝነት› ማዕረግ አቀዳጀኝ፡፡ የቃሊቲን የክብር ስፍራም አልነፈገኝም፡፡ ‹ደክሞሃል እረፍ› እያልኩ ስጽፍ የነበረው በቅንነት መሆኑን ተረድቶ እሱም በተራው በቅንነት የ14 ዓመታት እረፍት አዞልኛል፡፡ ታዲያ ልማታዊ መንግስታችን እንደዚህ አጥብቆ ምስጋናውን በተግባር እንዲገልጽልኝ ምክኒያት ከሆኑ ጽሁፎቼ መሀከል የተወሰኑትን ብጋብዛችሁ ምን

ይላችኋል?” ስትል ርዕዮት “የኢህአዴግን ቀይ እስክሪብቶ” መጽሐፏን ጀባ ብላናለች፡፡

የርዕዮት ትንታግ ብዕር ዛሬም እውነትን ይናገራል፡፡ በአሳሪዎች እጅ ወድቄአለሁ ብላ ህሊናዋን አላሰረችም፡፡ የዓለም አቀፉ የሴት ጋዜጠኞች ፋውንዴሽን 2012 ተሸላሚዋ ርዕዮት ዓለሙ ዛሬም እውነትን ትመሰክራለች፡፡ ብዕሯ የሚጐረብጣቸው “ሽብርተኛ” ብለው ቢፈርጇትም እሷ ግን ፈርጀዋታል፡፡ አሁንም እውነት ከመፃፍ ወደኋላ አላለችም፡፡ የአገራችንን እውነተኛውን ገጽታ ባለው መልኩ መቀበል የቻሉት ግን አድንቀዋታል፡፡

የአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት የሆነው የህገመንግስት አንቀጽ በተግባር ተሽሮ ኃላፊነትን ሊወጣ ባልቻለ ምርጫ ቦርድ ኢህአዴግ የሐሰት ምርጫ እያደረገ “አሸነፍኩ” እያለ በመራጩ ህዝብ ላይ ሲያላግጥ “ራሱን አውራ ፓርቲ ነኝ” እያለ በህዝብ ሲቀልድ እውነተኛ ብዕር ያስፈልግ ነበረና ፃፈች፡፡ ርዕዮት እንደምትነግረን በዚህ የተናደዱት አሳሪዎቿ ጉድጓድ ሲቆፍሩላት ቆዩ፤

የሴቶች መብትና እኩልነት ለመድረክና ጐዳና ማድመቂያ መዋሉን፤ እንዲያውም የሥርዓቱ ዋና ዋና ተዋናይ የሆኑ፤ “17 ዓመት ታግለን የገባን ነን” የሚሉ፤ ሳይቀሩ ሥልጣንና ገንዘብ ሲያገኙ አብረዋቸው ታግለው የገቡ ሚስቶቻቸውን እየፈቱ “የእኔ ቆንጆ” እያሉ በሚያቆለምጧቸው ዘመናዊ ሴቶች ሲቀየሯቸው “ለምን?” በማለት ተቸቻቸው፡፡ አኮረፉና ወጥመድ አዘጋጁላት፡፡

በኢትዮጵያ ፕሬስ ነፃነት ከቀን ወደ ቀን እየተዳፈነ አይን ያወጣ የአፈና ሥርዓት ሲዘረጋ ርዕዮት ፃፈች፡፡ ርዕዮትን ከፕሬስ መነጠል ፈለጉና አሴሩባት፡፡ ክቡርና ታላቅ

የሆነው የዜግነት ክብር ተዋርዶና ተሽሮ ሥራ ማግኛ የኢህአዴግ ተራ የአባልነት ደብተር ሲሆን እንደሌላው ዝም ብላ ከመቀበል “ልክ አይደለም” ካለች በኋላ ሥራ በዜግነት በሥራና በሞያ በእውቀት ውድድር ተደርጐ መሆን አለበት ብላ ፃፈች፡፡ ይህን ማለት ወንጀል ሆነና ዶለቱባት፤ የሃይማኖት አባቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ታላቅ ክብር አውርደው ለሥርዓቱ አጐብዳጅና ተላላኪ ሲሆኑ የቴሌቪዥን ማድመቂያና የማይመጥናቸው ሥራ ሲሠሩ በማየቷ ርዕዮት ፃፈችባቸው፤ ድሮውንም ከመስመሩ የወጡ ነበሩና “እንዴት በህፃናት እንሰደባለን? እንዴት በልጅ ስንሰደብ መንግስት ዝም ብሎ ይመለከታል” ብለው ባለሥልጣናት ዘንድ ሄደው አለቀሱ፡፡ “አይዟችሁ ወህኒ እንወረውርላችኋለን” ተብሎ ቃል ተገባላቸው፡፡ ዱለታውም ሴራውም ተቀናጀና ታሰረች፡፡ ርዕዮት “ሽብርተኛ” ተባለችና ተከሰሰች፤ ተፈረደባት፡፡

በርዕዮት ላይ የፈረዱ ዳኞች በእርግጠኝነት ህጉን ተረጐምን ብለው ፈርደዋል፡፡ ዐቃቢ ህጐችም የህግ የበላይነት ለማስከበር ብለን ጥፋተኛን ለህግ አቅርበናል ብለው እንደሚሉ አንጠራጠርም፡፡ ፖሊስም ተጠርጣሪ አግኝተን ለህግ እንዲቀርብ ሰርተናል ሊሉን ይችላሉ፡፡ ጠ/ፍ/ቤት ያለውን ብሏል፡፡ ሁሉንም ለታሪክ እንተወው!! ርዕዮት ዛሬ የ5 ዓመት ጽኑ እስረኛ ተብላ ቃሊቲ ትገኛለች፡፡

ርዕዮት “ዛሬም የታሰርኩበትን ፁሁፎቼን አንብቡልኝ” ብላ በመጽሐፍ መልክ ጠርዛ አቅርባልናለች፡፡ የቃሊቲ ብዕሯም ምን እንደሚል ከላይ አንብበነዋል፡፡ ዓለም የሸለማት እኛ ብዙም የማናውቃት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ዛሬና ትላንት ምን እንደፃፈች “የኢህአዴግን ቀይ እስክሪብቶ” መጽሐፍ ገዝቶ ማንበቡ የበለጠ እንድናውቃት ይረዳናል፡፡

የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ምን ይል ይሆን?

የዜጎችን ገቢ ያላገናዘበው ...ምክንያት ለዛሬ ተቀጥረው በደመወዝ የሚተዳደሩትን በቀጥታ በማነጋገር ጥቂቶችን ለመውሰድ ተገድጃለሁ፡፡

በዚህም መሰረት አነስተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው የጥጉ (የጥበቃ የጉልበት) ሰራተኞች አማካይ ገቢ እስከ 1 ዓመት ስልጠና የምስክር ወረቀት የወር ገቢ ያላቸው ከ800 ብር ደመወዝ፣ የዲፕሎማ ከ1200 ብር፣ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው 1600 ብር፣ የሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 2500 እና የዶክትሬት ድግሪ ያላቸው 3500 ብር አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ ያገኛሉ፡፡ ከተጠቀሰው ደመወዝም የስራ ግብር፣ የጡረታ ዋስትና፣ የአባይ፣… ወዘተ እየተባለ ከ15 - 20% እና ከዚያ በላይ የሚቆረጥም አለ፡፡

አንድ ጠንካራ ሰው ከሚያገኘው ከተጣራ ደመወዝ ከወጪ ቀሪ ሊቆጥብ የሚችለው ቢበዛ 1/4ኛውን ቢሆን ነው፡፡ የሚቆጥበውም ለተለያዩ ድንገተኛ

እና የረጅም ጊዜ ጠቀሜታ ላላቸው አገልግሎቶች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ እንኳ ቢሆን የ3,500 ብር ደመወዝ የሚያገኝ ሰራተኛ ከወጪ ቀሪ ሊቆጥብ የሚችለው በወር 700 ብር ሲሆን በ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር መሰረት ዝቅተኛውን ባለ 1 መኝታ ቤት ባለቤት ለመሆን 875 ብር በየወሩ መቆጠብ የግድ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፕሮጀክቱ ማንን ታሳቢ እንደሚያደርግ ዳግም ሊጤን የሚገባው ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ ሌላው ገንዘቡ ቢቆጠብ እንኳ የመርሃግብሩ ተፈጻሚነት ላይም ከፍተኛ ጥርጣሬ ያላቸው አሉ፡፡ እዚህ ላይ በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ት/ቤት የኢኮኖሚክስ መምህር እንዳልካቸው በድሉ (ስማቸው የተቀየረ) እንዳሉት ከሆነ እሳቸውም ከላይ የተሰጠውን ጥርጣሬ ይጋራሉ፡፡ ለጥርጣሪያቸው ምክንያት ያደረጉት በአሁን ወቅት መንግስት ያቀዳቸውን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት

ስለገጠመው ክፍተቱን ለመሸፈን ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የተለያዩ ገንዘብ መሰብሰቢያ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረጉን በማስታወስ አዲሱ 40/60 መርሃ ግብርም ከዛ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

እዚህ ላይ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እየሰሩ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተስፋሁንና አቶ ሞገስ በመርሃግብሩ ላይም ተቃውሞ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ምክንያት ያሉት መንግስት የከተማው ነዋሪ የአቅሙን ያህል በማህበር ተደራጅቶም ይሁን በግሉ ቤት እንዳይሰራ በሊዝ ስም በአዋጅ የመሬት ጭሰኛ ካደረገ በኋላ ቦታ ከልክሎ ገንዘብ አምጣና ቤት ይሰራልሃል ማለት ‹‹ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት›› ዓይነት ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ‹‹በተጨማሪም የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ሂደት ፍጻሜው አለመታወቁም እንቆቅልሽ ነው፡፡›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተለይ አቶ ሞገስና

አቶ ተስፋሁን ‹‹በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ በሀገሪቱ ላይ ትልቅ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ቀውስ በመፈጠሩ መምራት የማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ሲዳክር ይታያል፤ በዚህም ስህተቱን ለማረም ሌላ ስህተት እየተሰራ እንደሚገኝ እና በየመስሪያ ቤቱም የተረጋጋ ሁኔታ እንደሌለ›› ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም ወደሌላ አላስፈላጊ አቅጣጫ ከመሄድ ኢህአዴግ አሁን ሀገሪቱን መምራት አለመቻሉን አምኖ ስልጣኑን በሰላም መልቀቅ አሊያም ማጋራትና አብሮ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

እዚህ ላይ ይመለከታቸዋል የተባሉትን የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳንና የመስተዳድሩ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ክንዴን በመርሃ ግብሩ ዙሪያ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም ለተከታታይ ቀናት ስብሰባ ላይ እንዳሉ ከጽ/ቤታቸው በመገለፁ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡

ከ ገፅ 9 የዞረ....

Page 9: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

9Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ኢያ ደበርሣ (ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ)

ጉልበት እስከሚዝል ጀንበር እስከምትጠልቅ

ጠማማው እስኪቃና ጎባጣው እስኪታረቅ

እሪ እንላለን እንጮሀለን ገና፣

ተገፎ እስክናየው የበደል ደመና፡፡

የኢህአዴግ ሹመኞች ጆሮአቸው ተደፍኗል፡ ከላይ እስከታች ያሉት ሁሉም አይናቸው ታውሯል፡፡ በስልጣንና በመዋዕለ ንዋይ ፍቅር አቅላቸውን እስኪስቱ ሰክረዋል፡፡ የህዝብ ዋይታ እና እሪታ እነሱን አይሞቃቸው አይበርዳቸው! ግና ሞኝ ናቸው፤ እንደ ማሞ ቂሎ፡፡ ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ “ተመክሮ ተመክሮ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፣ ፈውስም የለውም” ይላልና ወደ ማስተዋላቸው ቢመለሱ ይበጃቸዋል፡፡ የሕዝቡ ቁጣ ለመገንፈል እየተፍለቀለቀ ነው፡፡ የገነፈለ ቀን ግን “ወዮ” ለእነሱ! ጠብመንጃቸውን ተገን አድርገው ለሁለት አስርት አመታት የናኙባት የኢትዮጵያ መሬት ለአፍታም አትሸሽጋቸውም፡፡ ሞተው ቢቀበሩ እንኳን ምድሪቱ አስከሬናቸውን ትተፋለች፡፡

የዛሬው ጽሁፌ ዓላማ የግፍ ጽዋ ሞልቶ የሚፈስባትን የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማን የሕዝብ ጩኸት ጆሮ ላለው ማሰማት ነው፡፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የህዝቡን ብሶት አስተውላ በኦህዴድ ግምገማ ስለመዘንጋቷ ያወሳችው እጅግ በጣም ጥቂቱን ነው፡፡ እስቲ እኔም የበኩሌን ልበል፡፡

ጥቂት ስለ አመሰራረቷ

ለገጣፎ ከለገዳዲ ከተማ ጋር ተዋህዳ ለገጣፎ ለገዳዲ በሚል በሁለት ቀበሌና በአንድ የከተማ አስተዳደር መመራት ከጀመረች ሐምሌ 2004 ዓ.ም ድፍን 6 አመቷ፡፡ ከ97 ታሪካዊ ምርጫ ማግስት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ነበር በአዲስ

መልኩ የተዋቀረችው፡፡ ቀደም ሲል በሰንዳፋ የገጠር ወረዳ ሥር የካ ገዋሳና የካዳሌ በሚል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነበር የምትተዳደረው ይህች አዲስ አበባ ጉያስር የተወሸቀችው ትንሽዬ ከተማ ከላይ እስከ ታች የስልጣን ኮርቻ ላይ ፊጥ ያሉትን የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ሹማምንትን ልብ አሸፈተች፡፡ ሁሉም ረጃጅም እጆቻቸውን ያለገደብ እየዘረጉ ምድሪቱን ተቀራመቷት፡፡ የፋሲካ ቅርጫ አደረጓት፡፡ እትብቱ የተቀበረበትን ህዝብ ከመሬቱ እያፈናቀሉ የቀን ሠራተኛ አደረጉት፡፡ የገበሬውን አንገት ማስገቢያ የሳር ጎጆ እያፈረሱ እነሱ ቢላ ቤታቸውን ገነቡ፡፡ ኢትዮጵያ ለእነሱ ገነት ለኢትዮጵያዊነት ግን ገሀነም፡፡

ለመሆኑ የለገጣፎ ለገዳዲ መሬት የማንነው?

በሕገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው “መሬት የህዝብና የመንግስት ነው፡፡” የሚለው አንቀጽ ለለገጣፎ ምድር አይሰራም፡፡ በለገጣፎ መሬት የኢህአዴግ ሹመኞች ሀንጡራ ሀብት ነው፡፡ ሲሻቸው ለዘመድ አዝማድ በስጦታ የሚቸሩት አሊያም በገሀድ የሚቸበችቡት፡፡ በል ሲላቸው በቤተሰቦቻቸው ስም የሚቀራመቱት፣ ከፈለጉም ባሳደጓቸው ውሾች ይዞታነት ካርታ የሚያወጡበት፡፡ በጣም የሚያስደንቀው ከነዋሪው ህዝብ በላይ ሦስትና አራት እጥፍ ካርታ እየተዘጋጀ ከ140 ካሬ ሜትር ስፋት ጀምሮ መቸርቸሩ ነው፡፡ ዛሬም ገበያው እንደደራ ነው፡፡ ገዋሣና የዳሌ አካባቢ ነዋሪ ገበሬም በሰበብ በአስባቡ መሬቱን ይቀማል፡፡ ቢጮህ ቢለፈልፍ እንደ እብድ ወይም እንደ ሰካራም ይቆጠራል እንጂ ሰሚ የለውም፡፡ ሕዝቡ በየዓመቱ “ካርታ ይሰጠናል” በሚል ቢጠባበቅም ሕዝቡን ማን ከሰው ቆጥሮት? ካርታና የለገጣፎ ነዋሪ የሰማይና የምድርን ያህል ተራርቀዋል፡፡ ሹማምንቱና የይዞታ ካርታ ግን ከባልና ከሚስት በበለጠ ተቆራኝተዋል፡፡

መንግሥት አድራሻው የት ነው?

አድራሻውን የምታውቁ ጠቁሙን፡፡ የለገጣፎ ህዝብ ከየትኛው መንግስት ዘንድ ቀርቦ እንደሚጮህ ግራ ገብቶታል፡፡ ቢጮህስ ድምፁን የሚሰማው አካል ያገኛልን? የ4 ኪሎው መንግስት እንደሆኑ ድርብ ህመምተኛ ሆኗል፡፡ ገና ከደደቢት ማህፀን ሲወጣ ነበር በደዌ የተመታው፡፡ አሁን ደግሞ እየፀናበት መጥቷል፡፡ የኦሮሚያ መንግስት እንደሁ ኦሮሞነቱን ፍፁም ዘንግቶታል፡፡ ለማንና ለምን እንደቆመ እንኳን አያውቅም፡፡ ሰሚያጣው የለገጣፎ ነዋሪ ግን እንደ የእምነቱ ወደ ፈጣሪው ጮኸ፡፡ ፈጣሪውም ሰምቶ መለሰ፡፡ መልሱ ግን የማስጠንቀቂያ ደወል ነበር፡፡ ፍርዱ ደግሞ አይዘገይም፡፡ ውሎ ሳያድር እግዚአብሄር ከዙፋኑ ብድግ ይልና የህዝቡን እንባ ያብሳል፡፡

የእግዚአብሄር ቁጣ ከአርአያም

ሰኔ 22 እና ሰኔ 25 2004ዓ.ም ፈጣሪ ለገጣፎ ለገዳዲ ላይ የቁጣ በትሩን ሰነዘረ፡፡ የግብፁ ፈርኦን የእስራኤልን ህዝብ ላለመልቀቅ እግዚአብሄርን በተገዳደረ ጊዜ ደጋግሞ የቁጣ ብትሩን ሰነዘረበት፣ በመጨረሻም ፈርኦን የውርደትና የሀዘን ማቅ ለብሶ ተረታ፡፡ አርብ ሰኔ 22/2004 መጠነኛ ዝናብ የቀላቀለው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ የከተማውን የጤና ጣቢያና የቴክኒክና ሞያ ተቋም ህንፃዎች አፈራረሰ፡፡ ሰኞ ረፋዱ ላይ ደግሞ አንዳችም የዝናብ ጠብታ በሌለበት የተነሳው ኃይለኛ ንፋስ የከንቲባውን ቢሮና ጥቂት የመኖሪያ ቤቶችን ጣራ ግንጥልጥሉን አወጣው፡፡ አደጋውም ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት አስከትሏል፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ክንድ ነው፡፡ እ/ር ጉዳዩ ከፈጠረው ህዝብ እንጂ ከቁሳቀስ ጋር አይደለም፡፡ በልማት ሰበብ የሰውን ልጅ ማጎሳቆልና ማሰቃየትን ፈጣሪ ለአፍታ ያህል እንኳ አይቀበለውም፡፡

ይድረስ ያገባኛል ለሚል አካል

የህዝቡን ብሶት በውል አጢኖ መፍትሄ የሚሰጥ ወገን ከተገኙ የነዋሪው ጥያቄ ከሞላ ጎደል የሚከተለውን ይመስላል፡፡

- ለጥቂት ሹማምንትና ደቀመዝሙሮቻቸው በገፍ ከሚታደለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ነዋሪው በነፍስ ወከፍ የዜግነቱን አንድ ካርታ እንዲያገኝ፣

- ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማስፈራራትና በማሰር ገበሬውን ከ እርሻ ቦታው ላይ ማፈናቀሉ በአስቸኳይ እንዲገታ፣

- ከከተማዋ ነዋሪ ቁጥር በላይ የተዘጋጁ ካርታዎች ምንጫቸው እንዲመረመር፣

- በከተማው ወጣቶች ስም በ140 ካሬ ሜትር የተሸነሸነው መሬት ለማን እንደ ተከፋፈለ እንዲጣራ፣

- ሙሰኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች እንዲጋለጡ፣

- የባለስልጣናቱ የሀብት ምንጮች በፀረ ሙስና ኮሚሽን በኩል እንዲጣራ፣

- የቀደሙትም ሆኑ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሹመኞች ተግባር በህዝብ እንዲገመገምና ነዋሪውን ሰብስቦ ማነጋገር ከምንም በላይ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ እንዲጤን፡፡

ምስጋና ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል

ወደረኞቻችሁ ቢበዙም እጅ አትስጡ! የህዝብን ጩኽት በመጮህ ብሶቱን ተጋሩት! ኢህአዴግ ቢያውቅበት ኖሮ ጋዜጣዋ ለመንግስትም ህፀፁን መንቀሻ መስታወት ነበረች፡፡ እናንተም ጩኹ፣ እኛም አብረናችሁ እንጮሃለን፣ ከዕለታት አንድ ቀን እንደ ባቢሎን ግንብ መናድ የሚገባው ይናዳል፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም የኛ ናት!

ሰሚ እስኪገኝ እንጮሀለን ሰማይና ምድርም ይጮሀሉ

ብስራት ወ/ሚካኤል[email protected]

ለዛሬ አነጋጋሪ እና ለዜጎች እጅግ ፈታኝ ከሆኑት መካከል መጠለያን (ቤትን) እንመልከት፡፡ በደርግ ሥርዓት ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ማንኛውም ዜጋ በግሉም ይሁን በማህበር ተደራጅቶ እስከ 500 ካሬ ሜትር የከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ያገኝ ነበር፡፡ በማኅበር የተደራጀው እና የቀበሌም ሆነ ሌላ መኖሪያ ቤት የሌለው ደግሞ በ20 ዓመት ከ7 ሺህ እስከ 14ሺህ ብር ክፍያ የህንጻ ቤት ባለቤት ተሆኗል፡፡ በዚህም ለቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ረጅም እድሜና ጤና የሚመኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቀላል አይደሉም፡፡ የቤትና የከተማ ቦታ ባለቤት ሆነዋልና፡፡ አንዳንዶቹም የፕሬዝዳንቱን ፎቶግራፍ ከሳሎናቸው ግድግዳ ላይ ለማስታወሻነት ሰቅለዋል፡፡ በምን መስፈርት እንደሆነ ባይታወቅም መጥመቅ ኢህአዴጋዊያን የቤት መስሪያ ቦታ አሊያም ሌሎች ጥቂቶችን እንደ በረሃ ዛፍ ጣል ጣል በማድረግ የቤት ባለቤት ለማድረግ ሲጣጣር ሌሎች ግን

ከቤታቸው ሲፈናቀሉና ሲሰቃዩ አይተናል፡፡

ኮንዶሚኒየም ይሰራላችኋልበከተሞች መጠለያ( ቤት) ለሌላቸው የቤት

ባለቤት ለማድረግ እንደተነደፈ የተነገረን ‹‹አዲሱ›› የቤት ልማት ፕሮጀክት በአብዛኛው ማንን ተጠቃሚ እንዳደረገ በየማዘጋጃ ቤቱ ሄዶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ችግሩ ዛሬም አልተቀረፈምና፡

በርግጥ ይሄ የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ግንባታ ከዛሬ 7 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም ሲጀመር በለጋሽ ሀገር ድጋፍ እጅግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በተለይም የጎዳና ተዳዳሪ፣ ጧሪ አልባ አረጋዊያንን እንዲሁም ጎልማሶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነበር፡፡

ነገር ግን በ1997 ዓ.ም በሀገሪቱ የተፈጠረውን ያልተጠበቀ የፖለቲካ ጡዘትን ተከትሎ ኢህአዴግ የቀድሞውን የቅንጅትን እንቅስቃሴ በመፍራት ለፖለቲካ ፍጆታ በተለይም የወቅቱን የምርጫ ድምጽ በመግዛት የከተማ ነዋሪውን የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ እንደ ቀልድ ከ400 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ሊመዘገቡ ችለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ባለፉት 7 ዓመታት ከተመዘገበው ነዋሪ ጋር ሲነፃፀር የተገነባው የቤት ቁጥር ከ15% አይበልጥም፡፡ ቀሪው ተመዝጋቢ ከሰማይ የሚወርድ ፍርፍር ያህል እየጠበቀ ይገኛል፤ በዚህ ሁኔታ በኢህአዴግ አካሄድ ከዛሬ 20 ዓመት በኋላ የሚሳካ አይመስልም፡፡

ከተገነቡ ቤቶች መካከል በስመ እጣ ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የቤት ባለቤት መሆናቸውና በጎን በሚደረግ ህገ ወጥ ምዝገባም ይከናወን

እንደነበር የቀድሞ ተመዝጋቢዎች በተለያየ ጊዜ እሮሮ ማሰማታቸው አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ተመዝግበው የነበሩ፤ ነገር ግን የስም ዝርዝራቸው ከፋይል ውስጥ የጠፋም እንዳለ በተደጋጋሚ መሰማቱ አይዘነጋም፡፡ ይሄ ደግሞ የገዢው ፓርቲ ግላጭ ባህርይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዳዲስ ቤት ፈላጊዎች ግን ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ አለመኖሩ ይታወቃል፡፡

40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ሲታይ

ይሄ አዲስ መርሃ ግብር የሚለው ደግሞ የመኖሪያ ቤት ፈላጊው ህዝብ የቤት ባለቤት መሆን ከፈለገ የሚፈልገውን የቤት መጠን ጠቅላላ ዋጋ 40% በ5 ዓመት ውስጥ በመቆጠብ 60% በመንግስት በሚመቻች ብድር የቤት ባለቤት መሆን እንደሚቻል ተገልጻDል፡፡ ይህም በ2005 ዓ.ም ይተገበራል ተብሏል፡፡

በ2005 ዓ.ም የመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡና በዛው ዓመትም 10ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳና በሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ ይፋ ተደርጓል፡፡ ይገነባሉ የተባሉት ቤቶች በግልፅ እነማንን ታሳቢ እንዳደረጉ በዝርዝር የተገለፀ ነገር የለም፤ በደፈናው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ያደርጋል ቢባልም በተገኘው መረጃ ግን እውን እንደማይሆን ያነጋገርኳቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

መንግስት ይፋ ያደረገውን የቤት ዓይነት በየወሩ የሚቆጠበውን የገንዘብ መጠንና ጠቅላላ

ዋጋ በጥቂቱ እንይ፡፡ ባለ 1 መኝታ ቤት የሚፈልግ ሰው በየወሩ 857 ብር መቆጠብ ያለበት ሲሆን የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ 128,590 ብር ነው፡፡ ባለ2 መኝታ ቤት ፈላጊ ደግሞ በየወሩ 1,337 ብር መቆጠብ ሲኖርበት የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ግን 200,475 ብር ሲሆን ባለ 3 መኝታ ቤት ፈላጊ በየወሩ 2,133 ብር መቆጠብ ያለበት ሲሆን የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ግን 320,000 ብር እንደሆነ ተገልጻDል፡፡ በእነኚህ ዋጋዎች ነው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንም ያካተተ ነው የሚል መርሃ ግብር ይፋ የተደረገው፡፡

በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ዝቅተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ የሚባሉትን ዜጎች የሚያገኙትንና ወጭ የሚያደርጉትን አማካይ ዋጋ አሀዝ መረጃ ለማግኘት የግድ የዓለምአቀፍ ተቋማትን አሊያም የፈረንጆችን ቤት ማንኳኳት ያስፈልጋል፡፡ ይህን መረጃ ማወቅ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው አሀዝ እና እውነታ ጋር ለማነጻጸር ይረዳል፡፡መረጃው ደግሞ የሚዘጋጀውና የሚለቀቀው በየ5 ዓመቱ በመሆኑ የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነታ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ስለሚሆን ለጊዜው ትቼዋለሁ፡፡

ምናልባት የተባለውን መረጃ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚመራው ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ደግሞ በየዓመቱ የሚፈለገውን ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት አይደፍርም፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ ብሄድም ወቅታዊ መረጃ የሚሰጠው በሚኒስቴር መስሪያ ፈቃድ ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን ሳውቅ የተለመደው የመረጃ መጋገር ስራ አለመጠናቀቁን ተረድቼ ተመለስኩ፡፡ በዚህም

የዜጎችን ገቢ ያላገናዘበው የ40/60 የቤት መርሃ ግብር

ወደ ገፅ 8 ይዞራል....

Page 10: News Paper No. 54 colour.indd

10 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

www.andinet.org

10 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ዳንኤል አበራ

ከጭጋጋማው የ2002 ዓ.ም ምርጫ በኋላ በጠራራው ፀሐይ በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድ መርዶ አሰሙን፡፡ የመርዶውም ዜማ “ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኗል! . . .” የሚል ነበር፡፡

ለ21 ዓመታት በከፋፍለህ ግዛ (divide & rule) ሥርዓት የአገሪቱን ተቃዋሚዎች እንደ ሰም አቅልጦ፣ ህዝቧንም እንደ ብረት ቀጥቅጦ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ በሪቮሉሽን ሳይሆን በኢቮሉሽን ከአውራነት ወደ አውሬነት ተለውጧል፡፡ ከአውራነቱ ይልቅ “አውሬነቱን” የሚያሳዩ ሁለት ባህሪያቱን እስቲ እንመልከት፡-

ኢህአዴግ ባስተዳደራቸው ዓመታት በረቀቁ ስልቶችም ሆነ በገሃድ አሳዛኝና አሰቃቂ የግድያ ወንጀሎች መፈፀማቸው፤

በዘመነ ኢህአዴግ ጎሣን ከጎሣ፣ የሃይማኖት ተቋማትን ከሌላ የሃይማኖት ተቋም ጋር ከማጋጨትም አልፎ የረቀቁና በስውር በሰዎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ አፈናዎችና ቶርቸሮች የስርአቱን አውሬነት ለማሳየት በጉልህ የሚጠቀሱት ናቸው፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አካባቢ የተደረጉ ጭፍጨፋዎች መንግስትን

በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያስከስሰው እንደሆነ አንዳንድ ተቋማት ያወሳሉ፡ በቅርቡ ዊክሊክስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የኢህአዴግ የደህንነት ኃይል በከተሞች አካባቢ የተፈፀሙ ፍንዳታዎች ላይ እጁ እንዳለበት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ባገኘው መረጃ መግለጹ ይታወቃል፡፡

ከደርግ ደም አፍሳሽ ተግባር ትምህርት ያልቀሰመው ይህ ፓርቲ ገና ከጅምሩ አገር ለምን ትገነጠላለች? ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጥይት፣ መምህራኑን ደግሞ በጡረታ አሰናብቷል፡፡

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ኦነግ፣ የሱማሌዎቹን ኦብነግ እና የአማራዎቹን ትናንት መአህድ ዛሬ ደግሞ ግንቦት 7 እያለ በየእስር ቤቱ አሰቃቂ እና አረመኔያዊ የአውሬነት ግፍ ፈጽሞባቸዋል፤በመፈፀም ላይም ይገኛል፡፡ ያለ ፍትህም የብዙዎች ህይወት እንዲጠፋም አድርጓል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ፓርቲ እነዚህን ግልጽ ወንጀሎች ሲያስተባብል ይስተዋላል፡፡

የቀበሮዋ ነገርአንድ የቆየ ተረት እንዲህ ይላል .

. . አንዲት ቀበሮ የበግ ግልገል ነጥቃ በመብላቷ ተይዛ ስትገረፍ እንዳልበላች ሸምጥጣ ትክዳለች፤ ነገር ግን በአፍዋ ላይ ደም ነበረባትና “ታዲያ ይህ በአፍሽ ላይ ያለው ደም ከየት የመጣ ነው?” ተብላ ስትጠየቅ” “እኔም የገረመኝ የዚህ ደም መገኘት ነው እኮ!” ብላ መለሰች ይባላል፡፡

እንደ ቀበሮዋ ሁሉ ይህ ፓርቲ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና አፈናዎችን “አይኔን ግንባር ያድርገው” በማለት ክዷል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ በአምንስቲ ኢንተርናሽናልና በሌሎች የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት

መግለጫ ቢወጣበትም ፓርቲው ግን ስህተቱን ከማረም ይልቅ የመልስ ምት ለማዘጋጀት ይሯሯጣል፡፡

በቢቢሲ “በአረንጓዴው ረሃብ” ዙሪያ የተሰራውን ዶክመንተሪ ፊልም በካድሬዎቹ አማካኝነት በአካባቢው ያሉ ሰዎችን በማስፈራራት፣ በማሰቃየት እና በመደለል እንዲዋሹ በማድረግ የቅጥፈት ድራማ ሰርቷል፡፡ በሶማሌ ክልል የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ የመልስ ምት በማዘጋጀት ለጥቅማቸው ባደሩ ጥቂት የለንደን ጎረምሳዎችን ሰብስቦ የራሱን የፈጠራ ፊልም አዘጋጅቷል፡፡ ባጭሩ ኢህአዴግ ማለት ይሄ ነው፡፡

ተቀናቃኝን ማጥፋት፡-“ጠላቶችህን ፈጽመህ ደምስሳቸው

ካልሆነ ግን የጭቃ ውስጥ እሾህ ይሆኑብሃል” በሚለው የእነ ማኪያቬሊን (the prince) እና የቅርቦቹ የእነ ሮበርት ግሪንን (48 laws of power) መፃህፍትን ያጠኑ የሚመስሉት የኢህአዴግ ባለስልጣናት የፖለቲካ ምህዳሩን ማጥበብና ማጥፋት እንጂ ማስፋትና ማልማትን አይወዱም፤

የኢንዶኔዥያው ዛፍበኢንዶኔዥያ የሚገርምና

የሚያስደንቅ አንድ ዛፍ አለ፡፡ ከዚህ ዛፍ ከሚያስገርመውና ከሚያስደንቀው ባህሪው አንዱ ሌሎች አትክልቶች እና እንስሳት በአጠገቡ እንዲበቅሉና እንዲኖሩ አለመፍቀዱ ነው፡፡ ሌሎች ዛፎች እንደ ድንገት በአጠገቡ ከበቀሉ በመርዛማ ባህሪው ከምድረ ገጽ ያጠፋቸዋል፡፡ ዛፉ በአጠገቡ ከእርሱ ሌላ የሌሎች ዛፎችን መኖር አይወድምና፡፡ ኢህአዴግም “ቁርጥ” ይህን ዛፍ ይመስላል፡፡

ኢህአዴግ ከተቀናቃኝ ፓርቲ ጋር አብሮ የመሥራት ፍላጎት አይስተዋልበትም፡፡ ከዚህ ይልቅ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጉድጓድን በመማስ ይታወቃል፡፡ ፓርቲው እንደ ኢንዶኔዢያው ዛፍ አጠገቡ ያሉ ተቀናቃኞቹን ማጥፋት የታደለውም ፀጋ ይመስላል፡፡

‹‹ አንተም ኑር ሌሎችም እንዲኖሩ አድርግ›› የሚለው በፍቅርና በፍትህ የሰለጠኑ ህዝቦች ህግ አይስማማውም፡፡ ይልቁኑም ለኢህአዴግ ‹ከራስ በላይ ነፋስ› ‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል› አይነት ተረት ይመቸዋል፡፡

“በእኔ ሳንባ ብቻ ተንፍስ፣ በእኔ እቅድ ብቻ ተመራ፣ በእኔ መንገድ ብቻ ተጓዝ፣ እኔን ብቻ ስማኝ” የሚል ከበታችነት ስሜት የሚመዘዝ “የእኔነት” ስሜት ይስተዋልበታል፡፡ ፓርቲው ያልጋገረው ዳቦ እንዳልጣፈጠ፣ ያልገባበት ነገር ሁሉ እንደተበላሸ ያስባል፡፡ እሱ የሌለበትን ስብሰባ እንደሽብርና ሴራ ይቆጥረዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉንም ቦታ በዝግ የጣሊያን “ካቴና” የፖለቲካ ታክቲክ ጠርቅሞታል፡፡ ጣሊያን እንኳን ‹‹ካቴና›› የተባለውን ዝግ የኳስ ጨዋታ ከተወች ብዙ ጊዜ ሆኗታል፡፡

ፓርቲው ከንግዱ ማህበረሰብ እስከ ሃይማኖት ተቋማት ከማጀት እስከ ካፌ ከዩኒቨርሲቲ እስከ መዋዕለ ህፃናት፣ ከአፓርታማ እስከ ፓርላማ፣ ከአርቲስት እስከ ፕሬስ ህትመት፣ ከኢቲቪ እስከ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ፣ ከምርጫ ቦርድ እስከ ፍርድ ቤት ሁሉን ለብቻው ተቆጣጥሮታል፡፡

ኢህአዴግ ከከሰሰህ በቃ! አንተ ወንጀለኛ ነህ፡፡ ከቻለ ወዳጆችህን በጠላትነት ያስነሳብሃል፤ ካልቻለ ግን አይተውህ የማያውቁ ሰዎችን በሀሰት ደልሎ ፊት ለፊት ያስመሰክርብሃል፤

ከተመቸው ደግሞ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ ዶክመንተሪ ፊልም ያሰራብሀል፡፡

የፍትህ አካሉን የራሱ ጉዳይና ጥቅም ብቻ ማስፈፀሚያ አድርጎታል፡፡ በአንዲት ሀገር የፍትህ አካሉ ጠንካራ ካልሆነ ጠንካራው የፍትህ አካል ነፃና ፍትሀዊ አይሆንም፡፡ ፓውል ክሬግ ሮበርትስ የተባለ ፀሐፊ ‹‹ የፍትህ አካሉ በተበላሸ ጊዜ ዜጎች በአምባገነኖች ክፉ አገዛዝ ስር ይወድቃሉ›› ብሏል፡፡ በኢትዮጵያም እየተከሰተ ያለው ነገር ይህን ይመስላል፡፡

ፓርቲው ሲያሰኘው “ልማታዊ ነጋዴ፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ ቄስና ሼክ” በሚሉ ቃላት ያደነቁርሀል፡፡ ደስ ሲለው በጦር ሜዳ ውስጥ እንዳለ ጄነራል ያደርገዋል፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ መልኩን ለውጦ እንደ ሀይማኖት ሰው በአምልኮት ስፍራ መገኘት ያምረዋል፡፡ ይህ ድርጊቱ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ቦታ መታየትና መገኘትን እንደምትወድ ቆንጆ ወይዘሪት ያስመስለዋል፡፡ ያልገባው ምስጢርና የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ግን ሁሉን ለመቆጣጠር ሲጥር ሁሉን ሊያጣው እንደሚችል አለማወቁ ላይ ነው፡፡ ትዕቢትና አለማወቅ ሁልጊዜ የፓርቲው መገለጫ ይመስላል፡፡

ኢህአዴግ የተለያዩ የፖለቲካ ጋዜጦችን መጽሄቶችን በረቀቁ የማጥፊያ ህጎች ከመቃብር በታች አውሏቸዋል፡፡ ለሆዳቸው ሳይሆን ለህሊናቸው ያደሩ የነፃነትና የሰላማዊ ታጋይ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችን አሸባሪ በሚል ተለጣፊ ስም እስር ቤት ወርውሯቸዋል፡፡ ጋዜጠኛውን በፕሬስ ህግ ሌሎችን በተለያዩ አሳሪ ህጎች ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡ ለኢህአዴግ ከአውራነት ይልቅ የአውሬነት ባህሪ ይስማማዋል የምንለው ለዚህ ነው፡፡ እውነት ነው!! አውሬነት ይስማማዋል፡፡

የኢንዶኔዥያው ዛፍ እና ኢህአዴግ

የጳጳሳቱና የቤተክህነቱ ገመናወደ ገፅ 12 ይዞራል....

ወደ ገፅ 12 ይዞራል....

ብሩክ ከበደ

ሰሞኑን በአንድ ቀን በአካልም በጽሑፍም የገጠሙኝ ግጥምጥሞሾች ወቸ ጉድ ሲያሰኙኝ ከርመዋል፡፡ ሲያመጣው እንዲህ አይደል፡፡ አንደኛው በአካል የገጠመኝ የጋዜጠኛ ወዳጄ ባለቤት ወልዳ እሷኑ ለመጠየቅ ገነት ሆቴል ጀርባ ወደ ሚገኘው ላንድ ማርክ ጠቅላላ ሆስፒታል አምርቼ የታዘብኩት ነው፡፡ ሆስፒታሉ መግቢያ በር ለመድረስ 50 ሜትር ያህል ሲቀረኝ ነጭ ጥምጣም የጠመጠሙ እንደ እሳት የሚፋጀውን የሰው ፊት ያለመዱ ለመሆናቸው መላ አካላቸው የሚናገርባቸው ጐልማሳ ሲፈሩ ሲቸሩ በቀኝ እጃቸው የያዙትን መስቀል አስቀድመው ያለኝን እንድረዳቸው በትህትና ጠየቁኝ፡፡ ከአኳኋናቸውና ከአማርኛ አጣጣል ዘዬአቸው ከተሜኛ አለመሆናቸው ከበቂ በላይ የሚያስረዳ በመሆኑ ከየትና ለምን እንደመጡ አጥብቄ ጠየኳቸው፡፡ የመጡት ከጐንደር እንደሆነና አዲስ አበባ ከሚገኙት አድባራት መሀል በአንዱ ለመቀጠር ሲሉ ደጅ ሲጠኑ በመቆየታቸው ስንቃቸው አልቆ ለልመና መዳረጋቸውን መሬት መሬት እያዩ አወጉኝ፡፡ እኚህ ምስኪን ጐልማሳ ካህን የጌታን መስቀል በቀኝ እጃቸው ይዘው በራስ መተማመናቸው መጥፋቱ የምጽአት ዘመን መቃረቢያ

ምሳሌ ይሆን? ስል ለራሴ የማይመለስ ጥያቄ አቀረብኩኝ፡፡

ፈጠን ብዬም በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የመቀጠሩን ጉዳይ እንዲረሱት በጥሞናና ከነ ምክንያቱ አስረዳኋቸው፡፡ ያነሣሁላቸውን ሀሳብ ምጽዋት የሚጠይቋቸው ሁሉ ስለነገሯቸው በእጅጉ መገረማቸውን ገለጹልኝ፡፡ የተነገራቸውን በጊዜ ካልፈፀሙ በየቀኑ በልመና የሚያገኙት ገንዘብ በከተማው ባህር ተውጠው እንዲቀሩ እንደሚያደርጋቸውና አስከሬናቸው የትም ወድቆ በመቅረት ለቤተሰባቸው የዘላለም ፀፀት እንደሚያተርፉ ጨምሬ ነገርኳቸው፡፡ ካህኑ እውነታቸውን ይሁን ውሸታቸውን ሚስጥሩ ያለው በፈጣሪ እጅ ቢሆንም ከሁኔታቸው ተነስቼ የደረስኩበትን ግምት ተንተርሼ የምለውን ብዬአቸው ተለያየን፡፡

ከእኚህ ግለሰብ ጋር ከተነጋገርኩ 4 ሰዓት በኋላ በቤተክህነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሌላ የፎቶ መስረጃ እጄ ገባ፡፡ በቀኑ በጉዳዮቹ ግጥምጥሞሽ እየተደነኩ ወረቀቱን በጥንቃቄ ማገላበጥ ጀመርኩ፡፡ በውስጡ የያዘው መልዕክት ያስደነግጣል ብቻ ሳይሆን ያማል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ያገለግሉ የነበሩና በኋላም አዲስ አበባ በመምጣት ከነጉድፋቸው የመጨረሻውን የሃይማኖቱን እርከን ጨብጠው 5ኪሎ ስለከተሙት ካህን ያጫወተኝን ውስጥ አውቃ ወዳጄን ታሪክ ለማንም ሳልተነፍስ ወይም ሳልጽፍ ብቆይም ዛሬ እኔ እጅ ብቻ ሳይሆን ሌላውም እጅ የገባው ሰነድ ግን የሌሎችንም ጨምሮ ይዘከዝክልኝ ገባ፡፡

አሁንም ቀደምት አበው

ከአረመኔዎች፣ ከፋሽስቶች ተከላክለውና ራሳቸውን ለጥይትና ለእሳት ዳርገው በሥሯና በፀበሏ ተሰባስበው ምህረትንና ጤንነትን በሚማፀኗት የኦርቶዶክስ እምነት ታላቅነት ስል ማንኛውንም ሚስጥሯን በተገቢውና አግባብ ባለው መልኩ የመጠበቅ የነፍስም ሆነ የሥጋ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ ይህንንም አደርገዋለሁ፡፡ ስብራቱ ያለው ግለሰቦች (ቡድኖች) ዘንድ እንጂ በእምነቱ አስተምህሮ በኩል እንዳልሆነ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም፡፡

ታላቁ የሃይማኖት ሊቅ ሊቀጠበበት አለቃ አያሌው ታምሩ ገና ከማለዳው የቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ይከበር፤ በምንም መልኩ ህብረት ከሌለን የሃይማኖት ተቋማትና አስተምህሮት ጋር የሚደረገው መጠን ያለፈ ግንኙነት ይቁም የሚሉና የመሣሰሉ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ከ50 አመታት በላይ በልበ ብርሃን ካገለገሏት ቤተ ክርስቲያን “የኢንዱስትሪ ሠላም በማደፍረስ” በሚል ክስ ያለ ጡረታ መሰናበታቸውን በሚገባ አውቃለሁ፡፡

ምንም እንኳን አለቃ ጡረታቸውን ቢያጡም በኦርቶዶክስ እምነት የሚከበሩ ክብረ በዓሎች ከሃይማኖቱ ጋር ያላቸው ታሪካዊ አመጣጥና ቁርኝትን በተመለከተ ለወገናቸው እንዲያስረዱልኝ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ከሚገኘው መኖሪያቸው ግቢ ካለች ሁለት ሰው ብቻ በምትይዘው ክፍላቸው ደጋግሜ ላናግራቸው ስሄድ ውስጣቸው የነበረው መንፈሳዊ ጥንካሬ፣ የሚንቦገቦገው ሀገራዊ ፍቅርና ስሜት አሁንም ድረስ በጉልህ ይታየኛል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ለጥንታዊቷ

ቤተ ክርስቲያን ህልውና ለነፍሳቸው ሳይሳሱ፣ ለድሎታቸው ሳይጨነቁ የሚሞቱላትንና የሚሟገቱላትን ከሥር ከሥር ለማስወገድ የተደረገ እርምጃ መሆኑ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል፡፡

ምዕመኖቿ የሰለጠነው ዓለም ቴክኖሎጂ በረከት ተቋዳሽ ሆነው ባሉበት ወቅት እውነትን፣ እውቀትንና፣ ጥራትን መሠረት ያደረገ መዋቅር ዘርግታ ተከታዮቿን በተቻለ አቅሟ መድረስ ያቃታት ቤተ ክርስቲያን ሁለመናዋ ከነሚስጥሯ ተደፍሮ ዙሪያዋን ገንዘባቸውን አጥሪዎች “መኒ-ላውንደሪግ” በደምም ይሁን በህገ ወጥ መንገድ የስበሰቡትን ሀብት ለማጠብ የሚጠጓት ራሷን የቻለች ግዙፍ የምንደኞችና የፖለቲከኞች ተቋም ሆና ለሚያገኛት ምዕመን ድንጋጤና ተስፋ መቁረጥ ተረባርበውበት እነ ታምራት ገለታ ጉያ ወስደው ቢሸጉጡት የሚደንቅ አይሆንም፡፡

ዛሬ በየቦታው ቤተ እምነት ይገነባል፡፡ ነገር ግን ወጥ የሆነ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ መተማመን፣ ሰላም፣ አንድነት ወዘተ ሲገነባ አይታይም፡፡ ቀደም ሲል “ቤተ ክርስቲያን በአፀዱ (በነገራችን ላይ ከሀገራችን ምድር ሊጠፉ የተቃረቡት እነ ኮሶ፣ ወይራ፣ ዝግባ የመሳሰሉት የሚገኙት በቤተ ክርስቲያን ግቢ ነበር፤ ያውም በከተማ ውስጥ) “የጨዋ ልጅ በአንደበቱ” ይታወቃል፡፡ የሚባልበት ዘመን አልፎ የቤተ እምነት ዙሪያ ገባው ለንግድ የሚውሉ ህንፃዎች እየተሰሩ ለፌሮ ብረት፣ ለአለማዊና መንፈሳዊ ሙዚቃዎች (አንዳንድ ቦታ የእምነቱ ተከታዮች ያልሆኑ ሰዎች ሱቆቹን ተከራይተው የራሣቸውን እምነት

የሚሰብክ አስተምህሮትና ሙዚቃ ይከፍታሉ)፣ ማሣጅ፣ ኬክ ቤት ወዘተ መሸቀጫ ውለው ዋናውን ቤተ አምልኮ ሸፍነው ድባቡን፣ ዝምታውን፣ መንፈሱን ቀምተውታል አባረውበታል፡፡ ከነዚህ የንግድ ቤቶች ጀርባ ለነፍስ የሚሠራ ሥራ ይኑር አይኑር አይታወቅም፡፡ ለዚህም የመርካቶውን ራጉኤል መጥቀስ ይበቃል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም የቀብር ቦታዎችን መልሶ ለቀብር ለማዋል በሚል መንገድም የሙታን ክብር ተገፎአል፤ ቤተሰብ በሙታኑ ቦታ ላይ ያዋለው ንብረት የጥቂት ጉልበተኞች ኪስ ማደለቢያ ሆኖአል፡፡ ለአጽም ማንሻ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለህ ካላነሣህ እኛ በምናዘጋጀው ቦታ እናኖረዋለን በሚለው ድፍንና ዘግናኝ ማስታወቂያ ቋሚ ተለክቶና ተበድሮ ገንዘብ እንዲያመጣ ከመደረጉ በላይ እንዲሳቀቅ ተደርጓል፡፡

ይህና ሌሎች አጉራ ዘለል ድርጊቶች ባስከተሉት ጦስ የተነሳም ከአሥር ሰዓት በኋላ እስከ ምሽት የሚሰጠውን ሃይማኖታዊ ትምህርትና መዝሙር ምክንያት በማድረግ የቤተ እምነቶችን ግቢ የፆታዊ ግንኙነት መቀጣጠሪያ ቦታ ከማድረግ አልፈው ነውር ሥራ የሚሠራበት መናፈሻ አድርገውታል፡፡ በዚህም ሐጢያታዊ ስራ ግራ የተጋቡ አብያተ ክርስቲያናት ወንድና ሴት በተወሰኑ ቦታዎች አብረው እንዳይቀመጡ የሚከለክል ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ደርሰዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ተጠናክራ ወጣቱ የወላጆቹን እምነት ተከትሎ እንዲዘልቅ የበኩላቸውን

Page 11: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

11Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ...

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ስር የሚተዳደረው የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ለሀዲያ ዞን ገበሬዎች የማይበቅል ዘር መሸጡን የአካባቢው ገበሬዎች ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ፡፡

እንደ ገበሬዎቹ ገለፃ ከሆነ ምርጥ ዘሩን የገዙት በውድ ዋጋ ነው፡፡ አቅም የሌላቸው ገበሬዎችም የማይበቅለውን ምርጥ ዘር በግድ እንዲገዙ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ገበሬዎቹ ከደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት የገዙትን የስንዴ ዘር በማሳቸው ቢዘሩም ለረጅም ጊዜ ባለመብቀሉ ከፍተኛ ሥጋት እንደተፈጠረባቸው ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የሚመለከታቸው አካላት የዘር

ወቅት ካለፈ በኋላ ለክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ቢያሳውቁም ዘሩን የሸጠው የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ሐምሌ አጋማሽ 2004 ዓ.ም ላይ ሌላ ምርጥ ዘር አምጥቶ ለገበሬዎቹ መተካቱ ተጠቁሟል፡፡ እንደ ገበሬዎቹ ገለፃ ከሆነ ዘግይቶ የተሰጠው ምርጥ ዘርም ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ አሁንም ስጋት እንዳደረባቸውና የተሰጣቸው ምርጥ ዘርም ስለመብቀሉ እርግጠኛ መሆን አለመቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

በተጠቀሰው ችግር ዙሪያ ያነጋገርናቸው የሀዲያ ዞን ግብርና እና ገጠር ልማት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መላኩ ባፋ የማይበቅል ምርጥ ዘር ለዞኑ ገበሬዎች መሸጡን በማመን

ዝርፊያ የፈፀሙ ፖሊሶች በአስተዳደሩ በነፃ ተለቀቁ

መንግስት ለሀዲያ ዞን ገበሬዎች የማይበቅል ምርጥ ዘር ሸጠ

በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ የፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ኮንስታብል ታጋይ ታደሰ እና ኮንስታብል ታሪኩ ሙላቱ በጋራ በመሆን ከአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ወደ ወረዳው የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን በማስቆም ተደጋጋሚ ዝርፊያ መፈፀማቸው ተጠቁሟል፡፡

በተለይ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈቀዱ የጊዶሌ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት እንደገለጹት ከሆነ ፖሊሶቹ ኃላፊነት ተጥሎባቸው የተመደቡበትን ስራ ጥለው የጦር መሳሪያ በመያዝ በተደጋጋሚ ዝርፊያ መፈፀማቸውንና በመጨረሻም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ቢደረግም በወረዳው አስተዳዳሪዎች ጣልቃ ገብነት የክሱ ሂደት እንዲቆም መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ በወንጀል ምርመራ ወቅትም ተከሳሾቹ በሚፈፅሙት ዝርፊያ የወረዳው አስተዳደር አካላት ድጋፍ እንዳደረጉላቸውና ከዝርፊያው የሚገኘውንም ይጋሩ እንደነበር እንደተደረሰበት ተጠቁሟል፡፡

ፖሊሶቹ ከዘረፏቸው ንብረቶች ውስጥ በኤግዚቢትነት ከተያዙ ንብረቶች መካከልም 8,350 ብር ጥሬ ገንዘብ፣ 15 ባለካሜራ ሞባይል ቀፎ፣ 30 ቻርጀርና ማዳመጫ፣ 12 ሚሞሪ ካርድና ስፒከር፣ 72 የሴቶች ታይት ሱሪ፣ 60 የሴቶች ፓካውት፣ 46 ባለኮፊያ የሴቶች ሹራብ እና 12 የወንድ ሸሚዞች መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡ እንደ ፖሊስ ምንጮቻችን ጥቆማ ከሆነ ያልተያዙ በርካታ የተዘረፉ ንብረቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገመት ተጨማሪ አስፈላጊው የማጣራትና

የምርመራ ስራ እየተሰራ እንደሆነ በመጠቆም ዘራፊዎቹ የወሰዷቸውን ንብረቶች ድጋፍ ካደረጉላቸው የወረዳው አስተዳደር አመራሮች ጋር ይከፋፈሉ እንደነበር መደረሱን አስታውሰዋል፡፡

ዘራፊ ናቸው የተባሉት ፖሊሶችም አስፈላጊው ምርመራ ተደርጐ በፍ/ቤተ ክስ ቢመሰረትባቸውም የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኪንተቦ እና ምክትላቸው አቶ ግንኙነት ኪንተቦ ጣልቃ በመግባት የክሱ ሂደት እንዲቋረጥና ተከሳሾቹም እንዲለቀቁ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን ከዚያም ኮንስታብል ታሪኩ ሙላቱ ወዲያው ከአካባቢው መጥፋቱ ተጠቁሟል፡፡

በተለይ ኮንስታብል ታጋይ ታደሰ የተባለው ተከሳሽ ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ ከአንድ ገበሬ እከፍላለሁ በማለት 1,000 ብር ብድር ከወሰደ በኋላ አልከፍልም፣ ከፈለክ ክሰሰኝ በማለቱ ሌላ ክስም እንደተመሰረተበት እና ጉዳዩ የደረሰው መርማሪ ፖሊስም ይዞት ወደ ፍ/ቤት ቢሄድም ኮንስታብል ታጋይ መርማሪው ላይ ሽጉጥ በመምዘዙ ተጨማሪ ክስ ተመስርቶበት የተሰጠውን የመንግስት መሳሪያ (ትጥቅ) እንዲያስረክብ የተሰጠውን ተዕዛዝ የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኪንተቦ ዳግም ነፃ እንዳወጡት ተገልፃDል፡፡ በዚህም የወረዳው አንዳንድ ፖሊሶችና የጊዶሌ ከተማ ነዋሪዎች የስራና የመኖር ዋስትናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን በመጠቆም የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን አይቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ነገር ግን በወረዳው አመራሮች ተባባሪነትና መመሪያ በሚፈጠር የፀጥታ ችግር የወረዳው ፖሊሶች ህዝብን ከመጠበቅ ይልቅ ራሳቸውን ወደ መከላከል እንደሚያመሩና ህዝቡም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስድ ሊያሳስቡ እንደሚችሉ በማስታወስ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ በተላይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በወረዳው ቢፒአር እና ቢኤስሲ በሚባለው አዲሱ የስራ መመሪያን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ያሉ ምሁራን ሰራተኞች እና አዳዲስ ተመራቂ ተማሪዎች ወደስራ እንዳይሰማሩ በማድረግ የወረዳው ካቢኔ አባላት ብቃት የሌላቸውን ዘመዶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመንግስት መስሪያ ቤት እየቀጠሩና እያሰማሩ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ከቤተሰብና ከዘመድ የተረፉ ክፍት ቦታዎችም በኢህአዴግ ህዋስ አደራጆች እየተሞላ እንደሆነና በተለይም በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት እና በግብርና ቢሮ ችግሩ በሰፊው እንደሚስተዋል ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኪንተቦ ጋር ጥረት ብናደርግም ስልጠና ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ምክትላቸው ወደ ሆኑት አቶ ግንኙነት ኪንተቦ ጋር ብንሞክርም ለስራ ጉዳይ ከቢሮ ወጥተው ወደ መስክ ስራ መሄዳቸው ከጽ/ቤታቸው የተገለፀ በመሆኑ ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

ሐምሌ አጋማሽ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለሚመለከተው አካል በማመልክት ንብረትነቱ የደቡብ ክልላዊ መንግስት የሆነው የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ከክፍያ ነፃ ሌላ ምርጥ ዘር በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ለገበሬዎቹ መታደሉን አስታውሰዋል፡፡ ወቅቱን በሚመለከትም ለገበሬው ሐምሌ 15 ቀን 2004 ዓ.ም አካባቢ ስለደረሰላቸው የተዘራው ምርጥ ዘር እንደሚበቅል አስታውቀዋል፡፡

በቅድሚያ የተሸጠው የማይበቅለው ምርጥ ዘርን በሚመለከትም የሚመለከተው አካል ናሙናውን ወስዶ እያጠና ስለሆነ ምክንያቱን መናገር እንደማይችሉ በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ክስ ጥፋተኛ ተብላለች፡፡ ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን” ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ርዕዮት ዓለሙ የፃፈችው “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶ” የተሰኘ መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ በራስ አምባ ሆቴል ፤ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተመርቋል፡፡ በምረቃው ዕለት ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ወላጅ አባቷ ጠበቃ ዓለሙ ጎቤቦ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም የመጽሐፉን ዝግጅት ምረቃ አስተባባሪ ለነበሩት የኮሚቴ አባላት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

በዕለቱ ቅድሚያ የተናገሩት ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም የወቅቱን የፍትህ ሥርዓት “በድቅድቅ ጨለማ” መስለው አቅርበውታል፡፡ ፕ/ር መስፍን እንዳሉት “ዛሬ የታሰረቺው ርዕዮት ብቻ ሳትሆን የታሰረው የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ አገራችን የተአምር አገር ናት፡፡ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ፍንጣቂ ብርሃን አለ፡፡ 14 ዓመት እስራትና 33 ሺ ብር ቅጣት የፈረዱ ዳኞች ባሉበት ሥርዓት 5 ዓመት የሚፈርድ ዳኛ መገኘቱ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ፍንጣቂ ብርሃን መኖሩን የሚያሳይ ተስፋ ነው” ብለዋል፡፡ በመቀጠል ንግግራቸውን ያቀረቡት ዶ/ር

ዳኛቸው አሰፋ ርዕዮትን ያወቋት በአንድ ወቅት የአዲስ ፕሬስ ጋዜጠኛ ሆና ስትሰራ ዩኒቨርስቲ ልታነጋግራቸው መጥታ እንደነበር ገልፀው አስተዋይነቷን አስምረውበታል፡፡ “በአሁኑ ጊዜ ለተማሪዎች ሌክቸር እንዳላደርግ ተደርጌ ደሞዝ ብቻ እየበላሁ እንድቀመጥ ተደርጌአለሁ፡፡” ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ “ሐሳብን በነፃነት ማንሸራሸር አስቸጋሪ መሆኑንን” ገልፀዋል፡፡

“የዚች ቆራጥና ጀግና ልጅ አባት በመሆኔ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል” ያሉት ወላጅ አባት ጠበቃ ዓለሙ ጎቤቦ “ርዕዮት የመጀመሪያ ልጃችን ናት” ካሉ በኋላ በቤት ስሟ “ሉሉ ባህርይዋም በተለያየ መልኩ የእኔን ይመስላል” ብለዋል፡፡ ዛሬ መሐላችን ባትኖርም መጽሐፏ ሲመረቅ ቤተሰቦቿ ደስ ብሎናል፡፡ መጽሐፏ የልጅ ልጄ ነው፡፡ እኔም የዚህ መጽሐፍ አያት ሆኜአለሁ፡፡ የመጽሐፉም መታሰቢያ ለታዋቂው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባልደረባና የጦር ጀት አብራሪ ለነበረው ኰሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ እንዲሆንላት በማድረጓ ደስ ብሎኛል፡፡ ልጄን የምመስላት በሻማ ነው፡፡ ከመታሰሯ በፊት ዛቻ፣ ስድብ መዋረድ ተፈጽሞባታል፡፡ ሁለት ወር ከ15 ቀን በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ስትታስር አልተለቀቀችም፡፡ ነገ ነፃ ሆና በተለያዩ መድረኳች

ሐሳቧን በነፃነት እንደምትገልጽ አልጠራጠርም” ብለዋል፡፡በመጨረሻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ነጋሶ “ርዕዮት ስለ ሃይማኖት አባቶች የፃፈችውን ሳነብ 97 ዓ.ም ትዝ አለኝ፡፡ በዚያን ዓመት ያሁሉ ሰው ሲጨፈጨፍ የሃይማኖት አባቶች ዝም ብለዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊው አቡነ ጴጥሮስ በሂትለር ዘመን በጀርመን ውስጥ የሂትለር ፋሺስታዊ ሥርዓት ተቃውሞ የሞተ የሃይማኖት አባትም አለ፡፡ እኔ የኢህአዴግ አባል ስለነበርኩ በኢህአዴግ ቋንቋ አካፋን አካፋ ማለት አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁን ወቅት የሃይማኖት አባቶች አገራቸውንና ህዝባቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ረስተዋል፡፡ ርዕዮት በይግባኝ የተፈረደባትን ተከራክራ አስቀንሳለች፡፡ እስከ መጨረሻው ተከራክራ ነፃ ትወጣለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ርዕዮት ዓለሙ በ2004 ዓ.ም ጐልታ የወጣች ወጣት ጋዜጠኛ ናት፡፡ በ2005 ዓ.ም ሌላ ጀግና ወጣት እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም የተለያዩ አገራዊና ወቅታዊ ግጥሞች እና ወጐች ቀርበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም በራስ አምባ ሆቴል ተመርቆ ገበያ ላይ የዋለው “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶ” የተሰኛ መጽሐፍም በአሁኑ ሰዓት ካዙዋሪዎች ላይ እየተነጠቀ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ከ ገፅ 1 የዞረ....

የእነ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው አሟሟት

አሁንም እያወዛገበ ነውበቅርቡ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም

በሞት የተለዩት የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ም/ፕሬዝዳንት የነበረው ታናሽ ወንድሙ አቶ ዳኛቸው እንግዳውና መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሰራተኛ የነበረው የአቶ ብርሃኑ ደምሴ አሟሟት አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ‹‹የመኪና አደጋው በድንገት የተከሰተ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬን እየፈጠረ መሆኑን ››አበክረው ይገልጻሉ፡፡

አደጋው በሚከሰትበት ወቅት አብረዋቸው መኪናው ውስጥ የነበሩትና ከአደጋው የተረፉትን ታናሽ ወንድማቸውን ወጣት ሱራፌል እንግዳውን አነጋግረነው ነበር፡፡ ሱራፌል በሰጠን መልስ ‹‹ በአሁን ጊዜ የአደጋውን መንስኤ ይሄ ነው ለማለት ተቸግረናል፡፡የአደጋውን መንስኤ አጣርቶ ማሳወቅ ያለበት የአካባቢው ትራፊክ ፖሊስ፤ የአካባቢው መደበኛ ፖሊስና የአካባቢው አስተዳደር ኃላፊዎች ናቸው፡፡ የምርመራ ውጤቱን በተደጋጋሚ ተመላልሰን ብንጠይቅ፤ አይደለም ሊነግሩን እኛን ለማነጋገርም ፍቃደኛ አይደሉም፡፡ አጥብቀን ስንጠይቃቸው የአደጋውን መንስዕኤ ለማወቅ እንደማይቻል አቋም ይዘው ይከራከሩናል፡፡እኛም በአሁኑ ጊዜ ከአደጋው ጀርባ ምን ነበር?ብለን እንድናስብ ተገደናል፡፡››በማለት መልሰዋል፡፡

ስለ አደጋው ሁኔታና ከአደጋው በኋላ የነበረውን ሁኔታ እንዲያስረዱን የጠየቅናቸው አቶ ሱራፌል ሲመልስ ‹‹ሁለቱም ወንድሞቼ ለስራ ስለሚቸኩሉ ከአዋሳ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ የጀመርነው ንጋት ላይ ነው፡፡ በተለይ ታዴ በእለቱ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ስለሚከፈት በስፍራው ለመድረስ እቅድ ነበረው፡፡አርሲ ነጌሌ አካባቢ የሚገኘው የፍተሻ ጣቢያ ላይ ተፈትሸን እንድናልፍ ተደረገ፡፡ እዚህ ፍተሻ ቦታ ላይ አንድ ሚኒባስ ቆማ ተመልክቼአለሁ፡፡ ዝዋይ ልንደርስ 40 ኪ.ሜትር ሲቀረን ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት ነበር፡፡ብርሃን ስለወጣ ይታያል፡፡አንድ የጭነት መኪና የቀኝ መንገዱን ትቶ የግራ ጠርዙን ይዞ በፍጥነት ወደ እኛ መጣ፡፡ ሹፌሩ ወደ ቀኝ አጥብቦ አጥብቦ ጠርዝ ደረሰ፡፡ ከፊት ለፊት መጣ ከዚያም እኛ የነበርንበት መኪና መንገዱን ለቆ ቦይ ውስጥ ገባ፡፡ ሹፌሩ ፍሬን ሲይዝ መኪናው አራት ጊዜ ተገለባበጠ፡፡ ከዚያ እኔ ቀና ብዬ ስመለከት መንገዱን ያስለቀቀን መኪና በፍጥነት መንገዱን አስተካክሎ ወደ መጣንበት አቅጣጫ ወደ አርሲ ነጌሌ በረረ፡፡ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያቺ ፍተሻ ቦታ ቆማ የነበረችው ሚኒባስ መጣች፡፡ የወንድማችንን የዳኛቸውን መሞት አረጋግጠው አስክሬኑን ጫኑት፡፡ ታዴና ሹፌሩ ህይወታቸው ባለማለፉ ያቃስቱ ነበር፡፡ ወደ ሆስፒታል እናደርሳቸዋለን ለሻይ ትሰጠናለህ አሉኝ፡፡ እሺ ብዬአቸው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲያደርሱን ጠየቅኳቸው፡፡ጉዞ ጀመርን፡፡ ሁለቱም በመንገድ ላይ ሞቱ፡፡ጥቁር አንበሳ እንደደረሱ መኪናውም ሹፌሩም ለሻይ ትሰጠኛለህ ያለኝንም ከዚያ በኋላ አላየኋቸሁም፡፡ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ስንጠይቅ የሚሰጠን መልስ አሉታዊ ሆኖብናል፡፡ አሁን ተረጋግቼ ሳስበው ያ መንገድ ዘግቶብን እንድንገለበጥ ምክንያት የሆነን መኪና ለምን ሸሽቶ አመለጠ? ተከታትሎ ለመያዝ ወይም ለማጣራት ለምን አልተፈለገም? ያ ፍተሻ ላይ ቆሞ የነበረው ሚኒባስ እንዴት ዝግጁ ሆኖ ቆመ? የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ተገደናል፡፡››ሲሉ መልሰዋል፡፡

የምርመራ መዝገቡን ያውቁታል ተብሎ ጥቆማ ወደ ተሰጠን አርሲ ነጌሌ ፖሊስ ባልደረባ ኢንስፔክተር ጎሳዬ ዘንድ ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ ደውለን ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ዜናውን ለጊዜው ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡

Page 12: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

12 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

የጳጳሳቱና ...የኢንዶኔዥያው ዛፍ ...

የግፍና የሰቆቃ እስር በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶችከኢንጅባራው ዘላለም

ባለፈው ጊዜ የግፍና የሰቆቃ እስር በቃሊቲ በሚል ርዕስ የቃሊቲን እስር ቤት ገበና ከብዙ በጥቂቱ ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡ ኢህአዴግ እስር ቤቶቹን “ማረሚያ ቤቶች” እያለ ቢጠራቸውም፣ መጠሪያው እውነተኛውን የእስር ቤቱን ገጽታ ስለማይገልፀው እንደ ቀድሞ ስሙ “ወህኒ ቤት” ተብሎ ቢጠራ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት የከፉ ናቸው ለማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የግፍና የሰቆቃ እስሩ እጅግ ሰብአዊነት በጐደለው ሁኔታ በፖለቲካ አስተሳሰብና በዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፡፡ ቃሊቲ ወህኒ ቤት እስር ቤት ብቻ ሳይሆን የመረጃ ማዕከልም ነው፡፡ የመላው አገሪቱ የዕለት ተዕለት መረጃ በትኩሱ በቅብብል ይደርሳል፡፡ በመላው የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ያለው ሁኔታም በየዕለቱ ይሰማል፡፡

ባለፈው ጽሁፌ ራሴን ለማስተዋወቅ እንደሞከርኩት በዚህ የዘረኞች ወህኒ ቤት 19 ዓመት ከ8 ወር ቆይቼአለሁ፡፡ እኔ ከዚህ ሳልወጣ አራትና አምስት ጊዜ ተመላልሶ የታሰረ እስረኛ አጋጥሞኛል፡፡ የሸዋሮቢት፣ የዝዋይና በቅርቡ ሥራውን የጀመረው የቂሊንጦ ከፍተኛ ወህኒ ቤት በመረጃ ደረጃ የሁለት የጐረቤታሞች ያህል መረጃ እንለዋወጣለን፡፡ በዚሁ መሠረት ዛሬ ህዝብ ስለማያውቃቸው ድብቅ እስር ቤቶችና በየድብቅ እስር ቤቶቹ ስለሚፈፀሙ ግፈኛ ድርጊቶች ላውጋችሁ፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ “በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካና የህሊና እስረኛ የለም” ይለናል፡፡ ምንም እንኳን መኖሪያ ቤታችን ቃሊቲ ቢሆንም የመንግስትን መረጃ በተሟላ ሁኔታ እንከታተላለን፡፡ ሬዲዮ ከተከለከልን ሦስት ዓመት ቢልፈንም፣ በቃሊቲ ኢቴቪ 24 ሰዓት ይሰራል፡፡ የውጭ ሚዲያዎች የሚያወሩትን ውጭ ካለው በበለጠ እንሰማለን፡፡ በተጨማሪም ጠያቂዎቻችን ሁሉንም ነገር ይነግሩናል፡፡

የሀገራችን ግዙፍ እስር ቤቶች ሰነድ እንደሚያመለክተን 90% የሚከተሉት ድርጅቶች እስረኞች ናቸው፡፡ ኦጋዴን ነፃ አውጭ ግምባር፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ ነፃነት፣ ትንሳኤ ኢትዮጵያ አርበኞች ግምባር፣ ኦነግ፣ የሲዳማ ነፃነት፣ ደሚት (የትግራዩ)፣ የአፋር ነፃነት ግምባር፣ የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ የደቡብ የፍትህና እኩልነት ግምባር፣ አርበኞች ግምባር፣ ግንቦት 7 ናቸው፡፡ ታሳሪዎቹ የድርጅቶቹ ተከታዮች አሊያም ተዋጊ አባሎቻቸው

ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ የድርጅቶቹን ስም እንኳን የሰሙት ከታሰሩ በኋላ ነበር፡፡ የየአካባቢያቸው ደህንነቶችና ካድሬዎች ከፖሊስና ከዐቃቤ ህግ ጋር እየተቀናጁ በፈጠሩት ክስ የተሰጣቸው ስም ነው-አሸባሪነት፡፡

በሀገራችን በሚገኙ እስር ቤቶች ማለትም ድሬደዋ፣ ቃሊቲ፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋሮቢት፣ ዝዋይ የፌደራል እስር ቤቶች ተብለው ሲጠቀሱ ከነዚህ ውጪ የክልል እስር ቤቶችና በበርካታ የክልል ከተሞች፣ በመሀል አዲስ አበባ በሚገኙ ቪላዎች፣ በደህንነት ተቋሞችና ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ጭምር ስውር እስር ቤቶች ተወቋቁመዋል፡፡ በደርግ ዘመነ መንግስት የተመሰረቱ በርካታ የሸቀጣሸቀጥና የእህል ማከማቻ መጋዘኖችን ኢህአዴግ ወደ ስውር እስር ቤትነት ቀይሯቸዋል፡፡

የራሱን ችግር ሳይፈታ ሰላም አስከባሪ ነኝ፤ የሚለው ወያኔ/ኢህአዴግ ገበናው ሲፈተሸ ራሱ ፀረ ሠላም ነው፡፡ ወጣቱን ኃይል ማሰር ተቀዳሚ የስርዓቱ አምባገነናዊነት ማሳያ ቢሆንም ይበልጥ የስርአቱን አስከፊነትና አደገኝነት የሚያረጋግጠው አባትና ልጆችን እንዲሁም ወንድማማቾችን፣ ባልና ሚስትን፣ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ፣ በዘር ምክንያት አድኖ በጭካኔ የሚያስርና ለዕድሜ ልክ እስር የሚወረውር አምባገነን ስርዓት ነው፡፡ የሚፈፅማቸውን ድርጊቶች ለተመለከተ ይህ ስርዓት የዘር ማጥፋት ድርጊት እየፈፀመ መሆኑም ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ለዚህ እኩይ ተግባሩ ቀድሞ ፈርዶ ለይምሰል የሚያቀርባቸው የክስ መዝገቦች የሚዘረዘሩት ክሶች፡-

የሀገርን ግዛትና አንድነትን መንካት

ሽብርተኛ

ኦነግ፣ ግንቦት 7 በሚል ነው፡፡

ይህን በአሁኑ ጊዜ “ሀገራችን ሠላም ነው፤ ዕድገት እያስመዝገብን ነው፡፡ ኢህአዴግ በምስራቅ አፍሪካ ተደማጭ ነው” እያለ ከሚነግረን የተለየነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ 21 ዓመታት ሙሉ ታፍኖ እየተገዛ ነው፡፡ መብቴን ሲል ተለጣፊ ስም እየተሰጠው ወደ እስር ቤት የሚወረወረው ወጣት ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነው፡፡ አገር ጥሎ የሚሰደደውም የትየለሌ ነው፡፡ ኢህአዲግ “ለሱማሌ ሠላም ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ ዲሞክራሲያችን ለአፍሪካ ምሳሌ ሆነ፤ እከሌ የሚባል ፈረንጅ ምስክርነቱን ሰጠ ወዘተ” በማለት የራሱን ጉድ ደብቆ ባዶ የፕሮፓጋንዳ ጩህቱን ይጮሀል፡፡ ይህን ባዶ ፕሮፓጋንዳ ማየት የፈለገ ሌላ ማስረጃ ሳያስፈልገው ሀገራችን ሠላምነች

ወይ? የተረጋጋ ፖለቲካ አለ ወይ? ብሎ ቢጠይቅ መልሱ ከኢቴቪ፣ ወይም ከአቶ ሽመልስ ከማል፣ (በረከት) ሳይሆን የገሀዱ ሀቅ ሀገሪቷ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ለማየት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን እስር ቤቶችን መፈተሸ በቂ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ድብቅ እስር ቤቶች ከሕዝብ ለምን ተደበቁ? ምንስ እየተሠራባቸው ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ዜጎች ከመላው ሀገሪቷ ተለቃቅመው የታጐሩበትን ሚስጢራዊ እስር ቤቶች ምስጢር ለማወቅ ይረዳችሁ ዘንድ የማውቀውን ላስረዳችሁ፡፡ ለምሳሌ የ90 ዓመቱ አዛውንት ከነልጆቻቸው የታሰሩበትን ቀልቤሳ ጢሎና ልጃቸው አብረሃም ቀልቤሳ፣ ከጉምዝ ብሔር የ85 ዓመቱ መንግስቱ ቦንድ፣ ከነልጁ የታሰረው ኢንጅነር ጁማ ሩፋኤል፣ ኦባንግ ኦሎቾ የጋምቤላ ጦር አዛዥ ወርቁ በለጠ የአርበኞች ግምባር (ም/ሊ)፣ የግንቦት 7ቱ ኮረኔል አበረ፣ ሻለቃ መኮንን፣ የሲዳማው ንቅናቄ አባላት፣ የሱማሌው ከሊፋ አሊ፣ የኦነግ መቶ አለቃ አብደላ አፋ ወዘተ . . . እውነት ለብሔራቸው ሥጋት፣ ለአገራቸው ሽብርተኛና ወንጀለኛ ሆነው ነው የታሰሩት? ወይስ ለብሔራቸው መብትና ጥቅም ለራሳቸው ነፃነት ሲታገሉ? ሀቁ ለኢህአዴግ ዘረኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ሥርዓት ሥጋት ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡ በእኔ እምነት የፖለቲካ እስረኞች ናቸው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዕድገቷም ሆነ ለውድቀቷ እነዚህ ህዝቦቿ ናቸው፡፡ ስለዚ ለምን ይህ ሁሉ የፖለቲካ እስረኛ ዜናው ለህዝብ እንዳይሰማ ተደረገ? በአብዛኛው የተያዙት በጦርነት ቆስለው ሱዳን ውስጥ በመታከም ላይ እያሉ ነው፡፡ የታሪክ ጠላታችን የሆነችው ሱዳን እያነቀች እየሰጠች ነው፡፡ ቢሆንም ትግሉ ተቀጣጥሎአል ብሎ መመስከር ይቻላል፡፡ ይህ ለህዝብ አንዳይሰማ ወያኔ/ኢህአዴግ የህዝብን ስሜት ለማስቀየር ሲምፖዚየም፣ ዐውደ ጥናት፣ የልማት ስብሰባ፣ ወጣት ሊግ፣ ሴት ሊግ እያለ ህዝብን ያደናግራል፡፡ መሠረታዊ ፍላጐት እንኳ ሟሟላት አቅቶታል፡፡ በሰፊው በገበያ ላይ ይገኙ የነበሩት ዘይትና ስኳር እንኳን ኮንትሮባንድ ሆነው ነጋዴዎችን በአፈና እያሳሰሩ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ ብዥታ ለመፍጠር ፕሮፓጋንዳ ሊነዛ ይችላል፡፡ ግን ሀቁን እስር ቤቶች አፍ አውጥተው ይናገራሉ፡፡ የወያኔ መንግስት ወንድም የሆነው የሊቢያ መሪ ጋዳፊ ከዚህ የበለጠ ምን ግፍ ሠራ? ሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ከአፍሪካ ቀንድ የተሻለ ዴሞክራሲ ስርዓት ዘርግተው ህዝባቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አፍሪቃ ቀንድ ግን ሰብአዊና ዲሞክራሲ ስርዓት

በፍፁም ያልዘረጉ ጨፍጫፊዎች የነገሱባት ናት፡፡ ቀጠናው ለረዥም ዓመታት በመንግስትነት የተቀመጡ አምባገነን መሪዎች ያሉበት ነው፡፡ ስለዚህ ከጋዳፊ ምንም የሚለያቸው ነገር የለም፡፡ ይገላሉ፣ አካለ ጐደሎ ያደርጋሉ፣ ያስራሉ፣ በባዶ ፕሮፓጋንዳ ህዝባቸውን ይዋሻሉ፡፡

ሌላው ድብቁ የስቃይ ቦታ ጦር ኃይሎች ጀርባ የደርግ ደህንነት የነበረው ግቢ ነው፡፡ ይህ ግቢ በከተማችን እንደወጡ የሚጠፉ ዜጐች አፋልጉኝ ፎቶ የሚወጣባቸው ዜጐቻችን የሚታጐሩበት ዘግናኝ ቦታ ነው፡፡ እዚህ ቦታ ሲገቡ ወደየት ቦታ እንደ ተወሰዱ እንዳያውቁ አይንዎትን እተያዙበት መኪና ውስጥ ይታሰራሉ፡፡ እዛ ግቢ ውስጥ ለረዥም ዓመታትም ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ የሰው ልጅ ስጋው ተበጣጥሶ የሚወድቅበት፣ በጋለ ብረት የሚቃጠልበት፣ ወንድ ልጅ እንደ እንስሳ የሚኮላሽበት፣ ጥፍሩ የሚነቀልበት፣ እንደ እንስሳ እንዲመገብ የሚገደድበት፣ የስቃይ ቦታ ነው፡፡ እዚህ እስር ቤት እስከ ሁለት ዓመት ታስረው ከቆዩ በኋላ ቅብብሎሹ ይቀጥላል፡፡ ወዴት? ካሉ ወደ ማዕከላዊ ይላኩና እንደ አዲስ ምርመራው ማዕከላዊ ይቀጥላል፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ለዚህ አይነቱ የግፍ ሰለባዎች ለመጥቀስ ያህል ዶ/ር ፈንታሁንንና መቶ አለቃ አብደላ ከሊፋን መጠይቅ ይቻላል፡፡ በዚህ የማሰቃያ ስፍራ የወንድ ብልት የዘር ፍሬ በስቴፕለር ይጣበቃል፡፡ ውሃ ኮዳ ይታሰርበታል፡፡ ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ እጅግ ዘግናኝ የግፍ ድርጊቶችማ ይፈፀማሉ፡፡

የስዊዲን ጋዜጠኞችና የእነ ከሊፋ አሊ እስርና ዶክመንተሪ ፊልም ቅንብር ጊዜውን ጠብቆ ይፋ ስለሚሆን ለዛሬው ልለፈው፡፡ ከዚህ ቀደም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቲርና የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅት ፊት ለፊት ስለተቃጠለችውም ታክሲም ጉዳይ ለጊዜው ላቆየው፡፡ በአጠቃላይ ግን በፈጠራ ዶክመንተሪ ፊልም ባዶ ፕሮፓጋንዳ መለፈፍ ከደርግ ውድቀት የአለመማር ውጤት ነው፡፡ “ምንም የፖለቲካ እስረኛ የለንም፡፡ ሀገሪቷ ሠላም ነች፡፡ የተረጋጋ ፖለቲካ አለ” እየተባልን እስከመቼ እንታለላለን? አሁን ዜጐች በየወህኒ ቤቱ ታጉረው ያሉትን የክስ መአት እያወቁ ህዝብን መዋሸት እስከመቼ?

ይህ ፁሁፍ እስከሚፃፍበትም ደቂቃ ኢህአዴግ በሁሉም የሀገሪቷ እስር ቤቶች አዳዲስ እስረኛ እያስገባ ይገኛል፡፡ ይህንን መካድ አይቻልም፡፡ እስር ቤቶች አፍ አውጥተዋል፤ ይህ እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ሲሆን በሰፊው የውሸት ድራማውን በማጋለጥ ወደ ፊት እናቀርባለን፡፡ ቸር እንሰንብት

ከ ገፅ 10 የዞረ.... ከ ገፅ 10 የዞረ....

ጥቂት ምክርኮንፊሺየስ የተባለ (ከ550-498 ዓ.ዓ) የኖረ

የጥንታዊቷ ቻይና የሃይማኖት መምህርና የኮንፊሽየሲዝም እምነት መስራች ነበር፡፡ አንድ ቀን ደቀ መዝሙሩ ጥያቄ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ጥያቄውም “መምህር ሆይ! የደስታን ምስጢር ልትነግረኝ ትችላለህን?” የሚል ነበር፡፡

ኮንፊሺየስም “የደስታ ምስጢር ምን እንደሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን ወደ ፊት መምህር ወይም የአገር መሪ ልትሆን ትችላለህና አንድ ምክር ልምከርህ . . .እሱም አንዲት ሀገር የምትጠፋበት ምስጢር ነው፡፡ አንዲት ሀገር የምትጠፋው መሪዎቿ ትችትን ወይም ምክርን መቀበል ባቆሙ ሰዓት ነው፡፡ መሪዎቿ ምክርን ማዳመጥ ሲያቆሙ ያን ጊዜ ሀገር ትጠፋለች” ብሎታል፡፡

ኢህአዴግ መስማት አይፈልግም እንጂ ብዙ መካሪዎች ነበሩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ‹‹ኢህአዴግ መስማትና ማየት የተሳነው መንግስት አይደለም›› ቢሉም ቅሉ ግን መንግስት የተቃዋሚዎችን ሃሳብ እና የጋዜጠኞችን ምክር ‹‹አልሰማም!!›› የሚል ባህሪ አለው፡፡

ፓርቲው የፍትህ ድምፆች፣ የነፃነት ጩኸቶችንና የእርቅ ጥሪዎችን መስማት የተሳነው ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ስህተቱን ማመን አይወድም፣ ስህተትን ማወቅ ያንን ስህተት ደግሞ ላለመስራት ይጠቅማል፡፡ ሆኖም ግን ፓርቲው ስህተቱን ስለማያምን አንድ ጊዜ የሰራውን ስህተት

በተደጋጋሚ ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ ስህተትን ማመን ከትናንት ዛሬ መሻሻልን ማሳየት ነው፡፡ ስህተት የለብኝም ማለት ግን በራሱ ትልቅ ስህተት ነውና፡፡

ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን በሰበሰቡ ዕለት አንድ ወጣት መምህር ጥሩ ምክር ለግሷቸው ነበር፤ አልሰሙትም እንጂ፡፡ ምክሩም “እባክዎትን ህዝቡን በቅንነት ይምሩ፣ ቅን ይሁኑ! ›› የሚል ተማጽኗዊ አሳብ ነበረው፡፡

ዛሬም ለኢህአዴግ ባለስልጣናት ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ዘላለማዊ የሆነ ስልጣን የለም፡፡ ከታላቁ እስክንድር እስከ ጁሊየስ ቄሳር፣ ከናፖሊዮን እስከ ሂትለር ‹‹ታላቅና አውራ ነን›› የሚሉ ሁሉም አምባገነን መሪዎች አልፈዋል፡፡ እናንተም እንዲሁ ዛሬ የያዛችሁትን ቦታ ነገ ትታችሁት ታልፋላችሁ፡፡

አገር እየጠፋች፣ ማንነት እየተበላሸ፣ ድሃ እየተበደለ እና ፍርድ እየተጓደለ ነው፡፡ ቢያንስ ህዝቡን አድምጡ፣ ህዝቡ ነፃነትና ፍትህ ይፈልጋል፡፡ አንድ ቀን የታፈነና የታመቀ ነገር ሲፈነዳ ኃይሉ ከባድና ሊቆጣጠሩት የማይቻል ይሆናል፡፡ የቅርቦቹ አምባገነኖች ቤን አሊ፣ ሙባረክና ጋዳፊ ትምህርት መሆን ይችላሉ፡፡ ካልሆነ ግን አወዳደቃችሁ እንደ ሮም አያምርምና ለሀገር ስትሉ፣ ለልጆቻችሁና ለመጪው ትውልድ ካሰባችሁ ከመጠላለፍ እና ጉድጓድ ከመማስ ወጥታችሁ ወደ እርቅና ወደ ፍቅር መንገድ ግቡ፡፡

መሠረት የጣሉትና በኋላ ላይ በደርግ ኮማንዶዎች በገመድ ታንቀው እንዲገደሉ የተወሰነባቸው ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ቴዎፍሎስ የከፈቱትን መንገድ በመከተል በየአጥቢያው ከሰዓት በኋላ ምዕመኑን እናስተምራለን ከሚሉት መካከል አንዳንዶቹ በኑሮአቸው፣ በትምህርታቸው፣ በህይወታቸው፣ በትዳራቸው ወዘተ ስኬትን በማጣት “ይቻላል” በሚል የደፋሮች መርህ ዘው ብለው የገቡበት፤ አሜሪካንና የበለፀጉ ሀገራትን ጨምሮ ሀብትን የምትመኝ “ወየውልህ” ሲሉ ከርመው መንገድ ሲመቻችላቸው ራሳቸው ቀዳሚ የሆኑትንና ሌሎች ለጥቅማቸው የሚተጉትን ሁሉ ቤተ ክርስቲያናችን መቀበሏና እየተቀበለች መገኘቷ ከመዕመኑ የሚሰወር አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ይህና ሌሎች አሳዛኝ ድርጊቶችንና ንግግሮችን ተከትሎ የሃይማኖት ሰዎችን የሚያከብር ሆነ የሚያምን አሊያም የሚናገሩትን የሚቀበል ለማግኘት አዳጋች የሆነው፡፡

አሁን አሁን የሃይማኖት ሰዎች ተልዕኮና ምግባር የመቀለጃ ብቻ ሳይሆን የኮሜዲያን ገቢ ማግኛ እስከ መሆን ደርሷል፡፡ የጳጳሳት አስኬማ (ቆብ) ከተራ የሰሌን ኮፊያ እኩል መታየት ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የሃይማኖቱ መሪዎችም ፎቶአቸው ከተሰቀለበት እንዳይወርድ፣ ከፈቃደ ፈጣሪና አገልጋዩ ስምምነት ውጪ የቆመ ሐውልት እንዳይፈርስ ወዘተ ከመትጋትና ከመመካከር ውጪ በትውፊቱ፣ በእምነቱ፣ በምግባሩ፣ በታሪኩ፣ ወዘተ እየጠፋላለው ትውልድ ቁብ የሰጡት አይመስልም፡፡

አጋጣሚው አልጋ በአልጋ የሆነላቸው ተኩላዎችም ምዕመኑን በሚያማልሉ የፈጣሪ ቃል፣ በሚታዩ ክስተቶች፣ በማይገባው ምናብ፣ ወዘተ እየተቀራመቱት ነው፡፡ በየመንደሩ በሚኒባስ ላይ

ተሰቅሎ በጄኔሬተር በሚሰራ ድምጽ ማጉያ የእገሌና እገሊት መዝሙር እየተባለ ያለ ከልካይ ይሸጣል፡፡ የሃይማኖት ማስተማሪያ የተባሉ መጽሐፍት ይሸጣሉ፡፡ ከመንገድ ላይ አልፎ የመኖሪያ በር እየተንኳኳ ለቤተክርስቲያን ማሠሪያ ገንዘብ አምጡ እየተባለ ይጠየቃል፡፡ ነገሩ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ መሆኑ ነው፡፡”

በተከበረችና ቅድስት በምትባል ሀገር ግብረሰዶማውያን እንዳይሰበሰቡ ድምፃቸውን ለማሰማት ተሰባስበው የነበሩ የሀይማኖት አባቶች ስብሰባቸው በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የሚከለክለውን ህገ መንግስት መንግስት ደፍጥጦት ሲገባ ምላሻቸው የቤተ ክርስቲያን ደውል ከማሰማት ይልቅ ዝምታን ነበር፡፡

ምሽትም የVOA የአማርኛው ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ለነበሩ የኦርቶዶክስ ጳጳስ ቃለ ምልልስ ሲያደርግላቸው እውነቱን ላለመናገር ሲልመጠመጡ ላዳመጣቸው ቅንጡ ህይወታቸው እንይዳዛነፍ የሚተጉ መሆናቸውን ለመገመት እምብዛም አያዳግተውም፡፡ የነዚህ ግለሰቦች አሳፋሪ ድርጊት መቼ እንደሚያቆምና የሃይማኖቱ መሪዎች ገመና ከመዝረክረክ እንዴት እንደሚያመልጥ የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡

እስከዛው ግን ሀውልቱም፣ ገመናውም፣ ገና አይሮፕላን እንገዛለን ያሉት እንስት ፉከራና፤ ------------- አላቸው የተባሉት ጳጳሳት ወዘተ ለጊዜው ይኖራሉ፡፡ ፈጣሪን የለም የሚያሰኘው ትዕግስቱም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ይኖራል፡፡ አንባቢም ገመና ድራማ ሳይሆን የገሐዱ ምድር እውነት መሆኑን አውቀህ ሃይማኖታዊ መፍትሄህን አጠናክር፡፡

Page 13: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

13Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ባሰናዳው ዝግጅት ላይ በርካታ ተዳሚዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በጽ/ቤቱ አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ላይ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ለውይይት የሚረዳ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን በፅሁፋቸው መነሻም በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ አድርገዋል፡፡

ኢ/ር ዘለቀ እንደገለፁት “ምርጫው ለኢህአዴግ በህዝቡ እንዳልተፈለገ ነግሮታል፡፡ ይህን የተገነዘበው ኢህአዴግም ከምርጫ 1997ዓ.ም. በኋላ የተለያዩ የማዳፈኛ ስልቶችን መጠቀም ጀመረ” በማለት የገዥውን ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ ጠቅሰዋል፡፡

ከጠቀሷቸው የኢህአዴግ መቆጣጠሪያ ስልቶች መካከልም የመጀመሪያው ነፃ ፕሬሱን መዝጋትና ለተቀሩት ትርፍራፊ ሚዲያዎች መቆጣጠሪያ ህግ ማበጀት ነበር፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ያደረገው የተለያዩ ሀሳቦች ህዝቡጋ እንዳይደርሱ ካለው ምኞት በመነሳት ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

በማያያዝም የፀረ ሽብርተኝነት፣ የመያድና ሌሎችንም የአፈና ህጐች በማውጣት ለሀገርና ህዝብ መልካም ለውጥ የሚታገሉትን ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና ጥቂት ነፃ ፕሬሶችን ለመቆጣጠር ያለመ መስመር ተከትሏል፡፡ ይህንን ተከትሎም የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳይኖርና ሀገሪቱ በሲስተም እንዳትመራ በማድረግ የግለሰቦች የበላይነት እንዲጐለበት የተጋ ስርዓት ሆኗል በማለት ትችትም አቅርበዋል፡፡

ኢህአዴግ ከ1997 በኋላ የተከተለው ራስን አግንኖ የማውጣት አቅጣጫ ሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚችልና አስተማማኝ መሠረት ያለው እንዲሁም ሁሉንም እኩል የሚጠቅም ኢኮኖሚ ለመገንባት አልቻለም፡፡ ሁልጊዜ ጊዜያዊ መፍትሄ በማፈላገለግ የተጠመደ ፓርቲ ነው፤ ኢኮኖሚን የሚያሳድገው ነፃ የሆነ ህዝብ ነውም ብለዋል፡፡

በማስከተልም ከላይ የዘረዘሯቸው ሁነቶች የፖለቲካ አለመረጋጋትና ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ሊፈጥሩ ችለዋል፡፡ ለአብነትም የመምህራን ጥያቄና የሙስሊም ወንድሞቻችን ጥያቄ ሊጠቀስ ይችላል በማለት ገልፀዋል፡፡

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳቶች በሚንቀለቀሉበት ሀገር ከተቃዋሚዎችስ ምን ይጠበቃል? በማለት በተቃውሞ ጐራ የተሰለፉ ሀይሎች ማድረግ አለባቸው ያሏቸውን ሁኔታዎች ዘርዝረዋል፡፡

ከነዚህም መካከል በህዝባቸው መታመን፤ ተተኪ አመራሮችን አሰልጥኖ መተካት፤ የረጅም ጊዜ ፕሮግራም ነድፈው ቋሚ ጠንካራ አባላትን ማፍራትና በተለይ ለዚች ሀገር አንዲት አስተዋፅኦ አደርጋለሁ ብለው የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች በመሰባሰብና በመዋሀድ አንድ ትልቅ ሀይል መመስረት ይገባቸዋል በማለት የመወያያ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡

ከቤቱም በርካታ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጐባቸው መርሀግብሩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

አንድነት ፓርቲ በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ተስጥቶበት በተዘጋው በነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ቁጥር 112546 “ተከሳሽ” ዓቃቤ ህግ በሚል ደብዳቤ ለውይይት ተብሎ ፍርድ ቤት የተጠራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ተወካይ ከፍተኛ አመራሮች የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣የተከበሩአቶ ግርማ ሰይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ትናንት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በድንገት ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደረገ፡፡

አንድነት በእነ አንዱዓለም አራጌ ላይ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ በተቃውሞ መግለጫ መስጠቱ በፓርቲው ፍርድ ቤቱ ላይ እና የፍትህ ስርዓቱ ላይ የተቃጣ ከፍተኛ ጥፋት ነው በማለት በስፋት ካተተ በኋላ ፓርቲው በአገሪቱ ለመድበለ ፓርቲ ግንባታ የሚያደርገውን ከፍተኛ አሰተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተግሳፅ እንዲታለፍ መወሰኑን የግራ ዳኛው ሁሴን ይመር በንባብ አሰምተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ በፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት የፓርቲው ተወካይ አመራሮች እንዳስረዱት ከሆነ ለውይይት ተብለው በቢሮ ውስጥ ጉዳዩን ለመስማት 3ኛ ወንጀል ችሎት ዳኞች ፅ/ቤት ውስጥ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ

በነፃው ፕሬስ ላይ የሚፈፀመው አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር(መድረክ ) ጥሪውን አቀረበ፡፡ መድረክ ጥሪውን ያቀረበው ሐምሌ 25 ቀን 2004 ዓ.ም ‹‹ በነፃው ፕሬስ ላይ የሚፈፀመው አፈና በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡›› በማለት ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

መግለጫው ‹‹ያለ ፕሬስ ከሚኖር መንግስት ያለመንግስት የሚኖር ፕሬስ እመርጣለሁ›› የሚለውን የቶማስ ጃፈርሰን ጥቅስ በማስቀደም የጀመረው የመድረክ መግለጫ በአሁኑ ጊዜ መንግስት በነፃው ፕሬስና በጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመ የሚገኘውን ድርጊት በመዘርዘር በጥብቅ አውግዞ ድርጊቱ እንዲቆም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ መድረክ በመግለጫው እንደዘረዘረው ‹‹በብዙ ሺህ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖች መስዕዋትነት የተገኘው ድልና የተጀመረው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ወደ ጎን ትቶ የጥቂት ግለሰቦች የፈላጭ ቆራጭነትና የአምባገነናዊ ስርዓት ግንባታ ከተጀመረ 21 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ በተለይ ከ1997ዓ.ም ጀምሮ ህገ-መንግስቱን በግልፅ በመጣስ ነፃውን ፕሬስ በማፈን ጋዜጠኞች ላይ በትሩን በማስነሳት ላይ ይገኛል›› ብሏል፡፡

በማያያዝም ‹‹ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ከ45 ቀናት በላይ በመደበኛ ስራቸው ላይ ባለመሆናቸው በኢህአዴግ አመራሮች መካከል በስልጣን ሽኩቻ እንደተፈጠረና አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስን ቦታ ተክተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች እንደገለፁት የቻይና ዲፕሎማቶች ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድርድር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ስዩም መስፍን ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ጋር በመምጣት ቤተመንግስት ሆነው የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዝግጅት ክፍላችን ይህንን ለማጣራት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ጋር ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ስልካቸው ባለመነሳቱ

እንዳሉ፤በችሎት በአስተናባሪው አረፍ እንዲሉ ተነግሮአቸው በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ ችሎቱ ስራ መጀመሩን እና ምንም በማያውቁት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት ሳይሰጡ ትዕዛዝ/ውሳኔ እንደ ተነበበላቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹም በፍርድ ቤቱ ድንገተኛ ውሳኔ መገረማቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ ለአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “ተከሳሽ አቃቤ ህግ” በሚል ፍ/ቤቱ ፓርቲውን ማነጋገር እንደሚፈልግ ቀጥሮ የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ፓርቲውን በመወከል ዋና ፀሐፊው አቶ አስራት ጣሴ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ አቶ አስራት በዳኞች ፅ/ቤት ተጠርተው ፓርቲው በነ አንዱዓለም የፍርድ ውሳኔን በመቃወም ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ከዳኞች ጋር ሲነጋገሩ እሳቸው ጉዳዩን በደንብ ባለመከታተላቸው ከሌሎች አመራሮች ጋርና ከፓርቲው የህግ አማካሪ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ መልስ እንደሚሰጡ በመግለፃቸው ለትናንት ሰኞ ከሌሎች አመራሮች ጋር እንዲመጡ በመግለፅ እንደሸኟቸው ተጠቁሟል፡፡

የሶሻሊስቱ ጎራ በመንኮታኮቱ ከምዕራባዊያን ባንክ ብድር ለማግኘት ሲባል ባህሪውን ደብቆ ዴሞክራሲያዊ ለመምሰል ቢሞክርም ውሉ አድሮ የደበቀውን ባህርይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይፋ እያውጣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ መንገዱን በሰፊው ተያይዞታል፡፡ ጋዜጠኞችን ከሙያ ስነ-ምግባር በማስፈንጠር ማንኛውም አማራጭ ሀሳብ እንዳይንሸራሸር ኢህአዴግና የመንግስት ስህተት እንዳይዘገብ መንግስት ነፃ ሚዲያዎችን እግር ቶርች በማሰር ጋዜጠኞችን ማሰር ፣ማዋከብና ማሳደድ ዋናው ተግባሩ አድርጎት ይገኛል፡፡›› በማለት አትቷል፡፡

በመግለጫው ‹‹ጋዜጦችን በጠራራ ፀሐይ ይነጥቃሉ፤ ጋዜጣ አዟሪዎች ላይ ወከባ፣ ዛቻና እገታ ይፈፅማል፡፡ መፃፍ አናቆምም፣ አንሰደድም ያሉ ጋዜጠኞች ላይ በየእለቱ ዛቻና ክትትል እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡በተለይ አንሰደድም፣ እንፅፋለን፣ እናሳትማለን በማለት ግልፅ አቋም በያዙት በፍትህ ጋዜጣ ላይ እገዳ የተደረገ ሲሆን በጋዜጣው አዘጋጆች ላይ ወከባና ክትትሉ ቀጥሏል፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ መንግስት እየፈፀመ ያለውን ህገወጥ ድርጊት አቁሞ ፍትህ ጋዜጣም በአስቸኳይ ወደ ህትመት እንድትመለስ ጥሪያችንን እናቀርባለን›› ሲል መድረክ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠይቀናቸው “አምባሳደር ስዩም መስፍን በአሁን ወቅት በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ናቸው፡፡ መደበኛ ሥራቸውም ይሄ ነው፤ ከዛ ውጭ እንደማንኛውም አምባሳደር ለስራ ጉዳይ ሀገር ቤት ይመጣሉ” በማለት ተጨማሪ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጤና አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እየተገለፀ ቢሆንም በቅርቡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጠ/ሚኒስትሩን መታመምና በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው በሐኪሞቻቸው እንደተነገራቸው ከማሳወቅ ውጭ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በግልፅ ማን እየመራ እንዳለ ከመግለፅ በመቆጠቡ ይታወሳል፡፡

ለውይይት የተጠሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በነፃው ፕሬስ ላይ የሚፈፀመው አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም መድረክ ጥሪ አቀረበ

አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ

ተጠቆመ

የ2004 ዓ.ም የግብር መክፈያ ቀንን ተከትሎ የነጋዴዎች ቅሬታ እየተበራከተ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ መርካቶ እና ሌሎች የንግድ ተቋማት አካባቢ ካለው የሀገሪቱ የንግድ መቀዛቀዝ የተነሳ ከዚህ በፊት የተተመነባቸውን የግብር ዋጋ መክፈል እንደማይችሉ አንዳንድ ነጋዴዎች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡

በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መሠረት የነጋዴዎች የግብር መክፈያ የጊዜ ገደብ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ሲሆን አንዳንድ ነጋዴዎች ግን ከንግዱ መቀዛቀዝ ምክንያትና ባለፈው የተተመነብን ከፍተኛ የግብር ዋጋ ይቀነስላችኋል ቢባልም አሁን ግን ገቢያችንን ያላማከለና በዘፈቀደ የተተመነብንን እንድንከፍል እየተገደድን ስለሆነ ምን የሰራነውን እንከፍላለን በሚል የንግድ ተቋሞቻቸውን ሊዘጉ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይም በክልሎችም በግብር ጉዳይ ቅሬታዎች እየተበራከቱ ሲሆን በተለይም በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው በሚዛን ተፈሪ ከተማ ያለው የአሁኑ የግብር ሥርዓት የከተማውን የነጋዴ ማኅበረሰብ እያመሰ መሆኑን

ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ በከተማው ያለው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በያዝነው ወር በመንቀሳቀስ የነጋዴውን የዕለት ገቢ በመጠየቅ ነጋዴው ከተገለፀው ሌላ ከ50-100% ተጨማሪ በማሰብ ከፍተኛ የግብር ጫና በመደረጉ የአካባቢው ነጋዴዎች ቅሬታ እንዳደረባቸው ተገልፃDል፡፡ ነጋዴዎችም በግብር አወሳሰኑ ላይ ያደረባቸውን ቅሬታ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ ቢፈልጉም ለቅሬታ የተቀመጠው የ5 ቀነ ገደብ ሳይታወቅ አልቋል በመባሉ የተጣለባቸውን እንዲከፍሉ መወሰኑ እንዳበሳጫቸው አንዳንድ ነጋዴዎች ከሥፍራው በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡

የከተማው ነጋዴዎችም ግብሩ ከአቅማችን በላይ ነው በሚል ግብሩን ላለመክፈልና የንግድ ተቋማቸውን ለመዝጋት የወሰኑም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ የፌደራል አገር ውስጥ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ኤፍሬምን ጠይቀናቸው በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ ነኝ በማለታቸው የባለስልጣኑን ሐሳብ ማካተት አልቻልንም፡፡

የግብር ጉዳይ ነጋዴዎችን እያስጨነቀ ነው

የሻማ ምሽትሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን አስመልክቶ የሻማ ማብራት ዝግጅት በአንድነት ፓርቲ ፅ/ቤት ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ በእለቱ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ለማሰብ ሁላችሁም ተጋብዘችሁዋል፡፡

ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮየአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት

Page 14: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

14 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

የማይጠረቃው የተቃዋሚ ... ከ ገፅ 7 የዞረ....

ግሩም አስፈው

ብዙዎቻችን የዘር ማጥፋት ወንጀል (The crime of genocide) ሲባል ወደ አእምሯችን የሚመጣው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጋራ ባህሪ (Identical) ያላቸውን የሰው ልጆች ማጥፋት ወይም መግደል የሚለው ትርጉም ነው፡፡ ነገር ግን የዘር ማጥፋት ወንጀል ከዚህ ባለፈ በብዙ መንገድ እና ዘዴ ሊፈፀም ይችላል፡፡ ትርጉሞቹም እንዲሁ ብዙ እና ሰፊ ነው፡፡

International law and world politics (p.222) የተባለ መጽሐፍ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ሰፋ ባለ መልኩ እንደሚከተለው ገልፆታል፡፡

1. የአንድ ቡድን አባላትን መግደል/Killing members of the group/

2. አዕምሯዊ አሊያም አካላዊ ጉዳት በቡድን አባላት ላይ ማድረስ/Causing serious bodly or mentally horm to members of the group/

3. Deliberately inflicting on the group conditions of life calculated to bring about its physical destruction in whole or in part

4. አንድ ቡድን የማይዋለድበትን እርምጃ መውሰድ/Imposing measures intented to prevent births with in the group/

5. የአንድን ቡድን ፍሬዎች በማስገደደ ወደ ሌላ ቡድን ማዛወር /Forcibly transferring children of the group to another group/

ወደ ዋናው ነጥብ ስንመለስ በኢትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከላይ በተራ ቁጥር አራት የተቀመጠው ነው፡፡ ወደ አማርኛ ሲተረጐም አንድን የህብረተሰብ የቡድን አባል ሆን ተብሎ እንዳይራባ ወይም እራሱን እንዳይተካ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚል ትርጉም አለው፡፡ በአሁኑ ሰዓት የመንግስት ሠራተኛው ወዶ ሳይሆን ተገዶ እንዳይራባ ወይም እራሱን እንዳይተካ ኢህአዴግ ጫና እያደረገበት ይገኛል፡፡ በዚህ እንደ እሳት በሚያቃጥል የኑሮ ውድነት እና እዚህ ግቢ በማትባል ደመወዝ ሠራተኛው የመከራ እና የስቃይ ህይወት በመግፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአብዛኛው ሠራተኛ ከዚችው ደሞዝ ከ30 በመቶ የማያንሰው የቤት ኪራይ ይከፍላል፡፡ ይህም ሆኖ እንደ ልብ ዘና የማታደርግ አልጋ

ማዘርጋት ብትችል እንኳ ወንበር የማትደግም ናት፡፡ ምን አልባት ትዳር ልያዝ ቢል (ብትል) በትንሹ ከ2000 -30000 ብር ለቤት ኪራይ ብቻ መመደብ አለበት፡፡ ይህ የብር መጠን ብዙ ቢመስልም ብዙም የረባ ነገር አይፈይድም፡፡ የሚገርመው በኢትዮጵያ ውስጥ ከ200 ብር በላይ የሚከፈላቸው ለረዥም አመታት የሥራ ልምድ ያላቸው እና አለቆቻቸው ካልጠመሙባቸው ከአመታት አንዴ ብቅ በምትል የደረጃ እድገት ሳያቋርጡ ተጠቃሚ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ሴቷም ሆነ ወንዱ ሰራተኛ ያላቸው አማራጭ በላጤነት ህይወትን መግፋት ነው፡፡ ይህንን ሁሉ የኑሮ ውጣ ውረድ ተቋቋመው እንኳ ትዳር ቢይዙ ልጁ ወልዶ ማሳደግ ለሠራተኛው የማይታሰብ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለይ በከተሞች ልጅ ወልዶ ማሳደግ ከፍተኛ ወጭ ይጠይቃል፡፡ ለምሳሌ በተራ የግል ትምህርት ቤት አንድ ልጅ ለማስተማር በእየወሩ ለት/ቤቱ የሚከፈለው ከአንድ የጥበቃ ወይም ፅዳት ሠራተኛ ደሞዝ በላይ ነው፡፡ ሌሎች ወጭዎች ከተደመሩበት ደግሞ አንድ መምህር ደሞዝ በላይ ነው፡፡ በዚሀ ላይ ሙሉ ግቢ መከራየት ስለማይቻል ከአከራዮቹ ጋር ስለሚኖር ልጅ ወልዶ በታምር ማሳደግ ቢችል እንኳ ሕፃኑ በግቢ ውስጥ በነፃነት ቦርቆ ማደግ አይችልም፡፡ ውሃ ያለአግባብ ቢያፈስ፣ ቢፀዳዳ አከራዮች ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ (እዚህ ላይ ሁሉም አከራዮች ማለት አይደለም፡፡ ደግ እና የተከራዮችን ልጆች እንደራሳቸው ልጆች የሚያዩ አከራዮች እንዳሉ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ምንም እንኳ ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም)

ስለዚህ ለመንግስት ሠራተኞች ልጅ መውለድ ማለት በህይወት ትልቅ ስህተት መፈፀም ማለት ነው፡፡ እራሱ ሊቋቋመው ባልቻለው የኑሮ ውድነት ላይ እና መመኘት እና መፈለግ እንጅ ማግኘት በማይቻልበት ሰዓት ሌላ አዲስ ፍጡር ከአለመኖር ወደ መኖር (From non existence to existence) ማምጣት እና ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ እና ለት/ቤት የሚከፈል ጠፍቶ ከጓደኞቻቸው በተለይ ወላጆቻቸውን ጠይቀው መግዛት አለመቻል፣ ታመው ወደ ሕክምና ተቋም ወስዶ ማሣከም ሳይቻል ሲቀር፣ ፊታቸው በረሃብ ሲጠወልግ ማየት ከምንም በላይ ልብን የሚሰብር ሐዘን ውስጥ ይጥላል፡፡ (አልወለድም የምትልዋ የአቤ ጉበኛ መጽሐፍ

አሁን ነበር መፃፍ የነበረባት፡፡ ያች ህፃኑን ውጣ ተወለድ እያለች ህፃኑን የምታስጨንቀው የኔብጤ (ለማኝ) ገፀ ባህሪ አሁን የመንግስት ሠራተኛውን ትወክላለች፡፡ አቤ አሁን ኖር ይህንን የኑሮ ውድነት ማየት ቢችል ምን ብሎ ይጽፍ ነበር? እግዚአብሄር ይመስገን አቤ ጉበኛን ብናጣም አቤ ቶክቻውን (አበበ ቶላ) አግኝተናል፡፡

ስለዚህ የመንግስት ሠራተኛ ሆኖ ትዳር መያዝ ቢችል እንኳን ልጅ ለመውለድ ማሰብ እብደት ነው፡፡ ከዚህም በላይ ጨካኝነት ነው፡፡ ሠራተኛው በአሁኑ ሰዓት ይህንን በመፍራት በላጤነት የመከራ ኑሮውን ይገፋል፡፡ የትዳር አጋር ባይኖረንም አልፎ አልፎም ቢሆን ወጣ እያሉ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈፀማችን አይቀርም፡፡ ይህም ለተለያዩ አባላዘር በሽታዎች በተለይም ለHIV/AIDS አጋልጦ በመስጠት ለዘላለሙ እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ምን ይህ ብቻ የዘመኑ ምስኪን ፍጡር ለሌሎች ተያያዥ ችግሮችም ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ሰማይ በነካበት ጊዜ እና ወር ጠብቆ በሚያገኛት እዚህ ግቢ በማትባል ደመወዝ የተመጣጠነ ምግብ ተመግቦ እራስን ከበሽታ ለመከላከል ይቅር እና በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ ስለማይችል በተፈጥሮ በሽታ የመቋቋም ኃይሉ ስለሚቀንስ እና ስለሚያጣ በቀላሉ መዳን ሲችል እስከ ወዲያኛው ያሸልባል፡፡ በሕክምና ለመዳን ለሠራተኛው አይታሰብም፡፡ ተመርምሮ መድኃኒት ለመግዛት ይቅር እና ካርድ ለማውጣትም የማይታሰብ ነው፡፡ በነዚህ እና ሌሎች ባልተጠቀሱ ችግሮች የተተበተበው የመንግስት ሠራተኛ እራሱን እንዳይተካ ተደርጓል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኘው ተዋናይ ኢህአዴግ ነው፡፡ ወልዶ አለመሳም በራሱ አንገት የሚሰብር ችግር ቢሆንም ወልዶ ልጅን እንደ ሣማ በሚለበልብ ኑሮ ውስጥ መክተት ደግሞ እጅግ በጣ የከፋ ችግር ነው፡፡

ኢህአዴግ ይህንን አስቦበትም ይሁን ሳያስብ የፖለቲካ ጥቅም አስገኝቶለታል፡፡ መንግስት ሠራተኛው ከሌላው የሕብረተሰብ ክፍል በተሻለ መልኩ ፊደል የቆጠረ ስለሆነ መንግስትን በአምክኖአዊ መንገድ የመንቀፍ፣ የማንቋሸሽ፣ የመተቸት ብሎም መንግስት ጥሩ ሲሰራ የማሞገስ እና የማወደስ ደረጃው ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህን ግን ማድረግ የሚችለው በመጠኑም ቢሆን አእምሮው ስለዳቦ እና ሽሮ ዋጋ ማሰብ እና መጨነቅ

ኢህአዴግ በመንግስት ሠራተኛው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል

ሲያቆም ነው፡፡ ይበላው ይጠጣው ያጣን ሰው ስለ መብት እና ዴሞክራሲ ብትነግረው አይሰማህም፡፡ ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ ነው የሚሆነው መልሱ፡፡ አብርሃም መስሎው እንደገለፀው የሰው ልጅ ፍላጐት በቅደም ተከተል የተቀመጠ ነው፡፡ ስለሆነ አንደኛው ሳይሟላ ወደ ሌላው ማለፍ አይቻልም፡፡

ለምሳሌ የሰው ልጅ ከዳቦ መግዣ ካልተረፈው ለህክምና ብሎ ገንዘብ አያስቀምጥም፡፡ ስለዚህ መንግስት የሠራተኛውን አእምሮ ሁሌ በዳቦ እና በሽሮ ሀሳብ እንዲወጠር ያደርገዋል፡፡ ሠራተኛው ዘወትር የሚያወራው ዳቦ ስንት ገባ ነው እንጅ መንግስት ምን ሠራ? ምን አደረገ? አይደለም፡፡ ጥያቄው መንግስት ለምን የዳቦ ዋጋ አይቀንስም ነው እንጅ ለምን ሰባዊ መብቶችን ይጥሳል አይደለም፤ ለዚህ ነው መንግስት ነዳጅ ጨመረ ቀነሰ እያለ በየወሩ በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ አምስት እና አስር ሣንቲሞች በመጨመር እና በመቀነስ ድራማ እየሠ በዚሁ ጉዳይ በመከራከር እና በመጨቃጨቅ ጊዜአችንን እንድናጠፋ የሚያደርገን፡፡ ጠ/ሚንስትራችንም ለአፍሪካ ዴሞክራሲ አያስፈልገውም ብለው በየመድረኩ የሚደሰኩሩት ለዚህ ነው፡፡ ለማኝ በማይቀበልበት ወቅት ሲፈልግ ከታክሲ ታሪፍ አምስት ሣንቲም ቀንሻለሁ ዘና በሉ ይለናል፡፡

ሌላው መንግስት ሠራተኛው ደሞዙ ከወር አልፎ ለሚቀጥለው ወር ስለማያደርሰው መንግስትን ለመቃወም እና ሰልፍ ለመውጣት፣ የሥራ ማቆም አድማ እና ሌሎች መንግትን በሚቃወሙ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ አይደፍርም፡፡ ምክንያቱም በአመጽ ከተሳተፈ አምባገነኑ መንግስት የአንድ ወር ወይም የሁለት ወር ደሞዙን ቢቀጣው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንበታል፡፡ በቀን አንዴም እንኳ እንደምንም ብሎ የሚቀምሳት ዳቦ ከነአካቴው ልተቀርበት ትችላለች፡፡ ለቤት ኪራይ የሚከፍለው በማጣት ከቤት ተባሮ የጎዳና ተዳዳሪ ሊሆን ይችላል፡፡ (በእርግጥ የኑሮ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ለወደፊት መንግስት ሰራተኛው በተለይ በአዲስ አበባ ቤት ተከራይቶ መኖር አይቻልም፡፡ የጐዳና ተዳዳሪ ከመሆን ሊታደገው የሚችል ነገር አይኖርም፡፡ ሌሎችም አስከፊ ችግሮችን በመፍራት መንግስት ሠራተኛውን ኢህአዴግ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ አድርጐታል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን ከጥቂት ወራት በፊት የተካሄደው የመምህራን አመጽ

ነው፡፡ መምህራኑ ማመጽ ቢጀምሩም ከወር ወር መሻገር ስላልቻሉ ግፍና በደል ቢፈፀምባቸው ይቅርታ እየጠየቁ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ መንግስት ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ከመሞት መሰንበት ነው እና በአብዞኞቹ ወደ ሥራ ተመልሰዋል፡፡

መንግስት ሠራተኛውን የተጐሳቆለ ኑሮ እንዲገፋ ማድረጉ ሌላም የፖለቲካ ጥቅም አስገኝቶለታል፡፡ የአሁኑን አያድርገው እና ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን እንደመጣ ከዋናዋና ችግሮች አንዱ የነበረው የስራቱ ተላላኪ ካድሬ እና አባላትን በበቂ ሁኔታ አለማግኘት ነበር፡፡ የነበሩት ጥቂት አባላት በተለይ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል እንደ ከሐዲ ስለሚቆጠሩ ይገለሉ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በወቅቱ የነበሩ አባላት እና ካድሬዎች አባልነን ብሎ ለመናገር ይቅር እና በሰው መሀል ስለ ኢህአዴግ ትንፍሽ አይሉም ነበር፡፡ በመጥፎ ካልሆነ በስተቀር ይህንን ችግር ለመፍታት ኢህአዴግ የወሰደው ስልታዊ እርምጃ መንግስት ሠራተኛውን የተንደላቀቀ ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አባላት ያልነበሩት በተንደላቀቀው ኑሮ በመደለል እና በመሳብ በቀላሉ አባል ሆኖ ለመመልመል ሰለባ ሆኑ፡፡ በእርግጥ ብዙ አባላቶች ከተጐሳቆለ ኑሮ ወጥተው የራሳቸው ከርሥ ከመሙላት አልፈው የዘመዶቻቸውን ኑሮ ሌላ መስዋዕት ያስከፍላቸዋል፡፡ የራሳቸው አእምሮ መጠቀም አይችሉም፡፡ የራሳቸውን ስሜት እና ሐሳብ የለቻውም፡፡ ሲጮህ የሚጮሁ የገደል ማሚቶዎች ይሆናሉ፡፡ እንደ ኮምፒዩተር የታዘዙትን ብቻ ይሰራሉ፡፡ ለአለቃቸው ስድስተኛ የስሜት ህዋስ በመሆን አለቃቸው ሲከፋ ይከፋሉ፣ ደስ ሲለው ደስ ይላቸዋል፡፡ አለቃቸው ሲከፋው ልምን እንደከፋው ደስ ሲለው ደግሞ ለምን ደስ እንዳለው እንኳ ደፍረው ለመጠየቅ አይችሉም፡፡ በጠቅላላው የአለቃው ተንቀሳቃሽ ኮምፒዩተር መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ይህ የማይስማማው ካለ የመባረር እጣ ፈንታ ስለሚገጥመው እና ወይም ኢህአዴግ ወይም ሲሰልለው እና አሳልፎ ሲሰጠው ከነበረው ሕዝብ ሳይሆን ስለሚቀር በአባልነቱ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሐሪ ነው፡፡ በበደላችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ወገናችሁ ብትመለሱ ያጣችሁትን ነፃነት መልሳችሁ ታገኛላችሁ፡፡ ከህሊና ወቀሳ እና ከአእምሮ ሁከት ነፃ ትሆናላችሁ፡፡ ሰው በምግ ብቻ አይኖርምና፡፡

እርቃኑን ቀርቷል፡፡ በመላው የኦሮሚያ ክልል የነበሯቸው ደጋፊዎችና የፓርቲያቸው አባላት የውሃ ሽታ ሆነዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የትግል አጋራቸውን እንኳን ፍፁም የዘነጓቸው ይመስላል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ከዶ/ር መረራ ቢብሱ እንጂ አይሻሉም፡፡ ዛሬ ዳዴ የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ግንባር ለመምጣት ሲጠየቁ አብዛኛዎቹ ፕሮፌሰር በየነ ባሉበት እንደማይረግጡ ይናገራሉ፡፡ በየትኛውም መድረክ ላይ የሚፈልጉትን ስልጣን ከተነፈጉ ውስጥ ውስጡን መነቆር ተጠቃሽ ባህሪያቸው ነው፡፡ ራሳቸውን የሰላማዊ ትግል ፊታውራሪ አድርገው ይኮፈሳሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ከቅርብ ወራት በፊት ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ብቸኛ የመድረክ ፓርቲ አሸናፊ ሆነው ፓርላማ

መግባታቸው ከህዝብ የተሰወረ ሚስጥር እንዳለ በማስመሰል ጥላሸት ለመቀባት ሞክረዋል፡፡ የግድ በየምርጫ ዘመኑ የኢህአዴግ አጃቢ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ሆነው የመግባት እድሉ ለሳቸው ብቻ መሰጠት አለበትን? አሁንም ያነጋገርኳቸው አንዳንድ የፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአዲሱ ግንባር ዙሪያ ከፕሮፌሰሩ ጋር በተያያዙ ስጋት አላቸው፡፡

ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል(ከ መአህድ እስከ መኢአድ)

ኢንጂነሩ የለየላቸው አምባገነን ናቸው፡፡ ለቅንጅት መፈራረስና ለሰላማዊ ትግሉ መኮላሸት የመጀመሪያው ተጠያቂ ናቸው፡፡ በእውናቸውም ሆነ በህልማቸው የሚያስቡት ሥልጣንን ብቻ ይመስለኛል፡፡ የአቶ መለስን ቦታ ለመተካት በምኞት ሰክረው ነበር፡፡ የመኢኣድ ሰሪ ፈጣሪ ሆነው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ደጋፊና አባላት

ያሉትን ፓርቲ ለመሃንነት ዳረጉት፡፡ በተለይም በአማራና በደቡብ ክልሎች ከገጠር እስከ ከተማ የተደራጀው የፓርቲው መዋቅር ተፈረካከሰ፡፡ አባላቱ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ሹመኞች ሰለባ ሆኑ፡፡ ፓርቲውን ለትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ዳረጉት፡፡ የህዝብን ትግልና መስዋዕትነት የገዢው ፓርቲ መሳለቂያ አደረጉት፡፡ ለዛሬው የፓርቲው አራት ቦታ መስነጣጠቅና መነጋገሪያ መሆን ዋንኛው ተዋናይ ኢንጀሩ ናቸው፡፡ እኚህ ሰው ከእድሜያቸው መግፋትና ከጤንነታቸው አንፃር ለፓርቲውም ህልውና ቀጣይነት ሲሉ የተከፋፈሉት አመራሮች አስታርቀው ስልጣናቸውን ቢያስረክቡ ምናለበት? በሌላ መልኩ መኢአድና አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ያነገቧቸው ዓላማዎችም ሆኑ የፖለቲካ አቅጣጫ ፍፁም የሚጣጣሙ በመሆናቸው ወደ ውህደት ለመምጣት አይቸገሩም፡፡ ውህደቱ ደግሞ ሰላማዊ ትግሉን አንድ እርምጃ በጥንካሬ ያራምደዋል፡፡ ይህ ውህደት የሚታለመው ግን ከኢንጂነር

ኃይሉ ከፓርቲው የስልጣን ኮርቻ ላይ መወገድ በኋላ ይመስለኛል፡፡

ጎልተው የታዩትን ዳሰስኩኝ እንጂ ጥቃቅን አምባገነኖችም በየፓርቲው ተሰግስገው ለሰላማዊ ትግሉ ጋሬጣ የሆኑም አሉ፡፡ ዛሬ አገሪቱ እጅግ ወሣኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ናፍቆት በሰላማዊ ትግል የሚገኝ የስርዓት ለውጥ ነው፡፡ ግለሰቦች በየስርጓጉጡ በስልጣን መሻኮታቸውን አስወግደው ህዝቡን ሊመሩ ይገባል፡፡ እውን እነዚህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ተሰባስበው የሚወክሉትን ህዝብ የዲሞክራሲ ባለቤት የማድረግ መሻቱ ካላቸው መድረክ፣ ግንባር . . . እያሉ ዙሪያ ጥምጥም ከመሄድና የሕዝቡን የትግል ስሜት ከማቀዝቀዝ ወደ እውነተኛ ውህደት ቢያመሩ ይበጃል፡፡ አሊያ ህዝብ ታግሶ ታግሶ አንድ ቀን “ሆ” ብሎ የተነሳ እለት ለገዢው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ለተቃዋሚ ፓርቲዎችም ወዮላቸው!

Page 15: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

15Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54 15Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M.h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሐምሌ 28 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ባካሄደው የገንዘብ ማሰባሰቢያ የራት ፕሮግራም ላይ በፓርቲው ሊቀመንበር

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የተደረገ የመክፈቻ ንግግር

እየተንገዳገደ ያለውን ...

www.andinet.orgwww.andinet.org

ከ ገፅ 7 የዞረ....

የተከበራችሁ እንግዶች!

የተከበራችሁ የአንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት!

የተከበራችሁ የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች!

የተከበራችሁ በአገር ውስጥም ሆነ ውጭ አገር ሆናችሁ ትኬት በመግዛት ለተሳተፋችሁ!

ከሁሉ አስቀድሜ በራሴና በፓርቲው ስም በዚህ የእራት ምሽት ላይ በመገኘታችሁ በታላቅ አክብሮትና ምስጋ እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ! እንዲሁም በትላንትናው እለት በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያን ወክላ የ1ዐ ሚትር ሩጫ ጥሩነሽ ዲባባ የወርቅ ሜዳሊያ ለአገራችን በማስገኘቷ ለአትሌቷና ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ ያለን እላለሁ፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

በቀጥታ ወደ እለቱ ፕሮግራም ዝግጅት ዓላማና ምንነት ከመግባቴ በፊት ምንም በስፋት የምታውቁት ጉዳይ ቢሆንም ስለ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ትንሽ ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ ዛሬ በአገራችን የሕግ የበላይነት፣ ነፃ የፍትሕ ሥርዓት ከመቼውም በላይ እየጠፉ ናቸው፡፡ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች በማንአለብኝነትና በግፍ እየተደፈጠጡ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ በየወቅቱ አዳዲስ የልማት መፈክሮችን እየፈጠረና 11.2% እድገት አሳይቻለሁ ቢልም ለብዙሃኑ ሠፊ ሕዝብ ያስገኘው የኑሮ መሻሻል የለም ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ ገብቷል፡፡ ከ4ዐ% የበለጠው የዋጋ ግሽበቱና ድህነቱ የሕዝበን ምሬት ጫፍ አድርሶታል፡፡ ለግሽበቱ ምክንያት ደግሞ የመንግሥት የላላ የገንዘብ ፖሊሲ ነው፡፡ መንግሥት መጠነ ሠፊ ገንዘብ ማሳተሙና በባንኮች ውስጥ ማከማቸቱና መበደር ከሚፈቀድለት በላይ መበደሩ ነው፡፡ በቀን አንድ ጊዜ መብላት የማይቻልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፡፡ መልካም አስተዳደር በመጥፋቱ ሙስና ተንሰራፍቶ ሕዝብን እያስለቀሰ ነው፡፡ አዲሱ የሊዝ አዋጅም የሕዝብን የንብረት ባለቤትነትን የገፈፈና ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ አምባገነናዊ እርምጃ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሰው የኢኮኖሚ እድገት በወረቀት ላይ እንጂ በምድረ ላይ የለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2ዐ11 ዓ.ም ምደባ እንደሚያሳየው ከሆነ ኢትዮጵያ ከ185 አገሮች መካከል በ174 ደረጃ ላይ ነው የትገኘው፡፡ 38.9% የኢትዮጵያ ሕዝብ በድህነት የሚማቅቅ ነው፡፡

ዛሬ በኢንቨስትመንት ስም ሠፋፊ መሬቶች ለውጭ ኩባንያዎች እየተሰጡ ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ለቻይና ኩባንያ 25ዐዐዐ ሄክታር ለሳውዲ ኩባንያ 1ዐ,ዐዐዐ ሄክታር ለስድስት የሕንድ ኩባንያዎች 2,465.ዐ12 ሄክታር ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ስፋት 5 እጥፍ የሚያክል ነው፡፡ የመሬቱ ኪራይ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ገበሬውን የመሬት ባለቤትነት መብት አሳጥቷል፡፡ የተፎከረለት የሥራ እድልም ላም አለኝ በሰማይ ነው፡፡

የአገሪቱንም የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ የተመረቱት ምርቶች በዶንያ ተጭነው ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ናቸው፡፡ በሙስና በሚስጥራዊነቱና በአስተዳደራዊ ችግሮቹ የሚታወቀው የመሬት ሽያጭ ድሆች ገበሬዎችን ገለልተኛ የደረገ ነው፡፡ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቲግሬቲ የተባለው ዓለም አቀፍ ተቋም እ.ኤ.አ ከ2ዐዐ3-2ዐዐ9 ዓም ድረስ 11.7 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ ወጥቷል የሚለው አንዱ የሙስናን አስከፊነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አንዱና ወሳኝነት ሚና ያለው የነፃ ሚዲያ መኖር ነው፡፡ ዴሞክራሲ በዳበረባቸው አገራት ውስጥ ነፃ ሚዲያ አራተኛው የመንገሥት አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ልክ እንደ ሕግ አውጭው ሕግ አስፈፃሚውና እንደ ነፃ ፍርድ ቤቶች ሁሉ፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ አያለ በአሁኑ ጊዜ በነፃ ጋዜጦችና ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ሕገ -ወጥ እርምጃ አሳሳቢና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ በአንድ በኩል ከሥራ ኃላፊነቱና ድርሻው ውጭ የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ባዘጋጀው አዲስ የውል ረቂቅ ላይ ቅድመ ምርመራ ወይም የሴንሰርሽፕን ሕግ በጓሮ በር እያስገባ ይገኛል፡፡ በዚህም በኤ.ፍ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 29 የተፈቀደውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽና የማሰራጨትን መብትን የሚያፍን ነው፡፡ በመሆኑም የውል ሰነዱን መፈረም በእራሱ ሕገ ወጥነት ነው፡፡

የውል ረቂቁ ሰነድ ጉዳይ ገና በአልተቋጨበት ሁኔታ ላይ ‹‹ ፍትሕ›› ጋዜጣ ከህትመት እንዲወጣ ዓይን ያወጣ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ እርምጃ እየተወሰደበት ነው፡፡ የሐምሌ 13 ቀን 2ዐዐ44 ዓም የፍትሕ ጋዜጣ ሕትመት በፍትሕ ሚኒስቴርና በዓቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት አማካኝነት እንዳይሰራጭ ተደርጓል፡፡ ሐምሌ 2ዐ ቀን 2ዐዐ4 ዓም ለሕትመት የተዘጋጀውን የፍትሕ ጋዜጣ ብርሃንና ሠላም አላትምም ብሏል፡፡ የሐምሌ 27 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ሕትመትም እንደታገደ ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲ ልሣን የሆነው ‹‹ፍኖተ ነፃነት›› ጋዜጣም ታላቅ ፈተና ላይ ነው፡፡ አንዴ ፕሌት የለም፡፡ ሌላ ጊዜ ማሽን ተበላሸ በሚል ሰበብ አስባብ ሕትመቱ እየተስተጓጎለ ነው፡፡ ነገ ተነገ ወዲያ ምን ሊከተል እንደሚችል መገመቱ አስቸጋሪ አይደለም፡፡ በአለፉት ጊዘያት በአዲስ ነገርና በአውራምባ ታይምስ ጋዜጦችና ጋዜጠኞች ላይ የደረሱት ችግሮች የወደፊቱን አመለካቾች ናቸው፡፡ ወደ ጨለማው ዘመን እየተመለስን ነው፡፡ ሕዝብ የማወቅና ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብቱ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑ በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ የሕግ የበላይነት ያለመከበሩ ጉዳይ ነው፡፡ በአባሎቻችንና በደጋፊዎቻችን ላይ በየጊዜው የተለያዩ በደሎች ይፍፀማሉ፡፡ ድብደባ፣ ሕገ-ወጥ እስራት፣ የእርሻ መሬት መቀማት፣ አፍኖ መሰወር፣ ከቀበሌ ቤቶች ማስወጣት፣ የንግድ ፍቃድ እድሳትን መከልከል፣ ማዋከብ፣ ወዘተ ናቸው፡፡ ጥቃቶቹም የሚፈፀሙት በመንግሥት የፀጥታ ኃላፊዎች፣ በቀበሌ መሪዎችና ካድሬዎች ነው፡፡ ትግሉ እየመረረ እየከረረና መጥፎ መልክ እየያዘ መጥቷል፡፡ የዚህ አንዱና መገለጫው መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ3 ዓም የፓርቲውን ም/ሊቀመንበረና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አንዱዓለም አራጌንና የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆኑትን አቶ ናትናኤል መካንን በሽብርተኝነት ከሶ በእስር ቤት በአሣሪዎቻቸውና በደረቅ ወንጀለኞች እንዲደበደቡና የከፋ ሰቆቃ እንዲደርስባቸው መደረጉ ነው፡፡

በአቶ አንዱዓለም አራጌ ላይ የእድሜ ልክ እስራትና በአቶ ናትናኤል መኮነን ላይ ደግሞ የ18 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡ እስራቱና ወከባው በዚህ የሚቆም ሳይሆን በባሰ መልኩ የሚቀጥል ለመሆኑ

ፍንጮች አሉ፡፡ ለዚህ ፈተና በቂና ዝግጁ ሆኖ መገኘት ወሳኝነት አለው፡፡ አንድነትና መድረክ የምር የሕዝብ ፓርቲ ሆኖ ለመገኘት ወደ ሕዝብ የሚደርሱበትን ሕዝብን ሊያንቀሳቅስ የሚችሉበትን ስልቶችን አዘጋጅተው ተግባራዊ ማድረግ የጠበቅባቸዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ አፈና በድፍረት ማጋለጥ ይጠበቅብናል፡፡ በሕዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን የፍርሀት ቆፈን በመቅረፍ ‹‹ለውጥ ይቻላል›› ‹‹ረሀብ በቃ›› ‹‹ ፍርሀት በቃ›› በአገራችን የሚገባንን ክብር ማግኘት አለብን ብሎ ሕዝብ እንዲነሳና በሠላማዊ ትግል ነፃነቱን እንዲቀናጅ ማድረግ አለብን፡፡ ለዚህ ደግሞ መልካም ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በአንድ በኩል ከነአንዱዓለም እስር በኋላ በርካታ ወጣቶች ከምንጊዜውም በላይ ፓርቲያችንን በመቀላቀል ላይ ሲሆኑ የነባር አባላት ተነሳሽነት በከፈተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋችንን የሚያለመልመው በእስር ላይ የሚገኙ የትግል አጋሮቻችን በፍረዱ ሂደትና በመጨረሻው የውሳኔ እለት ያሳዩት የመንፈስ ጥንካሬ፣ ቁርጠኘነትና ድፍረት ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

በአሁኑ ጊዜ አገራችን ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነች፡፡ የወደፊቱ የአገራችን የፖለቲካ አቅጣጫ ግልጽ አይደለም፡፡ ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር አደጋ ከፊታችን የተደቀነ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ወደ ጨለማ ዘመን መልሶን የተቃውሞ መገለጫ ብቸኛው መንገድ በኃይል መጠቀም ነው ወደ ሚል ድምዳሜ እንዳያደርስ ከፉኛ ያሰጋናል፣ ያስፈራናልም፡፡ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን የሚገባው ጉዳይ አሁን ያለው ሁኔታ እየከፋ ሄዶ አመጽ ቢቀሰቀስ ለአገሪቱና ለሕዝቡ ትልቅ ጉዳት መሆኑን ነው፡፡ ለአገሪቱ ህልውናም አሳሳቢ አደጋ አለው፡፡ የአመጽ ፍጥጫ መወገድ አለበት ማስወገድም ይቻላል፡፡ የጥላቻና የመጠፋፋት ፖለቲካ መወገድ አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅን መንፈስ in-good-faith በኢህአዴግ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል በሚሉ ባለድረሻ አካላት መካከል ድርድር፣ ውይይት በአስቸኳይ መጀመር አለበት፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነትን በሚመለከትም ግልጽና ደረጃውን የጠበቀ የሐኪም ሪፖርት በየወቅቱ መቅረብ መስጠት አለበት፡፡ ሕዝቡ ተገቢ መረጃ የሚሰጠው አጥቶ ለተለያዩ ውዥንብሮች መጋለጥ የለበትም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ስለሆኑ ሌሎች መጠየቅ የለባቸውም የሚለው ቀልድም መቆም አለበት፡፡ ጉዳዩ በሚገባው የኃላፊነት ደረጃና መንፈስ መያዘ ተገቢ ነው እንላለን፡፡

ኢህአዴግ ችግሮች ሲፈጠሩና ቀውሶች ሲያጋጥሙ ወደ እራሱ ማየቱን ትቶ እንደሁልጊው ለችግሮቹ ተጠያቂዎችንና ተከሳሾችን መፈለግ መሄድ ወቅቱ ያለፈበት ዘዴ ከመሆኑም ባሻገር ለማንም ጠቃሚም አዋጭም አይደለም፡፡ መንግሥት ከሁሉ አስቀድሞ በግፍ የአሠራቸውን የሕሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታቸው እንጠይቃለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሕዝብ ‹‹ሕምቢ ለነፃነቴ፣ እምቤ ለመብቴ፣ እምቢ ለሰብአዊና ለዴሞክራሲያዊ መብቶቼ›› ብሎ በአገዛዙ ላይ ቢነሳ አንድነት ፓርቲ የሕዝብን ተፈጥሮአዊ መብቶች ከማክበር ሌላ አማራጭ የሌለው መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

ሕዝብ ለነፃነቱ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ በገንዘቡ በእውቀቱና በጉልበቱ የሚችለውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁና ፍቃደኛ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ይገልፃል፡፡ ሆኖም አምባገነኑ የኢህአዴግ ሥርዓት በሕዝቡ መካከል በፈጠረው የፍርሀት ቆፈንና እየተከታተለ ተቃዋሚዎችን የሚደግፉ ባለሀብቶችን፣ ነገዴዎችን፣ ሠራተኞች የሚያጠቃቸውና ድምጥማጣቸውን የሚያጠፉቸው በመሆኑ በሥጋት ተሸብበው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አይደለም፡፡ ‹‹ፍርሀት በቃ›› እንላለን ‹‹ ነፃነት በነፃ አይገኝም›› እንላለን፡፡ የመጀመሪያው ተግባር እራስን ከፍርሀት ማላቀቅ ነው፡፡ ለመብት ለነፃነት ለአገር ባለቤትነት መከፈል ያለበት መስዋእትነት ሁሉ መከፈል አለበት፡፡ ለበርካታ አስርተ ዓመታት በአምባገነኖች መዳፍ ስር ሲማቅቅ የኖረው የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ጨቋኝ ሥርዓት ማስወገዳቸውንና በማስወገድ ላይ መሆናቸውን በምሳሌነት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ ሕዝብ በሠላማዊ መንገድ ለመታገል ቆርጦ ከተነሳ የእድሉና የሥልጣኑ ባለበት ከመሆን፣ ምንም የሚያግደው የሚያቆመው ነገር አይኖርም፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

እነዚህን ሁኔታዎች ሁሉ በምናይበት ወቅት ፀረ-አምባገነናዊ ትግሉን ለማጋጋልና አንድ እምርታ ለማሳየት የሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ መስራትና መዋሀድ አንዱ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም አንድነት ፓርቲ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መስከረም 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክን መስርቶ አብሮ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ የ5ዐ ዓመታት የዘመናዊ የፖለቲካ ትግል ያስተማረን ተሞክሮ ቢኖር የፖለቲካ ድል መቀናጀት የሚቻለው በተናጠል በሚደረግ ትግል ሳይሆን በተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብርና በሕዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲጨመርበት ብቻ ነው፡፡ ለዚህ የትብብር ጥያቄ ከዚህ ቀደም በርካታ የህብረት ጥረቶች ቢደረጉም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ አልተቻለም፡፡ በ1997 ዓም ምርጫ ወቅት ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ አግኝቶ የነበረው ቅንጅት ውስጥ የደረሰው መከፋፈልና በሕዝብ ስሜት ላይ ያደረሰው የቅስም መስበርና የተስፋ መቁረጥ መንፈስ በአሳዛኝ ምሳሌነቱ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ሆኖም በአለፉት አሳዛኝ ክስተቶች ተስፋ ያልቆረጡ የስድስት ፓርቲዎች ቅንጅት የነበረው መድረክ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንቦቻቸውን እንደ ገና መርምረውና የሚሻሻሉትን አሻሽለው ድርጅታዊ ብቃታቸውን በማጎልበት ከ‹‹ቅንጅት›› ወደ ‹‹ግንባር›› ሐምሌ 2ዐዐ4 ዓም በተደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ተሸጋግሯል፡፡ መድረክ በተመሠረተ አጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘና የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታት ከኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ ያለው ድርጅት ሆኗል፡፡ በሌላ በኩልም አንድነት ፓርቲ በስትራቴጂክ ፕላኑና በአምስት ዓመት እቅዱ ላይ ፓርቲዎችን የማሰባሰብ ዓላማውን ለማሳካት ከፍተኛና ውጤታማ ይሆናል የተባለውን እንቅስቃሴ በስፋት እየሄደበት ነው፡፡ ለዚህ ተግባር የተቋቋመው ኮሚቴም ከስምንት ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ ይህ ጅማሮ ውጤታማ እንዲሆን የፓርቲው አባላት ደጋፊዎችና ሕዝቡም የእራሱን ድጋፍ

እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ እጠይቃለሁ፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

ወደ ዛሬው ፕሮግራም ስንመጣ ኢህአዴግ የሚመራው መንግሥት ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፈጽሞ ለማጥፋት በሚያደርገው የአፈና እንቅስቃሴ በሕይወትና በሞት መካከል እንድንኖር እያደረገ ነው፡፡ በአጠቃላይ መድረክን በተለይም አንድነትን ‹‹በሽብርተኝነት›› ‹‹በፀረ-ሠላምነት›› ‹‹በሻዕቢያ ተላላኪነት›› ወዘተ እየወነጀለ እና አባላቱንና ነፃ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ከሶ እያስፈረዳባቸው ነው፡፡

በመሆኑም ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሕዝቡ ተደራጅተው እጅ ለእጅ ተያይዘው በሠላማዊ መንግድ ነፃነታቸውን መቀዳጀትና የአገራቸው ባለቤት መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተለይም ፓርቲዎች በሰው ኃይል በገንዘብና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እራሳቸውን አብቅተው የሕዝቡን የመከራ ጊዜ ማሳጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ የእራት ግብዣ አንዱና ዋናው ዓላማ ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ ነው፡፡ የአንድ ፓርቲ ጥንካሬ መሠረት በአጠቃላይ የአገሩ ሕዝብ ሲሆን በተለይ ደግሞ አባላትና ደጋፊዎቹ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ሥራ ደግሞ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል፡፡ የዚህ አቅም መሠረት በዘላቂነት ደግሞ አገር ቤትና ሕዝቡ መሆን አለበት፡፡ በመርህ ደረጃ ይህ ዱሮም የሚታመንበት ቢሆንም በተግባር ግን ብዙም ያልተሰራበት ነው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ፓርቲው ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ መልኩ የሚደገፈው በውጭ አገር ከሚገኙና ለአገራቸው እድገት፣ ልማናትና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሌት ከቀን ተግተው ከሚሰሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያኖች ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚም ለእነዚህ ኢትዮጵያውኖች ያለኝን ከፍተኛ አክብሮትና አድናቆት እንድ ገልጽ እንዲፈቀድልኝ እጠይቃለሁ፡፡ በየጊዜው በአገር ውስጥ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለትግሉ መጎልበት በቂ ገንዘብ ካልተገኘ የሚከፈለው መስዋእትነት ከባድና አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በዱሮው መንገድ ገንዘብ ከውጭ እየጠ በቁ መታገል ተገቢም የማይቻልም እየሆነ መምጣቱ ግንዛቤ ሊወስድበት ይገባል፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

በመጨረሻም ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ፕሮግራምን በማዘጋጀትና ለውጤታማነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የፋይናንስ ኮሚቴ አባላት፣

- የሥራ አስፈፃሚ አባላት

- የብሔራዊ ም/ቤት አባላት

- የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት

- የአዲስ አበባ ም/ቤትና ሥራ አስፈፃሚ አባላት

- የአዲስ አበባ ወረዳ ኮሚቴዎች አባላት

- በውጭ አገር የሚኖሩ የአንድነት የድጋፍ ሰጭ ኮሚቴዎች

- ቲኬቱን በመግዛት ለተባበሩን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍተኛ አክብሮቴንና ምስጋናዬን አቀርባለሁ:

አመስግናለሁ

የሕዝብ ሀቀኛ ትግል ያሸንፋል!

ለታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ለሕዝቡ ጥሪ ቢያስተላልፉ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይወጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ ለምሳሌ አንድነት ፓርቲ በሚጠራቸው ሕዝባዊ ስብሰባዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾቹ ግማሽ እንኳን አይሞሉም፡፡ ለምን? እዚህ ላይ ብዙ ምክንያቶችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ሕዝቡ ኢህአዴግ ተኩስ አስከፍቶ ያስገድለናል ብሎ ይፈራል፡፡ ይህ ደግሞ መሠረት የሌለው ፍርሃት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ በ1997 ንፁሓን ዜጐችን በጠራራ ፀሓይ በመትረየስ አስረሽኗአል፡፡ “እደበደባለሁ፤ እታሰራለሁ” ብሎ ሕዝቡ ይፈራል፡፡ “ከሥራና ከደመወዝ

እታገዳለሁ፤ ከቀበሌ ቤት እባረራለሁ፤ ሥራ የማግኘት ዕድሌ አደጋ ላይ ይወድቃል፤ ውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል እንዳላገኝ እደረጋለሁ፤ በየጊዜው ኢህአዴግ የሚወረውረውን ሰላሳና ሃምሳ ብር ድጐማ አጣለሁ፤” እያለም ይሰጋል፡፡ ነጋዴዎች “ታክስና ግብር ይጨመርብናል” ብለው ይፈራሉ፤ ሁሉም በየፊናው በየራሱ ምክንያት ይፈራል፡፡

“ታዲያ ምን ማድረግ አለብን?” በሀገራችን የኢህአዴግ ሥርዓት ተንኮታክቶ እንዲወድቅ የሚፈልገው ሕዝብ ቁጥር ከማይፈልገው ሕዝብ በእጅጉ ይበልጣል ብዬ እገምታለሁ፡

፡ ይህ ሕዝብ የዓላማ አንድነቱን አጠናክሮ፣ የሥራ እና የትምህርት ማቆምን ያካተተ ፍፁም ሰላማዊ ትግል ቢያደርግ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያገኝ አምናለሁ፡፡ ይህ ከሰላማዊ ሰልፍ እና ከሕዝባዊ ስብሰባ የሚሻልበት መንገድ አለ፡፡ የሥራ እና የትምህርት ማቆም አድማ ከቤት አለመውጣት ማለት ስለሆነ ከኢህአዴግ የጥይት አረር ያድናል፡፡ የመሪዎች መኖርም የግድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ መረጃን በቅብብሎሽ ማድረስን ጨምሮ በማኅበራዊ የግንኙነት መረቦች ተጠቅሞ የሥራና የትምህርት ማቆም አድማ ጥሪውን ማስተላለፍ ይቻላል፡

፡ ብዙ ጊዜ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የሚጠቀመው በዚህ ዘዴ ነው፡፡

በሰላማዊ ተቃውሞው ለቀርቡ የሚገባቸው ጥያቄዎች ከደመወዝ ጭማሪና ማሻሻያ፣ ከሊዝ አዋጅ መሻር፣ ከዋጋ ንረት፣ ከኮንዶሚኒዬም ድልድል ኢፍትሐዊነት፣ ከመሬት ፖሊሲ መሻሻል ከታክስና ግብር ከፍተኛ መሆን፣ ከፖለቲካ እስረኞች መፈታት፣ ከሃይማኖት ነፃነት፣ ከታክሲ ታሪፍ ኢፍትሐዊነት፣ ከሚዲያ ነፃነት ወዘተ ጋር የተያያዙ ቢሆኑ ሰፊ ሕዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዱ ይታመናል፡፡ ከልምድ እንደሚታወቀው የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን ማስቀደሙ

ጠቃሚ ነው፡፡

የዚህ ዓይነት ሰላማዊ ትግል ተጨባጭ ውጤት እንዲያስገኝ ለማድረግ ከሁሉም በላይ ህብረት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በቅርቡ በመምህራን የተሞከረው ሰላማዊ የሥራ ማቆም አድማ ሊጨናገፍ የቻለው በዚሁ ጠንቅ ነው፡፡ ሕብረት መኖሩ ሳይረጋገጥ ማንኛውንም ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መሞከር ለአደጋ ያጋልጣል፡፡ በሌላ በኩል የአሜሪካ እና የሌሎች ምዕራብያውያን መንግሥታት ሊያግዙን የሚችሉት በህብረት መብቶቻችንን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ስንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡

Page 16: News Paper No. 54 colour.indd

www.andinet.org

16 Fñt nÉnT ¥Ks® n/s@ 1 qN 2004 ›.M. h#lt¾ ›mT Q{ 2 q$. 54

ወንድሙ ደግፍ[email protected]

የለንደን ኦሎምፒክ ከተጀመረ ሰዓታትን ፤ቀናትን አልፎ ሳምንታትን እያስቆጠረ ይገኛል፡፡የኢትዮጵያ አትሌቶችም ከኬንያ አትሌቶች ጋር መተናነቅ ከጀመሩ እነሆ አምስት ቀናት ሆነው ፡፡ በመጀመሪያ ቀን ውድድር ማለትም ያሳለፍነው አርብ በ10,000 ሜትር በተደረገው የኬንያና የኢትዮጵያ ፍጥጫ በኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ 30፡20፡75 በሆነ ሰዓት አሸናፊነት ተደምድሟል፡፡ወርቁንም አንድ ብላ አስቆጥራናለች፡፡ በዚህ ውድድር የቡድን ሥራው ወርቅነሽን ንግስት ሲያደርግ ቪቪያን ቼሮይትን የነሀስ መዳሊያ ተጋሪ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የጥሩነሽ አጨራረስም ለአሰልጣኞች የቤት ሥራ ሰጥታቸው አልፋለች ምክንያቱም በ5,000 ሜትር መወዳደር መፈለጓን ገልፃለች ያለችበት አቋም ደግሞ 5,000 ሜትርን ወርቅ ከማግኘት የሚገድባት ነገር ያለ አይመስልም ፡፡ 5,000 ሜትር ብትወዳደርስ ?

እሁድ ረፋድ ላይ የተደረገው የሴቶች የማራቶን ሩጫ (ውድድር) ከ16 ዓመት በኋላ ወደ ቤቱ በቲኪ ገላና የኦሎምፒክ ሪከርድ በሆነ ሰዓት 2፡23፡07 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችላለች ፡፡

በዚሁ ማራቶን ውድድር ማሬ ዲባባ 23ኛ ስትወጣ አሰለፈች መርጋ 42ኛ በመውጣት

አጠናቃለች ፡፡ ይህ ውጤት ደግሞ ኢትዮጵያ በአፍሪካ 2ኛ በአለም 22ኛ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

በወንዶች በተደረገ 1,0000 ሜትር ከአራት የኦሎምፒክ ውድድር በኋላ የኢትዮጵያ አትሌቶች ወርቅ ማግኘት ሳይቻላቸው ቀርቷል ፡፡ በዚህ ውድድር ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል በትውልድ ሶማሊያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሆነው ሞ ፋራህ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ በሁለተኝነት አሜሪካዊ ሩፕ ሲሆን በሶስተኝነት ኢትዮጵያዊ ታሪኩ በቀለ የነሀስ ሜዳልያ ሲያገኝ ቀነኒሳ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የቡድን ስራ ከወትሮው ተዳክሞ ተስተውላል የገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም መታመም ተፅዕኖ የፈጠረ ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌቴክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂውን በአግባቡ መጠቀም ሳይችል ቀርቷል፡፡ በአቅም ማነስ (46 ሚሊዮን ብር) ወይስ ቸልተኝነት ?

ዛሬ ማክሰኞ ኢትዮጵያን የሚካፈሉበት ቀጣይ የማጣሪያና ፍፃሜ ውድድሮች ይከናወናሉ የሴቶች 5 ሺህ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ እንዲሁም 800 ሜ ግማሽ ፍፃሜ ሲደረግ 1500 ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ይከናወናል፡፡ መልካም እድል ለአትሌቶቻችን፡፡

ለምን ገመገማችሁን ብለው አሰልጣኞችን

ያግዳሉ

አቶ ዮሐንስ ዘውዱ ለረዥም አመታት በአትሌቲክሱ የግል ማናጀር በመሆን አገልግለዋል፡፡ እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ዙሪያ ከባልደረባችን ወንድሙ ደግፍ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በለንደን ኦሎምፒክ የአትሌቶች ቁጥር ከማብዛት ይልቅ የልዑካን ቁጥር በዝቷል እንዴት ይመለከቱታል?

አዎ! ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን ከማብዛትና ለሀገር ውጤት ከመቆርቆር ይልቅ የራሳቸውን ፍላጐት ያሚሉበት ጉዞ ነው? ምክንያቱም ከ20 በላይ የሚሆኑ ልዑካን ሲያመሩ ነፍሰጠርና ለውድድሩ የማይመለከታቸው ሰዎ ወደ ስፍራው አቅንተዋል፡፡ ይህንንም ውሳኔ ሲያሳልፉ እርስ በርስ ተመራርጠው ያደረጉት ነገር ነው፡፡

በ10,000 ሜትር ተጠባባቂ የነበረው ለሊሳ ደሲሳ ወደ ስፍራው አላቀናም የአትሌቱ ክስ ፌዴሬሽኑ የአቅም ችግር ወይስ ቸልተኝነት?

ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ቸልተኝነት ነው፡፡ የአቅም ችግር ነው እንዳንል ፌዴሬሽኑ በቂ ከሚባል በላይ ገቢ ማሰባሰቡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ብቻ መከናወኑ የተሻለ ውጤት እንዳናመጣና ክፍፍል እንዲኖር አድርጓል፡፡ ለምሳሌ ለሊሳ ወደ ስፍራው ሄዶ ቢሆን ኖሮ

ሴቶች ሁለት ወርቅ- - -ወንዶችስ ?

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ን በፋይናንስ ለማጠናከር በማሰብ የገቢ ማሰባሰቢያ የራት ግብዣ ተከናወነ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ጉለሌ አካባቢ በሚገኘው ግርማ ንዋይ ህንፃ አዳራሽ ምሽቱን በተከናወነው የራት ግብዣ ላይ በርካታ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝደንትና የወቅቱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደተናገሩት “ፓርቲውን በገንዘብ በመርዳት ትግሉን ለማገዝ በሀገር ቤትና በውጪ አገር በመሆን ትኬት ለገዙ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ” ካሉ በኋላ “ሰሞኑን አገራችን ባገኘችው የወርቅ ሜዳሊያ ለአትሌጾቹና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ባደረጉት ሰፋ ያለ ንግግር አተኩረው

ለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ ህገወጥ የመሬት እደላና ዝርፊያ መከናወኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ ከሆነ የከተማው ነዋሪ ቁጥር ከ4ሺህ የማይበልጥ ቢሆንም በህገወጥ መንገድ ከ21 ሺህ በላይ የቦታ ካርታ መሰጠቱን ደርሰውበታል፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎቹ የመኖሪያ ቤት ህጋዊ ካርታ ጠይቀው እንዳላገኙም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በቅርቡ ከገበሬዎች 30 ሄክታር ቦታ ለኮብልስቶን በሚል ሊፈናቀሉ እንደሆነና ማስጠንቀቂያም እንደደረሳቸው፣ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች በጠየቁት የመኖሪያ ቦታ ስምና ፎቶ ለሌላ ሰው ቦታና ካርታ እንደተሰራ ተጠቁሟል፡፡ ከላይ በተጠቀሱ ጉዳዮች ዙሪያ አካባቢውና ነባር የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም እስካሁን ሰሚ እንዳላገኙ በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡:

የአንድነት ፓርቲ የገቢ ማሰባሰቢያ የራት ግብዣ ተከናወነ

- ትኬት ለገዙና ትብብር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ቀርቧል

- የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ

በለገዳዲ ለገጣፎየመሬት ዝርፊያ እያወዛገበ ነው

የተሻለ ውጤት በተመለከትን ነበር፡፡

ስፖርቱ ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔም እንዳለ ይገለፃል፣ ይሄንን አንዴት አዩት?

ከቀኑት መካከል አቶ ዴቤ ጂሎ የፓርላማ የኢህአዴግ ተመራጭ እንዶሁም የብአዴን ቀኝ እጅ የሆኑት ወ/ሮ ብስራት ጋሻው ጠና ይገኙበታል፡፡

ፖለቲካ በፍፁም አብረው መሄድ አይችሉም! እንዳውም ፖለቲካው ስፖርቱ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ አመራሮቹ በፖለቲካ አመራር ላይ የሚገኙ በመሆናቸው በማን አለብኝነት የተለያዩ ስራዎችን ያከናውናሉ፡፡ ከዚህም አልፎ ለምን ገመገማቹን በማለት አሰልጣኞችን ያግዳሉ ካሉ፡፡ በፌዴሬሽኑ በጠንካራ ስራ የሚታወቁትን ወደ ስፍራው እንዳያቀኑ ማድረጋቸው (አቶ አድማሱ) በፌዴሬሽኑ መካከል ክፍፍል እንዲፈጠርና የተሻለ ውጤት እንዳይመዘገብ ምክንያት ሆነዋል፡፡

በቀጣይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ምን ውጤት እንጠብቅ? እስከ አሁን ከነበረው ሁኔታ ስንመለከት በቀጣይ ውድድሮች በወንዶች ጨለም ያለ ይመስላል፡፡ በሴቶች የተሻለ ውጤት ልናስመዘግብ እንችል ይሆናል፡፡ በእግርኳሱስ ሴቶች የተሻለ ውጤት እያሳዩን አይደል! በአጠቃላይ ግፋ ቢል 3 ወይም 4 ወርቅ ልናስመዘግብ እንችል ይሆናል፡፡

እንደተናገሩት “በአገሪቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኑሮ ውድነቱ እጅግ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ኢህአዴግ የሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲና መልካም አስተዳደር በመጥፋቱ እንዲሁም ሙስና ተንሰራፍቶ ህዝብን እያስለቀሰ በመገኘቱ ፤ አዲሱ የሊዝ አዋጅ የህዝብን የንብረት ባለቤትነት መብት የገፈፈ በመሆኑ፤ በኢንቨስትመንት ስም የአገር ሀብት ለባዕዳን እየተሰጠ ፤ በአገሪቱ ውስጥ ነፃ ሚዲያ እንዳይኖር በነፃ ጋዜጦችና በጋዜጠኞች ላይ ህገወጥ እርምጃ እየተወሰደና ህገመንግስቱን በመጣስ ቅድመ ምርመራ በጓሮ በር መጥቷል፡፡ በአባሎቻችንና በደጋፊዎቻችን ላይ ድብደባና ህገወጥ እስር ይፈፀማል፤ የህግ የበላይነት የለም፤ የእርሻ መሬት ማግኘትና የንግድ ፍቃድ እድሳት መከልከል፣ ማዋከብ ይፈፀማል፤” ሲሉ ዘርዝረዋል፡፡ የዶ/ር ነጋሶን ንግግር ሙሉ ዝርዝሩን በገጽ 15 ይመልከቱ

የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ መገርሳ ገለታ በበኩላቸው የከተማው ነዋሪ ከ5 ሺህ እንደማይበልጥና 21 ሺህ የከተማ ቦታ ካርታ ተሰርቷል የተባለው ሀሰት እንደሆነ፤ የከተማው ነዋሪ ቦታና ካርታ ጠይቆ የተከለከለ እንደሌለ፣ ከ2001 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኋላ የተሰጠም ሆነ የታደለ የቦታ ካርታ እንደሌለ ይልቁንም የመኖሪያ ቤት ቦታን በመተለከተ ከመንግስት መመሪያ ውጭ የተሰጠ አለመኖሩን በመግለፅ አስተባብለዋል፡፡

አያይዘውም የከተማው ከንቲባ የከተማው ነዋሪና የተሰራው የቦታ ካርታ ከ5 ሺህ እንደማይበልጥ ቢናገሩም ለዝግጅት ክፍላችን የደረሱ የከተማው ካርታ ሰነዶች ዝርዝር ግን ከ21.100 በላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ምንም እንኳ ከ2001 ዓ.ም በኋላ የከተማ ቦታ ካርታም ሆነ እደላ እንዳልተደረገ የገለጹ ቢሆንም ከ2002-2004 ዓ.ም የተሰሩ የቦታ ካርታ ሰነዶችንም ለማየት ችለናል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት መበራከቱ በማህበራዊ ህይወት እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩ ተገለፀ፡፡

በተለይ ከበጋ ወቅት ይልቅ በክረምት የተሻለ የመብራት አገልግሎት ይገኛል ተብሎ ቢጠበቅም እጅግ ብሶ በመገኘቱ ዜጎችን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉ የተጠቆመ ሲሆን ይህንንም ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ በተለያዩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ቢገለፅም እስካሁን መፍትሔ እንዳልተገኘ ታውቋል፡፡

የመብራት መጥፋቱ ችግር በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተለመደ የመጣ መሆኑንና በአዲስ አበባ ደግሞ በየወረዳ፣ ቀበሌ እና ቤቶች እየተለየ የመጥፋቱ ጉዳይ ግልፅ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡ ለተፈጠሩ ችግሮችም መፍትሔ ለማግኘት በመብራት ኃይል ነፃ ስልክ ጥሪ አገልግሎትና

በየዲስትሪክት ፅ/ቤቶች ቢደወልም ባዶ ተስፋ ከመስጠት ያለፈ መፍትሔ እንዳላገኙ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በሚፈጠረው የመብራት መጥፋት ችግርም የተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች መቆማቸውን፣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የስራ ማሽኖችና ኮምፒዩተሮች ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ለኪሳራ መዳረጋቸውን አንዳንድ ነጋዴዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ ችግር በአዲስ አበባ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ የምሽት ብርሃንና ምግብ ማብሰያ በማጣታቸው ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የ30ኛው የለንደን ኦሎምፒክ ውድድር ለመከታተልም አስቸጋሪ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከተሞች የመብራት መጥፋቱ እየተባባሰ የሄደ ቢሆንም መንግስት በበኩሉ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከኢትዮጵያ ለጅቡቲ መሸጡን ከዚህ በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን

በቅርቡ ደግሞ ለሱዳን ለመሸጥ በመስማማት የሙከራ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከላይ ለተፈጠሩ የመብራት መጥፋት ችግሮች ምክንያት፣ ችግሩ እስከመቼ እንደሚቀጥልና መፍትሔው መቼ እና እንዴት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ምስክር ነጋሽና ለመጠየቅ ጥረት ብናደርግም ‹ስብሰባ ላይ ነኝ› የሚል መልስ በመስጠታቸው የኮርፖሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት የውጭ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ አዲስ ታደለ የተፈጠረው የመብራት መጥፋት ችግር ከክረምቱ ጋር ፣ ከተፈጥሮና ከነፋስ ጋር ተያይዞ እንደሆነ በመግለፅ ችግሩን ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም በመግልፅ ችግሩ እስከመቼ እንደሚቀጥል ግን እንደማይታወቅ አስታውቀዋል፡፡

አያይዘውም ችግሩን ቶሎ ለመፍታት ያልተቻለው የምንጠቀማቸው አሮጌ የማሰራጫ መሳሪያም ችግር አብሮ እንዳለና ይህንንም ለመቀየር አንዱ የኢንቨስትመንት ችግር እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ሌላው በሀገሪቱ ነዋሪዎች የተፈጠረው ችግር መብራት ለጅቡቲ በመሸጡና ለሱዳንም ያለው እንዲሁም የሙከራ ሽያጭ ምክንያት እንዳልሆነና በቂ የመብራት ኃይል ለሀገሪቱ ነዋሪ መኖሩን በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም በተደጋጋሚ በመብራት መጥፋት ከፍተኛ ችግር ላይ በመሆኑ ጀነሬ ለመጠቀም መገደዱ ታውቋል፡፡ ከዛሬ 4 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የመብራት መጥፋት ችግር እንዳማይኖርና፤ በተለይም በ2000 ዓ.ም ‹‹ከእንግዲህ ሻማ ለልደት›› ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በተለያዩ ከተሞች የመብራት መጥፋት ችግር ቀጥሏል