77 - midroc · 2017-07-20 · 3 midroc newsletter volume 14, issue # 77 may — june 2014 addis...

12
1 Addis Ababa, Ethiopia Volume 14, Issue No. 77 May — June 2014 u¨<eØ Ñ뉋” Inside Pages 4 4 4 4 4 4 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO From the Chairman File In my country Ethiopia, I still plan to involve heavily and increase my investment in various sectors of the economy to contribute to a sustainable economic and social development. Our commitment and interventions in the different sectors of the economy are put in place to substantially bring about the growth of our country. ‹ያለምነውን ዕቅድ ከግብ የማድረስ አቅም እንዳለን................2 “We Would Like to Achieve Excellence ....................3 ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሬጂ ቀበሌ ለአካባቢው...................4 የቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ....................4 የመቻሬ ኮርፖሬት የሕፃናት ማቆያ ማዕከል ተመርቆ............4 ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ................................5 ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን ላይ ተካፈለ...............10 ከሠራተኞች ማኅደር...........................................................10 ........................................................11 ጠቅላላ ዕውቀት ................................................................11 mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR .............................12 4 4 4 4 4 Dr. Arega Yirdaw Receives Doctorate Degree in Education Dr. Arega Yirdaw, CEO MIDROC Ethiopia and President of Unity University received Doctorate Degree (EdD) in Education from Fielding Graduate University School of Educational Leadership and Change in USA, on July 19, 2014. The award is given in the presence of his family, representative from the CEO office and Ato Abennet G/Meskel, representing Sheik Mohammed Husein Ali Al-Amoudi and himself. Sheik Mohammed Husein Ali Al-Amoudi

Upload: others

Post on 03-Feb-2020

55 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

1Addis Ababa, Ethiopia

Volume 14, Issue No. 77 May — June 2014

u¨<eØ Ñ뉋”

Inside Pages

4

4

4

4

4

4

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

77

From the Chairman File

In my country Ethiopia, I still plan to involve heavily and increase my investment in various sectors of the economy to contribute to a sustainable economic and social development.

Our commitment and interventions in the different sectors of the economy are put in place to substantially bring about the growth of our country.

‹ያለምነውን ዕቅድ ከግብ የማድረስ አቅም እንዳለን................2 “We Would Like to Achieve Excellence ....................3ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሬጂ ቀበሌ ለአካባቢው...................4የቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ....................4የመቻሬ ኮርፖሬት የሕፃናት ማቆያ ማዕከል ተመርቆ............4 ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ................................5

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን ላይ ተካፈለ...............10ከሠራተኞች ማኅደር...........................................................10 ........................................................11ጠቅላላ ዕውቀት ................................................................11mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR .............................12

4

4

4

4

4

Dr. Arega Yirdaw Receives Doctorate Degree in Education

Dr. Arega Yirdaw, CEO MIDROC Ethiopia and President of Unity University received Doctorate Degree (EdD) in Education from Fielding Graduate University School of Educational Leadership and Change in USA, on July 19, 2014.

The award is given in the presence of his family, representative from the CEO office and Ato Abennet G/Meskel, representing Sheik Mohammed Husein Ali Al-Amoudi and himself.

Sheik Mohammed Husein Ali Al-Amoudi

Page 2: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

2

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

‹‹ያለምነውን ዕቅድ ከግብ የማድረስ አቅም እንዳለን እናውቃለን››የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን

• ‹‹ከግምታዊነት ይልቅ በመረጃ የተደገፈን ውይይት እናበረታታለን››ዶ/ር አረጋ ይርዳው

‹‹አብዝተን የማቀድና ዕቅዳችንን ከግብ ለማድረስ አቅም እንዳለን እናውቃለን›› ሲሉ የኢፌዴሪ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን አስገነዘቡ፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ‹‹አባይ ለልማት›› በሚል ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን የነፃነትና የሉዓላዊነት ምሣሌ የሆነችው ኢትዮጵያ በድህነት፣ በረሀብና በጉስቁልና ያሳለፈችው ጊዜ ላይመለስ ታሪክ ያደረገችበት ደረጃ ላይ ደርሳለች ብለዋል፡፡

አፈ ጉባዔው አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዓውደ ጥናት አገሪቱ ለተያያዘችው የልማት እርምጃ ታላቅ ድርሻ እንደሚያበረክትና ምሁራን ይህንን መሰሉን ዓውደ ጥናት በመጠቀም ተጨባጭ መረጃ በማስተላለፍ ለልማታችን ያለውን አስተዋፅኦ ማሳወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎቻችን ከግላዊ አመለካከትና ከግምታዊነት ይልቅ ዕውነታን መሠረት ባደረገ ተጨባጭ መረጃ ላይ በመመርኮዝ መወያየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ዩኒቨርሲቲው በዓመቱ መጀመሪያ ይህንን መሰሉን አገራዊ ጉዳይ ያማከለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዓውደ ጥናት እንደሚያዘጋጅ በዕቅድ መያዙን ጠቁመው በዚህ ምክንያት ሁሉም የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያ ሠራተኞች በዓውደ ጥናቱ ላይ ሊሳተፉ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

በዓውደ ጥናቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ፕሬስ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ‹‹የሰሜን አፍሪካ የውሃ ፖለቲካ ለአህጉሩ ያለው እንደምታ››፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት ኢንጂነርና የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ይልማ ስለሺ ‹‹የአባይ ውሀና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአህጉራዊ ትብብር ያለው ጠቀሜታ››፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሔራዊ የሕዝብ ተሳትፎ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ለማ ‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደትና ጠቀሜታው››፤ እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሔራዊ የህዝብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሰርፀድንግል ‹‹ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የዲፕሎማሲ ጥረት›› በሚል ጥናታዊ ፅሁፎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀረቡት ጽሁፎችም ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በዓውደ ጥናቱ ማጠናቀቂያ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ዩኒቨርሲቲው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ በሰኔ ወር እንደሚያከናውን ገልፀው በቀጣዩ ወር የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች የሕዳሴው ግድብ ግንባታ በሚከናወንበት ቦታ በመገኘት ጉብኝት እንደሚያካሂዱ አመልክተዋል፡፡

ከአውደ ጥናቱ መጠናቀቅ በኋላ ተሳታፊዎቹ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆኑትን ሰሚት ፓርትነርስ ኃ.የተ.የግ.ማ. እና ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ. ኩባንያዎችን የሥራ ሂደት ተዘዋውረው ጐብኝተዋል፡፡

ዓውደ ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት

ከዓውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በከፊል

Page 3: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

3

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

“We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality” Dr. Arega Yirdaw • Unity Convenes 13th Annual Multidisciplinary Research Conference

“We have a very serious problem regarding the quality of education in this country. We would like to work with public and private universities to overcome the problem. We would like to achieve excellence when it comes to quality”. This statement was made by Dr. Arega Yirdaw, President of Unity University and MIDROC Ethiopia (CEO) at the closing of the 13th Annual Multidisciplinary Research Conference, which was held at Mechare Meda Conference Hall, on June 21, 2014.

Speaking after he handed out Certificates to the presenters of research papers at the Conference, Dr. Arega noted that there is significant expansion of education in Ethiopia, which is good and needed but, it must be done, without compromising quality of education.

He further underlined, “Next year, we need to have papers on quality of education in Ethiopia”. The President made note of the good number of paper presenters from Arba Minch University and awarded the University a token prize of Birr 10,000 to contribute to the efforts of its Research Department.

Dr. Arega pointed out that the University is grateful to the paper presenters from public and private higher education institutions in the country. He underlined, “Research, as we are all aware, is an academic exercise of collecting and analyzing valid and reliable information with the aim of acquiring new, additional knowledge and experience”.

In this connection, Dr. Arega reiterated that human civilization in all walks of life is the result of “continuous inquiry and investigation by dedicated scholars and researchers like yourselves. Research, therefore, has, is, and will take centre stage in the long journey of human civilization”. The University President went on to note that research is not meant only “to know and possess what others have done before, but also to add one’s own new findings and discoveries to the already existing body of knowledge. That is how the world had reached where it is now”.

Dr. Arega dwelt at length on the multi-faceted benefits of research, among which he underlined, “Research is an important tool that drives scholars to undertake systematic scientific studies and investigations in their respective disciplines that would contribute to growth and development in all spheres of human activities. This requires the interest, dedication and sacrifice of academic leaders and instructors in higher education institutions to integrate teaching and learning exercise with the research activities in our respective institutions”.

In his welcome address Prof. Desta Hamito, Academic Vice President, Unity University, briefly noted about the history and growth of higher education in Ethiopia and subsequently gave

a brief account of the academic activities at Unity University. Further, Prof. Desta pointed out that Unity University had set a new educational direction or strategy in order to promote its academic activities. Accordingly, he underlined, “The degree offering would be limited to three fields, namely: Management and Leadership, Engineering and Technology and Health Sciences; and it would offer General Education in order to contribute its share to the national endeavour to improve the capacity of students who aspire to join universities”.

The Academic Vice President made note of the efforts being made by Unity University with a view to enhancing its endeavours towards contributing its modest share to improving the quality of education. To this end, Prof. Desta recalled the recent signing of Memorandum of Understanding with Addis Addis Ababa University. He underlined, “Unity University believes such collaborative efforts would promote the teaching-learning process, on one hand, and research undertakings, on the other. Similar other collaborative efforts are also underway”.

Further, Prof. Desta went into the research undertaking efforts at Unity University, whereby he made note of the establishment of the Research and Publications Office (RPO). According to Prof. Desta, the RPO is entrusted with, among other things, the task of preparing policy guidelines on research and ensuring their implementation. As regards other research-related activity of the University, Prof. Desta underscored the publication and dissemination of research outputs. In this connection, the Academic Vice President stated that the University had two major publications run under the auspices of the RPO, namely, Ethiopian Journal of Business & Development, and the Proceedings of the Annual Multidisciplinary Research Conferences.

Dr. Seletene Seyoum, Director, Research and Publications, after making the necessary introductions about the proceedings of the conference, noted that Unity University started convening the Annual Multidisciplinary Research Conference since 2002 and has convened 13 consecutive such conferences to date. The major themes of this latest Conference include Agriculture, Economic Growth, Education, Tourism, Health and Sanitation, and other cross-cutting issues. A total of 20 papers were presented. The researchers came from Addis Ababa University, Unity University, Haramaya University, Axum University, Arba Minch University, Ethiopian Civil Service University, Metu College of Teachers’ Education, Wolayita University and Tigray Agricultural Research Institute. The vast majority, that is, 30% of the presentations, were from Arba Minch University. In attendance were invited guests as well as academic and administrative staff of Unity University.

While attending the conference

Page 4: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

4

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የመቻሬ ኮርፖሬት የሕፃናት ማቆያ ማዕከል ተመርቆ ተከፈተ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ዋና መሥሪያ ቤት መቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር ‹‹የመቻሬ የሕፃናት ማቆያ ማዕከል›› ግንቦት 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ተመርቆ ለሠራተኞች ነፃ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ሕፃናት ማቆያውን መርቀው የከፈቱት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው የኩባንያዎቹ

ሠራተኞች ሕፃናት ልጆቻቸውን ወደ ማቆያው በመውሰድ ሥራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩና በአቅራቢያ ሆነው እንዲንከባከቡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ለሕፃናቱ ደህንነት መጠበቅ ማቆያው ከሚያደርገው እንክብካቤ በተጨማሪ ወላጆችም የላቀ ድርሻ እንደሚኖራቸው አሳስበው በድንገተኛ ሁኔታ ለሚከሰት ህመም የመጀመሪያ ህክምናና የአምቡላንስ አገልግሎት በመቻሬ ክሊኒክ ርዳታ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡ሕፃናት ማቆያው የማረፊያ፣ የመጫወቻ፣ የመመገቢያ፣ የመኝታና የመፀዳጃ አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ ያለው ሲሆን፤ የሕፃናቶቹ ወላጆች በተያዘላቸው ፕሮግራም መሠረት እንክብካቤ ያደርጋሉ፡፡በምረቃው ወቅት የቴክኖሎጂ ግሩፑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሕፃናት ማቆያውን ጐብኝተዋል፡፡

የቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ ዓመት ተከበረ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ ዓመት በዓል ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር የስብሰባ ማዕከል ተከበረ።

በዓሉን በማስመልከት የተዘጋጀውን ኬክ የቆረሱትና ንግግር ያደረጉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ቢሮው ሲመሠረት የነበረውን ሁኔታ በስፋት የዳሰሱ ሲሆን፤ ላለፉት 14 ዓመታት ኩባንያዎቹን አሁን ያሉበት የዕድገት ደረጃ ላይ ለማድረስና ቁጥራቸውን ወደ 20 ለማሳደግ የተካሄደውን ከባድ ውጣ ውረድ ዘርዝረዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ቁጥራቸው አምስት የነበሩት ኩባንያዎች አድገውና ተስፋፍተው ከስድስት ሺህ በላይ ለሆኑ

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሬጂ ቀበሌ ለአካባቢው ሕብረተሰብ መገልገያ ለሚያሠራው ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ

ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሬጂ ቀበሌ ለአካባቢው ሕብረተሰብ መገልገያ የሚውል ባለአንድ ፎቅ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ለማሠራት በዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኦ እና የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ዋና ሥራ አስኪያጅ መሠረት ድንጋይ ተጣለ፡፡ይህ የተከናወነው የአካባቢው ሕብረተሰብ፣ የአካባቢው የአመራር አካላት፣ የለገደንቢና የሳካሮ ወርቅ ማዕድን የሥራ ባልደረቦች በተገኙበት ነው፡፡ የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ወጪውን ከሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በተፈቀደው መሠረት ከሚሸፍነው ከሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ ጋር በ5.1 ሚሊዮን ብር የተዋዋለው የሁዳ ሪል እስቴት ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅና የፕሮጀክቱ ተጠሪ በሥፍራው በመገኘት ሥራውን ተረክበዋል፡፡

ሠራተኞች የሥራ ዕድል በመፍጠራቸው መደሰታቸውን ገልፀው፤ በቀጣይም የሥራና የልማት መስኮች እየታዩ የማስፋፋት ሥራ እንደሚሰራ በመናገር ለዚህ ዕድገት ምክንያት የሆኑትም ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲንን በሠራተኞች ስም አመስግነዋል፡፡

የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ

ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ከበዓሉ ተሳታፊዎች በከፊል

የሕፃናቱ ክፍል በተጐበኘበት ወቅት

የሕፃናት ማቆያው ተመርቆ ሲከፈት

Page 5: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

5

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች፣ እሀትማማችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የተካሄደው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አዘጋጅነት ለስድስት ወራት በልዩ ልዩ ዘርፎች ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ውድድር በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ፡፡

11ኛው የወዳጅነት የስፖርት ውድድር በሩጫ፣ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በዳማ፣ በቼዝና በዱላ ቅብብል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች ለስድስት ወራት ሲካሄድ ቆይቶ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፍፃሜ በቅቷል፡፡

በበዓሉ ማጠናቀቂያ ወቅት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በቅድሚያ ለበዓሉ መካሄድ ዋናው ምክንያት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለሀብትና ሊቀመንበር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ መሆናቸውን በማውሳት ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ይህንን መሰሉ ስፖርታዊ ውድድር በሠራተኞች መካከል መልካም ግንኙነትን ከመፍጠር ባሻገር የሥራ ተነሳሽነት እንዲኖርና የእኔነት ስሜት እንዲዳብር ያደርጋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ በተካሄዱት ውድድሮች ባሳየው ጥሩ ፉክክርና ዝግጁነቱ የመቻሬ እግር ኳስ ቡድን ወደ ብሔራዊ ሊግ እንደሚገባና የአትሌቲክስ ዘርፉም ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች ውጭ በተጋባዥነት የሚካፈሉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተጠናከረ መልኩ እንዲሳተፉና በስፖርት የዳበሩ ሠራተኞችና ዜጐችን የመፍጠር እንቅስቃሴ እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በበዓሉ ማጠናቀቂያ ለፍፃሜ የደረሱት የእግር ኳስ ቡድኖች ግጥሚያ አድርገው መቻሬ የእግር ኳስ ቡድን ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ቡድንን

ሁለት ለአንድ በማሸነፍ የ25 ሺህ ብር ተሸላሚ ሲሆን ከተጋባዥ ተቋማት ሁለተኛ የወጣው ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ የ15 ሺህ ብር፣ ሦስተኛ የወጣው ዳሽን ባንክ ደግሞ የ10 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የአንድ መቶ፣ የሁለት መቶ፣ የአራት መቶ ሜትርና የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ታላቅ ሩጫ እንዲሁም የዱላ ቅብብል ውድድር ተካሂዷል፡፡

ለስድስት ወራት በተካሄደው ውድድር ብልጫ ላመጡ ተፎካካሪዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ ስፖርታዊ ውድድር ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ስፖርት ቡድን አሸናፊ በመሆን ዋናውን ዋንጫ ወስዷል፡፡ ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ዴይላይት ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተ.የግ.ማ ስፖርት ቡድንና ከተጋባዥ ተቋማት ናሽናል ሞተርስ ኩባንያ የጥሩ ፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በዚሁ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር የቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎች (መቻሬ) የእግር ኳስ ቡድንን ጨምሮ ፖልሪዬስ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ናሽናል ሞተርስ፣ ሞሐ ለስላሣ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣ አዲስ ካተሪንግ፣ ሸራተን አዲስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ሆራይዘን አዲስ ጐማ፣ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕና ሜፖ ተካፋይ ሆነዋል፡፡

በስፖርት በዓሉ ማጠናቀቂያ ላይ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው፣ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በውድድሩ ብልጫ ያመጡት ቡድኖች ከዶ/ር አረጋ እጅ ዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

Page 6: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

6

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የስፖርት በዓሉ ታዳሚዎች በከፊል

Page 7: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

7

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

ከስፖርት በዓሉ ውድድሮች በከፊል

Page 8: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

8

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

ከስፖርት በዓሉ ውድድሮች ...

የኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ የእግር ኳስ ቡድን

የመቻሬ የእግር ኳስ ቡድን

Page 9: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

9

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የሽልማት አሠጣጥ ሥርዓት በከፊል

Page 10: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

10

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የሠራተኞች ቅጥር፣ ዝውውር፣ የለቀቁ፣ በጡረታ የተሰናበቱ፣ ጋብቻ የፈፀሙና ዜና ዕረፍት

ከሠራተኞች ማኅደር

የተቀጠሩአስናቀች በሪሁን በፋሲሊቲ ሜንቴናንስ I½ ህላዊ መስፍን½ በዛብህ ግርማ½ ኤልሳቤጥ ገብሩ እና አሮን ከበደ በጁኒየር ኢንፎርሜሸን ሲስተም አድሚኒስትሬተር½ ሀያት አብዱ አካውንታንት½ እመቤት ጭጭይበል በኦፊስ አቴንዳንት I በሲሲኦ፤ ኤልሳቤጥ ብሩ እና ዘካርያስ ካሣ አካውንታንት በሚድሮክ ወርቅ፤ አዛለች ገ/እግዚአብሔር በስትራክቸራል ኢንጂነር½ ሃይማኖት አለባቸው በስቶር ክለርክ½ ወልደአማኑኤል ካሣ በባክሁ ሎደር ኦፕሬተር½ እውነቱ ቱራ½ ሲሳይ ጌቱ እና ዋሲሁን አማኑኤል በቬኸክል ኦፕሬተር½ ክንፈ ባህሩ በሞባይል ክሬን ኦፕሬተር በሁዳ፤ትህትና ተረፈ እና መለሰ ማስረሻ በአሶሲዬት ኢንጂነር በኮስፒ፤ አለኸኝ በላይነህ½ ሬድዋን ታጁ X ቴዎድሮስ ሽመልስ በጁኒየር ስኬልማን½ ሚኪያስ ዘውዱ እና አክሊሉ ግርማ በፊለር እና ፓከር በኤም ቢ አይ፤ ኤፍሬም ደበሶ ገመቹ ዋቆ እና ዋቺፋ ጐበና በጁኒየር ፕሮቴክሽን ኦፊሰር½ እየሩሳሌም ዳንኤል አካውንታንት በትረስት፤ ኃይሉ ሰለሞን ረዳት ኤሌክትሪሺያን፣ አየለች ደመና ኦፊስ አቴንዳንት፣ ትዕዛዙ በላይ እና ዘመቻ ቢዶ ሹፌር ደረጃ ሁለት በዋንዛ፤ ገዛኸኝ ኃይሌ በክሊኒካል ነርስ በብሉ ናይል፤ አያሌው ሀሰን በሲኒየር አውቶ ሜካኒክ½ ¦Y¥ñT x¥r j¥¶ µ¹R በዩኤኤም፤

ወ/ት ፋሲካ የኋላሸት ኦፊሰር ላይብረሪ ሰርቪስ½ መንግሥቱ ውቡ ሲኒየር ሪከርድ ኦፊሰር½ መሰለ ገብሬ አሲስታንት ዲን½ ጥሪቴ ተስፋዬ ቼክ ፖይንት አቴንዳንት½ ሔኖክ ኤርትራ አካውንታንት½ ዶ/ር ታረቀኝ ዲአ እና አዲስ ገ/መስቀል መምህር½ ተስፋዬ ኃይሌ½ ታምራት ሁንዴ½ አስመሮም አበባው እና አበበ ተካ በአቴንዳንት ክሊኒንግ ሰርቪስ½ አስናቀች ሰይፉ በላይብረሪ አቴንዳንት½ አብዱ ይመር½ ኤርሚያስ ወርቅሉል½ ክንፈ ዮሐንስ እና ጀማል ሁሴን በመምህር የሥራ መደብ በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረዋል።

የለቀቁወ/ሮ በላይ ተክሌ ከኢኢኦ፤ አቢይ ተክሌ½ አጥናፉ አለማየሁ½ እንዳልካቸው ታደሰ½ ገነት ይልማ½ ደላለኝ ከበደ½ አምባቸው ሰብስቤ½ ሀ/ሚካኤል ደምሴ½ ለታ መንገሻ½ zµ¶ÃS µœ½ _§h#N m÷NN ከሚድሮክ ወርቅ፤ እየሩሳሌም ፋንቱ እና ዳግም ስብሃት ከሁዳ፤ ጌታቸው አለሙ ከኤም ቢ አይ፤ አዶላ ጎዳና እና ተሰማ ሞሲሳ ከትረስት፤ አዜብ ተፈራ እና አደይ ኃ/ሚካኤል ከቲ ኤን ኤ፤ ፍቅርዋ ባዴ ከብሉ ናይል፤ ብሩክ ጌታቸው½ ፍሬው አበበ½ ×/NS /d‰½ m÷NN xsͽ l¥ dúl"½ ׬N wNDxBq$ X ÂåL b!‰ kÁY§YT፤ l#cEà Ng#s@½ ዘሪሁን ጌታቸው½ ስዩም ጉታ½ ያሬድ አታለል½ ምህረት ሞገስ½ አህመድ ሰይድ½ ስመኝ አመኑ እና ምስራቅ ኃይሉ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል።

የተሰናበቱወ/ት ዮዲት ተስፋዬ ከአዲስ ጋዝና ፕላስቲክ፤ አቶ አበባው እንግዳ½

አብርሃም ደስታ½ መሰለ አምባዬ½ ለገሰ ገ/ሥላሴ½ ጀነነው ረታ ከቲ ኤን ኤ፤ ማሞ ካሳ እና ኤፍሬም አያሌው ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተሰናብተዋል።

የተዛወሩወ/ሮ ገነት ሸዋዬ ከሲኢኦ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በሱፐርቫይዘር ፕሮኪዩርመንት ሰርቪስ½ ሀብቴ ሙለታ ከሲኢኦ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በዳይሬክተር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርፕራይዝስ½ ሳምሶን ተረፈ ከሲኢኦ ወደ ዴይላይት በኢንጂነር½ ዳንኤል ጌታሁን ከሲኢኦ ወደ አዲስ ጋዝ በኢንጂነር½ ሚካኤል ምትኩ ከኢኢኦ ወደ አዲስ ጋዝ በተ/ዋና ሥራ አስኪያጅ½ ቤተል ጌታቸው ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሲኢኦ በሴክሬተሪ የሥራ መደብ፤ አስፋው ገ/ሥላሴ ከዴይላይት ወደ ሲኢኦ በሊደር ኮርፖሬት ቴክኖሎጂ ኤንድ ኢንጂነሪንግ፤ ገብረዮሃንስ ሀብተዝጊ ከሚድሮክ ወርቅ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በሲኒየር ጂኦሎጂስት½ ሚካኤል ግርማ ከሚድሮክ ወርቅ ወደ ኤልፎራ በአካውንታንት፤ አልማዝ ወልዱ ከሁዳ ወደ ሲኢኦ በማናጀር ኮንትራት ኦፕሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ፤ አዳነች ይሄይስ ከቲኤንኤ ወደ ሲኢኦ በሲኒየር ኦዲተር የሥራ መደብ½ በየነ ደሌሳ ከቲኤን ኤ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ፤ አብዱ ሰይድ ከዋንዛ ወደ ኤም ቢ አይ፤ እዮብ ፍቃዱ ከዴይላይት ወደ ኮስፒ ተዛውረዋል።

ጋብቻ የፈፀሙአቶ ማንያዘዋል ደሳለኝ ከወ/ት ሌሊሴ ጉደታ½ ወ/ት ቤተል ጌታቸው ከአቶ አንድነት በቀለ ከሲኢኦ፤ አቶ ወንድምአገኝ ሲሣይ እና ወ/ት መሰረት ጥላሁን ከዴይላይት፤ አቶ ኢዮብ አዳሙ ከወ/ት ርብቃ ይሳቅ½ ወ/ት ወይንሸት ፍቃዱ ከአቶ ቀበና ዲነግዴ ከብሉ ናይል፤ ወ/ሮ ቤተልሄም ብርቁ ከአቶ ኤፍሬም ባየልኝ½ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ ከወ/ሮ ዮዲት አለም½ አቶ ጌታቸው ጉደታ ከወ/ሮ ራሄል ኃይሉ½ አቶ ደረጀ እንዳለው ከወ/ሮ ይፍቱ ከሚሴ ከሬይንቦ፤ ወ/ት ቅድስት ከተማ ከአቶ ዮሴፍ አጽበሃ½ አቶ አሸብር ሃሰን ከወ/ት አበባ አዱኛ ከዩ ኤ ኤም፤ ጋብቻ ፈጽመዋል። ለሥራ ባልደረቦቻችን ጋብቻቸው የአብርሃምና የሣራ እንዲሆንላቸው እየተመኘን የደስታቸው ተካፋይ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ጡረታ የወጡአቶ ተገኔ አቲሞ ከሚድሮክ ወርቅ½ አቶ ባይሳ ዲባባ ከዋንዛ በጡረታ ተገልለዋል። ለሥራ ባልደረቦቻችን ቀሪው ዕድሜያችሁ መልካም የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

በሞት የተለዩ አቶ ናትናኤል ግርማ½ ሞገስ መላኩ እና ጆኒፈር ነ.ጋኩ ከሚድሮክ ወርቅ በሞት ተለይተዋል። ለሥራ ባልደረቦቻችን ቤተሰቦች እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን የሐዘናቸው ተካፋይ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ በ2ኛው የአፍሪካ የእንስሳት ምርት ውጤቶች ኤግዚቢሽን ላይ ተካፈለ• ኤግዚቢሽኑን ለማሳካት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስፖንሰር አድርጓል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆነው ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማ. በሚሌኒየም አዳራሽ ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ የእንስሳት ምርት ውጤቶች ኤግዚቢሽን ላይ ተሳትፏል፡፡

ኤግዚቢሽኑን በይፋ የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር መብራቱ

መለሰ ሲሆኑ፤ ይህንን መሰሉ በእንስሳት ምርት ውጤቶች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን የአምራቹን ክፍለ ኢኮኖሚ እንደሚያሳድገው ገልፀዋል፡፡

በኤግዚቢሽኑ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማህበርን ጨምሮ በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ በተጐበኘበት ወቅት

Page 11: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

11

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

በአሁኑ ወቅት ገዳይ ከሆኑት ሴቶችን ከሚያጠቁ በሽታዎች ውስጥ የማህፀንና ጡት ካንሰር የመጀመሪያዎቹን ደረጃዎች ይይዛሉ፡፡ ቀደም ሲል የማህፀን ካንሰር የሀብታሞችና በኢኮኖሚ የዳበሩ አገሮች ብቻ ችግር ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ ትልቁ ችግር የነበረው ይሄንን በሽታ ለማወቅ የሚቻልበት መንገድ ውስን ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች እየታመሙ ይሞቱ ነበር፡፡

ከ30-45 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡ የማህፀን ካንሰር በአብዛኛው የ“ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ ኢንፌክሽን” ለረጅም ጊዜ በሰውነት ውስጥ በመቆየት በሚያደርገው ሂደት የሚከሰት ነው፡፡ ምናልባት አንዲት ሴት በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ቫይረሱን ብታገኘው እስከ ቅድመ ካንሰር ምልክት ለመድረስ ቢያንስ በአማካኝ ከ10-15 ዓመታት ይፈጃል፡፡ በ15 ዓመቷ የግብረ ስጋ ግንኙነት ብትጀምር እስከ 30 እና 35 ዕድሜዋ ድረስ ላይታወቅ ይችላል፡፡ የቅድመ ካንሰር ምልክት በሰውነቷ አንድ ጊዜ ከታየና በማህፀን በር ላይ ከተከሰተ በኋላ ቅድመ ካንሰሩ ወደ ካንሰር ለመለወጥ ከ10-15 ዓመት ይፈጃል፡፡ ስለዚህ በቫይረሱ አማካኝነት በማህፀን ውስጥ ክፍሎች ላይ ለውጥ አምጥቶ፣ ቫይረሱ የማህፀን ግድግዳ ክፍሎችን በመበከል ወደ ቁስለት፤ቁስሉ ደግሞ ከማህፀን ባሻገር ወደ ደም ውስጥ በመግባት ወደ ሰውነት መተላለፍ የሚችልበት ነው፡፡

ቅድመ ካንሰር ወደ ካንሰርነት ሲለወጥ እንዴት ይታወቃል?

የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን ያለባቸው ሰዎች (በኢንፌክሽኑ የተያዙ ሰዎች) ወደ ቅድመ ካንሰርነት ለመቀየር ከ10-15 ዓመት ይፈጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ምንም ነገር ማድረግ አይቻልም፡፡ ቫይረሱን ለማከምም ሆነ ሌላ ህክምና ለማድረግ ጊዜው አይደለም፡፡ የቅድመ ካንሰር ምልክቱ ከታየ ግን ማከም ይቻላል፡፡ ቅድመ ካንሰሩን ማከም ከቻልን ወደ ካንሰር እንዳይሄድ ቆመ ማለት ነው፡፡ ከቅድመ ካንሰር፤ ወደ ካንሰር ከተቀየረ ደግሞ ለካንሰር የሚደረጉ ህክምናዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት ካንሰሩ በማህፀን የተወሰኑ ክፍሎች ላይ ብቻ የሚታይ ከሆነ ችግሩ የታየበት የማህፀኑን ክፍል ብቻ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ በአካባቢው ባሉ ቦታዎች ተራብቶም እንደሆነ እነዛ

እጢዎች አብረው የሚወጡበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ወደ ደም ውስጥ ከገባ በኋላ የሚሰጠው ህክምና የመድሃኒት ፤የቀዶ ጥገና ወይንም የጨረር ህክምና ነው፡፡ ይሄ የሚሆነው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ሳንጠቀም ከቀረን ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ30-40 ላሉ ሴቶች የቅድመ ካንሰር ምርመራ ካደረጉ እና ችግር እንዳለባቸው ካወቁ በነዚህ ህክምናዎች በሽታው ወደ ካንሰርነት እንዳይቀየር መከላከል ይቻላል የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ ቢቻልና አመቺ ቢሆን የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ክትባት መውሰድ ቫይረሱን ለመከላከል ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ክትባቱ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ አገልግሎት ላይ ይዋል ቢባል መሰጠት ያለበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ላልጀመሩ ሰዎች እንጂ ለጀመሩ ሰዎች አይደለም፡፡ ምክንያቱም የግብረሥጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች ቫይረሱ በሰውነታቸው ውስጥ ሊኖር ስለሚችል ነው፡፡ ከክትባቱ ውድነት አንፃርና በአሁኑ ሰዓት በሽታው ካንሰር ደረጃ ሳይደርስ መከላከል የሚቻልበት ቴክኖሎጂዎች ስላሉ እነዚህን መጠቀም ይመረጣል፡፡

የቅድመ ካንሰር ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሴቶች ላይ ከታየ ወደ ካንሰርነት የመለወጡ ሁኔታ በጣም አጭር ጊዜ ይሆናል፡፡ ኤችአይቪ በደማቸው ሴቶችን በፍጥነት ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ የማህፀን ካንሰር ነው፡፡ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ ከምንለው አንዱ ለሴቶች በተለይ የማህፀን በር ካንሰርን /ሰርቫይካል ካንሰር/ መከላከል አንዱና ትልቁ ነው፡፡ መታመምንና ሞትን የመቀነስ አቅሙከፍተኛ ነው፡፡ HIV በደማቸው ውስጥ ያሉ ሴቶች የሰውነታቸው የመከላከል ሃይል በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ኤችአይቪ በደሙ ያለበት ሰው ሁሉ ቅድመ ካንሰር አለበት ማለት አይደለም፡፡ ቅድመ ካንሰር ያለው በሙሉም ካንሰር አለበት ማለትም አይደለም፡፡

ቅድመ ካንሰርን ማከም ከተቻለ ካንሰርን መከላከል ይቻላል፡፡ ወደ ካንሰር ከተለወጠ በኋላ ግን ያለው አማራጭ ከፍተኛ ህክምና ነው፡፡

አብዛኛዎቻችን የበሽታ ምልክት ከታየብን በኋላ ነው ወደ ጤና ተቋማት መሄድ የምናዘወትረው ይህ ግን አግባብ አይደለም፡፡ በተለይ ካንሰር ምልክት የለውም፡፡ ከ30-35 ባለው ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ምርመራ ማድረጉ ምልክት የሌለውን ነገር በማወቅ ከችግሩ ራስን ለመጠበቅ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ጠቅላላ ዕውቀት

ካንሠርና ጉዳቱ

Page 12: 77 - MIDROC · 2017-07-20 · 3 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 77 May — June 2014 Addis Ababa, Ethiopia “We Would Like to Achieve Excellence When It Comes to Quality”

12

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 77 May — June 2014

Addis Ababa, Ethiopia

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

ዶ/ር አረጋ ይርዳውDr. Arega Yirdaw

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያChief Executive Officer, MIDROC Ethiopia

u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: Office of the Chief Executive Officer, MIDROC EthiopiaFax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

ግንዛቤን ማዳበር ለውሳኔ ቁልፍ ነው

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከፍ

ለማድረግ በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች

እጅግ የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ ከግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ

ማደግ ጋር ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር የሚደረገውን

ጉዞ ለማፋጠን የኃይል አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መሟላት

አስፈላጊ በመሆኑ የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ለመገንባት

ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በመገንባት ላይ ከሚገኙት በርካታ የኃይል

ማመንጫዎች ትልቁን ድርሻ የሚይዘውና የአገሪቱ ዜጎች

በጠቅላላው አሻራቸውን እያሳረፉበት የሚገኙት የሕዳሴው

ግድብ በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡ የዚህ የኃይል ማመንጫ

ግድብ ግንባታ መጀመር ከተበሰረበትና የመሠረት

ድንጋይ ከተቀመጠበት ዕለት አንስቶ ዜጐች ለግንባታው

የአቅማቸውን ያህል እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ቀደም ሲል በአገሪቱ በኢንቨስትመንት መስኮች በመሳተፍ

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት ባሻገር ለበርካታ ዜጐች

የሥራ ዕድል በመፍጠር ፈር ቀዳጅ የሆኑት ሼክ ሙሐመድ

ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ለሕዳሴው ግድብ ከለገሱት 1.5

ቢሊዮን ብር ሌላ እርሳቸው ባቋቋሟቸው ኩባንያዎች

ውስጥ የሚሠሩ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ

ኩባንያዎችና ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው ከ26

ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ በመግዛት ልገሳ ማድረጋቸው

ይታወሳል።

ለግድቡ ግንባታ የድርሻችንን ለመወጣት በገባነው ቃል

መሠረት ከገንዘብ ልገሳ ባሻገር ግድቡን በተመለከተ

የታችኛው የተፋሰስ አገሮች በስጋት መልክ የሚያነሱትን

ቅሬታ በባለሙያዎች በተጠናና በቂ መረጃ የተያዘበት

የግንዛቤ ማስጨበጫ ዓውደ ጥናት በማካሄድ በቂ ግንዛቤ

መፍጠርን አማራጭ አድርገን በመውሰድ መድረክ

አመቻችተናል።

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ እውቅ የዩኒቨርሲቲ

ምሁራን፣ የፖለቲካ ተንታኞችና መላው የሚድሮክ

ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች

በተሳተፉበት በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት

ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበውና ውይይት ተደርጐባቸው የተሻለ

መረጃ ለመያዝ ተችሏል፡፡ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ

በጥናት የተደገፈ በቂ ግንዛቤ ለማስያዝ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ

ጥረት አድርጓል ወደፊትም ያደርጋል። በጥናቱ ወቅት

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በድጋሚ የአንድ ሚሊዮን ብር የቦንድ

ግዢ አድርጓል።