መግቢያ€¦  · web view · 2016-10-21ቢሮው ያለበትን ክልላዊና...

224
ማማማ 1. ማማማማ....................................................................2 2. ማማማማ ማማማማ ማማ ማማማማማ ማማማ..........................................4 3. 2008/09 ማማማማማ ማማማ ማማማ ማማማማማ ማማማ ማማማ ማማማማማ ማማማማማማማ ማማማማማማማ ማማማማ...........................................................4 ማማማ ማማማ....................................................................7 ማማማማ ማማማማማ ማማማማማ.....................................................7 ማማማማ ማማማማ ማማማማ ማማማማማ...............................................7 ማማማ ማማማ...................................................................26 ማማማማማ ማማማማማ ማማማማማ..................................................26 1. ማማማ ማማማማ ማማማ......................................................................26 2007/08 ማማማ ማማማ ማማ ማማማ ማማ...........................................................33 2008/09 ማማማማ ማማማ ማማማ ማማማ............................................................34 2. ማማማማማማማ ማማማማ ማማማ ማማማማማ ማማማማ..........................................34 3. ማማማማማ ማማማ ማማማ ማማማማ ማማማማማ ማማ ማማ ማማማማማ.............................44 4. ማማማማማ ማማማማማማማ ማማማማማማ.....................................................49 1

Upload: lamkhanh

Post on 06-Apr-2018

336 views

Category:

Documents


17 download

TRANSCRIPT

ማውጫ

1. መግቢያ....................................................................................................................................................................2

2. የክልሉ ግብርና ቢሮ ተልዕኮና ራዕይ......................................................................................................................4

3. የ 2008/09 የግብርና ልማት ዕቅድ አጠቃላይ ዓላማ ግቦች መሰረታዊ አቅጣጫዎችና የማስፈፀሚያ ስልቶች.. .4

ክፍል አንድ.......................................................................................................................................................................7

የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም..............................................................................................................................................7

የልማት ሰራዊት ግንባታ አፈፃፀም...................................................................................................................................7

ክፍል ሁለት.................................................................................................................................................................... 26

የአበይት ተግባራት አፈፃፀም.........................................................................................................................................26

1. ሰብል ልማትና ጥበቃ...........................................................................................................................................26

የ 2007/08 ምርት ዘመን ዘር ብዜት ሥራ............................................................................................................................33

የ 2008/09 የመኸር ወቅት የዘር ብዜት...............................................................................................................................34

2. የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ስራዎች....................................................................................................34

3. የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም እና ውሃ ማሰባሰብ............................................................................44

4. የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት........................................................................................................................49

5. የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ሥርጭት..................................................................................................................52

6. የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ...........................................................................................................54

7. ግብርና ምርምር ተቋም..........................................................................................................................................59

8. የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ....................................................................................................................................63

9. አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ.................................................................................65

10. ኅ/ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጄንሲ...................................................................................................................75

11. የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን............................................................78

12. የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ.......................................................................................................................81

ደጋፊ የስራ ሂደቶች.........................................................................................................................................................95

ክፍል ሶስት....................................................................................................................................................................121

a. ከእቅድ አፈፃፀሙ አንፃር የታዩ ተሞክሮዎችና አበረታች ውጤቶች.......................................................................121

2. በልማትና በመልካም አስተዳደር የእቅድ አፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ ሃሳቦች....................122

2.1 የነበሩ ጠንካራ ጎኖች................................................................................................................................................122

2.2 ያጋጠሙ ችግሮች፤...................................................................................................................................................123

1

2.3 ለችግሮቹ የተሰጡ መፍትሔዎች................................................................................................................................123

3. በመልካም አስተዳደርና በኪራይ ሰብሣቢነት የተከናወኑ ተግባራት.......................................................................124

1.መግቢያ

ቢሮው ያለበትን ክልላዊና ሃገራዊ አደራ ለመወጣት ያስችል ዘንድ በዚህ አመት ታላላቅ ተግባራትን ማከናወን

ተችሏል፡፡ ከሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን መጀመሪያ ዓመትላይ በመሆናችንና እንዲሁም ከመጀመሪያው

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ይዘን ሳናሳካቸው የቀሩ ተግባራትን ለቅሞ ይዞ ወደ ተግባር በመግባት በተያዘላቸው

የጊዜ ሰሌዳና ወቅት ለመተግበር ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል፡፡

ያሳለፍ ነው የ 2007/08 በጀት ዓመት ከሌሎች ዓመታት ለየት የሚያደርገው በዓይነቱም ሆነ በስፋቱ አስደንጋጭ

የሆነ ድርቅ እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ክልል ማጋጠሙ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቋቋም ብሎም ለመቀልበስ እንዲቻል

በመስኖ ልማትና በተፈጥሮ ሃት ልማት አመርቂ በሚባል ደረጃ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ የክረምቱ ዝናብ መቆራረጥና

የስርጭት መዛባት መከሰቱን ፈጥኖ በመገንዘብ ቢሮው ሰብላቸው በእርጥበት እጥረት ምክንያት የተጎዳባቸውን

አ/ አደሮች ተስፋ ሳይቆርጡ ፈጥነው ወደ መስኖ ልማት እንዲገቡ ፈጣን እቅድ ተነድፎ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በዚህ

መሰረት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የዘር አቅርቦትና የውሃ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጅ የማቅረብ ስራ በስፋት

ተከናውኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዘላቂ ልማቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ የግድብና የማህበረሰብ

ኩሬዎች ግንባታዎች ተከናውነዋል፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራችንን ስንመለከት በድርቁ ውስጥ ሆነን እንኳን በገጠር የገነባነውን የልማት ሰራዊት

በአግባቡ ወደ ልማት ማስገባት የተቻለበት ቀጥሎም ወጥና ጥራት ያላቸው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች

የተከናወኑበት ጊዜ ነበር፡፡

የ 2008/09 መኸር ዘመንን በውጤት ለማጠናቀቅ እንዲያስችል የማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት ቀድሞ

የተከናወነበት፣ የዓመቱን እቅድ በፈፀሚና አስፈፃሚ ሃይሎች ፊት የጋራ የማድረግ ስራ የተሰራበት ነው፡፡ የሰብል

ልማት ስልጠና ከክልል እስከ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ መንደርና አ/ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ድረስ ማድረስ የተቻለበት

ነበር፡፡ በዚህም ከ 2 ሚሊየን የሚበልጡ አ/ አደሮች በስልጠናው እንዲሳተፉ እየተደረገ ሲሆን ስልጠናው የተያዘለትን

የጊዜ ሰሌዳ ጠብቆ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የዘንድሮው የሰብል ልማት ስራ ከሌሎች ዓመታት ለየት የሚያደርገው crop commodity cluster approach መከተላችን ነው፡፡ በዚህ መሰረት የቢራ ገብስ፤ ማሽላ፤ ስንዴ፤ በቆሎ፤ ጤፍና ሰሊጥ የተካተቱት

በመኸር ከሚሸፈነው ጠቅላላ 4.4 ሚሊየን ሄ/ ር ውስጥ (35%) የሚይዘው ማለትም 1,099,863 ሄ/ ር መሬት

በመሸፈን 42,280,090 ኩ/ ል ለማምረትና አማካኝ ምርታማነቱን ወደ 38.4 ኩ/ ል በሄ/ ር ለማድረስ ሰፊ የአቅም

ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡

2

በአ ጠቃላይ የተከናወኑ ተግባራት ለምርታማነትና ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አቅም መፍጠር

የተቻለበት ወቅት መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ የእቅድ ክንውን አፈፃፀም በሚከተለው መልኩ

በሁለት ክፍል ተጠናቅሮ ቀርቧል፡፡ ይህም ክፍል አንድ የሰራዊት ግንባታ ስራችን በተቋማችንና በአ/ አደሩ ያለውን

ሲያካትት ክፍል ሁለት አበይት ተግባራትን እቅድ ክንውን አፈፃፀም በሚከተለው መልኩ ይዞ ቀርቧል፡፡

2.የ ክልሉግብርና ቢሮ ተልዕኮና ራዕይ

ተልዕኮ

የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሠረት ያደረገ የአርሶ አደሩን ጉልበት በስፋት የሚጠቀም፣ ከሥነ- ምህዳር ጋር

የተጣጣመ፣ በዘመናዊ የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ የሚደገፍ የአክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠትና የግብርና

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የክልሉን አርሶ አደር ከድህነት ሕይወት በመሰረታዊነት በማላቀቅ በላቀ ደረጃ

ተጠቃሚ ማድረግ፡፡

ራዕይ

በክልሉ በ 2012 ከድህነት የተላቀቀ፣ መካከለኛ ገቢ ያለው እና ምቹ አካባቢ የተፈጠረለት ህብረተሰብ ማየት፡፡

3.የ 2008/09 የግብርና ልማት ዕቅድ አጠቃላይ ዓላማግቦች መሰረታዊ አቅጣጫዎችና

የማስፈፀሚያ ስልቶች

አጠቃላይ ዓላማ

3

የአካባቢ ፖቴንሽያልን መሰረት ያደረገ የተቀናጀ የግብርና ልማትን በማካሄድ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ

አሠራሮችን በመተግበር ምርትና ምርታማነትን ማሣደግና የአ/ አደሩን ገቢ ማሻሻል

አጠቃላይ ግቦች

ሁሉንም የስነ- ምህዳር ቀጣናዎች ያካተተ የተቀናጀ የግብርና ኮሞዲቲ ክላስተር ልማት በማካሄድ የአርሶ

አደሩን ገቢ ማሻሻል፡፡

የየአካባቢውን ፓቴንሻል ግምት ውስጥ ያስገባና ውኃን ማእከል ያደረገ የተፈጥሮ ሀበት ልማት በማካሄድ

የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ የአደጋ ተጋላጭነት መቀነስ፡፡

የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የግብርና ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ገቢን ማሳደግ፡፡

የአካባቢ ፖቴንሽያልን መሰረት ያደረገ የእንስሳት ሀብት ልማት በማካሄድ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት

ማረጋገጥ፡፡

ገበያን ማዕከል ያደረገና በሰርቶ ማሳያ የተደገፈ የኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት የአርሶ አደሩን

የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ማሳደግ፤የማስፋት ስትራቴጂውን ተግባራዊ ማድረግ፡፡

የሰው ሀይል ልማትና የተቋ ማት ግንባታ ማካሄድ፡፡

መሠረታዊ አቅጣጫዎች

ግብርና አሁንም የኢኮኖሚው እድገት ዋነኛ ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡ይህን ለማረጋገጥ የተቀናጀና

ውኃን መሰረት ያደረገ የተፈጥሮ ሀብት ስራ እንዲሁም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የግብርና ምርቶች

ለማምረት የሚያስችል የግብርና ኮመርሻላይዜሽን ክላስተር አካሄድ እንከተላለን፡፡

የአነስተኛ ይዞታ እርሻ ዋናው የግብርና እድገት መሠረት ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡

ግብርናው ፈጣን እድገትና መዋቅራዊ ለውጥን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲፈፀም ይደረጋል፡፡ ፈጣንና ዘላቂነት

ያለው የግብርና ልማት በማረጋገጥ በግብርና በራሱ እና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ ትራንስፎርሜሽኑን

እንዲያመጣ የሚያስችል አሠራር ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም የዘርፉን ተዋናዮች በተደራጀ አግባብ በማሳተፍ በአስተዋፅዋቸው ልክ

እንዲጠቀሙ ማድረግ

የማስፈፀሚያ ስልቶች

ሀ. የግብርና ልማቱን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል ተሳትፏዊና ገበያ መር የኤክስቴንሽን ስርዓት በመከተል

የማስፋት ስትራቴጅውን አሟልቶ መተግበር፡፡

ለ. አግሮ ኢኮሎጂን መሠረት ያደረጉ የልማት ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ የአካባቢን ፖቴንሽያል በላቀ ደረጃ

መጠቀም ፡፡

4

ሐ. የቴክኖሎጂ / ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት አግሮ ኢኮሎጂን መሠረት ባደረገና የአርሶ አደሩን ተሳትፎ ባረጋገጠ

መልኩ ማከናዎን፡፡

መ. የአደጋ ተጋላጭነትን በመቀነስ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ፡፡

ሠ. የግብርና ግብአት አቅርቦትና የሰብል ግብይትን በተሳለጠ መልኩ ለማካሄድ የኀ/ ስራ ማህበራትን የማደራጀትና

አቅማቸውን የማጠናከር ስራ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፡፡

ረ. የግብርና ግብአት አቅርቦትና የሰብል ግብይት በተሳለጠ መልኩ ለማካሄድ የኅብረት ስራ ማህበራትን የማደራጀትና

አቅማቸውን የማጠናከር ስራ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡

ሰ. የተቀመጡ መሠረታዊ አቅጣጫዎችና ግቦችን ለመተግበር በአደረጃጀት እና በአሠራር የተለዩ ክፍተቶችን

በማስተካከል ተቋማዊ የመፈፀም አቅምን የማብቃት ሥራ ማከናዎን፡፡

5

ክፍል አንድ

የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም

የልማት ሰራዊት ግንባታ አፈፃፀም በቢሮዉ ውስጥ የተጀመረው ጠንካራ የልማት ሰራዊት የመፍጠር እና የመገንባት ተግባር ተቋማዊ መልክ ይዞ ዘላቂነት በአለው መንገድ እንዲከናወን ማድረግ እና የተሟላ ቁመና ያለው የሲቪል ሰርቪስ ሰራዊት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በልማት ሰራዊቱ በአመራር ፣ በልማት ቡድን እና በ 1 ለ 5 አደረጃጀት ውስጥ የሚታዩትን የክህሎት ፣ የአመለካከት እና የስነምግባር ክፍተቶች በመሙላት የተፈጠረው የልማት ሰራዊት አደረጃጀት ወጤታማ እንዲሆን እና ሁሉም የተቋሙ ተግባሮች በተፈጠረው አደረጃጀት አማካኝነት ተፈፃሚ እንዲሆኑ ማድረግ

ለነገ የማይባል ስራ ሆኗል።

የተፈጠሩት አደረጃጀቶች ከላይ እስከ ታች የተገናኙ እና የልማት ሰራዊቱ አና አመራሩ አንድ ወጥ በሆነ የግንኙነት እና የትስስር ማዕቀፍ ውሰጥ እንዲገቡ ማድረግ ወቅታዊ በመሆኑ በየደረጃው ያለው አመራር የርብርብ ማእከል

የልማት ሰራዊት መፍጠር እና ተግባሮችን በተደራጃው የልማት ሰራዊት አማካኝነት በመፈፀም ትክክለኛ የግንባታ አቅጣጫ እንዲከተል እና ወጥነት ያለው አመራር እንዲሰጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የተደራጀው የልማት

ሰራዊት በየቀኑ እና በየሳምንቱ የሚያደርገውን ውይይት እና የሪፖርት ስርዓት ጊዜ እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲፈፅመው ተደርጓል፡፡

በአፈፃፀም ወቅት የጎላ አስተዋፅኦ የነበራቸውን ግንባር ቀደም ፈፃሚዎችን በየጊዜው መለየት እና የመገንባት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ሂደት ከሂደት፣ ዞን ከዞን ፣ማዕከል ከማዕከል፣ ኮሌጅ ከኮሌጅ፣ ወረዳ ከወረዳ፣ ቀበሌ ከቀበሌ፣ ልማት ቡድን ከልማት ቡድን፣ አንድ ለአምስት ከአንድ ለአምስት አደረጃጀት እርስ በርስ እንዲማማሩ

ልምድ ልውውጥ እንዲኖርና ሁሉንም ወደ ተሻለና ተቀራራቢ ደረጃ ለማምጣት በሚያስችል መልኩ ተግባራትን ለመፈጸም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት በበጀት አመቱ ቢሮው በሰራዊት ግንባታ በኩል የሚከተሉትን

ተግባራት አከናውኗል፡፡

የለውጥ ሰራዊት ግንባታ

ግብርና ቢሮ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በመንግስታዊ መዋቅር የተዘረጋ የልማት ቡድንና አንድ ለአምስት አደረጃጀቶች መሰረት በማድረግ ወደ እያንዳንዱ ግለሰብ አርሶ አደር መንደር ቤትና ጓሮ መድረስ የቻለ ባጠቃላይ

ወንድ 20,418 ሴት 6,409 በድምሩ 26,827 የሰው ሃይል ያለውና የክልሉን አርሶ አደር ሂወት በመለወጥ ለሃገርም ሆነ ለክልሉ ክፍለ ኢኮኖሚ መዳበር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ቢሮ ነው፡፡ ቢሮው ዞኖችን

ማዕከላትና ኮሌጆችን በመጨመር በ 118 የል/ ቡድኖችና በ 177 የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመደራጀት ወንድ 1022 ሴት 402 በድምሩ 1,424 የሰው ሃይል በመያዘ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡

6

በዚህ መሰረት የ 2007 ዓ. ም የቢሮውን እቅድ አፈጻጸም በመገምገም የተፈጸሙ እና ያልተፈጸሙ ተግባሮች አንጥሮ በማውጣትና ባልተሰሩና የነበሩ ችግሮች ተለይተው ከፈጻሚው ጋር የተሟላ ግልጽነት ተፈጥሮ ወደ ትግበራ

እንዲገባ ተደርጓል። የእቅዶችን አፈጻጸም እየገመገሙ ክለሳ ማድረግ እና እቅዱን ተፈጻሚ ሊያደርጉ የሚያስችሉ ስልቶች ተለይተዉ ተግባራዊ ተደርገዋል፤ በዚህ መሰረት አስቸኳይ የድርቅ ችግሮችን ሊታደጉ የሚችሉ የድርቅ

መከላከያና ማካካሻ የአጭር ጊዜ ዕቅዶች በተጨማሪነት ታቅደው ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

የዕቅድ ዝግጅትን በተመለከተ ከተቋሙ ስትራቴጅክ እቅድ የተቀዳ በጥረት ሊደረስበት የ ሚችል የ 2008 ዓ.ም የመ/ ቤቱና የስራ ሂደቶችን ዕቅድ በወቅቱና በአግባቡ በ BSC መሰረት እንዲታቀድ ተደርጓል፤ ከሂደቱ እቅድ የተቀዳ

በጥረት ሊደረስበት የሚችል የፈጻሚዎችና የስራ ሂደት መሪዎች የ 6 ወር ውልና ውጤት በወቅቱ ማጠናቀቅ ተችሏል ፣ የመ/ ቤቱን የእቅድ አፈጻጸም ከሰራተኞች ከተገልጋዮችና አጋር አካላት ጋር በየሩብ ዓመቱ

በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል ፣ ከእቅድ ዝግጅት እስከ ውጤት አሞላል ድረስ ያለውን የ አፈጻጸም አግባብነት አመራሩ በቢሮው ማኔጅመንት እየገመገመ መርቷል፡፡ የአቅም ክፍተትን በመለየት የተሰራ

የአቅም ግንባታ ስራን በተመለከተ በድጋፍና ክትትል ወቅት በተለዮ ክፍተቶች ማለትም የ ልማት ሰራዊት ግንባታ ሂደት፤

የዉጤት ተኮር ዕቅድ (BSC) ፤ ስለመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብና የስራ አፈፃፀም መመሪያን በተመለከ

ተለተከታታይ 6 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናዉ መነሻ ሁኔታ የስራ ሂደት መሪዎች የሪፎርም ተግበራት በተሟላ ሁኔታ ተረድቶ ሚናን መወጣት ላይ

እጥረቶች በመታየታቸዉ ቢሮዉ ይሄን ችግር ግምት ዉስጥ በማሰገባት ስልጠናዉ እንዲሰጥ ተደርጓል፡

የተሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና የወሰዱ በቢሮ ያሉ የስራ ሂደት መሪዎች እና የስራ ሂደት ተተኪዎች፤ ኬዝ ቲም

አስተባባሪዎች ፤ በ 10 ዞን ግብርና መምሪያ የሚገኙ የስራ ሂደት መሪዎች፤ ለ 3 የግብርና ኮሌጅ ኃላፊዎች እና የስራ

ሂደት መሪዎች፤ ለ 6 የማዕከላት ሃላፊዎች፤ በዞኖች እና በኮሌጆች ላሉ የለዉጥ አስተግባሪ ቡድኖች፤ በክልል ደረጃ

የተዘጋጀዉን ማንዋል መሰረት ተድርጎ ስልጠናዉ በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት ከአማራ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ

አሰልጣኞች ተሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረት አደረጃጀቶችን መሰረት አድርጎ በሚደረገው ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የልማት ቡድን እና የ 1 ለ 5 አደረጃጀት በአግባቡ ተደራጅተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፤ ግንባር ቀደም

ሰራተኞችን መለየት ተችሏል ፤ አመራሩም የስቪል ሰርቪስ የልማት ሰራዊት ግንባታን በአግባቡና በባለቤትነት መምራት አስችሎታል፤ አደረጃጀቶችን መሰረት ያደረገ ተከታታይነት ያለው መማማር እና ችግር ፈች ውይይት በመደረጉ የአመለካከት፣ የክህሎት፣ እና የስነምግባር ክፍተቶችን እየለዩ መሙላት ተችሏል፤ የለውጥ መሳሪዎችን በአግባቡ በመተግበር ተቋማዊ ለውጡን ማረጋገጥ ተችሏል ፡፡

በተቀመጡት የለዉጥ መሳሪያዎች አተገባበር በተመለከተ በተደረገዉ ድጋፍና ክትትል በቢሮ ያሉ ሂደቶች፤ የ 10 ሩ ዞኖች፤ ኮሌጆች አና ማዕከላት የአመታዊ አፈፃፀም እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡ በቢ ሮ ካሉ ስራ ሂደቶች በተሻለ

የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ያለ፤ የግብአት አቅርቦትና ሥርጭት ዋና የሥራ ሂደት፤የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ

የስራ ሂደት፤ ሲሆኑ በመካከለኛ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ያሉ፤ የግብርና ኤክስቴንሽን የስራ ሂደት፤ የመስኖ አት/ፍራ

7

የስራ ሂደት፤ የፕላንና ፕሮግራም የስራ ሂደት የውስጥ ኦዲት አገልግሎት የስራ ሂደት፤ የኢንፎርሜሽ ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ የስራ ሂደት፤የሰዉ ሀይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት፤ የሰበል ልማትና ጥበቃ

የስራ ሂደት፤የለዉጥ ትግበራ ድጋፍና ክትትል የስራ ሂደት፤ የ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት

ናቸው፡፡

በዞን ግብርና መምሪያ በለውጥ ትግበራ ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸዉ፤ዋግ ህምራ ዞን ግብርና መምሪያ፤ አዳጊ

አፈፃፀም የታየበት ዞን ነዉ፤ በተጨማሪደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያናአዊ ብሄረሰብ ዞን ግብርና መምሪያ በተሻለ

ደረጃ ይጠቀሳሉ፡፡

ደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ፤ ሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ፤

ኦ ሮሞ ብሄረሰብ ዞን ግብርና መምሪያ፤ አፈፃፀማቸው በየጊዜው እየተሻሻለ የ መጣና በመካከለኛ ደረጃ

የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሰ ሜን ሽዋ ዞን ግብርና መምሪያ፤ ከባለፈዉ አፈፃፀም የመቀነስ ሁኔታ የታየበት ዞን ነዉ፤

ሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያዎች በለውጥ ትግበራው ሰፊ ስራ

መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የግብርና ኮሌጆች እና ማዕከላት፤ በተመለከተ መ ርጦ ለማሪያም ግብርና ኮሌጅ፤ ባ ህር ዳር አፈር ምርመራ

ማዕከል፤ ባ ህር ዳር አዝዕርት ጥበቃ ክሊኒክ፤ ደሴ አፈር ምርመራ ማዕከል፤ የተሻለ አፈፃፀመ አሳይተዋል፡፡

ጎንደር አፈር ምርመራማዕከል፤ በመካከለኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡

ደ ብረማርቆስ አፈር ምርመራ ማዕከል፤ ኮምቦልቻ አዝዕርት ጥበቃ ክሊኒክ፤ ኮ ምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ፤

በሪፎርም ተግባራት ዉስንነት ያለባቸዉ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ የለውጥ ትግበራ ስራን የለውጥ ማስፈፀሚያ

መሳሪያ አድርጎ ለመጓዝ ተከታታይነት ያለው ስራመስራት እንደሚጠበቅ ይታመናል ከዚህ በተጨማሪ በተለይ

የአመለካከት ስራው በልዩ ትኩረት መከናወን ይጠበቅበታል፡፡

ወረዳወች ያሉበት የአፈፃፀም ደረጃ ስንመለከት በሁሉም ተግባራት በክልሉ 129 የገጠር ወረዳወች አሉ ከነዚህ

ውስጥ 127 ወረዳዎች በዞኖች በኩል በአጠቃላይ የግብርና ስራዎች አፈፃፀማቸው መሰረት በማድረግ የተፈረጁ

ሲሆን ያሉበት ደረጃ እንደ ሚከተለው ይሆናል፡፡

66 ወረዳዎች ማለትም (52%) የሆኑት በአፈፃፀማቸው በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል፣ 46 ወረዳዎች ማለትም

(36%) በመካከለኛ ደረጃ ፣ 15 ወረዳዎች ማለትም (12%) በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ናቸው፡ በቀበሌ ግብርና

ጽ/ ቤቶች፡ ደረጃ ቀበሌዎች ያሉበት የአፈፃፀም ደረጃ በክልሉ 3,182 ቀበሌዎች የተፈረጁ ሲሆን በተሻለ ደረጃ

1,561 ቀበሌዎች 49 % በመካከለኛ ደረጃ 1,169 ቀበሌዎች 36.7 % በዝቅተኛ ደረጃ 452 ቀበሌዎች 14 % ናቸው፡፡

ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በአሠራር፣ በአደረጃጀትና በግብአት አቅርቦት የተገኙ

ውጤቶች ሲገመገሙ የ 1 ለ 5 እና የልማት ቡድን አደረጃጀቶች የተቋሙን ስትራቴጅክ ግብ ከማሳካት አኳያ

አወንታዊ አስተዋፆ እያበረከቱ መሆኑ፣ በ 1 ለ 5 እና በልማት ቡድን ስራዎችን በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ እየገመገሙ

8

የአመለካከት ክፍተቶችን እየሞሉ መሄድ መልካም ጅምሮች መኖራቸዉ፣ የተቋሙ ሰራተኞች የህዝብ አገልጋይነት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣት መቻሉ፣ የስራ ሰአት ማክበር ለመንግስት ንብረት ተቆርቋሪነት

መጨመር እርስ በርስ የውድድር ስሜትና እርስ በርስ የመተጋገዝ ፍላጎት እየዳበረ መምጣቱ ፣ ከሂደት ሂደት

የልምድ ልውውጥ ማካሄዱ አመራሩም ሆነ ፈፃሚዉ የልማት ሰራዊት አደረጃጀቶች ስራን ወደ ተቀራራቢ አመለካከትና የአፈፃፀም ደረጃ የሚያደርስ የስራ መሳሪያ አድርጎ በማየት በኩል ያሉ መሻሻሎች፤አመራሩ

የሲቪልሰርቪስ የልማት ሰራዊትን ለመገንባት ክህሎቱ እያደገ መምጣቱ፣ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ስራን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የማጠናቀቅ ልምድ እየተሻሻለ መምጣቱ፣ በተቀመጠው አሰራርና አደረጃጀት መሰረት

የሰራዊት ግንባታው እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ትስስር ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑ፤በቢሮዉ በዞኖች

የልማት ቡድን አደረጃጀቶችን ተጠቅመዉ ግንባርቀደሞችን የመለየት ስራዎች የተከናወኑ መሆኑ በጥንካሬ

የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በተቋማዊ የሠራዊት ግንባታ ሥራችን አሁንም ቢሆን ያልተሻገርናቸው ችግሮች እንዳሉ በየደረጃው

በተደረጉ የሥራ ግምገማዎች መረዳት ተችሏል፡፡ በዋናነት የልማት ሰራዊት ግንባታን የመምራት ጉዳይ የሲቪል

ሰርቪስ ቢሮ ተግባር ብቻ አድርጐ የማሰብ ዝንባሌ በመኖሩ፤ የልማት ሰራዊት ግንባታ ሂደትን መምራትን በተመለከተ

በየደረጃዉ ያለዉ አመራር በባለቤትነት ይዞ ያለመምራት ችግር፤ ፈጻሚው በትንሹም በትልቁም የአመራሩን ጉትጐታ

የመፈለግ ዝንባሌ መኖሩ፣ የልማት ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር የሚያስገኘውን ፋይዳ አሳንሶ የማየት ዝንባሌ

መኖሩ፣የልማት ሰራዊት ግንባታን የክልልና የተቋሙ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማስፈፀሚያ አድርጎ ያለመያዝ

ችግር፣ስራን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል ፣ ግብረ መልስ የመስጠት ልምዱ በሚፈለገዉ መጠን አለመሄዱ፡፡

መካከለኛ አመራሩ በ 1 ለ 5 በየቀኑ በልማት ቡድን በየሳምንቱ የተሰጠዉን እቅድ የመከታተልና የመገምገም ስራ

የመቆራረጥ ችግር፤መካከለኛ አመራሩ በልማት ሰራዊት ፅንሰ ሀሳብ ምንነትና አስፈላጊነት የጠራ ግንዛቤ አለመኖሩ

በአደረጃጀት የተቀመጡ ተግባራትን በተሟላ ሁኔታ አለመፈጸምከዕውቀት፤ ክህሎት፤ አመለካከት ከአሰራርና

አደረጃጀት የ ታዩ ክፍተቶች ናቸው፡፡

የአርሶ አደር አደረጃጀት

የልማት ቡድን

የልማት ሰራዊት ግንባታ ስራችን በተመለከተ 3,143,903 አርሶ አደሮችን ያሳተፈ 115,160 የልማት ቡድን

ማደራጀት ተችሏል፡፡ አርሶ አደሩ በልማት ቡድን በመደራጀት የጋራ የልማት አጀንዳ በመቅረፅ እርስ በርስ

ልምድ እንዲቀያየርና ተመክሮ እንዲለዋጥ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በግለሰብ አርሶ አደሮች ማሳ ሰርቶ

ማሳያዎችንና የገበሬ በኣላትን ማከናወንና ማስተማር ተችሏል በዚህ መሰረት የግብርና ኤክስቴንሽን ተደራሽ

ለማድረግጥረት ተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረት መደራጀት ያለበት የልማት ቡድን 114,479 ፤ የአባላት ብዛት አባውራ 2,589,400 ፣ እማውራ 554,503 ፣ ድምር 3,143,903 ሲሆን የተደራጀ የልማት ቡድን ብዛት 115,160 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ

በተቀመጠው አጀንዳ መሰረት እየገመገሙ ስለመምራት ወይም ወቅታዊ ተገባራትን በመከታተል የቡድኖች 9

ደረጃ ስንመለከት የተሻለ 64,607 (56%) መካከለኛ 35,937 (31%) ዝቅተኛ 16,556 (14%) ሆነው ይገኛሉ ፡፡ ሰለዚህ በቀጣይ ድጋፍ በማድረግና በማጠንከር ዝቅተኛውን ወደ መካከለኛ መካከለኛውን ወደ ከፍተኛ

ደረጃ በማድረስ የተሻለ ልማት ቡድንና አርሶ አደር መፍመር ይጠይቃል፡፡

የአንድ ለአምስት

የአንድ ለአምስት አደረጃጀት አርሶ አደሮች በጋራ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ የውሃ መሳቢያ ሞተር የተጋጋጡ መሬቶችን ክለላ ችግኝ ተከላ የአፈርና ውሃ ጥበቃና መሰል ተግባራትን የሚያከናውኑበት በጋራ በተቀረፀ አጀንዳ የሚወያዩበት

አደረጃጀት ነው፡፡ ለምርትና ምርታማነት መጎልበት ለግብርና ኤክስቴንሽን መስፋፋት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው አደረጃጀት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መደራጀት ያለበት የአንድ ለአምስት የቡድን ብዛት 553,699 ፤ የአባላት ብዛት

አባውራ 2,589,400 ፣ እማውራ 554,503 ፣ ድምር 3,143,903 ነው፡፡ ተደራጅቶ ወደ ተግባር የገባ የተደራጀ የአንድ ለአምስት የቡድን ብዛት 554,585 ፤ የአባላት ብዛት አባውራ 2,589,400 ፣ እማውራ 554,503፣ ድምር 3,143,903 ፤ ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ እየገመገሙ ስለመምራት ወይም ወቅታዊ ተገባራትን

በመከታተል የቡድኖች ደረጃ የተሻለ 289,650 (52%) ፤ መካከለኛ 196,974 (36%) ፤ ዝቅተኛ 68,193 (12%) ይገኛል፡፡

የሴቶች አደረጃጀት

ባሳለፍነው በጀት አመት የሴቶችን አደረጃጀት ለማጠናከርና ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ ለመስራት ተሞክሯል በዚህ መሰረት መደራጀት ያለበት የልማት ቡድን ብዛት 121,475 ፤ የአባላት ብዛት 3,158,845

ሲሆን የተደራጀ የልማት ቡድን ብዛት 120,020 ፤ የአባላት ብዛት 3,158,845 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ተግባሩን እየገመገሙ ስለመምራት ወይም ወቅታዊ ተግባራትን በመከታተል የቡድኖች ደረጃ ስንመለከት የተሻለ

ደረጃ ላይ ያሉ 40,901 (35%) ፤ መካከለኛ 33,927 (32%) ፤ ዝቅተኛ 38,559 (33%) ናቸው፡፡

መደራጀት ካለበት የአንድ ለአምስት አደረጃጀት መደራጀት ያለበት የ 1 ለ 5 ቡድን ብዛት 592,119 ፤ የአባላት ብዛት 3,273,067 ፤ የተደራጀ የ 1 ለ 5 ቡድን ብዛት 592,119 ፤ ሲሆን የአባላት ብዛት 3,273,067 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ እየገመገሙ ስለመምራት ወይም ወቅታዊ ተገባራትን በመከታተል የቡድኖች ደረጃ

ስንመለከት የተሻለ 202,321 (81%); መካከለኛ 168,374 (67.5%); ዝቅተኛ 171,838 (66.5%) ነው፡፡ ቢሮው የስርኣተ ምግብ ባለሙያዎችን በክልል በዞንና በወረዳ ደረጃ በመዋቅር ማደራጀት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ የሴቶች ልማት ቡድን የመጠቀም ልምድ እየተጠናከረ እንዲመጣ አድርጓል፡፡

አደረጃጀቶች በጥንካሬና በዕጥረት

የልማት ቡድንና አንድ ለአምስት አደረጃጀቶች አርሶ አደሩ ግብአትና ቴክኖሎጂ በስፋት እንዲጠቀም እርስ በርስ መማማርና መደጋገፍ እንዲችል ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል፡፡ አጀንዳዎችን እየቀረፁ በጋራ መወያየት በጋራ ማረስ

በጋራ መዝራት በጋራ ማረምና መኮትኮት በጋራ በተፈጥሮ ሃብት ልማትና በመስኖ ልማት ስራዎች መሳተፍ የውሃ 10

መሳቢያ ሞተር ጂኦሜምብሬንና ሌሎች የውሃ ማሰባሰቢያ አውታሮችን በመቆፈር ባጠቃላይ በጋራ ወደ ልማት በመግባት በምርትና ምርታማነት ከፍተኛ ተነሳሽነት በመፍጠር ጉልህ ሚና ተጫውተዋል እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡

ይሁንየአርሶ አደሮች፣ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቁና ወደኋላ የቀሩ የል/ቡድኖችና የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶችም አሉ፡፡

አደረጃጀቱን በመጠቀም በየጊዜው የማይገናኙ አጀንዳ ቀርፀው የማይወያዩ ቢወያዩም ያዝ ለቀቅ በማድረግና ወጥነት በሌለው ሁኔታ መሆኑ በዚህ መሠረት ከልማቱ ግንባር ቀደም ተቋዳሽ ያልሆኑና በአደረጃጀት እንደገና መፈተሽና መደገፍ የሚገባቸው የል/ ቡድንና የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች የወረዳውም ሆነ የዞኑ ተግባራት ወጣ ገባ ያለና

ወጥነት የሌለው እንዲሆን አስችሏል፡፡ እዚህ ላይ የባለሙያ ድጋፍ አሰጣጥ ውሱንነት መታየቱ ለል/ቡድኖችና 1 ለ 5 አደረጃጀቶች መዳከም ምክንያት መሆኑን ተገምግሟል፡፡

በአጠቃላይ ከተደራጁ የአርሶ አደር ል/ ቡድን 56% ወደፊት የወጡ፣ 31% በመካከለኛ ደረጃ የሚኙ ሲሆን 13% በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉና ቀጣይ ድጋፍ የሚጠይቁ መሆናቸው ተለይቷል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ሁሉንም ወደ

ተቀራረበ ደረጃ ለማምጣት ሰፊ የማጠናከር ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ 61% የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች ወደፊት የወጡና በተሻለ አፈጻጸም ላይ የሚገኙ ሲሆን 31% በመካከለኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ 8% በዝቅተኛ ደረጃና ቀጣይ

ሰፊ ድጋፍ በሚጠይቅ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሴቶችና የወጣቶች ል/ ቡድን በትኩረት የማጠናከር ሥራ እና በቀጣይ ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ከአፈጻጸሙ መረዳት ይቻላል፡፡ ከአጠቃላይ የሴቶችና የወጣቶች ል/ ቡድን ሰፊ

ሥራና ልዩ ትኩረት የሚሰጥበት ተግባር መሆኑን ከግምገማችን መረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረት የማጠናከሩ ሥራ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል፡፡

ፈፃሚን ማዘጋጀት

ዕቅድ ትውውቅ

ዓመቱ የ GTP-2 መጀመሪያ አመት በመሆኑ ተቋማዊ አደረጃጀቶችንና የአርሶ አደር አደረጃጀቶችን የማጠናከር ሥራ በማከናወን ቀጣይ ፈጻሚን በአመለካከት በክህሎትና በግብዓት የማዘጋጀትና የማስታጠቅ ሥራው በዚህ

ግማሽ ዓመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተሠራ ተግባር ነበር፡፡ በዚህ መሠረት በክልል ደረጃ የንቅናቄ ዕቅድ በማዘጋጀት በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የታዩ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን በመገምገም

በ 2008 ዓ. ም መከናወን የሚገባቸውን ጉልህ ተግባራት መሠረታዊ አቅጣጫዎችንና የማስፈፀሚያ ስልቶችን በመንደፍ የክልል ሥራ ሂደቶች፣ የዞን ግብርና መምሪያወች የግብርና ሴክተርና ተጠሪ መ/ ቤት ኃላፊዎችና

11

የማዕከላት ሃላፊዎችና የግብርና ኮሌጅ ዲኖች የዞን ግብርና መምሪያ ሂደት መሪዎች፣ የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ም/ ኃላፊዎች በተገኙበት የዕቅድ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡

በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ፈፃሚን የማዘጋጀት ስራችን

በተከታታይ አመታት በተሰራው የግንዛቤ ማሳደግ ስራ የተፈጥሮ ሀብት መራቆትና መመናመን ችግርን በመቅረፍ በኩል ያለው እውቀትና ክህሎት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ በ 2008 ዓ. ም ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት

በመጀመሪያ ሰፊ የክህሎት ክፍተት የሚታይባቸው የአሰራርና የቴክኖሎጅ ክፍተቶች በየስነ- ምህዳሩ ለመለየት ተሞክሯል፡፡ ተጨባጭ የቴክኒክና የአሰራር ችግሮች ለመለየት አስቀድሞ የመስክ ዳሰሳ ተካሂዷል፡፡ በመስክ ዳሰሳ

ወቅት እጥረት ሆነው የተገኙትን ለማስተካከልና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ለባለሙያው ለማስረጽ ጊዜ ተወስዶ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ጎልተው ከታዩት እጥረቶች መካከል

በነባር በፊዚካል ስራ የተሸፈኑ ተፋሰሶችን ተጠቃሚትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ቴክኖሎጅዎችን አለመተግር በአስተሳሰብም አለመያዝ፣ የአካባቢን ችግር በዘላቂነት ሊቀርፍ የሚችል የቴክኖሎጅ አማራጮች ከአካባቢዉ

የመልማት አቅም ጋር አገናዝቦ አለመፈጸም፤ ስነአካላዊ እና ስነ ህይወታዊ ቴክኖሎጅዎች የሚያስገኙትን ጠቀሜታ

አልሞ አለመተግበር ሲሆኑ

o በዚህም በተለይ ከፍተኛ ተዳፋትነት እና ሰፊ የወል መሬቶች ባሉባቸዉ አካባቢዎች የጠረንፔዛማ እርከን

ስራ ከዉሃ ጋር አቀናጅቶ አለመፈጸም ፣

o ዝቅተኛ ተዳፋት ባለባቸዉ በተለይም ጥቁር አፈር በሚበዛባቸዉ አካባቢዎች የሳር ሰርጥ አለመስራት፣

o ከፍተኛ የቦረቦር ችግር ባለባቸዉ ካባቢዎች ቦረቦርና በቅርጽ ማስተካከልና ስነህይወታዊ ዘዴዎች የማዳን

ችግር፣

o በእርጥበት አጠር አካባቢዎች ደግሞ ሁሉንም ተግባራት ውኃን ማእከል አድርጎ አለመተግበር፣ ስራዎችን

በጥራትና በስፋት አለማከናወን

o ውኃን ማእከል አድርጎ አለመስራትና ባለሙያው ተጨባጭ የውኃ ምህንድስና እውቀት ይዞ በመገኘትም

አሁንም እጥረት ሆኖ መገኘት

o በደን ልማት ካለው ሰፊ አቅም አንጻር በመሰራት ላይ ያለው የደን እና ደን አግሮፎረስትሪ አቅም አንጻር

ክህሎት የሚነበብበት ስራ አለመስራት

o ሥነ- ምህዳርንና የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዝርያ መርጦ ማልማት አለመቻል፣

o የጥምር ደን እርሻ ቴክኖሎጂዎችን ትኩረት ተሰጥተው አለማከናወን

o የደን ውጤቶች አጠቃቀምና ዝውውር፣ የተፈጥሮ ደኖች ጥበቃ፣ የማህበራት ደኖች አጠቃቀምና ጥበቃ፣

በእጣንና ሙጫ አመራረት፣ አጠቃቀምና ልማት

o የባህርዛፍ ደን ልማትና አጠቃቀም፣ ላይ ችግሮች ታይተዋል፡፡

12

በዚህ መሰረት የተጠቀሱትን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የሚያስችሉና የመስክ መርጃ ሊሆኑ የሚችሉ ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ተደርጓል፡፡ የተዘጋጁት ማንዋሎች ባለፉት አመታት ከተዘጋጁትና ስልጠና ከተሰጠባቸው ማንዋሎች ያደጉና በተግባር በሚሰሩ ቴክኖሎጅዎች ላይ እንዲያተኩሩ ተደርጓል፡፡ ከአሁን በፊት በፊዚካል ስራ

የተሸፈኑ ተፋሰሶችን እና በቀጣይ ስራ የሚሰራባቸው ተፋሰሶች እንዴት ተጠቃሚትን ማረጋገጥ

እንደሚችሉ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ ስልጠናውን እስከ ወረዳና ቀበሌ በተሟላ መንገድ ለማድረስና የሚያስችሉና የመስክ መርጃ ሊሆኑ የሚችሉ ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ 18 የተለያየ ይዘት ያላቸው

ማንዋሎች የተዘጋጁ ሲሆን ከዚህ ውስት 7 በአፈርና እርጥበት እቀባ፣ 4 በውኃ ማሰባሰብና የመስኖ አውታር ግንባታና ጥገገና 7 በደን እና ጥምር ደን የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ስልጠናውም ተጨባጭ የክህሎት ችግርን በሚፈታ መንገድ ተሰጥቷል፡፡ ከግብርና ቢሮ እና ከጅ.አይ. ዜድ ባለሙያዎች በተጨማሪ በስራው እረጅም ልምድ ያላቸውና በጡረታ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ከባህርዳር እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ተጋብዘው እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ስልጠናው

ስነምህዳር ቀጠናን መሰረት አድርጎ የተሰጠ ሲሆን የምእራብ አማራና ምስረቅ አማራ ባለሙያዎች በተለያየ ክለስተር እንዲሰለጥኑ ተደርጓል፡፡ የምእራብ አማራ ሰልጣኞች በሜጫ ወረዳ የተግባር ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

የአመለካከት እና ክህሎት ስልጠና መስጠት

ባለፉት አመታት በተሰራው የግንዛቤ ማሳደግ ስራ የተፈጥሮ ሀብት መራቆትና መመናመን ችግርን በመገንዘብ ረገድ ያለው አመለካከት እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በዚህ አመት ከምንጊዜውም በላይ የተሟላ ግንዛቤ የተያዘበት ሁኔታ ተፈጥሯል ማለት ይቻላል፡፡ ይሁንና ከዚህ በፊት ከነበረን ልምድ በመነሳት በችግሩ ላይ መግባባት ከተደረሰ በኋላ ወደ ተግባር ሲገባ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀድመው እንዲለዩ በማድረግ በየደረጃው በተካሄደ የስልጠናና

የውይይት መድረኮችትግል ተካሂዶባቸዋል፡፡ በመሆኑም አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላትን በአመለካከት፣ በክህሎት በአሰራርና በአደረጃጀት ረገድ በብቃት የማዘጋጀት ጉዳይ ቅድሚያ ተሰጥቶት ተሰርቷል፡፡

ሀ/ ለዞን እና ወረዳ ሙያተኞች በክልል ደረጃ የተሰጠ ስልጠና መረጃ

የስልጠና አይነት የሰልጣኝ

ብዛት

የስልጠና

ቀናት

ውኃ ማሰባሰብና መስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ 165 15 አፈርና ውኃ ጥበቃ 428 6

ደን ልማት 269 6 ድምር 862 27

ለ/ የቀበሌ ባለሙያዎች ስልጠና

13

በክልል ከተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ቀጥሎ ዋና ፈጻሚ የሆኑትን የቀበሌ ባለሙያዎች የማሰልጠን

ስራ ተከናውኗል፡፡ ሁሉም ወረዳዎች በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን ማንዋል መሰረት አድርገው እንደየወረዳቸው

የስነምህዳር በተመረጡ ቴክኖሎጅዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተደርጓል፡፡ ስልጠናውን በተሻለ

መንገድ ለመስጠት የክልሉ መንግስት 7.2 ሚሊዮን ብር በመመደብ ሁሉም የወረዳና የቀበሌ ባለሙያዎች

ስልጠናውን እንዲውስዱ ተደርጓል፡፡

ዞንወረዳ ብዛት

የሰልጣኝ ቁጥር

የስልጠና ቀናት ዞን

ወረዳ ብዛት

የሰልጣኝ ቁጥር

የስልጠና ቀናት

ሰ/ወሎ 12 402 5 አዊ ብ/ዞን 11 608 ከ 5-6ምእ/ጎጃም 15 1352 5 ደ/ወሎ 21 1070 5ዋግ ብ/ዞን 7 442 ከ 6 -8 ሰ/ ሸዋ 24 1760 5.5ምስ/ጎጃ 17 1493 5 ኦሮ ብ/ዞን 5 288 ከ 3 -4ሰ/ጎንደር 20 2067 4-5 ክልል 142 10924ደ/ጎንደር 10 1439 ከ 5-7

ከቀበሌ ባለሙያዎች ስልጠና ጋር በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ችግሮች፣

o አንዳንድ የወረዳ ባለመያዎች ከሰልጣኙ ያነሰ ዝግጅት ማድረግናመሰረታዊ የክህሎትማነስ፣

o የሚሰለጥኑ ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅት፣የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድመለያየት

o የሰልጣኖች ቁጥርመብዛትና ለተግባር ስልጠናምቹ አለመሆን

o ለስልጠናው የተወሰነውን አነስተኛ ቀን የተለያዩ አካላትመሻማት

ሐ/ ለቀያሽአ/አደሮችየተሰጠስልጠና

የ 2008 የተፈጥሮ ሀብት ስራ ስፋትና ጥራት ባለዉ መልኩ ለመተግበር ያስችል ዘንድ የቀያሽ አ/አደሮች ባስተሳሰብ እና ክህሎት የተሻለ ሆኖ መገኘት ለምንሰራዉ የበጋ የተፈጥሮሀብት ልማት ስራችን ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡ በዚህም መሰረት ለ 265,046 ቀያሽ አርሶ አደሮች ከ 3-5 ቀናት ተግባር ተኮር ሥልጠና

ተሰጥቷቸዋል፡፡ በየተፋሰሱ የሚተገበሩ ቴክኖሎጅዎችን በመለየትለቀያሽ አ/ አደሮች የሚመጥን የስራ ማንዋል እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

መ/ በየደረጃዉ የንቅናቄ መድረኮች ማካሄድ

በ 2008 የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ አፈጻጸም ላይ የጋራ መግባባትና የድርጊት መርኃ ግብር ለማውጣት በክልል ደረጃ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ከ 143 በላይ የዞን ኮምንድ ፖስት አባላት፣

14

የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ በግብርና ቢሮ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ታህሳስ በ 11/2008 ዓ.ም ውይይት ተደርጓል፡፡ በአጭር ጊዜ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የቻለ እና አብዛኛውን የምእራብ አማራ ወረዳዎች

ሞዴል መነሻ የሚሆን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በሜጫ ወረዳ ተጎብኝቷል፡፡ ከክልል የውይይት መድረክ በመቀጠል ውይይቱ በዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ደረጃ ተመሳሳይ ውይይት እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡

ሠ/ የልምድ ልውውጥ ማካሄድ

በአመቱ ዞን፣ ወረዳና ተፋሰስ የመልካም ተሞክሮ ማዕከላት ሆነው የሚያገለግሉ ተፋሰሶችን በመለየትና፣ ከተመረጠው ተፋሰስ ልምድ በመውሰድ በየአካባቢው እንዲተገበር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ

ተደርጓል፡፡ በተለይ የብዙ አመት ልምድ ሳይኖረው በአጭር የተቀናጀ ተፋሰስ በመተግር የህብበረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የጀመረው ሜጫ ወረዳ የብዙዎቹ ምእራብ አማራ ወረዳዎችና የሰሜን ሸዋ መማሪያ

ወረዳ ነበር፡፡ ከሜጫ ወረዳ የተወሰደው ትምህርት በአመራር፣ባለሙያና የህብረተሰቡ ጥምረት በአጭር ጊዜ አካባቢን መጠበቅና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ሲሆን የአመራር ዋና መለኪያም ባለሙያውና መላ

ህብረተሰቡን የውስጥ ስሜትና መነሳሳት ወደልማት መቀየር መሆኑን አጉልቶ ያሳየ ነበር፡፡ በተለይ ደ/ጎንደር 1491 ፣ ሰሜን ሸዋ 730 ፣ ሰሜን ጎንደር 421 ተሳታዎች ልምድ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የተፋሰስ እቅድ ዝግጅት

በዚህ አመት የተከሰተዉ ድርቅ በአንድ በኩል ከሰራናቸዉ ተፋሰሶች የተገኙ ጥቅሞችን የምናጣጥምበት በሌላ በኩል ደግሞ የሰራነዉን ያክል ድርቁን ሊሸከም የሚችል የተፈጥሮሀብት ልማት ስራ ባለመስራታችን

የምንቆጭበት መሆኑን የተማርንበት ሲሆን ይህንንም መሰረት በማድረግ የዚህ አመት የተፈጥሮሀብት ልማት ለማከናወን ከምንጊዝዉም በላይ ጊዜ ተወስዶ በጥራት ከተሰሩ ስራዎች አንዱ የእቅድ ዝግጅት ስራችን ነዉ፡፡

በመሆኑም

o የክልሉን ስነ- ምህዳር መሰረት በማድረግ መሰረታዊ ችግሮችን በመለየት ለእያንዳንዱ ችግር መተግበር የሚገባቸዉን ቴክኖሎጅዎች በማቀድ ቀጠናን መሰረት ያደረገ ያሉንን የተፈጥሮሀብት ጸጋዎች መሰረት

በማድረግ የታቀደ ነዉ፡፡

o ሁሉም የተፈጥሮሀብት ልማት ስራዎቻችን ሲታቀዱ ዉሃን ማእከል በማድረግ እና የህ/ ሰብ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ የተቀናጁ ናቸዉ፡፡

በእቅዱ ወቅት የ 2008 የምንሰራቸዉ የአፈርና እርጥበት እቀባ ስራዎች የቴክኖሎጅ ትስስርና ቅብብሎሽ የሚታይበት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም የተፋሰስ ጥናትና ክለሳችን ጥራት ያለዉ መሆን እንዳለበት እንዲኖረው

15

ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት 7042 የነባር ተፋሰሶች ክለሳ፣ 838 አዲስ ተፋሰሶች ጥናት በድምሩ 7880 ተፋሰሶች በአጠቃላይ ሊጠና ከታቀደዉ (83%) ተጠንቷል፡፡

የግብዓት እና የልማት መሳሪያዎች ዝግጅት

በዚህ ዓመት ፈጻሚውን ሃይል ለማዘጋጀት የተሰጠውን ትኩረት ያክል በግብዓት አቅርቦት ረገድ የተሰራው ስራ የተሻለ ነበር፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ከዚህ በፊት የተሰራጩ የልማትና የቅየሳ መሳሪያዎች ቆጠራ በማጠናቀቅ፣

በአ/ አደሩ በግል ይዞት የሚወጣውን በመለየትና ከፍተቱ የሚሞላበትን አግባብ በማስቀመጥ ቀደም ብሎ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ ከሚያስፈልገው 2,708,470 ( አካፋ እና አዷማ) የነፍስ ወከፍ የልማት መሳሪያ 2,727,998

(101%) የተሟላ ሲሆን በቡድን ደረጃ ከሚያስፈልገው 1,083,388 የልማት መሳሪያ ( ድጅኖ እና መዶሻ) 227,373 (42%) የቡድን የልማት መሳሪያዎች ( ድጅኖ እና መዶሻ) ቆጠራ እና እንዲሟላ ተደርጓል፡፡ በነፍስ

ወከፍ ደረጃ የሚስፈልገው የልማት መሳሪያ በክልል ደረጃ በቂ ቢሆንም ግን በስርጭት ችግር ያለበት ነበር፡፡

የሚሰራ ሰዉ ሀይል መለየት፣ ማደራጀትና ስራው የሚሰራባቸውን አከባቢዎች መለየት

በ 2008 ላከናወንናቸው የተፈጥሮ ሀብት የልማት ስራ የሚሰራ ጉልበትን በጥራትና በተደራጀ መልኩ አስቀድሞ

በመለየትና በህብረተሰብ በማስተቸት ለልማት ስራ ዝግጁ በማድረግ በኩል እንደ ክልል 2,714,973 ወንድ

2041,746 ሴት በድምሩ 4,756,719 (95%) ጉልበት ተለይቷል፡፡

የሰብል ልማት የንቅናቄ መድረኮችን በተመለከተ

የተቀናጀ የግብርና ልማትንና የሰብል ክላስተርን በማካሄድ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበር

የሰብል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሻሻል ዓላማ በማድረግ ነው ወደ ተግባር የተገባው :: በዚህ መሰረት በ 2006/07 የምርት ዘመን የተገኘውን የዋና ዋና ሰብሎች 87.6 ሚሊየን ኩ/ ል አጠቃላይ ምርት

በ 30% በማሳደግ በ 2008/09 የምርት ዘመን በጠቅላላው 116,462,857 ኩ/ ል ምርት ለማምረት ጻቅዷል፡፡

የተነደፈውን ግብ ውጤታማ ለማድረግ በዘንድሮው ዓመት ከሌሎች ዓመታት ለየት ባለ ሁኔታ ለመፈፀም ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ ይህም ማለት ከአጠቃላይ የሰብል ልማታችን ውስጥ በስድስት ዋና ዋና ሰብሎች

ማለትም በበቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ የቢራ ገብስና ሠሊጥ ተመርጠው ክላስተርን መሠረት ባደረገ (Commodity Cluster Approach) 1,099,863 ሄ/ ር መሬት በማልማት 42,280,090 ኩ/ ል ምርት /36%/ ለማምረት ግብ ተቀምጧል፡፡

በዚህ መሰረት ተቋማዊ አደረጃጀቶችንና የአርሶ አደር አደረጃጀቶችን የማጠናከር ሥራ በማከናወን ቀጣይ ፈጻሚን በአመለካከት በክህሎትና በግብዓት የማዘጋጀትና የማስታጠቅ ሥራ በዚህ ዓመት በልዩ ትኩረት የተከናውነ ሲሆን

በክልል ደረጃ ክላስተርን መሰረት ባደረገ የተመረጡ የኮሞዲቲ ሰብሎች የንቅናቄ ዕቅድ እና በክልላችን በምግብ፣

16

በኢንዱስትሪና ኤክስፖርት ሰብልነት በዋናነት ጠቀሜታ ያላቸዉን ሰብል ዓይነቶች በመለየት በልዩ ትኩረት ሰነድና ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለባለሙያዎች አርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ይህንን ግብ በተቀመጠበት አግባብ መፈፀም እንዲቻል ፈፃሚውን የማዘጋጀት ሥራ ቁልፍ ተግባር ሆኖ ተግባር ተገብቷል፡፡ በዚህ መሠረት በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ፣ በቀበሌ እና በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ደረጃ በየደረጃው መድረኮች ተዘጋጅተው በአጠቃላይ 2,884,976 /82.5%/ አርሶ አደሮች በየደረጃው ሥልጠና

ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሥልጠናው ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው በተመረጡ ሰብሎች ብቻ ያተኮረና በተግባር የተደገፈ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ሥልጠና በተለይም የቢራ ገብስ ልማት ሥልጠና አርሶ አደሮችን በክልሉ በሚገኙ 3 የግብርና ኮሌጆች በማስገባት ማሰልጠን ተችሏል፡፡

በክልል ደረጀ የንቅናቄ መድረክ

በክልል ደረጃ በሰብል ልማት የንቅናቄ መድረኮች ተካሂደዋል፡፡ የክልል ዞንና የወረዳ የገጠር ኮማንድ ፖስት በተገኙበት ሰፊ የማቀጣጠያ መድረክ በማዘጋጀት የ 2008/9 የሰብል ልማት ዕቅድ ማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቢራ ገብስ ልማት በበቆሎ ሰብል ልማት ፓኬጅ ስልጠና በማሽላ ልማት ፓኬጅ በክልል ደረጀ ለባለሙያው እንዲሁም ለአርሶ አደሩ በወረታ ግብርና ኮሌጅና በመርጦለ ማርያም ግብርና ኮሌጅ በኮምቦልቻ

ግብርና ኮሌጅ የተግባር ስልጠና ከመሰጠቱ በተጨማሪ እያንዳንዱ ሰልጣኝ ባለሙያም ሆነ አርሶ አደር በተግባር ምዘና እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡ በዚህም እያንዳንዱ አርሶ አደር በተግባር ተመዝኖ እንዲያልፍ መደረጉ ለተግባሩ

ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዎፀኦ አድርጓል፡፡

በዞን ደረጃ የተደረገ የንቅናቄ መድረክ

በክልሉ ዞኖች ማለትም ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በ 13 ቱም ዞኖች የክረምት ስብችንን መሠረት በማድረግ የሰብል ልማት

የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ ለመድረኩ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የዞን የሥራ ሂደት መሪዎች ተሣትፈዋል፡፡ ከ 4,614 ተሣታፊ 4,451

ክፍል ሁለት

የአበይት ተግባራት አፈፃፀም

በክፍል ሁለት የሪፖርቱ ክፍል በክልል ግብርና ቢሮ እስክ ቀበሌ መንደርና አርሶ አደር ድረስ በሰብል ልማት፣

በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ፣ በመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት በግብአት አቅርቦትና ስርጭት በእንስሳት ሃብት

ልማት፣ በህብረት ስራ ማህበራት ማስፍፊያና ማደራጃ የስራ ክፍል፤ በግብርና ምርምር፤ በደን ልማትና ጥበቃ

እንዲሁም ዘር ብዜትና ዕጸዋት ኳራንታይን በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራት በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቶ

ቀርቧል።

17

1. ሰብል ልማት ና ጥበቃ

የሰብል ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደ ክልልም ሆነ እንደ ሃገር ለሚደረገው ሃገራዊ ድህነትን የመዋጋት ተግባር

ዋናውና በአመዛኙ ወሳኝ ምርት የሚጠበቅበት ወቅት የመኸር ሰብል ልማት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሰብል ልማት

ስራችን 85 በመቶ የሚሆነውን አርሶ አደር የሚሳተፍበት ወሳኝ ተግባራችን በመሆኑ በተቻለ መጠን በልዩ ትኩረት

ከእቅድ ዝግጅት እስከ ስልጠናና ትግበራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰርት በዚህ በተያዘው

የምርት ዘመን እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

የ 2007/08 ምርት ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም

ባሳለፍነው የመኸር ወቅት ተከስቶ የነበረውን የዝናብ መቆራረጥና ድርቅ ለመከላከል እንዲቻል በበልግ በዘነበው ዝናብ

የተገኘውን ጠብታ ውሃ በማሰባሰብ በወቅቱና ፈጥነው ሊደርሱ የሚችሉ የሰብልና የጓሮ አትክልቶችን በመዝራት በድርቅ

ለተጐዱ አካባቢዎች ችግሩን ለመቋቋም አቅም መፍጠር ተችሏል፡፡

በቀጣይ ጊዜያትም ውሃን በመያዝ የተሻለ ምርት ለማምረት ሰፊ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የደረሱ

የበልግ ሰብሎች በዝናብ እንዳይበላሹ ፈጥኖ በመሰብሰብ ማሣውን ለቀጣይ ሰብል ማዘጋጀት ትኩረት የሚሰጠው

ተግባር ነው፡፡ አልፎ አልፎ እየጣለ ያለውን ከባድ ዝናብ በተመለከተ በሰው፣ በእንስሳትና በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያስከትል

ጥንቃቄ ማድረግ ስለሚያስፈልግ ይህንን መሰረት ተደርጎ የተግባር ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል፡፡

በ 2007/08 የመኸር ሰብል ልማት እንቅስቃሴ ተጨባጭ ሁኔታ ስንመለከተው በ 2007/08 ዓ. ም ከበፊት አመት

በተሻለ መልኩ ጥሩ ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን ተጨባጭ ስራዎች መመልከት ይቻላል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በቂ እርጥበት በነበረባቸው አካባቢዎች በቂ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ማሰራጨት የተቻለ ሲሆን

በዚህም ከመቸውም ጊዜ በተለየ መልኩ ከ 3 ሚሊየም በላይ ማዳበሪያ ማሰራጨትና ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡

ይህም ከባለፈው አመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው ማየት የተቻለ ሲሆን በክልሉ ታሪክ ከ 3 ሚሊየን ኩ/ል

በላይ የአፈር ማዳበሪያ ሲሰራጭ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህን መሰረት በማድረግ በ 2007/08 የመኸር ሰብል

ምርትን በተመለከተ በማዕከላዊ እስታትስቲክስ ኤጄንሲ የመኸር ምርት ትንበያ መረጃ መሰረት በክልሉ 87.46 ሚሊየን

ኩንታል ምርት ተገኝቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሰብል ስብጥር በዳግም ሰብልና ሰብልን በቅብብሎሽ በመዝራት ከ 508,000 ሄ/ ር በላይ በሰብል

መሸፈን ተችሏል ይህ አሰራር በድርቅ ምክንያት ልናጣ የምንችለውን ምርት ለማካካስ በማካካሻ ዕቅድ እየተመራ

የተከናወነ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ከ 1.2 ሚሊየን ኩ/ ል በላይ የአካባቢ ዘርን በማበጠርና በዘር ልውውጥ ጥቅም

ላይ ማዋል የተቻለበት ነበር፡፡

የተሻለ ምርት በሚገኝበትና በቂ እርጥበት በነበረበት የምዕራብ አማራ የክልሉ ክፍል ለሰብል ተስማሚና ምቹ የአየር

ንብረት የነበረበት ሁኔታ በመኖሩ እንዲሁም በጥቁር አፈር ልማትና ህያው ማዳበሪያ በመጠቀም ሰፊ ማሳ መሸፈን

መቻሉ በ 2007/8 ምርት ዘመን ከባለፈው አመት የተሻለ ምርት ማግኘት እንደሚቻል አመላካች ተግባራት ናቸው፡፡

18

በዚህ መሰረት በ 2007/08 ምርት ዘመን ከመኸር ሸብል 87.46 ሚ/ኩ/ ል ማግኘት የተቻለ ሲሆን የበልግና የመስኖ

ምርትን ጨምሮ 90.6 ሚ/ኩ/ ል ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡

በድርቅ ውስጥ ሆነንና ከ 1.2 ሚ/ሄ/ ር የሚደርስ መሬት በዝናብ እጥረትና በድርቅ በተጎዳበት እንዲሁም

558,896 ሄ/ ር መሬት ሙሉ በሙሉ በድርቅ በወደመበት ሁኔታ እንዲሁም የዝናብ ስርጭቱ በ 1977 ዓ/ም

ከነበረው የድርቅና ረሃብ ወቅት በ 45% የቀነሰ የዝናብ መጠንና ስርጭት በተገኘበት አመት ላይ ሆነን ከባለፈው

ከ 2006/07 ምርት ዘመን

በ 200,000 ኩ/ ል ብቻ ያነሰ ምርት መገኘቱ ምን ያህል ጠንካራ ስራ እንደተሰራ መረዳት ይቻላል፡፡

የበልግ ሰብል ልማት

በ 2007/8 ዓ. ም የነበረው የበልግ ዝናብ አጥጋቢ ባለመሆኑ ምክንያት ያሳለፍነው የበልግ ወቅት እጅግ ዝቅተኛ

ምርት የተገኘበት አመት ነበር ይሁን እንጂ በያዝነው ምርት ዘመን በ 2008/9 የተፈጠረው እርጥበት ለበልግ ስራችን

ተስማሚ ስለነበር በዚህ አመት የታየው የበልግ አፈፃፀም የተሻለ ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በበልግ ወቅት

የታየውን እርጥበት ለመጠቀም የተቻለውን ያህል እርብርብ የተደረገ ሲሆን በመኸር ያጣነውን የሰብል ምርት ማካካስ

እንዲቻል በያዝነው የበልግ ሰብል ልማት 253,516 ሄ/ ር በማልማት 2,644,235 ኩ/ ል ለማምረት ታቅዷል፡፡

በዚህ መሠረት እስካሁን 1 ኛ እርሻ 219,062 ሄ/ ር ፣2 ኛ እርሻ 170,672 ሄ/ ር ፣ 3 ኛ እርሻ 93,518 ሄ/ ር እና

አራተኛ እርሻ 3,064 ሄ/ ር መሬት ማረስ ተችሏል፡፡ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር በ 1,977 ሄ/ ር በመብለጥ ያሳያል፡፡ ከታረሰው መሬት ውስጥ 193,927 ሄ/ ር በዕቅድ ከተያዘው 76.5% በሰብል ተሸፍኗል፡፡

ለዚህው የበልግ ስራ 2002.5 ኩ/ ል ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ እና 152,825.5 ኩ/ ል (71.7%) የተለያዩ

ዘሮች ቀርቦ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

እንደዚሁም ለበልግ ስራ 1,215,719 ሜ/ ኩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ /ኮምፖስት/ ለመጠቀም ከተዘጋጀው ኮምፖስት

ውስጥ 764,107 ሜ/ ኩ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይሁን እንጂ ልክ እንደ መኸር ወቅት ተገቢውን የማዳበሪያ መጠን

አለመጠቀም እና የታቀደውን ሄ/ ር ሙሉ በሙሉ በዘር አለመሸፈን በበልግ ስራችን የነበሩ እጥረቶች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የበልግ ሥራው በተሻለ ሁኔታ የተከናወነ መሆኑን የሚያመላክት ቢሆንም የተዘራውን ሰብል ወቅቱን

ጠብቆ መሰብሰብና ከጉዳት መጠበቅ በቀጣይ በትኩረት መሰራት የሚገባው ተግባር ነው፡፡

የ 2008/09 የመኸር እርሻ ሥራ ዝግጅት

የዚህ ዓመት የመኸር ሥራ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ የመጀመሪያው ባለፈው የመኸር

ወቅት ያጣነውን ምርት ለማካካስ ጥረት የምናደርግበትና ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ በቀጣይ የበልግ ወቅት

የሚኖረውን የዝናብ መመናመን እና በምርት ቅነሣ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ በሚያስችል መልኩ

በተጠናከረ ሁኔታ የምንቀሳቀስበት የመኸር ወቅት ነው፡፡

19

በዚህ መሠረት 4,465,835.76 ሄ/ ር መሬት በማልማት 116 ሚሊዮን ኩ/ ል ለማምረት ታቅዷል፡፡ እስካሁን

ባለው 4,330,842 ሄ/ ር (97%) ማረስ ተችሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ 131,611.63 ሄ/ ር በትራክተር የታረሰ መሬት ነው፡፡ በትራክተር ይታረሳል ተብሎ በሁለተኛው ዕትዕ

መጨረሻ አመት ከተያዘው 500,000 ሄ/ር ጋር ሲታይ የ 26.3% ድርሻ አለው፡፡

በዚህ መሠረት እስካሁን 2,786,660 ሄ/ ር መሬት በሰብል መሸፈን ተችሏል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ 62.4% በሰብል ተሸፈኗል፡፡ በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 1,328,075 ሄ/ር(51%) በመስመር ተዘርቷል፡፡

ክላስተርን መሠረት ያደረገ የተመረጡ የኮሞዲቲ ሰብሎች ዕቅድ አፈጻጸም

በዚህ በያዝነው የመኸር ወቅት ከሌሎች ዓመታት ሥራችን ለየት የሚያደርገው በተመረጡ የኮሞዲቲ ሰብሎች ላይ

በማተኮር ተጨማሪ ምርት ለማምረት መታቀዱ ነው፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ

ባለሙያዎችን እንዲሁም አርሶ አደሮችን በማሰልጠን በእያንዳንዱ የሰብል ኮሞዲቲ አርሶ አደሩም ሆነ ባለሙያው

በምዘና ስርኣት እንዲያልፍ ማድረግ ተችሏል፡፡

በዚህ መሠረት በ 6 የሰብል ዓይነቶች ማለትም የቢራ ገብስ፣ ማሽላ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ሰሊጥና ጤፍን

በ 1,118,635 ሄ/ ር መሬት በማልማት 42,280,090 ኩ/ ል ምርት በማምረት ከመኸር ዕቅዳችን 36% የሚሆነውን ምርት ከኮሞዲቲ ሰብሎች ለማልማት ታቅዷ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ በዚህ መሠረት፡-

1. ቢራ ገብስ

በምርት ዘመኑ በ 14,085 ሄ/ ር መሬት ላይ ቢራ ገብስ ለማልማት ታቅዶ 14,085 ሄ/ ር (100%) መሬት

ተለይቷል፡፡ ከተለየው መሬት ውስጥ 12,836 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10,539 ሄ/ ር በሰብል ተሸፍኗል

ከዚህ ውስጥ በሙሉ ፓኬጅ 2,916.5 ሄ/ ር መሬት ተዘርቷል። በዚህም የግብአት አጠቃቀምን በተመለከተ ጥቅም

ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 8,295.4 ኩ/ ል ሲሆን ማዳበሪያ ደግሞ 10,869 ኩ/ ል ነው፡፡

2. ማሽላ

በምርት ዘመኑ በ 135,425 ሄ/ ር መሬት ላይ ማሽላ ለማልማት ታቅዶ 104,718 ሄ/ ር (77%) መሬት ተለይቷል፡፡

ከተለየው መሬት ውስጥ 94,401.5 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 57,975.25 ሄ/ ር ከእቅዱ 43% ተዘርቷል፡፡ ከተዘራው መሬት ውስጥ 28,951 ሄ/ ር መሬት በመስመር የተዘራ ሲሆን 21,678 ሄ/ ር መሬት በሙሉ

ፓኬጅ የተዘራ ነው፡፡ በዚህም የግብአት አጠቃቀምን በተመለከተ ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 1,731 ኩ/ ል ሲሆን

ማዳበሪያ ደግሞ 21,608.6 ኩ/ ል ነው፡፡

3. በቆሎ

በምርት ዘመኑ በ 302,186 ሄ/ ር መሬት ላይ በቆሎ ለማልማት ታቅዶ 306,480 ሄ/ ር ከእቅዱ 101% የማሣ

ልየታ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከተለየው መሬት ውስጥ 306,480 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 285,883 ሄ/ር

20

ተዘርቷል፡፡ ከተዘራው መሬት ውስጥ 221,580 ሄ/ ሩ በሙሉ ፓኬጅ የተዘራ ነው፡፡ በዚህም የግብአት አጠቃቀምን

በተመለከተ ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 54,224 ኩ/ ል ሲሆን ማዳበሪያ ደግሞ 957,088 ኩ/ ል ነው፡፡

4. ስንዴ

በምርት ዘመኑ በ 322,596 ሄ/ ር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ 289,487.5 ሄ/ ር ከእቅዱ ›100% የማሣ

ልየታ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከተለየው መሬት ውስጥ 292,435 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 180,802 ሄ/ር

ተዘርቷል፡፡ ከተዘራው መሬት ውስጥ 123,577 ሄ/ ሩ በሙሉ ፓኬጅ የተዘራ ነው፡፡ በዚህም የግብአት አጠቃቀምን

በተመለከተ ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 83,403.9 ኩ/ ል ሲሆን ማዳበሪያ ደግሞ 160,895.5 ኩ/ ል ነው፡፡

ሰሊጥ

በ ምርት ዘመኑ በ 260,959 ሄ/ ር መሬት ላይ ሰሊጥ ለማልማት ታቅዶ 239,329 ሄ/ ር ከእቅዱ 92% የማሣ

ልየታ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከተለየው መሬት ውስጥ 210,334 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 192,059 ሄ/ር

ተዘርቷል፡፡ ከተዘራው መሬት ውስጥ 471.65 ሄ/ ሩ በሙሉ ፓኬጅ የተዘራ ነው፡፡ በዚህም የግብአት አጠቃቀምን

በተመለከተ ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 41.4 ኩ/ ል ሲሆን ማዳበሪያ ደግሞ 6,600.4 ኩ/ ል ነው፡፡

5. ጤፍ

በ ምርት ዘመኑ በ 220,021 ሄ/ ር መሬት ላይ ጤፍ ለማልማት ታቅዶ 181,650 ሄ/ ር ከእቅዱ 86% የማሣ ልየታ

ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከተለየው መሬት ውስጥ 188,888 ሄ/ ር የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 54,245 ሄ/ ር ተዘርቷል፡፡

ከተዘራው መሬት ውስጥ 30,034 ሄ/ ሩ በምርጥ ዘር፤ በማዳበሪያና በመስመር የተዘራ ነው፡፡ በዚህም የግብአት

አጠቃቀምን በተመለከተ ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር 2,418.73 ኩ/ ል ሲሆን ማዳበሪያ ደግሞ 61,200 ኩ/ል

ነው፡፡

የአፈር ለምነት ማሻሻል ተግባራት

የአፈር ለምነትን ለማሻሻል እንዲቻል የኮምፖስት ማዘጋጀትና መጠቀም፣ የአሲዳማ አፈር ልማት፣ የጥቁር አፈር

ልማትና የህያው ማዳበሪያ አጠቃቀም ሥራዎች በትኩረት ተግባራዊ ለማድረግ በዕቅድ ተይዘው እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መሰረት የኮምፖስት ዝግጅትና አጠቃቀም ስንመለከተው ለ 2008/09 ምርት ዘመን 62 ሚሊዮን ሜ/ኩ

ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ለመኸር 47,483,600 (77%) ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ

በአመለካከትና በክህሎት በአርሶ አደሩና በባለሙያው ዘንድ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ የሄደ ተግባር መሆኑን

መገንዘብ ያስችላል፡፡

ከተዘጋጀው ኮምፖስት ውስጥ 45,735,508 ሜ/ ኩ ኮምፖስት ለመኸር እንዲሁም 1,215,719 ሜ/ ኩ ለበልግ

ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ፡፡ የተዘጋጀ ኮምፖስት ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 0.56 ሚሊየን ሜ/ኩብ

በመብለጥ ያሳያል፡፡ የሚዘጋጅ ኮምፖስት ተብሎ በሁለተኛው ዕትዕ መጨረሻ አመት ከተያዘው 78 ሜ/ ኩብ ጋር

ሲታይ 60.4% ድርሻ ያለው በመሆኑ በጥሩ የአፈፃፀም ደረጃ የሚፈረጅ ተግባር ነው፡፡ ይህም የሚያመላክተው አርሶ

21

አደሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት እየሰጠ ያለው ትኩረትና የግንዛቤ ደረጃው እያደገ መምጣቱን

ነው፡፡ ከአፈር ለምነት ማሻሻያ ተግባራት መካከል የኮምፖስት ዝግጅት ለአፈር ለምነት መሻሻል ጉልህ አስተዋጸኦ ያለው ተግባር ነው፡፡

ሌላው የአፈር ለምነት ለማሻሻል ከምንጠቀምባቸው ተግባራትና ሳይንሳዊ አሰራሮች መካከል አሲዳማ አፈርን በኖራ የማከም ስራ ሌላው ተግባር ነው፡፡ አሲዳማ አፈር ልማትን በተመለከተ በዚህ ዓመት 160,000 ኩ/ ል ኖራ

በማቅረብ 8,000 ሄ/ ር አሲዳማ መሬትን ለማልማት ታቅዶ 22,003 ኩ/ ል ኖራ በመጠቀም 770.87 ሄ/ር

ለምቷል፡፡ የለማ መሬት ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 500 ሄ/ ር በመብለጥ ያሳያል፡፡ በሁለተኛው ዕትዕ

መጨረሻ አመት ይቀርባል ተብሎ ለተያዘው 200.000 ኩ/ ል ኖራ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡

በክልሉ የአሲዳማ አፈርን በኖራ ለማከም የሚያስችል የኖራ ማምረቻ መፍጮዎች ተተክለው ኖራ በማምረት ላይ

ይገኛሉ ስለዚህ የግብአት አቅርቦት ችግሩ እየተፈታ በመሆኑ የአሲዳማ መሬትን በኖራ የማከም ስራ ተጠናክሮ

እንዲቀጥል በአርሶ አደሩና በባለሙያው ዘንድ ያለውን የአመለካከትና የክህሎት ክፍተቶች እየለዩ ተደጋጋሚ የአቅም

ግንባታ ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባቸው ያመላክታል፡፡ በተለይ በአንዳንድ አርሶ አደሮች ዘንድ እየታየ ያለውን ኖራ

በነፃ ይቅረብልን አመለካከት መስበር ተገቢ ይሆናል፡፡ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም የሞዴል አርሶ

አደሮች ማሳ በሰርቶ ማሳያነት ማገልገልና በክህሎት ያለውን ክፍተት ለመድፈን በርትቶ መስራት ከባለሙያው

የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡

የጥቁር አፈር ልማት ስራ ትርፍ ውሃን በማንጣፈፍ በአንድ መሬት ላይ ሁለት ጊዜና ከዚያ በላይ ማምረት መቻል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በምርት ዘመኑ 460,000 ሄ/ ር በማጠንፈፍ 11,960,000 ኩ/ ል ምርት

ለማምረት ታቅዶ እስካሁን 189,934 ሄ/ ር ማሳ የጠነፈፈ መሆኑን መረጃው ያሳያል። በዚህም ተሳታፊ የሆኑ

አ/ አደሮች ወንድ 153,546 እና ሴት 10,301 ድምር 163,847 ናቸው፡፡

በክልሉ ከ 700,000 ያላነሰ የጥቁር አፈር እርሻመሬትመኖሩን የተደረጉጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ክልሉ ካለው

እምቅ አቅም ጋር ሲመዘን በዚህ የምርት ዘመን የተሰራው የጥቁር አፈር ማጠንፈፍ ከወቅቱ አንፃር ሲመዘን

የተሻለ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ምክንያቱም የጥቁር አፈር ልማት ስራ በቂ ዝናብ ባለበት ወቅት

በማንጣፈፍ የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የማሳዉ እርጥብት ሳይለቅና በተገኘዉ እርጥበት ሁሉ እርሻ መጀመርና በኒሽ ወቅት ዘር

ለመዝራትና ዳግምሰብል ለማምረት ያለዉን እድልመጠቀምትኩረትሚሰጠውተግባር ነው፡፡

የህያው ማዳበሪያ አጠቃቀም በ 2008/09 ምርት ዘመን 250,584 ሳቸት ህያው ማዳበሪያ በመጠቀም

62,646 ሄ/ ር መሬት በማልማት 1,503,504 ኩ/ ል ምርት ለማምረት የታቀደ ሲሆን 13,433 ሳቸት

በመጠቀም 3,358 ሄ/ ር እንዲለማ ተደርጎል ፡፡ በቀጣይ የጥራጥሬ ሰብሎች የሚዘሩበትን ወቅት በመጠበቅ ሰፊ

የህያው ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ይከናወናል፡፡ በአርሶ አደሩ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ሰፊ በመሆኑ የጥራጥሬ

ሰብሎችን በስፋት ለማምረትን ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

22

የ 2007/08 ምርት ዘመን ዘር ብዜት ሥራ

ክልሉ በምርጥ ዘር አቅርቦት ራሱን በመቻል ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ እርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ

መሰረት በክልሉ ምርጥ ዘርን ለማባዛት በተቆቋመው በአማራ ምርጥ ዘር ድርጅትና በግል ዘር አባዥ ድርጅቶች በ

2007/08 የመኸር ወቅት ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚህ መሰረት በኢንተርፕራይዙ 118,771 ኩ/ ል ምርጥ ዘር ተሰብስቦ 118,740 ኩ/ ል ተጎጉዟል ፡፡ ከተሰበሰበው ምርጥ ዘር ውስጥ 97,148 ኩ/ ል ምርጥ

ዘር ተበጥሮ በ 71,950 ኩ/ ል የናሙና ፍተሸ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5,226.76 ኩ/ ል በፍተሻው ወድቋል፡፡

ቀሪው ምርት ዘር ተበጥሮና ታሽጎ ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

የግል ዘር አባዥ ድርጅቶች በተመለከተ በግል ዘር አባዥ ድርጅቶች 54,130 ኩ/ ል ለማምረት እቅድ ተይዞ 46,217 ኩ/ ል (85%) ዘር ተሰብስቧል ፡፡ የግል ዘር አባዥ ድርጅቶች የክልሉን የምርጥ ዘር ፍላጎት ለማሟላት የበኩላቸውን

ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡ በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ከመኸር ዘር ብዜት በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ እና

በግል ዘር አምራች ድረጅቶች 164,988 ኩ/ ል ምርጥ ዘር ተሰብስቧል፡፡

ይህ ቁጥር የሚያመላክተው በዚህ ተግባር ጠንክረን መስራት ካልተቻለ በስተቀር የክልሉን ምርጥ ዘር ፍላጎት

በቀላሉ ማሟላት አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ በቀጣይ የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝም ሆነ የግል ዘር

አምራች ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰብ አርሶ አደሮች ለዘር ብዜት ስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራትና በቂ

ምርጥ ዘር በአይነትና በመጠን ለአርሶ አደሩ ማቅረብ እንደሚገባ ያመላከተ ተግባር ነው፡፡

የ 2008/09 የመኸር ወቅት የዘር ብዜት

በ 2008/09 መኸር ወቅት 22,228 ሄ/ ር መሬት ላይ በተለያዩ አባዥ ድርጅቶች ማለትም በአማራ ም/ዘር

ኢንተርኘራይዝ፣ በግል ድርጅቶችና ዩኒዬኖች የተለያዩ የሰብል ዝርያወችን ቅ/ መስራች መስራችና የተመሠከረለት

ም/ ዘር ለማባዛት የታቀደ ሲሆን የሚጠበቅ ምርትም 527,392 ኩ/ ል ነው፡፡ በመሆኑም እስከ አሁን በዘር የተሸፈነ

ማሣ 5,756.175 ሄ/ ር ሲሆን ለዚህም የቀረበ ዘር 6,910.585 ኩ/ ል ከዚህ ውስጥ የተሠራጨው 3,520.68 ኩ/ ል ነው፡፡

በዝርዝር ስንመለከተው፡-

1. አማራ ም/ ዘር ኢንተርኘራይዝ

በተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን በቅ/ መስራችና መስራችና የተመሰከረለት ዘር ለማባዛት የታቀደ 10,115 ሄ/ ር መሬት

የተከናወነ 3,416.4 ሄ/ ር አፈፃፀሙ 34% ነው፡፡

2. በየግል ዘር አባዥ ድርጅቶችና ዩኒዮኖች

23

በተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን በቅ/ መስራችና መስራችና የተመሰከረለት ዘር ለማባዛት ዕቅድ 12,113 ሄ/ ር ክንውን

2,339.81 ሄ/ ር አፈፃፀሙ 19.31% ነው፡፡

2. የ አትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ስራዎች

በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ

በ 2008 በጀት አመት የመስኖ ልማት ስራዎችን በልዩ ትክረት ለማከናወን በርካታ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በክልል ደረጃ ያሉ ባለሙያዎችን በመልካሳ ማሰልጠኛ ማዕከል በፌዴራል ደረጃ

የአሰልጣኞች ስልጠና እንዲሰለጥኑ ተደርጓል፡፡ በፌዴራል ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የክልሉን በመስኖና አትክልትና ፍራፍሬ እየሰሩ ያሉ የዞንና የወረዳ ባለሙያዎችን በምራብ አማራና በምስራቅ አማራ

በሁለት ቡድን በመክፈል የማሰልጠን ስራ ተከናውኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቀበሌ ደረጃ የመስኖ ኮንፈረንሶችን በማከናወን ከ 1.5 ሚሎየን በላይ አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡

ስልጠናው የተከናወነው በሰሃሴ ወር 2007 በመሆኑ የመስኖ ልማት ስራው የወንዝ የምንጭና የጉድጓድ ውሃ መጠን ሳይቀንስ ፈጥኖ ወደ ተግባር ለመግባት አስችሏል፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን የዝናብ እጥረት

ግምት ውስጥ በማስገባት የመስኖ ልማት የንቅናቄ መድረክ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በመቅደላ ወረዳ እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የመስኖ ንቅናቄ በኣል በማዘጋጀት የተግባር ምዕራፊን ማሰጀመር

ተችሏል፡፡

ከዘህ ጎን ለጎን ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የምርጥ ዘር ግብአትና የውሃ ማሰባሰቢያ ጆኦሜምብሮኖችን በስፋት ማሰራጨት ተችሏል፡፡

በተግባር ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት

በክልሉ ከመኸር ስራችን ቀጥሎ በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራና ከዓመት ዓመት ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት

የአርሶ አደሩን ህይወትና ኑሮ በማሻሻል አርሶ አደሩ ልጆቹን እንዲያስተምርና የዘመናዊ ኑሮ ተቋዳሽ እንዲሆን

በማድረግ ከዚህ በተጨማሪ በበጋ ወቅት የነበረውን የስራ ባህል በመቀየር ዓመቱን በሙሉ በስራ በማሳለፍ ምርት

እንዲያመርት ያደረገና በአርሶ አደሩ ህይወት በተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ተግባር ነው የመስኖ ልማት ስራችን፡፡

የመስኖ እርሻ ልማትን በመጠቀም የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብል ልማትን በማስፋፋትና ምርታማነትን በመጨመር

ጥራትና ደረጃዉን የጠበቀ ምርት በማምረትና ለገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩንና የአገሪቱን ገቢ ማሳደግ የዘርፉ

ዓላማ ነው፡፡

የዘርፉን ዓላማ ለማሣካት በዘመኑ ከባቢያዊ የመስኖ እርሻ ልማትን የሚያረጋግጥ በአመለካከት የተለወጠ፣

በክህሎት የዳበረ፣ በአሰራርና አደረጃጀቱ የተሻለና የተጠናከረ የመስኖ ግብርና ምክር አገልግሎት መስጠት የሚችል

ባለሙያ በየደረጃው መፍጠር፣በመስኖ እርሻ ልማት የተያዘዉን 885 ሽህ ሄ/ር እቅድን በተሟላ መንገድ በመፈፀም

24

አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ፣ በ 2007 ዓ. ም የነበሩ 13 የቡና ልማት ክላስተር ወረዳዎችን ወደ 23 ማስፋት፣

4.7 ሚሊዮን የነበረዉን የችግኝ ዝግጅት ወደ 6.1 ሚሊዮን በፕሮጀክት፣ 5.79 በመደበኛ በድምሩ 11.89 ሚሊዮን የቡና ችግኝ በማዘጋጀት 3641 ሄ/ ር ተጨማሪ መሬት ማልማት፣ ምርታማነትን ከ 3.7 ኩ/ ል በሄ/ ር ወደ

6.5 ኩ/ ል በሄ/ ር በማሣደግ 33,493 ኩ/ ል የቡና ምርት በማምረት 2500 ኩ/ ል ምርት ለማዕከላዊ ገበያ

ማቅረብ፣ የአካባቢዉን ስነ ምህዳር መሰረት በማደረግ በ 29 የቆላ፣ በ 43 የደጋ እና በ 8 የሙዝ ከላስተር

ወረዳዎች 9.3 ሚሊዮን የቆላ ፍራፍሬ ልማት ( ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ብርቱካን ወዘተ) ፣ 1.7 ሚሊዮን ደጋ ፍራፍሬ፣ 1.5 ሚሊዮን የሙዝ በድምሩ 12.4 ሚሊዮን ችግኝ በማዘጋጀትና ተከላ በማካሔድ የክልሉን የመስኖ ልማት ሽፋን

በማሻሻል የተጠቃሚ አርሶአደሩን ቁጥር 2,479,667 በነበረው ላይ 330,000 በመጨመር 2,809,667 ማድረስ የሚሉት ዋና ዋና ግቦችን በመንደፍ ነው በዚህ ዓመት ወደ ተግባር የተገባው፡፡

በዚህም መሠረት እስከዚህ በበጀት አመቱ እስከ 11 ኛው ወር ድረስ በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በ 2008 ዓ. ም በመስኖ ልማት ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት በዝናብ መቆራረጥና በድርቅ ያጣነውን ምርት ለማካካስ

ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም መሠረት የወንዝና የምንጭ ውሃ መጠን ሳይቀንስ ወደ ተግባር በመግባት በትንሽ ውሃ

በአጭር ጊዜ ሊደርሱ የሚችሉ ሰብሎችን ለመዝራት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡

በዓመቱ 885,112 ሄ/ ር መሬት በማልማት 106 ሚሊዮን ኩ/ ል ምርት ለማምረት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ሥራ

ተገብቷል፡፡ በተሰጠው ልዩ ትኩረትና ርብርብ በ 1 ኛ ዙር በነባር 769,577 ሄ/ ር እና በአዲስ 53,235 ሄ/ር

በድምሩ 822,812 ሄ/ ር /93%/ መሬት የታረሰ ሲሆን ከታረሰው በነባር 766,573 ሄ/ ር እና በአዲስ 51,680 ሄ/ ር በድምሩ 818,790 ሄ/ ር (99.4%) መሬት በዘር ተሸፍኗል፡፡ ከዕቅዱ 93% በዘር ተሸፍኗል፡፡የተዘራ መሬት

ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 10,573 ሄ/ ር በመብለጥ ያሳያል፡፡ ይህ የሚያስረዳን የመስኖ ልማት

ስራው ከአመት ወደ አመት የተሻለ አፈፃፀም እየታየበት የሄደና አርሶ አደሩ ለመስኖ ልማት የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ

መሆኑን መገንዘብ ያስችላል፡፡

የመስኖ ልማትን በግብአት በመታገዝ ለማልማት በተደረገው ጥረት የማዳበሪያ አጠቃቀም በሁለቱም ዙር

426,712 ኩ/ ል ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅ ያስረዳል፡፡

በሁለተኛው ዕትዕ መጨረሻ አመት ይሰራጫል ተብሎ ከተያዘው ማዳበሪያ 2,001,772 ኩ/ ል ጋር ሲታይ 21% ድርሻ አለው፡፡ የተሰራጨ ማዳበሪያ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 105,862 ኩ/ ል በመብለጥ

ያሳያል፡፡ ምርጥ ዘር አጠቃቀም በ 2 ቱም ዙር 111,110 ኩ/ ል ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ጥቅም ላይ የዋለ ምርጥ ዘር

ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጸጸር በ 17,151 ኩ/ ል በመብለጥ ያሳያል፡፡

ባጠቃላይ የ 2008 በጀት አመት የመስኖ ልማት ስራችን የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የረዳና ህብረተሰቡ በያለበት

ተረጋግቶ ወደ ልማት እንዲገባ ያስቻለ ከዚህ በተጨማሪ እይንዳንዷን ጠብታ ውሃ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለመጠቀም

የተቻለበት በምርጥ ዘርና በግብአት አጠቃቀም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መሻሻል የታየበት

25

ሁለተኛ ዙር መስኖ ልማት

በአንደኛዉ ዙር ከለማው የመስኖ መሬት ቀድመዉ ከተሰበሰቡ ሰብሎች ለሁለተኛ ዙር መስኖ ለማልማት ዕቅድ

256,525 ሄ/ ር መሬት ተይዞ ወደ ተግባር ተገብቷል በዚህ መሰር እስካሁን 181,116 ሄ/ ር መሬት የታረስ ሲሆን

ከታረሰው መሬት 180,350 ሄ/ ር መሬት ማለትም 70.3% በዘር ተሸፍኗል፡፡ የተሳተፉ አ/ አደሮች ቁጥር ወንድ

183,843 ሴት 26603 በድምሩ 210,446 አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል::

እስከአሁን በአዲስና በነባር በድምሩ 2,414,366 አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 290,905 ሴቶች

ናቸው፡፡

ምርት አሰባሰብን በተመለከተ በዚህ በጀት አመት በመስኖ ልማት የተገኘው ምርት ምንም እንኳን አጠቃላይ ምርት

ተሰባስቦ ያልተጠናቀቀ ቢሆንም በአጠቃላይ እስካሁን ከ 1 ኛ ዙር 90.6 ሚሊዮን ኩ/ ል እና ከ 2 ኛ ዙር 14.2 ሚሊዮን ኩ/ ል በድምሩ 104.7 ሚሊዮን ኩ/ ል ምርት በመስኖ ተገኝቷል ፡፡ ይህም ከእቅዱ 93.5% ነው፡፡ የመስኖ

ልማት ምርት መሰብሰብ መቻሉ በድርቅ ምክንያት ሊከሰት የነበረውን የገበያ አለመረጋጋት በማርገብ ትልቅ ሚና

ተጫውቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች በፍጥነት ሊደርሱ የሚችሉና በትንሽ የውሃ ፍጆታ

ሊደርሱ የሚችሉ እንደ ጎመንና ድንች ያሉ የጓሮ አትክልቶችን በማብቀል ህብረተሰቡ ከተመረተው ምርት ተጠቃሚ

በመሆን በሙሉ ተስፋ ወደ ስራ እንዲገባ አስችሏል፡፡

የቡና ልማት

በክልላችን ለቡና ልማት ስራ የተሠጠው ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተሸሻል መጥቷል፡፡ ቡና ልማት በክልሉ

አርሶ አደር ሂወት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥና የኑሮ ማሻሻል ከግምት ውስጥ

በማስገባት የክልሉ መንግስትና ግብርና ቢሮ በልዩ ትኩረት በማየት ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እየጠደረገ

የረገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ከመቸውም ጊዜ በተለየ መልኩ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ በአማራ ክልል ስም ማቅረብ

የተቻለበት ደረጃ ደርሰናል፡፡ በዚህ ምክንያት ይህንን ተግባር አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲቻል በርካታ ስራዎች

እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ከዚህ ውስጥ የቡና ልማት ዝግጅት ቀዳሚው ተግባር ነው፡፡

የቡና ልማት ችግኝ ዝግጅትን በተመለከተ በምርት ዘመኑ በመደበኛና በፕሮጀክት 11.89 ሚሊ/ ችግኝ ለማዘጋጀት

ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ እስካሁን ድረስ በድምሩ 11.501 ሚሊዮን ችግኝ የተዘጋጀ ሲሆን 96.72% አፈጻጸም

አሣይቷል፡፡ እስከአሁን ድረስ 2.88 ሚሊዮን ጉድጓድ ተዘጋጅቷል፡፡ በአጠቃላይ 43,750 አርሶ አደሮች ከዚህ

ውስጥ 4,267 ሴቶች አ/ አደሮችን በማሳተፍ 4.24 ሚሊየን ችግኝ ተጓጉዞ 4.06 ሚሊዮን ችግኝ በ 1618 ሄ/ር

መሬት ላይ ተተክሏል።

የቆላ ፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅትና ተከላ

26

የቆላ ፍራፍሬ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት 9.8 ሚሊዮን

የቆላ ፍራፍሬና 1.5 ሚሊዮን የሙዝ ችግኝ በድምሩ 11.3 ሚሊዮን የቆላ ፍራፍሬ ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዷ እስካሁን

6.8 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጀቷል። የተዘጋጀ ችግኝ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 2.34 ሚሊዮን ችግኝ

በመብለጥ ያሳያል፡፡በጠቅላላ በሁተኛው ዕትዕ መጨረሻ ይዘጋጃል ተብሎ ከተያዘው 56.63 ሚሊዮን እቅድ ጋር

ሲነጻጸር 12% ድርሻ አለው፡፡ እስከአሁን 3.32 ሚሊዮን ጉድጓድ ተቆፍሮ 2.03 ሚሊዮን ችግኝ ተጓጉዞ በ 7,853 ሄ/ ር መሬት ላይ 1.99 ሚሊዮን ችግኝ የተተከለ ሲሆን 46,855 አ/ አደሮች /6189 ሴቶች/ ተሳትፈዋል።

ደጋ ፍራፍሬ ልማት

በዚህ የበጀት ዘመን 1.7 ሚሊዮን የተከተበ 1.9 ሚሊዮን ያልተከተበ በድምሩ 3.67 ሚሊዮን ችግኝ ለማዘጋጀት

በእቅድ ተይዞ 1.116 ሚሊዮን የተከተበ 0.584 ሚሊዮን ያልተከተበ በድምሩ 1.7 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጅቷል፡፡

በዚህ ተግባር 3,125 አርሶ አደሮች ከዚህ ውስጥ 261 ሴቶች ተሣታፊ ሲሆኑ 393,484 ጉድጉድ ተቆፍሯል፡፡

በጠቅላላ በሁተኛው ዕትዕ መጨረሻ ይዘጋጃል ተብሎ ከተያዘው 24.27 ሚሊዮን እቅድ ጋር ሲነጻጸር 8% ድርሻ

አለው፡፡

በምርት ዘመኑ የተከሰተውን ድርቅ ጉዳት ለመቀነስ የተከናወኑ ተግባራት

በክልላችን የተከሰተውን የክረምት ዝናብ መቆራረጥና እጥረት ተከትሎ በምሥራቁ የክልላችን ክፍል በሚገኙ 8 ዞኖች፣ በ 83 ወረዳዎች፣ በ 802 ቀበሌዎች በተለያየ የጉዳት ደረጃ መጠን በሰብልና በእንስሳት ላይ ጉዳት

አስከትሏል፡፡ በዚህ ምክንያት በሰብል ምርት ሥራችንና በእንስሳት መኖና የመጠጥ ውሃ እጥረት አጋጥሟል፡፡ በዋግኸምራ፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብ/ ዞን፣ በሰሜን ሸዋ ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች

እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የክልሉ አካባቢዎች ማለትም በሰሜን ጎንደር ዞን ተከዜ ተፋሰስ አካባቢ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ምሥራቃማ ወረዳዎች እና በምሥራቅ ጐጃም ዞን በአባይ ሸለቆ አዋሳኝ ወረዳዎች ችግሩ በስፋት ጐልቶ የታየባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

ችግሩ ሰፋ ባሉ ዞኖችና ወረዳዎች የተከሰተ በመሆኑ የተከሰተው ድርቅ ከዚህ በፊት ከታዩትና ካሣለፍናቸው ሁሉ የከፋ መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም፡፡ በዚህ መሠረት የክልሉ ግብርና ቢሮ የችግሩን ስፋትና የጉዳት መጠን

በመረዳት ችግሩን መቀልበስ ባይቻልም እንኳ መቋቋም የሚያስችሉ ግቦችን ፈጥኖ በመንደፍ የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወንና አደጋውን ለመቀነስ ጥረት ተደርጓል፡፡

ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ

በ 2007/8 ዓ. ም የመኸር ዎቅት በኢሊ ኒኖ መከሰት ምክንያት የዝናብ ስርጭት ችግር እንደሚያጋጥምና በተለይ

በሰብልና እንስሳት ላይ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው በተነበየው መሰረት የሚገጥመውን የእርጥበት ችግር

ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ የክልሉን የዝናብ ስርጭት በ 1997 ዓ. ም ከነበረው ጋር በማዛመድ

የስነ ምህዳር ቀጣናውና መሰረት በማድረግ በየዞኖቹ የእርጥበት እጥረት ሊያጋጥመው የሚችል መሬት ስፋት፣

27

የሚያጋጥመው የእርጥበት መጠንና ይህን ችግር መቅረፍ የሚያስችሉ የቴክኖሎጅ አማራጮች ተመልክተው በክልል

ደረጃ ከተሰጠው ኦረንቴሽን ተከትሎ በወረዳ ደረጃ ለ 2,428 አመራሮችና 2,159 ባለሙያዎች ኦረንቴሽን በተዋረድ

ተሰጥቷል፡፡ በቀበሌ ደረጃ ለ 5,495 ባለሙያዎችና ለ 1,003,242 አ/ አደሮች በችግሩ ዙሪያና ችግሩን መቋቋም

በሚያስችሉ የቴክኖሎጅ አማራጮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ የተለያዩ ስራዎች እንዲተገበሩ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የተከሰተዉን አሉታዊ ተጽእኖ በአመዛኙ መቅረፍ የሚቻለው አርሶ አደሩ በማሳው ውስጥ

የምትገኘውን እርጥበት በጥንቃቄ ለሰብሉ እንዲደርስ ማድረግ ከቻለ ብቻ መሆኑን እንዲገነዘብ በማድረግ ሰፊ ስራ

ተሰርቷል፡፡

ችግሩን ለመከላከልና ለመቋቋም የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ ተግባራት

በየወረዳው ያለውን ሁኔታ በማየት ስራዎች በየደረጃው ትኩረት ተሰጥተው እንዲከናወኑና አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ

ጉዳዮችን በመለየት ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ቡድን

በምስራቅ አማራ በሰ/ ወሎ፣ ደ/ ወሎና ኦሮሚያ ዞኖች የመስክ ምልከታ የተካሄደ ሲሆን፣ በየደረጃው ያለውን አመራርና

ህብረተሰቡን የማወያየት ስራ ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ቡድን ደግሞ

በሰ/ ጎንደርና ዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች የመስክ ምልከታና የህብረተሰብ ውይይት ተደርጓል፡፡ ችግሩን

ለመከላከል ይቻል ዘንድ በክልል ግብርና ቢሮ በተዘጋጀው የመከላከያን የማካካሻ እቅድ መሠረት ስራዎች

በየደረጃው ተከናውነዋል፡፡

1. ውኃ ማሰባሰብ

አርሶ አደሩ በማሳው ውስጥ የምትገኘውን እርጥበት በጥንቃቄ ለሰብሉ እንዲደርስ ለማድረግ እንዲችል ጠብታ

ውሃን የማሰባሰብ ሰፊ የግንዛቤ ስራ ከተሰራ በኃላ ችግሩ ባለባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ባለፈው ክረምት ወቅት

ከ 493,869 ሄ/ ር በላይ የእርሻ መሬት የተለያዩ የእርጥበት እቀባ ስራዎች የተከናወነ ሲሆን አንጻራዊ በመሆነ

መንገድ ችግሩ በነበረባቸው አካባቢዎች የሰብል ምርትም ሆነ ለእንስሳት የሚሆን መኖ የተገኘው በእነዚህ

አካባቢዎች ነው፡፡ በተጨማሪም 633 ጊዜያዊ ግድቦች፣ 40 ሜ3 መያዝ የሚችል 4,152 አነስተኛ ኩሬዎች

በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተቆፍረዋል፡፡

በክልሉ ባሉ 7 የ ልማት ድርጅቶች በ 46 ማሽነሪዎች በ 7 ዞኖች በ 30 ወረዳዎችና 83 ቀበሌዎች 704,869 ሜ/ ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 170 ኩሬዎች ተገንብተው 114 (67%) ውሃ ይዘው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

በመጋዝን የከረመውን ጨምሮ ከ 4046 በላይ የጅኦሜምብሬን እንዲነጠፍ ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ድርቁን ለመከላከል በተመደበ በጀት 22,264 ጥቅል ጅ ኦሜምብሬን ተገዝቶ ተሰራጭቷል፡፡ በ 2007 ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመስኖ አውታሮችን በፍጥነት ተጠናቀው ወደስራ እንዲገቡ ከፍተኛ ርብርብ

ተደርጓል፡፡

ከፌዴራል መንግስት ለድርቅ መጠባበቂያ በጀት በተላከ ገንዘብ 51 ግድቦች ለመገንባት ስራ የተጀመረ ሲሆን የጥናት ዶክምንት ስራ ተጠናቆ የመሰረት ቁፋሮ ስራ የጀመሩ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን እና ሰሜን

28

ጎንደር ዞን 100% ፣ ደቡብ ወሎ 84% ፣ ደቡብ ጎንደር 83.3% ፤ሰሜን ወሎ 80% ሰሜን ሸዋ 75% ፤ ኦሮሞ

ብሄረስ ዞን 33% ላይ የሚገኙ ሲሆኑ እንደክልል የቁፋሮ ስራው 83.3% ላይ ደርሷል፡፡

የመሰረት ቁፋሮ ስራ ያጠናቀቁ ዞኖችና ወረዳዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ዞን 4 ወረዳዎች ሲሆኑ እነርሱም

ወረባቦ፣ መቅደላ፣ ተንታ እና ደላንታ የአምስት ግድቦች ፤ ዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን ጋዝጊብላ፣ ደሃና፣ ሰቆጣ፣ ሰሃላ፣

ዝቋላ እና አበርገሌ የአስር ግድቦች፤ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ ላይ አንድ ግድብ ስራ፤ ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና፣

ላስታ እና ዳውንት፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴና ሸበል ናቸው ባጠቃላይ 25 ግድቦች ቁፋሮ አጠናቀዋል፡፡

የግንባታ ስራ የጀመሩ ደግሞ፡ ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ እና ወረባቦ ሶስት ግድቦች ዋግ ህምራ ዞን ጋዝጊብላ፣ ደሃና፣

ሰቆጣ፣ ሰሃላ፣ ዝቋላ እና አበርገሌ በሚገኙ አስር ግድቦች ሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ አንድ ግድብ በጠቅላላ

በሁሉም ዞኖች አስራ አራት ግድቦች ላይ የግንባታ ስራ ተጀምሯል፡፡

የማህበረሰብ ኩሬ ግንባታን በተመለከተ ድርቁ በተከሰተባቸው በ 8 ቱ ዞኖች 232 ኩሬዎች ለማሰቆፈር በእቅድ

የተያዘ ሲሆን እስካሁን በ 215 ኩሬወች የቁፋሮ ስራ የተጀመረባቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 47 ኩሬዎች

ተጠናቀዋል፡፡

2. ሰብል ልማት

የዘር ስራው በወቅቱና በስፋት አለመጀመርና በሰብል ሊሸፈን የሚገባው መሬት በወቅቱ አለመሸፈን፣ አርሶ አደሩ

በመደበኛዉ ሁኔታ የሚዘራቸውን የሰብል አይነቶች በመተዉ ፈጥነዉ ሊደርሱ የሚችሉ እንደማሾ እና ሽምብራ

የመሣሠሉ የሰብል አይነቶችን እንዲዘራ መደረጉ፣ በአንዳንድ ወረዳዎች ቀደም ብለዉ በደረቅ የተዘሩ ሰብሎች ሳይበቅሉም የቀሩበት ሁኔታ መኖር ፣ በዚህም ከተዘራው ማሳ 165,557 ሄ/ ር ሳይበቅል የቀረ ሲሆን 146,980

ሄ/ ር በተተኪ ዘር መልሶ እንዲዘራ ተደርጓል፣ ይሁን እንጂ በተተኪ ዘር የተሸፈነውም ቢሆን በዝናብ እጥረት ሳቢያ

አለመብቀልና የበቀለውም ቢሆን የጠወለገ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፣

በተለያዩ ወረዳዎች በእርጥበት እጥረት ሳቢያ በርካታ ማሳዎች በዘር ሳይሸፈኑ የቀሩና ተዘርተውም ቢሆን ምርት

የማይሰጡትን በመለየት በ 8 ዞኖች በሚገኙ 42 ወረዳዎች በፌደራል መንግስት በጀትና በተለያዩ አካላት ድጋፍ

11,583 ኩ/ል ተተኪ ዘር ተገዝቶ ለ 52,119 አ/ አደሮች ተሰራጭቶ 9,856 ሄ/ር በዘር ተሸፍኗል፡፡ ከዚህ

በተጨማሪ በምዕራቡ አማራ የነበረውን በቂ እርጥበት በመጠቀም በምስራቁና ድርቅ በተከሰተባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ልናጣ የምንችለውን ምርት ለማካካስ በተነደፈው የማካካሻ ዕቅድ መሠረት 576,985 ሄ/ ር መሬት

በዳግም ሰብል ልማት በሰብል ስብጥርና በቅብብሎሽ ማልማት ተችሏል፡፡

በ 2008/9 የመኸር ወቅት የሚኖረውን የክረምት ዝናብ በመጠቀም የተሻለ ምርት ማምረት እንዲቻል ከመደበኛው የዘር ድልድል በተጨማሪ በተለያዩ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ከወዲሁ የዘር

አቅርቦት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ስንዴ ቀቀባ ዝርያ 3,255 ኩ/ ል ስንዴ ዳንፌ ዝርያ 2,508

29

ኩ/ ል ጤፍ ቁንጮ ዝርያ 1,399 ኩ/ ል ጤፍ ቦሰት ዝርያ 18 ኩ/ ል በቆሎ 661 ዝርያ 240 ኩ/ ል ማሽላ ጊራና 371 ኩ/ ል በድምሩ 7,791 ኩ/ ል ድርቅ ለተከሰተባቸው 8 ዞኖች ተገዝቶ ቀርቧል፡፡

3. መስኖ ልማት

የመስኖ ልማት ስራችን ከሌሎች አመታት ለየት የሚያደርገው ነገር በሚከተሉት ነጥቦች ነው፡፡

የዝናቡን ስርጭትና መጠን ቀድሞ በመገንዘብ የመስኖ ስራው ወንዞችና ምንጮች መጠናቸው ከመቀነሱ

በፊት እንዲጀመር መደረጉ፡፡

በትንሽ ውሃ ፈጥነው ሊደርሱ የሚችሉ ሰብሎችን እንዲዘሩ ለአርሶ አደሮች በኮንፈረንስና በስልጠናወች

መሰጠቱ፡፡

ፈጥነው ሊደርሱ የሚችሉ እንደ ስኳር ድንች ቁርጥራጭ፤ ጉመን፤ ድንችና ፤የመልካሳ በቆሎ የመሳሰሉትን

ሰብሎች ዘር አፈላልጎ ገዝቶ በማቅረብ በድርቅ ለተጎዱ አርሶ አደሮች ማቅረብ መቻሉ፡፡

የውሃ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጂዎችን በማስመረትና በመግዛት ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በስፋት

መሰራጨቱ

ውሃን በቅጠባና ሳይንሳዊ በሆን የአጠጣጥ ዘዴ አርሶ አደሩ እንዲጠቀም መደረጉ

አመታዊ የክልሉን የመስኖ በኣል አከባበርን በልዩ ትኩረት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢ እንዲከበር

መደረጉና በሁሉም ዘንድ ተነሳሽነት መፈጠሩ፡፡

አርሶ አደሩ በተከሰተው ድርቅ ተስፋ ቆርጦ አንገቱን እንዳይደፋ የመስኖ ኮንፈረንሶችን በስፋት በማካሄድ

በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉ ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

ድርቁ በተከሰተባቸው 8 ዞኖች በሚገኙ 71 ወረዳዎች ለመስኖ ልማት የሚያስፈልግ ግብኣት እንዲቀርብ በተደረገው

ጥረት መሰረት 8.03 ሚሊዮን የስኳር ድንች ቁርጥራጭ ቀርቧል ከዚህ ውስጥ 6.35 ሚሊየን ቁርጥራጭ በ 8 ቱ

ዞኖች በሚገኙ 42 ወረዳዎች ተከላ ተካሂዷል የተተከለው ቁርጥራጭ የመፅደቅ ኢንቨንትሪ በ 33 ወረዳዎች

የተወሰደ ሲሄን ከተወሰደው መረጃ 89% በጥሩ ብቅለት ላይ እንዳለና ምርት መስጠት እንደጀመረ ለማወቅ

ተችሏል፡፡

በተጨማሪ 37.21 ኩ/ ል ካሮት፤ 13,411 ኩ/ ል ድንች፤ 23.27 ኩ/ ል ጎመን ዘር፤ 1439 ኩ/ ል በቆሎ፤

1227 ኩ/ ል ሽንብራ፤ 48 ኩ/ ል ስንዴ፤ 20 ኩል ጤፍ፤ 494 ኩ/ ል ማሾ፤ 19.7 ኩ/ ል የሽንኩርት ዘር ፤ 11,,733 ሽንኩርት ኮረት፤ እንዲሁም 582.42 ሌሎች የጥራጥሬና የአዝርዕት ዘር በድምሩ 28,994.6 ኩ/ ል ዘር በድርቅ

በተጎዱ ኣካባቢዎች ለመስኖ ልማት አገልግሎት ውሏል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ድርቁ በተከሰተባቸው

ዞኖች ውስጥ ባሉ ወረዳዎች ከዚህ በፊት ይለማ ከነበረው በነባርና በአዲስ 500,504 ሄ/ ር መሬት ውስጥ በነባርና

በአዲስ በድምሩ 439,455(87%) ሄ/ ር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመስኖ ልማት ተሸፍኗል፡፡ በዚህ መሰረት

30

በነባርና በአዲስ መስኖ በድምሩ 1,550,945 አርሶ አደሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ድርቁ

በተከሰተባቸው ዞኖችና ወረዳዎች 12,265,669 ኩ/ ል ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡

3. የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም እና ውሃ ማሰባሰብ

በክልላችን ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በየአመቱ የአፈርና ውሃ ክለትን ለመከላከልና የተፈጥሮ ሚዛንን

ለመጠብ ከሚሰሩ ተግባራት መካከልና ዋነኛው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ተግባር ነው፡፡

አርሶ ሰደሩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም በልማት ቡድንና በአንድ ለአምስት የሚሰራ ጉልበትን በመለየት በክህሎት

የሚታዩ ክፍተቶችን ለማጥበብ በቀያሽ አርሶ አደሮች ስልጠናና በተግባር የተፋሰስ ልማት ስራ ክህሎትን በማዳበር

አሁን ባለንበት ደረጃ መድረስ ተችሏል፡፡ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በክልሉ በሚገኙ በሀሉም ዞኖች

ወረዳዎች ቀበሌዎችና ተፋሰሶች አመታዊ በአል በመሆን መከበር ከጀመረ አመታትን አሳልፉል፡፡ በዚህም በርካታ

ለውጦች ተመዝግበዋል፤ ከዚህ በፊት ተመናምነውና ተራቁተው የነበሩ አካባቢዎች መልሰው ማገገም ጀምረዋል፡፡

በተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራችን ካስገኝልን ትልቅ እውቀትና መነሳሳት አንዱና ዋነኛው የጠረጴዛ እርከን ስራ ነው፡፡

ይህ ተግባር አዲስ መሬት በመፍጠር መጣቶችን የመሬት ባለቤት ማድረግ የቻለና የስራ እድል የፈጠረ አዲስ

ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመኖ ልማት ስራው በድርቅ ለተጎዱ እንስሳት መኖ ማግኘት የተቻለው በተፈጥሮ

ሃብት ልማት ስራው ከተከለሉ ተፋሰሶች ነው፡፡ በዚህ መሰረት በዘንድሮው አመትም የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራው

ተጠንክሮ በመቀጠል የሚከተሉት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የአፈር እርጥበት እቀባ ስራ

ሰፊ ጉልበት የሚጠይቁና በሽፋን የሚለኩ ስራዎች የማሳ እና የጋራ ላይ እርከን ስራዎች እንዲሁም የቦረቦር ማዳን

ተግባራት ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት በዕቅድ ከተያዘው 610,090 ሄ/ ር ለማከናወን ተይዞ 526,986 ሄ/ ር (86%) የተከናወነ ሲሆን በዝርዝር የአፈርና እርጥበት እቀባ ስራዎች አፈፃፀም ሲታይ የማሳ ላይ እርከን 467,500 ሄ/ር

ለመስራት ታቅዶ 484,320 ሄ/ ር (104%) ተከናውኗል፡፡ ይህም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን

ዘመን ከተያዘው እቅድ አንፃር ሲታይ 28% የተፈፀመ መሆኑ በጥሩ ጎኑ የሚታይ ተግባር ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የምናየው የቦረቦር ማዳን ተግባር ሲሆን 21,340 ሄ/ ር ለመስራት ታቅዶ 15,954 ሄ/ ር (75%) ተከናውኗል፡፡ በ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን 65,621 ሄ/ ር ቦረቦር መሬት እንዲያገግም በማድረግ

ለተጠቃሚ ለማከፋፈል ለተያዘው እቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ቦረቦር የማዳን ተግባር ተጨማሪ አዲስ መሬት

ከመፍጠር ጋር የሚያያዝ የተለያዩ ማቴሪያሎች የሚጠይቅ ሰፊ የሰው ጉልበት የሚጠቀም ነገር ግን እየተቆረሰ

የሚሄውን መሬት ማዳን የሚችል ተግባር ነው፡፡ በዚህ መሰረት የተሰራው ስራ አበረታች ነው ብሎ መውሰድ ተገቢ

ይሆናል፡፡

በተራራ ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ

31

የጋራ ላይ እርከን በዚህ አመት 117,070 ሄ/ ር ለመስራት ታቅዶ 57,997 ሄ/ ር (50%) ተከናውኗል፡፡ የዚህም

አፈጻጸም በ ሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ከተያዘው እቅድ አኳያ በጥሩ ሁኔታ የተከናወነ መሆኑን ያሳያል ፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ተራራማ መሬቶችን ከልሎ እንዲያገግሙ ማድረግን በተመለከተ 452,700 ሄ/ ር ታቅዶ

233,796 ሄ/ ር (52%) ተከናውኗል፡፡ ይህ አፈፃፀም የሚያመላክተው በአጭር ቀናት ጥራቱን የጠበቀ ስራ

በማሰራት ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በዕውቀትና በክህሎት በማነፅ የስራዎችን የጥራትና ብቃት ደረጃ ማሳደግ

የተቻለ መሆኑን ነው፡፡

የጠረንፔዛማ እርከን የዚህ አመት እቅድ 4,180 ሄ/ ር ክንውን 2,572 ሄ/ ር (62%) ሲሆን ከ 2007 አፈፃፀም

አኳያ ሲታይ የ 347 ሄ/ ር ብልጫ አለው በዚሁም በ ሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ከተያዘው እቅድ አኳያ 5% አስተዋፅኦ አለው፡፡

የተለያዩ የውኃ ማስረጊያ እና የተከላ ስትራክቸሮች 12,349,942 ለማከናወን ታቅዶ 11,581,411 (94%) ተከናውኗል፡፡ የውሃ ማፋሰሻ እና መቀልበሻ ቦይ 5,303 ኪ/ ሜ ለማከናወን ታቅዶ 5,688 (107% ) ተከናውኗል፡፡ የተጋጋጠ ተራራማ መሬት በመከለል እንዲያገግም ማድረግ እቅድ 452,750 ሄ/ ር ሲሆን 233,796 (52%) ተከናውኗል፡፡ በተለያየ መሬት አጠቃቀም የተሰሩ ነባር የማሳ ላይ እና ጋራ ላየ እርከኖችን የደረጃ ማሳደግ እና

ጥገና ስራ ለመስራት 356,600 ሄ/ ር ታቅዶ 244,974 ሄ/ ር (69%) ተከናውኗል፡፡

የሣር ሠርጥ /Grass strip/ ልማት

በዚህ ዓመት በስፋት እንተገብረዋለን ብለን ከያዝነዉ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች አንዱ ሲሆን 5,461 ሄ/ ር ለማስራት

ታቅዶ 6,109 ሄ/ ር (112) ተከናውኗል፡፡ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት 4,068 ሄ/ ር አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር

በ 2,041 ሄ/ ር ብልጫ አለው፡፡ በዚህ መሰረት በስትራቴጅክ ዘመኑ ከተያዘው አጠቃላይ እቅድ በዚህ አመት በተሻለ

ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑ በአነስተኛ ጉልበት ሰፊ መሬት ከክለት የምናድንበት ቴክኖሎጅ ወደ ተግባር መገባቱና

ልምድ የተወሰደበት ተግባር በመሆኑ በቀጣይም ከህ/ ሰብ ጋር በመተማመን በተመረጡ ተፋሰሶች በስፋት

የምናስቀጥለዉ ተግባር ይሆናል::

የውሃ ማሰባሰብ ስራን በተመለከተ

የክልሉን የመስኖ ሽፋንን ለማሳደግ፣ ተጠቃሚነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥና በዚህ ዓመት በምስራቁ የክልሉ ክፍል

በዝናብ እጥረት የምናጣውን ምርት በመስኖ ለማካካስ በሚደረገው ጥረት ዘመናዊና ባህላዊ የመስኖ አውታሮችን

ቁጥር ዓመታዊ ፍሰታቸው አስተማማኝ በሆኑትም ሆነ ባልሆኑት ወንዞች ላይ ተስማሚ በሆነ ቴክኖሎጂ እየተደገፍን

ውሀን መያዝና መጠቀም ዋነኛው የዚህ በጀት ዓመት አበይት ተግባር ነበር::

በዚህ መሰረት በአዲስ 60 ዘመናዊ ወንዝ ጠለፋና ሌሎች ደጋፊና ማስፋፊያ የመስኖ አውታሮች ለስራ ዝግጁ

ለማድረግ የታቀደ ሲሆን 7,583 ሄ/ ር /113%/ ሊያለሙ የሚችሉ 79 ዘመናዊ የወንዝ ላይ የመስኖ አውታሮች

32

ለስራ ዝግጁ ሆነዋል፡፡ ይህም በ 5 አመቱ የጠለፋ ስራ ይሰራበታል ከተባለው 400 ወንዝ ውስጥ 20% መፈፀሙን ያመላክታል፡፡

የማህበረሰብ ኩሬ

በጀት ተመድቦላቸው ከሚሰሩት የውሃ አሰባሰብ ተግባራት መካከል የማኀበረሰብ ኩሬ ቁፋሮ አንዱ ነው፡፡ በዚህ

መሠረት 228 ኩሬ ለማስቆፈርና ለማስገንባት ታስቦ 228 ቅየሣ የተሠራላቸው ሲሆን 177 ቁፋሮአቸው 100% ተጠናቆ 112 ቱ ኩሬ ውሃ የያዙ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ግንባታቸው ከ 25-95% ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም በ 5 አመቱ

ይገነባል ተብሎ ከተያዘው 3000 የማህበረሰብ ኩሬ ውስጥ 6% መፈፀሙን ያመላክታል፡፡

ይህ ተግባር በልዩ ትኩረትና በትጋት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ተግባሮቹ የሚሰሩባቸው ቦታዎች አስቸጋሪነትና

የማቴሪያል እጥረቱን በመቋቋምና በመፍታት ሥራውን ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ሌላው ተግባር

ጂኦሜምብሬን ማንጠፍና ውሀ ማሰባሰብ ተግባር ነው በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት በቁጥር 40,000 ጂኦሜምብሬም ለማሰራጨት የታቅደ ሲሆን በዚሁ መሰረት ከሀምሌ 2007 ዓ. ም ጀምሮ 22,063 ጂኦሜምብሬን

ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፡፡ የተቆፈረ ጉድጓድ ብዛት በቁጥር 15,605 /39%/ ነው:: በአዲስ ጂኦሜምብሬን

202 ሄክታር መስኖ ሊያለማ የሚችል ውሀ ዝግጁ ተደርጓል:: ይህ ተግባር ከአመት አመት ዕድገት እያሳየ የመጣ

ተግባር ነው፡፡ አርሶ አደሩ ማንኛውንም የውሃ አማራጭ በመጠቀም ውሃ በማሰባሰብ የመስኖልማት ስራን በከፍተኛ

ሁኔታ በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም የውሃ ማሰባሰብ ስራ ትልቅ ድራሻ አለው፡፡

አነስተኛ ግድብ ግንባታ

በዚህ ዓመት ግድቦችን በመገንባት ዘላቂ ልማት ለማምጣት በክልሉ መንግሥትና በፌደራል ግብርና ሚ/ ር በጀት

በመመደብ 61 ግድቦች ለማሰራት በእቅድ ተይዞ፦ከዚህ ውስጥ 8 ቱ የመሠት ቁፋሮ የተጠናቀቀላቸው ሲሆን

የመሰረት ሙሊት ስራ የተጠናቀቀበት 9 ግድቦች ናቸው ከዚህ በተጨማሪ 10 ግድቦች ሙሉ በሙሉ ቁመታቸው

ተጠናቋል፡፡

ቀ ሪዎቹ ግድቦች ማለትም 34 በተለያየ የቁመት ደረጃ ሆነው በመሰራት ላይ ያሉ ሲሆን በድምሩ 58 ግድቦች

እየተሰሩ ያሉ ሲሆን አፈፃፀሙ ከእቅዱ 95% ነው ከዚህ ውስጥ 13 ግድቦች ተጠናቀዎል:: በ 5 አመቱ አነስተኛ

ግድብ በመገንባት ውሃ ለማሰባሰብ የተያዘ እቅድ 200 ውስጥ 29% መፈፀሙን ያመላክታል፡፡ ይህን ተግባር

ውጤታማ ለማድረግ የአካባቢን እውቀት የመጠቀምና ህብረተሰቡን የማስተባበርና ለልማት የማሰለፍ ሚናው ከፍተኛ

እንደነበር ማየት ይቻላል፡፡

ደንና አግሮ ፎረስትሪ

33

የ 2008 ዓ. ም ዕቅድ በዋናነት 3 ግቦችን ለማሳካት ያለመ ነው፡፡ ከእነዚህም ግቦች አንዱ የደን ሽፋንን አሁን ካለበት 14% ላይ በ 0.66% በማሳደግ ሽፋኑን ወደ 14.66% ማድረስ ፣ ሁለተኛው የደን ዘርፉን

ከኤክስፖርት፣ ከሀገር ውስጥ ገበያና ከኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር ከደን ምርት የሚገኘው ገቢ ለአጠቃላይ ክልላዊ GDP እድገት እንዲያበረክት ማድረግ ሲሆን በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ያሉንን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን

መጠበቅና መንከባከብ እንዲሁም በህገ- ወጥ መንገድ የሚዘዋወረውን የደን ሀብት መቆጣጠር በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በዚህ በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የተከላ ቦታ ልየ ታና ክለላ

የተከላ ቦታዎችን በመንግስት፣ በወል፣ በግልና በተለያዩ ተቋማት ደረጃ ካርታ በመስራት በተጠቃሚው ህብረተሰብ

በቃለ ጉባኤ በማስደገፍና ክለላ በማካሄድ መለየት ቅድሚያ የተሰጠው ተግባር ነው፡፡ በዚህም መሰረት በዓመቱ

በዕቅድ ከተያዘው 226,409.9 ሄ/ ር ውስጥ 409,501 ሄ/ ር (180%) ተከናውኗል፡፡

ክንውኑ ከዕቅድ የበለጠበት ምክንያት በዓመቱ መጀመሪያ በሥልጠናው ላይ የተከላ ቦታዎች ችግኝ ከመፈላቱ በፊት

መለየት እንዳለበት በተፈጠረው መግባባት አብዛኛዎቹ ዞኖች የተከላ ቦታዎችን መለየት ስለቻሉ ነው፡፡ በዚህ ረገድ

ምዕራብ ጎጃም ዞን የወል ተከላ ቦታን በተለይም ከ 50-100 ሄ/ ር በካርታ በማስደገፍና በቃለጉባኤ በመያዝ

እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው፡፡ የተለየው የተከላ ቦታ በተከላ አይነት ሲተነተን፣

ለግል ተከላ የተለየ መሬት ( ፓኬጅ ያሟላና ፓኬጅ ያላሟላ) 136,726 ሄ/ር(240% ) የወል ተከላ ቦታ ልየታ 71,393 ሄ/ ር (141%) ፣ ለሌሎች ተከላ ቦታ 189,228 ሄ/ር፣

ለመንግሥት ተከላ ቦታ 12,154 ሄ/ ር (270%) በ ድምሩ 409,501 ሄ/ ር (180%) ተለይቷል፡፡

ችግኝ ጣቢያ ማቋቋምና ማካሄድ

በዕቅድ ዘመኑ 1,528,283 አዲስ ችግኝ ጣቢያ ለማቋቋምና 489,127 ነባር ችግኝ ጣቢያ ለማካሄድ ታቅዶ

እስካሁን ክንውን በቅደም ተከተል በአዲስ ችግኝ ጣቢያ ዝግጅት 166,849 (11%) እና ነባር ችግኝ ጣቢያ

ማካሄድ 518,793 (106%) ነው፡፡ የአዲስ ችግኝ ጣቢያ ክንውን ያነሰበት ምክንያት በአካባቢው በተከሰተው

የውሀ እጥረት ምክንያት በግለሰብ፣ በማህበራት፣ በተቋማት እንዲሁም በልማት ቡድን ደረጃ በአዲስ ለማቋቋም

ባለመቻሉ ሲሆን በሚፈላው ችግኝ ላይም ቢሆን የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

ችግኝ ማፍላት

እስከ አሁን ተፈልቶ ለቆጠራ የደረሰ 2.07 ቢሊዮን (84%) ሲሆን ከተዘጋጀው ችግኝ ውስጥ የደን ችግኝ 1.43 ቢሊዮን (174%) ከዚህ ውስጥ 500 ሚሊዮን የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም ሁለገብ

እጽዋት 0.64 ቢሊዮን (25%) ተፈልቷል፡፡

34

በአጠቃላይ በክልሉ ለመኖ ችግኝ ማፍላት አፈጻጸም ማነስ እንደዋና ምክንያት እየተጠቀሰ ያለው የመኖ ችግኞች

ዘግይተው ስለሚዘሩ ለቆጠራ አልደረሱም የሚል ሲሆን ለተከላ ካለን ቀሪ ጊዜ አንጻር በትኩረት መሰራት ያለበት ስራ

ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ በበርካታ ችግኝ ጣቢያዎች የተባዛ በርካታ የሳር ዝርያ ያለ ቢሆንም እሱን ቆጥሮ በማስተላለፍ

በኩል ክፍተቶች ይስተዋላሉ፡፡ ባጠቃላይ ክልሉ ለደን ልማት ስራው የሰጠውን ልዩ ትኩረት ግምት ውስጥ

በማስገባትና የደን ሽፋናችንን ለማሳደግ በተሰራው ስራ የክልሉ የደን ሽፋን ከነበረበት 14% ላይ በ 0.66% በማሳደግ ሽፋኑን ወደ 14.66% ማድረስ ተችሏል፡፡ በተጨማሪ የደን አጠባበቅን ልማት ስራውን ተጠናክሮ

እንዲሄድ የማድረግ ስራ በነባርና አዲስ ችግኝ ጣቢያወች ተጠንክሮ ቀጥሏል፡፡

4. የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት

የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስለተሻሻሉ አሠራሮች በሚያሳምን መልኩ ለገጠር አርሶ አደሮች እውቀት

የሚተላለፍበት የትምህርት ሂደት ሲሆን አርሶ አደሮች ከአካባቢያቸው ጋር የሚጣጣም ውሳኔ እንዲወስኑ

ማስቻልም ነው፡፡ የግብርና ኤክስቴንሽን በሌላ በኩል በየዘርፉ ቀጣይነት ያለው መረጃ አርሶ አደሮች

እንዲያገኙ ማድረግ እና ያገኙትን መረጃ እና ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሚያስችላቸው የእውቀት፣ የክህሎት

እና የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ መርዳት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም በበጀት አመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና

ተግባራት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ

ቢሮው ከሚያከናናቸው ተግባራት መካከል በገጠር የሚገኘውን ስራ አጥ ወጣት ስራ ፈጣሪና ከገጠር ስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ግብርናው እምቅ አቅም እንዳለው ይታመናል፡፡ በዚህ መሰረት በዚህ አመት

ለገጠር ስራ እድል ፈጠራ ለወጣቶችና ለሴቶች ተጠቃሚነት ቢሮው በሰጠው ልዩ ትኩረት መሰረት በምርት ዘመኑ ለ 249,999 ወንድ እና ለ 250,001 ሴት በድምሩ ለ 500,000 ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዞ

ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ አፈፃፀሙን ስንመለከት ለ 206,558 ወንድ እና ለ 49,736 ሴት በድምሩ ለ 256,274 ወጣቶች (51.3%) የስራ እድል ተፈጥሮላቸዎል፡፡ አፈፃፀሙ በዝርዝር ሲቀመጥ፤

በእንስሳት ሃብት ልማት ወንድ 53,672 ፣ ሴት 15,854 ፣ ድምር 69,526 በመስኖ አት/ ፈራፍሬ ልማት ወንድ 69,535 ፣ ሴት 13,629 ፣ ድምር 83,164 በተፈጥሮ ሃብት ልማት ወንድ 42,493 ፣ ሴት 3,600 ፣ ድምር 52,093 በሰብል ልማት ወንድ 40,857 ፣ ሴት 10,654 ፣ ድምር 51,511 ናቸው፡፡ ይህ

ተግባር ቀጣይ በመሆኑ በተለይም በያዝነው የመኸር ወቅት የዝናቡን አጋጣሚ በመጠቀም በልዩ ልዩ የግብርና

ዘርፎች ተሳታፊ እንዲሆኑ በጥንካሬ ይሰራል፡፡ እቅዱን ስንመለከተው ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅብን ያመላከት

ተግባር ነው፡፡

35

የአ/ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ተግባራት

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት በክልሉ የግብርና ኤክስቴንሽን ስርፀት ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ተቋማት ናቸው፡፡

በክልሉ የአርሶ አደሩን ክህሎት ለማሳደግና ተግባራዊ ትምህርት ለመስጠት እንዲቻል የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ድርሻ ከፍተኛ ነው፤፤ በዚህ መሰረት በክልሉ ለተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በ 2988 ቀበሌዎች

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትን በመገንባት የውስጥ ቁሳቁስና ሰርቶ ማሳያ ቦታዎችን በማደራጀት አርሶ አደሩን በተግባር ማስተማርና ማስመረቅ ትችሏል፡፡

ማዕከላት በሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ የሚያንቀሳቅሱትን ተግባር በሚመለከተው የመንግስት ተቅም አዲት ማድረግ

የበጀት አመቱ አንዱ ተግባር በመሆኑ 1355 ማእከላትን ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ እስከዚህ በጀት አመት የኦዲት አገልግሎት

ያገኙት ማእከላት 456 ወይም የእቅዱን 19% ብቻ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ኦዲት ከተደረጉት ማእከላት ውስጥ ትርፍ

ክፍፍል ያደረጉ ማእከላት 296 ወይም 12% ብቻ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ አርሶ አደሩን በተለያዩ የግብርና ሙያዎች በማሰልጠንን ብሎም በምዘና ስርአት እንዲያልፍ በማድረግ ብቁ አርሶ አደር ለመፍጠር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በርካታ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት የተሟላ የሰርቶ ማሳያ ቦታ የሌላቸው መሆኑ ወይንም መሬት አልባ መሆናቸው፡፡ እንዲሁም የአንዳንዶቹ ተቋማት ግንባታ በጥራት መጓደልና በእርጅና ምክንያት የመፈራረስ አደጋ ያጋጠማቸው መሆኑ መሬት ያላቸውም ቢሄን በተሟላ ሁኔታ ወደ ተግባር መግባት አለመቻላቸው በተጨማሪ

ከክልሉ ለመነሻነት የተላከውን ገንዘብ በመጠቀም የሙከራ ስራዎችን በማከናወን በኩል ጉድለት መታየቱ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ለማስገባት እንቅፋት ሆኗል፡፡

ስለዚህ በተለይ የመሬት ይዞታ ጉዳይን በሚመለከት የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ በገጠር ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን እንዲፈታ ከቢሮው ጋር በመሆን በየዞኑና ወረደዎች ያሉ የግብርና መምሪያና ፅ/ ቤቶች ተባብረው መስራትና ይመበቅባቸዋል፡፡

ከላይ የተገለፁ ጥንካሬዎችና ችግሮች እንዳሉ ሆኖ በዚህ አመት በአርሶ ማሰልጠኛ ማዕከላት በአንደኛ ዙር

ለ 588,896 ወንድ እና ለ 56,846 ሴት በድምሩ ለ 645,742 አርሶ አደሮች ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ

477,425 ወንድ እና 40,520 በድምሩ ለ 517,945 (80%) ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጎል፡፡

በሁለተኛው ዙር ለ 419,516 ወንድ እና ለ 47,672 ሴት በድምሩ ለ 467,228 አርሶ አደሮች ስልጠና

ለመስጠት ታቅዶ 367,018 ወንድ እና 29,940 በድምሩ ለ 396,958 (85%) ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጎል፡፡

በሶስተኛው ዙር ለ 231,008 ወንድ እና ለ 24,271 ሴት በድምሩ ለ 255,279 አርሶ አደሮች ስልጠና

ለመስጠት ታቅዶ 183,717 ወንድ እና 173,01 በድምሩ ለ 201,018 (79%) ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጎል፡፡

36

5. የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ሥርጭት

የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት

በ 2008/09 የመኸር ዘመን 3,192,195 ኩ/ ል የአፈር ማዳበሪያ በአዲስ በመግዛት እንዲሁም የከረመውን

660,344.5 ኩ/ ል በመጨመር በአጠቃላይ 3,852,539 ኩ/ ል የአፈር ማዳበሪያ በአመቱ ለማቅረብና

ለማሰራጨት ታቅዷል፡፡

በዚህ መሠረት እስካሁን ድረስ በአዲስ ተገዝቶ ይገባል ተብሎ ከተያዘው 3,332,660 ኩ/ ል ማዳበሪያ ውስጥ

3,911,030 ኩ/ ል (>100%) ወደ ማዕከላዊ መጋዘን ገብቷል፡፡ የከረመ መጠን 660,344 ሲሆን ማዕከላዊ

መጋዘን ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 3,646,544 ኩ/ ል (95%) ወደ መሠረታዊ ማኀበራት ተጓጉዟል፡፡

መሰረታዊ ማህበራት ከቀረበው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 3,201,040 ኩ/ ል 88% ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች

ተሰራጭቷል፡፡

የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት

በምርት ዘመኑ 217,883 ኩ/ ል ምርጥ ዘር ለማቅረብና ለማሰራጨት ታቅዶ እስካሁን ድረስ ከአማራ ምርጥ ዘር

ኢንተርፕራይዝ፣ ከኢትዮጽያ ምርጥ ዘር ድርጅት ፣በመሰረታዊና በዩኒየኖች የከረመ እና ከግል ዘር አምራች ድርጅቶች

በድምሩ 232,242 ኩ/ ል ዘር ተሰብስቧል፡፡ ከተሰበሰበው ለስርጭት የቀረበ 233,230.34 ኩ/ ል ሲሆን

191,064 ኩ/ ል (82%) ምርጥ ዘር ለአርሶ አደር ተሰራጭቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር

ሲነጻጸር በ 300 ሽህ ኩ/ ል ይበልጣል፡፡

የላይም ውህድ አቅርቦትና ስርጭት

በ 2008/09 ምርት ዘመን በአዲስ 50956 ኩ/ ል እና የከረመ 3024.87 ኩ/ ል በድምሩ 53,980.87 ኩ/ል

ለማቅረብና ለማሰራጨት ታቅዶ 14,926 ኩ/ ል ተሰራጭቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከእቀዱ ጋር ሲነጻጸር 29.46% ነው ፡፡

የብድር አቅርቦትና አመላለስ በተመለከተ (ከ 2006/07 እስከ 2008/09 ድረስ)

በ 2008/09 ምርት ዘመን

o ብ ር 4,191,359,712.96 ለዩኒየኖች ብድር እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

በ 2007/08 ምርት ዘመን

o ከባንክ የተሰጠ ብድር ብር----3,973,393,361.24o ለባንክ የተመለሰ ከዋናና የወለድ ብር 3,288,514,001.42o ያልተመለሰ ቀሪ ብድር ዋናና ወለድ ብር---806,834,202.10

37

በ 2006/07 ምርት ዘመን

o ከባንክ የተሰጠ ብድር ብር----3,551,895,314.63 o ለባንክ የተመለሰ ከዋናና የወለድ የተመለሰ ድምር ብር 3,214,890,057.42o ያልተመለሰ ቀሪ ብድር ዋናና ወለድ ብር--------- 596,701,364.74

6. የእንስሳት ሀብት ልማትማስፋፊያ ኤጀንሲ

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የነበሩ ጥንካሬወችን እና እጥረቶችን

በመገምገም ከለያቸው ቁልፍ ችግሮች ዋናው ተግባሮችን በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ ለመፈጸም የሚችል የልማት ሰራዊት መገንባት አለመቻሉ እና በፊዚካል ተግባሮቻችን በዘርፉ ምሰሶ የሆኑትን በእንስሳት መኖ፣ በዝርያ

ማሻሻልና በእንስሳት ጤና የወጡ ፓኬጆችን እና የአሰራር ሞዳሊቲዎችን ያሟላና ሊሰፋ የሚችል ሞዴል መፍጠር አለመቻል መሆናቸውን በመለየት እነዚህን ችግር ለመፍታት በበጀት ዓመቱ በአመለካከቱ እና በክህሎቱ

የተስተካከለ ፈጻሚ ሀይል ለማዘጋጀት እና ተግባራት በተደራጀ የልማት ሰራዊት አግባብ እንዲፈጸሙ ለማድረግ በቅድመ ዝግጅት ወቅት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመረባረብ ተግባራትን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመገምገም በርካታ

የአቅም ግንባታ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

እንስሳት መኖ ልማት

የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እና በትኩረት መሰራት ያለበት በተለያዩ የመኖ

ማልሚያ ስልቶች መኖን ማልማት እና ስነ አመጋገቡን ማሻሻል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም በክልሉ ከ 2003 ዓ. ም ጀምሮ በስፋት በተሰራው የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ስራ ጋር ተያይዞ በየተፋሰሱ የተለያዬ የእንስሳት

መኖ በስፋት እንዲለማ መደረጉ፣ በውስን የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች የተጀመረው የመኖ ማቀነባበር እና የግል

ባለሀብቱ በተጀመረው የአግሮ ኢንደስተሪ የሚመረተው የኢንደስትሪ ተረፈ ምርት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣት እና

በተለይ በከተማ እና ከተማ አካባቢ ያለው የእንስሳት አርቢ ይህን የአግሮ ኢንደስትሪ ተረፈ ምርት ለእንስሳት መኖነት

የመጠቀም ፍላጎቱ እያደገ መምጣት፣ የሚጠበቀውን ያክል ባይሆንም ከመስኖ እና ከበልግ ጋር ተቀናጅቶ የእንስሳት

መኖ ማልማት አልፎ አልፎ ጅምር እንቅስቃሴወች መኖራቸው እንዲሁም የሰብል ተረፈ ምርትን በዩሪያ እና ኢኤም

38

በማከም ተበይነቱን ለማሻሻል ጅምር ስራወች መኖር፣ ልቅ ግጦሽን ለማስቀረት በተደረገው ጥረት በሜጫ እና

ፋርጣ ወረዳወች ለተሞክሮ የሚሆኑ እና ሊሰፉ የሚገባቸው ተግባራት መኖራቸው፣ በምእራብ ጎጃም ዞን በውስን

ወረዳወች የተሻሻለ መኖ በተለይ ሮደስ ሳር እና በደበቡብ ጎንደር ዞን በላይ ጋይንት ወረዳ ከስጋ እና ወተት ምርት ጋር

ማስተሳሰር የሚቀረን ተግባር ቢሆንም በስፋት እየለማ ያለውን የመኖ ጓያ በማልማቱ በኩል ሰፊ ስራ መሰራቱ ቀጣይ

ተጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው ተግባራት ቢሆኑም ከተፋሰስ ልማት ጋር ተያይዞ የለማውን የተሻሻለ መኖ በወቅቱ

ለእንስሳት መኖ አገልግሎት ከማዋል ይልቅ እንስት እየተራቡ ገርጅፎ እና አርጅቶ በየቦታው መታየቱ፣ በየደረጃው

ባለው ፈጻሚ እና አስፈጻሚ አካል ያለውን የአመለካከት ችግር ፈትቶ የልቅ ግጦሽ ስርዓትን በማስቀረት የእንስሳቱን

ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በኩል ሳይንሳዊ አሰራርን መሰረት አድርጎ አለመፈጸሙ እና በከፍተኛ ደረጃ እየተመረተ

ያለውን የሰብል ተረፈ ምርት በዩሪያ እና ኢኤም በማሻሻል ተበይነቱን እና የንጥረ ነገር ይዘቱን በማሻሻል የእንስሳቱን

ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በኩል የተሰራው ስራ እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው

ይገባል፡፡

በመሆኑም እስከ አሁን ባለው መረጃ 306.9 ሚሊዮን (22%) የመኖ ችግኝና ቁርጥራጭ ተዘጋጅቶ ለ 2008 ክረምት ተከላ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

እንስሳት ዘርያ ማሻሻል

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከአንድ የሀገረሰብ ላም በቀን የሚገኘው የወተት ምርት መጠን ከ 1.5 ሊትር የበለጠ አይደለም፡፡ ይህን የወተት ምርታማነት ለመጨመር የአገረሰብ ላሞችን ከተሻሉ የዉጭ ደም ዝርያ ካላቸዉ ጋር የሚያዳቅሉ በ 135 ወረዳዎች 238 የድቀላ ባለሙያዎች አሰልጥኖ በመመደብ የሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎትን ለማስፋፋትና ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት

ከበጀት አመቱ ዕቅድ አፈጻጸም አኳያ እስከአሁን 57,389 (41.4%) የአገረሰብ ላሞችን የተሻለ ደም ካላቸዉ ዝርያዎች ጋር በማዳቀል 22,759 /43.2%/ የተሸለ ደም ያላቸዉ ዲቃላ ጥጆችን ማግኘት ተችሏል፡፡ ይሁን

እንጅ በየደረጃዉ በነበረዉ አመራር የትኩረት ማነስ፤ በባለሙያዉ የክሎትና የቁርጠኝነት ችግር፤ የግብአትና የቴክኖሎጅ አቅርቦቱ በቂና ወቅታዊ አለመሆን አንዲሁም ቴክኖሎጂዉን ለመጠቀም በአርሶአደሩ እና በባለሙያዉ

የነበረዉ የግንዛቤ ዉስንነት የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራችንን ደካማ አድርጎታል፡፡

በሌላ በኩል የክልላችን አርሶ አደር በበግና ፍየል ሃብት ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በምዕራብ ደጋማ የአማራ ደጋማ ወረዳዎች በአካቢያችን በምርታማነቱ የሚታወቀዉን የዋሸራ በግ በመረጣ የተሸሉ አዉራዎችን

ወደአርሶአደሩ በማስገባት እንዲሁም በምስራቅ አማራ ደጋማ ዎረዳዎች የተሸሻሉ የአዋሲ መንዝ ዲቃላ አዉራዎችን በማስገባት የበግ ዝርያን ለማሻሻል ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በዚህ በጀት

አመት እስከአሁን 120,821 /116.8%/ የሚሆኑ የአዋሲ መንዝ ዲቃላ ግልገሎችና 195,778 /33%/ የሚሆኑ የዋሸራ ዲቃላ ግልገሎች ማዋለድ ተችሎአል፡፡ ነገር የተመረጡ አዉራዎች በአግባቡ ባለመመገብና

ጤንነታቸዉ ባለመጠበቁ ምክንያት መስጠት የሚገባቸዉን አገልግሎት አየሰጡ አለመሆን፤ እንዲሁም አዉራን ከአንዱ መንጋ ወደ ሌላ መንጋ እያዛወሩ ባለመጠቀም ምክንያት የዝምደ ርቢ ችግር መከሰት በእርባታዉ ላይ

39

መሰናክል ሆኖአል፡፡ የዚህ መሰረታዊ ችግር ባለሙያዉ ለአርሶአደሩ መስጠት የሚገባዉን ሙያዊ ምክር እና እገዛ ተከታታይና የአርሶአደርን ክሎት ሊያሳድግ በሚችል መልኩ አለመሆን የሚሉት ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የዶሮ ሃብት ልማትን በተመለከተ

ዶሮ ሃብት ልማት የስራ እድል ከመፍጠርና የምግብ ዋስትናን በፍጥነት ከማረጋገጥ አኳያ የሚኖረው ፋይዳ ትልቅ ነው፡፡ የዶሮ እርባታ ስራ በተለይ ለአነስተኛ አርቢዎች፣ መሬት ለሌላቸው/ ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶችን ወደስራ

ለማስገባትና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በክልል ደረጃም

በአመጋገብ ስርዓት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እና በከተሞችና በገጠር የሴቶችን እና የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ

ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንስሳት ኤጀንሲው የተለያዩ የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያዎች በክልሉ በተቋቋሙ ሁለት የብዜት ማዕከላትና ከሌሎች ምንጮች በስፋት በማቅረብ አሰራሩን ሊያሳልጥ የሚያስችል አዲስ የዶሮ ሃብት ልማት

የአሰራር ሞዳሊቲ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም እስከአሁን ባለው አፈጻጸም ለ 797 አሳዳጊዎች 1,733,556 (57.5%) የአንድ ቀን ዶሮ ጫጩቶች የገቡ ሲሆኑ ለ 9,561 ሴት ለአርቢዎች ደግሞ 212,451 የ 45 ቀን ዶሮዎች ተሰራጭተዋል፡፡ በተጨማሪም

በመደበኛ 1,113,993 የ 45 ቀን ዶሮዎች ለአርሶ አደሮች የተሰራጩ መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡

ይሁን እንጅ በአ/ አደሩ እና በወጣቱ የሚታየውን የአመለካከት ችግር ፈትቶ በሞዳሊቲው መሰረት አለመፈጸም፣

የዶሮው ቁጥር በዝቷል የሚለውን የተሳሳተ አስተሳሰብ ሰብሮ አርቢውን ተጠቃሚ ያለማድረግና አርሶአደሩና ሌላው አርቢ የሚያነሳቸውን የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ባለሙያው ሲያስተጋባ መታየት፤ ዶሮ ሃብት ልማት ላይ የሚደረግ ድጋፍና ክትትል እጅግ ዝቅተኛ መሆንና በዘርፉ በባለሙያዎች የኪራይ ሰብሳቢነት ዝንባሌ መታየቱ፤ ለዶሮዎች የቅድመ መከላከያ ክትባትና ሲታመሙ በፍጥነት ህክምና አለመስጠት፣ የእንስሳት እርባታና ጤና ባለሙዎች ተናበው ያለመስራት ችግርና ለዶሮ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ዶሮዎችን ማሰራጨት እና የተሰራጩት ደሮወች ያሉበትን ሁኔታ አለመከተታተል በአፈጻጸም የሚታዩ እጥረቶች ናቸው፡፡

የንብ ሃብት ልማት

ባለው ቅደመ ዝግጅት 31,455 የሽግግር ቀፎ የተሰራና 6,577 ዘመናዊ የቀረበ መሆኑን መረጃው ሲያመለክት በዚህ ስራም ወጣቶችን አደረጃጅቶ ወደ ስራ ከማስገባት አኳያ ጅምር እንቅስቃሴ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ በአካባቢ ቁሳቁስ በአነስተኛ ወጭ የሚሰራውን የሽግግር ቀፎ በማሰራት እና ህብረተሰቡን ተጣቃሚ በማድረግ በኩል ተግባሩን በትኩረት ይዞ አለመሰራቱ፣ በፍሬም ቀፎ ላይ የማነቢያ ቁሳቁስ እጥረት፣ የህብረ ንብና

ሰም እጥረት በአጠቃላይ ስራውን ውጤታማ ከማድረግ አንጻር የክትትልና ድጋፍ ውስንነቶች መሰረታዊ ችግሮች ናቸው፡፡

እንስሳት ማድለብ

40

በእንስሳት ማድለብ በበጀት ዓመቱ 2,002,000 የዳልጋ ከብት፣ 3,570,000 በግ እና 1,697,000 ፍየል በድምሩ 7,269,000 እንስሳት ለማድለብ ዕቅድ ተይዞ 1,529,094 / ከበጀት አመቱ 76.4%/ የዳልጋ ከብት፣

2,799,169/ ከበጀት አመቱ 78.4%/ በግ እና 587,290 ፍየል / ከበጀት አመቱ 34.6%/ በድምሩ 4,915,553 / ከበጀት አመቱ 67.6%/ እንስሳት ደልበዉ ለገበያ ቀርበዋል:: እንስሳትን በማድለብ ረገድ

እየተመዘገበ ያለው አፈጻጸም ከዓመት ዓመት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በዘርፉ ካለው ሀብት አኳያ ውስንነት ያለው

በመሆኑ የማድለቡ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ሲሆን በተለይ የስጋ ምርትን በሚጨምር ስሌት ያለው የመኖ

አቅርቦትና አመጋገብ በትኩረት ሊሰራ ይገባዋል፡፡

እንሰሳት ጤና አገልግሎት

ክልሉ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ባለቤት ይሁን እንጂ በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ምክንያት ተገቢውን ጥቅም እያገኘ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ችግሮች መካከል የእንስሳት በሽታዎች በስፋት መሰራጨትና የሚያደርሱት ጉዳት በጣም ከፍተኛ መሆን ይገኝበታል፡፡ በዓለም ላይ ከታወቁት 15 ድንበር ዘለል በሽታዎች መካከል 8 ቱ በዚሁ ክልል

ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ የክልሉ መንግስት ካለፉት ዓመታት ወዲህ ችግሩን ለመቅረፍ መከላከልን መሰረት ያደረገ የእንስሳት

ጤና አገልግሎት አሰራር እየተከተለ ከመሆኑም በላይ የእንስሳት ጤና ግብአት አቅርቦትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ

እልባት ለመስጠት በክልሉ ከተመደበው 110 ሚሊዮን ብር በጀት በተጨማሪ እያንዳንዱ ወረዳ ለእንስሣት

መድሃኒት ተዘዋዋሪ ፈንድ አገልግሎት የሚውል አካውንት በመክፈት ከ 1,000,000.00 ብር ያላነሰ እንዲመድቡ

አቅጣጨ ተሰጥቶ ተግባራዊ ከመደረጉ በላይ የዋጋ ምለሣ ስርዓት መዘርጋቱና ወደ ስራ መገባቱ በጥንካሬ

የሚወሰድ ተግባር ነው፡፡

የክትባት አገልግሎት

የእንስሳት ጤና አገልግሎት ዋና ስታራቴጂው በሽታን ቀድሞ በመከላከል የእንስሳቱን ጤንነት መጠበቅና የእንስሳቱን ምርታማነት ማሻሻል በዋናነት የተያዘ አቅጣጫ ሲሆን ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎችና መደበኛ

የበሽታ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በበጀት አመቱ ለ 31,018,000 እንስሳት የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ሩብ አመት 26,306,646 (84.8%) እንስሳት የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ በስትራቴጂው መሰረት መከላከል ላይ አተኩሮ ከመስራት ይልቅ ህክምና ላይ

ማተኮር፣ የተጠናከረና ተከታታይነት ያለው የእንሰሳት ጤና ኤክስቴንሽን / የግንዛቤ ማስጨበጥ/ ስራ አለመሰራቱ፣ አርሶ አደሩም ለክትባት ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆንና በሽታ ሲፈነዳ ብቻ የክትባት አገልግሎት መስጠት

የተለመደ መሆኑ እና የባለሙያ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ውስንንት ያለበት በመሆኑ በቀጣይ እነዚህን ውስንነቶች በማስተካከል ውጤታማ ስራ መስራትን ይጠይቃል፡፡

41

የተዘዋዋሪ የእንሰሳት መድሀኒት በጀት አፈጻጸም

እስከአሁን በተደረገው እንቅስቃሴ ከ 148 ወረዳዎች 105,331,043.00 ብር የተዘዋዋሪ በጀት ገቢ የተደረገ

መሆኑን ከወረዳዎች የተገኘው መረጃ ሲያመለክት እስከዚህ ሩብ አመት 1 ሚሊዮን ብርና በላይ የመደቡ 58 ወረዳዎች፣ ከ 1 ሚሊዮን ብር በታች የመደቡ 90 ወረዳዎች እና ምንም ያልመደቡ ወረዳዎች 2 ( ባቲና ፍኖተሰላም

ከተሞች) ናቸዉ፡፡

የኪሊኒክ ግንባታ

እንደሚታወቀው የቀበሌ ክሊኒክ በሌለባቸው በሁሉም ቀበሌዎች በዋነኛነት በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግሰት

ድጋፍ መሰራት እንዳለበት ከ 2006 ዓ/ ም ጀምሮ አቅጣጫ የተሰጠና ስራው የተጀመረ ሲሆን በዚህ በጀት አመቱ

294 ኪሊኒኮችን በወረዳና በቀበሌዎች ለመገንባት ታቅዶ እስከዚህ ሩብ አመት 241 ( ከበጀት አመቱ 81.9%) ብቻ የተሰራ ሲሆን ህብረተሰቡን በማስተባበር ግንባታውን ለመስራት ያለው ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ውስንነት ያለበት

በመሆኑ በቀጣይ ሊስተካከል ይገባል፡፡

7. ግብርናምርምር ተቋም

የግብርና ምርምር ኢንሰቲትዩት የተሰጠው ተልዕኮ የቴክኖሎጂ ማላመድ፣ ማፍለቅ፣ ማስተዋወቅና የመነሻ ቴክኖሎጂ

ማባዛትና ማቅረብ ሥራ ሲሆን በተለያዩ የምርምር መስኮች ጠቋሚ ውጤቶች እንደሚከተለው ተመልክተዋል፡፡

በመሆኑም በ 2008 በጀት ዓመት 91 ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ ዕቅድን ለማሳካት እንዲቻል በተስተካከለ ዕቅድ

645 ሙከራዎችን ለማካሄድ ዕቅድ ተይዞ 586 (90.85%) ማከናወን ተችሏል፡፡ ቀደም ሲል ከነበረው አፈፃፀሙ

ሊቀንስ የቻለው በኢሊኖ ክስተት ምክንያት ሙከራዎች በመቋረጣቸው ነው፡፡ በየምርም መስኩ ውጤት የታየባቸው

ሥራዎች፣

በሰብል ምርምር ዘርፍ ጤፍን በመስመር ለመዝራት እንዲቻል ታስቦ የተሰራው የጤፍ ፍሬን የማሳደግ ስራውጤት ታይቶበታል፡፡ የአብሽ ማረጋገጫ ሙከራ በሚመለከታቸው የዘር አፅዳቂዎች ተገምግሞ 2 ዝርያዎች ተለቀዋል፡፡

የበቆሎ nutrient omission ሙከራ የበቆሎ ምርታማነትን ለመጨመር አጋዥ ሊሆን እንደሚችል የዚህ ዓመት ውጤት አመላክቷል ፡፡ ይህ ስራ በጃቢጠህናን፣ አቸፈርና ሜጫ ወረዳዎ ች በተሰራው ሥራ እስከ 11.5 ቶን በሄክታር ከፍተኛ የምርት ውጤት ተመዝግቧ ል፡፡ በሰሊጥ ዝርያ ማሻሻል ጎንደር-1 የተባለ የሰሊጥ ዝርያ ከሁመራ-1

ዝርያ ጋር ሲወዳደር የ 25 በመቶ የምርት ብልጫ እንዳለው ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ትሪቲካሌ የማላመድ ሙከራ

ለሁለት ዓመት በላሊበላ፣ ድሃናና ወለህ እየተሰራ የነበረና የተጠናቀቀ ሙከራ ሲሆን፤ በዚህም ሎጋውሽቦ፣ ድልፋካርና

ስናን የተባሉ ዝርያዎች 30.32 ኩ/ ሄ፣ 27.43 ኩ/ ሄ እና 26.93 ኩ/ ሄ በቅደም ተከተል ከሌሎች ዝርያዎች የተሻለ

ምርት እንደሚሰጡ ተረጋግጧል፡፡ ሽንብራን በመስኖ በማላመድ ዝርያ መረጣ ሙከራ ከደሲ ዓይነቶች ወርቁ እና

ከካቡሊ ዓይነቶች አረርቲ የተባሉ ዝርያዎች 26.7 ኩ/ ሄ እና 27.87 ኩ/ ሄ በቅደም ተከተል ከሌሎች ዝርያዎች የተሻለ

ምርት ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪ መስኖ የጣፋጭ ስኳር ድንች ዝርያ የማላመድ ሙከራ ብርቱካኔ እና ሃዋሳ-83 42

የተባሉ ዝርያዎች 21.15 ቶን/ ሄ እና 20.62 ቶን/ ሄ በቅደም ተከተል ከሌሎች ዝርያዎች የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ

ተረጋግጧል፡፡ የድንች ዝርያ የማላመድ ሙከራ ይህ ሙከራ ለሁለት ዓመት በመስኖ እየተሰራ የነበረና የተጠናቀቀ

ሙከራ ሲሆን፤ በዚህም በለጠ እና ጌራ የተባሉ ዝርያዎች 20.86 ቶን/ ሄ እና 20.27 ቶን/ ሄ በቅደም ተከተል

ከሌሎች ዝርያዎች የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ ተረጋግጧል፡፡

የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት ዘር ለማምረት የመትከያ ጊዜቆቦላይ በመስኖ መስከረም መጀመሪያ አካባቢ መትከል ቦምቤ

ሬድ ዝርያ መጠቀም በሄ/ ር 119. ኩ/ ል ዘር አስገኝቷ ል የብቅለት መጠኑ ከ 85% በ ላይ እንደሆነ

ተረጋግጧል፡፡ የዲቃላ በቆሎ ማላመድ ቆቦ ላይ በመስኖ የተሰራ - - 5 4 5 55ኩ/ሄ BB -

661 50 ኩ/ ሄ ምርት አስገኝተዋል ፡፡ ከአካባቢው ዝርያ የ 40% ና 34% እያንዳንዳቸው በቅደም

ተከተል የምርት ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

በእንስሳት ምርምር ዘርፍ ንፁህ የዶርፐር በጎችን ምርታማነት የመገምገምና የማባዛት ሥራ ተከናውኖ 283 ንጹህ የዶርፐር በጎች በማደግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ንፁህ የቦር ዝርያ ፍየሎችን የመገመገምና የማባዛት ስራ ተከናውኖ ድቀላ ገብተው ከወጡት 31 ፍየሎች ውስጥ አብዛኞቹ እ ርጉዞች ናቸው፡፡ የመንዝ በግን በመረጣ የማሻሻልና ምርጥ

በጎችን የማባዛት ስራ በመከናወን ላይ ሲሆን ወደ ሙከራ ከገቡት 108 እናቲት የመንዝ በጎች ውስጥ 95 ንጹህ ግልገሎች ተወልደው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በመወሰድ ላይ ይገኛል፡፡ 60 የመንዝ እናቲት በጎች

የማድሪያ ሆርሞን በመጠቀም በሰው ሰራሽ ዘዴ የድቀላ አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የዋሸራ በጎችን መንደርን

መሰረት በማድረግ ለመምረጥና ለማሻሻል እንዲያስችል 13 የተመረጡ የዋሸራ ዝርያ ያላቸው አውራ በጎች

በቡድን ለተደራጁ ተሳታፊ አርሶ አደሮች ተገዝተው በማሰራጨት 65 እናቲት በጎች የጥቂ አገልግሎት

ተሰጧቸዋል፡፡ 38 በጎችም ተወልደው በማደግ ላይ ሲሆኑ፣ የተለያዩ መረጃዎች በመሰብሰብ ላይ ይገኛል፡፡

ለአውራነት የሚያገለግሉ ወንድ ፍየሎች በአርቢውማህበረሰብ የአውራመረጣ በማካሄድ የጥቂ አገልግሎት

እንዲሰጥ ተደርጐ 180 ዲቃላ ግልገሎች ተወልደዎል ፡፡ በ ፎገራ ወረዳ ከተሰራጩት የፎገራ ኮርማዎች በጠቅላላው 180 የፎገራ ላሞች በተመረጡ ኮርማዎች የጥቂ አግልግሎት ተሰጥቷቸዋል፡፡ እስከዚህ ሩብ

ዓመትም 72 ጥጆች ተወልደዋል፡፡ ሥራው ከተጀመረ ጀምሮ በጠቅላላው 203 የፎገራ ጥጆች ተወልደዎል፡፡ በሁለት ወረዳዎች ለ 1184 ላሞች የዉስጥ ጥገኛ መድሀኒት የማዋጥ እና ለ 946 የዳልጋ ከብቶች ደግሞ

የፓስቹሮሎሲስ ክትባት አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በአፈርና ውሃ ምርምር ዘርፍ በአፈርና ውሃ ምርምር ዘርፍ

የበቆሎ nutrient omission ጥናት የአንድ ዓመት ዉጤት እንደሚያሳየዉ በጃቢጠህናንና አቸፈር ወረዳዎች NPKSZn በአማካይ 75 እና 69.5 ኩ/ ል በሄክታር በቅደም ተከተል ሲያስገኙ በሜጫ ደግሞ NPK 77.3 ኩ/ ል ምርት አስገኝቷል፡፡ አሁን አርሶአደሩ በስፋት ይጠቀምበት የነበረው NP ማዳበሪያ ደግሞ በአማካይ

በጃቢጠህናን 38.5 ኩ/ ል፣ በአቸፈር 40.2 ኩ/ ል እና በሜጫ 53.5 ኩ/ ል በሄክታር ማግኘት ተችሏል፡፡

43

በምጥን ማዳበሪያ የተሠራው ሙከራ የሁለት ዓመት ውጤት በማሳዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነት ቢያሳይም በአማካይ ለ በቆሎ በደቡብ አቸፈር ወረዳ 150 kg ha-1 Formula 5 + 275 kg Urea ha-1 ለአካባቢው

ከተመከረው NP ማዳበሪያ በአማካይ የ 6 ኩ/ ል የምርት ጭማሪ ሲያሳይ በወንበርማ ወረዳ ግን ምንም ልዩነት

የለም፡፡

በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች በብቸና ምርምር ጣቢያ በጥቁር አፈር ላይ የተሠራው የዕቀባ ግብርና ሙከራ መሬት

ሳያርሱ ( በቅናሽ እርሻ) መዝራት በመጀመሪያው ዓመት ከአርሶ አደሩ አሰራር የ 14 ኩ/ ል ስንዴ ምርት ብልጫ

ሲያስገኝ በሁለተኛው ዓመት ደግሞ የ 30 ኩ/ ል የባቄላ ምርት ብልጫ በሄ/ ር በማስገኘት ምርቱን ወደ 50.5 ኩ/ል

ከፍ አድርጎታል፡፡

በደን ምርምር ዘርፍ የተፈጥሮ ደንን በተመለከተ በዋድላ፣ በሰቆጣና በወፍ ዋሻ አካባቢዎች ቅሪት ደኖች የመብቀል

ችሎታቸውን የመገምገም ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ያለን መረጃ እንደሚያመለክተው ዋድላ የዶጊት ሚካኤል

የተሰበሰበው የጽድ ዘር ከሌሎች ማለትም ከዋርካየ ማሪያም፣ ከአዲስጌ አቦና ከአዲስ አባባ ደን ምርምር

ማዕከል ከመጡት ዘሮች የተሻለ የብቅለትና የችግኝ አቋም አሳይቷል፡፡ የዕጣን ዛፍ በብዛት በሚገኝባቸው

አካባቢዎች ላይ የተባይና በሽታ ልየታ ጥናት ተካሂዶ ለናሙና ከተወሰዱት ዛፎች መካከል አብዛኞቹ የጥቃቱ

ሰለባ የሆኑ ሲሆን የጥቃቱ አይነት ያለምንም ልዩነት ትንሹንም ትልቁን ዛፍ እንደሚያጠቃ ለመለየት ተችሏል፡፡

ከተለያየ አገር የተሰበሰቡ የቅርከሃ ዝርያዎች በስሪንቃ፣ በአዴትና በጎንደር የማላመድ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በዚህም መሰረት Giant bamboo በስሪንቃና በአዴት ጥሩ እድገት አሳይቷል፡፡ ስሪንቃ ላይ በሁለት ወር

ውስጥ ከሁለት ሜትር በላይ እንደሚያድግ ለማየት ተችሏል፡፡ በ ኢንስቲትዩቱ ቲሹካልቸር የማራቢያ ዘዴዎችን ከሃርቡ ከሚገኘው Giant bamboo በማምጣት በላቦራቶሪና በሌላ ሁኔታ በመስክ እየተሞከሩ ይገኛሉ፡፡

የቴክኖሎጂ ትውውቅና አህዝቦት ሁለተኛው የምርምሩ ተልዕኮ ሲሆን በዓመቱ 25631 እስከዚህ ሩብ ዓመት ደግሞ 20504/3000 ሴ/ ተሳታፊዎችን በተለያዩ መንገዶች ( በቴክኖሎጅ ሰርቶ ማሳያና ቅድመ ማስፋት ስራዎች፤ በስልጠና፤ በመስክ ቀን፤ በአርሶ አደርና የዘር ማህበራት ቡድን፤ በአካባቢ ቀይር ፕሮግራም) ለማሳተፍ

ታቅዶ 18,614 (2,831 ሴት) ወይም የዕቅዱን 90.8% ለማከናወን ተችሏል፡፡

በቅድመ ማስፋት ሥራ በቅድመ ማስፋት ስራዎች የተመረተዉን ምርት ወደ ዘር ስርዓት ለማስገባት፡ ሽምብራ

ሰሊጥና የምግብና ቢራ ገብስ በሰ/ ጎንደር፤ ሽምብራ፤ ስንዴና ባቄላ በሰሜን ሸዋ፤ ስንዴና ጤፍ በላስታ ወረዳ

ሰ/ ወሎ ላይ፤ ጊራና 1 ማሽላ፤ ሶራ ዝርያ ስንዴ፤ ሽምብራና ባቄላ (ዶሻ) በሰሜንና ደቡብ ወሎ (በለጋምቦ፤

ዳዋጨፋ፤ቃሉ፤ ሃብሩ፤ መቄትና ዋድላ ወረዳዎች) ፤ በምስ/ ጎጃም ምዕ/ ጎጃምና አዊ ዞኖች የዳቦ ስንዴ፤ ባቄላ፤ ጤፍና

ትሪቲካሌ ላይ ጥራታቸዉን ጠብቀዉ እንዲመረቱና ለዘር አገልግሎት እንዲዉሉ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም በጎንደር

140 ኩንታል የሚደርስ የሽምብራና ሰሊጥ ዘር ተገኝቷል፡፡ በስሪንቃ ደግሞ በሰባት ዓይነት ሰብሎች ወደ 2500 ኩንታል ዘር ተመርቷል፡፡ ደብረብርሃንና አዴትም እንደዚሁ የዘር ምንጭነት የሚዉሉ የተለያዩ ሰብሎችና ዝርያዎች ምርት

ተሰብስበዋል፡፡

44

የአርሶ አደር የምርምርና ስርፀት ቡድን (FREG) ማደራጀት የተለያዩ የተሳትፎአዊ ቴክኖሎጅ ትዉዉቅ ስራዎች

በነበሩት 79 ያክል ቡድኖች ላይ 2 አዳዲስ ቡድኖች በእንስሳት ቴክኖሎጂዎች ላይ በማዋቀር 81 የደረሱ ሲሆን

በአጠቃላይ 18614 (2831 ሴት) አርሶ አደሮች ታቅፈው የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እየሆኑ

ይገኛሉ:: በአንጻሩ ደግሞ ከነበሩት የአርሶአደር ምርምር ቡድን ውስጥ አቅማቸዉን በማጎልበት በአጠቃላይ በአራት

ማእከላት 1239 (229 ሴት) አባላት ያላቸዉ 15 ማህበራት ተመስርተዉ በዘር ብዜትና ግብይት ላይ በመሳተፍ

የዘር ፍላጎትን ከማሟላት አንጻር ክፍተኛ አስተዋጾ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ያጋጠሙ ችግሮች

በመጨረሻም የምርምሩን ተግባራት በመፈጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመጥቀስ፤ በቂ የምርምር ጣቢያና የዘር ማባዣ መሬት እጥረትና የዘር ብዜትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በሰው ኃይል አለመደራጀት፣ የበጀትእጥረት፣

ተሽከርካሪ፣ ትራክተርና ዘመናዊ የእርሻ መሣሪዎች እጥረት፣ የማዕከላት ደ/ ሥራ ሂደት ኃላፊዎች የደመወዝ ማስተካከያ አለመፈቀድ፣ የማዕከላት ቢሮ ማርጀትና ጥገና አለመኖር፣ የሙከራ ጣቢያዎች አጥሮቻቸው መፈራረስ፣ የላቦራቶሪና የምርምር ፋሲሊቲዎች በበቂሁኔታ አለመሟላት፣ የዘርመጋዘን እጥረት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

8. የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

ችግኝ ጣቢያ ማቋቋምና ማካሄድ፣

በምርት ዘመኑ በቁጥር 52 ችግኝ ጣቢያ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዞ ክንውን 70 ሲሆን አፈፃፀሙ 134.6% ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ 46 ቱ ችግኝ ጣቢያዎች የሚካሄደው በአረንጓዴ ኢንተርፕራይዝ በተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶች ነው፡፡ 20 ሚሊዮን ችግኝ ለማፍላት በእቅድ ተይዞ 15.349 ሚሊዮን የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙ 76.75% ነው፡፡

8,000 ሄ/ ር የተከላ ቦታ ለመለየት ታቅዶ 9,953 ሄ/ ር ተከናውኗል አፈፃፀሙ 124% ነው፡፡ 31,305 ሄ/ ር የደን

ርክክብና ጥበቃ ለማከናወን እቅድ ተይዞ 24,843 ሄ/ ር የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙ 79% ነው፡፡ 43,018 የመንግስት ደን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት እቅድ ተይዞ 27,104 ተከናውኗል አፈፃፀሙ 63% ነው፡፡

37,540 ሄ/ ር የደን ክለላ ካርታ ለማዘጋጀት እቅድ ተይዞ 28,554 ሄ/ ር ተዘጋጅቷል አፈፃፀሙ 76% ነው፡፡

8,603 ሄ/ ር የማኔጅመንት ፕላን ለማዘጋጀት እቅድ ተይዞ 6,089 ሄ/ ር ተከናውኗል አፈፃፀሙ 71% ነው፡፡ 1,984 ሄ/ ር የደን እንክብካቤ ለመስራት እቅድ ተይዞ 668 ሄ/ ር የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙ 34% ነው፡፡ 32 የአረንጓዴ

ኢንተርፕራይዞች በችግኝ ማፍላት ስራ እንዲሳተፉ እቅድ ተይዞ 46 ተከናውኗል አፈፃፀሙ 143% ነው፡፡ በቁጥር

43,700 ፖል ለማምረት ዕቅድ ተይዞ 15,193 ተከናውኗል አፈፃፀሙ 34% ነው፡፡ 5,803 ሜ/ ኩ ጣውላ

ለማምረት ዕቅድ ተይዞ 2,078 ሜ/ ኩ ተከናውኗል አፈፃፀሙ 36% ነው፡፡ 150,656 ሜ/ ኩ ማገዶ ለማምረት

እቅድ ተይዞ 29,672 ሜ/ ኩ ተከናውኗል አፈፃፀሙ 19% ነው፡፡ 48,319 ሜ/ ኩ የግንባታ እንጨት ለማምረት

ተይዞ 8,110 ሜ/ ኩ ተከናውኗል አፈፃፀሙ 16% ነው፡፡ 13,260 ሜ/ ኩ የፋብሪካ ግንድ ለማምረት (ከ 15 ሳ. ሜ በላይ) እቅድ ተይዞ 4,727 ተከናውኗል አፈፃፀሙ 35% ነው፡፡ 50.5 ኪ. ሜ መንገድ ለመስራት ዕቅድ

45

ተይዞ 33.46 ኪ/ ሜ የተሰራ ሲሆን አፈፃፀሙ 66% ነው፡፡ በቁጥር 49 የደን ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች ለማቋቋም

ዕቅድ ተይዞ 40 የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙ 81% ነው፡፡ 348 ኩንታል የደን ዘር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ

158.115 ኩንታል የተሰበሰበ ሲሆን አፈፃፀሙ 45% ነው፡፡ 152,184,359 ብር ገቢ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ

ብር 91,116,828 ገቢ ተደርጎል አፈፃፀሙ 59.87% ነው፡፡ ለ 30,635 ወንድ እና ለ 15,955 ሴት በድምሩ

46,590 የስራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዞ ለ 51,599 ወንድ እና ለ 21,705 ሴት በድምሩ 73,304 የስራ

እድል የተፈጠረ ሲሆን አፈፃፀሙ 157% ነው፡፡

የደን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናትና ትግበራ

ኢንተርፕራይዙ የደን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን በማስጠናት በተወሰኑ ፕሮጀክቶች ወደ ትግባራ ተገብቶ በማምረት ሂደት ላይ ይገኛል፣ የተወሰኑ ፕሮጅክቶች ደግሞ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን እንደዚሁም የተወሰኑ

ፕሮጀክቶች ተጠንተው የበጀት አቅማ ችን ሲፈቅድ ለመተግበር በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች በዝርዝር

ሲታዩ ፡- 3 የእንጨት መሰንጠንቂያ ፋብሪካዎች / ኮምቦልቻ፣ ደ/ ማርቆስ እና እንጅባራ/ ወደ ተግባር ገብተው በማምረት ላይይገኛሉ፣ 1 የእንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካከ ቻይና ባለሃብት ጋር በጋራ ተቋቁሞ ወደ ትግበራ በመግባት በማምረት ላይ ይገኛል፣ 2 የእንጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካዎች በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛሉ /ደ/ታቦርና

ደ/ሲና/ ፣ በሰሜን ሽዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ 1 የእንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከቻይና ባለሃብት ጋር በጋራ በመገንባት የሙከራ ምርት በማምረት ላይ ይገኛል፣ በደብረሲና ከተማ የሚቋቋም 1 የፓርቲክል ቦርድ/ችፕውድ/

ፋብሪካ የፕሮጀክት ጥናት ተጠናቆ ተቀምጧል፣ በደ/ ታቦር ከተማ የሚቋቋም 1 የእንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ጥናት ተጠናቆ ብድር የማፈላለግ ሂደት ላይ ነው፡፡

9. አደጋመከላከልናምግብዋስትና ፕሮግራምማስተባበሪያ

የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ታዓማኒነትን ማሳደግ ፣

በክልሉ ውስጥ የሚታይን የአደጋ ስጋት ሁኔታ መከታተል ይቻል ዘንድ በ 11 ወሩ ውስጥ ከ 129 የገጠር ወረዳዎች 47 ሳምንታዊና 1¸419 ወርሃዊ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ለማሰበሰብ ታቅዶ 47

(100%) ሳምንታዊ መረጃ እና 1¸328 (94%) ወርሃዊ መረጃ በማሰባሰብና አደራጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ በማድረስ የዝግጁነት አቅምን እንዲጠናከር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት

የሚመለከታቸው መ/ ቤቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ሁኔታ በወቅቱ እውቅና እንዲኖራቸው በማድረግ የአደጋ ስጋት ምላሽ ስራዎች እንዲሰራ አስፈላጊው መረጃ ማድረስ ተችሏል፡፡

የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባራት እንዲከናወኑ በማድረግ የዝግጁነት አቅምን ማሳደግ ፤

በዚህ አመት አንድ የመኸር ዝናብ አጀማመርና የእርሻ ስራ እንቅስቃሴ ጥናት ለማካሄድ ታቅዶ 1 (100%) ጥናቱ በሁሉም ዞኖችና ወካይ ወረዳዎች ላይ የተካሄደ ሲሆን ፤ መረጃዎችን በወቅቱ ለጽ/ ቤቱ በማቅረብ ውይይት

46

ተደርጎበት የዝግጁነት አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችን በክልልና በሃገር አቀፍ ደረጃ ማከናወን ተችሏል፡፡

እንዲሁም በግማሽ ዓመቱ የቅድመ ምርት ግምገማና ጥናት ስራዎችን በማከናወን በቀጣይ በክልሉ ሊኖር የሚችለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ ለማወቅ ይቻል ዘንድ አንድ የመኸር ቅድመ ምርት ግምገማና ጥናት

በፌደራልና በክልል በተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሰረት በክልሉ በሚገኙ 8 ዞኖች በ 83 ወረዳዎች ለቀጣይ 9 ወራት 2,298,494 ህዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በጥናት ተለይቶ ለፌደራል

የተላከ ሲሆን ድጋፉም እየቀረበ ይገኛል፡፡

የአስቸኳይ አደጋ ቅኝት ጥናት ፣

በክልሉ የአደጋ ስጋት ተጋርጦባቸዋል ተብለው በክትትል በተለዩት አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ ጥናት በማካሄድ የጥናት ውጤት ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማቅረብ በታቀደው መሰረት፤ እስከዚህ ሩብ ዓመት ስድስት ጊዜ

፡-

ምስ/ ጎጃም ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተን የሰውና እንስሳት ምግብና መኖ ችግር ለማጥናት፣

ከአዊና ምዕ/ ጎጃም ዞኖች ወጭ በሚገኙ 8 የክልሉ ዞንና የተመረጡ ወረዳዎች ላይ የተከሰተን የሰው ምግብ ዋስትና ክፍተት ለማጥናት

በዋግኽምራ ዞን በህብረተሰቡ ላይ በተከሰተው ምግብ ክፍተት ምክንያት በት/ ቤቶች ላይ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ የሚፈጠርን ክፍተት ለማጥናት

የአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ስጋት በ 8 ዞኖች በማከናዎን በህብረተሰቡ ላይ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ ዳሰሳዊ ጥናት ተካሂዷል፣

በክልል ደረጃ የመኸር ቅድመ ምርት ግምገማ እስከሚካሄድ ድረስ ችግር በሚኖርባቸው ወረዳዎች ያለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ ለማጤን በፌደራል የሚመራ አስቸኳይ የባለሙያዎች ቡድን ተዋቅሮ በተለያዩ ወረዳዎች ጥናቱ ተካሂዶ ለ 1,423,936 የህብረተሰብ ክፍሎች ለ 3 ወር ድጋፍ እንዲቀርብ

ተደርጓል፣

እንዲሁም በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተውን የድርቅ ሁኔታ ለማጤን በክልል አመራሩ የሚመራ ሶስት የባለሙያዎች ቡድን በተለያዩ ወረዳዎች የመስክ ዳሰሳዊ ጥናት በማካሄድ ችግሮችን በየደረጃው

በመለየትና ምላሽ በመስጠት ህብረተሰቡ ከቀየው ሳይፈናቀል አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጓል ፡፡

በምዕራብና ምስራቅ አማራ ክልል ያለውን የጎርፍ ስጋት ለመከላከል ይቻል ዘንድ በሁለት ቡድን ክልሉን በመክፈል የጎርፍ ግብረሃይሉንና ህብረተሰቡ በንቃት አንቅስቃሴ እንዲያደርግ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ሁሉም የጎርፍ

ተጠቂ ወረዳዎችና ዞኖች መጠባበቂያ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ በማድረግ በመረጃውም በመነሳት የክልሉን የጎርፍ መጠባበቂያ ዕቀድ ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡

47

የዝናብ ሁኔታና የእርሻ ስራ እንቅስቃሴ

በ 2008 በጀት ዓመት የበልግ ተጠቃሚ በሆኑ 3 (ሰ/ ሸዋ፣ ደ/ ወሎ፣ ሰ/ወሎ) ዞኖች በዘር ለመሸፈን ከታቀደው

227,864 ሄ/ ር መሬት ዉስጥ እስካሁን 203,074 ሄ/ ር (89%) መሬት የታረሰ ሲሆን ከታረሰው ደግሞ

166,268 ሄ/ ር (82 %) በዘር ተሸፍኗል፡፡ እንዲሁም በ 2008/09 ምርት ዘመን በመኸር ይታረሳል ተብሎ ከታቀደዉ 4,465,836 ሄ/ ር መሬት ዉስጥ 3,849,566 (86.2%) ሄ/ ር መሬት የታረሰ ሲሆን 854,940

ሄ/ ር (22%) በዘር ተሸፍኗል፡፡

የመጠባበቂያ እቅድ ማዘጋጀት

በዚህ አመት 1 የመጠባበቂያ እቅድ (የጎርፍ) ለማዘጋጀትና ሃብት በማፈላለግ ታቅዶ 2 የመጠባበቂያ እቅድ ( የጎርፍና የዝናብ እጥረት ምላሽ) በማዘጋጀት በ 2007/8 መኽር ዝናብ በክልሉ ብዙ አካባቢዎች ለተከሰተው

የዝናብ እጥረትና ተያይዞ ለመጣው የሰብል መድረቅ፣ የእንስሳት መኖና ውሃ ችግር እንዲሁም የሰው ምግብ ድጋፍ ምላሽ የሚሆን ሃብት የማፈላለግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በክረምቱ ሊደርስ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት 26

ወረዳዎች የተለዩ ሲሆን ለዚህም የሚያስፈልገው ምግብ እና ምግብ ነክ ያለሆኑ ቁሳቁሶች በመለየት 88,573,302 ብር በጀት የሚያስፈልግ መሆኑን የተዘጋጀውን ዕቅድ ሰነድ ለሚመለከታው የመንግስት (በክልልና

በፌደራል ደረጃ) እና በአጋር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በማስራጨት ምላሽ እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡በመሆኑም ለክልል ገንዘብና ኢ/ ትብብር ቢሮም ከሚያስፈልገው በጀት ውስጥ 10¸624¸000 ብር

በጀት ከክልል መንግስት እንዲሽፈን ጥያቄ ቀርቦል፡፡

ትኩረት የሚሹ ወረዳዎችን የመለየት ሥራ

በዚህ አመት በዋግኽምራ ዞን ሁለት ወረዳዎች ( ዳህናና ጋዝጊብላ) የአስቸኳይ ጊዜ የስነ- ምግብ ጥናት የተካሄደ ሲሆን ውጤቱንም ለሚመለከተው በማድረስ ምላሽ እንዲያደኙ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሌላ

በኩል በክልሉ በሁሉም ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች የመኸር እና የበልግ ምርት፣ የጤናና የስነ- ምግብ ሁኔታ፣ የገበያ፣ የትምህርት፣ የውሃ እና ሌሎች መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ በበጀት ዓመቱ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን

ወረዳዎች በየሩብ አመቱ አንድ ጊዜ ይለያሉ፡፡ በዚህም መሰረት ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሶስት በመለየት ለዝግጁነት ይረዳ ዘንድ ለፌደራል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ /DRMFSS/ ተልኳል፡፡

በዚህም መሰረት እስከዚህ ወር ድረስ ደረጃ አንድ 44 ፡ ደረጃ ሁለት 27 ፤ ደረጃ ሶስት 7 ወረዳዎች በድምሩ 78 ወረዳዎች ተለይተው ለፌደራል ተልኮ ምላሽ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለሚጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማቅረብ የህብረተሰቡን ህይወት መታደግ

የተከሰተዉን ችግር ለመቋቋም ከፌደራል መንግስት በሶስት ዙር ብር 356,445,999 ፤ የክልሉ መንግስት 200 ሚሊዮን ብር ለተጎጅ ቤተሰቦች ለእለት ምግብ ድጋፍ የሚዉል ፣ ብአዴን 30 ሚሊዮን ብር የጤና ባለሙያዎች

101,268 ብር ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ብር 5 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ በድምሩ 591,547,267 ብር

48

ለተለያዩ ስራዎች ማስፈጸሚያ ከተለያዩ አካላት ተገኝቶና ተመድቦ የተለያዩ የአደጋ ቅነሳና የምላሽ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል ፡፡

ከዚህ ውስጥ ብር 157,343,540 ለውሃ ማሰሳሰብ ጅኦሜምብሪየን ግዥና ለአነስተኛ ግድቦች ሥራ፤ 75 ሚሊዮን ብር ለክልሉ መጠባበቂያ እህል ግዥ፤ 60 ሚሊዮን ብር ለአስቸኳይ ጊዜ መጠጥ ውሃ

አቅርቦት ፣ 76,752,733 ሚሊዮን ብር የእርዳታ እህልና መጠጥ ዉሃ ማቅረብ እንዲቻል ለመንገድ ከፈታ፣ ጠረጋና ማስተካከል ሥራ ለማሽነሪ ኪራይና ለነዳጅ፣ 21 ሚሊዮን ብር ለጤና ጥበቃ ቢሮ

ለመድሃኒት አቅርቦት፣ ብር 93,324,006 የተተኪ ዘር፣ ለእንስሳት መኖና መድሃኒት ግዥ፣ በድምሩ ብር 483,852,410 ለተለያዩ የአደጋ ቅነሳ ሥራዎች ተደልድሎ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ፡፡

ከ 7 የክልሉ ልማት ድርጅቶች 46 ማሽነሪዎች በ 7 ዞኖች በ 83 ቀበሌዎች በማሰማራት፤ 704,869 ሜ/ ኩ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 170 ኩሬዎች ተገንብተዋል ፤ 17 የአፈር ግድብ ተቆፍረዋል ፣ ከ 406

በላይ ጅኦሜምብሬን እንዲነጠፍ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም 54 ግድቦችንና 228 ኮሬዎችን በሰው ጉልበት ለመስራት ታቅዶ እስከአሁን 26 ግድብና 148 ኩሬዎች ቁፋሮ በተለያዩ ወረዳዎች ተጀምሯል ፡፡

በዝናብ እጥረቱ በተከሰተዉ ድርቅ ያጣነዉን የምርት መጠን ማካካስ እንዲቻል 9,856 ሄ/ ር መሬት የሚሸፍን 11,583 ኩ/ ል ተተኪ ዘር በፌደራል መንግስት በጀትና በተለያዩ አካላት ተገዝቶ ለ 52,119 አ/አደሮች

ተሰራጭቶ ተዘርቷል፣ እንዲሁም የዝናብ እጥረቱ በተከሰተባቸዉ 8 ዞኖች ለሚገኙ ህብረተሰቦች ለ 2008/09 መኸር የተተኪ ዘር ጥያቄ ለ 618,840 ህብረተሰብ 278,485 ሄ/ ር መሬት ሊሸፍን የሚችል 165,156

ኩ/ ል የተተኪ ዘር ፍላጎት ተሰባስቦ ለሚመለከታቸዉ ድጋፍ እንዲደደደርጉ ጥያቄ ቀርባል ፡፡

በ 8 ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ 36 ወረዳዎች በተላከ የገንዘብ ድጋፍ 31,761 ኩ/ ል በላይ የእንስሳት መኖ ተገዝቶ ለ 126,339 እንስሳቶች ምግብነት እንዲውል ለ 35,468 ቤተሰቦች ተከፋፍሏል ፣

በ 14 ወረዳዎች በ 350 ቀበሌዎች የመጠጥ ዉሀ ችግር ባለባቸዉ በጊዚያዊነት ለመፍታት በተለይም በቀበሌ ደረጃ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና ችግሩ ላለባቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች 1096 አህዮችን በመግዛት የዉሀ

ማመላለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል፣

በክልሉ መንግስት፣ በፌዴራል ውኃ ፤መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ በዩኒሴፍ እና በአካባቢው ባሉ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የመጠጥ ዉሃ ችግሩን ለማቃለል 1,379 ካርቶን ( ቢሻንጋሪ፣ ዉሃ አጋሪ

እና ፒዩር) 24 ድርሃም ክሎሪን እና 33,500 ስትሪፕ አኳታብስ የዉሀ ማከሚያ ኬሜካሎች ከዩኒሴፍ ድጋፍ ተደርጎ ለተጠቃሚዎች ተሰራጭቷል፡፡

የህብረተሰቡን የአደጋ ምላሽ ግንዛቤ ማሳደግ

የህብረተሰቡን አደጋ የመከላከል አቅምና የእርስ በርስ የመረዳዳት ባህልን ማጎልበት ይቻል ዘንድ በተፈጥሮ አደጋ ( የጎርፍ፣ ድርቅ፣ በረዶና የመሬት መንሸራተት) ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች/ ወረዳዎች ላይ 13,000 ( ወ 6,500

49

ሴ 6,500) ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የቅስቀሳና ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ 13,500 (ወ 10,500 ፣ ሴ 3,000) የህብረተሰብ ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በወረዳዎች በኩል መስራት የተቻለ ሲሆን ፣

በተፈጠረዉ የዝናብ እጥረት ምክንያት የተከናወኑ ተግባራት

በ 2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ኢሊኖ /Eli nino/ ክስተት ሳቢያ በክልላችን በተለያዩ አካባቢዎች

የክረምት ዝናብ በመዘግየቱና የዝናብ ስርጭቱም ባለመስተካከሉ የእርጥበት እጥረት ችግር እንደተከሰተ ይታወቃል፡፡

ችግሩ በ 8 ዞኖች ( ዋግኽምራ፣ ሰ/ ወሎ፣ ደ/ ወሎ፣ ኦሮሚያ፣ ሰ/ ሸዋ፣ ምስ/ ጎጃም፣ ደ/ ጎንደር፣ ሰ/ጎንደር) በሚገኙ

83 ወረዳዎችና በ 802 ቀበሌዎች በ 1.6 ሚሊዮን ሄ/ ር መሬት ተከስቶ ጉዳት አድርሷል ፡፡ ችግሩን በተቀናጀ ሁኔታ

ለመከላከል ይቻል ዘንድ በክልል ደረጃ የአደጋ ስጋት ቅነሳ እቅድ /Sectorial Plan/ ተዘጋጅቶ ስራዎች በየደረጃው

ተከናውነው በሰው ህይወትና በእንስሳት ላይ ጉዳት ሳይደርስ ችግሩን ለመከላከል ተችሏል ፡፡

በዘንድሮው ዓመት የተከሰተውን ድርቅ ለመመከት የሚያስችል አቅም በየደረጃው የተገነባበት እንደነበር የታየበት

ሲሆን አቅም ሲባል የአደጋ ስጋትን አስቀድሞ የማወቅ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ የማስቀረት፣ አይቀሬ ሆኖ ከመጣ

ደግሞ በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ወቅታዊ ምላሽ በማቅረብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነበረበት

ሁኔታ መደበኛ ኑሮውን እንዲቀጥል የማድረግ ሃገራዊ እና ህዝባዊ አቅም እንደማለት ነው፡፡ ድርቅ በየደረጃውየአደጋ

ስጋትን አስቀድሞ በማወቅ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ የማስቀረት፣ አይቀሬ ሆኖ ከመጣ ደግሞ ጉዳት ሳያደርስ

ፈጣን ምላሽ በማቅረብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነበረበት ሁኔታ መደበኛ ኑሮውን እንዲቀጥል የማድረግ ሃገራዊ

እና ህዝባዊ አቅም ተገንብቷል ማለት ይቻላል፡፡

በውኃ ማሰባሰብ

በሃምሌና ነሃሴ ወራት በክልሉባሉ 7 የልማት ድርጅቶች በ 46 ማሽነሪዎች በ 7 ዞኖች በ 30 ወረዳዎችና 83 ቀበሌዎች 704,869 ሜ/ ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 170 ኩሬዎች ተገንብተው ውሃ ይዘው ጥቅም የሰጡ

ሲሆን 17 የአፈር ግድብ የተቆፈረ ሲሆን ከ 4000 በላይየጅኦሜምብሬንእንዲንጠፍተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በበጋው ወራት በየአካባቢው የሚገኘውን የዝናብ ውሃ በአግባቡ ሰንቆ ለመያዝ የውሃ ማሰባሰብ

ስራዎች በህብረተሰብ ተሳትፎ፣ በክልልና በፌደራል መንግስት በጀት ድጋፍ፣ በምርታማነት ሴፍቲኔት እና በሌሎች

የበጀት ድጋፎች የተለያዩ የውሃ ማሰባሰብ ስራዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

ከነዚህም መካከል፤

በ 8 ዞኖች በተለያዩ ወረዳዎች 61 ግድብ /Gravity Dams/ ለመስራተ ታቅዶ በ 58 የመሰረት ቁፋሮ

ተጀምሮ የ 4 ግድቦች ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ሌሎች በመሰራት ላይ ናቸው፣

50

o በ 8 ዞኖች በተለያዩ ወረዳዎች 228 የማህበረሰብ ኩሬ /community pond/ ለመስራት ታቅዶ የ

175 ኩሬዎች ቁፋሮ ስራ ተጠናቆ ከዚህ ውስጥ 96 ኩሬዎች ውሃ የያዙ ሲሆን በተለይም ከፍተኛ የውሃ

ችግር በነበረበት በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ፣ በሰቆጣ እና በዳህና ወረዳ አገልግሎት

በመስጠታቸው ትልቅ እፎይታን ፈጥረዋል ፡፡

መስኖ ልማት

በመስኖ ልማት በክልል ደረጃ በዕቅድ ከተያዘው 885,112 ሄ/ርመሬትውስጥ 811,808 (91.72%) ሄ/ር

መሬት በአንደኛ ዙር መስኖ በዘር ተሸፍኗል ፡፡ ድርቁ በተከሰተባቸው ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች ከዚህ በፊት ይለማ

ከነበረው በነባርና በአዲስ 500,504 ሄ/ ር መሬት 439,455 (87%) ሄ/ ር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመስኖ

ለምቷል፡፡ በመስኖ ልማት ስራውም 1,550,945 አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎችም

12,265,669 ኩ/ ል ምርት በመስኖ ለማግኘት ተችሏል ፡፡

የተተኪ ዘር አቅርቦት

ለበልግ ሰብል ልማት በ 4 ቱ ዞኖች 149,423 ኩ/ ል (70%) ዘር ቀርቦ ተዘርቷል፡፡ በተጨማሪም በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ከመደበኛው በተጨማሪ በተለያዩ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ለመኸር ምርት 7,791 ኩ/ል

( ስንዴ ቀቀባ ዝርያ 3,255 ኩ/ ል፣ ስንዴ ዳንፌ ዝርያ 2,508 ኩ/ ል፣ ቁንጮ ጤፍ 1,399 ኩ/ ል፣ ቦሰት ጤፍ 18 ኩ/ ል፣ በቆሎ 661 ዝርያ 240 ኩ/ ል፣ ማሽላ ጊራና ዝርያ 371 ኩ/ል) በ 8 ዞኖች ለሚገኙ ወረዳዎች

ቀርቧል፡፡

እንስሳት ሃብት ልማት

በክልላችን የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ሃብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች

እየተወሰዱ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስ በድምሩ 5,243,642 እንስሳት ለመኖና ለውሃ እጥረት ተጋላጭ እንደሆኑ

ይገመታል፡፡ ድርቁ የከፋ አደጋ በእንስሳት ላይ እንዳያደርስ ለመከላከል ይቻል ዘንድ አራት የተለያዩ አቅጣጫዎች

ተቀይሰው እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ድርቁ ባለባቸው 8 ዞኖች በተለያዩ ወረዳዎች እስካሁን በድምሩ 881,428 እንስሳት የተሸጡ ሲሆን የተሻለ መኖና ውሃ ወዳለባቸው ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች 509,216 እንስሳት

የማንቀሳቀስ ስራ ተሰርቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች ዝናብ በጥሩ ሁኔታ እየዘነበ በመሆኑ የእንስሳት

መኖና ውሃ ሁኔታ ሊሻሻል እንደሚችል የሚገመት ሲሆን ወደተለያዩ አካባቢዎችም ተንቀሳቅሰው የነበሩ እንስሳት

ወደቀያቸው እየተመለሱ ይገኛል፡፡

የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም/PSNP/

በክልሉ ስር በሰደደ የምግብ ዋስትና መታጣት ችግር ውስጥ የሚገኘውን ሕዝብ በልማታዊ ሴፍቲኔት ኘሮግራም

በማሣተፍ የምግብ ክፍተቱን ለመሙላት እና የጥሪት መመናመንን ለመከላከል በ 2008 በጀት ዓመት

51

1,890,985 ( ወንድ 895,316 እና ሴቶች 995,679) ህዝብ በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ

ይሆናል ፡፡

ለዚህም በ በጀት ዓመቱ ለመደበኛ ትራንስፈር ለተጠቃሚዎች ክፍያ ለመፈፀም በብር 1,451,369,000 ፤ በእህል

27,980 ሜ/ ቶን ጥራጥሬ እና 7,461 ሜ/ ቶን ክክ በእቅድ ተይዞ እስከ አስራ አንደኛው ወር ብር

1,000,910,807 ከፌደራል ለክልሉ ተልኮ ክልሉም ለሁሉም ተጠቃሚ ወረዳዎች በመደልደል ሙሉ በሙሉ

ለወረዳዎች ወደ ታች አዉርዷል ፡፡ለጥር ፤ ለየካቲት፤ ለሚያዝያ እና ለግንቦት ወራት ከተላከላቸዉ ብር

996,394,487 ዉስጥ ብር 976,897,078 (98 %) ለተጠቃሚዎች ክፍያ ተፈጽሟል ፡፡

በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በ 14 ወረዳዎች በመንግስትና መንግሰትታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለ 431,559 ተጠቃሚዎች 354,418 ኩ/ ል እህልና ጥራጥሬ በዕቅድ ተይዞ እስከ አስራ አንደኛው ወር 223,107 ኩ/ል

እህል እና ጥራጥሬ ወደ ወረዳዎች ደርሷል ፡፡ ከዚህ ዉስጥ 149,553 ኩ/ ል ለተጠቃሚዎች ተሰራጭቷል፡፡

በማህበረሰብ ልማት ስራዎች ተጠቃሚዎችን በማሳተፍ ዘላቂ የማህበረሰብ ጥሪት መገንባትና ለማህበራዊ

አገልግሎት ምቹ ሁኔታ መፍጠር

የማህበረሰብ ስራዎች የፕሮግራሙን ተጠቃሚዎች በተለይም ሊሰራ የሚችለውን የህብረተሰብ ክፍል መሰረት

በማድረግ በተጠቃሚው ጉልበት( የማህበረሰብ ጉልበት) እና በዚሁ ተጠቃሚ ጉልበት ልክ ተሰልቶ በሚመጣው

የካፒታል በጀት መሰረት በማድረግ የ 2015/16 ዕቅድ ተይዞ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ተግባራትን በቅደም ተከተላቸው

በጊዜ ሰሌዳ በመፈጸም ላይ ነው፡፡

የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሙ የማህበረሰብ እሴት በመፍጠር የምግብ ዋስትና መታጣት ችግርን በዘለቄታው ለመፍታት እንዲችሉ ተፋሰስን መሰረት አድርጎ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የመሠረተ ልማትሥራዎችን

ሲከናወኑ ቆይተዋል በመከናወን ላይም ናቸዉ፡፡ በመሆኑም የማህበረሰብ ልማት ተጠቃሚዎችን በአቅራቢያቸው

በሚመረጡ ተፋሰሶች በአፈርና ውሀ ጥበቃ፣ በደን ልማት፣ በጥምር የደን ልማት፣ በውሀ ሀብት ልማት፣

በመስኖ ልማት በመሰረተ ልማትና በመሳሰሉት ስራዎች በማሳተፍ በኑሮ መሰረት ማሻሻል እና ለማህበራዊ

አገልግሎት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ስራዎች በመሠራት ላይ ቢሆኑም እስከዚህ ሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና

የሴፍቲኔት ንዑስ ፕሮጀክቶች ዕቅድ ክንዉን እንደሚከተለዉ ቀርቧል ፡፡

በተለያዩ የኑሮ መሰረት መሻሻያ ተግባራት 65,594 (32,963 ወንድ እና 32,545 ሴት) የቤተሰብ

ኃላፊዎችንና ወጣቶችን በማሳተፍ የቤተሰብ ጥሪትን ማሳደግ

የኑሮ መሠረት ማሻሻያ የስራ ዘርፍ ዋና ዓላማ ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸውን ቤተሰቦች በልማታዊ

ሴፍቲኔት ፕሮግራም ትራንስፈር የምግብ ክፍተታቸውን ከመሙላት ጎን ለጎን በተለያዩ ግብርና በሠብል ልማትና

በእንስሳት ሀብት ልማት፤ ከግብርና ዉጭ የገቢ ማስገኛ ተግባራት እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ የስራ ዘርፎች

እንዲሳተፉ በማድረግ ሀብት ፈጥረዉ ምግብ ዋስትናቸዉን በዘላቂነት እንዲያረጋግጡ ማስቻል ነዉ፡፡

52

የማማከር አገልግሎት

ትኩረት የሚያደርገው ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው:: በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉት በፍላጎት ስለሆነ የምክክር መድረኩ ተጠቃሚች በፕሮግራሙ ለመሳተፍ ወይም

ላለመሣተፍ እንዲወስኑ ያስችላቸዋል ፡፡ በመሆኑም በዓመቱ ለ 277480 የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ በአሥራ አንድ ወራት ለወንድ 146823 ሴት 91677 በድምሩ 238051

የሴፈቲኔት ተጠቃሚዎች የማማከር አገልግሎት አገኝተዋል፡፡ ይህም አፈጻጸም ከዓመቱ ዕቅድ 86% ነው፡፡

በቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚ ልየታ

የማማከር አገልግሎት ካገኙት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች መካከል በራሳቸው ፍላጎትና አቅም በቤተብ ኑሮ ማሻሻያ perogerame ድጋፍ ለማግኘት የተለዩ ተጠቃሚዎችን የሚያመላክት ሲሆን ዓመታዊ ዕቀድ 81994 ሲሆን

በአሥራ አንድ ወራት የተለዩት ወንድ 86207 ሴት 31109 በድምሩ 87316 ናቸው፡፡ አፈጻጸም ከዓመቱ ዕቅድ

106% ነው፡፡

የኑሮ ማሻሻያ ቡድን አደረጃጀት

ለቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚነት የተመረጡት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለምሳሌ ሥልጠናና ድጋፍ ለማግኘት በቡድን መደራጀት አለባቸው፡፡ ይህም ድጋፍ የሚሰጥ አካላት በአንድ ላይ ለማግኘት

ያመቻቸዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን የተመለመሉ ደንበኞችን በአማካይ በአንድ ቡድን 30 የሚገኙበት በ 2596 ቡድን ለማደራጀት ታቅዶ 72767 ኣባላት በ 3677 ቡድኖች ተደራጅተዋል፡፡ ይህም አፈጻጸም

አባላቱ 93% ሲሆን ቡድን 142% ነው፡ የቡድን አደረጃጀት ከፍተኛ የሆነበት በአማካይ 30 አባላት በአንድ

ቡድን እንዲደራጁ ታሳቢ ተደርጎ ነበር የታቀደው፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ አከባቢዎች የህብረተሰቡ አሰፋፈር

የተራራቀ በመሆኑና አመቺ ባለመሆኑ በአማካይ 20 አባላት እንዲኖሩት ሆኖ እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡

10. ኅ/ ሥራማህበራትማስፋፊያ ኤጄንሲ

አዲስ ህ/ ስራ ማህበራትን ማቋቋም

በ 2008 በጀት ዓመት በዓይነት 22 በብዛት 411 ኅ/ ሥራ ማህበራት ተቋቁመው ለአባሎቻቸው አገልግሎት

በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በ 5 ቱ ዓመት ዕቅድ/GTP-2/ ከተቀመጠው ከመጀመሪያው ዓመት ግብ ጋር ሲነጻጸር

በማቋቋም የ 11 ወራት አፈጻጸም 67% ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል 3 ዬኒዬኖች / 2 የዘር ብዜት 1 የቡና ግብይት/ ማቋቋም የተቻለ ሲሆን በመሠረታዊ ኀ/ ሥራ ማኀበራት

ደረጃ 11,654 ወንድ እና 2,044 ሴት በድምሩ 13,798 አባላትን እና በዬኒዬን ደረጃ ደግሞ 35 አባል

53

መሠረታዊ ኀ/ ሥራ ማኀበራትን በመሥራች አባልነት ይዘው እንዲመሰረቱ ማድረግ ተችሏል፡፡

ነባር ህ/ ማህበራትን ማጠናከር

የአባላትን ቁጥር ከማሳደግ አኳያ

በበጀት ዓመቱ በ 12,390 መሠረታዊ /ህ/ ት ሥራ ማህበራት በድምሩ 274,737 አባላት እንዲታቀፉ በመደረጉ

የአባላት ሽፋን 91.47% መደረስ ችሏል፡፡

የካፒታል አቅም በማሳደግ በኩል

በበጀት ዓመቱ በተሠራው ሥራ የመሠረታዊ ህ/ስ/ ማህበራት ካፒታል ብር 126,049,965 የደረሰ ሲሆን ከበጀት

ዓመቱ ዕቅድ የ 65.64% ድረሻ አለው፡፡

የግብይት ትስስርና የግብርና ምርት ግብይት እንቅስቃሴአችን

በዚህ በጀት ዓመት የክልሉ ሕ/ ስራ ኤጄንሲ ምርት አቅራቢ 25 ዩኒየኖችን ከምርት ፈላጊ ዩኒየኖች ጋር ተከታታይና

ወጥ በሆነ መንገድ በዘለቄታ የግብይት ትስስሩን 415,291 ኩ/ ል ምርት ለማቅረብ እና ለመቀበል የውል ስምምነት

በመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ 201,309 ኩ/ ል ግብይት መፈጸም ተችሏል፡፡

በ 2008/2009 ምርት ዘመን የህ/ ስራ ማህበራትን የግብይት ድርሻ ለማሳደግ 12,279,061 ኩ/ ል የግብርና

ምርት ግዥ ለመፈጸም ታቅዶ እስከ አሁን የተገዛ 669,523(41%) ኩ/ ል በብር 510,319,110 ግዥ

ተፈጽሟል፡፡

ለሰሊጥና ነጭ ቦለቄ ምርት ግብይት አገልግሎት የሚውል በዘርፉ ለሚሳተፉ 9 ሁለገብ የገ/ህ/ ስራ ማህበራት ብር

265 ሚሊዮን በመንግስት ዋስትና ተፈቅዶ በድምሩ ብር 60 ሚሊዮን /22.65%/ ከባንክ ወጪ ሆኖ ግብይት

እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡በዚህም ጸሐይ ዩኒየን 7,220 ኩ/ ል የውጭ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ 718,248 ዩኤስ ዶላር/ ብር 16,063,940/ ገቢ እንዲገኝ በማድረግ የክልሉን ብሎም የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት

ማሳደግ ችሏል፡፡

የ ኮሚሽን ምርት ግብይት አፈፃፀም

ኅ/ሥ/ ማኅበራትን ወደ ዘመናዊ እና አባላትን የላቀ ተጠቃሚ በሚያደርገዉ የኮሚሽን ግብይት ዉስጥ ለማስገባት

ከባለፈዉ ዓመት ጀምሮ በተመረጡ ፓይለት ዩኒዬኖችና መሠረታዊ ኅ/ሥ/ ማኅበራት እየተሠራ ይገኛል። በቆሎ ምርት-15,141" ስንዴ- 4,638 "ጥጥ-16,993" ጤፍ-520 በድምሩ 39,145 ኩ/ ል በኮሚሽን ምርት ግብይት

ተካሂዷል፡፡

የሰብል ምርት ግብይት አፈጻጸም፣

54

በምርት ዘመኑ ወደ 1.6 ሚ/ ን ኩ/ ል የተለያየ ሰብል በኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት ለመግዛት እቅድ ተይዞ

እስከ አሁን የተገዛ 669,523(41%) ኩ/ ል በብር 510,319,110 ግዥ ተካሂዷል፡፡

የኤክስፖርትእንቅስቃሴ እስከዚህ ወር ድረስ ፀሃይ ዩኒዩኒን 7,220 ኩ/ ል ሰሊጥ እና ኑግ ወደ

ቻይና፣እስራኤል፣ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ኤክስፖርት በማድረግ 718,240 ዩኤስ ዶላር ወይም ብር

16,063,940 ገቢ እንዲገኝ በማድረግ የክልሉን ብሎም የሃገሪቱን የወጭ ምንዛሬ ግኝት ማሳደግ ተችሏል፡፡

ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ፣

ኀ/ ሥራ ማኀበራት የአባላቱን ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ

ለሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት በክልላችን ከሚገኙ 2,141 መሠረታዊ ኀ/ ሥራ ማኀበራት እና 38 ዬኒዬኖች የሠራተኛ ቅጥር

ለመፈፀም በተያዘው እቅድ መሠረት እስካሁን 850 መሠረታዊ ኀ/ ሥራ ማኀበራት 1,415 /585 ሴቶች/ እና

በ 24 ዬኒዬኖች 27/16 ሴቶች/ ቅጥር ሠራተኞችን በድምሩ 1,442/601 ሴቶች/ ሥራ ፈላጊዎችን በመቅጠር

ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኃላፊነታቸው አኳያ ኀ/ ሥራ ማህበራት ጉልህ ሚናቸውን በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

የህ/ ስራ ማህበራትን ቁጠባ ከማሳደግ አንጻር

በበጀት ዓመቱ የገንዘብ ቁጠባ ህ/ ሥራ ማህበራት ብር 157,758,246 በመቆጠብ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ

74.60% ሸፍነዋል፡፡

የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ/ ስራ ማህበራት የብድር ስርጭት

የገንዘብ ቁጠባ ህ/ ስራ ማህበራት በበጀት ዓመቱ ብር 392,785,527 /151.6%/ ለአባሎቻቸው በማበደር

ለተለያዩ ተግባራት እንዲውል በማድረግ ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡

የህ/ ስራ ማህበራት የሂሳብ ምርመራን በተመለከተ

የህ/ ስራ ማህበራት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ሂሳባቸው እንዲመረመር በአዋጁ በተቀመጠው መሠረት በዚህ በጀት

ዓመት የሂሳብ ምርመራ የተደረገላቸው መሰረታዊ ህ/ ስራ ማህበራት 4,374 /63.32% ሲሆኑ ሁለተኛ ደረጃ

ህ/ ስራ ማህበራት ዩኒየኖች ደግሞ 54/ 84.37%/ ናቸው፡፡የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ካገኙት 975 ህ/ስራ

ማህበራት በድምሩ ብር 34,772,383 ጉድለት ተከስቷል፡፡አገልግሎቱን ካገኙት ሕ/ ስራ ማህበራት መካከል

3,458 ማህበራት ከጉድለት ነጻ ናቸው፡፤ እስከአሁን ከተከሰተው ጉድለት ውስጥ ብር 24,858,807 /23.53%/ ማስመለስ ተችሏል፡፡

11. የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችጥራት ቁጥጥርኳራንታይን

በመኸር የእጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር

55

በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር የማድረግ ስራን በተመለከተ በበጀት አመቱ 27,256.5 ሄ/ ር መሬትና 613,399 ኩ/ ል ምርት የመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ እስከ ዚህ ወር ድረስ በተደረገ የስራ እንቅስቃሴ

15,374.63 ሄ/ ር መሬትና 339,627.5 ኩ/ ል የሚገመት ምርት የጥራት ቁጥጥር ተደርጎበታል አፈፃፀሙም

53.77% ያህል ነዉ፡፡የጥራት ቁጥጥር ከተደረገበት የዘር ማሳ 13,791.8 ሄ/ ር ያህሉ መሬትና 339,627.1 ኩ/ ል ያህሉ ምርት እስከታየበት የእድገት ደረጃ ድረስ የጥራት ደረጃዉን አሟልቶ የተገኘ ሲሆን 1291.2 ሄ/ር

ማሳና 16,601.5 የሚገመተዉ ምርት ግን የዘር ጥራት ደረጃ መስፈርቱን ያላሟላ በመሆኑ ለዘርነት እንደማይዉል

ተረጋግጧል፡፡

በመኸር የጥራት ቁጥጥር ከተደረገበት ማሳ

በበጀት ዘመኑ በሰብል ዘር ብዜት ይሸፈናል፤ የጥራት ቁጥጥርም ይካሄድበታልም ተብሎ ከታሰበዉ 27,256.5 ሄ/ ር የዘር ማሳ ዉስጥ በዘር ሰብል ተሸፍኖ የጥራቱ ቁጥጥር የተደረገበት 15,291.6 ሄ/ ር ሲሆን ቀሪዉ

11,964.9 ሄ/ ር ማሳ ግን በታቀደዉ መሰረት በዘር ሰብል በመሸፈኑ የጥራት ቁጥጥር ሳይካሄድበት ቀርቷል፡፡

በመስኖ

በበጀት አመቱ በሁለት የመንግስትና በሶስት የግል ዘር አምራች ድርጅቶች በመስኖ የሚመረት የዘር 2410.67 ሄ/ ር ያህል መሬት ላይ እና 22880 ኩ/ ል ምርት ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማካሄድ ታቅዶ እስከዚህ ሩብ ዓመት ድረስ

በቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች በተደረገው እንቅስቃሴ 733.816 ሄ/ ር የዘር ማሳ ፍተሻ ተደርጎበት 620.237 ሄ/ር

መሬትና 14558.68 ኩ/ ል የሚገመት ምርት እስከታየበት የእድገት ደረጃ ድረስ የጥራት ደረጃውን አሟልቶ የተገኘ

ሲሆን 20.35 ሄ/ ር መሬት የሸፈነ ሰብልና 43.7 ኩ/ ል የሚገመት የምርት መጠን ከጥራት ደረጃው በታች ሆኖ

በመገኘቱ ለዘርነት አገልግሎት እንዳይውል ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡

የመስኖ ዘር ልማት እቅዱ 2410.67 ሄ/ ር መሬትና 22880 ኩ/ ል የነበረ ቢሆንም ዘር አምራች ድርጅቶች በተለያዩ

ምክንያቶች እቅዳቸውን ሳያከናውኑ በመቅረታቸው የጥራት ቁጥጥር ስራው የተሰራው ከታቀደው መሬት 30.44% መሬት ላይ እና በ 63.63% ምርት ላይ ብቻ ነው፡፡

የቅድመ መስራች ዘር ኢንስፔክሽን

በምርት ዘመኑ በድምሩ 188.25 ሄ/ ር መሬትና በቅድመ ዘር ለመሸፈን ታቅዶ 188.25 ሄ/ ር የተሸፈነ ሲሆን ከዚህ

ዉስጥ 188.25 መሬትና 2449 ኩ/ ል ምርት መስፈርቱን ያሟላ ሆኖ ሲገኝ 1.5 ሄ/ ር መሬትና 22.5 ኩ/ል

የሚገመት ምርት መስፈርቱን ባለማሟላቱ ወድቋል፡፡

የዘር ማሰባሰብና ማዘጋጀት ተግባራት

ዘር ጥራቱ እንደተጠበቀ ተሰብስቦና ተዘጋጅቶ ወደ ስርጭት መሄድ ይችል ዘንድ ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ስለሆነም እስከዚህ ወር ድረስ ባለው የዘር ማሰባሰብና ማዘጋጀት ሂደት 183,882.2 ያህል ኩንታል ዘር የተሰበሰበ

56

ሲሆን ከተሰባሰበው ዘር 128430.9 ኩ/ ል ያህሉ ተማዘጋጅቶ 127941.525 ኩ/ ል ያህሉ ናሙና ተወስዶበት

114815.4 ኩ/ ል ያህሉ የጥራት ቁጥጥር ስራ ተከናውኖበታል፡፡

በክምችትና በላቦራቶሪ የዘር ጥራት ፍተሻ

አዲስ ዘር በላቦራቶሪ መፈተሽ በተመለከተ በበጀት አመቱ ከ 616117 ኩ/ ል የዘር ምርት ላይ 4149 ያህል ወካይ

ናሙናወችን በመውሰድ የዘር ጥራትን ለመፈተሸ ታቅዶ እስከያዝንው 11 ወር ድረስ በተለያዩ የዘር ሰብሎች

116071.301 ኩ/ ል ምርት ላይ 462 ወካይ ናሙናዎችን በመውሰድ የፍተሻ ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚህም ፍተሻ

ከተደረገበት የዘር ምርት በ 425 ናሙና የተወከለው 109968.6 ኩ/ ል ምርት የጥራት ደረጃውን ያሟላ ሆኖ

በመገኘቱ ለዘርነት አገልግሎት እንዲዉል የተወሰነ ሲሆን በ 37 ናሙና የተወከለው 6102.701 ኩ/ ል ምርት ግን

የጥራት ደረጃውን ያላሟላ በመሆኑ ለዘር አገልግሎት እንዳይውል ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡

የከራሚ ዘር ፍተሻ በበጀት ዓመቱ ፍተሻ እንዲደረግበት ጥያቄ የቀረበልንን ከራሚ ዘር ሙሉ በሙሉ ለመፈተሽ እቅድ

ተይዞ እስከዚህ በዚህ ወር በ 879 ናሙናዎች የተወከለ 47275.8 ኩ/ ል የዘር ምርት ፍተሻ ተደርጎበት በ 404 ናሙናዎች የተወከለው 38391.9 ኩ/ ል ምርት የትራት ደረጃውን ያሟላ በመሆኑ ለዘርነት አገልግሎት እንዲውል

የተወሰነ ሲሆን በ 475 ናሙና የተወከለው 8883.89 ኩ/ ል ዘር ግን የጥራት ደረጃውን ባለማሟላቱ ለዘርነት

አገልግሎት እንዳይውል ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡

የዘር ጤና ፍተሻ የዘር ጤና ፍተሻ በላቦራቶሪ ፍተሻ በሚደረግባቸዉ ሁሉም የዘር ናሙናዎች ላይ እንዲተገበር

የሚታሰብ ቢሆንም እስካሁን ግን ሁሉም ላቦራቶሪዎችን በከራሚ ዘሮች ላይ ሲተገበር አይስተዋሉም፡፡ ደሴ በ 47 ናሙናዎች ላይ ፍተሻ በማድረግ ስራውን የጀመረ ሲሆን ጎንደር ደግሞ በ 45 ናሙናዎች ላይ ፍተሻ ማድረጉን

በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ በመሆኑም በድምሩ እንካሁን በ 92 ናሙናዎች ላይ የዘር ጤንነት ፍተሻ ተደረጓል፡፡ በአጠቃላይ

ወደ ላቦራቶሪ መጥተዉ በሚፈተሹ ሁሉም ዘሮች የዘር ጤንነት ፍተሻ መተግበር መቻል እንዳለበት ታዉቆ ሌሎችም

ሁሉቱ ቅ/ጽ/ ቤቶች ማለትም ባህር ዳርና ደብረማርቆስ ወደዚህ ስራ ያልገቡ በመሆናቸው መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ዘር አምራች ድርጅቶችን መከታተልና መደገፍ

በጥቅሉ እስከዚህ ወር ማሳደስ ከነበረባቸዉ 21 ያህል ዘር አምራች ድርጅቶች መካከል 14 ያህል የብቃት

ማረጋገጫ እድሳት አካሂደዋል፡፡ በተጨሪም በጎንደር ቅርንጫፍ ስር 1 እና በባህርዳር/ ማርቆስ ስር 2 በባህር ዳር

ስር 1 በድምሩ ለ 4 አዲስ ዘር አምራች ድርጅቶች ወደ ዘር ማምረት ስራ ለመግባት የሚያስችል የብቃት መረጋገጫ

ተሰጥቷል፡፡

የዘር ማሳን በጂ.ፒ. ኤስ /GPS/ መለካትና ካርታ ማዘጋጀት

57

የ መስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር ስራን ይበልጥ ተዓማኚ ለማድረግ GPS የተባለዉን ቴክኖሎጂ መጠቀም ወሳኝ

መሆኑ ታምኖበት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ በመሆኑም 3500 ሄ/ ር በእቅድ ተይዞ ክንዉን 4119.35 የተከናወነ ሲሆን

አፈፃፀሙም 117.65% ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመስኖ የዘር ብዜት ማሳዎች ጎንደር 52.37 ሄ/ር

ደብረማርቆስ 152 ሄ/ ር ደሴ 103 ሄ/ ር ባህር ዳር 17.65 ሄ/ ር በድምሩ 326.64 ሄ/ ር ማሳ በጂ.ፒ.ኤስ

በመታገዝ የጥራት ቁጥጥር ስራ ተከናውኖበታል፡፡

የደንና መኖ ዘር ጥራት ቁጥጥር

የደንና መኖ ዘር ችግኝ ጣቢያ ኢንስፔክሽን ማካሄድ ስራ ቢያንስ በዓመቱ ዉስጥ 295 በቁጥር ተይዞ በ 11 ወር ዉስጥ 280 በቁጥር ይሰራ ተብሎ ከተያዘዉ እቅድ እስከዚህ ሩብ ዓመት 159 በቁጥር በመሰራቱ አፈፃፀሙ

54% ለመሆን ችሏል፡፡

አትክልትና ፍራፍሬ ዘር ጥራት ቁጥጥር

የደጋ ፍራፍሬ ኢንስፔክሽንን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ በግል በመንግስትና በማህበራበ ችግኝ ጣቢያዎች

3,510,000 ያህል ችግኞች ላይ የጥራ ቁጥጥር ላመካሄድ ታቅዶ እሰከ ያዝንው 11 ወር ድረስ 636,904 ያህል ችግኝ የጥራት ቁጥጥር ተደርጎበታል፡፡

የደጋ ፍራፍሬ እናት ዛፍ የጥራት ቁጥጥርን በተመለከተም በ 410 እናት ዛፎች ላይ የጥራት የጥራት ቁጥጥር

ላመድረግ ታቅዶ በ 173 እናት ዛፎች ላይ የጥራት ቁጥጥር ተደረጓል

የቆላ ፍራፍሬ የጥራት ቁጥጥር ሌላው በስፋት የሚከናወን ተግባር ሲሆን በያዝንው በጀት ዓመት በመንግስት በግልና

በማህበራ ችግኝ ጣቢያዎች በ 4,350,000 ችግኝ መካከል በ 1,377,388 ያህል ችግኝ ላይ የጥራት ቁጥጥር

ተከናውኗል፡፡

12. የአማራምርጥዘር ኢንተርፕራይዝ

የዘርማምረት /ብዜት/ አፈፃፀም

ኢንተርኘራይዙ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅትና ከተለያዩ ምርምር ማዕከላት መነሻ ዘሮችን በማሰባሰብ

በአርሶ አደርና በግል ባለሀብቶች መሬት በኮንትራትና በራሱ ዘር ማባዣ እርሻ ምርጥ ዘር ያባዛል፡፡

በዚህ መሰረት በ 2007/2008 መኸር ወቅት በዋና ዋና ሰብሎች ማለትም የዳቦ ስንዴ፣ በቆ፣ የብራ ገብስ፣ ጤፍና

የሌሎችንም ስብሎች በርካታ ዝርያዎች በ 12,823 ሄ/ ር መሬት ላይ በመዝራት 326,500 ኩንታል ዘር ለማምረት

አቅዶ 9,328.4 ሄ/ ር ( የዕቅዱ 73%) በዘር የሸፈነ ሲሆን 119,147 ኩ/ ል ምርጥ ዘር ተሰብስቧል፡፡አፈፃፀሙ

ካለፈው ምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር የ 21.4% የምርት ብልጫ አለው፡፡ ከመኸር ወቅት በተጨማሪ በ 2008 ዓ.ም

በመስኖ በ 1877 ሄ/ ር መሬት ላይ 36,800 ኩንታል ለማምረት በማቀድ ወደ ተግባር ተገብቶ 458.4 ሄ/ ር መሬት

(24.4%) ተዘርቶ 1,150 ኩንታል ምርጥ ዘር ተሰብስቧል፡፡ቀሪው በመስኖ የተባዛ ምርጥ ዘርም በመሰብሰብ ላይ

ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ በመኸርና በመስኖ 9,787 ሄ/ ር መሬት ተዘርቶ 120,297 ኩንታል ልዩ ልዩ ምርጥ ዘር

58

ተሰብስቧል፡፡አፈጻጸሙ ሲታይ ከዕቅዱ 33% ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ 4% በላይ ብልጫ

አለው፡፡

በ 2008/2009 ምርት ዘመን ደግሞ በ 10,115 ሄ/ ር መሬት የተለያዩ ሰብሎችን ምርጥ ዘር በማባዛት

246,587 ኩንታል ለማምረት ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 3,154.8 ኩንታል

መስራች ዘር ቀርቦ ከዚህ ውስጥ 1,208.3 ኩንታል የተሰራጨ ሲሆን የተዘራው መሬትም 1,874.2 ሄ/ ር ነው፡፡

የመስራች ዘር አቅርቦት፣ ስርጭትና የዘር ሥራ እንቅስቃሴው በየሰብሉ የዘር ወቅት ቅደም ተከተል በመከናወን ላይ

ይገኛል፡፡ ከተዘራው መሬት ውስጥ 359 ሄ/ ር መሬት በኢንተርኘራይዙ የዘር ማባዣ መሬት የተዘሩ ድቃይ በቆሎና

አኩሪያተር ሰብሎች ይገኙበታል፡፡

ዕቅዱን ለማሣካት መስራች ዘር አቅርቦ ከማሰራጨት በተጨማሪ የድቃይ በቆሎ የዘር ብዜት በሚካሄድባቸው

አካባቢዎች ለሚገኙ 56 ከዞን እስከ ቀበሌ ለተውጣጡ የግብርና አመራሮችና ባለሙያዎች የሁለት ቀን የዕቅድ

ኦሬንቴሽንና የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በቢራ ገብስ ደግሞ ከዞን እስከ አርሶ አደሩ ድረስ ከግብርና ቢሮ ጋር

በመቀናጀት የተደራጀና የመፈፀም አቅምን ሊያጎለብት የሚችል የክህሎት ስልጠና እስከ ቀበሌ ድረስ ለሚገኙ 297 ባለሙያዎች የ 8 ቀንና ለ 797 አ/ አደሮች የ 8 ቀን ተሰጥቷል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የምርት ወቅቶች አፈፃፀም ሂደት ከታዩት መሻሻሎች መካከል ከበርካታ ምርምር ማዕከላትና

ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የተለያዩ ዝርያዎችን ቅ/ መስራችና መስራች ዘር በአመዛኙ በወቅቱ ማቅረብ፣ በቢራ

ገብስና ድቃይ በቆሎ የተሻለ አቅም የሚፈጥር ስልጠና መሰጠቱ፣ የብዜት ተሣታፊ አ/ አደሮች መረጃ በወቅቱ

ተሰብስቦ ወደ ኮምፒውተር መግባቱ፣ የገበያ ጥናት በወቅቱ መከናወኑ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ከተከናወነው በላይ ላለመፈፀም በእጥረት ከሚጠቀሱት መካከበል ዋና ዋናዎቹ የዘር ስርጭትን

በተሟላ ዝግጅትና ጠንካራ ክትትል በወቅቱ የመፈፀም ክፍተት፣ በመስክ ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ችግሮችን ለይቶና ፈቶ

የመምጣት ውስንነት ( በተለይ በድቃይ በቆሎ) ፣ ሥራዎች ሲሰሩ በኢንተርኘራይዙ ወጭና ገቢ ላይ የሚያሳድሩትን

ተፅዕኖ እየመዘኑ በጥንቃቄ አለማከናወን፣ የቻግኒ የዘር ብዜት ሥራን የተሟላ መረጃ የመያዝና ውጤታማነቱን

ይበልጥ ለማሣደግ አልሞ የመስራት ክፍተት፣ በመለዋወጫ ችግር ምክንያት የትራክተር ጥገና መዘግየት፣ የቻግኒ

የዘር መሰብሰብ ሥራ የተራዘመ ጊዜ መውሰድ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተም የመስራች ዘር አጥረት፣ የቀረበውም በተለያዩ ምክንያቶች ሙሉ በሙሉ ጥቅም

ላይ አለመዋል ፣ በኢሊኖ ሳቢያ የተከሰተው የዝናብ እጥረት በምርታማነትና በዘር ጥራት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ፣

በኢንተርኘራይዙ እርሻ ለሚባዛው ዘር የቀን ስራተኛ እጥረት፣ የቆጋ መስኖ ውሃ መቀነስና የቆቦ ራያ መስኖ ኘሮጀክት

የትራንስፎርመር ችግር ለመስኖ ዘር ብዜት አፈፃፀም ማነስ የጐላ ተፅዕኖ ማሣደሩ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥራ አፈፃፀም

በመስክ ኢንስፔክሽንና በዘር ማሰባሰብ ወቅት የዘር ጥራት ቁጥጥር ማካሄድ፡-

59

በ 2007/2008 መኸር ወቅት የተዘሩትን ሰብሎች በተለያዩ የሰብል የዕድገት ደረጃዎች በመስክ ላይ በተካሄደ የጥራት ቁጥጥር (Field Inspecition) ከተዘራው 9,328 ሄክታር መሬት ውስጥ 8,668 ሄክታር ዝቅተኛ የጥራት ደረጃውን ያሟላና ከዚህም 217449 ኩንታል ምርጥ ዘር ሊገኝ እንደሚችል በተካሄደው ኢንስፔክሽን

ተገምቷል፡፡780 ሄክታር መሬትና 8,343 ኩንታል የሚገመት ዘር በመስክ ኢንስፔክሽኑ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውድቅ ተደርጔል፡፡ከተዘራው መሬት ውስጥ የተወሰነ መሬት በእርጥበት እጥረት ምክኒያት የብቅለትና የዕድገት ችግር ስለነበረበት የመስክ ኢንስፔክሽን አልተካሄደበትም፡፡ በመስክ ኢንስፔክሽን ካለፈው ማሳ ይገኛል ተብሎ

ከተጠበቀው ምርት ውስጥ በተካሄደው የፊዚካል ዘር ጥራት ቁጥጥር ጥራቱን ያሟላውን 119,147 ኩንታል ምርጥ ዘር ለማሰሰባሰብና ግዥ ለመፈጸም ተችሏል፡፡ በመስክ ኢንስፔክሽን ይገኛል ተብሎ ከተገመተው ምርት

አንጻር የተሰበሰበው አፈጻጸም 55% ሲሆን ባለፈው አመት ከነበረው የ 44% አፈጻጸምና ከዘመኑ የዝናብ መጠንና

ስርጭት መዛባት አንጻር ሲታይ ኢንተርፕራይዙና በየደረጃው የሚገኘው የግብርና መዋቅር በዘር አሰባሰብ ላይ

ያደረገው ጥረት መሻሻል ያሳየ መሆኑን ያመለክታል፡፡

በ 2008 መስኖ ወቅት በተደጋጋሚ በተካሄደው የማሳ ላይ ኢንስፔክሽን በዘር በተሸፈነው 458 ሄ/ ር መሬት ላይ የሚገኘው ሰብል በሙሉጥራቱን የጠበቀ በመሆኑ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ከዚህ መሬት 8,717 ኩንታል ምርት

ሊገኝ እንደሚችል የተገምቷል፡፡ምርቱ ገና ተሰብስቦ ባይጠናቀቅም እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስየፊዚካል ጥራት ቁጥጥር መስፈርቱን ያሟላ 1150 ኩንታል ዘር መሰብሰብ ተችላል፡፡

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ መኸርና መስኖ ወቅት 9,786 ሄክታር መሬት ላይ በተባዛው ምርጥ ዘር በተካሄደው ተደጋጋሚ የመስክ ኢንስፔክሽንተቀባይነት ካገኘው 9,126 ሄክታር መሬት ላይ ይገኛል ተብሎ ከተገመተው

226,166 ኩንታል ውስጥ የቀረበውን ዘር በሙሉ ፈትሾ የፊዚካል ዘር ጥራቱን ያሟላውን 120,297 ኩንታል የተለያየ ሰብል ምርጥ ዘር መሰብሰብ ተችሏል፡

የላቦራቶሪ ዘር ጥራት ፍተሻ ማካሄድ፡-

በውስጥ ላቦራቶሪ የዘር ጥራት ፍተሻ ማካሄድ፤

በመኸርና በመስኖ ተባዝቶ ከተሰበሰበው 120297 ኩንታል ያልተበጠር ምርጥ ዘር ላይ 593 ናሙናዎች በመውሰድ ዝቅተኛ የጥራት መስፈርቱን አሟልቶ የተገኘው 113,393.24 ኩንታል ዘር እንዲበጠርና እንዲዘጋጅ በማድረግ ለእ/ዘሌ/የግ/ግ/ጥ/ቁ/ካ/ ባለስልጣን ጥራቱ ተረጋግጦ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

ተበጠሮ የተዘጋጀው ምርጥ ዘር የኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት ብቅለቱ፣ ጥራቱ፣ የእርጥበት መጠኑና አደራደሩ ዝቅተኛ የጥራት ደረጃውን ያሟላ መሆኑ እየተረጋገጠ በማያሻማ ሁኔታ

በእያንዳንዱ ከረጢት ላይ በታግ እንዲፃፍ ተደርጋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከ 2007 በጀት ዓመት ሥርጭት ተርፎ በመጋዘን ተከማችቶ ከከረመው 17540.25 ኩንታል ምርጥ ዘር ውስጥ ለ 2008 በጀት ዓመት ለዘር አገልግሎት ለማዋል የቆይታ ጊዜውን ከግምት አስገብቶ በድጋሜ

በላቦራቶር ጥራቱ መረጋገጥ ካለበት ዘር ላይ 87 ናሙና በመውሰድ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጧል፡፡

60

ዘር ማበጠርና ዝግጅት

ኢንተርፕራይዙ ባስገነባቸው አራት የዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ጣቢያዎች በ 2008 በጀት ዓመት በመኸርና በመስኖ አባዝቶ ያሰባሰበውን ምርጥ ዘር በወቅቱ ለተጠቃሚው ለማሰራጨት እንዲቻል ከጥር ወር አጋማሽ ጀምሮ

በማበጠር 113161 ኩንታል ንጹህ ዘር ማዘጋጀት ችሏል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ አመት የተሰባሰበው ዘር የንጽህና ውጤቱ በአማካኝ 95% ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በኢሊኒኖ ሳቢያ ከአየር መዛባት ጋር በተያያዘ በተለይ ቀቀባ የዳቦ ስንዴ ዘር በከፊል ውጤታማነቱ ዝቅተኛ እንደሆነ ለማወቅ ችልናል፡፡ ሌላው ሰብልና ዝርያ ጥሩ

እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

የማበጠርና የማዘጋጀት ሥራው እንደ ሰብሉ የዘር ወቅት ቅደም ተከተል በፕሮግራም የተመራ ሲሆን ካሁን በፊት ከማበጠር መዘግየት ጋር በተያያዘ የዘር ሽያጭና ስርጭት ላይ ይታይ የነበረው መጓተት በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በማበጠር ወቅት ከጥራት፣ ከኬሚካል አጠቃቀም፣ ከዘር አቀማመጥ ጋር ይፈጠር

የነበረው ችግር በተለይ ከባህር ዳር ጣቢያ ውጭ በሚገኙት ጣቢያዎች እየተሻሻለ የመጣ በመሆኑ የማበጠሩና ዝግጅት ሥራው በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡

በውጭ ላቦራቶሪ የዘር ጥራት ፍተሻ ማካሄድ፤

ኢንተርፕራይዙ በራሱ የውስጥ ላቦራቶሪ የዘር ጥራት ፍተሻ በማካሄድ አበጥሮ ያዘጋጀውን 113161 ኩንታል ምርጥ ዘር ለሥርጭት የሚያበቃ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት በአራት

የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች በወቅቱ ናሙና እንዲወሰድና እንዲረጋገጥ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በአራቱ የእፅዋት ዘርና ሌ/የግ/ ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች 565 ናሙናዎችን እንዲወስዱ በማድረግ ጥራቱን የማረጋገጥ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ ከተወሰደ የዘር

ናሙና ውስጥ ኮምቦልቻ ከተወሰደው ናሙና 98 ኩንታል፤ በደ/ ማርቆስ ከተወሰደው ናሙና 400 ኩንታል፤ ባህር ዳር ከተወሰደው ናሙና 7743 ኩንታል በድምሩ 8241 ኩ/ ል በብቅለት ችግር ምክንያት ወድቋል፡፡ በየሰብሉ

ዓይነት ሲታይ የዳቦ ስንዴ ቀቀባ ዝርያ 7637.5 ኩንታል፣ ማሽላ ጊራና-1 85 ኩንታል ድቃይ በቆሎ እናት ዘር 150 ኩንታል የቢራ ገብስ ሆልከር 13 ኩንታል ፣ አኩሪ አተር 353 ኩ/ ል በአጠቃላይ 8241.5 ኩንታል ዝቅተኛ

ደረጃውን ባለማሟላቱ የወደቀ ቢሆንም የብቅለት መጠኑ ከ 80% በላይ የሆነው የዳቦስንዴ ቀቀባ ዝርያ ለአደጋ ጊዜ የዘር አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከ 2007/2008 መኸርና መስኖ ወቅት ስርጭት ተርፎ ከነበረው ዘር ውስጥ በድጋሚ የላቦራቶር ምርመራ ከሚያስፈልገው የጤፍ፣ የድቃይ በቆሎ፣ የዳቦ ስንዴና የቢራ ገብስ ምርጥ ዘር በተወሰደው

ናሙና መሰረት የጥራት ደረጃውን ያሟላው 11347 ኩንታል ሲሆን ያላሟላው ደግሞ 938 ኩንታል የድቃይ በቆሎ መስራች ዘር፣ የዳቦ ስንዴና የቢራ ገብስ ምርጥ ዘርነው፡፡

የዘር ማከምና የመጋዘን ርጭት ሥራ አፈፃፀም በተመለከተ፤

የጎተራተባይመከላከል

61

በዚህ ዓመት የጐተራ ተባይን ለመከላከል በከረመውና በዘመኑ በተሰባሰበው ዘር ላይ በተካሄደው ክትትልና ቁጥጥር 67767 ኩንታል ምርጥ ዘር በ 21265 ፎስቶክሲን ታብሌት በመጠቀም የማከምና የጐተራ ተባይን አስቀድሞ በመከላከል ከጉዳት ነፃ የማድረግ ሥራ ተካሂዷል፡፡

የመጋዘን ርጭት ማካሄድ

በዓመቱ ለዘር ማከማቻ አገልግሎት በሚውሉ መጋዘኖች ላይ የቅድመ መከላከል ስራ ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሰረት 16 መጋዝኖችን 14.30 ሊትር ዲያዝኖን 60% ኢሲ በመጠቀም ርጭት ተከናውኗል፡፡ በመሆኑም ዓመቱን ሙሉ

መጋዘኖች ተከፍተው እንዲናፈሱ፣ ፅዱና ለሥራ ምቹ እንዲሆኑ በማድረግ ጤናማ ዘር ለማሰራጨት ችለናል፡፡

የፀረ- አረም ኬሚካል ርጭት

በዚህ ዓመት በቻግኒ በተዘራው 343.24 ሄክታር የድቃይ በቆሎ ዘር ብዜት ማሳ ላይ 1055 ሊትር የቅድመ ብቅለት አረም መከልከያ (ፀረ- አረም) ኬሚካል ቡትራዚን 48% SC ርጭት ተካሂዳል፡፡ በተመሳሳይ በማሳ

ዙሪያና በብሎክ መካከል የሚገኘውን አረም ለማጽዳት በ 4 ሄክታር መሬት ላይ 19 ሊትር የድህረ ብቅለት አረም መከላከያ ኬሚካል ትረስት ሴት 360 ኤስ ሲ ርጭት ተካሂዷል፡፡

ሰንጠረዥ 1. በበጀት ዓመቱ መኸርና በመስኖ በድምሩ የተመተ፣ የተበጠረናጥራቱ ተረጋግጦ ለስርጭት የተዘጋጀ ም/ ዘር በዓይነትና በመጠን

ተ.ቁ የሰብል ዓይነት

ዝርያ ጠቅላላ የተሰበሰበ ዘር

በኩንታል

የተበጠረ ዘር መጠን

በኩንታል

ዝቅተኛ የጥራት ደረጃውን ያሟላ ዘር

በኩንታል

ብቅለቱ ከ 80-84.9% ሆኖ ለአደጋ ጊዜ

ሊሰራጭ የሚቻል ዘር በኩንታል

የደቀ/ ለአደጋ ጊዜ ስርጭትም

የማይውል/ ዘር በኩንታል

1 የቢራ ገብስ ሆልከር 4,776 4504 4,491 - 13

2 የዳቦ ስንዴ ቀቀባ 44,341.36 40263 32,626 7,037 ኩ/ል 600

ዳምፌ 34,221 34136 34,136 -

ህዳሴ 3,263 3,241 3,241 -

ሌሎች ዝርያዎች 83 80 80 -

ንዑስ ድምር 81,908.4 77720 70,083 7037 600

BH-540 8,100.6 7,127 7,127 -

BH-661 14,741.3 14,174 14,174 -

BH-660 942 957 957 -

62

3 ድቃይ በቆሎ

BH-545 199.74 192 192

መስራች 158.7 150 150

ንዑስ ድምር 24,142.3 22,600 22,450 150

4 ጤፍ

እጹብ 2,277 2,046 2,046 -

ቁንጮ 5,727.8 5,561 5,561 -

ሌሎች ዝርያዎች 67 60 60 -

ንዑስ ድምር 8,022.75 7,667 7,667

5 ሌሎች ሰብሎች

የሌሎች ሰብሎች ዝርያዎች

1446.7 670 584.7 840.64

ጠቅላላ ድምር 120,296 113161 105,276 7,187 1453.64

በአጠቃላይ የዘር ጥራትና ቁጥጥር ሥራ አፈፃፀም ከላይ የተገለፀው ሲሆን የዘር ጥራትን ለማስጠበቅ በየደረጃው

ለሚገኙ ሙያተኞች ስልጠና በመስጠት፣በየአከባቢው የተባዛው ዘር ቶሎ ተሰብስቦ እንዲጓጓዝ ለማድረግ የነበረው

ድጋፍና ክትትል አበረታች የነበረ መሆኑ፣ያልተበጠረን ዘር በወቅቱ የውስጥ ላቦራቶር ምርመራ በማድረግ ለብጠራ

ዝግጁ ለማድረግ የተሳለጠ ስራ በመስራት ረገድ የነበረው አበረታች ጥረት፣ ለዘር ጥራት ቁጥጥርና ዘር ማበጠር

ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ቁሣቁሶችን ቀድሞ ለማሟላትና በወቅቱ አበጥሮ ለስርጭት ዝግጁ ለማድረግ የተደረገው

ጥረት፣ በመጋዘን የተከማቸን ዘር በጎተራ ተባይ እንዳይጋለጥ በንቃት እየተከታተሉ በማከም በኩል የተሰራው ሥራ፣

ዘር አባዝተው ላስረከቡ አ/ አደሮች የዘሩ ዋጋ በወቅቱ እንዲከፈል የባለሙያዎች ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ መሻሻል

የታየበት ዓመት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ በዘር ጥራትና ቁጥጥር በኩል የተስተዋሉና ቀጣይ መደገም የማይገባቸው ችግሮች ወቅታዊ ባልሆነ

ዝናብ ሣቢያጥራቱዝቅተኛ የሆነ ዘር ባለሙያዎች በመግዛታቸው በኢንተርኘራይዙ ገቢ ተጽዕኖ መፍጠሩ ለአብነት

ቀቀባ የዳቦ ስንዴ፣ የምርት ግመታውን ለአ/ አደር በመንገር ጥራት የሌለውን ዘር በዚያ ልክ ርክክብ እንዲፈፀም

አ/ አደሩ ጫና መፍጠሩ፣ በውስጥ ላቦራቶሪ አልፏል የተባለው ዘር በውጭ ላቦራቶሪ ሲረጋገጥ የተወሰነው የመውደቅ

ሁኔታና የውስጥ ላቦራቶሪ ጥራትና ታማኝነት መቀነስ፣ የኢንተርኘራይዙ ባለሙያዎች የጥራት ቁጥጥር ሥራ ሙሉ

ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን እያወቁ ለዞንና ወረዳ ባለሙያዎች ሥራውን በመስጠት ጥራት የሌለው ዘር መሰብሰብ፣

በልምድም በዕውቀትም የተሻሉ የኢንተርኘራይዙ ከፍተኛ ባለሙያዎች በዘር አሰባሰብ ወቅት ያደረጉት ድጋፍና ክትትል

ውስንነት ስለነበረ የጥራት ችግርን ሳይሰፋ በአፋጣኝ ችግሩን ተገንዝቦ በአለመፍታት ኢንተርኘራይዙን ለተጨማሪ

ወጪ መዳረጉ፣ በባህር ዳር ጣቢያ በታግ አፃፃፍ፣ በኬሻ አጠቃቀም ላይ በተወሰኑ ዝርያዎች ስህተት በመፍጠር ያንን

ስህተት ለማረም ለተጨማሪ ወጪ መዳረግ፣የዘር ጥራትን ለማሻሻል ስራዎች ሲሰሩ ወጭን ለመቀነስ አልሞ

የመስራት ውስንነትና የመሳሰሉት በበጀት ዓመቱ በዘር ጥራትና ቁጥጥር ሥራ አፈፃፀም ላይ የታዩ ችግሮች

በመሆናቸው በቀጣይ ችግሮች እንዳይደገሙ በጥንቃቄ መሥራት ይጠበቃል፡፡

የዘር ግብይት ሥራ አፈፃፀም፤

63

ኢንተርኘራይዙ በዘመኑ 120,297 ኩ/ ል ዘር ሰብስቦ በማበጠር 113,161 ኩ/ ልና ከ 2007 በጀት ዓመት

ስርጭት ከተረፈው 17,735 ኩ/ ል ምርጥ ዘር በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅትና ከተለያዩ ምርምር

ማዕከላት ለብዜት አገልግሎት 1,483 ኩ/ ል የተበጠረ ምርጥ ዘር ገዝቶ ያቀረበ ሲሆን በድምሩ 132,380 ኩንታል ዘር ለብዜትና ለምርት አገልግሎት እንዲውል አዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ

የተሸጠና የተሰራጨ ዘር 120,798 ኩንታል ነው፡፡ አፈፃፀሙ ከተዘጋጀው 91.28% ሲሆን ካለፈው ዓመት

ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ የ 21.7% ብልጫ አለው፡፡ ይህም የዘመኑ የዘር ሽያጭ አፈፃፀም የተሻለ

መሆኑን ያሳያል፡፡

የዘመኑ የምርጥ ዘር ስርጭትና ሽያጭ የተከናወነው በሶስት ዓይነት አሰራር ሲሆን ይህም ዩኒየኖች በቀጥታ

ከኢንተርኘራይዙ ጋር የዱቤ ሽያጭ ውል ይዘው ዘሩን ተረክበው ለአ/ አደሩ በማሰራጨት፣ የተለያዩ መንግስታዊና

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የዘሩን ዋጋ በቅድሚያ ለኢንተርኘራይዙ ገቢ በማድረግ ዘሩን ተረክበው በማሰራጨትና

ሌላው ደግሞ በቀጥታ የዘር ሽያጭ አሰራር መሰረት ኢንተርኘራይዙ ከመሰረታዊ ማህበራት ጋር ውል ይዞ ዘሩን አቅርቦ

በማህበራት በኩል ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት ነው፡፡

በዚህም መሠረት ከሐምሌ 1/2007- ሰኔ 30/2008 የተሰራጨ ምርጥ ዘር ዓይነትና መጠን እንደሚከተለው

ቀርቧል፡፡

ተ.ቁ የሰብል ዓይነት የተሸጠ ዘር መጠን በኩ/ል ድምር

በዩኒየኖች በተለያዩ ድርጅቶች በቀጥታ ዘር ግብይት

1 በቆሎ 10,309 1,536 7,191 19,036

2 የቢራ ገብስ 5,648.25 66 - 5,714.25

3 የምግብ ገብስ 216 15 - 231

4 የዳቦ ስንዴ 38,680.65 43,180 - 81,860.65

5 ማሽላ 63 1,471 - 1,534

6 ጤፍ 1,604.6 9,949 - 11,553.6

7 ሩዝ - 8 - 8

8 ሽምብራ 104.5 62 - 166.5

9 ምስር 421 100 - 521

10 አተር 34 5 - 39

11 ሰሊጥ - 134 - 134

ድምር 57,081 56,526 7,191 120,798

64

ከላይ በሰንጠረዥ እንደተመለከተው የተሸጠው ዘር በዩኒየኖች 47.2% ፣ በድርጅቶች 46.8% እና በቀጥታ ዘር

ግብይት 6% ድርሻ ያለው ሲሆን ለዘመኑ ዘር ሽያጭ የድርጅቶች ድርሻ ካለፉት ዓመታት አንፃር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ

ነው፡

በበጀት ዓመቱ የም/ ዘር ግብይት አንቅስቃሴ ከባለፉት ዓመታት በብዛት በመሸጥ በኩል የተሻለ የነበረ ሲሆን

ይኸውም የሚሸጠው ዘር በወቅቱ ተበጥሮ በመቅረብ በኩል መሻሻል የታየበት መሆኑ፣ በቆሎን በቀጥታ ዘር ግብይት

እንዲሸጥ የነበረው ድጋፍና ክትትል ጥሩ የነበረ መሆኑ፣ የጥራት ደረጃውን ያሟላ ም/ ዘር በየጊዜው ለግብርና ቢሮ

በማሣወቅ እንዲደለደል የነቃ ክትትል የነበረ መሆኑ፣ የንብረት ክፍል ሠራተኞች እረፍት ቀናቸውን ጨምረው

በመጠቀም የም/ ዘር ደንበኞቻችን በወቅቱ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ፣ በዩኒየኖችም ሆነ በቀጥታ ዘር ግብይት

የተሸጠ ዘር ገንዘብ በወቅቱ ለኢንተርኘራይዙ እንዲገባ የነበረው የተደራጀ ክትትል ጥሩ የነበረ መሆኑ፣ ለማህበራት

የተደረገው የኮሚሽን ክፍያ በወቅቱ መፈፀሙ፣ የም/ ዘር ግብይት ሥራ እንቅስቃሴ በሂደቱና በተቋሙ ሥራ አመራር

በጥብቅ የግምገማ ሥርዓት መመራቱ ዋና ዋና ጥንካሬዎች ሲሆኑ በዘር ግብይት ወቅት የታዩ እጥረቶች የመረጃ

ስርዓቱ ጠንካራ ባለመሆኑ ተለዋዋጭ መረጃ ማስተላለፍ፣ የዘር ገቢና ወጪ በወቅቱ አለመመዝገብ፣ ለቀጥታ ዘር

ግብይት የቀረበው በቆሎ BH-661 ሙሉ በሙሉ በአለመሸጡ መልሶ በማጓጓዝ በኢንተርኘራይዙ ላይ ወጪ

መጨመሩ፣ ዘር በዱቤ የወሰዱ አንዳንድ ዩኒየኖችና መሠረታዊ ማህበራት ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ አለማድረግ

የመሳሰሉት በበጀት ዓመቱ የተስተዋሉ ችግሮች በመሆናቸው በቀጣይ ዓመት መፍታት ይጠበቃል፡፡

የፋይናን ስሥራ አፈፃፀም

በዚህ በጀት ዓመት ለመደበኛ ሥራ ማስፈፀሚያዎች ብር 37,335,294 ብር ለልማት ሥራዎች ማስፈፀሚያ

423,435,302.40 በድምሩ 460,770,597.74 ብር በቦርድ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በዚህ መሠረት

ለልማት የተመደበው ገንዘብ በባንክ ብድር እንደሚሸፈን ታሳቢ ተደርጎ በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት

150,000,000 ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ በሰጠው ዋስትና መሠረት ብድር ወስደን ሁሉንም

ብድር እስከ ወለዱ ድረስ ተመላሽ ተደርጓል፡፡

የኢንተርኘራይዙ ገቢ አሰባሰብ

በበጀት ዓመቱ ከዘርና ከልዩ ልዩ ቁሣቁስ ሽያጭ ብር 220,356,049.72 ገቢ ተሰብስቧል፡፡

የኢንተርኘራይዙ ወጪ አፈፃፀም

በበጀት ዓመቱ ለዘር መግዣ፣ ለዘር ማጓጓዣ፣ ለኬሚካልና ለዘር ማቀነባበሪያ ቁሣቁስ መግዣና ለዓመቱ

መደበኛ ሥራዎች በጠቅላላ ብር 181,378,053.83 ወጪ ተደርጓል፡፡

የኢንተርኘራይዙ ገቢና ወጪ ሲመዛዘን ያልተጣራ ትርፍ ብር 338,779,775.89 ተገኝቷል፡፡

65

የኘሮጀክት ገንዘብ አጠቃቀም ሲታይ በሲሚቶ ኘሮጀክት ለልዩ ልዩ ሠ/ ማሣያዎች ማስተዋወቅያ ቢውል

የሚቻል ብር 430,874 ብር የተለቀቀ ሲሆን እስከአሁን ጥቅም ላይ የዋለ ብር 133,870 ሥራ ላይ

ውሏል፡፡ ቀሪው ገንዘብ በቀጣይ በአመት የኘሮጀክቱ ተግባራት ሥራ ላይ የሚውል ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በጀት የኢንተርኘራይዙን የአለፉት ዓመታትን ሂሳብ ለማጥራት ያልተመዘገበ ሂሳብ

ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳብን ለመለየት ጥረት በመደረግ ላይ ሲሆን የበጀት ዓመቱን ሂሳብ ግን በየቀኑ

የገንዘብ ቆጠራ፣ የሂሳብ ምዝገባ፣ ጠንካራ የውስጥ ኦዲት ክተተል እየተደረገ ጤናማ የሂሳብ አቋም

እንዲኖረው በመደረግ ላይ ነው፡፡

በዘር ሽያጭ እንቅስቃሴ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች በተመለከተ

ዩኒየኖች በዱቤ የወስዱትን ዘር በወቅቱ ገንዘቡን አለመመለስ

በቀጥታ በቆሎ ዘር በ 4 ዞን፣ ዙሪያ ወረዳና በ 139 መሠረታዊ ማህበራት ዘር በማቅረብ ለመሸጥ ጥረት

ቢደረግ ግብይት ኢንተርኘራይዝ ለከፍተኛ ወጪ መዳረግ አንዳንድ የማህበራት ቁጥር ሠራተኞች ከግል አባዥ

አ/ አደሮች መደለያ ገንዘብ እየተቀበሉ የኢንተርኘራይዙ ዘር ሽያጭ ማዳከም፤

የሸጡበትን ገንዘብ ለሰብል መግዣ መጠቀም ማቻከል የውላ ህብ/ሥራ/ ማህበር፣ የኢንተርኘራይዙን ዘር የሸጡበትን

ገንዘብ በሌላ አቅራቢ ድርጅት ባንክ ሂሳብ ማስገባት ሁ/ እጅ ሽያጭ እነሴ ወረዳ ሹም መቀመጫ፣ ሂሳቡ

ሳይስተካከል ኮሚሽን ቆርጦ ማስቀረት፣ የሸጡት ገንዘብ በወቅቱ ለኢንተርኘራይዙ አለማስገባት በበጀት ዓመቱ የታዩ

ጐላ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡

በዚሁ በጀት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጠቅላላ 58,648 ኩ/ ል ወይም ከጠቅላላው 47% ዘር

በመግዛታቸው ለኢንተርኘራይዙ ዘር ሽያጭ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

የኘሮጀክት ሥራዎች

የግንባታሥራዎች

ከደብረ ብርሃን ከተማ አቅራቢያ የዘር ማበጠሪያ ማሽን ቤት ግንባታና የማበጠሪያ ማሽን ተከላ ሥራ ጋር ተያይዞ

ከተቋራጭና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነትና ክትትል በማድረግና በየጊዜ የሚፈጠሩ ችግሮችን

በመፍታት የቤቱ ግንባታና የማበጠሪያ ማሽን ተከላው እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡ ለማበጠሪያ ጣቢያው

የሚያስፈልገውን ትራንስፎርመር በበላይ አመራሩ ጠንካራ ድጋፍ ጭምር እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ለመብራት ሀይል

ማስገቢያ የሚያስፈልግ በጀት የምስራቅ አፍሪካ ምርትና ምርታማነት ኘሮጀክት እንዲሸፍንልን ጥያቄ በማቅረብ

428,822.91 ብር አስፈቅዶ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ የመጀመሪያ ዙር የማሽን ቤቱ ርክክብም ተደርጐ

የዘር ማበጠር ሥራ ተከናውኗል፡፡ ለጣቢያው የቧንቧ ውሃ ለማስገባት የሚያስፈልገው ገንዘብ ቀደም ብሎ ለከተማው

የውሃ አገልግሎት ጽ/ ቤት ገቢ ተደርጐ ውሃ የማስገባቱ ሥራ በመገባደድ ላይ ይገኛል፡፡

66

የቻግኒ ዘር ማባዣ ጣቢያ የትራክተር መጠለያ ግንባታና የግቢ አጥር ሥራ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ክትትል ተደርጐ

ተጠይቆ የመጨረሻ ዙር ርክክብ ተፈጽሟል፡፡ በአጥር ግቢው ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ

ኘሮጀክት የጣቢያው ጽ/ ቤትና ማከማቻ መጋዘን ባለፈው ዓመት ተገንብቶ የተጠናቀቀ በመሆኑ በሶስት ቦታዎች

ተበታትኖ የቆየው የጣቢያው ንብረት በአጥሩ ግቢ ውስጥ በአንድ ቦታ እንዲሰባሰብ ተደርጎ ለጥበቃና ለንብረት

ቁጥጥር ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

በተጨማሪም በሶስቱ ነባር የዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ጣቢያዎች ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ

ችግሮችን በመፍታት ረገድ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በኮምቦልቻ ተቋርጦ የነበረው የቧንቧ ውሃ

ችግር ተፈትቷል፡፡ የእንጅባራ የዘር ማከማቻ መጋዘን ጣሪያ የማፍሰስ ችግር በተቋራጩ /በአውስኮድ/ እንዲጠገን

ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ሌሎች

ለዘላቂ ልማት ግቦች ማሣኪያ ለክልሉ ከተለቀቀው በጀት በግብርና ቢሮው በኩል ጥያቄ አቅርበን ተጠቃሚ ለመሆን

343,179,475.99 ብር የሚያወጣ ክልላዊ የዘር ላቦራቶሪና ተጨማሪ የዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ጣቢያዎች

ለማቋቋምና በነባር ጣቢያዎች የግንባታ ማስፋፊያ የኘሮጀክት ኘሮፖዛል ተዘጋጅቶ ለግብርና ቢሮ ቀርቧል፡፡ ጥያቄው

ለክልሉ ካቢኒ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሥራዎችን ለማስፈፀም የነበረው ክትትል አበረታች ሲሆን በሌላ በኩል ግን ወደ ግንባታ ከመገባቱ

በፊት በዲዛይን ላይ / በቻግኒ የትራክተር መጠለያ/ የነበሩ ክፍተቶች ለይቶ ያለማስተካከል፣ የተዘረጋው መብራት

ከመጀመሪያ ርክክብ በኃላ በክትትልና ጥበቃ ክፍተት የተከሰተ ብልሽት የጽ/ ቤቱና የመብራቱ መስመር ዝርጋታ

ተጠይቆ አለመጠናቀቁ፣ ወደ ትራክተር መጠለያው የሚደወስደው መንገድ አለመገንባት የታዩ እጥረቶችና በቀጣዩ

ዓመት መስተካከል የሚገባቸው ናቸው፡፡

የሰው ኃይል ማሟላትና የሥራ ዕድል ፈጠራ፤

ኢንተርኘራይዙ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ያለው ሰራተኛ ቋሚ ወንድ 85 ሴት 24 በድምሩ 109 ፣ ኮንትራት ሰራተኛ

ወንድ 21 ሴት 2 በድምሩ 23 ሲሆን የቋሚና ኮንትራት ሰራተኛ ድምር ወንድ 106 ፣ ሴት 26 በጠቅላላው 131 ሰራተኞች ናቸው፡፡

ከተጠቀሰው የሰራተኛ ብዛት 22 ቋሚ /15 ወንድና 7 ሴት/ እና 6 ኮንትራት / ወንድ 5 ፣ ሴት 1/ በድምሩ 28 ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ የተቀጠሩ አዲስ ሰራተኞች ናቸው፡፡ ኢንተርኘራይዙ ተጨማሪ የሰው ኃይል በማሟላትና

የነባሮችንም የመፈፀም አቅም በማሣደግ በበጀት ዓመቱ ያቀደውን ተግባር በማሣካት ረገድ በቀጥታ ተጠቃሚ

ከመሆኑም በተጨማሪ ለ 28 ዜጐች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

የሥራ ዕድል ከመፈጠር አኳያ በየጊዜው የሚመጣና የሚቀር የቀን ሰራተኛ በመኖሩ ቁጥሩን በውል ማስቀመጥ

ባይቻልም በቻግኒ ዘር ማባዣ ጣቢያ በበጀት ዓመቱ 60,375 ሰ/ ቀን በወቅታዊ የዘር ብዜት ሥራዎች ተሰማርቶ

ሰርቷል፡፡

67

የቅጥር አፈፃፀም ረገድ በአመላመልና በፈተና ሂደትና ውጤት ላይ ጥንቃቄ በማድረግና ፍትሀዊ አሰራርን በጠበቀ

መልኩ በመፈፀሙ የተሻሉ ሠራተኞች ለማግኘት መቻሉ በጥንካሬ ይወሰዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን አዲስ ሠራተኞች

ተቀጥረው ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ወደ ሥራ ማስገቢያ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑ

በሥራ አፈፃፀም ሂደት የተስተዋሉ ክፍተት ነው፡፡

ደጋፊ የስራ ሂደቶች

1. በግዥ ንብረትና አስተዳደር ዘርፍ በኩል

በግዥና ንብረት አፈፃፀም፤-

68

በበጀት አመቱ በእቅድ 2 ጊዜ የጥቅል ግዥ ለመፈፀም የታቀደ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት ለመምራት ከሁሉም የስራ ሂደቶች የግዥ ፍላጎት እንዲሰበሰብ በማድረግ ግ ዠው በመፈጸም ለተጠቃሚዎች ንብረቱ እንዲሰራጭ

ተደርጋል ፡፡

የግዥ የአፈፃፀም ሂደት ሲታይ፤-

በግልጽ ጨረታ

በበጀት በአመቱ በመደበኛ በ 15 ጊዜ ድግግሞሸ የ 820,543.68 ብር በግልጽ ጨረታ እና በተለያዩ ፕሮጀክቶች በ 10 ጊዜ ድግግሞሸ የ 2,446,040.00 ብር በግልጽ ጨረታ ግዠ ተፈጽ ýል፡፡

በውሰን ግዠ ጨረታ

በመደበኛ በጀት በ 23 ጊዜ ድግግሞሸ የ 1,833,104.00 ብር በውስን ጨረታ ግዠ ተፈጽሟል፡፡

በፕሮፎርማ ግዠጨረታ

በመደበኛ በጀት በ 88 ጊዜ ድግግሞሸ የ 1,416,301.5 ብር እና በተለያዩ ፕሮጀክቶች በ 95 ጊዜ ድግግሞሸ የ 1,921,628.38 ብር በፕሮፎርማ ጨረታ ግዠ ተፈጽሟል ፡፡

በቀጥታ ግዠ ጨረታ በመደበኛ በጀት በ 104 ጊዜ ድግግሞሸ የ 1.425.792.5 ብር ፣ በተለያዩ ፕሮጀክቶች 92 ጊዜ ድግግሞሸ

የ 64.427.99 ብር እና በእንሰሳት ኤጀንሲ በጀት በ 18 ጊዜ ድግግሞሸ የ 15,704.00 ብር በቀጥታ ግዠ ተፈጽሟል፡፡

በአጠቃላይ በተለያዩ የግዠ ዘዴዎች ግ ዠው ተፈጸመ ቢሆንም በተለይ በመደበኛ በጀት ሊፈጸም ከታቀደው አካያ

ሲታይ አፈጻጸሙ ከእቀዱ በላይ የተፈጸመ መሆኑን ያሳያል፡፡

69

በተለይ የቀጥታና የፕሮፎርማ ግዠ የድግግሞሹን ቁጥር ከፍ እንዲል ካደረገው መካከል በእቅድ ያልተያዙና ደራሽ የሆኑ የግዥ ጥያቄዎች በየጊዜው ሲቀርቡ በቢሮው ታምኖባቸው የተገዙ ቢሆንም ግዝ በእቅድ

መገዛት ስላለበት ለወደፊት በየሂደቱ ለስልጠና እና ለሌሎች የሚቀርቡ የግዥ ጥያቄዎችና እንዲገዙ በሃላፊዎች የሚመሩ ትእዛዞች ቀድሞ በእቅድ እንዲያዝ ትኩረት ቢሰጠው ፡፡

በበጀት አመቱ ብዛቱ 700,475 በሞዴል 19 ገቢ ከሆነው የተለያዩ ግብአት አላቂና ቋሚ እቃዎች ውስጥ ብዛቱ 700,186 የሆነው እቃ በወጪ ተመዝግቦ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ ቁጥራቸው ከ 100 በላይ

ለሚደርሱ ለተጠቃሚዎች በየሰማቸው ያለባቸውን ንብረት የማሳወቅ ሰራ ተከናውናል፡፡

በጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ዙሪያ፤

o የሁሉም ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የመድን ሽፋን እንዲያገኙ ተደርጓል፤

o ለአንድ መኪና አዲስ ታርጋ እንዲወጣ ተደርጓል፡

o ዓመታዊ የነዳጅ፤ የፎቶኮፒ ና የመስተንግዶ አገልግሎት በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ድርጅቶች ውል ተይዞ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጋል፤

o አጠቃላይ የግቢ ውበት ስራ እንዲሰራ ጥረት ተደርጓል፤

o ለስራ አገልግሎት በተገቢው መንገድ የተሽከርካሪ ስምሪት ብዛቱ 1,577 እንዲሰጥ ተደርጓል፤

o እስከ አመቱ መጨረሻ ብዛታቸው 72 የሚደሬሱ ተሽከርካሪዎች የሰርቪሰ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጋል፤

በፋይናንስ እንቅስቃሴ ዙሪያ ፤-

በየወሩ ወቅታዊ የሂሳብ ምዝገባ ተከናውኗል፤

እሰከ 4 ኛው ሩብ አመቱ መጨረሻ 196 ጊዜ የእለት ሳጥን ቆጠራ ተደርጎል፤

ለዋና ኦዲተር ኦዲት ዲተሮቾ ለኦዲት መረጃ በአግባቡ እነዲቀርብ ተደርጋል፤የዲት ግብረ መልሰ ወቅቱን በጠበቀ እንዲሰጥ ተደርጎል፤

ከልዩ ልዩ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የተሰበሰበ ገቢ 129,064.11 በህጋዊ የገቢ ደረሰኝ ገቢ እነዲደረግ ተደርጎል፤

ተሰብሰባል፤ ከልዮ ልዮ ገቢ የተሰበሰበ የገንዘብ መጠን በብር -----17,550.66፤

በበጀት አመቱ ብዘቱ 5,727 የሆነው የወጪ ሰነዶች ሂሳቡን በአግባቡ በመመርመር እንዲወራረዱ በማደረግ በአግባቡ ምዝገባ እንዲከናዎን ተደርጎል፤

በወቅቱ የተከሰተውን ድረቅ ለመከላከል የተመደበን በጀትና አጠቃቀም ሲታይ፤-

ተራ

ቁጥር

የበጀት ድጋፍ ያደረገው መ/ ቤት ሰም የተመደበው በጀት የተወራረደ የገንዘብ መጠን

በጀት ከወጪ ቀሪ

አፈጻጸ

ም በ%

70

1 ከፌደራል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት

ሚኒሰት/ ለዘር ገብአትና ለመሰኖ ግንባታ ግዠ/

99,775,740 84,805,095.3 14,970644.70

84.99

2 ከፌደራል እነሰሳት ሃብት ልማት

ማሰፋፊያ ሚኒሰት/ ለእንሰሳት መኖ

ግዠ/

48,000,000 25,519,945.83

22,480,054.17

53.16

3 ከክልሉ ምግብ ዋሰትና የተላከ 132,856,329 59,640,587.37

73,215,741.63

44.89

ድ/ምር 280,632,06 169,965,628.50

110,666,440.50

60.56%

ከላይ የተገለጸው አፈጻጸም ሲታይ አፈጻጸሙ ዝቅ ያለበት ምክንያት ገንዘቡ በበጀት አመቱ አጋማሸ የተላከ

ከመሆኑ በተጨማሪ ገንዘቡ የተላለፈላቸው የግብርና ሴክተሮች ፈጥኖ ሰራ ላይ በማዋል በወቅቱ ሂሳቡን በጥራት ባለማወራረዳቸው ምክንያት ሲሆን ገንዘቡ ከተላከበት ጊዜ አካያ ሲታይ አፈጻጸሙ የተሸለ ደረጃ ነው ማለት

ይቻላል..

በፋይናንሰ አሰራር ዙሪያ ከሂሳብ ሰራተኞች ጋር በጋራ በመነጋገር ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለሁሉም ፈፃሚዎች የሰራ ክፍፍል ተሰጦል፤

ሌሎች ሰልጠናዎች ላይ የውሎአበልና የማሰተባበር ሰራ እነዲከናዎን ተደርጋል፤

በአጠቃላይ የተለያዩ በዘርፉ የፋይናነሰ ደራሸ ሰራዎች ሲቀርቡ አሰፈላጊነቱ እንዲረጋገጥ በማድረግ አሰፈላጊው አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጋል፤

2. የሰው ሃይል

ምልመላና መረጣ

በበጀት አመቱ በመደበኛ 12 ሰራተኞችን ለመቅጠር በእቅድ ተይዞ 72 ተከናውኗል፤ እንደዚሁም በፕሮጀክት 20 ሰራተኞችን ለመቅጠር በእቅድ ተይዞ 72 ተከናውኗል፡፡

በበጀት አመቱ ለ 16 የቢሮ ሰራተኞች የደረጃ እድገት ለመስጠት ታቅዶ 14 ተከናውኗል፡፡

71

በበጀት አመቱ 6 ሰራተኞችን ወደ ቢሮው እና 13 ሰራተኖችን ወደ ፕሮጀክት ለማዛወር እቅድ ተይዞ 18 ወደ

ቢሮና 3 ሰራተኖች ወደ ፕሮጀክት እንዲዛወሩ ተደርጎል፡፡

ለ 18 የኮንትራት ሰራተኞች ውል ለመያዝ እቅድ ተይዞ ለ 15 ሰራተኞች ውል እንዲይዙ ተደርጎል፡፡

ለ 52 የኮንትራት ሰራተኞች ውል ለመደስ እቅድ ተይዞ ለ 30 ሰራተኞች ውል እንዲያድሱ ተደርጎል፡፡

አስራ ሰባት ሰራተኞች ተያዥ እንዲያሲዙ ለማድረግ እቅድ ተይዞ 17 ሰራተኞች ተያዥ እንዲያቀርቡ ተደርጎል፡፡

አስራ አምስት ሰራተኞች ከሙከራ ቅጥር ወደ ቋሚ ቅጥር ለመቀየር እቅድ ተይዞ 15 ሰራተኞች ወደ ቋሚ ቅጥር እንዲቀየሩ ተደርጎል፡፡

ለ 11 ሰራኞች በመደበኛና በፕሮጀክት ምደባ ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ 11 ሰራተኞች ምደባ ተሰርቷል፡፡

ጥቅማ ጥቅም እና ዲሲፒሊን በተመለከተ

ለ 150 ሰራተኞች የአመት ፍቃድ ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ 278 ሰራተኞች የአመት ፍቃድ እንዲሰጣቸው

ተደርጎል፡፡

ለ 50 ሰራተኞች በስራ ምክንያት የአመት ፍቃድ መውጣት ላልቻሉ ሰራተኞች የአመት ፍቃዳቸውን ለማዛወር እቅድ ተይዞ ለ 70 ሰራተኞች ፍቃዳቸው እንዲዞር ተደርጎል፡፡

ለ 7 ሰራተኞች የኬርየር ተጠቃሚ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ 39 ሰራተኛ ተጠቃሚ ማድረግ ተች ተችሏል፡፡

የደንብ ልብስ ተጠቃሚ ለሆኑ 113 ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት ማስረጃ ለ 80 ሰራተኞች፤ የትብብር ደብዳቤ ለ 105 ሰራተኞች እንዲሁም 32 የዋስትና ደብዳቤ

ለመስጠት በእቅድ ተይዞ ለ 70፤94፡25 በቅደም ተከተል ሰራተኞች አገልግሎት አገኝተዋል፡፡

የቢሮው ተራተኞች የጡረታ መለያ ቁጥር እንዲያገኙ ለ 10 ሰራተኞች በእቅድ ተይዞ ለ 27 ሰራተኞች እንዲያገኙ

ተገኝተዋል፡፡

ስልጠና መስጠት

የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪ እና የ 2 ኛ ዲግሪ ሰራተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ በቅደም ተከተል 20፤20 በእቅድ

የተያዘ ሲሆን 32 እና 17 ሰራተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል፡፡

3. ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዘርፍ

1.የአ.ይ. ቲ ዘርፍ

የሶፍትዌር ልማት

የቢፒአርን ስራ አውቶሜት ለማድረግ ታስቦ የሶፍትዌር ማልማት ስራው በኢንሳ በኩል ከሁለት አመት በፊት የተጠናቀቀ

ቢሆንም በሙከራ ወቅት በዳታ ላይኑ እና በዳታቤዙ ላይ በገጠመው ችግር ምክንያት እስከ ከታህሳስ ወር 2008

72

ዓ. ም ድረስ ይህ የቢ.ፒ. አር አውቶሜሽን ሳይሰራ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ ጥረት የዳታ ላይን መስመር ክልል ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ የተቀረፈ ሲሆን

አሁን ባለበት ደረጃ ይህንን ሲስተም ለመጠቀም ከሂደቱ ባለሙያ መድበን እየተከታተልን ነው ነገር ግን ዞኖች ላይ

ያለው የዳታ ላይን ችግር ግን እንደቀጠለ በመሆኑ ይህንን ሲስተም ለመጠቀም ዞን ላይ ያለውን የዳታ ላይን ችግር

ለመፍታት ጥረት ላይ እንገኛለን፡፡

የክልሉ ፖርታል ለመከታተል የድህረ ገጽ አጠቃቀምና አስተዳደር ስልጠና ለሂደቱ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናውም መሰረት ድህረ ገጹ በአሁነ ሰአት ባለሙያ ተመድቦለት በአዲስ መልክ አፕዴት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የማህበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም የሪፖርቲንግ እና ዳታቤዝ ሶፍፈት ዌየር ለማሰራት በማሰብ ሙሉ ቴክኒካል ሰነድ በሂደቱ

ተዘጋጅቶ አልቆ አሁን ከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር ወደ ቀጣይ ተግባራ በመግባትስራዉ በሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ከ FAO ጋር በመተባበር በአራት ወረዳዎች የ MIS ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘነድ የሚያስፈልገው ዲቨሎፕመንት

አልቆ ለአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠቷል፡፡ በተጨማሪም 30 የወረዳ እና ዞን የአሲቲ እና ፕላኒግ ባለሙያወች ለ 5 ተከታታይ ቀናት በባህርዳር የኒቨርሲቲ ከፕላን እና ፕሮግራም ጋር በምሆን ስልጠናዉን ሰጠናል፡፡

በቅርቡ ለሚመለከታቸው የወረዳ ባለሙያዎች ስለ አጠቃቀሙ ስልጠና ይሰጣል፡፡

ከ ATA ጋር በመተባበር የኢንፑት ትራንኪንግ ማለትም የግብአት ሥራን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ሲስተም

ዲቨሎፕ ሆኖ ያለቀ ሲሆን አሁኑ ሰአት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡

የጅኦ ዳታቤዝ ዌየብ ቤዝ ለማጠናቀር ከ ATA ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን የመጀመሪያ ድራፍትዳንግላ

ላይ በተደረገ ወርክሾፕ ይህ ጆኦ ዳታ ቤዝ ዌየብ ሳይት ተተችቶ በአሁኑ ሰአት የመጨረሻ የመስተካከያ ሥራ

በ ATA በኩል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ከ Tule International University ጋር በመተባበር ቢሮውን ጨምሮ የአራት የክልል ቢሮዎችን

የ IVR ሲስተምቴክኖሎጅ ተጠቃሙ እንዲሆኑ በማሰብ ከዩኒቨርስቲው ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን

ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ ያለውን የመረጃ ፍሰት እና አሁን ያለበትን የመረጃ እና የመሰረተ ልማት

ችግር ተጠንቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት የተደገ ሲሆን ቀጠይ መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች

ለመሰራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የመሰረተ ልማት ዝርጋታ

73

በኤጅፒ የበጀት ድጋፍየከባቢያዊ መሰረተ ልማት ዝርጋታና የብሮድ ባንድ የኢንተርኔት አገልገሎት እንዲኖራቸው

በቢሮው ውስጥ አዲስ ለተገነቡ ክፍሎች ግልጋሎቱን እንዲያገኙ በማሰብ ቴክኒካል ሰነድ አዘጋጅተን ጨርሰን በአሁኑ

ሰዓት የኔትወርክ ኢንስታሌሽኑ ተጠናቆ ሁሉም ክፍሎች ተገቢዉን አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በቢሮው የ WiFi አገልግሎት እንዲኖር የሚያስፈልገውን ቴክኒካል እስፔስፍኬሽን በማዘጋጀት ቴክኖሎጅው በተግባር

ለማዋለወ አስፈላጊውን ዝግጅት አልቆበአሁኑ ሰዓትኢንስታሌሽኑ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በቅርቡ ስራ ላይ ይውላል፡፡

ለእፅ/ዘር/ሌሎ/የግ/ግብ/ጥ/ቁ/ኳ/ ባለስልጣንየኔት ወርክ ዝርጋታ የሚያገለግሉ ዕቃዎች እስፔስፍኬሽን ማዘጋጀት እና

የቴክኒክ ድጋፍ ተደርጎ የብሮድባንድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሂደታችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልገሎት

በቢሮው ስር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 438 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ያሉ ሲሆን የእነዚህን የኤሌክትሮኒክስ ማለትም 153 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣130 ላፕቶፖች፣ 108 ፕሪንተሮች፣ 28 እስካነሮች፣ 14 ፎቶ ኮፒየሮች እንዲሁም 5 ፋክስ

ማሽኖች የዕለት ከዕለት ጤንነት የመከታተል ስራ ሰፊ ጊዜ የሚወሰድ ተግባር ነው፡፡ በዚህም መሰረትበበጀት አመቱ

ሁሉም አገልግሎት ጠያቂ ሂደቱ ባዘጋጀው ፎርም ላይ የጥገና ጥያቄውን እየሞላ በቅደም ተከተል በወቅቱ

እየተስተናገደ ይገኛል፡፡

በቢሮው ውስጥ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ያሉትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ብዛት፣ ያሉበት ክፍል እና የሚሰሩ እንዲሁም

የማይሰሩትን የመለየት ሥራ ተሰርቷል

የኔትወርክ አስተዳደርና እና ጥገና ሥራ

ይህ ስራ በየቀኑ የሚሰራ ሲሆን ከዶሜን የሚወጡ ኮምፒውተሮችን እንደገና ወደ ዶሜን የማስገባት ወደ 78 ኮምፒውተሮች ላይ የተሰራ ሲሆን 64 አዲስ ኮምፒውተሮችን ወደ ዶሜን አስገብተን የሰርቪስ ተጠቃሚ አድርገናል

በተጨማሪም 33 ነባር ኖዶችን ጥገና ያካሄድን ሲሆን 5 ኮምፒውተሮችን ሼር በማድረግ ለተጠቃሚዎች

አዘጋጅተናል፡፡

የደራ ወረዳ ኢንተርኔት ኔት ወርክ ዝርጋታን በቢሯችን ባለሙያዎች ማከናወን ተችሏል፡፡

የሲስተም ማስተዳደር ስራ

አሁን ያለው የዳታ ቤዝ ሰርቨር ከአስራአንድ አመት በፊት የተገዛ እና ወደ ኋላ የቀረ እና የተሟላ ፓወር ሴት አፕ የሌለው

በመሆኑ የዳታ ቤዝ ሰርቨር እና አብረውት ሊሟሉ የሚገቡ ቁሳቁሶች በአዲስ መልክ ቢደራጁ የተሻለ ነው፡፡ ይሁን እና

አሁን ባለን አቅም አክቲቨ ዳይሬክተሪውን በየቀኑ በመከታተል ሰርቪስ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በየቀኑ ሰርቨር ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍታትና የመፈተሽ ስራ በአማካይ በቀን ለአንድ ስዓት

ተካሂዷል፡፡

74

የስፔስፊኬሽን ማዘጋጀትና የጨረታ ዶክመንት መገምገምና ኢንሰፔክሽን ማካሄድ በቢሮው የሚገዙ የኤሌክትሮኒክስ

ዕቃዎች የጨረታ ዶክመንት የመገምገምና የኢንሰፔክሽን ስራ የሚሰራው በዚሁ ክፍል ነው፡፡ በዚህም መሰረት በበጀት

አመቱ ከ 365 በላይ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችወቅታዊና ዘመኑ የሚጠይቀውን የኤሌክትሮኒክ እቃ ስፔስፊኬሽን

ማዘጋጀትና በዚህው አግባብ ገቢ መሆናቸውን የመከታተል ስራ ተሰርቷል፡፡

ለቢሮው ሰራተኛ መሰረታዊ የኮመፒዩተር አጠቃቀምና ቀላል የኤሌከትሮኒክስ ጥገና ስልጠና ለመሰጠት የማንዋል

ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የማሰልጠኛ አዳራሽና የኮመፒዩተር ላብ ባለመሟላቱ ስልጠናውን መስጠት አልተቻለም፡፡

የቢሮው አንቲቫይረስ የተገዛበት ላይሰንስ ቀን ያለፈ በመሆኑ ግዥውን ጠይቀንና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ

ዕንዲገዛ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት 250 ኮምፒዩተሮች ላይ ለመጫን ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር

በተያያዘም የተገዛው አንቲቫይረስ የአንድ አመት ብቻ ላይሰንስ ያለው በመሆኑ የቀጣይ በጀት ዓመት የአንቲቫይረስ ግዥ

ዕቅድ አንዲያዝ ተደርጓል፡፡

2. የሶሺዮኢኮኖሚክስ ዘርፍ

በዚህ ዘርፍ የተፈቀደ የስራ መደብን ለማሟላት በተደጋጋሚ በቅጥርና በዝውውር ሟላት በተደረገው ጥረት መሰረት

በታሳቢ አንድ ሠታሰተሰቲክስ ባለሙያ የተቀጠረ በመሆኑ የግብርና መረጃዎችን ማደራጀት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

3. የጂ.አይ. ኤስ ዘርፍ

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና የመተንተን ዘዴዎች ላይ ስልጠና መስጠት በሚለው ተግባር ስር

በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከነዚህም መካክል፡

መሰረታዊ ጂ.አይ. ኤስ፤ ጂ.ፒ. ኤስ፤ ጉግል% ርዝና የሶሸ ዮ ኢኮኖሚ መረጃ ላይ የስምንት ቀን ስልጠና ለ 28 የክልል

ባለሙያዎች ( ግብርና ቢሮ (4) ፤ ደንና አካባቢጥበቃ (2) ፤ ሜትሪዎሎጂ ኤጀንሲ (2) ፤ አደጋ መከላከል (3) ፤ እንስሳት

ኤጀንሲ (2) ፤ ጎንደር ዩንቨርሲቲ (1) ፤ ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጂ (1) ፤ ከሁሉም ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ሀብት

ባለሙዎች (10) ፤ የግብርና ቢሮ አይ.ሲ. ቲ ባለሙያዎች (3) እንዲሁም ከክልሉ ለተውጣጡ 140 የወረዳ የአፈርና

ውሃጥበቃ ባለሙያዎች ስልጠናው ከተሰጠ በኋላ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተመረጡ ተፋሰሰሶች ላይ የተፋሰስ ልማት

ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ መረጃዎችን እንዲያደራጁና የተፋሰስ ልማት ዕቅድም እንዲያዘጋጁ ተደረጓል፡፡ በዚህም

መሰረት፡-

በጂ.ፒ. ኤስ የተፋሰስና ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎችንመሰባሰብና መጠቀም፤

75

የመሬት አጠቃቀምና ሽፋንን ከጉግል% ርዝበማውጣት ለተፋሰስ ልማት ዕቅድ ዝግጅት የሚሆን መረጃ ማደራጀት

ዲጂታል ኢሊቬሽን ሞዴል በመጠቀም የተፋሰሶችን ተዳፋትነትና አግሮ ኢኮሎጂ መረጃ ማዘጋጀትና መጠቀምን፤

ጉግል% ርዝን በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የተሰራበትንና ያልተሰራበትን የተፋሰስ ክፍል መለየትና

ከተለያዩ ምንጮች የሚገኙ የዝናብ፤ የአፈር፡ ድንጋያማነት፤ መረጃዎችን በመጠቀም ለሶስት ቀናት በሥልጠናዎች

አካባቢ ከሚገኙ ተፋሰሶች የአንድ ተፋሰስ የልማት ዕቅድ ማዘጋጀት ችለዋል፡፡

በሥልጠና ወቅት ላብቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ለመጡ 95 ባለሙያዎች የጂ.አይ. ኤስ፤ የጂ.ፒ. ኤስና ጉግል%ርዝ

ፕሮፌሽናል ሶፍት ዌሮችን ለመጫን ጥረት ተደርጓል፡፡

ለበስድስት ዙር ስልጠና ለወሰዱ 168 ሰልጣኞች በሙሉ የተፋሰስ ልማት ዕቅድን ለማዘጋጀት የሚያስችል

ስፓሻል መረጃዎች ተደራጅተው ተሰጥተዋል፡፡

የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ባቀረበልን ጥያቄ መሰረት ለ 25 ባለሙያዎች የአምስት ቀን የጂ.አይ.ኤስ

መሰረታዊ ሠልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከ FAO በተገኘው ብር 453 357.00 የጂ.አይ. ኤስ ለክልል፤ ለዞንና ለወረዳ ባለሙዎች ሥልጠና በመስጠት በጀቱን

በወቅቱ መጠቀምና ለሚመለከታቸው ሪፖረት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

በቢሮው የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብት ባለሙያዎችን በመረጃ አሰባበሰብ፤ ማደራጀትና መተንተን ላይ ሥልጠና መስጠት

የሚያስችል የመነሻ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለተጥሮ ሃብት ኃላፊዎች የቀረበ ቢሆንም ባለሙያዎች በተደራራቢ ስራ የተጠመዱ

በመሆኑ ስልጠናውን መስጠት አልተቻለም

በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው እገዛ፤ የድጋፍና ክትትል ስራ ማከናወን በሚለው ዕቅድ ውስጥም፡

ሥልጠና ከወሰዱ ወረዳዎች መካከል አራት ወረዳዎችን በአካል በመገኘት ድጋፍና ክትትል ተደርጓል፤ ሌሎች

ወረዳዎችን በስልክ ለመከታተልና ለመደገፍ ጥረት ተደረጓል፡፡

ለሃብሩ፤ ለቃሉና ላይ ጋይንት ወረዳ ባለሙያዎች የተፋሰስ ልየታ፡ የመሬት ሽፋንና አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች

መሰረታዊ የጂአይኤስና የጂፒኤስ አጠቃቀም ላይ ለተለያ ተግባራት ወደ ወረዳዎች በሄድኩባቸው ወቅት ዕገዛ

ተደርጓል፡፡

ለምስራቅ ጎጃም ዞን የተፈጥሮ ሃብት ባለሙያ የመሬት ተዳፋትነት መረጃ አዘጋጃጀትና ከአፈር፤ ከዝናብ መረጃና

ከሌሎች ጋር በመጠቀም እንዴት የተፋሰስ ልማት ካርታ እንደሚዘጋጅ ተከታታይነት ባለው መልኩ በስልክ ድጋፍ

ተደርጓል፡፡

76

ለአንድ የዳንግላ ወረዳ የተፈጥሮ ኃብት ባለሙያ፣ ሁለት የአባይ ተፋሰስ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባለሙያዎች

እንዲሁም አንድ የግብርና ቢሮ ባለሙያ የጂ.አይ. ኤስ ሶፍትዌር የመጫን ስራ ተሰርቷል፡፡

በዘመናዊ መልኩ የተደራጁና የተተነተኑ መረጃዎችን በመጠቀም ክልላዊ ጥናቶችን ለማድረግና ለውሳኔ ሰጪና ፖሊሲ አውጪ አካላት በተገቢው የተተነተነ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችሉ፡-

የክልሉን የዝናብ ስርጭት በዞንና በወረዳ ደረጃ የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጀቶ ለሚመለከታቸው ክፍሎች ተሰራጭቷል፡፡

የቡና፤ የተለያዩ ሰብሎችንና የእንስሳትን ፖቴንሺያል ወረዳዎች በካርታ የማዘጋጀት ስራ ተከናውኗል፡፡

ዛፍን መሰረት ያደረገ የመልክዓ ምድራዊ መልሶ ማልማት ስራ ሊከናወንባቸው የሚችሉ የክልላችን ፖቴንሺያል ቦታዎችን የመለየትና በካርታ የማዘጋጀት ስራ ተከናውኗል፡፡

የቆጋ ላይኛው ተፋሰስ ልማት ዕቅድ ሲዘጋጅ ተሳትፎ በማድረግ የመሬት ተዳፋትነት፣ የዝናብ መጠንና ስርጭት፣ የአፈር፣ የመሬት ሽፋንና አጠቃቀም፣ አግሮ ኢኮሎጂ፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የተሰራባቸውን

ቦታዎች የመለየት ስራ፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ያልተሰራባቸውን ቦታዎች እንዲሁምየተፋሰስ ዕቅድ ለመስራት የሚያስችል ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡

በክልሉ ቢራ ገብስ ለማምረት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመምረጥ በተደረገው ጥናት የዝናብ መጠን፣ ከፍታና የመሬት አጠቃቀምና ሽፋንን መሰረት በማድረግ ቦታዎችን በወረዳ ደረጃ የመለየትና ምን ያህል ሄክታር ምቹ

ቦታ እንዳለ የሚያሳይ ካርታና ተያያዥ መረጃ በማዘጋጀትና በወረዳ ደረጃ በመተንተን ለቢሮው የጥናት ቡድን በወቅቱ ማቅረብ ስራ ተከናውኗል፡፡

የመገጭ ግድብ ላይኛው ተፋሰስ ልማት ዕቅድ ሲዘጋጅ ተሳትፎ በማድረግ የመሬት ተዳፋትነት፣ የዝናብ መጠንና ስርጭት፣ የአፈር ዓይነት፣ የመሬት ሽፋንና አጠቃቀም፣ የግድቡ ሪዘርቪየር ሊያርፍ የሚችልበትን ቦታ የመለየት ስራና ስፋቱን የማወቅ፣ ከሪዘርቪየሩ በ 30 ሜትር ርቀት ያለውን ቦታ የመለየትና ስፋቱን ማወቅ

የሚያስችሉ መረጃዎች ተዘጋጅተዋል፡፡

የክልሉን የመሬት ተዳፋትነት ማወቅ የሚያስችል ካርታና ተያያዥ መረጃዎችን በዞንና በወረዳ ደረጃ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ቢሆንም በስራ መደራረብ ምክንያት ስራው አልቆ ለተጠቃሚዎች

መድረስ አልቻለም፡፡

በክልሉ በመስኖ የለማውን የእርሻ መሬት ለመለየትና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን ለማደራጀት የመነሻ ሰነድ የተዘጋጀ ቢሆንም በአሰራር ዘዴው ውጤታማነትና በሚፈጀውየሰው ኃይልና የፋይናንስ መጠን ላይ

ለመወያየትና ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር የጋራ ሃሳብ ለመያዝ ስራው በአራት ወረዳዎች ማለትም ከምስራቅ አማራ ሁለት እንዲሁም ከምዕራብ አማራ ሁለት ወረዳዎች ተመርጠው የስሚዝ ፕሮጀክት ባደረግልን የገንዘብ ድጋፍ ወደ ስራ ለመግባት በተደረሰው ስምምነት፡

የተመረጡት ወረዳዎችን በመስኖ የለማ መሬትና ተዛማጅ መረጃዎችን ለማሰባሰብ፤ ለመተንተን የሚያስችል የመነሻ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

ከሚመከለታቸው የወረዳ፣ የዞን፣ የክልል ባለሙያዎች ጋር እንዲሁም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ የግብርና ምርምር አባላትና ከስሚዝ ፕሮጀክት ባለመያችና አማራሮች ጋር የግማሽ ቀን ምክክር

77

በጃቢጠህና ወረዳ የመስኖ መረጃ ጥናት ውጤት፣ አጠቃላይ የመስኖ መረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችና በጥናቱ የተተገበሩ ዘዴዎችን በማቅረብ ምክክር ተደርጓል፡፡

በቃሉና በሃብሩ ወረዳዎች ስር ለሚገኙ 64 የቀበሌ የመስኖ ባለሙያዎች በጂ.ፒ. ኤስ አጠቃቀም ላይ የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በቃሉና በሃብሩ ወረዳዎች ከሚገኙ 64 ቀበሌዎች መካከል የ 62 ቀበሌዎች መረጃ በጂፒኤስ የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፡፡ ከቃሉና ከሀብሩ ወረዳ ቀበሌዎች መካከል ከፍተኛ

የመስኖ አውታር ያላቸወ 2 ቱ ቀበሌዎች ተመርጠው የመስኖ አውታር መረጃ የማጥራት ስራ

ተሰርቷል፡፡

በ 2006 ዓ. ም የተሰጠውን የጃቢጠህናን ወረዳ መረጃ ለማጥራት በተደረገው ጥረት

መሰረትም ፡- ለ 13 ቀበሌ ባለሙያዎች የአንድ ቀን የጂፒኤስ ስልጠና ተሰጥቷል

በጃቢጠህናን ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች መካከል ከፍተኛ የመስኖ አውታር ያላቸው አስራ ሦስት

ቀበሌዎች የመስኖ መረጃ የማሰባሰብና የማደራጀት ስራዎች ተከናውኗል፡፡

ለመረጃ ፈላጊዎች ካርታዎች ተዘጋጂተው ተሰጥተዋል:: በክልላችን የሚገኙ የመንግስት ጥብቅ ደኖችን ሰፓሻል መረጃ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፡፡

4. ሌሎች ስራዎች

ክልሉ ባቋቋመው የጥሪ ማዕከል አንድ ባለሙያ መድበን አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

በምስራቅ አማራ እና በምእራብ አማራ ላይ በአትክልት እና ፍራፍሬ ዙሪያ በተሰጠዉ ስልጠና ላይ በመገኘት

የሙያ ድጋፍ አድርገናል፡፡

ቢሮዉ ከተለያዩ 15 መስሪያ ቤቶች የሙያ ትብብር ተጠይቆ አስፈላጊውን የሙያ ትብብር ለጠያቂ መስሪያ

ቤቶች ማለትም በባለሙያ ቅጥር፣ በኤሌክትሮኒክስ ቴክኒካል ስፔክ ዝግጅት የመሳሰሉትን ሂደታችን ድጋፍ

አድርጓል፡፡

ለ 9 ዞኖች፣ ለ 15 ወረዳዎች እና ለ 1 ማዕከል ሙያዊ ድጋፍ አድርገናል፡፡

4. የሕዝብ ግንኙነት

የህዝብ ንቅናቄ የተፈጠረባቸው ሁነቶች፡-

የ2007 ዓ. ም የአረንጓዴ ዋንጫ በዓልማክበር

ጥቅምት 05/2008 ዓ. ም የተከበረ ሲሆን ዓላማውም በ 2007 ዓ. ም ለተሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ስራዎች

ይሁንታን ለመስጠት እና ለ 2008 ዓ. ም እቅድ ትግበራ በፈጻሚዎቸ መካከል መልካም የሆነ ውድድርን

78

ለመፍጠር ታስቦ የተሰራ ነው፡፡

ከእርሻና ተ/ ሀብት ሚ/ ር ፤ከክልል ተጠሪ መስሪያ ቤቶች፤ሁሉም በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች እና አደረጃጀቶች

የተሳተፉበት ነበር፡፡

በ 2008 ዓ. ም የአረንጓዴ ዋንጫ በዓል ፕሮግራም ላይ ለተለያዩ ተቋ ማት የክልሉ ግብርና ቢሮ ውጤታማ

ዞኖች፤ወረዳዎች እና አደረጃጀቶች የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የግብርና ቢሮ ኃላፊ፣ም/ ቢሮ ኃላፊዎች፤የተፈጥሮ ሀብት የስራ ሂደት፤አጋር

ዩኒቨርስቲዎችንና የምርምር ተቋ ማትን መስከረም ወር ላይ 2008 ዓ. ም ስለ ተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ

ስራ አፈጻጸምና ስለ አረንጓዴ ዋንጫ በአል አስመልክቶ ቃለ- መጠይቅ በማድረግ የሰጡንን አስተያየት እና

ምልከታዎችንመረጃ በመያዝ ለዶክመንተሪ ፊልምና ለመፅሔት ግብዓት እንዲሆን ተደርጓ ል፡፡

የአማራ ክልል የአርሶ አደሮች ፌስቲቫልና የግብርና ኤግዚቢሽንና ባዛር ተካሒዷል

የክልሉ ግብርና ቢሮ በክልል ደረጃ ያካሄደው የአማራ ክልል የአርሶ አደር ፌስቲቫልና የግብርና ኤግዚቢሽንና

ባዛር የተካሄደው ከ 35 ኛው የብአዴን ምስረታ በአል ተከትሎ ከህዳር 12 እስከ 16/2008 ዓ. ም ነበር፡፡

በፕሮግራሙም ከ 110 በላይ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች፤ሚኒስትሮች፤ተጠሪ መ/ቤቶች፤

ወጣቶች ፤ሴቶች፤ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች፤ በከተማው ውስጥ የሚገኙ የግልና የመንግስት መ/ቤቶች

የታደሙበት የግብርና ኤግዚቪሽንና ባዛር ተካሂዷል፡፡አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጅዎች፤ምርት እና አገልግሎት

የተዋወቀበትና የተሻሻጡበት ፕሮግራም ነበር፡፡ይህም ለአርሶ አደሮችና በግብርና የተሰማሩ ባለሃብቶች

እንዲሁም ለሸማቾችመነቃቃትን የፈጠረ ትእይንት ነበር ብሎመውሰድ ይቻላል፡፡

በፕሮግራሙመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር የፓናል ውይይት ተደርጎ በበአሉ በነበሩ ጥንካሬና ድክመቶች ላይ

ውይይት ከተካሄደ በኋላ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት በመስጠት የበአሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡በፌስቲቫሉም

ውጤታማ ለሆኑና ሀብት ላፈሩ አርሶ አደሮች የተለያየ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ፕሮግራሙም የቀጥታሚዲያ ስርጭት እንዲያገኝም ተደርጓል፡፡

በተካሄደው የአርሶ አደሮች ፌስቲቫል

37 አዲስ ተሸላሚ አርሶ አደሮች

28 አዲስ ተሸላሚ ወጣቶች

37 አዲስ ተሸላሚ ሴቶች

42 ወደ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮች

11 የቀበሌ ጽ/ ቤት ሃላፊዎች

11 የቀበሌ ባለሙያዎች

10 ወረዳዎችና 10 ዞኖች ተሸላሚ ሆነዋል

የ2008 ዓ. ም የግብርና ልማት የእቅድ ትውውቅ በባህርዳር ከተማ ላይ ተካሂዷል፡፡

79

ለሁሉም የዞን አስተዳዳሪዎችና የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፤የወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ኃላፊዎች እና የተለያዩ

ባለድርሻ አካለት የ 2008 ዓ. ምእቅድ ትውውቅ በየደረጃው አስከ ቀበሌ ድረስ የተሠተጠ ሲሆን ሰፊ የሚዲያ

ሽፋን እንዲያገኝም ሆኗ ል፡፡

የእቅድ ኦሬቴሽኑ ሲሰጥ በምስልና በድምጽ እንዲሁም በቃለ- ጉባዔ እንዲያዝ ተደርጓል፡፡

ዋና ዋና የሚባሉ እና አንኳር ጥያቄዎች በተለያዩ ሃላፊዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አሰተያየቶችና ጥያቄዎች

ተለይተውና ተደራጅተው ለሚመለከታቸው አካላትና ለስራ ሂደቶች ተሰጥቷል፡፡

1. የመስኖ ማስጀመር በዓል በማካሄድ ለመስኖ ስራ የተሻለ መነሳሳት እንዲፈጥር

አስችሏል፡፡

በክልለ ደረጃ የመስኖ ማስጀመር የንቅናቄ መድረክ በመፍጠር በመስኖ የስራ ዘርፍ የተሻለ ስራ እንዲሰራ

ለማድረግ የዘንድሮ የመስኖ ማሰጀመር ፕሮግራም በሰ/ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ላይ

ተካሂዷል፤ በቂ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

2. ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሰብሉን እንዳይጎዳው ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመታገዝ የመኽ ር ሰብል

የመሰብሰብ ስራ ተሰርቷ ል፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብሉ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ 30 ኮንባይን ሀርቨስተር ከተለያዩ የግልና

የመንግስት ድርጅቶች በማስመጣት በምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ወንበርማ እና ደብረ ኢሊያስ

ወረዳዎች የ 10 643 አርሶ አደሮች 6918 ሄ/ ር ማሳ በመውቃት 295 955 ኩንታል የስንዴ ሰብል

በኮንባይን ሀርቨስተር ተሰብስቧ ል፡፡አርሶ አደሮችም ጊዚያቸውና ጉልበታቸው እንደተቆጠበላቸው አስተያየት

ሰጥተዋል፡፡ሥራውም ለቀጣይ አመት የተሸለመነሳሳት እንዲፈጥር ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶታ፡፡

3. የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ አጀማመር በክልል ደረጃ በደቡብ ወሎ መቅደላ

ወረዳ ላይ በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ የማስጀመር ስራ በክልል ደረጃ በደቡብ ወሎ መቅደላ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙም ከፌደራል፤የክልል ፤የአጎራበች ዞኖች እና የመቅዳላ ወረዳ አርሶ አደሮች ዕንደ ቀፎ ንብ

በመትመም ስራውን በይፋ ጀምረውታል ፡፡በአብዛኛው የክልሉ የተለያዩ ቦታዎችም በተመሳሳይ ቀን የተፈጥሮ

ሀብት ልማት ስራው ተጀምፘ ል፡፡ ስራው ሲጀመር ከ 5000 ህዝብ በላይ የተገኘበት ሲሆን ሌሎች

አካባቢዎችም ተሞክሮውን እንዲወስዱ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኘ ተደርጓል፡፡

4. የቢራ ገብስ ልማት የንቅናቄ መድረክ በሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ላይ ተካሂዷል፡፡

የቢራ ገብስ ልማት ማልማት የሚችሉ ደጋማ ለሆኑ 32 ወረዳዎች ለሚኖሩ አርሶ አሮች ሙያዊ ስልጠና

የተሰጠ ሲሆን የሚያመርቱትን የቢራ ገብስም በተሻለ ዋጋ ውል አስቀድሞ በመያዝ ለዳሸን ቢራ ፋብሪካ

በማቅረብ አርሶ አደሮቹ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ተመቻ ቷ ል፡፡በመሆኑም ጎንደር ከተማ ላይ

80

የሚመለከታቸው የግብርና አመራሮች፤ ባለሙያዎ ችና አርሶ አደሮች በተገኙበት የእቅድ ትውውቅ መድረክ

ተካሂዷል፡፡ መድረኩም ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ በማድረግ ወደስራው ያልገቡ ወረዳዎችን ለማነሳሳት

ጥረት ተደርጓል፤መረጃውም ተቀርጾ በመረጃ ክምችት ክፍላችን እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

5. ኢሊኖ ባስከተለው ድርቅ ምክኒያት ሊደርስ የሚችለውን የድርቅ ችግር ለመቋቋ ም የቀውስ ጊዜ እቅድ (Crisis's Communication Plan) ታቅዷ ል፡፡

በኢሊኖ ምክኒያት በክልላችን 8 ዞኖች፤83 ወረዳዎች እና በ 802 ቀበሌዎች ድርቅ የተከሰተውን ድርቅ

ለመቋቋ ም ሰፊ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራ ተሰርቷ ል፡፡ስለሆነም የእንሰሳት መኖ ድርቁ ካልተከሰተበት

አካባቢ ህ/ ሰቡ በድርቁ ለተጎዱት እገዛ እንዲያደርግ በማድረግ፤በፍጥነት ሊደርሱ የሚችሉና ድርቅን

ሊቋቋ ሙ የሚችሉ ጓ ሮ አትክልት ዘሮችን፤የስኴ ር ድንች ቁርጥራጮችን ወ.ዘ. ተ በማድረስ የተለያዩ ስራዎች

ተከናውነዋል፡፡

የድርቁን ችግር ሁሉም የግብርናው ሴክተር ባለሙያና የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲረዳውና ባለቤት

አደርጎ ለመፍትሄውም ጭምር እንዲሳተፉ ለማድረግ የፓናል ውይይት አካሂደናል፡፡ከክልሉ መንግስት

አቅጣጫ ተሰጥቶ መንግስታዊ ከሆኑ ድርጅቶች ታላላቅ ማሽነሪዎች ድርቁ በተከሰተባቸው ቦታዎች

በመንቀሳቀስ እየሰሩ ያለውን ስራ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

6. በበጀ ት አመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና የሂደቱ ስራዎች

የአሌክትሮኒክስ ሚደያን በመጠቀም የተከናወኑ ስራዎች

o በዓመቱ 52 የቲሌቪዥን እና የራዲዮ ዜናዎች ለማሰራጨት ታቅዶ አስካሁን 47 ዜናዎች

ተዘጋጅተው በተለያ መንገድ ተሰጭተዋል፡፡

o በዓመቱ 12 ፕሮግራሞች ለማዘጋጀት ታቅዶ በመስኖ፤በሰብል ስብሰባ፤በተፈጥሮ ሃብት ልማት

ንቅናቄና በምርጥ አርሶ አደር ተሞክሮ ላይ 4 ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው ተሰራጭተዋል፡፡

o በአመቱ በተለያዩ ጉዳዮች ማለትም በመስኖ ልማት አጀማመር፤በመኸር ሰብል ልማት

አጀማመር፤በተ/ል/ ስራ አጀማመር፤በተለያዩ ሁነቶች መካሄድና በመሳሰሉት ላይ 6 ጋዜጣዊ

መግለጫዎች ለመስጠት ታቅዶ ባጠቃላይ 9 ጋዜጣዊመግለጫዎች ተሰጥተዋል፡፡

o በአመቱ 3 ዶክመንተሪ ፊልሞች ለማዘጋጀት ታቅዶ በተ/ሃ/ል/ ጥ፤በሰብል ልማትና በመስኖ

ልማት ላይ 3 ተዘጋጅተው ለሚመለከተው ሁሉ ተሰራጭተዋል፡፡

በዊብ ሳይት እና ሶሻልሚዲያ የተሰሩ ስራዎች፡- በአመቱ 52 መረጃዎች በዌብ ሳይት ለመልቀቅ ታቅዶ አስካሁን 3 ጊዜ የቢሮውን መሰረታዊ እና

ወቅታዊመረጃዎች ለተጠቃሚው ተለቀዋል፡፡

በአመቱ 252 የሚዲያ ሞኒቶሪንግ ስራ ለመሰራት ታቅዶ እስካሁን 198 ጊዜ የሚዲያ ሞኒቶሪግ

ስራ ተሰርቷል፡፡

81

52 ዜናዎች አጫጭር የጽሁፍመረጃዎች ሶሻልሚዲያ ላይ ተለቀዋል፡፡

54 ወቅታዊነት ያላቸው የግብርና ስራ ዜናዎች በሶሻልሚዲያ ላይ ተለቀዋል፡፡

25 አስተሳሰብን ሊቀይሩ የሚችሉ ጽሁፎች ወይም አርቲክልስ /Articles/ ሶሻል ሚዲያ ላይ

ተለቀዋል፡፡

ከ 470 በላይ በየስራ ዘርፉ የተመረጡወቅታዊ ፎቶግራፎች ሶሻልሚዲያ ላይ ተለቀዋል፡፡

የህትመት ሚዲያዎችን በመጠቀም በኩል የጠሰሩ ስራዎች

o በአመቱ ሁለት ጊዜ መጽሄት ለማሳተም ታቅዶ በእቅዳችን መሰረት በሰብል ልማትና በተ/ሀ/ልማት

አፈጻጸሞች ላይ 2 ጊዜ መጽሄቶች እያንዳዳቸው 1500 እና 1200 እትሞች ታትመው

ተሰራጭተዋል

o በእቅዳችን መሰረት 2 ጊዜ ብሮሸሮች እያንዳዳቸው 1000 እትሞች በድምሩ 2000 ታትመው

ተሰራጭተዋል

o ምንም እንኳ በእቅድ ባይያዝም በተፈጠረው አጋጣሚ በተገኘ ገንዘብ ድጋፍ ስለኢፋስ መስኖ ልማት

አፈጻጸም የሚዘግብ እያንዳንዳቸው ከ 32 እስከ 72 ገጽያላቸው 3 ቡክሌቶች ታትመው

ተሰራጭተዋል

o በአመቱ 100 መልእክቶችን የያዙ ባነሮች ለማሳተም ታቅዶ እስካሁን 62 ባነሮች ታትመው ጥቅም

ላይውለዋል፡፡

o የተለያዩ መልእክቶችን የያዙ 4200 በራሪ ወረቀቶችን ለማሳተም ታቅዶ በአመቱ 500 በራሪ

ወረቀቶችንማሳተምና ማሰራጨት ተችሏል፡፡

የአረንጓዴ ዋንጫና የአርሶ አደር ፌስቲቫልን የሚያንጸባርቁ 2 ቢል ቦርዶችን ለማሳተም ታቅዶ 2 ታትመው ስራ

ላይውለዋል፡፡

ለሁለቱም ሁነቶች የሚሆኑ 400 ስቲከሮችን ለማሳተም ታቅዶ በእቅዳችን መሰረት 400 አስቲከር ታትመው

ተሰራጭተዋል

7. የፓናል ውይይት

በተለያዩ ጉዳዮች ማለትም በተከሰተው ድረቅ ላይ፤በህዳር 11 የብአዴን ምስረታ 35 ኛ በአል ላይ በብሄር

ብሄረሰቦች ቀን ላይና በግንቦት 20 25 ኛ አመት በአል ላይ በአመቱ 4 የፓናል ውይይት ለማካሄድ ታቅዶ 4 ጊዜ የፓናል ውይይቶች ተካሂዷል

8. ልምድ ልውውጥ

ለመ/ ቤቱ ሰራተኞች 4 ጊዜ የልምድ ልውውጥና የመስክ ጉብኝት ለማካሄድ ታቅዶ 2 ጊዜ ተካሂዷል፡፡

82

9. ከመረጃ ዴስክ የስራ እንቅስቃሴዎች አኳያ፤

ቢሮው በያዘው ውል መሰረት ከሀምሌ ወር ጀምሮ በየጊዜው የሚመጡ የህትመት ውጤቶችን /ጋዜጣና

መፅሄቶችን/ ለሚመለከተው የስራ ሂደት እንዲሰራጩ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት

አ. ዘመን አማርኛ ----------------2564 ኢ.ት. ህራልድ እንግሊዝኛ------ 1504 ሪፖርተር አማርኛ-----------------400 ሪፖርተር እንግሊዝኛ---------------32

በኩር--------------------------------564 ሜዲካልመጽሄት-------------------32 ዘመንመጽሄት----------------------40 አደዲስ አድማስ ጋዜጣ----------32

በመረከብ በወቅቱ ለተገልጋዮች እንዲደርስ ሆኗል፡፡

ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚመጡ የህትመት ውጤቶች ለእየስራ ሂደቱ በወቅቱ

ተሰራጭቷል፡፡

ከክልሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር በመቀናጄት በቢሮው ውስጥ የተለያዩ መረጃዎችን ለሚፈልጉ

ደንበኞች አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል

የተለያዩ አዋጅ፤መመሪያዎችና ደንቦች በሚመጡበት ጊዜ ለተጠቃሚ ተደራሽ በሚሆን መልኩ ተደራጅተዋል፡፡

9.1 ከቤተ መጽሃፍት አገልግሎት አሰጣጥ አኳያ

በቢሮው የቤተመፅሐፍት አገልግሎት ከሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የእንተርኔት አገልግሎ ት፣የንባብ አገልገሎት እና የመፅሐፍት ትውስት አገልግሎት ሲሆኑ ለ 950

የውስጥና ለ 1220 የውጭ ደንበኞች የጋዜጣ ንባብ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

1150 ደንበኞች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል

9.2 ከኦዲዮ ቪ¡ ዋል ስራዎቻችን አኳያ የተሰሩ ተግባራት

o 60 መረጃዎችን ለመረጽ ታቅዶ 42 መረጃዎች ተሰባስበው 8 ቱ አየር ላይ ውለዋል ከፊሎቹ

ደግሞ ለቀጣይ ስራችን ይሆኑ ዘንድ ተደራጅተው ተቀምጠዋል፡፡

o 10 የፎቶ ሙቪ ለማቀናበር ታቅዶ 7 የተለያዩ ፎቶ ሙቪዎች ተዘጋጅተዋል፡፡

5. የለዉጥ ትግበራ የስራ ሂደት

በየደረጃው ያለው አመራርና ፈጻሚ የተጠናከረ ቁመና ይዞ ተልኮውን እንዲወጣ ማድረግ፣

የ 2008 ዓ.ም ዕቅድ ማዘጋጀት

የ 2007 ዓ.ም የቢሮውን እቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ ተገምግሞ የተፈጸሙ እና ያልተፈጸሙ ተግባሮች፣ ጥሩ አፈጻጸሞች ተለይተው ከፈጻሚው ጋር በመግባባት ለ 2008 ዕቅድ ግብአት እንዲሆኑ በ ማድረግ ታቅዷል።

የ 2008 ዓ.ም እቅድ ተዘጋጅቶ ከፈጻሚው ጋር የተሟላ ግልጽነት ተፈጥሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ተደርጓል።

የእቅዶችን አፈጻጸም እየገመገሙ ክለሳ ማድረግ እና እቅዱን ተፈጻሚ ሊያደርጉ የሚያስችሉ ስልቶችን ተለይተዉ

ተግባራዊ ተደርገዋል፤

83

በየደረጃው ያለውን አመራር የግንባር ቀደም መሪነት ቁመና እንደይዙ ማድረግ

የአመለካከት እና የክህሎት ችግሮችን በመለየት ለዉጡን በእምነትና በባለቤትነት አንዲይዙ የሚያስችል የአቅም

ገንባታ ስራዎች በተከታታይ ለአመራሩና ለፈፃሚዎች ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጋል።

የአቅም ክፍተትን በመለየት የተሰራ የአቅም ግንባታ ስራን በተመለከተ ፤

በድጋፍና ክትትል ወቅት የተለዮ ክፍተቶችን በእቅዱ መሰረት በሁለተኛዉ እና በአራተኛዉ እሩብ አመት ከዚህ በታች

በተዘረዘሩት የለዉጥ መሳሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፤

የስልጠናዉ መነሻ ሁኔታ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ የስራ ሂደት መሪዎች የሪፎርም ተግበራት በተሟላ ሁኔታ

ተረድቶ ሚናን መወጣት ላይ እጥረቶች በመታየታቸዉ ቢሮዉ ይሄን ችግር ግምት ዉስጥ በማሰገባት ስልጠናዉ

እንዲሰጥ ተደርጓል ፤

የስልጠናዉ አይነትየሰልጣኝ

ብዛትየስልጠና

ቀናት የ ልማት ሰራዊት ግንባታ ሂደት በተመለከተ፤ የዉጤት ተኮር ዕቅድ(BSC) በተመለከተ፤ የስራ አፈፃፀም መመሪያ የመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብን በተመለከተ፤የስራ አፈፃፀም

መመሪያን በተመለከተ፤ድምር 106 6

በ አገልግሎት አሰጣጥ /Custemr service/በተመለከተ 118 4 ጠቅላላ ድምር 224 10

ስልጠና የተሰጠዉ፤

የተሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና የወሰዱ በቢሮ ያሉ የስራሂደት መሪዎች እና የስራ ሂደት ተተኪዎች፤ ኬዝ ቲም

አስ ባባሪዎች ፤ በ 10 ዞን ግብርና የሚገኙ የስራ ሂደት መሪዎች፤ ለ 3 የግብርና ኮሌጅ ለከፍተኛ ኃላፊዎች እና የስራ

ሂደት መሪዎች፤ ለ 6 የማዕከላት ሃላፊዎች፤ በዞኖች እና በኮሌጆች ላሉ የለዉጥ አስተግባሪ ቡድኖች፤ በክልል ደረጃ

የተዘጋጀዉን ማንዋል መሰረት ተድርጎ ስልጠናዉ በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት በአማራ ስራ አመራር አሰልጣኞች

እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ /custemr servic/ ስልጠናዉ የተሰጠዉ በቢሮ ለሚገኙ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ፤

ለኬዝ ቲም አስተባባሪዎች፤ ለአንድ ሂደትመሪ ሲሆን ስልጠናዉን በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት በአማራ ስራ አመራር

84

አሰልጣኞች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

በየዞኑ ላሉ የለዉጥ አስተግባሪዎች ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል

በ 10 ሩ ዞን ላሉ የለዉጥ አስተግባሪ ቡድኖች ለሁለት ቀን በተሻሻለዉ የልማት ሰራዊት ግንባታማልዋል ላይ

ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡

ሌላዉ በዞኖች አሁን እየተሰራ ባለዉ ስራ እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዩች ላይ ሰፌዉይይት ተደርጓል፤

የቋሪት ተሞክሮም ቀርቧል፤

በየደረጃው ያለውን አመራር አፈጻጸም መገምገም፣ ግምገማዊ ሥልጠና መስጠት፣ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ ማሰማራት በሚል ታቅዶ

አደረጃጀቶችን መሰረት አድርጎ በሚደረገው ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሰራተኞችን መለየት ተችሏል፣

አመራሩም የስቪል ሰርቪስ የልማት ሰራዊት ግንባታን በአግባቡ (በባለቤትነት) መምራት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፣

መንግስታዊ አደረጃጀቶችን በመደገፍ እና የለውጥ መሳሪያወችን በአግባቡ በመተግበር ተቋማዊ ለውጡን ማረጋገጥ በሚል ታቅዶ አፈፃፀሙ እንደሚከተለዉ ቀርቧል፤

በመንግስት አደረጃጀት ስር ያሉትን የልማት ቡድን እና የ 1 ለ 5 አደረጃጀት በአግባቡ ተደራጅተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፣

የግብርና ልማት ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ላይ ለፈፃሚዎች ግንዛቤ ተፈጥሯል፤

አደረጃጀቶችን መሰረት ያደረገ ተከታታይነት ያለው መማማር እና ችግር ፈች ውይይት ማድረግ፣

የአመለካከት፣ የክህሎት፣ እና የስነምግባር ክፍተቶችን እየለዩ መሙላት ተችሏል፣

የለውጥ መሳሪዎችን በአግባቡ በመተግበር ተቋማዊ ለውጡን ማረጋገጥ ላይ መሻሻሎች ታይተዋል፣

በቢሮው ያሉት ዋና እና ደጋፊ የስራ ሂደቶች እቅዳቸውን በ BSC እንዲያከናውኑ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግን በተመለከተ፤

ከተቋሙ ስትራቴጅክ እቅድ የተቀዳ በጥረት ሊደረስበት የሚችል የ 2008 ዓ.ም የመ/ቤቱና የስራ ሂደቶችን ዕቅድ በወቅቱና በአግባቡ በ BSC መሰረት እንዲታቀድ ድጋፍ ተደርጓል፤

ከሂደቱ እቅድ የተቀዳ በጥረት ሊደረስበት የሚችል የፈጻሚወችና የስራ ሂደት መሪወች የ 6 ወር ውልና ውጤት በወቅቱ ማጠናቀቅ ተችሏል፣

የመ/ቤቱን የእቅድ አፈጻጸም ከሰራተኞች ከተገልጋዮችና አጋር አካላት ጋር በየሩብ ዓመቱ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል፣

ከእቅድ ዝግጅት እስከ ውጤት አሞላል ድረስ ያለውን አፈጻጸም አግባብነት አመራሩ እየገመገመ እንዲመራ

ተደርጓል፤

85

ግንባር ቀደሞችን በመደገፍ ተቋማዊ ለውጡን ማረጋገጥን በተመለከተ፤

በቢሮ ደረጃ ያለው ግንባር ቀደም ሃይል የግብርና ስራዉን እንዲደግፍ እና እንዲያጠናክር ምቹ ሁኔታወችን በመፍጠር ተቋማዊ ለውጡን ለ ማረጋገጥ ጥርት ተደርጓል፣

የመልካም አስተዳደር እና የልማት አቅሞችን የሚያደናቅፉ የኪራይ ሰብሣቢነት አመለካከትንና ድርጊትን ማዳከምን በተመለከተ፣

እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ዕቅድ ማቀድ እና መተግበር አበረታች

ሁኔታዎች ታይተዋል፤

በመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፤

የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጮችን በመለየትና የማድረቂያ ስልቶችን በመንደፍ ወደ ተግባር መግባትና ውጤት ማምጣት

የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በተመለከተ በድጋፍ ወቅት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነዉ፣

የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን ለማዳከም የሚያስችሉ ስልቶችን በሂደት ደረጃ እንዲለዩ የተደረገበት ሁኔታ አለ ፣

የተመዘገበ ዉጤት

ለ 2 ዐዐ 8 ዓ. ም ሊያሰራ የሚችል የአመት፤ የ 6 ወርና የወር ዕቅድ በየሂደቱ እንዲታቀድ መደረጉ፣

የልማት ሰራዊት ሊመራ የሚችል አመራር እና ፈጻሚ እየተፈጠረ መሆኑ(በአመለካከቱ እና በክህሎቱ ወደ ተቀራራቢ ደረጃ እየደረሰ ያለ መሆኑ)፣

በቢሮው የግንባር ቀደሞች ሚና እየሰፋ መምጣቱ፣

የህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሰ አመራር እና ፈጻሚ የተፈጠረ መሆኑ፣

ተቋማዊ ለውጡን በአግባቡ የሚተገብር የግብርና ልማት ሰራዊት እየተገነባ መሆኑ፣

በቢሮ ደረጃ እየሰፋ የመጣ/የተለወጠ ተቋማዊ አሰራር እያደገ መምጣቱ፣

በውጤታማነት የተተገበረ የለውጥ ኘሮግራም እንዲኖር መደረጉ፣

ልማታዊ አስተሳሰብ እያደገ መምጣቱ ፣

ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ሥርአት እየመጣ መሆኑ፣

ስራዎችን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል ልምዱ እየዳበረ መምጣቱ፤

በስራ ሂደቶች መካከል ቅንጅታዊ አሰራር ከጊዜ ወደጊዜ እየዳበረ መምጣቱ፣

ለተደረገዉ ድጋፍና ክትትል፤ ግብረመልስ መሰጠቱ፤

በክልል ደረጃ ግንዛቤ በተያዘበት አግባብ በዞኑ ያሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን በመለየት ግንዛቤ እንዲፈጠር መደረጉ#

ባጠቃላይ የለዉጥ ስራዉን የስራ መሳሪያ አድርጎ በመያዝ በኩል አበረታች ሁኔታዎች ታይተዋል፤

86

ወቅታዊ ሪፖርቶች፤

የሂደቱ አመታዊ እቅድ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ እንዲደርስ ተደርጓል፤

በማስጀመሪያ ምዕራፍ፤ በትግበራ ምዕራፍ፤በማጠቃለያ ምዕራፍ በሪፎርም አፈፃፀም ቢሮዉ ያለበትን ሁኔታ

የሚገልጹ ሪፖርቶች ለሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ኃብት ልማት ቢሮ ሪፖርት ቀርቧል።

በዝግጅትና በትግበራ ምዕራፍ በሪፎርም አተገባበር ዙሪያ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ለመደገፍ ቼክ ሊስት

ተዘጋጅቶ በቢሮዉ ለሚገኙ 11 የስራ ሂደቶች፤ ለ 10 ዞን ግብርና መምሪያዎች፤ ለ 3 ቱ ኮሌጆች እና ለ 6 ማእከላት እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል፤ በዚህም መሰረት ድጋፍና ክትትል ተደርጎ በጥንካሬና በእጥረት የታዩትን

በግብረመልስ እንዲደርስ ተደርጓል።

በቢሮዉ ለተመረጡ ግንባር ቀደሞች ተግባርና ኃላፊነታቸዉን እንዲያዉቁ ተደርጓል፤

በየሳምንቱ የተሰሩ ስራዎችን የሚገልጽ ሪፖርት ለፕላንና ፕሮግራም እንዲደርስ ይደረጋል፤

በቢሮ ለሚገኙ የሂደት ፀሃፊወች በመረጃ አያያዝ ዙሪያ በድጋፍና ክትትል ወቅት በታዩ ክፍተቶች ላይ በመመስረት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፤

በስራ ሂደቶች የመልካም አስተዳደር እቅድ እንዲታቀድ ተደርጓል፤

የዜጐች ቻርተር ሰነድ ለሁሉም ሂደቶች ካሁን በፊት የተዘጋጀዉን ክለሣ እንዲደረጉ ተደርጎ፤

በሁሉም ዞን እና ኮሌጆች የለዉጥ አስተግባሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎል ለአስተግባሪ ቡድኑም ስልጠና

ተሰጥቶ ወደስራ እንዲገቡ ተደርጓል፤

6. አገልግሎት አሰጣጥና በቅሬታ ማስተናገጃ

የአገልግሎት አሰጣጥ ስልት ለመቀየስ የአስተያየት መስጫ ጽሑፎችን በማዘጋጀት የተገኘውን ገንቢ

አስተያየት በመቀመርና ሥራ ላይ በማዋል ቅሬታዎችን ተቀብሎ ፍትሃዊ ውሣኔ ለመስጠት

የጉዳዮችን ጭብጥ በመመርመር በቅድሚያ በስምምነት መጨረት ይህ ካልሆነ ጉዳዩን አጣርቶ

የውሣኔ ሃሣብ ለኃላፊ በማቅረብ ተፈጻሚቱን ክትትል በማድረግ ለደንበኞች ርካታ ማስገኘት

አስፈላጊ ነው። በዚህም በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ቅሬታን ተቀብሎ ፍትሃዊ ውሣኔ መስጠትን በሚመለከት፤

የቀረበ ቅሬታ ብዛት 20 በስምምነት የተፈታ 14 ቢሮ ኃላፊው ውሣኔ የተሰጠበት 6

87

በስምምነት የተፈቱ ቅሬታዎችን በሚመለከት

የተለያዩ ስምንት ቅሬታዎችን ከሰው ኃይል የሥራ ሂደት ጋር በመነጋገር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ከመርአዊ የመጡ ቅሬታ አቅራቢዎች ከሚመለከተው ከተፈጥሮ ሀብት የሥራ ሂደት ጋር በመነጋገር

መፍትሔ እንዲያገኙ ተደርጓል

አንድ ቅሬታን ከግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል።

አንድ ቅሬታ ከዕፅዋት ክሊኒክ የሥራ ሂደት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል

አንድ ቅሬታን ከ AGP ፕሮጀክት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል።

አንድ ቅሬታን ከ SLM ፕሮጀክት አካውንታንት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል።

አንድ ቅሬታን ከቅሬታ አቅራቢዎች ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል

የተሠሩ ሥራዎች፤

አስተያየት መስጫ ቅጽ ለሥራ ሂደቶች በመስጠት አስተያየት በመቀበልና የተሰጠውን አስተያየት በማየት

ችግሩ እንዲፈታ እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በአስተያየት መስጫ ሣጥንና መዝገብ የቀረቡ አስተያየቶችን በአንድ ለአምስትና በልማት ቡድን የውይይቱ

አካል አድርገው በግብዓትነት ላይ መጠቀም ላይ ጥሩ ጅምሮች ታይተዋል።

የአገልግሎትአሰጣጥን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ከሚያስችሉት መሣሪያዎች አንዱ የሆነውን የሠራተኛ

ደረት ባጅ በማሠራት ለሠራተኞች ተሰራጭቷል።

የአቅጣጫ ተቋሚ ለሠራተኛውን ስም በበሩ ላይ በመለጠፍ ባለጉዳዩ የሚፈልገውን በቀላሉ እንዲያገኝ

ተመቻችቷል።

አቅጣጫ ጠቋሚን በተመለከተ ውጭ ላይ ለተለጠፈው ፎቶግራዶማች የቢሮ ቁጥር በማስቀመጥ ተገልጋዩ

በቀላሉ እንዲያገኝ ተደርጓል፤

88

ክፍል ሶስት

a. ከእቅድ አፈፃፀሙ አንፃር የታዩ ተሞክሮዎችና አበረታች ውጤቶች

በየደረጃጃዉ ያለዉን ሙያተኛ በአፈጻጸማቸዉ መሰረት በደረጃ የመለየት ስራ በመስራት ዕርስ በርስ የዉድድር

መንፈስ የተፈጠረ መሆኑ፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴቶች 1 ለ 5 ቡድን በበልግ የተዘራን የማሾ ስብል ላይ

በአደረጃጀታቸዉ መሰረት የአረም ስራን ያከናወኑ መሆኑ፤የአባወራ ልማት ቡድን፤ የሴቶች ልማት ቡድን፤ የወጣቶች

ልማት ቡድን እና 1 ለ 5 ቡድን በወቅታዊ ስራዎች አፈጻጸማቸዉን መሰረት በማድረግ የደረጃ ፍረጃ በመስጠት

በመካከላቸዉ የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር መደረጉ፤

በአረንጓ ዴ ዋንጫ በዓል ዞኖች ወረዳዎችን ቀበሌዎችን እንዲሆም ተፋሰሶችን መሸለምና ማበረታታት

መቻሉበአምስተኛው የአርሶ አደሮች ፌስቲቫል አርሶ አደሮችን ባለሙያ ተቋማትና አጋር ድርጅቶችን ዕውቅና መሰጠት

መቻሉቢሮው ወደፊታ የወጡ ግንባር ቀደሞችን እውቅና በየስድስት ወሩ መስጠቱ በአራኣያነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ባለሙ ያው ሰኣት የማክበርና በስራ ሰአት የመንግስትና የህዝብ አገልጋይነቱን በመረዳት የሚያሳየው ተነሻሽነትበቢሮ

ውስጥ የተከሰተውን የቢሮ ጥበት ለመፍታት ተጨማሪ ክፍል በመገንባት ለባለሙያው ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር

መቻሉድርቅ በተከሰተበት ወቅት በተፈጥሮ ሃብት ልማት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውበመስኖ ልማት ቀድሞ

ወደ ተግባር መገባቱና የመስኖ በኣልን ድርቅ በተከሰተባቸው ወረዳዎች በማከናወን የህብረተሰቡን ተነሳሽነት

በመጨመር የገበያ መረጋጋት መፈጠሩቢሮው በለውጥ ትግበራ ተግባራት ከሌሎች ቢሮዎች ጋር በመመዘን የታሻለ

ሆኖ በተሻለ ደረጃ መመደቡና መነቃቃት መፈጠሩ በመልካም ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው፡፡

2. በልማትና በመልካም አስተዳደር የእቅድ አፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ

የመፍትሄ ሃሳቦች

2.1 የነበሩ ጠንካራ ጎኖች

አመራሩ ከመቸዉም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ለለዉጡ በሰጠዉ ከፍተኛ ትኩረት እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ

የሚታየዉ መነሳሳት አበረታች መሆኑ፤

እስከታ ች ድረስ መዋቅር ያላቸዉ የስራ ሂደቶች ድጋፍና ክትትል ሲያደርጉ የሪፎርም ተግባራትን በቼክ ሊስታቸዉ

በማካተት የሚደግፉበት አሰራር በየጊዜዉ መሻሻል ማሳየቱ፤

ሰራተኛው የሪፎርም ተግባራትን ለመፈፀም ያለዉ ተነሳሽነት ከቀን ወደ ቀን እያደገ መምጣቱ፤

ከዞኖችም ጋር የተፈጠሩ ትስስሮች፤ እንዲሁም ዞኖች ላይ በተሟላ ሁኔታ ወደ ስራ ለመግባት ከሚታየዉ

መነሳሳት፤ የለዉጥ ስራ ለግብርና አይሆንም ሳይሆን የዛሬ ጥያቂያቸዉ እንዴት እንስራዉ የሚል መሆኑ ሌላዉ

የተገኘዉ ለዉጥ ነዉ፤

89

በዞኖች የተቋቋመዉ የለወጥ አስተግባሪ ቡድን የሪፎርም ተግባራትን በባለቤትነት ይዞ ለመፈፀምና የታዩ

ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ ለማስፋት የታዩ ክፍተቶችን ለማኔጅመንት በማሳየት እየሰራ ያለዉ ስራ ከዞን ዞን ያሉትን

ልዩነቶች በማጥበብ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ የሚታዩ ጅምሮች አበረታች መሆናቸዉ፤

የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ባደረገዉ ግምገማ ካሁን በፊት ከነበረዉ አፈፃፀማችን በተሻለ ሁኔታ ላይ መሆናችን፤

በዘርፉ ሰራዊት ለመገንባት ይቻል ዘንድ ሶስቱ የልማት ክንፎች ተሳስረውና ተመጋግበው የተቋሙ አበይት

ተግባራት በተቀመጠው የአሰራር ስርዕት መሰረት እንዲፈፀሙ የተደረገው ጥረት፤

በበጀት አመቱ የተደረገው የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ያለምንም ጫጫታ መፈፀሙ

በእሊኖ ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ህብረት ስራ ማህበራቱ ለሚመለከተው አካላት ሁሉ በወቅቱ

የምግብ ሰብል ማቅረብ መቻሉ

በዩኒየኞች መካከል ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች እና ምርት አጠር አካባቢዎች ዩኒየኞች ጋር በቋሚነት

የግብይት ትስስር መድረክ በፍጠር የዋጋ ውድነቱን ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉ

2.2 ያጋጠሙ ችግሮች፤

በወቅታዊ የግብርና ተግባራት ብቻ ርብርብ ማድረግና ለተግባራት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እያስተሳሰሩ

አለመመራት በበጀት ዓመቱ ያጋጠመ ችግር ነበር፡፡

የለዉጥ አተገባበር የሥራ ሂደት በራሱ ተግባር የለዉም ነገር ግን የተግባራት ማስፈፀሚያ መሳሪያ መሆኑን

ተቀብሎ በተሟላ ሁኔታ መስራት ላይ ለዉጡ ከተጀመረበት ጊዜ አንፃር ሲታይ መዘግየት ይታያል፤

ለሰርቶ ማሳያ የሚውል የግብዓት አቅርቦት ስራ መጓተትና ጊዜ ጨራሽ ሆኖ መገኘቱ፤

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማትን በሚፈለገው መንገድ ለማጠናከርና ለማደራጀት በየደረጃው ያለው አመራር ቁርጠኝነት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆን

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት የሰርቶ ማሳያ ቦታ በሁሉም ተቋማት አለመሟላት

በግብርናው መስክ የተፈጠረውን የስራ ዕድል በቋሚ የስራ መስክ ማሠማራት ይልቅ በጊዜአዊ የስራ እድል

ማዘንበል፣

በተቀመጠው እስትራቴጂ መሰረት የደን፣ የፍራፍሬና የመኖ ችግኝ ጣቢያዎችን የስራ እድል ፈጠራ መሰረት አድርጎ ለተደራጁ ወጣቶች ለማስተላለፍ በክልሉ የተዘጋጀው መመሪያ በየወረዳው ማግኘት አለመቻሉ፣

ሁሉንም ሰብሎች በመስመር መዝራት ያለመቻል

በውስን የአበይት ተግባራት አፈፃፀም በታቀደው ልክ አለመፈፀም

2.3 ለችግሮቹ የተሰጡ መፍትሔዎች

ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ የሚገኙ ሲሆን በተለይ ለ 2008/09 ምርት ዘመን ቀድሞ የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት በማካሄድ፣ ዝናቡ ቀድሞ በጀመረባቸው ዞኖች የእርሻ ስራው

90

በማፋጠን የበቆሎ ዘር ስራው ቶሎ እንዲሰራ ሰፊ እንቅስቃሴ መደረጉ፣ ዘር አምራች ድርጅቶች በወቅቱ

ያባዙትን ዘር መሰብሰብ፣ ለችግሮች የተሰጡ መፍትሔ ናቸው

3. በመልካም አስተዳደርና በኪራይ ሰብሣቢነት የተከናወኑ ተግባራት

እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ዕቅድ ማቀድ እና መተግበር አበረታች ሁኔታዎች ታይተዋል፤ በመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፤ የኪራይ

መሰብሰቢያ ምንጮችን በመለየትና የማድረቂያ ስልቶችን በሂደት ደረጃ በመለየትና ወደ ተግባር በ መግባት ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በተመለከተ በድጋፍ ወቅት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነዉ

በጥንካሬ

ስራዎችን በተቀመጠላቸው አግባብ እየገመገሙ፤ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ መመራት መቻሉ፤

በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያዎች በአመለካከት፤ በክህሎት፤በአሰራርና በግባአት ያሉባቸውን ችግሮች

ለመፍታት ሰፊ ስልጠና መሰጠቱ፤

በዘርፉ ሰራዊት ለመገንባት ይቻል ዘንድ ሶስቱ የልማት ክንፎች ተሳስረውና ተመጋግበው የተቋሙ አበይት

ተግባራት በተቀመጠው የአሰራር ስርዕት መሰረት እንዲፈፀሙ የተደረገው ጥረት፤

በበጀት አመቱ የተደረገው የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ያለምንም ጫጫታ መፈፀሙ

በእሊኖ ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ህብረት ስራ ማህበራቱ ለሚመለከተው አካላት ሁሉ

በወቅቱ የምግብ ሰብል ማቅረብ መቻሉ

በዩኒየኞች መካከል ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች እና ምርት አጠር አካባቢዎች ዩኒየኞች ጋር በቋሚነት

የግብይት ትስስር መድረክ በፍጠር የዋጋ ውድነቱን ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉ የሚጠቀሱ ተግባራት

ናቸው፡፡ ባጠቃላይ በአመቱ በተከናወኑ ተግባራት አርሶ አደሩንና ክልሉን የሚጠቅሙ ጉልህ ተግባራት

የተከናወኑ ሲሆን በተለይም በዚህ አመት የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በመስኖና

በተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ የተከናወኑ ተግባራት በሃገር ደረጃ ድርሻቸው ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉ ለሃገራዊ

ዕድገት ድርሻውን እንዲወጣ አድርጓል፡፡

91