ነፍስን ከአደጋ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው›› ·...

16
በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! 79ኛ ዓመት ቁጥር 256 ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ዋጋ 5.75 ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል! ገጽ 8 ገጽ 7 ገጽ 2 በውስጥ ገጾች መንዙማ- ኢድ ተጨማሪ 61 ሰዎች በኮረና ቫይረስ ተያዙ «ለነገ ባለፀጋነት ዛሬ ሰውን መርዳት» - አቶ ሳቢር አርጋው ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፡- በዓለም የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ነፍስን ከአደጋ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ 1 ሺ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ትናንት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ስጋውንም ሆነ ነፍሱን ከኮረና ቫይረስ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታው መሆኑን አስታወቁ፡፡ የእስልምና ሃይማኖት ‹‹ነፍሳችሁን ጥፋት ላይ፤ አደጋ ላይ አትጣሉ ይላል» ያሉት ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ነፍስን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ የኢድ ሶላት ግዴታ አለመሆኑን አመልክተዋል:: በመሆኑም በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ሙስሊሞች የኢድ ሶላታቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በቤታቸው ውስጥ መስገድ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አንድ ሰው ብቻ ሆኖ መስገድ እንደሚቻልም ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ገልጸዋል:: የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር በዓል ሁለት ገጽታ እንዳለው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ መጥፎ ገጽታው፤ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መዘያየር፣ መጠጋጋት እና ››ነፍስን ከአደጋ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው›› - ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ››ነፍስን... ወደ ገጽ 4 ዞሯል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት መልዕክት ገጽ 4

Upload: others

Post on 25-May-2020

66 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

79ኛ ዓመት ቁጥር 256 ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ዋጋ 5.75 ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል!

ገጽ 8ገጽ 7ገጽ 2በውስጥ

ገጾች

መንዙማ- ኢድተጨማሪ 61 ሰዎች

በኮረና ቫይረስ ተያዙ

«ለነገ ባለፀጋነት ዛሬ ሰውን መርዳት»

- አቶ ሳቢር አርጋው

ዋለልኝ አየለ

አዲስ አበባ፡- በዓለም የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ነፍስን ከአደጋ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ 1 ሺ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ትናንት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ስጋውንም ሆነ ነፍሱን ከኮረና ቫይረስ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታው መሆኑን አስታወቁ፡፡

የእስልምና ሃይማኖት ‹‹ነፍሳችሁን ጥፋት ላይ፤ አደጋ ላይ አትጣሉ ይላል» ያሉት ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ነፍስን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ የኢድ ሶላት ግዴታ አለመሆኑን አመልክተዋል:: በመሆኑም በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ሙስሊሞች የኢድ ሶላታቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በቤታቸው ውስጥ መስገድ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አንድ ሰው ብቻ ሆኖ መስገድ እንደሚቻልም ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ገልጸዋል::

የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር በዓል ሁለት ገጽታ እንዳለው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ መጥፎ ገጽታው፤ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መዘያየር፣ መጠጋጋት እና

››ነፍስን ከአደጋ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው››

- ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ

ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

››ነፍስን... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር

አብይ አህመድ ለመላው

የእስልምና እምነት ተከታዮች

ያስተላለፉት መልዕክት

ገጽ 4

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 2

ዜና

አዲስ አበባ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የተለያዩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ለእስልምና እምነት ተከታዮች ''እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የዒድ አልፈጥር ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ'' ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የዘንድሮው ታላቁ የረመዳን ወር በፆም፣ እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ በመመካከር፣ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት ማለፉን አስታውሰዋል።ወቅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተበት በመሆኑ ራስን በመጠበቅ እንዲሁም ለሌሎች ወገኖች በመጠንቀቅ አስተውሎት በተሞላበት አግባብ የጥንቃቄ መመሪያዎች ተግባራዊ ሲደረጉ መቆየታቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የመደጋገፍ እና የጥንቃቄ ልምምዱን ይበልጥ በማፅናት፣ በቀጣይ ጊዜያት ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመግታት እንዲሁም ሊያደርስ የሚችለውን የከፋ ጉዳት ለመቀነስ የጥንቃቄ መመሪያዎቹን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ

የዘንድሮ የረመዳን ወር ያለፈው የኮሮናቫይረስ በዓለምና በኢትዮጵያ ላይ ስጋትም ጥፋትም እያደረሰ ባለበት ወቅት መሆኑን አስታውሰዋል።

የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዚህ ቅዱስ ወር በታላቅ መሰብሰብና ስግደት ያከብሩት የነበረ እንደሆነ አስታውሰው ዘንድሮ በዚህ መልኩ ለማክበር ሁኔታው አለመፍቀዱን አመላክተዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ ለሌሎች የሃይማኖት ተከታዮች በሚያስተምር መንገድ ጾምና ስግደቱን በቤቱ ሆኖ በማሳለፍ የሚያስመሰግን የመከላከል ተግባር እየተወጣ መቆየቱን ያስታወቁት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥንቃቄው በበዓሉ ዕለትም ሆነከዚያ በኋላ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮቹ ሌሎችን ለመርዳት ሲያደርጉት የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር መመልከታቸውንም ገልጸዋል፤ ምሥጋናም አቅርበዋል።

የኮሮናቫይረስ ስርጭት በየቀኑ እየጨመረ በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርና ለበዓሉ የሚሆን ግብዓቶችን ሲገዛ አስፈላጊውን አካላዊ ርቀት እንዲጠብቅና ጥንቃቄ አድርጎ እንዲከውንም አሳስበዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ

አሻድሊ ሃሰን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ወር ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያሳየውን ጥንቃቄና መረዳዳት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪውን ያቀረቡት 1441ኛውን የረመዳን ጾም ፍቺ በዓል ምክንያት በማድረግ ከትናንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ ነው ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሃሰን በመግለጫቸው እንዳሉት በክልሉ የሚገኘው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በአዋጅ የተቀመጡትን ክልከላዎች ተግባራዊ በማድረግ መልካም ምሳሌነቱን አሳይቷል ።

“በመስጊድም ሆነ በአደባባይ ተሰብስቦ አምልኮ ከማካሄድ በመቆጠብ አምልኮውን በቤቱ በማከናወን ራሱንና ሌሎችን ከቫይረሱ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት አድርጓል ” ሲሉ አድንቀዋል፡፡

እርስ በርስ በመረዳዳት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ለማገዝ ያደረገው ጥረትም በምሳሌነት እንደሚጠቀስ አቶ አሻድሊ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

“እንደአገር አሁን ያለንበት ወቅት አስቸጋሪ ነው” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ኮሮና ቫይረስ የህብረተሰቡን ጤና ከማወክ አልፎ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያመጣ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ለእስልምና

እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ፦ ባለፉት24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 61 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገለፀ ።ከኮረና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች 151 መድረሳቸውንም የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 3ሺ 757 ሰዎች መካከል 61 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 43 ወንድ እና 18 ሴት ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከ15 - 70 የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። 11 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣5 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሲሆኑ፣45 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያልነበራቸው መሆኑን አመልክተዋል ።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 48 ከአዲስ አበባ ፣ 3 ከአፋር፣ 1 አማራ ፣ 7 ከሶማሌ ፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል ለይቶ ማቆያ የነበሩ መሆኑንም ጠቁመዋል ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 23 ሰው ከበሽታው ማገገሙን አስታውቀው፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151 መድረሱንም አመልክተዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 መሆኑን ጠቁመው ፣ ከእነዚህም ውስጥ 336 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።እስካሁን ለ 76ሺ962 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መሰራቱንም ገልጸዋል።

በቫይረሱ 5 ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለት የውጭ አገር ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ አይዘነጋም።

ተጨማሪ 61 ሰዎች

በኮረና ቫይረስ ተያዙ

ወንደሰን ሽመልስ

አዲስ አበባ ፦ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን (ህዝበ ወያኔ ሃርነት ትግራይ) በቃህ ሊለው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር አስታወቁ:: 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሓት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደመጠቃለሉ መቃረቡን አመለከቱ፡፡

ሊቀመንበሩ አቶ ደረጀ በቀለ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፤ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውን አካሄድ ተገንዝቧል በቃህ ሊለው ይገባል፡፡

የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አመልክተው፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ የህወሓትን አመራሮች በቃችሁ ሊሏቸው እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ እንደማይቀበለው መገንዘባቸውን የጠቆሙት አቶ ደረጀ፤ ህዝቡ ከድህነት መውጣትን የሚፈልግ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ህወሓት የዘረፈውን ወደአውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር እንደሌለም መታዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ይገነዘባል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ህዝቡ መገንዘቡን አመልክተዋል። የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ህወሓትን በቃህ ሊሉት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

እንደእርሳቸው ማብራሪያ፤ የህወሓት አመራሮች በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት አከማችተዋል፡፡ በአንጻሩ በክልሉ የእለት ጉርሱን፣ ጫማና ልብስ ማሟላት እንኳን ያቃተው ህዝብ (በተለይ በገጠሩ) ተፈጥሯል፡፡

የህወሓት አመራሮች ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ህዝቡ ነጻ መውጣት ነበረበት፣ ቢያንስ ትንሽ መሻሻልም ሊያሳይ ይገባ ነበር፡፡ ስለሆነም የትግራይ ህዝብ፣ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የሚያደርጉትን ድጋፍ ማቆም አለባቸው ሲሉ መክረዋል፡፡

በየክልሉ ተበትነው ያሉና በውጭ አገራት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ድጋፍ ቆም ብለው እንዲያስቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሚያደርጉት ድጋፍ በአገራቸው ለውጥ ስለመኖሩ መመልከት

"የትግራይ ህዝብ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል"- አቶ ደረጀ በቀለ፣

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር

እንዳለባቸው፣ ህወሓት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለትግራይ ህዝብ ምን አደረገ? ብለው ሊያስተውሉ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል::

ችግር ሲመጣባቸው መቀሌ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ክልሉን ባስጎበኟቸው ጊዜ አምባሳደር ስዩም መስፍን በተገኙበት የጉብኝት መርሐ ግብር የአምባሳደር ስዩም የትውልድ አካባቢ መመልከታቸውን አስታውሰው፤ የአካባቢው ነዋሪዎች አምባሳደር ስዩምን ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከመመልከት ውጪ በአካል አይተዋቸው እንደማያውቁ እንደነገሯቸውም ነው የገለጹት፡፡

በክልሉ፣ በሌሎች ክልሎችና በውጭ አገራት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ሕወሓት ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው እንደሚገባ በመጠቆም፤ የትግራይ ሕዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ እንዲችል ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን በመጠቆምም፤ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ

ብሎ የሚፎክረው ህወሓትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ የህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ተናግረዋል:: ህዝቡ ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ኢትዮጵያዊነቱን እንደሚያከብር መገንዘባቸውንም አቶ ደረጀ ተናግረዋል::

ህወሓት ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም ብለዋል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ሥራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባር እንዳልሆነም አስታውቀዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ የሚገኝ፣ በአፈና ውስጥ ያለ፤ ከስጋት ያልተላቀቀ መሆኑን ገልጧል:: እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ የሚፈልግ፣ ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ መሆኑንም ጠቁመዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ እንደሚኖርበት አመልክተዋል፡፡

ከአቶ ደረጀ በቀለ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ በገጽ 12 ላይ ይመልከቱ፡፡

አጎናፍር ገዛኽኝ

አዲስ አበባ፡- የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሶስት ነጥብ 16 ቢሊዮን ብር ግዥ መፈጸሙን አስታወቀ። የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ዳፋሊ፤ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ተቋማቸው በ2012 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለማከናወን ካቀዳቸው ሥራዎች 3 ቢሊዮን 160 ሚሊዮን 778 ሺህ 591 ብር ግዥ በመፈጸምና ንብረቶችን በማስወገድ የእቅዱን 84 ነጥብ 3 በመቶ አከናውኗል። በዘጠኝ ወራት ከተገዛው 3 ነጥብ 16 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1 ቢሊዮን 809 ሚሊዮን 727 ሺህ 331 ብር ለፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠቀሙባቸው የኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ አቶ አቶ መላኩ ማብራሪያ ቀሪው 1 ቢሊዮን 341 ሚሊዮን 55ሺ 260 ብር የስትራቴጂክ የስንዴ ግዥ ሲሆን ግዥው ተፈጽሞ ውሉን እንዲያስተዳድሩ ለብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተልኳል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ስድስት ተሽከርካሪዎች ግዥ በብር 9 ሚሊዮን 996 ሺ ግዥ ተፈጽሞ ለተቋሞ ተሏልፏል። የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የተሽከርካሪ ችግር ለመቅረፍም የ305 መኪኖች ግዥ በ8 ሚሊዮን 4ሺ 60 ዶላር ተገዝተው ጅቡቲ ወደብ ደርስዋል። በጠቅላላው በዘጠኝ ወራት ውስጥ ግዥ የተፈጸመው ከ27 አቅራቢዎች ጋር ሲሆን 54 ውሎች መፈረማቸውንም ገልጸዋል። ንብረት ማስወገድን በተመለከተም ዳይሬክተሩ፤ 95 ተሽከርካሪዎችን፣ ቁርጥራጭ ብረቶችንና ሌሎች እቃዎችን በማስወገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 44 ሚሊዮን

አገልግሎቱ የ3 ነጥብ 16 ቢሊዮን ብር

ግዥ ፈጽሟል

አገልግሎቱ የ3... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ፎቶ

ዳኜ

አበራ

Website - www.press.et Email - [email protected] Facebook - Ethiopian Press Agency

ርዕሰ አንቀፅ

ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ

አዲስ ዘመን

የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ

ስልክ ቁጥር - 011-126-42-22

ዋና አዘጋጅአንተነህ ኃ/ብርሃን ወ/መድህን

አድራሻ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከወረዳ 06የቤት ቁጥር 319ኢሜይል - [email protected]ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-40

ምክትል ዋና አዘጋጅአልማዝ አያሌውስልክ ቁጥር - 011-126-42-10

አዘጋጆች ተገኝ ብሩ ጽጌረዳ ጫንያለው አብረሃም ተወልደ አጎናፍር ገዛኸኝ ዳግም ከበደ ሞገስ ፀጋዬ

አምደኛ

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍኢሜይል - [email protected] ስልክ - 011-156-98-73ፋክስ - 011-156-98-62

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍልስልክ ቁጥር - 011-156-98-65

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያስልክ - 011-1-26-43-39

ማከፋፈያስልክ ቁጥር - 011-157-02-70

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 3

ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ ሀሳባቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።

እንወራወር

የታማኝነት ስሙ ለነገም ይተርፋል!

አገራዊ የትብብር፣ የአንድነት እና የጋራ ጥረቶቻችንን ለማዳከም የሚፈታተኑን ችግሮች በየዘመናቱ አጋጥመውናል። በተለመደው የአርበኝነት ትጋት፣ አንድነትና መስዋዕትነት የመክፈል ታላቅ ተጋድሎ ግን ብዙዎቹን ችግሩ ሳይበረታ ተወጥተ ናቸዋል። ድል ተመተዋል። አገርንም መታደግ የታፈረች፣ የተከበረች፣ ውብና ህብር ኢትዮጵያን እስከአሁን ማቆየት ተችሏል። ይህን ክብር በአባቶቻችን ጥንካሬ መወጣት የቻልን ቢሆንም ቅሉ ከዚሁ ከኛው ጉያ የወጡ ባንዳዎች ዞረው ወገናቸውን መውጋታቸው በጥቁር ታሪክ ላይ መመዝገቡም ከድል ጀርባ ያለ ሌላኛው ጨለማ ጎናችን ነው።

የባንዳዎች ክህደት ታሪክ ዘመናትን ይሻገራል። ምክንያቱ ደግሞ የሚበዘብዙትና ለትውልድ የሚተ ክሉት የሚለመልም ሳይሆን መጥፎ የታሪክ አሻራ በመሆኑ ነው። በተለይ በዚህ የኮሮና ወረርሽኝ በተስፋፋበት ወቅት ለህዝብና ለሀገር ታማኝ ያልሆኑ ባንዳዎች መኖራቸውን ስንሰማ ህዝብና መንግሥት ማንን ማመን አለበት የሚለው ጉዳይ በእጅጉ ያሳ ስባል።

በየዘመናቱ ስለአገር እና ስለሕዝብ የሚያስቡ፤ የትኛውንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ፤ የቁርጥ ቀን ልጆች ብቅ ብቅ ይላሉ።ታሪካዊ አሻራቸውንም ለትውልድ ትተው ያልፋሉ። በዚህ መልኩ እየተሟገቱ ያለ ድካምና ዕረፍት የሚተጉ እንቁ የአገር ልጆች የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒ የቆሙትን ለዝርፊያ ቀዳዳ ፈላጊ ሙሰኞችን መርገም ስላለብኝ ነው ዛሬ ብዕሬን ያነሳሁት።እነዚህ ሰዎች ጥቅማቸው አገራቸው ነች።በጥቅማቸው አገርና ሕዝብን ሸጠውም ብዙ ዋጋ እያስከፈሉ ቀጥለዋል። ነገም ማስከፈላቸው አይቀሬ ነው።ደማቸው ገንዘብ ነውና።

ዛሬም አገራችን ወቅቱ በፈጠረው ችግር ውስጥ ሆና ይህንን ሃሳብ ባናነሳ ደስ ይል ነበር።ሆኖም የሰውን ልጅ ዋጋ እያስከፈለ ቢሆንም በዚያው ልክ የእንቅርት

ላይ ጆሮ ደግፍ የሆኑ ፍልፈሎች መጥተውብናልና ዝም ማለቱ ያዳግታል።

ህሊና ያለው ስለ አገሩ ትንሽ የሚያስብ ሰው፤ በአፈፃፀም መመሪያው ከተዘረዘረው ውጪ እንደ አይፎን ስልክና አፕል ላፕቶፖች ሕገ ወጥ ግዥ መፈፀሙ ምን የሚሉት ሃሳብ ነው።ለዚያውም ለአንድ ላፕቶፕ 152 ሺህ ብር እና ለአንድ ሞባይል 94 ሺህ ብር ማውጣት ድሃና ነገ የተሻለ ለመሆን የምትጥርን ሀገር መካድ ይመስለኛል።ከዚያ አልፎ ሲጠቀሙበት የነበረውን ሀብት ለሌላው መጠቀሚያነት እንዲውሉ ለመንግሥት ገቢ አድርጉ ሲባል በፍጹም ፈቃደኛ አልሆኑም።ታዲያ ይህ ጤነኝነት ነው ትላላችሁ።እንደ እኔ እንደኔ ለህዝብ ለመሥራት ሳይሆን ገንዘብና ጥቅም ያናወዛቸው ሰዎች ወደዚያ እንደገቡ ይሰማኛል።

በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ባላደርግም አንድ ነገር ከጅምሩ የተበላሸ ይመስለኛል።የከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ለማሻሻል የሚኒስትሮች ምክር ቤት በነሐሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥር መ30-899/56 ባወጣው መመሪያ በአንቀጽ 8 ቁጥር 4 ተመላሽ የማይደረግ ሞባይልና ላፕቶፕ ለአንድ ጊዜ ተገዝቶ እንዲሰጥ ሲወስን ዝርዝር መመሪውም አብሮ አለመውጣቱ! አገር ወዳድ ሰው መጀመሪያ ራሱን ለአገሩ መስጠት አለበት።በዚህም በራሳቸው የሚያደርጉበትን መንገድ መቀየስ ይቻል ነበር።ተቋማትን ማራቆት ግን አገርን ከመሸጥ ይተናነሳል ብዬ አላስብም።ተቋማቱ ከሌሉ አገር በማንኛውም መልኩ ልትለወጥ አትችልም።ዛሬም የሆነው ይህ ይመስለኛል።

ይህንን ግዢ ከፈጸሙት መካከል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አንዱ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ጉዳዩን አስገራሚ ያደርገዋል።ምክንያቱም ብዙዎችን የሚያፈራ፤ በስነምግባር የሚያንፅ ከምረቃ በኋላ አገር ተረካቢ ይሆናሉ የምንላቸውን ዜጎች በአርዓያነት የሚመራ ተቋም ብልሹ አሠራር መከተሉ እጅጉን ያማል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “ከዚህ በኋላ ቢያንስ አንሰርቃችሁም” ብለው ለህዝብ ቃል ቢገቡም በእሳቸው የሚመሩ አንዳንድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ግን ከተፈቀደላቸው ውጪ የላፕቶፕና ሞባይል በተጋነነ ዋጋ በማስገዛት የህዝብና የመንግሥትን ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ለግል ጥቅም እያዋሉ መሆኑ አያጠያይቅም።በእርግጥ ሰው ተቀምሶ አይታወቅ።ሥራው ሲያጋልጠው አውጥቶ መጣል ይቻል ይሆናል እንጂ።

ምንም አፍረት ያልፈጠረባቸው እነዚህ ሰዎች «አዛዥ ታዛዥ የለም» በሚል ህሳቤ የኮሮና በሽታ ከፈጠረው ስጋት በላይ አገራዊ ስጋት በመሆን ከሕግ ውጪ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ጥቅማቸውን ሞሉ።ህዝብ እንዳይራብ በማለት ብዙዎች ያላቸውን እያካፈሉ ባሉበት እነርሱ ግን ተሰብሮ ለሚወድቅና ዘላለም ለማይዙት እቃ ብዙ ህዝብ ዳቦ በልቶ የሚያድርበትን ገንዘብ በዘበዙት።ታዲያ አሁን ምን ሞራል ኖሯቸው ተገዙልን፤ ልዘዛችሁ፤ አድርጉ ወዘተ የሚሉት።ቆይ እስኪ እውነቱን እናውራ ሳይሰጡ መሰጠት አለ እንዴ?

የአገሬ ሰው ‹‹ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል›› ይላል። አሁንስ አመላቸው አለቅም ብሎ ለቸግር ጊዜ ተብሎ ለህዝብ እየተሰበሰበ ያለውን ገንዘብ ቢበሉትስ አገር ምን ይውጣታል።እንጃ አላውቅም መልሱን ለእናንተው ልተወው።እንደ እኔ እነርሱ ስለአገር አፍ ሞልቶ ለማውራት የቱንም ያህል ሞራል የላቸውም።እንዲህ ያለው ኃላፊነት የጎደለው፣ አገራዊ ትብብርና መደጋገፍን የሚያሳንስ የግዢ ስርዓት፤ አገርን እንደ ካሮት ወደታች እንድታድግ የሚያደርግ ነውና መሳሳታችሁን አውቃችሁ ዛሬውኑ ህዝባችሁን በቶሎ ይቅርታ ጠይቁ።የአገርን ዘላቂ ጥቅም ከማሳጣት ያለፈ ርካሽ ሥራችሁ የትም አያደርሳችሁምና መንግሥት ተጠያቂ ሳያደርጋችሁ ራሳችሁን በመጠየቅ ታማኝነታችሁን ማሳየት ይኖርባችኋል የመጨረሻ መልዕክቴ ነው። ሰላም!

ዒድ አልፈጥርን በመረዳዳትና በጥንቃቄ!

በመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ክብር የሚሰጠው የረመዳን የጾም ወር ተጠናቆ ዛሬ

የኢድ አልፈጥር በዓል ሆኗልና ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን እንላለን! ረመዳን፤ ሙስሊም ምእመናን ራሳቸውን የሚያንፁበት፣ ወደ አምላካቸው በልዩ ሁኔታ የሚቀርቡበትና የኢማን እውቀታቸውን የሚያሳድጉበት ልዩና የተከበረ የፆም ወር ነው።

የረመዳን ወር ከሌሎቹ ወራቶች የተለየና ትልቅ የሚያደርገው፣ ምእመናን ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት አንስቶ እስከ ጠለቀችበት ጊዜ ድረስ ከምግብ፣ ከውሃ፣ ከመጥፎ ንግግር እና ባህሪ ተቆጥበው የሚያሳልፉት በመሆኑ ነው፡፡ ረመዳን በቁርአን እውቀት አዕምሮ የሚበለጽግብትና በመንፈሳዊ እሴቶች ተሐድሶ ተወስዶ የሚወጣበት ወር ነው፡፡ ምእመናን መንፈሳዊ ጥንካሬን ለማግኘት እምነቱ የሚያዘውን የአመጋገብ ዘይቤ የሚለውጡበትና በጾምና ስግደት የሚተጉበት ወቅትም ነው፡፡

በእስልምና ዕምነት ጾም ለምዕመኑ ትዕግሥት፣ ትህትና እና መንፈሳዊ ትምህርት ይሰጠዋል ተብሎ ይታመናል። ረመዳን ለ”አላህ” ሲባል የሚፆም ፆም እንደሆነና ሙስሊሙ ምዕመን ለሠራው ኃጢያት ምህረትን የሚጠይቅበት፣ ዕለት ተዕለት ለሚሠራቸው ኃጢያቱ ይቅርታን የሚለምንበትና ፈጣሪ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ዘንድ የሚጸልይበት ወር መሆኑን የእምነቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ።

ረመዳን በየዓመቱ በሙስሊሙ ህብተረሰብ ዘንድ በናፍቆት የሚጠበቅ ወር ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ደግሞ በተለይም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ልዩ ገጽታን የተላበሰ ወር ሆኖ አልፏል። ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ወረርሺኝ በህዝቦች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ሲባል በመስጊድ የሚደረጉ የኅብረት ስግደቶች በዚህ

ዓመት ሊከናወኑ አልቻሉም። ቀደም ሲል በረመዳን የፈጥር ወቅት የሚደረጉ በጋራ የማፍጠር ሥነ ስርዓቶችም ከዚሁ ወረርሺኝ ስጋት ጋር በተያያዘ በተለመደው መልኩ ሊከናወኑ አልቻሉም። በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመንግሥትንና የሃይማኖት አባቶችን መልዕክት ተከትለው የተሰጡ ትዕዛዛትን በመተግበራቸው ላቅ ያለ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።

ምንም እንኳን የኮሮና ወረርሺኝ በርስ በርስ መቀራረቡና አብሮ ማፍጠሩ ላይ ተጽእኖ ቢፈጥርም መረዳዳቱንና መተጋገዙን ግን በፍጹም ሊያስቀረው አልቻለም። በጾሙ ወቅት የተደረጉ በርካታ የማዕድ ማጋራትና ምስኪኖችን የማገዙ ተግባር ለዚህ አባባላችን መልካም ማስረጃ ናቸው። በዘንድሮው የረመዳን ወር አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገራችን በርካታ ማዕድ የማጋራትና የተቸገሩ ዜጎችን የመደገፍ ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህ ቅዱስ ተግባር ላይ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትጵያውያን ጭምር ተሳታፊ ነበሩ።

ጾሙ ይህን በመሰለ ስኬት መጠናቀቁ ትልቅ የደስታን ስሜት የሚፈጥር ነው። ዒድ - አልፈጥር ትርጉሙ ራሱ የፆም ማጠናቀቂያ ክብረ - በዓል እንደማለት ነው፡፡ ዒድ አልፈጥር በብዙ ሀገሮች በተለያዩ መንገዶች ቢከበርም የጋራ የሆነ አንድ ነገርን ግን ይዟል፡፡ ይሄውም በበዓሉ ቀን ሁሉም አማኞች በጠዋት ተነስተው ልዩ የሶላት ስግደት ወደሚደረግበት ቦታ መትመማቸው ነው። የእምነቱ ተከታዮች በቡድን እየሆኑ ተክቢራ (የበዓሉ የውዳሴ ዜማዎች) በማድረግ ወደ ስግደቱ ቦታ ይተማሉ፡፡ ከስግደት መልስ ምእመናን የበዓል ድግስ አድርገው ከቤተሰብ፣ ከዘመድ - አዝማድ እንዲሁም ከጐረቤት ጋር በዓሉን በደስታ ያሳልፋሉ፡፡

ምንም እንኳን ይህ ከላይ የተገለጸው ሥነስርዓት ሁሌም በበዓሉ የሚከናወን ቢሆንም ዘንድሮ ግን በሰው ልጆች ህይወት ላይ የኮሮና ወረርሺኝ ከደቀነው ስጋት ጋር ተያይዞ በዓሉን በጥንቃቄ ማክበር የግድ ብሏል። ዘንድሮ የሚከበረውን 1 ሺህ 441ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር እንድሪስ ባስተላለፉት መልዕክት “ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የዒድ በዓል ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ በማድረግ መሆን ይኖርበታል። በመሆኑም ሁሉም የዒድ ሰላትን በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል። በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን ይገባዋልም” ብለዋል።

ስለሆነም መላው የሙስሊም ማህበረሰብ የዒድ አልፈጠርን በዓል ሲያከብር አንድም ኮሮናን ለመከላከል መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ ዕርምጃዎች በመተግበር በሌላ በኩል አቅም ያጡ ወገኖችን በማሰብና በመርዳትም ጭምር ሊሆን ይገባል! መልካም በዓል!

ጽጌረዳ ጫንያለው

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 4

ዜና

ከ1ኛ ገጽ የዞረ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1441ዓመተ ሂጅራ ኢድ አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፡፡ ኢድ ሙባረክ፡፡

የረመዳን ወር ስጋዊ ፍላጎትን በመንፈሳዊ ጽናት መርታትንና ራስን ማስገዛትን የመማሪያ ወር ነው፡፡ ሰው ከምድራዊነቱ ባሻገር ያለውን ሰማያዊ ዓለም በጥቂቱ የሚቀምስበትም ወቅት ነው ይባላል፡፡ ብዙዎች ረመዳን ሲገባ በከፍተኛ ደረጃ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡ በአንጻሩ ሲወጣ ግን ያዝናሉ፡፡ ከአንዳች ከፍታ የወረዱ መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ በተለይ እንደዘንድሮ ባለወቅት የሚጾም የረመዳን ወር የመጣውን ወረርሽኝ የማሸነፊያ ትልቁ መሳሪያ ነውና ጾሙ ከአእምሮ የሚጠፋ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም የጾሙን ወር የተቀበልነውም የምንሸኘውም የኮሮና ወረርሽኝ ከከፈተብን ጦርነት ጋር ፊት ለፊት የተጋጠምንበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በመሆኑ ነው፡፡

ሙስሊሞች ታላቁን ረመዳንን ከመስጂድ ሳይለዩ ለማሳለፍ ዓመቱን ሙሉ በጉጉት ይጠብቁታል፡፡ ዘንድሮ ግን ይህንን ማድረግ አልቻሉም፡፡ ብዙዎች ጾሙን ያሳለፉትና ስግደቱን የሰገዱት በየቤታቸው በመሆን ነበር፡፡ ይህንን ወቅት በትዕግስት፤ በታዛዥነትና በአርቆ አሳቢነት ላሳለፋችሁ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ ህዝባችን ሳይጎዳ ወረርሽኙን እንድናሳልፈው ሲሉ መራር የሆነውን ውሳኔ ያሳለፉትን የሃይማኖት አባቶችና የእነርሱን ትዕዛዝ ያከበሩትን ሙስሊም ወገኖቻችንን የኢትዮጵያ ታሪክ በኩራትና በአድናቆት ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የእኛንም የወገኖቻችንንም ህይወት ለመጠበቅ የረመዳን እሴቶች ትሩፋት የላቀ መሆኑን አምነን ነው ጾሙን የጀመርነው:: እስከ ኢድ አልፈጥር ዋዜማ የነበሩትን ጊዜያት ብዙዎች ንጽህናቸውን በመጠበቅ ፣ ከመጨባበጥ በመቆጠብ፣ አካላዊ ርቀትን በማክበር ፣ እርስ በእርስ በመተጋገዝ ፣ በቤታቸው በመቀመጥና ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ የሚቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል፡፡ ጾሙን በሰላም አሳልፎ ለኢድ ያደረሰን ፈጣሪ የወረርሽኙንም ወቅት አሳልፎ ለመልካሙ ጊዜ በሰላም እንደሚያደርሰን ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ኢድ ሲባልም በየዓመቱ መመላለስ ማለት ነውና ቀጣዩን ኢድ ከኮሮና ወረርሽኝ በጸዳ መልኩ እንደምናከብረው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ኢድ አልፈጥር ሙስሊሞች በረመዳን ወሩን ሙሉ ጾመው ሲፈቱ የሚከበር የጾም ፍቺ በዓል ነው፡፡ በዓሉ በውስጡ ታላላቅ ጥበቦችንና አላማዎችን እንደያዘ የእምነቱ ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡ በኢድ ሰላትና በተክቢራ አላህን ከፍ ማድረግና ማመስገን ፣ ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ መደሰትና ሌሎችን ማስደሰት ፣ ችግረኞችን መርዳት፣ ማህበራዊ ትስስሮችን ማጠናከርና የመሳሰሉት በዓሉ ከሚታወስባቸው ድንቃድንቅ ተግባራት መካከል በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡

በረመዳን ወር ጾመኛን በማስፈጠር ፣ ሰደቃ በመስጠት የተጀመረው የመተሳሰብ ጉዞ በኢድ ዋዜማ በዘካ ተልፈጥር እንደሚጠናከር ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ የዘካ ተልፈጥር አካፋዮች ወይም ሰጪዎቹ እና ተቀባዮቹ በተለያየ አንጻር የሚታይ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ዘካተልፈጥር ከሰጪዎቹ አንጻር ሲታይ የረመዳንን ጾም ሲጾሙ ሰው በመሆናቸው የፈጸሟቸውን ጥቃቅን ስህተቶችና ጉድለቶች እንዲሽርላቸው በማሰብ የሚፈጸም ነው፡፡ ከተቀባዮቹ ወገን ደግሞ ችግረኛ ሙስሊሞች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ እንዲያሳልፉ ለማገዝ የተደነገገ ነው፡፡

የእስላም ሊቃውንት እንደሚያብራሩት፤ ዘካ ተልፈጥር ለበዓሉ ከሚመገበው ውጪ ትርፍ ምግብ ባለው ሙስሊም ሁሉ ላይ በግዴታነት ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ እንደምንረዳው የእለት ጉርሱን ሳያገኝ በዓል ን የሚያሳልፍ ወገን እያለ በዓልን በበዛ ቅንጦት ማሳለፍ ወገን ዛሬ ተርቦ ሳለ ለነገ ብሎ ማከማቸት ዘካ ተልፈጥርን እንዳለማውጣት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

ዘካ ተልፈጥር ጾም እንዲጾሙ ግዳጅ የሌለባቸውን ሕጻናትና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ጭምር አካቶ በእያንዳንዳቸው ሰዎች ብዛት በነፍስ ወከፍ በአንድ ሰው አንድ ቁና ወይም ሁለት ኪሎ ተኩል ገደማ ያህል ያወጣል፡፡ ወይም በአካባቢው በተለምዶ ከሚመገቡት የእህል

አይነት ወይም የዚያን ተመን ያህል በገንዘብ ተሰልቶ ይሰጣል፡፡ ዘካተልፈጥር የሚሰጠው የኢድ ማሳለፊያ ላጣ ችግረኛ ሰው ነው፡፡ ተቀባዩም በተራው የተቀበለው ዘካ ከበዓሉ እለት ፍጆታው የሚተርፍ ከሆነ እርሱም በተራው ለሌሎች ዘካ ተልፈጥርን የመስጠት ወይም የማካፈል ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ልማድ ከእምነታዊ ጸጋው ባለፈ ማህበራዊ ኑሮን በማጠናከር በኩል ለአገር የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የጎላ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሌላው የኢድ ውበት ዘመድ ከዘመድ፣ ጎረቤት ከጎረቤት ጋር መጠያየቅ ፣ መመራረቅና አቅም በፈቀደ መጠን ደስታን ለመግለጽ ቤት ያፈራውን መቋደስ ነው፡፡

አማኙ ስጦታ ይቀያየራል፤ በተለይ ለበዓሉ ማረድ የማይችሉ ችግረኛ ጎረቤቶች ካሉ እነርሱን በስጦታው ማሰብ ግዴታ ነው፡፡ የምንሰጠው ስጦታ አነስተኛ ቢሆንም እንኳ ዋናው እነርሱን ማሰባችን ነው፡፡ ቡካውና ሙስሊም እንደዘገቡት፤ ነብዩ መሀመድ ሰላዋልዩ ሰላም እንዲህ ሲሉ መክረዋል፡፡ እናንተ ሙስሊም ሴቶች ሆይ የፍየል ሸኮናን የሚያህል አነስተኛ ነገር ቢሆንም እንኳ ጎረቤት ለጎረቤት ስጦታ ማበርከትን አትናቁ፡፡ ይህንን መሰል እስላማዊ እሴቶችን በመጠቀም የኮሮና ወረርሽኝ የከፈተብንን ጦርነት ከመከላከል ጥረታችን ጎን ለጎን እርስ በርስ የመደጋገፍ ባህላችንን አጠናክረን እንቀጥል ለማለት እወዳለሁ፡፡

አቅም በፈቀደ መጠን ማዕዳችን እናጋራ፤ ችግረኛ ወገኖቻችንን በእውቀት ፣ በገንዘብና በቁስ እንደግፍ:: አንድነትን የማጠናከር ተግባሮቻችንን ወደተቀሩት 11 ወራትም እናዝልቃቸው፡፡ ለአንድ ወይም ለሁለት ዓመት ብቻ ሳይሆን በእድሜ ዘመናችን ሁሉ የሚከወን የጽድቅ መንገድ እናድርጋቸው፡፡ ነብዩ መሀመድ ሰላዋልዩ ሰላም ማዕድ ስለማጋራት ሲያስተምሩ ቡካውና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ለሁለት ሰዎች የተዘጋጀ ምግብ ለሦስት ሰዎች ይበቃል፡፡ ለሦስት ሰዎች የተዘጋጀው ምግብ ደግሞ እንዲሁ ለአራት ሰዎች ይበቃል ብለዋል፡፡ ይህንን የነብዩን አስተምህሮ ብንተገብር በምግብ እጥረት አንድም ሰው ወደጎዳና እንደማይወጣ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ኮሮና በዓለም ላይ ብርቱ ክንዱን በማሳረፍ አደጋ እያደረሰ ያለው ሰዎች ራሳቸውን በመቆጣጠር የመከላከያ መንገዶች ላይ ሳይዘናጉ መተግበር ስላልቻሉ ነው:: ነብዩ መሀመድ ሰላዋልዩ ሰላም በእርሳቸው ምልከታ ራሳችንን መቆጣጠር መቻል ታላቅ ቦታ ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል አንዱና ዋነኛው ጉዳይ መሆኑን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፡፡ ‹‹ ጀግና ወይም ብርቱ ለማለት ሰዎችን ታግሎ የጣለ ሳይሆን በንዴት ጊዜ ራሱን የተቆጣጠረ ሰው ነው›› ሲሉ ራስን መቆጣጠር መቻል ጀግንነትና ብርታት መሆኑን አስተምረዋል፡፡ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር የገጠምነውን ትግል በድል የምንወጣው በሽታው የሚተላለፍባቸውን መንገዶች ሁሉ ራሳችንን በመቆጣጠርና በመግራት ከዘጋናቸው ብቻ ነው፡፡

የኮሮና በሽታ ለሀያላኑ እንኳን ያልተበገረ ክፉ ወረርሽኝ እንደሆነ ሁላችንም አይተናል፡፡ ራሳችንን ለሃይማኖት አባቶችና ለጤና ባለሙያዎች ምክር፣ ትዕዛዝ ተገዢ ካደረግን በጾሙ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያሳዩትን ብርታትና ቁርጠኝነት ካስቀጠልነው ኢትዮጵያ ወረርሽኙን በመቋቋም የምትመሰገን አገር ትሆናለች፡፡ የሚቀጥሉትን የኢድ በዓላት ከአሁኑ በተሻለና የዘንድሮውን ገድል በሚዘክር መልኩ እንደምናከብራቸው ተስፋ አደርጋለሁ:: ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የእምነት ተከታዮች ጋር እያደረጉት ባለው ትብብር ፣ ትግግዝና መተሳሰብ ከቀጠሉ ወረርሽኙ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን መማሪያ እንጂ መማረሪያ እንደማይሆንብን አምናለሁ፡፡

በዘመን መቁጠሪያው ምክንያት የጾምና የጸሎቱ ጊዜ አሁን ቢወጣም እኛ ግን ከጾምና ከጸሎቱ አሁንም እንደማንወጣ ተስፋ አለኝ፡፡ ከጥሩ ምንጭ የቀዳችውን ውሃ በጀርባዋ አዝላ እንደምትጓዝ እናት በጾሙ ወቅት ያገኘናቸውን እሴቶች በልባችን ይዘን እንደምንቀጥል አልጠራጠርም፡፡

በድጋሚ እንኳን ለ1441 ዓመተ ሂጂራ የረመዳን ጾም ፍቺ ኢድ አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡ ኢድ ሙባረክ ፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለመላው የእስልምና እምነት

ተከታዮች ያስተላለፉት መልዕክት

በመስጊዶች በጋራ ሶላት ማድረግ የማይቻል መሆኑ ነው:: ሌላው አስደሳች ገጽታ ደግሞ ህዝባዊ አንድነት፤ የመንግሥትና የህዝብ መተባበር የታየበት ነው ብለዋል፡፡

በረመዳን ወቅት የነበረው ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ስርጭት መተላለፉን አስታውሰው፤ ለመንግሥት፤ ለመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ከትናንት በስቲያ ለተደረገው የቦታ ርክክብም በራሳቸው እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እንደተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ገለጻ፤ የረመዳን ስጦታ ከዕለቱ ቀደም ብሎም ሆነ ከረመዳን በኋላ መስጠት ይቻላል፡፡ የፊጥር ቀን ግን ግዴታ ነው፡፡ ወደ ሶላት ከመወጣቱ በፊት ስጦታው ይሰጣል፡፡ በፊጥር ቀን ስጦታ ካልተሰጠ ፆሙ እንዳልተፆመ ይቆጠራል፡፡ ፆሙ ተቀባይነት እንዲያገኝም ስጦታ መስጠት ይገባል፡፡

ስጦታ የሚሰጠው ወደ ሶላት ከመወጣቱ በፊት የነበረ ቢሆንም በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተለየ አሠራር እንደሚኖረው አመልክተው፤ ማን መስጠት እንዳለበት፣ ለማን መሰጠት እንዳለበት፣ በምን

ያህል መጠን እና በምን ሁኔታ መስጠት እንዳለበት በበዓሉ ዋዜማ ለምዕመናኑ በማይክራፎን ትምህርት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

‹‹እኛ ሙስሊሞች ችግር ያለብን ይመስላል›› ያሉት ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ፤ የሚለያይና የሚከፋፍልንን ነገር በማጥፋት በአንድነትና በመተዛዘን መሥራት ይጠበቅብናል፤ መለያየትና መከፋፈል ከበዛ ፈጣሪም ይቆጣናል ብለዋል፡፡ ‹‹ከወንጀል ካልተቆጠብን ከዚህ የከፋም ሊመጣ እንደሚችል አሏህ አሳይቶናል፤ መስጊድ ውስጥ መጣላት አሏህን ያስቀይማል፤ አሏህ መስጊድን በማስዘጋት አሳይቶናል፡፡ ዲን በገንዘብ፣ በብሄር፣ በሥልጣን አይሸጥም›› ሲሉም መክረዋል፡፡ መንግሥት አንድ ሁኑ እያለ ምዕመናኑ መከፋፈሉና መለያየቱ ከአማኝ የማይጠበቅ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው አንድ ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ሲከበር በመስጊድ ውስጥ ከ15 ሰው በላይ መሆን እንደማይቻል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑላማ ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

››ነፍስን ከአደጋ...

167 ሺህ 579 ብር ገቢ መገኘቱንም አመልክተዋል። የገበያ ዋጋ ጥናት በማድረግ በሽያጭ የሚወገዱ 68 የተለያዩ ሞዴል ተሸከርካሪዎችን፣ 135 ዓይነት የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣ 48 ጠረጴዛዎች ፣ 19 የተለያዩ የኔትወርክ አክሰሪዎች ፣ የ8 ዓይነት ሞዴል አዲስ ተሽከርካሪዎች ግዥዎች እና 11 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ወቅታዊ የገበያ ዋጋ አገልግሎት ማጥናቱንም ጠቁመዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከባለድርሻ አካላትና ከተገልጋዮች ጋር አገልግሎቱ በሚያከናወናቸው

ስራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ በችግሮች ላይ ለመወያየትና መፍትሄ ለማስቀመጥ እንዲቻል 450 ከሚሆኑ ተጠቃሚ መስሪያ ቤቶችና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ሶስት ጊዜ፣ በአገልግሎቱ ስራዎች ላይ በቀጥታ ትስስርና ግንኙነት ካላቸው 16 ቁልፍ ባለድርሻ አካላት፣ ከፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከተጫራቾች ጋር በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ አፈጻጸም ዙሪያ መድረኮች ማካሄዱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ከ2ኛው ገጽ የዞረ

አገልግሎቱ የ3 ነጥብ 16 ቢሊዮን...

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 5

ገና ልጅ ሆኖ አባቱ የባንክ ቤት ሰራተኛ መሆኑን እጅግ ይጓጉ ነበርና ተምሮ የባንክ ሰራተኛ እንዲሆን አብዝተው ይወተውቱት ነበር። ተደጋግሞ የተነገረው የባንክ ቤት ሰራተኝነት

እሱም ወደደውና ባንከር ለመሆን አለመ። በእርግጥ በሂሳብ ስራ (አካውንቲንግ) ትምህርቱን አጠናቆም ስራ ተቀጥሮ ነበር። የሚወደው የሙዚቃ ሙያ ከስራ ለመሰናበቱ ምክንያት ሆነው እንጂ። ከአሰሪው ጋር ያጋጨው ሙዚቃ የዝናን እርካብ ያስረገጠው በኢትዮጵያዊያን እውቅናንና ስኬትን ያጎናፀፈው ሙያ ሆነው - አስገኘው አሽኮ (አስጌ ዴንዴሾ)።

ባህላዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ በዘመናዊ የሙዚቃ ጥበብ አድምቆ የሚያቀርባቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ለተከታታይ አመታት በተለያዩ የሽልማት መድረኮች የአመቱ ምርጥ ሙዚቃ ተብለው ለውድድር ቀርበውለታል። በተላይ በ2010 ዓ፣ም “ባሌ ሮቤ” የተሰኘው ነጠላ ዜማው የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል በአዲስ ሚዩዚክ አሸልሞታል። በራሱ ተገጥመው በሚያምር ቅላፄ የሚንቆረቆሩ የሙዚቃ ስራዎቹ በመላው ሀገሪቱ ከፍ ያለ ተቀባይነትና ዝናን አጎናፅፈውታል።

ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ ባሳለፈው የትምህርት ቤት ህይወቱ በተለያዩ የስነፅሁፍ ክበባት በመሳተፍና ስሜቱን የሚገልፁለት ግጥሞችን በመፃፍ ውስጣዊ ፍላጎቱ ባገኘው አጋጣሚ የመግለፅ ብርቱ እንደነበር ያስረዳል። ወደሙያው ከመግባቱ በፊት ሙዚቃ ስሰማ አንዳች የሚያክለፈልፍ ስሜት ውስጤ ይገባ እንደነበር ያስታውሳል። የሰዎችን ሙዚቃ ማዜም የራሱን ስንኖች እየሞከረ መዝፈን ያዘወትር እንደነበር ይናገራል።

በዛሬው የዝነኞች የዕረፍት ውሎ አምዳችን ይሄንን

«ስኬት እራስን መሆን ነው» አስገኘው አሽኮ (አስጌ ዴንዴሾ)

ፍልቅልቅና ዝነኛ የሙዚቃ ባለሙያ አነጋግረን እነሆ የዕረፍት ጊዜ መቆያዎ ብለናል። መልካም ንባብ።

የእረፍት ጊዜና መዝናኛዎቹስራዬም እረፍቴም ሙዚቃና ከሙዚቃ ጋር

የተያያዙ ናቸው። ያለዜማ ቆይታ፣ ያለ ሙዚቃ መዝናናት ለእርሱ የማይታሰብ መሆኑን ይናገራል። ስራዬን እንደ እረፍት ቆጥሬው የምዝናናው በሙዚቃ ነው በማለት ለሙያው ያለው ጥልቅ ፍቅር ይገልፃል። ያለውን የእረፍት ሰዓቱን በአብዛኛው ከቤተሰቦቹ ጋር ማሳለፍና ከስራ ባልደረቦቹ ጋር መጨዋወትን ልምዱ ነው።

ነገር ግን ከከተማ ወጥቶ መዝናናት፣ ሲኒማ እየገቡ ፊልም ማየት፣ መዝናኛ ቦታዎች ላይ ተገኝቶ የማይረሱ ጊዜያትን ማሳለፍ አስጌ ሞክሮት አያውቅም። ከቤተሰቡ በተለይም ከባለቤቱ ተደጋጋሚ መሰል የመዝናኛ ቦታና ሁኔታዎች እንተግብር ጥያቄ አሁን ላይ እየተነሳ ስለሆነ የዚህ አይነት መዝናኛዎች መሞከሩ በቅርቡ እንደማይቀር ይገልፃል።

ቤተሰብ ጥየቃና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ ነው። በስራ አጋጣሚ ከተገናኛቸው ሰዎች ጋር በቀላሉ የመላመድና የመግባባት ችሎታን የታደለ ጨዋታ አዋቂም ነው። ሰዎችን በቀላሉ ቀርቦ እራሳቸውን መስሎ መልካም የሆነን ድባብ በመፍጠር ለሰዎች ምቾትን ይፈጥራል። በአጋጣሚ ቀርበውት እጅግ የተዛመዳቸው ብዙዎች መሆናቸውንም ይናገራል።

የባህል ምግብ ፍቅር ጥሎብኝ ዘመናዊ ምግቦችን አማራጭ ካጣሁ እንጂ

ፈፅሞ አልመርጥም የሚለው ዝነኛ የሙዚቃ ባለሙያ ከምግቦች መሀል መርጬ ቀድሜ የሚነሳው የቦቆሎ

ቂጣ ነው ብሎ ፈገግ አድርጎናል። ጎመንና ቆጮም ከማዕዱ ላይ ባይጠፋ ይመርጣል። አስጌ ድግስ ተጠርቶ ማዕድ ሲቀርብ አይኖቹ የሚፈልጉት ባህላዊ ምግቦች መኖር አለመኖራቸውን ነው።

የልብስ ምርጫ የለበሰው ሁሉ እራሱ ላይ

እንደሚያምርበት ለመግለፅ ሰዎች ጆንያ ብትለብስም ያምርብሀል ይሉታል። ያለምርጫ ከመልበሻ ሳጥኑ ውስጥ ያገኘውን ልብስ ተጎናፅፎ መገኘትን ይመርጣል። አዘውትሮ ቁምጣና ቀለል ያሉ ልብሶች ይለብሳል። በባህላዊ ሙዚቃው ዘርፍ ጎልቶ የወጣው አስጌ ለስራው የሚገጥም በባህላዊ አለባበስ ሲታይም ባህሉን እጅጉን አጉልቶ የሚያሳይ የሚገጥምም ልዩ ውበት ደርቦ ይገኛል። “እራስ በመሆን ውስጥ የስኬትን ደጃፍ መርገጥ ይቀላል፤ ስኬትም እራስን በመሆን የሚጎናፀፉት ድል ነው።” የሚለው አስጌ ባህል ወዳድና ስለ ባህል ያለው እይታ ጥልቅ ነው።

የሙዚቃ ባለሙያው መልዕክት “ሁሉን ገታ አድርገን ወደ ራሳችን እንመለስ። እዚያ

ውስጥ አንድነትና ህብረታችን፤ መረዳዳትና አብሮ መቆማችን ከፍ ብሎ ይገኛል። አንዳችን ለሌላችን

ሮዛ ሆስፒታል ልጅዋ ጋር ሆና ስልክዋ ጠራ የደወለው ባለቤትዋ ነበር። በላይ እሰጥሀለው ብሎት የነበረው ለልጃቸው ማሳካሚያ የሚሆን ገንዘብ ምክንያት ፈጥሮ እንደማይሰጠው እንደነገረው ሲያረዳት ተስፋዋ ተሟጠጠ። አልጋ ላይ በጀርባው ተንጋሎ አይኖቹን የሚያንከራትተው ልጅዋን እያየች የእናትነት አንጀትዋ አላስችል ሲላት ለማልቀስ ክፍሉን ለቃ ወጣች። አምርራ አለቀሰች፤ የምታደርገው ጨንቋታል አይንዋ እያየ ልጅዋን ለማጣት እየተቃረበች መሆኑን ተረዳች።

ከቆይታ በኋላ የእጇ ስልክ ተጣራ በላይ ነበር። ስለ ልጅዋ ጠየቃት እጅግ መታመሙን ነገረችው። ፍላጎቱ የስዋ ተስፋ መቁረጥ ማየትና እጅ መስጠትዋን መመልከት ነበርና ለፍላጎቱ መቃረብዋን እጅጉን በሚመኝ ተስፋ ደጋግሞ ጥያቄ አነሳ። “ልጅሽን ማሳከሙን አትፈልጊውም? እያየሽው ሊሞት አይገባም። ምን አታልቂ ነገር ምነው ቃሌን ልጠብቅ ብለሽ…” ይሄኔ አልቻለችም አቋረጠቸው። ሳትፈልገው የሚገባውን ለመነገር ተጣደፈች።

“አንተ ሰው አይደለህም አውሬ ነህ። ጓደኛዬ ብሎ የቀረበልህን ለእድገትህ በሚማስን ባልንጀራህ ላይ የምታደባ እርኩስ ነህ።” ሰውነትዋ እየተንቀጠቀጠ

ንግግርዋን ቀጠለች። “ በልጆችህ እናት መማገጥህ ሳያንስ በልጄ መታመም ሰበብ ደካማነቴን አይተህ ስጋዊ ፍላጎትህን ለመሙላት የምታስብ ድንጋይ ነህ። ሁለተኛ በዚህ መልክ አንዳች ሙከራ አደርጋለሁ ብትል በጓደኛህ ብቻ አይደለም በሚስትህ ፊት ሙከራህን ሁሉ እውነታው አውጥቼ አዋርድሀለሁ።” ብላ ጆሮው ላይ ስልኩን ዘጋችው።

በላይ እጅግ ተናደደ ንዴቱ የሚያደርገውን አሳጣው። መኪናውን አስነስቶ ሁሌም ወደ ሚያዘወትርበት ባር አቀና። የቀረበለትን መጠጥ ደጋግሞ እየተጎነጨ ፍላጎቱን ያኮላሸው የስድብ ናዳ ደጋግሞ ማሰብ ያዘ። ስልኩ ደጋግሞ ይጠራል። ባለቤቱ ናት። ማንሳት ፈፅሞ አልፈለገም። ደጋግማ ደወለች፤ አይቶ ምላሽ ሳይሰጥ ድምፁን አጥፍቶ ጠረጴዛው ላይ አኖረው።

ከቆይታ በኋላ በተለየ ድምፅ ወደ ስልኩ የገባው የፅሁፍ መልዕክት ከተቀመጠበት አፈናጥሮ አስነሳው። በተደጋጋሚ ስትደውል ምላሽ አልሰጥ ያላት ባለቤቱ ነበረች ምልዕክቱን የላከችለት። ልጁ ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰበትና ያሉበት ሆስፒታል ነገረችው። በሩጫ ከነበረበት ባር አፈትልኮ ወጥቶ መኪና ውስጥ ገባ አንድ አስተናጋጅ ተከታትሎ “ሂሳብ አልከፈሉም ጌታው” አለው፤ በላይ ድንጋጤ በቀላቀለው ችኮላ ረስቶ የነበረውን

ያሳረፈ መርዶ (መጨረሻ ክፍል)

የመጠጥ ሂሳብ ከፍሎ ወደ ፊት አፈተለከ። በአንድ ከፍተኛ ሆስፒታል ውስጥ ባለቤቱ በእንባ

ርሳ አገኛት። “ልጄ እንዴት ነው? አሁን ምን አደረጉለት?” በማለት አንዴ የማይመለሱ ብዙ ጥያቄዎችን አከታተለላት። “ድንገተኛ ክፍል ውስጥ አስገብተው እያከሙት ነው በጣም ሰግቻለው ልጄ በጣም ተጎድቷል።” ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ባልዋ ላይ ተጠመጠመች።

ወደ ድንገተኛ ክፍል አመራ። ስለ ልጁ አንዲትን ነርስ አስቁሞ ሲጠይቅ እንዲረጋጋና ህክምና ላይ መሆኑ ነገረችው። ብዙም ሳይቆይ ቅድም ያናገራት ነርስ ወደ በላይና ባለቤቱ በመቅረብ “ልጃችሁ እየታከመ ነው፤ ደህና ነው ለክፉ አይሰጠውም። ነገር ግን ብዙ ደም ፈሶታል ለዚያ ደግሞ ደም ያስፈልገዋል። ከሁለት አንዳችሁ መስጠት ይኖርባችኋል።” ነርስዋ ንግግርዋን ሳትገታ በላይ ላቦራቶሪው የት እንደሆነ ጠይቆ ወደዚያው አመራ።

በላይ ከማይወዳት ሚስቱ ያገኛቸው ልጆቹን ይወዳቸዋል። ሚስቱን ሳይፈታት የመቆየቱ ሚስጥር ሁለቱ ልጆቹ ናቸው። አሁን አደጋ የደረሰበት ልጁ ደግሞ እጅግ የሚወደው ነው። ምንም እንዲሆንበት ፈፅሞ አይፈልግም። ልጁ የፈሰሰው ደም ከፍተኛ በመሆኑ ከሆስፒታሉ ደም ባንክ ለልጁ የሚሆን ደም ተወስዶ እንደሚሰጥና ለዚያ ምትክ እንደሆነ ተነግሮት አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኋላ ደም ሰጠ። ልጁ በሁለተኛው ቀን ጤንነቱ እየተሻለ በመሄዱ መናገር ቻለ። በላይ ልጁ ያለበት ክፍል ውስጥ ሳለ አንዲት የህክምና ባለሙያ ገብታ ዶክተሩ ሊያናግረው እንደሚፈልግ ነገረችው።

ከዶከተሩ የጠበቀው ስለልጁ መስማትን ነበር። ነገር ግን ፍፁም ባልጠበቀው መልኩ የሰጠው ደም ሲመረመር ያገኙት ውጤት መነሻ አድርጎ ስለራሱ ጤና አንዳንድ ጥያቄዎች ሲያቀርብለት ግራ ተጋባ። ጤና ምርመራ በድጋሚ ማድረግ እንዳለበትም ነገረው። እጅጉን ተደናገጠ። ድጋሚ ተመረመረ።

ልጁ ተሽሎት እቤት ቢመለስም የበላይ ውጤት ግን ያልተጠበቀ ነበር። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በላይ ያላንኳኳው ሆስፒታል ያላማከረው ልዩ ስፔሻሊስት ሀኪም አልነበረም። ነገር ግን የሚሰማው ተመሳሳይ ውጤት ነበር። በደሙ ውስጥ የተገኘው የደም ካንሰር እጅጉን የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱንና ቀድሞ መታከም ባለማቻሉ ወይም ባለማወቁ መዳን የማይችልበት ደረጃ መድረሱ ነው።

በተቻለው መጠን እረፍት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ምን አልባትም እዚህ ምድር ላይ የሚቆይበት ጊዜ የረዘመ እንደማይሆን ሀኪሞች ደጋግመው ነገሩት።

ልበ ደንዳናው በላይ በሰማው መርዶ ዓለም አስጠላችው። ስለ ሰው ብዙ ያሴር በሰዎች ላይ ተረማምዶ ለራሱ ምኞት መሳካት ይሮጥ የነበረው ሩጫ መገታቱን ተገነዘበ። በብርቱ ሀዘን ተዋጠ። ለሰዎች ቀና ሆኖ የማያውቀው በላይ በህይወት ዘመኑ የሰራችው ክፉ ነገሮች ገዝፈው ታዩት። በዙሪያው ያሉ ሰዎች ላይ ያደረጋቸው ተገቢ ያለሆኑ ክፉ ተግባራት እያንዳንዱ ታዩት። ኤልያስን ደጋግሞ አሰበው።

ስራ ቦታው ከሄደ ቀናት አልፈዋል። ኤልያስ ሁሉንም ሸፍኖ ይሰራል። ድርጅቱን እየመራለት ቆየ። ዛሬ እቤት ለብርቱ ጉዳይ እንደሚፈልገው ነግሮ እቤት አስጠርቶታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ጓደኛውን ኤልያስ በቀናነት ተመለከተው። ጓደኛው ላይ የሰራውን ክፉ ተግባር ፊት ለፊቱ ሲያየው እጅግ ገዘፈበት።ፀፀት ተሰማው። የሰራበትን በደል ባይክስ እንኳን የተጨነቀበትና ህይወቱን የሚገራለትን አንድ ነገር ለማድረግ አስቦ ነበር ያስጠራው።

ኤልያስ የጓደኛውን ሁኔታ በማየት ስለተፈጠረው ነገር ጠየቀው። በላይ የጤናው ሁኔታ ዘርዝሮ ነገረው። ልበ ቀናው ኤልያስ ስለጓደኛው እጅግ በጣም አዘነ። ስለወዳጁ አነባ። ካቀረቀረበት ቀና ሲል እጁ ዘርግቶ እየሰጠው ያለ ወረቀት ላይ አይኑ አረፈ። በእንባ የራሱ አይኖቹን እየጠራረገ “ምንድ ነው በላይ” በማለት ጥያቄ አቀረበ። በላይ እንዲቀበለው አመለከተው።

ሁለት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር የተፃፈበት ቼክ። ኤልያስ “ምን ላድርገው ስራ…” ብሎ ጠየቀ። ኖ.. ይሄ አንተ እስከዛሬ እኔ ጋር ያቆየኸው ገንዘብ ነው። ልጅህ ታሟል መዳን እየቻለ በብር እጦት ነው ሆስፒታል ያለው። እሱን አሳክምበት። እንተም ሁሌ በዚህ መልክ መቆየት የለብህም እራስህን መለወጥ አለብህ ብሩ የአንተ ነው።” ኤልያስ ከበላይ የተሰጠውን ቼክ ያመነው ባንክ ሄዶ ብሩን ወደ እራሱ አካውንቱ ካዞረው በኋላ ነበር። ከዚያን ክንፍ አውጥቶ መብረር ልጁና ሚስቱ ጋር መድረስን ተመኘ። የተጨነቀቸው ባለቤቱ ከጭንቀትዋ ሊገላግል ልጁን፤ የአብራኩን ክፋይ ማሳከሚያ ብር ማግኘቱ ሊነግራት ቸኩሎ። ተጣደፈ። ተፈፀመ

በመኖር ወደ ዋናውና እውነተኛ ማንነታችን እንመለስ” የዝነኛው የሙዚቃ ባለሙያ ለእኛ የቀረበ ታላቅ መልዕክት ነው። አበቃሁ ቸር ይግጠመን።

ተገኝ ብሩ

ተገኝ ብሩ

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 6

ወሬ ማጨሻ ስፍራዎች

ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሦስት መስሪያ ቤቶችን ጓዳ አንጎዳጎድኩ። እነዚህ ተቋሞች አንድ ነገር እንደሚያመሳስላቸው ታዝቤያለሁ፡፡ ዜጎች በዩኒቨርሲቲ፤ በመስሪያ ቤቶችና መኖሪያ መንደሮች አካባቢዎች ሰብሰብ ብለው ስለ አንድ ጉዳይ በተለይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ሃሳቦችን በመሰንዘር እንደሚወያዩ ይታወቃል። በዚህም በሁለት ከፍ ሲልም በሦስት ጎራ ተከፍሎ መከራከርም የተለመደ ነው፡፡

በየሰፈሩም ቢሆን ሰብሰብ ተብሎ እስከ ምሽት ሦስት እና አራት ሰአት ድረስ ትኩረት ስለሚስቡ ጉዳዮች መወያየት በወጣቶችም ሆነ በተለያየ የእድሜ ክልል ላይ በሚገኙ ሰዎች አዲስ ነገር አይደለም። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጊቢ ውስጥ ከዋናው ጉዳይ ውጪ ስለፍቅር የሚወራበት፣ ሴቶችና ወንዶች ሰብሰብ ብለው የሚያወጉበት፣ ፖለቲካ የሚፈጭበት እና የችከላ ቦታዎች በስፋት አሉ፡፡

በእርግጥ እነዚህን ለምሳሌነት አነሳሁኝ እንጂ ሌሎችም አይጠፉም፡፡ ሁሉም ደስ ወዳለው እየሄደ ሃሳብን በሃሳብ ይመለክታል፤ አንዱ ለሌላው ያዋጣል። ይህ ደግሞ በየእለቱ ከአዲስ ሰዎች ጋር ለመተዋወቅ እድልን ይፈጥራል፡፡ ከፍ ሲልም ሊያወዳጅ ይችላል፡፡ ጉዳዩ የሰው ልጆች ባህል መሆኑን ለማመላከት ከጥንት ጀምሮ እንደሚፈፀም በርካታ መረጃዎችን በማንሳት ማሳየት ይቻላል።

የዛሬ ምልከታዬ በዋናነት በአገራችን በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መዝናኛ ክበብ ውስጥ ክርክር ስለሚደረግበት አንድ ቦታ ማውሳት ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ደንበኞች የሚስተናግዱባቸው ቦታዎች የራሳቸው የሆነ መለያ ቁጥር ተሰጥቷቸዋል፡፡ አስተናጋጆችም አንድ፣ ሁለት እና ሦስት ወዘተ. የሚል የመለያ ቁጥር አላቸው፡፡ በዚህ መሰረት ደንበኞቻቸውን ያስተናግዳሉ፡፡

ቁጥር ከተሰጣቸው ቦታዎች መካከል አስተናጋጆች

በቅፅል ስሙ ‹‹ሲጋራ ተራ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ እኔ ግን ወሬ ማጨሻ ቢባል የተሻለ ይመስለኛል፡፡ መጠሪያውን ያገኘው በቦታው ላይ ከሚቀመጡ ሰዎች ባህሪ አንፃር ነው፡፡ በብዛት የሚያዘወትሩ ሰዎች ሲጋራቸውን ማግ እያደረጉ ወሬ የሚያጨሱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ቡና እየጠጡ እና ቁርሳቸውን እየበሉ የሚሳተፉም ሆነ የሚታዘቡም በስፍራው ይታደማሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የዚያ ሰፈር ደንበኛ ስላልነበርኩ፤ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉ ሲያወሩ ብሰማም ትኩረት ሰጥቼው አላውቅም ነበር። አንድ ቀን ግን የቦታውን ሁኔታ ከሚያውቅ ጓደኛዬ ጋር ሄደን ቁጭ አልን፡፡ አረፍ ከማለቴ ብዙ ነገሮች ሲወሩ (እየተነሱ ሲጣሉ) ሰማሁኝ፡፡ በስፍራው ተገኝቶ የራስን ሃሳብ አለመሰንዘር ከባድ ነው፡፡ ድንገት እራስን ከአንዱ ሃሳብ ጋር አዛምዶ አመክንዮን ሲወረውሩ ያገኙታል።

በወሬ ማጨሻ ስፍራዋ ፖለቲከኞቻችን ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ‹‹ፖለቲካንና ኤሌክትሪክን በሩቅ ነው›› እያሉ የሚያስፈራሩባት አባባል ቦታ ካለማግኘቷም በላይ ቃሏ ትዝ የምትለው ተከራካሪ የለም፡፡ እየተመረጠ እሳት እሳቱ ይወራል፡፡ በእርግጥ ‹‹ጋዜጠኞች›› በመሆናቸው ለሻይ አረፍ ሲሉ ይህን መሰል ሃሳብ መሰንዘሩ የሚጠበቅ ነው፡፡

ብዙ ዝምተኛ የሚመስሉ የስራ ባልደረቦቼ በሲጋራ ተራ ወሬ ለማጨስ ማርሽ ቀያሪዎች ናቸው፡፡ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ በጥቅሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ይወራሉ፡፡ በስፋት ይተነተናሉ፡፡ አንድ ወሬ ይወለዳሉ፤ በፍጥነት ያድጋሉ፤ ይሞታሉ፡፡ በጥቅሉ ለማውራት ‹‹እኛ እና እነሱ ›› ብሎ መፍራት የለም፡፡ በሀያሏ አሜሪካ በቅርብ እስከተዋለደችው ደቡብ ሱዳን ድረስ የማይንኳኳ በርና የማይነሳ ሀሳብ አይገኝም፡፡ የሚጎነተለው ተተንኩሶ፤ የሚብጠለጠለው ይጎሻሸማል። የሚወደሰውም እንደዛው፡፡

ስለ አገራችንም ፖለቲካ አንዱ ብድግ ብሎ አሁን ያሉ ችግሮች ሁሉ በቅርብ እንደሚፈቱና ከወቅታዊ ችግር በዘለለ ዘላቂ ችግር እንዳልሆነ ሲናገር ፤ በሌላ

ጎራ የተሰለፈው ቡድን ደግሞ የኢትዮጵያ እድሜ ከአንድ ቀን የጸሀይ ውሎ እንደማይበልጥ በማስረጃ ‹‹እውነት ነው እንዴት?›› እስክትል ድረስ አስረድቶ ሊያሳምንህ ይሞክራል፡፡ በወሬ ማጨሻ ቦታ የአገራችን ፖለቲከኞች ምን እንደሚባሉ ቢሰሙ ብዬ ልከትበው አሰብኩና ከዚህም በላይ ሃሳብ በሃሳብ እንደሚደባደብ ሲገባኝ አለፍኩት።

ከላይ ካነሳሁላችሁ መነሻ አመክንዮ በተጨማሪ እንዲህ አይነት ክርክር እና ውይይት የማውቀው በመፅሐፍ ላይ የ1960ዎች ትውልድ እየተባሉ የሚጠሩ ተማሪዎችን ነው፡፡ ካፒታሊዝምን ጠልተው ሶሻሊዝምን አምልከው የእነ ሌሊን መፅሐፍትን እንደሕይወት መርህ ቆጥረው የሚከራከሩት ማለት ነው፡፡

በዚህ ስፍራ ከታደምኩ ወዲህ እንዲያውም የአገራችን ፖለቲከኞች ከስሜታዊነት ነፃ ሆነው ክርክር ማድረግ ከፈለጉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጎራ ቢሉ ከወቀሳ ይተርፋሉ የሚል እምነት አሳድሮብኛል። ጥሩ ልምድም እንደሚያገኙም አልጠራጠርም፡፡ ያው አለ አይደል ልምድ ልውውጥ ጥሩ ነው መቼም። በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ ውይይት ከመልመድም፤ የአንድን ሰው እውነት ከማጣጣልና ከመንቀፍ ይልቅ፤ ሃሳብን በሃሳብ የመመከት ጥሩ ልምድ መቅሰም ነው፡፡

እናማ ሃሳቤን ከማጠቃለሌ በፊት በመጨረሻ ይሄን ሃሳብ ጣል ለማድረግ ወደድኩ። ችግሮችን በክርክር የመፍታት ልምዱ ደካማ ለሆነ ማህበረሰብ ‹‹የወሬ ማጨሻ›› ተብላ እንደተሰየመችው ስፍራ በተመሳሳይ በተለያዩ ቦታዎች እንዲህ ያሉ የበረከቱ ጉሊቶች መኖር አለባቸው የሚል ሃሳብ አለኝ፡፡ በተለይ ደግሞ በመስሪያ ቤት፣ በትምህርት ቤት እና በመዝናኛ ቦታዎች ቢዘወተሩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ይኖራቸዋል፡፡ በተለይ ሃሳብን በነፃነት ለመተንፈስ።

አንዳንድ ወዳጆች በአጋጣሚ አልያም አስበውበት ወደ አራት ኪሎ ብቅ ካሉ ‹‹ወሬ ማጨሻ›› ጎራ በማለት፤ በአምስት ብር ቡና እየተጎነጩ ዋጋ የማይወጣለትን ሃሳብ እንደሚያዋጡ በሚስጥር ሹክ ማለት እወዳለሁ። ሰላም!

አብርሃም ተወልደ

ንስር እስከ ሰባ ዓመት በሕይወት የመኖር ጸጋ ተሠጥቶታል። ነገር ግን ይህን የ70 ዓመት የዕድሜ ፀጋ አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ ዓመቱ ላይ በሕይወቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅበታል። ይኸውም ንስሩ አርባኛ ዓመት ዕድሜው ላይ እረዥምና እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ እንደ እንጨት ይገተራሉ። ስል የነበረው ማቁርቱም ወደ አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አንድኖ እንዳይዝ ያግደዋል። ያረጁ ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር ስራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል። በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል።አንድም ሞትን አሜን ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት (5 ወር) የሚፈጅ ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድ።በለውጡ ሂደት ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮችን ተግባራት መፈጸም ይጀምራል። በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ካለ ተራራ በመውጣት ጎጆውን ይቀልሳል። ከዚያም ተራራው አለት ላይ ይቀመጥና የታጠፈውን ማንቁርቱንና ጥፍሮቹን ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቁ ያደርጋል። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የህመም ስሜት አለው። አዲስ ማንቁርት እስኪያበቅል ምግብ አይበላም። የገረረውና

ወጋ ወጋ

ድንቃ ድንቅ

አየህ የሰከኑ ለታ የታመመ ሃሳብ ከስሩ ይጠልላል። ዝቃጭ ሆኖ እንደሚቀር ልክ እንደ ጠላው አተላ። እንደ ጠጁ አንቡላ!...። መቅበዝበዝ ክፉ ነው ወንድሜ። የጠለለን ያደፈርሳል። ያኔ ደግሞ አእምሮ ይታወካል፤ የጠራው ሃሳብ ይናወጣል። ግርዱ ከፍሬው ተሳክሮ የጎደለ ፍትህ ይወለዳል።

የሰከኑ ለታ…ታዲያ! የትናንት በደል ይዘቅጣል። የያኔው ጥላቻ ይሽራል። ከባዶ ወሬ ይልቅ ህዝብ በእውነት ይሰክራል። ከወንድምህ የነጠለህ ሰይጣን ድል ሆኖ በአደባባይ ይዋረዳል። አሁን የያዝከው እውነት እናትን ከልጇ የሚነጥል የክፋት መንፈስ ነው። ለምን ተሸነፍኩ የሚል እንጂ ቅሌትን በፀፀት የመሻር ምንም ፍላጎት የሌለው።

አሁን ላይ ያጋጠመን እውነት የኛን ታሪክ ይመስላል ወንድሜ። በተዛባ ትርክት ብዙሃኑን የህሊና እውር አድርጎ ለራስ ቁራሽ ደስታ የሚፈልግ ሞልቷል። ሰከን ብለህ ስታስተውል አይደለም ከወንድምህ ከራስህ የሚያጣላህ የናት ጡት ነካሽ ዙሪያህን ከቦታል።

እመነኝ ወንድም ዓለም አይንህና ጆሮህ ነን ያሉህ የመገናኛ ብዙሃን ልክ እንደ አርቴፊሻሉ እሳት የሚሰብኩህ ፕሮፓጋንዳ ‹‹superficial truth›› ከእውቀት እና ጥበብ ጋርዶሃል። የዘራፊ አመል እንዲህ ነው ወንድሜ። ተፅዕኖ የሚፈጥሩ እና የገንዘብ አቅም ያላቸው ግለሰቦች ማህበረሰቡን ወደ ለምለሙ ሜዳ ሳይሆን ጥልቅ ወደ ሆነው ገደል እንደሚመሩት እወቅ።

ምን መሰለህ ወንድሜ ፍሬውን ከገለባው ለመለየት፤ መንሽ እንደሚያስፈልገን ሁሉ እውነቱን ‹‹ከተዛባው እውነት›› ለመነጠል ጥበብ ‹‹wisdom›› ሊኖርህ ይገባል። በሰንሰለቱ ተጠፍረው እንደተያዙ የዋሻው እስረኞች አንተም ሆንክ ሁሉም ህዝቤ ጠፍሮ ከያዘው ‹‹አለማወቅ›› በጥሶ ለመውጣት ሃሞት ያስፈልጋል። እውቀትን መከተል እውነትን ማሳደድ ይኖርብሀል። ነፃ የሚያወጣውን ጥበብ እንደመሻት ማለት ነው።

ማመን ያለብን ወንድሜ በመርዝ በተለወሰ ቃላቶች እያረሰረሱን እነርሱ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ የሚወስዱንን ጥቂቶችን ሳይሆን ፤ መርምሮ የሚያውቀውን መዝኖ የሚረዳውን ህሊናችንን ነው። ለዚህ ደግሞ እውቀትን መከተል ይኖርብናል። ነፃ አውጪዎችህ ነን ቢሉህም፤ እውቀት እንጂ ጥቂቶች ነፃ እንደማያወጡህ ተረዳ። እንዲህ ብዬ ልደምድም ወንድሜ…

መልካም ፍሬዎች በአንድ ጊዜ አይበቅሉም። የክፋት ፍሬዎችም እንዲሁ፡፡ ስኬታማ ሰዎች አይን ባወጣ ሌብነት ካልሆነ በቀር በአንድ ሌሊት ሀብት አያከማቹም፡፡ እውቅናም ሆነ እውቀት በአንድ ምሽት አይገኙም፡፡ የእኔና የአብዛኛዎቻችን ችግር ይህ ነው። ስኬትም ሆነ ውድቀት በአንድ ቀን ጥረት የሚመጡ ይመስለናል፡፡ መች ይሄ ብቻ ፤ ዛሬ የስኬት ፍሬ ዘርተን ነገ በቅሎ ማየት እንሻለን። የተፈጥሮን ኡደት መጠበቅ አቅቶን የዘራነውን እየነቀልን በትግስት ማጣት ወጥመድ እንወድቃለን፡፡ ጎጠኞች የዘሩት የክፋት መንገድ በአንድ ምሽት እንደ አረም ተነቅሎ፤ ካልተጣለ ብለን በድብርት ማቅ ውስጥ እንወድቃለን። እምነት እናጣለን፡፡ ለዘመናት የበቀለው መልካም የአንድነት ፍሬ በዓመታት የአረም ዳዋ የሚለብስና የሚነቀል ይመስለናል፡፡ ማስተዋል አቅቶን ለአያቶቻችን ጆሮ ነፍገን፡፡

ነፃ አውጪዎችህ ነን !

ከእርሶ ለእርስዎ ተገኝ ብሩ * በግብፅ አቋም እየተገረምኩ ነው፤ እሷን ለማናደድ ምን ላድርግ ? ሳሚ ሳሚ (ከጉርድ ሾላ ) መልስ - 8100 ላይ ደጋግመህ “A” ብለህ ላክ * ቁመቴ አጭርና ደቃቃ ነኝ፡፡ የወደድኳት ልጅ ደግሞ ረጅም

ግዙፍ ወንድ እንደምትወድ ሰምቻለሁ ምን ላድርግ? ቶማስ ነኝ ከሳር ቤት መልስ -በአመለካከትህ ገዝፈህ ተገኝ* ከእጮኛዬ ጋር ሁሌ እንጨቃጨቃለን፤ ሰሞኑን ደግሞ እርሷ

እንጋባ እኔ ደግሞ እንቆይ በማለት እየተጋጨን ነውና ምን አስተያየት አለህ፡፡

ሰመረ አብርሃ (ከመቀሌ)መልስ- ከመጋባታችሁ በፊት ተግባቡ * አሜሪካ በአባይ ጉዳይ ከግብፅ ጎን መሆንዋ አብሽቆኛል፤ አንተ

ይህንን ስትሰማ ምን ተሰማህ? ገብሬ (ከወሊሶ ) መልስ- ነገ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ* ክረምቱን እንዴት ልታሳልፍ አስበሀል? በላይነህ ከአዳማመልስ- በችግኝ ተከላ* ልጅ እፈልጋለሁ ግን ማግባት አልፈልግም ምን ይሻለኛል? ሰላም (ከቦሌ)መልስ - ሳይዘሩ ማጨድማ ደስ አይልም * የሰሞኑ መዘናጋት ምን የሚያስከትል ይመስልሀል? ካሳሁን (ከውቅሮ)መልስ - እልቂት. አሁን ኢትዮጵያን ቀጥ አድርገው ያቆሟት ተቃዋሚ የፖለቲካ

ፓርቲዎች ናቸው ይባላል፤ እውነት ነው አይደል? ሰላማዊት (ከ ፒያሳ) መልስ- በነገር ደግፈው ?. ፈጣሪ ከኮሮና ይጠብቀኛል ብለው የማይጠነቀቁ ሰዎችን

ምከርልኝ የኔነህ (ከአዳማ ) መልስ- “ ግመላችሁን አስራችሁ በኔ ተመኩ” ያለውን ገልብጠው

ሰምተው ይሆናላ

ሞገስ ፀጋዬ

ዳግም ከበደ

ዳግም ውልደት

የታጠፈውን ማንቁርት እንዲሁም ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ ማንቁርትና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናቶች ይታገሳል። ማቁርቱና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው ከመብረር ያገዱትን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ እንዲተኩ ማድረግ ነው። ይህን እልህ አስጨራሽና አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት የፈጀውን የለውጥ ጉዞ ከአካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን በማወጅ ቀጣይ ሰላሳ ዓመታትን በትኩስ ኃይል ለመኖር አሀዱ ብሎ መብረር ይጀምራል።

ንስር ሰባ ዓመት ለመኖር በአርባ አመቱ አሰቃቂ ስቃይን

ያሳልፋል

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 7

በጋዜጣው ሪፖርተር

ወሩ ግንቦት ወቅቱ ደግሞ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቁ የረመዳን ፆም ተጠናቆ በዓሉ የሚከበርበት ቀን ላይ እንገኛለን። በዛሬው የዘመን ጥበብ አምድ ላይም ይህን ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ ስለ አንድ ጉዳይ በስፋት ለመዳሰስ ፈቅደናል።

ነገሩ እንዲህ ነው። የእምነቱ ተከታዮች አምላካቸውን በልዩ ልዩ መልኩ ያመሰግኑታል፤ ያመልኩታል። ከዚህ ውስጥ ቀዳሚው ደግሞ በከበሮ በሚታጀብ መንዙማ ስነ ስርዓት የሚከናወነው ነው። የእስልምና እምነት ተከታዮች በመደበኛው ጊዜ በተለያዩ የምስጋና መልዕክት ባላቸው የተለያዩ ስርዓቶች አምልኮታቸውን ይፈፅማሉ። ለዚህ እንዲረዳቸው የዜማ መሳሪያ ሲጠቀሙም ይስተዋላል።

በአንዳንድ ልዩ ክብረ በዓላት ላይ ደግሞ ጥበባዊ የማመስገኛ ዘይቤው ለየት ብሎና መንገዱን ቀይሮ እናስተውላለን። ለምሳሌ ያህልም በዚህ በያዝነው ወቅት ከባድ እራስን የመግዛት፣ የማምለክና ከዓለማዊው ጩኸት የመራቅ ጊዜ ነው። በመሆኑም አምላካቸውን (አላህ)ን የሚያስቡበት ለምስጋና የሚጠቀሙበት የዜማ ስልት መንዙማ ይሆናል።

መንዙማ በእርግጥ በሌሎችም የፆም እና አዘቦት ቀናቶች ጥቅም ላይ የሚውል ቢሆንም በረመዳን ጊዜ ግን በልዩ ሁኔታ ሰፊውን ቦታ ይይዛል። መነሻችን ላይ ጠቆም አድርገን እንዳለፍነው ለዛሬ በዝርዝር የሚከተሉትን ጉዳዮች እንመለከታለን፤ መንዙማ በረመዳን ወቅት ለምን ጥቅም ላይ ይውላል? ጥበባዊና ሃይማኖታዊው ፋይዳው ምን ይመስላል? መንዙማን ለአምልኮ ስርዓት መጠቀም መቼ ተጀመረ? ዜማው በየትኛው የዜማ እቃ ጋር ተደምሮ ይቀርባል ? የግጥሞቹ መልክቶችስ ምን ይመስላሉ? የሚሉትን እናነሳለን።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም አገር አቀፍ የመንዙማ ጉባዔ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ ወቅት ደግሞ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታይ አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ተገኝተው ነበር።

በወቅቱ ‹‹የመንዙማ ግጥምና ዜማ በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥናታዊ ፅሑፍ በማቅረብ ሰፊ ማብራሪያ የሰጠው የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪና ጋዜጠኛ ተሾመ ብርሃኑ ከማል ነበር። ይህን ግብዣ ያደረገለት ደግሞ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር፡፡ ለዛሬ መንዙማ በተመለከተ ይዘንላችሁ ለምንቀርበው ማብራሪያ ሰፊውን ድርሻ በመውሰድ የፅሑፋችን ማጠንኛ የሆኑ ሃሳቦችን አቀብሎናል። የእስልምና እምነትን በተመለከተ ለምንፈልገው ማብራሪያ በተለያዩ ጊዜያቶች በድምፅም ሆነ በኢሜል አድራሻ በፅሑፍ ለሚልክልን ሰነድ በቅድሚያ ልናመሰግነው እንወዳለን።

መንዙማ ምንድን ነው?የእስልምና ጉዳይ ተመራማሪው ‹‹መንዙማ››

የዓረብኛ ቃል ሲሆን የተገኘውም ነዞመ፣ ከተሰኘው ሥርወ ቃል እንደሆነ ያስረዳናል፡፡ ትርጉሙም አዘጋጀ፣ አደረጀ፣ ትክክለኛ ቦታ ላይ አስቀመጠ፣ አስተካከለ፣ ተስተካከለ፣ አልሺዕር የሚል ቃል ሲጨመርበት ነዞም አልሺዕር ግጥም መደርደር፣ መግጠም፣ ቃላትን፣ ሐረጎችን፣ ስንኞችን በትክክለኛ ቦታቸው ማስቀመጥ መደርደር እንደሆነም ይገልፃል፡፡ ኢንተዞመ፣ ተነዞመ፣ ተናዞመ፣ ሲሆን ደግሞ አዘገጃጀት፣ አደረጃጀት፣ አደራደር የሚል ስሜት ይሰጣል ይላል፡፡ ተንዚሙል ሺዕር ሲሆን ግጥምና ቅኔ የግጥምን ሥነ ጽሑፋዊ ውበት በተከተለ ሥልት፣ ሥርዓት፣ አካሄድ በቅደም ተከተል ማስቀመጥ፣ መደርደር፣ ለወጣለት ዜማ ወይም ለሚወጣለት ዜማ እንዲሆን አድርጎ መድረስ የሚል አንድምታ አለው ይለናል፡፡

‹‹መንዙማ ከሌላው ግጥም የሚለየው ከእስልምና እምነት ጋር የተያያዘ መንፈሳዊ ግጥም በመሆኑ ነው›› በማለትም እስከአሁን ሲነገር የነበረው የመንዙማ ትርጉም በዚህ የሚተካ ከሆነ ዜማውንና ግጥሙን፣ እንዲሁም ውዝዋዜውንና የምት መሣሪያውን የሚያጠቃልል ገላጭ ስም ማውጣት አስፈላጊ ይሆናል

ይለናል፡፡ መንዙማ ከግጥምና ከዜማ አንፃር የጥናቱ ፀሐፊ ተመራማሪ አቶ ተሾመ ብርሃኑ

‹‹መንዙማ ከግጥምና ከዜማ አኳያ ሲፈተሽ የተደረሰው በየትኛው ዘመን ነበር? ወይም የትኛውን ዘመን ያንፀባርቃል? ዘመን አይሽሬ ነው ወይስ የአንድ ዘመን ብቻ እያሉ መተንተን ሊጠይቅ ይችላል›› በማለት በምሳሌነት

«እንዴት አደርክ ብለው እንዴት አደርክ አለኝ አልሃምዱሊላሂ ሊቀር ነው መሰለኝ» የሚል

እንጉርጉሮ ቢገጥመን የትኛውን ጊዜ እንደሚያንፀባርቅ መገመት ይቻላል እያለ አመክንዮውን ያስቀምጣል፡፡

እንደ ተመራማሪው ገለጻ፤ መንዙማ ከዘመኑ ጋር የሚያድግ፣ አገሪቱ ከሌሎች አገሮች ጋር በሚኖራት ግንኙነት የሚጎለምስ ስለሆነ ግጥም በወዲያኛዎቹ አያቶቻችን ዘመን፣ ግጥም በአባቶቻችን ዘመንና ግጥም በእኛ ዘመን ብሎ መተንተን ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የዛሬ 70 ዓመት ገደማ ሐጂ ባደረገበት ጊዜ መካንና መዲናን ዓይቶ የድንጋይና የአሸዋው ክምር፣ ስለአነስተኛዎቹ የመኖሪያ ቤቶች፣ ፅዳት ስለጎደላቸው ምግብ ቤቶች፣ ስለዓረብ ምጽዋት ፈላጊዎች፣ ስለተላላፊ በሽታዎች ቢቃኝ፣ በዚህ ዘመን የሚቃኘው ደግሞ ስለፎቆቹና መንገዶቹ ውበት፣ ስለመብራቱና በመብራት ስለተሠሩት ውብ ጌጦች፣ ስለመኪኖችና ስለሌሎች አስገራሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሊጽፍ ይችላል፡፡

ግጥምና ዜማ እንዳይሰበሩ ጋዜጠኛና የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪው

ተሾመ፤ ከመንዙማ ጋር ግጥምና ዜማ አብረው የሚኖሩ ሲሆን ገጣሚዎቹና ዜማ አውጪዎቹም በሚያውቁት፣ በታያቸው፣ በበራላቸው፣ በተረዳቸው መንገድ ሐሳብ የሚያመነጩና የሚያዜሙ ሲሆኑ የግጥምና የዜማ ደራሲዎቹም ዘመን አይሽሬ ሥራ ሊያበረክቱ እንደሚችሉት ሁሉ ለጊዜው አንጎራጉረው የሚተውት ሊሆን ይችላል ይለናል፡፡

‹‹ከመንዙማ ግጥምና ዜማ ጋር የሚነሳው ዋናው ቁም ነገር ደራሲዎቹ እነማን ናቸው? ከየት ናቸው? በኅብረተሰቡ የነበራቸው ወይም ያላቸው የላቀ ደረጃ እስከ ምን ድረስ ነው?›› የሚለው አቶ ተሾመ፤ ከዚህም በተጨማሪ በግልጽም ሆነ በረቀቀና በጠለቀ ምስጢራዊ መንገድ የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው? ጥልቀቱና ምጥቀቱ ምን ያህል ነው? ቅርፁ ምን ያህል ማራኪ በሆነ ውበት ይዘቱን ገልጾታል? ብሎ መመርመር ያስፈልጋል በማለት የተጠቀሱትን ጥብቅ ጥያቄዎች ማንሳት እንደሚያስፈልግ ይነግረናል፡፡

ተመራማሪው አቶ ተሾመ ጥናቱን በሚሠራበት ወቅት ሼክ ኑረዳኢም አወል ከሐሸንጌ (ደቡብ ትግራይ) አስረድቶኛል ብሎ ባስቀመጠው ሃሳብ ላይ እንደሚያነሳው፤ መንዙማ ጥንታዊ የፈጣሪ ማመስገኛ፣ የነብዩ ሙሐመድ (ሱዓወ) ማወደሻ፣ የፈጣሪ አሀድነትን ማስተማሪያ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ በሰሜን ኢትዮጵያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የንጉሥ (ወሎ) ሙጃሂዱ በግንባር ቀደምነት እንደሚጠቀሱ፣ ቀጥሎም የአና ሸኾች እንደሚመጡ፣ ከአናም ወደ ዳና፣ ከዳና ወደ ጫሌና ወደ ሌሎች እንደ ተዛመተ አስቀምጧል፡፡

የወንድሙ ልጅ መሐመድ ዓረብ ዓብዱራህማንም ደግሞ፤ በራያ መንዙማ የሚደረሰውም ሆነ የሚዜመው በመርህ ላይ ተመስርቶ እንደሆነ እንደጠቀሰለት አንስቶ በተለይ በአና ወጣት ዓሊሞች ትክክለኛውን አቅጣጫ ተከትለው እንዲጓዙ የሼኮች ክትትል ይደረግ እንደነበረ፣ ነገር ግን ጉዳዩ ጠለቅ ያለ ጥናትና ምርምር እንደሚያስፈልገው እንደነገረው በጥናቱ ላይ አስፍሯል፡፡

ይህ ተመራማሪ በሰሜኑና በማዕከላዊው የአገራችን ክፍል ስለመንዙማ ሲነሳ ከ200 ዓመት ያልበለጠ ታሪክ ስለሚጠቀስ ተጨማሪ ጥናቶችን አጥንቶ ወደ ትክክለኛው ዘመን መድረስ እስከሚቻል ድረስ ባሉት ላይ ማተኮር የግድ እንደሚሆንም ይነግረናል፡፡

ይህም ሆኖ የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የሐረሪ መንዙማ ታሪክ መኖሩና ከአናም ሆነ ከዳና ሊቀድም እንደሚችል ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ የባሌና የአርሲው ሰይድ ኑርሁሴን እስከአሁን ድረስ ውብ በሆነ ዜማና ውዝዋዜ መቅረቡ ምስክር መሆኑን በምክንያትነት ያነሳል፡፡

መንዙማ- ኢድ

ከበሮው ለመንዙማ መዘመሪያ የሚጠቀሙበት ነው፤

የዓረብኛ «መንዙማ›› ምንጮች» ‹‹የዓረብኛ መንዙማዎች መሠረታቸው ፈጣሪን

ከማመስገን ከማወደስ፣ ለፈጣሪና ለነብዩ መሐመድ (ሱዓወ) ያላቸውን ፍቅርና አድናቆት ከመግለጽ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው›› የሚለን ጋዜጠኛና ተመራማሪ ተሾመ፤ ወደ ፈጣሪ የሚወስዱት መንገዶች ከቁጥር በላይ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው ይላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሀቅ መረጃ ሳይንስ የሆነው ሱፍያ በውስጡም ተጓዡ ለጉዞው የሚያስፈልጉትን ምግብ፣ ብርሃንና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሲሆኑ መድረሻ ወደቦቹም መንፈሳዊ ሥርዓቶቹ ማለትም ጠሪቃዎቹ መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ እነሱንም ከዚህ እንደሚከተለው በሁለት በመክፈል የበለጠ ያብራራቸዋል።

የሀቅ መንገዶችም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ሲከፈሉ፣ የመጀመርያው ተጓዡ ከመጓዙ በፊት የሚሰጠው ወይም የሚማረው ነው፡፡ ይህም ትምህርት ትንሽ መብላት፣ ትንሽ መጠጣት፣ ትንሽ መተኛት፣ ዚክርን ማብዛትና አስፈላጊ ካልሆኑ ማኅበራዊ ግንኙነቶች መገታትን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ዚክሮቹም ሰባት ሲሆኑ አንዱ ከፈጣሪ (ከአላህ) በስተቀር ሌላ የለም፤ ፈጣሪ፣ እርሱ፣ ሀቁ፣ ዘለዓለማዊው፣ የተብቃቃው የሚሉት ናቸው፡፡

እነዚህን የፈጣሪ ስሞች ደጋግሞ በማውሳት ሰባት የመንፈስ ደረጃዎችን ያልፋል፡፡ ሰባት የመንፈስ ደረጃዎች እርኩስ መንፈስ አዛዥ፣ ራስን የማውገዝ መንፈስ፣ የዕረፍት መንፈስ፣ የፍስሐ መንፈስ፣ የመንፃት ማለትም እንከን የለሽ የመሆን መንፈስ ናቸው፡፡ ይህንን መንገድ የሚከተሉት ሁሉንም ነገር ዓለማዊ ነገር ሁሉ ትቶ ሸሪዓው በሚፈቅደው መሠረት መሪዎቻቸውን ወይም አስተማሪዎቻቸውን እየተከተሉ በፈጣሪ ፍቅር ማለትም በዓሽቅ ተሞልቶ ወደ ሀቅ መጓዝ ነው፡፡

ዓሽቅ ማለት ጥሬ ትርጉሙ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘና ፍፁም የሆነ ፍቅር ውበት ወይም አካላዊ ወዘና ሲሆን፣ ሱፊዎች እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ፍቅር የሚሰጡት ለዘለዓለማዊው ንጉሥ፣ ለግርማዊነቱና በግርማዊነቱ ለሚገለጽ ውበቱ ነው፡፡

ሙላ ጃሚዕ የተባለ ሰው ስለፈጣሪ አስገራሚና አስደናቂ ውበት ሲገልጽ፣ ‹‹የግብፅ ሴቶች የዩሴፍን ውበት ሲመለከቱ ከመደነቃቸው የተነሳ ይዘውት በነበረው ሳንጃ እጃቸውን ከቆረጡ፣ ጌታ ሆይ ያንተን ግሩም ድንቅ ውበት ቢመለከቱ ኖሮ በያዙት ሳንጃ ልባቸውን ይሰነጥቁ ነበር፤›› ብሏል፡፡ ይህም ከፍተኛ ዓይነት ውበትና ፍቅርን (ዓሽቅን) ይፈነጥቃል፡፡

መውጫ ደራሲ፣ተመራማሪና ጋዜጠኛ ተሾመ ብርሃኑ

መንዙማ መጠናት፣ መተንተንና መታወቅ ያለበት የኢትዮጵያ ረቂቅ ቅርስ ነው ይላል፡፡ መንዙማ ከተደረሰበት፣ ከተዜመበት፣ ከተማሩበት፣ ከደረሱበትና ከደራሲያኑ ጋር የተሰናሰለ መሆኑን በመጠቆምም ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ቅርስ ጋር በጥብቅ የተያያዘ መሆኑን ማስተዋል እንደሚገባ ይመክራል፡፡ በወቅቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም ሆነ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ አገራዊ ሀብት ትኩረት ማድረጋቸው የሚመሠገን መሆኑን ጠቅሶ ወደፊትም የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ጥልቅ ጥናት ማድረግና ጥናቱን ማሳተም ያስፈልጋል የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ ይህን ማድረግ ከተቻለ ‹‹ኢስላሚክ ቱሪዝምን በማስፋፋት የአገር ልማት አጋር ማድረግ ይቻላል›› በማለት ሃሳቡን ይደመድማል።

«የዓረብኛ መንዙማዎች

መሠረታቸው ፈጣሪን

ከማመስገን ከማወደስ፣

ለፈጣሪና ለነብዩ

መሐመድ (ሱዓወ)

ያላቸውን ፍቅርና

አድናቆት ከመግለጽ ጋር

በጥብቅ የተያያዘ ነው»

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 8

ጽጌረዳ ጫንያለው

«ለነገ ባለፀጋነት ዛሬ ሰውን መርዳት»- አቶ ሳቢር አርጋው

ፎቶ

- ዳ

ኜ አ

በራ

«ሰርቼ አረካሁም፡፡ ለአገሬ ገና ብዙ የማበረክተው እንዳለ አምናለሁ፡፡ ወገኔን በድርጅቴ አማካኝነት ለማገዝ አስባለሁ›› ይላሉ፡፡ ሰዎች በስራቸው ብቻ እንዲያውቋቸው ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ቃለ ምልልስ ስናወራቸው እንኳን «ለመገናኛ ብዙሃን ለማውራት የሚበቃ ሥራ ሰርቻለሁ ብዬ አላስብም፡፡ ሆኖም ለሌሎች አርአያ ይሆናል ካላችሁ ጥያቄያችሁን ለመመለስ ዝግጁ ነኝ» በማለት ነበር ፈቃደኝነታቸውን የቸሩን፡፡ የአልሳም ኩባንያ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳቢር አርጋው።

ለተቸገሩ ደራሽነታቸው በዝምድና፤ በሰፈርና በሃይማኖት የተገደበ አይደለም፡፡ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ባይ ናቸው፡፡ ብዙዎችን ከችግራቸው እንዲላቀቁ ያግዛሉ፡፡ የአጎታቸው ድጋፍ እርሳቸውን እንዳቆማቸው ሁሉ ሌሎችም በእርሳቸው ድጋፍ ተለውጠው ማየትን ይሻሉ፡፡ ከትንሽ ሱቅ ተነስተው ዛሬ የግዙፍ ኩባንያዎች ባለቤት የሆኑት በእገዛ መሆኑን ስለሚረዱም «ሰዎችን በዕለታዊ ነገር ከማገዝ ይልቅ ሕይወታቸው ላይ ለውጥ የሚያመጣ ድጋፍ ማድረግ ይገባል›› አቋማቸው ነው፡፡ ለዚህም የስራ እድል መፍጠርን ያስቀድማሉ፡፡

ስኬትና የህይወት ልምድ እንዴት መጣ? እዚህ ከመድረሳቸው በፊት ያለፉት የህይወት ፈተና ምን ይሆን? የሚለውንና መሰል ተሞክሮዎችን

እንዲያካፍሉን ለዛሬ «የሕይወት ገጽታ» አምድ እንግዳችን አድርገናቸዋል፡፡

ልጅነት ተወልደው ያደጉት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በሰደን ሶዶ ወረዳ፤ አሌአበባን በምትባል ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤ ልዩ ስሟ አዳዘር በምትባል መንደር ውስጥ ነው። እትብታቸው በተቀበረበት ስፍራ እስከ 16 ዓመታቸው ኖረዋል። በልጅነታቸው አርሰዋል፤ ኮትኩተው አርመዋል፤ ከብት አግደዋል። አቶ ሳቢር በልጅነታቸው ከሁሉም ጨዋታ የሚመርጡት በባህሉ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ‹‹የገና ጨዋታ›› ሲሆን፤ በጨለለቅ ሜዳ ላይ ከክርስትና እምነት ተከታይ ጓደኞቻቸው ጋር ያለ ገደብ መጫወታቸውን መቼም አይረሱትም። በእርግጥ ጨለለቅ ቦታው የቤተክርስቲያን ነው። ግን ክርስቲያን እስላም የሚባል ነገር በአካባቢያቸው ዘንድ ተለይቶ የሚታይ አልነበረም። በዚህ ምክንያት ባለታሪካችን የልጅነት ትዝታ ዘላለም ከአዕምሯቸው እንዳይጠፋ ታትሟል። ዛሬ ድረስ የትውልድ መንደራቸውን ለማስታወስ ሲሉ ትልቁንና ብዙ ያለፋቸውን ሕንጻ የልጅነት ትዝታቸው ይሆን ዘንድ ‹‹ጨለለቅ›› ብለው ሰይመውታል። በባህሪያቸው ተጫዋች ናቸው። ከገና ጨዋታ በተጨማሪ ‹‹አስተርዮና አዳብና›› ተብለው የሚከበሩ የሴቶች ጨዋታ መመልከት ያስደስታቸው ነበር። ጊዜው እስኪደርስ በናፍቆት ይጠብቁት እንደነበርም ያስታውሳሉ። ለእናታቸው የመጀመሪያም የመጨረሻም በመሆናቸው በእንክብካቤ ያደጉት ባለታሪኩ፤ የግብርናውን ሥራ ከአባታቸው ተረክበው ሲሰሩ ውጤታማ ነበሩ። የያዙትን በውጤት ያጠናቅቃሉ። በተለይም በታዳጊነታቸው ጊዜ በእርሳቸው ደረጃ ይሰራሉ ተብለው የማይታሰቡ ስራዎችን ‹‹እሰራዋለሁ›› ካሉ ቤተሰብ አመኔታ ጥሎባቸው ሥራውን ይሰጧቸው እንደነበር ይናገራሉ። በተፈጥሮ ከባድና አይሞከሩም የሚባሉትን ስራዎች ይመርጡ እንደነበር ያስታውሳሉ። የአቅም ውስንነት እንኳን ቢገጥማቸው የጀመሩትን ከግብ ሳያደርሱት አያቋርጡም። ይህ ደግሞ ለዛሬው ጥንካሬያቸው መሰረት እንደሆናቸው አጫውተውናል። ቤተሰቡን ከሚያግዙበት ሥራ መካከል እርሻ በጣም ይወዱ እንደነበር የሚያነሱት አቶ ሳቢር፤ ለቤተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢውም ደቦ በባህሉ አጠራር ‹‹ግቦ›› እየተባለ በሚጠራው ላይ ቤተሰቡን ወክለው በመሄድ የሚያስመሰግን ሥራ ይሰሩ እንደነበርም ያስታውሳሉ። በአካባቢው ዘንድ በሰው ወዳድነታቸውና በታዛዥነታቸው የሚታወቁት አቶ ሳቢር፤ ያላቸውን ማካፈል ያስደስታቸዋል። ይህ ደግሞ ዛሬ ድረስ በእምነት የተገደበ ድጋፍ እንዳያደርጉ አግዟቸዋል። ያደጉበትን ባህል እንዲያስቀጥሉም ረድቷቸዋል። ያደጉበት ማህበረሰብ የሁሉንም እምነት በእኩል ደረጃ የሚታይበት በመሆኑ እርሳቸውም ከዚህ ትምህርት ወስደዋል። እንደውም ከአስተዳደጋቸው አንጻር እንደክርስቲያኑ ሁሉ ገና ልዩ በዓላቸው እንደነበር ይናገራሉ። በቤት ውስጥ ብቸኛ ልጅ በመሆናቸው ከብዙ ነገር ራሳቸውን ይቆጥቡ እንደነበር የሚያነሱት እንግዳችን፤ ጥል የሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ላይ መገኘት

አይወዱም። በዚህም ከማንም ጋር ሳይጋጩ ነው የልጅነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት።

ያልተማረ ምስጢር የለውም ‹‹ያልተማረ ሰው ምስጢር የለውም። ያለውን ሁሉ ሰው ያውቅበታል። በራሱ ስኬት ላይ ለመድረስ የሚያስችለውን መንገድም ይዘጋበታል›› የሚሉት እንግዳችን፤ ያለመማር የተለያዩ እቅዶችን እንደሚያስተጓጉል ይናገራሉ። በዚህ የተነሳ ብዙ ነገሮች አጋጥሟቸዋል። ‹‹አለመማሬ ከዚህ የላቀ ደረጃ ላይ እንዳልደርስ አድርጎኛል። ግን ቅድሚያ ሰርቶ መኖር ስላለብኝ ብቻ ትኩረቴን በሥራዬ ላይ አድርጌ ዓመታትን አለፍኩኝ›› በማለትም፤ በግል ለመማርም ብዙ ጥረት እንዳደረጉ ይገልፃሉ። በተለይ የቋንቋ ትምህርት። ይህም ቢሆን አልተመቻቸላቸውም። ከ25 ዓመታት በላይ የተለያዩ አገራትን ሲጎበኙም የሚንቀሳቀሱት በአስተርጓሚ ነው። ከዚህ ለመውጣት ግን መማር ግዴታ መሆኑን እንደሚያምኑ ያነሳሉ። እንደርሳቸው ገለፃ ‹‹ተስፋ መቁረጥ ባህሪዬ ስላልሆነ አሁንም በስተርጅናም ቢሆን ከቁጭቴ ለመዳን እማራለሁ›› ይላሉ። ትምህርትና ቋንቋን ሲያነሱ አንድ ነገር ግን አጥብቀው ይናገራሉ። የተማረ ማለት እንግሊዚኛ ብቻ ያወቀ ነው ብሎ መወሰድ እንደሌለበት። ይልቁንም የአገሩን ክብር ላለማስነካትና እንደሌሎች አገሮች ስለአገራቸው ለመኖር ከፈለጉ የአገር ቋንቋን በሚገባ አውቀው ሊኖሩበት ይገባል ይላሉ። ለአብነትም ቱርክንና ቻይናን ያነሳሉ። ማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ ቅድሚያ የሚሰጡት ለአገራቸው ቋንቋ ነው። ስለዚህም ይህንን ማድረግ ይገባል።

ችግር ያልበገረው ነጋዴ አቶ ሳቢር የጀመሩት ሥራ መሰናክል የበዛበት ቢሆን እንኳን ሳያጠናቅቁ መረታትን አይፈልጉም። በዚህም ከትንሽ ተነስቶ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደረስ ያውቃሉ። ለዚህ ደግሞ አርኣያቸው አጎታቸው ነበሩ። ስለእርሳቸው ሲያነሱ ‹‹የህይወቴ ቤዛ ነው›› የሚለው ከአንደበታቸው አይጠፋም። የማንም እገዛ ሳይታከልበት ዳገቱን መውጣት ከባድ ነው። በዚህም ለዛሬ ስኬቴ አጎቴ ሐጂ ኢስሃቅ በሽር የማይተካ ሚናን ተጫውቷል። ከዚያ በተጨማሪ የሥራ ባልደረቦቼ እጅግ የማመሰግናቸው ናቸው። ትናንትን ተሻግሬ ዛሬን እንዳየው አድርገውኛል ይላሉ። በ18 ዓመታቸው አዲስ አበባን ረግጠዋል። በአጎታቸው ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመስራት የንግዱን ዓለም ተቀላቅለዋል። በሱቃቸው በመስራት ልምድ ቀስመዋል። ቆየት ካሉ በኋላ የራስ የሆነ ነገር እንደሚያስፈልጋቸው በማመን ከአጎታቸው ጋር ተመካከሩ። ደጉና ሰዎችን በአይን አይተው ምን መስራት እንደሚችሉ የሚረዱት አጎታቸውም በራሳቸው ቢሰሩ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆኑ ስለተረዱ 10 ሺህ ብር ሰጥተዋቸው በሽርክና እንዲሰሩ ሁኔታዎችን አመቻቹላቸው። በዚህ ሥራ ላይ አምስት ዓመታትን እንደቆዩ ያጫወቱን ባለታሪኩ፤ በሽርክና ሲሰሩ ከነበሩበት ሱቅ ለቀቁ። በዚህም ብዙ ፈተና ደረሰባቸው። ግን ተስፋ መቁረት በእርሳቸው ዘንድ ቦታ አይሰጠውምና ወደ ሌላ ስራ ገቡ። ይኸውም የለስላሳ መጠጥ ችርቻሮ ንግድ ነበር። አቶ ሳቢር በትዕግስት ፈተና ይታለፋል ብለው ያምናሉ። በዚህም ትንሽ ትልቅ ስራ በማለት ሳያማርጡ መስራት

ይወዳሉ። ይህ ደግሞ ላቀዱትና የልጅነት ህልማቸው ለሆነው ባለጸጋነት እንዳበቃቸው ይናገራሉ። 1974 ዓ.ም ለእርሳቸው የስኬት መጀመሪያ ጊዜ እንደነበር የሚያወሱት ባለታሪኩ፤ ከአጎታቸው ዳግም 17 ሺህ ብር የሚገመት የሸቀጥ እቃ ተበድረው አነስተኛ ሱቅ ከፈቱ። ይህ ስራ ደግሞ ለብርቱውና ፈጣኑ አቶ ሳቢር ውጤታማ ያደረጋቸው ነበር። እንዳውም በአንድ ዓመት ውስጥ ብድራቸውን መመለስም አስችሏቸዋል። ከዚያ ንግዱና ተፈላጊነታቸው በመጨመሩ በ1987 ዓ.ም ‹‹ሳም ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር›› በሚል ስያሜ መሰረቱ። ከጅምላ ንግድ ወደ አስመጪና አከፋፋይ የገቡት እንግዳችን፤ ሌሎች እህት ድርጅቶችንም ማቋቋም የቻሉት ከዚህ በኋላ ነው። በዚህም በ1991 ዓ.ም አልሳምና ሊና የተሰኙ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅቶችን መሰረቱ። በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተው ምርቶችን እያመጡም በአገር ውስጥ ማከፋፈሉን ተያያዙት። ቀጣዩ ጉዟቸው ደግሞ ከውጭ አምራች ድርጅቶች የወኪል አከፋፋይነት ሥራን በመቀበል በአገር ውስጥ የማከፋፈል ሥራ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ቢ 29 ሳሙና፣ ኪዊ የጫማ ቀለም፣ ቢክ እስኪርብቶ፣ ኤፒፒ ጎልደን ፕላስ የፎቶ ኮፒ ወረቀት፣ ኤስ 26 የሕጻናት ወተት፣ የኤቬሬዲና ኢነርጃይዘር ባትሪ ድንጋይ፣የቫይኪንግና የሳኒያ የምግብ ዘይቶችና የቤኮ

ቴሌቪዥንና የቤት እቃዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢንዶኖዢያ ኩባንያ ከሆነው ‹‹የፒቲ ሲናር አንጆል›› ጋር ሽርክና በመመስረት ቢ-29 እና ሌሎች የዱቄት ሳሙናዎችን በማምረት በአገር ውስጥ ማከፋፈል የቻሉት አቶ ሳቢር፤ በሥራቸው ውጤታማ የሚያደርጋቸውን አልሳም ጨለለቅ ህንጻን ገንብተዋል። ቀጥለው ደግሞ በሊና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኩል ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት አክሲዮን ማህበርን ከመንግስት በመግዛት ማስተዳደር ጀመሩ። የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካን በማቋቋም ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉንም የተቀላቀሉት እንግዳችን፤ በሪል ስቴት ዘርፉም የማይተካ ሚናን እየተጫወቱ ይገኛሉ። በቀጣይም ቢሆን በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ህዝባቸውንና አገራቸውን ማሳደግ እንደሚፈልጉ አጫውተውናል። በተለይም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በሪልእስቴት፣ በማኑፋክቸሪንግና በወጪ ንግድ ዘርፎች የበለጠ መስራትና ትውልድ ተሸጋሪ ስም መትከልም እንደሚፈልጉ አጫውተውናል። አቶ ሳቢር በሥራ ህይወታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥረው የስራ እድል የፈጠሩ፤ በበርካታ የፕሮጀክት ሥራዎቻቸውም ከሰባት መቶ በላይ ሰዎች ሥራ እንዲያገኙ ያስቻሉ ናቸው። ከዚያም በዘለለ ብዙዎች በኩባንያቸው ሰርተው እንዲለወጡ

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 9

ፎቶ

- ዳ

ኜ አ

በራ

አግዘዋል። ቤተሰብ መስርተውም የራሳቸውን ድርጅት እንዲያቋቁሙ አድርገዋል። ለዚህ ደግሞ ያበቃቸው በስራው ልክ ሰው ማግኘት እንዳለበት ስለሚያምኑና ቃላቸውን ስለማያጥፉ ነው። አቶ ሳቢር ውጤታማ መሆንን በግል ደረጃ የሚያስቡ አይደሉም። በህብረት ማደግ የስኬት ምንጭ እንደሆነ ያምናሉ። በዚህም የሰሩትን በእኩል ደረጃ ተካፍለው ለዛሬ ስኬታቸው እንደበቁ ያስረዳሉ። በስራዎች በርካታ መሰናክሎች ገጥሟቸዋል። ግን መፍትሄው አሁንም መስራት ነው ብለው ያምናሉ። ችግር መምጣቱን ማንም ሰው ሊጠላው አይገባም። በሥራ ህይወት መውደቅና መነሳት ያሉ ናቸው። በዚህም ችግሩ የመጣው ከተኛንበት እንድንነቃ ነው፤ ወቅቱ የጠየቀውን ተዛማች ሥራዎችን እንድንሰራ ያስችለናል፤ የመፍትሔ አካልም ያደርገናል በማለት ያስባሉ። ‹‹ላለመውደቅ ሥራን በአግባቡ መከታተል ያስፈልጋል። የመውደቁን መንስኤ አውቆ የሚነሳበትን ዘዴ መቀየስም ይገባል›› የሚሉት እንግዳችን፤ በዚያ ላይ ንጹህነት ከምንም በላይ አብልጦ መውደድ በአላህ ዘንድ ድጋፍን ይቸራልና መጠቀሙ ተገቢ ነው ይላሉ። በታማኝነት ሥራዎችን ማከናወን፤ የንብረት አስተዳዳሪ እስከሆኑ ድረስ ሥራው ስኬታማ መሆን እስኪችል ድረስ መተኛት አይገባም የሚል ጠንካራ እምነት አላቸው። ተጨንቆ ተስፋ መቁረጥና ተጨንቆ ችግርን መፍታትን መለየትም ያስፈልጋል የሚል ምክርም ስኬትን ለሚሹ ይለግሳሉ።

ክርስትና በእርሳቸው ዓይን አቶ ሳቢር ባደጉበት አካባቢ የእስላምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች አብሮ መብላት መለያቸው ነው። ልዩነት ያለው ሥጋ ላይ እንደሆነ ቢታሰብ እንኳን ሥጋ የተበላበት እቃ በአመድ ይታጠባል እንጂ ልዩነት ባለው መልኩ አይሰበክም። በዚያ ላይ አንዱ ቤት ሙስሊም ቀጥሎ ያለው ደግሞ ክርስቲያን በመሆኑ አንዱን ከአንዱ ነጥሎ ለመኖር ያስቸግራል ይላሉ። ጉርብትና ቤተሰባዊነት ነው ተብሎ ስለሚታመንም የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሚደረግም ይገልፃሉ። ‹‹የአብዛኞቻችን ቤተሰቦች በጋብቻም ሆነ በስጋ ከክርስትናው እምነት ተከታዮች ጋር ዝምድና አላቸው››

በማለት፤ ይህ ደግሞ በሁለቱ እምነቶች መካከል የአስተምሮ ልዩነት እንጂ ቤተሰባዊነት እንዳልተገደበ የሚያመላክት መሆኑን ያነሳሉ። ለዚህም ማሳያው የእሳቸው አክስት ክርስቲያን መሆኗና በዓላትን በተለይም ፋሲካን እርሷ ቤት ሄደው እንደሚያሳልፉ ይናገራሉ። ሌላው ከክርስቲያኖች ጋር ያላቸውን ቅርበት ያነሱበት ደግሞ በቀያቸው የነበራቸውን የአስተዳደግ ሁኔታ ነው። በበዓለወልድ ዓመታዊ ክብረበዓል ላይ ታቦት ሲወጣ ያለልዩነት ታቦታቱን አጅበው ማስገባታቸው ነው። ጥምቀት ላይም እንዲሁ ማድረጋቸው ሁለቱ እምነቶች ከአስተምህሮ በስተቀር በማህበራዊ መስተጋብር አንድ እንደሆኑ ያሳያል ይላሉ። ‹‹እምነት የግለሰብ ነው። የሚያምንበትን በጥልቀት ማወቅና በዚያም መኖር አለበት ብዬ አምናለሁ›› በማለትም፤ ይህንን ተከተል ብሎ ማስገደድ እንደማይመቻቸው ያነሳሉ። ለዚህ ደግሞ አስተዳደጋቸው መሰረት ሆኗቸዋል። ዛሬም ለልጆቻቸው እያደረጉ ያለውም ይህንኑ ነው። በእምነታቸው ማሳወቅ ያለባቸውን ፈፅመዋል። ግን ከእሳቸው ውጪ አላሏቸውም። የሰዎችንም እምነት የሚያጎድፍ ነገር ሲናገሩ መስማትም እንዲሁ። ገጠር ማደግ እውነተኛ ኢትዮጵያዊነትን መማር ነው ይላሉ እንግዳችን። ባህሉን ፣ አኗኗሩን፤ ልባዊ ፍቅርን ያሳውቃል፤ ያኖራልም። በተለያዩ ፖለቲካዎችና በባዕድ ማንነት ቢፈተኑም መውደቅ እንዳይኖርበትም ያደርጋል። ምክንያቱም ስሜቱ ከአዕምሮ ውስጥ የተተከለ በመሆኑ ለማስወጣት ይከብዳልና ነው። ከስኬት በኋላ ማንን ላግዝ በሚለው ውስጥ ሲመጣም ቤተሰብ ፤ የአካባቢ ማህበረሰብና አገር የሚለው የሚመጣውም በዚህ ማንነት ስለሚታደግ መሆኑን ይገልፃሉ። በተለያዩ አገራት ስዞር አንድ ነገር አይቻለሁ ይሄውም ሁሉም ሰው አገሩን በጣም ይወዳል። ስለ አገሩ መልካም እንጂ መጥፎ መተንፈስን አይፈልግም። ራሱን ሸጦ አገሩን ማሳደግም ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው። በተለይም በብልጠት ስለአገሩ የሚያደርገው ነገር በጣሙን ያስገርማቸዋል። ምንም የሌለው ሆኖ ሳለ አለኝ ብሎ ያተርፋል። እዚህ ግን ከአገሩ ይልቅ ውጪ ናፋቂ መብዛቱ ያስቆጫቸዋል። መለመን ካለመስራት

መቅደሙ ያበሳጫቸዋል። ያለውን ሀብት ተጠቅሞ አገር ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ይናገራሉ።

ኢድ እንዴት ይለፍ ሁሉም እምነት መረዳዳትን፤ አንዱ ለአንዱ መኖርንና ካለው ላይ ማካፈልን ያስተምራል። መስጠት ደግሞ አብሮ ይዞት የሚመጣው በረከት ብዙ ነው። እናም ኢድም ማለፍ ያለበት በመስጠትና ብዙ በረከት በማግኘት መሆን እንዳለበት ይገልፃሉ። በተለይም ነብዩ መሀመድ የሚያስተምረን የጀነት መግቢያችን ልግስናችን መሆኑን ነውና በተለይም በዚህ ጊዜ ይህንን ማድረግ ውዴታ ሳይሆን ግዴታችን ነው ይላሉ። ባለሀብትነት ጸጋ የሚሆነው ገንዘብ ስላለ ሳይሆን ከሰዎች እኩል ሲኖርበት ነው። ተመሳስሎና ከእነርሱ ጋር ተግባብቶ፤ እኩል እንዲያድጉ ሲጣርበት ነው። አለኝ ብሎ መኩራራት ሳይሆን ሌሎችም እንዲኖሩት ማድረግ ነው። ኖረንም አልኖረን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አብሮ ማደግ ራስን ብቻ ሳይሆን አገርንም ያሳድጋልና ጸጋውን በዚህ እየተረጎሙ ኢድን ማሳለፍ ይገባልም በማለት ወገኖቻቸውን በቅን አባታዊ መንፈስ ይመክራሉ። ‹‹ኢትዮጵያዊነት አንዱ መለያው አብሮ መብላትና መጠጣት ነው። ይህንን ደግሞ ወቅቱ አይፈቅድም›› የሚሉት አቶ ሳቢር፤ በተለይ ኢድ ብቻን ማሳለፍ በጣም ስሜቱን ያጠፋዋል በማለት ቁጭታቸውን ይገልፃሉ። እንደውም በዓሉ በዓል አይመስልም ይላሉ። ግን ከመሞት መሰንበት ያስፈልጋልና ዛሬን መቻል ግድ መሆኑን ይገልፃሉ። ‹‹ገጠር ከአሳደገኝ ማህበረሰብ ጋር ማሳለፍ እፈልግ ነበር›› በማለትም፤ ያንንም ይሄን ናፍቀው ዓመቱን ሙሉ ይጠብቁ እንደነበር ተናግረዋል። ኮሮና በመምጣቱ የተነሳ ብዙ ነገር አሳጥቷቸዋል። ሆኖም ጊዜውን መምሰል ነገን ለማየት ይጠቅመል ብለው ያምናሉ። ሌሎችም ይህንን ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ። ‹‹የዘንድሮ ረመዳን አንድ ላይ የሚፈጠርበት አልነበረም። ሆኖም ለሚያልፍ ጊዜ ማለፍ የሌለበትን ሕይወት መገበር አይገባምና አድርጌዋለሁ›› የሚሉት እንግዳችን፤ አሁንም ቢሆን ቢመረንም ኢድን በየቤታችን በማሳለፍ አላህ ለዓመቱ በሰላም እስከሚያደርሰን፤ ጨለማውን እስኪገልጥልን እንጠብቅም ይላሉ። ጾም ጥሩ ነገር እንድንሰራ የሚያደርገን ነው። በዚህም ሰው ከቤቱ ስለማይወጣ ረመዳን ከመድረሱ በፊት ለእስልምናውም ሆነ ለክርስቲያኑ እምነት ተከታዮች ከ350ሺህ ብር በላይ በማውጣት በአካባቢያቸው ላሉ ሰዎች ለግሰዋል። ጊዜው መኖርና አለመኖርን የሚወስን ነውና በቀጣይም ይህንን መሰል ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። መቼ እንደምንሞት እንኳን አናውቅምና ልብ እንበለው ይላሉ። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ከሦስት የሥራ ባልደረቦቼ ጋር፤ በኦሮሚያ ክልል አንድ ሚሊዮን ብር ደግሞ ብቻዬን የሰጠሁት በኮሮና ምክንያት ወገኔ እንዳይቸገር በማሰብ ነው የሚሉት ባለታሪኩ፤ ብዙ የሚያስደስቱን ነገሮች ቢቀሩም መተጋገዛችን ግን ደስታን ይሰጣልና አሁንም እናጠንክረው ሲሉ ይመክራሉ። እስከዛሬ ከሚያወጡት ምጽዋት በላይ አሁን ማድረግ በመቻላቸው በረከት እንዳለበት አምናለሁ ብለውናል። ስለዚህም በቀጣይም ይህንኑ ድጋፋቸውን እንደሚያስቀጥሉ አጫውተውናል።የኮሮና መምጣት ብዙ ነገሮችን አስተካክሏል። የመጀመሪያው ጥሩ ነገር ማድረግ ምን ያህል እንደሚያስደስት አሳይቷል። ለአገር ሰው መኖርና መርዳት በምን ያህል ሁኔታ አሁን ላይ እንዳለም አመላክቷል። በተጨማሪ በፖለቲካው ውስጥ የነበረንን መከፋፈልና ጽንፍ የወጣ አስተሳሰብን አቁሟልም ይላሉ። ስለአንድነትና ኮሮና ብቻ እንድናስብ፤ ማረን እንድንልና ስለ ስራችንም ቆም ብለን እንድናስታውል አድርጎናል። ይህ ደግሞ ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን አይነት ገጽታ እንደሚኖራት ጠቁሟል። ምክንያቱም ወገንተኝነት የሌለበት ድጋፍ በእያንዳንዱ ሰው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳርፏልና ነው። ኢድን ስናከብርም ሆነ ከኢድ በኋላ ኮሮና እንዲ ወገድ ወደ አላህ መጸለይ አለብን። ጊዜአዊ አድርግልን ልንለውም ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ለማለፍ ይቸግረናል። ስለዚህም መንግስት ቢያንስ በየአካባቢው የሚያግዙበትን መንገድ ቢዘረጋ የተሻለ አማራጭ ይኖራል። በዚህ ደግሞ ኢድን አሁን እያደረግን ያለውን አብዝተን እያደረግን ማሳለፍ አለብንም ይላሉ። ‹‹ሰው ሲኖር ሥራ ይኖራል፤ ቢዝነስም ያድጋል። ከሌለ ግን በማንም ማደግ አይቻልምና ‹‹ለነገ ባለጸጋነታችን ዛሬን

ለሰው መስራት ይገባናል›› መልዕክታቸው ነው። አበርክቶ

መጀመሪያ ከ20 ዓመታት በላይ የኖሩት በሸጎሌ አካባቢ ነው። እናም በዚያ አካባቢ የለመዱት የገጠሩ ባህል ተግባራዊ እንዲሆን ብዙ ጥረዋል። ለአብነት ምንም ገንዘብ በሌላቸው ጊዜ በቡሄ ጊዜ ሆያ… ሆዬ እየጨፈሩ ሲመጡ በኪሳቸው ያላቸውን ይሰጡ ነበር። እናም የሰፈሩ ልጆች ያንን ልምድ አድርገው በዓመት አይቀሩም። ይህ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያላቸውን ድጋፍ ከፍ እያደረጉት እንዲሄዱ አስቻላቸው። ትንሽ ገንዘብ ከመስጠት አልፈው እርድ የሚፈጽሙበት ሁኔታዎችን ፈጥረውላቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ወደ ጦር ሃይሎች አካባቢ ሲገቡም ቢሆን ያንን ልምዳቸውን አልተውም። እንደውም ከፍ አድርገውት በአካባቢው የሚገኙ ችግረኞችን ማገዝ ላይ አተኩረዋል። ከአንድ በሬ ጀምረው እስከ አምስት በሬ ድረስ በዓላት በመጡ ቁጥር እያረዱ ቅርጫ እንዲወስዱ አድርገዋል። በሃይማኖታችን ጉርብትና ከሥጋ ዘመድ በላይ ነው። በዚህም ነው ይህንን እንዳደርግ የሆንኩት ይላሉ። ስለዚህም የአገር አበርክቷቸውን የጀመሩት ሰውን በመርዳት ነበር። ከዚያ ከአጎታቸው ልጅ ጋር በመሆን በትውልድ ቀያቸው የተለያዩ ለማህበረሰብ ጥቅም የሚውሉ ተግባራትን አከናውነዋል። በዋናነት የሚያነሱት ግን ሶስት ነገሮችን ሲሆን፤ የመጀመሪያው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት እንደርሳቸው ያልተማረ እንዳይኖር ለማድረግ በተወለዱበት አካባቢ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ክፍል ትምህርት ቤት ገንብተው ማስረከባቸውን ነው። መንገድም ቢሆን አሰርተዋል። ድልድዮችንም አሁን ድረስ እያሰሩ ይገኛሉ። በተጨማሪ አንድም ቀን ንጹህ የመጠጥ ውሃ አግኝቶ የማያውቀውን ማህበረሰብ በእድሉ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ።

ቤተሰብ ‹‹ቤተሰብን ሳስብ ለምን አመለጡኝ የምላቸው ብዙ ነገሮች ይፈጠሩብኛል። በሥራዬ ምክንያት ቤተሰቤ እንዳይርበውና እንዳይጠማው እጥራለሁ እንጂ ከእኔ ጋር በሚያሳልፈው ነገር ይጠቀማል ብዬ ብዙ አላስብም ነበር›› ይላሉ የዛሬ እንግዳችን። ሆኖም ኮሮና መጥቶ ቤት መዋል ስጀምር በቤት ውስጥ ብዙ ያላየኋቸው ደስታን የሚፈጥሩላቸው ነገሮች እንደነበሩ መታዘባቸውንም ይናገራሉ። መጀመሪያ አካባቢ እንዲህ ሥራ ሳይበዛባቸው ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ሲያደርሱ ያገኟቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ቀረቤታችን በእጅጉ የተራራቀ ነው። በዚህም እንዳጎደሉባቸው ይሰማቸዋል። ትንሹን ልጃቸውን ግን ከ10ኛ ክፍል በኋላ በደንብ ተከታትለውታል። ኮሮና ደግሞ ይበልጥ አስተ ዋውቆናልም ይላሉ። ቁጣን ከአባቴ ወርሻለሁ የሚሉት እንግዳችን፤ የማይመስለኝን ነገር ሰዎች ሲያደርጉ ካየሁ ዝም አልልም ይላሉ። በዚህም ልጆችም ሆኑ ሰራተኞች ከስህተታቸው እንዲታረሙ ይገስፃሉ። ቁጣዬ ግን ጊዜያዊ መሆኑም ሁሉም ይረዱኛል ይላሉ። እናም አሁን ላይ ለማህበራዊ ህይወት ጊዜ መስጠት እንደሚያስፈልግ በመረዳታቸው ብዙ ነገሮች ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን ይገልፃሉ። በዚህም ቤተሰቤ ተደስቷል ብለውናል። የስምንት ልጆች አባትና የአስራ አንድ ልጆች አያት የሆኑት አቶ ሳቢር፤ ልጆቻቸው ሁሉም በሚባል ደረጃ የእርሳቸውን ፈለግ ተከትለዋል። ከእርሳቸው የሚለዩት ሁሉም ተምረው በቂ የተባለ እውቀትን ከገበዩ በኋላ በንግድ ዓለም ውስጥ መሰማራታቸው ነው።

መልዕክት ሰው አላማ ሊኖረው ይገባል ይላሉ አቶ ሳቢር። የሚደርስበትን ማወቅ እንዳለበትም እንደዚሁ። ሰውን አላህ ሲፈጥረው ሁሉን ነገር አመቻችቶለት ነው። እርሱ መስራት የሚችለውንም ነገር አሳይቶታል፤ እድሉንም ቸሮታል። ይህንን አምኖ ደግሞ መስራቱ የሰውዬው ሃላፊነት ነው። ምድር ለቆ እንደሚሄድ ማመን አለበት። ለዚህም የገባው ማስተማር ያልገባው ደግሞ ለመረዳት መሞከር ይኖርበታል የሚል መልክት ያስተላልፋሉ። ‹‹ተርፎት የሚሰጥ ማንም የለም። ስለዚህም ካለው ላይ መስጠትን ልምድ ማድረግ ይገባል›› በማለትም ከዚህ የሚልቀው ደግሞ ሥራን መፍጠር መሆኑን ከልምዳቸው በመነሳት ይመክራሉ። ይህ ሃሳባቸው እውቀትና ገንዘብ የተራራቁ በመሆናቸው ማቀራረብ ይገባል ከሚል ይመነጫል። ከራስ በላይ ለሰው መኖርም ይገባል በማለት ሃሳባቸውን ይቋጫሉ።

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 10

ባህልና ቱሪዝም

ፊቼ ጫምበላላ - ከአደባባይ ወደ ቤት አብርሃም ተወልደ

የፊቼ በዓል በአፈ ታሪክ አቶ ገነነ አበራ ስለ በዓሉ ከአፈታሪኩ ተነስተው እንደተናገሩት የፊቼ በዓል መጠሪያውን ያገኘው ፊቾ ከምትባል የሲዳማ ሴት ነው። ፊቾ ዕድሜዋ ለአቅመ ሔዋን ሲደርስ በሲዳማ ብሔር ባህልና ሥርዓት መሠረት ተዳረች። ይህች ሴት በየዓመቱ ለወላጆቿ፣ ወንድሞቿ፣ ለዘመድ አዝማድና ጎረቤት ቡርሰሜ (ከእንሰት ላይ የሚፋቅ ቆጮ በእሳት ላይ ተነኩሮ እና ቅቤ በብዛት ተጨምሮበት የሚዘጋጅ ባሕላዊ ምግብ) እና እርጎ በመያዝ በየዓመቱ በሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሚውልበት ዕለት በቋሚነት ትጠይቃቸው ነበር። በዓሉ የሚውለው በተመሳሳይ ቃዋዶ (በሲዳማ ብሔር የቀን አቆጣጠር የሳምንቱ የመጀመርያ ቀን) ሲሆን በአፈ ታሪኩ መሠረት ፊቾ ያመጣችውንም ምግብ በዚሁ ዕለት ምሽት ላይ ዘመድ አዝማድ፣ የአካባቢ ጎረቤትና ቤተሰብ ተሰባስበው ይመገቡት ነበር። አባቷና ታዳሚዎች ዘወትር የፊቾን ደግነትና ያመጣችውን ምግብ በማድነቅ ይመርቋታል። ፊቾ ይህንን በተደጋጋሚ ስትፈጽም ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ የአካባቢው ነዋሪዎች ፊቾ በመሞቷ ጥልቅ ኀዘን ተሰማቸው። ከዚህም በላይ የእሷ ድግስ ታዳሚ የነበሩ ሰዎች ይህችን ሩህሩህ ደስታ ፈጣሪ ሴት በዘላቂነት ለማስታወስ ቀደም ሲል እርሷ ምግብ ይዛ የምትመጣበትንና ግብዣው የሚካሄድበትን የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ቀን በስሟ ፊቼ ብለው ሰየሙት። የፊቼ በዓል ሁሌም በቃዋዶ ቀን የሚውልበት ምክንያት ቀኑ በብሔሩ የሳምንቱ የመጀመሪያውና ታላቅ ቀን ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ነው። በበዓሉ ሁሉም ሰው የሚያርፍበት ነው። ከብቱም ሳይቀር እናት ከጥጃዋ የምትውልበት ቀን ነው። የተጣላ ካለም ፍቼ ጨምበላላ ማለትም አዲስ ዓመት ሳይገባ ይቅርታ መጠያየቅ ግዴታው ነው። የተፋቱ ባል እና ሚስት ቢኖሩ እንኳን በዋዜማው ቀን ተጣልታ የወጣችበት ቤት የቀድሞ ባሏ ጋር ሄዳ እርቅ ማድረግ ይገባታል። ይሄ የሚደረገውም በዓሉ የእርቅ የሰላም በዓል ነው ተብሎ ስለሚታሰብ መሆኑን ይናገራሉ።

ማኅበራዊ ክንዋኔዎች አቶ ገነነ በበዓሉ የሚከወኑ ተግባራትን ሲዘረዝሩ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ለሁለት ሳምንታት ያህል በድምቀት የሚከበር ሲሆን አከባበሩም ቅደም ተከተላዊ ሥርዓትና ሒደት ያለው ነው። ከእነዚህ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች መካከል የመጀመርያው ላኦ ወይም ምልከታ ነው። የፊቼ በዓል ሁሌም በብሔሩ የሳምንቱ የመጀመርያው ቀን ማለትም በቃዋዶ ቢውልም ቀኑ በየዓመቱ በተመሳሳይ ቀን ስለማይውል መቼ እንደሚውል ተለይቶ የሚታወቀው በባህላዊ ቀን ቆጠራ ስሌትና የሥነ ክዋክብት ምልከታ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የሥነ ክዋክብት ምልከታውን የሚያከናውኑት አያንቶ የተሰኙ የሥነ ክዋክብት ጠበብቶች ናቸው።

አያንቶዎች ቡሳ የተሰኙ ኅብረ ክዋክብት ከጨረቃ አቀማመጥ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማገናዘብ ማለትም የክዋክብቱ ከጨረቃ የመቅደምና ወደ ኋላ የመቅረት ሁኔታ በትኩረት በመከታተል በተለይ ከክዋክብቱ መካከል አውራ የሆነችው ኮከብ ከጨረቃ መቅደሟን ሲያረጋግጡ ፊቼ በቀጣይ ቀናት ውስጥ ባለው የቃዋዶ ዕለት እንደሚውል እንደሚወስኑ አቶ ገነነ ይናገራሉ። ከዚያም የሥነ ክዋክብት ምልከታውን የሚያከናውኑት አያንቶዎች የፊቼ በዓል የሚውልበትን ቀን ለጎሳ መሪዎች ወይም ገሮ ያሳውቃሉ። አያንቶዎች ባቀረቡት ሐሳብ ላይ ተመስርተው የጎሳ መሪዎች ከጪሜሳዎች ወይም የበቁ አረጋውያን ጋር ሶንጎ ወይም የአዛውንቶች ስብሰባ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ በኋላ ቀኑ በአዋጅ ለኅብረተሰቡ እንዲገለጽ ከስምምነት ይደርሳሉ። የጎሳ መሪዎችም በየአካባቢያቸው በሚገኙ የገበያ ሥፍራዎች የበግ ቆዳ ረዥም ዘንግ ላይ ሰቅለው በመያዝ ለኅብረተሰቡ የፊቼ በዓል የሚውልበትን ቀን ያውጃሉ (ላላዋ ያደርጋሉ)። ከላላዋ በኋላ ሳፎቴ ቄጣላ (የመጀመርያው ባህላዊ ጭፈራ) ይቀጥላል። ዋናው ክብረ በዓል ከመከበሩ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ከዋዜማ ጀምሮ እንኳን አደረሰህ እንኳን አደረሰሽ መባባል ይጀመራል። በዓሉም ቢሆን መከበር የሚጀመረው ከዋዜማው ቀን ጀምሮ ሲሆን እስከ ሁለት ሳምንትም ይቀጥላል። በበዓሉ ዕለት እንዲሁም በቀጣይ ቀናት የሚከናወኑ ተግባራትን አቶ ገነነ ሲያስረዱ “ሁሉቃ” በመባል የሚታወቀው ደግሞ ማንኛውም ችግር ይሁን ቅራኔ

የሚተውበት እርቅ የሚደረግበት በዳይ እና ተበዳይ በፍቅር በመተቃቀፍ ሰላም የሚያወርዱበት ነው። በአጠቃላይ “ሁሉቃ” ያለፈውን በመተው የወደፊት የማየት ተምሳሌት ነው። ሌላኛው ክዋኔ ደግሞ ይላሉ አቶ ገነነ በታዋቂው የብሔረሰቡ መለያ በሆነው “ሻፌታ” ዋንጫ መሰል የመመገቢያ ቁስ ዙሪያ ልጅ አዋቂ፤ ሠራተኛ አሠሪ፣ ታላቅ ታናሽ የሚባል ሳይኖር ሁሉም በእኩልነት በመሰብሰብ ባህላዊ ምግብ የሆነውን ቡርሳሜ የሚቋደሱበት ነው። በማህበረሱቡ በጉጉት የሚጠበቀው ሌላኛው ደግሞ “ጉዱማሌ” ወይም አደባባይ በመውጣት የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች የሚከናወኑበት ነው ይህም ስብስብ ሁሉም በአንድነት የሚገኝበት ማንም የማይከለከልበት ሁሉም በእኩል የሚደሰትበት ክዋኔ ነው።

ፍቼ ጨምበላላ በዘመነ ኮሮና በዚህ ዘመን የፊቼ ጨንበላላ አከባበር ምን እንደ ሚመስል እንዴት እንደሚከበር ለህዘብ ግንኙነቱ ላነሳንላቸው ጥያቄዎች ሲያስረዱ በዓሉ በባህሪው የህብረት እና የአደባባይ ባህል እንደሆነ ጠቅሰው የተከሰተው ወረርሽኝ ደግሞ በህብረት ሰብሰብ ማለትን የሚከለክል ነው። የበዓል አከባበሩን በህብረት አሻፈረኝ ተብሎ ቢደረግ ደግሞ ዋነኛ የቫይረሱ የመተላለፊያ መንገድ አካላዊ እርቀትን አለመጠበቅ በመሆኑ ህዝባችንን ለዚህ በሽታ እንደ መጋበዝ ይሆናል። በተለይ ዘንድሮ ዞኑ ክልል ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ከተከበረውም በላይ ሁሉም የሲዳማ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ሊያከብረው ተዘጋጅቶ እንደነበር አቶ ገነነ

አውስተው በኮሮና ወረርሽኙ ምክንያት ግን አይደለም በድምቀት ሊከበር ቀድሞ እንደነበረው ማክበር አልተቻለም። እንደ ህዝብ ግንኙነቱ ገለጻ አያን ቶዎች ወይም አባቶች በወሰኑት መሰረት በአገር ላይ አንድ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ሲከሰት በዓሉ ከአደባባይ ወደ ቤት ይመለሳል። ልክ እንደ ዘንድሮ በዓል አከባበር ሁሉ ከዛሬ 40 ዓመት በፊት አገር ላይ በተከሰተ አደጋ ምክንያት በቤት ውስጥ ፊቼ ጨንበላላን ለማክ በር ማህበረሰቡ ተገዶ እንደነበር ያስታ ውሳሉ። ዘንድሮም በዓሉ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ መከበር አልተ ቻለም። ነገር ግን በዓላዊ ስነስርዓቱ አንዱም ሳይጓደል ማህበረሰቡ በቤቱ እያከበረ ይገኛል። ለዚህም የአባቶችን የመንግሥትንና የጤና ባለሙያ ምክር በመስማት ማህበረሰቡ ቤት በመሆን እያከበረ መሆኑንም ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በየወረዳው እየዞሩ ምልከታ እንዳካሄዱም አቶ ገነነ ገልጸዋል። በዓሉ የአንድ ወይም የሁለት

ቀን አለመሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣዮቹ የበዓሉ ቀናቶች ጥንቃቄ መደረጉ እንደሚቀጥል አክለዋል። ማህበረሰቡ ለአባቶች ሃሳብ እና ስልጣን የሚገዛ መሆኑን አቶ ገነነ ይናገራሉ። ትዕዛዛቸውን አልቀበልም፣ አሻፈረኝ አልታዘዝም ካለ ደግሞ አባቶች ቅጣት ይጥሉበታል። ቅጣቱም ከህብረተሰቡ እስከ መገለል የሚያደርስ ነው። ማንኛውም ህብረተሰብ ፣ ቤተሰብም ሆነ ግለሰብ በማህበር፣በመረዳዳት ውስጥ የኖረ ስለሆነ ከማህበረሰብ መገለል አይፈልግም ፤ስለዚህም ይላሉ አቶ ገነነ የአባቶችን ስልጣን በመጠቀም ወረርሽኙ በህብረተሰቡ ዘንድ እንዳይስፋፋ እንደ ፊቼ ጨንበላላ ያሉ አካላዊ መቀራረብን ከሚፈጥሩ ማህበራዊ ክዋኔዎች እንዲርቁ በማዘዘም ፣ በማስጠንቀቅም፣በማስተማርም በዓሉ እንዲከበር እየተደረገ ነው። አቶ ገነነ በመጨረሻም እንዳሉት በሚመጡት ዓመታት ብዙ በዓላትን ለማክበር እንዲህ ያሉ ፈታኝ ጊዜያትን በትዕግስትና የአባቶችን ምክር በመስማት ማለፍ ያስፈልጋል። የሲዳማ ህዝብም ለአባቶች ሃሳብ እና ምክር የሚገዛ ጨዋ ማህበረሰብ በመሆኑም በዓሉን ከአደባባይ ወደ ቤት በመውሰድ ነው ያከበረው። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት ፣የባህልና የሳይንስ ድርጅት(ዩኔስኮ) ፊቼ ጨምበላላን በሰው ልጆች የማይዳሰሱ ወካይ ቅርሶች ውስጥ የመዘገበው በ2008 ዓ.ም ኅዳር ወር ላይ መሆኑ ይታወሳል። ዘመን መለወጫው የጤና ፣የሰላም፣ የይቅርታ፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን እንመኛለን። ‹‹ አይዴ ጨምበላላ ›› ሰላም!!

«ዘመን የሰው ልጆች የታሪክ፣ የማንነት፣ የባሕል፣ የሥነ ልቡና እና የህልውና መከተብያ፣ መሳያ፣ መበየኛ፣መንደፍያ እና ማቆያ ትንግርታዊ ሰሌዳ ነው። ይህንን ድንቅ ሸራ በመቁጠር በመቀመር በማስላት እና በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ የሚዘወርበትን ሥርዓት በመዘርጋት የሚጠቀምበት ማኅበረሰብ ደግሞ እርሱ ከዘመን ጋር የማይሄድ ከዘመንም ጋር የማይመጣ በዘመን ገላ ላይ ትናንት በአባቶቹ ዛሬ በራሱ እና ነገም በልጆቹ ህያው የሚሆን ታላቅ ሕዝብ ነው። የሲዳማ ሕዝብ ይህን ታላቅ የሥልጣኔ አበርክቶ አጥሮ፣ ጠብቆ አቆይቶልናል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተናገሩት እንደመግቢያ እንዲሆነኝ ንግግራቸውን ተውሻለሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸው በዓላት ተወዳጅ ከሆኑት ውስጥ የዘመን መለወጫ በዓል አንዱ ነው። እንደ ዕፅዋት ሁሉ ሰው በመስከረም ላይ በተስፋ ስሜት ይለመልማል። ከዋዜማ ጀምሮ በየቤቱ ጨፌና ቄጠማ ይጐዘጐዛል። አበባ በሥርዓት እየተዘጋጀ በየቦታው ይቀመጣል። በተለይም ልጆች አዳዲስ ልብሳቸውን ለብሰው በደስታ ይፈነድቃሉ። የሚያበሩት ችቦና የሚያነዱት እሳት በግርማ ምሽት ሲንቀለቀል ውጋገኑ ከአገር አገር ከሰፈር ሰፈር ከቦታ ቦታ... ይታያል። ይህ የዘመን መለወጫ በዓል ግን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል በተመሳሳይ ወራት እና ስነስርዓት አይደለም የሚከበረው። የተወሰኑ ቦታዎች በተለይም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች አከባበሩ ይለያል። የዘመን መለወጫ በዓሎቻቸው ከሚለዩባቸው መካከል የሲዳማ ዘመን መለወጫ አንዱ ነው። «ፊቼ ጫምባላላ» በመባል የሚታወቀው የሲዳማዎች የዘመን ቀመር በከዋክብት ዑደት ላይ የተመሠረተ ነው። ብርሃናቱ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትም የተፈጠሩት ስለ አራት ነገሮች መሆኑንም ኦሪቱ ያብራራል። ለምልክቶችና ለዘመኖች፣ ለዕለታትና ለዓመታት በማለት። ትውፊታዊውና ኦሪታዊው መጽሐፍ ስለ ብርሃናት ተፈጥሮ ይገልጻል። ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ በሰማያት ብርሃናት ተደረጉ ይለናል። ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በማታ እንዲገዛ ከዋክብትንም ፈጠረ ሲል ያክልበታል። ምልክቶች ሲል በዓሎቹንና ጾሞችን፤ ዘመኖች ሲል አራቱን ወቅቶች ክረትምና በጋ፣ በልግና ፀደይን፤ ዕለታትና ዓመታት ሲልም እንደየትውፊቱ ያሉትን አቆጣጠሮች ማመልከቱ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን እና ጸሐፍቶች ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ብዙ ባህል ያላት አገር እንደመሆኗ ከዘመን ቆጠራ አኳያ በየአካባቢው ባሉ ነገሮች፣ ብሔረሰቦች የየራሳቸው መገለጫ የሆኑ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር አላቸው። ከእነዚህም መካከል የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት የመዘገበው የሲዳማ የዘመን አቆጣጠር ይገኝበታል። እኛም ስለበዓሉ ከመነሻው እስከ አሁን ድረስ ያለውን ጠቅላላ መረጃ ሊሰጡን የሲዳማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገነነ አበራ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ሽማግሌዎች የከብት ሞራ በመመልከት ቀጣዩን ዘመን ይተነብያሉ

11አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም

ቦጋለ አበበ

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ስፖርቶች በዓለም መድረኮች መታየት ከጀመረች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ተቆጥሯል። በእነዚህ ዓመት አገሪቱን ሦስት የተለያዩ መንግሥታት መርተዋታል። አንድ መንግሥት የሚከተለው ርዮተ ዓለም በአንድ አገር ላይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጽዕኖ የማሳደሩን ያህል በአንድ አገር ስፖርት ላይም የራሱ የሆነ አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎችን ማሳረፉ የግድ ነው። አንድ የፖለቲካ ስርዓት በስፖርቱ ላይ ብቻም ሳይሆን የስፖርቱ ዋና ተዋናይ የሆነው ግለሰብ ላይም ተመሳሳይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ እርግጥ ነው። የአንድ አገር የፖለቲካ ስርዓት በዲፕሎማሲ፤ በኢኮኖሚ፤ ልማትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ስፖርቱንና ስፖርተኛውን መንካቱ አይቀሬ ነው። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ አገራችን የምትከተለው የፖለቲካ ስርዓት በአገሪቱ ስፖርት ላይ የተለያዩ አዎንታዊና አሉታዊ ጎኖችን ማሳደሩ አልቀረም። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የነበረው የፖለቲካ ስርዓት ለአገራችን ስፖርት ካበረከታቸው አዎንታዊ ጎኖች አንዱ ከዲፕሎማሲ እውነታዎች አኳያ ይቀኛል። አገራችን ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከሌሎች አገሮች ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በላቀ መልኩ ማሻሻሏ የሚካድ አይደለም። ይህም በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች በተለይም መል ካም ስም ባላት የአትሌቲክስ ስፖርት ኦሊምፒክንና የዓለም ቻምፒዮናን በመሳሰሉ ታላላቅ መድረኮች የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራት የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ እኤአ ከ1956 ከሜልቦርን ኦሊምፒክ ጀምሮ በኦሊምፒክ መድረኮች ተሳታፊ መሆን ችላለች። ከእዚህ ጊዜ አንስቶ አስራ ሰባት ያህል ኦሊምፒኮች ቢካሄዱም ኢትዮጵያ በሁለቱ ተካፋይ መሆን አልቻለችም ነበር። እኤአ በ1984 አሜሪካ ሎሳንጀለስ ባስተናገደችው የኦሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያ በወቅቱ የሶሻሊዝም ርዮተ ዓለም ተከታይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በእዚህ ታላቅ መድረክ መካፈል አልቻለችም ነበር። ከአራት ዓመት በኋላም 1988 ላይ የአፓርታይድ ስርዓትን በመቃወም በሲዎል ኦሊምፒክ ላይ አልተገኘችም። ኦሊምፒክን በመሳሰሉ ታላላቅ የስፖርት መድረኮች በፖለቲካ ርዮተ ዓለም ልዩነት የተነሳ መካፈል አለመቻል አንድን አገር ከሜዳሊያ በዘለለ በርካታ ነገሮች እንደሚያሳጣ አያከራክርም። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ በሁሉም የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮናዎች ላይ ቀርታ አታውቅም። በእነዚህ ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ሜዳሊያ ከመሰብሰብ ባሻገር መድረኩን ተጠቅማ ገፅታዋን ለመገንባትና ራሷን ለማስተዋወቅ ጠቅሟታልም። በእነዚህ መድረኮች የዘወትር ተሳታፊ መሆኗም የአገሪቱን ስፖርት እንዲነቃቃና ስፖርተኛው ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል። አንድ ስፖርተኛ ራሱን በኦሊምፒክ መድረክ በማሳየት ዓለም አቀፍ ተጠቃሚነትን እንዲያገኝ ከሌሎች አገራት ጋር ያለን መልካም የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እዚህ ጋር ቁልፍ ሚና እንዳለው መገንዘብ ይቻላል። ስፖርተኞቻችን የግል ውድድራቸውን በሌሎች አገሮች ለማድረግ ወደ አንድ አገር በቀላሉ ለመግባት መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚኖረው አስተዋፅኦ ግልፅ ነው። ይህም ስፖርተኞች በተለይም አትሌቶቻችን በተለያዩ ዓለማት ተዟዙረው በስፖርቱ ያላቸውን ተሰጥኦ ተጠቅመው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ወገኖችና ለአገር ሲተርፉ እንድንመለከት አድርጓል። እዚህ ላይ የአገራችን አቪዬሽን ዘርፉ መዘመንና በበርካታ አገሮች ተደራሽ መሆን ለአትሌቶቻችን እንደ ልብ የፈለጉት አገር በረው የትራንስፖርት ጉዳይ ሳያሳስባቸው ጊዜና ገንዘባቸው ሳይባክን ውድድሮች ላይ እንዲገኙ ማስቻሉ መንግሥት በትራንስፖርት ልማቱ ያከናወነውን ተግባር ዋጋ እንድንሰጠው እንገደዳለን። ስፖርት በዘመናችን ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በሆነበት በእዚህ ወቅት አትሌቶቻችን በሌሎች አገሮች ላባቸውን አፍሰው ያመጡትን ገንዘብ አገራቸው ላይ ሠርተው እንዲለወጡበት መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቷቸው

ሁኔታዎችን በማመቻቸት ወደ ኢንቨስትመንቱ እንዲገቡ አድርጓል። በእዚህም በርካታ አትሌቶቻችን በሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህም ሁኔታ ስፖርተኞቻችን ወደ አደጉት አገራት ለውድድር ወጥተው ከመቅረት ይልቅ ያገኙትን ይዘው ተመልሰው ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ዜጎት እንጀራ ሲከፍቱ እንድንመለከት አድርጓል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የአንድ ህብረተሰብን አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ ምርታማነትን የሚያጎለብት፥ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና ያለው የዜጎች መሰረታዊ መብት እየሆነ መጥቷል። ይህን ልብ ያለው የ1990 ዓ.ም የተቀረፀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲ በየደረጃው መላውን ህብረተሰብ በስፖርት በማሳተፍ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ቀዳሚ ዓላማው አድርጎታል። ለዚህም መላው ህብረተሰብ በሚኖርበት፥ በሚሠራበት እና በሚማርበት አካባቢ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በየደረጃው ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል። የዚህን ፖሊሲ አቅጣጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተፈፃሚ ለማድረግ የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ፅንሰ ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1996 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው የኢፌዴሪ ስፖርት፤ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር የተጠነሰሰው። የኦሊምፒክና የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን መርህ መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በስፋት በማሳተፍ እና ተጠቃሚነቱን በማጎልበት የበርካታ ባህልና ትውፊቶች ባለቤት የሆኑ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በአንድ መድረክ ተገናኝተው የባህል እና ልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ታስቦ ፖሊሲው እንደተቀረፀ የመጀመሪያው የጥናት ሰነድ ላይ ተቀምጧል። ይህም አገራችን በምትከተለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን በማጠናከር በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ መተሳሰብ እና መቀራረብ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ታምኖበታል። በዚህም የአገራችን ስፖርት ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን ማየት ተችሏል። ዘመናዊና ግዙፍ ስቴድየሞች በየክልሉ መገንባታቸው፤ አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት አካዳሚና በተለያዩ ስፖርቶች የወጣት ፕሮጀክቶች መጀመራቸው የአገራችን ስፖርት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት የተጓዘባቸው መንገዶች ናቸው። የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለአገሪቱ ትልልቅ መሠረተ ልማቶችን አስገ

ኝቷል፡፡ ለውድድሩ ሲባልም ትልልቅ ስታዲየሞች በክልሎች ተገንብተዋል፡፡ በመገንባት ላይም የሚገኙ በርካታ ናቸው፡፡ በባህር ዳር፣ ሐዋሳና መቐለ የተገነቡት ዘመናዊ ስታዲየሞች ከመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አልፈው ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የሚያስተናግዱ ሆነዋል፡፡ አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያ የአፍሪካን ሁለተኛውን ትልቅ የእግር ኳስ ዋንጫ የ2020 አፍሪካን ኔሽን ቻምፒዮን ሺፕ(ቻን) አዘጋጅነት ዕድል እንድታገኝ እነዚህ ስቴድየሞች ካፍን ማሳመን የቻሉበት አጋጣሚ ነበር(ባይሳካም)። ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በየሁለት ዓመቱ የሚካሄዱትን መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ እያሳዩ ያለው ፉክክር ወደ መጋጋል ደረጃ ለመምጣቱ አንዱ ማሳያ፣ ውድድሮችን ለማዘጋጀትና መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ ለመገኘት የሚያደርጉት ሽር ጉድ ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእነዚህ ስቴድየሞች ግንባታ ሂደትም በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፈጠሩ ባሻገር በግንታው ዘርፍ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሊንቀሳቀስ ችሏል። በዚህም የአገራችን ተቋራጮችን አቅም ከማሳደጉ በተጨማሪ በዘርፉ ትልቅ የእውቀት ሽግግር ሊደረግ ችሏል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ስቴድየሞች ግንባታ በብዙ መልኩ የሚነሱ እንከኖች የሉም ማለት አይደለም፡፡ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታም ቢሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታለመለትን ዓላማ ስቶ ወዳልተፈለገ እኩይ ተግባር መቀየሩና የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ በእነዚህ ዓመታት በአገራችን ስፖርት ከታዩ አንኳር የሆኑ አሉታዊ ጎኖች ዋነኛው ከአትሌቲክስ ስፖርት ውጪ ሌሎቹ ስፖርቶች መዳከማቸውና እድገት አለማሳየታቸው ይጠቀሳል። ለእዚህም በርካታ ምክኒያቶች ይቀመጣሉ። ቀደም ሲል አንድ ክለብ ሲቋቋም ያደገ ወይንም ተከታይ ያለው ስፖርት ብቻ ይዞ መቋቋም አይችልም። ይህ ማለት አንድ እግር ኳስ ክለብ ለማቋቋም ሌሎች ከአምስት ያላነሱ ስፖርቶችን ማቀፍ የሚያስገድድ ሁኔታ ነበር። ይህም አንድ ስፖርት ብቻ ተነጥሎ እንዳያድግና ሌሎች ያላደጉ ስፖርቶች ተያይዘው እንዲያድጉ የሚያስችል ነበር። አሁን ላይ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በመቅረቱ በርካታ ክለቦች የፈለጉትን ስፖርት ብቻ ይዘው በመጓዛቸው በርካታ ስፖርቶች ሲወድቁ እንመለከታለን። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ከአትሌቲክስና እግር ኳስ በተጨማሪ ቮሊቦል፤ ቅርጫት ኳስ፤ እጅ ኳስና ሌሎች ስፖርቶች ከሌሎች አገሮች ጋር ተፎካካሪ ነበረች። አሁን ላይ ይህ ገፅታ ተቀይሮ ከእግር ኳስና አትሌቲክስ ውጪ ባሉት ስፖርቶች እንኳን ወደ ውጭ አገር ሄደን ጠንካራ ተፎካካሪ ልንሆን በአገር ውስጥም ጠንካራ እንቅስቃሴ ሲደረግባቸው ለማየት ተቸግረናል።

በስፖርት መሰረተ ልማቶች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ እየሆኑ ቢመጡም በአገራችን ስፖርት መሰረት የሆኑ የተለያዩ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ሕንፃና ቤት ተሠርቶባቸው እናገኛለን። ይህም በምንታወቅባቸው በተለይም በእግር ኳስ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚወጡ ተጫዋቾችን እንድናጣ ማድረጉ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች የሚስማሙበት ነው። በሌላ በኩል የሚታየው አሉታዊ ጎን ከአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቢሆንም ወደ ፊት ትኩረት ተደርጎ ሊሠራበት የሚገባ አብይ ጉዳይ ነው። ለበርካታ ስፖርቶች መዳከም ዋነኛ ምክኒያት የፌዴሬሽኖች የገንዘብ አቅም ማነስ ነው። መንግሥት ለስፖርት ኮሚሽን ከሚበጅተው ገንዘብ ተመፅዋች ሆነው እንደልብ መራመድ የከበዳቸው አገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጥቂት አይደሉም። እነዚህ ፌዴሬሽኖች ውድድሮችን ለማካሄድ ስፖርቱን ለማሳደግ አንድና አንድ ችግራቸው የገንዘብ አቅም ነው። እነዚህ ፌዴሬሽኖች የመንግሥት እጅ ከመጠበቅ ይልቅ በራሳቸው የገንዘብ አቅማቸውን ለማጠናከር መሥራት እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል። ይሁን እንጂ እነዚህ ፌዴሬሽኖች ራሳቸውን በገንዘብ የሚያጠናክሩበት አቅም እስኪፈጥሩ ድረስ መንግሥት አሁን ከሚበጅትላቸው ገንዘብ በዘለለ ወጥ የሆነ አደረጃጀት ፈጥሮላቸው ዘላቂ የሆነ መስመር በመዘርጋት በኩል ክፍተቶች አሉ። መንግሥት ለፌዴሬሽኖች ዓሣ ከመስጠት ይልቅ ዓሣ የሚያጠምዱበትን ዘዴ ሊያስተምራቸውና መንገዱን ሊያሳያቸው ይገባል። እስከዚያው ድረስም አሁን የተሠሩት መሰረተ ልማቶች ከጋሪው ፈረሱ የቀደመ እንዳይሆኑ ዓመታዊ በጀታቸው ቢያንስ በርካታ ውድድሮችን በዓመት ውስጥ ማስተናገድ የሚያስችላቸውና በኋላ መሰረተ ልማቱ ተሟልቶ ስፖርቱ ኋላ እንዳይቀር በአንድ ላይ መጓዝ የሚያስችል መላ አልተፈጠረም፡፡ የአገራችን ስፖርት ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ በእንዲህ ዓይነት የቁልቁለት ጉዞ በመራመድ ዛሬ ላይ ደርሷል። ካለፈው መጋቢት 2010 ወዲህ አገሪቱ በአዲስ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባሆንም የለውጥ መንገድ ላይ መሆኗ አይካድም፡፡ ይህ የለውጥ ማዕበል በፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ገብቶ አገር በማረጋጋት የተጠመደ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል የስፖርቱን ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ ሲመለከተው አይስተዋልም፡፡ ሁሉም ነገር ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ሲመለስና የፖለቲካ ውጥረቱ ሲረግብ ግን የስፖርቱን የቁልቁለት ጉዞ ሽቅብ እንዲጓዝ የማድረግ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚጠብቀው ከወዲሁ ማስታወስ ግድ ነው፡፡

የሦስት አስርት ዓመታት የቁልቁለት ጉዞ

በስፖርቱ ዘርፍ በርካታ መሰረተ ልማቶች ቢገነቡም ስፖርቱ ማደግ ባለበት ደረጃ አላደገም፤

ስፖርት

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 12

ወንድወሰን ሽመልስ

የህዝቦች ብሶት የወለደው ትግል የሆነውን አገራዊ ለውጥ ተከትሎ በርካቶች በጋራ ተከባብረው የሚኖሩባት ለሁሉም የምትመች ህብረ ብሔራዊት አገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተባበረ አቅም ሲተጉ ይስተዋላል:: በአንጻሩ ላለፉት 27 ዓመታት በነበረው አገዛዝ ወቅት ህዝብ ይልቅ ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን ቅድሚያ ሰጥተው የሚኖሩ ኃይሎች ከለውጡ አጋዥነትና አባልነት ራሳቸውን ለማግለል ሲማስኑ መታዘብ ተችሏል:: ዛሬም ህዝብና አገር አንድም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተጨነቁ ባሉበት፤ ሁለተኛም ከህዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ በአገር ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ አደጋ እያንዣበበ ባለበት ሁኔታ ላይ ከአገርና ህዝብ ይልቅ የራስን ጥቅምና ስልጣን ለማስቀደም አጥብቀው ሲጥሩ እየታየ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ህወሓት አብይ ማሳያ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት ከህዝብ ይልቅ ለራስ ጥቅምና ስልጣን ሲል የህዝብን ጤና አደጋ ላይ ጥሎ ምርጫ ላካሂድ ማለቱ የዚህ እማኝ ምግባሩ ማሳያ ነው:: አሁን ላይ ይህ ተግባሩ ጎልቶ ይውጣ እንጂ ላለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው የለውጥ ጉዞ ውስጥ ከአጋዥነት ይልቅ የአደናቃፊነት ሚና እንደነበረው የሚታወቅ የአደባባይ ተግባሩ ነበር:: ለዚህ ተግባሩም ያግዙኛል ካልሆነም ልጠቀምባቸው እችላለሁ ብሎ ያሰባቸውን ኃይሎች መልምሎ በስልጣን ዘመኑ ከአገርና ህዝብ ጉሮሮ ነጥቆ ባካበተው ሀብት ለማጥመድ ሲሰራም ተስተውሏል:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል እንዲመሰረት በፋይናንስ ሲደግፈው የነበረው ስብስብ ነው፤ ይህ ስብስብ ግን የህወሓትን የሴራ ጉዞ በተረዳበት ወቅት የሀሳብ ልዩነት መፈጠሩ ተሰምቷል፡፡

እኛም በዛሬው እትማችን የዚህ ጥምረት ዓላማ ምን ነበር፤ የጥምረቱ ስብስብና የህወሃት የአጋርነት ጉዞ ምን ይመስላል፤ ዛሬ ላይ የጥምረቱና የህወሓት ትስስር በምን መልኩ ሊሻክር ቻለ፤ ጥምረቱ ዛሬ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና መሆን ስላለባቸው ጉዳዮች እንዲሁም ተያያዥ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር፤ እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ከሆኑት አቶ ደረጀ በቀለ ጉደታ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ይዘን ቀርበናል፡፡

አዲስ ዘመን፡- የፌዴራሊስት ኃይሎች ማን ነው? የስብስቡ ዓላማስ ምንድን ነው?

አቶ ደረጀ፡- የፌዴራሊስት ኃይሎች ማለት በመጀመሪያ ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የተሰባሰቡ 35 የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ አዲስ አበባን ጨምሮም ሶማሌን፣ አፋርን፣ ሐረሪን፣ ትግራይን፣ አማራን፣ ኦሮሞንና ሌሎችንም ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈ እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የዳሰሰ ነው:: በመጨረሻም ከእነዚህ 35 ፓርቲዎች ውስጥ ፍቃድ ለማግኘት ለምርጫ ቦርድ ያመለከትነው 25 ፓርቲዎች ናቸው:: ስለዚህ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ማለት የእነዚህ 25 ፓርቲዎች ስብስብ ነው፡፡

የመሰባሰባችን ዋና ዓላማ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በኢትዮጵያ አንድ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን፤ ለዚህም በጋራ ለመንቀሳቀስና በጋራ ለመስራት ብሎም በጋራ ለመታገል እና ለአንድ የምርጫ ክልል ተጋግዞ ለመወዳደር ነው:: ከዚህ ባለፈም አንዱ የሚያውቀውን ለማያውቀው እንዲያስረዳ የተሰባሰበ ስብስብ ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ጥምረት ምን መሰረታዊ አገራዊ አጀንዳዎችን ይዞ ነው የተሰባሰበው?

አቶ ደረጀ፡- ከአገራዊ አጀንዳዎቻችን መካከል የመጀመሪያው በአገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን መስራት ነው:: ከዚህ ባለፈም በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጭቆና ተላቅቀው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ብሎም እንዲያለሙ ማስቻልን መሰረት ያደረገ ነው። ይህ ደግሞ እንደዚህ ቀደሙ አመራር ተልኮላቸው ወይም ተሰይሞላቸው ሳይሆን

በራሳቸው እንዲሾሙ፤ በልማቱም ቢሆን በራሳቸው ሃብትና አቅም የሚለሙበትን እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ነው:: ለዚህ ደግሞ ሁሉም በራሱ ብሔርና ክልል የራሱን ፖለቲካዊ አጀንዳ መጫወት እንዲችል፤ ያንን ደግሞ በጋራ አምጥተን በአንድ ማዕከል በኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ስር ለማስተባበርና ለመምራት እንዲቻል ያለመም ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ጥምረቱ አገራዊ ወይስ ክልላዊ ገጽታን የተላበሰ ነው? ምናልባት እንደ ዓላማውና አጀንዳዎቹ አገራዊ ከሆነ የፌዴራሉን መንግስት መቀመጫ አዲስ አበባን ትቶ መቐሌ ላይ ምስረታና ጉባኤውን ማካሄዱ ለምን አስፈለገ?

አቶ ደረጀ፡- ስብስቡ አገራዊውንም ክልላዊውንም ገጽታ የተላበሰ ነው:: ለምሳሌ፣ ሕወሃትን ጨምሮ የእኛም ፓርቲ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ክልላዊ ፓርቲ ነው:: ሌሎች አዲስ አበባ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉ አገራዊ ፓርቲዎችም አሉ:: ይህ የ25 ፓርቲዎች ተናጥላዊ ገጽታ ሲገለጽ ነው:: ነገር ግን የእነዚህ ስብስብ የፈጠረው ጥምረት ግን አገራዊ ገጽታን ተላብሶ የሚንቀሳቀስ ነው:: ጥምረቱ ለምስረታውም ሆነ ለጉባኤው መቐሌን የመረጠበት ምክንያት ነበረው፡፡

ምክንያቱም እነዚህ ፓርቲዎች ራሱ ህወሓት ያጫቸው ናቸው:: የራሳቸው የሆነ ፋይናንስም የላቸውም:: ማናኛውም የፓርቲው አባል ራሱን ከማንቀሳቀስ በተረፈ ሌሎችንም ሆነ ህዝቦችን አንቀሳቅሶና አዳራሽም ተከራይቶ የአበልና ትራንስፖርትም ከፍሎ ማንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ አለ:: ለዚህ የገንዘብ ፋይናንስ አቅም ያለው ህወሓት ነው:: ህወሓት ለትራንስፖርት፣ ለሆቴል፣ ለምግብ ሆነ ለሌሎች ሎጅስቲክ አገልግሎቶች የሚሆን አቅም ስላለውና እሱው ስለጠራን ነው እዛው ጀምረን፣ ሁለት ስብሰባዎችን መቐሌ ያካሄድነው:: መቐሌ መሰባሰብ ያስፈለገንና እዛው እንድናዘልቅም አስገዳጅ የሆነብን የፋይናንስ ምንጫችን ህወሓት ስለሆነ ነው፡፡

ይህ ደግሞ የአባላቱ የፋይናንስ አቅም ማጣት ውጤት ሲሆን፤ እኛ ወደመቐሌ ስንሄድ የአውሮፕላን ትኬት ተልኮልን፣ ሆቴል ተይዞልን፣ ሌሎችም አስፈላጊ ወጪዎች ተሸፍነውልን ነው:: በዚህም ጅግጅጋም፣ አዲስ አበባም፣ አፋርም፣ ድሬዳዋም፣ ሐዋሳም፣ ወላይታም፣ ጅማም ሆነ ሌሎች ቦታዎች ላሉ ሁሉ የአውሮፕላን ትኬት ባሉበት እየተላከ፤ ሁሉንም ወደ መቐሌ በመውሰድና ወጪያቸውን በመሸፈን ነው ስብሰባው የሚካሄደው:: በዚህ መልኩ የሁሉንም ፓርቲዎች አበል፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ ምግብና ሌሎችን ወጪዎች የሚሸፍነው ህወሓት ነው፤ እርሱ ሁሉም ነገር መቐሌ እንዲካሄድ ስለሚፈልግ ነው መቐሌ ላይ የሆነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በዚህ መልኩ ተሰባስባችሁ ጥምረት ፈጥራችሁ ስትሰሩ የጋራ የሆነ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች የፓርቲ ሰነዶች ነበሯችሁ? በዛ መሰረትስ በምን መልኩ ትሰሩ ነበር?

አቶ ደረጀ፡- የጋራ የሆነ መመሪያ፣ ደንብና ማኒፌስቶ አለን:: ፍቃድ እንዲሰጠን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ያቀረብነው ሁሉንም ነገር አሟልተን ነው:: ይሄንንም በስብስቡ ስም አደራጅተንና በዛ ላይም ተወያይተን አጽድቀንም ነው:: እያንዳንዱ ፓርቲ በራሱ ማህተምና በራሱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጽድቆም ነው ያቀረብነው:: ምርጫ ቦርድም ጥያቄያችንን ተቀብሎና የሚመረምረውን መርምሮኖ በ25ቱ ፓርቲዎች አማካኝነት መመስረት እንደሚቻል ባቀረበው ግብረ መልስ መሰረት እኛም መልስ ሰጥተን ፈቃዱን እየተጠባበቅን ባለንበት ወቅት ነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥቶ ሂደቱን ያጓተተብን:: ወደ ጉዳዩ ስመለስ ግን እንደ ስብስብ የምንሰራውም ሆነ የምንመራው በእነዚህ ሰነዶች መሰረት ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በዚህ መልኩ በሰነዶች ታግዛችሁ የምትሰሩ ከሆነ መቐሌ ካለው የህወሓት ስብስብ ጋር ያላችሁ አጋርነት በምን መልኩ የሚገለጽ ነው? በዚህ ትብብርስ ምን ያክል ተጉዛችኋል?

አቶ ደረጀ፡- መቐሌ ካለው የህወሓት ስብስብ ጋር ያለን አጋርነት በፋይናንስ ነው:: ሌላ ነገር የለም:: ህወሓት አዳራሽ

እንቀሳቀስ ስንል ፋይናንሱንም ዝም አሉን:: ቢሮ መክፈትም ከተማውን ሙሉ በሙሉ ዞረናል፤ ሆኖም በተለያየ ምክንያት በዛ አነሰ በሚል ሰበብ እስካሁን ቢሮውንም አልከፈትንም፡፡

በዚህ ምክንያት ብዙ መራራቆች እየተፈጠሩ መጡ:: ይሄን ተከትሎም በህወሓት በኩል ሰዎችንና ፓርቲዎችን መለያየት መጣ:: ፓርቲዎችን በመለያየት ሂደትም መጀመሪያ አቅፈው የያዙትና ገንዘብም ሊሰጡ የፈለጉት ከትግራይ የተወከሉትን የፓርቲ አባላት ነው:: ቀጥሎ ደግሞ ከአዲስ አበባ የተወከሉ አንዳንድ ፓርቲዎችን አቅፈው ለመያዝ ሞከሩ:: ከኦሮሞ ያሉት በፊቱንም እየተንጠባጠበ ወደ ስድስት የማንሞላ ብቻ ቀርተን ስለነበረ እነዚህንም ለመበታተን በእኔ ላይ ጫና ለመፍጠር ሞከሩ:: ይህ ደግሞ እኔ ሰብሳቢ ስለሆንኩ ሲሆን፤ ስብሰባው መቐሌ ካልሆነ በስተቀር አዲስ አበባ ላይ ጽህፈት ቤትም ሆነ ስብሰባም አይቻልም በሚል ነበር፡፡

ይህ ደግሞ የማይሆን ነበር:: ምክንያቱም ለምሳሌ፣ እኔ መኖሪያዬ አዲስ አበባ ነው፤ የወከልኩትም የኦሮሞን ህዝብ ነው:: ስለዚህ መቐሌ መኖርም ሆነ በመቐሌ ስብሰባ ማካሄድ አልችልም:: ሌሎቹም በተመሳሳይ የየክልላቸውን ህዝብ ወክለው ያሉ እንደመሆኑ መቀመጫቸውን መቐሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ማድረግ የሚፈልጉ በመሆኑ ማዕከሉ አዲስ አበባ እንዲሆን ነው የሚፈልጉት:: በመሆኑም የነበረው አቋም ማዕከሉ አዲስ አበባ ሆኖ ስብሰባውም አዲስ አበባ ይሁን፤ ስብሰባውን በዙር ክልል ላይ የሚደረግ ከሆነም መቐሌ ብቻ ሳይሆን፡ ሀዋሳም፣ ሰመራም፣ ጅግጅጋም፣ በህር ዳር እና ሐረርም እያልን ማካሄድ አለብን የሚል ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ እንደ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት እናንተ (ህወሓቶችን) አንድ ፓርቲ ናችሁ፤ ሆኖም ለምሳሌ፣ ከሶማሌ ሶስት ፓርቲ አለ፣ አፋር ወደ ሁለት አሉ፣ ከኦሮሚያ ወደ ስድስት አሉ፣ እናም ማዕከላችንን አዲስ አበባ ካላደረግን እኔ ወደዛ አልመጣም በሚል የሀሳብ ልዩነት ተፈጠረ:: እኛም ይሄን መሰረት አድርገን ከባለሃብቶች ገንዘብ አግኝተን ስብሰባ አዲስ አበባ ስንጠራ ነው የበለጠ ልዩነቱ ሊፈጠር የቻለው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ህወሓቶች ከመቐሌ ውጪ በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት እንዳይከፈትም ሆነ ስብሰባ እንዳይካሄድ ያልፈለጉበትን ምክንያት ጠይቃችኋቸዋል? ምክንያታቸው ምንድን ነበር?

አቶ ደረጀ፡- በምክንያትነት የሚያቀርቡት ነገር የለም:: ከእነርሱ አኳያ እንዲሁ እንደተረዳሁት ከሆነ ግን ፍርሀት ነው:: ለምሳሌ፣ እኛ ይሄ ጥምረት በፓርቲ ሊቀመናብርት መመራት አለበት ነው የምንለው:: ስብሰባ ሲኖር ደግሞ ከሊቀመናብርት ባለፈ ከአባላትም እስከ ስራ አስፈጻሚ ድረስ የሚሰበሰቡበት ጊዜ አለ:: በስራ አስፈጻሚ ሲሰበሰቡ ደግሞ ዶክተር ደብረጽዮንን ጨምሮ እዛ ያሉት ሁሉም ናቸው መሰብሰብ ያለባቸው:: ጽሕፈት ቤቱ እዚህ ከሆነም ሊቀመንበሩ ናቸው እዚህ መሳተፍ ያለባቸው:: ይህ ሲሆን የመፍራት ጉዳይ ካልሆነ፤ በሌላ ምክንያት ለምን መሳተፍ

ፎቶ

ዳኜ

አበራ

ይከራይልናል፤ የምግብ፣ ትራንስፖርትና አበል ይችለናል:: ከዚህ ውጪ ሚስጢራቸውን ለእኛ በተለይም ከመሀል አገር፣ ከወደ ምስራቅ እና ከምዕራብም ለሄዱት በግልጽ አያስቀምጡም:: እናም የእነርሱ አጋርነት በፋይናንስ ረገድ ነው:: እስካሁንም የቆየነው በፋይናንስ አጋርነታቸው ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከፋይናንሱ ባለፈ ወደ መቀሌ ስትሄዱ ዓላማና አጀንዳ አድርጋችሁ በሄዳችሁባቸው ጉዳዮች ላይ ያላችሁ አጋርነትስ እስከምን ድረስ ነው?

አቶ ደረጀ፡- ለጋራ ግብ ብለን የሄድነው፣ እኛ እንግዲህ መጀመሪያ እንደጠቀስኩት በአገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ለማምጣት፤ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ማስቻልን እቅድ በማድረግ ነበር:: ይሁን እንጂ የህወሓት ፍላጎት የጋራ ዓላማችንን ሳይሆን የራሱን ዓላማ በእኛ ላይ ለመጫን ነው የሚፈልገው:: ብዙውን ጊዜ እኛ የምንቀርጸውን አጀንዳ አይቀበልም ነበረ:: የራሱን አጀንዳ ያቀርባል፤ የእኛን አጀንዳ ደግሞ በሚቀጥለው እንወያይበታለን ይላል:: በዚህ መልኩ የራሱን እያስቀደመ የእኛን እያሳደረ ከመሄድ በዘለለ፤ የእኛን ለመቀበል አይፈልግም:: የራሱን አጀንዳ ግን እኛ ላይ ለመጫን ይጣጣራል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ይህ ማለት በአብሮነት ጉዟችሁ እናንተ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ፓርቲ ሀሳብን በነጻነት አቅርቦና አንሸራሽሮ የጋራ የማድረግ መብትና ነጻነት የላችሁም፤ በአንጻሩ የህወሓት የበላይነትና ፈላጭ ቆራጭነት ነግሶ የራሱን ዓላማ እንዲፈጸምለት የመስራት አካሄድ የነበረበት ነው እያሉኝ ነው?

አቶ ደረጀ፡- እንደዛ ነው:: ምክንያቱም አንደኛ፣ በፋይናንስም እስከረዳን፤ ሆቴልም እስከተከራየልን እና ትራንስፖርትም እስከቻለን ድረስ እርሱ በሁለት በሶስትና አራት አባላት ድረስ እየተሳተፈ እኛን አንዳንድ (በሊቀመንበር ወይም በምክትል ሊቀመንበር ወይም በዋና ፀሐፊ) እንድንሳተፍ በማድረግ ብዙውን ነገር የሚያንቀሳቅሰው በራሱ ነው:: በስራ አስፈጻሚ ደረጃ መድቦ ነው የሚያንቀሳቅሰው፤ የህወሓት ሊቀመንበርም ራሳቸው ሰብስበው እንዲህ ነው፣ እንዲህ ነው የሚሉበት ወቅትም ነበረ:: እናም ብዙውን ጊዜ የእነርሱን አመለካከትና ሀሳብ እኛ ላይ ለመጫን ነው የሚንቀሳቀሱት:: አጋርነቱንም የሚፈልጉት ለዚሁ ነበር፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ባለው ሂደት በመካከላችሁ ልዩነት መፈጠሩ አደባባይ የወጣ ጉዳይ ነው:: ልዩነቱ እንዲፈጠር ያደረገው መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው?

አቶ ደረጀ፡- የልዩነታችን ምንጭ ህወሓቶች የሚፈልጉት የፌዴራሊስት ኃይሎች ሁል ጊዜ መቐሌ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው:: እኛ ደግሞ በሁለተኛው የመቐሌ ስብሰባችን ላይ የወሰንነው በሚቀጥለው ጽህፈት ቤትም አዲስ አበባ ወይም ማዕከል ላይ ለመክፈት፤ መደበኛ ስብሰባችንንም ማዕከል ላይ ለማካሄድ ነው:: አሁን እኛ ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን እዚህ ፋይናንስ ስጡንና

ወቅታዊ ጉዳይ

«የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ

ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው»

- አቶ ደረጀ በቀለ፣የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 13

እንዳልፈለጉ እኛ አናውቅም:: ነገር ግን ስብሰባም ሆነ ዋና ጽህፈት ቤት አዲስ አበባ መሆን የለበትም፤ መቐሌ መሆን አለበት የሚል አቋም አላቸው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በ35 የጀመረው ስብስብ በ25 ጸንቶ ጥምረቱን መፍጠሩ ይታወቃል:: ሆኖም በተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት አሁን ላይ እናንተ ወደ አዲስ አበባ ስትመጡ የተወሰኑት ከህወሓት ጋር መሆናቸው ታውቋል:: ይሄን በቁጥር ቢገልጹልን? በጥምረቱ አባላት መካከል ይሄን መሰል መከፋፈል የተፈጠረበትን ምክንያትም ቢያስረዱ?

አቶ ደረጀ፡- የጥምረቱ 25 አባል ፓርቲዎች ያቀረብነውን ጥያቄ ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ መሆናቸውን አረጋግጦ በደብዳቤ ያሳወቃቸው ናቸው:: ከእነዚህ 25 ውስጥ ደግሞ አዲስ አበባ የተሰባሰብነው 18 ፓርቲዎች ነን:: ህወሓትን ጨምሮ ሰባቱ መቐሌ የቀሩ ናቸው:: በመሆኑም 18ቱ ፓርቲዎች ከፌዴራሊስት ኃይሉ ጋር እየተንቀሳቀሱ ያሉ ናቸው:: ለዚህ መከፋፈል ያበቃው ደግሞ ሌላ ምንም የሚጠቀስ መሰረታዊ ጉዳይ የለም:: ዋናው ጉዳይ መቐሌ ካልሆነ የሚለው የህወሓት ምክንያት አልባ ሴራ ነው:: እኛ ደግሞ ማዕከሉ አዲስ አበባ ይሁን የምንል ሃይሎች ነን፡፡

ስብሰባው አዲስ አበባ እንዳይካሄድና መቐሌ እንዲካሄድ ደግሞ ህወሓት ለእኔም ጭምር እዚህ ድረስ የአውሮፕላን ትኬት ልኳል:: አልጋ የት እንደተያዘልኝም ተነግሮኛል:: ሆኖም ልዩነቱ የተፈጠረው በዋናነት መቐሌ በመሄድና አዲስ አበባ በመሄድ ነው:: በዚህም 18ታችን እዛ ላለመሄድ በመወሰን አዲስ አበባ ቀርተናል:: እንደሰማሁት ከሆነ ህወሓት የተቀሩትን የራሱ አጋር እንዳደረጋቸው ሲሆን፤ እኛ ወደ አዲስ አበባ አንመጣም የሚል አቅጣጫ ይዘዋል፡፡

እነዚህ ፓርቲዎች ደግሞ በፊትም የሚንቀሳቀሱት በትግራይ አካባቢ ሲሆን፤ የተወሰኑት ደግሞ በአዲስ አበባ ነበር:: በመሆኑም እዛ የቀሩት የትግራይ እና የአዲስ አበባ ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ከህወሓት ጋር ሶስቱ የትግራይ እና በልጅ መስፍን የሚመራውን ፓርቲ ጨምሮ ከአዲስ አበባ ያሉ ናቸው:: ከእነዚህ ውጪ ሌሎች የሶማሌ፣ የአፋር፣ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብና ሌሎችም ክልሎችን የወከሉ ፓርቲዎች በሙሉ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ነው ያሉት፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከሰሞኑ አዲስ አበባ ላይ ያካሄዳችሁት ስብሰባ ዓላማው ምንድን ነው? ምንን መሰረት ያደረገስ ነው?

አቶ ደረጀ፡- ስብሰባው ግልጽ ነው:: ለእነሱም ነግረናል:: ይሄ የተለየ ፖለቲካዊ አጀንዳ የያዘ አይደለም:: የስብሰባው ዓላማም ሆነ መሰረት አንድም ጥምረቱ ጽህፈት ቤቱንም ሆነ ስብሰባውን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ መወሰኑን ለመግለጽ ነው። ከዚህ ባለፈ ደግሞ አገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም ምርጫውን ተከትሎ ህወሓት የያዘው የብቻ ውሳኔ ላይ ያለንን አቋም ማሳወቅ ነው:: ከአገራዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ስለ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህም ህዝባችን ከዚህ ወረርሽኝ መጠንቀቅ እንዳለበት እና እኛም እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ጥምረት ጉዳዩ ስለሚመለከተን ህዝባችን ከዚህ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለበት የራሳችንን መግለጫ ለመስጠት/ለማውጣት ነው፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ፣ የ2012ቱን አገራዊ ምርጫ የተመለከተ ሲሆን፤ በዚህን ጊዜ ሰው ተራርቆ በሚንቀሳቀስበት፣ ተራርቆ በሚበላበት፣ ከቤት በማይወጣበትና ፍርሃት ባለበት ሰዓት ምርጫ ማካሄዱ አግባብ አይደለም የሚለውን አቋማችንን ያሰማንበትን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነው:: ሶስተኛም፣ እኛ ከገዢው ፓርቲ ጋር መደጋገፍም ሆነ ተቃውሞ ቢኖረንም በአገር ጉዳይ አንድ መሆናችን ለመግለጽ ነው። በዚህም የህዳሴ ግድቡ የሁላችንም ጉዳይና ፕሮጀክት እንደመሆኑ ይሄንን የሚመለከቱ ማናቸውንም ጉዳዮች ብሎም ከውጪ የሚመጡ ተቃውሞዎችን ከመንግስት ጎን ሆነን ለመከላከል ያለንን አቋም ለመግለጽ ነው፡፡

በግድቡ ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም ነገሮች ከመንግስት ጎን ሆነን አብረን መከላከል አለብን እንጂ መቃወም የለብንም፤ ግንባታውም ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መቋረጥ የለበትም:: ለምን ቢባል፣ ግድቡ የእናቶች፣ የወጣቶች፣ የአዛውንቶች በጥቅሉ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አሻራ እና ላብ እስከሆነ ድረስ ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን የአገርና ህዝብ ህልውና ጉዳይ በመሆኑ ነው:: እኛም ይሄንን አቋም ነው ያራመድነው፡፡

ከዚህ ውስጥ ግን ህወሓት ምርጫውን አካሂዳለሁ አለ:: ያንን ምርጫ ለማካሄድ ግን እንደ ስብስብ ኃይሉ የጋራ ስምምነት እኛን ማሳወቅ አለበት:: ምክንያቱም እኛ ልናውቅ እና ወይ ልንቃወም ወይም ልንደግፍ ይገባል:: የጋራ ጥምረት እንደመሆኑ በጋራ ነው ወስነን መሄድ የነበረብን፤ በጋር የተመሰረተ ጥምረት እንደመሆኑም መግለጫውን መስጠት

ተወልጄ የኖርኩ ነኝ፤ ነገር ግን ስርኣቱ ወይም የህወሓት አስተዳደር ለእኔም ሆነ ለአካባቢው ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ አብዛኛው በችግር ውስጥ ያለ፤ በእድሜ መግፋት ምክንያት ከቤት የማትወጣው ባለቤቴም ሆነች እኔም በቤተ ክርስቲያን እርዳታ ኑሮዬን እየገፋሁ የምንኖር ህዝቦች ነን ነበር ያሉኝ:: በህወሓት አገዛዝ ምክንያትም በርካታ ወጣቶች ከአገር ለመውጣትና ለመሰደድ ስለመብቃታቸውም ነው ያጫወቱኝ፡፡

ይሄን ከመስማቴና ክልሉን በተለይ ገጠራማውን አካባቢ ከመመልከቴ በፊት፤ እኔም የነበረኝ ግንዛቤ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች በተለየ መልኩ እንደተጠቀመ፤ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ብዙ ነገር እንዳገኘ ነበር:: እንደኔ ሁሉ ሌሎችም እንዲሁ ሊያስቡ ይችላሉ:: እውነቱ ግን ይሄ አይደለም፤ የትግራይ ህዝብ ጭቆና ውስጥ ነው ያለው:: የትግራይ ህዝብ በኢኮኖሚው አሁንም ወደኋላ የቀረ ነው:: የኢኮኖሚው ችግር ደግሞ ከምግብ እስከ አልባሳት በሚፈልገው ልክ እንዳያገኝ ያገደው ህዝብ ነው:: መቐሌን ጨምሮም በየከተማው ያለ ወጣትም መስራት በሚችልበት እድሜውና ሰዓቱ ያለስራ ከጠዋት እስከ ማታ በየበረንዳውና በየመንገዱ ላይ ባሉ የጀበና ቡናዎች ወንበር ላይ ተቀምጦ ዳማ እና ካርታ ሲጫወት የሚውልበትን እውነት ተመልክቻለሁ:: ከዚህ በተቃራኒው ግን ጥቂት የህወሓት አባላትና ወደ ህወሓት የሚጠጉ ሰዎች ግን የናጠጠ ኑሮ ይኖራሉ፡፡

ስለዚህ ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአንድ ላይ ማየት የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: ምክንያቱም፣ ከዚህ በፊት ከአመራሮቹ ስንሰማ እና እኔም ትግራይ ስሄድ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ፤ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው ብዬ ነበር የምወስደው:: አሁን ውስጡ ገብቼ ባየሁት መሰረት ግን በጣም የተራራቁ ናቸው:: ህዝቡ ከእጅ ወደ አፍ በሆኑ ኑሮ ውስጥ ነው ያለው:: ጥቂት የህወሓት አመራሮችና እነርሱን ተጠግተው ያሉት ግን በጣሙን ከህዝቡ የራቀና ሊነጻጸርም በማይችል የናጠጠ ኖሮ ውስጥ ነው ያሉት:: በትላልቅ ሆቴሎች ነው የሚዝናኑት:: ህዝቡ ግን አሁንም ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው:: በመሆኑም የህወሓት ጥቂት ቡድኖች እንደሚሉት ህዝቡን እና ህወሓትን አንድ ላይ ጨፍልቆ ማየቱ ተገቢ አለመሆኑን፤ እነዚህ ጥቂት የህወሓት አመራሮች የሚሉትም በጣሙን የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: እኔም ትግሬ ሁሉ የተጠቀመ፤ ትግሬ ሁሉ የህወሃት አባል የሆነ አድርጌ ሳይ የነበረበት ሁነት የተሳሳተ መሆኑን አይቼ በመገንዘብ፤ ይሄን ምስል ያስያዘኝ የህወሓት አሳሳች የሴራ ምስል መሆኑን በተግባር አረጋግጫለሁ፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከፌዴራሊዝም አንጻር እርሶ ስለ ፌዴራሊዝም ካለዎት ግንዛቤ በመነሳት እንዲሁም ህወሓት በቃል ከሚናገርለት ፌዴራሊዝምና የፌዴራሊዝም ጠበቃነት አኳያ፤ በጥምረት አብረው በቆዩበት ጊዜ በህወሓት ቤት ፌዴራሊዝም በቃል እና በተግባር እንዴት የሚገለጹ ሆነው አገኟቸው?

አቶ ደረጀ፡- ፌዴራሊዝም እኮ የእኩል አስተዳደር

ወቅታዊ ጉዳይ

የነበረብን በጋራ ነው:: ሆኖም ወደ 20 የሚሆኑት የጥምረቱ አባላት ምርጫውን አናካሂድም እያሉ ባለበት ሁኔታ ህወሓት ለብቻው ይሄን ውሳኔ ማሳለፉ ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡

ምክንያቱም ሰው ሊመርጠን የሚችለው ሰላምና ጤነኛ ሆኖ ሲኖር ነው:: አገርም ተማምኖ መሄድ ሲችል ነው:: ካልሆነ በጀብደኝነት ተነስቼ ምርጫ ላካሂድ ብል አያዋጣም:: እኛም ይሄን ስለምንገነዘብ ለምን እኛን ሳታማክሩ መግለጫ ሰጣችሁ ብለንም ጠይቀናል:: ሆኖም ይህ የግሌ ነው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይመለከታችሁም የሚል ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው:: እኛም በበኩላችን የስብስቡ አባል እስከሆናችሁና የጋራ ስምምነት እስካለ ድረስ መፈጸም ያለበት በጋራ እንጂ በአንድ ፓርቲ የግል ፍላጎት አይደለም፤ አካሄዱም አንድነት አያመጣም፤ ምክንያቱም፣ ሶማሌው ለብቻ አንድ ሲል፣ አፋሩም ሌላ ሲል፣ ኦሮሞውም ለብቻው ሌላ ሲል ነገሮች ልክ አይመጡምና ምርጫውን ማካሄድ አትችሉም በማለታችን በመካከል ጭቅጭቅ ነበር:: የአዲስ አበባው ስብሰባ መሰረትና አንዱ ዓላማ በዚህ መልኩ ከጥምረቱ አቋም ውጪ ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የወሰነው ግላዊ ውሳኔ ተገቢም ትክክልም አለመሆኑን ለመግለጽ ነው::

አዲስ ዘመን፡- በዚህ ሁሉ ሂደት ውስት ከህወሓት ጋር በጥምረት በቆያችሁባቸው ጊዜያት ቀደም ሲል ከውጭ ስትሰሙትና ስትገምቱት ከነበረው አንጻር ስለ ህወሃት ባህሪና እውነተኛ ማንነት ምን የተለየ ነገር ተገነዘባችሁ?

አቶ ደረጀ፡- እውነት ለመናገር፣ ከህወሓት የተረዳነው ባህሪ አንዱ፣ ህወሓት ማለት የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው:: የተወሰኑ ቡድኖች ብዬ ስል የትግራይ ህዝብ ወይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪውም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልን ስታይ ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም:: ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ:: በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት የተመለከትኩት እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም:: ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው፡፡

ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው:: ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው:: ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው:: ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዘቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ ነው፡፡

እንዳየሁት ከሆነ ህዝቡ መፈናፈኛ ስላጣ ነው ዝም ያለው:: ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው:: እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ

ነው:: ፌዴራሊዝም ስንልም የጋራ አስተዳደር ማለታችንም ነው:: ህወሓት ግን የእኩል አስተዳደር ብሎ ነገር የለውም:: ህወሓት የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: የህወሓት አመራሮች ቦረና ያለውን ከብት አርቢ ነው፤ ሶማሌ ያለውን እንዲህ ነው እያሉ ከመናገር ውጪ፤ ቦረና ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ ሶማሌ ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ እንዲሁም የአካባቢውን ልማት መምራት ይችላል ብሎ የሚያስብ ቡድን አይደለም:: የራሱን የበላይነት ብቻ ለማንጸባረቅ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: ይሄን የበላይነቱን ለማረጋገጥም በየቦታው የራሱን የስለላ መረብ በመዘርጋት የሚሰራ ቡድን ነው፡፡

ፌዴራሊዝም ማለትኮ የመጀመሪያው ጉዳይ ራስን ማስተዳደር ነው:: በራስ መዳኘት ነው:: በራስ ቋንቋ መማር ነው:: ህወሓት ግን ያንን ለይምሰል ይናገር እንጂ ውስጥ ገብተን ስናየው የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚጨፈልቅ ቡድን ነው:: ይሄንን መብት ጨፍልቆም እሱ እንዴት መግዛት እንደሚችል የሚያስችለውን የወጥመድ መረብ የሚዘረጋ ነው:: ለዚህ ደግሞ በስለላ መረብ በጣሙን የተሳሰረ ነው:: በሆቴልም ሆነ በየትም ያለ ሰራተኛን በዚህ መረብ ውስጥ በማስገባት የስለላ መረቡ አባል አድርጎታል:: ከዚህ አንጻር ለምሳሌ እኔ በጅማ ወይም ኢሉባቦር አካባቢ ሄጄ አንድ ነገር ስፈጽም የህወሓት ሰላዮች እዛው ስላሉ ወዲያው መረጃው ይደርሰዋል:: ስለዚህ እኔ በጥምረቱ ውስጥ ካለሁት ሰው ይልቅ እነርሱን ይቀበላል:: ይህ ደግሞ የፌዴራሊዝሙን ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለውን የሚያፋልስ ነው፡፡

የዚህ ጨፍላቂነቱ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ፤ እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችና ምርጫ አናካሂድም በሚሉበት ወቅት እርሱ አካሂዳለሁ ማለቱ የራሱን የበላይነት ለማንጸባረቅ የሚያደርገው ድርጊት ነው:: ከዚህ ባለፈ ስለ ህዳሴው ግድብ ያገባናል ብለን ሁላችንም ፓርቲዎች ስንናገር፤ ስለሱ ጉዳይ መንግስትን እንጂ እኛን አይመለከትም ማለቱ ነው:: ይሄን የሚል ድርጅት ደግሞ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ሊሆን አይችልም:: ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት ከዳር እስከዳር ያሉ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ህዝቦች ፕሮጀክት ሆኖ ሳለ፤ ይሄን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነው ግድብ አያገባንም ብሎ መናገር አግባብነት የሌለው፣ ስለፌዴራሊዝም የማያስብና የራሱን ኑሮ ብቻ ለማንቀሳቀስ የሚጥር ድርጅት መሆኑን ነው የተረዳሁት፡፡

አዲስ ዘመን፡- እርሱ ከውጪ ሆነው ሲያዩት እና በውስጡ ሆነው ሲያዩት ስለ ህወሓት ከተገነዘቡት አንጻር፤ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስለ ህወሓት ሊያውቁት ይገባል ብለው የሚነግሩትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?

አቶ ደረጀ፡- አንደኛ ለትግራይ ህዝብ ነው መልዕክት የማስተላልፈው:: ይሄውም ህወሓት ላለፉት 40ም ይሁን 50 ዓመት ታግሏል:: አንድ ትግል ደግሞ ወደ ህዝቡ ሰርፆ ይገባና ያድጋል፤ ያለበለዚያ ደግሞ ይከስማል:: አሁን በህወሓት ላይ የምናየው ይሄንኑ ነው:: ምክንያቱም ላለፉት 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሃት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደ መጠቃለሉ እንደመሆኑ መጠን፤ አሁን ላይ የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ አይቀበለውም:: ህዝቡም አሁንም በድህነቱ ያለ እንደመሆኑ ከድህነት መውጣትን ይፈልጋል:: ምክንያቱም ህወሓት የዘረፈውን ወደ አውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር የለም::

ስለዚህ በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለ ህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ተረድቷል:: የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ተገንዝቧል:: ይሄን የተገነዘበ ህዝብ ደግሞ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል:: የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል:: የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ህወሓትን በቃህ ሊሉት ይገባል:: ለዚህ ደግሞ አንድም፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ ሁለተኛም አንድ ነገር የተወሰነ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያቆም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ የህወሓትን አመራሮች እዚህ ጋር በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል፡፡

ለምን ቢባል፣ እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን ሀብት አካብተዋል:: ይህ ሀብት ደግሞ በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከ ተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት ነው:: በክልሉ ደግሞ ለእለት ጉርሱም ሆነ ለእግሩ ጫማ እና ለሰውነቱ ልብስ መለወጥ ቀርቶ ማሟላት ያቃተው ህዝብ (በተለይ ገጠሩ) ተፈጥሯል:: እናም እነዚህ አመራሮች እውነትም ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ያ ህዝብ ነጻ መውጣት ነበረበት:: ቢያንስ ትንሽ እንኳን መሻሻል ማሳየት ነበረበት:: ስለሆነም እኔ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የማስተላልፈው ይሄ

ገጽ 14 አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም

ለህዝቡ የጠቀመው ነገር የለምና ለህዝቡ የሚጠቅም ፓርቲ ማግኘት ስላለባቸው ለእርሱ የሚያደርጉት ድጋፍ ማቆም መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ድጋፍ እያጣ አሁንም ወደ ከተማ የተሰበሰበ እንደመሆኑ፤ አሁን ያለውና የቀረውም ማቆም አለበት:: ይሄን በማድረግም ለራሳቸው የሚበጀውን ማሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

በየክልሉ ተበትነው ያሉም ሆኑ በውጭ አገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ቆም ብለው ማሰብ መቻል አለባቸው:: በሚያደርጉት ድጋፍ በአገሬ ላይ ምን ለውጥ መጣ? ምንስ ታየ፣ የትስ ደረሰ? ማለት አለባቸው:: ህወሓት 27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለእኛ ለትግራይ ህዝቦች ምን አደረገ? ብለው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው:: ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች ዛሬ ችግር ሲመጣ ወደዛ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን ሄደው አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው:: ለዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤ ክልሉን ባስጎበኙኝ ጊዜ ከተመለከትኳቸው አከባቢዎች አንዱ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትውልድ አካባቢ ነበረ:: በወቅቱ ስንጎበኝ እርሱም አብሮን ነበር:: የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደሰማሁት ግን አምባሳደር ስዩም ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከማየት ውጪ በአካል አይተውት እንደማያውቁ ሲገልጹ ነበር፡፡

እናም በዚህ መልኩ አካባቢያቸውን በልማት ማገዝ ቀርቶ በአካል ሄዶ መመልከት ሳይችሉ የኖሩ አመራሮች፣ ዛሬ ችግር ሲገጥማቸው ወደ ህዝቡ ገብተው ህዝቡን ለሌላ ጭንቀት ይባስ ብሎም ከሌላው ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግልጽ ይታያል:: እነርሱ ሲደላቸው እርሱ ሲቸገር የነበረው ህዝብ በእነርሱ ሴራ ዛሬ ከእነርሱ ጋር ተጨፍልቆ እንዲታይ እያደረጉትም ይገኛል:: እናም በክልሉ ያለውም ሆነ በሌሎች ክልሎች ብሎም በውጭ አገራት ያለው የትግራይ ተወላጅ ይሄን ሊያውቁ፤ ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው፤ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሁሉ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ መቻል አለበት፡፡

ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ደግሞ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው:: ዛሬ ላይ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ ብሎ የሚፎክረው ህወሃትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ በህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ማወቅ ይኖርበታል:: ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ወጥቶ የድጋፍ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረግ ቢባል እንኳን አምስት በመቶ እንኳን አያገኝም:: ይሄንንም በክልሉ ቆይታዬ በነበረኝ ጉብኝት ከተለያዩ አካላት (ምሑራንና ህዝቡን ጨምሮ) ባደረኩት የሀሳብ ልውውጥና ውይይት መገንዘብ ችያለሁ:: ህዝቡ ለህወሃት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡

ህወሓትም ቢሆን እንደሚያወራው ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሰራው ስራ የለም:: ይልቁንም ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ በትግራይ ውስጥ በክልሉ ከተወለዱ ህዝቦች እና ጥቂት የመንግስት ስራን ማዕከል አድርገው ካሉ ዜጎች ውጪ በትግራይ የሚኖርም፤ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖረውም አለመደረጉ ነው:: ለምሳሌ፣ በክልሉ አንድም ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ሆቴል ያለው፤ ፋብሪካ የከፈተም የለም:: በአንጻሩ በሌሎች የክልል ከተሞችና ክልሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆቴልም ሆነ በሌሎች በርካታ ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ስራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባርም አይደለም::

በዚህም ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ ህዝብ ነው:: ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ ይኖርበታል:: ህወሓት እንደሚለውም ሁሉም ትግሬ የህወሓት አባል ወይም ደጋፊ ነው ብለው ማሰብም የለባቸውም:: በአንጻሩ ሁሉም ትግሬ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ማሰብ፤ ንጹሁን ህዝብም ከሰላዩና ዘራፊው ለይተው ማየት አለባቸው:: ምክንያቱም ዛሬ ከህወሓት ጥቂት ቡድኖች ጋር ያሉት አንድም እነዚሁ የቡድኑ አባላት፤ ሁለትም ከህወሓት ጋር በፈጠሩት ትስስር እርሱንም መከታ አድርገው ሲዘርፉና የሰውን ንብረት ጭምር ሲበዘብዙ የነበሩ ቡድኑን ከተውት ያላቸውን የሚያጡ የሚመስላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ፡፡

አዲስ ዘመን፡- አሁን ላይ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? ምንስ ይፈልጋል?

አቶ ደረጀ፡- አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳይ ስናይ የታየውን አገራዊ ለውጥ/ሪፎርም ተከትሎ አገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ነው:: አገር ያለ መሪ ልትኖር ስለማትችልም ይህ መሆኑም ያለበት ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከሰተ:: ይህ በሽታ ሲገባ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህዝብ ነው እንጂ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም አስተዳደር ወይም ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚንስትርነት አይደለም:: ህዝቡ ደህና መሆን ስላለበት መጀመሪያ ለህዝብ ጤንነትና ደህንነት ነው:: ሆኖም አሁን የፖለቲካ አሰላለፉን ስናይ በአብዛኛው አንድ ላይ እየተሰበሰበ ነው ያለው:: እኛም በዚህ መልኩ ሰብሰብ ማለታችን ይሄ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ስለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ይሄንን ማድረግን ወይም ሰብሰብ ማለትን ይፈልጋል፡፡

ምክንያቱም በዚህ መልኩ አንድ ላይ መምጣት ይገባል እንጂ፤ እኔ የመንደር ፖለቲካ አቋቁሜ ኢትዮጵያ ላይ እንደፈለኩ መጮህ አልችልም:: አንድ ላይ ከመጣንና ድምጻችን መሰማት ከጀመረ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን አለብኝ:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኔ ወይም ስሆን ደግሞ ኦሮሞን አስደስቼ አማራን ማስከፋት የለብኝም፤ አማራን አስደስቼ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን ማስከፋት የለብኝም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ነው ማየት ያለብኝ:: የእኛም ጥምረት ለዛ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ያቀፈውና በሁሉም ክልሎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ለሚደርስ ችግርና ተጽዕኖ ሁላችንም ተጠያቂ ነን፤ ሁላችንም ይመለከተናል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው፡፡

በመሆኑም በአገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ አመራር በያዘው አካሄድ አገር አቀፍ ሆኖ ቢንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: በዚህ እንቅስቃሴው ሌሎችንም ለማሳተፍ መሞከሩም ጥሩ ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲናገሩ “ልንረዳችሁ የምንችለው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ላይ ስትሰባሰቡ ነው” ነው ያሉት:: በዚህ ንግግራቸው “ስትጨፈለቁ ነው” አላሉም፤ “ስትሰባሰቡ” ነው ያሉት:: ስትሰባሰቡ ግን እንደማንኛውም አገር አስርም እንሁን አምስትና አስራ አምስት በእውነት ለህዝብ የምንታገል፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ በዓላማ የምንገናኝ ሰብሰብ ማለት እንችላለን፡፡

ለምሳሌ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ በኦሮሞነቴ ሶማሌውን እንደራሴ ነው ማየት ያለብኝ:: አንዱ አማራም አንዱን ደቡብ እንደራሱ ነው ማየት ያለበት:: በዚህ መልኩ አንዱ ሌላውን እንደራሱ ማየት እንጂ ነጣጥሎ ማየት የለበትም:: በዚህ መልኩ እንደ ኢትዮጵያዊነት ማየት እና በኢትዮጵያዊነት መታገል፤ በህዝባችን ላይ ፍትህ ሲጓደል ለፍትህ መቆም ይገባል:: የፖለቲካ መሪ ማለትም ለህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እንጂ ለመዝናናት የተዘጋጀ አይደለም:: ሞት እንኳን ቢመጣ እቀበላለሁ ብሎ የገባ ነው:: በመሆኑም በዚህ መልኩ ሞት እንኳን ቢመጣ ካንተ በፊት እኔ እቀበላለሁ ብዬ እስከገባሁ ድረስ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብሰብ ብለን በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡

ካልሆነ ለአንዷ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ወይም ለሚኒስትርነት ቦታ ሁሉም ሊደርስ አይችልም:: 110 ሚሊዬን ህዝብም ሆነ 107 ፓርቲ ይሄን ማድረግ አይችልም:: ሆኖም 110 ሚሊዬኑም ህዝብ አገሬ ነው ብሎ በእኩልነት ያለመሳቀቅ ህግን አክብሮ እንደ ልቡ የሚኖርበትን አገር መፍጠር ይቻላል:: አሁን ያለው አመራርም ከልምድ የሚመነጭ የፖለቲካ አመራርነት ብስለት ይጎድለው እንደሆን እንጂ ይሄን ከማድረግ አኳያ አቅም አለው:: ለምሳሌ፣ እኔ ባለሁበት ኦሮሚያ ክልልን ብንወስድ በዞንና ወረዳ እስከ ቀበሌ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚቀመጡ አመራሮች በህዝብ አስተዳደር ልምድ ማነስና በፖለቲካው ካለመብሰል የተነሳ የውሳኔ ሰጪ አካላት ማነስ ይስተዋላል:: እነዚህ ደግሞ በመቀራረብ ወይም በጓደኝነት የመጡ እንጂ በህዝብ ተተችተውና ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው:: ከዚህ ውጪ ግን እንደ ብልጽግና ፓርቲ እንዳየሁት ጥሩ ፕሮግራም ነድፏል:: ይህ ፕሮግራምም ኢትዮጵያም ብዝሃነቷን ጠብቃ አንድ የሚያደርጋት መሆኑንም ተመልክቻለሁ:: ባህርዳር፣ ጅግጅግ፣ ሐዋሳ፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጅማም ሆነ ነቀምቴ፣ ወዘተ. ያለው ብልጽግና ፓርቲም አንድ አይነት በሆነ አሰራርና ፕሮግራም የሚመራ መሆኑም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡

ለምን ከተባለ ብዝሃነትን አስጠብቆ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያመጣልና ነው:: እኛም ለዛ ነው ፌዴራሊስት ብለን ከሶማሌውም፣ ከአፋሩም፣ ከአማራውና ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ ሆነን ስንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን ለመፍጠር ነው:: ለምሳሌ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለምርጫ ሲቀርብ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደረው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ በራሱ አርማ ቢወዳደርም እንደ አገር የሚንቀሳቀሰው በጥምረቱ ዓርማ ጥላ ስር ሆኖ ነው:: ስለዚህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን

ማድረግ የሚገባንን ነው:: እናም ህብረ ብሔራዊ የሆነ ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ወደላይ እናውጣ የሚለውን ማሰብ አለብን:: የወቅቱም ፖለቲካ በዚህ መልኩ መስራትና መተባበርን ነው የሚፈልገው፡፡

ይህ ካልሆነና በመንደር ካሰብን እንደ ህወሓት ተመልሰን እንገባለን:: እናም እንደዛ ማሰብ የለብንም:: እኛ የተለያየን ቢሆንም ለአንድነት ነው የምንታገለው:: ለአንድ ኢትዮጵያም ነው የምንታገለው:: እናም ይሄንን በጥንካሬና በአንድነት በሁላችንም ፖለቲከኞች ዘንድ መሆን ያለበት ነው እንጂ፤ እኔ ግዙፍ ነኝ፣ እኔ ትንሽ ነኝ፣ እኔ አገሪቷን መጠበቅ እችላለሁ፣ እኔ አገሪቷን ማረጋጋት እችላለሁ የሚለው አይሰራም:: ይሄ ቦታም የለውም:: ምክንያቱም አገር ከተበጠበጠ ይሄ ትርጉም የለውም:: በአገር ሰላም ከሌለ የትም ቢሆን ወልዶ ሊስም፣ ንብረት ሊያፈራም አይችልም:: በመሆኑም የወቅቱ ፖለቲካ ጎጠኝነትና መንደርተኝነትን መተው የሚጠይቅ ነው:: እኔም ይሄ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት ቢቀር ደስ ይለኛል፡፡

አዲስ ዘመን፡- እርሶም እንዳነሱት ወቅቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ምርጫ 2012 መራዘሙ ይታወቃል:: ሆኖም የምርጫውን መራዘም ተከትሎ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል፤ ሌሎች ኃይሎች ደግሞ የሽግግር መንግስት መመስረት አለበት ሲሉ ተደምጧል:: እርሶ በዚህ ላይ ያለዎት እይታ ምንድን ነው?

አቶ ደረጀ፡- እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫው መራዘም አለበት ከሚሉት ቡድን ነኝ:: ምክንያቱም ምርጫ የሚመርጠን ዛፍ ቅጠሉ አይደለም፤ ሕዝብ ነው:: ህዝብ ደግሞ ሊመርጠን የሚችለው ጤና ሰላም ሲሆን፤ እንደልቡ ወጥቶ መግባት ሲችል ነው:: ልጁን እንደ ልቡ ማሳደግ ሲችል ነው:: እኔም የምመርጠው ህዝብ ለማስተዳደር ነው እንጂ መሬቷን ብቻ ለማስተዳደር አይደለም:: ህዝብ ለማስተዳደር ደግሞ ህዝቡ ሰላም ሆኖ እኔን መምረጥ መቻል አለበት:: ይሄን መሰረት በማድረግም ነው እኔ ምርጫው ይራዘም ከሚሉት ውስጥ የሆንኩት፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ (ኦነን)ም የወረርሽኙን ዓለማቀፋዊ ሁነቱን በመመልከትና እንደ ስፔንና ጣሊያን ባሉ አገራት የተስተዋለውን የሰው ልጆች እንደ ቅጠል መርገፍ በማየት ገና ቫይረሱ በኢትዮጵያ እንደተከሰተ ነው ችግሩ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት በማሰብ ምርጫው መካሄድ የለበትም ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት ሊሰጥ ይገባልና መራዘም አለበት የሚል አቋሙን ያሰማው:: አሁን ላይ ደግሞ ቫይረሱ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው:: ይህ ሂደት ደግሞ በከተሞች ያለውን ያክል የጤና መሰረተ ልማት በሌለው ብሎም ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ባለበት የገጠሩ ክፍል ከገባ ደግሞ አደጋው የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው:: ትልቁ ስጋትም ይሄው ነው፡፡

ወረርሽኙ ወደገጠር እንዳይገባ ደግሞ በጸሎት ጭምር ፈጣሪን መማጸን ይገባል:: ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስገንዘብ እና ገበያ መውጣት ቢያስፈልገው እንኳን ሁሉም ከመሄድ ይልቅ የየሰፈሩን ሰብሰብ እያደረገ አንድ ሰው ገብይቶ እንዲመለስ በማድረግ ራሱን እንዲጠብቅ ማስቻል ይገባል:: ይሄን በሃላፊነት የሚመራ መንግስት አስፈላጊ እንደመሆኑም ምርጫው ተራዝሞ አሁን ያለው መንግስት ምርጫ እስኪካሄድ መቆየትም ግድ የሚለው ተግባር ነው:: እኛም ታግለን አታግለንም በአሸናፊነት ብንመረጥ ሌላውም ፓርቲ ቢመረጥ ይሄንኑ ህዝብ ለማስተዳደር ነው:: ለዚህ ደግሞ አሁን ምርጫ ይካሄድ የሚለው ሀሳብ ጤነኛ ያልሆነ፣ ከራስ ጥቅም በዘለለ ለህዝብ ደህንነት ያላሰበ ፍላጎት በመሆኑ ተገቢ አይደለም:: እናም ቅድሚያ ለህዝብ ጤናና ደህንነት መሰጠቱ ተገቢ ነው፡፡

የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚለው ሀሳብም ለእኔ

የብጥብጥ ሀሳብ ነው:: እንደ ገና ወደ ብጥብጥ እንመለስ ማለት ነው:: ምክንያቱም በዚህ የሽግግር መንግስት ውስጥ እነማን ናቸው የሚሳተፉት? 107 ፓርቲዎች ይግቡ ወይስ 107 ሽማግሌዎች ይካተቱ ወይስ 107 ምሑራን ይግቡ? የሚለው ጉዳይ ትልቅ የውዝግብ ምክንያት የሚሆን ነው:: እንደ እኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውዝግብ አሁን ያለው መንግስት ወይም አመራር ላይ ያለው አካል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ማሻገር ከቻለ መቀጠል የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም:: የሽግግር መንግስት እንደገና ማቋቋምም አስፈላጊ አይሆንም:: የሽግግር መንግስት ይቋቋም ማለት ወንበር እንያዝ ማለት ካልሆነ በስተቀር ትርፍ የለውም:: ምክንያቱም የሽግግር መንግስት የሚያስፈልገው ቢያንስ አገር ችግር ውስጥ ስትወድቅ እና ህዝቡ ባለው መንግስት አመኔታ ሲያጣ ሊተገበር ይችል ይሆናል እንጂ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ የሽግግር መንግስት አስፈላጊ አይደለም:: ሆኖም አሁን ያለው መንግስት እስከ ምርጫ ድረስ ሲቀጥል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ መስራት፤ ይሄን በሽታ እንዴት እንለፈው በሚል ከጤና ሚኒስቴር የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተፈጻሚ በማድረግ፤ ተገቢውን የመከላከልና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት ስራን በማከናወን ህዝቡን ለማሻገር መስራት ይኖርበታል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ጋር በተያያዘ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት፤ ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን ተግባራዊ የሚያደርግበት ነው:: በመሆኑም ሌሎች ክልሎችም ይሄንኑ ተገንዝበው ምርጫ ለማካሄድ መወሰን አለባቸው፤ ሲል ይደመጣል:: በዚህ ላይ የእርሶ እይታ ምንድን ነው?

አቶ ደረጀ፡- ህወሓት ምርጫ ይካሄድ ብሎ የሚያወራው ለህዝቡ አስቦ አይደለም፤ ለራሱ ነው:: ይሄም ለራሱ አፍኖ በያዘው አካባቢ ለቀጣይ አምስት ዓመት ቀጣይ ኮንትራት ለማግኘት እና ያንን ዋስትና ለመያዝ ነው:: ይሄ በዚህ ጊዜ ምርጫ ይካሄድ ማለት ደግሞ ለህዝብ አለማሰብ ነው:: ይሄንን አይነትና አባባልና አካሄድ ደግሞ ማንኛውም ክልል አይቀበለውም:: ይሄንንም ምናልባት ከህወሓት ጋር አብረው የቆሙት አራት ያክሎቹ ካልሆኑ በስተቀር በቀላሉ ከጥምረቱ አባል ፓርቲዎች መረዳት ይቻላል:: ለምሳሌ፣ ጎረቤቱ ያሉ የአፋር ፓርቲዎች ይሄን አካሄድ ስለማይቀበሉ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ስብሰባ የመጡት:: ከእኛው ጋር ምርጫው መራዘም አለበት ብለው ወስነው ነው የሄዱት:: ከአፋር ድረስ የመጡትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች አባል ፓርቲዎች በዚህ መልኩ ምርጫው መራዘም አለበት ብሎ የጋራ ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ ለራስ ስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ከማሰብ የሚመነጭ ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት መስጠት እንደሚገባ በግልጽ ያሳየ እርምጃ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ስለ ምርጫ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለይበት ሁኔታ የለውም:: የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ እስከሆነ ድረስ ህወሓት ብቻውን ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ማለቱ ለምንድን ነው? የሚለው በራሱ መታየት ያለበት ነው:: ምክንያቱም ብቻውን ምርጫ ቢያካሂድ እንኳን ፓርላማ እዛ ሊቋቋም ነው ወይስ 38 የፓርላማ አባላት ከተመረጡ በኋላ እዚህ ያሉትን ተክተው አዲስ ሊገቡ ነው? ወይስ በትግራይ ብቻ ተወስኖ ሊቀር ነው? የሚለውን እንኳን በወጉ ያላገናዘበ ነው:: እናም አገራዊ ምርጫ ሲካሄድ አንድ እና የፌዴራል ምክር ቤቱን ጨምሮ እስከ ወረዳ ያሉ የምክር ቤት አባላት የሚመረጡበት ነው:: የምርጫ ዘመናቸውም አንድ ነው:: ይሄን ችግር ተከትሎ ምርጫው የተላለፈው እንደ አገር እንደመሆኑም፤ ሶማሌ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ደቡብ፣ ወይም ድሬዳዋ ለብቻዬ አካሂዳለሁ ሳይሉ ሁሉም ናቸው እንዲተላለፍ የወሰኑት፡፡

ይህ ደግሞ ሊሆን የሚገባው እና ተገቢም እርምጃ ሲሆን፤ ለህዝቦቻቸው ደህንነት ያላቸውን ተቆርቋሪነት እና ከምንም በፊት ለህዝብ ጤንነት መጨነቃቸውን ያሳያል:: ከዚህ ባለፈም እንደ አገር የተላለፈ ውሳኔን አንዱ ክልል ተነስቶ እኔ ውሳኔውን አልቀበልም ስለዚህ በክልሌ ምርጫ አደርጋለሁ ሊልም አይችልም:: ቢልም ማድረግ አይችልም:: ምክንያቱም አካሄዱ ሰዋዊም ሆነ ህጋዊ መሰረት የለውም:: እናም እንደ አገር የተወሰነ ውሳኔን አንዱ እንደፈለገ ተነስቶ ካላካሄድኩ ብሎ ቡራ ከረዩ ካለ ይህ ለእኔ ሕገ ወጥነት ነው:: ከዚህ አኳያ የህወሓት ፉከራም ሆነ ነገ አንዱ ክልል ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ቢል ይህ ህገ ወጥ ከመሆኑም ባለፈ በህዝቦች ጤናና ደህንነት ላይ መቀለድ ነው:: እናም ይህ አካሄድ የቀልድ እና በህዝብ መጫወት፣ ከማን አለብኝነት የሚመነጭ ለህዝብም ክብር አለመስጠት ነው:: ከዚህ ባለፈ ግን ተግባሩ አጀንዳ ፈጥሮ የትግራይን ህዝብ አዕምሮ በዚህ የመያዝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንድ ምርጫ ቦርድ እንዳለ እና ምርጫውም በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ እየታወቀ ምርጫው እንደማይካሄድ እሙን ነው:: ይሄንንም ህወሓት በደንብ ያውቀዋል፡፡

ወቅታዊ ጉዳይየትግራይ ህዝብ በድህነት

ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ

ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም

እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት

ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን

የሚናፍቅ ህዝብ ነው

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 15

አዲስ ዘመን፡- የጥምረቱን ስብሰባ በአዲስ አበባ ማድረጋችሁን እና የህወሃትን አቋም ማውገዛችሁን ተከትሎ “በገንዘብ ተገዝተው ነው” የሚል ድምጽ እየተሰማ ነው:: ይሄን ምን ያክል እውነት ነው? ከዚህ በኋላስ የጥምረቱ የፖለቲካ ተሳትፎና አካሄድ በምን መልኩ የሚቀጥል ነው?

አቶ ደረጀ፡- ከስም ማጥፋቱ ጋር በተያያዘ እኔ በፊትም ከህወሓት ጥሩ ነገር አልጠብቅም:: ከበደ ወይም ደረጀ ገንዘብ ወሰደ የሚሉትንም በተመለከተ ሁሉም እዚሁ ስላሉ ማረጋገጥም ይቻላል:: ካለም ከማን ወሰዱ የሚለውን በግልጽ መናገር ይገባቸዋል:: ዋናው ነገር ይሄን ያናገራቸው እነርሱ በፋይናንስ ምክንያት የዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሊያደርጉ ያሰቡበትን አካሄድ ሰብረን አዲስ አበባ ስብሰባችንን ማድረጋችን የፈጠረባቸው ስብራት ለማካካስ የሚያደርጉት ስም የማጥፋት ሙከራ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡

አዲስ አበባ ያካሄድነው ስብሰባም ቢሆን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህወሓት ፋይናንሱን ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ ሁለት ባለሃብቶች ስፖንሰር አድርገውን ያካሄድነው ነው፤ በዚህ ድጋፍ ሂልተን ሆቴል ተከራይተን ስለተሰበሰብን መንግስት ወይም ብልጽግና ፓርቲ ሰጣቸው ብለው የሚናገሩትን የተሳሳተ ነገር ከጭንቅላታቸው ቢያስወጡ መልካም ነው:: ምክንያቱም ይሄ የስም ማጥፋት ዘመቻቸው ድሮም የተለመደ እና የተካኑበትም ስለሆነ፤ ሲያደርጉትም የኖሩት ስለሆነ እንጂ እኛ አሁንም ሆነ ድሮም የምንኖረው በራሳችን ነው፤ በቀደም ያካሄድነውን ስብሰባም እነዚህ ሁለት ድርጅቶች ናቸው የረዱን እንጂ ከመንግስት ያገኘነው አምስት ሳንቲም የለም:: ብልጽግና የሚባል ፓርቲ ለእኛ ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገልንም፡፡

በመሆኑም እኛ አሁንም ቢሆን ለወደፊቱ ስብሰባ ብንጠራም ሆነ ቢሮ ብንከፍት በእነዚህ በፌዴራሊዝም እምነት ባላቸው ባለሃብቶች ድጋፍ ነው:: ይሄን የሚያደርጉትም በፌዴራሊዝሙ ማንነታችን ይከበራል ብለው ስለሚያምኑ፤ እኛም እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ጠንክረን እንድንወጣ ፍላጎት ስላላቸው ነው:: ለምሳሌ፣ ጽህፈት ቤት ፈልጉ ለአንድ ዓመትና ለሁለት ዓመት እንከፍልላችኋለን፤ የቢሮ ቁሳቁስ እናሟላላችኋለን ያሉን የግል ድርጅቶች አሉ:: የሂልተንን ክፍያ በራሱ ለጥምረቱ ተሰጥቶ የተከፈለ ሳይሆን ራሳቸው ናቸው ሄደው የከፈሉት:: ይሄን መንግስት ወይም ብልጽግና ፓርቲ ወይም ሌላ ድርጅት ሳይሆን ባለሃብቱ ነው እያደረገ ያለው:: አለ ካሉ ደግሞ ማቅረብ ይችላሉ፤ ይኖርባቸዋልም:: ደግሞም አላደረገውም እንጂ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ የደገፈን ቢሆን ኖሮ እነርሱስ ሲሰጡን ከርመው የለም እንዴ? እነርሱ ከየት አምጥተው ነው ሲሰጡን

የነበረው? ከህዝብ ጉሮሮ ነጥቀው፣ ከመንግስት ካዝና አውጥተው ነው እኮ:: ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ህዝባቸው ስንት የሚያስፈልገው ነገር እያለ አይደል እኛን የአውሮፕላን ትኬት ቆርጠው፤ ሆቴል ይዘው፤ ምግብ ችለውና አበል ከፍለው ሲያመላልሱንና ሲያዝናኑን የነበረው:: አልሆነም እንጂ ቢሆንና እንደነርሱ ሁሉ አንዱ ፓርቲ መጥቶ ቢረዳን ምን ችግር አለው? እናም ይህ ውንጀላ ሀሰተኛ የህወሓቶችና ግብራበሮቻቸው ሩጫ አካል ነው ፣ የራሳቸውን ለመደበቅ የሌሎችን ስም ባልሆነ መንገድ ለማጠልሸት የሚደረግ ጥረት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ከዚህ ባለፈ ቀጣይ የእኛ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚሆነው እና በተሳትፏችንም ለመስራትም እንዲሆንም የምናስበው በኢትዮጵያ የተረጋጋ መንግስት እንዲኖር፤ ኢትዮጵያም ልማቷ እንዲፋጠን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነቱ ተጠብቆ በሰላም አብሮ እንዲኖር፤ ባህልና እሴቱን አጎልብቶ ታሪክ ሰሪም የታሪክ ባለቤትም የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው:: ከዚህ በተጓዳኝ አሁን ላይ የምንሰራውም ሆነ የምንመኘው ህዝባችን የህዝባችን ጤና ተጠብቆ በሳላም ይሄን ወረርሺኝ እንዲያልፈውና ቀጣይ የሚከናወነው ምርጫም ህዝብ በነጻነት የሚፈልገውን መምረጥ የሚችልበት እድል እንዲፈጠር ነው:: ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚሆነውና የሚያምረው ህዝብ ሰላምና ጤና ሲሆንና የህዳሴ ግድባችንን ስናጠናቅቅ ነው:: ምርጫ ከዛ በኋላ ነው መሆን የሚችለው፡፡

ምክንያቱም ምርጫ ማለት ለጥቅም የሚፈልጉት ካልሆነ በስተቀር የምትመረጠው ህዝብን ዝቅ ብሎ ለማስተዳደርና ለህዝብ ለመገዛት እንጂ እንደከዚህ ቀደሙ በህዝብ ጭንቅላት ላይ ለመቀመጥ አይደለም:: እናም ምርጫው የተፈለገው ህዝብን ለማገልገል ከሆነ ይሄን ያህል ሩጫና ጥድፊያም አያስፈልግም:: ህዝቡ ከፈለገህ በማንኛውም ጊዜ ይመርጥሃል:: ይሄንንም እኔ ቀደም ሲል ወደ ምክር ቤት ስገባ የበደሌ ህዝብ በመረጠኝ ጊዜ ተገንዝቤያለሁ:: እናም የራስን የምርጫ ዓላማ ከህዝቡ ፍላጎት ጋር አጣጥሞ ማስኬድ፤ ለራስ ጥቅም ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል፤ እንዲሁም በህዝብ ምርጫም ማንኛውም ፓርቲ አሸንፎ ስልጣን ላይ ቢወጣም አሜን ብሎ ለመቀበልም ዝግጁ መሆን ይገባል እንጂ በጀብደኝነትና በማን አለብኝነት የሚሆን መሆን የለበትም:: እኛም በቀጣይ የሚኖረን ተሳትፎና አካሄድም ይሄንን መሰረት ያደረገ ነው የሚሆነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ዛሬ ላይ ኮሮናን ተቋቁሞ ከማለፍ እና ነገ ውጤታማ/የተሳካ ምርጫ ከማካሄድ አኳያ በማን ምን መሰራት ይኖርበታል?

አቶ ደረጀ፡- ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው

ይሄን አስቸጋሪ ጊዜ ማለፍ ነው:: ምክንያቱም ምርጫ የሚመረጠው ህዝብ ሲኖር እንደመሆኑ፤ ወጣቱም ሆነ ሁሉም ዜጋ ከዚህ በሽታ ራሱን መጠበቅ አለበት:: ባለው ሁኔታም የሞቱትን ነፍስ በሰላም እንዲያርስ፤ የታመሙትን ፈውስን እንዲያገኙ ምኞትም ጸሎታችንም ነው:: በህመሙ ያልተያዙት ደግሞ ራሳቸውን መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን፡ ለዚህም የጤና ሚንስትር የሚየወጣውን መመሪያና ምክረ ሀሳብ መተግበር ይገባለ፣ ርቀትን መጠበቅ፣ በተቻለ መጠን ቤት መቆየት፣ እጅን መታጠብና የመሳሰሉት ደግሞ ተገቢ ነገሮች ናቸው:: በዚህ መልኩ ህዝቡ ራሱን ከጠበቀ እና በመንግስት በኩልም አስፈላጊው ስራ ከተሰራ ኢትዮጵያ ከዚህ ወረርሽን ነጻ ትወጣለች:: ይህ ሲሆን ነው ስለምርጫ ማሰብ የሚቻለው:: በዚህ ወቅትም ወረርሽኙን በመከላከል ሂደት ውሰጥ ሁሉም የየራሱ ሃላፊነት ይኖረዋል፡፡

ለምሳሌ፣ በመንግስት በኩል ህዝቡ በፍላጎቱ እንዲመርጥ የሚችልበትን እድል መፍጠርና መስጠት አለበት:: የአንድ ፓርቲ ምክር ቤት ማየት ስለማንፈልግ ህዝቡ የፈለገውን ይምረጥ:: ምክንያቱም የተለያዩ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት ምክር ቤት እንዲኖረን ያስፈልጋል:: የሀሳብ ልዩነቶች የሚንሸራሸሩበትም የሚስተናገዱበትም ምክር ቤት ማየት እንፈልጋለን:: የህዝባችን ጥያቄ የሚሰማበት ምክር ቤትም ማየት እንፈልጋለን:: አንድ አዋጅ ሲቀርብ ክርክር የሚነሳበትና በክርክር ዳብሮ የሚያልፍበትን ሁኔታ ማየት እንፈልጋለን:: ምክንያቱን አሁን እንዳለው የአንድ ፓርቲ ስብስብና አንድ አይነት ሀሳብ የሚንጸባረቅበት ሳይሆን አገራዊ ሁነቶችና ፍላጎቶች ተነስተው ሰፊ ውይይትና የህዝብ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት የክርክር አውድ ሊኖረው ያስፈልጋል:: በዚህ መልኩ የህዝቦች ድምጽ የሚሰማበት፣ ተወካዮቹም የአከባቢያቸውን ድምጽ ለፓርላማው ማቅረብ፣ የአገራቸውን ፍላጎትም ለዓለም አቀፍ መድረክ ማሰማት የሚችሉ መሆን አለባቸው:: ይህ ሲሆን ነው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን መሆን የምትችለው፡፡

ለዚህ ደግሞ መንግስትም ሆነ ያሉት ድርጅቶች ህዝብን ነጻ በማድረግ በነጻ ፍላጎታቸው እንዲመርጡ እድል መስጠት አለባቸው:: አንተ አገሌን መረጥክ ተብሎ ተጽዕኖ ሊደረግበት እና ሊታሰር ሊገረፍ ሊሰደድ አይገባም:: ምክንያቱም ሁሉም ዜጋ የአገሩ ባለቤት፤ ለአገሩም ተጠያቂ ነውና :: ስልጣን ላይ ያለው ብቻም ሳይሆን ተፎካካሪውም የአገሩ ባለቤት እንደመሆኑ ይሄን ታሳቢ አድርጎ ሊንቀሳቀስም ሊሰራም ያስፈልጋል:: ከህዝባችን የሚጠበቀውም፣ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱን በተግባር የሚያረግግጥበትን አካሄድ መከተልና ለጋራ ሰላሙና ደህንነቱ በጋራ ሊሰራ ያስፈልጋል:: ስለዚህ ምርጫው በዚህ መንፈስ መካሄድም፤ እስካሁን የተለመደውን የሌብነትና ማጭበርበት አስቀምጦ ትቶ

በነጻነት መመረጥም አለበት:: በህዝብ የተመረጠውንም አሜን ብለን መቀበል አለብን:: በመሆኑም ምርጫው አዲስ አካሄድና አጀንዳ የሚታይበት አዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ሊሆን ይገባል:: ለዚህም መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝቡ የሚጠበቅበትን አውቆ በአገራዊ ሃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስም መስራትም ይጠበቅባቸዋል፡፡

አዲስ ዘመን፡- በመጨረሻም እድሉን ልስጥዎ እና በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ ቢያስተላለፉ?

አቶ ደረጀ፡- እኔ የምለው ህዝባችን በተለያዩ ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶችና ግለሰቦች ሳይወናበድ አገሩን በአንድነት መጠበቅ አለበት:: ለህዳሴ ግድቡም ከዳር መድረስ በአንድነት መስራት አለበት:: ለዚህ እውን መሆንም ሆነ አሁን ወረርሽኝ ሆኖ አደጋ እየጋበዘ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት እንደ አንድ ሰው መስራት ይኖርበታል:: በመንግስትና ጤና ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል:: ምክንያቱም ፖለቲካ ያልፋል፤ ፓርቲና አስተዳደርም ያልፋል፤ እንደ ንጉሳውያኑ፣ የደርግ እና የኢህአዴግ ስርዓት ማለፍ ሁሉ የብልጽግና ፓርቲ ዘመንም ጊዜውን ጠብቆ ያልፋል:: የማያልፉት ህዝብና አገር ናቸው:: እኛ እንኑርም አንኑርም አገር እንደ አገር ትኖራለች፤ ህዝብም በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ይዘልቃል:: ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን፣ እኛ እንደ ሰው የምናልፍ ቢሆንም አገርና ህዝብ ዘላቂ መሆናቸውን ተገንዝበን ለአገርና ህዝብ ደህንነት ቅድሚያ ሰጥተን መስራት ይገባናል፡፡

ከዚህ ውጪ ለፖለቲካ ብለን ወይም በአንዳንድ ምክንያቶች መተሳሰርና መገዳደል የመሳሰሉትን መተውና ማቆም፤ በአንድነትም መንቀሳቀስ አለብን:: አንድ ከሆንን እንጠነክራለን፤ ከተለያየን ግን እንላላለን፤ እንፈርሳለን:: ስለዚህ አንድነታችንን ማጠናከርና በአንድነት መነሳት አለብን:: ፖለቲካውም ሆነ ሁሉ ነገር አላፊ ነው፤ አንድነታችን ግን ማለፍ የለበትም:: ከዚህ ውጪ እና እንደ ፓርቲ የፌዴራሊስት ኃይሎች በመላው ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል:: በመላ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰውን ኃይል ደግሞ ሕዝባችን ከጎኑ ሊሆንና ካጠፋ ከጥፋቱ እንዲታረም፤ ካለማም በልማቱ እንዲጠነክር ሊያግዘው ያስፈልጋል:: የጥምረቱ አባሎች ደግሞ ከህብረተሰቡ ጎን ሆነው በተለይም አርሶ አደሩ ከወረርሽኙ ራሱን ጠብቆ የምግብ እህል እጥረት እንዳያጋጥም ጠንክሮ እንዲሰራ ከጎኑ ሆነው ሊያግዙትና ሊያበረታቱት ይገባል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ለቃለ ምልልሱ ስለተባበሩኝ አመሰግናለሁ፡፡

አቶ ደረጀ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

ወቅታዊ ጉዳይ

አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 32

ዜናዕለተ ሰንበት

ለልጆች

ዕለተ ሰንበት

ለወላጆች

ማህበረሰብ የለውጥ አቅም ነው!

ልጆች! በቤት ውስጥ ብዙ ስራዎችን እየሰራችሁ እንደሆነ እገምታለሁ፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን እየተስፋፋ በመሆኑ ደጋግማችሁ እጃችሁን በውሃና በሳሙና ለሃያ ሰከንድ መታጠብና አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዳለባችሁ እንዳትረሱ፡፡ ለጨዋታ ብላችሁም ከቤት መውጣት የለባችሁም።

ልጆች ዛሬ ሃሳባቸውን የሚያካፍሉን የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው። ዛሬ እነሱን እንግዳ ያደረኩት የዒድአልፈጥር በዓልን ምክንያት አድርጌ መልዕክት እንዲያስተላልፉላችሁ ነው። በደንብ ተከታተሏቸው።

በቅድሚያ ያነጋገርኩት ተማሪ ሙዘይድ ኑረዲን ይባላል፡፡ የሚማረው በአጋዚያን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ በኮሮና ምክንያት በብዛት ጊዜውን በቤት ውስጥ ነው የሚያሳልፈው። ‹‹ትምህርት ቤት ሊከፈት ስለሚችል

ብንነፋፈቅም ዒድን በቤታችን

መፅሐፍቶቼን እያነበብኩ ነው፡፡ ከቤት ከወጣሁኝ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርጌ ነው፡፡ መጫወት ስፈልግም በጊቢ ውስጥ ሁለት ሆነን ንክኪ በማይፈጥር መንገድም ነው፡፡ እቤት ውስጥ ስውል ብዙ ጊዜ ስላለኝ እንዳይደብረኝ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አደርጋለው፡፡ በተለይ ኳስ አዘውትሬ እጫወታለው። የግል ንጽህናዬንም ከበፊቱ በተሻለ እየጠበኩኝ ነው።›› ብሎኛል። ልጆች ተማሪ ሙዘይድ ጎበዝ አይደል። እድርግ የተባለውን የጥንቃቄ መመሪያ ሁሉ እየተገበረ ነው። እናንተስ?

ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል ስለሆነ ሁሉም ሰው ሳይዘናጋ በዓሉን በየቤቱ ማሳለፍ ይኖርበታል፡፡ ሰዎች

በአንድ ቦታ ሆነው መቀመጥም የለባቸውም ሲል ምክር ለግሷል፡፡ በመጨረሻም ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ እና ለቤተሰቦቹ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ በማለት ሃሳቡን አካፍሎናል፡፡

ሌላኛው ተማሪ አብዱላዚዝ የኑስ ይባላል፡፡ የሙዘይድ ጓደኛ ሲሆን የሚማረው በአጋዚያን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ ኮሮና አስፈሪ በሽታ ስለሆነ ሳንዘናጋ መጠንቀቅ አለብን። ከወረርሽኙ መትረፍ የሚቻለው በመጠንቀቅ ብቻ ስለሆነ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረኩኝ ነው ብሎናል፡፡

ተማሪ አብዱላዚዝ ያለፈው ወቅቱ ፆም ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከቤት እንደማይወጣ ይናገራል፡፡ በቤት

ሞገስ ፀጋዬውስጥ ሲሰግድም ተራርቀው እና በደንብ ታጥበው መሆኑን ነግሮኛል፡፡ በዚህ ወቅት ልጆች በማጥናት እና የሚያዝናኑ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አብዛኛውን ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ ማሳለፍ አለባቸው፡፡ የኢድ አልፈጥር በዓል እንደበፊቱ ባለመሰባሰብ መከበር እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ከጓደኞቼ ጋር ብንነፋፈቅም በስልክ መደዋወል እንችላለን። ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ልጆች! እናንተም ከቤት ባለመውጣትና መጫወት ስትፈልጉ ደግሞ በጊቢ ውስጥ ብቻ መጫወት አለባችሁ። እንዲሁም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መሞከር እንዳትረሱ፡፡ በተለይ ደግሞ በማንበብ እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ተግባራዊ በማድረግ ሳትሰለቹ ጊዜያችሁን በአግባቡ ማሳለፍ አለባችሁ፡፡ መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል ይሁንላችሁ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ለዕረፍት ጊዜዎ

የሒሳብ ስሌት ሠንጠረዥ ጨዋታ ጥያቄ ቁጥር አንድ ከውድዬ ሲሳይ

ውድ ልጆች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ለዛሬ ተዘጋጅቶ የቀረበላችሁ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ የሒሳብ

ስሌት ጥያቄ ነው፡፡ ከታች እንደምትመለከቱት በሠንጠረዥ ውስጥ ቁጥሮች ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህን

ቁጥሮች በአግድመት እና በቁልቁለት ድምራቸው ውጤቱ 18 መምጣት አለበት፡፡ ይህንን ስታደርጉ

ግን በአንድ ቀጥታ መስመር ውስጥ ተደጋጋሚ ቁጥሮችን መሙላት አይፈቀድም፡፡ በተደጋጋሚ

በመሞከር ትክክለኛውን ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጉ፡፡ እኛ ደግሞ በቀጣዩ ሳምንት ትክክለኛውን

ምላሽ እናቀርባለን፡፡ በተከታታይም ይህን መሰል አዝናኝ፤ አስተማሪና አዕምሮን የሚያሰራ ጥያቄዎችን

ስለምናቀርብ ተከታተሉ፡፡ እናንተም እንዲህ አይነት አመራማሪ ጥያቄዎችን በመላክ ተሳተፉ፡፡

4 7

6

3 6

3 5

18 18 18 18

ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል ስለሆነ ሁሉም ሰው

ሳይዘናጋ በዓሉን በየቤቱ ማሳለፍ ይኖርበታል

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

‹‹በአሁኑ ጊዜ መላው ህብረተሰብ በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ኢ-ሥነምግባራዊ ድርጊቶችን ሊኮንንና ሊዋጋ ይገባል”

የግሉ ዘርፍ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይሁንና ዘርፉ ከሥነምግባር

ጉድለት፣ ከሙስና እና ብልሹ አሠራር ጋር በተያያዘ ስሙ እየተነሣ ይገኛል። ምንም እንኳን በግሉ ዘርፍ የተሠማሩ አብዛኞቹ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘርፉ የሚጠይቀውን ሥነምግባር ተከትለው በመሥራት

ስልክ ቁጥር፡- 011-552 77 79 00/ 011 552 77 85 ፋክስ፡- 011-553 69 89 011-557 77 86 ኢሜይል፡- [email protected] ፖ.ሳ.ቁ፡- 34798/99

እራሳቸውንና ኅብረተሰቡን እያገለገሉ የሚገኙ ቢሆንም ጥቂቶቹ ግን መነሻና መድረ ሻቸውን ትርፍ ብቻ አድርገው ወዳል ተገባ አቅጣጫ ሲያመሩ ይታያል። በአንዳንድ ሥነምግባር በጎደላቸው አካላት ሌሎች ህገ-ወጥና ኢሥነምግባራዊ ድርጊቶች እየተፈፀሙ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከል በአሁኑ

ጊዜ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀነውን የኮቪድ-19 (ኮሮና) ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ ሰው ሰራሽ የዕቃ እጥረት መፍጠር፣ በተለያዩ ምርቶች ላይ ባዕድ ነገሮችን መቀላቀል፣ ስውር በሆነ መልኩ በመነጋገር የዕቃዎችን ዋጋ ማናር እና ደንበኛን በአግባቡ ያለማስተናገድ የሥነምግባር ችግሮች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።

ይህ ዓይነት አካሄድ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ላይ ብሎም በዜጎች ደህንነት ላይ መሰናክል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በመሆኑም የንግዱ ማህበረሰብ፣ መንግሥትና በአጠቃላይ መላው ህብረተሰብ ይህን ኢ-ሥነምግባራዊ ድርጊት ሊኮንንና ሊዋጋ ይገባል።

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

18

18

18

18