የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) facilitators guide...ባለፈው...

6

Upload: others

Post on 10-Apr-2020

15 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ
Page 2: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ

ክፍለ ጊዜ 3የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና)

ሌሎችን ከራሳቸው ማስቀደም ይፈልጋሉ፣ ባሎቻቸው ወይም ሌላ የቤተሰብ አባላት ከእነሱ ጋር የበለጠ ወይም የተሻለ እንዲመገቡ ወይም ቀድመው እንዲመገቡ ይሻሉ፣

ለማረፍና ለመመገብ በቂ ጊዜ የላቸውም፡፡

ይበሉ፡ ‹‹በዛሬው ስብሰባችን፣ በእነዚህና በሌሎችም ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ እንወያያለን፡፡››

‹‹ ንግስት ንቦች በየቀኑ በቤተሰብ የምግብ ጊዜያት እንዲሁም በመክሰስ ወቅት የሚመገቧቸውን የምግብ ዓይነቶች ማቀድና መወያየትን እንለማመዳለን፡፡››

‹‹ እንደዚሁም የንግስት ንቦች ባሎች፣ እናቶችና አማቶች ንግስት ንብ ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ህፃን እንዲኖራት ማድረግ ስለሚገባቸው በርካታ ነገሮች እንወያያለን፡፡

ደረጃ 4፡- የኋለኛው የዘር ደረጃ ወቅት መልካም የአመጋገብ ሥርዓትና አንዳንድ የተለመዱ ተግዳሮቶች

1. ንግስት ንቦች ምንም እንኳን በርከት ያለ መጠን ያለው ምግብና ኮከብ ምግቦችንም ጨመር አድርገው መመገብ ቢያስፈልጋቸውም፣ አንዳንድ ጊዜ ይህን ለማድረግ ችግሮች አሉባቸው፡፡

ለምሳሌ፡- በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወቅት አንዳንድ ነፍሰጡር ሴቶች በርከት ያለ ወይም የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን ከተመገቡ፣ ጽንሱ ይፋፋል፤ ይህም በወሊድ ጊዜ አስቸጋሪ ያደርገዋል በማለት ሆን ብለው ኮከብ ምግቦችንም ያስወግዳሉ፡፡

2. ነፍሰጡር ሴቶች በቂ ምግብ የማይመገቡና ኮከብ ምግቦችንም የሚያስወግዱ ከሆነ፣ በቂ ምግብ ያለማግኘት ችግር ይገጥማቸዋል፡፡በዚህም የተነሳ በቀላሉ ከመውለድ ይልቅ ውርጃን ወይም በሚወልዱበት ጊዜ በራሳቸውና በህፃኑም ህይወት ላይ አደጋን ያባብሳል፡፡

ንግስት ንቦች በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወቅት ለራሳቸው ጥንካሬ እና በማህጸን ውስጥ ላለው ዘር ህጻን ጥንካሬ እና ጤንነት በርከት አድርገው መመገብ ያስፈልጋቸዋል፡፡

የዘር ህፃኑ አእምሮ እና የሰውነት አካል በፍጥነት የሚያድግበት ወቅት ስለሆነ ትክክለኛ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡

በቂ ምግብ የማትመገብና ኮከብ ምግቦች የሆኑትን ፍራፍሬዎች የማትወስድ ንግስት ንብ ራሷንና ዘር ህፃኗ ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲቆዩ የሚያስችላቸውን የአመጋገብ ሥርዓት ትነፍጋለች፡፡

የምግብ መጠንን መጨመር፣ ኮከብ ምግቦችን በርከት አድርጎ መመግብ፣ የአይረን ኪኒን መውሰድ፣ የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ ስለመውለድ አስቀድሞ ለማቀድ ከትዳር አጋር ጋር በመነጋገር ለአስተማማኝ አወላለድ የሚረዱ ጥሩ መንገዶች ናቸው፡፡

የዚህ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት አብይ ርዕሶች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በኮከብ ምግቦች የእናቶችን ምግብ ማመጣጠን

ለሁለት መመገብ

ለጥንካሬ መመገብ (ጠናካራ እናት፣ ጠንካራ ህፃን)

ለጤናማ የወሊድ ወቅት መዘጋጀት

የንግስት ንብን የሥራ ጫናን መጋራት እና የቤተሰብ ድጋፍ

እለታዊ የአመጋገብ ማስታወሻ ጨዋታ ምንጣፍ እና የምግብ ካርዶች

የእናቶችን ምግብ ማመጣጠን ፖስተር

የሚና ጨዋታ ካርዶች ለ3 ትንንሽ ቡድኖች

የቤተሰብ ማስታወሻ

ደረጃ 1፡- እንኳን ደህና መጣችሁይበሉ፡- ለመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት የዳበረ የማኅበረሰብ ውይይት ሦስተኛ ክፍለ ጊዜ እንኳን ደህና መጣችሁ ፡፡

ደረጃ 2፡- ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ ቤተሰብ አባላት የአይረን ኪኒን ማስታወሻ የቀን መቁጠሪያ ፖስተር ሰጥቼ ነበር፡፡

1. ስንቶቻችሁ ናችሁ የአይረን ኪኒን ማስታወሻ የቀን መቁጠሪያውን አጠቃቀም ለትዳር አጋራችሁ ወይም ለቤተሰብ አባላት ያሳያችሁ?

2. ስንቶቻችሁ ናችሁ የዶሮ ቤት አሠራር መመሪያ ለትዳር አጋራችሁ ወይም ለቤተሰብ አባላት ያሳያችሁ?

3. እነዚህን ነገሮች ስንት ሰው እንደፈጸማቸው በዳበረ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለ ጊዜ 3 የዘገባ ቅፃችሁ ላይ ጻፉ፡፡

ይበሉ፡- ለቤተሰቦች የንግስት ንብ የአመጋገብ ሥርዓት በጣም አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ነፍሰጡር ሴቶች እንደዚሁም ጡት የሚያጠቡ ሴቶች የሚመገቡት ለሁለት ስለሆነ፡፡ የእናቶች የአመጋገብ ሥርዓት የተሻሻለ ከሆነ ታዳጊው ዘር ህፃን ጠንካራ፣ ጤነማና ብሩህ ይሆናል፡፡

ደረጃ 3፡- የዕለቱን ስብሰባ ርዕስ ፡- የኋለኛው ዘር (ከ3 -9 ወር የእርግዝና ወቅት) የአመጋገብ ሥርዓት

ጥያቄ፡ በተገላጭ ሰሌዳው ላይ ምን ምን ይታያችኋል

መልስ፡ የምትስቅ ነፍሰጡር ሴት፣ ሙዝ ይዛ

ይበሉ፡ «በዛሬው ስብሰባችን ስለዘር ህፃናት (በእናታቸው ማህጸን ያሉ) እና ነፍሰጡር እናቶችና ቤተሰብ ይህ ዘር ህፃን ብሩህ፣ ጤናማ እና ጠንካራ ሆኖ እንዲያድግ በኋለኛው የእርግዝና ወቅት ምን ማድረግ እንደሚችሉ መነጋገራችንን እንቀጥላለን፡፡ ዘር ህፃን ምን ማለት እንደሆነ ማን ሊያስታውሰን ይችላል?» ከ 2-3 የሚሆኑ ሰዎች ይህን ጥያቄ እንዲመልሱ ይፍቀዱ፡፡

ይበሉ፡ የዘር ህጻን በማህፀን ውስጥ በማደግ ላይ ያለ ህፃን ነው፡፡

1. ነፍሰጡር ሴቶች በመጀመሪያው የእርግዝና ወቅት በርከት ያሉ ምግቦችን እና ኮከብ ምግቦችን መመገብን በተመለከተ የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ ተግዳሮቶች ከእናንተ መካከል ሊያስታውሰን የሚችል አለ; ከ 2-3 የሚደርሱ ተሳታፊዎች እንዲመልሱ ያድርጉ

ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው መብላት፣ ለራሳቸው ብለው ምግብ ማዘጋጀት፣ ወይም የተለየ ምግብ መመገብ ምቾት አይሰጣቸውም፡

Page 3: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ
Page 4: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ

ደረጃ 6፡- ማርባትና ማብቀል 1. የተሻለ የዶሮዎች መኖ አዘገጃጀት መመሪያን ከቤተሰብ ማስታወሻው ላይ ለተሳታፊዎች ያንብቡላቸው፡፡ ባሎችና ቤተሰቦች

ንግስት ንቦቻቸው በየቀኑ ዕንቁላልን የመሳሰሉ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦችን እንዲመገቡ እንደሚረዱ ግለፁ፡

2. የዶሮ መኖን በቀላሉ ለማዘጋጀት የሚረዱ 9 ደረጃዎችን ለተሳታፊዎች ያንንብቡ፡፡

3. ተሳታፊዎችም የዶሮ አረባብ ተመክሮዎቻቸውን እንዲያጋሩ ይጠይቁ፡፡

4. ዶሮ የማያረቡ ከሆነ፣ ዕንቁላልን ስለመግዛት ዕውቀት እንዲያጋሩ እርዷቸው

ሀ ዶሮዎችንና ዕንቁላሎችን የት እንደሚገዙና የዶሮና የእንቁላል ዋጋም ስንት እንደሆነ ጠይቋቸው፡፡

ደረጃ 7፡- ማዘጋጀት፣ ማቆየት፣ ማከማቸት

ቋንጣን ማዘጋጀትና ሳይበላሽ እንዲቆይ ማድረግ

1. ሁልጊዜ ምግብ ከማዘጋጀታችሁ በፊት እጆቻችሁን በሣሙናና ውሃ መታጠብ ያለባችሁ መሆኑን አስታውሱ

2. ስጋ በመግዛት ስጋውን በረጅሙ ዘልዝሉት

3. በርበሬ ወይም አዋዜ፣ ዘይት፣ጥቂት የሎሚ ጫማቂ፣ የኮረሪማ ዱቄትና ጨውን ቀላቅሉ፡፡

4. የተዘለዘውን ሥጋ በበርበሬ ቅልቅሉ እያሻችሁ ዘፍዝፉት፡፡

5. ንፋስ በሚገባበት ክፍል ውስጥ ከፍ ብሎ በተወጠረ ገመድ ላይ (ህፃናት ወይም ድመትና ውሻ እንዳይደርሱበት ) ሥቀሉትና እንዲደርቅ ለትንሽ ቀናት አቆዩት፡፡

6. ቋንጣ በዝናብ ወራት መዘጋጀት የለበትም፣ አየሩ ርጥበት ስለሚኖረው ቶሎ አይደርቅም፡፡

7. ቋንጣ እንደ ወጥ፣ ፍርፍር በመሳሰሉት ምግቦች ላይ ይጨመራል ወይም እንደዚሁ ለመክሰስ ይበላል፡፡

ጥያቄ፡ በተገላጭ ሰሌዳው ላይ ምን ምን ይታያችኋል

መልስ፡ ኮከብ ምግቦች፣ ትልቅ እና ትንሽ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ የዶሮ መኖ የምታዘጋጅ ሴት፣ ዶሮዎች

ደረጃ 5፡- የእናቶች ዕለታዊ የአመጋገብ ማስታወሻ ጨዋታ1. የንግስት ንቦችን ዕለታዊ የምግብ ማስታወሻ ለመለማመድ እንዲረዳን አዝናኝ ጨዋታ እንጫወታለን ፡፡

2. እለታዊ የምግብ ማስታወሻ መጫወቻውን እና የኮከብ ምግብ ካርዶቹን ለተሳታፊዎች አሳዩ፣ ጨዋታውንም እንዴት እንደሚጫወቱ ይግለፁላቸው፡፡

ሦስቱ ትልልቅ ሳህኖች (ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት) ቤተሰብ በየቀኑ የሚመገቡአቸው ምግቦች ናቸው፡፡

ሁለቱ ትንንሽ ሣህኖች ደግሞ የየቀን መክሰሶች ናቸው፡፡

እያንዳንዱ ቡድን የምግብ ካርዶችን በመመልከት ንግስት ንቦች በየቀኑ በመደበኛ ምግብና በመክሰስ ወቅት መመገብ በሚኖርባቸው አማራጮች ላይ ይወያዩ፡፡

አስታውሱ፡- ንግስት ንቦች በየቀኑ ቢያንስ አንድ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦችን መመገብ አለባቸው፡፡ ባለሦስት ኮከብ ምግቦች ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ምግቦች ናቸው፡፡

አስታውሱ፡ እንደዚሁም ንግስት ንቦች ከሚመገቡት ምግቦች ጋር በየቀኑ ቢያንስ አንድ ባለሁለት ኮከብ ምግቦችን መመገብ አለባቸው፡፡ እነዚህም በምግብ ላይ የሚጨመሩ ፍራፍሬና አትክልት ናቸው፡፡

3. ተሳታፊዎችን በ3 ትንንሽ ቡድኖች በመከፋፈል ክብ ሰርተው እንዲቀመጡ ያድርጉ፡፡

4. አንድ እለታዊ የምግብ ማስታወሻ ማጫወቻ ምንጣፍና የምግብ ዝርዝር ካርዶችን ለእያንዳንዱ ቡድን አከፋፍሉ፡፡

5. በመዘዋወር ቡድኖቹ ጨዋታውን እንዴት እየተጫወቱት እንደሆነ ተከታተሉ

6. በንግስት ንቦቻቸው የየቀን የምግብ ዝርዝር ላይ እንዲወያዩና የምግብ ካርዶቹን በመመልከት በየቀኑ በመደበኛነት ከሚመገቡት እና ከመክሰሳቸው ጋር ሊሄድ የሚችለውን በመምረጥ ትክክለኛ ምርጫ እንዲያደርጉ አበረታቱ፡፡

7. ከ20 ደቂቃ በኋላ ፡ ሁሉም ወደ ትልቁ ቡድን እንዲመለሱ ጠይቁ፡፡ ከእያንዳንዱ ትንሽ ቡድን አንድ ሰው በትንንሽ ቡድኖቻቸው የተደረገውን የጨዋታ ሂደት እንዲያጋሩ ይጠይቁ፡፡

ሀ እለታዊ የምግብ ማስታወሻ ጨዋታን መጫወትን ወደዳችሁ?

ለ የቀኑን የንግስት ንብ የምግብ ዝርዝር ስለማቀድ የቀለላችሁ ምን ነበር?

ሐ የቀኑን የንግስት ንብ የምግብ ዝርዝር ዕቅድ በምታዘጋጁበት ጊዜ ቡድናችሁን ያጋጠሙት አንዳንድ ተግዳሮቶች ምን ነበሩ?

መ የንግስት ንብን የቀን የምግብ ዝርዝር በምናቅድበት ጊዜ ትክክለኛ ምርጫ እንድናደርግ እንዲረዳን ከትንሽ ቡድናችን የተቀበልነው አንዳንድ ምክር ምንድነው?

8. ውይይቱን ለማጠቃለል እነዚህን ነጥቦች ጥቀሱ፡-

ይህ ጨዋታም ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የየቀን የምግብ ዝርዝርን የማቀድ ተግባርን ለማከናወን ይረዳል

ንግስት ንቦች በእርግዝናቸው ጊዜ በየቀኑ የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን ለማቀድና ለመመገብ የትዳር አጋሮቻቸውና የቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በቤት ውስጥ ኮከብ ምግቦች የማይገኑኙ ከሆነ፣ ንግስት ንቦች ለማርባት፣ ለማብቀል ወይም ኮከብ ምግቦችን ለመግዛት የባሎቻቸው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

Page 5: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ
Page 6: የኋለኛው ዘር (ከ 3-9 ወር ያለ እርግዝና) Facilitators Guide...ባለፈው ክፍለ ጊዜ አንድ ላይ ባደረግነው ስብሰባ፣ ለዘርና ችግኝ

ጥያቄ፡ በተገላጭ ሰሌዳው ላይ ምን ይታያችኋል

መልስ፡ አንበሳ፣ አህያ፣ ማርና ውሃ

ደረጃ 8፡- መወያየትና በጋራ መወሰን - የሚና ጨዋታይበሉ፡‹‹አሁን ንግስት ንቦችና ህፃኖቻቸው ጠንካራና ጤናማ መሆን እንዲችሉ በርከት ያሉ ምግቦችን እንዲመገቡ ለመርዳት ከትዳር

አጋሮቻችንና ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዴት እንደምንነጋር የምንለማመድበት ጊዜ ነው፡፡››

1. ንግስት ንቦችና ህፃኖቻቸው በርከት አድርገው እንዲመገቡ፣ ሰፊ ዕረፍት እንዲያገኙና ኮከብ ምግቦችን በብዛት እንዲመገቡ ስለመርጃ መንገዶች ከቤተሰቦቻችን ጋር ጥሩ ውይይት ማድረግን ለመለማመድ በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ የሚና ጨዋታዎችን እንጫወታለን፡፡ ከዚያ በፊት ሁላችንም እያየን የሚና ጨዋታውን ፈጠን አድርገን በአንድነት እንጫወታለን፡፡

2. ሦስት ፈቃደኞች በመጠየቅ ወደፊት እንዲመጡ ያድርጉ፡፡ እያንዳንዱ ፈቃደኛ የሚና ካርዶቹን በደረታቸው ላይ እንድይዙ የርዷቸው፡-

የመጀመሪያው በጎ ፈቃደኛ የአንበሳን ካርድ በደረታቸው ላይ በመያዝ የአንበሳን ገጸ ባህሪ ወክሎ/ላ እንደሚሠራ/ ምትሠራ ይንገሩ ፡፡

ሁለተኛው በጎ ፈቃደኛ የአህያን ካርድ በደረታቸው ላይ በመያዝ የአህያን ገጸባህሪ ወክሎ/ላ እንደሚሠራ/ምትሠራ ይንገሩ፡፡

ሦስተኛው በጎ ፈቃደኛ የማርና ውሃ ካርድ በደረታቸው ላይ በመያዝ የማርና ውሃ ገጸባህሪ ወክሎ/ላ እንደሚሠራ/ምትሠራ ይንገሩ፡፡

የሚና ጨዋታውን ከቡድን አባላት ጋር በምታስተባብሩበት ወቅት የሚከተለውን ርእስ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲወያዩ ያድርጉ

ነፍሰጡር እናቶች በየቀኑ ብዙ ኮከብ ምግቦችን እንድታገኝ ምን ማድረግ እንደሚችሉ

የእኔ ሚስት/ባል/ምራት አንቺ እኔ ኮከብ ምግቦችን በየቀኑ ለመመገብ ምግቦቹ በሚገኙባቸው መንገዶች ላይ እንወያይ፡፡

3. የመጀመሪያው በጎፈቃደኛ፡- በራሱ/ሷ ሚና ላይ እንዲቆይ/ትቆይና እሱ/ሷ አንበሳ እንደነበሩ የሚገልጽ የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች እንዲሉ

ይጠይቁ፡- (በጣም ቁጡ፣ በጣም ትዕግስት የለሽ፣ ጯሂ )

4. ሁለተኛው በጎፈቃደኛ በራሱ/ሷ ሚና ላይ እንዲቆይ/ትቆይና እሱ/ሷ አህያ እንደነበሩ የሚገልጽ የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች

ይበሉ፡- (ምንም መልስ የማይሰጥ በጣም ጸጥ ያለ፣ የማይጨነቅ)፡-

5. ሦስተኛው በጎፈቃደኛ፡- በራሱ/ሷ ሚና ላይ እንዲቆይ/ትቆይና እሱ/ሷ ማርና ውሃ እንደነበሩ የሚገልጽ የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች እንዲሉ

ይጠይቁ፡- (በራሱ የሚተማመን፣ ደግና ተቆርቋሪ፣ በሌሎች የሚደነቅ)

6. አሁን የትልቁን ቡድን አባላት፡- ምን እንዳዩ እና ምን እንደሰሙ እንዲያስረዱ ይጠይቁ፡፡

ሦስቱም በጎፈቃደኞች ሚናዎቻቸውን ደህና አድርገው ተጫውተዋል?

ከእነዚህ ሦስት የተግባቦት ስልት ዓይነቶች መካከል የምታውቋቸውን ወይም አነጋግራችኋቸው የነበሩ ሰዎችን ያስታውሳችሁ አለ?

የትኛው የተግባቦት ስልት፡- አንበሳ፣ አህያ፣ ማርና ውሃ ውይይትን የሚያበረታታና ከትዳር አጋሮቻችንና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር መፍትሔዎችን ለመፈለግ ይበልጥ ውጤታማ መንገድ ይመስላችኋል?

7. ማርና ውሃ የተግባቦት ስልትና በእነዚህ ስብሰባዎች የተማርነው መረጃ ወደ ቤት በመውሰድና ከቤተሰብ ጋር በምናደርገው ውይይት

ወቅት ልናዳብረው የሚገባ ክህሎት መሆኑን ግለጹ፡፡

8. አሁን በትንንሽ ቡድኖች ማርና ውሃን በመመሰል አንደምንለማመድ ግለጹ፡፡ ተሳታፊዎችን በ3 ትንንሽ ቡድኖች እንዲመድቡ ይንገሩአቸው፡

9. የሚና ጨዋታ ካርዶችን አውጡና ለእያንዳንዱ ቡድን አንድ ስብስብ አከፋፍሉ፡፡ በአንድ ጊዜ 2 ሰዎች የሚና ጨዋታውን እንደሚጫወቱ፣ ሌሎቹ የቡድን አባላት ደግሞ እንደሚከታተሉ፣ ከ5 ደቂቃ በኋላ የሚና ጨዋታው እንደሚቆምና ሲከታተሉ የነበሩት ለሁለቱ ተለማማጆች ግብረ መልስ መስጠት እንደሚገባቸው ለቡድኖቹ ንገሩ፡፡

10. የቤተሰብ አባላትን ሚና በሚጫወቱበት ወቅት ማርና ውሃ የመገናኛ ስልት መነጋገርን መለማመድ እንደሚገባቸው፣ በራስ የመተማመን ስሜት፣ ለመተወን የሚችሉትን ማድረግ እንዳለባቸውና ሌላው ሰው ሚናውን ሲጫወት በሚያዳምጡበት ጊዜም ታጋሽና ደግ መሆን እንደሚገባቸው ለትንንሽ ቡድኖች ይንገሩ ፡፡

11. ከ10 ደቂቃ በኋላ አዲስ ሰዎች ሚና የመጫወቱን ተራ ይውሰዱ ዘንድ ቡድኖቹ በፍጥነት እንዲለዋወጡ ይጠይቁ፡፡

12. ሁሉም የሚና ጨዋታውን የማከናወን ዕድል ካገኙ በኋላ ወደትልቅ ቡድን እንዲሰበሰቡ በማድረግ ከየትንንሽ ቡድኑ አንድ በጎፈቃደኛ ከሚና ጨዋታ ተሞክሮዎቻቸው በጥቂቱ እንዲያጋሩ ይጠይቁ፡-

ከሚና ጨዋታው ምን ተማርን?

ከትንንሽ ቡድን አባላት ያገኘነውን የማርና ውሃ የተግባቦት ክህሎቶቻችንን እንድናሻሽል የሚረዳን ምክር ምንድነው?

ንግስት ንብ እናቶች ለጥንካሬ እንዲመገቡ፣ የአይረን ኪኒን እንዲወስዱ፣ ሰፊ ዕረፍት እንዲያደርጉና ለጤናማ የወሊድ ጊዜ እንዲዘጋጁ ስለመርዳት ከቤተሰብ አባላት ጋር ለመወያየት ይበልጥ ዝግጁነት ይሰማናል?

ይበሉ፡- ‹‹አስታወሱ የሚና ጨዋታው ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ንግስት ንቦች ኮከብ ምግቦችን ይበልጥ እንዲመገቡ፣ በየምሽቱ የአይረን ኪኒን እንዲወስዱና ሰፊ የዕረፍት ጊዜ እንዲኖራቸው ለመርዳት ከቤተሰብ አባላት ጋር እንዴት እንደሚወያዩ የመለማመድ ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡››

ደረጃ 9፡- ወደቤት የሚወስዱ ቁሳቁሶችና ሥራዎች1. ወደቤት የሚወሰደውን የእናቶች ምግብ ማመጣጠን ፖስተር አከፋፍሉና ፖስተሩ ስለሚከተሉት ነገሮች እንዲሚያስታውሰን ግለጹ፡-

ንግስት ንቦች በየቀኑ ቢያንስ አንድ ባለ 3-ኮከብ ምግብ እና በየምግቡም ባለ 2-ኮከብ ምግብ በመጨመር መመገብ ያስፈልጋቸዋል፡፡

እንደዚሁም ንግሰት ንቦች በርከት ያለ መክሰስ በመመገብ፣ በቤተሰብ የመመገቢያ ጊዜያትም በርከት አድርገው በመመገብና የቤተሰብ ምግብ ሲያዘጋጁም በመቅመስ የሚመገቡትን የምግበ መጠን መጨመር ያስፈልጋቸዋል፡፡

የቤተሰብ አባላትም ንግስት ንቦች ይበልጥ እንዲመገቡ ማበረታታት ይገባቸዋል፡፡

የቤተሰብ አባላት የሥራ ጫናቸውን በመጋራትም ሰፊ የዕረፍት ጊዜ እንዲኖራቸውና እንዲመገቡም መርዳት ይገባቸዋል፡፡

2. የዶሮ መኖ አዘገጃጀት መመሪያ ከቤተሰብ ማስታወሻው ክፍለ ጊዜ 3 ላይ የሚገኘውን ዘጠኝ ነጥቦች ያንብቡላቸው

3. የግለሰብ ተሞክሮዎችን ከቤተሰብ ማሰታውሻው ክፍለ ጊዜ 3 ላይ ያለበትን ቦታ በመጠቆም ጮክ ብለው ያንብቡላቸው

ነፍሰጡር ሴት መክሰስ ስትበላ፡ በየቀኑ በርከት ያሉ ባለ 3 ኮከብና ባለ 2 ኮከብ ምግቦችን “ለሁለት እመገባለሁ”

ደረጃ10፡- መዝጊያ1. ቀጣዩ ስብሰባ መቼ እንደሚሆን ለሁሉም ተሳታፊዎች ያስታውሱ

ይበሉ ስለነበረን ስብሰባ አመስግናለሁ››