lidetalemariam miyazia 2006

11
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ: - ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ፡- ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” (ሉቃ. 18፣1-8) ሰው በሥጋ ለመኖር ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱ የመተንፈስ ሥርዓት ነው። ሰው የሚተነፍሰው ስለፈለገ ወይንም ስላልፈለገ፣ ደስ ስላለው ወይም ስለ ከፋው፣ ስለበላ ወይም ስላልበላ፣ … አይደለም፤ ለሕልውናው ወሳኝ ስለሆነ ብቻ እንጂ። መተንፈስ ለሥጋዊ ሕይወት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ የጸሎት ሕይወት ለመንፈሳዊው ሕይወት ቀጣይነት ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱና ዋንኛው ነው። የምንጸልየው፣ ጸሎት የነፍሳችን እስትንፋስ ስለሆነና የሕልውናችን ምንጭ ከሆነው ፈጣሪያችን ጋር መገናኘት ስለሚያስፈልገን ነው። ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸሎትን የሚሰማ አምላክ እንደ ሆነ ይነግረናል። አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል። ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል(መዝ. 64፣1-2) ። የጸሎታችን መልስ የሚመጣው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን እሺ፣ ቆይ (ጠብቅ)፣ አልያም አይሆንም አይጠቅምህም በማለት ሊሆን ይችላልና የእግዚአብሔርን አሳብ መስማትና መስማማት ይገባናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ባልገባን ወይም ባልተረዳነው መንገድ ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቶ ለጸሎታችን እኛ እንደጠበቅነው ዓይነት ምላሽ ባይሰጥስ እኛ ምን እናደርግ ይሆን? ጸሎት እግዚአብሔርን የማምለክ ሕይወት ነው ብለን እንቀጥላለን ወይስ አኩርፈን ከአምላካችን እንርቃለን? ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኛ መንገዳችን ነውና በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ ማቋረጥ አይገባንም። ሰይጣን ተስፋ በማስቆረጥ ከጌታችን ሊለየን ቢነሣም እኛ ግን ጸንተን አምልኮታችንን መቀጠል አለብን። ለዚህ ትምህርት መነሻ የሆነን በማኅበራችን ውስጥ ከ1978 እስከ የካቲት 30/2006 ዓ.ም. በጸሎት ክፍል አገልጋይነትና ተጠሪነት ስላገለገለችውና በቅርቡ ወደ እግዚአብሔር ስለተጠራችው እህታችን አብነት የሆነ የጸሎት ሕይወት ለማንሣት ስለወደድን ነው። እረፍቷን አስመልክቶ በነበረው ፕሮግራም ላይ ብዙዎች እግዚአብሔርን በማክበር ስለ ጸሎት ሕይወቷ ይመሰክሩ ነበር። በትዳር የተጎበኙት የወርቅዬ ጉልበት የሌለበት ትዳር የለም ይሉ ነበር፤ እርሷ ግን በጋብቻ ሕይወት አላለፈችም ነበር። የእርሷ በጌታ የሆነ የጸሎት እገዛና ብርቱ እርዳታ ባይኖር ኖሮ ቤተሰባችን ዛሬ ያለውን ሰላምና እረፍት አያገኝም ነበር ያሉም ነበሩ። እርሷ በሥራ በጣም ዝላ፣ ደክማና፣ በህመም ሁና እንኳን አገልግሎቷን አታቋርጥም ነበር። በቅርብ የሚያውቋት አገልጋዮች ብዙ ያልተመለሱ የግል የጸሎት ርዕሶች ቢኖራትም በዚህ ሳትማረር እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው፣ ክብር ለእርሱ ይህን በማለት በጽናት እንደ ቆመች ይመሰክሩላታል። ውድ ወገኖች፣ በሁሉ ሊታይ የሚገባው ጌታ ኢየሱስ ነውና በእርሷ ሕይወት ስለተገለጠው ክብሩ እናመሰግነዋለን። ወደ ራሳችን እንመለስና የጸሎት ሕይወታችን በእግዚአብሔር መንፈስ ሲፈተሸ ምን ይመስላል? ጌታ ዝም አለኝ ብለን መሠዊያችንን አፍርሰን ከዙፋኑ ስር ርቀናል ወይስ አምልኮቴ አይቋረጥም ብለን ጸንተናል? ዓይኖቼም በመከራ ፈዘዙ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ” (መዝ. 87፣9)። እህት ወርቅነሽ ታሪኩ (ወርቅዬ) የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር ሥራ አመራርና የጸሎት ክፍል አገልጋይ የነበረች በቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር እየተዘጋጀ በነጻ የሚታደል 1 121024 አዲስ አበባ 18ኛ ዓመት ቁጥር 8 ሚያዝያ 2006 ዓ.ም. ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ቆሮ. 11፣28 ዐቢይ መልእክት ዐቢይ መልእክት

Upload: sisay-tekle

Post on 28-Dec-2015

75 views

Category:

Documents


3 download

DESCRIPTION

Monthly Newsletter of NSMCF Newsletter

TRANSCRIPT

Page 1: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ:- ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ፡- ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” (ሉቃ. 18፣1-8)

ሰው በሥጋ ለመኖር ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱ የመተንፈስ ሥርዓት ነው። ሰው የሚተነፍሰው ስለፈለገ ወይንም ስላልፈለገ፣ ደስ ስላለው ወይም ስለ ከፋው፣ ስለበላ ወይም ስላልበላ፣ … አይደለም፤ ለሕልውናው ወሳኝ ስለሆነ ብቻ እንጂ። መተንፈስ ለሥጋዊ ሕይወት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ የጸሎት ሕይወት ለመንፈሳዊው ሕይወት ቀጣይነት ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱና ዋንኛው ነው። የምንጸልየው፣ ጸሎት የነፍሳችን እስትንፋስ ስለሆነና የሕልውናችን ምንጭ ከሆነው ፈጣሪያችን ጋር መገናኘት ስለሚያስፈልገን ነው።

ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸሎትን የሚሰማ አምላክ እንደ ሆነ ይነግረናል። “አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል። ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል” (መዝ. 64፣1-2)። የጸሎታችን መልስ የሚመጣው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን እሺ፣ ቆይ (ጠብቅ)፣ አልያም አይሆንም አይጠቅምህም በማለት ሊሆን ይችላልና የእግዚአብሔርን አሳብ መስማትና መስማማት ይገባናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ባልገባን ወይም ባልተረዳነው መንገድ ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቶ ለጸሎታችን እኛ እንደጠበቅነው ዓይነት ምላሽ ባይሰጥስ እኛ ምን እናደርግ ይሆን? ጸሎት እግዚአብሔርን የማምለክ ሕይወት ነው ብለን እንቀጥላለን ወይስ አኩርፈን

ከአምላካችን እንርቃለን? ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኛ መንገዳችን ነውና በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ ማቋረጥ አይገባንም። ሰይጣን ተስፋ በማስቆረጥ ከጌታችን ሊለየን ቢነሣም እኛ ግን ጸንተን አምልኮታችንን መቀጠል አለብን።

ለዚህ ትምህርት መነሻ የሆነን በማኅበራችን ውስጥ ከ1978 እስከ የካቲት 30/2006 ዓ.ም. በጸሎት ክፍል አገልጋይነትና ተጠሪነት ስላገለገለችውና በቅርቡ ወደ እግዚአብሔር ስለተጠራችው እህታችን አብነት የሆነ የጸሎት ሕይወት ለማንሣት ስለወደድን ነው። እረፍቷን አስመልክቶ በነበረው ፕሮግራም ላይ ብዙዎች እግዚአብሔርን በማክበር ስለ ጸሎት ሕይወቷ ይመሰክሩ ነበር። በትዳር የተጎበኙት የወርቅዬ ጉልበት የሌለበት ትዳር የለም ይሉ ነበር፤ እርሷ ግን በጋብቻ ሕይወት አላለፈችም ነበር። የእርሷ በጌታ የሆነ የጸሎት እገዛና ብርቱ እርዳታ ባይኖር ኖሮ ቤተሰባችን ዛሬ ያለውን ሰላምና እረፍት አያገኝም ነበር ያሉም ነበሩ። እርሷ በሥራ በጣም ዝላ፣ ደክማና፣ በህመም ሁና እንኳን አገልግሎቷን አታቋርጥም ነበር። በቅርብ የሚያውቋት አገልጋዮች ብዙ ያልተመለሱ የግል የጸሎት ርዕሶች ቢኖራትም በዚህ ሳትማረር እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው፣ ክብር ለእርሱ ይህን በማለት በጽናት እንደ ቆመች ይመሰክሩላታል።

ውድ ወገኖች፣ በሁሉ ሊታይ የሚገባው ጌታ ኢየሱስ ነውና በእርሷ ሕይወት ስለተገለጠው ክብሩ እናመሰግነዋለን። ወደ ራሳችን እንመለስና የጸሎት ሕይወታችን በእግዚአብሔር መንፈስ ሲፈተሸ ምን ይመስላል? ጌታ ዝም አለኝ ብለን መሠዊያችንን አፍርሰን ከዙፋኑ ስር ርቀናል ወይስ አምልኮቴ አይቋረጥም ብለን ጸንተናል? “ዓይኖቼም በመከራ ፈዘዙ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ” (መዝ. 87፣9)።

እህት ወርቅነሽ ታሪኩ (ወርቅዬ) የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር ሥራ አመራርና የጸሎት ክፍል አገልጋይ የነበረች

በቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር እየተዘጋጀ በነጻ የሚታደል 11 121024 አዲስ አበባ

18ኛ ዓመት ቁጥር 8 ሚያዝያ 2006 ዓ.ም.

ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ቆሮ. 11፣28

ዐቢይ መልእክትዐቢይ መልእክት

Page 2: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

“በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፡- ልትድን ትወዳለህን? አለው። ድውዩም፡- ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ” (ዮሐ. 5፣2-9)።

ይህ በሽተኛ ሰው (መጻጉዕ) ለ38 ዓመታት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። ፈውስ ባለበት ስፍራ ተኝቶ ሳይፈወስም ብዙ ጊዜያት አሳልፏል። የእግዚአብሔር መልአክ አንዳንድ ጊዜ እየመጣ ውኃውን ሲያናውጥ ቀድሞ ወደ ውሃው የገባ ፈውስ የሚያገኝ ቢሆንም እርሱ ግን ወደ ውሃው የሚያስገባው ሰው ስላልነበረው ብዙ ዕድሎችን አጥቷል። ብዙዎች እየዳኑ በሚሄዱበት ስፍራም ለረጅም ዓመታት ያለረዳትና ድኅነት እንደነበር ያወቀና ያዘነ ጌታ ኢየሱስ ሊረዳው መጣለት። ይህ ሰው ለጌታ ሰው የለኝም ሲል ብሶቱን ተናገረ። አሁን የመጣለት ጌታ ደግሞ ውኃውን የሚያናውጸውን መልአክ የሚልክ ጌታ ነበርና በቃሉ ሥልጣን ፈውሶ አልጋውን አሸከመው።

እግዚአብሔር ለእኛ ሊሠራ ሲነሣ ራሱ በክብር ይመጣልናል፤ በጉዳያችን ላይ ዘወትር ሊደርስልን የሚችል እርሱ ብቻ ነውና። አሁንስ የመጨረሻዬ ነው ስንል እርሱ ሲመጣ ግን አበቃልን ያልንበትን ሁኔታ የነገሮቻችን አዲስ ጅማሬ ያደርገዋል። እስኪ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑንን አሳቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ እያወጣን እንመልከት፡-

1. የሰራፕታዋ መበለት፤ (1ነገ. 17፣1-16) ይህች ሴት በእግዚአብሔር ነቢይ በኩል የመጣውንና ለማያምን ሰው ከባድ መስሎ የሚታየውን ቃል አምና ተቀበለች። የመጣላት መልእክት ያለውን አሟጠሸ ስጪና ሌላ የማያልቅ በረከት ይመጣልሻል የሚል ነበር። ቃሉን በመታዘዟ የሕይወቴ የመጨረሻ ምዕራፍ ነው ያለችውን ሁኔታ እግዚአብሔር ከነልጇ በሕይወት የሚኖሩበት ምዕራፍ መጀመሪያ አደረገው። “እርስዋም ሄዳ እንደ ኤልያስ ቃል አደረገች እርስዋና እርሱ ቤትዋም ብዙ ቀን በሉ። በኤልያስም እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዱቄቱ ከማድጋው አልተጨረሰም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አልጎደለም” (ቁ. 15-16)።

2. ዘካርያስና ኤልሳቤጥ፤ (ሉቃ. 1፣8-23) ልጅ የመውለድ ዕድሉ እንደተሟጠጠ ቆጥሮ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ እግዚአብሔር መጥቶ በልጅ በረከት ጎበኘው፤ በዘካርያስ ሕይወት የምንመለከተው፡-

ሀ. የለመነውን አለማግኘት ከአምላኩ አላራቀውም፡- “እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት” (ሉቃ. 1፣8-9)። የልጅ ጥያቄው ባይመለስም እግዚአብሔርን የማገልገል ውሳኔውን ሳይለውጥ በጽናት ሲያገለግል ይታያል። የሚያልፈውን ነገር አጣን ብለን

በጸሎታችን ውስጥ ምላሹ እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ይሁን ብለን ዘወትር በጸሎት መትጋት አለብን። ከሁሉ በላይ የእርሱ ከእኛ ጋር መሆን በቂና ከበቂም በላይ መሆኑን አጥብቀን ልንረዳ ይገባናል። ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቶ ያልመለሰልን ጊዜው ገና ስለሆነ አልያም የማይጠቅማችሁ ነው ብሎ ቢሆንስ?

“ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡- ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው” አለ (ማቴ. 17፣4)። ቅዱስ ጴጥሮስ ብዙ ቤተሰባዊ ችግሮችና የሥጋ ጥያቄዎች ቢኖሩትም በተራራ ላይ የጌታን ክብር ሲያይ ሁሉን በመርሳት ነው ይህን ያለው። በአንድ ባሕር ውስጥ የሚኖሩ ሦስት ዓሶች ዘወትር ሊበሏቸው ከሚያሳድዷቸው ሁለት ሻርኮች የተነሣ ተጨንቀው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ይባላል። እግዚአብሔር ተገለጠና ምን ላድርግላችሁ? ቢላቸው፡- 1ኛው ዓሳ በአካሌ በሙሉ ዓይን ብትሰጠኝ ከየትኛውም አቅጣጫ ሲመጡብኝ ቶሎ በማየት አመልጣለሁ አለ። 2ኛውም እኔ ደግሞ ትልቅና ባሕሩን ሰንጥቆ ለመውጣት የሚያስችሉ ክንፎችን እፈልጋለሁ፣ ሻርኮቹ መብረር ስለማይችሉ አይደርሱብኝም ሲል መሻቱን ገለጸ። 3ኛው ግን እኔ ምንም አልፈልግም ብቻ በሄድኩበት ሁሉ አንተ ከእኔ ጋር እንድትሆን ነው የምፈልገው በማለት ልመናውን አቀረበ። ጌታም እንደለመናችሁት ይሁንላችሁ አላቸው። ወዲያውም አነዚያ ሻርኮች ባለ ብዙ ዓይኖች የሆነውን ዓሳ ከበፊቱ የበለጠ ጎልቶ የሚታይና የሚያምር መሆኑን አይተው ሲቀርቡት እርሱ ከሩቅ አያቸውና መሸሽ ይጀምራል። በኋላ ወደ ባሕሩ ዳር ሲቀርቡ በአንዲት ትንሽ ጉድጓድ ወደተጠራቀመች ውኃ ውስጥ ይገባና በደስታ እየዘለለ ከቻላችሁ ኑ፣ ያዙኝ እያለ መፎከር ጀመረ። ሻርኮቹ እንደማያገኙት አስበው ተስፋ ቆርጠው ተመለሱ። ቀጥሎም ኃይለኛ ፀሐይ ሲወጣ በትንሿ ጉድጓድ ያለውን ውኃ አደረቀውና ዓሳው ሞተ። ወደ ሁለተኛው ዓሳ ሲመጡ ገና ሲቀርቡት አሁንማ አታገኙኝም ብሎ በጠንካራ ክንፎቹ ባሕሩን ሰንጥቆ ወደ ላይ በመውጣት መብረር ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ከባሕሩ በላይ ርቆ ይበርር የነበረና በጣም የተራበ ንስር፡- እግዚአብሔር ሆይ እባክህ አብላኝ፣ እባክህ አብላኝ እያለ ሲለምን ዓሳውን አገኘና ጌታዬ በክልሌ አግኝቼው የማላውቀውን ወደ እኔ በማምጣት ስለመገብኸኝ አመሰግናለሁ እያለ ዋጥ ያደርገዋል። እነዚያ ሻርኮች በጣም ተበሳጭተው ወደ 3ኛው ዓሳ በቁጣ ሲመጡ አንደኛው ሻርክ ጓደኛውን ተው፣ ተው አለው። ሌላኛው ሻርክ ለምን? ሲለው ዓሳው በተንቀሳቀሰ ቁጥር የማይለየው የሰው ጥላ ከኋላው አይታይህም? ዓሳውን እንበላለን ስንል ወግቶ ቢገድለንስ? ይቅርብን በማለት ተመለሱ ይባላል።

እንግዲህ በጸሎት ሕይወታችን አብዝተን እንድንጸናና የሚበልጠውን መለመን እንድንችል የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ይብዛልን።

ዘሀለወ ምስሌሁ ወልድ ቦቱ ሕይወት። 1ዮሐ. 5፣12 ሚያዝያ 2006

ልጁ ያለው ሕይወት አለው ። 1ዮሐ. 5፣12 22 121024 አዲስ አበባ

ከጉባዔ መድረክ ከጉባዔ መድረክ

Page 3: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

እግዚአብሔር ያከብራል፤ ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ተገፍተን በጦብ ምድር መቀመጣችንንም ይፈቅዳል። ምክንያቱም የመሠራት ቦታና ጊዜ ነውና። ዮፍታሔ የአሞንን ልጆችን ለመግጠም ሲወጣ ለእግዚአብሔር ስዕለትን መሥዋዕት ለማቅረብ ተሳለ፤ ዘላለማዊ አምላክም ድልን ሰጠው። ድሉ ከተገኘ በኋላ ለድሉ መሥዋዕት ሆና የቀረበችው ግን ልጁ ነበረች። ልጁ የመጀመሪያ ሆና የወጣችው ጀግናን ለመቀበል ነበር፤ አባቷ ግን ይዞላት የመጣው ደስታ አልነበረም። ይዞላት የመጣው ዛሬ ልጆቻችን ከእኛ እንደሚጠብቁት ደስ የሚል፣ የሚበላ ወይም ሌላ መልካም ስጦታ አልነበረም። ይልቁንም ሞቷን ነበር። ብዙዎቻችን ስለ መሥዋዕት ስናስብ በአእምሮአችን የሚመጣው የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በእርሱ ምትክ የሚሰዋ በግ ስለላከለት የይስሐቅን መሠዋት አናይም። ዮፍታሔ ልጅ ግን ተሠዋች፤ እርሷም አባቷ ለእግዚአብሔር የገባውን ስዕለት እንዲያፈርስ አልፈለገችም። ዮፍታሔ በዚህ ጦርነት ከልጁ ጀምሮ ብዙ ነገር አጥቷል፣ በብዙ ተጎድቷል። በመጀመሪያ በወንድሞቹ የጋለሞታ ልጅ መባሉና የአባቱን ርስት እንዳይወርስ መገፋቱ፣ ተሰድዶ በጦብ ምድር መቀመጡ፣ በኋላ ደግሞ በጠላቶቹ ላይ ያገኘውን ድል ሳያጣጥም ልጁ በመሥዋዕትነት ማለፏ፤ በዚህ ሁሉ ላይ ደግሞ የኤፍሬም ልጆች በድሉ ማግስት ድል የሰጠውን እግዚአብሔርን ከማክበር ይልቅ እኛን አላማከርክም በሚል ሰበብ የኤፍሬም ልጆች ቤቱን በእሳት እንደሚያቃጥሉ ዛቱበት፤ ይህም ወደ መጨረሻው ጦርነት እንዲያመሩ አደረጋቸው። ሺቦሌት የሚለው ጥያቄ በዚህ ጦርነት ወቅት የተነሣ ፈተና ነበር። ሺቦሌት ማለት ወራጅ የምንጭ ውኃ ወይም የእህል ዘለላ ማለት ነው። መልሱ በገለዓዳውያን ልጆች እንጂ ሌላ ዜግነት ባለው ሰው ሊመለስ አይችልም። ብዙዎቻችን ስለ ዜግነት ጠንቅቀን እንረዳለን። ዜጋ የራሱ የሆነ መብትና ግዴታ አለው። ዜጋ የአገሩን ሕግ ከማክበር ግዴታ ጋር በዜግነት ማግኘት የሚገባውን ማንኛውንም ክብርና ጥቅም ያገኛል። በሐዋ. 16፣36 ጀምሮ ጳውሎስና ሲላስ የሮም ሰዎች ሆነው ያለ ፍርድ በመታሠራቸው አሳሪዎቹ እንደ ፈሩ እንመለከታለን። ይህም የሮምን ሰዎች አለፍርድ ማሰር ወይም መግረፍ አለመቻሉንም ይገልፃል። የሐዋ. 22፣24-25 ላይም ይህንኑ አስረግጦ ይነግረናል። ስለዚህ ዜግነት የከበረ ነው። ሺቦሌት ዜጋ ያልሆነ ሊጠራው የማይችል ስም ነበር። ሺቦሌት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም ገለዓዳዊ መሆን ያስፈልጋል። ሺቦሌት በጭንቅ ጊዜ ሊጠራ የሚችል ስም፣ ሺቦሌት የማይደርቅ ወራጅ ውኃ፣ ሺቦሌት የሚያረሰርስ፣ ከሞት የሚያስመልጥ ነበር። ሰዎች የብዙ አገሮችን ቋንቋ ሊናገሩ ይችሉ ይሆናል፤ እንደ ዜጋው አጥርተው ሊናገሩ ግን አይችሉም። ዜጋ የሆነ ሰው ሁለት እርግጠኛ የሚሆንበት ነገር አለ።

በማማረር ከማያልፈው ጌታ መራቅ የለብንም።

ለ. የአገልግሎት ጉዳይ ከኑሮ ጋር አይያያዝም፡- ማገልገላችንን በኑሮአችን መሙላትና መጉደል ላይ መመሥረት የለብንም። እንደ ነቢዩ ዕንባቆም “ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል” (ዕን 3፣17-19) በማለት ልንጸና ይገባል።

ሐ. እግዚአብሔር የገባልን ተስፋ ተፈጽሞ ሳናይ አንሞትም፡- አረጋዊው ስምዖን እጅግ አያሌ ዘመናት ቢኖርም ኪዳኑ እስኪፈጸምና የተገባለትን ተስፋ ፍጻሜ እስኪያይ ድረስ አልሞተም። ጌታ ኢየሱስን ከታቀፈ በኋላ ራሱ በቃኝ አስናብተኝ አለ። (ሉቃ. 2፣25-32)

3. መርዶክዮስና አስቴር፤ በእነዚህ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የምናስተውለው፡-

ሀ. ለወገን ዋጋ መክፈል፡- መርዶክዮስ የሚያሳስበው የወገኖቹ ጉዳይ ነበር። ራሴን ላድን ቢል በንግሥቲቱ አስቴር በኩል ሊሆንለት ይችላል። እርሱ ግን ልብና አሳቡ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ነበርና ስለ ወገኖቹ ዋጋ ለመክፈል እስከ መጨረሻው ቆረጠ። ለ. የአምልኮ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም፡- አይሁድ እንዲጠፉ አዋጅ የወጣበትን ምክንያት መርዶክዮስ ለሐማ አልሰግድም ማለቱ ነው። ይህን በሰው ሰውኛ ስንመለከተው ቀላል ነገር ይመስለል። መርዶክዮስ የእግዚአብሔር በሆነው ጉዳይ ላይ ያለው አቋም የጸና ነበርና ሐማን በመፍራት የአምላኩን ክብር ለሰው ለመስጠት አልፈለገም፤ ስለ እምነቱ ወደ ኋላ አላለም። ሐ. በጎ ነገር ማድረግ የኅሊና ጉዳይ ነው፡- መርዶክዮስ ንጉሥ አርጤክስስን ከሞት ያዳንኩበት ታሪክ ይታወቅልኝ በማለት ሹመት ሽልማት ለማግኘት አልሮጠም። ይህንን በጎ ነገር ያደረገው ለኅሊናው ብሎ ነው፤ በጎ ነገር ስናደርግ ኅሊናችን ይደሰታል። የምናደርገው በጎ ነገር ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር የሚከብርበትና ኅሊናችንን የሚያስደስት መሆን አለበት። በዚህ ሁሉ ላይ ግን ስለ ስሙ የተደረጉ በጎ ነገሮችን የማይረሳ አምላክ በሰማይ መኖሩን አንዘንጋ።

† ጠላት የሚፈልገው ለእርሱ ወድቀን እንድንሰግድ፣ ለፈቃዱ እንድንገዛ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር በሆነው ነገር ጸንተን ስንቆም ጠላታችን መጨረሻችሁ ብሎ ባዘጋጀው ነገር ላይ እግዚአብሔር ይገለጥና ለእኛ የአዲስ ነገር ጅማሬ የጠላታችን ደግሞ መቀበሪያ ይሆናል።

† በሥጋ ጉድለታችን የምንጨነቅባቸው ነገሮች ሁሉ አላፊ ናቸው። ለክርስቲያን ዋናው ነገር ከሥጋ ሞት በኋላ ያለው የትንሣኤ ኑሮ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም” (ዮሐ. 5፣24)።

† እግዚአብሔር በወደደው ሰዓት ይሠራል፤ ለእኛ አበቃ፣ ተዘጋ፣ አለቀ ተቆረጠ የምንለውን ነገር እርሱ ግን መጀመሪያ ሊያደርገው ይችላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ዕብ. 13፣8 33 121024 አዲስ አበባ

እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ ዘትማልም ወዮም ውእቱ ወእስከ ለዓለም። ዕብ. 13፣8 ሚያዝያ 2006

ሺቦሌት

Page 4: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

1ኛ. ደፋር ነው፡- ዜጋ ሲናገር በድፍረት ነው። ቋንቋው የራሱ እንደሆነ ያውቀዋል፤ አጥንቶ በመምጣት ሳይሆን ያደገበትንና የሚያውቀውን ነው የሚናገረው። 2ኛ. ጥያቄም የለበትም፡- አቅጣጫው ይታወቃል፤ ከተቃራኒ ወገንም አይሰለፍምና ጥያቄ የለበትም። ከላይ በዝረዝር በቀረበው አሳብ መሠረት ሺቦሌት ማለት ፡-

1. ወራጅ ውኃ 2. የእህል ዘለላ 3. ማምለጫ 4. ላላወቁት ደግሞ ማሰናከያም ነበር።

እንግዲህ ስለ ሺቦሌት ይህን ካልን ለአዲስ ኪዳን ሰዎች ይህን ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች አስረግጦ ሊነግረን የሚችል ታላቅ ስም እንዳለን ማወቅ አለብን። ይኸውም ኢየሱስ የሚለው የከበረ ስም ነው።

1. ሺቦሌት ማለት ወራጅ የምንጭ ውኃ ነው፤ ወራጅ የምንጭ ውኃ የማይቆም፣ የማያልቅ ነው። ጌታ ኢየሱስ እኔ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነኝ ይላል። በዮሐ. 4 ላይ እንደምናነበው አንዲት ሳምራዊት ሴት ውኃ ፍለጋ ወደ ያዕቆብ ጉድጓድ ሄደች። በዚያም ከያዕቆብ የሚበልጠውን ታላቅ ጌታ አገኘች። ያዕቆብን ታላቅ ሰው ነበር፤ በብልጠትም እግዚአብሔርም እየረዳው በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አልፏል። ነገር ግን ያዕቆብ ለራሱም ውኃ ያጣበት ጊዜ ነበር። በዘፍጥ. 29 እንደምናነበው ለረጅም ዓመት ባሪያ የሆነላት ራሔል ልጅ በማጣቷ አዝና ልጅ አምጣ ዓይነት ጥያቄ ስታነሣ የተናገረው ቃል አለ። እኔ ልጅን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ፈንታ ነኝን? አለ፤ የያዕቆብ ጉድጓድ ውኃ ሊደርቅ ይችላል። ጌታ ኢየሱስ ግን የማይደርቅ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነው። እንዲያውም ወደ እርሱ የተጠጋ ዘላለም ከሆዱ የሕይወት ውኃ ይፈልቃል፤ ለሌሎችም ይተርፋል እንጂ አይጠማም። እኛስ ማድጋችንን የደቀንነው የት ላይ ነው? ከያዕቆብ ጉድጓድ ላይ ወይስ የሕይወት ውኃው ከማያልቀው ከኢየሱስ ላይ? በ1ኛ ቆሮ. 10፣4 ላይ እንዲህ ይላል፡- “ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ”። ከዚህ ታላቅ ዓለት እነሙሴ ጠጥተዋል አላለቀም፤ እነ ዳዊት በኋላም ነቢያት እንዲሁም ሐዋርያት፤ ዛሬም እኛ ጠጣን አላለቀም። ገና እስከ ጌታ መምጫ ቀን ድረስ ትውልድ ይጠጣዋል፣ አያልቅም። 2. ሺቦሌት የእህል ዘለላ ነው፤ ጌታ ኢየሱስ እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ ብሏል (ዮሐ. 6፣35)። እንዲያውም በዮሐ. 15፣1 ላይ፡- “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው” ይላል። እንግዲህ ገበሬው የማይደክም፣ ዘወትር የሚሠራ፣ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋ፣ ትጉህና መልካም የሆነ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ይህ እንጀራ የማያልቅ ነው። በነፃ እንድንበላው የተሰጠን እውነተኛ የነፍሳችን ምግብ ኢየሱስ ነው። 3. ሺቦሌት ማምለጫ ነው፤ በአዲስ ኪዳን ማምለጫችን ኢየሱስ ነው። በ1ኛ ጴጥ. 2፡6 ላይ፡- “እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” ይላል። በእርሱ ያመነ አይጠፋም፣ የሞትን ባሕር ይሻገራል፣ ያልፋል ማለቱ ነው።

አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል 1ቆሮ. 15፣20 44 121024 አዲስ አበባ

ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥአ እምኩሎሙ ሰብእ ምውታን 1ቆሮ. 15፣20 ሚያዝያ 2006

ብዙዎች ይህንን ማለፋቸውን እንደ ቀላል ያዩታል፤ ነገር ግን የተከፈለው ዋጋ ቀላል አይደለም። 4. ሺቦሌት ማሰናከያም ነው፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ያላመነ ይፈረድበታል። “ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው” (1ጴጥ. 2፣7-8)። ሰው በኢየሱስ ካላመነ ተሰናክሏል፣ የሞት ባሕርንም መሻገር አይችልም። ይህን ታላቅ ስም እየጠራን የሞትን ባሕር ለመሻገር ደግሞ ዜጋ ልንሆን ይገባል። በፊልጵ. 3፣20 ላይ ሐዋርያው “እኛ አገራችን በሰማይ ነው” ይላል። አገራችን በሰማይ ከሆነ ዜግነታችን ሰማያዊ ነው፤ ሰማያዊ ዜጋ ደግሞ ሁለት ታላላቅ ነገሮች ሊኖሩት ይገባል።

ሀ. ሰማያዊ ዜጋ ደፋር ነው፤ የሚደፍረው ከራሱ ማንነት የተነሣ ሳይሆን ከክርስቶስ የተነሣ ነው። በሐዋ. 19፣14 ላይ የአስቄዋ ልጆች ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ ስም ብለው ሲናገሩ ክፉው መንፈስ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ ኢየሱስንም አውቀዋለሁ እናንተ እነማን ናችሁ? ብሎ ተነሣባቸው፣ በዚያ ጊዜ ሁሉም ፈሩ ይላል። ምክንያቱም ማንም ሰው ዜግነት ሳይኖረው፣ ሙሉነት ሳይሰማው ሊጠራው የሚችለው ስም አይደለምና። ዛሬ እኛ ስሙን በድፍረት የምንጠራው ሰማያዊ ዜጎች ስለሆንን ነው።

ደግሞም ከክርስቶስ የተነሣ በድፍረት ቃሉን ልንነግር ይገባል። የእሳቱን ባሕር ያመለጥን ሰላማችን እንደ ወንዝ የፈሰሰ ነው። በግንባራችን ላይ የታተመብን የእውነተኛው ጌታ የክርስቶስ ስም በልባችንም የሚኖረውም እርሱ ነው እንጂ ስስት፣ ሌብነት፣ ጥል፣ ክርክር፣ ምዋርት፣ አድመኝነት አይደለም። ስለዚህም በድፍረት መሬቱን ልንረግጥ፣ ልንሄድ፣ ነጻነታችንን ልንመሰክር፣ ቃሉን ልንነግር ይገባል። ክርስቶስ እስከ መጨረሻው ጠርቆ ከመንገድ ያስወገደው ጠላታችን ይፈርና ይሸማቀቅ እንጂ እኛ ለምን እንሸማቀቃለን?

ለ. ሰማያዊ ዜጋ ሥጋዊ ነገሩ ሊከብድና ሊጫነው አይገባም፡- ዜግነታችን ክቡር ነውና ጉዳያችን በላያችን ላይ ሆኖ ሊጫነን አይገባም። ጉዳያችን በላያችን ሊነግስ ሲፈልግ አይሆንም ልንለው ይገባል። በዘኁል. 20፣10 ላይ የፈርዖን አምላክ የተባሉት ሙሴና አሮን “ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው፡- እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው”። ይህ የሚሆነው ከከፍታችን ስንወርድና ጉዳያችን አስጨንቆን ከላይ ሲሆን ነው። ጉዳያችን ከላይ ካልሆነ በእሳት ውስጥም ቢሆን ከጌታ ጋር እናልፋለን፤ ካልሆነ ግን ጉዳያችን እሳት ሆኖ ይበላናል። በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ የምናገኛቸው ሦስቱ ወጣቶች በእሳቱ ውስጥም ከጌታ ጋር ነበሩ፤ እሳቱ አለ፣ ይነድዳል ወጣቶቹም በሕይወት ይመላለሱ ነበር። ያለመቃጠላቸው ምክንያቱ እሳቱ ከላይ ስላልነበረ ነው። ጉዳያችን ምንም ታላቅ ቢሆን ከዜግነታችን በላይ ቦታ ልንሰጠው አይገባም።

Page 5: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

ክርስቶስ የሚለው የማዕረግ ስም ሌላው መገለጫው ንጉሥነት ነው። ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ነቢይና ካህን እንደሆነ ሁሉ ንጉሥም ነው።

ንጉሥ የሚለው ቃል ቀጥተኛ ፍቺ፡- በአንድ ሕዝብ ላይ ሙሉ ሥልጣን ያለው፣ ገዢ፣ በቅን ፈራጅ፣ መሪ አስተዳዳሪ የሚለውን ሁሉ የሚገልፅ ቃል ነው። በዘመነ ብሉይ እስራኤላውያን ንጉሥ ያስፈልገናል ባሉ ጊዜ በሳሙኤል ቀቢነት አስቀድሞ ሳኦል ቀጥሎም ዳዊት በንጉሥነት ተሹመው ነበር። ሳኦል በተቀባበት ንግሥና ባለመታመኑ እግዚአብሔር እርሱን ሽሮ ዳዊትን ካነገሠ በኋላ የዳዊትን መንግሥት (ዙፋን) የዘላለም እንዲሆን ቃሉን ሰጠ። የዳዊትም መንግሥት ጸንቶ ቆመ ። ከእርሱ ጀምሮ እስከ ሴዴቅያስ ድረስ ብዙ ነገሥታት ነግሠዋል። አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሰኙ አብዛኞቹ ግን በክፋት መንገድ በመሄድ በእግዚአብሔር ላይ ያምጹ ነበር። በእርግጥ የዳዊት መንግሥት በኋላ ለሚነሣው የክርስቶስ መንግሥት ምሳሌ ነበር። ነቢያትም “የዳዊት ልጅ” የተሰኘው ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚነግሥ ትንቢትን ተነበዩ፡- “እነሆ ለዳዊት ቤት ጻድቅ ቁጥቋጦ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፣ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፣ ይከናወንለታልም፣ በምድር ፍርድን ጽድቅን ያደርጋል” (ኤር. 23፣5)

“አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አመጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዢ የሚሆን ይወጣልናል” (ሚክ. 5፣2) የክህነት ሥልጣን ለሌዊ ነገድ እንደተሰጠ ሁሉ ገዢነትም የይሁዳ ነገድ ነበር። ይህ ሥልጣን ፍጹምና የማይሻር በመሆኑ ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ ከሆነው ከዳዊት ዘር ተገኘ። በዘፍጥረት ውስጥ “በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም። የገዢም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፤ ገዢ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል” (ዘፍጥ. 49፣10) በማለት ያዕቆብ ልጆቹን በባረከበት መባረክ ውስጥ ተንብዮአል።

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። 1ቆሮ. 1፣23 55 121024 አዲስ አበባ

ወንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ። 1ቆሮ. 1፣23 ሚያዝያ 2006

ዳዊትም በዘመኑ በእርሱ ዙፋን ስለሚቀመጠው የናዝሬቱ ኢየሱስ ዘላለማዊ ንግሥና “እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። .... ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ። እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ” (መዝ. 2፣6-9) ሲል ተናግሯል።

ነቢዩ ዳንኤልም በራእይ እንዳየውና እንደተነበየው፡- “… እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው” (ዳን. 7፣13-14)። በተጨማሪም መዝ. 45፣7፤ ኢሳ. 7፣14፤ 9፣6-7፤ ዘካ. 9፣9 ስለ መሢሁ (ክርስቶስ) ንግሥና በዘመነ ብሉይ የተነገሩ ትንቢቶች ናቸው። ታዲያ በአዲስ ኪዳን የተጠበቀው ሲመጣ ትንቢቶቹ ፍጻሜ፣ ጥላዎቹ አካል፣ ምሳሌዎቹ ፍቺ አግኝተዋል። ኢየሱስ የተጠበቀው መሢህ ነው። ስለሆነም በዳዊት ዙፋን ለዘላለም እንደሚነግሥ፣ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት፣ ግዛቱም የዘላለም ግዛት እንደሆነ የተጻፈው በሙሉ ተፈጽሟል። ይህንንም ለማረጋገጥ ስለ ኢየሱስ ንጉሥነት በአዲስ ኪዳን የተጠቀሱትን ጥቅሶች ማገናዘብ ጠቃሚ ነው፡-

“እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም” (ሉቃ. 1፣31-33)።

አይሁድ ኢየሱስ ለሞት የሚያበቃው ወንጀል ፈጽሟል ብለው ከከሰሱበት ምክንያት አንዱ ራሱን ንጉሥ አድርጓል የሚል ነበር። ነገር ግን የትንቢቱ ቃልና የሚመጣው መሢህ ሥልጣን ከእነርሱ ተሰውሮ እንጂ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ እንደሆነ በቤተልሔም ሲወለድ ሊሰግዱለት የመጡት የምሥራቅ ነገሥታት (ሰብዓ ሰገል)፡- “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?” (ማቴ. 2፡1) በማለት በጠየቁ ጊዜ ያረጋገጡት እውነታ ነው። መጥተውም በቤተልሔም ለተወለደው ሕፃን በመስገድና መባ በመስጠት ንጉሥነቱን ገልጸዋል። ኢየሱስ በዕለተ ሆሳዕና በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ፡- “ሆሳዕና በአርያም፣ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” (ማቴ. 21፣9) እየተባለለት ወደ ከተማይቷ በመግባት ንጉሥነቱን ገልጧል። በዚህም፡- “ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በአህያይቱ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” (ዘካ. 9፣9) የተባለውን ትንቢት ፈጽሞታል። ራሱን ለሰው ልጅ አሳልፎ በመስጠት በጎልጎታ አደባባይ ቤዛነቱን በፈጸመ ጊዜም ከመስቀሉ አናት ላይ ኢ.ና.ን.አ (ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ) የሚል ጽሕፈት በማጻፍ ጲላጦስ ንጉሥነቱን አውጇል። አይሁድ ንጉሥ ነኝ እንዳለ ብለህ ፃፍ ቢሉት እንኳን የጻፍኩትን ጽፌአለሁ አልለውጠውም በማለት ንጉሥነቱን አስረግጦ መስክሯል። የይሁዳ አንበሳ፡- ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ፣ ከዳዊት ሥር የበቀለ እውነተኛ ንጉሥ ነው። በየዘመኑ ይነግሡ የነበሩ የአይሁድ ነገሥታት የይሁዳ አንበሳ እየተባሉ ይጠሩ ነበር። ይህም የሆነው ያዕቆብ ልጁ ይሁዳን ሲመርቀው “‹‹ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው። ልጄ ሆይ ወጣህ። እንደ አንበሳ አሸመቀ አንደ ሴት አንበሳ አደባ ያስነሣው ዘንድ ማን ይችላል? በትረ መንግሥት

ትምህርተ ድኅነት ትምህርተ ድኅነት ትምህርተ ድኅነት

ክፍል 10ክፍል 10ክፍል 10

ትምህርተ ድኅነት ወይም የዘላለም ሕይወት ትምህርት የክርስትና እምነት አስተምህሮ ማዕከል ነው። ይህም የሰው ልጅ ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ መከራ፣ የመስቀል ላይ ሞትና፣ ትንሣዔ የተከፈለለትን ዋጋና የተሰጠውን ጸጋ በማመን ከኃጢአት ኃይልና ከዘላለም ፍርድ ነፃ ወጥቶ የእግዚአብሔርን መንግስት የመውረሱን እርግጠኛነት የሚያስረዳ ትምህርት ነው። ይህን መሠረታዊ እውነት በቀዳሚነት አስረግጦ መስበክ የማይችል ትምህርት እውነተኛ የወንጌል ትምህርት አይደለም።

Page 6: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

ከይሁዳ አይጠፋም። የገዢም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል ገዢ የሆነው እስኪመጣ ድረስ . . .” (ዘፍጥ. 49፣9-10) በሚለው ትንቢት መሠረት ነው።

አንበሳ የኃይል፣ የማሸነፍ፣ የብርታትና የበላይነት ምልክት ነው።

ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ አሸናፊ ንጉሥ ነው። ማንም ይረታው ዘንድ

አይችልም። የእርሱ አሸናፊነት በጦርነት አይደለም የማሸነፍ ኃይሉ

ያለው ፍጹም ፍቅሩ ላይ ነው። ዓለምን በፍቅር ያሸነፈ ከክርስቶስ

በስተቀር ማንም የለም፣ ወደፊትም አይኖርም።

ኢየሱስ ኃያል አምላክ ሲሆን ዝቅ ብሎ በሰው ምሳሌ ተገኝቶ ለሞት ይኸውም ለመስቀል ሞት የታዘዘ ሆነ (ፊል. 2፣5-11)። እኛን ከሕግ እርግማን ይዋጀን ዘንድ በእንጨት ላይ በመሰቀል የተረገመ ሆኖ ተቆጠረልን (ገላ. 3፣13)። እርሱ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ለመሻር በሥጋና በደም የተካፈለ (ዕብ. 2፣14) –ከይሁዳ ነገድ ተወለደ። ደግሞም የሞትን፣ የኃጢአትንና የዲያቢሎስን ኃይል ሰብሮ በድል አድራጊነት የተነሣ- የድል ጌታ፣ የይሁዳ አንበሳ ነው። ኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ በክብር እና በድል አድራጊነት ሰማያ ሰማያትን ሰንጥቆ በግርማው በአባቱ ቀኝ ተቀምጧል። እርሱ አሸናፊ ንጉሥ በመሆኑ የንጉሥ ልጆች ለሆንን ለእኛም የማሸነፍ ሥልጣንን ሰጥቶናል። በሰማያትም የታረደው በግ፣ የይሁዳ አንበሳ እየተባለ ይመሰገናል። በተለይ የተዘጋውን ማኅተም ማን ይከፍተዋል? መጽሐፉን ማን ይዘረጋዋል? ይህንን ለማድረግ የሚችል ሥልጣን ያለው ማነው? እያለ ለሚያለቅሰው ለዮሐንስ የተሰጠው ምላሽ ይህንኑ ያረጋግጣልና።

… አታልቅስ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ (ራእ. 5፣1-5)።

ይህ አሸናፊነት የተገኘው በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። በዮሐንስ ራእይ ላይ መላእክቱ፣ ሽማግሌዎቹና ከነገድና ከቋንቋ የተዋጁት በሙሉ፡- “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹን ትፈታ ዘንድ ይገባሃል። ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ ይነግሣሉ” (ራእ. 5፣9-10) በማለት ክብር ሲሰጡት እንመለከታለን። በቅዳሴያችንም ይህንኑ የክርስቶስን ሥልጣን እየመሰከርን እናመሰግናለን፡-

… ኢየሱስ ክርስቶ ዘሠረፀ እምይሁዳ ወእምሥርወ ዕሴይ፣ ዘሥልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት ዕብይ ወባርኮት ውዳሴ ወማኅሌት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን።

ትርጓሜው፡- ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ከእሴይም ሥር የተገኘ፣ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ የሆነ ነው። ክብርና ምስጋና ገናነነት ቡራኬና ውዳሴ መመስገን ለእርሱ ይገባዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

(ሥርዓተ ቅዳሴ ገጽ 170፣45)

ይ ቀ ጥ ላ ል

እነሆ፣ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ፣ የመዳን ቀን አሁን ነው 2ቆሮ. 6፣2 66 121024 አዲስ አበባ

ወናሁ ይእዜ ዕለት ኅሪት ወናሁ ዮም ዕለተ አድኅኖት 2ቆሮ. 6፣2 ሚያዝያ 2006

ለእውነት መታዘዝን መከልከል፣ የሚያባብል ባዕድ ድምፅ መስማት፣ አደገኛ አዝማሚያ ነውና እናስተውል! የዚህ መልእክት ጥናት የሚደርስህ ወንድም ሆይ፣ (በጥቅል የሚነገረው ለወንዱም፣ ለሴቷም ነው።)

† ከኀጢአትህ ንስሐ በመግባት ትታዘዛለህ? † ራስህን ለጌታ በመስጠት ትታዘዛለህ? † በደሙ አዳኝነት ታምነህ ታዝዘሃል? † የሞተልህ እርሱ (ጌታ) ለዘወትር (ለቀጣይ) መታዘዝ ይጠራሃል፤ ዕለት በዕለት (በየዕለቱ) በሕይወትህ (በሁለንተናህ) ትታዘዘዋለህ?

ጌታ ለገለጸልን እውነት መታዘዝ፣ በዚያም እስከ መጨረሻ መጽናት ከሁሉ በላይ ነው።

ቁጥር 9፡- “ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል።” ይህ የጥንት ምሳሌያዊ አባባል ነው፤ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 7ን ከዚህ ጋር አስተያይ። (ጥቂቱ) አንዱ ክፉ ሰው ብዙውን በጎ ሰው ወደ ክፋት የሚወስደው አይደለምን፤ (ጥቂቱ) ክፉ ግብር ብዙውን በጎ ግብር ወደ ክፋት የሚለውጠው አይደለምን ማለትን ያመለክታል። የኦሪቱ ሥርዓት ፍቅር እንደ ዱር እሳት ይስፋፋል፤ የሐሰት መምህራን ብዙ የሚቀጣጠል ነገር ሁልጊዜ ለሥራቸው ማግኘት ይችላሉ። የሐሰት ትምህርትም በቀላሉ የመስፋፋት ኃይል አለው። ክህደት ሲጀመር ቀላል ነገር ይመስላል፤ ከጊዜ በኋላ ግን አደገኛነቱ ግልጥ ሆኖ ይታያል። እርሾ ጥቂት ሆኖ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ብዙ የሆነውን ሊጥ ወደ ቡኮነት (መቡካት) እንደሚቀይር፣ እንዲሁም ሐሰተኛ ትምህርት በጥቂቱ ተጀምሮ፣ ሕይወትን ሁሉ፣ ማኅበርን በሙሉ ሊቀይር ይችላል።

እነዚያ ሐሰተኛ መምህራን ለገላትያ ምእመናን ያቀረቡላቸው ትምህርት አደገኛነቱ ለጊዜው ግልጥ ሆኖ ባይታይም' ክርስቶስን ወደ መካድ ያደርስ ነበር። ምክንያቱም የክርስቶስን የማዳን ሥራ እንደማይበቃ ቆጥሮ፣ በተጨማሪ ሰው ለመዳን በክርስቶስ ማመን ብቻ ሳይሆን፣ ተገርዞ የሙሴን ሕግ መጠበቅ አለበት ይላልና። ይህ በእርሾ የተመሰለው ሐሰተኛ ትምህርት በእንጭጩ ካልታረመ ከላይ እንደተገለጸው ከክርስቶስ ተለይቶ መውደቅን ያስከትላል። ቁጥር 10፡- “የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው።”

ሐዋርያው የገላትያ ምእመናን ክርስቶስን ፈጽመው ክደው ወደ ሙሴ ሕግ እንደማይዞሩ በጌታ ይተማመናል። በራሳቸው አስተዋይነት ከስሕተት ይጠበቃሉ ብሎ ሳይሆን፣ ጌታ ሕዝቡን ስለሚጠብቅ፣ የገላትያን ምእመናን ከዚህ አጥፊ ስሕተት እንደሚጠብቃቸው በጌታ ያለውን መተማመን ይገልጻል። አንድም “የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ” ሲል፣ ምእመናኑ ከእርሱ ሌላ አሳብ ባለመውሰድ (ባለመስማት)፣ እርሱን በጥንቃቄ እንደሚያደምጡ (እንደሚሰሙ) ያለውን እምነት ያረጋግጣል።

እንዲሁም “የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር” ሲል፣ ሐሰተኛ መምህራን መኖራቸውን መጠራጠሩ ሳይሆን፣ አሳሳቹ ማን እንደሆነ መጠቆም ስላልፈለገ ይመስላል። ዳሩ ግን ወደ ዓመፅ የሚቀሰቅሳቸው ያልታወቀ

የጳውሎስ መልእክታት ጥናትየጳውሎስ መልእክታት ጥናት

ካለፈው የቀጠለ (17)

Page 7: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

ሰው በመቃወም ራሱን ያቀርባል፤ በምእመናኑ ላይ በጎ የሆነ እምነት ቢኖረውም፣ ከእውነት መንገድ የሚያናውጣቸው ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ መሸከሙ (ቅጣትን መቀበሉ) እንደማይቀር ያስረዳል። ቁጥር 11-12፡- “ነገር ግን፣ ወንድሞች ሆይ፣ እኔ ገና እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? እንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል። የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።” “እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ” የሚለው ጳውሎስ ጌታን ከማመኑ በፊት ለአይሁድ ሃይማኖት የነበረውን ቅንዓት ይጠቁማል። አሁንም እንደበፊቱ መገረዝን ቢሰብክ ኖሮ፣ ስደቱ ይቆም ነበር፤ ከአይሁድ ይደርስበት የነበረው ስደት ነው። አይሁድ ጳውሎስን በጥብቅ ያሳደዱበት ምክንያት የሙሴ ተቃዋሚ አድርገው ስላዩት ነበር። “የመስቀል ዕንቅፋት”፡- የክርስቶስ መስቀል (በሞቱ የተገኘው ድል) በውጤቱ ምንም ተጨማሪ የሰው ጥረት አይፈልግም። መስቀል (የክርስቶስ ሞት) ብቻውን የድኅነት መለኮታዊ መንገድ ነው፤ የሰው ምግባር ወይም ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለድኅነት መጥቀም የሚችል ቢሆን (ከሆነ) መዳን በጸጋ መሆኑ ይቀራል (1ቆሮ. 1፣18-25)። የመስቀል ዕንቅፋት ሥርዓት በመፈጸም ለድኅነት ተስፋ ማድረግ፣ በግዝረትና በሙሴ ሥርዓተ ኦሪት ተስፋ ማድረግ ነው። “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ … ነው” የመስቀሉ ቃል ለአይሁድ መሰናክል የሆነበት ምክንያት መገረዝን ስለሻረና በሥራ መጽደቅን ስለተቃወመ ነበር። አሁንም በዘመናችን የመስቀሉን ቃል በተለያየ መንገድ የሚሰናከሉበት አሉ፤ ምክንያቱም በራስ ኃይል መደገፍን ይሻሉና፤ የመስቀሉ ቃል ደግሞ ይህን ይቃወማል። ሐዋርያት የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በመስበካቸው ቢሰደዱም፣ የመስቀሉ ዕንቅፋት እንዲወገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል። “የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ”፡- ይህ አባባል በአንድ በኩል በመገረዝ ምክንያት ሁከት የሚፈጥሩ (ምእመናንን ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥሉ) ሰዎች ከመካከላችሁ ይውጡ፣ ይወገዱ ወይም ይወገዙ (ይለዩ) ማለትን ያመለክታል። በሌላ በኩል ደግሞ ራሳቸው ይቆረጡ (በራሳቸው ይገረዙ) ወይም ይሰለቡ፣ በሚገረዙበት ጊዜ ሸለፈቱን ብቻ ሳይሆን ከነሥሩ ይቆረጡ ማለት ነው። ከዚህ አንፃር ሲታይ የተሰለበ ሰው እንደ ብሉይ ኪዳን ሥርዓት ከሕዝቡ ጋር ኅብረት አይኖረውምና፣ እነዚህ መገረዝን የሚሰብኩ ሰዎች በሐሰተኝነታቸው ምክንያት መገረዛቸው ከእግዚአብሔር ጉባኤ ተቆርጠው የመወገዳቸው ምልክት ሆነ ማለት ነው። ለ. ከሕግ ነፃ መሆን የሥጋ ባሪያ መሆን አይደለም፤ (5፣13-15) ቁጥር 13፡- “ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፣ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።” ግዕዛነ ነፍስን ወደምታገኙባት ወደ ወንጌል ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን በሥጋዊ ፈቃድ ተስባችሁ ለግዕዛነ ነፍስ ለወንጌል ምክንያት አትሹላት ለማለት ነው። ክርስቲያናዊ ሕይወት በመንፈስ ስለሚመራ፣ ፈቃደ ሥጋን ከመፈጸም ይጠበቃል። ክርስቲያን ከኦሪት ሕግ በታች ባይሆንም ኑሮው ሕገ-ወጥ ሕይወት አይደለም። የአማኞች አርነት (ነጻነት) በፍቅር

በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል ዮሐ. 3፣18 77 121024 አዲስ አበባ

ወዘሰ ኢየአምን ቦቱ ወድአ ተኮነነ እስመ ኢአምነ በስመ ወልደ እግዚአብሔር ዋህድ ዮሐ. 3፣18 ሚያዝያ 2006

መመላለስና አንዱ ለሌላው በፍቅር ባሪያ መሆን ማለት ነው። የእርስ በርስ አገልጋይነት የፍቅር ኑሮ ነው። ይህ የፍቅር መንገድ በኀጢአት እንድንኖር አይፈቅድም፤ ምክንያቱም የፍቅር መንገድ የሕጉም መንገድ አርነት ወይም ነጻነት የሚለው የክርስቲያንን መንፈሳዊ ነጻነት ነው። ይህ ነጻነት ለሰው ልጅ ያለው የእግዚአብሔር ዓላማ ሲሆን፣ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ መሆን ነው (ዮሐ. 8፣32-36፤ ሮሜ 8፣2)። የዚህ ነጻነት አጠቃቀም ከሞራል (ግብረ ገብ) አንፃር መተርጐም አለበት። እውነተኛ ነጻነት ሌሎችን ማገልገል ያስከትላል። ለሥጋ ነገር ዕድል በመስጠት በነጻነት መጠቀም አይቻልም። ጳውሎስ ይህን ተጨባጭ ዓለም ወይም ሰውን ያለ አገባብ እየወቀሰ አይደለም፤ “ሥጋ” የሚለው ቃል ቀደም ብሎ ተጨባጩን አካል ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር። በዚህ ምዕራፍ ግን ሥነ ምግባራዊ አንድምታ ያለው ሆኖ፣ የኃጢአት ዝንባሌ ያለውን የወደቀን ሰው ይገልጻል። በተቃራኒው ፍቅር በመልካም ትርጉሙ ለሌሎች በጎነት መሥራትን፣ የጋራ አገልግሎት ውጤት ሆኖ፣ የክርስቲያን የነጻነት ፍሬ መሆን አለበት። እዚህ ላይ በፍቅር መተሳሰብ ለክርስቲያን ቤተ ሰዎች እንደሆነው፣ ለሁሉም ሰው ፍቅሩ በእኩል የሚታይ ነው። በክርስቶስ የማመን ትክክለኛ መገለጫ ነውና። ክርስቲያናዊ መተሳሰብ በወንጌል ነጻነት ውስጥ ደስተኛና ፈቃደኛ ሆኖ እርስ በርስ፣ አንዱ ሌላውን ማገልገል ነው። ቁጥር 14፡- “ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፣ እርሱም፡- ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።” ጌታችንም ከጻፎች አንዱ ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ የትኛዋ እንደሆነች ሲጠይቀው፡- “… በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኀይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም፡- ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።” ብሏል (ማር. 12፣30-31)። ይህም ፍቅረ አምላክ ፍቅረ ቢጽ፣ (አምላክን መውደድ፣ ባልንጀራን ማፍቀር) ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ሕግን ሁሉ ይፈጽመዋል አለ፤ ያም ቃል ፍቅር ነው። ፍቅር ሕግን ሁሉ ይፈጽማል ማለት በፍቅር የሚመላለስ ሰው ሌላው ሕግ ሁሉ በሕይወቱ ተፈጻሚ ይሆናል ማለት ነው። እርስ በርስ በፍቅር ማገልገልን ሕግም ይደግፋልና። እንዲሁም ሐዋርያው በሮሜ መልእክቱ፡- “እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፣ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። … በዚህ፡- ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል። ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።” ይላል (ሮሜ 13፣8-10)። ባልንጀራ ማለት አይሁዳዊ ብቻ እንዳልሆነ ጳውሎስ ቀደም ሲል አሳይቷል፤ (3፣28)። ክርስቲያን በመስቀሉ ነፃ ከወጣ በኋላ የእግዚአብሔርን ስነ ምግባራዊ መርሆዎች ለመጠበቅ ይተጋል። በአማኝ ሕይወት የሕጉ መፈጸም የሚከናወነው (የሚገኘው) ራስን ለማጽደቅ በሚደረገው የትሩፋት መታዘዝ አይደለም፤ ነገር ግን በክርስቶስ አጽዳቂነት በኩል መጽደቅ (ጽድቅን መቀበል) እና በፍቅር በመታዘዝ ነው (ሮሜ 8፣4)። ከሕግ ነፃ መሆን ውጤቱ ሕግ የለሽ መሆን አይደለም፤ በጸጋ ውስጥ ሆነን በጎ አድራጎትና ግብረ ገባዊነትን መያዝ የበለጠ የክርስቲያን ግዴታዎች ናቸው (ሮሜ 6፣1-14)። ስለዚህ ከሕጉ ነፃ መሆን ማለት የፍቅር ባሪያ መሆንና በፍቅር አማካይነት የሕግ ፈጻሚ መሆን ማለት ነው። በክርስትና ነጻነት ምክንያት ሕግን መሻር በክርስትና

Page 8: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

በክርስትና ትምህርት ውስጥ ቦታ የለውም። በክርስቶስ የዳኑት በፍቅር መንገድ መራመድን ያሳያሉ፤ የፍቅርም መንገድ ሕጉን ይፈጽመዋል እንጂ አይቃወመውም። ቁጥር 15፡- “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።” በዚህ ጥቅስ የተመለከተው የገላትያ ሰዎች ችግር ምን እንደሆነ አልታወቀም። በሰዎች መካከል የሚፈጠር ጥቃቅን ጥል፣ ወይም በይሁዲነት ትምህርት የሚፈጠሩ ጥልቅ ልዩነቶች ይሆናል። እዚህ ላይ “እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ” የሚለው ጠንካራ አገላለጥ ኅብረቱ የመጥፋት (የመፍረስ) አደጋ ውስጥ መሆኑን ያመለክታል። አባባሉ፡- እያንዳንዳችሁ አንዱ ሌላውን በጥላቻ ቢያጠቃውና ብትከፋፈሉ የቤተ ክርስቲያናችሁን መቃብር እየቆፈራችሁ መሆኑን ተገንዘቡ እንደማለት ነው። በፍቅር ያለመመላለስ ተቃራኒው በጥላቻ መመላለስ ነው። ሁለት ውሾች እርስ በርስ መናከሳቸውን ካላቆሙ እርስ በርስ እንደሚጋደሉ ሁሉ፣ ምእመናንም በፍቅር ካልተመላለሱ በጥላቻና በሐሜት ቢናቆሩ እርስ በርስ ይጠፋፋሉ፤ ኅብረታቸውም ይፈርሳል። መከፋፈል፣ ራስን ማስቀደምና ሌላውን መግፋት የጥፋት መንገዶች ናቸው። የፍቅር መንገድ ግን የሕይወትና የሰላም መንገድ ነው።

ምዕ. 6 እግዚአብሔር ሙሴን ሲያበረታታው፡- "በጸናች እጅ ይለቅቃችኋል" አለው። ይህም እስራኤልን ነጻ በማውጣት ሂደት ውስጥ ጠላት በቀላሉ እንደማይለቅ ሲያመለክተው ነው። በክርስትና ሕይወትም እግዚአብሔር የገባልንን ተስፋ እንቀበል ዘንድ ተግተን በጽናት ሰልፉን መወጣት አለብን። በመጀመሪያ ላይ ሙሴ ይህ ስላልገባው ነው በእያንዳንዷ ተቃውሞ ውስጥ ከንፈረ ቆላፍ ነኝ፣ ሌላ ሰው ይሂድ ሲል የሚሰማው። "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ሲል በሚገጥሙህ ነገሮች ሁሉ አምላክህ ከአንተ ጋር ሆኜ አበረታሃለሁ፣ ኃይል እሆንሃለሁ ማለቱ ነው። "… አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም" (ዳን. 11፣32፤ ማቴ. 14፣26-27፤ ማር. 6፣49)። ሙሴ ከበረታ በኋላ ግን የተቀበለውን የተስፋ ቃል በመያዝ እስራኤልን ያበረታታ ነበር። እግዚአብሔርም በዚህ የተስፋ ቃል ወደ ሕዝቡ እንዲቀርብ ነገረው። "…እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ" (ቁ. 6፤ ኢሳ. 40፣1)። በተቃራኒው ደግሞ ጠላት ቀንበሩን በማክበድ፣ ፈተናውን በማብዛት የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይሰሙ (እንዳይቀበሉ) ለማድረግ ይጥር ነበር። "ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ ከከባዱም ሥራ የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም" (ቁ. 9)። እግዚአብሔር ነጻ ትወጣላችሁ ብሎ ሲናገር ምንም ነገሮች ቢከብዱብን ዘወር ብለን ወደ እግዚአብሔርና ወደ ተስፋ ቃሉ መመልከት ይገባናል። ይህን ማድረግ ካልቻልን በእምነት መጽናት ያቅተናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። 1ዮሐ. 5፣21 88 121024 አዲስ አበባ

ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወብነ ሕይወት ዘለዓለም። 1ዮሐ.5፣21 ሚያዝያ 2006

"ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር" (ቁ. 3)። ይህን ሲል እነዚሁ አባቶች አምላካቸውን አላወቁትም ነበር ማለት ሳይሆን ማንነቱንና ባሕርይውን በሚገልጠው “ያሕዌ” በሚለው ስሙ አልተገለጠላቸውም ለማለት ነው። ያሕዌ የሚለው ቃል ትርጓሜው ያለና የሚኖር፣ እንደ ባሕርዩ የሚሠራ ማለት ነው። ከሙሴ ዘመን ጀምሮ ግን ለእስራኤል በዚሁ ስሙ ከብዙ ተስፋ ጋር ተገልጦላቸዋል። የእግዚአብሔር የተስፋ ቃላት፡-

† እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡- ለሙሴ ጩኸት በተደጋጋሚ የተሰጠ ምላሽ † ከግብፃውያን ባርነት ነጻ አወጣችኋለሁ፡- የነጻነት ተስፋ † በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድ እታደጋችኋለሁ፡- የእግዚአብሔር ማዳን ሲገለጽ በጠላት ላይ የሚደርስ ፍርድ (ቅጣት) ታላቅ ነው † ለእኔ ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፡- ከጠላት አገዛዝና ከኃጢአት ቀንበር ከተፈቱ በኋላ የሚቀጥል ሂደት (2ቆሮ. 6፣17-18) † አምላክ እሆናችኋለሁ፣ ታውቁኛላችሁ፡- እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ነው (ዮሐ. 17፣3) † የተስፋይቱን ምድር ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡- እግዚአብሔር በሚጎበኝ ጊዜ ከእርሱ የሚሰጥ መልካም ብድራት፤ እግዚአብሔር እንደ ገና ለፈርዖን ተናገር ሲለው ሙሴ ግን ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ስለገባ ከንፈር ቆላፍ ነኝ ሲል የመጀመሪያውን ምክንያቱን አነሣ። ፈተና ሲበዛ ድጥ ሆኖ ወደ ኋላ የሚያንሸራትተን ሳይሆን እግዚአብሔርንና የሰጠውን ተስፋ አይተን የበለጠ በመጽናት ወደፊት የምንደረደርበት ሊሆን ይገባል። "በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና" (ያዕ. 1፣12)።

የሕዝበ እስራኤል ነጻ መውጣት የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ነው። ይህም በዘፍጥ. 3፣15 የተገባው ተስፋ ይፈጸምና ዓለም ሁሉ ይድን ዘንድ የማይቀለበስ መለኮታዊ ሥራ ነበር። ሰይጣን የእስራኤልን ጉዞ በመንገድ ሁሉ ይቃወም የነበረውም ከዚህ የተነሣ ነበር። የባሳንና የሴዎን ነገሥታት ጦር ይዘው ለምን ተነሡ? የእስራኤል ጥያቄ የሰላምና የደካማ መንገደኛ ሆኖ ሳለ ለምን ተቃወሙአቸው? “በመንገዳችሁ ብቻ እንሂድ፣ የምንፈልገውን በገንዘባችን እንግዛ … ቢሏቸውም እነርሱ ግን ሠራዊት አሰልፈው የወጡት የእስራኤል ጉዳይ ከዓለም ሁሉ መዳን ጋር የተያያዘ መሆኑን ያወቀ ጠላት አነሣስቷቸው ነው (ኤፌ. 1፣3-10)። እኛም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ የማዳን ዕቅድ ውስጥ አለን፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ደግሞ ማስቆም የሚችል የለም። ስለዚህም በሚገጥመን ፈተና ሁሉ በተስፋ እንጽና። ሙሴ የራሱን ማንነት በማየት ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል? አለ (ቁ. 30)። እግዚአብሔር ግን አበክሮ እያሳየው ያለው ፈርዖን ሊሰማህ የሚችለው እኔ በአንተ በኩል በምገልጠው ድንቅና ተአምራት ነው እያለ ነው። ዛሬም ሰዎች ሊሰሙንና ሊቀበሉን የሚችሉት ከእኛ የንግግር ችሎታ ወይም አቀራረብ የተነሣ አይደለም። ሙሴ እየደጋገመ ላለመታዘዝ ምክንያቶችን ሲደረድር እግዚአብሔር ግን ከሰፊ ትዕግስቱ የተነሣ ተቆጥቶ አላጠፋውም፤ ይልቁንም ደጋግሞ አጽናናው እንጂ።

ይ ቀ ጥ ላ ል

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትየመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

Page 9: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

ቅርርብ አልነበረንምና ተገረምኩ። እቤቴ ገባሁና ላልተቀበልኩት፣ ላላነበብኩት ደብዳቤ ምላሽ መጻፍ ጀመርኩ። ምን ብለሽ ይሆን የጻፍሽልኝ? … እናትሽ መጥፎ እየነገረች አለያይታን ነው እንጅ እኛ‘ኮ እንወድሻለን ብለሽኝ ይሆን? ስለ እናቴ ካላችሁ የተሳሳተ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን እኔንም አባት ምን እንደሆነ ሳላውቅ እንዳድግ አድርጋችሁኛል:: ምን ብለሽ ይሆን የጻፍሽልኝ? … አሁን ውጭ አገር ሄጃለሁ እኔ አለሁልሽ ልትይኝ ይሆን? ሁል ጊዜም ያለልኝ አሳዳጊዬ እግዚአብሔር ስለሆነ ምንም አልፈልግም:: ምን ብለሽ ይሆን የጻፍሽልኝ? ... አሁን አድገሻል ነገሮችን ከሁሉም አቅጣጫ ማገናዘብ ትችያለሽ ልትይኝ ይሆን? በማስተዋል ያሳደገኝ አምላኬ በፊትም መዝኜ እንዳይ ረድቶኛልና ልታባብይኝ አትሞክሪ:: ምን ብለሽ ይሆን የጻፍሽልኝ? . . . እያልኩ ልትለኝ ትችላለች ብዬ ያሰብኩትን ጥያቄ እየደረደርኩ የራሴን ምላሽ እየሰጠሁ ቀጠልኩ የሆነው ሆኖ አንድ ቀን ታሪኬ ተጽፎ መጽሐፉን ለልጅ ልጆችሽ ስታነብቢ ምስኪን ባለታሪክ ብለሽ በራስሽም ላይ ትፈርጅ ይሆናል በማለት ሦስት ገጽ ደብዳቤ ጻፍኩላት። ብስለት በመሰለ ሁኔታ መራር ደብዳቤ ጽፌ እርሷንም እራሴንም በቂም አሠርኩ። አጠፋሁ፤ ለጥፋቴ ማስታወሻ ደግሞ እኔ ወደ ኮሌጅ ስሄድ ደብዳቤውን እንድትልክላት የሰጠኋት ጓደኛዬ ፎቶ ኮፒ አድርጋ አስቀምጣው ነበርና የጌታን መንገድ አብልጠን በፈለግን ጊዜ ድርጊቴ ጸጸት ሆነኝ። በነገሬ ላይ የእርሷ መልዕክት፡- “አይዞሽ ከእንግዲህ እንረዳዳለን” የሚል ነበር። ይህ ከሆነ ከዓመታት በኋላ የአባቴ እናት ሞተችና እቤታቸው ሄጀ ለቅሶ ደረስኩ። ለማልቀስ ግን አልሞከርኩም። ይልቁንም ወንድ አያቴን ስላገኘሁት ተደስቼ ቆይቼ እንደተመለስኩ አስታውሳለሁ። ከክፍለ ሃገር ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። አገር ውስጥ ከነበረችው የአባቴ እህት ጋር መደዋወል ጀመርን። አንድ ሐሙስ ቀን ደውላልኝ ፡- “ምርቃትሽ መቼ ነው?” አለችኝ። ከነገ ወዲያ ቅዳሜ ነው ግን ብዙም ዝግጅት አላደርግም እናቴ መጥታልኛለች እሷ መገኘቷም ደስ እንዲላት ብዬ ብቻ ነው አልኳት። አርብ ከሰዓት በኋላ ለእኔ ምርቃት ከክፍለ ሃገር መጣች። ፍቅር ለዓመታት የተገደገደውን የጠብ ግድግዳ ደረመሰው። እናቴና አክስቴ ባንድ ጣራ ስር፣ ባንድ ማዕድ ቀረቡ። “ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!” አትሉልኝም። ልብ በሉ አሁን የአባቴ እህት አላልኳትም “አክስቴ”እንጂ፤ ተቀራረብና። የ2005 ዓ.ም. የማኅበራችን መሪ ቃል “እነሆ አዲስን ነገር አደርጋለሁ እርሱም አሁን ይበቅላል" ኢሳ. 43፣18 የሚል ነበር፤ ይህንን ያዙልኝ። ባለፈው ለበዓል እናቴጋ ወደ ክፍለ ሃገር ሄጀ በነበረ ጊዜ አክስቴን ልጠይቃት ሄድኩ። አሟት ፈቃድ ላይ ነበረች። ሁኔታዋ ጥሩ ስላልመሰለኝ አዲስ አበባ መጥታ እንድትታከም ተነጋገርን። አክስቴ ሕመሟ ካንሰር እንደሆነና በሕክምና የሚረዳበትን ደረጃ እንዳለፈ ሲነገረን ቀሪ ዕድሜዋን የምትፈልገውን በማድረግ ስቃይዋን በመቀነስና ፍጹም ፍቅርንና አብሮነትን በማሳየት እጅግ ደስተኛ እንድትሆን እግዚአብሔር ረዳን። ከሁሉ በላይ የምትደሰትበት ጉዳይ ደግሞ የኔንና እህቷን መቀራረብና ፍቅር ስታይ ነበር። እኔ ብሞት እህቴ ብቻዋን አይደለችም የሚለው አሳብዋ በግልጽ ይታይ ነበር። ሁለቱም አክስቶቼ ጋር በቤት ውስጥ ጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል መማማር፣ ስለ ንስሐና ሥጋ ወደሙን (ቅዱስ ቁርባን) ስለ መቀበል ከተነጋገርን በኋላ ወንጌልን የተማሩ መልካም ንስሐ አባት አግኝተን ወልድ ያለው የዘላለም ሕይወት አለው የሚለውን በመረዳት የጌታን ሥጋና ደም ተቀበለች። ለካስ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ ያደረገን ለቀሪውና አላፊው ቤተሰባዊነት ብቻ አልነበረም ለሰማያዊው መንግሥቱም ጭምር እንጅ። "ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!"

ለኔ ከሆነልኝ አስቀድሜ ቀደም ባሉት ጊዜያት የሰማሁትን የአንድ አባት ታሪክ ልንገራችሁ። እግዚአብሔርን በማመስገን የሚኖሩ አባት ነበሩ አሉ። በነገር ሁሉ “ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!” እያሉ የፈጣሪን ሥራ ያደንቁ ነበር። አንድ ዕለት በጫካ መካከል ሲያልፉ ዘንዶ አጋጠማቸውና ሊውጣቸው ወደ እርሳቸው መጣ። እርሳቸው ደግሞ አፈጣጠሩን ተመልክተውና አስተውለው በመደነቅ እንደልማዳቸው፡- “ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!” እያሉ የፈጣሪን ጥበብ ማድነቅ ያዙ፤ ዘንዶውም አፉን ከፍቶ ሲጠጋቸው የአፉን ስፋት፣ የአካሉን መወናጨፍና ጥርስ እንደሌለው እያዩ “ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!” ማለታቸውን ቀጠሉ። ይበልጥ አፉን በከፈተና በተሳበ ቁጥርም ይህንን አድናቆታቸውን ለአምላካቸው ሲያቀርቡ አፉ እየተከፈተ እየተተረተረ ሄዶ ዘንዶው ለሁለት ተሰንጥቆ ሞተ አሉ። ምስጋና ያልተጠበቀ ድል አለው። እግዚአብሔርን “ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!” እንድትሉልኝ ላወራላችሁ የፈለግሁት ዓመታት የተቆጠረበት የተበጠሰ ሐረጌን መቀጠል ላነሣ ነው። አባቴን ሲሞት እጅግ ሕፃን ነበርኩና በደንብ አላስታውሰውም። ከመሞቱ በፊት በእናቴና በአባቴ ቤተሰቦች መካከል ከባድ ቅራኔ ተፈጥሮ ነበር። ጠባቸው ምን ያህል የከረረ እንደነበር የምረዳው ከቀብር መልስ በእናቴ ቤትና በአባቴ ቤተሰቦች ቤት ድንኳን ለየብቻ ተጥሎ ኀዘንተኛ ለየወገናቸው እንዳስተናገዱ ስሰማ ነው። ከዚህም በኋላም ሁኔታው ተባበሰ እንጂ አልበረደም። የአባቴ ቤተሰቦች የራሳቸው ታሪክ እናቴም የራሷ ብሶት ነበራቸው። እኔ ግን ያለ አባት (የሥጋ አባት) ማለቴ ነው ማደጌ ሳይሆን በልጅ ሕይወት ውስጥ የአባትን አስፈላጊነት እስከማላውቀው ድረስ በአእምሮዬ ክፍተት ተፈጠረ። ወንድ በቤት ውስጥ ምን ፋይዳ እንዳለው መረዳቱ እንኳ ለእኔ እጅግ ፈታኝ ነበር። ከቤተሰቦቼ ከወንድ አያቴ በስተቀር ክፍተቴን ሊሞላ የሚችል ምትክ ፍቅር ያሳየኝ ሰው አልነበረም። መንገድ ላይ ሳያቸው እንዲስሙኝ እፈልጋለሁ። አክስቶችሽ አለፉ ሲሉ ስሰማ ወጥቼ አያቸዋለሁ፤ ቅርበትና ፍቅርን ግን አላየሁም። አምላኬ አሳደገኝ፤ እውነት ነው የምላችሁ የአባትን አስፈላጊነት ላስብ እንኳ የምሞክረው የጓደኛዬን አባት በማሰብ ነው ። ይህ ከበድ ያለ የልጅነት ጊዜ የኅሊና ጉዳት (childhood trauma) ነበር። አዋቂዎች ሕፃናት አይረዱትም ብለው የሚያልፉአቸውና ቸል የሚሏቸው ክስተቶች ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትሉም ይችላሉ። አድጌ ወደ ኮሌጅ ልገባ በነበረበት ወቅት አንደኛዋ የአባቴ እህት መንገድ ላይ አገኘችኝና እህቷ ወደ ውጭ አገር መሄድዋን ነግራኝ እዚያ ሆና ደብዳቤ ጽፋልሻለችና እሰጥሻለሁ አለችኝ። ልብ በሉ እሰከዚህ እድሜዬ ድረስ ምንም

ወአልቦ ካልእ ስም በታሕተ ሰማይ ዘይትወሀብ ለእጓለ እመ ሕያው በዘ የሐዩ። የሐዋ.4፣11 ሚያዝያ 2006

እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋ. 4፣11 99 121024 አዲስ አበባ

'እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።' መዝ. 66፥16

Page 10: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር። 2ጢሞ. 3፣14 1010 121024 አዲስ አበባ

ወአንተሰ ሀሉ በዘተመሀርከ ወተአመንክ። 2ጢሞ. 3፣14 ሚያዝያ 2006

እግዚአብሔር እንግዲህ ይላል፡- “የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ÷ የጥንቱንም ነገር አታስቡ። እነሆ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፣ እርሱም አሁን ይበቅላል፣ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ” ኢሳ. 43፣18። አምላካችን አዲስን ነገር አደርጋለሁ ሲለን አብዛኛዎቻችን ከፊት ለፊታችን ባለ የሕይወት ምዕራፍ ላይ ልናየው የወደድነውን አስበን ሊሆን ይችላል። የእግዚአብሔር አሳብ ግን ልዩ ነው። እርሱም አሁን ይበቅላል ነው ያለን። ገና የሚበቅል ነገር ሲያድግ እናያለን፤ ቀጥሎም ደግሞ ያፈራል፤ ያፈራውም ይበላል። ከዚያም በላይ ሌላ የሚዘራ ዘር ይኖረዋል። በምድረ በዳ፣ አቅጣጫው ወደዚህ ወደዚያ ነው በማይባልበት ቦታ መንገድን እንደማወቅ ወሳኝ ነገር የለም። በበረሃም እንደ ውኃ ውድ ኃብት ከቶ አይገኝም ይባላል። እግዚአብሔር ግን የሰጠን ቃል ላንድ ጊዜ የጥማት እርካታ የሚሆን ውኃ ብቻ ሳይሆን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ የሚል ነው። የሚፈስሱ፣ አካባቢን ሁሉ የሚያረሰርሱ ወንዞች። ለኔ እግዚአብሔር ይህን ነው ያደረገልኝ። ቀድሞ በዕድሜዬ ያልነበረው አዲስ ፍቅርና ቤተሰባዊነት በቀለልኝ። እግዚአብሔርን ሥራህ ግሩም አልኩት። መላና መድኃኒት የሌለውን የአክስቴን ሕመም ያለስቃይ በታላቅ ተስፋ እንድትቀበለው ረዳልን። ከሁሉ በሚልቀው የሕይወት መንገዱም መራልኝ። የምትመኘውን የነፍሷን የመዳን መንገድ ሰጣት። እግዚአብሔር ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ከውጭ ለመጣችው አክስቴም በውጭው ዓለም ኑሮ ተጽዕኖ ረስታው የነበረውን መንፈሳዊ ሕይወት አደሰላት። በተጨነቀችበት ቀርቦ በማጽናናት የሕይወት ውኃ ወንዝን አደረገላት። "ግሩም ያንተ ሥራ ድንቅ ያንተ ሥራ!" የታመመችዋ አክስቴ ወደ አምላኳ ተሰበሰበች። በመጨረሻው ደቂቃ አንቺ ያስተማርሽኝን ጸሎት እየጸለይኩላት ስላለፈች ሳስበው ደስ ይለኛል አለችኝ፣ የእህቷን ስንብት ስትነግረኝ። እግዚብሔር ስንብትንም ያሳምራል። እግዚአብሔር ዘላለም በቃሉ ይገኛል። ሳናስተውል ስንቀር ውለታውን እንዘነጋ ይሆናል እንጂ እግዚአብሔር ቃሉን አምነን በተቀበልን ላይ ሁሉ አዲስን ነገር አድርጓል። እህቴ አሁን በዘላለማዊ አባቷ እቅፍ ውስጥ መሆኗን ሳስብ ደስ ይለኛል። የአባቴ እህት ያልኳትን በኋላ አክስቴ አሁን ደግሞ እህቴ አልኳት፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበደለኛውን ሰው የኃጢአት ዕዳ በመክፈል ከአባቱ ጋር አስታርቆን የለምን? እንዲሁ በእኔና በእህቶቼ መካከል የነበረውን የጠብ ግድግዳ አፍርሶ ሰላምን አደረገ። እንግዲህ አንድነታችን በዚህ ምድር ብቻ የሚቀር ሳሆን በሰማያዊውም መንግሥት የሚቀጥል ሆኖልናልና እህቴ ናት። “… በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ።” ወንዙ የሚፈስስ፣ የሚቀጥል፣ የማያቋርጥ ሂደት ያለው ነውና እግዚአብሔር እንደተናገረው ወደ ውጭ የተመለሰችዋ አክስቴም የሚከተለውን የእምነት ታሪክ ኢ-ሜይል አደረገችልኝና በጌታ አሠራር ተደነቅኹ። ሐኪሙ፡- "የታመምከው ሕመም ጊዜ የሚሰጥም የሚድንም አይደለም" በማለት ለሕመምተኛው የሕመሙን ሁኔታ ነገረው፤ ታካሚ፡- "ዶክተር መሞቴ ነው ማለት ነው? አንድ ነገር ብቻ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ በዚያኛው ጫፍ (ከሞትኩ በኋላ) ምን አያለሁ?" ሐኪሙ፡- የሚመልሰው ግራ ገብቶት የሕመምተኛውን ክፍል ከፍቶ ሊወጣ ሲል በሩን የመቧጨር ድምጽ ሰምቶ ሲከፍተው መኪናው ውስጥ ትቷት የመጣ የመሰለው ድንክዬ ውሻው ዘላ ገባች። ሐኪሙም ወደ ሕመምተኛው ዘወር ብሎ፡- "ይህች ውሻዬ ከዚህ በፊት እዚህ ቦታ መጥታ አታውቅም። በሩን ለማስከፈት ግን ትቧጭር ነበር። ምክንያቱም እኔ ጌታዋ ከበሩ ጀርባ እንዳለሁ እርግጠኛ ናት። ስላንተም አንድ ነገር አውቃለሁ በወዲያኛው በኩል ጌታህ አለ" አለው። በዘመናት ሁሉ ታማኝ ለሆነው ለአባታችንና ለአምላካችን ለእግዚብሔር ምስጋናና ክብር ይሁንለት።

እህታችሁ አፀደ ማርያም ነኝ።

በእግዚአብሔር ስም ሰላምታዬ ይድረሳችሁ፤ በየወሩ በሚወጣው ጽሑፋችሁ የእግዚአብሔርን በረከት እያገኘሁ ስለሆነ አምላኬን አመሰግነዋለሁ። ለዛሬው እኔም በበኩሌ ጥያቄ የሆነብኝን ነገር ላነሣ እፈልጋለሁ። ይኸውም “የሙታንን መንፈስ መጥራት” የሚባል ነገር በአካባቢዬ ይወራል። ለምሳሌ አንድ ሰው በሰው እጅ ቢገደልና ገዳዩ ካልታወቀ ወይም ለሥራ ብሎ እንደ ወጣ በዚያው ሞተ ተብሎ ለቤተሰቦቹ ቢነገርና ቤተሰቦቹ በአሟሟቱ ላይ የሚጠረጥሩት ሰው ካለ ሙታን ጠሪ ወደሚባሉ ሰዎች ሄደው ያስጠይቃሉ። በዚህ ጊዜ ሟች ይቀርብና እንዴት እንደ ሞተ ይናገራል ይባላል፤ ይህ በእግዚአብሔር ቃል እንዴት ይታያል? ምን ያህልስ ትክክል ነው?

እህታችሁ ወለተ ኪዳን ነኝ። ውድ ጠያቂ እህታችን ሰላመ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን። በመጀመሪ መናፍስት ጠሪ (familiar spirit) ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንመልከት። መናፍስት ጠሪ ርኩሳን መናፍስትንና የሞቱ ሰዎች መናፍስትን በድግምት የሚጠራና የሚጠይቅ ነው። ድምጽ የሚመጣ የሚመስለው ከመሬት ስለሆነ ደጋሚው (the medium) ጆሮውን ወደ መሬት ተክሎ፣ ድምጽ የሚሰማ ዓይነት ሆኖ ይቀርባል። ይህ ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ከቶ የተጠላ ነው። “አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ” (ዘዳግ. 18፣11)። ሲገኝም ፍርዱ ሞት ነበር። (ዘሌዋ. 20፣6፤ 1ዜና. 10፣13-14፤ 2ነገ. 23፣24) እህታችን እንዳነሣሽው የወገናችንን “ትክክለኛ” አሟሟት ለማረጋገጥ ወደ መናፍስት ጠሪ እንሂድ የሚሉ ሰዎች አሉ። የተሣሣተ ቢሆንም በእነርሱ አመለካከት ይህን የሚያደርጉት በጥርጣሬ ወደ በቀል እንዳይገቡና ልባቸው “እንዲያርፍ” ነው። ወደ መናፍስት ጠሪው ሲሄዱ ደጋሚው የመረጠው ሰው ይቀርብና ሰይጣናዊ ተግባሩ ይከናወናል። በዚህ ጊዜ ሟርተኛው ይኸው የሞተው ሰው ቀርቧል የገደለኝ እከሌ ነው፤ አልያም ሰው አትጠርጥሩ የወንዝ ውኃ ነው የበላኝ ሬሳዬም እዚህ ዓይነት ቦታ ይገኛል … ብሏል ይላል። በዚህም “ማረጋገጫ” ሰዎች ሰይጣናዊ አሠራርን ይቀበላሉ። ሰዎች ከሞቱ በኋላ እንደገና ከሰዎች ጋር የሚገናኙበት፣ ወደ ሕያዋን ምድር የሚመጡበት ምክንያት የለም። “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው” (ዕብ. 9፣27) ይላልና ሰዎች ከገቡበት የዘላለም ስፍራቸው መውጣት አይችሉም። ለዚህ ማረጋገጫችን የሃብታሙ ነዌና የድሃው አልዓዛር ታሪክ ነው። በሉቃ. 16፣22-30 እንደተጻፈልን ከገነት ወደ ሲኦል፣ ከሲኦል ወደ ገነት አልያም ከሞት በኋላ ካለ ስፍራ ወደ ምድር መመለስ እንደማይቻል ያስተምራል። እዚህ ላይ የሚነሣው ጥያቄ መናፍስት ጠሪው የሚያናግረው ማንን ነው? የሚለው ነው። መልሱ ሰይጣንን (ርኩስ መንፈስን) ነው የሚል ይሆናል። ሰይጣን በተወሰነ ደረጃ የተከናወኑ ነገሮችን ያውቃል። ይህን ስንል በሁሉም ቦታ ያለውን የማወቅ ችሎታ አለው ማለት ሳይሆን በእርሱ የአገዛዝ መዋቅር ውስጥ በየደረጃው የሚሾሙ አለቆች፣ መናፍስትና ጭፍሮች አሉ። እነዚያ ደግሞ መረጃን በየደረጃው ለበላያቸው እያስተላለፉ እንደሚሠሩ ማስተዋል ይቻላል። ስለዚህ በድግምቱ የሚጠራው ሰይጣን ሲሆን በእርሱ ክልልና ዕውቀት ሥር የተፈጸመውን ያውቃል፤ ያንንም መረጃ ሟቹን ተመስሎ ያቀርባል። የሚታለለው መፍትሔ ፍለጋ የሚሄደው ሰው እንጂ መናፍስት ጠሪው በደገመ ጊዜ የሚመጣው ሰይጣን እንደ ሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህ ጥሩ ማስረጃ የምትሆነን ንጉሥ ሳኦል ሊያማክራት የሄደችው በዓይንዶር የነበረችው መናፍስት ጠሪ ናት። በ1ሳሙ. 28፣7-19 ላይ እንደምናነብበው ሳኦል እንድታስነሣለት የፈለገው ነቢዩ ሳሙኤልን እንደ ሆነ ነግሯት ነበር። ነገር ግን ሴቲቱ በለመደችው የጥንቆላ አሠራር የተገለጠው ሰይጣን ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ትክክለኛው ሳሙኤል በመሆኑ ነው ደንግጣ የጮኸችውና የተጨነቀችው። “ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ

Page 11: LIDETALEMARIAM MIYAZIA 2006

ቀስ ብላ እማዬ በጣም ደከመሽ አይደለም? አለችና ተጠግታ አቀፈቻት። እናቷም ደግሞ ምን ልትጠይቂኝ ይሆን? ፊትሽ ላይ ያስታውቃል የእኔ ቆንጆ አለችና ግንባሯ ላይ ሳመቻት። ሐናም፡- እማዬ ዛሬ ቤተሰባችን ሁሉ እንዲህ የሚጣደፈው ለምንድን ነው? እኛ ቤት ብዙ እንግዳ ይመጣል እንዴ? ስትል ጠየቅች። እናቷም አይ ልጄ አይደለም፤ ነገ እኮ ፋሲካ ነው፣ ዓመት በዓል ታውቂያለሽ? ሌሊት ተነሥተን ዶሮ ወጥ እንበላለን፣ ጠዋት ደግሞ ዳቦ ተቆርሶ በጉ ይታረዳል፣ አንቺም የተገዛልሽን አዲስ ልብስና ጫማ ስታገኚ ደስ ይልሻል አለቻት።

ሐና በፊቷ ላይ ግራ መጋባት እየታየባት አልገባኝም አለች። እኔ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ለፋሲካ መዝሙር ታቀርባላችሁ ተብለን ሰሞኑን ስለ ትንሣኤ እየተማርን ነበር። ፋሲካ የሚከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሲኦል ለማዳንና ከሰይጣን እስራት ለመፍታት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞቱንና በሦስተኛው ቀን ከሞት መነሣቱን በማመን ነው ብለው ነው ያስተማሩን። ስለዚህ የፋሲካን በዓል ስታከብሩ መቅደም ያለበት የምግብና የልብስ ነገር አይደለም፤ ስለ እኛ የሞተውንና የተነሣውን ጌታ በማሰብና በማክበር ነው ተብለናል። ሌሊቱን በዝማሬና በቅዳሴ እንዲሁም ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል ፋሲካን አክብሩ፤ ይህ ከሌለበት ትልቅ ስሕተት ነው ብለውናል። እኛ ቤት ደግሞ ይህ ነገር ያለ አልመሰለኝም አለች ሐና።

የሐና እናትም ትንሽ በሀዘንና በጸጸት ስሜት ውስጥ ሁና እግዚአብሔር የአንቺን ልብ አይቶ ሁላችንንም ይቅር ይበለና! ይህ ሁሉ የእኛ ድካም ለሆዳችን ብቻ እኮ ነው። ሁሉም ልጆቼ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል ቢማሩ እንዴት መልካም ነበር። በተሳሳተ መንገድ ስንሄድ እንዲህ እንዳንቺ እያስተማሩ ይመልሱን ነበር አለች።

ልጆች እናንተስ ከዚህ ታሪክ ምን አስተዋላችሁ? በሰንበት ትምህርት ቤታችሁ ስለ ፋሲካ ምን ተምራችኋል? በቤታችሁስ የፋሲካ በዓል እንዴት ነው የሚከበረው? የበዓሉ ዋና መልእክት ምንድን ነው? የምታውቁትን ጻፉልን።

“እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና” (1ቆሮ. 5፣7)።

የላካችሁልን መልእክቶች ደርሰውናል። አገልግሎታችንን በተመለከተ ስለምትሰጡን አስተያየት እግዚአብሔር ይባርካችሁ። በቀጣይም እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት የመዳንን ወንጌል ለማዳረስ በምናደርገው መንፈሳዊ ሩጫ አስተያታችሁ ጠቃሚያችን ነውና ጻፉልን። ደግሞም "በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ" (2ተሰ. 3፣1-2)።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ጮኸች ሴቲቱም ሳኦልን፦ አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ? ብላ ተናገረችው። ንጉሡም፡- አትፍሪ ያየሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፦ አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ አለችው” (ቁ. 12-13)። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ከወደደ በፈለገበት መንገድ ሳይገደብ የራሱን እጅ የማስገባት ሥልጣን ስላለው ነው። (ዳን. 4፣35፤ 2ነገ. 1፣4)

ማጠቃለያ ሀ. መናፍስት ጠሪነት ሰይጣናዊ አሠራር መሆኑንና እግዚአብሔር እንደሚጠላው መረዳት አለብን። “እርሱም፦ የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?” (ኢሳ. 8፣19)።

ለ. ሰው ከሞተ በኋላ በየትኛውም ዓይነትና መንገድ በሕይወት ካሉ ሰዎች ጋር የሚገናኝበት መንገድ የለውም። አንዳንድ ሰዎች የሚወድዱት ሰው ከሞተ በኋላ በሕልሜ እናቴን አይቼአት፣ ባለቤቴ መጥቶ፣ … ይላሉ። ይህ አንድም ከሰዎቹ የልብ አሳብ የሚመነጭ (መክ. 5፣3) አልያም ሰይጣን የራሱን ፈቃድ ለማከናወን እንዲመቸው መስሎ እየቀረበ ሊሆን ይችላል። በአገልግሎታችን የሞተ አባቴን፣ ወንድሜን፣ እህቴን አየሁ ብለው ለማከሩን ወገኖች የሰይጣን አሠራር ሊሆን ስለሚችል ተመስለህ የምትቀርበኝ ሰይጣን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እቃወምሃለሁ ብለው እንዲጸልዩ ነግረናቸው ነገሩ ከዚያ በኋላ ፈጽሞ ከሕይወታቸው እንደራቀ መስክረውልናል።

ሐ. ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወት ዘመኑ በነበረው ውሳኔና ምርጫ፤ ማለትም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሲወርስ የሞተለትን አምላክ አውቆና ወስኖ ያልተከተለ ከሆነ ወደ ሲኦል ይወርዳል። በዚያ ላይ ሥልጣኑ የእግዚአብሔር ብቻ ነው። “ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ” (ራእ. 1፣8፤ ማቴ. 17፣3)

መ. መናፍስት ጠሪነት ሰይጣናዊ አሠራር መሆኑን ከተረዳን በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት በመታጠቅ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በጸሎት ማፍረስ አለብን። “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ” (1ዮሐ. 3፣9)።

ውድ ወገኖቻችን እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ የምታውቁት ነገር ወይም የሰማችሁት ካለ ጻፉልን።

አስተዋይዋ ሐና ሐና በትንሣኤ (ፋሲካ) ዋዜማ ቤተሰቧ የሚያደርገውን ዝግጅት፣ ግርግርና ሩጫ በመገረም ትመለከታለች። ልጅ ናት ብለው ስለሚያስቡ ስለሚደረገው ዝግጅት ዝርዝር የሚነግራት አልያም አንቺ ደግሞ ለምን ቁጭ ትያለሽ? ይህን ሥሪ የሚላት የለም። እርሷ ግን የቤተሰቡን ሁኔታ በመገረምና በጥያቄ ውስጥ ሆና ትመለከታለች።

ታላላቅ ወንድምና እህቶቿን ምን እያደረጋችሁ ነው? ብላ ስትጠይቅ፡- አንቺ ሕፃን ነሽ፣ ምን ታውቂያለሽ? ምንስ ይገባሻል? ዝም ብለሽ ተቀመጪ ብለዋታልና ማንን መጠየቅ እንዳለባት ተጨንቃለች። እናቷ ሐናን ብልህና አስተዋይ ልጅ ናት እያለች ሁል ጊዜም ከልብ እንደምትሰማት ታውቃለች። ዛሬ ግን እናቷ በጣም ሥራ በዝቶባት ስላየቻት … የተገዛው በግ ገመዱን እንዳይበጥስና እንዳይጠፋ ጠብቁ፤ ቤቱን በደንብ ጥረጉና ሣር ይጎዝጎዝ፤ አዲሱን ሶፋ አስተካክላችሁ አስቀምጡት፤ ለዚህ ሁሉ ቤተሰብ ሦስት ዶሮ እንዴት ይበቃል?፣ የደፋሁት ዳቦ እንዳያርርብኝ፤ …እያለች በጣም ትጣደፍ ስለነበር እርሷን መጠየቅ አልደፈረችም። በኋላ ግን፣ የለም መጠየቅ አለብኝ ብላ ወሰነችና እናቷ ወደነበረችበት የምግብ ማብሰያ ክፍል ሄደችና

እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል ኢሳ. 14፣3:: ሚያዝያ 2006

በተጨማሪም 1. ከቤተ መንግሥት ደጃፍ እና የካታኮምብ ሰማዕታት የተባሉ

ተውኔቶች ሁለቱም በቪሲዲ 2. መጋረጃው ሲገለጥ (ከውቃቢ/ሰይጣን ቤት አገልጋይነት የተመለሰን

ወንድም ምስክርነት የያዘ) መጽሐፍ 3. መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ለማጥናት የሚረዳ ጥራዝ 4. በካሴት የተዘጋጁ ስብከቶች

እንዴት ማግኘት (መግዛት) እንደምትችሉ ለመረዳት፣ ለጥያቄና አስተያየት፣ ለምክርና የጸሎት እርዳታ፣ በማኅበሩ ተዘጋጅቶ በነጻ የሚሰጠውን መንፈሳዊ የተልእኮ ትምህርት ለመከታተል፣ አገልግሎቱን ለማገዝ፣ በመ.ሣ. ቁ. 121024 ልትጽፉልን ወይንም በ

0911- 64-75-91 / 0118- 30-14-28/ 0911- 67-10-16ደውላችሁ ልታነጋግሩን ትችላላችሁ

በቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር የተዘጋጀ የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 አዲስ አበባ

የድረ-አምባ (website) አድራሻ: www.lidetalemariam.org ኢ-ሜይል (e-mail): [email protected] 1111

የልጆች አምድየልጆች አምድየልጆች አምድ