ethiopian friendship & cooperation idir | annual general ... fileየዕድሩ ዳኛ...

6

Upload: others

Post on 28-Oct-2019

4 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ
Page 2: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ

የዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤

ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ በሄዱ ቁጥር አዲስ ትውልድ ከሚረከበው ከእዚህ ባሕልና ልምድ መሀከል የሚሻሻለውን አሻሽሎ፤ ሊቀር የሚገባውን ትቶ እንዲሁ በተራው እሱን ለሚተካው ትውልድ ያስተላልፋል። ዘመኑና ወቅቱ በትክክል ባይታወቅ ለረጅም ጊዜ በአገራችን የነበረ፤ በችግር ጊዜ መረዳዳት ከእዚያም አልፎ ሁሉም በተራ በሚደርሰውን የሞት ፅዋ ሀዘን በመተጋገዝ አጋርነትን ለማሳየት ዕድር ትልቁን ሚና ሲያበረክት የቆየ አኩሪ ከሆኑት ባሕላችን አንዱ ነው።

እኛም ከቤተሰቦቻችን ቀጣይ ተረካቢ እንደመሆናችን ተረድተን የቀዬ ርቀት ሳይወስነንና አገልግሎቱንና ጥቅሙን ተልመን ከሰባት ዓመት በፊት የመሰረትነው እድራችን ዛሬ የጅማሬ ዕድሜውን ጨርሶ የእድገት ምልክቶችን እያሳየ ይገኛል። ታዲያ ይህ ዕድር አገልግሎቱ የሰፋና የዳበረ፤ ብሎም ውስን ከሆኑት ተግባራት በመሻገር ሌሎች አባላት ሊገለገልባቸው የሚችሉ በርካታ አገልግሎቶችን መፍጠርና ማዳበር እንዳለብን ሲሰማኝ የመላው አባላትን አስተዋጽኦ ምርኩዝ አድርጌ ነው።

፩ኛ - ሕግና ደንቡን በትክክል መገንዘብ፤

ከሁሉ በፊት እኛው እራሳችን የደነገግነውን ሕግና ደንብ በትክክል መረዳትና ማክበር ዋነኛው ሲሆን ከነባራዊ ሁኔታዎችና ከምንኖርባት ከእዚች ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳይጣላብን በሰላማዊ መንገድ ዕቅዳችንን ሁሉ ለማሳካት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በየጊዜው ማሻሻልና ማስተካከል ተገቢ ነው። ይህ ግን ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ሁሉም የእድሩ አባል ሙሉ ተሳትፎ ሲኖረው ነው። የመወያየት ባሕላችንን አዳብረን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ ለመቅረፍ መፍትሄው ሁሉ ያለው ከእኛው ከአባሉ ነው። የሕግ የበላይነት በሰፈነበት በእዚች ሀገር እየኖርን እንደው በዘፈቀደ ወይም በዘልማድ ተራምደን እድራችንን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ አዳጋች ነው። ለሥራችን፣ ለአገልግሎታችን፣ ለአንድነታችን እንዲሁም ለወደፊቱ እድገታችን ሁሉ ሊዳኘንና ሊመራን የሚችለው የመተዳደሪያ ደንባችን ብቻ ይሆናል። ለእዚህ ተግባራዊነት በሕገ ደንቡ ላይ የሚጨመረውን ወይም የሚቀነሰውን ለማስተያየትና ለመወሰን እያንዳንዱ አባል ቢያንስ አንድ ጊዜ በስብሰባ ላይ በመገኘት የበኩሉን ሁሉ ማበርከት ትንሹ ግዴታ ነው።

፪ኛ - የረጅም ጊዜ ፕላንና እቅድ ማውጣት፤

ወደፊት አስርና ሃያ ዓመት አርቀን ብንተልም ይህ እድራችን ምን ዓይነት የአገልግሎት ደረጃ ላይ እንዲደርስ እንፈልጋለን? ምን እንጠብቅ? ለእኔ እንደሚመስለኝ ይህንን ግሩም አኩሪ የሆነ ባሕላችንን እዚህ ለምንወልዳቸው ልጆቻችን የማውረስ ሀላፊነት አለብን። ይህንን ለማድረግ ግን ከእነሱ የአኗኗር ዘይቤ ጋር እያስታረቅን፤ የባሕላችን መነሻው ሳይለቅ እንዲረዱትና አእምሯቸው ሰርጎ እንዲቀረጽ የእያንዳንዳችንን ተጨማሪ ጥረት ይጠይቃል። በሰፊውና በረጅሙ እየተለምን እንደእቅዳችን ከተራመድን ይህ እድር ትልቅ፣ አገልግሎቱ የሰፋ ሆኖ ጥሩ ድርጅት እንደሚሆን ዕምነቴ የፀና ነው።

“People, they don’t plan to fail but they fail to plan.”

መግቢያ በዕድሩ ዳኛ - - 2:30

ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት -- 3:00

የዓመቱ ሪፖርት በዕድሩ ዋና ጸሀፊ 2:45

አዲስ የሥራ አስኪያጅ ምርጫ 4:20

የሕግ ደንብ ማሻሻያ ስለማጽደቅ - 3:15

የአማካሪ ኮሚቴ ምርጫ - 4:00

Page 3: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ

Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General Meeting |

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር በሲድኒ | ዓመታዊ የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

3

Finance Report for the period ended 30 June 2017

Opening Balance as at 1 July 2016 $ 72,196.63

INCOME

Contribution (Include $520 unidentified fee) $ 20.334.40

Donation for family gathering event $ 300.00

Interest on term deposit $ 526.20

Interest transaction account $ 9.95

Total income for the financial year $ 21,170.55

EXPENSES

Payment to members $ - - - - -

Expenses for family gathering event $ 728.00

Office expenses (Annual renewal of Fair trading and web site host and otehrs.) $ 214.40

Total expenses $ 942.40

Net Cash at Bank as at 30 June 2017 $ 92,424.78

Term deposit $ 72,856.67

Transaction account $ 19,568.11 $ 92,424.78

Add Contribution not yet received at June 30, 2017 $ 517.89

Less Contribution paid in advance at June 30, 2017 $ 3,829.00

Net balance as at June 30, 2017 $ 89,113.67

Page 4: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ

Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General Meeting |

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር በሲድኒ | ዓመታዊ የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

4

77 የጠቅላላ አባላት

ብዛት

40 አባላት በቀጥታ ተቆራጭ አከፋፈል ዘዴ ይጠቀማሉ

(Automatic Direct Debit)

*******

517 ያህል ደረሰኝ የተቆረጠላቸው ክፍያዎች ተከናውነዋል። 355ቱ ለከፋዮቹ በኢሜይል ተልኳል።

በአለፈው የበጀት ዓመት በቀጥታ ተቆራጭ አከፋፈል ዘዴ (Automatic Direct Debit)

ተጠቃሚ የነበሩት አባላት ቁጥር ብዛት 32 ነበር።

*****

66 አባላት ለመልዕክት ልውውጥ ሲባል የኢሜይል አድራሻቸውን

መጠቀም ተችlሏል። ባጠናቀቅነው የበጀት ዓመት ብቻ የዓመቱን ወይም የጥቂት ወራትን

በቅድሚያ የመክፈል ዘዴ ከሚጠቀሙት አባላት ውስጥ ለ28ቱ

የክፍያ ማስታወሻ (Reminder note)

የያዘ 43 ኢሜይል ተልኳል።

Page 5: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ

Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General Meeting |

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር በሲድኒ | ዓመታዊ የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

5

መንገደ ምርቃና መሄድ ከተቻለ ሂዱ ሌላ አስሱ፤ ከወዲያኛው ዓለም፤

ምጠቁ ጥለቁ ይቅናችሁ ግድ የለም።

ምጠቁ ጥለቁ በጉም ሀሳብ ሕዋ በምርቅንቅን ዓለም።

……. ግን ………

ያ ክር ሲበጠስ

ሲከጅል መመለስ

ምርቃናው ሲሰበር

እውነት ሲበረበር _ _ _

ማንነት ሲቀለም

በፍኖተ ቅዠት በምርቅንቅን ዓለም

ወሳጅ መንገድ እንጂ መላሽ መንገድ የለም።

(ይስማዕከ ወርቁ - ‘የወንድ ምጥ’)

የእኔ ውብ ከተማ

«… ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር

ያለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር?

የእኔ ውብ ከተማ-

ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር

የእኔ ውብ ከተማ-

መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር

የእኔ ውብ ከተማ የእኔ ውብ ሀገር

የሰው ልጅ ልብ ነው፤

የሌለው ዳርቻ፤ የሌለው ድንበር።

ሕንጻው ምን ቢረዝም፤ ምን ቢጸዳ ቤቱ

መንገዱ ቢሰፋ፤ ቢንጣለል አስፋልቱ

ሰው ሰው ካልሸተተ፤ ምንድነው ውበቱ? …»

(ኦሮማይ ከበዓሉ ግርማ)

« …ጽጌረዳ ቀለሟ፤ ቀይ ብቻ ነው ብሎ ዘበት

ያንት ጎዳና ወደ ሲኦል፤ የእኔይቱ ወደ ገነት

… ብሎ ፍጥም፤ ዝግት፤ ግርግም

ፍካሬ እቡይ፤ ዛሬ የለም።

ጠብ ያለሽ በዳቦን ፤ አልፈን

ተቸንፈን …አሸንፈን፤ አቸንፈን … ተሸንፈን

አቦ ተወኝ ! እባክህን

ባንኳኳን ልንኳኳን፤ መከራ ነው የመከረን። … »

( እ ር ግ ማ ኔ ን መ ል ስል ኝ - ለ ሎሬ ት ጸ ጋዬ ገ / መ ድ ኅ ን የ ተጻ ፈ )

ከ እ ሳቱ ተሰ ማ

White Sponge Cake

Ingredients 5 eggs, at room temprature 150 grams Caster sugar 150 gramsFlour Vanilla

Method 1. Grease 8inch cake tin and line base

with baking paper 2. Preheat oven to 180c. Sift flour 3. Beat eggs and flour in a large bowl

until mixture is thick and tripled in volume.

4. Gradually fold in sift flour over the egg mixture until combined.

5. Bake for 20min or until cake spring back when gently touched.

Butter Cream

Ingredients 150 grams caster sugar 50 ml water 3 eggs 500 grams butter

Method 1. Boil caster sugar and water. 2. Beat eggs in a large boil until it’s thick. 3. Pour boiled sugar over beaten eggs and beat until mixture is cold. 4. Gradually add soft butter and beat until mixture is thick.

Custard Cream

Ingredients 3 egg yolks 3 cups milk ½ cup custer sugar 1/3 cup corn starch Pinch of salt

Method 1. Beat egg yolks well in medium bowl, gradually stir in milk until

blended. 2. Mix sugar, cornstarch and salt in a large heavy saucepan. Gradually

stir in a small amount of milk mixture, making a smooth paste. 3. Gradually stir in remaining milk mixture until blended. 4. Cook over midium-low heat, stirring constantly, until mixtures

thickens and comes to a boil, 20 to 25minutes. Remove from the heat immediately.

«… የሰው ወርቅ አያደምቅ፤ ይላል ሰው ተላላ

የእኛ ወርቅ ምነው፤ ታደምቃለች ሌላ … » (ቀኝ ዮፍታሄ ንጉስ)

Page 6: Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General ... fileየዕድሩ ዳኛ መልዕክት፤ ብዙ የከበሩ ባሕልና ልምዶች አሉን። ዘመን እየተቆጠሩ

Ethiopian friendship & cooperation IDIR | Annual General Meeting |

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ዕድር በሲድኒ | ዓመታዊ የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

6

አግድመት

2. «... ይሄ ልጅ ተብሰከሰከ እንቅልፉ መጣም መሰል። እስቲ ያን __2__

አቀብለኝ። ...»

5. «... ‘ ከሴራ ዲና ይወድልሻል አሉ። ደሞ ከመቼ ጀምሮ ነው ከሴተኛ አዳሪ ጋር

__5__ የሆንሽው?’አፋቸውን አሽሟጠጡ ... »

7. « ... ወልዶ ለመሳም፣ ዘግኖ ለመቃም ያብቃችሁ። የሣቅ ፣ የደስታ __7__ ያዘለ

ቤት ይሁን! ... »

8. ልምድና ስርዓት እንዳይጓደል አጥብቆ ተከራካሪ የሆነ ሰው ፤

11. __11__ ብለው የወጡት ባሻ፤ ጫካው በልቷቸው ካሰቡት ያላሰቡት

ቀደማቸውና ሳይመለሱ ቀሩ።

13. « … መሀል አናት በሚያቃጥል ጠራራ ፀሀይ ፣ ጥላ ሞቴ እንደ ጥቁር ምንጣፍ

እግሮቼ ስር በውሀ እጦት የተሰነጣጠቀ ምድር ላይ እኔ በማሽላ ማሳ መካከል

እንደ __13__ ሰንጥቄ ሳልፍ ግራና ቀኝ እየታከኳቸው የሚያልፉ ሞተው

የደረቁ ቅጠሎች ተንሿሹ። …»

14. «…ለካንስ የእምዬ ማርያም ምስል እያሉ የሚልኩልን የአዲስ አበባን

__14__ ኖሯል።…»

17. «… ከጓደኞቼ ጋር ሰፈራችን ውስጥ ትልቅ አገራዊ ዓላማ እንዳለን ወይ ፅዋ

እንደሚጠጡና __15__ እንዳቆሙ ትልልቅ ሰዎች ተሰብስበን

ተቀምጠናል።… »

18. ሞጣ ____18____ ምነው አይታረስ

በእሬሳ ላይ መጣሁ ከእዚያ እስከዚህ ድረስ።

20. «… በጠይምና የቀይ ዳማ ቆነጃጅት መሀልእንደ ዓላማ ሰንደቅ ከሩቅ የምትታይ

ሶፊያ የተባለች ቀይ __20__ ዶሮ ግብር ከተባለ መንደሯ ማልዳ ተነስታ…»

22. « …ጎን ለጎን ተጋድመዋል። የሚያብረቀርቅ ነጭ __22__ ባላቸው ጋቢዎች

ውስጥ ተጠቅልለው ማንኛው አባቴ፤ ማንኛዋስ እናቴ እንደሆኑ አውቃለሁ? …»

25. «…በመልካም ጥርሳቸው የክትክታ __25__ ነክሰው… »

26. « …አሁንማ የት ትሄዳለች ብለሽ ነው! ጦቢያ እንደሆነች አባራታለች።

__26__ እየጋገረች ነው። ሳለ ጉልበቷ ሰርታ ትበላለች። …»

27. የአሰቡት፣ የአለሙት ከግብ ሲደርስ፤

ተፈላጊዎቹ ቃላቶች

ስኬታዊ ውዝግብ እርዚቅ

እዳይት ግንብ አንጋሬ

ቅሬ ቀራንዮ መጅ

መንድብ ጃምዮ ሳርጢስ

መቅናት ዳግማዊ ማዘል

ቢትወደድ ወግአጥባቂ አውገረድ

ጥልቆ አርቃቂ ሳንኬቶ

ተርተቢኛ አድሩስ ትምህርት

አብሽሎ ማሟጫ ቆነጃጅት

ቁልቁል

1. «... ጠረጴዛው ላይ ባለው ሳሙና ላይ ከተሰካው __1__ የሚነሳ ማለፊያ

ጠረን ከቤት ሞልቶ እየፈሰሰ … »

3. ሕገ ደንብ ፀሀፊ

4. ባሻ መንገሻ ያለ አቻ እድሜያቸው ልጅ እግር ቢያገቡ __4__ ጭራሽኑ

ሽምግልናቸውን አፋጥኖ አሳጣቸው።

6. በጥንት የንጉሳዊ አገዛዝ ዘመን የማዕረግ ሥም የነበረ።

9. የቤተ መንግሥቱ ዙሪያ የ __9__ አጥር እንኳንስ የሰው ፍጡር ይቅርና

የመሬት ነፍሳትም ለመግባታቸው ያጠራጥራል።

10. «… ትከሻው ላይ ያለችው የዘወትር መገልገያ የሆነችው __10__

ድንክ ስለቷን ታበስራለች።…»

11. «… ወንዶቹ የወጠጤና የበከል ፍየሎች __11__ ትከሻቸው ላይ

አሳርፈው ……»

12. በገጠሩ የሀገራችን ክልል ጥሬ እህል ለመፍጪያ ይጠቀሙበታል።

15. « … ሄጄበት የማላውቀው የዞብል ሰፊ ምድር የ__15__ ሰብል ለብሶ

ይታየኛል… » `

16. ዕውቀትን ማዳበሪያ መንገድ፤

19. « … ወድቆ ያገኘውን ዕቃ ግራና ቀኝ ገላምጦ ያነሳ እድለኛ፤ ከረጢት

ውስጥ ቡና መስሎ የታሰረው ጠጠር፤ በወረቀት ውስጥ __19__

መስሎ የታሰረውም አፈር እንደሆነ ያያል። …»

21. ክርክር ፤

23. የተደገመ ድርጊት ወይም ሁኔታ፤

24. « …አረንጓዴ ፈርጥ ያላት የብር __24__ የማርያም ጣታቸው ላይ

አጥልቀዋል። …»

ወደዕድሩ ሂሳብ መዝገብ ማናቸውንም ዓይነት

ክፍያ ማከናወን ከፈለጉ

Commonwealth Bank (Blacktown)

Account No. : 10548769

BSB No. : 062339

ስንቶቹን ቃላቶች ያስታውሳሉ ? ( ለማመሳከ ሪ ያ የ ዕድሩን ድዕረ - ገጽ ይ ጎብኙ )