“ዐማራነት”። · 5 | p a g e ገጽ፡፭-፲፤ *ገጽ፡፹፰፦ sidur tehillas...

11
1 | Page አጣምመው፡የጻፉብን፡ታሪካችንን፡በተጠንቀቅ፡ካላነበብነው፡ስሕተቱን፡እናራባዋለን። ነሐሴ፡፭፡ቀን፡፪ሺ፬፡ዓመተ፡ምሕረት። ገጽ፡፩-፲፤ “ኢትዮጵያ፡ታበጽሕ፡ዕድዊሃ፡ኀበ፡እግዚአብሔር።»»ኢትዮጵያ፡ዕጆቿን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ ትዘረጋለች”።መዝሙር፡፷፰፡፴፮፡»»ቀጥሎም፡በሌላ፡በኩል፦”ወወሀብኮሙ፡ሲሳዮሙ፡ለሕዝበ፡ኢትዮጵያ፡»»አንተ፡ እግዚአብሔር፡ለኢትዮጵያ፡ሰዎችም፡ምግባቸውን፡ሠጠሃቸው”።መዝሙር፡፸፫፡፲፬፡»»*ገጽ፡፯፦በሃይማኖት፡ካባ፣የሚ ሠራ፡ደባ።በሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡በርሃኑ።መስከረም፡፳፻፡ዓመተ፡ምሕረት። “ዐማራነት”። “(ከመኮንን ተድላ) ዐማራ፣ ዐምሃራ ከተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ እንደሆነ የቋንቋው ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ዐምሃራ `ዐም` እና `ሃራ `ከተሰኙት ሁለት የዕብራይስጥ ቃሎች ጥምረት የተመሠረተ እንደሆነም ሊቃውንቶቹ ይናገራሉ፡፡ ዐም ማለት ሕዝብ ሲሆን ሃራ ማለት ደግሞ ነፃ ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ቃሎች ባንድነት ሲጣመሩ `ነፃ ሕዝብ` የሚለውን ትርጉም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ዐማራነት የኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና የሰረጸው ፣ፍቅር፣ወንድማማችነት፣አንድነትና ነፃነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጀግንነት፣ኩራት ፣አስተዋይነት፣ታጋሽነት፣አትንኩኝ ባነትና አርቆ ተመልካችነት ተለንቅጠው የተዋሀዱት ኢትዮጵያዊ ኅብረተሰብ ነው”፡፡ተብሎ፡የተገለጸውን፡ስናነብብ፡እጅግ፡በጣም፡አዘንን። ከዚህ፡በላይ፡በተከበሩ፡ወንድማችን፡መኮንን፡ተድላ፡ተጽፎ፡የተላለፈልንን፡ስንመለከት፡በዋቢ ነት፡የተጠቀሰውዐማራ፣ ዐምሃራ ከተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ እንደሆነ የቋንቋው ሊቃው ንት ይናገራሉ”፡፡ የሚለው፡ዐረፍተ፡ነገር፡ቀልባችንን፡ስለ፡ሳበው፡መታረም፡እንዳልለበት፡ተገንዝበና ል።ምንጩንም፡ለዋቢነት፡እንዲረዳ፡መጠቀስ፡ነበረበትና፡ጸሐፊዎች፡እነማን፡እንደ፡ሆኑ፡መገለጽም፡ ነበረበት።በደፈናው፡”የቋንቋው፡ሊቃውንት፡ይናገራሉ”።ብሎ፡ማለፉ፡ለመከታተል፡አይረዳንምና። የዕብራይስጥም፡ፊደል፡ከግዕዝ፡የተወረሰና፡በዛ፡ያሉ፡የግዕዝ፡ቃላትን፡ወራሽ፡ስለ፡ሆነ፡”ዐም፡ሐራ”፡የተ ባሉት፡ቃላት፡መሠረታቸውም፡ይሁን፡ፍቻቸው፡ግዕዝ፡እንጂ፡ዕብራይስጥነት፡የልላቸውም።የሰው፡ ዘር፡መገኛና፡የግዕዝ፡ፊደል፡ባለቤት፡ኢትዮጵያ፡በነ፡ድንቅ፡ነሽ፡(ሉሲ)፡ታሪኳን፡እያስመሰከረች፡ባልለ ችበት፡ወቅት፡የቋንቋ፡አበዳሪ፡እንጂ፡ተበዳሪ፡አድርገን፡ስንገልጻት፡የውጭው፡ዓለም፡ጠልቀን፡ባለማሠ ባችን፡ይሳለቅብናል።ይንቀናል።ለባሕልና፡እሴቶቻችን፡የማናሥብ፡መሆናችንን፡አመልካች፡እንሆናለ ን።ስለዚህ፡ለወደ፡ፊቱ፡ጥንቃቄ፡እንድናደርግ፡በትሕተና፡እናሣሥባለን። ባጭሩ፡ከላይ፡የሠፈረው፡ቃል፡አባባል፡እንዲህ፡ነው።ታዋቂው፡ፕሮፌሰር፡ ጄምስ፡ሄንሪ፡ብርስቴድ፡”የግንዛቤ፡ንጋት”፡በተሰኘው፡መጽሐፋቸው፡ኢትዮጵያ፡ለዓለም፡ ለመጀመሪያ፡እውነትንና፡ሐሰትን፡ያሳወቀች፡አገር፡ናት።ይህም፡ለሃይማኖት፡መሠረት፡ ነው።ሥልጣኔን፣ባሕልን፣ሥነ፡ምግባርን፡አዳብራና፡ይዛ፡የተገኘች፡አገር፡ናት።ይህም፡ የግዮን፡ሥልጣኔ፡በመባል፡ይታወቃል።የሚገርመው፡ግን፡ጥንታዊው፡ባሕል፡እምነት፡

Upload: others

Post on 29-Oct-2019

44 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

1 | P a g e

አጣምመው፡የጻፉብን፡ታሪካችንን፡በተጠንቀቅ፡ካላነበብነው፡ስሕተቱን፡እናራባዋለን።

ነሐሴ፡፭፡ቀን፡፪ሺ፬፡ዓመተ፡ምሕረት። ገጽ፡፩-፲፤ “ኢትዮጵያ፡ታበጽሕ፡ዕድዊሃ፡ኀበ፡እግዚአብሔር።»»ኢትዮጵያ፡ዕጆቿን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ትዘረጋለች”።መዝሙር፡፷፰፡፴፮፡»»ቀጥሎም፡በሌላ፡በኩል፦”ወወሀብኮሙ፡ሲሳዮሙ፡ለሕዝበ፡ኢትዮጵያ፡»»አንተ፡ እግዚአብሔር፡ለኢትዮጵያ፡ሰዎችም፡ምግባቸውን፡ሠጠሃቸው”።መዝሙር፡፸፫፡፲፬፡»»*ገጽ፡፯፦በሃይማኖት፡ካባ፣የሚ ሠራ፡ደባ።በሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡በርሃኑ።መስከረም፡፳፻፡ዓመተ፡ምሕረት።

“ዐማራነት”። “(ከመኮንን ተድላ) ዐማራ፣ ዐምሃራ ከተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ እንደሆነ የቋንቋው ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡

ዐምሃራ ፣`ዐም` እና `ሃራ `ከተሰኙት ሁለት የዕብራይስጥ ቃሎች ጥምረት የተመሠረተ እንደሆነም ሊቃውንቶቹ ይናገራሉ፡፡ ዐም ማለት ሕዝብ ሲሆን ሃራ ማለት ደግሞ ነፃ ማለት ነው፡፡ ሁለቱ

ቃሎች ባንድነት ሲጣመሩ `ነፃ ሕዝብ` የሚለውን ትርጉም ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ዐማራነት

የኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና የሰረጸው ፣ፍቅር፣ወንድማማችነት፣አንድነትና ነፃነት፣ ፍትሐዊነት፣ጀግንነት፣ኩራት ፣አስተዋይነት፣ታጋሽነት፣አትንኩኝ ባነትና አርቆ ተመልካችነት ተለንቅጠው የተዋሀዱት ኢትዮጵያዊ ኅብረተሰብ ነው”፡፡ተብሎ፡የተገለጸውን፡ስናነብብ፡እጅግ፡በጣም፡አዘንን።

ከዚህ፡በላይ፡በተከበሩ፡ወንድማችን፡መኮንን፡ተድላ፡ተጽፎ፡የተላለፈልንን፡ስንመለከት፡በዋቢ

ነት፡የተጠቀሰው፡”ዐማራ፣ ዐምሃራ ከተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ እንደሆነ የቋንቋው ሊቃው ንት ይናገራሉ”፡፡ የሚለው፡ዐረፍተ፡ነገር፡ቀልባችንን፡ስለ፡ሳበው፡መታረም፡እንዳልለበት፡ተገንዝበና ል።ምንጩንም፡ለዋቢነት፡እንዲረዳ፡መጠቀስ፡ነበረበትና፡ጸሐፊዎች፡እነማን፡እንደ፡ሆኑ፡መገለጽም፡ነበረበት።በደፈናው፡”የቋንቋው፡ሊቃውንት፡ይናገራሉ”።ብሎ፡ማለፉ፡ለመከታተል፡አይረዳንምና።የዕብራይስጥም፡ፊደል፡ከግዕዝ፡የተወረሰና፡በዛ፡ያሉ፡የግዕዝ፡ቃላትን፡ወራሽ፡ስለ፡ሆነ፡”ዐም፡ሐራ”፡የተ ባሉት፡ቃላት፡መሠረታቸውም፡ይሁን፡ፍቻቸው፡ግዕዝ፡እንጂ፡ዕብራይስጥነት፡የልላቸውም።የሰው፡ዘር፡መገኛና፡የግዕዝ፡ፊደል፡ባለቤት፡ኢትዮጵያ፡በነ፡ድንቅ፡ነሽ፡(ሉሲ)፡ታሪኳን፡እያስመሰከረች፡ባልለ ችበት፡ወቅት፡የቋንቋ፡አበዳሪ፡እንጂ፡ተበዳሪ፡አድርገን፡ስንገልጻት፡የውጭው፡ዓለም፡ጠልቀን፡ባለማሠ ባችን፡ይሳለቅብናል።ይንቀናል።ለባሕልና፡እሴቶቻችን፡የማናሥብ፡መሆናችንን፡አመልካች፡እንሆናለ ን።ስለዚህ፡ለወደ፡ፊቱ፡ጥንቃቄ፡እንድናደርግ፡በትሕተና፡እናሣሥባለን።

“ባጭሩ፡ከላይ፡የሠፈረው፡ቃል፡አባባል፡እንዲህ፡ነው።ታዋቂው፡ፕሮፌሰር፡ጄምስ፡ሄንሪ፡ብርስቴድ፡”የግንዛቤ፡ንጋት”፡በተሰኘው፡መጽሐፋቸው፡ኢትዮጵያ፡ለዓለም፡ለመጀመሪያ፡እውነትንና፡ሐሰትን፡ያሳወቀች፡አገር፡ናት።ይህም፡ለሃይማኖት፡መሠረት፡ነው።ሥልጣኔን፣ባሕልን፣ሥነ፡ምግባርን፡አዳብራና፡ይዛ፡የተገኘች፡አገር፡ናት።ይህም፡የግዮን፡ሥልጣኔ፡በመባል፡ይታወቃል።የሚገርመው፡ግን፡ጥንታዊው፡ባሕል፡እምነት፡

2 | P a g e

ገጽ፡፪-፲፤

ሁሉ፡የፈለቀውና፡የተገኘው፡ከኢትዮጵያ፡ሆኖ፡ሳልለ፡አይሁዶች፡ሁሉንም፡እምነትና፡ባሕልን፡ከኢት ዮጵያ፡ቀድተው፡ልክ፡ከእነሱ፡የተገኘ፡አድርገውና፡አስመስለው፡ለዓለም፡አቀባይና፡የመጀመሪያዎቹ፡እነሱ፡እንደሆኑ፡አድርገው፡ይናገራሉ።ኢትዮጵያውያን፡መሆናቸው፡ቀርቶ።አይሁዶች፡ምንም፡የራሳ ቸው፡የሆነ፡ነገር፡ከቶ፡የላቸውም።በሙሉ፡ከኢትዮጵያ፡ነው፡የወሰዱት፡ሲሉ፡የኢትዮጵያን፡የሥልጣ ኔ፣የእምነትና፡የባሕል፡ሁሉ፡መጀመሪያ፡እንደሆነች፡በመጽሐፋቸው፡አረጋግጠዋል”።»»»*ገጽ፡፭-፮፡»

በሃይመኖት፡ካባ፣የሚሠራ፡ደባ።በሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡ብርሃኑ።መስከረም፡፳፻፡ዓመተ፡ምሕረት።ጸሐፊው፡አይሁዶችን፡ወቃሽ፡ያልሆኑ፣ፕሮፌሰር፡ጄምስ፡ብርስቴድ፡እራሳቸው፡አይሁድ፡ናቸው።

ሠንጠረዥ፡ሁለት፦ ከግዕዝ፡የተወሰደው፡የግሪክ፡ፊደል፡ቅጅ፤ THE ETHIOPIA ALPHABET 4250- B.C. // THE GREEK ALPHABET HAVE

BEEN TAKEN FROM THE ETHIOPIC 1100-900 B.C.*እንደ፡ላይኛው፡ገጽ፡፶፩፤»»» ማሳሰቢያ፦ ሌሎችን፡ሠንጠረዦች፡በግዜ፡እጥረት፡በገለጻ፡ብቻ፡እንጂ፡እንደ፡ሠንጠረጅ፡አንድ፡አልቀዳናቸውም።

ገጽ፡፶>>፪*በሃይማኖት፡ካባ፣የሚሠራ፡ደባ።በሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡ብርሃኑ።መስከረም፡፳፻፡ዓ.ም.

3 | P a g e

ገጽ፡፫-፲፤

ሠንጠረዥ፡ሦስት፦ ከግዕዝ፡የተገኘው፡የላቲን፡ፊደል፤ THE ETHIOPIAN, 4200 B.C, // THE LATIN, 507 B.C. FROM THE ETHIOPIC ALPHABET TO THE LATIN ALPHABET. *እንደ፡ላይኛው፡ገጽ፡፶፪፤»»»

“በተለምዶ፡የዐረብኛ፡አኅዞች፡ተብለው፡የሚነገሩት፡አሥር፡የቁጥር፡መደቦች፡በቀጥታ፡ከግ ዕዝ፡ለመቀዳታቸው፡አሁንም፡መልካቸውንና፡ቅርፃቸውን፡ይመለከቷል”።*እንደ፡ላይኛው፡ገጽ፡፶፫፤»»»

*ገጽ፡፵፰፦ኢትዮጵያ፡የዓለሙ፡መፋረጃ፡በንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ።

4 | P a g e

ገጽ፡፬-፲፤

*ገጽ፡፹፰፦ SIDUR TEHILLAS HASHEM NUSACH HA-ARI ZAL

ከይሁዳውያን፡የዬዕለቱ፡ጸሎት፡ማከናወኛ፡መጽሐፍ።

*ገጽ፡፵፯፦ኢትዮጵያ፡የዓለሙ፡መፋረጃ።በንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ።

5 | P a g e

ገጽ፡፭-፲፤

*ገጽ፡፹፰፦ SIDUR TEHILLAS HASHEM NUSACH HA-ARI ZAL

በጻፏቸው፡በርካታ፡መጻሕፍት፡እንደ፡ተረዳነው፡ሁሉ፡ሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡ ብርሃኑ፡ስለ፡መሠረተ፡ትምህርት፡አሰጣጣችን፡ከፍፍ፡ያለ፡የማሻሻያ፡ፍላጐት፡ነበራቸው።ይመኟቸው፡ከነበሩት፡ማሳሰቢያዎቻቸው፡ጥቂቶችን፡እንሆ!፦

”አውቀን፡በድፍረት፣ሳናውቅ፡በስሕተት፡ከሆነም፡ግንዛቤ፡እንድንወስድበት፡እጅ ግ፡በጠና፡ላስገነዝብ፡እወዳለሁ።ያልሉኝም፡አቤቱታዎች፡በሚከተሉት፡ቅርሶቻችን፡ላይ፡ያተኩራል።

አንደኛ፦ ይህ፡የሰው፡አፍ፡መፍቻ፡ቋንቋ፡የሆነው፡ግዕዝ፡በሥርዓተ፡ትምህርቱ፡ ገብቶ፡እንዲሠጥ። ሁለተኛ፦ የግዮን፡ወይም፡የዓባይ፡ስም፡ተለውጦ፡”ናይል”፡እንዳይባል። ሦስተኛ፦ አበሻና፡አቢሲኒያ፡የሚሏቸው፡መጠሪያዎች፡ኢትዮጵያ፡የሚለውን፡

ስምና፡መታወቂያ፡ማደብዘዢያና፡ማደናገሪያ፡ስለሆኑ፡እንዳይባሉ፡ ማድረግ።

አራተኛ፦ እንዲሁም፡የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ቋንቋ፡የስሙ፡አጠራር፡ከአማርኛ፡ወደ፡ ኢትዮጵያውኛ፡እንዲለወጥ፡ናቸው። የአማርኛን፡ስም፡ለመለወጥ፡ኢትዮጵያውኛ፡እንዲባል፡ያሳሰቡትንም፡ከሚጋሯቸ

ው፡ውስጥ፡የተከበሩ፡ንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ፡ኢትዮጵያዊኛ።ሊቁ፡አባ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡ኃይሉ፡ኢትዮጵያዊኛ።አቶ፡ስለሺነህ፡ገላነህ፡ለኅትመት፡ከተዘጋጀ፡የግል፡

መዝገብ:ኢትዮጵያኛ።ቢባልስ፡እያሉ፡በሐሣቡ፡የመተባበራቸውን፡ቅን፡አመለካከት፡ለግሠ ዋል።

*ገጽ፡VIII:-መጽሐፈ፡ሰዋስው።ከአለቃ፡ታየ፡ገብረ፡ማርያም፡ተጽፎ፡በዘመንፈስ፡ቅዱስ፡አብርሃ፡ትጋት፡በ፲፱፻፶፰፡ዓ.ም.ታተመ።

ባለ፡ቀዩ፡መሥመር፡ኩሽ፡ማለት፡ነው።

6 | P a g e

ገጽ፡፮-፲፤

*ገጽ፡፪፻፳፫፦ክፍል፡ሦስት፣ባልንጀራዬ፡የምለው፡ፍጡር፡ማነው?።በንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ።

*ገጽ፡፬፻፲፪፦ኢትዮጵያ፡የዓለሙ፡መፋረጃ።በንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ።

7 | P a g e

ገጽ፡፯-፲፤

*From Practical Japanese-English Dictionary. በአቶ፡ስለሺነህ፡ገላነህ፡ለኅትመት፡ከተዘጋጀ፡የግል፡መዝገብ።

ይኸ፡ጃፓንኛ፡ደግሞ፡ሂራጋናና፡ካታጋና፡የሚሏቸው፡ከቻይና፡የወረሱትን፡ካንጂ፡ፊደሎች፡ድምፅ፡አናባቢ፡ሲሆኑ፡አቶ፡ስለሺነህ፡ገላነህ፡ከኢትዮጵያ፡የተወረሱ፡ናቸው፡ብለው፡ያምናሉ።ሮማጂ፡ያሉት፡ግን፡የላቲን፡ፊደል፡ማለታቸው፡ነው።አጠቃቀማቸውም፡ሂራጋና፡ለውስጥ፡ሀገራዊ፡ስሞች፡ወይም፡ቁሳቁሶች፣ካታጋናን፡ለውጭ፡አገር፡ስሞች፡ወይም፡ቁሳቁሶች፡መጠሪያ፡ይጠቀሙባቸዋል።ሮማጅውን፡ግን፡የውጭ፡አገር፡ዜጋዎች፡ጃፓንኛ፡ያለ፡አስተማሪ፡አንብበው፡ማጥናት፡እንዲችሉ፡የተዘጋጀ፡ነው።ኢትዮጵያኛ፡ፊደሎቻችን፡እንዴትና፡መቸ፡እንደ፡ተወረሱ፡ግን፡ለታሪክ፡ተመራማሪዎች፡አደራ፡ብለዋ ል።አንድ፡አመላካች፡ግን፡ከአቶ፡ታደሰ፡ገብረኪዳን፡ *ገጽ፡፪፦”የኢትዮጵያ፡ቀን፡አቆጣጠር፡(ካላንደ ር)፡ታርክ፡ባጭሩ”፡አቅርበዋል። “የሰው፡ልጅ፡ህልውናው፡የተረጋገጠው፡የዛሬ፡፩፻፷፡ሺህ፡(160000)፡ዓመታት፡(ዓመት)፡ገደማ፡በኛ፡የኦሞ፡ሸለቆ፡የኖረችው፡ቅድመ፡አያታችን፡(ቅመአያታችን)፡በሕይወት፡ቆይታልንና፡ዘር፡አፍርታ፡በማለፏ፡ነው።ከሷ፡በፊት፡የኖሩት፡ሴቶች፡የወለዷቸው፡ሴቶች፡ዝርያቸው፡በምድር፡ላይ፡አይገኝም።አሁን፡በመላው፡ዓለም፡የምንገኘው፡ከ፮፡(6)፡ቢሊዮን፡በላይ፡ሴቶችና፡ወንዶች፡አፍርታ፡ባታልፍ፡ኖሮ፡ዛሬ፡በዓለም፡ላይ፡የሰው፡ዘር፡የሚባል፡ፍጡር፡አይኖርም፡ነበር”።

http://www.assimba.org/Articles/yeEthKalendar Tarik.pdf. http://www.youtube.com/watch?v=mm-4cvm41dQ&feature=player_embedded እነዚህ፡ማስረጃዎችን፡ስንመረምር፡አቶ፡ስለሺነህ፡የጃፓንኛ፡ሂራጋናና፡ካታጋና፡የሚሏቸው፡ከላይ፡እንድተጠቀሰው፡ከኢትዮጵያ፡ለመሄዳቸው፡አማላካቾች፡ናቸው።ምናልባትም፡ሊቀ፡ሊቃው ንት፡ፍቅሬ፡ቶሎሳ፡ያስረዱት፡በስማቸው፡እስያ፡ብለው፡ሰይመው፡በመንገሥ፡ይገዙ፡የነበሩት፡ዐፄ፡

8 | P a g e

ገጽ፡፰-፲፤ እስያኤል፣ወታደሮቻቸውና፡አቶ፡ታደሰ፡ገብረኪዳን፡የጠቀሷቸው፡ባለ፡ታሪኮች፡ሳይወድስዷቸው፡እንዳልቀሩ፡ያስገምታል። ወገኖች፡ሆይ! ሰፊዋ፡ሀገራችን፡ተቆራርጣ፣ተቆራርጣ፡ይህችን፡ለይስሙላ፡የቀረች፡ኢትዮጵያችንን፡ለመከላከ ል፡ቆርጠን፡ካልተነሣን፦ባሕላችን፣ቋንቋችን፣ሥነ፡ጽሑፋችንና፡ሥነ፡ምግባራችን፡የምንለውን፡ጥራት፡ባልለው፡ተግባር፡ኢትዮጵያውያን፡በሚያስሰኝ፡እያሳየነው፡አይደለም።አነጋገራችንን፡ጉራማይሌ፡የው ጭ፡አገር፡ቋንቋዎችን፡እየዘነቅነው/እየቀየጥነው፡ነው።አጻጻፋችን፡ነብባር፡ሥርዓተ፡ነጥቦችን፡የሳተ፡የእግልጣሩን፡አጻጻፍ፡በመኮረጅ፡ላይ፡ነን።የኢትዮጵያኛችንን፡ፊደል፡ትኩረት፡ባለ፡መስጠት፡በላቲኑ፡ፊደል፡መጽጻፉ፡የፊደላችንን፡ማንነት፡ታርካዊ፡ቀደምትነትና፡በሂደት፡የተሻሻለ፡እንዳልሆነ፡ያስገምታ ል።የፈረንጅ፡ጸሐፊ፡ስለ፡ሀገራችን፡ቆንጽሎ፡ማለት፡በደንብ፡ሳይረድዳ፡የሚጽፋቸውን፡ዋቢ፡በማድረ ግ፡ሳያጥጣሩ፡ስሕተቱን፡እንዲዛመት፡እየተደረጋ፡መሆኑን፡አለ፡ማሠብ፣»»ለምሳሌ፦አሁን፡”ዐምሐራ”፡”ከዕብራይስጥ”፡መጥጣ፡እንደ፡ተባለው።አያሌዎችና፡ብቁ፡ሊቀ፡ሊቃውንት፡ስላሉን፡እነሱን፡ከመጠዬ ቅ፡ፈረንጅ፡መጠየቅን፡ቅድሚያ፡ሰጭ፡ሆነን፡አመኔታ፡እንዲኖረን፡ማድረጋችንና፡ለምሁር፡ወገኖቻችን፡ምሥጢሮቻችንን፡ከማካፈል፡ይልቅ፡ለውጭ፡ዜጋዎች፡ለማካፈል፡መውደዳችን፡”የቆጡን፡አወርድ፡ብላ፡የብብቷን፡ጣለች፡ያሰኜናል”።ስሞቻችንን፡እያወላገዱ፡የሚጠሩን፡ማንነታችንን፡ለመፈታተን፡ነው።ታሪካችን፡በተወላጆቹ፡ካልተጻፈ፡ትክክለኛ፡ስሞችንና፡አስከብባሪ፡እሴቶቻችንን፡እናጣለን።ከሊቀ፡ሊቃውንት፡ወገኖቻችን፡እንደ፡ተገልለጸልን፦»»አበሽ፣አበሻ፣ሐበሽ፣ሓበሻ፣አቢሲንያ፣ኩሽ፣ብሉ፡ናይል፣ጃንደረባው፣ሌሎች፡ሌሎችንም፡እያሉ፡የሚጠሩን፡ማንነታችን፡እንዳይታወቅና፡ንቀት፡ነው።ከግዜ፡ብዛትም፡የኢትዮጵያውያንነት፡መታወቂያወቻችንን፡እንዳንገነዘብ፡ለማድረግ፡ነው።ስድብ፡ነው።ጥቁር፡ነጭን፡ለማገልገል፡የተፈጠረና፡የማያሥብ፡ነው።ብለው፡ስለሚገምቱ፤እኛን፡ፊታቸው፡የተቃጠለ፣ጥቁር፣(ኩሽ)፡ስልብ፡……፡በማለት፡ዐቅደው፡ዕውነተኛው፡ኢትዮጵያዊ፡ስማችን፡ባሕሉን፡ይዞ፡እንድይቀጥል፡ስለሆነ፡ተንኮላቸው፡ይግባን።በሌሎች፡ዓለማት፡አካለ፡ስንኩል፡ሆነው፡በተሽከርካሪ፡ወንበር፡እዬተጓዙ፡አገር፡ይገዙ፡እንደ፡ነብበሩና፡አመሪካ፡አንደኛዋ፡እንደ፡ነብበረች፡ከታሪክ፡አንብበናል።ዕውነታው፡ይህ፡ሆኖ፡ሳልለ፣በኢትዮጵያ፡ባለ፡ታሪኮቻችን፡በቅጽል፡ስማቸው፡አጠራር፡ቀደምትነት፡ያልለውን፡”ጃንደረባ”፡ብለው፡የሚጠሩት፡የተከበረው፡የንግሥት፡ኅንደኬ፡

በጅሮንድና፡የክርስትና፡ሃይማኖትን፡ተቀብሎ፡የዓለማት፡እምነት፡መርህ፡የነበረው፡ስም፡ባኮስ፡ነው።

ግንዛቤ፡በማድረግም፡የዚህ፡የዚህማ፡በአሮጳውያን፡ቅኝ፡ግዛት፡ሥር፡ከነበሩ፡አግሮች፡ሕዝቦች፡በምን፡እንለያልለን?።መልያና፡መታወቂያች ን፡ቋንቋውችንና፡የሱም፡መግለጫ፡የሆኑት፡ፊደሎቻችን፡ናቸው።ዛሬ፡ስማችንና፡ሃይማኖታችንን፡ብቻ፡ሳይሆን፡የለወጥነው፡ፈደሎቻችንንም፡ለውጠናል።”እንደ፡ምሳሌ፡የሚጠቀሱት፡ወገኖቻችን፡ቢኖሩ፡በአሜሪካ፡ያሉት፡አፍሪቃን፡አሜሪካን፡ናቸው።እኒህን፡ወገኖቻችንን፡ከአፍሪቃ፡አፈናቅለው፡አሜሪካ፡ሲያመጧቸው፡የማንነታቸው፡ማጥፊያ፡አድርገው፡የወሰዱት፡በመጀመሪያ፡ስማቸውን፡መቀየርና፡መለወጥ፡ነበር።ከዚያም፡የመጡበትን፡ቦታና፡አድራሻ፡ሳይነግሯቸው፡አፍነው፡እንደ፡እንስሳ፡ሲሸጧቸው፡ሲለውጧቸው፡መኖሩ፡ነው።አሁን፡ትልቁ፡የእነሱ፡የእግር፡እሳት፡የሆነው፡ከየትኛው፡የአፍሪቃ፡አገር፣ከየትኛው፡ቋንቋ፡ተናጋሪ፡ክፍል፡መወለዳቸውን፡ያለማወቁ፡ነው።በትክክል፡ቢያውቁት፡ኖሮ፡ወላጆቻቸውን፡ወደ፡መጡበት፡የአኅጉር፡ክፍል፡በመሄድ፡ቋንቋቸውን፡አጥንተው፡እሱም፡ቢኖር፡ወደዚያም፡ሄደው፡ለመኖር፡የሚመኙት፡ወገኖቻችን፡ብዛት፡ቁጥር፡ሥፍር፡የለውም።በኛ፡እንኳን፡ያላቸው፡መንፈሳዊ፡ቅናት፡በቋንቋ፡የሚገልጹት፡አይደለም።የራሳችን፡ፊደል።የራሳችን፡ቋንቋ።የራሳችን፡ምግብ፡አሠራር፣አለባበስና፡ወግ፡ማዕርግ፡ምን፡ያህል፡ታላቅ፡ፀጋና፡በርከት፡መሆኑን፡የምንረዳውና፡የምንገነዘበው፡ከእነሱ፡ጋር፡ቁጭ፡ብለን፡ስንወያይ፡ነው።ሳናውቀው፡በጣታችን፡ላይ፡ያለውን፡የወርቅ፡ቀለበት፡ከጭቃ፡ላይ፡እንደ፡ጣልነው፡ያስቆጥራል።

9 | P a g e

ገጽ፡፱-፲፤ ወደ፡ጥቁር፡ወገኖቻችን፡መለስ፡ስንል፡የነገሯቸውና፡ያስጠኗቸው፡ጥቁር፡የነጭ፡አገልጋይ፡መሆኑንና፡ከነጭ፡በታች፡ሆኖ፡መፈጠሩን፡ነው።ከዚህም፡በላይ፡ታሪክ፡እንደ፡ሌላቸው፡አስጠንተዋቸዋል።እን ኳን፡ታሪክ፡የሰው፡ነፍስ፡እንኳን፡እንደ፡ሌላቸው፡እየነገሩ፡ነው፡የገዟቸው።እድሜ፡ለወላጆቻችን፡ደማ ቸውን፡አፍስሰውና፡አጥንታቸውን፡ከስክሰው፡ሁሉን፡ነገር፡ጠብቀው፡በክብር፡ለኛ፡አስረክበውናል።እኛስ?።እኛማ፡እኛ፡እንጂ፡ሥራቸውንና፡ድካማቸውን፡አይጥ፡የበላው፡ልቃቂት፡አላደረግነውምን???።ይሁን፡እንጂ፡በወጣቱ፡ትውልድ፡ተስፋ፡እናደርጋለን።ወደ፡ማንነታችው፡ይመለሳሉ።ማንነታቸውን፡ያውቃሉና፡ያከብራሉ፡ብለን፡ከፍተኛ፡ተስፋ፡እናደርጋለን።በዚህም፡እንጽናናለን”።*ገጽ፡፴፫-፴፬፤በሃይማኖት፡ካባ፣የሚሠራ፡ደባ።በሊቀ፡ሊቃውንት፡ለይኩን፡ብርሃኑ።

ከላይ፡እንደ፡ተገለጸው፡ባርነት፡ምን፡ያህል፡አስከፊ፡መሆኑን፡ለመረዳት፡የተሞከረው፡በጽሑ ፍ፡ሲሆን፤በምሥል፡ቢታይ፡ሁኔታውን፡አክብዶ፡ለወጣቱ፡ትውልድ፡ያሳያል፡ብለን፡ስላመንና፡ነጭ፡ብሎ፡እራሱን፡በሰየመው፡ዘረኛም፡እንደሚታረሱ፡በሬዎች፡በቀንበር፡ማነቂያ፡ባርነት፡ይካሄድበት፡እንደ፡ነበረ፡ለማመልከት፡ከኅዋ፡ሰሌዳ፡አውታሩ፡ፈልገን፡ያገኘነውን፡ለማስረጃ፡እንሆ!፡ከዚህ፡በታች፡ያልሉትን፡ተመልከቱ።በተጨማሪም፡ወደ፡ዓረብ፡አገር፡ለሥራ፡በሚጐርፉት፡እህቶቻን፡ላይ፡ዓረብ፡የቤት፡እመቤቶቻቸው፡”በገንዘቤ፡የገዛሁሽ፡አገልጋዬ፡ነሽና”፡………፡እየተባሉና፡ያለፈቃዳቸው፡በመደፈ ርም፣በፈላ፡ውኃ፡በመገሸርም፡እንደ፡ተሠቃዩ፡በዜናና፡ተንቀሳቃሽ፡ምሥል፡ያዬነው፡ስለሆነ፡በምናቀር ብላችሁ፡ምሥል፡ማስረጃ፡ሥቃያቸውን፡እንደረዳ፡ያደርጋልና፡ሕይወታቸውን፡ያጠፉትንም፡በጸሎተ፡ኅሊናችን፡እናሥባቸው።

10 | P a g e

ገጽ፡፲-፲፤

ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ያልለን፡ትሥሥር፡ብርቱ፡ሆኖ፡እንጂ፣እስታሁን፡እንዳልነበርን፡ሁነን፡ነበርነ።አሁን፡በእግዚአብሔር፡የልለሹ፡ፍልስፍና፡አስተዳደር፡የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ተሠቃዬ፡እንጂ፤ሃያ፡ዐራት፡ሰዓታት፡የእግዚአብሔር፡ስም፡የሚጠራባትና፡ጸሎቷ፡የሚሰምርላት፡ሀገር፡ኢትዮጵያ፡ብቻ፡ናት፡ብንል፡የምንሳሳት፡አይመስለንም።»»»እንዴት፡አደራችሁ?፦ እግዚአብሔር፡ይመሥገን።እንዴት፡ዋላችሁ?፦ እግዚአብሔር፡ይመሥገን።ከአሁን፡በኋላ፡ምን፡ትሠራላችሁ?፡- እግዚአብሔር፡ያውቃል፣የእግዚአብሔር፡ፈቃዱ፡ከሆነ፡ድንጋይ፡እንፈልጣልለን፣ጠላቶች፡እንዳያጠቁን፡እንከላከላለን።ነገ፡ምን፡ለማድረግ፡ዐቅዳችኋል?፦ እግዚአብሔር፡ካለ፣ከጓደኞቻችን፡ጋራ፡የተለምነውን፡እንደፍናልለን።………፡በመሳሰሉ”ለጥያቄዎች፡ሁልሉ፡መልስ፡እግዚአብሔር፡ከአፍ፡አይለይም።ስለዚህ፡ልቦና፡ሰጥቶን፡ከምሁሮቻችን፡ጋራ፡መልካም፡ቀበት፡አድርገን፡በበለጠ፡ለማሻሻል፣ለመፋቀር፣ለመረዳዳትና፡ለመተባ በር፡ያብቃን።አሜን።

ለዋቢነት፡ከጠቀስናቸው፡መጻሕፍት፡መግዛት፡ለሚፈልጉ፦

፩ኛ፦ ሊቀ፡ምሁር፡ሐጎስ፡ዓለማዬሁ፤ (፩-በነፃ፡ኑር። ፪-በሃይማኖት፡ካባ፣የሚሠራ፡ደባ።) 7102 Sycamore Avenue Takoma Park, Maryland 20912 Telephone (301) 270-1739 ፪ኛ፦ ንቡረ፡ዕድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ፤ [email protected] ፫ኛ፦ ሊቀ፡ሊቃውንት፡ፍቅሬ፡ቶሎሳ፤ [email protected]

ኢትዮጵያ፡በክብረ፡ነፃነቷ፡ለዘላለም፡ትኑር።አሜን።

ዜናማርቆስ፡መርሐ፣ሰሜን፡አመሪካ፤

እ፡ጦማር፦ [email protected]

11 | P a g e